ዶ/ር አብይ ጽ/ቤት “በኦሮሚያ ጉዳይ ጣልቃ አይገቡም” – ግርማ ካሳ

የአቶ ለማ ጽ/ቤት
” አቶ ለማን ማናገር አትችሉም”

የኦሮሞ ክልል መሬት አስተዳደር
“ቤታችሁ ከመፍረስ አይድንም። ልንተባበራችሁ አንችልም”

ዶ/ር አብይ ጽ/ቤት
“በኦሮሚያ ጉዳይ ጣልቃ አይገቡም”

ይሄን ጊዜ የኦሮሞ ቡድኖች ቢሆኑ ኖሮ የመጡት …..እናንተው አረፍተነገሩን ጨርሱት …

ቢቢሲ ከዘገበው የተወሰደ
—–

“ሌላኛዉ አስተያት ሰጭ እንደገለጹት ደግሞ “ሚስቴ ከወለደች ሦስት ቀኗ ነዉ። ከቤት ተባርራ ጎዳና ላይ ነች። ቤቱን ሲያፈርሱት እባካችሁ ሚስቴ ከወለደች ሦስት ቀኗ ነዉ ትንሽ ታገሱኝ ስል ‘ምን አገባኝ ከእኔ አልወለደች’ ሲል አንደኛው ምላሽ ሰጠኝ። እኔም የሚሰማ መንግሥት ይኖራል ብዬ ለአቤቱታ ትቻት መጣሁ። ሜዳ ላይ በተወጠረ ሸራ ውስጥ ነው ያለችው። ምን እንደሆነች አላውቅም” ሲሉ የተሰማቸውን ሐዘን ይገልፃሉ።

ትናንት ቤታቸዉ የፈረሰባቸዉ ግለሰቦች ዛሬ ጠዋት ተሰባስበዉ ወደ ኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ቢሮ ቢያመሩም እሳቸዉን ማናገር አትችሉም ተብለው ወደ ክልሉ መሬት አስተዳደር ቢሮ መላካቸውን ነግረውናል። ነገር ግን ከክልሉ መሬት አስተዳደር ቢሮም ያገኙት ምላሽ “ቤታችሁ ከመፍረስ አይድንም። ልንተባበራችሁ አንችልም” የሚል መሆኑን ገልጸውልናል።

አቤቱታ አቅራቢዎቹ በመቀጠል ወደ ጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ቢያመሩም “ጉዳያችሁን እዛዉ ጨርሱ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኦሮሚያ ጉዳይ ጣልቃ አይገቡም” የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸዉ ለቢቢሲ ተናገረዋል።”

ኦሮሞ ያልሆነ በኦሮሞ ክልል ቤት ሰርቶ እንዲኖር አይፈለገም #ግርማካሳ

አቶ አዲሱ አረጋ የኦህዴድ ከፍተኛ አመራር፣ የዜጎችን ቤት የማፍረስ ሂደቱ እንደሚቀጥል፣ እንደው የበለጠ ተጠናክሮ እንዲሚቀጥል መግለጻቸው የኦ.ኤም.ኤኑ ግርማ ጉተማ ዘግቧል”

” Obboo Addisu Arega Kitessa from ODP’s secretariat office underscored today that the demolition of illegal houses will continue—even to be intensified” ሲል ነው የጻፈው።

አንደኛ – እነ አቶ አዲሱ ራሳቸው ሕግ ወጥ መስተዳድሮች ናቸው። ኢፍትሃዊ በሆነ ፣ በተጭበረበረ ፣ የመቶ በመቶ የዉሸት ምርጫ ነው መንግስት ስልጣን የያዙት። ሕግወጥ ሆነው ስለ ሕጋዊነት የማውራት የሞራል ብቃቱ የላቸውም።

ሁለተኛ – የሚያፈናቅሉት የአዲስ አበባ ዙሪያ ኦሮሞ ካልሆኑት ለማጽዳትና ኦሮሞዎች ከሌላ ቦታ አምጥቶ ለማስፈር እንጂ ሕግን ለማስክበር አይደለም። እነ አቶ አዲሱ ሕግ ወጥኘጥ ኦሮሞ አለመመሆን ነው። ሕገ ወጥ ቤቶች የሚሉት ኦሮሞ ያልሆኑ ወይንም ኦሮሞ ሆነው የነርሱ አመላከካት የማይጋሩ ዜጎችን ቤት ነው። ጭንቀታቸው በአዲስ አበባና በአዲስ አበባ ዙሪያ እነርሱ ኦሮሞ የሚሉትን በቁጥር እንዴት የበላይ እናድርገው የሚለው ነው።

ሶስተኛ – እየተፈናቀሉ ያሉ ወገኖች የቤት ባለቤትነትስ ሰነድ ያላቸው፣ ማስረጃ ያላቸው፣ የመብራትና የዉሃ አግልግሎት የቀረበላቸው፣ ለነዚህ አጋለግሎቶች ክፍያ ሲከፍሉ የነበሩ ናቸው።

አራተኛ – ቤቶቹ ሕግ ወጥ ናቸው ቢባልም እንኳን፣ ሕጻናት፣ አረጋዉያን፣ እናቶች ..አሉ። ሕግ ወጥ ነው ተብሎ፣ ሌላ ማረፊያ እንደ መንግስት ሳይዘጋጅላቸው፣ ሜዳ ላይ መበተን የለየለት አረመኔነት ነው።

አቶ አዲሱ ይሄንን ድርጒት ማውግዘ ሲገባው ድርጊቱን ደግፎ መናገሩ ከማሳዘን በላይ የሚያበሳጭ ነው። ከአንድ የመንግስት ባላስልጣን የሚጠበቅ ሳይሆን የለየለት ዉንብድናና መንግስታዊ ሽብርተኘንት ነው።

ለገጣፎ – ስለፍቅር በስምአብ ይቅር! (በውቀቱ ስዩም)

በውቀቱ ስዩም

Addis Ababa, Legetafo demolition anda displacements.

የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) እያካሄደ ባለው ቤት የማፍረስ ዘመቻ በለገጣፎ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ቤቶቻቸው እየፈረሱ ጎዳናላይ ተበትነዋል።

በዙረት ካገኘሗቸው እውቀቶች አንዱን በማካፈል ወጌን ልጀምር:: ያፍሪካ ስደተኞች ያንዱን ያውሮፓ አገር ድንበር አቋርጠው ይገቡና አንድ ከተማ ውስጥ አድፍጠው ይቀመጣሉ:: በከተማው ባንድ ስፍራ ላይ መንግስት ገንብቶ ያልጨረሰው ባዶ ህንፃ ይኖራል:: ስደተኞች ከለታት አንድ ቀን ተደራጅተው ህንፃውን ወርረው ይይዙታል:: የህንፃውን አፓርታማ ተከፋፍለው መኖር ይጀምራሉ:: መንግስት እንዴት ተደፈርኩ ብሎ ለወግ ያክል ያዙኝ ልቀቁኝ ይላል :: የታጠቀ ህግ አስከባሪ ልኮ አካባቢውን ይቀውጣል:: ወድያው ጠበቆች ሳምሰናይታቸውን አንጠልጥለው ከተፍ ይሉና የሰው ልጅ መጠልያ የማግኘት መብቱን ጠቅሰው ለስደተኞቹ ይከራከራሉ:: የማታ የማታ ጠበቆች ያሸንፋሉ:: “ወራሪዎች ” ኑዋሪዎች ሆነው ይቀጥላሉ::

አውሮባዎች በዚህ ሁኔታ ውስጥ ምን እያሉን ነው:- ያለህግና ደንብ አገር አይኖርም:: ይሁን እንጂ ዞሮ ዞሮ ህግና ደንብ ሰውን ለማገልገል የተፈጠሩ መሆናቸውን አንርሳ:: ከርህራሄና ከፍቅር ተቃራኒ የቆመ ህግ መሻሻል ወይም መወገድ አለበት::

መድረሻ ያጡ ዜጎች : በለገ ጣፎ : ጠፍ መሬት አግኝተው: ቤት ሰርተው ቤተሰብ መስርተው ግብር እየከፈሉ ይኖሩ ነበር:: አስተዳደሩ ግሪደር ልኮ ቤታቸውን አፈረሰባቸው:: ለምን? ” ለአረንጓዴ ቦታ የታጨውን ቦታ በህገወጥ መንገድ ሰሩበት!! ህግ ህግ ነው “ጥሩ!! ግን ዜጎችን ከቤታቸው አውጥቶ ጎዳና ላይ መጣል ሌላ ህገወጥነት አይሆንም?

መንግስትና ህዝብ በጋራ ድል የሚያረጉበት መፍትሄ በጊዜ ይፈለግ!! ቤታቸው የፈረሰባቸው ሌላ ምትክ ቦታ ይሰጣቸው!! ኪሳራውም ይከፈላቸው!! ለምን? እያንዳንዱ ርምጃ አፀፋ ይጋብዛል :: ሶስት መቶ ሰው ስታፈናቅል ሶስት መቶ ሽፍታ ታፈራለህ :: ለመናፈሻ ያሰብከው ሜዳ : ነገ መከሳከሻ ሆኖ ታገኘዋለህ:: አረንጉዋዴ ሳይሆን በደም የቀላ መስክ ይጠብቅሃል::

ባገራችን ” ስለፍቅር በስመ አብ ይቅር ” የምትል አሪፍ ተረት አለች:: የዚህን ተረት መነሻ እንዲህ ሊሆን ይችላል:: አንድ ክርስቲያን ሙስሊም ባለንጀራውን ቤቱ ይጋብዛል:: ራት ላይ ሁለቱ ወዳጆች ማእድ ለመቁረስ ተቀምጠዋል:: ጋባዡ ራቱን በክርስትያን ደንብ የመጀመር ግዴታ እንዳለበት ያውቃል:: ግን ይሄንን በማድረግ የወዳጁን ስሜት ማስቀየም አልፈለገም:: ምን ይሻላል?? ለጊዜው የማእዱን ስርአት ሊያልፈው ወሰነ:: ” ስለፍቅር በስመአብ ይቅር::” ብሎ ማእዱን በገለልተኛ መፈክር ጀመረው::

The terminal የሚለው የስፒል በርግ ፊልም ላይ ህግ የሚያመልክ ያውሮፕላን ጣቢያ ባለስልጣን አለ:: አለቃው ከለታት አንድ ቀን እንዲህ አለው:: ” አንዳንዴ ለፍቅር ስትል ህጉን ባላየ ማለፍ አለብህ :: የዚህ አገር መሰረት ፍቅር ነው::

እኔ የዚህ አገር መሰረት ፍቅር ነው አልልም:: የኢትዮጵያ መሰረት በዋናነት ጉልበት ግድያና ማፈናቀል ነው:: ግን ይሄ ትውፊት የሆነ ቦታ ላይ መገታት የለበትም?!

የኢሳት ጋዜጠኞች ዛሬ ታስቦ የዋለውን የሰማእታትን ቀን ለመዘከር በየካቲት አስራ ሁለት የሰማእታት ሀውልት ስር የአበባ ጉንጉን ሲያኖሩ
 የኢሳት ጋዜጠኞች ዛሬ ታስቦ የዋለውን የሰማእታትን ቀን ለመዘከር በየካቲት አስራ ሁለት የሰማእታት ሀውልት ስር የአበባ ጉንጉን ሲያኖሩ

ባለፉት 6 ወራት ሀገሪቱን ከጎበኙ የውጪቱሪስቶች 1 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር ገቢ ተገኘ

አዲስ አበባ፣የካቲት 12፣2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ)

ባለፉ ስድስት ወራት ከውጪ ሀገራት ቱሪስቶች 1 ነጥብ 4 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ማግኘት መቻሉን የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ ።

ይህ የተባለው የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር በባህር ዳር ከተማ እያካሄደ ባለው የ6 ወራት የስራ አፈፃፀም ግምገማ ላይ ነው ።

በስራ አፈፃፀም ግምገማው ላይ ባለፉት 6 ወራት ከውጪ ሀገራት ቱሪስቶች 2 ነጥብ 7 ቢሊየን ዶላር ገቢ ለማግኘት  ታቅዶ 1 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር ማግኘት መቻሉን የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳ ተናግረዋል ።

በግማሽ አመቱ 380 ሺህ 376 የሚሆኑ የውጪ ሀገር ቱሪስቶች በኢትዮጵያ የሚገኙ የተለያዩ የቱሪስት መዳረሻዎችን መጎብኝታቸው ነው የተገለፀው።

ይህ ውጤት ሚኒስቴሩ የእቅዱን 53 በመቶ ያከናወነ መሆኑን የሚያሳይ ነው ያሉት ሚኒስትሯ፥የቱሪስት ፍሰቱ ግን 46 በመቶ መሆኑን ጠቁመዋል ።

የቱሪስት ፍሰቱ ካለፉት ዓመታት ጋር ሲነፃፀርም በተሻለ ሁኔታ መጨመሩን ዶክተር ሂሩት ተናግረዋል ።

በተያያዘ ዜና በ2011 በጀት ዓመት ለመጠገን ዕቅድ ከተያዘላቸው 26 ቅርሶች ውስጥ የላሊባላ ውቅር ዓብያተ ክርስቲያናት፣የጅማ አባ ጅፋር ቤተ መንግስትና የአክሱም ሀውልት ቅድሚያ የሚሰጣቸው መሆኑ ተገልጿል።

በናትናኤል ጥጋቡ

በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የሰብአዊ መብት ጥሰት የፈፀሙ የማረሚያ ቤት ሃላፊዎች ላይ ክስ ተመሰረተ

ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ላይ በደረሰው ቃጠሎ በተነሳው ረብሻ ምክንያት የሰብአዊ መብት ጥሰት የፈፀሙ የማረሚያ ቤት የፖሊስ አባላት ላይ ክስ ተመሰረተ፡፡

ተከሳሾች በቅደም ተከተላቸው መሰረት ኦፊሰር ገብረማርያም ወልዳይ አብርሃ፣ ሱ/ኢን/ት አስገለ ወልደ ጊዮርጊስ ወ/ማርያም፣ ዋ/ሱ/ኢን/ት አሰፋ ኪዳኔ ተድላ፣ ዋ/ሱ/ኢን/ት ገ/እግዚአብሄር ገብረ ሃዋርያት፣ ዋ/ሱ/ኢን/ት ተክላይ ሀይሉ ተክለ ሃይማኖት፣ ዋ/ሱ/ኢን/ት አቡ ግርማ ወ/ሚካኤል፣ ዋ/ሱ/ኢን/ት አዳነ ሀጎስ ህሻ እና ዋ/ሱ/ኢን/ት ገብራት መኮንን ገብሩ ናቸው

ተከሳሾች በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች የቂሊንጦ፣ የዝዋይ እና የሸዋ ሮቢት ማረሚያ ቤት በተለያየ የሃላፊነት ደረጃ ሲሰሩ የነበሩ ናቸው፡፡

የክሱ ዝርዝር እንደሚያስረዳው ነሀሴ 28 ቀን 2008 ዓ.ም በግምት ከጠዋቱ 1 ሰዓት እስከ 3 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ቂሊንጦ ማረፊያ ማረሚያ ቤት ላይ በደረሰው ቃጠሎ በተነሳው ረብሻ ምክንያት ከኃላፊዎች በተሰጠው ትዕዛዝ ማንነታቸው ባልተለየ የማረሚያ ቤት የፖሊስ አባላት በተተኮሰ ጥይት በታራሚዎች ላይ ከባድ አካላዊ ጉዳት እና ህይወታቸው እንዲያልፍ ተደርጓል፡፡

በተፈጠረው የማረሚያ ቤት ቃጠሎ ምክንያት ከ400 በላይ የሚሆኑ በእስር ላይ የነበሩ ታራሚዎችን ወደ ሸዋሮቢት ተሃድሶ ልማት ማረሚያ ቤት እንዲወሰዱ በማድረግ የነበራቸውን ንብረት በመቀበል በባዶ እግራቸው በቁምጣ ብቻ በመኪና ላይ እንዲጫኑ ተከሳሾቹ ማድረጋቸውን ክሱ አመልክቷል፡፡

ሸዋ ሮቢት ማረሚያ ቤት ሲደርሱም በመስመር በማሰለፍና በማረሚያ ቤት ፖሊስ አባላት በዱላ በመደብደብ፣ 175 የሚሆኑ ታራሚዎችን ደግሞ ባዶ ቤት የሴሚንቶ ወለል ላይ እንዲተኙ በማድረግ፣ ለሁለት ለሁለት በካቴና በማሰር ለረዥም ጊዜ በማቆየት፣ በካቴና እጃቸውን ሁለት ሁለት እያደረጉ በማሰር በባዶ እግራቸው መፀዳጃ ቤት እንዲጠቀሙ በማድረግ፣ እጃቸውን ሳይታጠቡ ምግብ እንዲመገቡ እና ህክምና በመከልከል ብሎም ከቤተሰብ ጋር እንዳይገናኙ አድርገዋል ብሏል ክሱ፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ምርመራ ጨርሰው ወደ ሌላ ክፍል ሲዘዋወሩ ለ42 ቀናት ከአልጋ ጋር ለ24 ሰዓት በካቴና በማሰር፣ 37 የሚሆኑ ተበዳዮች ፍርድ ቤት ረበሻችሁ በማለት ከ3 እስከ 6 ወር እጃቸውን በካቴና አስሮ ጨለማ ቤት ውስጥ በማሰር፣ ግለሰቦች የለበሱትን ልብስ በማስወለቅ ቲሸርትና ቁምጣ በማስለበስ እና በፌሮ ብረት እንዲደበደቡ በማድረግ ኢ- ሰብአዊ ድርጊት እንዲፈጸምባቸው ያደረጉ በመሆኑ በፈጸሙት ስልጣንን ያለአግባብ መጠቀም ወንጀል ተከሰዋል፡፡

የተከሳሽ ጠበቆች የዋስትና መብታቸው እንዲከበር የተከራከሩ ቢሆንም የተከሰሱበት ወንጀል የዋስትና መብት የሚያስከለክል በመሆኑ ፍርድ ቤቱ አልተቀበለውም፡፡

ተከሳሶችም በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ ወንጀል ችሎት ዐቃቤ ህግ የመሰረተባቸው ክስ በችሎቱ ተነቦ ለቀረበባቸው ክስ መልስ ይዘው ለመቅረብ ለየካቲት 27/20011 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል፡፡

ምንጭ፦ የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ

ልዕልት ሳራ ግዛው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል

ልዕልት ሳራ የግርማዊ ዐፄ ኃይለሥላሴ ልጅ የልዑል መኮንን ኃይለ ሥላሴ ባለቤት፣ የንጉሡን አመራር የሚቃወሙ የኢትዮጵያ ወጣት ተማሪዎች ንቅናቄ አመራር ከነበሩት አንዱ የነበረውና አፍንጮ በር አካባቢ የተገደለው የጥላሁን ግዛው ታላቅ እህት ነበሩ።

በ1920 ዓም በአዲስ አበባ ከተማ የተወለዱት ይህቺ ውብ ልዕልት እቴጌ መነን ካለፉ በኋላ በእሳቸው ምትክ የንጉሱ ልዩ አጃቢ በመሆን ወደ ተለያዩ ግዛቶች በመጓዝ አገልግለዋል። እንዲሁም በእንግሊዝ አገር በነርስነት ሙያ ተመርቀው እንደ ልዕልት ፀሐይ በኢትዮጵያ ውስጥ በግዜው በነበሩት በተለያዩ ሐኪም ቤቶች በመዘዋወር ያለምንም ክፍያ በራሳቸው ፍቃድ የበጎ አድርጎት አግልግሎት ለህብረተሰቡ ያበረከተቱና የተለያዩ የውጭ ሃገራት ቋንቋዎች የመናገር ችሎታ ስለነበራቸው የቤት መንግስት አስተርጓሜ ሆነውም ያገለገሉ ታላቅ ሴት ነበሩ።

በደርግ ለአስራ አምስት አመታት በእስራት ያሳለፉት ልዕልት የኖሩበትን ፊውዳል ስርዓት የማይወክሉ ይህቺ ውብ ልዕልት በዘመናቸው ያደረጓቸው ከዋጋ በላይ የሆነ ልባዊ አስተዋጾ ለአሁን ትውልድ ሴቶች አርአያ ይሆናል።

Petros Ashenafi Kebede

ግንቦት 7 ለኢትዮጵያዊነት ቆሚያለሁ የሚለን የምሩን ወይስ ድራማ እየሰራብን? (ግርማ ክሳ)

እሁድ የካቲት 10 ቀን 2011፣ ግንቦት ሰባት በደብረ ማርቆስ ከተማ ሕዝባዊ ስብሰባ አድርጓል። ስብሰባው የተሳካ ስብሰባ እንደነበረ ነው ደብረ ማርቆስ ነዋሪ ከነበሩ የደረሰኝ መረጃ የሚገልጸው። የተለቀቁ ፎቶዎችም ይሄንን በግልጽ የሚያሳዩ ናቸው።

አንዳንድ ጽንፈኛ ቤተ አማራዎች የደብረ ማርቆስ ህዝብ ላይ፣ “ለምን ግንቦት ሰባትን ደገፋችሁ ?” በሚል ነው መሰለኝ ጣት ለመቀሰር የሞከሩም አሉ። ይህ ማሳዘን ብቻ ሳይሆን አሳፋሪም ነው። የደብረ ማርቆስ ሕዝብ ፣ ማን እንደሆነ፣ አገር ሁሉ የሚያውቀው ነው። “የኛን የአማራነት ፖለቲካ ለምን አልተቀበለም ?” ብሎ አፍላፊ መካፈት ትርፉ መላላጥ ነው።

ከዚህ በፊት ብዙ ጊዜ ጽፊያለሁ። የአማራ ወይንም አማርኛ ተናጋሪ ማህበረሰብ፣ እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሄረተኛው ፣ በትግራይና ኦሮሞ ብሄረተኛ ፖለቲከኞች ላለፉት ሃያ ሰባት አመታት፣ እንደ ጠላት እየታየ፣ ተለይቶ ሲጠቃና ሲገለል ነበር። አሁንም እንደተገለለ ነው። ከዚህም የተነሳ፣ “ራሳችንን መከላከል ስላለብን ፣ የሕልዉና ጉዳይ ነው” በሚል እንደ አብን ያሉ በአማራነት ስም ተደራጅተዋል። መደራጀታቸውን ባልደግፈውም፣ እንደማልቃወም፣ ለምን እንደተደራጁም እንደምረዳ በመግለጽ፣ በሂደት ግን ከአማራነት አልፈው አድማሳቸውን ካላሰፉ በቀር ለጊዜው ድጋፍ ቢያገኙም፣ ብዙ ዘልቀው መሄድ እንደማይችሉ መክሪያለሁ።

ሆኖም የአማራ ድርጅቶች “አንድ አማራ ለሁሉም አማራ፣ ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ” የሚል አግላይ መፈክር እያነገቡ፣ ውስጣችን አለ የሚሉትን ኢትዮጵያዊነትን ከማጉላት ይልቅ፣ አማራነትን ብቻ ማጉላታቸው ለብዙ ወገኖች፣ እኔንም ጨምሮ ምቾት አልሰጠም።

የደብረ ማርቆሱ ሰልፍ እንደ አብን ላሉ ድርጅቶች ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ ሰልፍ ነው። አንደኛ ከአማራ ድርጅቶች ሕዝቡ፣ “አማራ ተበደለ” ከማለትና ብሶት ከማሰማት ውጭ ግልጽ አማራጭ አልቀረበለትም። ሕዝቡን የሚመጥን፣ ወደፊት የሚያሻግር፣ መግለጫ ከማውጣት ያለፈ፣ መፍትሄዎችን የሚያስቀምጥ አማራጮችን ማቅረብ መጀመር አለባቸው። ሁለተኛ ኢትዮጵያዊነት ማጉላት መጀመር አለባቸው። መግለጫዎቻቸው ራሱ ‘አማራ” የሚል እንጂ “ኢትዮጵያ” የሚል ብዙ አይነበብበትም። ያስ መስተካከl መቻል አለበት።

አንዳንዶች ደብረ ማርቆስ የታየው በአማራነት ላይ በደንብ ስላልሰራን ነው ይላሉ። ይህ ስህተት ነው። እመኑኝ በደንብ በአማራነት ሰራን ያሉባቸው ቦታዎችም፣ የደብረ ማሮቆስ አይነት እንደውም የበለጠ ሕዝባዊ የኢትዮጵያዊነት ትእይንት ይደረግባቸውል። ከዚህ በፊት ተደረጎባቸውም ያውቃል፡፡ የፈለገ የአማራነት ፖለቲካና ፕሮፖጋንዳ ቢደረግም የአማራ ማህበረሰብ ደምና አጥንቱ ኢትዮጵያዊነት ነው። ደብረ ማርቆስ ፍንትው ባለ መልኩ ይሄንን አረጋግጣለች። የደብረ ማርቆስ ሕዝብ ስነ-ልቦና ከሌላው የአማራ ክልል ስነ-ልቦና በምንም አይለየም። አማራነት ላይ በደንብ አልሰራንም በሚል የበለጠ አማራነት ላይ ከማጠንከር፣ ሕዝቡ ጋር ያለውን ይዞ፣ ከአማራነት ወደ ተሻለው፣ ከፍ ወዳለው ማደግ ይሻላል። ወደ ኢትዮጵያዊነት።

በአንጻሩ የግንቦት ሰባት ካድሬዎችም ሲቀውጡት እያየን ነው። ጎጃም የግንቦት ሰባት ነው እያሉ። አይ የካድሬ ነገር። የግንቦት ስባቱ ጦማሪ ናትናኤል መኮንን ፣ “ህዝብ እውነተኛ ዳኛ ነው ሥልህ የታገለለትን የተሰቃየለትን፣ የሞተለትን እና ለእውነት ከምር አታግሎ የሚያታግለውን ያውቃል” ሲልም የደብረ ማርቆስ ሕዝብ ለግንቦት ሰባት ሰልፍ የወጣው፣ ግንቦት ሰባት ስላታገለው እንደሆነ ጽፏል። ይህ ከእዉነት የራቀ አባባል ነው።

አንደኛ – የደብረ ማርቆስ ሕዝባዊ ስብሰባን ያደራጁት ከጥቂት አመታት በፊት በዳያስፖራ፣ “የሰላማዊ ትግ አይሰራም” እያሉ፣ ግንቦት ሰባቶች ራሳቸው እንዳይደገፉ ሲዶልቱባቸው የነበሩ፣ የቀድሞ የአንድነት ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች ናቸው። ያኔ አንድነቶች ወያኔን ብቻ ሳይሆን ግንቦት ሰባትንም ነገር ሲታገሉ የነበሩት። ስለዚህ ግንቦት ሰባቶች ያደራጁት እንዳልሆነ በግልጽ መታወቅ አለበት።

የቀድሞ አንድነቶች ያንን የሚያደርጉት ለምንድን ነው ብላችሁ ብትጠይቁኝ ደግሞ መልሱ ቀላል ነው። ለአገር ትቅም ሲሉ፣ ያለፈውን ረስተው፣ የቀድሞ አንድነቶች ከግንቦት ሰባት ጋር አብረው ለመስራት ከመስማማታቸው የተነሳ ነው። በነገራችን ላይ ከዚህም በፊት በአዳማና በአርባ ምንጭ የተደረጉ የግንቦት ሰባት ስብሰባዎችንም የቀድሞ አንድነቶች ነበሩ ያዘጋጁት። ያው ግንቦት ሰባት ሌላው በሰራው ክሪዴት መውሰድ የለመደ ድርጅት ስለሆነ ለቀድሞ አንድነቶች እንኳን እውቅና መስጣት አልሞከረም። ትዝ የሚላችሁ ከሆነ በጎንደር የሸፈቱ አርበኞች አንዳንድ እንቅስቃሴዎች ሲያደርጉ ግንቦት ሰባት ቀድሞ በኢሳት ብቅ ይልና፣ ይሄን አደረኩ ብሎ ፕሮፖጋንዳ ይነዛ ነበር። ያው የድሮው ባህል ነው አሁን እነርሱ ጋር ያለው።

ሁለተኛ – የደብረ ማርቆስ ሕዝብ፣ ግንቦት ሰባት እንኳን ሕዝቡን ሊያደራጀና ሕዝቡን ሊያታግል ቀርቶ ሕዝቡን ላለፉት በርካታ አመታት ሲያጭበረብር የነበረ ድርጅት እንደሆነ ጠንቅቆ ያወቃል። ነገር ግን ሕዝቡ አማራጭ አላገኝም። ሕዝቡ ከአማራነት ኢትዮጵያዊነት ስለሚቀድምበት በአሁኑ ወቅት ደግሞ የገንዘብ አቅም ያለው፣ ሜዲያ(ኢሳት) ያለው፣ የሚታየው፣ ለኢትዮጵያዊነት ቆሚያለሁ የሚለው ድርጅት ግንቦት ሰባት ስለሆነ፣ ለግንቦት ሰባት ብሎ ሳይሆን፣ ግንቦት ሰባት አራምደዋለሁ ስለሚለው ኢትዮጵያዊነት ሲል በነቂስ ወጥቷል። የዛሬው የደብረ ማርቆስ ሕዝባዊ ትእይንት የግንቦት ሰባት ትእይንት ሳይሆን የኢትዮጵያዊነት ትእይነት ነው። ጉዳዩ ያለው ግንቦት ሰባት ጋር ሳይሆን ኢትዮጵያዊነት ጋር ነው። ስለዚህ የግንቦት ሰባት አባላትና ደጋፊዎች ትንሽ ሰከን ብትሉ ጥሩ ነው።

አንዳንድ ወገኖች ግንቦት ሰባት ማለት ኢትዮጵያዊነት ነው ይላሉ። እኔ ይሄን አልቀበለም። ግንቦት ሰባት ኢትዮጵያዊነት አቀንቃኝ ስለመሆኑ ማረጋገጫ የለኝም። የግንቦት ሰባት የፖለቲካ ፕሮግራም ፣ የፖለቲካ አቋም ምን እንደሆነ አላውቅም። የዜግነት ፖለቲካ እናራመዳለን ይላሉ፣ ግን የዜግነት ፖለቲካ ጸር የሆኑትን የጎሳ አወቃቀርና ኢትዮጵያዊነትና ዜግነትን የማያንጸባርቅ ሕገ መንግስት እንዲሻሻል ሲናገሩ አይሰሙም። በኦሮሞ ክልል ኦሮሞ ስላልሆኑ ብቻ ዜጎች እንደ ሁለተኛ ዜጋ ሲቆጠሩ ፣ ሲፈናቀሉ፣ ልዩነት ሲደረግባቸው ያንን ሲቃወሙ፣ ለነዚህ ወገኖች ሲሞግቱ አይታዩም። ለነርሱ ዘርና ጎሳ ከተሸነሸነው መሬት ውጭ ለሚኖሩ ሌሎች ማህበረሰብ የዜግነት መብት ሲከራከሩ አይሰሙም። በአዲስ አበባ ላይ ያላቸው አቋም ግልጽ አይደለም። የታከለ ኡማን አስተዳደርን የሚደገፉ ናቸው። በአጠቃላይ ግንቦት ሰባት ለሕዝብ ይፋ ያደረገው የፖለቲካ ፕሮግራም የለም። ስለዚህ ምንም ሰነድ፣ ፕሮግራምና ማኒፊስቶ ሳይኖር እንዴት ብለን ነው ግንቦት ሰባት የዜግነትና የኢትዮጵያዊነትን ፖለቲካ የሚያራመድ ነው የምንለው ??

በኔ እይታ ግንቦት ስባት

– አሁን ያለው የጎሳ አወቃቀር ፈርሶ ከጎሳና ዘር ጋር ያልተገናኛ፣ ማንኛውም ዜጋ በሁሉም የአገሪቷ ክፍሎች ዘሩ፣ ሃይማኖቱ፣ ሳይጠየቅ እንደ መጤ ሳይቆጠር፣ መኖር ፣ መስራት፣ መነገድ፣ መመረጥ፣ መምረጥ ….የሚችልበት አወቃቀር እንዲኖር
– አሁን ያለው ሕግ መንግስት ዜግነት ላይ ያተኮረ መሆነ መልኩ እንዲሻሻል

የሚጠይቅ የፖለቲካ ማኒፊስቶ ይዞ ከመጣና፣ በዚህ ማኒፌስቶ ዙሪያ ለመታገል ከተዘጋጀ ድጋፌ አይለየዉም። የኔ ብቻ አይደለም፣ እንደውም እኔ ደገፍ አልደገፍኩ ብዙ የሚለወጠው ነገር የለም፣ ግን የመላው ጎጃም፣ ጎንደር፣ወሎ፣ ሸዋ፣ ቦንጋ፣ ሶዳ፣ ጂንካ፣ ድሬዳዋ፣ አዳማ፣ ቢሾፍቱ፣ አሰላ ….የአብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብን ድጋፍ ያገኛል።

ያ ካልሆነ ግን ላይ፣ ላይ ላዩን የዜግነት ፖለቲካ እያለ ፣ ውስጥ ውስጡን ግን የኦህዴድ/ኦዴፓ ደጋፊና አጋፋሪ፣ አሁን ያለው አፓርታይዳዊ የኦሮሞ ክልል እንዲቀጥል የሚፈልግና የአማራ ማህበረሰብ የኢትዮጵያ ብሄረተኛውን አወናብዶ ለፖለቲካ ስልጣን መንጠላጠያ ብቻ ለማድረግ የሚሰራ ድርጅት ከሆነ ግን (ላለፉት በርካታ አመታት ሲያወናብድ እንደነበረው) እመኑኝ መተፋቱ የማይቀር ነው።

ደራ ጥያቄን ተከትሎ ቅምብቢት፣ አቢቹ፣ አዳማ ….መቀጠላቸው አይቀርም (ግርማ ካሳ)

ከአንድ አመት በፊት በደራ ጉዳይ ሰፋ ያሉ ጦማሮች ለቅቄ ነበር። በተለይም በኦሮሞ ክልል የሚኖሩ ኦሮሞ ያልሆኑ ማህበረሰባት ላይ የሚደርሰው በደል፣ አፓርታይዳዊ ተጽኖና አድልዎ እንደማያዋጣና አንዱ የበላይ ሌላው የበታች ሳይሆኑ ሁሉም ዜጎች እኩል የሚታዩበት ስርዓት መፍጠር አስፈላጊ መሆኑን አጠንክሬ ለረጅም ጊዜ ተከራክሪያለሁ።

በተለይም ኦሮሞና አማራ የተደባለቀ፣ ለዘመናት አብሮ የኖረ በመሆኑ፣ ኦሮሞንና አማራን በክልል መለየት መዘዙ በጣም የከፋ እንደመሆነ በማሳሰብ ፣ በተለይም ኦሮሞዉም አማራዉም እኩል የሚታዩበት፣ ኦሮምኛና አማርኛ የስራ ቋንቋ የተደረጉበት ሸዋ የሚባለ የፌዴራል መስተዳደር እንዲኖር ክፊት አድርጊያለሁ።

የአማራዉና የኦሮሞዉን መተሳሰር ዶ/ር አብይ “አማራና ኦሮሞው ሰርገኛ ጤፍ ናቸው” በማለት፣ አቶ ገዱ ደግሞ “አማራና ኦሮሞ ሰምና ፈትል ናቸው” በማለት ነበር ለማሳየት የሞከሩት። አሁንም አቶ ገዱን በመጥቀስ “ኢትዮጵያ ውስጥ በደንብ ቢጠና የአማራና የኦሮሞን ያህል የተቀላቀለ ህዝብ የለም” ።

ከአመት በፊት በጦመርኩት፡

“በኦሮሚያ ሰሜን ሸዋ ደራ ውስጥ የተወለደ አማራ ገበሬ ክልሉ ኦሮሞ ስለሆነ ብቻ ፍርድ ቤት ለመሔድ የአማርኛ ማመልከቻውን፣ ደረሰኝ ወዘተ በኦሮምኛ አስተርጉሞ መቅረብ አለበት፡፡ በዚህ መልኩ ገበሬው ለብጣሽ ሪሲት ሳይቀር መቶ ብር ወይም ከዚያ በላይ አውጥቶ ያስተረጉማል፡፡ ብዙ ኢንተርፕራይዞችም የአማርኛ ደብዳቤን በማስርጎም ሥራ የደሃ ገበሬዎችን ሀብት ይዘርፋሉ፡፡ በዚህም ምክንያት 20 ወይም 30 ገጽ ያለው አቤቱታ ለማስተርጎም ብዙ ሺህ ብሮች ስለሚያስፈልግ ከፍትኅ ሥርዓቱ እንዲገለሉ ያደርጋል ማለት ነው፡፡ በመሠረቱ እንኳንስ ትንሽ የማይባሉ ዜጎች ያሉበት አካባቢ ሆኖ አንድ ሰውም ቢሆን በራሱ ቋንቋ ፍትኅ ማግኘት የሚያስችል ሥርዓት መኖር መቻል ነበረበት፡፡ ከዚህም በከፋ በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ትምህርት የመማር መብት የሌላቸው ዜጎች ሚሊዮኖች ናቸው” በሚል በክፍፍሉ የተጎዱ ወገኖች ቁጥር ቀላል እንዳልሆነ ነበር የገለጽኩት።

ስለ ደራም ፣ “በኦሮሞ ክልል የተረሳ፣ አማርኛ ተናጋሪዎች በብዛት ያሉበት ወረዳ ነው። የደራ ወረዳ። ወረዳው መጀመሪያ ደረጃ ለምን ወደ ኦሮሞ ክልል እንደተቀላቀለ ግልጽ አይደለም። በሁለተኛ ደረጃ በወረዳው አንድ በኦህዴድ የተሰራ ትምህርት ቤት፣ ብጣሽ መንገድ..አለመኖሩ በአገሪቷ ያለውን ኢፍትሃአዊነት በግልጽ የሚያሳይ ነው። ” በማለት የደራ ህዝብ እየደረሰበት ያለውን አጋልጫለሁ።

በደራ አማርኛ ተናጋሪው ከ75% በላይ ነው። በቅምቢብት ከ 60%፣ በአብቹ ደግሞ ከ 50% በላይ።

እነዚህ ወረዳዎች አማራ ክልል ጋር የገጠሙ ሲሆን ወደ ኦሮሞ ክልል ግን እንዲጠቃለሉ ተደርጓል።ምክንያቱን ቢጠየቅ የሚሰጠው መልስ ግጽና ቀላል ነው። የአማራ ማህበረሰብ ሕወሃትና ኦነግ አገሪታኡን ሲሸነሽኑ “ተሸናፊ” ስለነበረ ብዙ አማርዎች ወይንም አማርኛ ተናጋሪዎች የሚኖሩባቸው አካባቢዎች ወይ ወደ ትግራይ አሊያም ወደ ኦሮሞ ክልል እንዲጠቃለሉ ተደርጓል።

ደራ፣ አካባቢዉ ወደ 13 ቀበሌዎች ያሉት ሲሆን በጎጃም የአባይ ወንዝ፣በወሎ የወለቃ ወንዝ፣በመረሀቤቴ የወንጪት ወንዝ እና ወደ አዲስ አበባ የጀማ ወንዝ ያዋስኑታል። አማርኛው ተናጋሪው ከከ80% በላይ ሆኖ ወደ ኦሮሞ ክልል እንዲጠቃለል ተደረጎ ለሃያ ሰባት አመታት ኦሮምኛ ብቻ የስራ ቋንቋ በተደረገበት፣ አፓርታይዳዊ ዘረኛ የኦሮሞ ክልል እስጥ ሁለተኛ ዜጋ ተደረገው ሲኖሩ ነበር።

የደራ ህዝብ በአሁኑ ወቅት ድምጹን እያሰማ ነው። እክሉእንት፣ ፍትህ እያለ ነው። በአገራችን ሁለተኛ ዜጋ ተደረጎ መቂጠር ይብቃ እያለ ነው።፡ኦሮምኛ ባለመቻላችን ጭቆና አይፈጸምበን እያለ ነው።

አሁንም መፍትሄው የአማራ የኦሮሞ ክልል ሳይባላ ይሆእ በታሪካ አብሮ የኖረን፣ የተዋለደን ማህበረሰብ ሸዋ በሚል መስተዳደር ውስጥ፡ማቀፉ ብቻ ነው።

### የውጫሌ ውል ከዲፕሎማሲ እይታ አንፃር ### Mes Demoze


· 

የዓድዋ ጦርነት መነሻ የሆነውን የውጫሌን ውል መፈራረም ከኢትዮጵያ አንፃር እንደ ታሪካዊ ስህተት ቢታይም ያመጣብን ችግር በውስጡ ያልታሰበ በረከትም ነበረው፡፡ በዘመናዊው የዓለም ፖለቲካ በውል የተሳሰሩት ሀገራት አንዱ ሀገር ሌላውን እንደ ሀገር መኖር መቀበሉንና እውቅና መስጠቱን ማረጋገጫ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ የውጫሌው ውል ለኢትዮጵያ እንደ ሀገር የመኖር እውቅናን አትርፏል ማለት ነው፡፡ ይህን በተመለከተ ሬይሞንድ ጆናስ ሲያብራራ “በ19ኛው ክፍለ ዘመን አውሮፓውያን ከአፍሪከ ሀገራት ጋር መዋዋላቸው ያልተለመደ ስለነበር የውሉ 17ኛው አንቀፅ ምንም ችግር ቢኖረውም ጣሊያን ከኢትዮጵያ ውል ማሰሯ በራሱ ጣሊያን ምኒልክ ለሚያስተዳድሯት ኢትዮጵያ አውቅና መስጠቷን ያሳየ ነበር” ሲል ያትታል፡፡ ፀሀፊው ሲቀጥልም “ራስ መኮንንና ቀሪዎቹ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን አባላት ነሃሴ 27 ቀን 1889 እ.ኤ.አ ሮም ላይ ከባቡር ሲወርዱ ለአፍሪካ ድል ነበር፡፡ ከሰሀራ በታች ባለችው አፍሪካና በአውሮፓ መካከል በሰለጠነው ዘመን የመጀመሪያው የከፍተኛ ደረጃ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙትነት ነበር” ይላል፡፡ የውጫሌ ውል ትርጓሜ ኋላ በጦርነት ቢቋጭም በመነሻው ግን ለኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ እውቅና በር የከፈተ እንደነበር መገንዘብ ይቻላል፡፡

የውጫሌ ውል ቅቡልነት በአውሮፓ ሀገራት

“ጣሊያኖች የውጫሌን ውል አንቀፅ 17 በተመለከተ ለሌሎች መንግስታት ከመናገራቸው በፊት ሁለት ሳምንት ቀደም ብለው ለሩሲያ አሳወቁ” ይላል ሃሮድ ማርከስ “አፄ ምኒሊክ” በሚለው መፅሀፉ፡፡ ይህም መስኮብ የጣሊያን ኢትዮጵያን ለመቆጣጠር እቅድ ላይ እንቅፋት እንዳትፈጥር ለማድረግ ነበር፡፡ የውጫሌን ውል ጣሊያነኛ ትርጉም እንግሊዝና ጀርመን በመቀበላቸው፤ አፄ ምኒሊክ “ንጉሠ ነገሥት መሆኔን እወቁልኝ” በሚል ለላኩት ደብዳቤ የሰጧቸው ምላሽ በሞግዚትዎ በኢጣሊያ በኩል ደብዳቤው ይድረሰን የሚል ነበር፡፡ በሌላ ወገን የፈረንሳይና ሩሲያ መንግስታት ግን የጣሊያንን ሞግዚትነት አለመቀበላቸው ለኢትዮጵያ ነፃነቷን ጠብቃ መቆየት የጎላ ሚና ተጫውቷል፡፡

ፈረንሳይ ፡-

ፈረንሳዮች የጣሊያንን በእንግሊዝ ታግዞ የሚደረገውን ኢትዮጵያን የመቆጣጠር ፍላጎት አልወደዱትም ነበር። ከጦርነቱ አስቀድሞ ኢትዮጵያ ለውጭ ንግድ ግንኙነቷ በፈረንሳይ ስር የሚገኘውን ኦቦክ (ጅቡቲን) ለመጠቀም ስትጠይቅ መፍቀዷ ኋላም ለጦርነት ዝግጅት ሲጀመርም ከጣሊያን እውቅና ውጭ የጦር መሳሪያ ወደ ኢትዮጵያ ለማስገባት ይህንኑ ወደብ አጼ ምኒለክ እንዲጠቀሙ መስማማታቸው ይህን ፍላጎታቸውን የሚያሳይ ነው።

መስኮብ

ተክለጻዲቅ መኩሪያ “አጼ ምኒልክና የኢትዮያ አንድነት” በሚለው መፅሀፋቸው የኢትዮጵያና የመስኮብ መንግስትና ቅድመ ዓድዋ ግንኙነትን ሲገልጹ “የጣሊያኖች አጥቂነት በከፋበት ሰዓት የመስኮብን እርዳታ ማግኘት አስፈላጊ ነበር፡፡ ለዚህም በፊታውራሪ ዳምጠው ከተማ የሚመራ ልዑካን ቡድን ወደ ሩሲያ ሲያመራ በንጉሠ ነገሥቱ ዳግማዊ ኒኮላ የተደረገለት እጅግ የደመቀ የክብር አቀባበል ኢጣሊያኖችን እጅግ እስቆጣ” ሲሉ ይገልፃሉ፡፡

የውጫሌ ውል እንደውል ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ግንኙነት እንደ ነፃ ተዋናይ የመሳተፍ መብቷን በተግባር ያሳየ ሲሆን፤ ከዓድዋ ጦርነት በፊትም የኢትዮጵያን የውጭ ግንኙነት ነፃነት በ17ኛው አንቀጽ ለመገደብ የሞከሩት ኢጣሊያኖች ሀሳባቸው አልሰመረም፡፡ በተቃራኒው ኢትዮጵያ ከአውሮፓ ኃያላን ጋር የሁለትዮሽ ግንኙነት በመፍጠር ለዓድዋ ጦርነት የጦር መሳሪያ በበቂ አቅርቦት እንድታገኝ አድርጓል፡፡ ይህም በዓድዋ ጦርነት ኢትዮጵያ በወራሪዋ ኢጣሊያ ላይ ለተቀዳጀችው የበላይነት መንገዱን አመቻችቷል ፡፡

#የጥቁር_ህዝብ_ኩራት
#ዓድዋ_123 
#የኢትዮጵያውያን_ድል
#VictoryofAdwa
#Ethiopia

የዓድዋ ድልና እቴጌ ጣይቱ Minilik Salsawiየዓድዋ ድልና እቴጌ ጣይቱ

1. ቅድመ ጦርነት

የዓድዋ ጦርነት ከመጀመሩ በፊት ሃገር እስክትረጋና የጦር መሳሪያ እስኪሠበሠብ ድረስ አፄ ምኒልክ ከኢጣልያ ጋር የነበረውን ግንኙነት ፍፁም ብልጠት በተሞላበት ዲፕሎማሲያዊ መንገድ ሲያስኬዱት ነበር። 
እቴጌ ጣይቱ ከእርሳቸው በፊት ከነበሩትም ሆነ ከሳቸው በኋላ ከመጡት እቴጌዎች የሚለዩት በመንግስቱ ሥራዎች ውስጥ እየገቡ ያማክሩ፣ ታላላቅ ሃገራዊ ጉዳዮችንም ከንገሡና ከመኳንንቱ ጋር በመምከር ውሳኔ እንዲተላለፍም ያደርጉ ስለነበር ነው።

ለዓድዋ ጦርነት መነሳት ትልቁን ሚና የተጫወተው የውጫሌን ውል ጉዳይ ሊያስፈፅም የመጣው የአጣልያ ቆንስላ ኮንት አንቶሎኒ በአንቀጽ 17 ተቃውሞውን አሠምቶ ኢጣልያ ጦርነት እንደምታስነሳ በምኒልክ ቤተመንግስት ውስጥ ሲፎክር እቴጌይቱ የመለሱለት እንዲህ በማለት ነበር

“ … የዛሬ ሳምንት አድርገው፡፡ እኔ ሴት ነኝ ጦርነት አልወድም፤ ነገር ግን ሀገሬ እንደዚህ ያለ ክብር የሚነካ ዘለፋ ከምትሸከም ጦርነትን እመርጣለሁ፡፡ ሂድ መንገዱን ጨርቅ ያድርግልህ እግሩን ለጠጠር፤ ደረቱን ለጦር አስጥቶ፤ ደሙን ለሀገሩ ፍቅር አፍስሶ፤ ለአፈሩ ክብር ለብሶ፤ እሱ ወድቆ ሀገሩን የማያቆም እዚህ ያለ እንዳይመስልህ! ሂድ! የኢትዮጵያን ሰው ባታውቀው ነው፡፡ ለሀገሩ መሞት ማለት ለሀበሻ ጌጡ ነው፡፡ ሂድ ባሻህ ግዜ ተመለስ ተሰናድተን እንጠብቅሃለን፡፡ ያንተን ወንድነትና የጣይቱን ሴትነትም ያን ጊዜ እናየዋለን ሂድ መንገዱን ጨርቅ ያድርግልህ፡፡”

ይሄ የእቴጌይቱ ንግግር በወቅቱ ያሳደረው ጫና ቀላል የሚባል አልነበረም ለአብዛኛው ዘማች አርበኛ ” ሴቷ እንኳን ……” የሚል እሳቤን በውስጡ እንዲኖር ሲያደርግ በተጨማሪም ለኢጣልያ ጦር የሠጠው ግምት አናሳ እንዲሆንና ድል ማድረግ እንደሚችልም ውስጡን እንዲያሳምን አድርጎታል። እዚህ ንግግር ላይ ለሃገር ያላቸውን ከፍ ያለ ፍቅር ያሳያል አይደለም የሃገር ዳር ድንበሯ ተነክቶ ይቅርና ዘለፋን እንኳን መቋቋም የማይችል አመለካከት እንደነበራቸውም ያሳያል ……ሃገሬ እንደዚህ ያለክብር የሚነካ ዘለፋ ከምትሸከም ጦርነትን እመርጣለሁ ….

2. ጦርነቱ ላይ

በዓድዋ ጦርነት እቴጌይቱ በራሳቸው በኩል 5,000 ጦር ይዘው የዘመቱ ሲሆን በተጫማሪም ስንቅ በማዘጋጀት፤ የደከመውን በማበርታት፤ የቆሠለውን በማከም፤ የሚሸሸውን በመገሰፅ ታላቅ ተጋድሎን ሲፈፅሙ ውለዋል። 
የዕለቱን የእቴጌይቱን ውሎ ጸሃፌ ትዕዛዝ ገብረሥላሴ እንዲህ ይተርኩታል
……. በዚህ ቀን በዓድዋ በዐይናችንን ያየነውንና በዦሮአችን የሠማነውን ለመጻፍ ችግር ነው። በዚህ ጊዜ እቴጌ ጣይቱ በማጅራታቸው ድንጋይ ተሸክመው በጉልበታቸው ተንበርክክከው በጋለ ፀሎት ወደ እግዚአብሔር ይጸልዩ ነበር። እቴጌ ጣይቱ ጥቁር ጥላ አስይዘው አይነርግባቸውን ገልፀው ወደፊት ጉዟቸውን ቀጠሉ። ወዲያውም የኋላው ወታደር ሲያመነታ አይተው “በርታ ምን ሆነሃል ድሉ የኛ ነው በለው” በማለት ሲያበረቱ ሁሉም ወደፊት ገፋ። እቴጌይቱ በዚህን ቀን የሴትነት ባህሪያቸውን ትተው እንደወንድ ወታደሮቻቸውን በግራና በቀኝ አሠልፈው ወደ ጦርነቱ ገቡ። ቁስለኛና ምርኮ የያዘውም ወደኋላ ሲመለስ ባዩት ጊዜ “ንጉሡ ሳይመለሱ ወዴት ነው የምትመለሱት? ምርኮኞቻችሁንና ቁስለኞቻችሁን ለኔ ስጡኝና ተመለሱ ……. በማለት ጦሩን ያበረቱ ነበር። 
ከውጫሌ ውል ጀምሮ ያልተለዩትና በኢጣልያኖች ሃሳብ ሲናደዱ የቆዩት እቴጌይቱ የቁርጡ ቀን ሲመጣ 
በፈጣሪ በጣም ይታመኑ ስለነበር በፀሎት መጀመራቸውን ጦርነቱ ሲፋፋምም ይዘው የዘመቱትን 5000 ጦር ይዘው መሃል ገብተው ያዋጉ እንደነበር በመጨረሻም ቁስለኛን ሲያክሙ የደከመውንም ሲያበረቱ በመዋል ታላቅ ስራን ፈፅመዋል። ከዚህም በተጨማሪ እቴጌይቱ ለኢትዮጵያው ዘማች ብቻ ሳይሆን ለኢጣልያኖቹም ምን ያህል ሩህሩህ እንደነበሩ ማሳያው ምርኮኞቹን ጥለውላቸው ከሄዱ በኋላ እንደ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ጣልያኖቹንም በማከምና ውሃ በመስጠት ሲንከባከቡ እንደነበር ተፅፎ ይገኛል ይሄም ምን ያህል ይቅር ባይ ልብ እንደነበራቸው ያሳያል። ከጦርነቱ ፍፃሜ በኋላ የኢትዮጵያ አርበኛ ሲጨፍር “አዳም አዳምን ገደለና ይሄ ሁሉ ደስታ ለምን ነው?” የሚለው ንግግራቸው ምንም ጠላት ቢሆኑ እንኳን በሠው ልጆች ሞት መደሰት እንደማይገባ የሚያሳይ ነው። 
ሃገር በምን አይነት መስዕዋትነት እንደቆመች አንዘነጋም።

#የጥቁር_ህዝብ_ኩራት
#ዓድዋ_123
#የኢትዮጵያውያን_ድል
#victoryofAdwa
#Ethiopia