ጥቂት “ስለ አቶ በረከት ልጆች” (ገዛኸኝ ሰርቤሳ)

የአቶ በረከት ስምኦን በሌብነት ተጠርጥረው መታሰራቸውን ተከትሎ እሳቸው በሌብነት ብቻ ሳይሆን በሌሎች ጉዳዮችም ሊጠየቁ እንደሚገባ በቀደም እለት የኢሳት ቴሌቭዥን ባቀረበው እና አቶ ኤርሚያስም የተሳተፉበትን ውይይት አጣጠሜዋለሁ፡፡ እናም የውይይቱ ጭብጥ ባጭሩ አቶ በረከት ስምኦን ሊጠየቁ የሚችሉባቸው ጉዳዮች

 • በሰብአዊ መብት ጥሰት (ያሳሰሯቸው፣ ደብዛቸው እንዲጠፋ ያሰወሯቸው፣ ምናልባትም በድብቅ ያስገደሏቸው በርካታ ዜጎች እንዳሉ በስፋት ይነገራል)፣
 • በ97 ምርጫ ወቅት እና ከዚያ በኋላ በርካታ በአገርና በዜጎች ላይ ያደረሷቸው እና እንዲደርስ ያስደረጓቸው ወንጀሎች፣
 • ስልጣንን ያለአገባብ በመጠቀም ለግልና ለፖለቲካ ትርፍ ማዋል፣
 • ሀሰተኛ እና አሳሳች ወሬ በመንዛት እና እንዲሰራጭ በማድረግ፣
 • በፍርድ ቤት አሰራር ጣልቃ በመገባትና ፍትህን በማዛባት (ዳኞችን በቀጥታ በማዘዝ፣ በህግ ቁጥጥር ስር ያሉ ጥፋተኞችን ከህግ ውጭ ከእስር በማስፈታት፣ ያለጥፋታቸው እና ያለበቂ ማስረጃ ሰዎች እንዲታሰሩ እና እንዲንገላቱ በማድረግና በማስደረግ)
 • በአገሪቱ የገንዘብ ስርዓት ውስጥ ባንኮች ያላአገባብ የማይሰበሰብ ብድር እንዲሰጡ  በማድረግ፣
 • የፖለቲካ ሴራ በማካሄድ አገሪቱን ወደአልተፈለገ አቅጣጫ እንደትጓዝ የማድረግ ሙከራዎች እና

በተመሳሳይ ተጨማሪ ወንጀሎች ሊጠየቁ እንደሚገባ ሌሎች የሚጋሩኝ የሚመስለኝ የግሌም እምነት ነው፡፡

በአጭሩ ይህን ጉዳይ ላንሳ እንጂ አሁን ማውጋት የፈለግኩት የፕሮፓጋንዳ ማሰራጫ፣ የመንግስት ሰራተኞችን የሚሰልል እና የሚያስፈራራ አሰራር እና ይህን ለማስፈፀም በየመንግስት መሰሪያ ቤቶች አሰማርቷቸው ስለነበር እና አሁንም በስራቸው ላይ ባለዑት እና አተ በረከት ስምኦን ስለአሰማራቸው ቅጥረኞች ወይም “የአቶ በረከት ልጆች” ጉዳይ ነው፡፡

“የአቶ በረከት ልጆች” ያልኳቸው በየመንግስት መስሪያ ቤቶች “በከፍተኛ ደመወዝ” እንዲመደቡ የተደረጉ እና ከመንግስት ሰራተኞች አስተዳደር ደንብና ስርዓት ውጭ በርካታ ስርዓት አልባ የሆነ ጉዳይ ሲፈፅሙና እና የስለላ ስራ ሲያከናውኑ የነበሩ የስርዓቱ ቅጥረኛችን ጉዳይ ለመጠቆም ነው፡፡

ከምርጫ 97 በኋላ ኢህአዴግ መንግስት የሚሰራውን ስራ የማሳወቅ ስራዬን ለመወጣት በሚል የመንግስት ኮሙኒኬሽን መስሪያ ቤት ካቋቋመ በኋላ በአቶ በረከት የወያኔያዊ ስልት እና አካሄድ ከክልሎች የመንግስት መስሪያ ቤቶች እንዲሁም ምናልባትም ከመንገድ ሊሆን ይችላል የእነሱን አላማ በጭፍን ይሁን የግል ጥቅም ለማግኘት የሚደግፉ ሰዎችን በማሰባሰብና በማእከል በማሰባሰብ በየመንግስት መስሪያ ቤቱ “የኮሚኒኬሽን ኦፊሰር” በሚል የስራ መደብ ያለምንም መዋቅር ደመወዝ ተቆርጦላቸው እንዲመደቡ ተደርገዋል፡፡ ለእነዚህ “ስርዓት አልባ ተቀጣሪዎች” ደመወዝ ደግሞ ለቀድሞ የተፈቀደ መዋቅር የሚጠይቀው የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ያለምንም የመዋቅር ጥያቄ የተጠየውን ሁሉ ይፈቅድ ነበር፡፡ እነዚህ ባለልዩ ባለመብቶች እና የፓለቲካ ተመዳቢዎችን ነው “የአቶ በረከት ልጆች” የምንላቸው፡፡

“የአቶ በረከት ልጆች” ተፈጥሯዊ ገፅታ

 1. “የአቶ በረከት ልጆች” በየመንግስት መስሪያ ቤቱ ሲመደቡ ከመስሪያ ቤቶች መዋቅር ውጭ እንዲሆን መደረጉ በወያኔያዊ ስልት የተለየ ትኩረት የተቸራቸው ናቸው – በአቋሯጭ አዳጊዎች ናቸው፡፡
 2. “የአቶ በረከት ልጆች” የመንግስት ኮሚኒኬሽን ኦፊሰርነት ስራን ያገኙት ለሁሉም ዜጎች አኩል የመወዳደርን እድል በመንፈግ ሲሆን የስራ እድሉን እንዲያገኙ የተደረጉት በፖለቲካ መስፈርት ብቻ መሆኑ ልዩ ባህርያቸው ነው፡፡
 3. “የአቶ በረከት ልጆች” ለኮሚኒኬሽን ኦፊሰርነት የስራ ደረጃ የሚያስፈልገውን የትምህርትና የሙያ ተፈላጊ መስፈርት አሟልተው ሳይሆን በፖለቲካ አመለካከታቸው እና ለፖለቲካ አቃጣሪነት እና ለስለላ ስራ ፈቃደኝነትን ብቻ የሚጠይቅ እና ከየትኛው አይነት ሙያ (እኔ በቅርበት የማውቃቸው እንኳ የስታቲስቲክስ፣ የኬሚስትሪ፣ የሂሳብ፣ የጂኦግራፊ … አንዳዳንዶች ደግሞ ምናልባትም “የምንም” ሙያ ያላቸው ነበሩ፣ የሚገርመው አሁንም አሉ – ሰሚና የሚፈራቸው ግን ያላቸው አይመስልም፡)፡፡
 4. “የአቶ በረከት ልጆች” በፈቃደኝነት ከየቦታው ተሰባስበው መጥተው በአዲስ አበባ የቤት ችግር እንዳይገጥማቸው ከመንግስት ቤቶች አስተዳደር ድርጅት (የመንግስት ኪራይ ቤቶች አስተዳደር) በቅድሚያ ቤት እየተፈለገ የተሰጣቸው ናቸው -የወያኔ እንቆጳዚዮን ናቸዋ፡፡
 5. “የአቶ በረከትን ልጆች” ከሌላው የኢህአዴግ የነበረችው የኢፌድሪ የሚሏት አገራቸው ስር ካሉ እና በህግና ስርዓት ተቀጥረው ከሚሰሩ የመንግስት ሰራተኞች የሚለያቸው መስፈርት “የአቶ በረከት ልጆች” መሆናቸው ሲሆን የአቶ በረከት የግልና ለስርዓቱ በታማኝነት ለማቀጣር ብቁና ዝግጁ መሆናቸው ብቻ በቂ ነበር፡፡
 6. “የአቶ በረከት ልጆች” ዋና ፍጥረት የኢህአዴግ መንግስት የመረጃ እጥረት እንዳይኖርበት እና በመንግስት መስሪያ ቤቶች ውስጥ ያለው የሰራተኛ ሃይልን የመቆጣጠሪያ መሳሪነታቸው ነበር፡፡ በየመስሪያ ቤቱ የስራ ሁኔታ እንዲሁም ሰራተኞች በተፈላጊ ትኩረት በሚያስፈልግ ጉዳይ ላይ ያላቸው እንቅስቃሴ የመሰለልና ለጌቶቻቸው ሪፖርት ማቅረብ ዋነኛ የተፈጠሩበት ስራ ሲሆን በአንዳንድ ተቋማት ሃላፊዎችም ጭምር ይሰለሉ ነበር፡፡ የሚፈሩ ሃላፊዎችም እንደበሩ የሚታወቅ ነው፡፡
 7. ሌላው “የአቶ በረከት ልጆች” የመንግስትን ፕሮፓጋንዳ የወያኔን መራዥ የፖለቲካ ርእዮት በተለያየ ስብሰባዎች፣ የመልእክት ማስተላለፊያ ዘዴዎች በመጠቀም ሰራተኞችን በግድም በውድ የመጋት እና እንዲቀበሉት የማድረግ ተግባር የተፈጠሩበት በፍላጎታቸው የተጎናፀፉት የስራ ባህርያቸው ነበር፡፡

“የአቶ በረከት ልጆች” የስራ ላይ ባህርይና አፈፃፀም

“የአቶ በረከት ልጆች” እንደየግለ ባህርያቸው ቅርፀት የተለያዩ ሊሆኑ እንደሚችሉ መገመት ሳያስፈልገው የሰው ልጅ የባህርይ ብዙህነት ብቻ መመልከት በቂ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ለወያኔ ስርዓት ታማኝነትና የፕሮፓጋንዳ መሳሪያዊነት በምርጫቸው ጥቅም ላይ የዋሉ እንደሆነ በስፋ የሚታይ ባህርያቸው ነው፡፡ የስርዓቱ መገለጫ የእነሱም መገለጫ በመሆኑ የግል ጥቅም እና ባቋራጭ ማደግ ተመሳሳይነት ይታይባቸዋል፡፡ ፀሃፊው “የአቶ በረከት ልጆች” በመየመስሪያ ቤቱ የመመደብ እና ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ ቁጥጥር የማካሄድ ስርዓት ከተዘረጋ ጀምሮ በሁለት መስሪያ ቤቶች ሰርተዋል፡፡ እናም ከፀሃፊው የእውን ልምድ እና ከሌሎች ተሰላይ የመንግስት ሰራተኞች የቃረሟቸውን “የአቶ በረከት ልጆች” አፈፃፀም ለምልከታ ያህል እንደሚከተለው በአጠሪራ (አጠሪራ በአጭር በአጭሩ በአጭሩ የቀረበ አንኳር ሃሳብ እንደማለት ተደርጎ ይወሰድ)ቀርቧል፡፡

 • የግንቦት 20 በዓል በየመስሪያ ቤቱ ሲከበር በዝግጅት ላይ የሚቀር ሰራተኛን መመዘገብ፣ ማስጠንቀቂያ የመስጠትና የማሰጠት፣
 • “የባንዲራ ቀን” ሲከበር ማን ተሳተፈ ማን አልተሳተፈ ይመዘገባል፣ ሲያስፈልግም ተፈላጊውን እርምጃ የማስወሰድ፣
 • መንግስት መረጋጋት ሲሳነው በሚያደርግው የመንግስት ሰራተኞችን የመገምገም አካሄድ ዋነኛ ተዋናይ በመሆኑ የመንግስት ተቃዋሚ ናቸው በሚሏቸው እና ምንም አይነት ምልክት በማያሳዩ ተጠርጣሪዎች ላይ የግምገማ ናዳ የማውረድ ስራ በማከናወን ለፈሪ ዎች የፍርሃትና የኢህአዴግ አስፈሪ ገፅታን ማያሳየት ሚና ይጫወታሉ፣
 • በተለያዩ የስራ፣ የግለሰብ እና የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ ለአቶ በረከት ወይም ለመንግስት ኮሚኒኬሽን መስሪያ ቤት ሪፖርት የሚያደርጉ በመሆኑ በአንዳንድ ቦታ የመስሪያ ቤት ሃላፊዎችን ጭምር የማስፈራራት ሁኔታ ታይቷል፣
 • የስራ ግምገማ አቅጣጫን በሚፈልጉት አቅጣጫ እንዲሄድ የማስደረግ፣
 • ለበላይ ሃላፊዎች መረጃ በመስጠት ሰራተኞች እንዲባረሩ የማስደረግ ስራ ይሰሩ ነበር፡፡ በተግባር በነበርኩበት መስሪያ ቤት የገጠመኝን ለማንሳት ያህል በወቅቱ የህዝብ ግንኙነቱን ጃላፊ እና አንድ የቡድን መሪ ለመባረራቸው ምክንያት እራሱ የኮሚኒኬሽን ኦፊሰሩ መሆኑን ሲናገር ሰምቻለሁ፡፡ እነዚህ ሰዎች ሲባረሩ የበላይ ሃላፊው ጠርቶ ልቀቁ ወይም ማህደራችሁን አበላሸዋለሁ በማለታቸው ከማይጋፉት ጋር መጋፋት ስለሆነባቸው መልቀቂያ እንዲያስገቡ ተደርግው ተባረዋል፡፡ የተባረሩት በመሰሪያ ቤቱ ሃላፊ በተሰጣቸው ውሳኔ ቢሆንም በማህደራቸው የተያያዘው ሰነድ ግን በገዛ ፈቃዳቸው እንደለቀቁ ተደርጎ ነው በሀሰት የተቀመጠው፡፡
 • አንዳንዶቹ በእርግጥ በእውን የገጠመኝ ነገር ደመዎዝ ያንሰኛል በማለት አዲስ መደብ እንዲከፈት በማስደረግ ያለምንም ውድድር፣ በማይገባ መንገድ የደመወዝ ጭማሪ እንዲያገኝ የሚያስደርጉ ነበሩ፡፡ ይህ ልምድ ደግሞ የአብዛኞቹ “የአቶ በረከት ስምኦን ልጆች” ባህርይ ነው፡፡
 • ከሌላው በተለየ ሁኔታ እና ያለምንም ውድድር በድርጅታቸውና በመንግስት በኩል ልዩ ልዩ የትምህርት እድል እንዲያገኙ የሚደረግ ሲሆን ዋናውን የመሰሪያ ቤት ስራ እየሰሩ የሚኖሩ የተመልካችነትና ምን ዋጋ አለው ወደሚል ዝንባሌ የመግፋትና ሞራል የመጣል ሚና እንዲጫወቱ ከፍትኛ ሚና ተጫውተዋል፡፡
 • “የአቶ በረከት ልጆች” በትክክልኛ አገላለፅ የመንግስት ሰራተኞች ናቸው ለማለት የሚያስችል መስፈርት የማያማሉ ቢሆንም በመስሪያ ቤቶች ዋና ዋና እና ወሳኝ ኮሚቴዎች ውስጥ የመመደብ እና የሚፈልጉትን ውሳኔ ማስወሰን ስራ ያከናውኑ ነበር፡፡

በበኩሌ “ስለ አቶ በረከት ልጆች” በጥቂቱ በተወሰነ መስሪያ ቤት እንዲያውም በሁለት መስሪያ ቤት፣ በሌላ እንዲያውም በአብዛኛው ከአንድ መስሪያ ቤት ብቻ ያየሁትንና የገጠመኝን ልምዴን ለማሳየት ሞክሬአለሁ፡፡ በየመስሪያ ቤቱ በእነዚህ “የፓለቲካ አቃጣሪነት ሰራተኞች” አፈፃፀም እና ያስከተሉት በደልና ግፍ ቢዘረዘር በርካታ መሆኑን አልጠራጠርም፡፡ ይህን “የአቶ በረከት ልጆች” የአሰራር ስርዓት እንዲዘረጋ እጃቸው ከዘረጉት ዋናዎች መካከል አቶ ኤርምያስ ለገሰም እንደነበሩበት በስፋት  የሚነገር በመሆኑ እሳቸውም ስርዓቱን ከድተው አሁን ውጭ አገር የሚኖሩ በመሆኑ ይህን ፅሁፍ ካነበቡት እራሳቸው ቢናገሩበት ጥሩ ይመስለኛል፡፡

አመሰግናለሁ – ስላነበባችሁኝ፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s