### በዓድዋ ጦርነት የመጨረሻ ሠዓታት ላይ የጣልያኖች ሁኔታ ### Mes Demoze


### በዓድዋ ጦርነት የመጨረሻ ሠዓታት ላይ የጣልያኖች ሁኔታ ###

” ባህር ዘሎ መምጣት ለማንም አትበጅ
እንደ ተልባ ሥፍር ትከዳለች እንጅ
አትረጋም ሀገር ያለ ተወላጅ “

በጦርነቱ ዋዜማ በምንሊክ ጦር የተተከለው ድንኳን ሲታይ፣ ከብዛቱ የተነሳ አፍሪካ አውሮፓን ለመጠራረግ የተነሳች ይመስል ነበር። ይሄን ባዩ ጊዜ የተሸበሩት የጣሊያን ወታደሮች ሁሉ፣ የስንብት ደብዳቤ ለቤተሰቦቻቸው እንደፃፉ ኢን አፍሪካ የተሰኘው መፅሃፍ ይገልፃል፡፡ ከደብዳቤዎቹ አንዱ እንዲህ ይነበባል፡፡

“ራሶቹ ጥቂት የእግር መንገድ በሚያስጉዝ ርቀት ላይ ተሰይመዋል፡፡ በአንድነት ወደ እኛ እየመጡ ነው፡፡ አዛዣችንም እንድናፈገፍግ ብቻ እየነገረን ነው፡፡ የዚህም ውጤት መጨረሻው ገብቶናል፡፡ ጦሩ እየገፋ እስኪመጣ ብቻ እንጠባበቃለን፡፡ የኛ ነገር እያበቃ ነው፡፡ አሁን የማስበው አቅመቢስ ለሆኑት ወላጆቼ ነው፡፡ እነሱ ምንም ነገር ቢገጥማቸው ከጎናቸው እንድትሆን አደራ እልሃለሁ” ይላል መቶ አለቃ ሚሴና ለጓደኛው የላከው ደብዳቤ ነበር፡፡

የጣሊያን ወታደሮች ተስፋ መቁረጥም ቀስ በቀስ ወደ ዋናዎቹ የጦር መሪዎች እንደተዛመተ ሱልካፓ ዓድዋ የተሰኘው መፅሃፍ የጣሊያኑን መቶ አለቃ ሮፓ አሟሟት እማኝ አድርጎ እንዲህ ፅፎታል፡፡

“መቶ አለቃ ሮፓ ጦሩን የሚመራው ፈረስ ላይ እየሆነ ነበር፡፡ ሁለት ፈረሶቹም ከጭኑ ስር እየተመቱ ወድቀዋል፡፡ በመጨረሻው ቀን ፈረስ ላይ ለመውጣት ሲሞክር ጎኑን ተመታ፡፡ ሲወድቅ ያዩት የጣሊያን ወታደሮች ሊያነሱት ተሯሩጠው ሄዱ፡ እሱም እያቃሰተ እንዲህ አለ፡፡ ‘እኔ ሽማግሌ ስለሆንኩ ተውኝ፡፡ እናንተ ግን ወጣት ስለሆናችሁ ከዚህ መዓት ራሳችሁን አድኑ፡፡’ ይህን እንደተናገሩ በፊቱ ተደፍቶ ህይወቱ አለፈ፡፡”

በመጨረሻም የዚህ ተስፋ መቁረጥ በሽታ ወደ ዋናው ጄኔራል ዳቦርሜዳ ተዛመተ፡፡ ሁኔታውን በቦታው ላይ የነበረው ካፒቴን ሚናሪ እንዲህ ያስታውሰዋል፡፡ “ጄኔራል ዳቦርሜዳ ከመድፈኞቹ አጠገብ ወዲያ ወዲህ ሲወዛገብ አየዋለሁ፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ በላብ ተውጦ እና ሰውነቱ ተሸብሮ አየሁት፡፡ ሁኔታው ያሳዝናል ፤ በጭንቀት ብቻውን ያወራ ነበር፡፡ የጥይት በረዶ ሲዘንብበት ከሃሳቡ ይነቃና ፊቱን ወደ መኮንኖች በማዞር የተለመደውን ፈገግታ ያሳያል፡፡ ከጧት ጀምሮ ከሌሎች ክፍለ ጦሮች የደረሰው ወሬ የለም፡፡ ጦሩ የተሰወረ ይመስላል፡፡ እውነትም የመጨረሻ ቀናችን ጊዜ እየተቃረበ መምጣቱ የተሰማን በዚህ ጊዜ ነው ሲል ሚናሪ ይናገራል፡፡” በመጨረሻም ዳቦርሜዳ የፈራው አልቀረም ህይወቱን በኢትዮጵያ ጀግኖች ተነጠቀ፡፡ በደፈረው የሃገራችን መሬት ወድቆ ቀረ።

#የጥቁር_ህዝብ_ኩራት
#ዓድዋ_123 
#የኢትዮጵያውያን_ድል
#VictoryofAdwa
#Ethiopia

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s