የዶር አረጋዊ በርሄ ነገር!!! ጨቛኟ የአማራ ብሄርም ጭቆናዋን እስካላቆመች ድረስ ህብረተሰባዊ ዕረፍት አታገኝም ወንድይራድ ሀይለገብርኤል

ዶር አረጋዊ ህወሀትን ከመሰረቱት ረድፈኞች ጎራ የሚሰየሙ ብቻ ሳይሆኑ የድርጅቱም የመጀመሪያው ሊቀመንበር ብቻ ሳይሆን የማታገያ ማኒፌስቶውንም በእጃቸው የፃፉ (የቀረፁ) ግለሰብ እንደነበሩ ይታወቃል። “ተቃወምኩ” ብለው ከተሰደዱ በዃላም ቢሆን “የትግራይ ዲሞክራሲያዊ ትብብር” የተሰኘ ድርጅት ቀልሰው እንደነገሩም ቢሆን ወዲያ-ወዲህ ማለታቸው አልቀረም። “ለውጡን” ተከትሎም በተሰደዱ በ40ኛው አመታቸው ለሀገራቸው ምድር በቅተዋል። ከገቡም በዃላ በየመድረኩና መገናኛ ብዙሀኑ ዙሪያ አብዝተው ይስተዋላሉ።

=====

ጠቅላይ ሚንስትር አብይ “”የፖለቲካ ድርጅቶች ምክክር”” አሰኝተው በከፈቱት መድረክ ላይም በተጋባዥ ተናጋሪነት ተሰይመው ንግግር ከመጀመራቸው በፊት — “”በማወቅም ይሁን ባለማወቅ እስከዛሬ ድረስ ሀገሬን ችግር ውስጥ ለከተታት ፖለቲካ የኔም አስተዋፅዖ ስለነበረበት የኢትዮጵያ ህዝብ ይቅርታ እንዲያደርግልኝ ከልብ በመነጨ አክብሮት እጠይቃለሁ””– ብለው በመናገር ከተሰብሳቢው “”አርአያ”” በተሰኘ አድናቆት ሞቅ ያለ ጭብጨባ ተችሯቸው ነበር።
=====

ይህንን ያሉት ዶር አረጋዊ ባልተጠበቀ ብቻ ሳይሆን በሚያሳፍር ሁኔታ ቃላቸውን በአደባባይ በልተው OMN ከተባለው የጀዋር ቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር በትናትናው ዕለት ቃለ-መጠይቅ ሲያደርጉ እንዲህ ሲናገሩ ሰማናቸው —

ጋዜጠኛው — “”ህወሀት ውስጥ በነበረዎ የፖለቲካ ተሳትፎ እና በሰሩት ስራ ይፀፀቱ ይሆን””? ብሎ ሲጠይቃቸው —

ዶር አረጋዊ — “”በፍፁም አልፀፀትም። የሚያፀፅት ስራም አልሰራውም””። ሲሉ መለሱለት። —

በዚህ አያበቃም—-

ጋዜጠኛው — “”ህወሀት በአማራ ህዝብ ላይ በደል ፈፅሟል የሚለውን ክስስ ይቀበላሉ”” ሲል ጠየቃቸው—

ዶር አረጋዊ — “”አልቀበልም። በደል የፈፀሙት አመራሮቹ ናቸው — ድርጅቱ ህወሀት በአማራ ህዝብ ላይ በደል ለመፈፀም አልተነሳም — ለመበደልም አላለመም በድሎም አያውቅም”” በማለት መለሱ።
=====

“”ወልቃይትስ የአማራ መሬት ነው የትግሬ””? ብሎ ሲጠይቃቸው ደግሞ — “”በህገ- መንግስቱ ቛንቛን መሰረት አድርጎ በተከለለው የግዛት አከላለል የወልቃይት ህዝብ ትግረኛ ተናጋሪ በመሆኑ ወልቃይት ወደትግራይ መከለሉ አግባብ ነው”” — ካሉ በዃላ — “”እንደአለመታደል ሆኖ በዚህኛውም ሆነ በዛኛው ወገን ጥሩ መሪዎችን ባለማግኘታችን ይሄው ጦርነት ሊያጋጥሙን ቆርጠው ተነስተዋል”” ሲሉ አሁንም በመሪዎቹ ላይ ያላቸውን ምሪት ገለጡ።
=====

እስኪ በራሳቸው በዶር አረጋዊ የዕጅ ፅሁፍ የተፃፈውን የህወሐት ማኒፌስቶን እየፈተሽን የዶር አረጋዊን ንግግር እንመርምረውና የሰውየውን እውነተኛ ማንነት እንገምግም —-

እውን ህወሐት የአማራውን ህዝብ በጅምላ ወንጅሎ አልተነሳም? ዶር አረጋዊ እንደሚነግሩን አማራው የተበደለ በህወሐት መሪዎች እንጅ እንደድርጅት መርሃግብር ተቀርፆለት አልነበረም? በዶሩ የተፃፈውን የህወሐት ማንፌስቶ ቃል በቃል በማስቀመጥ እንመርምር —-

የህወሐት ማኒፌስቶ 1968 ዓ/ም

3: ሕብረተሰባዊ ሁኔታዎች

ሀ፡ ራስን መጣል (ዲ-ሁማናይዜሽን)

“”ከቀን ወደ ቀን እየተባባሰ የሚሄደው የኢኮኖሚ ብዝበዛ በሰፊው የትግራይ ህዝብ ላይ ድህነት፡ ረሀብና ውርደት እየተደጋገመ እንዲደርስ አድርጓል። በተጨማሪም የትግራይ ህዝብ ለረጅም ዘመን ሰብዓዊና ፖለቲካዊ መብቱ ተነፍጎ ሲጠላና ሲናቅ እንዲሁም አድልዎ ሲፈፀምበት ቆይቷል። ይህም በደል ጨቛኟ የአማራ ብሔር ሆን ብላ መመሪያዋ አድርጋ ስትሰራበት የቆየች በመሆኑ ነው —–በዚህም የተነሳ ሰፊው የትግራይ ህዝብ ኑሮው እንዲቆረቁዝ ተደርጓል — በዚህም ምክንያት የስራ ማጣት ችግር፡ ሽርሙጥናና ስደትን ከማስከተሉም በላይ ራስን መጣልና መንከራተት የትግራይ ህዝብ ዕለታዊ ተግባሩ ሆኖ ይገኛል። ስለሆነም ህዝቡ ተጠራጣሪና የተጠላ እንዲሆን በመደረጉ በህብረት መኖር የማይችል ሆኖ ይገኛል””” ይላል።

እንግዲህ ዶር አረጋዊ ለዘረዘሩት የትግራይ ህዝብ ችግሮች በሙሉ ተጠያቂ አድርገው ማኒፌስቶ የቀረፁት የአማራውን ብሄር (ህዝብ) በጅምላ እንዲህ ፈርጀው በጠላትነት በማስቀመጥ ነው። የአማራውን ህዝብ በጅምላ የፈረጀ ማኒፌስቶ ቀርፀው ህወሐትን ከፈጠሩ በዃላ —“””የለም አማራ የተበደለው በአመራሮቹ እንጅ በድርጅቱ በህወሐት አደለም””” — ይሉናል።
=====

ይቀጥላል—-

ለ፡ የህብረተሰቡ ወደ ዃላ መቅረትና እረፍት ማጣት

“”ሰፊው የትግራይ ህዝብ ስራ አጥቶ በሽርሙጥናና በስደት ወ…ዘ…ተ… ብቻ ሳይሆን በረሀብ፡ በድንቁርናና በበሽታ እየተሰቃየ ይኖራል። —- ለችግሩ መሰረታዊ ምክንያት ኢምፔሪያሊዝም — ይሁን እንጅ ጨቛኟ የአማራ ብሄር የምታደርገው የኢኮኖሚ ብዝበዛና የፖለቲካ ጭቆና ታክሎበት ነው። —- ጨቛኟ የአማራ ብሄርም
ጭቆናዋን እስካላቆመች ድረስ ህብረተሰባዊ ዕረፍት አታገኝም።””

በማለት የአማራን ብሄር (ህዝብ) በጅምላ “”ጨቛኝ”” ብሎ በመፈረጅ ተጠቂም ተጠያቂም አድርገው ዶር አረጋዊ የድርጅታቸውን ማኒፌስቶ በታይፕ ራይተር ሳይሆን በራሳቸው የእጅ ፅሁፍ አርቅቀዋል። ይሄንን ያክል በደል ለፈፀሙበት ለአማራው ህዝብ ዛሬም ጠላትህ መሪዎቹ እንጅ ህወሐት አልነበረም ሲሉ በአደባባይ ሊቀልዱበት ግን ድፍረቱን አላጡትም።
=====

ይቀጥላል——

ወልቃይት ወደትግራይ የተካለለው በህገ-መንግስታዊ የቛንቛ ፌደራሊዝም አግባብ ነው ያሉን ደግሞ በ1968 በቀረፁት የድርጅታቸው የህወሐት ማኒፌስቶ የሚከተለውን ካስቀመጡ በዃላ ነው —

የትግራይ ግዛት

“”” —- የትግራይ መሬት በደቡብ ኣለዃና፡ በሰሜን መረብ ሲያካልሉት በምዕራብ በኩል ደግሞ ወልቃይትንና ፀለምትን ያጠቃልላል”””” ይላል።

በዶር አረጋዊ የተፃፈው የህወሐት ማኒፌስቶ በዚህ አላበቃም። ዶሩ የአማራ ህዝብ ትግሬነትን በማጥፋት፡በማስካድና የትግሬን መሬት በመውረር ጭምር በማኒፌስቷቸው ከሰውታል፡ የትግራይን ህዝብም —

“”በአማራ ከመጥፋትህ በፊት በመሪ ድርጅትህ በህወሐት ስር ታቅፈህ በመታገል አማራን አጥፋ””” ሲሉ በአማራው ህዝብ ላይ ለደረሰው የዘር ማፅዳት፡ ማጥፋትና፡ መሬት ወረራ ግንባር ቀደም ተጠያቂ መሆናቸውን በራሳቸው የዕጅ ፅሁፍ የተፃፈው የህወሐት ማኒፌስቶ ቀዳሚ ማስረጃ ነው።
=====

አማራን የበደሉት የህወሐት መሪዎች (እርሳቸው ከድርጅቱ ከከዱ በዃላ የነበሩትን ማለታቸው ነው) እንጅ ድርጅቱ አደለም የሚለውን ቀልዳቸውን አጥብቀው የሚገፉት ከተጠያቂነት አመልጣለው ብለው በማሰብ ከሆነ ዶሩ የሚያታልሉት እራሳቸውን ብቻ እንጅ የአማራውን ህዝብ አለመሆኑን ጠንቅቀው ሊገነዘቡት ይገባል።

የአማራን ቤት ያቃጠለውን የመጀመሪያውን ክብሪት ለኩሶ እሳቱን የቆሰቆሱትን ብቻ በመወንጀል ከተጠያቂነት ለማምለጥ ሙከራ ማድረግ የራስን ስውር ማንነት ገላልጦ ከማሳየት ውጭ ሌላ ፋይዳ የለውም።

ህወሐት ከስር መሰረቱ በአማራ ህዝብ መቃብር ላይ የትግሬን የህይወት ዘንባባ ለማለምለም የተነሳ ፀረ አማራ ድርጅት ነው። በተግባር ተከስቶ ያየነውም ይሄው ነው። ቀዳሚ ምስክሩም በዶር አረጋዊ አማራን ከምድረገፅ ለማጥፋት ታልሞና ታቅዶ የተቀረፀው የድርጅቱ ማኒፌስቶ ነው።

የሚገርመው ነገር እኒህ ግፈኛ ሰው በቅርቡ በዶር አብይ የተሰየመው የደንበርና የማትነት ኮሚሲዮን አባል ተደርገው መመረጣቸው ነው። በማኒፌስቶ ወልቃይትና ጠለምት የትግራይ መሬት ነው በማለት በ1968 ዓ/ም የቀረፁ ግለሰብ እንዴት ነው ዛሬ የደንበርና ማንነትን ጉዳይን ፍትሀዊ በሆነ አግባብ አይተው ወልቃይት የአማራ ተፈጥሮአዊና ታሪካዊ ዕርስት ነው ብለው የሚዳኙት? ቀልድህን ተው ዶር አብይ። እንዴትስ የአማራን ህዝብ ብትንቀው ነው እንዲህ አይነት አሳፋሪ ስራ ለመስራት የደፈርከው? እረ እየተስተዋለ።

ታዲያ እንደዶር አረጋዊ ያሉ እጃቸው በአማራ ደም የከረፋ ግለሰቦች ያሉበትን የሰላምና እርቅ ኮሚሲዮን የአማራ ህዝብ የሚቀበለው እንዴት ነው?

እረ ይሄ የፌዝ ስራ አያዋጣም ዶር አብይ!! በትናቱ አስተሳሰብ የዛሬውን አማራ ማዘናጋትም ሆነ ማሞኘት አይቻልህም።

ወንድይራድ ሀይለገብርኤል

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s