ባለቤት አልባ ከተሞችን መንግስት ይታደጋቸው (ድራንዝ ጳውሎስ (ከባህር ዳር)

እንዲህ እንደ ዛሬው የሕዝብ መሰብሰቢያ አዳራሾች ባልበዙበት፣ ማባራዊ ድረ ገጾችና ሚዲያዎች ባልተስፋፉበት፣ የሕዝብ መወያያ አጀንዳ እየተቀረጸ ውይይት በማይካሄድበት በጥንት ዘመን በአገራችን በአስተዳደር እርከን ላይ የነበሩ የአገር ግዛት አስተዳዳሪዎች በሕዝብ ዘንድ የነበራቸውን ተቀባይነት ለማረጋገጥ Çእረኛ ምን አለ?È ይሉ እንደነበር በታሪክ ድርሳናት ይወሳል፡፡ ይህ ደግሞ ሕዝብን ለማዳመጥ የሚጠቀሙት ራሳቸው የፈጠሩት ሚዲያ መሆኑን ማረጋገጥ ይቻላል፡፡ ሕዝብን የሚያዳምጠው ሲያጣ አቤቱታው ከጠቅላይ ግዛት ወደ አገር ግዛት ልክ እንደ ተላላፊ በሽታ ይዛመታል፡፡ ከዚያም አልፎ ራሱን በራሱ ማዳመጥ ይጀምራል፡፡ በልቡ መከፋቱንንና ጩኸቱን ሰምቶ የሚደርስለት ሲያጣ

የልቤን መከፋት ሆዴ እያዳመጠ፣

ሊመረው ነው መሰል ነገር አላመጠ፡፡È የሚል የመገፋት ፉከራ አዘል እንጉርጉሮ ሲያሰማ ብልጥ አገር ገዥ የዝሆን ጆሮ ይሰጠኝ አልሰማሁም አይልም፡፡ ይልቅ በምላሹ

እዚያ ማዶ ሆኖ አንድ ሰው ተጣራ፣

ወዲህ ማዶ ሆኖ አንድ ሰው ወይ አለው፣

ሳናውቀው ነው እንጂ ይህ ነገር የኛ ነው፡፡ በሚል ሕዝቡ የተከፋበትን ጉዳይ ማድመጥ፣ ለተከፋበት ጉዳይ ምላሽ መስጠት ይጀምራል፡፡ ይህ ደግሞ የብልጥ አገር ገዥ፣ አስተዳዳሪ መርህ ነው፡፡ ሕዝብን እረኛ የሚወክልበት ዘመን፡፡ እረኞች ዘንድ ዝምታ ከሰፈነ ሕዝቡ ለመንግስት ያለው ተገዥነት ያሳብቃል፡፡ በጥንት ዘመን የነበረውን የሕዝብና የመንግስትን መደማመጥ ያነሳሁት ያለ ነገር አይደለም፡፡ ከየካቲት 9 – 14 ቀን 2011 ዓ.ም መደመርለኢትዮጵያ ከተሞች ብልጽግና“ በሚል መሪ ቃል በሶማሌ ክልል ዋና ከተማ  በጅግጅጋ ከተማ በተካሄደው 8ኛው የከተሞች ፎረም የኢትዮጵያ ከተሞችን የጎረቤት ሀገሮችን ጨምሮ 163 ከተሞችንም ያሳተፈ እንደነበረ ቢነገርም አማራ ክልልን ወክለው ስለተገኙ 32 ከተሞችና የክልሉ መንግስት ስለከተሞች ዝግጅት ትኩረት ስለነፈጋቸውና ከተሞችን የሚመራው ተቋም ሕይወት አልባ መሆኑን ለመግለጽ ነው፡፡

የፎረሙ ዋና ዓላማ በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሴክተር ባሉ የማዕዘን ድንጋዮች /Pillars/ አፈጻጸም መሰረት ያደረገ በከተሞች መካከል ዉድድር እንዲደረግና በአግባቡ የፈጸሙትን ለማበረታታት ሌሎች ከተሞች ደግሞ ከዚህ መልካም ተሞክሮ በመማር የተሻለ አፈጻጸም እንዲያስመዘግቡ ለማበረታታትና የከተማ ነዋሪዎችን፣ የመንግስትና ሌሎች ባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ እና ትብብር በማጠናከር፣ መልካም ተሞክሮዎችንና ልምዶችን በማስፋፋት፣ እንዲሁም ከተሞች እሴቶቻቸውን በማስተዋወቅና በማጎልበት ጠንካራ መሰረት ያለዉ የከተማ ህዝብ ንቅናቄና ተጠቃሚነትን ለመፍጠር ነው፡፡

ከተሞች የራሳቸውን በጎ ገጽታ በማጎልበትና በመሸጥ፣ ልማታቸውን በማፋጠን የእርስበርስ ትውውቅና የመማማር ዕድል በመፍጠርና ከተሞች ያላቸውን ዕምቅ አቅም /በኢንቨስትመንት፣ በንግድ፣ በቱሪዝም፣ በታሪካዊ፣ ባህላዊና ማህበራዊ እሴቶች/ በማስተዋወቅ በኩል የፎረሙ ፋይዳ የጎላ እንደነበረ ይነገራል፡፡

ይሁን እንጂ በዚህ በጅግጅጋው የከተሞች ፎረም በምድብ 3:- 20 ሺህ ህዝብና ከዚያ በላይ ነዋሪ ያላቸው ከተሞች መካከል የከሚሴ ከተማ ራስን በማስተዋወቅ የሁለተኛ ደረጃ ከማግኘቷ ውጭ የአማራ ክልልን ወክለው የተሳተፉት 31ዱ ከተሞች ተጠቃሚነታቸውና ውጤታማነታቸው ከተሳትፎ ያልዘለለ ነው፡፡ በተለይ በሜትሮፖሊታን ደረጃ ላይ ያሉ ባህር ዳር፣ ጎንደርና ደሴ ከተሞች በምድባቸው ደረጃ አለማግኘታቸውን ስንታዘብ ከክልሉ መንግስት ጀምሮ ከተሞችን የሚመራው ክልሉ ከተማ ልማት፣ ቤቶችና ኮንስትራክሽን ቢሮ ለፎረሙ ዝግጅትና ለሚገኘው ፋይዳ የሰጠውን የትኩረት ማነስ ያመላክታል፡፡

እንዴውም ከታዳጊ እስከ ሜትሮፖሊታን ደረጃ ያሉ የአማራ ክልል ከተሞች በስርዓትና በተገቢው መንገድ ባለመመራታቸው ከተሞች ማንን ይመስላሉ? ተብሎ ሲጠየቅ አመራሩ እንደተባለ በአንድ መድረክ የታዘብኩት ከዚህ ላይ ማንሳት እወዳለሁ፡፡

ከተሞቻችን ባለፉት ስርዓቶች አስተዋይ በማጣት በድህነት ችጋር ውስጥ ተተብትበው መኖራቸው ሲነገር እንዳልነበር ዛሬም የተፈጠረው ምቹ ሁኔታና በህገ መንግስቱ የተፈቀደውን የመልማት መብታቸውን ተጠቅመው መልካም አስተዳደር የሰፈነባቸውና በሥራ ዕድል ፈጠራም የማይተካ ሚና እንዲጫወቱ በማድረግ በኩል የክልሉ መንግስት ለበርካታ ዓመታት ዓይኑን ሸፍኖታል፡፡ በፎረሙ የተቀመጠውን ዓላማና የሚያስገኘውን ጠቀሜታ ባገናዘበ መልኩ በመደገፍና በማዘጋጀት በኩል ምንም ዓይነት ሥራ እንዳልተሠራ በድፍረት መናገር ይቻላል፡፡ ከተሳትፎ በዘለለ ተወዳዳሪ ሆኖ ለመቅረብ የተደረገው ጥረት ከዚህ ግባ የሚባል እንዳልሆነ ከማጠቃለያው ውጤት መረዳት ይቻላል፡፡

ከዚህ በፊት በዚሁ መድረክ በአገሪቱ ካሉ ከተሞች የተገኘውን ተሞክሮ በማስፋትና የፎረሙን አስፈላጊነት በውል በማጤን ተገቢውን አመራር በመስጠት፣ ተግባሩን የሚመለከተው ዳይሬክቶሬት በዕቅድ ይዞ በመምራት፣ በጀት መድቦ በማስፈጸም በኩል የጎላ እንቅስቃሴ እንዳልተደረገ በግልጽ ማየት ተችሏል፡፡

ይባስ ብሎ ተግባሩን በዕቅድ የያዘው በቢሮው የከተሞች አቅም ግንባታ መልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ለፎረሙ ተሳታፊ ከተሞች ድጋፍ ማድረግ ሲገባው ጭራሽ የማይመለከታቸውና የፎረሙን ጽንሰ ሀሳብ ያልተረዱ፣ ተቋሙን ለሚመሩት የበላይ ኃላፊዎች ቅረቤታ ያላቸው ከሕዝብ ግንኙነት፣ ከሕግ አገልግሎትና ከውስጥ ኦዲት የተውጣጡና ባለሙያዎችን መርጦ ጅግጅጋ ድረስ መላክስ ተገቢ ነወይ? ቢሮው ከውድቀት የማይማሩ፣ ታጥቦ ጭቃና አድሮ ቃሪያ የተሰባሰቡበት አመራሮች ያሉበት ስለሆነ የክልሉ መንግስት በክልሉ ሰላምና መረጋጋት ለማስፈን በሚያደርገው እንቅስቃሴ በነካ እጁ ተቋሙንም ሆነ የክልሉን ከተሞች ሊለባኛቸው ይገባል ባይ ነኝ፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s