እስኪ ሁሉም ያንብበው ስለ አዲስ አበባ ሕገ መንግስቱ ምን ይላል? (ሰርፀ ደስታ)

ከታች አለላችሁ አጭር እኮ ነች፡፡ ሁሉም አንብቦ ይረዳ፡፡ ሕግ ከአለ፡፡ ለመሆኑ የሕ ባለሙያዎች ዝምታ እንዴት ነው? አዲስ አበባ በሕግም በተፈጥሮም የአዲስ አበባ ነዋሪ ነች፡፡  ይሄ አዲስ አበባ የሁሉም ነች የሚል ማደንቆሪያ ይቁም፡፡ በዚህ አይነት ማደናገሪያ ነው ከሕግ ውጭ እየተፈነጨ ያለው፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ራሱን በራሱ የማስተዳደር ሙሉ ስልጣን አለው!!!!

እኔ ከጅምሩ ስናገር ነበር ችግሩ ያለው ወያኔ ጋር ሳይሆን የኦሮሞ ፖለቲካ ውስጥ ነው፡፡ ወያኔ ከጀምሩ የኦሮሞ ፖለቲካ ጥላቻና ዘረኝነት ላይ ያተኮረ እንደሆነ በደንብ ስለገባት ይሄንኑ በመጠቀም ነበር 27 ዓመት የኖረችው፡፡ አሁን ችግሩ አፍጦ ስለመጣ ሁሉም እየተረዳው መሠለኝ፡፡ገልጠን መናገር የማንፈልገው እውነት አለ፡፡ ይሄን ጉዳይ ብዙ ኦሮሞ ነን የሚሉትም ያውቁታል፡፡ ግን በኦሮሞነት ስለደነዘዙ በራሳቸው ጭምር በአንገታቸው ሲባጎ እየሳቡ ይመስላል፡፡  የኦሮሞ አክራሪዎች ኢትዮጵያን ለማፍረስ ያልፈነቀሉት ድንጋይ የለም፡፡ ዛሬ ቄሮ ባመጣው ለውጥ እየተባለ የሚፎከረው እውነቱ በጀዋር ሲመራ የነበረው ቄሮ ዓላማ አድርጎ ተነስቶ የነበረው አገርን ለማፍረስ ነበር፡፡ ይሄን ሴራ ለማ አመከነው እንጂ፡፡ በትግሉ ከሸዋ ኦሮሞ ውጭ ለለውጡ ሳይሆን ሲሰሩ የነበሩት አገር ለማፍረስ ነበር፡፡  እንደእውነቱ ለማን ዛሬ ተናገረ በተባለው ጉዳይ መመዘን አልፈልግም፡፡ ለማ አሁንም ቢሆን ተቸግሯል የሚለው እምነቴ እንዳለ ነው፡፡ ችግር አለ፡፡ የለማ ጥፋት ግን ቆፍጠን ያለ አቋም ላይ መቆም ቢችል አሸናፊ ይሆን ነበር፡፡ ችግሩ በኦሮሞነት ሲያባብለው የነበረ እባብ ዛሬ ጎልበት እንዲያገኝ እድል መክፈቱ ላይ ነው፡፡ ኦፒዲኦ ውስጥ እጅግ አደገኛና አረመኔ የኦነግ አባላት አሉ፡፡ ከዛም ከፍ ሲል፡፡ ችግር አለ! ግን ማንም ቢሆን ለእነዚህ ወሮበሎች ፊት መስጠት የለበትም፡፡ አገራችንን እናድን፡፡ ብዙ ኦሮሞ በአልገባው ነገር የዘረኝነትና ጥላቻ መርዝ ተግቶ በጥላቻ ወድቋል፡፡ ፍትህ ሥርዓት የሚባል ነገር አጥቷል፡፡ ከዚህ በኋላ በጉልበት እንጂ በመነጋገር የሚያምን አልሆነም፡፡ ብዙ ኦሮሞ ተለክፏል፡፡ የሰሞኑ የአዲስ አበባ ጎዳይ ብዙዎችን እንድታዘብ እድል ሰጥቶኛል፡፡ በጣም ሰለማዊ የሚባሉት ሁሉ ሳይቀሩ አዲስ አበባ የኦሮሞ ነች ወሮበላ አስተሳሰብ ተበክለዋል፡፡  የአዲስ አበባው ጉዳይ እነ አብይ ትልቅ ሸፍጥ እየሰሩ እንደሆነ እሰጋለሁ፡፡ ለመሆኑ ግን ያኔ በግርግር አዋጅ ተብሎ የተነገረንን አንድ ሕግ አዋቂ ጠፍቶ ነው? ይሄን ሰነድ ያዘጋጀው ማን ነው? ይሄን ጉዳይ የሚመለከታቸው የሕ ባለሙያዎች እንደገና አንብበው ቢያብራሩልን ጥሩ ነው፡፡

ሕገመንግስት በተባለው የኦነግና-ወያኔ የሴራ ሰነድ ላይ ልዩ ጥቅም ተብሎ የተባለው ምንድነው፡፡ ይሄን ሰነድ ያዘጋጁት ኦነግና-ወያኔ ነበሩ፡፡ በአዲስ አበባ ጉዳይ ምን አልባትም የወያኔ ባለስልጣናት ስላልፈለጉ ሊሆን ይችላል ይሄ ሰነድ ስለ አዲስ አበባ የሚለው የሚከተለውን ነው፡፡ እንግዲህ ሕገ መንግስት የሕጎች ሁሉ የበላይ እያሉ የሚጭፍሩትን ይሄንኑ ሰነድ መሠረት ባደረገ አዲስ አበባ በግልጽ ራሷን የቻለች ከተማ እንደሆነች እየታወቀ በጉልበት ከሕግ አግባብ ውጭ አዋጅ እስከማውጣት የተሄደበት ሂደት በምን ምክነያት ነው፡፡ የሕገ መንግስቱ አንቀጽ 49 እንደሚከተለው ይነበባል፡፡ ይቅርታ አማርኛው ስላላገኘሁት ነው

ሕገመንግስቱ በግልጽ የሚለው ከላይ እንደምታነቡት ነው፡፡ ለመሆኑ

ልዩ ጥቅም ምንድነው? እንደምታነቡት ልዩ ጥቀም የተባለው የአዲስ አበባ ከተማና የኦሮሚያ ክልል የአስተዳደር ወሰን ስለሚጋሩና አዲስ አበባ ብዙ አገልግሎቶች ከኦሮሚያ ታገኛለች በሚል ተሳቢነት አዲስ አበባ ለሚቀርብላት አገልግሎት ተመጣጣኝ የሆነ የገንዘብ ሊሆን ይችላለ ወይም የልማት ሥራ ለኦሮሚያ ከምታገኘው ገቢ እንደምታስብ እንጂ የኦሮሞ ጥቅም ማለት አደለም፡፡ በደንብ ይነበብ

የሰሞኑ የኦሮሚየ መንግስት መግለጫ ከሕግ አንጻር፡ በአዲስ አበባ ጉዳይ ላይ የይገባኛል ይቅርና በሕግ የአዲስ አበባ አስተዳደር ካልፈለገ የክልሉን መቀመጫን ማንሳት ይችላል፡፡ ሕግ ስለጠፋ እንጂ፡፡ ሲጀምር የኦሮሚያ ክልል ጽ/ቤት አዲስ አበባ ውስጥ በልዩ ጥቅምነት ከሚታሰቡት የአዲስ አበባ አገልግሎት ነው፡፡

አዲስ አበባ የማን ናት? በተፈትሮም በሕግም አዲስ አበባ የነዋሪዎቿ ነች፡፡ ይሄ አሻሚ ያልሆነ እውነት ነው፡፡ ይሄ አዲስ አበባ የሁሉም ነች የሚል ማደናገሪያ እንዲቆም፡፡ አሁን ወሮበሎቹ ከህግ ውጭ እንደፈለጋቸው እንዲፈነጩ ስለተደረጉ እንጂ እውነት ሕግ ቢኖር እየሆነ ያለውን ትልቅ ወንጀል ነው፡፡ አገር በወሮበላ አስተሳሰብ አትመራም፡፡ ሕገ-መንግስቱ እኮ በግልጽ የሚለው የአዲስ አበባ ከተማ ተጠሪነቱ ለፌደራለ መንግስቱ ነው ነው!! ሕዝቡም ራሱ በሚመርጠው ነው የሚወከለው፡፡ አስተዳደሩም እንደዛው፡፡ ይሄ ሁሉ ነው አሁን እየተጣሰ ያለው፡፡  ለአዲስ አበባ የወለጋ ኦነግ አይስንም፡፡

አዲስ አበባን ፊንፊኔ ለማለት ያስቻላወ አዋጅ በምን ሥልጣን ነው? እነ ጀዋር በሰጡት ሰነድ ካልሆነ፡፡ የኦሮሞ ፖለቲካ አገርና ታሪክን ለማውደም ቆርጦ እየሰራ እያየንው ነው፡፡ ብዙ ሙከራ ታሪካዊ ቦታዎችን ለማውደም ብዙ ተሴሯል፡፡ ከዝቋላ አቦና አሰቦትን ጋዳማቶችን ጨምሮ፡፡ ኤሬቻን ዝቋላ ላይ አከብራለሁ ብሎ ያወጀ መንግስት ነኝ የሚል ነው እኮ፡፡ ዝዋይን ባቱ ብሎ በጉልበት ቀይሯል፡፡

ሰሞኑን አንድ ባይሳ ወቅ ወያ ለተባሉ መልስ የሰጠሁበትን አንድ ዐለም ሰው ከቅንነት መሰለኝ በጽሁፌ አስተያየት ሰጥቷል/ለች፡፡ አስተያየት ሰጭው የባይሳ አመለካከት ትክል ነው ባይ ነው፡፡ አደለም፡፡ ባይሳ ሕገመንግስቱን የተረጎመው በኦሮሞነት እንጂ ስለሕሊናና እውነት አደለም፡፡ አዲስ አበባን የኦሮሚያ ዋና ከተማ ነችና ኦሮሚያ መብት አለው እያለን ነው፡፡ ኦሮሚያ አዲስ አበባን ለዋና ከተማነት መረጠ ከተማዋም ከኦሮሚያ ተጠቃሚ በመሆኗ የኦሮሚያን መንግስት ጽ/ቤቶች ለማስተናገድ ፍቃደኛ ሆነች እንጂ ኦሮሚያ በከተማዋ ላይ እንዲወስን አደለም፡፡ በግልጽ እኮ የኦሮሚያ መንግስት በአዲስ አበባ በጎ ፈቃድ ነው መቀመጫውን አዲስ አበባ ላይ ያደረገው፡፡ ሕጉ በግልፅ የሚተረጎመው እንደዚህ ነው፡፡ የአፍሪካ ሕብረት አዲስ አበባ ላይ ዋና ከተማውን ስላረገ የኢትዮጵያ አስተዳዳሪ አደለም፡፡ ነገሩ ባጎረስኩ እጄን ተነክስኩ አይነት ነው፡፡ ለመሆኑ ግን የኦሮሚያ መንግስት ነኝ ባዩ አዲስ አበባን ይቅርና ኦሮሚያን የማስተዳደር ሕጋዊነት አለው?ይሄ ለሁሉም ክልልች ተመሳሳይ፡፡ ዘሬ ኦሮሚያን የሚያስተዳድረው መንግስት ሳይሆን ኦዴፓ የተባለ የኦሮሞ ቡድን ነው፡፡ ሕግና ዲሞክራሲ ቢኖር የሚወሰነው በሕዝብ ድምጽ ነው፡፡ ቀጥሎ ራሱን የኦሮሞ ነኝ እያላና ስለሌሎች አያገባኝም እያለ መንግስት ሊሆን አይችልም፡፡ የብዙ ክልል ሕገ-መንግስ ሰነዶች በግልጽ ጽረ-ሕዝብ አንቀጾችን ነው የሚጠቀሙት፡፡ የኦሮሚያው ሕገመንግስት የክልሉ የበላይ ባለሥልጣን ኦሮሞ ነው ነው የሚለው፡፡ በክልሉ የሚኖሩ ሌሎች ሕዝቦች ሥልጣን የላቸውም፡፡ የሱማሌውም ሌላውም እንደዛ ነው ከአማራ ክልል ሕገ-መንግስት በቀር፡፡ የፌደራል መንግሰት ተብዬው እንዲህ ያለው ሕገ-ወጥ እንቀጽ በሕገ-መንግስታችን በአሉት አውጥተው ዝም ነው ያለው፡፡ እንደ እውነቱ አብዲ ኢሌ ኦሮሞን ከጂግጂጋ ሲያሶጣ ከክልሉ ሕገ-መንግስት አንጻር ትክክል ነው፡፡

ለለማ አንድ ብርሀኑ ሌንጂሶ የተባለ አክራሪ ኦሮሞ የፌንፊኔን ጉዳይ በፍጥነት አንድታስበብት ብሎ የጻፈለትን አነበብኩት፡፡ እንግዲህ በሕግና ስርዓት እንጂ የማንም ወሮበላ በሚሰጠው ትዕዛዝ መንግስት መሆን አይቻልም፡፡ ለማ በዚህ ቁማር ውስጥ ገብቶ ከሆነ ይሞክረው፡፡ አዋጅ ሲያወጡ እነጀዋር ጽፈው ሰጥተዋቸው ነበር፡፡ አሁን አዋጁን ባለመተግበራቸው ችግር ነው፡፡ ይሄ አዋጅ ገና ብዙ ጥያቄ ማስነሳቱ አልቀረም፡፡ አሁን ሕዝብ ነቅቷል፡፡ በዱላና በገጀራ እንወጣዋለን በሚል አስተሳሰብ የት እንደሚደረስ እናያለን፡፡

ሰሞኑን ኢሳት የተሳሳተ ዜና አወጣ ተብሎ የኦሮሚያ መንግስት እከሳለሁ ፍቃዱም መነጠቅ አለበት አለ ተብሎ ፌስ ቡክ ላይ አይቻለሁ፡፡ ኢሳት ይሳሰታል፡፡ ውስጥም ችግር አለ፡፡ የኦሮሚያው መንግስት ግን የተባለውን ብሎ ከሆነ አላማው ኢሳትን ሕግ ስለተላለፍ ሳይሆን ለማጥፋት ነው፡፡ በይፋ አዲስ አበባን በቁጥጥር ስር ለማድረግ በሁሉም ተዘጋጅተናል፡፡ ቄሮን የጀመርከውን ጨርስ ብዬ መልዕክት ማስተላለፍ ብቻ ነው ለእኔም ሥራ ቀለለልኝ እየላ ሲደፋ የነበረው ወሮበላ ሲያስተላለፍበት የነበረውን ሚዲያ እየሰራ ኢሳት የተሳሳተ ዜና ዘግቧል ተብሎ ፍቃደ ለመንጠቅ፡፡ ይሄው ተመሳሳይ ሻጥር ግንቦት ሰባቶችን ለመክሰስ ሙከራ ታደርጉም እንደነበር አውቀናል፡፡ ለዛም ነበር ያ በዘረኝነት የተመረዘ ሰውዬ አብይ አንዳርጋቸውን ቤተመንግስት ለምን ጋበዘ ብሎ አብእ የሆነው፡፡ ግልጽ ነው የኦሮሞ ፖለቲካ የተመሠረተው ጥላቻና ዘረኝነት ላይ ነው!

አሳዛኙ ጉዳይ ሕዝቡ ተጨቁነሀል ምናምን እያሉት በደረቅ ውሸት የጥላቻና ዘረኝነት ትርክት እየሞሉት ባዶውን እያስቀሩት ይኖሩበታል፡፡ 50 ዓመት ስለኦሮሞ ጭቆና ተወራ፡፡ ኦሮሞ ከንግዱም፣ ከኢትዮጵያዊ ማንነቱም፣ ከወሳኝነቱም ወጥቶ ዛሬ የዎረበላ ፖለቲካ ተከታይ ሆኖ ማንም ወደፈለገው ይዘውረዋል፡፡ እንደነ ጂጂና ጀዋር ያሉ ተራ ወሮበሎች የኦሮሞን ቀልብ ለመሳብ እድል ያገኙትም በዚህ ምክነያት ነው፡፡ ዛሬም ላለፉት 150 ዓመት ከተጫነህ አገዛዝ ይሉታል፡፡ ቁማርተኞቹ፡፡ ቆም ብሎ ላስተዋለው ይገርማል፡፡ ከ150ው 50ው ዓመት ይሄው ነጻ እናወጣሀለን ብለው ስለመበደሉ ብቻ እያወሩ ይባስ የራሱን እሴቶች እርግፍ አድርጎ እየተወ የወሮበሎች አስተሳሰብ ባሪያ እየሆነ ነው፡፡

አሁንም እላለሁ ኦሮሞ ነን የምትሉና ጤነኛ አስተሳሰብ ያላችሁ ሕዝቡን ታደጉት፡፡ የሕዝቡን ስነልቦና ከተጨቋኝነት መንፍስ አውጡት፡፡ የኦሮሞ ፖለቲካ ኦሮሞን እያመከነ ነው፡፡ ይሄን የኦሮሞ ፖለቲካ መንገድ አማራ ክልል እየሞከሩ ያሉ አሉ፡፡ ከወዲሁ ይተሰብበት ሳይቃጠል በቅጠል ነው፡፡ አብን የተባለው አሁን መሻሻል እያመጣ ነው፡፡ ለሕዝብ የተገዥነትና የተጨቋኝነት መንፈስ እየረጩ ሕዝብን የበታች አድርጎ ማኖር ከምንም የከፋ ወሮበላነት ነው፡፡ የኦሮሞ ፖለቲከኞች ኦሮሞን ያደረጉት እንደዛ ነው፡፡ ወያኔና ኦነግ በአማራ ላይ ዘመቻ የከፈቱ መስሏቸው ነፍጠኛ ምናምን ብለው ሊያሸማቅቁ ሞከሩ፡፡ የሚገርመው የነፍጠኝነት ስም ለአማራው ጥሩ መንፈስ ነው የሆነው፡፡ ተጨቆንክ ከመባል ጨኮንክ መባል የተሻለ ነው፡፡ እንጂመ ኦነግና-ወያኔ ብዙ ሞክረው ነበር፡፡ አሁን የሱማሌ ክልለ ፕሬዘዳንት የሆኑት ሙስጠፌ ተጨቁነናል ብሎ ሞቆዘመን ከመጠሉ፡፡ ተጨቁነናል የአስተሳሰብ ችግር እንጂ እውነት ላይ የተመሠረተ አለመሆኑን ከዚህ በፊት ሲናገሩ ነበር፡፡ ዛሬ የሱማሌን ሕዝብ እየታደጉት ነው፡፡ ተጨቁኜአለሁ ከሚለው አስተሳሰብ ለአገር ግንባታና ታሪክ ድርሻ አበርክቼአለሁ የሚሉ ብዙ የሚል ትርክቶችን ብዙ የሱማሌ ምሁራን አሁን እየተናገሩ ነው፡፡ የኦሮሞ ትልቁን ድረሻ ያበረከቱ አባቶችን ሁሉ እርግፍ አርጎ መተው ብቻም ሳይሆን ጭራሽ ከአማራ ጋር ተባብረዋል በሚል ከጠላቶች እንደ አንዱ ቆጥሮ ዛሬ ባዶውን እነጀዋር ይጫወቱበታል፡፡ ጎበና ደጬን ያለከበረ ኦሮሞ መቼም ቢሆን እራሱ ሊከብር አይችልም፡፡ ታላላቅ ጀግኖችን ስማቸውን እንኳን ለመጥራት ይቀፈዋል፡፡ ኦሮሞን በአገር አስተዳደርም ሆነ ልዕለና ከፍ ያደረገው ሚኒሊክ ዛሬ ኦሮሞን ስሙ ሲጠራ ያስደነብረዋል፡፡ በተሞላው የዘረኛና የጥላቻ ትርክት ከ150 ዓመት በፊት በስኬታማነቱና ለዓለም አዲስ ምዕራፍ ከፋች በሆነው ሚኒሊክን እጠላለሁ ብሎ ይሄው ዛሬ ዓለም ሚኒሊክን በክብር ባነሳ ቁጥር ይሄው እየባነነ ይኖራል፡፡ የኃይለስላሴ ሐውልት በአፈሪከ ዩኒየን ለመን ተሰራ ብሎ በጣላቻና ዘረኝነት ይቃጠላል፡፡ እንግዲህ ዘረኝነትና ጥላቻ እንዲህ ነው፡፡ እውነት፣ ፍቅርና ታላላቆች በተነሱ ቁጥር እየደነበሩ መኖር ነው፡፡ እንግዲህ አለም የሚያውቀው እውነተኛውን ታሪክ እንጂ እነተስፋዬ ገ/አብ የፃፉትን የጥላቻ ድግምት ወይም የኦነጋውያንን ስብከት አደለም፡፡ የእኔ የሚለው አንደም ነገር እንዳይኖረው አድርገው ይነግዱበታል፡፡ ኦሮሚያን ከንኦሮሞቲ፣ ፊንፊኔን ሀንዱራ ኦሮሞቲ፡፡ እያሉ እንደፈለጋቸው ይጋልቡታል፡፡ ኦሮሞን ለመምራት የጥላቻና ዘረኝነት ንግግሮች ወሳኝ ናቸው፡፡ ለዛም ይመስላል የሰሞኑ ብዙ የሕዝብ ድጋፍ የነበራቸው የኦዴፓ መሪዎች ንግግር ኦሮሞን ለማስደሰት በሚል፡፡  በኋላ እንዲህ በአለ ሁኔታ ከታሪክም ከድርሻም ባዶ አድርገው ለእነዙ መሣሪያነት ይጠቀሙበታል፡፡

ዛሬ እነ አብይ በሰጧቸው አድል እንቅልፍ አጥተው ከኦሮሚያ አልፈው ሌሎችን ክልሎችንም ሠላም ለማሳጣት እየሰሩ ነው፡፡ የሲዳማው እንቅስቃሴ በኦሮሚያው አክራሪ ቡድን የሚታገዝ እንደሆነ እንረዳለን፡፡ አይጥ ላመሏ የድመት አፍንጫ ትልሳለች ሆነና ሲዳማም ውስጥም አሁን እየደነፋ ያለ ቡድን ተፈጥሯል፡፡ ሲዳማ ክልል አደለም አገር መሆን መብቱ ነው፡፡ አዋሳን ግን አያገኛትም፡፡ ይሄ የወሮበላነት አመለካከት ዛሬ የኦሮሞው ወሮበላ ቡድን ጃስ እንዳላቸው የሚቀጥል መሰሏቸዋል፡፡ እንደእውነቱ ኦሮሚያም ሲዳማም ከኢትዮጵያ ውጭ አንኳንስ ሁለቱ ውስጥ እርስ በእርስ ሳምንት መቆየት አይችሉም፡፡ ዛሬ ሌሎች ኃላፊነት የሚሰማቸው ጋር አብረው ስለሚኖሩ እንጂ ሕዝብና አገር ለመምራትማ ይሄው የምናየው ነው፡፡

አብይ አህመድና ለማ ምን አልባት ተቸግራችሁ ይሆናል ግን ብዙ ሰው አሁን ላይ ሊሰማችሁ በሚችልበት አደለም ድርጊታችሁ ሁሉ፡፡ እያሴራችሁ ከሆነ የትም አትደርሱ፡፡ እዚህ የደረሰችሁት በኢትዮጵያዊነት እንጂ በኦሮሞነት እንዳልሆነ ታውቁታላችሁ፡፡ ከኦሮሞ ይልቅ ትልቁ ደጋፊያችሁ ሌላው ነበር፡፡ አብዛኛው ኦሮሞ ሊደግፋችሁ የሚችለው ሌላውን መጥላታችሁን ሲያውቅ ነው፡፡ ይሄ አስተሳሰብ ነው ኦሮሚያ ውስጥ አጅግ ተንሰራፍቶ ያለው፡፡ አቋማችሁን ግልጽ አድርጉ፡፡

ሰሞኑን ጌታቸው ረዳ በዋልታ ቀርቦ ሲናገር ሰማሁት፡፡ ብዙ እውነቶች አሉት ሰውዬው፡፡ ለዛሬ ችግር የዳረገን የወያኔ-ኦነግ ጥምር ሴራ እንደሆነ አውቃለሁ፡፡ ጌታቸው ረዳ ሲናገር፡፡ ኦሮሚያ ውስጥ ትልቁን ዝርፊያ ሲፈጽም የነበረው የኦሮሚያ አስተዳደር ነው ሲል፡፡ ከእውነትነቱም በላይ በቁጭት ነው፡፡ እኔም እረዳለሁ፡፡ አሁን በወያኔ የምናመካኝበት ጊዜ አደለም፡፡ በግልጽ እየታየ ያለው የኦሮሞ የወሮበላ ፖለቲካ አስተሳሰብ አገርን እየተገዳደረ መሆኑ ነው፡፡ ለወያኔ ጥሩ አጋጣሚ ሊሆን ይችላል ግን ከኦነግ ወያኔ በብዙ እንደሚሻል አሳምሬ አውቃለሁ፡፡ ኦነግ ማለት ጫካ ውስጥ የነበረው እንደይመስላችሁ፡፡

ሰሞኑን ቴድሮስ ጸጋዬ ብዙ መረጃዎችን ለሕዝብ ይፋ እያደረገ መሆኑን ተከትሎ ብዙዎቻችን ልጁን ስናወግዘው ከነበረው ጊዜ አንጻር በራሳችን እያፈርን ነው፡፡ ቴድሮስ የራሱ ተልዕኮ ሊኖረው ይችላል፡፡ የሚያቀርባቸው መረጃዎች ግን ወሳኝ ናቸው፡፡ ሰሞኑን አብይ የሴቶች ቀንን አስመልክቶ ጀግና የለም ብሎ የተናገረውን የተቸበት እይታውን አድንቄያለሁ፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥማ ጀጋ ሞልቶ ነበር፡፡ ቢያንስ አገሪቱን እስከዚህ ያደረሱ ዛሬም ከወሮበላ ጋር ስልጣንና ሠራዊት ሳይኖራቸው አገራቸውን ለመታደግ ትንቅንቅ የየዙ አሉ፡፡

ቅዱስ አምላክ እግዚአብሔር አገራችንን ይጠብቅ! ለሁላችንም ማስተዋሉን ይስጥ! አሜን!

ሰርፀ ደስታ

የኦሮሞ ፖለቲካ ክሽፈት ምክንያቶች (ሚኪይ አምሃራ)

ኦህዴድ ህወሃትን ገፍትሮ እንደ አዲስ ሃይል ከመጣ በኋላ በመላ ሀገሪቱ ከፍተኛ ተቀባይነት አግኝቶ ነበር፡፡ ነገር ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኦሮሞ ፖለቲካ ከለር ቀይሮ ጭራሽ ለህዝብ ስጋት ሁኗል፡፡ የተወሰኑ ምክንያቶችን ለማየት እንሞክር፡፡

የስነልቦና ችግር
——
የመጀመሪያዉ የኦሮሞ ፖለቲካ ድክመት የስነልቦና ችግር ያለበት መሆኑ ነዉ፡፡ ይህ የስነልቦና ችግር የመላ ኢትዮጵያ ህዝብ ለኦሮሞ ፖለቲከኞች ያሳየዉን ተቀባይነት በመመልከት እንኳን ሊድን አለመቻሉ ነዉ፡፡ ኦሮሞ በቁጥር የበዛ ቢሆንም የኦሮሞ ኢሊቶች ግን ህዝቡን ልክ የአንድ ጎጥ ወይም በመቶወች የሚቆጠር አድርገዉ በመሳል ባህላቸዉ እና ቋንቋቸዉ በአንድ ለሊት ይጠፋል ብሎ የማሰብ ሁኔታ ይታያል፡፡ ሌላኛዉ ስነልቦናዊ ችግሩን የሚያሳየዉ ጥገኛ የመሆን ለምሳሌ ህወሃትን አዳኛቸዉ አድርገዉ የማየት፤ ኦሮሞን የታደገዉ እና የሚታደገዉ ህወሃት ነዉ ብሎ የማሰብ እንጅ እኛ በራሳችን እንደ ህዝብ እንቆማለን ብሎም ለኢትዮጵያ እንሆናለን የሚል አስተሳሰብ አለማዳበር፡፡ ከዚህም በላይ አማራን እንደ threat የማየቱ ነገር ትልቁ ድክመታቸዉ ነዉ፡፡ ይህ የስነልቦናዊ ድክመት ወይም inadequacy feeling ከአዲግራት እስከ ሞያሌ እንዲሁም ከመተማ እስከ ጅቡቲ የሚያክል ሀገር አስተዳድር ተብሎ ህዝቡ ባርኮ የሰጠዉን ነገር ትቶ በሙሉ የኦሮሞ ፖለቲከኛ አንዲት ከተማን ካልተቆጣጠርኩ ብሎ ላይ እና ታች ሲረግጥ ይዉላል፡፡ለዛዉም የማይሳካዉን አጀንዳ፡፡ ይሄም ህዝቡ በእነሱ ላይ እምነት እንዲያጣ ከፍተኛዉን ሚና ተጫዉቷል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስቴሩ ሁለት ልብ
——
ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ በሁለት በኩል ታሪካዊ ሰዉ ለመባል ይፈልጋል፡፡ አንደኛዉ በኦሮሞ በኩል ታሪክ ሰርቶ ማለፍ ፈለገ፡፡ ሁለተኛዉ በኢትዮጵያ በኩል ታሪካዊ መሪ ሁኖ ማለፍ ይፈልጋል፡፡ ነገር ግን ከጥንፈኛ የኦሮሞ ፖለቲከኞች የሚነሱ አንዳንድ አጀንዳወች ባጠቃላይ ከኢትዮጵያ ፕሮጀከት ጋር የሚጋጭ ሆኖ መገኘቱ ጠቅላይ ሚኒስቴሩ አቋም እንዳይኖራቸዉ ብሎም ጥሎ የመሸሽ ሁኔታ ይታይባቸዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ኦሮሞን ላለማስከፋት ፡ ሌላዉን ኢትዮጵያዉን ላለማስከፋት የሚለዉ አካሄዳቸዉ ዋጋ እያስከፈላቸዉ ይገኛል፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ አሁን ላይ እንዲህ ነገሮችን በቸልታ የሚያይ ሳይሆን leadership ይፈልጋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ይሄን አላሳዩም፡፡ መሪ ደግሞ በችግር ጊዜ አለሁ ብሎ የሚወጣ መሆን አለበት፡፡ምናልባትም ከሁለቱ ያጣ አንድ ወደ ሆነ ሁኔታ እያመራ ነዉ ያለዉ፡፡

የአዲስ አበባ አጀንዳ
——
የኦሮሞ ፖለቲከኞች አዲስ አበባን ልክ እንደ አንድ ወረዳ ወይም ዞን በማየት ቀልል አድርጎ የእኛ ነዉ ማለታቸዉ ምን ያህል ህዝቡን እንደናቁት እና እንዳላወቁት ያሳያል፡፡ አዲስ አበባን አጀንዳ ሲያደርጉ እነሱ የሚመስላቸዉ በቀጥታ ከአማራ ጋር የሚደረግ የፖለተካ ትግል ይመስላቸዋል፡፡ የአዲስ አባባ አጀንዳ የኢትዮጵያ ህዝብ አጀንዳ ነዉ፡፡ እንኳን አይደለም ሌለዉ ህዝብ አዲስ አበባ ከተማ ዉስጥ ያለ ኦሮሞ አሁን ጥንፈኞች የሚያቀነቅኑትን ትርክት ያን ያህል የሚቀበለዉ አይደለም፡፡ የኦሮሞ ፖለቲከኞች በቡራዩ አካባቢ የደረሰዉን ችግር እንደቀላል ነገር ሲያዩት ደፍረዉ እንኳን ለማዉገዝም የተቸገሩበት ወቅት ነበር፡፡ ነገር ግን ህዝቡ ይህ ከለዉጡ ጋር ተያይዞ የመጣ እና ወደፊት ሊከሰት የማይችል ነገር ነዉ በሚል ኦህዴድን ወይም የኦሮሞ ፖለተካን ያን ያህል ተጠያቂ አላደረገም፡፡ የኦሮሞ ፖለቲካ ወደ መቃብር የወረደዉ ሰንዳፋ ላይ ከኦሮሞ ዉጭ ያሉትን ቤቶች ሲያፈርሱ፤ ቀጥሎም የአዲስ አበባ ህዝብ እድሜ ልኩን ለቤት እያለ ሲቆጥብ ኖሮ እዝች ኮንዶሚኒየም አንድም ሰዉ ድርሽ አይልም መባሉ ባጠቃላይ የኦረሞን ፖለተካ ትናንት በተስፋ እንዳልተመለከተዉ ዛሬ ህዝቡ በከፍተኛ ጥርጣሬ ብቻ ሳይሆን እያወገዘዉ ይገኛል፡፡ ይህ ክስተት እንዲያዉም የቡራዩን ጭፍጨፋ የተቀነባበረ ለመሆኑ ህዝቡ ማረጋገጫ አገኘ፡፡ ያም ሳያንስ አዲስ አበባ ላይ መዋቅሩን በሙሉ በኦሮሞ መሙላቱ ይህ የመንግስት መዋቅር ደግሞ በቀጥታ ከህዝቡ ጋር በቀን ተቀን የሚገናኝ በመሆኑ የእነ ለማ እና ታከለ ቡድን የሸፍጥ ቡድን ነዉ ብሎ ለመቀበለል ህዝቡ አልተቸገረም፡፡

የስራ አጥ ወጣትን የማጀገን ተልኮ
——–
ስራ የሌለዉን ወጣት ሰልፍ ዉጣ፤ መንገድ ዝጋ የሚል ከዛሬ ሁለት አመት በፊት ስብሃት ነጋ እና ቤተሰቡን ወደ መቀሌ ለመሸኘት የተጠቀሙበትን ስልት የአዲስ አባባን ህዝብ ለማስፈራራት መጠቀማቸዉ ሌላዉ የኦሮሞን ፖለተካ ክፉኛ ያሳጣ ነዉ፡፡ ስብሃት እና 14 ቤተሰቦቹ በሰለፍ ወደ መቀሌ መላክ ተችሎ ይሆናል ነገር ግን የአዲስ አበባን 7 ሚሊየን እና ከዚያ በላይ ህዝብ ቄሮ መጣልህ (በነገራችን ላይ የስራ አጥ ወጣቶች ስብስብ እንጅ አላማ ያለዉ ሀገር ለመገንባት የሚያገለግል ቡድን አይደለም) እያሉ ከበሮ መደለቅ ከመላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ የሚያጣላቸዉ መስሎ አልታያቸዉም፡፡ እነሱ የመሰላቸዉ ከአማራ ልህቅ ጋር በመፋጠጥ የፖለተካ የበላይነት በማግኘት እራስን የማርካት ስራ ነበር ለማድረግ የተፈለገዉ፡፡እነዚህ እና ሌሎች ምክንያቶች ተደማምረዉ የኦሮሞ ፖለተካን ህዝቡ እንደዛ አጨብጭቦ እንዳልተቀበለዉ ዛሬ ላይ የአዲስ አባባ ነዋሪ እንኳን በቲቪ ቀርበዉ እንባ እየተናነቃቸዉ ከከተማዉ ዉጡ ልንባል እንችላለን ሲሉ ማየት ብቻ ለኦሮሞ ፖለተካ ትልቅ ዉድቀት ነዉ፡፡ በነገራችን ላይ ይሄ ስራ አጡን ወጣት ቄሮ ምናምን እያሉ የሚያጀግኑት መጀመሪያ ኦህዴድን ይበላል ቀጥሎ የኦሮሞን ህዝብ ይበላል፡፡

አዴፓ/ብአዴን እና ወታደሩ
——–
አዴፓ መቼም አጋጣሚ አያጣም የመጠቀም ችግር ካልሆነ በቀር፡፡ የአዲስ አበባ ጉዳይ ለአዴፓ/ብአዴን ትልቅ እንጀራ ይዞ ነዉ የመጣዉ፡፡ የኦህዴድ ተቀባይነት መሽመድመድ ሰዉ አሁን ተስፋ ያደረገዉ አዴፓን ነዉ፡፡ አዴፓ/ብአዴን ይሄን አጋጣሚ ተጠቅሞ እራሱን ወደ ወሳኝ የሀገሪቱ ፖለተካ ቡድን ማሳደግ እና ሰፊ ተቀባይነት መገንባት ይችላል፡፡ ይሄን ሲያደርግ የግድ ከኦህዴድ ጋር እሰጣ እገባ እና የቃላት ዉርዋሮሽ ላያስፈልገዉ ይችላል፡፡ ይልቁን የኦሮሞ ፖለቲከኞች የሚገፉትን በህዝቡ ዘንድ ተቀባይነት የሌለዉን የአዲስ አባበን እና ሌሎች አጀንዳወች firm በሆነ እና በማያሻማ መልኩ መልስ መስጠት ብቻ ነዉ የሚጠበቅበት፡፡ ባላንስ ከማድረግ አልፎ የመሪነት ሚናን የመጫወት፤ የመወሰን፤ እና የመደራደር አቅምን ከፍ የማደርግ ስራ ከሰራ ፕሮፋይሉን ማሳደግ ይችላል፡፡ ጥያቄዉ ግን አዴፓ/ብአዴን እየገፋ የሚመጣዉን የኦህዴድ አጀንዳ የመከላከል ስራ ብቻ በመስራት dormant ሁኖ ይቀጥላል ወይስ ከመከላከል አልፎ የመሪነት ሚና እየተጫወተ ህዝቡን ከጎኑ ያሰልፋል የሚለዉ ነዉ? ያም ሆነ ይህ ግን በባለፈዉ ሁለት አመታት ኦህዴድ ያሳየዉን ጥንካሬ አሁን ላይ ገደል የከተተዉ ሲሆን በአንጻሩ ADP ቀስ በቀስ እራሱን የማጠናከር ስራ እየሰራ እና ኦህዴድ በባለፈዉ አንድ አመት እና ከዚያ በላይ የተጫወቱወን ሚና ADP ለመጫወት እድሉ አለዉ እየተዘጋጀም ይመስላል፡፡ ለምሳሌ የድርጅቱን ሴክሬታሪ መቀየሩ፤ የክልሉን ፕሬዝደንት መቀየሩ እንዲሁም አዲስ አባባ ላይ ኢንጅነር እንዳወቅ ጠንከር ያለ አቋም እንዲይዝ ማድረጉ፤ ከዛም አልፎ ደመቀ መኮነን የኦሮሞ ጥንፈኞችን በቀጥታ የሚነካዉ የባህርዳሩ ንግግር ይሄን የሚያሳይ ይሆናል፡፡

ዶ/ር አብይ አሜሪካንም ትናንት ደግሞ ፈረንሳይን ወታደሩን እንዲሁም አጠቃላይ የጸጥታዉን ሁኔታ እንዲያግዙ መጠየቁ ምናልባትም በወታደሩ ዉስጥ የሆነ ነገር እንዳለ መገንዘብ ይቻላል፡፡ በእርግጥ ከወታደር ቤት እየለቀቁ ወደ ክልል ልዩ ሃይል የሚቀላቀለዉ መብዛት ወታዱሩም እንዳልተረጋጋ ያሳያል፡፡ ከዛም አልፎ ወታደሩ በተመደበበት አካባቢ የፖለተካ ወገንተኝነት ማሳየቱ ለምሳሌ በምእራብ ጎንደር አካባቢ የነበረዉ ወታደር ከመንግስት ትዛዝ ዉጭ ፖለተካዊ ሁኖ በመገኘቱ እንዲወጣ ተደርጓል፡፡ ትልቁ የዶ/ር አብይ ችግር ወታደሩ ዉስጥ ታማኝ ቤዝ አለመኖሩ ነዉ፡፡ ህወሃት የራሷ ሰወች ነበሯት በመሆኑም ወታደሩን በሚገባ ተቆጣጥረዉት ነበር፡፡ አሁንላይ ግን ኦሮሞም ሆኖ አብይን ሳይሆን ኦነግን የሚደግፍ ወታደሩ ዉስጥ መኖሩ ጠቅላይ ሚኒስቴሩ እምነት እንዳይጥል አድርጎታል፡፡ ወታደሩን የሚከላከል ናሽናል ጋርድ ማቋቋሙ በራሱ ይሄን ያሳያል፡፡ ከዛም ባለፈ ግን ምናልባትም ምእራብየዉያን በስለላ ተቋማቸዉ አማካኝት ሀገሪቱ collapse ታደርጋለች ብለዉ ያሰሉ ይመስላሉ፡፡ ወታደሩም ይሄን ሊያቆመዉ እንደማየችል ለጠቅላይ ሚኒስቴሩ ሹክ በማለት ይሄን ለመከላከል እናግዝህ ያሉት ይመስላሉ፡፡

ተጠላም ተወደደም የዚህች ሀገር ችግር ከዚህ በኋላ በወታደር ብዛት እና ጥንካሬ የሚፈታ እና የሚቆም አይሆንም፡፡ በዋነኛነት ሊያቆመዉ የሚችለዉ የኢኮኖሚ አድገት ብቻ ይመስለኛል፡፡ 20 እና 30 ሚሊየን በወር ዉስጥ 5 ቀን እንኳን የማየስራ ወጣት ተይዞ ሀገር ይረጋጋል ቢሉኝ የምቀበለዉ አይደለም፡፡

ሚኪይ አምሃራ

ከአርበኞች ግንቦት 7 የተሰጠ መግለጫ፣ ዋልታ ለረገጡ አጥፊ ጽንፈኞች አገራችንን እንዳናስረክብ እንጠንቀቅ!

ለዘላቂው የሚበጀንን ለዘብተኛውን መንገድ ትተን ዋልታ ለረገጡ አጥፊ ጽንፈኞች አገራችንን እንዳናስረክብ እንጠንቀቅ!

ከአርበኞች ግንቦት ሰባት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ፣

Patriotic Ginbot 7 logo

የአርበኞች ግንቦት 7 ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መጋቢት 3 ቀን 2011 ዓም በሀገሪቱ ያለውን የለውጥ ሂደትና እያጋጠሙ ያሉትን ተግዳሮቶች እንዲሁም ድርጅቱ እራሱን አክስሞ ከሌሎች ድርጅቶች ጋር በመዋሀድ በቅርቡ የሚፈጠረውን አዲስ ፓርቲ በተመለከተ እየተሰሩ ያሉትን ሥራዎች ባጠቃላይ ለመገምገም አስቸኳይ ስብሰባ አድርጓል።

ሥራ አስፈጻሚው ብዙውን ጊዜውን ያጠፋው አሁን በሀገሪቱ እየታዩ ያሉትንና በዚህ ከቀጠሉ የለውጡን ሂደት ፍጹም ሊያሰናክሉ ይችላሉ ብሎ ያመናቸውን የተለያዩ ኩነቶች በጥልቀት በመገምገም ነበር። በትግራይና በአማራ ክልል ያለውን አደገኛ ውጥረትና የጦርነት ነጋሪት፤ በአማራ ክልል ውስጥ በቅማንትና በአማራ ማንነት ስም የደረሰውንና እየደረሰ ያለውን የንጹሀን ዜጎች ሕይወት መጥፋትና የብዙ ዜጎቻችንን መፈናቀል፤ በቤንሻንጉል፤ በሶማሊያ ክልል፤ ዘርን መሰረት ባደረገ ግጭት የደረሰው የንጽሀን ዜጎች ሕይወት መጥፋት፣ ንብረት መውደምና መፈናቀል፤ በደቡብ ክልል በተለያዩ ቦታዎች ላይ ከማንነት ጋር በተያያዘ (ለምሳሌ በቅርቡ በጌዲኦ ወገኖቻችን ላይ የደረሰውን መፈናቀል፤ በሀዋሳ ከተማ በተደጋጋሚ የታየው አሳፋሪ የስርአተ አልበኝነት ድርጊትና ይህም በከተማው ነዋሪ መሀከል የተፈጠረው ግጭት…ወዘተ) በየጊዜው የሚታየው የሰብአዊ መብት ረገጣና ግጭት እንዲሁም በሰላማዊ የፖለቲካ ሂደት ላይ በየጊዜው የወረዳና የዞን መስተዳደሮች እየፈጠሩ ያሉት የማሰናከል ስራ፤ በኦሮሚያ የተለያዩ አክራሪ ኃይሎች እየፈጠሩ ያለው አለመረጋጋትና እነኝህ አክራሪ ኃይሎች በሚያነሷቸው አጀንዳዎች በሕዝቡ ሰላምና በክልሉ መረጋጋት ላይ እየፈጠሩ ያለው ችግር፤ እንዲሁም እነኝሁ አክራሪ ኃይሎች አዲስ አበባን በተመለከተ የሚሰጧቸዉ ፍጹም ሀላፊነት የጎደላቸው መግለጫዎች በአዲስ አበባም ሆነ በኦሮሚያ ክልል መስተዳደር ላይ እየፈጠሩ ያለው ጫና፤ በዚህም ጫና በመወጠር፣ በኦሮሚያ ክልል መንግሥት የተሰጠው መግለጫ፤ ይህ መግለጫ በአዲስ አበባ ከተማ ሕዝብ ላይ የፈጠረው የፍርሀት ድባብና ይህንን የፍርሀት ድባብ በመጠቀም በከተማው ውስጥ ያሉ ወጣቶች “ልንወረር ነው” የሚል ጭንቀት ውስጥ መግባት፤ ከዚያም የመገፋት ስሜት የሚፈጥረው እልህ ውስጥና ሲከፋም እራስን የመከላከል የደመነፍስ ስሜት ውስጥ ለማስገባት የሚደረጉ ሀላፊነት የጎደላቸውን እንቅስቃሴዎችና የሶሻል ሚዲያ ጦርነቶች በጥሞና መርምረናል።

እነኝህን የተለያዩ ኩነቶች ለየብቻቸው ለምንና እንዴት ተፈጠሩ ከሚለው ባሻገር እነኝህ ኩነቶች በጋራ የሚሰጡትን የሀገሪቱን ተጨባጭ ስእልና ተደምረው በለውጡ ሂደት ላይ እየፈጠሩ ያለውን ድባብ በተቻለ መጠን ከስሜት በመውጣት ምክንያታዊ በሆነ መንገድ ለመረዳት ሞክረናል። ይህ አጠቃላይ ሁኔታ በቶሎ መፍትሄ ካልተፈለገለትና በዚሁ እንዲቀጥል እድል ከተሰጠው የለውጡን አቅጣጫ ከማስለወጥ ባሻገር በሀገራችን ላይ ሊያመጣ የሚችለውን አደጋ በአንክሮ ተመልክተናል።

ሀገሪቱ የነበረችበት ፍጹም አምባገነናዊ ሥርዓት ከከተታት እጅግ አስቸጋሪ ያለመረጋጋት ሁኔታ ለጊዜውም ቢሆን ወጥታ፤ ከዚህ በፊት እንዳለፍንባቸው ሁሉንም ነገር ስር ነቀል በሆነ አብዮታዊ ሂደት መፍታት የሚያስከትለውን አስከፊ ውጤት በመረዳት፤ ፍጹም አሸናፊና ተሸናፊ በማይኖርበት ሁሉንም ባቀፈ ለዘብተኛ የሪፎርም ሂደት ወደ እውነተኛና ዘላቂ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ መሄድ ይቻላል በሚል በከፍተኛ ተስፋ ከ11 (አሥራ አንድ) ወራት በፊት የለውጥ (ሪፎርም) ሂደት መጀመሩ ይታወቃል። ይህ የለውጥ ሂደት የፈጠረው ተስፋ ግን ቀስ በቀስ ጥግ በያዙ በከረሩና የራስንና የተወሰነ ቡድንን ፍላጎት ብቻ ባስቀደሙ ኃይሎች ግፊትና ጫጫታ ማህበረሰባችንን ወደ ጭንቀት፤ አልፎም ዋናውንና ዘላቂውን የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ሊያሰናክል ወደሚችል አደገኛ አቅጣጫ እየገፉት ይገኛሉ። እንዲህ አይነት ኃይሎች የለውጡን አጀንዳ ከተቆጣጠሩት ከዚህ በፊት ሀገሪቱ አግኝታ የነበረችውን የለውጥ እድሎች እንዳመከንናቸው ይህንንም የለውጥ እድል አምክነን ሀገራችን ልትወጣ ወደማትችለው ቀውስ ልንከታት እንችላለን የሚል ከፍተኛ ስጋት አድሮብናል።

ሥራ አስፈጻሚው ይህን የለውጥ ሂደት ለማደናቀፍ የሚሞክሩ ኃይሎችን ስሜትና ፍላጎት ለመረዳት ሞክሯል። በአንድ በኩል ከዚህ በፊት የመንግሥት ስልጣንን በመያዝ ሲያገኙት የነበረው ጥቅም እንዳይቀርባቸው የሚሞክሩ ወይንም ለውጡ ከዚህ በፊት ለሰሯቸው በደሎች ቂም መወጫ ይሆናል ብለው የሚሰጉና በየክልሉ በተለያየ የስልጣን ደረጃ ላይ የሚገኙ ጸረ ለውጥ ኃይሎች እንዳሉ ተገንዝበናል።

በሌላ በኩል ደግሞ ይህ አገራችን የተያያዘችዉ የለውጥ ሂደት ለሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚሆንና ሁሉንም ኢትዮጵያዊ በእኩልነት የሚያይ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመፍጠር መሆኑን በመዘንጋት የራሳቸውንጠባብ ቡድን ፍላጎት ማሟላትን ዋና አላማቸው አድርገው፤ የመንግሥት ስልጣንን የሁሉም ዜጎች ፍላጎት ማስጠበቂያና መብት ማስከበሪያ መሳሪያ ሳይሆን በቡድን በቡድን ለዘውጌ ባለተራው የሚታደልና በዚህም ሥልጣን ባለ ተራው የፈለገውን የሚያደርግበት አድርጎ በመውሰድ “ተራው የኛ ነው” በማለት “የድርሻቸውን” ለመውሰድ የቋመጡ፤ ወይንም ሥልጣን በነኝህ ቡድኖች መካከል በሚደረግ ድርድር የሚታደል ስለሚሆን “የድርሻችንን” ለማግኘት ራሳችንን ለዚያ ማዘጋጀት አለብን ብለው የሚያስቡ ናቸው።

ሶስተኛው አይነት አደናቃፊ ደግሞ ይህ የተያዘው የለውጥ ሂደት ሳይሆን ያለፉት 28 አመታት ውጤት የሆነና “የለውጥ ኃይል” የሚባለውም ያንን ሥርዓት በለውጥ ስም በብልጣብልጥነት ለማስቀጠል የሚሞክር ስለዚህም ሁኔታው ሲረጋጋለት የቀድሞውን ሥርዓት ምናልባትም በአዲስ ፊቶችና በአዲስ የዘውጌ ኃይል የበላይነት መልሶ የሚያስቀምጥ ስለሆነ የለዉጥ ኃይሉ እንዳይረጋጋ ማድረግ ትክክለኛ የትግል እስትራቴጂ ብቻ ሳይሆን በዚህ ሂደት ሁኔታዎች ወደ በፊቱ ይዞታቸው መመለሳቸው የማይቀር ስለሆነ ለውጥ አለ ብሎ ራስን በየዋህነት ከማሞኘት እራስን ለመጪው ግጭት/ትግል ማዘጋጀት ተገቢ ነው ብሎ የሚያምን ኃይል ነው።

የእነኝህ ሶስት ኃይሎች ባህሪይና ድርጊት አገራችን ዉስጥ እውነተኛ ዴሞክራሲዊ ሥርዓት ለመገንባት የሚደረገዉን ጥረት ለከፍተኛ ፈተና ዳርጎታል። እነዚህ ኃይሎች ለውጡን ለማደናቀፍ የሚፈልጉበት የውስጥ ግፊታቸው የተለያየ ቢሆንም ሶስቱም እርስ በርሳቸው ይመጋገባሉ። በለውጡ ሂደት የሚመጡ ማናቸውንም አይነት እንቅፋቶች በማጦዝ ለውጡን ለመጠምዘዝ ይሞክራሉ። የሀሰት ወሬዎች ይፈበርካሉ ወይንም ግማሽ እውነት ያባዛሉ፤ ሆን ብለው ጠላት ይፈጥራሉ፤ የኔ የሚሉት ቡድን ወይንም ማህበረሰብ “ተጠቅቻለሁ” የሚል የቁጭት ስሜት ውስጥ እንዲገባ የተቻላቸውን ሁሉ ያደርጋሉ በዚህም ሂደት ሊሰማቸው የሚችልን ደመ ሞቃት ወጣት ኃይል በስሜት እየቀሰቀሱ በዙሪያቸው ይሰበስባሉ፤ ግጭት ውስጥ እንዲገባም ይገፋፉታል። አንዳቸው ሌላኛውን በስሜት ሊያነሳሳ የሚችል ዘለፋ ይረጫሉ ወይንም ለማስፈራራት ወይንም አንገት ለማስደፋት ይሞክራሉ። ይህ የመጠፋፋት ሂደት ግን እነሱ እንደሚያስቡትና እንደሚመኙት አንዱን አሸናፊ ሌላውን ተሸናፊ አድርጎ የሚጠናቀቅ አይሆንም። የነኝህ ኃይሎች የጋራ እንቅስቃሴ ለውጡን ለመቀልበስ ቢችል እንኳን የሚገኘው ውጤት ሁሉንም የሚያጠፋና እግረመንገዱንም ሀገሪቱን በሙሉ ጠራርጎ ሲኦል የሚከት መሆኑን ለመገንዘብ ነብይ መሆን እይጠይቅም። በየቦታው በእነኝህ ኃይሎች የሚተነኮሱ ግጭቶች የሚያስከትሉትን የመቶዎች እልቂትና የሚሊዮኖች መፈናቀልን ባይናችን እያየነው ያለው ነውና!!!

በዚህ ሁኔታ እንደ ድርጅታችን ያሉ ለውጡ እውነተኛ አላማው የሆነውን ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት በመፍጠር እንዲቋጭ የሚፈልጉ የፖለቲካ ድርጅቶች፤ ለውጡን የሚደግፉ የመንግሥት ኃይሎች፤ የሲቪክ ማህበራት፤ ምሁራን፤ ግለሰቦች፤ ምን ማድረግ አለባቸው? ከዚህ አኳያ በቅርብ ጊዜ ታሪካችን ካለፉትና ከመከኑት የለውጥ ሙከራዎች ምን እንማራለን? የመጀመሪያውና በጣም ወሳኝ የሆነው የቅርብ ጊዜ ታሪካችን ትምህርት፤ የለውጥ ሂደቱን አጀንዳ እንደነኝህ አይነት በርጋታ ማሰብ የማይችሉ፤ በምክንያታዊ ትንተና ሳይሆን በስሜት የሚጋልቡ ዋልታ ረገጥ አክራሪ ኃይሎች የለውጥ አጀንዳውን ከተቆጣጠሩት ጥፋት እንጂ ምንም በጎ ነገር ይመጣል ብለን መጠበቅ እንደማንችል ነው። በ1966ቱ የለውጥ ጊዜ አጀንዳውን የተቆጣጠሩት አክራሪና ጥራዝ ነጠቅ የሶሻሊስት እምነት ተከታዮች ምንም አይነት ሌላ አማራጭ አናይም፤ “ንጹህ እምነታችንን” የሚበርዝ ማናቸውም ለዘብተኛ አመለካከት ከጠላትም በላይ ጠላት ነው ብለው ፈርጀው በውሀ ቀጠነ እርስ በርሳቸው ሲራኮቱ ደጋፊዎቻቸውን አስበልተው፤ ብዙ እናቶችን ማቅ አስለብሰው፤ ሀገሪቱን ለመከራ ዳርገዋት አለፉ። በነኝህ ጽንፈኛ አመለካከት የተለከፈው ባለጊዜ ወታደራዊ ኃይል ለሁሉም የተለያየ አመለካከት ጉልበትን እንደመፍትሄ ይዞ ሲገፋ አገሪቱን በወጣቶች ሬሳ ሞልቶ፤ ኢኮኖሚውን አድቅቆ፤ በተረኛው ባለጉልበት ተሸንፎ በውርደት ለቀቀ። ከዚህ አመለካከት ያልወጡና ይበልጡንም ማህበረሰቡን በዘር በመከፋፈል የስልጣን ጊዜያቸውን ለራሳቸው ጥቅም ለማዋል የተንገበገቡ ኃይሎች ከየትኛውም በኩል የሚመጣን ለዘብተኛ አካሄድ ገፍተውና ያለኛ ለሀገርና “ለብሄር ብሄረሰቦች” የሚያስብ የለም ብለው የዘረጉት የዝርፊያ ሥርዓት ራሳቸውን ጠልፎ ጥሎ እዚህ አይነት ምስቅልቅል ውስጥ ሀገሪቷን ከተዋት የራሳቸውን “የብሄር ምሽግ” ቆፍረው ተቀምጠዋል። የተለያዩ ጥቅሞችና ፍላጎቶች ያሉበትን የኛን አይነት ድሀ ሀገር በአንድ አይነት አክራሪ አመለካከት ብቻ ወጥረን ማህበረሰቡን በሰላም እናኖራለን ማለት በፍጹም የማይቻል ቅዠት መሆኑን ይኸው የራሳችን ሀገር የቅርብ ጊዜ ታሪክ ትምህርት ሊሆነን ይገባ ነበር።

ይህ ለውጥ እንዲሳካ ከተፈለገ ለዘብተኛ ኃይሎች የለውጡን አጀንዳና ሂደት መቆጣጠር መቻል አለባቸው። ለውጡን የሚደግፉና ግቡን እንዲመታ የሚፈልጉ የፖለቲካ ድርጅቶች ከጊዜያዊ የፖለቲካ ጥቅም ይልቅ ለሀገር መረጋጋትና ለእውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት መመስረት ተሰባስበው መስራት ይጠበቅባቸዋል። የስልጣን ትግሉን ሀገር ከተረጋጋ በኋላ በሚደረገው ምርጫ ይደርሱበታል። በየጊዜው ባክራሪዎች በሚነሳ ጫፍ የረገጠ አጀንዳ ተተብትበው እንዳይወድቁ መጠንቀቅ አለባቸው። የሲቪክ ማህበረሰብ አባላት የሀገራቸውን ጉዳይ ለጥቂት አክራሪዎች አሳልፈው ሳይሰጡ ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ምስረታ ከልባቸው መስራት አለባቸው። ሁኔታው መስመር እየሳተ ሲሄድ ከዳር ቆመው ሊመለከቱ በፍጹም አይቻላቸውም። እነሱንም ያጠፋቸዋልና! ለውጡን ከዳር ለማድረስ ለጊዜው የመንግሥትን ስልጣን የያዙ “የለውጥ ኃይሎች” ባክራሪ ኃይሎች ጩኅት ሳይረበሹና እነሱን ለማማለል በሚል በምንም አይነት ከዋናው የሀገር ሰላም ማስጠበቅና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ሽግግር ሀላፊነታቸው ሳይዘናጉ ለውጡን በሰላማዊ መንገድ ብቻ እንዲሄድ ሁኔታውን ማመቻቸት ይጠበቅባቸዋል። እነኝህ ኃይሎች ከዚህ ሰፊ የጋራ አጀንዳ ውጭ ማንኛውንም የተለየ ቡድን የሚደግፉ ወይንም የራሳቸውን የወደፊት የፖለቲካ እድል እያሰሉ የሚሄዱ ከመሰሉ ማህበረሰቡ በሰፊው የሰጣቸውን አመኔታ ያጡና ሀገሪቱን ለአደጋ እንደሚዳርጓት መገንዘብ ይኖርባቸዋል፤ ይህንንም በተግባር ማሳየት ይጠበቅባቸዋል። የሀገሪቱ ምሁራን በተረጋጋና ምክንያታዊ በሆነ ትንተና የለውጡን ሂደት መዳረሻና ሊገጥሙት የሚችሉትን ተግዳሮቶች ሳይታክቱ ማህበረሰቡን በማስተማር ለውጡ አቅጣጫውን እንዳይስት ከልባቸው መስራት አለባቸው። የሚዲያ አካላትና አርቲስቶቻችን ያለእውነተኛ ዴሞክራሲ ሙያቸው ራሱ ትርጉም የሌለው እንደሆነ አውቀው ለውጡ እዚያ እንዲደርስ መግፋት፤ የአክራሪ አስተሳሰቦችን አደጋ ማጋለጥ ይጠበቅባቸዋል። እንዲህ አይነት የለዘብተኛ ኃይሎች ትብብርና በለውጡ ሂደት የሚኖራቸዉ ቀጥተኛ ተሳትፎ ብቻ ነው ይህንን ለውጡ የተጋረጠበትን አደጋ መከላከልና ሁላችንም የደከምንለትን እውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እውን ሆኖ ማየት የምንችለው።

አርበኞች ግንቦት 7 ይህ ለውጥ የታለመለትን ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መስርቶ እንዲቋጭ ከመፈለግ ባሻገር በአሁኑ ጊዜ ምንም ሌላ አላማ የለውም። የምንሰራው የድርጅት ሥራ ኢላማው ዘላቂ ዴሞክራሲያዊ ሥርአትን በጠንካራ መሰረት ላይ ለማቆምና የሀገሪቷን ስትራቴጂካዊ ጥቅም ለማስጠበቅ ያለመ ነው። እውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት በጠንካራ መሰረት ላይ መቆም የሚችለው ሁሉንም ዜጎች በእኩልነት በሚያይ፤ ዜግነትን መሰረት ባደረገ ፖለቲካ ነው ብለን ከልባችን እናምናለን። ይህንንም ለሁሉም ህዝባችን ያለምንም መታከት እናስተምራለን። ይህን እምነታችንን ግን በማንም ላይ በጉልበት ለመጫን አንሻም። በሰላማዊ መንገድ በሚደረግ የሀሳብ ትግልና፤ በመጨረሻም በነጻና ፍትሀዊ ምርጫ ማህበረሰቡ የወሰነውን ውሳኔ ለመቀበል ምንም ችግር የለብንም። ይህ እንዲሆን በመጀመሪያ ሰላም እንዲሰፍን ይገባል። ያለሰላም ፖለቲካ የለም። ያለ ሰላም ዴሞክራሲ የለም። ያለሰላምና እውነተኛ ዴሞክራሲ ደግሞ ሀገር አይኖርም።

ሰላምና እውነተኛ ዴሞክራሲ ብሎም ሀገር እንዲኖር፣ ከወረዳ ጀምሮ እስከ ከፍተኛው የመንግስት የሥልጣን እርከኖች ድረስ ያሉት የሃላፊነት ቦታዎች በራሱ በሕዝቡ በተመረጡ ሃላፊዎች መያዝ ይኖርባቸዋል ብሎ አርበኞች ግንቦት 7 ከልብ ያምናል። ክልሎች በክልሉ ሕዝብ በተመረጡ መሪዎች፤ ከተሞች በራሱ በከተማው ሕዝብ በተመረጡ ከንቲባዎች (የፌደራሉ ከተማ የሆነችውን አዲስ አበባን ጨምሮ)፤ ወረዳዎች በራሱ በወረዳው ሕዝብ በተመረጡ አስተዳዳሪዎች፤ ቀበሌዎችም የቀበሌውን ጉዳይ በተመለከተ የሚመሯቸውን ሰዎች እራሳቸው የቀበሌው ነዋሪዎች የሚመርጡበት ሁኔታ ሲኖር ብቻ ነው እውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ፌደራሊዝም ሊኖር የሚችለው ብለን እናምናለን። ከዚህም ባሻገር የፌደራል መንግሥቱ ባጠቃላይ የሀገሩ ሕዝብ መመረጥ ያለበት ብቻ ሳይሆን በሕግ የተቀመጠለትን ሥልጣን በብቃት መተግበር የሚችል ጠንካራ ፌደራል መንግሥት መሆን አለበት ብለን እናምናለን። ድርጅታችን ይህን እምነቱን ተግባራዊ ለማድረግ በየወረዳው ሕዝብን የማሰባሰብ የማሰልጠንና የማደራጀት ሥራ ላይ ያለውን አቅም በሙሉ በመጠቀም እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። የዚህ እንቅስቃሴ ሂደት ሌሎች መሰል ሀገራዊ ድርጅቶችን አካቶ በሚቀጥሉት ጥቂት ሳምንታት ከወረዳ ጀመሮ በሚዋቀር በአዲስ ሀገራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ምስረታ የሚጠናቀቅ ይሆናል።

በመጨረሻም የተለያዩ፣ የሀገርና የሕዝብ፣ ደህንነት፣ ፍላጎትና ጥቅም፣ ግድ የማይሰጣቸው ቡድኖች፣ በየግዜው የሚቀስቅሱት ግጭትና አለመረጋጋት ከቁጥጥር ውጭ ቢወጣና የተጀመረውን የሀገር ማዳን ለውጥ መስመሩን ቢስት፣ የሚፈጠረው እጅግ አደገኛ ሀገራዊ ሁኔታ ማንም አሸናፊና ተሸናፊ የማይሆንበት ምድራዊ ሲኦል እንደሚፈጥር አርበኞች ግንቦት 7 ቅንጣት ያህል ጥርጥር የለውም። ስለዚህ ማናቸውም የህብረተሰብ ክፍል፣ ድርጅት፣ ቡድንና ግለሰብ፣ የጽንፈኛ ቡድኖችና ግለሰቦች ለሚፈጥሩት ጊዚያዊ የግጭት ስሜት ሰለባ እንዳይሆንና እንዲያውም በሚቻለው ሁሉ የለውጡን ሂደት በመደገፍ፣ ኢትዮጵያን እውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ሀገር ለማድረግ በሚደረገው ጥረት በሚቻለው ሁሉ እንዲሳተፍ ፣ አርበኞች ግንቦት 7 ወገናዊ ጥሪውን ያስተላልፋል።

ኢትዮጵያ ለዘላላም ትኑር፣
አርበኞች ግንቦት 7፣ የአንድነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ፣
መጋቢት 2011 ዓም

የስቃይ ገፈት የሚጋተው የጌዲኦ ተፈናቃይ ህዝብ (መስከረም አበራ)

መስከረም አበራ

Displaced Ethiopia's Gedio people.

ቋንቋን መሰረት ያደረገው የጎሳ ፌደራሊዝም አስከፊ ገፆቹ ብዙ ናቸው፡፡በመሰረታዊነት የሰውን ልጅ በጎሳው ከልሎ ማስተዳደር ከሰውልጆች ተፈጥሯዊ መስተጋብር የማይገጥም አካሄድ ነው፡፡የሰው ልጅ መሬት ጠበበኝ ብሎ ሽቅብ ወደ ጠፈር በሚምዘገዘግበት በዚህ የሰለጠነ ዘመን ቋንቋን መሰረት ያደረገ ክልል ከልሎ አንዱን የክልል ባለቤት ሌላውን ባይተዋር የሚያደርግ አስተዳደር መዘርጋት ከዘመን መጣላት ነው፡፡አሁን ዓለማችን ያለችበት ሁለንተናዊ እድገት እትብት በተቀበረበት አካባቢ ብቻ የሚያስቀምጥ ያህል ቀላል አይደለም፡፡የእኛ ሃገር ፖለቲካ ደግሞ እትብቱ የተቀበረበትን መሬት  እያየ እዛው ላልተቀመጠ ሰው የመከራ ገፈት የሚግት ነው፡፡ ዕትብቱ በተቀበረበት ሃገር እየኖረ ያለውም ቢሆን የወላጆቹ፣የሰባት ጉልበቱ እትብት የተቀበረበት ቦታ ሌላ ከሆነ የጎሳ ፖለቲካ ወለድ ስቃዩ አያልፈውም፡፡

እንዲህ ያለው ለወሬ የማይመች ህሙም ፖለቲካዊ መስተጋብር አጀማመሩ ጨቋኝ እየተባለ ባልበላው የሚብጠለጠለውን የአማራ ህዝብ ከሃገሪቱ ዳርቻ ለማሳደድ ተብሎ የተቀመረ የህወሃት፣የሻዕብያ እና የኦነግ ቀመር ነበር፡፡ይህ ደማቅ ውሸት እውነት ተደርገ በመለስ ዜናዊ እና አሽከሮቹ አፍ ሲነዛ ስለኖረ ተቀባይነት አግኝቶ ኖሯል፡፡ የጎሳ ፖለቲካው እና ፌደራሊዝሙ ሲፈጠር የታቀደለትን አማራውን እያደኑ የማሳደዱ ስራ ለረዥም ዘመን በተሳካ ሁኔታ ሲሰራበት ቆይቷል፡፡ሆኖም እሳትን ሃላፊነት በማይሰማው ሁኔታ ካያያዙት በኋላ አካሄዱን የሚወስነው ራሱ እሳቱ ነውና ከባለቤቱ ቁጥጥር ውጭ ሆኖ ያገኘውን ሊበላ ይችላል፡፡የሃገራችን የዘር ፖለቲካም እንዲያ ነው!አማራውን ለመብላት ተብሎ ነደደ ውሎ አድሮ ግን ‘አማራው በአንድ ላይ ሲጨቁናቸው የኖሩ ናቸው’ የተባሉ ዘሮችምን እርስ በርስ እያናከሰ ይገኛል፡፡የጌዲኦ እና የጉጅ ህዝቦች ለሌላ የነደደው የጎሳ ፖለቲካ እሳት እየለበለባቸው ያሉ ህዝቦች ናቸው፡፡

የጌዲኦ እና የጉጅ ህዝቦች ለረዥም ዘመን አብረው የኖሩ፣ እኩል በእኩል በሆነ ሁኔታ ኦሮምኛም ኤዲኦኛም የሚናገሩ ህዝቦች ናቸው፡፡ሁለቱን ህዝቦች በሚናገሩት ቋንቋ “ጉዲኦ” እና “ጉጅ” ብሎ መለየት አስቸጋሪ እንደሆነ በህዝቦቹ ላይ ጥናት ያደረጉ ምሁራን ፅፈዋል፡፡በተለይ በጉጅ እና በጌዲኦ ድንበር አካባቢ “ጌዲኦ” በሚል የሚጠራ ሰው “የጉጅ ኦሮሞ” ከሚባለው ሰው ባልተናነሰ ኦሮምኛን የሚያቀላጥፍ ነው፤ጉጅውም እንደዛው ጌዲኦኛን አቀላጥፎ ያወራል፡፡በዚህ ምክንያት ህዝቦቹን ለይቶ በአንድ ክልል መከለል አስቸጋሪ ነው፡፡ በታሪክም ቢሆን ጦር አዋቂዎች እና ሃይለኞች ተደርው የሚወሰዱት የጉጅ ኦሮሞዎች እንደነሱው ኦሮሞ ከሆኑት ቦረናዎች፣አርሲዎች እና  ሲዳማዎች ጋር በተለያየ ምክንያት የመጋጨት ታሪክ ያላቸው ሲሆኑ ከጌዲኦዎች ጋር ግን የስምምነት እና የትብብር ታሪክ እንዳላቸው ነው ጥናቶች የሚያሳዩት፡፡

Displaced Ethiopia's Gedio people.
Displaced Ethiopia's Gedio people.

የጦር አዋቂነታቸው የሚነገርላቸው ጉጅዎች ከጌዲኦ ጋር የስምምነት ታሪክ ሊኖራቸው የቻለው አንድም ጌዲኦዎች እህል አምራች፣ጉጅዎች ደግሞ ከብት አርቢ በመሆናቸው በምርት ልውውጥ ተደጋግፈው የሚኖሩ በመሆኑ፣ሁለትም ጌዲኦዎች እምብዛም የጦረኝነት ባህል ስለሌላቸው በግብርና ላይ የሚያተኩሩ ህዝቦች በመሆናቸው ጌዲኦዎችን መውጋት በጉጅዎች ዘንድ ተቀባይነት ያለው ተግባር ስላልሆነ፣ ሶስትም ‘በጌዲኦ እና በጉጅ ቀደምት አባቶች ዘንድ በሁለቱ ህዝቦች መሃል መጋደል እንዳይኖር  የተደረገ መሃላ አለ፤ይህን መተላለፍ እርግማን ያመጣል’ ተብሎ የሚታመን እምነት ስላለ እንደሆነ አሰበ ረጋሳ “Ethnicity and Inter-ethnic Relations: the ‘Ethiopian Experiment’ and the case of the Guji and Gedeo” በሚል ርዕስ የሰራው ጥናት ያመለክታል፡፡እነዚህን ኢኮኖሚያዊ እና ባህላዊ እሳቤዎች ተላልፎ አንዳንዴ በሁለቱ ህዝቦች መሃከል ግጭት ቢከሰት እንኳን “ጎንዶሮ” በሚባው በሁለቱም ህዝቦች እኩል በሚሰራበት የይቅርታ እና እርቅ ባህል አማካይነት ሰላም ሲወርድ እንደኖረ ይሄው ጥናት ያስረዳል፡፡

እንደዚህ በሰላም የኖሩ ህዝቦች ዛሬ ለመጋደል እና ለመፈናቀል/ማፈናቀል ያበቃቸው ምንድን ነው? የሚለው ወሳኝ ጥያቄ ነው፡፡የአሁኑ ቋንቋን መሰረት ያደረገው ፌደራሊዝም ስራ ላይ ከመዋሉ በፊት የጌዲኦ እና ጉጅ ህዝቦች የሲዳሞ ክፍለሃገር በሚባለው አከላለል ውስጥ አብረው ተከልለው ይተዳደሩ ነበር፡፡ሆኖም የጎሳ ፌደራሊዝም ስራ ላይ ሲውል ጉጅዎቹ ወደ ኦሮሚያ ክልል፣ጌዲኦዎቹ ደግሞ በደቡብ ክልል ውስጥ እንዲተዳደሩ ሆነ፡፡እነዚህ ህዝቦች ግን እንደማንኛውም አብሮ እንደኖረ ህዝብ የተቀላቀሉ ስለሆኑ በጌዲኦ እና ጉጅ መሃከል መስመር አውጥቶ፣ በተለያዩ ክልሎች ውስጥ ማካለሉ እጅግ አስቸጋሪ ነገር ፈጠረ፡፡በዚህ ምክንያት ብዙ ጉጅዎች በደቡብ ክልል ወደሚገኘው  ወደ ጌዲኦ ዞን ፣በርካታ ጌዲኦዎች ደግሞ በኦሮሚያ ክልል ወደሚገኘው ምዕራብ ጉጅ ዞን እንዲካለሉ ሆነ፡፡

Displaced Ethiopia's Gedio people.
Displaced Ethiopia's Gedio people.

በዚህ አከላለል ጉጅዎች በተለይ ‘በርካታ መሬቶች ወደ ጌዲኦ ተካለውብናልና ራሳችንን በራሳችን የማስተዳደር መብታችንን ተነፍገናል፤ያለ አግባብ በጌዲኦ ዞን ስር እንድንተዳደር በመደረጋችን ማንነታችን ተጨፍልቋል፣የትምህርት፣የስራ እና የስልጣን እድል ከጌዲኦዎች እኩል እያገኘን አይደለም’ የሚል ቅሬታ ለመንግስት ያቀርባሉ፡፡ጌዲኦዎች በበኩላቸው በርካታ መሬታችን ያለ አግባብ ወደ ኦሮሚያ ክልል ጉጅ ዞን ተካሏል፣እስከ ቡሌ ሆራ(ሃገረ ማርያም) ድረስ ያለው መሬት ይባናል የሚል ጥያቄ ያነሳሉ፡፡ ይሄው ንትርክ ወደ ግጭት አድጎ በ1987 ዓም ላይ በሁለቱ ብሄረሰቦች መሃከል2000-3000 ሰዎችን ህይወት የቀጠፈ ትልቅ መጋደል አስከትሎ ነበር ይላል ከላይ የተጠቀሰው የአሰበ ረጋሳ ጥናት፡፡

ይህን መጋደል ለማስቆም በኦህዴድ የሚመራው ኦሮሚያ ክልል እና በደኢህዴን የሚመራው ደቡብ ክልል ከፌደራሉ መንግስት ጋር በመተባበር በአከራካሪዎቹ ስድስት ወረዳዎች ላይ ህዝበ-ውሳኔ እንዲደረግ ሆነ፡፡በህዝበ ውሳኔው መሰረት አራት ወረዳዎች እዛው ጌዲኦ ዞን ውስጥ እንዲረጉ ሲሆን ቀሪዎቹ ሁለቱ ወረዳዎች ወደ ኦሮሚያ ክልል ጉጅ ዞን እንዲካለሉ ተደረገ፡፡ ሆኖም መፍትሄ ያመጣል የተባለው ሪፈረንደም ጌዲኦዎቹንም ሆነ ጉጅዎቹን ሊያስደስት የሚችል አልሆነም፡፡’የፌደራሉ መንግስት በብሄር ፌደራሊዝሙ ብዙ ግዛታችንን ለጌዲኦዎች ሰጥቶብናል’ ብለው የሚያስቡት ጉጅዎቹ ‘ሪፈረንደሙን የመራው መንግስት ለጌዲኦዎች ያደላል’ ብለው ያስባሉ፡፡በዚህ ላይ ከስድስቱ አራቱ ተመልሰው ወደ ጌዲኦ  ዞን መካለላቸው ቅሬታቸውን አባብሶታል፡፡ጌዲኦዎች በበኩላቸው ‘በሪፈረንደሙ ለጉጅዎች የተሰጠው ሁለት ወረዳ መሬት ያለአግባብ የሄደ ለእኛ የሚገባ ነው’ ብለው ያስባሉ፡፡

በዚህምክንያት ሪፈረንደሙ የታሰበውን ሰላም ሳያመጣ ቀረ፡፡አካባቢውም በሁለቱ ብሄረሰቦች በሚነሳ ግጭት ውጥረት እንዲቀጥል ሆነ፡፡ውጥረቱ ተባብሶ በ1990 የበርካታ ሰዎችን ህይወት የቀጠፈ ላይ ሌላ ግጭት ተቀሰቀሰ፤የበርካታ ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡የፌደራል መንግስቱ ተከታታይ ስብሰባዎችን እና ባህላዊ የእርቅ ስነ-ስርዓቶችን ቢያከናውንም በሁለቱ ህዝቦች መካከል የቀደመ ሰላማቸውን መመለስ አልተቻለም፡፡ከሪፈረንደም እስከ ጎንዶሮ ድረስ የሚያደርገው ሙከራ ሁሉ ያልተሳካለት ህወሃት መራሹ ፌደራል መንግስት መላ ሲጠፋው እንደሚያደርገው የጉጅዎች እንቅስቃሴ በኦነግ የሚደገፍ ነው እያለ ሰዎችን ማሰር ጀመረ፡፡እስሩ በጉጅ ኦሮሞዎች ዘንድ የሃይማኖት መሪ ተደርጎ የሚታመንበትን አባ ቃሉ እስከማሰር ደረሰ፡፡የታሰሩት አባ ቃሉ እስርቤት ህይወታቸው ማለፉ የጉጅ ኦሮሞዎችን ቁጣ አባባሰው፡፡መንግስትም በመላ-ቢስ እስሩ እና የጉልበት አካሄዱ ቀጠለበ፡፡

የመንግስት ጉልበት የበረታባቸው ጉጅዎች መንግስት የሚያንገላታቸው ለጌዲኦዎች አግዞ እንደሆነ መገንዘብ ጀመሩ፡፡መንግስትም የጉጅዎቹን እንቅስቃሴ ከኦነግ ጋር አያይዞ በጭካኔው ቀጠለበት፡፡ይህ የመንግስት ብስልት የጎደለው አካሄድ በጌዲኦ እና ጉጅ ታጋዮች መካከል ያለውን መቃቃር እያባባሰው ሄደ፡፡በዚህ መሃከል በሁለቱም ዞኖች ውስጥ የሚኖረው የጉዲኦም ሆነ የጉጅ ህዝብ እንግልት ውስጥ ወደቀ፡፡በተለይ በጉጅ ዞን የሚኖሩ ጌዲኦዎች ህይወታቸውን አደጋ ላይ በሚጥል መጥፎ ሁኔታ ውስጥ መኖር ጀመሩ፡፡

Displaced Ethiopia's Gedio people.

ነገሮችን ከማሻሻል ይልቅ በማባሱ የጉልበተኝነት አካሄድ ሲሄድ የኖረው ህወሃት ከማዕከላዊ ስልጣ ወርዶ ኦዴፓ ስልጣን ሲይዝ፣ኦነግ ደግሞ በአካባቢው መንቀሳቀስ ሲጀምር በጉጅዎቹ በኩል እንቅስቃሴው እየተፋፋመ ሄደ፡፡ኦነግ በአካባቢው የሚንቀሳቀስ መሆኑ ደግሞ በጉጅ ዞን ለሚኖሩ ጌዲኦዎች እጅግ አደገኛ ሁኔታ ፈጠረ፡፡አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ወደ ስምንት መቶ ሽህ የሚደርሱ ጌዲኦዎች ጉጅ ዞንን ለቀው ወደጌዲኦ ዞን እንዲፈናቀሉ ሆነ፡፡የተፈናቃዩ ብዛት የረድኤት ድርጅቶችን ጉልበት ፈተነ፡፡ህፃናት በክረምት ከቤታቸው ወጥተው በአሳዛኝ ሁኔታ ሜዳ ላይ ፈሰሱ፣ከትምህርት ገበታቸው ተፈናቀሉ፣ሴቶች፣አዛውንቶች በማያውቁት ሰበብ ከቤታቸው ወጥተው ሜዳላይ ወደቁ፡፡የዚህ ሁሉ ምክንያቱ ባለፈው የህዝብ ቆጠራ መሰረት በምዕራብ ጉጅ ዞን 14% የሚሆነው ሰው ጌዲኦ ሆኖ በመገኘቱ ውለው አድረው ከተባዙ መሬቱ የእኛ ነው የሚል ጥያቄ ያመጣሉ የሚል እሳቤ ከጉጅዎቹ ዘንድ በመነሳቱ ነው፡፡ይህ ከጎሳ ፌደራሊዝሙ ያገኘነው አስከፊ ቱርፋት ነው ንፁሃንን ከቤታቸው አውጥቶ እያንገላታ ያለው!

መፈናቀሉ ከአንድ አመት በፊት ሲጀመር ስምንት መቶ ሽህ የሚደርሰው የጌዲኦ ተፈናቃዮች ቁጥር አሁን ወደ 1.4 ሚሊዮን እየተጠጋ እንደሆነ “irinnews.org” የተባለው ድረ-ገፅ “Etheiopia’s Neglected Crisis: No easy way home for doubly displaced Gedeos” በሚል ርዕስ ከቀናት በፊት ባወጣው ፅሁፍ  አስነብቧል፡፡ ይህ ቁጥር ሃገራችንን በሃገር ውስጥ ተፈናቃዮች ብዛት ከዓለም አንደኛ ያደርጋታል፡፡የድረ-ገፁ ዘገባ ተፈናቃዮቹ ከአንድ አመት ለዘለለ ጊዜ ከቤታቸው ወጥተው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሃገር ውስጥ ተፈናቃዮች ሊያዙበት ይገባል ብሎ ካወጣው መስፈርት እጅግ በወረደ ሁኔታ እየኖሩ፣ህፃናት በምግብ እጥረት እና በሽታ እየተሰቃዩ እንደሆነ ያትታል፡፡

እንደ ዘገባው አራት በአራት በሆነች ድንኳ ውስጥ የአራት አባወራ ወደ ሰላሳ የሚጠጉ በተሰቦች ተፋፍገው ይኖራሉ፡፡በዚህ ላይ የረድኤት ድርጅቶች ገብተው እነዚህን ወገኖች እንዳይታደጉ መንግስት በምዕራብ ጉጅ ዞን አድርጎ ወደ ተፈናቃዮቹ የሚወስደውን መንገድ ጠርቅሞ ዘግቷል፡፡በዚህ ምክንያት ህፃናት፣አረጋዊያን ሴቶች እና ሌሎች ተፈናቃዮች ኮሌራን በመሰለ ተላላፊ በሽታዎች፣በምግብ እጥረት፣በውሃ እጦት እየተሰቃዩ እና ማንም ሳያውቅላቸው እያለቁ እንደሆነ ጋዜጠኛው ያነጋጋራቸው የዓለም አቀፍ ረድኤት ድርጅት ሰራተኞች ተናግረዋል፡፡መንግስት ወደ ተፈናቃዮቹ የሚወስደውን መንገድ ለረድኤት ድርጅቶች የዘጋው ተፈናቃዮቹን ወደ ነበሩበት ወደ ምዕራብ ጉጅ ዞን እንዲመለሱ ለማስገደድ ነው ይላሉ የረድኤት ሰራተኞቹ፡፡ተፈናቃዮቹ ደግሞ ከአንድም አራት ጊዜ በኦሮሚያ ክልል ጉጅ ዞን ወደሚገኘው ቀያቸው ለመመለስ ሞክረው በታጣቂ ቡድኖች እና ዘረኛ ጎረምሶች በደረሰባቸው ህይወትን አደጋላይ የሚጥል ማስፈራራት እና ዘረፋ ምክንያት ወደ ጌዲኦ ዞን መልሰው መላልሰው ለመፍለስ ተገደዋል፡፡

ጋዜጠኛው ያነጋገራቸው ተፈናቃዮች እንደሚሉት የመንግስትን ቃል አምነው እና አክብረው ተወልደው አድገው ወደኖሩበት የጉጅ ዞን ቀያቸው ሲመለሱ በተመለሱበት ቀን ማግስት ማታ በቡድን ሆነው የሚመጡ ታጣቂዎች እና ስለታማ ነገር የያዙ ጎረምሶች ይዘውት የመጡትን ነገር ሁሉ ተዘርፈው፣ቀየውን ለቀው እንዲሄዱ ጥብቅ ማስፈራሪያ እንደተነገራቸው ይገልፃሉ፡፡በዚህ ሁኔታ ከአንድም አራት ጊዜ ስለተመላለሱ ጉጅ ዞን መሄድ እንደሚያፈራቸው እና እንደማይፈልጉ አበክረው ገልፀዋል፡፡ ሆኖም መንግስት የተፈናቃዮቹን ደህንነት በአስተማማኝ ደረጃ  ባላስጠበቀበት ሁኔታም ሰዎቹ ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ይፈልጋል ብቻ ሳይሆን ያስገድዳል፡፡መንግስት የተፈናቃዮቹን መመለስ የሚፈልገው በቅርቡ አደርገዋለሁ ለሚለው ህዝብ ቆጠራ በቀያቸው እንዲገኙ ነው፡፡በተጨማሪም “ተፈናቃዮቹ አሁን ተመልሰው ሚያመርቱትን መሬት ለመጭው ክረምት ለእርሻ ካላዘጋጁ በሚቀጥለው አመት ተረጅ እንዳይሆኑ ስጋት ስላለን ነው” ይላሉ የአደጋ መከላከል ኮሚሽነሩ አቶ ምትኩ ካሳ ለድረ-ገፁ በሰጡት መልስ፡፡በሞት ሰቀቀን እና በከፍተኛ የስነልቦና አለመረጋጋት ላይ የቆየ ህዝብ እንዴት አምራች ሊሆን እንደሚችል ተናጋሪው ባለስልጣ ብቻ ናቸው የሚያውቁት፡፡

ይህ የመንግስት ምክንያት እጅግ አሳዛኝም ሰብዓዊነት የጎደለውም ነው፡፡በመጀመሪያ ነገር እነዚህ ተፈናቃዮች አንድ አመት ሙሉ ሲንገላቱ እንደ መንግስት ስቃያቸውን በሚመጥን ሁኔታ ትኩረት አልተሰጣቸውም፡፡ አንድ የተደረገ ነገር ቢኖር የሰላም ሚኒስትር የተባሉት ወ/ሮ ሙፈሪያት ከሚል አምና ተፈናቃዮቹን መጎብኘታቸው ነበር፡፡የሚኒስትሯ ጉብኝት “ከተፈናቃዮቹ ውስጥ 90%ን ወደቀያቸው መልሰን እያቋቋምን ነው” የሚል የውሸት ሪፖርት ከማዥጎድጎድ ውጭ ያመጣው ነገር የለም፡፡እንዴውም ወ/ሮ ሙፈሪያት ራሳቸው ተፈናቃዮቹ ወደቀያቸው እስካልተመለሱ ድረስ የረድዔት እርዳታ እንዳይደርሳቸው መንገድ መዘጋት እንዳለበት ማዘዛቸውን ነው ከላይ የተጠቀሰው ድረ-ገፅ ያስነበበው፡፡

ተፈናቃዮች ወደቀያቸው ከተመለሱ ህይወታቸው አደጋ ላይ መሆኑን ከአንድም ሶስት አራት ጊዜ በተግባር ተመላሰው አረጋግጠው እየተናገሩ በግድ ካልተመለሱ የረድኤት አቅርቦት እንዳይደረግላቸው የማዘዝ ጭካኔ  መንግስትነትን ቀርቶ ተራ ሰውነትን አይመጥንም፡፡ችግር ባይሆንበት ማንም ከቤቱ ወጥቶ ሜዳላይ የመሰጣት እና በረሃብ የማለቅ ፍላጎት የለውም፡፡ ሰዎቹ የኖሩበትን መንደር የፈሩት ያዩትን አይተው ነው፡፡በጉጅ ዞን ኦነግ ከነጠመንጃው እንደሚንጎራደድ እየታወቀ፣መንግስት ራሱ በቴሌቭዥኑ “ይህን ያህል ወረዳ በኦነግ ቁጥጥር ስር ነው” እያለ እየተናገረ ምስኪን ሰዎችን ወደሞት ሂዱ ካልሆነ እዚህ በረሃብ ሌላ ሞት ይጠብቃችኋል ማለት በጣም አሳዛኝ አረመኔነት ነው፡፡

የሰው ልጅ ተፈናቃይም ቢሆን ክብር ያለው፣በምርጫው መኖር ያለበት ፍጡር ነው፡፡የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው ሲመለሱ ህይወታቸውን አደጋ ላይ የሚጥል ስጋት ሳይኖራቸው፣በግድ ሳይሆን ወደው፣መመለሳቸው ሌላ መፈናቀል እንደማያስከትል ተረጋግጦ፣ሰብዓዊ ክብራቸውን ባስጠበቀ ሁኔታ መሆን እንዳለበት ደነግጋል፡፡ይህ ቀርቶ ባዕዳን ረጅዎች ለሰዎቹ የእለት ጉርስ  ሚደርስበትን ነገር ሲጠይቁ የራስን ወገን በረሃብ ለመግደል መጨከን በጣም አሳዛኝ ነገር ነው፡፡

ከመንግስት በተጨማሪ የኢትዮጵያ ህዝብም ከሱማሌ ክልል ለተፈናቀሉ፣ከአዲስ አበባ ዙሪያ ለሚፈናቀሉ ወገኖቹ የሚያሳየውን የወገንተኝነት መቆርቆር በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩት የጌዲኦ ተፈናቃዮችም ማሳየት አለበት፡፡ ችግራቸውን በተለያዩ ሚዲያዎች ማንሳት አለበት፤ በፍጥነት ወደተረጋጋ ኑሯቸው የሚመለሱበት መንገድም የሚገኘው ለነገሩ ትኩረት ሰጥቶ በመነጋገር ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች በየማህበራዊ ድረ-ገፁ ብቅ እያለ ወደቀ ሲባል ተሰበረ የሚል ዘረኛ አክቲቪስት ስለሌላቸው ሰማይ ሙሉ ችግራቸው እንደቀላል ነገር መቆጠር የለበትም፡፡እነዚህ ተፈናቃዮች ለሁላችንም ወገን የሆኑ ኢትዮጵያዊያን ናቸውና ሰብዓዊነት የሚሰማው ኢትዮጵያዊ ሁሉ ብሶታቸውን ሊያስተጋባላቸው ያስፈልጋል፡፡

ለኢትዮጲያ ና ለህዝቧ የሚበጀው ነገር – (ክፍል ፫) ከሙሉቀን ገበየው

በከፍል ፪ ጽሑፌ ከ27  አመታት የአፈናና አስከፊ አገዛዝ ቦኋላ የሽግግሩን ሂደቱን በመንግስትነት የሚመሩት ሙሉ በሙሉ ካልፈርሰው አገዛዝ የተወከሉ “የለውጥ ፈላጊ” መሪዎችና በተፈጠርው ለውጥ የፖለቲካ አጀንዳቸውን ለማራመድ በተሰባሰቡ ወገኖች በኩል የተዘነጋውን ወሳኝ የሽግግር ወቅት ስራና ወደፊት ሊያጤኑት የሚገባቸውን መሰርታዊ የሃገርችንና ህዝብ ችግር መፍቻ መሳሪያዎችን በማብራራት ነበር። በተለይ  የይቅርታ እርቅ ና የህዝብ መግባባት መድርኮችን ባስቸኳይ አስፍላጊንትና የከፋፍልህ ግዛው ፖሊስን ማዳክምና ማጥፋት ወሳኝ ተግባርቶች መሆናቸውን፤ በተለይም ሊከትል የሚችለውን ሌሎች የለወጥ ስራ እንዴት እንድሚያቀለው በመግለጽ ነበር። የሽግግሩ መንግስት መሪዎችን እርጋታንና ማስተዋልን ትኩርትን እንዲያካብቱ በመምከር በተለይም ፋይዳ ያለው ፍኖት- ካርታ በግልጽ በመንደፍ የለውጡን ምህዋር  ማሳየት እንዳለባቸው ተገልጿል።

በክፍል ፪ መሰርታዊ አገራዊ መግባባት ሳይደርግ ለምርጫው መቻኮል ትርፉ ኪሳራ መሆኑን፤ እንዲሁም ወያኔ ላገዛዙ ያመቸው ዘንድ በላያችን ላይ የተከለው ህዝብ ያልመከረበትን ህገ- መንግስት ወደፊት የጥፋት ምንጭ ስለሚሆንብን መምርመር እንዳለብን ፣ካስፈለገም አዲስ ማርቀቅ ወይም ማሻሻል እንደሚያስፈልግ፤ በጎሳ ላይ የተመሰርተ ፖለቲካ ወይም ስርአት አግላይና የሚለያይ መሆኑን አጽኖ በመስጠት በጎሳ መድራጅትን ጎጂ መሆኑን፤ ህዝቡን አስተምረን በህግ ማስቀርትና በዜግነት የሰው መስርትነት ላይ የተነሳ ስርአተ-መንግስት እንድሚያስፈልገን በመግልጽ ነበር። ወያኔው አስምሮ የሰጠንን ህዝብ ያልመከረበትን የክልል ወሰን አጥፈተን፤ በመከርነብት አዲስ የፌድራል መንግሳታት ሀገርና ህዝብን የሚያሳድጉ  በሚጠቅም  መልክ የተዝጋጁ፤ ህዝቡ ለስልጣን ቅርብ እንድሆን የሚያመቻቹ፤ እንዲሁም እንድ ኢትዮጵያ ላለ ታሪካዊና ታላቅ አገርና ህዝብ የአገራችን አስተዳድር ፕሬዝዳንታዊ እንዲሆንና  ከፍለ ሃገራትም (federal regional state)  እንዲሁም ትላልቅ ከተሞች   በህዝብ በሚምርጡ አስተዳድሪዎችና ከንቲባዎች  ( Governor and mayor ) ቢተዳደሩ መልካም እንድሆነና ፤ ባንድ ዋና ከተማ ላይ ከምንረባረብ፣ ወደፊት የተለያዩ  ከተሞች ን እንዲመስርቱና ያሉትንም እንድስፋፉ ቢድርገ የተሻለ መሆኑን በመግለጽ ነበር።

በዚህኛው ጽሁፌ የመምለከትው ሁሌም የምንሸሸውና የማንነጋግርበት፤ ነገር ግን ሊሁን የሚችል ትልቅ አደጋን መመልከት ነው።  ወያኔው ለ 27 አመት ባቀነቀነው ብልሹ ዘርን መሰርት ያደርገ ፖለቲካ ህዝቡ እክ እንትፍ ቢያደርገውም ስርአቱ ሙሉ ለሙሉ ስላልፈርሰና ከውስጡም በመጡ “የለውጥ ፈላጊዎች” ከነ እድፋቸው የሽግግሩን ሂደት በመሪንት በማያዛቸው፤ በተለይ ደግሞ የዘር ፖለቲካን የሚያቀነቀኑ ከወያኔው ጋ ተመሳሳይ አቋም የነበራቸው ነገር ግን ወያኔ ስልጣን ሳያጋራ ያባረራቸው  የጎሳ አክራሪ የፖለቲካ ድሪቶ ፓርቲዎች ሀገር ቤት ከንግሳንግሳቸው ያለ ስርአተና ህግ እንዲገቡና እንድፈንጥዙ በመደርጋቸው እንዲህም በጥላቻና ልይኑት ላይ ያተኮረ ግማሽ እውነት ይዘው በተጋነነ ትርከት ህዝቡ ወስጥ ከነሚድያቸው እንዲገቡ ስለፈቀደና፤ ህዝቡንም በፕሮፓጋንዳ ሰመምን ውስጥ በማስገብታቸው፣  ህዝቡ ሲታገለው የነበርውን የ 27  አመታት የዘር ፖለቲካ ፈተና በሌላ መልክ ከሽነው በማቀርብቻው፤  እነዚ ሃይሎችን የሚያስታግስ ተመሳሳይ ሰላማዊ ጸረ-ዘር ፖልቲክኛ ስብስብን እድል ባለማግኘቱና ባለመበርታቱ ህዝቡን ወደተሳሳት መንግድ ሊመሩት ችለዋል። ነግር ገን ምን ያህል እንድሚያራምዳቸ የምናወቀው ወደፊት ነው።

ባንድ በኩል ይቅርታና እርቅ እንዲሁም የህዝብ መቀራረብ እንዳይደርገ እይከለከሉ፣ በሌላ በኩል የጥላቻ ና የልዩነት መዝሙር እየዘፈኑ፣ በማስፈራርት፣ በመሳርያ ሀይል አገር እይዘረፉና እንዳልተገራ  ወይፈን እይፈንጩ ከልካይ በመጣታቱ ( ህግን ማስከብር ባልመቻሉ)  አገራችን እንዚህን የስልጣን ጥም ባሰከርቸው ሰዎች ወይም ስብስቦች ህልም ና ቅዠት ውስጥ ልትገባ  በቅታለች። ይህም  ወያኔ ህዝብን ሳያማክር ለአገዛዙ በሚያመቸው ከፋፍለህ ግዛው መልክ  በሰፍርላቸውና ባሰመረላቸው ድንበር መሰርት በማድርግ የመገንጠል ጥያቄ ሊመጣ ይችላል። ችግሩ መገንጠሉ ሳይሆን በህዝብ ፈቃድ ላይ የተመሰርተ ሳይሆን ለስልጣን፣ ለታሪክ ሽሚያ እንዲሁም ሃብት ለማካበቻ የሚጠቅማቸውን ጥቂት አለን አለን የሚሉ የጎሳ ፖለቲካ ነጋዴዎችን  መሆኑ ነው። ችግር ቢፈጠርና ከቁጥጥርቸው ውጪ ቢሆን ህዝቡን አጋልጠዉ እንርሱ የያዙትን የአሚሪካን ፣የአውሮፓ እንዲሁም ካናዳ ና አውስትርሊያ ፓስፖርታቸውን ይዘው ከነቤተሰቦቻቸው ይፈርጠጣሉ። የእሳት ማገዶ የሚሆነው ግን ሰፊው ህዝብ ነው።

በህግም ይሁን በጉልበት የሚፈልጉትን አገር የመገንጠልና መንግስት የመሆን ህልም ወይም ቅዥት እንድመልከተው። እንኳን የተለያዩ መንግስት ሆነው ባንድ ፊዴራላዊ መንግስት ጥላ ስር ውስጥ እንኳን ሁነው በመሬትና ወሰን ይገባኛል ስንት እልቂትና ህዝብ እንድተፈናቀለ የቅርብ ግዜ ትውስታቸን ነው።

እነ ኦነግና አጫፋሪ አክቲቭስቶቹ የሚምኝዋትን  ኦሮሚያ የምትባል ሃገር  ወያኔ በሰፍረላት ድንበር ወስን ተግነጥላ  መንግስት ትሁን እንብል። በምስርቅ በኩል ክ1000 ኪሎሚትር በላይ ከኢትዮጵያ ሶማሌ ጋ ትዋሰንላች። ይህ በህዝብ ፈቃድ ሳይሆን በወያኔው ለአገዛዝ ያመቸው ዘንድ ያሰመርው የድንበር መስመር የሃስት ስለሆነ ወደ ማያባራ ጦረነትና መፈናቃል በዚያ በኩል ይፈጸማል። በሰሜን በኩል ከአማራ ከሚባል መንግስት ጋ ደግሞ ብዙ የሚያጋጭ ድንበርና የታሪክ  የፕሮፕጋንዳ ቁርሾ ስላለ ሌላ ጦርነት ይጠብቃታል፤በምራብ በኩል ከደቡብ ህዝቦች በተለይም በጉጂና ጌድዏ እንዲሁም በሌሎችም ጋ የወሰንና የተፈጥሮ ሃብት ሽሚያ ጦርነት ይፈጥራል።

ኦሮሚያ ውስጥ ከ15  ሚሊዮን በላይ የሌላ ጎሳ ተወላጅ  ኢትዮጲያን ይኖራሉ። እንዚህም ዝም ብለው እጃቸውን አጣጥፈው በሚመስረተው የጎስኛ መንግስት ጋ ለመኖር ይቸገራሉ። ወይ ሁለተኛ ዜጋ ሁኑ ይባላሉ ወይም ኦሮሚያን  ልቀቁ ተብለው ሌለ ጦርነትና እሳት ይፈጠራል። ሌላው አዲስ አበባ የሁሉ ኢትዮጲያዊ  ዜጋ  መኖርያን በህዝብ ሃብት የተመሰርተችን ከተማ  ራሱን የቻለ ትልቅ ችግር ይሆናል። ባጠቃላይ  ማስርጃዎቹ የሚያሳዩት ትልቅ የጦርነት ቀጠና የሆንች ኦሮሚያ ስትሆን የርስ በርስ ጦርነት አውድማ ትሆንና ሶማሊያ፣ ሶርያ የቀድሞዋ ዩጎዝላቪያ አይንት እልቂትና እጣ ይሆናል። በዚያን ግዜ ዋና ዋና አጋፍሪዎቹ ህዝቡን ማገደው ወደ አሜሪካና ካናዳ ፣አውሮፓ አውስትራልያ  ይፈረጥጣሉ።

ይህ ጥፋት  የሚደርሰው በኦርሚያ መገንጠል ብቻ  አይደለም። አማራ የሚባል አገርም ልገንጠል ቢል ተመሳሳይ እጣ ነው የሚደርሰው። ትግራይም ልገንጥል ብትል አሁን ወያኔ ከሌሎች ቦታዎች ነጥቆ የወስዳቸውን መሪቶች ይዞ ልገንጥል ቢል በደቡብ አማራ ከሚባል መንግስት ጋ፣ በምስራቅ ከአፋር ከሚባል መንግስት ጋ፣ በሰሜን ከኤርትራ ጋ ስትዋጋ መንሮዋ ነው። ይህም ብቻ አይደለም ፖሊትከኞቹ ማየት እና መስማት የማይፈልጉት ሀቅ ግን አብዝኛው ኢትዮጲያውያን በደም የተቀላቀለ መሆኑን ነው። በተለይ መሃል አገር ያለው ኦሮሞና አማራ፣ በሰሜን ትግራይና አማራ፣ በምስራቅ ሱማሌና ኦሮሞ እንዲሁም በሌሎች  ቦታዎች ሁሉ የተዛመደ ህዝብ ነው።

የአገራችን ህዝብ በነዚህ የፖለቲካ ነጋዴዎች የተሸረበውን ሴራ በድንብ ማጤን ይኖርበታል። ምልክቶቹን  በመላው አገርችን በተለይም በኦርሚያና ኢትዮ ሶማልያ ድንበር፣ በጊድዮና በጉጂ፣ በሲዳማና ወላይታ፣ በአሶሳ አክባቢ፣ በቢንሻንጉል እንዲሁም በሰሜን አማራና ትግራይ ህዝቦች ላይ የደርሰውን የቅርብ ግዜ እልቂቶችና ጥፋቶችን ማስተዋል ይገባል።

እነዚ በጎሳ የመገንጠል የሚያቀነቅኑ የፖለቲካ ነግዴውች በዚያ ብቻ አይበቁም። ቢቻልቸው የገንጥሉትን ሃገር ደሞ በሃይማኖት ሊገንጥሉትና ሊከፋፍሉት መጣራቸው አይቀርም። ኦርሚያ ብቻ ብለው አይቆሙም። እንደ ገና ባአውራጃ  የሀረር፣የወለጋ፣ የሸዋ የቦረና የሚል ሌላ አባዜውች ይገባሉ። አማራን እንገንጥል የሚሉ ደግሞ  ጎጃም፣ ጎንደር፣ ሸዋ፣ ወሎ ማለታቸው አይቀርም።

እውነቱ እንግዲ ይሄ ነው።እንገንጠላለን ብለው የሚያስፈራሩትም የሚገጥምቸው ለምለምና ሰላም የሞላበት አገር ሳይሆን እሳትና ሞት ነው።  ይህ ማስፈራርታቸውንም ሌለው ህዝብ አውቆ አደባቸውን እንዲገዙ፣ ህዝቡንም ለአሳት እንዳይጥሉ በመነጋገርና በመከራከር ይሄ የሽግግሩ መንግስት የሰጣቸውን ከልካይ የለብኝም ሜዳ መስምር ማስያዝ ያስፈልጋል።

እንዚ የፖለቲካ ነጋዴዎች የሚፈልጉትን አገር መግነጠል ሲራ ሳይሳካልቸው የሚቀር መስሎ ሲታያቸው ደግሞ ሌላወን ኢትዮጵያዊ ዜጋ ላይ የበላይ ሁነው እነሱ በሚዘውርዋት በስም ብቻ ኢትዮጲያ የምትባል አገር መሪዎች መሆንንም ያልማሉ። ወያኔው ከፋፍሎ ለ27  አመታት እንደገዛን  ሁሉ እንርሱም ድርሻው አሁን የኛ ነው በሚል ስሌት ይህን ምስኪን ህዝብ ለአዲስ የመክራ አገዛዝ ያዘጋጁታል።

27  አመታት ሙሉ ህዝቡ ያለመታከት የሞተለትና የደከመብትን ሰላማዊ ትግል፡ ባለቀ  ሰአት ተቀላቅለው፤ የነበሩበትን አስክፊ ሰርአት ሙሉ ለሙሉ ሳይጠፉ፣ ከተቻለ ራሳቸውንና የአዲሲቷ ኢትዮጲያ ገዥዎች ለማድርግ፤ ካልተቻለም እንደገና ራሳቸውን ከመጡበትት ጎሳ ፖለቲካ ጫካ ውስጥ ገብተው  ባክራሪዎቹ ይዘመር የነበረውን ሁሉ፣ ቀድሞ አደራጊና አስፍጻሚ የመሆን ሽኩቻ ውስጥ ገብተዋል። ለእወነተኛ አገራዊ ለውጥ የተነሱትን  ሰዎች ከመካክላቸው  እያራቁ፣ እያባረሩ  ያአክራሪዎችን አጀንዳ ና ጥፋት ፈጻሚ በመሆን በመጀምርያ በድብቅ ቦሗላም በግልጽ ሴራ ላይ ተስማርተውል።

የጎሳ ፖለቲካና የመገንጠል አባዜ የያዛቸው የፖለቲካ ነጋዴዎቹ አዲስ ጥናትና ቀመር በድንብ አዘጋጅተው ስለመጡ፣ የኢትዪጵያ ህዝብ እስኪነቃ ድርስ ብዙ ጥፋት ያደርሳሉ። ከሚጠቀሙበት ዘዴ አንዱ በሚከተለው ምሳሌ ይገለጻል። አላማቸው በሞሶቡ ውስጥ ካለው ሙሉሙል ዳቦውች አንዱን  ማግኝት ቢሆንም ፡ አንዱን  ሙሉምል ይሰጠኝ ብለው ሳይሆን  የሚጠይቁት  ሞሶቡ ይገባኛል ብለው የቤቱን ባለቤት ይሞግቱታል። ሰውየውም ተድናግጦ አይ ሞሶቡን ሳይሆን ባይሆን አምስት  ሙሉሙል ነው የምስጥህ ይለውና አምስቱን ሙልሙል ያስርከባል። የአክራሪዎች የፖለቲካ ነጋዲዎች አሁን ያለውን የሽግግር መንግስት በዚህ መልክ እየጠይቁት አመራሮችን ግራ እያጋቡ ካሰቡት በላይ  ይሰበስባሉ። ረጋ ብሎ ላስተዋለ አሁን ጎልተው የሚታዩት  የፖለቲካ አጀንዳዎች በብዛት የአገራችን  ህዝብ ችገር፣ የደከመበት፣ የታገለበትን  አጀንዳ ሳይሆን እንዚህ አክራሪዎች የሚጠይቁትና የሚሰብሰቡትን ነው።

(ክፍል ፬ ይቀጥላል)።

ለኢትዮጲያ ና ለህዝቧ የሚበጀው ነገር – (ክፍል ፬ ) ከሙሉቀን ገበየው

በክፍል ፫ ጽሁፌ ያንሳሁት ሃሳብ በተለይ  ሁሌም የምንሸሸውና የማንነጋግርበት፤ ነገር ግን ሊሁን የሚችል ትልቅ አደጋን መመልከት ነበር።  ወያኔው ለ 27 አመት ባቀነቀነው ብልሹ ዘርን መሰርት ያደርገ ፖለቲካ ህዝቡ እክ እንትፍ ቢያደርገውም ስርአቱ ሙሉ ለሙሉ ስላልፈርሰና ከውስጡም በመጡ “የለውጥ ፈላጊዎች” ከነ እድፋቸው የሽግግሩን ሂደት በመሪንት በማያዛቸው፤ በተለይ ደግሞ የዘር ፖለቲካን የሚያቀነቀኑ ከወያኔው ጋ ተመሳሳይ አቋም የነበራቸው ነገር ግን ወያኔ ስልጣን ሳያጋራ ያባረራቸው  የጎሳ አክራሪ የፖለቲካ ድሪቶ ፓርቲዎች ሀገር ቤት ከንግሳንግሳቸው ያለ ስርአተና ህግ እንዲገቡና እንድፈንጥዙ በመደርጋቸው እንዲህም በጥላቻና ልይኑት ላይ ያተኮረ ግማሽ እውነት ይዘው በተጋነነ ትርከት ህዝቡ ወስጥ ከነሚድያቸው እንዲገቡ ስለፈቀደና፤ ህዝቡንም በፕሮፓጋንዳ ሰመምን ውስጥ በማስገብታቸው፣ ዋና አልማቸው አድርገው የያዙትን ማስፈራርያ የመገንጠል ጥያቄን እውን ቢያደርጉትና ቢሆንስ እወንታው ምን ይሆን የሚለውን ነበር።   ገንጥዬ ነጻ አገር አደርጋታለው የሚሉትን ስንመርመርው እንድሚያስቡት ማርና ወተት የሚፍስባት ሃገር ሳትሆን ወያንሌው በፈጠራላቸው የሃሰት  ወስንና ድንብር ምክንያት ከአጎራባች ክልሎች ጋር ያምያቕርጥ ጦረነትና አሳትና ለቅሶ፣ የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ መግባትና የሶማሊያን፣ የሶርያን፣ የየመንን እንዲሁም የቀድሞ ዩጎዝላቪያን እጣ መጋራት እንድሚሆን፤ ዋና አቀንቃኞቹ ግን ህዝቡን ማግደው እነርሱ የያዙትን  የአሜሪካ፣ የካናዳ የአውሮፓና አውስትርሊያ  ፓስፖርታቸውን ይዘው እንደሚፈርጥጡ፤ ቢሳካልቸው በሃይማኖት  እንዲሁም በአውርጃና በመንድር ነፃ አገር እንሁን ገደብ ድርስ እንድሚወርዱ ተብራርቶል።  ያም ካልታሳካልቸው እንደ ወያኔው የራሳቸውን ጎሳ ስም በምጠቀም በሌሎች ላይ በበላይነት በመቀመጥ “ድርሻውና ግዜው የኛ ነው” የሚል ሌላ አገዛዝ ቀንበር ለመጣል ተዘጋጅተውና ስትራተጂ ነድፈው መምጣታቸው ተብራርቶል።

በዚህኛው የመጨረሻ ክፍል ጽሁፌ የምመለከትው ጉዳይ የለውጡ አራማጆች፣  “መሪዎች” እንዲሁም ህዝቡም  በዚህ ሽግግር ወቅት ትኩርት እንዲሰጡባቸው የሚገባቸው ጉዳዮች ሲሆኑ ባጠቃላይ በ፫ ክፍል ላቀርብኩት ጽሁፋ ማጠቃልያና መድምድሚያ ነው።

አገራችን ኢትዮጲያ  መስቀልኛ መንግድ ላይ እንድመሆኗ በሚቅጥሉት ወራቶች የሚወሰኑ  ሃገራዊ ጉዳዮች እንደምታቸው ለርዥም ዘመን የሚሆን ስለሆነ ጥንቃቄና ማስትዋል ያለበት ትልቁን ሃገራዊ ሃሳብ ሰላምና አንድነት፣ የህዝብ መቀራረብን የአብሮ ማደግን፣  በተለይም ግፍና ጭቆናን የሚቀርፍና የዜግነት መብት የሚስምርበት ዲሞክራስያዊነትን  መሰረት ያደርግ መሆን አለብት። አንጋፍው ፕሮፌሰር መስፍን ወልማርያም በመፀሃፋቸው እንዳሰፈሩት የኢትዮጲያ ህዝብ ያቄማል፣ ግዜ ጠብቆ መንግስትን ለማውርድ አብሮ ያግዝና አውርዶ ወደ ቤቱ ይመልሳል ነግር ግን ወድፊት የሚቀመውን መንግስት ግን አይሰራውም ያሉት ተደጋጋሚ የቅርብ ግዜ የታሪክ እውንታን ደግሞ እንዳይፈጸም ህዝቡም ለዘላቂ ለውጥ መንሳስትና የሚመጣውን የመንግስተ ስርአት በዘላቂነት በአዲስ መልክ ሰርቶ መሆን አለበት ቤቱ መግባት ያለበት።

በቅርቡ አንድ ታዊቅ ወጣት የፖለቲካ ሰው እንድተናግሩት ያአገራችን  ና የህዝቡ ቀንበር ዋናው ችግሩ ባገዛዝም  በተቃዋሚውም አመራር ያሉ የፖለትከኞች መጥፎ  የፖለቲካ ልምድ ነው።የችግሩ አንዱ መፍቴህ መሪዎቹ፣ የፖልቲካ ፓርቲዎቹ ከህዝቡ ጥያቄና ፍላጎት ጋር ለመጣጣም፣ ለመለወጥ ዝግጁ መሆን  አለባቸው።  ይህ ትልቅ እውነት ያለው አነጋግር ነው። የመጥፎ እድል ጉዳይ ሆኖ አብዛኛው ፖለቲኮኞቻችን ወደ ፖለቲካው አለም ሲገቡ  ለህብረትስቡ የሚጠቅም ስራ ለምስራት አስበን ነው  ሳይሆን እንዴት ጥቅም፣ ስልጣን፣ ሃይል፣ ሃብት፣ ታዋቂነት እንድሚያግኙ ዋናው አላምቸው አድርገው ነው። ይህንን እውንታ እንርሱ ቢክዱትም  (at subconscious level that is the truth) ድርጊታቸው የሚያሳየው ግን ያንን ነው።   እነርሱ ሳይለውጡ እንምራዋለን የሚሉትን ህዝብ ችግር እንዴት በዘላቂነት  ሊለውጡ ይችላሉ?

ነገሮችን ከስር መስረቱ ቀለል  ባለ መልክ እንመልከትወ። በ ታሪክ አጋጣሚም ይሁን በእግዚሃቤር ፈቃድ አብዛኞቻችን ኢትዮጲያ ተፈጥረናል ወይም ተውልደናል። ባአለም ላይ ያሉ አብዝኞዎቹ ሃገራት  ሁሉ አሁን ያሉበት የአገር ህዝብና ወሰን ላይ የደረሱት በተለያየ ግዜ የህዝብ ፍልሰትና በጦረነት ውጤት መሰረት ነው። ይሄ ነገር በኛ አገር ብቻ የሆነ አይደለም። የሰው ልጅ ከታሪክ ይማራል እንጂ የቀድመውን ታሪክን አሁን አይኖርውም። እኛም ይህን ማወቅ ይኖርብናል።የሰው ልጆች ማህበራስባዊ  ና ታሪካዊ እውንታዎች   የሚያስየን በተለይ ባለፉት 50-100 አመታት ያይነው የተማርነው እውንታ፡ ሰዎች በመውያየት በመነጋገር የጋራ ሰላም፣ ብልጽግና እንዲሁም እድገት ሊይመጡ መቻላቸውን ነው። የአውሮፓ አገራት ለዚህ ትልቅ ምሳሌ ናቸው። አንዱ ሌላውን ጨቁኖ  ሊዘልቅ እንድማይቻል ከአለም እንዲሁም ከራሳችን የትግል ልምድም የምናውቀው ነው።

አሁን ያለንበት አገራችን ኢትዮጲያ የጋራ ቤታችን ናት። ለሁላችንም በእኩልነት ዜግነት ሊኖርን ይገባል። አንዱ ከሌላው የበለጠ ዜጋ ሊሆን አይችልም ወይም አይገባም። ይህም እንዲሆን መፍቀድ የለብንም። ይህን የጋራ ቤታችንን አውቀን፣ ተክባበርን ካልጠበቅናት ሌለ ሃይለኛ ሊወስዳት ይችላል። አባቶቻችን ካለም ሃገራት ሁሉ በተለየ ትልቅ  ውልታ ያደርጉልን ይህችን ሃገር በጋራ ሁነው  ሀይለኞች እንዳይውስዱብን አጥንቻቸውንና ደማቸውን አፍሰው ለኛ ያስርክቡን ታሪካዊ አገር ናት። እኛ ደግሞ ከነሱ የተሻለ የመንግስት ስርአትና መስርተንና  ሀገር ጠብቀን ለልጆቻችን ማስርክብ ግዴታ አለብን። ካለበልዚያ የተረከብነውን አደራ  የማንውጣ በታሪክም በወድፊቱም ትውልድ ተወቃሾች እንሆናለን።

አገራችን ላንዱ እናት ለሌላው የአንጀራ እናት እንድትሆን ማደርግ የለበንም። ሁላችንም እኩል ልጆቹዋ የምንሆነው በዜግንታችን ላይ መሰረት ያደርገ መንግስት ስንመስርት ነው።  በጎሳ፣ በህይማኖትና በቋንቋ መሰርት አድርገን እርስ በርሳችንን መካከል አጥር   ከሰራን ሃገራችን የጋር አገርና እኩል ልጆችዋ አንሆንም። እኩልንት የጎደልባቸው ወንድሞቻችን መብታቸውን ለማግኝት ይታገላሉ ፤ ይህም ሰላም  ያደፈርሳል፣ በዚህም አገር ትደማልች ወገንም ይሰቃያል። ሌላው ቢቀር አባቶቻችን በመካክላቻው የነበርውን መጨቛቖን ወደ ጎን አድርገው ያስርከቡንንም አገር አፍርሰን ቤት አልባ ህዝብ እንሆናልን።

ታድያ መፍቴው ምንድን ነው?

ከዚህ ትንሽ ገለጻ የምንገንዘበው፣ በዜግንት ሁላችንም እኩል የሆንብት መንግስት መስርተን  በመካክልችን ያለው የ ቋንቋ የባህል የወግ የመሳሰለውን ልዩንታችን ጌጥ አደርገን በመከባብር የጋር ማደርግ ስንችል ነው። እያንዳንዱ ኢትዮጲያዊ  ዜጋ ነኝ ብሎ በኩራት የሚናገረውና ውስጡም የሚያምነው በየትም የአገራችን ክፍል ተዘዋውሮ ህብት አፍርቶ ህግ አክብሮ መኖር ሲችል ነው። ይህን ለማድርግ ደግሞ  አሁን ያለንበት የሽግግር ግዜ በሚወሰኑ ታላላቅ ጅማሮውች  የሚመስርት ይሆናል።

ቀደም ብዬ ባቀርባኳቸው ፅሁፎች ላይ እንዳብራራውት መድርግ ያለባቸውን አንኳር ጉዳዮች አቀርባለው። ሃስቦቹ ቀድምው የተብራሩ ስለሆነ ለማጠቃለል ያህል እንደ ቅድመ ተከተልቸው እንዲፈጸሙ እዘርዝራልሁ።

 1. የሽግግሩ የለውጥ መሪዎች ከቀደመው ስርአት የመጡ “የለወጥ ፈላጊዎች”  በመሆናቸው በሙሉ ሃይልና ፍላጎት ሽግግሩን ሊወጡት ብቻቸውን ስልማይቻላቸው የተለያዩ ነገር ግን አገርና ህዝብ አዳኝ አመለካከት ያላቸውን ያገር ሽማግሌዎችን፣ ሙሁራንን፣ የሞያ ማህበራትን ቢያካትትና ባገራችን ውስጥ ያሉ የፖልቲካ ድርጅቶችን ሁሉ የሚሰበስቡብት ምክር ቤትን  እያማከረ የለውጡን ሂደት ማፈጠን።
 1. ላልፉት 45-50 አመታት አሁን ባለው የአገራችን ህዝብ ላይ የተፈጸመን በደልና የክፋት ስራ በዳይና ተብዳይ ተግናኘትው (የፖልቲካ ድርጅቶችንም ጨምሮ)  የይቅርታ፣የእርቅ የፍርድ በህዝብ መካከል የመግባቢያ ሰፊ መድርክ ተደርጎ (ከ ደቡብ አፍሪካ ልምድ መማር ይቻላል) ያለፈውን የክፋት የቂም በቀል የሃዝን ድባብ ዘግተን  በአዲስ እህት-ወንድማምችነት በዳይና ተበዳይ ይቅር ተባብለው በሰላም የሚኖሩባት ሃገር መስርተ መጣል።
 1.  ሕዝባችን ለመከራና ለብዝበዛ የተጋረጠው ገዥዎች የተጠቀሙበትን የከፋፍልህ ግዛው የልዩንት መሳርያ  የሆነውን ፖሊሲና ህግ አፍራሽ መሆኑን ትልቅ አጽኖት ተሰጥቶት፤ በህዝቡም ዘንድ በፖለቲካ ፓቲዎችም ዘንድ ያንን አስከፊ ባህል ተመልሶ እንዳይመጣ መስማማት።
 1. ለወደፊት ትልቅ በሽታ የሚሆነብንን የከፋፍልህ ግዛው ህጋዊ መሰረት የሆነውን  ወያኔ ላገዛዙ ያምቸው ዘንድ በላይችን ላይ የጫነውን ህግ-መንግስት መመርመር፣ ካስስፈለገንም የልዩንታችን የሚያስፋ  መሰርት የሆኑትን ህጎች ማውጣት ወይም ህዝብ ሁሉ የሚመክርበት አዲስ ሀገ-መንግስት ማጽደቅ።
 1. በዘር ላይ የተመሠረት ፖለቲካ ፓርቲ አገር አፍርሽና ህዝብ ረባሽ  ስለሆነ  ህዝቡንና የፖለቲክ ፓርቲዎችን አነጋግሮ ተምክሮ ተስማምቶ በዘር ላይ ወይም ጎሳ ላይ የተመሰርተ የፖለቲካ ድርጅትን በህግ ማገድ።
 1. በመንግስት መንበር ላይ የተቀመጡት ሃላፊዎች የአገርና የህዝብ ሰላምን፣ የደህነንትን ህግ ማስከበር ግዴታቸውን እንዲውጡ መስራት አለበት። ህግ ወጥ ሀይለኞችን፣ ከህግ ውጪ መሳሪይ ታጥቀው ህዝቡን የሚያስፍራሩ ወንጅለኞችን ስብስብ እንዲሁም በማን አለበኝነት ባደባብይ ህዝብን ከህዝብ የሚያጛጭ፣ ለጦርነት የሚያንሳሳ ፕሮፕጋንዳን የሚነዙ ግልሰቦችን ወይም ስብስቦችን  እንዲሁም ሚዲያ ተቋማትን በህግ ጥላ ስር ማድርግ።
 1. የአገር ሰላምን የህዝብ ደህንንትና ጸጥታን የማያውክ ነገር ግን የተለያይ ሃሳቦችና አመለካከቶችን የሚቀርቡብትን ነጻ ሚዲያን ህትመትን መፍቀድ ማበራታት።
 1. በሽግግር ላይ ያለው የፊዴራሉም ሆነ የክልል መንግስታት  ስልጣን ላይ የተቀመጡት በትክክልኛ የህዝብ ድምጽ ተምርጠው ሳይሆን ገዠው ወያኔ ይመራው የነበረው መንግስት ሁሉን አግልሎ፣ ራሱን ብቻ አስቀምጦ በማስፈራርት በተደርገ የሃሰት ምርጫ መሆኑን አመነው፤  እውንትኛው የህዝብ ምርጫ እስኪምጣ ድርስ ሽግግሩን ከማፋጠን እና ከመድግፍ ወጪ ህዝብን በህዝብ ላይ የሚያስነሳ፣ ዜጎችን የሚያፍናቅል  ፕሮፕጋንዳና የግልጽም የድብቅ አስተዳደራዊ ውሳኔ ከማድርግ እንዲቖጠቡ ማድርግ፡፤ ያደርጉትንም በህግ መጠየቅ።
 1.  ባልፉት 27 አመታት ለደረሱ በደሎች ህግ-ወጥ ስራዎች ምንም እንኳ ወያኔ የአንብሳውን ድርሻ ቢይዝም አብርው ሁነው በህዝብ ላይ ሰቆቃና በደል ያድርሱ የነበሩ የኢህአዴግ ና ተባባሪዎቻቸው የሆኑ ሌሎች ፓርቲ ካድሬ እንዲሁም ባለስልጣኖችን  በእኩል ለፍርድ ማቅረብ። በትግርይ ያሉ ወድንሞቻችን ሀገር ውስጥ የሚድርገው ለውጥ የነርሱም እንዲሆነ የሚያስችልን ስራ መስራትና  በሽግግሩ ሂድት ላይ በዋና ተሳታፊ እንዲሆኑ ማድርግ።
 1. በመንግስት  ሃላፊነት የተቀመጡ መሪዎች  የሚሰጧቸው አዲስ የሽግግር ግዜ ሹመቶች በጎሳ ወይም በጥቅም ወይም ድብቅ የፖለቲካ አላማ ለማራመጃ እንዳይሆን፤ በብቃትና ለህዝብ በሚጠቅም መልክ መሆን አለበት። ይህንንም ያለው ፓርላማ አባላት በብቃት ይከታትሉት ለማለት ቢያስችግርም (የህዝቡ እውንትኛ ተውካይነታቸው በነጻ ምርጫ ስላልተመርጡ)  ገለልትኛ የአገር ሽምግሌዎች ቢመረምሩት። ሚዲያውም ይህንን እያጋለጠ ጥፋትን አስቀድሞ ማስቆም የሚቻልበትን መንግድ ማስያዝ ግዲታ አለበት።
 1. ለዲሞክራሲ መሰርታዊ ቅድም ሁኒታዎች የሆኑትን የመንግስት መዋቅሮች  እንደ ነጻ የፍርድ ቤትን፣ ፖሊስ፣ መክላከያ ሃይል፣ የጸጥታ ሲኩሪት መዋቅርን፣ ሚዲያን፣ የሰእባዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችን (እንባ ጠባቂ ተቋሞችን) የምርጫ ኮሚሽን በነጻነትና በገለልትኛ እንዲዋቀር፤ ላለው መንግስት መሳርያ ሳይሆን ለተመርጠ መንግስት ሁሉ የሚታዘዝ ተቋም እንዲሆኑ ማድርገ ። ይህም በብቃትና በችሎታ በትምህርትና ልምድ ላይ የተመስርተ እንጂ በፖለቲካ አመልካክት ደጋፊንት መስረት  ላይ እንዳይሆን ብርቱ ስራ መስራት። ሚዲያውም ይህን እያረጋገጠ መዘገብ።
 1. ሀገራዊ መግባብትና የህዝብ እርቅ ሳይፈጸም እንዲሁም በህግ ህዝብንና አገርን የሚበትን አንዱን በአንዱ ላይ የሚያስንሳ የሚያጋጭ ዘምቻን ሳይገደብ ለምርጫ ሩጫ እንዳይድርግ።
 1. አሁን አገር በመምራት በመንግስት መንበር ላይ ያሉ ሃላፊዎች በህዝብ ምርጫ ስልጣኑን የያዙ አለመሆናቸውን አወቀው ነገር ግን “የለውጥ ፈላጊ”  የቀድመው ስርአት አካል መሆናቸውን ና ለህዝብ በሰጡት ተስፋ  የተቀብላቸው መሆኑን አውቀው፤ 27 አመታት ሙሉ የተደርገውን የህዝብ ትግል ዘላቂ፣ ሰላምዊ ዲሞክራስያዊ የህዝብ አንደንት ያለብት አገርን ለመምስርት ለሽግግር ግዜ ብቻ  እንዲያገለግሉ  በከፍትኛ ሀገራዊና የህዝብ አደራ እንዲመሩ፤ ላድርጉትም ለሚያደርጉትም መልካም ስራ ህዝቡና ታሪክ የሚያመስግንቸው ሲሆን ለሚሰሩት ባለማውቅ ስህተት ህዝቡን ይቅርታ እየጠየቁ ለሚውስዱት ውሳኔም  እንዲሁም ማድርግ የነበርባቸው ግን ሳይወስኑ ለሚቀሩ ወሳኝ ጉዳዮች (conscious omission) እንዲሁም ጥፋት ሃላፊነቱንና ተጠያቂነትን መቀበል ይኖርባቸዋል። የሚወስኑትን እያንዳንዱ ወሳኝ ውስኔ  “ይሄ  ነገር አገር ና ህዝብ ይጠቅማል? የህዝብ አንድነትን መግባብትን ያጠናክራል? ለተገፉና ለተርሱ ወገኖችን ችግር ለመቅርፍ ያግዛል? ፍታህዊና ሞራላውንት አለው?” ብለው ሁሌም ራሳቸውን እንዲጠይቁ ይገባል።

የዚህ  የሽግግር ግዜ ውጤቱ  ለ50 አመታት የተደከምትን የህዝብ ትግል እውን ማድርጊያ፤  በዜግንት እክሉነት፣ በህዝብ መቀራርብ ህብረት  ላይ፣ ዲሞክራሲ የሰፈንባት፣ ሃይልኞች የማይፈንጩባት፣ ስልጣን በሰላምና በህዝብ ምርጫ  የሚያዝበት፣ ድሃ የማይበደልባት ስልጣን ለህዝብ ቅርብ የሆነብትን የመንግስት ስርአት  ለማምጣት ሁላችንም ይህን የሽግግር ግዜ እውን እንዲሆን ማገዝ ያለብን ሲሆን ሙሉ አደራውን ለእህት-ውንድሞቻችን ብቻ ሰጠተን እንርሱን መውቅስ ሳይሆን፤ ዋናው አላማ እንዲሳክ  በመተባበር ችግሩን ሰላማዊ በሆነ በመነጋገር እይፈታን የህዝቡን ራእይ እውን ለማደርግና አግርችንን ታላቅ አገር ለማድርግ  አግዚሓቤር አምላክ ይርዳን።

ህወሓት ያቦካውን ሉጥ ኦህዳዴ ሲጋግር፤ ብአዳን ማገድ ያቀብሊሌ!! ጎበዜ ! በኢትዮጵያ ከአሁን በኋሊ ከመሸ፤ ተመልሶ አይነጋም !! (አሥራዯው ከፈረንሳይ)

መግቢያ :

በዙህ መጣጥፌ ያሇወትሮዬ በጥያቄ መጀመሩን መርጫሇሁ :

 • ሇመሆኑ ሶርያ ከኢትዮጵያ ምን ያህሌ ትርቃሇች ?!
 • የመንስ ከኢትዮጵያ ርቀቷ ምን ያህሌ ነው ?!
 • ጎረቤታችን ሶማሉያስ ?!
 • የነዙህን አገራት ሁኔታ ያጤነ፤ የማንኛውም አገር ሕዜብስ በእሳት መጫወት ይገባዋሌ ?!

ዯግሞስ !

 • የኦቦ ሇማ መገርሳ  ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው !  አባባሌ በቅጽበት ወዳት ተነነ ?! ወይስ ከበፊቱም ሇሽንገሊ ነበር ?
 • የጠ/ምኒስትር አብይ አህመዴ ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዜቦቿን ይባርክ !” የሚሇው ምኞትና ህሌም ምነው ባጭሩ ተቀጨ ?!

ወይስ ባንዴ ወቅት፤ አቶ መሇስ ዛናዊ ሇትግራይ ኢትዮጵያዊ ወንዴሞቻችንና እህቶቻችን፤ “እንዯ ወርቅ በዕሳት ከተፈተነው ከትግራይ ህዜብ በመፈጠሬ እኮራሇሁ” ብሇው፤ የትግራይን ህዜብ የአፍ ጮማ እንዲስቆረጡ፤ አብይ አህመዴም በተራቸው፤ በዙያው በሚያዲሌጥ ጭቃማ መንገዴ፤ መጓዘን መረጡ ?!

የመዯመሩ አባዛ :

ከጠ/ ምኒስትር አብይ አህመዴ ጋር አብረን ተዯምረናሌ እያለ፤ አብይና የሇውጥ ፈሊጊው ቡዴን ቀን ሲገነቡ የዋለትን፤ ማታ ማታ እንዯ ጃርት እየቆፈሩ በማፍረስ፤ ከሕዜብ አጣሌተው፤ የተጀመረውን ሇውጥ ሇመቀሌበስ፤ ላት ተቀን የሚሠሩ፤ መሰሪዎች መኖራቸውን አጢነዋሌ ?!

የመዯመሩ አባዛ በጎሣ ኮታ ብቻ እየተሰሊ፤ ዕውቀትና ችልታ ሇላሊቸው ሰዎች፤ እንዯ ጠበሌ መታዯለ፤ የሚያመጣውን ችግር፤ የሇገጣፎ ሕዜብ መፈናቅሌ፤ በቂ ማስረጃ ሆኗሌ::

የመዯመር ጭንብሌ አጥሌቀው፤ ከመሬት ስበት በከፋ፤ ጠ/ምኒስትሩንና ቡዴናቸውን ወዯ ታች የሚጎትቱ፤ ቦርቧሪዎችን በብብታቸው አቅፈው ብዘ ርቀት መጓዘ እንዯማይችለ በመረዲት፤ ከጎሣ ኮታ ይሌቅ፤ ሥሌጣን ዕውቀትና ችልታ ሇተካኑ፤ አገራዊና ወገናዊ ፍቅር ሇተሊበሱ ዛጎች በመስጠት፤ ተነጣጥሇን ከመጥፋት ይሌቅ፤ አብረን በመዯጋገፍና በመከባበር እየሠራን፤ አገራችን ኢትዮጵያንና ሕዜባችንን እዴናገሇግሌ ቢያዯርጉ፤ ያን ጊዛ ” ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዜቦቿን ይባርካሌ ” !!

ክቡር ጠ/ ምኒስትር ! ጎሠኝነትና  ረኝነት በሚሰበክባት አገር አንዴነትን፤ ላቦች በነገሡበት ምዴር ብሌጽግናን፤ ጦር በሚሰበቅባት አገር ሠሊም፤ አይኖርምና: ኢትዮጵያን በምርቃት ብቻ እንዯማያቀኑ ተገንዜበው፤ የህወሓትን ብቻ ሳይሆን፤ የኦህዳዴ፤የብአዳንና የዯህዳን፤ ቱባ ቱባ ላቦችን፤ በሌመና ሳይሆን በተግባር በሕግ የበሊይነት ሇፍርዴ በማቅረብ፤ ኢትዮጵያን በብዘ ቢሉዮን ድሊር ዕዲ  ፍቀው፤ ዴሃው ሕዜባችንን እያስራቡ፤ የ ረፉትን የኢትዮጵያ ሃብት እንዱመሇስ ያዴርጉ::

ላሊው ግሌጽ እንዱሆንሌን የምንሻው ጉዲይ :

 • ሇመሆኑ! ጠ/ ምኒስትሩ ማነው ?! አብይ አህመዴ ወይስ ጃዋር መሃመዴ ?!

ሌክ እንዯ አቶ መሇስ ዛናዊ፤ በፈሇገው ጊዛ በቴላቪዥን መስኮት ብቅ እያሇ፤ በመቀመጫው ሊይ በመቁነጥነጥ፤ እጆቹን እያወናጨፈ፤ ጣቶቹን ቀስሮ ሕዜብ ሲያስፈራራና፤ ሁለንም አክሳሪ የሆነ የጎሥና የ ር ፖሇቲካ ሲረጭ፤ ምነው አዯብ ግዚ የሚሌ መካሪ፤ ወይም ህግ ጠፋ ?!

 • ጃዋር የሚዴያ ባሇቤት ነኝ ባይ ነው ፤ መሌካም እንኳን ሆነ ! ሇመሆኑ የገን ቡ ምንጭ፤ ከየት ? ከማንና ? እንዳት ተገኘ ?!
 • ከጃዋር በስተጀርባ አብሮነታችንን እየናደ ፤ የጎሣና የ ር ግንብ የሚገነቡሌንስ እነማን ናቸው ?!
 • ጃዋርና የጃዋር አይዝህ ባዮች፤ ከምርጫው በፊት፤ በምርጫው ወቅትና፤ ከምርጫው በኋሊስ ምን እየዯገሡሌን ነው ?! ጎበዜ ! ጠርጥር፤ በገንፎ ውስጥ አይጠፋም ስንጥር፤ እንዱለ ሆኗሌና::

ከራሳቸው በስተቀር፤ ማንንም የመወከሌ ህጋዊ መብት የላሊቸው፤ የፖሇቲካ አመንዣኪዎች፤ የስሌጣን ቋንጣ ሇመቀሊወጥ ስሇፈሇጉ ብቻ ፤ ከያለበት ተጠራርተው ሕዜባችንን በጎሣና በ ር ፖሇቲካ ሲያምሱ ምነው ሃይ የሚሌ አካሌ፤ ወይም ህግ ጠፋ ?!

ተ ቅዜቀው የሚያነቡ የእናት ጡቶች፤ ሇጆሮ የሚሰቀጥጥ የሕፃናት ሇቅሶ፤ የሃ ን ጉም የቋጠረ የአባቶች ትካዛ፤ ዯስታን ሳይሆን ሃ ን ሇማጨት የተዯገሠሇት ወጣት፤ በማህፀኗ ተስፋን ሳይሆን ሞትን አርግዚ፤ መከራን ሇመውሇዴ የምታጣጥር እንስት ሇማየት ምነው ተቻኮሌን ?

በሕብረ ብሄር ሌጆቿ ተጎናጉና ውብና ያማረች፤ ጠንካራና ጤናማ ኢትዮጵያን በማየት ፈንታ፤ በጎሣ ካራ ተገዜግዚ የተበጫጨቀች፤ዴሃና ዯካማ ኢትዮጵያን ማየት፤ የማንኛችንም ምርጫ ይሆናሌ ብዬ ስሇማሊምን ተስፋ አሌቆርጥም :: አሁንም ጊዛው ገና ስሊሌመሸ፤ ሇአንዴነታችን አብረን  ብ እንቁም:: አንዴም ቀን ብትሆን ዕዴሜ ናትና !!

ወገኖቼ ! ሇሠሊም እንጂ ሇጠብ ምክንያት ሞሌቷሌ፤ ውሃ ቀጠነም ብል መጣሊት ይቻሊሌ:: ትሌቁ አዯጋ

ከአሁን በኋሊ በኢትዮጵያ ውስጥ በሚፈጠረው ችግር፤ አሸናፊና ተሸናፊ አይኖርም፤ በእርግጠኝነት መናገር የሚቻሇው ነገር ቢኖር፤ ሁሊችንም ተሸናፊዎች እንዯምንሆን ነው ::

በዙህ ሁሊችንም ከሳሪዎች በምንሆንበት የጥፋት ጎዲና፤ የጎሳና የ ር ፖሇቲካ እያፏጩ፤ ላሊውን አግሊይ በሆነ ንፉግ ፖሇቲካ፤ እሽኮሇላ በመጨፈር፤ ተራው የእኛ ነው፤ ወይንም ጊዛው የእኛ ነው የሚለን፤ የአስተሳሰብ ዴንክዬዎች፤ ያሌተረደት ወይም ያሌታያቸው ጉዲይ ቢኖር፤ የአስተሳሰብ አዴማሳቸውን ሳያሰፉ፤ የጎሣ ጥብቆ ሇብሰው ፤ የ ረኝነት ጋቢያቸውን እያራገቡ፤ አብሮነታችንን በመናዴ፤ ብዘ ምዕተ ዓመታት ወዯ ኋሊ ጎትተው በዴቅዴቅ ጨሇማ፤ እኛንና እራሳቸውንም ጭምር፤ ሁሊችንም አብረን የመቃብራችን አፋፍ ሊይ መቆማችንን ነው::

ጠባብ በሆነ አስተሳሰብ፤ ሁለን አግሊይና፤ አብሮነትን የሚሸረሽር፤ አገር አጥፊ የጎሣና የ ረኝነት ፖሇቲካ እያቀነቀኑ፤ ኢትዮጵያን የመሰሇ ሕብረ ብሔር፤ ትሌቅና ባሇ ብዘ ታሪክ፤ ብልም የአፍሪካውያን የነፃነት ቀንዱሌ፤ በጀግኖች ሌጆቿ ዴሌ አዴራጊነት፤ የዓሇም አቀፍን ቀሌብ የሳበች፤ ውብ አገር ማስተዲዯር በእጅጉ ያዲግታሌ ::

ሰሞነኛ የፖሇቲካ ሱቅ በዯረቴዎች፤ ጊዛው ያሇፈበት የፖሇቲካ ሸቀጣቸውን፤ ከያሇበት ሸክፈው በመምጣት፤ ኢትዮጵያንና ሕዜቧን፤ ቤተ ሙከራ ሇማዴረግ ከሚያዯርጉት አጉሌ መሯሯጥ፤ እንዱቆጠቡ ከወዱሁ እንመክራሇን እናሳስባሇንም ::

ምን ቢቸግረው፤ ምንም ያህሌ ቢራብ፤ ይህ ኩሩ ሕዜብ፤ አክ! ብል ወዯተፋው አስከፊ ስርዓት ዲግም እንዯማይመሇስ፤ ጉሮሯቸውን እየተናነቀ፤ ሆዲቸውን እየጎረበጠ፤ ቢያስቸግራቸውም ሉውጡት የሚገባ ሃቅ መሆኑን እንነግራቸዋሇን ::

ሇ27 ዓመታት የችግራችን መንስኤ የሆነውን፤ የ ርና የጎሣ ፖሇቲካ የሚያራምደ፤ የዚሬው የመፍትሔ አካሌ ሇመሆን እንዯሚቸገሩ ስሇምናውቅ፤ በጎሣ አንቀሌባ እንዯታ ለ፤ በኢትዮጵያ ሕዜብ ጀርባ ሊይ እሹሩሩ እያሌን እንዯማናቀብጣቸው፤ ቁርጣቸውን ከወዱሁ ይወቁ :: አገርና ሕዜብ፤ የሚገባውን ክብርና እንክብካቤ ማግኘት ሲገባው፤ በአጠያፊ የጎሣና የ ር ፖሇቲካ ሉታመስ አይገባም::

ጥሊቻ ሲነግሥ ፍቅር ይኮስሳሌ፤ ጎሠኝነት ሲያብብ አብሮነት ይጠወሌጋሌ፤ በመንዯርና በክሌሌ ዯረጃ ብቻ ስናስብ፤ አገር ይከስማሌ፤ ህዜብ ከህዜብ ይጋጫሌ፤ ዯም መቃባት ይመጣሌ፤ ይህ እንዲይሆንና በወገኖቻችን ሊይ ግፍና መከራ የምንጋብዜ፤ አገር ገዲይ ትውሌዴ እንዲንሆን በእጅጉ እንጠንቀቅ ::

ባሇንበት በዙህ 21ኛው የስሌጣኔ  መን፤ ዓሇም ወዯ ትንሽ መንዯርነት ተቀይራ፤ ሁለም ነገር በፀሐይ ፍጥነት፤ በሚሇዋወጥበት፤ የሳይንስና የቴክኖልጂ  መን፤ በጎሣ አጥር ተከሌሇው፤ በመንዯር ዯረጃ በመተራመስ፤ ጥሊቻ የሚያገሱ ኮርማዎችን፤ ሌንጠየፋቸው ይገባሌ:: በአገር፤ በክፍሇ ዓሇምና:በዓሇም አቀፍ ዯረጃ፤ በሁሇንተናዊነት ( universalist ) ዯረጃ ማሰብ የተሳናቸው፤ የአስተሳሰብ ሰንካሊዎች በመሆናቸው፤ ሰው ብቻ ሳይሆን፤ ግኡዞ መሬትም በእጅጉ ትጠየፋቸዋሇች ::

ማሳረጊያ

ህወሓት በ’ራሱ አምሳያ ጠፍጥፎ የፈጠራቸው፤ ጎሣንና  ርን መሠረት ያዯረጉ፤ ኦህዳዴና ብአዳን የተባለ የጎሳ ዴርጅቶች፤ በቅርቡ ኦዳፓ እና አዳፓ የሚሌ የዲቦ ስም አውጥተናሌ ቢለም፤ ሁሇቱም የተፈጠሩት፤ እንዯ ህወሓት ከጅብ ቆዲ በመሆኑ፤ ቅኝታቸው አሁንም ያው የጥንቱ ዓይነት፤ እንብሊው እንብሊው የሚሇው ስሇሆነ፤ የኢትዮጵያን ህዜብ በ ርና በጎሳ ፖሇቲካ እያባለ፤ አንደ በላሊው ወገኑ ሊይ ጦር እየተማ  ፤ ህይወት በየዕሇቱ ይቀጠፋሌ፤ ብዘዎች ከመኖሪያ ስፍራቸው እየተፈናቀለ ሜዲ ሊይ ፈሰዋሌ:: ዚሬ በአራቱም የአገሪቷ ማዕ ን፤ የሚቃጠሌ ቤት፤ የሚቀጠፍ ሕይወት፤ የሚ ረፍ ሃብት፤ ከስፍራው የሚፈናቀሌ የህዜብ ብዚት አግሪቱን አጥሇቅሌቋሌ ::

ህወሓት ከነ ዯንዯሳም ላቦቹ፤ የትግራይን ሕዜብ እንዯ ዋሻ ወይም እንዯ ጫካ ቆጥሮ፤ በትግራይ ሲወሸቅ፤ አሽከሮቹ ኦህዳዴና ብአዳን ዯግሞ፤ ህወሓት ያቦካውን ሉጥ (የጎሣና የ ር ፖሇቲካ) ኦህዳዴ ሲጋግር: ብአዳን ዯግሞ የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪ፤ ኢትዮጵያዊ ወንዴሞቻችንና እህቶቻችንን ሇማገድነት በማቅረብ ይማግዲሌ ::

አክሳሪ የሆነውን፤ የጎሣና የ ር ፖሇቲካ፤ ሂትሇር በጀርመን፤ ሞሶልኒ በጣሉያን፤ ሞክረውት ትርፉ፤ ሇብዘ ሚሉዮን ሕዜብ ዕሌቂት፤ ሇመሊው ዓሇም የኢኮኖሚ ዴቀት እንዯነበር፤ ከታሪክ መማር ያቃታቸው፤ የአስተሳሰብ ዴሃዎች፤ ዚሬ በኢትዮጵያ እንዯ መፍትሔ በመቁጠር፤ እንዯ ኮሶ ሉግቱን ሲፈሌጉ፤ እንቢ ! የማሇት አቅምና ዴፍረቱ፤ ሉኖረን ይገባሌ ::

የአስተሳሰብ ዴህነት ከዴህነቶች ሁለ በእጅጉ የከፋ በመሆኑ፤ በአንዴነታችን አብረን፤ ጠንካራና፤ የበሇፀገች አገር ዛጎች መሆን ስንችሌ፤ ሁሊችንም ተበታትነን ዯካሞችና ዴሆች ሆነን ሇመሞት አንቸኩሌ::

በአንፃሩ፤ ሇኢትዮጵያ አንዴነትና ሌዖሊዊነት፤ ሇዛጎች ሰብአዊ መብት መከበርና ሇእኩሌነት፤ ቆመናሌ የሚለት የአንዴነት ኃይልች፤ ግማሾቹ ቆመው ማንቀሊፋት ብቻ ሳይሆን፤ ተኝተው ሲያንኮራፉ፤ ላልቹ ዯግሞ፤ ከጎሣ ፖሇቲካ አቀንቃኞች ጋር፤ የተቧዯኑ በመሆናቸው፤ ቀን ጠብቀው ሚዚን ወዯ ዯፋበት ሇመሇጠፍ፤ ወይም ሇመንሸራተት፤ ያዯፈጡ መሆናቸውን ስናይ በእጅጉ እናዜናሇን::

ዴሃው ገበሬና ሠራተኛ፤ እራሱ ሳይማር፤ ግብር እየከፈሇ በነፃ ያስተማረው፤ ምሁር ተብዬ በበኩለ፤ አዴፍጦ አጎንብሶ እየበሊ፤ አገሩና ወገኖቹ፤ እራሱም ጭምር አስጊና ቀውጢ ወቅት ሊይ ሆነው፤ ከምቾት ክሌለ ስንዜር ታህሌ ርቀት እንኳን ፈቀቅ ሇማሇት ያሇመዴፈሩ፤ በጣም ከማሳ ኑም በሊይ በእጅጉ ያሳፍራሌ !!

 • የጨው ተራራ ሲናዴ :ሞኝ ይስቃሌ፤ ብሌህ ያሇቅሳሌ  ልሬት ፀጋዬ ገብረመዴህን ዴሌ ሇኢትዮጵያ ሕዜብ !

እግዙአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዜቧን ይባርክ !!

የኦዴፓ ክንብንብ ሲወርድ (በመስከረም አበራ)

በመስከረም አበራ

Ethiopian writer, Meskerem Abera.

መስከረም አበራ

ሃገራችን ኢትዮጵያ ከህወሃት አረመኔያዊ አገዛዝ ለመላቀቅ ባደረገችው የትግል ምጥ “የለማ ቡድን” የተባለ የድንገቴ ልጅ ታቀፈች፡፡ይህ ቡድን አለ ወይስ የለም የሚለው ራሱ ሲያጠራጥር ነበረ፡፡መኖሩ ከተረጋገጠ በኋላ ደግሞ ከህወሃት ባርነት ነፃ የመሆን አለመሆኑ ነገር ብዙ ሲያከራክር ቆየ፡፡ከህወሃት ነፃ መሆኑን ፈጣሪ ጌታውን ራሱን ህወሃትን ከስልጣን ገፍትሮ ጥሎ አሳየ፡፡በስተመጨረሻው እንደ አውሬ አድርጎት የነበረውን ህወሃትን ገፍትሮ በጣለ ቅፅበት ኦዴፓ የኢትዮጵያን ህዝብም በአደንዛዥ ፍቅር ጣለ፡፡የፍቅር ብዛት ትንታግ ተቃዋሚውን ገራም ባለሟል፣አዋቂውን አላዋቂ፣ተጠራጣሪውን አማኝ አደረገለት፡፡የወዳጅ ጠላቱ በፍቅር ሰመመን ውስጥ መውደቅ  ኦዴፓ የሚሰራው ሁሉ በመላዕክት ጉባኤ የተወሰነ ቅዱስ ሃሳብ ተደርጎ እንዲወሰድ አደረገ፡፡ብዙው ሰው በፅኑ ፍቅር መመታቱን ያጤነው ኦዴፓ ከአባቱ ኦነግ፣ከጌታው ህወሃት የወረሰውን ዘረኝነቱን ፈራ ተባ ሳይል ያስኬደው ጀመር፡፡

የመጀመሪያው የኦዴፓ እውነተኛ ማንነት የተገለጠው ስልጣን በያዘ ማግስት ህግ ጠረማምሶ የአዲስ አበባ ምክርቤት አባል ያልሆነ ሰው የከተማዋ ከንቲባ አድርጎ ሲሾም ነው፡፡ ኦዴፓ የፌደራል ስልጣን ላይ ተስተካክሎ ሳይቀመጥ ገና እንዲ ያለ ህግ የመጣስ ድፍረት ያሳየው በአዲስ አበባ ላይ የነበረውን አላማ ለማስፈፀም ካለው ጉጉት አንፃር ነው፡፡ታከለ ዑማ የአዲስ አበባ ከንቲባ ተደርጎ የተሾመው ሰውየው ከኦሮሞነቱ በተጨማሪ  የሰፈረበት የኦነግ መንፈስ ብርታት ስለተፈለገ ጭምር ነው እንጅ በአዲስ አበባ ካውንስል ውስጥ ኦሮሞ ፈልጎ ማግኘት አስቸግሮ አይደለም፡፡ከሁሉም በላይ ግራ አጋቢው አዲስ አበባን መምራት ያለበት ኦሮሞ ብቻ ነው የሚለው ህግ ከየት እንደመጣ ነው፡፡

የኦዴፓ ክንብንብ የወረደበት ሌላው አጋጣሚ የኦነግ ሼኔ አመራሮችን ወደ አዲስ አበባ መግባት ተከትሎ በቡራዩ የተደረውን አሳዛኝ  ጭፍጨፋ ማዳን ሲችል አለማዳኑ፣ነገሩ ከተከሰተ በኋላም ገዳዩን በጥብቅ የህግ ክትትል ስር ለማድረግ ወገቤን ማለቱ ነው፡፡ይህ ሳያንስ የአዲስ አበባ ወጣቶችን ለቃቅሞ ከሃገር ዳር አውጥቶ ሁለትም ወር ሙሉ በበረሃ እስርቤት ማጎሩ ነው፡፡በበኩሌ የኦዴፓ ነገር የበቃኝ የዚህ ጊዜ ነው፡፡ ኦዴፓ መራሹ መንግስት ያንን ሁሉ የአዲስ አበባ ወጣት ያለምክንያት ሲያስር ለመታሰራቸው በቂ ምክንያት ያላቸውን የቡራዩ ነፍሰ-ገዳዮች በብር ዋስ እየፈታ ነበር፡፡በዚህ ላይ የአዲስ አበባ ልጆች መታሰራቸው ትክክል እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ የኦዴፓ ዋና ዋና ባለስልጣናት እየተፈራረቁ ያስረዱን ነበር፡፡የአዲስ አበባ ወጣቶች እስር ደግሞ ማንን ለማስደሰት እንደሆነ ግልፅ ነበር፡፡ከዚህ በኋላ ኦዴፓ ከህወሃት ባላነሰ ስልጣን እና ዘረኝነት የሚያመጡትን ብልግና የመድገም “ብቃት” እንዳለው መገመት ከባድ አልነበረም፡፡ አሁን እያደረገ ያለውም ይሄንኑ ነው፡፡

በሶስተኝነት የማስቀምጠው በግሌ ኦዴፓን የመረመርኩበት አጋጣሚ የሃገር መከላከያ ሰራዊት አባላት ቤተ-መንግስት መግባታቸውን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፓርላማ የተናገሩት ንግግር ነው፡፡ጠ/ሚ አብይ በፓርላማ ተገኝተው “የወታደሮቹን ቤተ-መንግት ሰተት ብሎ መግባት እንደቀላል ነገር በቴሌቭዥን ያወራሁት በአዲስ አበባ ዙሪያ ያሉ ኦሮሞዎች መንግስታችን ወደቀ ብለው በፈረስ እንዳይደርሱ ፈርቼ ነው” ብለዋል፡፡ፍቅር አይኑን ላልሸበበው ሰው ይህ ንግግር ብዙ ትርጉም አለው፡፡ከሁሉም በላይ ግን አብይ “የሁሉም ኢትዮጵያዊ ጠቅላይ ሚኒስትር ነኝ” ሲሉ የባጁትን ንግግር ልባዊነት ጥያቄ ውስጥ ይከታል፡፡አብይ ቦምብ ሲወረወርባቸው በእጁ የተከላከለላቸው የአዲስ አበባ ህዝብ ቢሆንም ለእርሳቸው የክፉቀን ደራሽ፣የዙፋናቸው ደጀን ሆኖ የሚታያቸው የሆሎታ እና የሱሉሉታ ፈረሰኛ ኦሮሞ ነው፡፡ከዚህ መረዳት የሚቻለው የዘር ፖለቲከኛ የአንገት እና የአንጀት ወዳጅ እንዳለው ነው፡፡የዘር ፖለቲከኛ ከዘሩ ህዝብ ጋር እኩል ያየኛል፣የእኩልነት ፖለቲካ ያመጣልኛል ብሎ መድከምም ለቂልነት የሚዋሰን ነገር ነው፡፡

አራተኛው እና ዋናው ክንብን አውራጅ ስራ የተሰራው ህግን እና ደምብን ባልተከተለ መንገድ ከኦሮሚያ ክልል ለመጡ ሰዎች የአዲስ አበባ ነዋሪነት መታወቂያ በገፍ መታደል ሲጀምር ነው፡፡ነገሩን በጣም አሳፋሪ የሚያደረገው ነገር ደግሞ መታወቂያው የተሰጠው ከንቲባው በገዛ አንደበታቸው “በአዲስ አበባ ማንኛውንም አይነት መታወቂያ መስጠት አቁመናል” እያሉ በሚያወሩበት ጊዜ መሆኑ ነው፡፡ከዚህ የባሰው አስገማች ነገር ደግሞ ይህን የእብሪት እና ማንአለብኝነት ህገወጥ አሰራር ያጋለጠችን ወ/ሮ ሰናይት የተባለች የእውነት ሴት ከስራ ማባረሩ ነው፡፡ከስራ መባረሯ ተሰምቶ በህዝብ ዘንድ  ጉም ጉም ሲያስነሳ ሴትዮዋን ወደ ስራዋ ለመመለስ ተብሎ የተፃፈው ደብዳቤ አስተዛዛቢ ነው፡፡የደብዳቤው ይዘት ኦዴፓ በህወሃት ቤት በአሽከርነት ሲያድግ እንዴት ጌታውን መስሎ እንዳደገ አመላካች ነው፡፡የህወሃትን መልክ ጠልቶ ቢቸግረው ኦዴፓን ያመነው ህዝብ ደግሞ በማንም ውስጥ መልሶ የህወሃትን መልክ የማየት ፍላጎትም ትዕግስትም የለውም፡፡ይህን አለመረዳት የውርደት ሞት ይገድላል!

ቀድሞ ከተገለፁት በልጦ በኦዴፓ እውነተኛ ማንነት ላይ ግልፅ ምስክር የሆነው የለገጣፎ ቤት የማፍረስ ክስተት ነው፡፡ይህ በምላስ ሊጋርዱት የማይችሉት ያፈጠጠ ገበና ነው፡፡የለገጣፎው ነገር ኢህአዴግን የመሰለ ዘረኛ ድርጅት ዙፋን ላይ አስቀምጦ ስለ ሰብዓዊ መብት ማውራት ለቅሶቤት እንደመዝፈን ያለ ዕብደት እንደሆነ ያስመሰከረ ሃቅ ነው፡፡የለገጣፎው ቤት የማፍረስ ዘመቻ ኢ-ሰብአዊነት ብዙ የተባለለት ስለሆነ ወደዛ መግባቱ ላያስፈልገኝ ይችላል፡፡ይልቅስ ጉዳዩን አስመልክቶ የኦዴፓ መራሮች የሚናገሯቸውን ንግግሮች ተንተርሰን የፓርቲውን ማንነት ወደመመርመሩ ማለፉ የተሻለ ይሆናል፡፡

የለገጣፎው ቤት የማፍረስ አካሄድ እንዴት ትክክል እንደሆነ የሚያስረዱ የኦዴፓ ባለስልጣናት በተለይ ከንቲባዋ ወ/ሮ ሃቢባ ነገራቸውን የሚጀምሩት የለውጥ/የተሃድሶ አመራር መሆናቸውን በመጥቀስ ነው፡፡የለውጥ አመራር ነኝ ባይዋ ሴትዮዋ ወ/ሮ አዜብ እንዳደረጉት በኢሳቷ ጋዜጠኛ ኢየሩሳሌም ተክለፃዲቅ ጆሮ ላይ ስልክ ጠርቅመው ዘግተዋል፡፡ስልክ መዝጋቱን ያመጣው ጋዜጠኛዋ የማያፈናፍን ጥያቄ በማቅረቧ ነው፡፡ ወ/ሮ ሃቢባ ስልክ ከመዝጋታቸው በፊት ምንም አይነት ሰው እንዳላፈናቀሉ፣የመፈናቀሉን ወሬ የሰሙት በኢሳት እንደሆነ ተናግረው ሳይጨረርሱ ደግሞየፈረሰው ቤት ሁለት መቶ ሆኖ ሳለ  ኢሳት አራትመቶ ብሎ ማውራቱ ልክ እንዳልሆነ ይናገራሉ፡፡ሁለት መቶ ቤት ፈርሶ ምንም ሰው የማይፈናቀለው እንዴት እንደሆነ ለማወቅ እንጓጓሁ ስልኩን ጠርቅመው ዘግተው አረፉት፡፡

ከኢሳት እንዲህ የተሰናበቱት የለገጣፎ ከንቲባ ወ/ሮ ሃቢባ የቡራዩውን ከንቲባ አስክለው “OMN” በተባለው ቴሌቭዥን ላይ በአካል ቀርበው ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ቤት ማፍረሱ እንዴት ትክክል እንደሆነ ለማስረዳት ሁለቱም ከንቲባዎች ከ2004 በፊት እና በኋላ የሚል ነገር ያስቀምጣሉ፡፡ከ2004 በፊት ግንባታ ያደረጉ ሰዎች ህጋዊ ካርታ እንዳገኙ ጠቅሰው ከ2004 በኋላ የሰፈሩቱ እና ከከተማው ማስተር ፕላን ጋር ግጭት ያለው አሰፋፈር የሰፈሩ (ለምሳሌ በማስተር ፕላኑ የኦሮሞን ባህል ለማሳደግ ሲባል የፈረስ መጋለቢያ፣የአረንጓዴ መናፈሻ ቦታዎች ተደርገው የተቀመጡ ቦታዎች ላይ የገነቡ) ሰዎች ቤታቸው መፍረሱ ህግን የማስከበር ስራ እንደሆነ ደጋግመው አስረድተዋል፡፡

ቤት የፈረሰባቸውን ሰዎች ገበሬውን አታለው በትንሽ ዋጋ መሬቱን ገዝተው የሰፈሩ መሬት ወራሪዎች እንደሆኑ ሁለቱም ከንቲባዎች ያስረዳሉ፡፡ይህ የዘር ፖለቲካ አይነተኛ መገለጫ ነው፡፡መሬት የብሄር ብሄረሰቦች ነው በሚለው ህገመንግስታዊ ድንጋጌ መሰረት ገንዘብ ሲፈልግ መሬቱን መጤ ለተባለ ሰው የሸጠ ብሄር ብሄረሰብ ገንዘቡ ሲያልቅበት መሬቱንም የመከጀል መብት ያለው ይመስለዋል፡፡ይሄን አስቂኝ ክርክር ከገበሬው እሻላላሁ ብሎ ስልጣን ላይ የተወዘፈ የዘር ፖለቲካ ባለስልጣንም እንደሚጋራው የለገጣፎዋ ከንቲባ ወ/ሮ ሃቢባ እና ቢጤዋ የቡራዩው ከንቲባ ምስክር ናቸው፡፡ወ/ሮ ሃቢባ ህዝብን ማፈናቀላቸው፣ከቤት ጋር ህይወት ማፍረሳቸው ለኦሮሞ ህዝብ ጥቅም የመስራታቸው መገለጫ እንደሆነ፣ከዚህ በፊትም እንዲሁ ለኦሮሞ ህዝብ ጥቅም ሲታገሉ እንደኖሩ፣ወደፊትም በዚህ እንደሚቀጥሉ ኮራ ብለው ተናረዋል፡፡ከዚህ የምንረዳው የኦህዴድ የለውጥ አመራር ተብየው በዘረኝነቱ ህወሃትን የሚያስንቅ እንደሆነ ነው፡፡

“ገበሬው ተታሎ በዝቅተኛ ዋጋ መሬት ሸጠ” የሚለው ከእውቀት ነፃ የሆኑ ዘረኛ ባለስልጣናት ክርክር አስቂኝም አስገራሚም ነው፡፡ ገበሬው ተታሎ በትንሽ ዋጋ የሚሸጠው መሬቱን ብቻ የሆነው እንዴት ነው?ገበሬው ምነው ተታሎ ኩንታል ጤፉን  በአምስት መቶ ብር ሸጦ አያውቅ? ምነው ተታሎ ሰንጋ በሬውን በአንድ ሽህ ብር ሲሸጥ አልታየ?ይህ ከአዝጋሚ ጭንቅላት የሚመነጭ ክርክር አላማው “ወገንን” አድኖ “መጤን” ለማጥቃት ነው፡፡ገበሬው ተታለለ የሚለው መሬት መሸጥ ህገወጥ መሆኑንም ሳያውቅ ነው የሸጠው፣ተታሎ በትንሽ ዋጋ ስለሸጠ የሚገባውንም ጥቅም አላገኘም በሚል መሬቱን ሼጦ የበላውን “ወገን” አርሶ አደር ነፃ በማድረግ “መጤው” ላይ እርምጃ ለመውስድ ያለመ አካሄድ ነው፡፡እውነታው ግን ሌላ ነው፡፡ ገበሬው መሬቱን የሚሸጠው ግራቀኝ አስቦ፣የሚጠቅመውን አውቆ ነው፡፡በተለይ ከ1997 ወዲህ ህወሃት መራሹ ኢህአዴግ  የአዲስ አበባ ዙሪያ መሬቶችን በኢንቨስትመንት ስም እየቀማ፣ለገበሬው የአይብ መግዣ የማይሆን ካሳ ከፍሎ ማፈናቀል ጀምሮ ነበር፡፡ይሄኔ ገበሬው መንግስት መጥቶ በማይረባ ገንዘብ  ሳያፈናቅለው በፊት መሬቱን በጣም በተሻለ ዋጋ ለግለሰቦች መሼጡን አማራጭ አድርጎ ወስዶ ነበር፡፡እንዲህ ጥቅም ጉዳቱን አመዛዝኖ የሸጠው ገበሬ ነው እንግዲህ ተታሎ በርካሽ ሸጠ የሚባለው፡፡

ከገበሬው ቀጥሎ ማዳን የተፈለገው ደላላም፣ባለስልጣንም ሆኖ መሬቱን ሲቸበችብ የነበረውን የኦህዴድ ባለስልጣን ነው፡፡ከገዥም ከሻጭም የበለጠው ጥፋተኝነት ያለው በነዚህ ካድሬዎች ላይ ሆኖ ሳለ የእነሱ ጥፋተኝነት በለሆሳስ ይታለፍና ጦሱ ሁሉ የሚወድቀው ኦደፓ ከቆመለት የኦሮሞ ህዝብ ውጭ የተወለዱ፣”ያለግዛታቸው መጥተው ቤት የሰሩ ሰዎች” ላይ ነው፡፡ይህ የኢህአዴግ ዘረኝነት አይነተኛ መለያ ነው፡፡እነዚህ በበስልጣናቸው ላይ ደላላነት እና ሌብነት የደረቡ ባለስልጣናት ላይ የማይጨከነው አሁን ደግሞ ተገልብጠው “የለውጥ አመራር” ተብለው የአብይን እና የለማን ዙፋን የሚሸከሙ ስለማይጠፉ ነው፡፡

ከለገጣፎ ቤቶች መፍረስ ጋር ተያይዞ በ”OMN” ማብራሪያ ከሰጡት የቡራዩ ከንቲባ ንግግር ደግሞ ጉዳዩ ህገ-ወጥ ያሉትን ግንባታ ከማፍረስ አለፍ ያለ አላማ እንዳለው መረዳት ይቻላል፡፡ከንቲባው ስለጉዳዩ ሲያስረዱ መሬት ወራሪዎቹ አንድ ቤት ከገዙ በኋላ ብዙ ዘመድ አዝማዳቸውን እየጎተቱ እንደሚያመጡ፣በአንድ መሬት ግዥ ሰበብ በተገዛው ጊቢ ውስጥ ብዙ ሰው እንደሚሰፍር በምሬት ገልፀዋል፡፡ይህ ንግግራቸው የፓርቲው ጠብ ከቤቱ ግንባታ ብቻ ሳይሆን በቤቱ ውስጥ ከሚኖሩ ግለሰቦች ማንነት እና ብዛት ጋር የተያያዘ እንደሆነ ሳያውቁት ጠቁመዋል፡፡

ወ/ሮ ሃቢባ ከተል ብለው እነዚህ ሰዎች እዚህ አካባቢ መጥተው የሰፈሩት የሆነ ድብቅ ዓላማ ይዘው እንደሆነ ተናግረዋል፡፡በሴትዮዋ አስተሳሰብ ሰዎቹን ለገጣፎ የወሰዳቸው የቤት ችግር ሳይሆን ኦሮሞ ሳይሆኑ ኦሮሚያን የመውረስ “እኩይ” ሃሳብ ነው፡፡በዚህ ያልበቃቸው ሃቢባ የሰዎቹ መፈናቀል ከፍተኛ የሚዲያ ሽፋን ያገኘው(በሃቢባ አነጋገር ጫጫታ ያስከተለው) ተፈናቃዮቹ ሚዲያ ከሚጮህት ሁለት ክልል የመጡ በመሆኑ እንደሆነ ንዴት እየተናነቃቸው ተናገሩ፡፡አሁንም ሳያውቁት ማፈናቀሉ ዘር የለየ እንደነበር በገዛ አንደበታቸው አወጁ! ስልጣን ለመያዝ የዘረኝነት ልክፍት እንጅ እውቀት እና ማገናዘብ ከማይጠየቅበት ከኢህአዴግ ቤት እንዲህ ያለ ኩርማን ሃሳብ ያው ሰው ከንቲባ ሆኖ ቢገኝ ገራሚ ነገር የለውም፡፡

የሃገሪቱን ህዝብ በሰፊው ሲያነጋግር፣የኦዴፓን ማንነትም በገሃድ ሲያሳይ የሰነበተውን የለገጣፎውን የቤት ማፍረስ ተግባር አስመልክቶ ገዥውን ኦዴፓን የሚመሩት ዶ/ር አብይም ሆኑ ክልሉን ኦሮሚያን የሚመሩት የነወ/ሮ ሃቢባ አለቃ አቶ ለማ መገርሳ ትንፍሽ ሳይሉ መሰንበታቸው የሚያሳየው ከግፉ ተቃራኒ መቆማቸውን ሊሆን አይችልም፡፡ሳምንት ቆይተው ስለጉዳዩ ሲናገሩም ጠ/ሚንስትሩጭራሽ  አልሰማሁም ሲሉ አቶ ለማ በዝምታቸው ቀጥለዋል፡፡ ከሁሉ የሚብሰው ደግሞ የዜግነት ፖለቲካን እናራምዳለን የሚሉ ፓርቲዎች ዝምታ ነው፡፡ይህ ነገር የዜግነት ፖለቲካ ሁነኛ ጠበቃ የሌለው የፖለቲካ አሰላላፍ ለመሆኑ ፍንጭ ሰጭ ነው፡፡