የአድዋ ድል የሁላችንም ነውአስገራሚዎቹ የሀዲያና የከምባታ ዘማቾች በአድዋ

በአፄ ዳግማዊ ምኒልክ የጦር አበጋዞች የከምባታና የሀዲያን ክልል ህዝቦችን ለማስገበርና በማእከላዊ መንግሥት ስር ለማጠቃለል በ1882 አም የተጀመረው የጦርነት ዘመቻ የተጠናቀቀው በ1885 አም ላይ ሲሆን ከሶስት አመታት በሁዋላ በተቀሰቀሰው የአድዋ ጦርነት ላይ ገና ከቁስላቸው ያላገገሙት የክልሉ ህዝቦች ለአገራቸው ነፃነትና ሉአላዊነት ስሉ በግንባር ቀደምትነት ተሰልፈው ተዋግተዋል፣ ከፍተኛ መስዋዕትነትም ከፍለዋል። የአድዋ ጦርነት የክተት አዋጅ በአፄ ዳግማዊ ምኒልክ የታወጀው በመስከረም ወር 1888 አም ነበር። የክተት አዋጁ እንደታወጀ የጎጃም፣ የቤጌምድር ፣የወሎና የላስታ ህዝብ ከ300 እስከ 500 ኪሎሜትር ያህል፣ የሸዋ፣ የሐረር ፣ የባሌ፣ የአርሲ፣ የከምባታና ሀዲያ፣ የሲዳሞ፣ የጅማ፣ የከፋ፣ የወላይታ፣ የወለጋና የኢሉባቡር ጦር ደግሞ ከ600 እስከ 1,000 ወይም 1,500 ኪሎሜትር ድረስ ርቀት ያለውን አገር በእግሩ እያቋረጠ ቀንና ሌሊት፣ ሃሩርና ቁር ሳይገታው አቀበቱንና ቁልቁለቱን እየወጣና እየወረደ ያለማወላወል ለወሳኙ ጦርነት ወደሰሜን የጦርነት ግንባር እንደተጓዙ የአካባቢው ተወላጅ የሆነው የዲልባቶ ደጎዬ ፅሁፍ ያስረዳል።

የከምባታና የሐዲያ ክልል የገባር ገበሬ ሠራዊትን በዋና የጦር አበጋዝነት የመሩት በ1888 አም የክልሉ ገዥ የነበሩት የአፄ ምኒልክ ያክስት ልጅ የነበሩት ደጃዝማች በሻህ አቦዬ ነበሩ። የከምባታን ዘማቾች የመሩት በወቅቱ የከምባታ ባላባት የነበሩት ቀኛዝማች ሞሊሶ ሄላሞ ድልበቶ ሲሆኑ ከእርሳቸው ጋር የዘመቱትን የከምባታ ገበሬ ጦረኞች የተሟላ ዝርዝር ለማግኘት ባንችልም 1) ላላምዳ መሎሮ፣ ከሄጎ ጌዮጣ፣ 2) አበጋዝ ትሮሬ ዋዶሌ፣ ከቃጫ፣3) ጌንቤራ ግዴቦ፣ ከደጋ ቀዲዳ፣ 4) ወልደማርያም ባጂ ፣ከገረምባ፤ 5/ መልከቶ ለታ ለቾሬ፣ ከሰረራ መዝመታቸውን የከምባታ አዛውንት አረጋግጠዋል። የሐዲያ ዘማቾች የተመሩት በፊታውራሪ ጌጃ ገርቦና በሌሎችም የሐዲያ መሪዎች እንደነበር ይነገራል፣ በጽሑፍ የተቀመጠ መረጃ ስለሌለን የዘማቾቹን ብዛትና የስም ዝርዝር ለማቅረብ አልተቻለም። በነበረው የዘመቻ ልማድ መሰረት ደጃዝማች በሻህ አቦዬ ወንድ ሴት ሳይባል በብዙ ሺህ የሚቆጠር የከምባታና የሀዲያን ገበሬ ሠራዊት ይዘው አድዋ ከደረሱ በሁዋላ ዳግማዊ ምኒልክ በሰጡዋቸው መመሪያ መሰረት ቀድመው የጠላትን ምሽግ የከበቡና ያስጨነቁ ጀግና ሰው እንደነበሩ ይተረካል።

ደጃዝማች በሻህ አቦዬ የከምባታና የሐዲያ ጀግኖችን አስከትለው በአድዋ የጦር ሜዳ በአምባ ኪዳነምህረት ግንባር ከኢጣሊያ የጦር አዛዥ ከጄኔራል አልቤርቶኒ ጦር ጋር በተደረገው ብርቱ ትንቅንቅ በከፍተኛ ወኔና ጀግንነት ሲዋጉና ሲያዋጉ ሳለ በጠላት ጥይት ተመትተው የወደቁ ስመጥር የጦር ሰው ነበሩ። በመሪ አዝማቻቸው ሞት የተቆጩት ጭፍሮቻቸው ከጦርነቱ ፍፃሜ በሁዋላ ብዙ የኢጣልያ ምርኮኞችን ለአፄ ምኒልክ በማስረከብ ፈንታ በበቀል መፍጀታቸው በታሪክ ተመዝግቦ ይገኛል።

የአድዋ ጦርነትና የተገኘው አንፀባራቂ የኢትዮጵያውያን ድል መላውን አለም ያስደነቀ የታሪክ ክስተት ነበር፣ ለዝንተአለም የሚቆይ ታሪካዊ ድል። የአንዲቷ አፍሪቃዊት ነፃ አገር ኢትዮጵያ በኃይል ነፃነቷን ለመግፈፍ፣ ግዛቷን ለመድፈርና በሕዝቦቿ ላይ የተገዥነት ቀንበር ለመጫን ባህር ተሻግሮ የመጣን ጠላት የካቲት 23/1888 አም አድዋ ላይ ድባቅ መታች፣ ድል አደረገች። ከሁለት ሺህ አመታት በፊት ሀኒባል በሮማውያን ላይ ካገኘው ድል በማያንስ ሁኔታ በአለም ያስተጋባውና ኢጣልያኖችን ያሸማቀቀው የአድዋ ድል አፍሪቃ በአውሮጳ ላይ እንዳገኘው ድል የሚቆጠር ታላቅ የተጋድሎ ውጤት ነበር፣ ነውም። የአድዋ ድል የከምባታና የሐዲያ እንዲሁም የሌሎች ክልሎች ህዝቦች ሁሉ የአንድነት፣ የህብረትና የመስዋዕትነት ውጤት ከመሆኑም በላይ ማናቸውንም ተመሳሳይ ብሔራዊ ወይም አገርአቀፍ ችግርና ፈተና ለመቋቋምና በድል ለመወጣት የምንችለው እንደአድዋው ወቅት በህብረትና በአንድነት ስንቆም ብቻ እንደሆነ የሚያረጋግጥ ታሪካዊ ድል ነው። በሌላ አንፃር ብዙ ሺህ ኢትዮጵያውን ውድ ሕይወታቸውን የሰውበት ጦርነት ስለነበር ለበርካታ ሺህ ቤተሰቦች በመላ አገሪቱ የመሪር ሐዘን ወቀት እንደነበር መዘንጋት የለበትም። ሆኖም ለነፃነት የተከፈለ ውድ ዋጋ ነበር፣ ነፃነትም ምንኛ ውድ እሴት እንደሆነ ምንጊዜም መዘንጋት አይኖርብንም። አዎን፣ “ነፃነት ነፃ አይደለም”(“Freedom is not free”).

ምንጭ:- ዲልባቶ ደጎዬ

ጅጂን ለመታደግ ግብረኃይል ይቋቋም! (መስቀሉ አየለ)

ተቀማጭነቱ በአሜሪካን አገር የሆነው የአድማስ ሬዲዮ ኒዮርክ ድረስ ተጉዞ ለረጅም ግዜ አነጋጋሪ በነበረው የጅጅ ህይወት ዙሪያ አጠር ያለ ዘገባ በመስራት በአይነ ህሊና ሲማትሯት ለነበሩ አድናቂዎቿ ጆሮ የሚሆን የጥቂት ደቂቃ የቃላት ልውውጦች በመቅረጸ ድምጽ አስቀርቶ ከማሰማትም ባለፈ ከመድረክ የተሰወረችበት ዋነኛው ምክንያት በገጠማት የጤና እክል መሆኑን በመጥቀስ ” ጅጅ በጣም ብዙ ጽሎትና ትንሽ እርዳታ ትፈልጋለች ” ሲል ዝምታውን ሰብሮታል። ጋዜጠኛው የራሱን ግዜ ወስዶ ይኽን ያህል አመት እንቆቅልሽ የነበረውን የጅጅን ሁኔታ በከፊል ማሳወቅ በመቻሉ አድናቆት ሊቸረው ይገባል።

ጅጅ የኢትዮጵያን ሙዚቃ ወደሌላ ከፍታ የወሰደችና ገና ወደፊትም ይዛን ብዙ ልትጓዝ የምትችልበት የጸጋ ጥግ ላይ ሳለች እንዲህ እንቅፋት ሲመታት እርሷ ያለችበትን ትክክለኛ እውነት ፈልጎ በማወቅና “የቤተሰቧንም ሆነ የእርሷ ፕራይቬሲ ሊጠበቅላቸው ይገባል” በሚሉ ተጻጻሪ ኩነቶች መካከል ተወጥረን ብዙ መስቀል አስተኩሰናል። ነገር ግን በአንድም በሌላም የዚህች የንጋት ኮከብ ችግር ሳይፈታ ምናልባትም ከድጡ ወደማጡ እየሆነ እዚህ ደርሷል።ዛሬ ደግሞ ይኽ ባይተዋርነት አንድ ነጥብ ላይ ሊቋጭ ይገባል ስንል ዝም ብለን አይደለም።

ጅጅ የህዝ ሃብት ናት። ጅጅ የትናት ማንነታችንን የምናይባት እትሮኖስ፤ የዛሬውን ክፉ ቀን የምንሻገርባት ምርኩዛችን የነገውን ራእያችንን የምንሰንቅባት ሰባሰገል ናትና የእርሷ ጉዳይ የጥቂት ቤተሰቦቿ የግል ችግር ሆኖ የቆየበት አያያዝ እዚህ ላይ ሊያበቃ ይገባል። የሃገራችን ከያኔያን አንድ ነገር ሲገጥማቸው ወደ ሸህ አላሙዲን ማንጋጠጡ ለዛሬው እውነት የማይመጥንባቸው በርካታ ምክኛቶች እንዳሉ የታወቀ ነው። እንዲህ ያሉ የጥበብ ፈርጥችን በግዜው አለመታደግ ማለት ደግሞ ምን ማለት እንደሆነ ትናንት በአቶ ፍቃዱ ተክለማርያም ፍጻሜ የደረሰው የልብ ስብራት ገና በቅጡ አልተጠገንምና ከእርሱ መማር ያለብን ነገር እንዳለ ይሰማኛል።

ዝምታው በዚሁ ከቀጥርልር ለጅጅ ከዛሬ ይልቅ ነገ ይበልጥ የማይከብድበት አመክንዮ የለምና አንድ ነገር በፍጥነት እንዲተገበር የግድ ይላል። ስለዚህ ታዋቂ ሰዎች፣የኃይማኖት አባቶችና የጅጅ ቤተሰቦች እንዲሁም ማናቸውም “ቴዎድሮስ ተሾመ” ከተባለ የተስቦ ዓይነት ነጻ የሆኑ በሙዚቃውና በጥበቡ ኢንደስትሪ ውስጥ ያሉ ባለሙያዎችና የሚዲያ ሰዎች የተካተቱበት አንድ ሁነኛ ግብረኃይል ተዋቅሮ በቶሎ ወደ ስራ ሊገባ ይገባል።

ነፍሳቸው ለኪነጥበብ ምን ያህል ቅርብ እንደሆነ በዚህ አጭር ግዜ ውስጥ የታዘብን በመሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዚህ ግብረኃይል ሰብሳቢ ቢሆኑ ፈርጀ ብዙ ጥቅም ይኖረዋል። ያም የማይቻል ከሆነ ደግሞ ከአንጋፋዎቹ ባለሙያዎች ጋሽ ማህሙድ ወይንም ቴዲ አፍሮ ቦታውን እንዲሸፍኑት ሊደረግ ይችላል።

ምንም ይሁን ምንም ግን ዝምታው እዚህ ላይ ያብቃ እና እንቁዋን እንታደግ። እርሷን መታደግ ታሪክንም፣ ኪነጥበቡንም መታደግ ነው።

ባለቤት አልባ ከተሞችን መንግስት ይታደጋቸው (ድራንዝ ጳውሎስ (ከባህር ዳር)

እንዲህ እንደ ዛሬው የሕዝብ መሰብሰቢያ አዳራሾች ባልበዙበት፣ ማባራዊ ድረ ገጾችና ሚዲያዎች ባልተስፋፉበት፣ የሕዝብ መወያያ አጀንዳ እየተቀረጸ ውይይት በማይካሄድበት በጥንት ዘመን በአገራችን በአስተዳደር እርከን ላይ የነበሩ የአገር ግዛት አስተዳዳሪዎች በሕዝብ ዘንድ የነበራቸውን ተቀባይነት ለማረጋገጥ Çእረኛ ምን አለ?È ይሉ እንደነበር በታሪክ ድርሳናት ይወሳል፡፡ ይህ ደግሞ ሕዝብን ለማዳመጥ የሚጠቀሙት ራሳቸው የፈጠሩት ሚዲያ መሆኑን ማረጋገጥ ይቻላል፡፡ ሕዝብን የሚያዳምጠው ሲያጣ አቤቱታው ከጠቅላይ ግዛት ወደ አገር ግዛት ልክ እንደ ተላላፊ በሽታ ይዛመታል፡፡ ከዚያም አልፎ ራሱን በራሱ ማዳመጥ ይጀምራል፡፡ በልቡ መከፋቱንንና ጩኸቱን ሰምቶ የሚደርስለት ሲያጣ

የልቤን መከፋት ሆዴ እያዳመጠ፣

ሊመረው ነው መሰል ነገር አላመጠ፡፡È የሚል የመገፋት ፉከራ አዘል እንጉርጉሮ ሲያሰማ ብልጥ አገር ገዥ የዝሆን ጆሮ ይሰጠኝ አልሰማሁም አይልም፡፡ ይልቅ በምላሹ

እዚያ ማዶ ሆኖ አንድ ሰው ተጣራ፣

ወዲህ ማዶ ሆኖ አንድ ሰው ወይ አለው፣

ሳናውቀው ነው እንጂ ይህ ነገር የኛ ነው፡፡ በሚል ሕዝቡ የተከፋበትን ጉዳይ ማድመጥ፣ ለተከፋበት ጉዳይ ምላሽ መስጠት ይጀምራል፡፡ ይህ ደግሞ የብልጥ አገር ገዥ፣ አስተዳዳሪ መርህ ነው፡፡ ሕዝብን እረኛ የሚወክልበት ዘመን፡፡ እረኞች ዘንድ ዝምታ ከሰፈነ ሕዝቡ ለመንግስት ያለው ተገዥነት ያሳብቃል፡፡ በጥንት ዘመን የነበረውን የሕዝብና የመንግስትን መደማመጥ ያነሳሁት ያለ ነገር አይደለም፡፡ ከየካቲት 9 – 14 ቀን 2011 ዓ.ም መደመርለኢትዮጵያ ከተሞች ብልጽግና“ በሚል መሪ ቃል በሶማሌ ክልል ዋና ከተማ  በጅግጅጋ ከተማ በተካሄደው 8ኛው የከተሞች ፎረም የኢትዮጵያ ከተሞችን የጎረቤት ሀገሮችን ጨምሮ 163 ከተሞችንም ያሳተፈ እንደነበረ ቢነገርም አማራ ክልልን ወክለው ስለተገኙ 32 ከተሞችና የክልሉ መንግስት ስለከተሞች ዝግጅት ትኩረት ስለነፈጋቸውና ከተሞችን የሚመራው ተቋም ሕይወት አልባ መሆኑን ለመግለጽ ነው፡፡

የፎረሙ ዋና ዓላማ በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሴክተር ባሉ የማዕዘን ድንጋዮች /Pillars/ አፈጻጸም መሰረት ያደረገ በከተሞች መካከል ዉድድር እንዲደረግና በአግባቡ የፈጸሙትን ለማበረታታት ሌሎች ከተሞች ደግሞ ከዚህ መልካም ተሞክሮ በመማር የተሻለ አፈጻጸም እንዲያስመዘግቡ ለማበረታታትና የከተማ ነዋሪዎችን፣ የመንግስትና ሌሎች ባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ እና ትብብር በማጠናከር፣ መልካም ተሞክሮዎችንና ልምዶችን በማስፋፋት፣ እንዲሁም ከተሞች እሴቶቻቸውን በማስተዋወቅና በማጎልበት ጠንካራ መሰረት ያለዉ የከተማ ህዝብ ንቅናቄና ተጠቃሚነትን ለመፍጠር ነው፡፡

ከተሞች የራሳቸውን በጎ ገጽታ በማጎልበትና በመሸጥ፣ ልማታቸውን በማፋጠን የእርስበርስ ትውውቅና የመማማር ዕድል በመፍጠርና ከተሞች ያላቸውን ዕምቅ አቅም /በኢንቨስትመንት፣ በንግድ፣ በቱሪዝም፣ በታሪካዊ፣ ባህላዊና ማህበራዊ እሴቶች/ በማስተዋወቅ በኩል የፎረሙ ፋይዳ የጎላ እንደነበረ ይነገራል፡፡

ይሁን እንጂ በዚህ በጅግጅጋው የከተሞች ፎረም በምድብ 3:- 20 ሺህ ህዝብና ከዚያ በላይ ነዋሪ ያላቸው ከተሞች መካከል የከሚሴ ከተማ ራስን በማስተዋወቅ የሁለተኛ ደረጃ ከማግኘቷ ውጭ የአማራ ክልልን ወክለው የተሳተፉት 31ዱ ከተሞች ተጠቃሚነታቸውና ውጤታማነታቸው ከተሳትፎ ያልዘለለ ነው፡፡ በተለይ በሜትሮፖሊታን ደረጃ ላይ ያሉ ባህር ዳር፣ ጎንደርና ደሴ ከተሞች በምድባቸው ደረጃ አለማግኘታቸውን ስንታዘብ ከክልሉ መንግስት ጀምሮ ከተሞችን የሚመራው ክልሉ ከተማ ልማት፣ ቤቶችና ኮንስትራክሽን ቢሮ ለፎረሙ ዝግጅትና ለሚገኘው ፋይዳ የሰጠውን የትኩረት ማነስ ያመላክታል፡፡

እንዴውም ከታዳጊ እስከ ሜትሮፖሊታን ደረጃ ያሉ የአማራ ክልል ከተሞች በስርዓትና በተገቢው መንገድ ባለመመራታቸው ከተሞች ማንን ይመስላሉ? ተብሎ ሲጠየቅ አመራሩ እንደተባለ በአንድ መድረክ የታዘብኩት ከዚህ ላይ ማንሳት እወዳለሁ፡፡

ከተሞቻችን ባለፉት ስርዓቶች አስተዋይ በማጣት በድህነት ችጋር ውስጥ ተተብትበው መኖራቸው ሲነገር እንዳልነበር ዛሬም የተፈጠረው ምቹ ሁኔታና በህገ መንግስቱ የተፈቀደውን የመልማት መብታቸውን ተጠቅመው መልካም አስተዳደር የሰፈነባቸውና በሥራ ዕድል ፈጠራም የማይተካ ሚና እንዲጫወቱ በማድረግ በኩል የክልሉ መንግስት ለበርካታ ዓመታት ዓይኑን ሸፍኖታል፡፡ በፎረሙ የተቀመጠውን ዓላማና የሚያስገኘውን ጠቀሜታ ባገናዘበ መልኩ በመደገፍና በማዘጋጀት በኩል ምንም ዓይነት ሥራ እንዳልተሠራ በድፍረት መናገር ይቻላል፡፡ ከተሳትፎ በዘለለ ተወዳዳሪ ሆኖ ለመቅረብ የተደረገው ጥረት ከዚህ ግባ የሚባል እንዳልሆነ ከማጠቃለያው ውጤት መረዳት ይቻላል፡፡

ከዚህ በፊት በዚሁ መድረክ በአገሪቱ ካሉ ከተሞች የተገኘውን ተሞክሮ በማስፋትና የፎረሙን አስፈላጊነት በውል በማጤን ተገቢውን አመራር በመስጠት፣ ተግባሩን የሚመለከተው ዳይሬክቶሬት በዕቅድ ይዞ በመምራት፣ በጀት መድቦ በማስፈጸም በኩል የጎላ እንቅስቃሴ እንዳልተደረገ በግልጽ ማየት ተችሏል፡፡

ይባስ ብሎ ተግባሩን በዕቅድ የያዘው በቢሮው የከተሞች አቅም ግንባታ መልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ለፎረሙ ተሳታፊ ከተሞች ድጋፍ ማድረግ ሲገባው ጭራሽ የማይመለከታቸውና የፎረሙን ጽንሰ ሀሳብ ያልተረዱ፣ ተቋሙን ለሚመሩት የበላይ ኃላፊዎች ቅረቤታ ያላቸው ከሕዝብ ግንኙነት፣ ከሕግ አገልግሎትና ከውስጥ ኦዲት የተውጣጡና ባለሙያዎችን መርጦ ጅግጅጋ ድረስ መላክስ ተገቢ ነወይ? ቢሮው ከውድቀት የማይማሩ፣ ታጥቦ ጭቃና አድሮ ቃሪያ የተሰባሰቡበት አመራሮች ያሉበት ስለሆነ የክልሉ መንግስት በክልሉ ሰላምና መረጋጋት ለማስፈን በሚያደርገው እንቅስቃሴ በነካ እጁ ተቋሙንም ሆነ የክልሉን ከተሞች ሊለባኛቸው ይገባል ባይ ነኝ፡፡

የዶር አረጋዊ በርሄ ነገር!!! ጨቛኟ የአማራ ብሄርም ጭቆናዋን እስካላቆመች ድረስ ህብረተሰባዊ ዕረፍት አታገኝም ወንድይራድ ሀይለገብርኤል

ዶር አረጋዊ ህወሀትን ከመሰረቱት ረድፈኞች ጎራ የሚሰየሙ ብቻ ሳይሆኑ የድርጅቱም የመጀመሪያው ሊቀመንበር ብቻ ሳይሆን የማታገያ ማኒፌስቶውንም በእጃቸው የፃፉ (የቀረፁ) ግለሰብ እንደነበሩ ይታወቃል። “ተቃወምኩ” ብለው ከተሰደዱ በዃላም ቢሆን “የትግራይ ዲሞክራሲያዊ ትብብር” የተሰኘ ድርጅት ቀልሰው እንደነገሩም ቢሆን ወዲያ-ወዲህ ማለታቸው አልቀረም። “ለውጡን” ተከትሎም በተሰደዱ በ40ኛው አመታቸው ለሀገራቸው ምድር በቅተዋል። ከገቡም በዃላ በየመድረኩና መገናኛ ብዙሀኑ ዙሪያ አብዝተው ይስተዋላሉ።

=====

ጠቅላይ ሚንስትር አብይ “”የፖለቲካ ድርጅቶች ምክክር”” አሰኝተው በከፈቱት መድረክ ላይም በተጋባዥ ተናጋሪነት ተሰይመው ንግግር ከመጀመራቸው በፊት — “”በማወቅም ይሁን ባለማወቅ እስከዛሬ ድረስ ሀገሬን ችግር ውስጥ ለከተታት ፖለቲካ የኔም አስተዋፅዖ ስለነበረበት የኢትዮጵያ ህዝብ ይቅርታ እንዲያደርግልኝ ከልብ በመነጨ አክብሮት እጠይቃለሁ””– ብለው በመናገር ከተሰብሳቢው “”አርአያ”” በተሰኘ አድናቆት ሞቅ ያለ ጭብጨባ ተችሯቸው ነበር።
=====

ይህንን ያሉት ዶር አረጋዊ ባልተጠበቀ ብቻ ሳይሆን በሚያሳፍር ሁኔታ ቃላቸውን በአደባባይ በልተው OMN ከተባለው የጀዋር ቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር በትናትናው ዕለት ቃለ-መጠይቅ ሲያደርጉ እንዲህ ሲናገሩ ሰማናቸው —

ጋዜጠኛው — “”ህወሀት ውስጥ በነበረዎ የፖለቲካ ተሳትፎ እና በሰሩት ስራ ይፀፀቱ ይሆን””? ብሎ ሲጠይቃቸው —

ዶር አረጋዊ — “”በፍፁም አልፀፀትም። የሚያፀፅት ስራም አልሰራውም””። ሲሉ መለሱለት። —

በዚህ አያበቃም—-

ጋዜጠኛው — “”ህወሀት በአማራ ህዝብ ላይ በደል ፈፅሟል የሚለውን ክስስ ይቀበላሉ”” ሲል ጠየቃቸው—

ዶር አረጋዊ — “”አልቀበልም። በደል የፈፀሙት አመራሮቹ ናቸው — ድርጅቱ ህወሀት በአማራ ህዝብ ላይ በደል ለመፈፀም አልተነሳም — ለመበደልም አላለመም በድሎም አያውቅም”” በማለት መለሱ።
=====

“”ወልቃይትስ የአማራ መሬት ነው የትግሬ””? ብሎ ሲጠይቃቸው ደግሞ — “”በህገ- መንግስቱ ቛንቛን መሰረት አድርጎ በተከለለው የግዛት አከላለል የወልቃይት ህዝብ ትግረኛ ተናጋሪ በመሆኑ ወልቃይት ወደትግራይ መከለሉ አግባብ ነው”” — ካሉ በዃላ — “”እንደአለመታደል ሆኖ በዚህኛውም ሆነ በዛኛው ወገን ጥሩ መሪዎችን ባለማግኘታችን ይሄው ጦርነት ሊያጋጥሙን ቆርጠው ተነስተዋል”” ሲሉ አሁንም በመሪዎቹ ላይ ያላቸውን ምሪት ገለጡ።
=====

እስኪ በራሳቸው በዶር አረጋዊ የዕጅ ፅሁፍ የተፃፈውን የህወሐት ማኒፌስቶን እየፈተሽን የዶር አረጋዊን ንግግር እንመርምረውና የሰውየውን እውነተኛ ማንነት እንገምግም —-

እውን ህወሐት የአማራውን ህዝብ በጅምላ ወንጅሎ አልተነሳም? ዶር አረጋዊ እንደሚነግሩን አማራው የተበደለ በህወሐት መሪዎች እንጅ እንደድርጅት መርሃግብር ተቀርፆለት አልነበረም? በዶሩ የተፃፈውን የህወሐት ማንፌስቶ ቃል በቃል በማስቀመጥ እንመርምር —-

የህወሐት ማኒፌስቶ 1968 ዓ/ም

3: ሕብረተሰባዊ ሁኔታዎች

ሀ፡ ራስን መጣል (ዲ-ሁማናይዜሽን)

“”ከቀን ወደ ቀን እየተባባሰ የሚሄደው የኢኮኖሚ ብዝበዛ በሰፊው የትግራይ ህዝብ ላይ ድህነት፡ ረሀብና ውርደት እየተደጋገመ እንዲደርስ አድርጓል። በተጨማሪም የትግራይ ህዝብ ለረጅም ዘመን ሰብዓዊና ፖለቲካዊ መብቱ ተነፍጎ ሲጠላና ሲናቅ እንዲሁም አድልዎ ሲፈፀምበት ቆይቷል። ይህም በደል ጨቛኟ የአማራ ብሔር ሆን ብላ መመሪያዋ አድርጋ ስትሰራበት የቆየች በመሆኑ ነው —–በዚህም የተነሳ ሰፊው የትግራይ ህዝብ ኑሮው እንዲቆረቁዝ ተደርጓል — በዚህም ምክንያት የስራ ማጣት ችግር፡ ሽርሙጥናና ስደትን ከማስከተሉም በላይ ራስን መጣልና መንከራተት የትግራይ ህዝብ ዕለታዊ ተግባሩ ሆኖ ይገኛል። ስለሆነም ህዝቡ ተጠራጣሪና የተጠላ እንዲሆን በመደረጉ በህብረት መኖር የማይችል ሆኖ ይገኛል””” ይላል።

እንግዲህ ዶር አረጋዊ ለዘረዘሩት የትግራይ ህዝብ ችግሮች በሙሉ ተጠያቂ አድርገው ማኒፌስቶ የቀረፁት የአማራውን ብሄር (ህዝብ) በጅምላ እንዲህ ፈርጀው በጠላትነት በማስቀመጥ ነው። የአማራውን ህዝብ በጅምላ የፈረጀ ማኒፌስቶ ቀርፀው ህወሐትን ከፈጠሩ በዃላ —“””የለም አማራ የተበደለው በአመራሮቹ እንጅ በድርጅቱ በህወሐት አደለም””” — ይሉናል።
=====

ይቀጥላል—-

ለ፡ የህብረተሰቡ ወደ ዃላ መቅረትና እረፍት ማጣት

“”ሰፊው የትግራይ ህዝብ ስራ አጥቶ በሽርሙጥናና በስደት ወ…ዘ…ተ… ብቻ ሳይሆን በረሀብ፡ በድንቁርናና በበሽታ እየተሰቃየ ይኖራል። —- ለችግሩ መሰረታዊ ምክንያት ኢምፔሪያሊዝም — ይሁን እንጅ ጨቛኟ የአማራ ብሄር የምታደርገው የኢኮኖሚ ብዝበዛና የፖለቲካ ጭቆና ታክሎበት ነው። —- ጨቛኟ የአማራ ብሄርም
ጭቆናዋን እስካላቆመች ድረስ ህብረተሰባዊ ዕረፍት አታገኝም።””

በማለት የአማራን ብሄር (ህዝብ) በጅምላ “”ጨቛኝ”” ብሎ በመፈረጅ ተጠቂም ተጠያቂም አድርገው ዶር አረጋዊ የድርጅታቸውን ማኒፌስቶ በታይፕ ራይተር ሳይሆን በራሳቸው የእጅ ፅሁፍ አርቅቀዋል። ይሄንን ያክል በደል ለፈፀሙበት ለአማራው ህዝብ ዛሬም ጠላትህ መሪዎቹ እንጅ ህወሐት አልነበረም ሲሉ በአደባባይ ሊቀልዱበት ግን ድፍረቱን አላጡትም።
=====

ይቀጥላል——

ወልቃይት ወደትግራይ የተካለለው በህገ-መንግስታዊ የቛንቛ ፌደራሊዝም አግባብ ነው ያሉን ደግሞ በ1968 በቀረፁት የድርጅታቸው የህወሐት ማኒፌስቶ የሚከተለውን ካስቀመጡ በዃላ ነው —

የትግራይ ግዛት

“”” —- የትግራይ መሬት በደቡብ ኣለዃና፡ በሰሜን መረብ ሲያካልሉት በምዕራብ በኩል ደግሞ ወልቃይትንና ፀለምትን ያጠቃልላል”””” ይላል።

በዶር አረጋዊ የተፃፈው የህወሐት ማኒፌስቶ በዚህ አላበቃም። ዶሩ የአማራ ህዝብ ትግሬነትን በማጥፋት፡በማስካድና የትግሬን መሬት በመውረር ጭምር በማኒፌስቷቸው ከሰውታል፡ የትግራይን ህዝብም —

“”በአማራ ከመጥፋትህ በፊት በመሪ ድርጅትህ በህወሐት ስር ታቅፈህ በመታገል አማራን አጥፋ””” ሲሉ በአማራው ህዝብ ላይ ለደረሰው የዘር ማፅዳት፡ ማጥፋትና፡ መሬት ወረራ ግንባር ቀደም ተጠያቂ መሆናቸውን በራሳቸው የዕጅ ፅሁፍ የተፃፈው የህወሐት ማኒፌስቶ ቀዳሚ ማስረጃ ነው።
=====

አማራን የበደሉት የህወሐት መሪዎች (እርሳቸው ከድርጅቱ ከከዱ በዃላ የነበሩትን ማለታቸው ነው) እንጅ ድርጅቱ አደለም የሚለውን ቀልዳቸውን አጥብቀው የሚገፉት ከተጠያቂነት አመልጣለው ብለው በማሰብ ከሆነ ዶሩ የሚያታልሉት እራሳቸውን ብቻ እንጅ የአማራውን ህዝብ አለመሆኑን ጠንቅቀው ሊገነዘቡት ይገባል።

የአማራን ቤት ያቃጠለውን የመጀመሪያውን ክብሪት ለኩሶ እሳቱን የቆሰቆሱትን ብቻ በመወንጀል ከተጠያቂነት ለማምለጥ ሙከራ ማድረግ የራስን ስውር ማንነት ገላልጦ ከማሳየት ውጭ ሌላ ፋይዳ የለውም።

ህወሐት ከስር መሰረቱ በአማራ ህዝብ መቃብር ላይ የትግሬን የህይወት ዘንባባ ለማለምለም የተነሳ ፀረ አማራ ድርጅት ነው። በተግባር ተከስቶ ያየነውም ይሄው ነው። ቀዳሚ ምስክሩም በዶር አረጋዊ አማራን ከምድረገፅ ለማጥፋት ታልሞና ታቅዶ የተቀረፀው የድርጅቱ ማኒፌስቶ ነው።

የሚገርመው ነገር እኒህ ግፈኛ ሰው በቅርቡ በዶር አብይ የተሰየመው የደንበርና የማትነት ኮሚሲዮን አባል ተደርገው መመረጣቸው ነው። በማኒፌስቶ ወልቃይትና ጠለምት የትግራይ መሬት ነው በማለት በ1968 ዓ/ም የቀረፁ ግለሰብ እንዴት ነው ዛሬ የደንበርና ማንነትን ጉዳይን ፍትሀዊ በሆነ አግባብ አይተው ወልቃይት የአማራ ተፈጥሮአዊና ታሪካዊ ዕርስት ነው ብለው የሚዳኙት? ቀልድህን ተው ዶር አብይ። እንዴትስ የአማራን ህዝብ ብትንቀው ነው እንዲህ አይነት አሳፋሪ ስራ ለመስራት የደፈርከው? እረ እየተስተዋለ።

ታዲያ እንደዶር አረጋዊ ያሉ እጃቸው በአማራ ደም የከረፋ ግለሰቦች ያሉበትን የሰላምና እርቅ ኮሚሲዮን የአማራ ህዝብ የሚቀበለው እንዴት ነው?

እረ ይሄ የፌዝ ስራ አያዋጣም ዶር አብይ!! በትናቱ አስተሳሰብ የዛሬውን አማራ ማዘናጋትም ሆነ ማሞኘት አይቻልህም።

ወንድይራድ ሀይለገብርኤል

### በዓድዋ ጦርነት የመጨረሻ ሠዓታት ላይ የጣልያኖች ሁኔታ ### Mes Demoze


### በዓድዋ ጦርነት የመጨረሻ ሠዓታት ላይ የጣልያኖች ሁኔታ ###

” ባህር ዘሎ መምጣት ለማንም አትበጅ
እንደ ተልባ ሥፍር ትከዳለች እንጅ
አትረጋም ሀገር ያለ ተወላጅ “

በጦርነቱ ዋዜማ በምንሊክ ጦር የተተከለው ድንኳን ሲታይ፣ ከብዛቱ የተነሳ አፍሪካ አውሮፓን ለመጠራረግ የተነሳች ይመስል ነበር። ይሄን ባዩ ጊዜ የተሸበሩት የጣሊያን ወታደሮች ሁሉ፣ የስንብት ደብዳቤ ለቤተሰቦቻቸው እንደፃፉ ኢን አፍሪካ የተሰኘው መፅሃፍ ይገልፃል፡፡ ከደብዳቤዎቹ አንዱ እንዲህ ይነበባል፡፡

“ራሶቹ ጥቂት የእግር መንገድ በሚያስጉዝ ርቀት ላይ ተሰይመዋል፡፡ በአንድነት ወደ እኛ እየመጡ ነው፡፡ አዛዣችንም እንድናፈገፍግ ብቻ እየነገረን ነው፡፡ የዚህም ውጤት መጨረሻው ገብቶናል፡፡ ጦሩ እየገፋ እስኪመጣ ብቻ እንጠባበቃለን፡፡ የኛ ነገር እያበቃ ነው፡፡ አሁን የማስበው አቅመቢስ ለሆኑት ወላጆቼ ነው፡፡ እነሱ ምንም ነገር ቢገጥማቸው ከጎናቸው እንድትሆን አደራ እልሃለሁ” ይላል መቶ አለቃ ሚሴና ለጓደኛው የላከው ደብዳቤ ነበር፡፡

የጣሊያን ወታደሮች ተስፋ መቁረጥም ቀስ በቀስ ወደ ዋናዎቹ የጦር መሪዎች እንደተዛመተ ሱልካፓ ዓድዋ የተሰኘው መፅሃፍ የጣሊያኑን መቶ አለቃ ሮፓ አሟሟት እማኝ አድርጎ እንዲህ ፅፎታል፡፡

“መቶ አለቃ ሮፓ ጦሩን የሚመራው ፈረስ ላይ እየሆነ ነበር፡፡ ሁለት ፈረሶቹም ከጭኑ ስር እየተመቱ ወድቀዋል፡፡ በመጨረሻው ቀን ፈረስ ላይ ለመውጣት ሲሞክር ጎኑን ተመታ፡፡ ሲወድቅ ያዩት የጣሊያን ወታደሮች ሊያነሱት ተሯሩጠው ሄዱ፡ እሱም እያቃሰተ እንዲህ አለ፡፡ ‘እኔ ሽማግሌ ስለሆንኩ ተውኝ፡፡ እናንተ ግን ወጣት ስለሆናችሁ ከዚህ መዓት ራሳችሁን አድኑ፡፡’ ይህን እንደተናገሩ በፊቱ ተደፍቶ ህይወቱ አለፈ፡፡”

በመጨረሻም የዚህ ተስፋ መቁረጥ በሽታ ወደ ዋናው ጄኔራል ዳቦርሜዳ ተዛመተ፡፡ ሁኔታውን በቦታው ላይ የነበረው ካፒቴን ሚናሪ እንዲህ ያስታውሰዋል፡፡ “ጄኔራል ዳቦርሜዳ ከመድፈኞቹ አጠገብ ወዲያ ወዲህ ሲወዛገብ አየዋለሁ፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ በላብ ተውጦ እና ሰውነቱ ተሸብሮ አየሁት፡፡ ሁኔታው ያሳዝናል ፤ በጭንቀት ብቻውን ያወራ ነበር፡፡ የጥይት በረዶ ሲዘንብበት ከሃሳቡ ይነቃና ፊቱን ወደ መኮንኖች በማዞር የተለመደውን ፈገግታ ያሳያል፡፡ ከጧት ጀምሮ ከሌሎች ክፍለ ጦሮች የደረሰው ወሬ የለም፡፡ ጦሩ የተሰወረ ይመስላል፡፡ እውነትም የመጨረሻ ቀናችን ጊዜ እየተቃረበ መምጣቱ የተሰማን በዚህ ጊዜ ነው ሲል ሚናሪ ይናገራል፡፡” በመጨረሻም ዳቦርሜዳ የፈራው አልቀረም ህይወቱን በኢትዮጵያ ጀግኖች ተነጠቀ፡፡ በደፈረው የሃገራችን መሬት ወድቆ ቀረ።

#የጥቁር_ህዝብ_ኩራት
#ዓድዋ_123 
#የኢትዮጵያውያን_ድል
#VictoryofAdwa
#Ethiopia

ብላቴናው አርቲስት ቴዲ አፍሮ ነጠላ ዜማ! ሹመቴን መልሱ” የሚል ድንቅ የሆነ ነጠላ ዜማዉን ለቀቀ

. ሹመቴን መልሱ
===========
ጎራዉ ያለ እንደሆን ባለምባራስ ደስታ
ዘራፍ ያለ እንደሆን ባለምባራስ ደስታ
ጠላት ይጠፋዋል መደበቂያ ቦታ
ፊታዉራሪ ፍላቴ
ግራዝማች በሀፍቴ
አዛዥ ለጥ ይበሉ
ቀኝ አዝማች በአካሉ
ዣንጥራር ባያለዉ
ደጃዝማች እንዳለዉ
እንዲህ ነዉ ካልቀረ አንጀት አርስ ሹመት
ለድል የሚያበቃ ጦር ይዞ ቢዘምት
የጣሊያን ጄኔራል ኮከቡን ደርድሮ
በለጋባሞ ዜር ስንት አሳሩን ቆጥሮ
ድል አርጎት የኛ ሰዉ ፎከራን በኩራት እንደተመለስን
ስልጣኔ መስሎን የሱን ስም ወረስን
ሟቹ ጄኔራልነዉ ገዳይ ፊት አዉራሪ
ስም እንዴት ይዋሳል ደፋር ሰዉ ከፈሪ
በጠላት ሬሳ ላይ ቆመን እያቅራራን
በድላችን ማግስት የኛን ሹመት ንቀን ከሆንን ኔተራል:
ባናዉቀዉ ነዉ እንጅ የዛን ቀን ሙተናል
ኮኔሌል አይበሉን ያገሩን ያገሩን አርበኛ
ጄኔራል አይበሉን ያገሩን አርበኛ
ፈረንጅ አይደለም ሀበሻ ነን እኛ
የሟች ስም አይደለም የገዳይ ሰዉ ምሱ
በደም ተበላሽቷል ባለ ኮከብ ልብሱ
ገድየዉ ሳበቃ ባስታጠቁኝ ወኔ
በሱም አይጥሩኝ ቆሞ እንዲሄድ በኔ
ጄኔራል ድል ሆኖ ስላለፈች ነፍሱ
ይበሉ ጃንሆይ ሹመቴን መልሱ
ፊት አዉራሪ ካታካምቦ
ሊጋባ ዴሊቦ
አዛዥ ለጥ ይበሉ
ቀኝ አዝማች አካሉ
ዣንጥራር አበጋዝ
እንዲህ ነዉ አንጀት አርስ ሹመት
ለድል የሚያበቃ ጦር ይዞ ቢዘምት
ፈቃድወ ከሆነ ግርማዊ ተፈሪ
እንዳገሬ ሹመት በሉኝ ፊት አዉራሪ
በሟች ከመጠራት ስለሚሻል እሱ
ይበሉ ጃን ሆይ ሹመቴን መልሱ

የዛሚ 90.7 ሬዲዮ “ክብ ጠረጴዛ” ፕሮግራም ለዓመታት ስንቱን ንጹሃን ዜጋ ውስጡን እንዳቆሰለና እንዳደማ ቤት ይቁጠረው (ጋዘጠኛ ኤልያስ ገብሩ)

የዛሚ 90.7 ሬዲዮ “ክብ ጠረጴዛ” ፕሮግራም ለዓመታት ስንቱን ንጹሃን ዜጋ ውስጡን እንዳቆሰለና እንዳደማ ቤት ይቁጠረው …ብዙዎቹን እያዘንን፣ እየቆሰልን ጭምር ለዓመታት ሰምተናቸዋል።

ከሚሚ ስብሃቱ ከማልረሳቸው መካከል …መስከረም 03 ቀን 2003 ዓ.ም እነ አንዷለም አራጌን (ስሙ ተጠቅሶ) “መንግስት እንዴት ይታገሳቸዋል፣ ህጋዊ እርምጃ ሊወሰድባቸው ይገባል። እስከመቼ ይታገሳቸዋል” የሚል ይዘት ያለው የይታሰሩ ሃሳቧን በፕሮግራም አስተላልፋ፣ በዚሁ ዕለት ከሰዓት በኋላ አንዱዓለም አራጌ ከእስክንድር ነጋ ጋር በግፍ ታስረው ወደማዕከላዊ ተልከዋል።

አንጻራዊ ልውጥ የተባለው አንዱ የግፍ እስረኞች መፈታት መሆኑ ይታወቃል። እና ሚሚ “የጮህኩለት ለውጥ እውን ሆናል” በማለት ቁም ነገር መጽሄት ላይ የሰጠችው ቃለ ምልልስ፣ እነአንዱዓለምንና የግፍ እስረኞችን ማስፈታት አይደለም። በግልጽ ይታሰሩ ስትል ነበርና!

ስንቱን በትውስታ ዘርዝረን እንችላለን ….ማፈር አለመቻል ግን በደንብ አለ!

#ኢትዮጵያ!
#ዓለም!
ጋዘጠኛ ኤልያስ ገብሩ

‹‹ሉሲ የሰላምና የፍቅር ጉዞ›› – ቋሚ የጭካኔና ግፍ አዋጅ፣ በድን አጽም የሰላምና የፍቅር አማላጅ! ከዶክተር ድሉ ዋቅጅራ

‹‹ሉሲ የሰላምና የፍቅር ጉዞ›› – ቋሚ የጭካኔና ግፍ አዋጅ፣ በድን አጽም የሰላምና የፍቅር አማላጅ!

ከዶክተር ድሉ ዋቅጅራ
.
.
ግልብ አእምሮ ደርዝ ያለው፣ እየተቀናጀ የሚጎለብት ተግባር ሊከውን አይችልም፤ ይህ ደግሞ የአብዛኞቹ የለውጡ መሪዎች መለያ እየሆነ ነው፡፡ 
.
የለውጡ መሪዎች በህይወት ቆመው የዜጎችን ቤት እያፈረሱ፣ ህጻናትንና አዛውንቶችን ሜዳ በትነው ሰላምና ፍቅር እየነሱ፣ የበሰበሰ አጥንት ከሙዚየም አውጥተው ለሰላምና አፍቅር አማላጅነት ይልካሉ፡፡ በዚህ ዘመን ከዚህ በላይ ድንቁርና የወለደው ግልብነትና የህዝብ ንቀት የወለደው ምጸት አይገኝም፡፡ 
.
ከወራት በፊት የአዲስ አበባን የመንገድ ዳር ለንግድ ፈቅዶ፣ የእግረኛ መንገድ ሳይቀር በላስቲክ ዳስ ያዥጎረጎረ፣ የለውጥ መሪ ዛሬ የከተማ ውበት ጠፋ ብሎ የህዝብ ጎጆ ይደረምሳል፡፡ በፍርድ ቤት የእስር ማዘዣ የተቆረጠለትን ተጠርጣሪ ወደ ህግ አቅርቦ ህግን ያላስከበረ የለውጥ መሪ፣ ከህግ በላይ ማንም እንደሌለ ለማሳየት የዜጎችን መኖሪያ በቡልዶዘር ይንዳል፡፡ 
..
አዲስ አበባ ላይ ዜጎችን ፍቅርና ሰላም ነስተው ደም እያስለቀሱ፣ አጽም ለሰላምና ፍቅር ምልጃ አፋርና ሱማሌ ይልካሉ፡፡ ለነገሩ ካለማወቅ የተደረገ ቢሆንም፣ ቋሚ የጭካኔና ግፍ አዋጅ፣ በድን አጽም የሰላምና የፍቅር አማላጅ መሆናቸው ዘመኑን በሚገባ ይገልጸዋል፡፡ 
.
አንድ ነገር ግን መታወቅ አለበት፤ ለውጡ ያለ ጥያቄ የምንቀበለው ሀይማኖት አይደለም፤ መሪዎቹም እየበደሉ እንኳ ተንበርክከን የምንማጸናቸው መላእክት አይደሉም፡፡ ይህን የሚገነዘብ የለውጥ መሪ ፣ ለውጡን ለማምጣት ከፈሰሰው የሰማእታት ደም ጋር በለውጡ ሳቢያ የሚፈስ የተበደሉ ዜጎች እንባ እንዲቀላቀል መፍቅድ የለበትም፡፡ ያለዚያ ወደ ደምና እንባ ቅብብሎሽ ታሪካችን እንመለሳለን፡፡

እነሆ መሃከለኛው መንገድ ! አማራጭ የሽግግር ኣሳብ

ገለታው ዘለቀ ከተባበረችው አሜሪካ

2/19/19

መግቢያ

ኢትዮጵያ ሽግግር ላይ በመሆኗ ዜጎቿ ተስፋን ሰንቀዋል:: ምንም እንኳን ስጋቶች በግራም በቀኝም የተደቀኑ ቢሆንም ነገር ግን የህዝቡ ተስፋ ሃያል ነው። በተጨባጭ እየተወሰዱ ያሉ የለውጥ ርምጃዎች ብዙዎችን አነቃቅተዋል። ታዲያ የከረምንበት ፖለቲካ ውጤትና ራቅ ካለ ዘመን ጀምሮ ሲንከባለል የመጣ ችግር አለና ይህን የማሰናከያ ድንጋይ ገለል ኣድርጎ ዴሞክራቲክ ኔሽን ለመሆን ስርዓታዊ ለውጦችን ይጠይቃል። ወደ ዴሞክራሲ ለምናደርገው ሽግግር በርግጥ የስርዓቶች ለውጥ ብቻ ሳይሆን የአስተሳሰብ ለውጥ ማምጣት ኣለብን። ትርክቶቻችንን ከውጭ ወደ ውስጥ፣ ከውስጥ ወደ ውጪ እያገላበጥን አይተን የሚጠቅመንን ይዘን የማይጠቅመንን እያራገፍን በፍጥነት ወደ ዴሞክራሲ ማምለጥ ኣለብን።

እኛ ኢትዮጵያውያን እንደ ታሪካችን አልተራመድንም። ከብዙ ኣፍሪካውያን ወደ ኋላ ቀርተናል። ይህ ሊቆጨን ይገባል። በመሆኑም በሽግግሩ ወቅት የተሻለ ስርዓታዊ ለውጥ ለማምጣት የተሻለና የላቀ ኣሳብ ያስፈልገናል። ዶክተር ኣብይ እንዳሉት የምናመጣው የመፍትሄ ኣሳብ ደግሞ ሃገር በቀል የሆነ መሆን ያስፈልገዋል። ሀገሮች በኩረጃ ችግሮቻቸውን ኣልፈቱም። ከሌላው ዓለም የሚማሩት ነገር ቢኖርም ነገር ግን ሃገሮች ሁሉ የየራሳቸውን መፍትሄ እያመጡ ነው ችግራቸውን የፈቱት። ስለዚህም ችግሮቻችንን በማጥናት ሃገር በቀል መፍትሄ ለማምጣት መጣር አለብን። ከዚህ በፊት ስንከተላቸው የነበሩ ትርክቶች አንዳንዶቹ ከኛ ጋር የማይሄዱ ነበሩ። የኛን ማህበረሰብ በምልዓት የማይገልጹ ነበሩ። ታዲያ እነዚህ ትርክቶች ከኛ ጋር የማይሄዱ ሆነው በግድ

እንዲሄዱ ስናደርግ የሚፈጠር ማህበራዊ ምስቅልቅል ይኖራል። ችግሮቻችንን መለየትና መፍትሄ ማምጣት የኛ ድርሻ ነው። 

ሃገርን ሃገር የሚያሰኘው በጠገጉ ስር ያለው ማህበራዊ ት ስ ስር ነው። ይህ ትስስር ደግሞ የተለያዩ መርሆዎች ይኖሩታል። እኛ ኢትዮጵያውያን የሚኖሩን የትስስር መርሆዎች (organizaing principles) ለሃገራችን ሰላምና ልማት እጅግ ወሳኝ ናቸው። ብሄሮችን እንዴት ቀጥታና ተዋረድ ማስተሳሰር ፈለግን? የብሄሮችና የዜጎች ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትስስሮች በምን ህግ ሊገዙ ይገባል? የሚለው ነገር በሚገባ መጠናት አለበት። 

በዚህች ጽሁፍ ስር የማቀርበው ነገር ለሃገራችን መሰረታዊ ችግሮች አማራጭ መፍትሄ ለመስጠት ነው። በተቻለ መጠንም በአዲስ ሃገራዊ ማህበራዊ ኪዳን ላይ በሚደረግ የከፍተኛ ቃል ኪዳን ትስስር የኢትዮጵያን መጻኢ እድል ለማስተካከል ነው።

ወደ መፍትሄ ከመሄዴ በፊት ድህነቱ፣ የመልካም ኣስተዳድሩ ችግር እንዳለ ሆኖ ነገር ግን ከነዚህ ችግሮች እንዳንወጣ የሚያናቁሩ፣ሰላም የሚነሱ፣ ዴሞክራሲን እንደ ልብ እንዳንለማመድ የሚያደርጉ መሰረታዊ ችግሮች በፖለቲካ ትርክቶቻችንና በመንግስት ስርዓታችን ውስጥ አሉ። በስርዓታችን ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ኣንዳንድ ኤለመንቶች ሰላማችንን የሚያናጉ ግጭትንና መፈናቀልን የሚያመርቱ ናቸው። የማንነት ጉዳይ፣ የአስተዳደር ጉዳይ፣ የወሰን ጉዳይ ከግጭት መንደር ለምን አይርቁም? መፈናቀልና ግጭት ለምን ይከተሏቸዋል? ከፍቅርና ከመደመር ሰፈር ርቀው ለምን ለግጭት ቀረቡት? ከስርዓቶቻችንና ከትርክቶቻችን ምን ዓይነት ሶሻል ካፒታል አመረትን? ስርዓታችን ለኢኮኖሚ እድገትና ለፍትህ ያላቸው አስተዋጾ ምን ይመስላል? ብለን የምንመረምርበት ዘመን ላይ ነን። በቅርቡ የኢትዮጵያ ፓርላማ እነዚህን ጉዳዮች ያጠና ዘንድ ኮሚሽን ማቋቋሙ የሚያሳየው ቁምነገር በነዚህ ጉዳዮች ኣካባቢ ብዙ አሳሳቢ ችግሮች መኖራቸውን ነው:: ሃገራችን ኢትዮጵያ በረጅም 

ዘመን ታሪኳ ብዙህ ሆና የኖረች ሃገር ብትሆንም ነገር ግን ብዝሃነትን በሚገባ አላስተናገደችም። በተለይም ከብሄር ማንነት ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ላይ ብዙ ችግሮች አሉባት። በመሆኑም ሃገራችን ለውጥ በፈለገችበት በ1960ዎቹ የተማሪዎች ንቅናቄ ጊዜ የማንነት ጉዳይና የብሄር ጥያቄ መነሳቱ ትክክል ነበር። ችግሩ ይህንን ጥያቄ ጠቅላይ ጥያቄ በማድረግ የችግሮቻችን ሁሉ ማጠንጠኛና ሁለንተናዊ ማሳያ ሆኖ መቅረቡ ነበር ስህተቱ ። የብሄር ጥያቄ ጥያቄዎችን ሁሉ ጠቅልሎ መዋጡ በኢትዮጵያ ውስጥ ሁሉን ነገር ፖለቲካዊ ወደአደረገ የፖለቲካ ትርክትና ስርዓት ውስጥ ኣስገብቶናል። የሰውን ልጅ ሁለንተና ፖለቲካዊ  ማድረግ  ደግሞ  ከዴሞራሲ  መርሆዎች  ጋር ስለማይሄድ ይህ ትርክት ወደምንፈልገው ዴሞክራሲ እንዳንዘረጋ እየጠለፈ ይጥለን ጀመር። ፖለቲካዊ ያደረግነው ማንነት ሁሉ የስልጣን ቅርምት ውስጥ ከቶናል። ዋናውን የጋራ ችግር መዋጋት ትተን ወደ ጎን በማንነት፣ በአስተዳደር፣ በወሰን ጉዳይ ተያያዝን። ስለዚህም የሚፈለገውን ያህል ሁለንተናዊ ለውጥ ማምጣት አልቻልንም። በርግጥ ለዚህ ተጠያቂው ሁላችንም ነን።

እንግዲህ ሃገራችን ሽግግር ላይ ስትሆን ወደፊት የተሻለ ስርዓት ገንብታ ለመኖር እንድትችል ከዚህ ለውጥ ባሻገር የምትገባበትን ቤት በዚህ በሽግግሩ ወቅት ኣሳምረን መስራት ኣለብን። ይህ የሽግግር ወቅት የጽሞና ጊዜ ነው። ከፍ ሲል እንዳልኩት በተለይ የማህበረሰባችንን የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካና ማህንበራዊ ትስስሮች የፍልስፍና መሰረት፣ ከዴሞክራሲ መርሆዎች ጋር ያላቸውን ዝምድና፣ የሚያመርቱትን ማህበራዊ ካፒታል፣ ወዘተ የምንገመግምበት ሰዓት ነው።

መፍትሄ ወዳልኩት ኣሳብ ከመምጣቴ በፊት ያሉትን መሰረታዊ ስርዓታዊ ችግሮች እንደሚከተለው አንድ ሁለት እያልኩ ላቅርብና ወደ መፍትሄው እመጣለሁ

ጎልተው የሚታዩ ችግሮቻችንና በሽግግሩ ወቅት መፍትሄ የሚሹ ችግሮች የሚከተሉት ናቸው:-

1.  የማንነት ኣያያዝ

በኢትዮጵያ ውስጥ ሁለት ገንነው የወጡ ማንነቶች ያሉ ሲሆን እነዚህ ማንነቶች የብሄር ማንነትና ብሄራዊ ማንነት ናቸው። እነዚህ ሁለት ማንነቶች ሳይፈራረሱ፣ ሳይደባደቡ አብረው የሚኖሩበት ስርዓት አልገነባንም። አንዱ ዋና ችግር ይሄ ነው። ህገመንግስታችን ራሱ ኣንቀጽ ሰላሳ ዘጣኝ ላይ ኣንዱን ፈራሽ አንዱን ኣፍራሽ ያደርገዋል። ብሄራዊ ማንነት በብሄር ማንነት ሊመታ ወይም ሊፈርስ የሚችልበት ስርዓት ነው ያለን። በየትኛውም ጊዜ ሊፈርስ በሚችል የጋራ ቤት ውስጥ ዘላቂ ሰላምና ልማት ኣይታሰብም። ኣንዱ ችግራችን ይሄ ነው። እንደ ስርዓት ብቻ ሳይሆን በብሄራዊ ማንነት   ዙሪያ ግልጽነት የለም። የብሄር ማንነት ስንል የሚገነባው ከባህል ከቋንቋ በተያያዘ ሲሆን ብሄራዊ ማንነትን የሚሰራው ኤለመንት ምንድን ነው? ብለን ኣጥብቀን ኣልጠየቅንም። የብሄራዊ ማንነት መገንቢያ ኤለመንቶችን አንጥረን አላወጣንም። በመሆኑም ብሄራዊ ማንነታችን ወይም ኢትዮጵያዊነታችን በአደባባይ ኣቅም ኣንሶት ሰነበተ። ዛሬ ዶክተር ኣብይ ከወደቀበት ኣንስተው ከፍ ሲያደርጉት ሲታይ የኢትዮጵያ ህዝብ ደስ ብሎት እናያለን። ፖለቲካችን ቤቱን የሰራው በዋናነት በየብሄሩ ሲሆን ብሄራዊ ማንነትን እንደ መገናኛ መድረክ ብጤ ያየነው ይመስላል። ይህ ደግሞ ኣካባቢያዊ ጡንቻዎችን ያፈረጥምና የርስ በርስ ግጭትን ያመጣል።

2. የ “ራስ” (Self) ትርክት

በስርዓታችን ውስጥ መስመር ያለፈ የ “ራስ” (Self) ትርክት መኖሩ ኣንዱ ሌላ ችግር ነው።

ራስ (self) ማለት ምን ማለት ነው? ከሚለው ብያኔ ጀምሮ ወደታች በተግባር ሲወርድ ብዙ እምቅ ግጭቶችን ይዟል። ይህ ትርክት ምን እንደሆነ ኣልተመረመረም። ይህ ትምህርት ከሚከተሉት ማእዘኖች አንጻር በጥብቅ ሊታይ ይገባዋል:-

1. ከኢትዮጵያውያን ማህበረ ፖለቲካ (sociopolitics) ታሪክና ጉዞ ኣንጻር

2. ከኢትዮጵያውያን ብሄሮች ስነ-ኑባሬ (ontology) አንጻር

3. ከኢትዮጵያውያን የሃይማኖት ዋና እሴቶች (core values) አንጻር

4. ከኢትዮጵያውያን የወደፊት እድል (future of the nation) ኣንጻር

5. ይህ ትርክት በጋራው ቤታችን ውስጥ ምን ዓይነት የስልጣናት ቀመር (power sharing formula) ይጠይቃል ከሚለው ጥያቄ አንጻር

6. በጋራው ቤታችን ውስጥ ምን ዓይነት ማህበራዊ ሃብት (social capital) ያመነጫል ከሚለው አንጻር

7. ይህ ትርክት ከዘመናዊነቱና ዴሞክራሲን ለማንሸራሸር ከመርዳቱ ኣንጻር በጥብቅ መመርመር ይገባናል።

በስርዓቶቻችን ውስጥ የምናመጣቸው ትርክቶች ሁሉ የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካና የማህበራዊ ትስስሮቻችንን የሚገዙ ገዢ ሃሳቦች ስለሆነ እነዚህ ጉዳዮች ላይ ብዙ እውቀትና ኣቅምን ማፍሰስ ኣለብን። እኔና እኛ ሳይጠፋፉ ወይም ኣንዱ ባንዱ ላይ ሳይነሱ የሚያኖር ስርዓት ያስፈልጋል።

  1. የበጀት ፌደራሊዝም (fiscal federalism)

የበጀት ፌደራሊዝማችን በራሱ በተለይ ራስ ከሚለው ትርክት ጋር ተያይዞ የተፈጥሮ ሃብት ኣጠቃቀምና የባለቤትነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ ብዙ እምቅ ችግሮችን ኣምጥቷል። የተፈጥሮ ሃብትን የመቀራመት ችግር ውስጥ ገብተናል።

  1. የማንነት ድምጽ (identityvote)

የገባንበት የፖለቲካ ትርክት በጅጉ ለማንነት ድምጽ (identity vote) ኣጋልጦናል። ይህ ችግር በዴሞክራሲ መርሆዎች ላይ እንድንረማመድ የሚያደርግ ሁኔታ ተፈጥሯል። ብሄሮች የብሄራቸውን ሰው በስልጣን 

ከፍታዎች ላይ የማየት አይን በሃይል ተከፍቷል። ደምና ኣጥንት ቆጣራ ውስጥ ገብተናል።

5. ብዝሃነት

ሃገራችን ኢትዮጵያ ብዙህ እንደመሆኗ ይህንን ብዝሃነት ለማስተናገድ የሄደችባቸው ሁለት መንገዶች አደገኞች ናቸው። ቀደም ባለው ጊዜ ወደ ምስለት (assimilation) ያዘነበለ አካሄድ የተከተለች ሲሆን ይህም የብሄሮችን ማንነት አደጋ ላይ የጣለ ነበር። ባለፉት ሃያ ሰባት ኣመታት አካባቢ የተከተልነው የሶሺዮ ፖለቲካል ቲየሪ ደግሞ ከምስለት ወደ ልዩነት ያደላ የፖለቲካ ኣስተሳሰብ ነበር። ሁለቱም ከብዝሃነት ጋር የተጻረሩ ኣካሄዶች ናቸው። ብዝሃነት ማለት በአንድ የፖለቲካና ኢክኖሚ ማህበረሰብነት ጥላ ስር ብዙ ብሄር ወይም ሃይማኖት ሆኖ መኖር ማለት ነው። ብዝሃነት ማለት አንድነት ከብዙህነት ጋር ተደምሮ የሚኖርበት ረቂቅ ህግ ነው። ብዙነት ለአንድነት ተግዳሮት የማይሆንበት፣ ኣንድነት ለብዙነት ተግዳሮት የማይሆኑበት ስርዓት ማለት ነው። እኛ የተከተልናቸውን ስርዓቶች ስናይ ቀደም ሲል የነበረው ስርዓት አንድነት ለልዩነቶች ተግዳሮት እንዲሆን ያደረገ ሲሆን ኣሁን ያለነብት ስርዓት ደግሞ ልዩነት ለአንድነት ተግዳሮት እንዲሆን ኣድርጓል። በተለይ አሁን ያለንበት ስርዓት ልዩነትን እያፈካ አንድነትን ያኮሰሰ ነው። ይህ ትርክት ኣደገኛ ነው። ባለፈው ጊዜ በኢትዮጵያ ትቅደም! ስም የብሄሮች ማንነት

ተደፈጠጠ። በአሁኑ ጊዜ በብሄር ይቅደም! ስም ኢትዮጵያዊነት በብሄር ክንድ ተደፈጠጠ፣ ፈራሽ ሆኖ ተዋቀረ። በደርግ ጊዜ ብሄር ፈራሽ ሊሆን ይችላል እንጂ ኢትዮጵያ ኣትነካም የሚል ነበር። በአሁኑ ጊዜ ደግም ተቃራኒው መጣ። እነዚህ ሁለቱም ትምህርቶች ከብዙህነት (pluralism) ጋር የተጋጩ ናቸው። ብዙህነት ልዩነትንና ኣንድነትን በአንድ ጊዜና ቦታ ማኖር የሚያስችል ሳይንስ ነው። ብዙህነት 

ማንነቶችን ውድድር ውስጥ ሳያስገባ ማስተናገድ የሚችል ነው። አንድ ዜጋ ከሃይማኖትህ ማንነት እና ከሃገርህ የቱ ይበልጥብሃል? ተብሎ መፈተን ወይም መጠየቅ የለበትም። ሁለቱንም ወዶ መኖር ይችላል። ዋናው ጉዳይ ግን ለሃይማኖቱና ለፖለቲካው የተለያዩ መስመሮችን ማበጀት ነው የብዝሃነት ትምሀርት የሚመክረን። የብሄር ማንነትና የብሄራዊ ማንነት ጉዳይም እንደዚሁ ነው። ማበላለጥ ሳይሆን ሁለቱንም ሳይፈራረሱ መጠበቅ ነው ብዝሃነት ትምህርት የሚያስተምረን። የሃገራችን ፖለቲካ መሰረታዊ ችግር እዚህ ጋር ነው።

  1. ሳቢ ህግ (pulling force)

በፌደራል ስርዓታችን ውስጥ ያለው ሳቢ ህግ (pulling force) ማንነት በመሆኑ ሌሎች ማንነቶችን የሚገፋ ሃይል አምርቶብናል። ይሄ መሰረታዊ ችግር ነው። ስርዓቱ ሲዋቀር እንዲሳሳቡ የተፈለገው ተመሳሳይ ማንነቶች በመሆናቸው ልዩነትንና ኣንድነትን በኣንድ ጊዜና ቦታ ማኖር የሚያስችል ስርዓት እንዳንገነባ ተግዳሮት ሆኖብናል። ተመሳሳይ ማንነቶች ሲሳሳቡ ልዩ የሆነውን ማንነት የሚገፋ ሃይል ሳናውቀው ኣምርተን ቁጭ ኣልን። በአንድ የፖለቲካ ዩኒት ውስጥ ልዩነቶች በሰላም መኖር አልቻሉም። ዛሬ በሚሊዩን የሚቆጠር ዜጋ የሚፈናቀለው የዚህ የመሳሳብ ህግ የፈጠረው ኣላስፈላጊ ሌላ ገፊ ሃይል ስላመጣብን ነው ::

  1. የኔሽን ግንባታ

የኔሽን ግንባታ ስራችን ተጓቷል። የተበታተነ ኔሽን ሆነን ኣንድ ሃገር ለመመስረት ኣንችልም። የምንከተለው የፖለቲካ ትርክትና ስርዓት ለኔሽን ቢዩልዲንግ ስራ የማይመች ነው። አንድ ሆነን ብዙ ደግሞ ብዙ ሆነን አንድ መሆን የምንችለው ቡድኖች ለሃገር የሚሆኑ መስዋእቶችን ኣጭደን ሳንበላ ስንቀርና ለብሄራዊ ማንነት መስሪያ የሚሆነውን ዋልታና

 ማገር ምሰሶ አዋጥተን ስንሰራ ነው። አንድ ነን የሚያሰኘን የሆነ አንድ የሚያደርገን ዋና ጉዳይ ሲኖር ነውና ለዚህ ለብሄራዊ ማንነት ሁላችን መዋጮውን ማዋጣት አለብን።

  1. ምርጫ

ዴሞክራሲያዊ ምርጫ የሚኖረው የሃሳብ ትግል ባለበት ሃገር ነው። መድብለ ፓርቲ ስርዓት ማለት ሜዳው ተስተካክሎ፣ ዳኛና ታዛቢ ባለበት ህዝብ ፈራጅ ሆኖ ፓርቲዎች በሃሳብ የሚታገሉበት ጨዋታ ነው። በዚህ ጊዜ ታዲያ መሰረታዊ ጉዳዮች በብሄራዊ መግባባት የሚፈቱ ናቸው። መጀመሪያ ብሄራዊ መግባባት (national concensus) ያስፈልጋል። በሆነ የጋራ ማንነት ስር ነው ምርጫ የሚኖረው። ግማሹ በብሄር ግማሹ በበብሄራዊ ኣንድነት ግማሹ በመልክዓምድር ተሰልፎ የምርጫ ድግስ የለም። ዴሞክራሲ መደላድል ይጠይቃል። የሆነ የጋራ ማንነት ሳይኖር ዴሞክራሲ የለም። ዴሞክራሲ በአንድ የሆነ ማንነት ስር ያደሩ ዜጎችን የሚያስተዳድር ስርዓት ነው። ስለዚህ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ የሆኑ ስር ነቀል ልዩነቶችን ይዘን ምርጫ መግባት ወደ ዴሞክራሲ ኣያሻግረንም። ለዚህ ነው በሽግግሩ ሰዓት ኪዳን ያስፈልጋል የምላችሁ። የጋራ የሆነ መነሻ ይዘን ከዚያ በሁዋላ በፖሊሲ ተያይዘን መከራከር እንችላለን። በመድብለ ፓርቲ ስርዓት ውስጥ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ለምርጫ ሮጠው አንዱ አንዱን እያሸነፈ ስልጣን ቢቀያየሩም የመጠፋፋት እድል ግን የለም። እርስ በርስ አይጠፋፉም። የሃገራችን ፖለቲካ ከምርጫው በሁዋላ መጠፋፋት አለበት። ለምሳሌ የአንድነት ፓርቲ ኣሸንፎ ስልጣን ቢይዝ የፖለቲካ መስመሩና የፌደራል ስርዓቱ የተለየ ስለሆነ በዘውግ ላይ የቆሙትን ፓርቲዎች ያጠፋል። በዜግነት ላይ የተመሰረተ ፖለቲካውን ተግባራዊ ሲያደርግ እነዚህን የብሄር ድርጅቶች ያጠፋል። 

የብሄር ድርጅቶች ደግሞ ይህን ያንድነቱን ፓርቲ አንዳንድ የህብረተሰብ ክፍል ሳይቆጣ እንዲኖር ለማድረግ መደራጀታቸውን ኣይከልክሉ እንጂ ወደ ስልጣን እንዲመጡ ኣይሹም። እንዲህ ዓይነት ስርነቀል ለውጥ የያዙ ሃይላት ወደ ምርጫ ሳይሆን መጀመሪያ መሄድ ያለባቸው ወደ ብሄራዊ መግባባት ነው። የሆኑ ዋና ዋና ጉዳይ ላይ ቃል ኪዳን ገብቶ ነው ምርጫ መግባት የሚቻለው። 

ኣሰላለፍን ማሳመር ያስፈልጋል። አሁን ባለው ሁኔታ ምርጫ ማድረግ የአንዱን በሬ ፊት ወዲህ የሌላውን በሬ ፊት ወዲያ ኣድርጎ እርሻ እንደመጀመር ይቆጠራል። 

9. የሃብት ዝውውር

በኢትዮጵያ ውስጥ በአስራ ዘጠኝ ስልሳዎቹ የተነሳው የመሬት ላራሹ ጥያቄ ታሪካዊና ፍትሃዊ ነበር። ይሁን እንጂ ሃገራችን ይህንን ጥያቄ እስካሁን በተገቢው መንገድ ባለመመለሷ ለተለያዩ ችግሮች ኣንድም በቀጥታ ኣለያም ለችግሮቹ ገባር በመሆን እየጎዳን ነው። በኢትዮጵያ ሁኔታ ስለሃብት ዝውውር ስናነሳ መሬት ነው ትልቁ ሃብትና ይህንን ሃብት የያዝነብት ፖሊሲ መጠናት ኣለበት። የሃብት ዝውውራችን ጉዞ የሚያሳየው መሬት ኣንዴ በፊውዳል፣ ቀጥሎ  በመንግስት ፣ ቀጥሎ በብሄሮች አካባቢ ነው

የተዘዋወረው። በተለይ በአሁኑ ሰዓት ስቴቶች የመሬት ባለቤት በመሆናቸው የመጣ የወሰንና የድንበር ጥያቄ ኣለ። ከዚህ በላይ የዜጎች መሰረታዊ መብት ኣልተከበረም። ዋና ዋና የምንላቸው ችግሮች ከፍ ሲል ያነሳናቸው ሲሆኑ እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍ የሚከተለው መፍትሄ ይጠቅማል።

የመፍትሄ ኣሳብ

1. አዲስ ሃገራዊ ኪዳን መግባት

ሃገራዊ ኪዳን ማለት ህገመንግስት ማለቴ ኣይደለም። ሽግግራችን እጅግ ያማረ እንዲሆን ህዝቡን መሰረት ያደረገ ቃል ኪዳን ውስጥ መግባት የሽግ ግራችን የመጀመሪያ ደረጃ ቢሆን መልካም ነው። ይህ ቃል ኪዳን የምለው ጉዳይ በይዘቱና በአገላለጹ የኢትዮጵያውያን ቃል ኪዳን (covenant)ነው። በውስጡ ሊይዛቸው ከሚገባቸው ጉዳዮች መካከል:-

1. ኢትዮጵያውያን ከእግዚአብሄር በታች የማትከፋፈል ኣንድ ህዝብ ነን የሚል

2. ተደምረን ለመኖር፣ ብዝሃነትን ለማክበር እርስ በርስ ለመረዳዳትና ለሰላም መቆማችንን የሚገልጽ

3. ኢትዮጵያውያን ለተገፉ ሁሉ የምንቆም መሆናችንን የሚገልጽ

4. ያለንን ሃብት የኔ የኔ ሳንል የእኛ ብለን ለመኖር ቃል መግባታችንን የሚገልጽ

5. ኢንተርጀነሬሽናል የሆነ የተፈጥሮ ሃብት ኣጠቃቀምን በሚመለከት

6. ለዓለም ሰላምና ልማት መቆማችንን የሚገልጽ

7. የሪፐብሊክ ሃገር መመስረታችንን የሚገልጽ

8. እሴቶቻችንን ኣክብረን የምንኖር ኢትዮጵያዊ ጨዋነትን የምናከብር መሆናችንን የሚገልጽ ቃል ኪዳን ያስፈልገናል።

ይህ ቃል ኪዳን በህዝቡ ከተፈረመ በሁዋላ ለትውልድ የምናሻግረው ዶግማዊ ኪዳን ይሆናል። ሃገር የሚባለው ጠገግ የሚቆመው በዶግማና ቀኖና ነው። ሃገር ራሱ ዶግማ ሲሆን በየግዜው የምናሻሽለው ህግና ኣሰራር ደግሞ ይኖረናል። የሚነካና የማይነካ ቃል ነው ሃገርን የሚመሰርተው። ስለዚህ ዶግማዎቹን ኣውጥተን ከላይ ማስቀመጥ ሽግግራችንን በጣም ያሳምረዋል። ለወደፊት የረጋ ሃገር ይኖረናል። ይህ ኪዳን ፖለቲካዊ ሳይሆን ማህበራዊ ይሆንና የሃገራችን ዶግማዊ ዶክመንት ይሆናል።

ዶግማዊ ቃል ኪዳን ያስፈልገናል የሚያሰኘን በሚከተሉት ጉዳዮች ነው

  1. ለኔሽን ቢዩልዲንግ መሰረት ስለሚሆን ነው። ኔሽን ሊገነባ የሚችለው በዚህ ቃል ላይ ነው።

2. ለሲነርጂ ወይም መደመር። ተደምረን ለመኖር መደመር የሚያመጣውን የላቀ እሴት (greater value) ለመጠቀም ይህ ቃል ኪዳን ኣሳሪ ይሆናል

3. በህገመንግስት የማይገለጹ የሞራል፣ የህብረተሰብ መተሳሰሪያ ገመዶችን ኣንጥሮ ኣውጥቶ በቃለ መሃላ ለማጽናት። እንዋደድ፣ እንረዳዳ እንተማመን የሚሉትን ዋና ዋና የህብረተሰብ መተሳሰሪያ መረቦች በህገ መንግስት ኣንገልጻቸውም። እነዚህ ማህበራዊ ሃብቶች ከምንም በላይ ለህዝብ ትስስር መሰረት ናቸውና ይህንን ለመግለጽ ይጠቅመናል። ማበራዊ ሃብት(social capital) ረቂቅ ከመሆኑ የተነሳ

በህገ መንግስት ኣይገለጽም። በዚህ ኪዳን ላይ ግን በመሃላ መልክ መግለጽ ይቻላል።

4. የማይነበብ የህዝብን ዶግማዊ ኪዳንን (hiden covenant) ለመግለጽ። ዶግማዊ ኪዳናችንን ኣውጥተን መግለጻችን ኣንድነትን ያጠነክራል።

5. ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትን የመቀራመት ኣዝማሚያ ስለነበረ ይህንን ለመለወጥ ይህ ኪዳን ያስፈልጋል።

6. አርበኛ ዜጎችን ለማፍራት። ሃገር ወዳድ ዜጎችን ለማፍራት።

(covenant patriotism) 7. ለብሄራዊ መግባባት

8. መንግስታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች ይህ ኪዳን ለራእያቸው መነሻ የተጻፈ ሰነድ ይሆንላቸዋል።

9. ሃውልት ኣድርገን እናስቀምጣለን። ተተኪው ትውልድ ይጠብቃል።

10. የሃገርና የህዝብ ልእልናን ከፍ ኣድርጎ ለማሳየት

በነዚህ በሌሎች በርካታ ምክንያቶች ይህ ኪዳን ይረዳናልና በሽግግር ወቅት ይህ ነገር ቢታሰብ መልካም ነው።

2.  ሄራን ማሻሻል

(ሄራ የምለው ህገመንግስት የሚለው ቃል በሚገባ ገላጭ ስላልሆነ ነው በዚህ አገባብ ሄራ ማለት ህገ-መንግስት ወይም(constitution) ማለት ነው።)

ሄራችን እንደ ሰነድ የሚሻሻል ዶክመንት ይሆናል። ትልቁ ቀኖናችን ይሆናል። ይህ ሄራ ሲዘጋጅ የሪፐብሊክን ጽንሰ ሃሳብ የሚገልጽ፣ ለቡድንና ለግል መብት

የሚጨነቅ፣ ማንነትን የማያፈራክስ፣ የኢትዮጵያን ዳርድንበር የሚገልጽ፣ ለገጸ በረከቶቿ እውቅና የሚሰጥ፣ ዘመናዊ የሆነ ሄራ ያስፈልገናል። በተጨማሪ ሄራችን ለህዝቡ ሃገራዊ ቃል ኪዳን ክብርና ልእልና የሚሰጥ ይሆናል። ሄራችን መሰረታዊ ህግ ይሆነናል።

  1. የሁለትዮሽ የፌደራል ስርዓት

የሁለትዮሽ የፌደራል ስርዓት (Two wing Federalism) ማለት ምን ማለት ነው?

ሁለትዮሽ የፌደራል ስርዓት ማለት የብሄር የባህል ፌደራል ስቴትና የዜጎች ፌደራል ስቴት በአንድ ጊዜ መመስረት ማለት ነው። ይህ ሲስተም ቡድኖችን ከአሲምሌሽንም ያወጣቸዋል። ሁለቱ ስቴቶች የሚመሰረቱት በህገ መንግስት ሲሆን የብሄር ባህላዊ ፌደራል ስቴት የሚመሰረተው ከሁሉም ባህላዊ ማንነቶች በባህላቸው መሰረት ተውጣጥተው የሚመሰርቱት የአርበኞች ቤት ነው። ይህ ቤት በስሩ የባህልን ጉዳይ፣ የሰላምና እርቅ ጉዳይ፣ የሙዚየም ጉዳይ፣ የኬር ቴከር ጉዳይን ይመራል። ቡድኖች ሁሉ ባህላቸውን እንዲጠብቁ ስቴቶችን ይፈጥራል። እነዚህ ስቴቶች ከቦታ ውጭ ይሆናሉ። ምን ማለት ነው? በመሬት ላይ የሚሰመር ግዛት ሳይሆን የሚኖራቸው የዚያ ብሄር ቡድን ባሉበት ቦታ ሁሉ ባህላዊ መንግስቱ ገዢ ይሆናል።

በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ የዜጎች የፌደራል ስርዓት ግንባታ ነው። ይህ የፌደራል ስቴት በመሬት ላይ የሚነበብ ካርታ ይኖረዋል። ለአስተዳደር ኣመቺነት፣ ቋንቋ ወዘተ ታሳቢ ኣድርጎ የሚመሰረት ዘመናዊ የፌደራል ስቴት ይሆናል። እነዚህን ስቴቶች ካንቶን ብለን ልንሰይማቸው ይቻላል። ልክ እንደ ስዊዘር ላንድ የተለያዩ ካንቶኖችን መፍጠርና የፌደራል ስርዓቱን ማቋቋም ይቻላል። ይህ የፌደራል ስቴት የፖለቲካ፣ የልማት የኢኮኖሚ የትምህርት ጉዳዮቻችንን የምናካሂድበት ሲሆን የብሄር ፌደራል ስቴቶቹ ደግሞ ከፍ ሲል ያነሳናቸውን ስራዎች ይሰራሉ። ይህን በማድረግ በአንድ በኩል የባህል ኢእኩልነትን እያጠፋን እኩልነትን እያመጣን በሌላ በኩል ደግሞ ለጋራው ቤታችን በጋራ በመስራት ኣገራችንን ኢትዮጵያን ከድህነት በማላቀቅ የዜጎችን ህይወት እናሻሽላለን።

ለምን ሁትዮሽ የፌደራል ስርዓት ኣስፈለገን?

1. ብዙህ ስለሆንን ብዙህነትን ለማስተናገድ በጣም የተሻለ ሲስተም ስለሆነ

2. ባህላዊ ማንነትንና ፖለቲካዊ ማንነትን ለይቶ ምርታማነትን ለማምጣት

3. በብሄራዊ ማንነትና በብሄር ማንነቶች መካከል ያለውን ግጭት ለመቅረፍ

4. ሃገርን በሁለት ጠንካራ ምሶሶ ለማቆም

5. የጠፉ ባህሎቻችንን ለማስመለስ፣ የተበጠሱ አኩሪ ታሪኮችን ለመቀጠል

6. የፍትህን ገበታ ለማስፋት

7. የተለያዩ እድሎችን ለማስፋት፣ብዙ በሮችን ለመክፈት፣ ለፈጠራ ስራ፣ ያለንን ማህበራዊ ሃብት ወደ ኢኮኖሚ ሃብት ለመቀየር

8. የዜግነት ፖለቲካንና የብሄር ፖለቲካን ለማስታረቅ

9. የብሄሮችን ጥያቄ ለመመለስ

10. እሴቶቻችንን ለመጠበቅ ይረዳናል።

በነዚህና ሌሎች በርካታ ምክንያቶች የሁለትዮሽ የፌደራል ስቴት ግንባታው ኣስታራቂ ሃሳብ ነው። በተለይም ደግሞ በቡድን መብትና በግለሰብ መብት ለተራራቀው ፖለቲካችን ይህ ሲስተም መካከለኛና ሁሉን ኣስታራቂ ሲስተም ነው። ሃገራችንን ሳናጣ በሌላ በኩል ብሄራዊ ማንነታችንን ሳናጣ ኣብረን መኖር እንድንችል የሚያደርግ ስርዓት ነው። በአጠቃላይ የሁለትዮሽ ወይም ባለሁለት ክንፍ የፌደራል ስርዓት ማለት የፌደራል ስርዓትን በኢትዮጵያ ሁኔታ ለማስተናገድ የሚያስችል የፌደራል ስርዓት ማለት ነው። ኢትዮጵያዊ ፌደራሊዝም ማለት ነው። የፈደራል ስርዓት ለባህል ማንነት ብዙ የሚጨነቅ ባለመሆኑ በኛ ሁኔታ ብዝሃነትን ማስተናገድ የሚችል የፌደራል ስርዓት ለማምጣት ታስቦ ነው። ሃገር በቀል ፌደራሊዝም ነው። ብዝሃ ፌደራሊዝም ማለት ነው።

4. ቋንቋ

ስርዓታዊ ለውጥ ስንል ቋንቋንም ይመለከታል። ቋንቋ መግባቢያ ብቻ ሳይሆን የማንነት መግለጫ ነውና እጥፍ ድርብ ክብርና ጥንቃቄ ይሻል። የሰው ልጅ በቋንቋው የመናገር በቋንቋው የማሰብ ሙሉ ነጻነት ኣለው። የራሱ ቋንቋ ያለው ኣንድ ማህበረሰብ ሃገር ሲመሰርት ከነቋንቋው ተከብሮ ሊኖርበት ይገባል። በቁጥሩ በማነሱ ቋንቋው ኣይነካበትም። ስለዚህ የቋንቋ ኣጠቃቀማችንን ማስተካከል ኣንዱ የሽግግር ዋና ሃሳብ ነው። በዚህ ጥናት መሰረት ኢትዮጵያ በሚከተለው መንገድ የቋንቋ ህጓን ልታሻሽል ይገባል

1.  ብሄራዊ ቋንቋ።

የብሄራዊ ቋንቋነት ታይትል ሁሉም ብሄሮች ሊጎናጸፉ ይገባል። የሁሉም ቋንቋዎች ዝርዝር በህገመንግስት መቀመጥ ኣለበት። እነዚህ ቋንቋዎች ሁሉ የኢትዮጵያ ሃብት ናቸው ስንል የብሄራዊነት ደረጃን እናጎናጽፍ።

2.  ኦፊሺያል ቋንቋ

የኢትዮጵያን ቋንቋዎች በሙሉ በታችኛው የስልጣን ርከን ላይ ኦፊሺያል እናድርግ። ዜጎች በማዘግጃ ቤት ኣካባቢ በቋንቋቸው ይገልገሉ።

3. የህብረት ቋንቋ ይኑረን

ይህ ቋንቋ የፌደራል ቋንቋ ብቻ ሳይሆን ታች ድረስ በአራቱም ኣቅጣጫ አገልግሎት ላይ ይዋል። ይህ ቋንቋ ኢትዮጵያውያንን ሁሉ ወደ ጎን የሚያገናኝ ቋንቋም ይሆናል። የፌደራሉን የህብረት ቋንቋ ከአንድ በላይ ማድረግ ይቻላል።

4. እንግሊዘኛ

ኢትዮጵያ ከሌላው ዓለም ትገናኝ ዘንድ የተሻለ ተወዳዳሪ ትውልድ ለማፍራት እንግሊዘኛን ጠንክረን እናስተምር በቋንቋ ዙሪያ እነዚህን ማሻሻያዎች ካደረግን በአግልግሎቱም በማንነት መገለጫውም ቦታውን ያገኛል። የዜጎች በቋንቋ የመጠቀም መብት ይከበራል። ቋንቋዎች ያድጋሉ።

5. የሃብት አያያዝ  መሬት ለአራሹ

ኢትዮጵያ ሃገራችን ብዝሃነትን በማስተናገድ በኩል ችግሮች እንዳሉባት ሁሉ በሃብት ዝውውር ጉዳይም ከፍተኛ ችግር ኣለብን። በሃገራችን ሁኔታ ሃብት ስንል ዋናው ሃብት መሬት ነው። ኣብዛኛው ህዝብ ገበሬ ነው፣ ኢኮኖሚያችንም በዚህ ላይ የተመሰረተ ነውና። በኣስራ ዘጠኝ ስልሳዎቹ የመሬት ላራሹ ጥያቄ መነሳቱ ልክ ነበር። ያ ጥያቄ የተመለሰበት ኣግባብ ግን 

ችግር ነበረው። ደርግ የሃገሪቱን ሃብት ከፊውዳሎች ቀማና ለአብየታዊ መንግስት ኣደረገው። ገበሬው በገመድ ኣንዳንድ ጥማድ ስለደረሰው የተሻለ ለውጥ መሰለንና ተደስተን ይሆናል እንጂ ለውጡ ግማሽ መንገድ ሄዶ ነው የቀረው። ሁለተኛውን የሃብት ዝውውር ስናይ (ከመሬት ሃብት ኣንጻርየአስራ ዘጠኝ ሰማኒያዎቹ ነው። በዚህ ወቅት ደግሞ ሃብት ወደ ቡድኖች ዞሯል። ተመልከቱ፣ መጀመሪያ መሬት በፊውዳሉ እጅ ነበር ሲቀጥል ወደ መንግስት ተዛወረ ቀጥሎ ደግሞ የህዝብና የመንግስት በሚል ሽፋን የቡድኖች ሆነ። እነዚህ የሃብት ዝውውሮች የየራሳቸው ማነቆ ኣላቸው። በተለይ መሬት የቡድን ሲሆን የመጣው ጉልህ ችግር በቡድኖች መካከል የይገባኛል ጥያቄን

የወሰን ጥያቄን ነው። ይህ ችግር የሚፈታው የሃብት ዝውውርን በማሻሽል ነው። ይህ ዝውውር ደግሞ ከፍ ሲል ባነሳነው የኢትዮጵያውያን ኪዳን መሰረት መሬት በሚከተሉት ይዞታዎች ስር እንዲሆን ስንስማማ ነው።

1. በግል

የመሬት ባለቤትነትን ዜጎች ሊጎናጸፉ ይገባል።

2.  በኮሙኒቲ ።

የእምነት ተቋማት፣ ወይም የግጦሽ መሬት፣ ወይም የባህል መከወኛ ቦታዎች በቡድን ሊያዙ ይገባል

3. መንግስት ።

መንግስት በግለሰብና በኮሚኒቲ ያልተያዙትን መሬቶች፣ ደኖች፣ ታራራዎች ሰማይና ወንዞች ሊይዝ ይችላል።

ይህ ለውጥ የቡድኖችን የወሰን ጥያቄ ይፈታል። ቡድኖች በቀበሌና በኩሬ ውሃ የሚጋደሉት መሬት የቡድን የወል ሃብት ስለሆነ ነው። የመሬት ፖሊሲ ሲለወጥና መሬት የግል ሲሆን በወልቃይት ጉዳይ ኣማራና ትግራይ ኣይዋጉም። ጉጂና ቡርጂ አይጋጩም። ኦሮምያና ሶማሌዎች ኣይጋጩም ወዘተ። መሬት ለአራሹ ማለትም ይሄው ነው። መሬት ላራሹ ማለት ለብሄሩ ወይ ለመንግስት ሳይሆን ለሚሰራበትና መስራት ለፈለገ ዜጋ ሁሉ ነው። በሌላ በኩል ኣስተዳደራዊ ጉዳዮችንም ቢሆን ይህ ኪዳን ይፈታል።

 ኢትዮጵያውያን ሃገር ሲመሰርቱ ከራስ ትርክት ወጥተው በእኛ ኪዳን ኣብረው ሲኖሩ ከስርዓታችን ውስጥ ራስ ወዳድ ኣስተዳደርን እናጠፋለን። ገፊ ሃይሎችን እናባርራለን።

ማጠቃለያ

ከፍ ሲል እንዳነሳነው በሃገራችን የፖለቲካ ህይወት ውስጥ ማንነት ግጭትን ኣምራች የሆነ ሃይል ኣምጥቷል። ማንነት በራሱ የሚያጋጭ ስለሆነ ሳይሆን ማንነት ወደማይፈልገው ጨዋታ ውስጥ በመግባቱ ነው። ልኩ ያልሆነ ማልያ ስለለበሰ ነው። ስለዚህ ነው ባህላዊ ማንነትንና ፖለቲካዊ ማንነትን ነጥለን ለማካሄድ ሰርጀሪ ያስፈልጋል የምንለው። ሃይማኖትና ፖለቲካ የተለያዩ ናቸው እንዳልነው ሁሉ ባህልንም ከዚህ ነጥለን ኣውጥተን ነገር ግን የቡድን መብት ይጠበቅ ዘንድ ለቡድን መብት ጠገግ መስራት ይገባናል።

የዜግነት ፖለቲካ ኣራማጆች የቡድንን መብት እውቅና እንዲሰጡ በአንጻሩ ደግሞ የቡድን መብት ኣማኞች ለዜግነት መብት ክብር እንዲሰጡ ያስፈልጋል። ለዚህ ደግሞ ይህ ሲስተም ያግዘናል። ብሄራዊ ማንነትና የብሄራዊ ማንነት ተጠባብቀው እንዲኖሩ ያደርጋል። ይህ ስርዓት ከሁሉ በላይ በጎ የሆነ ማህበራዊ ሃብት እንድናመርት ያደርገናል። በተለይ ባለፉት ሁለት ኣስርት ዓመታት በጣም በሚያሳስብ ሁኔታ የወረደው ማህበራዊ ሃብታችን ነው። ማህበራዊ ሃብታችን ጠፍቶ ሃብታም ብንሆንም ያንን ያለማነውን እናጠፋዋለን። ማህበራዊ ሃብት (social capital) ሃብት ነው የሚባለው ማህበረሰብ የሚያመርተውና ኢንቨስት የሚያደርገው ነገር ስለሆነ ነው። ማህበራዊ ሃብትን ለማምረት ደግሞ ዴሞክራሲ፣ ሳይንሳዊ ፖለቲካ ማራመድ ኣለብን። ከዚህ በተጨማሪ በተለይ በአሁኑ ሰዓት መንግስትን ኣሳስቦት ኮሚሽን እስከማቋቋም የደረሰበትን የማንነት፣ የኣስተዳደርና ወሰን ጉዳይ ለመፍታት እንዲህ ዓይነት ሲስተም በጣም ኣዋጭ ነው። በኢትዮጵያ ውስጥ የወሰንን ጥያቄ ለመፍታት በስቴቶች መካከል የሚደረግ የመሬት ላይ መስመር ኣይፈታውም።

 በጉጂና ቡርጂ መሃል በአማራና ትግራይ መሃል በኦሮምያና ሶማሊያ መሃል በሁሉም ኣካባቢዎች የወሰን ጥያቄ የሚነሳው መሬት በብሄሮች ስለተያዘ ነው።

ስለዚህ ይህ ሞዴል ሳይሸራረፍ በስራ ላይ ከዋለ ኢትዮጵያ ታሪካዊ ለውጥ ኣድርጋ ዓለምን ልታስደምም ትችላለች። ከሁሉ በላይ ደግሞ የጠፉ ባህሎቻችንን በማስመለስ ኢትዮጵያውያን ግርማና ሞገሳችንን እናስመልሳለን። የባህል ፌደራል ስቴቱ ሲቋቋም በራያና በትግራይ መካከል ግጭት ኣይኖርም። በቅማንትና ኣማራ መካከል ግጭት ኣይኖርም። በደቡብ የሚነሱ የክልል ጥያቄዎች ምላሽ ኣገኙማለት ነው። ወደፊት በነዚህ ጉዳዮች ላይ እንወያያለን። ለዛሬው ግን ከፍ ሲል ያነሳሁትን ኣሳብ ጠቅልሎ የያዘውን ስእላዊ ማሳያ ቀጥሎ ይመልከቱ። ይህ ቤት የኢትዮጵያ ቤት ይሆን ዘንድ ምኞቴ ነው።

እግዚኣብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ!

geletawzeleke@gmail.com 

የኢትዮጵያ ሮድ ማፕ

የቋንቋ ማኔጅመንትና ኣሰራር

ህገመንግሰታዊ መብታችን ይከበር በሚል መሪ ቃል በሀዋሳ ሰለማዊ ሰልፍ ተደረገ

በሰለማዊ ሰልፉ ከሲዳማ 36 ወረዳዎች እና ከተማ መስተዳድሮች የተውጣጡ እንዲሁም የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች የተሳተፉበት ነው።

ሰለማዊ ሰልፈኞቹ “ህገ መንግስቱ ይከበር ! የሲዳማ የክልልነት ጥያቄ መልስ ይሰጠው! የሪፈረንደም ቀን ይወሰን !” የሚሉና መሰል መፈክሮችን እያሰሙ ነው።

መነሻውን ከሀዋሳ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ያደረገው ሰላማዊ ሰልፍ በሀዋሳ ዓለምአቀፍ ስታዲዮም መዳረሻውን በማድረግ እንደሚጠናቀቅ ተገልጿል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ/ደኢህዴን/ ከወራት በፊት ባደረገው በ10ኛ መደበኛ ጉባኤው የሲዳማ ብሔር በክልልነት የመደራጀት ጥያቄ ተቀብሎ ለህዝበ ውሳኔ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መምራቱ ይታወሳል።

በኬኔዲ አባተ