ዳግማዊ አፄ ሚኒሊክ አቶሚክ ቦንብ ነበራቸው እንዴ? (ከሰርቤሳ ክ.)

ከሰርቤሳ  ክ.  April 24 /  2019)

ዳግማዊ አፄ ሚኒሊክ

አገራችን ኢትዮጲያ የብዙ ጎሳዎችና ቛንቛዎች  አገር ናት። ከ 5000 አመት በላይ ታሪክ እንዳላት ብዙ ማስርጃዎች ያሳያሉ (1) ። በዘመናት የአገራችን  ግዛት ሲሰፋና ሲጠብ የኖረ ሲሆን እንድዚሁም ጎሳዎችና ቋንቋዎቹም እንዲሁ ሲሰፍና ሲጠቡ ኖርዋል። አብዛኞቹ በአለም ላይ ያሉ አገራት ድንበር በጦርነት ከዚያም በሚከተለው ወጤትና ስምምነት የሚጸኑ  የድንበር ወስኖች ናቸው (2) ። አገራችን ኢትዮጲያም በዚሁ ታሪካዊ ሂደት ያለፍች ስትሆን ኢትዮጲያ ብቻ በጦርነት ወሰኗን የመሰርተች የሚመስላቸው ብዙ የተሳሳቱ ወገኖች አሉ። ነግስታቱ ሲጎብዙ፣ ሃብት ሊያፋሩ፣ሃይማኖት ማስፋፋት ሲፈልጉ  ግዛታቸውን ብዙ  ግዜ በጦርነት አንዳንዴም በጋብቻ በሚመስረት ዝምድና በመዋሃድ ያገር ድንበርና ህዝብ ያሰፋሉ። ይህ ባውሮፓ ና በጥንታዊ  የመካከልኛው እንዲሁም የሩቅ ምስራቅ አገሮች ሁሉ የሆነ ነው።

አሁን የምናውቃትን ዘመናዊ ኢትዮጲያ ከነ ዳር ድንበሯና ወስኗ  ለቀሪው ትውልድ ያስርከቡት የዳግማዊ አፄ ሚኒልክ መንግስት ነው። አገራችን ስታንስ በዘመነ-መስፍንት ግዜ ( 18ኛው ክ/ ዘምን  ሁለተኛው አጋማሽና   19ኛው  ክ/ዘመን የመጀመርያ አጋማሽ)  የነበርቸው የተበታትኑ የሰሜን  አውራጃዋችን  ስታክል፤   ስትስፋ ደግሞ ባፄ አምደ ጽዮን ዘመነ መንግስት (14 ክ/ዘምን መጀምርያ አጋማሽ 1314-1344)  የአሁኗን ኤርትራ፣ ጅቡቲ፣ ሱማሌን ሁሉ ያከተተች ግዛት ነበረች። በአኩሱም መንግስት ዘመን (ከ 2-10 ክ/ዘመን)  ግዛቱ አንዳንዴም ቀይ ባህርን አልፎ ያሁኗን የመን ይጭምር ነበር (3,4,5)።

በተለይ አምስት  የሚሆኑ የታሪክ ክስተቶች  የጥንታዊት ኢትዮጲያን  ህዝብ ጎሳና ቑንቛ እንዲሁም የግዛት ወሰኑን  እጅጉን ሲለዋውጠ ችሏል።

የመጀምርያው ያክሱምን ዘምነ መንግስት የወደቀበት 10ኛው  ከፍለ ዘመን  ባፈ ታሪክ በዩዲት ዘምን ግዜ ሲሆን 960  ይህም  የአክሱም መንበር መንግስትና ስልጣኔ ወድቆ  ወደ ዛግዌ ስርወ መንግስት  የተለውጥችበት ዘመን ነው። በዚያን ግዜ በምእራብና በሰሜን አሁን ሱዳን የነበረውን አገር ሁሉ  ቀርቶ የዛግዊ መንግስት ወደ ሮሃ  (ላሊበል) ሲከትም ወደ ዳቡብ ግን  ግዛቱን አስፍቷል።  የዛግዌ ስረወ-መንግስትም የራሱን ስልጣኔ አሻራ ትቶ አልፎል(4, 6)።

ሁለተኛውግዜ1270  ይኩና አምላክ  ከሸዋ ንግስናውን  ወደ ኢትዮጲያ ንጉሰ ነግስትነት በአቡነ ተክልሃይማኖት እርዳታ ከዛግዌ ስረው መንግስት (10-13 ክ/ዘምን)  ከተርከበ ቦኋላ በተለይም በጀግንንቱ ወደር የሌለው  ንጉሰ ነግስት አጼ አምደ ፂዮን  የኢትዮጲያን ግዛት እጅግ አስፍቶ ታልቅ ግዛት አድርጓት ነበር። በምስራቅ ያሁኑዋ ጅቡትን፣ እንዲሁም ሱማሌን  ሁሉ ያካተተ ሲሆን አብዛኛውን በጦርነት ና በሰላም  ስምምነት ያስፋፍው ግዛት ነበር።  እጅግ ብልህ ስለ ነበር  በያዛቸው ግዛቶች ያገሩን ሰው እየሾመ  ሃይማኖታቸውን ስይቀይሩ  ባህላቸውን እንደያዙ ለማአከዊው መንግስት እንዲገብሩ ያድርግ ነበር። በዚህም  የርሱ  ግዛት የታወቁትን  ያዳል ሱልጣን፣  የይፋት እንዲሁም ዳውሮ  ግዝቶች ሁሉ ያካተቱ ነበር (4,5)።

ሶስተኛው ግዜ 16ኛው ክፈለ ዘመን መጀምርያ አጋምሽ  አጼ ልብነድንግል  ዘመን  በተለይም  ግራኝ አህመድ (አህመድ ኢባን ኢብራሂም አል ጋዚ)  የተደርገው ትልቅ ጦርነት  1527-1543 የቀድሞውን ኢትዮጲያ የህዝብ ቑንቋ፣  ጎሳ ና  የ ሃይማኖት አስላልፈ በይብልጥ ለውጦታል።  በተደርገው 14 አመት ጦርነት የቀድሞዋ ኢትዮጲያ  እጅጉን የተቀይርችበት፣ ሃብቷ  የተዘርፈበት፣ ቤተ ክርስትያኖትች የተቃጥሉበት፣ የጽሁፍ ታሪኳ የጠፋብት ሲሆን፤ በሌላም በኩል እስልማና ወደ ስሜን ኢትዮጲያ የተስፋፋበት፤  በተለይም ደግሞ ከጦርነቱ ቦሗል ሁለቱ ሃያላን ማለትም ንጉሱና የሓረሩ አሚር በጦርንቱ ደክመው ደቀው ስልነብር  በደቡብ ኢትዮጲያ ይኖሩ የነበሩ ኦሮሞ ወገኖቻችን  ወደመሃል አገር  እስከ መካከልኛው ሰሜን ኢትዮጲያና እንዲሁም በምስራቅ ኢትዮጲያ አስከ ሓርር ግዛት  ባጭር ግዜ  የፈለሱብት ታሪካዊ ወቅት ነበር። በዚህም ሳቢያ የኢትዮጲያ ህዝብ፣ ጎሳና ቑንቓ እጅጉን ከበፊቱ ተለውጦል(4,5) ።

አራተኛው ዘመን ከ1769 to 1855 ድረስ  የቆየው ዘመነ- መስፋንት ኢትዮጲያ በታሪኳ ሁሉ ያንስችበትና  የተለያዩ የአውርጃ መሳፍንቶች  ከመሃል መንግስት ተንጥለው  የራስቸውን አግዛዝ  የመሰርቱብት ግዜ ሲሆን፤ የድቡብ ና ምስርቅ ኢትዮጲያ  ሙሉ ለሙሉ  የተነጠለብት ግዜ ሲሆን፤  ጎንድር ፣ጎጃም ፣ወሎ፣ ሸዋ ና የትግሬ አግር ( ትግርይና ኤርትራ በክፊል ) በተበታትነ  የራስ አገዛዝ ወይም እጅግ ልል በሆነ መአክልዊ መንግስት ስር ነብሩ ። ከ ኦሮሞ ወገን የነብሩ ክርስትያን የየጁ ሰዎች ማእክላዊ ኢትዮጲያን ጎንደር ፋሲለደስ ቤተ-መንግስት ተቀምጠው ይገዙም ነበር  ። (በይበልጥ የሚታውቁት እቴጌ  መነን እንዲሁም ልጃቸው ትንሹ ራስ አሊን ይጨምራል)። ዓፄ ቲውድሮስ  (ዳግማዊ)  ተንስተው አንደ አገር አስኪ ያደርጉቸው ድርስ የኢትዮጲያ መአክልዊ መንግስት የተዳከምባት የመስፍንቶች አውራጃ ስብስብ ነበርች።  እሳቸውን የተከተሉት  ነግስታት በተለይመ አጼ የሐንስ  4ኛ   ፌድራል በሚመስል  አስትዳድር ንጉስ ተከል ሃይምኖትን በጎጃም፣ ንጉስ ሚኒልክን በሸዋ፣  ንጉስ ሚካኤልን በውሎ  አድርገው፤ ሰሜኑን  ኢትዮጲያ ራሳቸውን ይዘው  የኑጉሶች ሁሉ ንጉስ (ንጉስ ነግስት ሆነው ) አገር አስፈትው ጠብቀው ኖረዋል(3, 4)።

ንጉስ ሚኒሊክ እድገታቸው በሸዋ ቤትመንግስት በአባታቸው ንጉስ ሃይለ መልኮት ሲሆን  ቦሗላም በምርኮና እስራት  ባፄ ቴድሮስ መቅደላ አንባ ታስረው በነበሩበት ጌዜ የ መኳንንቱ ልጆች ከሚሟራቸው የጦር፣ አገር አስተዳድርና አገዛዝ  ባሃልዊ ትምህርት በተጨማሪ በፅህፍም እንዲሁም ባፈ-ታሪክም የቀደሞዋን ገናና  የኢትዮጲያን  ወሰነን ታሪክ ይማሩ የነብሩ ሲሆን፤ በዚያ የሚያልፍ ተማሪ ሁሉ ስልጣን ቢይዝ ያንን  ታላቅ ገናና እገርና ታሪክ ለመመልስ ይመኝ ነብር(3)።

ንጉስ ምንሊክ ካፄ ቴዎድሮስ መቅደላ አንባ  በ ሃምሌ  1965 አምለጠው ሸዋ ያባታቸው አገር ከገቡ ቦሃላ የሸዋ ንጉስ ሆኑ። አፄ የሐንስም  4ኛ ሃይለው የኢትዮጲያ ንጉሰ ነግስት ሲሆኑ በሳቸው ስር የሸዋና ደቡብ ኢትዮጲያ ንጉስ ሆኑ።

አምስተኛው ዘመን፡ ንጉስ ሚኒሊክ የቀድሞ “ያባቶቻቸው የሆነውን ግዛት”  ለመምለስ ይመኙ ነብረና  በወቅቱ የነበረው የሃያላን አውሮፓ አገራት ና የቀኝ ግዛት አሰለልፈ  እንዲሁም ካፄ ዮሓንስ የሚደርስባቸውን ተጽኖ ለምቛቋም ግዛታቸውን በጦርነትና በሰላም ያስፋፉ ጀምር። አጼ ምንሊክ ያኔ ይናግሩ የነበሩት አዲስ አገር ልግዛ ወይም ላሰልጠን ሳይሆን ‘ያብቶቼ ግዛት የሆነውን ግዛትና ህዝብ ልመስል’  ብለው ነብር፡፤ እርግጥ ነው ግዛት መስፋፍት ተከትሎ የሚመጣ ሃብት፤ የሰው ሃይል አዲስ ምሬት እንዲሁም ጦርነት የሚያስከትለውን ሰቆቃና ጭግር እንዳለ ሁኖ።

በዚህም ሳቢያ ንጉስ ሚንሊክ ካብሮ አደጎቻቸውና ጋድኞቻቸው ከነበሩ የሸዋ ኦሮሞች ከነ ራስ ጎበና  ጋ በመሆን አገር ማስፋቱን ገፉብት።  በብልሃታቸው የሚታወቁት ንጉስ (ቦኋል ንጉሰ ነግስት አጼ ምንሊክ ዳግማዊ)  ግዛታቸውን ሲያሰፉ ሁለት መንገዶችን ይከተሉ ነበር። አንዱ ‘በሰላም ግባና ገብር’ ሲሆን  እምቢ ያለውን ደግሞ በጦር ሃይል ያስግብሩት ግዛቱንም ይወስዱብት ነበር። ይሁን እሳቸው ብቻ ሳይሆኑ ብዙ ነግስታት የተጠቀሙበትና የፈጸሙት ክስተት ነው። በዚህም መስረት ንጉስ ሚኒሊክ በምስራቅ፣ ደቡብ አና ማአክላዊ ምራብ ኢትዮጲያ ዘምተው በውድቴና ግዴታ የአሁኗን ኢትይዮጲያ መስርተዋል። ከሸዋ በስተ ሰሜን ያለውን አገር ሁሉ አፄ የሐንስ መተማ  ላይ ከዱርብሾች ጋ ሲዋጉ በማለፋቸው በወቅቱ በሃይልም በማግባባትም  መሳፍንቱን ሁሉ ማሳምን የቻሉት እሳቸው ነብሩና ንጉስ-ነግስት ተቀብለው የሁሉ ኢትዪጲያ ገዠ ሆኑ(3)።

ዳግማዊ ሚንሊክ  የያኔውው የሸዋ ንጉስ ሆንው አገር ሲያቀኑ በጦርነትም በፍቅርም ብዞዎችን አስግብትዋል። በሰላም አልገባ ካልቸው ሁሉ ጋ ጦርነት አድርግዋል። በጦርንቱም አብዝኞቹ የሸዋ ኦሮሞና አማረኛ ተናጋሪ የነበሩ ወታዳሮች ሲሆን የሚከተላቸው መሪዎችም ብዞዎቹ የሸዋ ኦሮሞዎችና የሸዋ አማርኛ ተናጋሪዎች  ነበሩ(3 4)።

መቼም ጦርንት መልካም ነገር የለውም፡፤ ብዙ የሰው ሞትና መቁሰል እንዲሁም የንብርት ዝርፊያና ጥፋት ያመጣል። በተለይ አልገብርም  ባለ መሪና ተከታዮቹ ዘንድ  ይሄ ይበርታል። የተማረኩ ወታድሮችም በጥንቱ ዘመን እንድ ባርያ ይቆጥሩም ነብር። በጨልንቆ ፣ አሩሲ   እንዲሁም በወላይታ የተደርጉ ጦርነቶች ብዙ ደም ፈሶባቸውል። ከሁለቱም ወገን።

ከነዚህ የቀድሞ ታሪካችን የምንማረው፣ ዛሬ ልንወቃቀስበትና ሌላ የቂም ጦርነት ለማድርግ የምንዘጋጅበት ሳይሆን ከአባቶቻችን የተሻለ ሰው ለመሆን ከነሱ መልካምን የምንማርበት፤ መልካም ያለነበረውን ስራቸውን  ኣውቀን  ተመሳስይ ዽርጊት እንዳይፈጸም ለማድረግ ነው። ይህን ለማድርገ ደግሞ  እውነትኛ ታሪክ ላይ ተመርኩዘን እንጂ በውሸትና በተጋነነ ሁኔታ  የሚጻፈውንና የሚሰራጨውን ታሪክ የሚባል  ልቦልድ ጭምር  ከተቀበልን አይበጀንም።

አንዳንዴ በሚያስትዛዝብ መልክ የሚነግረው የሃሰት ታሪክ ለማንም አይጠቅምም። በዚህ ላይ ደግሞ ተማርን የሚሉ ሰዎች የፕሮፓጋንዳ ፖለቲካ አለማ ለመስራት ብለው ታሪክ አጣመው፣ ትልቅ ውሸት  ሲቆልሉ አንድም ለሌላ  ጥፋት፣ ሌላውን ሰው ለማነሳሳት ሲሆን በሌላ በኩል ሲታይ  ደግሞ እነርሱንም ለትልቅ ትዘብት ይጥላቸዋል፡፤

ሚኒልክ 5  ሚሊዮን ኦሮሞ ጨረሱ የሚባለውለው የሃስት ተርት ከነዚህ  የፖልቲካ ፕሮፓጋንዳ መካከል አንዱ ነው።  ይህን ፕሮፕጋንዳ  አልጂዘራን ጨምሮ  ተስታፊ ሁነውብታል (8,9) ።  ለመሆኑ ያን የሚያክል ህዝብ የሚኒልክ ጦር የሚጨርሰው  የኒኩለር ወይም አቶሚክ ቦንብ ሲኖረው ብቻ ነው። አቶሚክ ቦንብ  ደግሞ  ለመጀምርያ ጦርነት ላይ የዋለው አሜርካኖች በጃፓን  ከተሞቸ  ሔሮሽማና ናጋሳኪ ላይ 1945 የጣሉ ግዜ ነው። ያም ሆኖ ሁለቱ ጅምላ ጨራሽ ቦንቦች  የሞቱቱ ሰዎች ቁጥር ወደ 250 ሺ  ነበር (7)።

የሚኒሊክ ጦር ሚግ 29፣ F16  ወይስ ሚራዥ ወይም ታይፉን  ጂቶች ነበሩት ወይስ ያን ያህል ህዝብ  የሚያጠፋው በምን ይሆን?   እነዚህ ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎች ሁሉ የተሰሩት ሚኒሊክ ከሞቱ ብዙ አምታት ቦኋለ ነው። ኬሚካል ጭስም እንደዚሁ።

የዛን ግዜ  ከ 6 000 ጠምንጃ ባላይ የሌላቸውን አጼ የሓንስን ለመድፈር ያልሞከሩ አጼ ሚኒሊክ  የሚኖራቸው የቀድሞ ጠብ መንጅ እጅግ ከዛ ያንሰና አውቶማቲክ እንኳ አይደለም። የዛሬው AK-47 ጠብመንጃ ከዚያን ግዜው  50  ጠምንጃ ቢደመር አይሰትካክለውም። 1870  አፄ ሚኒሊክ ያላቸውን የጥንት ቁመህ ጠብቀኝ ጠመንጃ ሁሉ ተደምሮ  3000 አይሞላም ነበር። እንዴት ተብሎ ነው 5 ሚሊዮን ህዝብ በዚያ የሚጨፈጨፈው?  ጥይቱስ ከይትኛው ፋብሪካ ነው የሚመርተው? ጦሩንስ የሚያጓጉዙብት የትኛው መርከብ አውሮፕላን እንዲሁም ከባድ ሚኪና ኖሮ ነው?

ከ30  አምታት በላይ የፈጀው የ ኢትዮጲያና ኤርትራ  ጦርነት (1961-1991) ከባድ መሳርይ፣ መድፍ፣ ታንክ ፣ ሚሳይል እንዲሁም የጦር አውሮፕላኖች ሄሊኮፕተሮች  ሁሉ ተጨምሮ  ከሁለቱም ወገን ያለውቀር ከ 255 000 በታች ነው (8) ። እንዴት ተብሎ ነው የንጉስ ሚኒሊክ ጦርነት  አብዛኛውን ግዜ ከአንደ ቀን ያነሰ በሰአታትት ጦርነት  ያን ያህል በጦርና ጎራዴ እንዲሁም ሗላ ቀር ጠምንጃ ያን ያህል ህዝብ የሚጨርሰው?

በዚያን ግዜ የነበርውን የኢትዮጲያ ህዝብ ሁሉ ቢደምር እንኳ 6 ሚሊዮን  በላይ አይሆንም (11)። ያ ጥፋት ተድርጎ ቢሆንማ እንዴት ተብሎ ባሁን ግዜ የኦሮሞ ህዝብ በቁጥሩ ከሁሉ ኢትዪጲያ ህዝብ ሊበልጥ ቻለ?

ስለ ጦርነት ክፋት ካነሳን  ዮዲት በ አክሱም ላይ ያጠፋቸው፣ ግራኝ አህመድ በክርስትይኖች ና ሰሜን ኢትዮጲያ ያጠፋው፣ እንዲሁም  በኦሮሞ ፍልስት የጠፋው ህዝብና አገር፣ በዘመን መሳፍንት ሁሉ  ጦርነት የጠፋው ሰው፣ አጼ ዮሐንስ ጎጃም ላይ የፈጸሙት  አሰቃቂ ጦርንትና  እንዲሁም የእሳት ማቃጠል  ሁሉ ወደር የማይግኝለት  ጥፋቶች ናቸው።

ከታሪካችን በመማር አሁን አለም ከደርሰበት  ስልጣኔ ና አኗኗር በመመልከት በጋራ ሊያኖርን የሚችለውን የሰው ልጅ፣ ኢትዮጲያውያን ሁሉ እኩል በህግ ፊት የሚሆነውን ስራኧት  ለመምስርት መጣር አለብን። አባቶቻችን ከፈጸሙት ስህተት ተምርን በሌላ በኩል ከቅኝ ግዠዎች አገራችንን ጠብቀው አገር ያወርሱንን አያሰብን  በተለይ አሁን የተጀምርወን የለውጥ ጉዞ እንዲሳክ ጠንክርን መስራት አለብን።

ካለፉት 50  አመታት እንኳ መማር አለብን፤ ስንት ወገኖቻቸን በህይወት የምናውቃቸው ተገደሉ፣ተሰደዱ ተፍናቀሉ። ይህ ሁኔታ አሁንም ድርስ እየቀጠለ በተለይ የሃሰት ታሪክ እይተነገረ፣  እይተጋነነ ና እይተዋሸ ስልሚቀርብ ጥልቅ ጥፋት በወገኖቻችን በአሰቃቂ ሁኔታ እየተፈጸመ  ነው።

ሓውልት መስራት ለመማርያና ተመሳሳይ ነገር እንዳይፈፀም ከሆነ መልካም ነው፤ ግን በእውነት ለይ የተመሰረተ መሆን ይኖርበታል። የሃውልት መስራት ውድድር ከሆነ ካላይ ለተጠቀሱት ሌሎችንም  ጨምሮ ብዙ ሃውልቶች በሙሉ  ኢትዮጲያ መሰራት ሊኖርበት ነው። ሃወልት መስራት ወይስ  ከድሮው ታሪካችን በሃቅ ላይ የተመሰርተ መግባብት ደርሰን የወደፊቱን ኢትዮጲያ መምስርት ይሻለናል?  ያ ነው ትልቅ ሃውልት ለሁሉም የሚበጅ።

የወያኔ አገዛዝ በተለየ ሁኔታ ላግዛዝ ያመቸው ዘንድ ያለፈውን ታሪካችንን አዛብቶ ፣ ቆርጦ, ቀጥሎ፣ ዋሽቶ እንዲሁም አጋኖ የቀረበውን በጥሬው መቀበል እንደ ገና ለሌላ  ፍጀት ነው የሚዳርገን። ይልቅስ ስላልፈው ያልኖርበትን  ግዜ ታሪክ እልህ ይዞን ስንዳክር ያሁኑንና የምንኖርበትና የወደፊቱን ለልጆቻችን የሚሆነው ግዜና አገር በመልካም መሰረት ላይ ማቆሙን ዘነጋን።

በመደበኛ እንዲሁም በሶሻል ሚዲይ ተጽኖ ፈጣሪ አክቲቭስቶች፣ እንዲህም የታሪክ ተማራማሪዎች፣ የፖለቲካ ሰዎች ፣ወጣቶች ፣ አስተማሪዎች እንዲሁም የአገር ሽማግሌዎች  በተለይም በስልጣን ላይ ያላችሁ ወገኖች፤   ይህን የሃሰትና የቅጥፍት ፕሮፓጋንዳን  በማጋልጥ በትክከለኛውን ልንማርበት በሚችል፣ ሊያግብባን በሚችል መልኩ እንዲቀርብ፤ በተለይ ባለፈ ጊዜ ሳይሆን ባሁኑና ለሚመጥው ግዜ ላይ  የተሻለ ስራ እንዲሰራ የዜግነትና የ ሰው መሆን  ሃላፊንት ና ግዴታ አለብን።

መረጃዎች

 1. http://www.ethiopianadventuretours.com/about-ethiopia/ethiopian-history.
 2. https://www.nationalgeographic.org/encyclopedia/border/
 3. አጤ ምኒሊክ  ከ ጳውሎስ ኞኞ  መጸሃፍ  1984 አ ም
 4. የኢትዮጲያ ታሪክ፣ መጸሃፍ ፤ ትርጉም አለማየው አበበ  2006 አ ም
 5. The Oromo of Ethiopia, 15001850, with special emphasis on the Gibe region. Degree: Ph.D. Date awarded: 1983. Author: Hassen, M. Supervisor(s) Oliver R. A , London
 6. https://en.wikipedia.org/wiki/Gudit
 7. https://en.wikipedia.org/wiki/Atomic_bombings_of_Hiroshima_and_Nagasaki
 8.  https://en.wikipedia.org/wiki/Eritrean_War_of_Independence
 9. https://www.aljazeera.com/indepth/opinion/2013/07/2013714133949329934.html
 10.  https://mereja.com/forum/viewtopic.php?t=68587
 11.  http://www.populstat.info/Africa/ethiopic.htm

ይቅርታ እና ይቅር ባይነት (በዲያቆን ዳንኤል ክብረት)

ዲያቆን ዳንኤል ክብረት

የመንግስት መገናኛ ብዙሃን የተለዩ አስተያየቶችን በመጠኑ ማስተናገድ መጀመር ምልክት ከሚታይባቸው መካከል አዲስ ዘመንን ያነሳሉ።ከ1933 ጀምሮ ለየዘመኑ ገዢዎች ቁጭ በል ሲሉት ቁጭ እያለ እንደ ዘመኑ እየተለዋወጠ እዚህ የደረሰው በሕዝብ ሀብት ከሚተዳደሩ የሕዝብ ያልሆነው አዲስ ዘመን ትንሽ መልኩን ቀየር ለማድረግ እየሞከረ ነው ብዙ እንደማይዘልቅ የኖረበት ልምድ ምስክር ነው። ለሁሉም የዳንኤል ክብረትን ሀሳብ ይዞ ወጥቷል። መንግስትን የሚሞግቱ አቅጣጫ የሚያሳዩ አስተያየቶችን ወደፊት በስፋት ሊስተናገዱ ይገባል። ያንብቡት ሼር ያድርጉት

ይቅርታ እና ይቅር ባይነት
April 20, 2019 21

ከሳምንት በፊት ከአንድ አንባቢያችን በኢሜይል አድራሻችን አንድ መልዕክት ደረሰን። በመልዕክቱ መሰረት በስልክ ተጨዋወትን። አንባቢያችን በመጋቤ አዕምሮ አምዳችን የምናቀርባቸው የአዕምሮ ምግቦችን በጣም እንደወደዳቸውና እርሱም በተለያዩ ጊዜያት ከተለያዩ ድረገፆች ያሰባሰባቸው የአዕምሮ ምግቦች እንዳሉት ነገረን።

ካሰ ባሰባቸው የአዕምሮ ምግቦች መካከል እርሱ ይበልጥ ከወደዳቸው ታሪኮች መካከል አንባ ቢዎቻችን እንዲማሩባቸው ያሰባቸውን የተወሰኑትን ላከልን። እኛም በአንባቢ ምርጫ ከተላኩልን የአዕምሮ ምግቦች መካከል ለዛሬ በዲያቆን ዳንኤል ክብረት በአንድ መድረክ ላይ የተነገረውን የአዕምሮ ምግብ እንዲህ አቀረብነው።

ይቅርታ እና ይቅር ባይነት መገኛው የት ይሆን?

ቂም በቀል ጊዜያዊ የሆነ እርካታን ለስጋችን ይሰጠው ይሆናል እርሱም ቢሆን ቀን አልፎ ቀን ሲተካ ይፀፀታል። ያጣሁትን መልሼ ላላገኝ ይህንን ማድረጌ ምን ጠቀመኝ? ለምንስ የሰነፎችን መንገድ ተከተልኩኝ? እያለ ራሱን መውቀሱ አይቀሬ ነው። በደልን በበደል፣ ክፋትንም በክፋት፣ ተንኮልንም በተንኮል እንሸፍናለን በሚል የዋህ አስተሳሰብ ታስረን የነገሮችን ውል ከማጥፋት ይልቅ ጥፋ ትን ተራርሞ ክፍተትን በይቅርታ መሙላቱ የታላቅነትና የአስተዋይነት ብሩሕ ምልክት ነው።

ይህ ይቅርታና ይቅር ባይነት መገኛው የት ይሆን? እንደ እኔ አመለካከት ይቅርታ እና ይቅር ባይነት ምንጩ መንፈሳዊ ሕይወት ነው። ምንም እንኳን ይቅርታ መደራረግ ለስጋዊ ኑሯችንም ታላቅ ጠቀሜታ ቢኖረውም ዋናውና ከዚህ የሚበልጠው ግን መንፈሳዊው ዋጋ ነው።

ይህንን መንፈሳዊ ዋጋ ያገኝ ዘንድ ዘወትር የሚተጋ ሰው ልቡናው ለይቅርታ የፈጠነ ነው። በዚህ ምድር በበዳዩ ከተበደለው በደል ይልቅ በሰማይ የሚያገኘው ክብር ሚዛን ይደፋለታል። እዚህ ላይ ግን ሁላችንም ልንገነዘበው የሚገባን ነገር አለ። ይቅር ባይነት ቀላል አይደለም። እንደማንኛውም ክብርን እንደሚያጎናፅፍ ተጋድሎ ሁሉ እርሱም ከፍተኛ ተጋድሎ ያሻዋል።

በአፋችን ለመናገር እንደሚቀለው ያህል ለመተግበሩ ቀላል አይደለም። ይቅር ለማለት ስናስብ ብዙ ፈተናዎች ፊታችን ይጋረጣሉ። ፈተናው ከራስ ይጀምራል የቤተሰብ ፈተናም አለው። እንዲሁም የአካባቢ ተፅዕኖም አለው።

እነዚህን ፈተናዎች በድል አድራጊነት መወጣት የሚችል ሰው ነው። ይቅር የሚለው እና ሰማያዊውን ክብር ከእግዚአብሔር ዘንድ የሚያገኘው። ቁርሾን በሆድ ይዞ ዘወትር መበላላትን፣ መጠፋፋትን እና ልኩን/ለኳን አሳያታለሁ ባይነትን የዘወትር መገለጫው የሆነውን ስጋችንን ሰማያዊውን ተስፋ አሻግራ ወደምትመልከተው ነፍሳችን ስናስገዛ መንፈሳዊነት በሕይወታችን በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ እንደተለኮሰ ሻማ ከሩቅ ያበራል።

የዚያን ጊዜ የበደሉንን አካላት መጥተው ይቅርታ እስኪሉን ሳንጠብቅ አስቀድመን ይቅርታ ይቅርታ ወይም ይቅር ባይነት የሰው ልጅ በዚህ ዓለም በሚኖርበት ወቅት በተለያዩ ማኅበራዊ ትስስሮች ወይም ግንኙነቶች አማካኝነት ከሌሎች የማኅበረሰቡ ክፍሎች ጋር ለሚኖረው ጤናማ የኑሮ ጥምረት ትልቅ ድርሻ አለው ብዬ አምናለሁ።

ይቅር መባባል ያለፈ በደልን አጥቦና አስወግዶ ለቀሪው ህይወት አዲስ ልቡናን በመፍጠር ግንኙነታችንን ወደ ተሻለ የኑሮ ምዕራፍ ያሸጋግረዋል። በአንድ ወቅት በታሪክ አጋጣሚ ተበዳድለው፣ ተቀያይመው፣ ተኮራ ርፈው ከዚያም ባለፈ ደም ተቃብተው እና ለቂም በቀል ሌት ተቀን በሃሳብም በግብርም ይሯሯጡ የነበሩ የኅብረተሰብ ክፍሎችን በልቡናቸው የተቋጠረውን የመጠፋፋት ሕልምና ዕቅድ ወደ ጎን ትተው አንዱ ካንዱ በጋብቻ እስከ መጣመርና አንዱ ላንዱ ዋስ ጠበቃ እስከመሆን ያደርሳቸዋል።

በዚሁ መልካም አጋጣሚ ምክንያትም ሊጠፋ የነበረው ሕይወት፣ ሊፈስ የነበረው ደም እናሊጎድል የነበረው አካል ከጥፋት፣ ከመፍሰስና ከመጉደል ይድናል። ከዚህም ባለፈ ቂም በቀል በይቅርታ እስካልተደመደመ ድረስ ጥፋቱ መቋጫ የለውም። አንዱ ላለፈ በደሉ አዲስ በደል ሲፈፅም ሌላኛውም አፀፋውን ሲመልስ የሁለቱም ወገኖች በምድር ላይ በሕይወት እስካሉ ድረስ መጠፋፋቱ ይቀጥላል። እንዲህ ዓይነቱ ለይቅርታ ቦታ አለመስጠት በተለይ ከሌላው ዓለም በተለየ መልኩ በእኛ በኢትዮጵያውያን ይብሳል።

ምክንያቱ ምን ይሆን? በምጣኔ ሃብት አለማደጋችን፣ በቴክኖሎጂ አለመበልፀጋችን ወይም ገና ያልደረስንበትና ያልተማርነው ዘመናዊ ትምህርት ይኖር ይሆን? ትልቁ መንስዔ ከእነዚህ ምክንያቶች መካከል እንዳልሆነ የምንገነዘበው እነዚህ ምክንያቶች ሞልተው የተትረፈረፉላቸው ወገኖቻችን ይባስ ብለው የችግሩ ሰለባ እነሱ መሆናቸው ነው።

ይቅርታና ያደግንበት ማህበረሰብ

ያደግንበት ማኅበረሰብም ሲወርድ ሲዋረድ በመጣው በአትንኩኝ ባይነትና ክንዴን ሳልንተራስ እንዴት እደፈራለሁ? አስተሳሰቡ በደንብ አድርጎ አጥምቆናል። ገና ከእናታችን ማኅፀን ከመውጣታችንም ደም መላሽ ብሎ ስም ያወጣልናል።

አንደበታችን እማማ አባባ ማለት ሳይጀምር በቂም በቀል ዲፕሎማ ከቤተሰባችን እና ከአካባቢያችን በከፍተኛ ማዕረግ እንመረቃለን። ከዚያ በኋላ ልክ ግብፃውያን እናቶች ልጆቻቸውን አባይ ሕይወትህ ነው እያሉ እንደሚያሳድጉት ሁሉ ለእኛም የስማችንን ትርጓሜ ከወደፊቱ ሥራችን ዕቅድ ጋር እየተነገረን እናድጋለን።

ከዚህም በተጨማሪ ሕዝብን እናዝናና በታለን በሚል ሽፋን የሚወጡ ዘፈኖችም የራሳቸው ተፅዕኖ አላቸው። የአንድን ግለሰብ አስተሳሰብ ለመግለፅ እንዲሁም ለግጥሙ ቤት መድፋት እንጂ ጭብጡ በማኅበረሰቡ ላይ የሚያመጣውን አሉታዊ ተፅዕኖ ባለማስተዋል የሚዘፈኑ ዘፈኖች አሉ።

«ተበድዬስ ይቅርታ አልልም የቀረው ይቅር እንጂ» የሚል ዘፈን ሲያዳምጥና አብሮ ሲያንጎራጉር ያደገ ሰው ለይቅርታ ያለው ቦታ ቢያንስ ኸረ እስከ ጭራሹም ባይኖረውምን ይደንቃል? ሁላችንም እንደምናስታውሰው በጀግኖች አባቶቻችን ቆራጥ ተጋዳይነት ለጥቁር ሕዝብ ሁሉ የሚተርፍ የነፃነት ፋና በዓድዋ ተራሮች ተንቦግቡጎ ባልጠበቀውና ባላሰበው መልኩ ድል የተደረገው የኢጣልያ መንግሥት ይህንን በዓለም አቀፍ አደባባይ የውርደት ሸማ ያለበሰውን የኢትዮጵያውያን ተጋድሎ ቂም ለመወጣት በተጠቀመው የመርዝ ጋዝ እጅግ ብዙ ወገኖቻችን በመሪር ስቃይ አልፈዋል።

እስቲ እነዚህን የነፃነታችን አምድና ለዛሬው እኛነታችን የሕይወትን መስዋዕትነት ከፍለው ስማቸውን በልባችን ፅላት ላይ በወርቅ ማኅተም ያተሙትን ወገኖቻችንን አንድ ጊዜ ቆም ብለን እናስባቸው። በዚያን ጊዜ እንደዚያ ያለውን የጭካኔ ርምጃ እንዲወሰድ ያዘዘውን አካል ብናገኘውና ከእግዚአብሔር ዘንድ የሚያገኘው።

ቁርሾን በሆድ ይዞ ዘወትር መበላላትን፣ መጠፋፋትን እና ልኩን/ለኳን አሳያታለሁ ባይነትን የዘወትር መገለጫው የሆነውን ስጋችንን ሰማያዊውን ተስፋ አሻግራ ለምትመለከተው ነፍሳችን ስናስገዛ መንፈሳዊነት በሕይወታችን በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ እንደተለኮሰ ሻማ ከሩቅ ያበራል።

የዚያን ጊዜ የበደሉንን አካላት መጥተው ይቅርታ እስኪሉን ሳንጠብቅ አስቀድመን ይቅርታን እናደርግላቸዋለን። የሰማያዊው ክብር ባለቤቶች መሆናችንን እናውቃለንና ይቅርታውን ባደረግን ወቅት ከመቼውም ይበልጥ ውስጣችን በሐሴት ይሞላል። የሰላም እንቅልፍም እንተኛለን።

አዲስ ዘመን ቅዳሜ ሚያዝያ 12/2011

በዲያቆን ዳንኤል ክብረት

አንድ ሀገር! አንድ ሕዝብ! ኢትዮጵያችን ሕዝባዊ ንቅናቄ (ኢትዮጵያችን) – (ልሳን ኢትዮጵያችን ቅጽ 3 ቁጥር 5)
ሚያዝያ 05 ቀን 2011 ዓ.ም.

ኢሕአዴግና ደጋፊዎቹ የ“ለውጥ” እንቅፋቶች

የድምጽ ቅጂውን ለማድመጥ እዚህ ይጫኑ https://www.youtube.com/watch?v=oRK2p86xt7c

ኢትዮጵያችን እንደ ሀገር ለመኖሯ ጥርጥር የለንም። ትላንትም ዛሬም ነገም ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኖራለች! ይህ ለኢትዮጵያ እንደ ሀገር የህልውናዋ ጉዳይ በበርካታ ሕይወት የተገነባ ነው። ለሀገራችን ልምላሜ ፣ ለዘላለም ሀገር ሆና እንድትኖር የጀግኖች ልጆቿ አጥንትና ደም የዘላለም ሕይወት ሆኗታል ወደፊትም ይሆናታል። በትንሹ የሦስት ሺህ ዘመን ታሪክ ያላት ሀገራችን ወቅትን እየጠበቀ የተፈታተናት የባዕድ ወራሪ በርካታ ልጆቿን ቢነጥቃትም ኢትዮጵያዊ ሀገርነቷን አላጣችም። በነገሥታት ዝና እና የይገባኛል ውጥረት ያሳደገቻቸውን ልጆቿን አጥታለች።  በዘመነ መሳፍንት ሹኩቻ ሁሉም ልንገሥ ባይ የቀሰቀሰው የእርስ በርስ ግጭት ያተረፈው ቢኖር ክቡር ሕይወትን መገበር ነበር። ኢትዮጵያ አንድነቷን አጠናክራ በአንድ ማዕከላዊ አስተዳደር ትተዳደር ዘንድ የተከፈለው መስዋዕትነት ቀላል አልነበረም። በተለይ ከዓፄ ቴዎድሮስ አገዛዝ ወዲህ ሀገራችን እንደገና በአንድ ማዕከላዊ መንግሥት ብትተዳደርም የእርስ በእርስ ፍትጊያውም ጋብ አላለም፤ የባዕዳን ትኩረትም አልቀነሰም። ምስጋና ይግባቸውና ለጀግኖች ልጆቿ ዛሬ አርበኞች ለምንላቸው “ለሀገር መሞት ኩራት” ብለው እኛ እንድንኖር ሞተውልናል። አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ ዓላማችን ዘላለማዊ መለያችን ይሆን ዘንድ የነፃነት ተምሳሌት አድርገውታል። ዓፄ ቴዎድሮስ በመቅደላ፣ ዓፄ ዮሐንስ በመተማ ሰንደቅ ዓላማችንን በአጽማቸው አውለውልበዋል። አሉላ አባ ነጋ በዶጋሌ ሰንደቅ ዓላማችን ለዘላለም ይውለበለብ ዘንድ ታሪክ ሰርተዋል። ምኒልክ በዐድዋ በሰንደቅ ዓላማችን ወራሪ ጣልያንን ድባቅ መምታት ብቻ ሳይሆን የነፃነት ተምሳሌት፤ የአፍሪካ ኩራት አድርገውታል። በአምስቱ ዓመት የጣሊያን ወረራ አርበኞቻችን በሰንደቅ ዓላማችን አዋጊነት ቅኝ አገዛዝን ከሀገራችን ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ አርኣያ፣ ተምሳሌት ለነፃነት ይሆን ዘንድ ሕይወት ከፍለውበታል። “ጀግንነት እንደ ኢትዮጵያ!” ብለው የአፍሪካ ሀገሮች ለነፃነት ክብራቸው የእኛን፣ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ በተለያየ አቀማመጥ አውለብልበው ዘምረዋል። ታሪክ ስንል ትንሽ እውቀት ያለው ዜጋ ይህንን ይገነዘባል። እንጻፍ ብንል የማያልቅ፣ የማያሳፍር፣ ተዓምር የሚያሰኝ ሳይሆን የሆነ ታሪክ አለን። ዓለምና የወረሩን እንኳ ሳይቀሩ እንደ ሀገር ስለ ኢትዮጵያዊነታችንና ስለ ክብራችን፣ ኩራታችን፣ ጀግንነታችን መስክረውልናል።

ኢትዮጵያ ማንም ቅኝ ገዥና ወራሪ ጠፍጥፎ ያልሰራት በመሆኗ ልንኮራ ይገባናል። ኢትዮጵያችን ቅኝ ገዥዎች ሊተክሉባት በአቀዱት ሃይማኖት እጇን ያልሰጠች፣ ለባዕድ ቋንቋ ያልተገዛች የራሷ ቋንቋ ባለቤት እና ሆሄያት ያላት ብቸኛ አፍሪካዊ ሀገር በመሆኗ እንኮራለን። ኢትዮጵያ እስልምና ሃይማኖትን ተቀብላና አማኙንም አክብራ በአንድ ቤት ከክርስትና እምነት ጋር አስተቃቅፋና አቅፋ በኖረች ሀገራችን እንኮራለን። ኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ የሰው ልጅ መገኛ ታሪካዊ የድንቅነሽ/ሉሲ እናት መሆኗ ያኮራናል። የታሪካዊ ቅርሶች አክሱም፣ ላሊበላ፣ ፋሲለደስ፣ ሐረር ግምብ ወዘተ. ተጠሪ በመሆናችን እንኮራለን። ኢትዮጵያ በረሃን መጋቢ፤ ምድረበዳን ሀገር ያደረገች የዐባይ ባለቤት መሆኗ ያኮራናል። ኢትዮጵያ ብቸኛዋ የዋልያ/ኒያላ፣ ጭላዳ ዥንዠሮ ዋሻ በመሆኗ እንኮራለን። ኢትዮጵያ ከሰማንያ የማያንሱ የቋንቋ ባለቤትና የጎሳ/ነገዶች እናት በመሆኗ ኑሪልን፣ ክበሪልን እንላለን። የ13 ወር ፀጋ፣ የራሳችን የወራትና ባህላት አቆጣጠር ያለን ብቸኛ የጳጉሜን ባለቤት የመሆናችን ምስጢር ያኮራናል። የትግሬ ጭፈራ፣ የጎጃም እስክስታ፣ የጎንደር አዝማሪ፣ የወሎዬ ከምከም፣ የኦሮሞ ረገዳ፣ የጋምቤላ እምቢልታ፣ የሲዳማ ወላይታ፣ የጉራጌ አሽቃሮ፣ የእስላም ዝያራ፣ የክርስቲያን ሽብሸባ ወዘተ. አድማቂ ባህል ባለቤት ኢትዮጵያችን ታኮራናለች። የገና ጀምበር ቢባልም ቀንና ምሽቱ ያልተዘበራረቀ እኩል አመቻችቶ ለተቸራት ሀገራችን እንኮራለን። መጤነታችን ኢትዮጵያ፣ እድገታችን ኢትዮጵያ፣ ሕይወታችን ኢትዮጵያ፣ ፈጣሪያችን ኢትዮጵያ፣ ሞታችን ኢትዮጵያ በመሆኗ ክብር ይሰማናል።

አዎ! ስለ ሀገራችን ውብነት እንተርክ ካልን “መኃልዬ ዘማህሌት ኢትዮጵያ” ለእኛ ብቻ ሳይሆን ለዓለምም ከነድህነቷ ውብ ናት። እኛ ሀገር ስንል ከቃላት በላይ እየገለጽናት ነው። እናታችን ናትና ችግራችን ችግሯ፣ ረሃባችን ረሃቧ፣ ልቅሷችን ልቅሶዋ፣ ደስታችን ደስታዋ፣ ሀዘናችን ሀዘኗ መሆኑን በመገንዘብ ነው።

ሀገራችን ኢትዮጵያን ዛሬ ለደረስንበት ያደረሳት በተለይ በአለፉት 50 ዓመታት በገጠሟት ብልሹ አገዛዞች ምክንያት ከዓለም የሥልጣኔና ዕድገት ደረጃ መራመድ አለመቻሏ ነው። በነፃነቷ ያልተደፈረች አፍሪካዊ ሀገር እንደመሆኗ ተፈጥሮ የሰጣትን ሀብት ተጠቅማ ልጆቿን መመገብ አለመቻሏ፤ የእናታችን አለማዘን ሳይሆን ቀፍድደው የያዟት፣ በሀገር ስም የተስገበገቡባት፣ በሀገር ስም ትውልድ የፈጀባት አገዛዞች ኢዴሞክራሲያዊ አካሄድ ያመጣባት ጣጣ ነው። ሲባባስም ሀገር ከሀዲ በዘርና በቋንቋ ከፋፍሎ ለአለፉት 28 ዓመታት ቀፍድዶ መያዝ ብቻ ሳይሆን ሊበጣጥሳት ከአራቱም ማዕዘን እየወጠራት ይገኛል። በብሉሹ አስተዳደር ሥር በመውደቋ ክብሯን ረሃብ፣ ችግር፣ ጉስቁልና፣ ስደት ደፍሯታል። አገዛዞች በተቀያየሩ ቁጥር እድገቷ እስር ቤቶች ሁነዋል። ማንኛውም አገዛዝ ሊመለከተውና ትኩረት ሊሰጠው ያልቻለው የሕዝብ መባዛት፣ መዋለድ እጅጉን እያሻቀበ ዛሬ በመቶ ሚልዮን የሚቆጠር ሕዝብ አቅፋለች። የብልሹ አገዛዝ ያመጣብንን ድህነት፣ ኋላ ቀርነት፣ ድንቁርና፣ በሽታ ተገን በማድረግ የአንድ ዘር የበላይነት እንደነበርና ሀገር እንዳስተዳደረ ዘረኝነትን መለዮው አድርጎ 28 ዓመት የገዛው ኢሕአዴግ በረቀቀ ዘዴ ሀገራችንን ከአስከፊ የእርስ በርስ ግጭት ሊከታት እየተንደረደረ ነው።

ሀገራችን ኢትዮጵያን በአንድነቷና በክብሯ የቀኑባት ከጥንት እስከዛሬ አላረፉላትም። የኦርቶዶክስ እምነቷን ለማጥፋትና ለማሽመሽመድ ባዕዳን ኃይሎች ሀገር በቀል ከሀዲዎችን በእጅ አዙር በመግዛት በግራኝ አሕመድ፣ በዮዲት ጉዲት ዘመን ቢጥሩም በርካታ አብያተ ክርስቲያናትን ከማቃጠልና ከመዝረፍ ባሻገር በተከፈለ ከባድ መስዋዕትነት ሃይማኖቷን አስጠብቃና ድል መትታ ዛሬም አለች፤ ነገም አልፋ ኦሜጋ ትኖራለች።  የድርቡሾች ጥቃት፣ የእንግሊዞች ዝርፊያ፣ የጣሊያን ወረራ በርካታ ቅርሶቻችን እንዲወድሙና እንዲዘረፉ ምክንያት ቢሆኑም ሀገራችን ግና ቀጥላለች። ጥንትም፣ አሁንም፣ ወደፊትም ኢትዮጵያ ነች።

በሀገራችን ታሪክ ግራኝ አሕመድ ለ16 ዓመት፣ ዮዲት ጉዲት ለ40 ዓመት ወያኔ/ኢሕአዴግ ለ28 ዓመት አማራንና ኦርቶዶክስ እምነትን ለማጥፋት ጥረዋል። አልተሳካላቸውም። 28 ዓመት የገዛው ህወሓት/ኢሕአዴግ እራሱ አውጥቶ፣ እራሱ አጽድቆ ሀገርና ሕዝብ ላይ በከመረው ሕገ መንግስት ዛሬ ሀገር ልትበተን፣ ሕዝብን እርስ በእርስ ሊያባላ የጫረው እሳት አድራጊዎችን እንደሚፈጅ በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል። ጥፋት ቢኖርም ኢትዮጵያችን ትኖራለች። ዛሬ በመንግሥት ደረጃና በአንዳንድ የዘር ድርጅቶችና በኢሕአዴግ አገዛዝ የጥቅም ተካፋዮች ተግባር ላይ ሊውል ተቀጣጣይ ፈንጂ የሆነው ሕገ መንግሥት አንቀጽ 39 እና 47 ላይ ተደርሷል። ኢትዮጵያን የመበታተን ፈንጂው የተቀበረባቸው እነኚህ አንቀጾችን ተግባራዊ ለማድረግ “ጊዜው ዛሬ ነው” ብለው ለተነሱ ኃይሎች በሀገራችን ላይ ጉዳት ቢያደርሱም የመጨረሻው ተሸናፊዎች እንደሚሆኑ አንጠራጠርም። ዘርንና/የቋንቋ ተገን ያደረገ የግዛት አከላለል፤ ተዋዶና ተከባብሮ የኖረን ሕዝብ መከፋፈል፤ ከአቀንቃኝ ድርጅቶች፣ አክቲቪስቶችና ዘላለማቸውን ለመጣው ሁሉ አሸርጋጅ ምዑራን በቀር በየትኛውም ዘር ኅብረተሰብ ዘንድ ተቀባይነት የማይኖረው ውሃ በወንፊት ሩጫ ነው።

በኢሕአዴግ አገዛዝ ዘመን ለሥራ ዋስትናና ለሌላ ጥቅማ ጥቅም አገዛዙን ደግፋችሁ ላላችሁና ዛሬም ኢትዮጵያዊነት ዝማሬ ላስበረገጋችሁ መስመራችሁ ከሀገርና ሕዝብ ጎራ ይሆን ዘንድ ምክራችንን እንለግሳለን።  ለአለፉት 50 ዓመታት የአምባገነኖችና የዘራፊዎች በትር ዘር ሳይመርጥ ሁሉም ላይ ያረፈ የመሆኑ ሀቅ እየታወቀ ሀገር እንደበደለች ታሪክ ሲፈጠር መስማቱ ማብቃት ይኖርበታል። ኢትዮጵያ ክብሯንና ማንነቷን ጠብቃ ትኖር ዘንድ ወደድንም ጠላን ዘርንና ቋንቋን ተገን ያደረገ አከላለል ማብቃት ይኖርበታል። ዘርንና ቋንቋን፣ ሃይማኖትን፣ ፆታን ተገን አድርጎ የሚፈጠር የፖለቲካ ድርጅት ማብቃት ማለት የኢትዮጵያን አንድነት ማስጠበቅ መሆኑን አጥብቀን እናስቀምጣለን። የጎሳዎችንና የነገዶችን መብት ማወቅ ማለት ተካሎና መስመር አስምሮ አትድረሱብኝ የማይሰራ ቅዠት ነው። የዴሞክራሲ መብት ሀገር ለመገነጣጠል፣ አንድ ጎሳ/ነገድ በሌላ ላይ ለማነሳሳት ሊሆን አይገባውም። ይህ እንዲያበቃ “ሀገር የመገነጣጠል” ቁልፉ ኢሕአዴግና ሕገ መንግሥቱ ላይ በመሆኑ ሁለቱም ማብቃት እንዳለባቸው አጠንክረን ስንታገል ኦሮሞ፣ አማራ፣ ትግሬ፣ ጉራጌ፣ ወላይታ፣ ጋምቤላ፣ አፋር፣ ኦጋዴን፣ ሐደሬ፣ ሲዳማ፣ አኝዋክ፣ ሌላም ሌላ ችግር የለባቸውምና ከድሮው በበለጠ የዜግነት መብታቸውን አስከብረው እንደሚነሱ አንጠራጠርም።ችግራቸው የዜግነት መብታቸውን አግኝንተው፣ ጎሳና ነገድ ሳይመርጡ በመረጡት ተመርተው፣ ወሰን ሳይገድባቸው የትም ሠርተው፣ የትም ተምረው፣ የትም ኑረው፣ አንድ ሰንደቅ ዓላማ አውለብልበው፣ ስለ አንድ ሀገር ዘምረው የኢትዮጵያን ትንሳዬ የሚያዩበትን እንጂ የናፈቁት፤ “አውቅልሃለው፣ ወክዬሃለሁ” ባይ ሀገር ተረት ለሆነችባቸው ፖለቲከኞችን አይደለም።

በመገነጣጠል አባዜ በቅዠት ለተዋጡ “ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር” ስንል ጉዟችን ኦሮሞን፣ ትግራይን፣ አማራን እና ሁሉንም የተለያዩ ጎሳና ነገዶች ይዘን እንደሆነ ሊሰመርበት ይገባል። የመጨረሻ ግቡ ኢትዮጵያን ለመበተን ካልሆነ በቀር ኦሮሚያ መንግሥት ሊሆን አይችልም። ትግራይ በህወሓት/ወያኔ ቁጥጥር ሥር ተገንጥላ አትኖርም። የምሥራቅ ኢትዮጵያ ሶማሌ ወገኖቻችን ከኢትዮጵያ ሊለዩ አይታሰብም። ደቡብ ኢትዮጵያውያን፣ ጋምቤላ፣ አፋር ዛሬም ለኢትዮጵያ ዘብ ቋሚዎች ናቸው።  ለዚህም ነው የመገነጣጠል አባዜ ውድቀቱና ጉዳቱ ለሁሉም እንደሚሆንና ማንም ሳያሸንፍ መልሳ ኢትዮጵያ አንድ ሀገር! ሆና እንደምትቀጥል ትንቢት ሳይሆን ሀቅ ነው። ድህነቷ ጠንካራ መሠረቷን አላሳጣትምና።

የአረቃቀቁ ታሪክ አድሎዓዊ፣ አጨቃጫቂና አስቀድሞ በታቀደ ተግባር ስለሆነ የኢሕአዴግ ሕገ መንግሥት ከፀደቀበት ወቅት አንስቶ ለትልልቅ ብሔራዊ ችግሮች መፈጠርና መባባስ ዋነኛው ምክንያት ሆኗል። ይህንን ሕገ መንግሥት መሠረት አድርገው ሥራ ላይ ከዋሉት ዕቅዶች በቁጥር አንደኛው  ዘርንና ቋንቋን መሠረት ያደረገው የፌደራል ሥርዓት ተብዬው ነው።

እንደ ተመሠረተበት ሕገ መንግሥት ሁሉ የፌደራል ሥርዓቱም ከወላጁ ይህንኑ አጨቃጫቂና አድሎአዊ ባህርይ ወርሷል። የኢሕአዴግ ፌደራል ሥርዓት ተብዬው እነዚህ የሕገ መንግሥቱ አስከፊ ገፅታዎች በተግባር በመሬትና በሕዝብ ላይ በሥራ ስለሚተረጎም የሚያደርሳቸው ጥፋቶች ጥልቀትና ስፋት በወረቀት ከሰፈረው ሕገ መንግስት በብዙ እጅ የከፋ ነው።

ዘርንና ቋንቋን ተገን ያደረገው ፌደራል ክልሎችና እነዚህን የሚያስተዳድሩት መንግሥታት ለአለፉት ሁለት አሥርተ ዓመታት በላይ ህወሓት መር የነበረው የፌደራል ሥርዓት ዓይነተኛው መገለጫ  ናቸው። እነዚህ የፌደራል ክልሎች የተመሠረቱት ወይም በተገቢው አነጋገር ኢትዮጵያን የሸነሽኑት ከብዙ ዓመታት ቀደም ብሎ በረሃ በታቀዱ ለም መሬት የመያዝ ውጥኖች፣ በመናኛ የ“ታሪክ” ማስረጃዎች፣ ቋንቋዬ የተነገረበት ሁሉ የክልሌ አካል ነው ወዘተ. በሚሉ አደናጋሪ ምክንያቶች ነበር።

እነዚህ ክልሎች የተመሰረቱባቸው ምክንያቶችና የተካሄደው ሽንሸና፡ በሕገ መንግሥቱ የተቀመጡት አንቀጾች በሥራ ላይ መዋል ጋር እየተዳመረ በጥቂት ጊዜያት ውስጥ ችግሮች ይከሰቱ ጀመር። ከክልሌ ውጣ፡ “ማንነቴ” ይከበር፣ ቋንቋዬ ይከበር፣ የራሴ ክልል ልሁን ወዘተ የሚሉ ለመፍትሔ ቀርቶ ለማስተናገድም፣ ለማጥናትም የሚያውኩ ጉዳዮች በየክልሎቹ ይነሱ ጀመር፡ አሁንም እየተንሱ ነው።

እነዚህ ከውሽልሽሉ ሕገ መንግሥት አረቃቀና ከእሱው የእንግዴ ልጅ የፌደራል ሥርዓቱ አመሠራረት የፈለቁት አይቀሬና በተፈጠሩበት አሠራር መላ የማይገኝላቸው ችግሮች የሕዝብ ሰላም ከማደፍረስና ውጥረት ከማንገስ አልፈው ወደ ጎሳ/ዘር ግጭቶች፣ በሺዎች፣ በአሥር ሺዎችና በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የማህረሰብ አባላት መፈናቅልና የንብረትና ሕይወት መጥፋት ዳፋ ሆኑ። እየሆኑም ነው። ይኸው የሀገር ውስጥ መፈናቀል በአሁኑ ወቅት ከ 3 ሚሊዮን የሚበልጡ ዜጎችን ሰለባ አድርጓል። ቋንቋንና ዘርን ያማከለው ፌደራል ክልላዊ ሥርዓት ሲጸንስም፣ ሲወለድም፣ ሲድህም፣ ጥርስ ሲያወጣም፣ ወፌ ቆመችሲባልም እንደጥላ የተከተለው በሰላም ይኖሩ በነበሩ ጎሳዎች/ነገዶች መሃል መፈራራት፣ መጠራጠር፣ ስጋት፣ ግጭትናመፈናቅል ነው። በድሃ ሀገራችንና ሕዝብ ላይ ይህንን ችግር ጨምሮላታል። የፌደራል ክልል ሥርዓቱ ከሃያ ስምንት ዓመት ዕድሜው በኋላ መገለጫው ወይም አሻራው ይኸው በየክልሉ ውስጥ እርስ በእራስ፣ በክልልና-ክልል መሃል ባሉ ጎሳዎች/ነገዶች መሃል መቃቃርና በሰላም ተረጋግቶ አለመኖር በተጨማሪ የወሰን ነጠቃም አይዘነጋም። ሰሞኑንም አድማሱን አስፍቶ የተወሰኑ ዘሮች በተለይ አማራው፣ ጉራጌው  ላይ ያነጣጠረ የጅምላ ጭፍጨፋ፣ ንብረት ማውደም፣ ሴቶችን መድፈር የመጨረሻው መጀመሪያው በሰሜን ሸዋ የተለያዩ ወረዳዎች ተጀምሯል።

በአጭሩ ሕገ መንግሥቱ፡ ፌደራል የክልል ሥርዓትን አስከተለ፡  የፌደራል የክልል ሥርዓት ደግሞ በበኩሉ በሕዝብ  መሃል መፈራርትና መፈናቀልን አመጣ። ይህ ጉዳዩ በተለይ በአሁኑ “የለውጥ” ጊዜ በኢትዮጵያችን ላይ እያደረሰ ካለው ከፍተኛ የሰላምና የፀጥታ ስጋት ምክንያት ዘላቂ ፈውስ እስኪገኝለት ማስታገሻ መፍትሔ እንደሚያስፈልገው ግልፅ ነው። ነገር ግን ከላይ በአጭሩ እንዳየነው በህወሓት መሩ ኢሕአዴግ በሥራ ላይ የዋለው ሕገ መንግሥትና መዘዙ የሆነው የፌደራል ሥርዓት ያደረሰውና እያደረሰ ያለው ችግር “የማይታያቸው” እና ምንም ዓይነት መፍትሔ ቀርቶ መሻሻልም አያስፈልግወም የሚሉ አክራሪ ሃይሎች አሉ።

የፓርቲና የመንግሥት መዋቅር

የኢሕአዴግ አገዛዝ ዓይነተኛ መገለጫው የፓርቲና የመንግሥት ድንበር አለመለየቱ ነው። ከመንግሥት ከፍተኛ የበላይ አመራር ጀምሮ እስከታች በወረደው የዕዝ ሰንሰለት ማለትም ከምኒስትሮች እስከ ዝቅተኛ እርከን ባለው የመንግሥት መዋቅር ያሉ መንግሥተኞች በአብዛኛው የኢሕአዴግም አባላት ናቸው። ስለሆነም በፓርቲና በመንግሥት መሃል የሚኖረው ግንኙነት ተምታቶ የፓርቲ የፖለቲካ ሥራና የመንግሥት የሕዝብ አገልግሎት ተግባራት በአብዛኛው በተለይ በክልል መንግሥታት ውስጥ ልዩነት አይታይባቸውም። በተጨማሪም የመንግሥት ሠራተኞች የኢሕአዴግ ፓርቲ አባላት የሆኑት በሚሰሩበት መደበኛ ሥራ ላይ እያሉ ነው። በሀገራችን በተለይ ሥልጣን በያዘ ፓርቲ ውስጥ በአባልነት የሚገባው በአብዛኛው የመንግሥት ዝቅተኛና መካከለኛ እርከን ሠራተኞች ለሕዝብና ሀገር አገልግሎት ሳይሆን የሥራ ዋስትናና ዕድገት ይገኝበታል በሚል እሳቤ ነው።

በተጨማሪም የኢሕአዴግ ፓርቲ አባልነትና ደጋፊነት የሚያስገኘው ዘርፈ ብዙ ጥቅም ለመንግሥት ሠራተኞች ብቻ ተወስኖ አልቀረም። ተማሪዎችና ወጣቶች የሥራ ዕድል ለማግኘት፣ በአነስተኛ ንግድ ለመቋቋምና የመነሻ ብድር ለማግኘት፣ ነጋዴዎች ከሚደርስባቸው የግብርና የተለያዩ ተፅዕኖዎች ከለላ ለማግኘት፣ ሌሎችም የሕብረተስብ ክፍሎች ኑሮን ለማቃናት ወዘተ ሲሉ የፓርቲው አባላትና ደጋፊዎች ሆነዋል። “ወይን ለኑሮ” በሠፊው ሲባል የነበረው ይህንን ቁልጭ አድርጎ ይገልፀዋል። የፖለቲካ እምነት ወይም ሕዝብ ለማገልገል ሳይሆን ኑሮን ለማሳካት ዋስትናና የጥቅም ተጋሪ ለመሆን ሲባል ብዙዎች ፓርቲውን ተቀላቅለዋል። በአንድ ወቅት በኢሕአዴግ ራሱ እንደተገለፀው 4.5 ሚሊዮን ያህል አባላት አሉት።

ይህ የፓርቲ አባላት 4.5 ሚሊዮን አሃዝ ማለት ከ100 ሚሊዮን ሕዝብ ከአምስቱ ኣንዱ የኢሕአዴግ ሰው ነው ማለት ነው። ከዚህ የአባላት ቁጥር ጋር በገንዘብም የሚረዱትን፣ በተስፈኝነት የሚደግፉትንና ከላይ እንደተገለፀው ለኑሮም፣ ለንግድም፣ ለሥራ ዋስትናም ሲባል በኢሕአዴግ እረጅም እጅና መረብ የተያዙት ዜጎች ቁጥር ከፍተኛ ነው። ይህ የሚያሳየው “ኢሕአዴግ”ነት ባለፉት 28 ዓመታት ውስጥ የኑሮ ዘይቤ እየሆነ መምጣቱን ነው። ይህ ጤናማ ያልሆነ ማህበረሰባዊ ግብረገብነት የሌለው ኑሮን ለማሳካትና ጥቅም ለማግኘት የሚደረግ አባልነት እና ደጋፊነት አደገኝነቱና ደንቃራነቱ የሚወጣው አሁን ኢትዮጵያችን እንደምትገኝበት ዓይነት የጥገና ለውጥ ጊዜ ውስጥ ነው። ኢሕአዴግ እንደ ፖለቲካ ፓርቲ፣ እንደ መንግሥት ባላቤትነቱ ማሕበራዊ ግብረገብነትን ከማስጠበቅና ዜጎች ኑሯቸውን ከመንግሥትና ፖለቲካ ነፃ ሆነው በሃቀኝነትና በቀጥተኛነት መኖርን አርኣያም፣ አስተማሪም መሆን ሲገባው ድርጊቶቹና የፖሊሲ አፈጻጸሞቹ ሁሉ የዚህ ቀጥተኛ ተቃራኒ ናቸው። አባላትና ደጋፊዎቹም እንደዛው።

ሥራውን፣ ንግዱን፣ ጥቅሙን ወዘተ በአጠቃላይ ኑሮውን ከኢሕአዴግ በሥልጣን መቆየት ጋር ያቆራኘው አባልና ደጋፊ ሁኔታዎች ሲቀየሩ መስጋቱና ለተቃውሞ መነሳቱ የሚገርም አይደለም – የሥራ፣ የንግድ የጥቅምና የኑሮ ዋስትናው ከገዢው የኢሕአዴግ ሥልጣን ጋር ስለተሳሰረ! ይህ የጥገና ለውጥ ስጋትና ተቃውሞ ይበልጥ ተጠናክሮ የሚታየውና ለሀገርና ሕዝብ አደገኛ ችግር የሚሆነው በከፍተኛ የመንግሥትና የኢሕአዴግ የፖለቲካ ሹመኞች ሲካሄድ ነው። እነዚህ ኀይሎች ካላቸው የፓርቲና የመንግሥት የሥልጣን እርከን፣ በሚያዙት የድርጅትና የፓርቲ መዋቅርና የዕዝ ሰንሰለት፣ ማሕበረሰባዊ መረብና ግንኙነት በሌሎች በበርካታ መንገዶች ለውጥን የማደናቀፍና የመቅልበስ ፍላጎታቸው ይስተዋላል። ዋና ዋናዎቹን ለማቅረብ፡-

 1. ክልል መስተዳድሮች

የክልል መስተዳድሮች አብዛኛዎቹ ለይስሙላ በሚደረገው ምርጫና የሕዝብ ድጋፍና ተቀባይነት አግኝተው ሳይሆን በቀጥተኛ የፓርቲና የመንግሥት አካላት የተመረጡ የፖለቲካ ሹመኞች ናቸው። በአውራጃ፣ ወረዳ፣ ዞንና ክልል፣ ፌደራል ምክር ቤት ወዘተ የሚመደቡት ለኢሕአዴግ ባላቸው ታማኝነት ነው። ሟቹ ጠቅላይ ሚ/ር በፓርላማ እንደተናገሩት “ለኢሕአዴግ ታማኝ ከሆነ ማንንም እንሾማለን” ማለት ሁኔታውን ግልፅ ያደርገዋል። ሁለት ጉዳዮች የዚህ የኢሕአዴጋዊ ስንኩል አሠራርና አስተሳሰብ ቀጥተኛ መዘዝ ናቸው። አንደኛው በሃላፊነት ቦታ ላይ የሚታጩትም ሆነ የሚቀመጡት ሰዎች ለሥራው የሚያስፈልግ የትምህርት ልምድ፣ ባህርይና ሥነምግባር ለመመዘኛነት አለመዋሉ ነው። ይህም ሰዎቹን በሥራና ሃላፊነታቸው ብቁነትና መተማመን የሌላቸውና የተቀባይነት ችግር የሌላቸው ይሆናል። ለነገሩ ይህ የተቀባይነት ችግር ከፍተኛ የኢሕአዴግ መንግሥትና ፓርቲ ባለሥልጣናትም ያለባቸው ሲሆን በዚህም ምክንያት መንግሥት ራሱ የዚህ ሰለባ ነው። ሁለተኛው ደግሞ በሁሉም በተለይ ግን “ጥቅም” ገንዘብና ምቾት ያስገኛሉ በሚባሉ ነገር ግን ብዙ የትምህርትና የሥራ ልምድና ሌሎችም አስፈላጊ ብቃቶች በሚጠይቁ ቦታዎች ሳይቀር የማይመጥኑ ሰዎች ሲመረጡ በዕውቀት ሥራውን ማስኬድ የሚችሉት ይታለፋሉ። ይህ ሞራል ይነካል፣ አገልግሎትና  ሥራ ይበድላል፣ ችሎታው ያላቸው መገለልና ወደ ግል ሥራ ወይም ወደ ውጪ እንዲመለከቱ ያደርጋል።

እንግዲህ በክልል የሥልጣን እርከኖች ከላይ እስከታች የተሰገሰጉት “በኢሕአዴጋዊ ታማኝነት” የተመረጡ፣ ያለአንዳች ማመንታትና መጠየቅ የተነገራቸውን የሚፈፅሙ የፓርቲ “ሎሌዎች” ናቸው። ከዚህ አልፎ ግን ሊሠመርበት የሚገባው ጉዳይ እነዚህ ሰዎች ሥልጣናቸው ብቻ ሳይሆን ጠቅላላ ሕልውናቸው ከኢሕአዴግ ሥልጣን ላይ መቆየት ጋር የተቆራኘ ነው። የሚይዙት መኪና፣ የሚያገኙት የገንዘብ ገቢ፣ በንግድ፣ በመሬት ይዞታ በሌላውም ማሕበረሰባዊ ኑሮ ዘርፍ ያላቸውን ተፅዕኖ ወዘተ የሚያሳጣ ለውጥ ደመኛ ጠላታቸው ነው። በሥልጣን የባለጉበት ጉድና የሠሩትም ወንጀሎችን የሚያጋልጥ ለውጥን አሁንም በእጃቸው ባለው ሥልጣንና ከመሰሎቻቸው ጋር በመተባበር ለውጥን ማስቆምና ማደናቀፍ ዋና ሥራቸው ነው። በተጨማሪም ለውጡ ከተሳካ ከተጠያቂነት ቢተርፉም እንኳ ፈፅሞ ያልጠበቁት ከዓመታት በፊት እንደነበሩት “ተራ” ዜጋ ወደመሆን መመለሳቸው ማለትም ወደ ሥራ ፈትነት፣ የአንደኛ ደረጃ መምህርነት፣ አነስተኛ ነጋዴነት፡ ዝቅተኛ እርከን የመንግሥት ተቀጣሪነት ወዘተ ከዕንቅልፍ እያባነነ ያሰቃያቸዋል።  ስለሆነም በሕገ ወጥ መንገድ የጦር መሣሪያ ማዘዋወር፣ የመንግሥት ሥራና መመርያ ላይ መለገምና አለመፈፀም፡ ዘርን ከዘር ማጋጨት እና ሕዝብ የሚያቆስል፣ የሚያበሳጭና የሚያስቆጣ ተግባራት በራሱ በመንግሥትና በሕዝብ ቢሮ ሆነው ያሤራሉ፣ ያስፈፅማሉ። ለዚህም ነው የኢሕአዴግ ሥርዓት ከነግሳንግሱ ማብቃት ስንል ይህ በመንግሥታዊ አካል ውስጥ የተሰገሰጉ የጥቅም ተካፋዮችን አቅፎ መሠረታዊ ለውጥ በሀገራችን አይመጣምና ነው።

 1. “ልዩ” ፖሊስ

የክልል “ልዩ” ፖሊስ ሃይል በቀጥታ በክልል ሹመኞችና ካድሬዎች የሚታዘዝ የታጠቀ ሃይል ነው። በምሥራቅ ኢትዮጵያ “ሶማሌ ክልል” እንደታየው ይህ ሃይል የሕዝብ ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ ሳይሆን በስሙ “ፖሊስ” ይባል እንጂ የሚጠብቀውና የሚከላከለው የክልል ባለሥልጣናትን ደህንነትና ትዕዛዛቸውን ነው። “ልዩ” ፖሊስ ሃይል ለፌደራል መንግሥትና ፖሊስ የማይታዘዝ ተጠሪነቱ በተግባር በክልል፣ አውራጃ፣ ወረዳ፣ ዞን ለተዋቀረው የክልል “መንግሥት” የኢሕአዴግ ፖለቲካ ሹሞችና ካድሬዎች ነው።

መሠረታዊ የፖሊስ ተግባር ሕግ ማስከበርና ማስፈፀም የሕብረተሰቡን ሰላም መጠበቅ ነው። ለዚህም የሚሰጠው የሙያ ሥልጠና አደረጃጀቱና የሚሠማራበት ግዳጅ ይህንን መሠረታዊ ተግባሩን በብቃት እንዲወጣ ነው። “ልዩ” ፖሊስ በስሙ ፖሊስ ከመባሉ በቀር የሚሰጠው ሥልጠና በየክልሉና በየጊዜው የተለያየ ነው። በኢትዮጵያችን በጠቅላላው ያለው አንድ ሕገ መንግሥት (የተንሸዋረረ ቢሆንም)፣ ከረጅም ዓመታት ጀምሮ እየተሻሻለ አሁንም በሥራ ላይ ያለው አንድ ወንጀለኛ መቅጫ ሕግና አንድ የፍትሐብሔር ሕግ ነው። የፖሊስ ተግባር እነዚህን የሀገሪቱን ሕግጋት ማስጠበቅና የጣሱትን ሕግ ፊት ማቅረብ፣ ፍርዱንም ተከታትሎ ማስፈፀም ነው። ይህም ማለት እነዚህን ለማስከበርና ለማስፈፀም የሚሰጠው የፖሊስ ሥልጠና ተመሳሳይነት ሊኖረው ይገባል – በሥራም በቤተሰብ ጉዳይም የፖሊስ አባላት በሀገሪቱ ተዘዋውረው መሥራት እንዲችሉ። “ልዩ” ፖሊስ ግን “ልዩ” የሚለው የስሙ ቅጥያ እንድሚያመለክተው የሀገሪቱን ሕግጋት ማስከበር ሳይሆን የክልል ሹመኞችን ፍላጎትና ትዕዛዝ እንዲያስፈፅም የተዋቀረ ነው።

በምልመላውም በኩል እንደ ሌላው ዓለም ሁሉ የወንጀል ተግባር ያልፈፀመ፣ መልካም ሥነምግባር ያለው፡ ያለአድሎ ግዴታውን መወጣት የሚችል ወዘተ የሚሉ ሙያዊና ግለሰባዊ መስፈረቶችን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል። ይህ ሙያዊ መሥፈርት ደግሞ ለተራ ፖሊስ ብቻ ሳይሆን ለኦፊሰርነት ወይም ለአዛዥነት የሚመለመሉትንም ይጨምራል። ይህም ሙያዊ መሥፈርት በፖሊስ አባላት ተጠብቆ መቆየቱ በየጊዜው በፖሊስ ሠራዊት የዕዝ ሰንሰለት ይመረመራል። የፖሊስ አባላት በተዋረድ ትዕዛዝ ማክበር፣ ግዴታን መወጣት፣ የሥራ አፈፃፀም ንቃት ወዘተ ይመዘናል፡፡ የእርማት እርምጃ ሲያስፈልግ የሥነሥርዓት ቅጣትም ይደረጋል። “ልዩ” ፖሊስ ግን እንደ ኢሕአዴግ ባለሥልጣናት ሁሉ በታማኝነትና በተለይም በነገድ ወይም በዘር መስፈረት ስለሚመለመል ታማኝነቱና የሚቀበለውም፣ የሚያስፈፅመውም ትዕዛዛት የክልል መስተዳድር ታማኝ ሹመኞችና የፖለቲካ ካድሬዎች የሚነግሩትን ያለመጠየቅ ነው። ለዚህም አንድ ማሳያ ከአዲስ አበባ ወጣቶች ፖሊስ እንዳይመለመል ለረጅም ጊዜ በህወሓት መሩ ኢሕአዴግ የነበረው አሠራር ነው። ከሕብረተሰቡ መሃል የወጡ የፖሊስ አባላት ጉዳቱ ጉዳታቸው ሆኖ የሚታያቸው ዜጎች ለ”ልዩ” ፖሊስነት አይመለመሉም።

“ልዩ” የፖሊስ ሃይል በፌደራል መንግሥት አለመታዘዙ፣ በነገድና ታማኝነት መመልመሉ ወዘተ ጋር ተዳምሮ በሥራው የሚያገኛቸው ጥቅማ ጥቅሞችና “ተፈሪነት” “ልዩ” ፖሊስ ሃይል የፈጠረውን፣ ያሰለጠነውን፣ የሥራና የጥቅም መስክ የከፈተለትን የክልል አስተዳደር ሥልጣን ላይ እንዲቆይ፣ ተቃዋሚ ንቅናቄ ከተነሳበትም በሃይል ለመደፍጠጥ የተዘጋጀ “ልዩ” ሃይል ነው። በአንዳንድ ክልሎች እንደታየው የ“ልዩ” ፖሊስ ሃይል መለዮውን አውልቆ እንደ ሲቪል ተላብሶ ረብሻ ሲመራና በጦር መሣሪያ እየታገዘ የዘርና የሃይማኖት ግጭቶችን ሲመራ ነው። በቅርቡ አዲስ መመርያ ይወጣል የተባለው የ“ልዩ” ፖሊስ ሃይል የመሣሪያ ትጥቅ “ሚያስተካክል” ነው። መደበኛ ፖሊስ ሕግ ለማስከበርና የሕዝቡን ሰላምና ደህንነት ለማስከበር ከሚያስፈልገው እጅግ የላቀ ከጦር ሠራዊት የማይተናነስ ትጥቅ ነው “ልዩ” የፖሊስ ሃይል ያለው።

ይህ “ልዩ” ፖሊስ ሃይል አሁን ኢትዮጵያችን ባላችበት የ“ለውጥ” ጊዜ ከታማኝ የክልል መስተዳድር ሹመኞችና ካድሬዎች ጋር እጅና ጓንት በመሆን በመሣሪያ ዝውውር፡ የሃሰት መታውቂያ ይዞ የዘር ግጭት በመቀስቀስና ሌሎችም ለውጡን በሚያደናቅፉ ሤራዎች ቀንደኛ ተሳታፊ ነው። እንደ ሕገ መንግሥቱ ድንጋጌም ፖሊስ ከፓርቲና ሌላም ወገንተኛ ፖለቲካ ነፃ ወይም ገለልተኛ መሆን ሲግባው አመላመሉም፣ አሰላጣጠኑም፣ የሥራ መመሪያና የሚሰጠው ተልዕኮም ከዚህ ተቃራኒ ነው።

 1. ደህንነትና ስለላ

የደህንነትና የስለላ መዋቅሩ በክልል መስተዳድሩ፣ በ“ልዩ” ፖሊስ፣ በፓርቲ አባላትና ካድሬዎች እየታገዘ የገዛ ራሱን ዜጎች በመሰለል የሚታወቅ ነው። ሁሉም የክልልና ፌደራል መንግሥት ቅርንጫፎች ለዚህ የስለላ ሃይል ታዛዥ ናቸው። የተቃወሙትን ብቻ ሳይሆን ይቃወሙኝ ይሆናል “በሆዳቸው ይሰድቡኛል” ብሎ የገመታቸውን ግለሰብ ዜጎች ለመከታተል፣ ስልካቸውን ለመጥለፍ፣ ቤታቸውን ለመበርበር፣ ዓይን ሲያወጣም ማስፈራራትና ያለአግባብ ማሠር የሚያደርግ ሕገ መንግሥቱንም ሆነ ሌሎች የሀገሪቱ ሕግጋትን የማያከብር ስውር ሃይል ነው።

በሰለጠኑ ሀገራትም እንደሚስተዋለው የደህንነት ሃይል የሀገርና ሕዝብን ሰላምና ሉዓላዊነትን የሚቀናቀኑ ሃይሎችን በፖሊስና በጦር ሠራዊት ብቻ መቋቋም ስለማይቻል የሚመሠረት ነው። የመንግሥት አስተዳደር (Government) እና የመንግሥት መዋቅር (The State) የተለያዩ ናቸው። መንግሥትን የሚመሠርቱት ፓርቲዎች፣ ፕሬዚዳንቶች፣ ጠቅላይና ሌሎች ሚንስትሮችና የአስተዳደር ባላሥልጣኖች በሕዝብ ምርጫም፣ በሕዝባዊ ንቅናቄም ይለወጣሉ። የመንግሥት መዋቅር ግን በዘላቂነት የሀገርን፤ ሲቪልም ሆነ ወታደራዊ ጉዳዮችና ሌሎችንም እንደ ትምህርት፣ ጤና፣ ንግድ፣ የገንዘብ ተቋማት ወዘተ ያሉ ቋሚ የሀገርና ሕዝብ ሕልውናን የሚመራ ነው። የደህንነት ዋና ተግባርም ይህን ቋሚ የመንግሥት መዋቅርን ደህንነት የመጠበቅና ይህንንም ለሚረከቡት አስተዳደሮች መተላለፉን መጠበቅ ነው። የመንግሥት መዋቅር (The State) የሀገር መሠረት ነውና።

በየክልሉና በሀገር ደረጃ የተዘረጋው የደህንነትና ስለላ ተቋም ግን ሥልጣን ላይ ያለው መንግሥትና ፓርቲ በያዙት ሥልጣን የመቆየት ዓላማቸውን ይፈታተናሉ የተባሉ ዜጎችንና ተቃዋሚ ፓርትዎችን መሰለል፣ ማስጨነቅና ማዋከብ ሲበዛም ማሠርና ማሰቃየት ነው። የሚያሳዝነው ደግሞ በኢሕአዴግ ዘመን የሚታየው የመንግሥትና የፓርቲ “ቅልቅል” በስለላ መርቡ መደረጉም ነው። በሀገር ውስጥ ያሉ ካድሬዎችና የፓርቲ አባላት የስለላ መዋቅሩ አስፈፃሚ ናቸው መሆንም ይጠበቅባቸዋል። በውጭ ሀገራት ያሉ በየኤንባሲውና ቆንስላዎች ውስጥ የተሰገሰጉ የዘር ተዋጽዖ ምድብተኞች በዲፕሎማቲክ ስም የሚዘዋወሩ ካድሬዎች ሳይቀሩ ተቃዋሚ የሚባሉ ዜጎችን ስምና ፎቶ ወደ ዋናው የስለላ መ/ቤት ያስተላልፋሉ – ቦሌ ላይ የሚደረገው የ“ኢምግሬሽን” ማጣራት ይህን የተላለፈ ዝርዝር ማጣራት ይጨምራል። የስለላ ድርጅቱ ከዚህም አልፎ ዜጎችን ለአጎራባች ሀገሮች እያፈኑ መውሰድንም ያከናውናል። ወደ 5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በመክፈል ከየመን የተደረገው የግንቦት 7 ፀሃፊ ድርጊት የሚያሳየው ይህንን የሥርዓቱን ዕድሜ ለማቆየት የሚደረግው ጥረት ወሰን እንደሌለው ነው።

የዚሁ የስለላና የመንግሥት ደህንነት አካል የሆነው በየክልሎቹ የተዘረጋው መረብ እንደ “ልዩ” ፖሊስ ሃይል ሁሉ በየቤተሰቡ ደረጃ ከሚደረግው የአንድ-ለ-አምስት ጥርነፋ ጃምሮ ባለው መዋቅሩ ጥቅም ያስገኘለትን መንግሥት፣ ፓርቲና ሥርዓትን የሚቀይር ባለው አቅም ሁሉ ለውጥን ከማደናቀፍና ከመቀልበስ አያርፍም።

በጥቅሉ ዘርዘር አድርገን ከላይ ያስቀመጥናቸው መታየት ያለባቸው ውስብስብ ጉዳዮች  እንደ መንግሥት ኢሕአዴግ፣ እንደ ፓርቲ ኢሕአዴግ፣ እንደ ስለላ ኢሕአዴግ እየመራት በአለው ብቸኛ የ28 ዓመት አገዛዙ ኢትዮጵያ ወደ ተፈላጊው ሀገራዊና ሕዝባዊ ሥርነቀል አይደለም አዝጋሚ ለውጥ እንደማታመራ እኛ ሳንሆን ምድር ላይ ያለው ዋይታና ልቅሶ መስካሪ ነው። ዛሬ የ28 ዓመቱ የዘረኛ አገዛዝ ኢሕአዴግ ወደ ዘር እልቂት እየተሸጋገረ ነው። እስከ አፍንጫው በታጠቀ ሃይል ሕፃናት፣ አዛውንት እናትና አባቶች እየተገደሉ፣ እየተጋዙ፣ ሴቶች እየተደፈሩ፣ ወጣቶች እያለቁ፣ ባለንበት ሀገር ኢሕአዴግ ድረስልን ሳይሆን ከዘረኛ ኩታንኩቱ ጋር ያበቃ ዘንድ መነሳሳት ዋነኛው አማራጭ መሆኑን “አንድ ሀገር! አንድ ሕዝብ! ኢትዮጵያችን ሕዝባዊ ንቅናቄ” አበክረን እናስገነዝባለን። ሀገራችን ኢትዮጵያ ወደ እርስ በእርስ ግጭት እንዳታመራ፣ ኢትዮጵያ እንደ ሀገር እንድትቀጥል፣ ዘርንና/ቋንቋን ተገን ያደረገ ከፋፋይ ሥርዓት እንዲያበቃ፣ ከፊታችን የተጋረጠውን ዋይታና ሰቆቃ ለመመከት ልንደፍር የሚያስፈልገው የኢሕአዴግ አገዛዝ እጁን ለሀገር አድን የሽግግር መንግሥት እንዲያነሳ ነው።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይባርክ!

አንድ ሀገር! አንድ ሕዝብ! ኢትዮጵያችን ሕዝባዊ ንቅናቄ

ሚያዝያ 05 ቀን 2011 ዓ.ም. (April 12, 2019)

ማሳሰቢያ ፡

 • ውድ ወገኖቻችን ይህንን “አንድ ሀገር! አንድ ሕዝብ! ኢትዮጵያችን ሕዝባዊ ንቅናቄ” «ኢትዮጵያችን» ዕትም በተለይ በሀገር ቤት ኮምፒዩተር የማግኘት ዕድል ለሌላቸው በማባዛት ታሰራጩት ዘንድ ቀና ትብብራችሁን በትህትና እንጠይቃለን።
 • “አንድ ሀገር! አንድ ሕዝብ! ኢትዮጵያችን ሕዝባዊ ንቅናቄ” መስከረም 8 ቀን 2009 ዓ.ም. እራሱን ይፋ ያደረገ ሕዝባዊ ድርጅት ሲሆን የንቅናቄውን ማንፌስቶና ፕሮግራም ethiopiachen.org ከሚለው ድረ ገጻችን ማግኘት ትችላላችሁ።

ስልክ፡  703 300 4302

ኢሜል ፡ ethiopiachen2009@gmail.com

ድረ ገጽ ፡ www.ethiopiachen.org , www.ethiopiachen.com

ምሥለ ገጽ ፡ 1H1H Ethiopiachin

የአዲስ አበባ ባለአደራ ምክር ቤት (ባልደራስ)ጋዜጣዊ መግለጫ

የጋጥ ወጦች ድርጊት ትግላችንን እንድናጠናክር ያደርገናል

የአዲስ አበባ በለአደራ ምክር ቤት ከህዝብ የተሰጠውን ተልዕኮ ለማስፈፀም ላለፉት 35 ቀናት ደፋ ቀና እያለ ይገኛል፡፡ በዚህ ጊዜ 3 ህዝባዊ ስብሰባዎችና አንድ ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት ሞክሮ፣ ሁሉም በአዲስ አበባ መስተዳድር ተፅዕኖ ተደርጎባቸው፣ ሁለቱን ለመሰረዝ ተገዷል፡፡ አንዱ ጋዜጣዊ መግለጫም ቢሆን፣ ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅም መልኩ ክልከላ ተደርጎበታል፡፡
ይህ ሁሉ መንግስታዊ ህገ ወጥነት አግባብ እንዳልሆነ፣ የምክር ቤቱ ሰብሳቢና ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ በተገናኙበት ጊዜ ተማምነውዋል፤ በቀጣይነትም፣ መስተዳድሩ ከህገ ወጥ ተግባራቱ ተቆጥቦ ህዝባዊ ስብሰባዎች ያለምንም ተፅዕኖ እንዲደረጉ ስምምነት ላይ ደርሰው ነበር፡፡
ይህ ስምምነት ሰኞ ዕለት ተደርሶ፣ በማግስቱ፣ ማክሰኞ፣ ለመስተዳድሩ በገባ ደብዳቤ፣ በቀጣዩ ቅዳሜ ሚያዚያ 5/2011 ዓ.ም በ24/መገናኛ በሚገኘው ኮከብ አዳራሽ የቦሌና አቃቂ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ህዝባዊ ስብሰባ ለማድረግ እቅድ መያዙን፣ ለዚህም የፖሊስ ጥበቃ እንዲደረግ ተጠይቋል፡፡ ሆኖም፣ እስከ ዓርብ ድረስ የመስተዳድሩ ምላሽ በመጥፋቱ፣ ለራሳቸው ለምክትል ከንቲባው በቴክስት እንዲያውቁት ተደርጓል፡፡ በመጨረሻም፣ ዓርብ ዕለት በተሰጠ የቃል ምላሽ፣ በህጉ መሰረት ስብሰባ ለማድረግ እንደ ማይከለከል፣ የፖሊስ ጥበቃ ለማድረግ ግን መስተዳድሩ ፈቃደኛ አለመሆኑ ተገልጿል፡፡
በዚህ ተስፋ ባለመቁረጥ፣ ስብሰባውን በራሳችን ኃይል እያስጠበቅን ለማከናወን ወስነን በቦታው ላይ የተገኘን ቢሆንም፣ ስብሰባው ከመጀመሩ በፊት በመኪና ተጭነው የመጡ ኦሮምኛ ተናጋሪ ወጣቶች፣ በቡድን በቡድን ተደራጅተው በአካባቢው ከመሰማራታቸውም በላይ፣ ወደ ስብሰባው አዳራሽ በመምጣት ሁከት ለመቀስቀስ ሞክረዋል፡፡ ይህንን ለፖሊስ ብናሳውቅም፣ በመጨረሻ ላይ፣ “ጥበቃ አይደረግላችሁም” የሚል እጅግ አሳፋሪና ኃላፊነት የጎደለው ምላሽ ተሰጥቶናል፡፡ በዚህ የጋጥ ወጦች ስልት ስብሰባ እንዳናደርግ በእጅ አዙር ጋሪጣ ተደቅኖብን፣ ራሳችንን ለመከላከል በቂ ኃይል ቢኖረንም፣ የህዝብ ደህንነትንና የሀገረን ሰላም በማስቀደም ስብሰባውን ሰርዘናል፡፡
እንደዚህ ዓይነቱ ጋጥ ወጥ አካሄድ፣ በባለአንጣነት እየተፈረጀ ላለው ለአዲስ አበባ ህዝብ ብቻ ሳይሆን፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለተጀመረው የዲሞክራሲ ሽግግር አደገኛ በመሆኑ፣ አስቸኳይ የማስተካከያ እርምጃ እንዲወሰድ አጥበቀን እንጠይቃለን፡፡
የማስተካከያው እርምጃ ቢወሰድም ባይወሰድም ግን፣ ሰላማዊ ትግላችን ከመቼውም ጊዜ በላይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ለወዳጆቻችንም ሆነ ለተቀናቃኞቻችን ማሳሰብ እንወዳለን፡፡ ቁርጠኝነታችንንም በቀጣይነት በምንወስዳቸው ሰላማዊ የተግባር እርምጃዎች እናሳያለን፡፡

የአዲስ አበባ ባለአደራ ምክር ቤት

ሚያዚያ 7/2011 ዓ.ም አዲስ አበባ

ኢትዮጵያ ላይ አትዶልቱ! አያዋጣም! የጊዜ ጉዳይ እንጂ ወራዳና መሣቂያ ትኾናላችኁ!haratewahido ሐራ ዘተዋሕዶ

Repoter Amharic Editorial Miyazya 6 2011
 • አገርን ከሚፈልጉት ሥልጣን በታች የሚያዩ ራስ ወዳዶችና ጀሌዎቻቸው  ኢትዮጵያን ለማጥፋት እየዶለቱ ነው፤ እነዚኽን እኵዮች ተባብሮ ማስቆም የኢትዮጵያውያን ሓላፊነት ነው፤ 
 • በኢትዮጵያ ላይ መዶለት አያዋጣም፤ ያዋጣል የሚል ካለም የጊዜ ጉዳይ እንጂ ውርደት ተከናንቦ፣ የታሪክና የመጪውትውልድ መሣቂያ ይኾናል!
 • ሕዝቡ የድህነት አረንቋ ውስጥ ተዘፍቆ እያለ፥ ወሬ፣ ሐሜት፣ አሉባልታ፣ ጥላቻ፣ ራስ ወዳድነት፣ ርእይ አልባነት፣ ግጭትናትርምስ ለኢትዮጵያ ፋይዳ የላቸውም
 • ኢትዮጵያን ከገባችበት ማጥ ውስጥ ለማውጣት መረባረብ ሲገባ፣ የጎሣ አጥር ውስጥ ኾነው በገሃድ የሚቃዡ ምሁራንተብዬዎች እንደ እንጉዳይ ፈልተዋል
 • በዐደባባይ ኢትዮጵያዬ እያላችኹ ከመጋረጃው ጀርባ የምታሤሩም ኾነ፣ በድፍረት ተሞልታችኹ በግልጽ ኢትዮጵያንለማፍረስ የምትባዝኑ መቼም አይሳካላችኹም!
 • ኢትዮጵያን ከራሳችኹ ሥልጣንና ጥቅማ ጥቅም በታች የምትመለከቱ ፖሊቲከኞች፣ አክቲቪስቶች ወይም ሌላ መጠሪያያላችኹ ሁሉ እጃችኹን ከኢትዮጵያ ላይ አንሡ!
 • በኢሕአዴግ አመራሮች መካከል ለአገር ክብርና ህልውና ደንታ የማይሰጥ አካሔድ በፍጥነት መቆም አለበት፤ ሥልጣንበትምህርት፣ በተመሰከረለት ልምድ ክህሎት እንጂ በኮታ እየተሸነሸነ የቅራኔ ምንጭ ኾኖ አገር መበጥበጥ የለበትም፤
 • በዚህ ጊዜ ለኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት፥  የሕዝቧ አንድነት፣ ወጣቶች ጥራት ያለው ትምህርትና አስተማማኝ ገቢ ያለውሥራ ነው፤ የሞራልና የሥነ ምግባር ትምህርት በመስጠት አገራቸውን ከልብ እንዲወዱ ማስቻል ተገቢ ነው
 • ከመጠን ያለፈ ድህነት ሕዝቡ አናት ላይ እያናጠረ በከንቱ ግብዝ መኾን አያዋጣም፤ ለግል ሥልጣንና ጥቅማ ጥቅም ሲባልበአገር ላይ መዶለት ነውር ነው፤ ስለዚህ ኢትዮጵያ ላይ አትዶልቱ መባል አለበት!

***

(ሪፖርተር፤ ርእሰ አንቀጽ፤ ሚያዝያ 6 ቀን 2011 ዓ.ም.)

ኢትዮጵያ ከሥልጣን በላይ ናት፡፡ ኢትዮጵያ ከማናቸውም ጥቅማ ጥቅሞች በላይ ናት፡፡ ኢትዮጵያን የማያስቀድም ሥልጣን፣ ጥቅም ወይም ሌላ ነገር ተቀባይነት የለውም፡፡ ኢትዮጵያን ከራሳችኹ ሥልጣንና ጥቅማ ጥቅም በታች የምትመለከቱ ፖሊቲከኞች፣ አክቲቪስቶች ወይም ሌላ መጠሪያ ያላችኹ ሁሉ እጃችኹን ከኢትዮጵያ ላይ አንሡ፡፡ ያልተገራ አንደበታችኹን አደብ አስገዙ፡፡ ድብቅ ዓላማችኹ መቼም ቢኾን ይጋለጣልና በከንቱ አትፍጨርጨሩ፡፡ በዐደባባይ ኢትዮጵያዬ እያላችኹ ከመጋረጃው ጀርባ የምታሤሩም ኾነ፣ በድፍረት ተሞልታችኹ በግልጽ ኢትዮጵያን ለማፍረስ የምትባዝኑ መቼም አይሳካላችኹም፡፡ ኢትዮጵያ ለዘመናት የገጠሟትን ፈተናዎች እየተሸጋገረች እዚህ የደረሰችው፣ በጀግኖች ልጆቿ ተጋድሎ መኾኑን ታሪክ ይመሰክራል፡፡ ከታሪክ መማር የማይፈልጉ ግን በተደጋጋሚ ቢያደቡም፣ ኢትዮጵያ በልጆቿ ትግል እዚኽ ደርሳለች፡፡ በኢትዮጵያ ላይ መዶለት አያዋጣም፡፡ ያዋጣል የሚል ካለም የጊዜ ጉዳይ እንጂ ውርደት ተከናንቦ፣ የታሪክና የመጪው ትውልድ መሣቂያ ይኾናል፡፡

ለኢትዮጵያ መፃኢ ዕጣ ፈንታ አዎንታዊ ሚና ሊኖራቸው የማይችሉና ሰላሟን የሚፈታተኑ በሙሉ፣ ቢቻል ከገቡበት የጥፋት ጎዳና ሊመለሱ ይገባል፡፡ ይህ የማይኾንላቸው ከኾነ ደግሞ አጥፊ እጃቸውን መሰብሰብ አለባቸው፡፡ ይህ ጉዳይ ሲነሣ በመጀመሪያ በፌዴራልም ኾነ በክልል ብሔራዊ መንግሥታት ሥልጣን ይዘው፣ ሓላፊነታቸውን በሚገባ መወጣት ያልቻሉ አመራሮች ራሳቸውን ኦዲት ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡ አገሪቱን በብሔር እየተቧደኑ እንደ ቅርጫ መቀራመት ከአኹን በኋላ መቆም አለበት፡፡ በተለይ በገዥው ግንባር ኢሕአዴግ አባል ድርጅቶች አመራሮች መካከል የሚስተዋለው፣ ለአገር ክብርና ህልውና ደንታ የማይሰጥ አካሔድ በፍጥነት መቆም አለበት፡፡ ሥልጣን በትምህርት፣ በተመሰከረለት ልምድ፣ ብቃትና ክህሎት መያዝ እንዳለበት ሊታወቅ ይገባል፡፡ ሥልጣን ከአገር ህልውና በላይ ስላልኾነ አደብ መግዛት የግድ ይኾናል፡፡ ሥልጣን በኮታ እየተሸነሸነ የቅራኔ ምንጭ ኾኖ አገር መበጥበጥ የለበትም፡፡ ለሥልጣንና ለሚያስገኘው ጥቅም እየተቧደኑ አገር ላይ መቆመር ሊያበቃ ይገባል፤ በአገር ህልውና ቀልድ የለምና፡፡

ለኢትዮጵያ በዚህ ጊዜ የሚያስፈልጋት የሕዝቧ አንድነት ነው፡፡ በአንድነት በመቆም ሰንደቋን ከፍ አድርጎ ወደ ታላቅነት ክብሯ መመለስ፣ የልጆቿ የተቀደሰ ተግባር መኾን ይኖርበታል፡፡ የኢትዮጵያ ወጣቶች ጥራት ያለው ትምህርትና አስተማማኝ ገቢ ያለው ሥራ ያስፈልጋቸዋል፡፡ የሞራልና የሥነ ምግባር ትምህርት በመስጠት አገራቸውን ከልብ እንዲወዱ ማስቻል ተገቢ ነው፡፡ ከሌብነት፣ ከሱስና ከአልባሌ ድርጊቶች ተወግደው ለነፃነት፣ ለእኩልነትና ለፍትሕ ተሟጋች እንዲሆኑ መቀረፅ አለባቸው፡፡ አገር ለማጥፋትና ለማተራመስ የሚያደቡ መሰሪዎች መሣሪያ እንዳይኾኑ፣ ከቤተሰብ ጀምሮ እያንዳንዱ አገሩን የሚወድ ዜጋ ድጋፍ ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡ ወጣቶችን ላልተገባ ዓላማ ሊጠቀሙ የሚፈልጉ ሓላፊነት የማይሰማቸው ግለሰቦችና ቡድኖችን፣ በቁርጠኝነት በአንድነት ማስቆም ተገቢ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ወጣቶች ለአገራቸው ህልውና በጽናት መቆም የሚችሉት፣ አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ከጎናቸው በቁርጠኝነት ሲቆሙ ብቻ ነው፡፡ ኢትዮጵያን ወዳልተፈለገ አቅጣጫ ሊወስዱ የሚፈልጉ ኀይሎችም ሊገቱ የሚችሉት፣ ኢትዮጵያውያን እንደ ጥንቶቹ አባቶቻቸውና እናቶቻቸው በአንድነት ሲቆሙ ብቻ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ሕዝብ ድህነት ከመጠን በላይ ያንገሸገሸው ነው፡፡ ከአሳፋሪውና ከአንገት አስደፊው የመረረ ድህነት ውስጥ ወጥቶ እንደ ሰው መኖር ይገባዋል፡፡ ሕዝቡ የድህነት አረንቋ ውስጥ ተዘፍቆ ወሬ፣ ሐሜት፣ አሉባልታ፣ ጥላቻ፣ ራስ ወዳድነት፣ ርእይ አልባነት፣ ግጭትናትርምስ ለኢትዮጵያ ፋይዳ የላቸውም፡፡ ኢትዮጵያ በተለያዩ ጊዜያት አግኝታቸው ያመለጧት ወርቃማ ዕድሎች ያስቆጫሉ፡፡ ከ40 ዓመታት በፊት በነጭና በቀይ ሽብር አንድ ትውልድ አጥታለች፡፡ ከዚያም በኋላ በርካቶች ተገድለዋል፤ ታስረዋል፤ ተሰደዋል፡፡ መንግሥታት በተለዋወጡ ቁጥር ሕዝብ የጠበቃቸው ቀርተው የማይፈልጋቸው ክፉ ነገሮች እየተጫኑበትና ልጆቹ እስር፣ ስደትና ሞት ዕጣ ፈንታቸው ነበር፡፡ ሰብአዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ታፍነው ኢትዮጵያውያን ቁም ስቅላቸውን ዐይተዋል፡፡ ከዚያ መራር አዙሪት ውስጥ በስንት መከራ መውጣት ቢቻልም፣ አሁንም ትክክለኛውን መንገድ ለመያዝ ባለመፈለጉ ከተስፋ ይልቅ የስጋት ደመና ያንዣብባል፡፡ አገርን ከሚፈልጉት ሥልጣን በታች የሚያዩ ራስ ወዳዶችና ጀሌዎቻቸው ኢትዮጵያን ለማጥፋት እየዶለቱ ነው፡፡ እነዚኽን እኵዮች ተባብሮ ማስቆም የኢትዮጵያውያን ሓላፊነት ነው፡፡

የምትለብሰው የላት የምትከናነበው አማራት እንደሚባለው፣ በአሁኑ ጊዜ በድህነትና በኋላቀርነት በምትማቅቅ አገር ውስጥ ተማርን ባዮች ማገናዘብ አቅቷቸዋል፡፡ ኢትዮጵያን ከገባችበት ማጥ ውስጥ ለማውጣት መረባረብ ሲያዋጣ፣ የጎሣ አጥር ውስጥ ኾነው በገሃድ የሚቃዡ ምሁራን ተብዬዎች እንደ እንጉዳይ ፈልተዋል፡፡ ኢትዮጵያ እጅግ በጣም ሰፊ ለም መሬት፣ አመቺ የኾነ የአየር ንብረትና ጠንካራ ወጣት የሰው ኀይል ይዛ ትራባለች፡፡ የአፍሪካ የውኃ ማማ ኾና ትጠማለች፡፡ የገዘፈ ታሪክ ባለቤት ኾና የአገሮች ጭራ ናት፡፡ አሁንም በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሕፃናት ተመጣጣኝ ምግብ ስለማያገኙ ይቀነጭራሉ ወይም ይሞታሉ፡፡ ከድህነት ወለል በታች የሚኖሩ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ካሉት በታች፣ ከሞቱት በላይ ኾነው ከአንገፍጋፊ ድህነት ጋራ ይኖራሉ፡፡ ሚሊዮኖች መጠለያ አልባ ናቸው፡፡ በከተሞች በሚያሳፍር ኹኔታ ነዋሪዎች የትራንስፖርት፣ የውኃ፣ የኤሌክትሪክና የማዘጋጃ ቤት አገልግሎቶችን የሚያገኙት በኋላቀር አሠራሮች ነው፡፡ አዲስ አበባን ጨምሮ ብዙዎች ከተሞች የቆሻሻ መጣያ ናቸው፡፡ የድኻ ድኻ አገር ታቅፎ እንደ ደላቸው አገሮች እዚህ ግቡ በማይባሉ ጉዳዮች በነጋ በጠባ መተራመስ ትዝብት ላይ ይጥላል፡፡ ከመጠን ያለፈ ድህነት ሕዝቡ አናት ላይ እያናጠረ በከንቱ ግብዝ መኾን አያዋጣም፡፡ ለግል ሥልጣንና ጥቅማ ጥቅም ሲባል በአገር ላይ መዶለት ነውር ነው፡፡ ስለዚህ ኢትዮጵያ ላይ አትዶልቱ መባል አለበት!

ወጣት ሆይ! ለህልውናህም ሆነ ለክብርህ ወደ ባህልህ! (በላይነህ አባተ)

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)

አገር ይቃጠላል ሕዝብ ግን ለፖለቲካ ፍጆታ መንገድ ጠረጋ በአዋጅ ተጠርቷል፡፡ እንደ መንገድ ጠረጋው ቃጠሎን ለማጥፋት ሕዝብን በአዋጅ ለመጥራት ምን ያህል ገንዘብ ይጠይቃል? ላሊበላን ከመፍረስ ለማዳን ሕዝብን በአዋጅ ለመጥራትስ ምን ያህል ጥበብ ይጠይቃል? ጣናን በአረም ከመድረቅ ለማዳን ሕዝብን በአዋጅ ለመጥራትስ ምን ያህል ጉልበት ያስፈልጋል? በከንቲባ ከፈረሱ ቤቶች መንገድ የወደቁትን ህጻናትና እርጉዝ ሴቶች ወደነበሩበት የሚመልስ አዋጅ ለማወጅስ ምን ያህል በጎ ፈቃድ ይጠይቃል? በዘመናዊ መሳሪያ የሊጥ ዕቃና ዳቦ የሰረቁ የወታደር ልብስ ለባሽ ሽብርተኞችን ችሎት ለማቅረብስ ምን ያህል ጊዜ ያስፈልጋል?

ወጣት ሆይ! ህልውናህን የመፈታተኑ አደጋ በህይወትህና በቅርስህ በከፋ ሁኔታ ቀጥሏል፡፡ ይኸንን አደጋ ደርምሰህ ህልውናህን ለማስቀጠልና በክብር ለመኖር ወደ አያቶችህ ባህልና ጀግንነት መመለስ ግድ ይላል፡፡

ሃይማኖትህ ዓለም በቅዱሳን የምትመራ የፍትህ ምድር እንድትሆን ያዝዛል፡፡ ዳሩ ግን የትናንትናዋም ሆነ የዛሬዋ ዓለም ለጉልበተኞች እንጅ ለቅዱሳን ተመችታ እንደማታውቅ ታሪክ ይመሰክራል፡፡ ድርሳናትም ዓለም የጉልበተኞች እንጅ የቅዱሳን ሐብት የሆነችበት ዘመን እንዳልነበረ አስረድተዋል፡፡

ጉልበተኞች ጉልበትን በጠመንጃ፣ በስብከትና በገንዘብ እንደ ጆፌ መጭልፈው ዓለምን እንደ ኳስ እያነጠሩ ሲያሽከረክሯት ኖረዋል፡፡ ዓለም እስከ ዓለም ፍጣሜም ተጉልበተኞች መዳፍ መውጣቷ ያጠራጥራል፡፡ ይህ እውነታ ጉልበት ለህልውና ያለውን ወሳኝ ሚና ያመለክታል፡፡ ጉልበት ለህልውና ያለው ወሳኝ ሚና በዳርዊን ምርምር ተረጋግጧል፡፡ ዳርዊን “ሰው በአዝጋሚ ለውጥ ተፈጠረ” ያለው ስብከት ውሀ ባይቋጥርም “ጉልበታም ደካማውን አጥፍቶ ዓለምን ይቆጣጠራል!” የሚለው ክርክሩ ትክክል እንደነበር ያለም ታሪክ ይመሰክራል፡፡

ጉልበት ለህልውና የሚጫወተውን ወሳኝ ሚና አያቶችህ ተረድተውት እንደነበር ግብራቸው ይመሰክራል፡፡ አያቶችህ በአጥንታቸው ካስማነትና በደማቸው ምርግነት ገንብተው በጠበቋት አገር እንደ ጠላት የምትገደለው፣ የምትፈናቀለውና የምትሰደደው ያሁኑ አማራም እንደ አያቶችህ ከአውሬዎች ራስህን ተከላክለህ ትውልድን ለማስቀጠል ከጥበብ ጎን ለጎን የጉልበትን ጠቀሜታ መገንዘብ ይኖርብሃል፡፡ እግዚአብሔር ሰውን በመልኩ ፈጠረው” ከሚለው የድስት ሺህ ዘመን እምነትህ በተጨማሪ በዚች ከንቱ ዓለም ለህልውና ጉልበት አስፈላጊ መሆኑን መረዳት ይኖርብሃል፡፡ እግዚአብሔር “ቀኝህን ሲመታህ ግራህን ስጥ”ን ያዘዘው አምላክ በመልኩ የፈጠረው ሲመታህ እንጅ ሰይጣን ተእግዚአብሔር ፈልቅቆ በተንኮልና በጭካኔ ያደቆነው አውሬ ሲነክስህ አለመሆኑን ማወቅ ይኖርብሃል፡፡

ሰይጣን ተእግዚአብሔር ጉያ ነጥቆ ያደቆነው ወራሪ ቀኛቸውን ሲመታቸው ግራቸውን በመስጠት ፋንታ አያቶችህ ወራሪውን እንደ አውሬ በመቁጠር እንደ አንበሳ አግስተው ከአናቱ ተጎምረው እስተንፋሱን እየዘጉ ዘርረውታል፡፡ እንደ አያቶችህ ተአውሬዎች ራስህን ተከላክለህ በክብር ለመኖር ያያቶችህን ፈለግ መከተል ይኖርብሃል፡፡ ሁለት እጅ፣ ሁለት እግር፣ ሰላሳ ሁለት ጥርስና እሚናገር ምላስ ያለውን ሁሉ እግዚአብሔር በመልኩ እንደፈጠረው ሰው በመቁጠር “ለኢትዮጵያ ህልውና ስል ቀኝ ፊቴን ሲመቱኝ ግራ ፊቴን ሰጠሁ” የሚል በምድር የመኖር መብትህን የሚነሳ በሰማይም ከገነት የሚያርቅህን ጅል ዐመል ማቆም ይኖርብሃል፡፡ ለግማሽ ክፍለ ዘመን የዘር መጥረግ ወንጀል እየተፈጠመብህና በእየ አስር አምቱ በሁለት ሚሊዮን እየጎደልክ ህልውናህ እንዳያከትም ያያቶችህን ፈለግ መከተል ይኖርብሃል፡፡ ያያቶችህን ፈለግ መከተል እንድትችልም ወደ ባህልህ መመለስ ግድ ይልሃል፡፡

ከባህሉ ያፈነገጠ ማህበረሰብ ከባህሩ እንደሸሸ አሳ በህልውናው አደጋ ይጋረጥበታል፡፡ አማራ በጀግና አፍላቂ ባህሩ በሚዋኝበት ዘመን ከዱር አራዊት አንበሳና ነብርን፤ ከሰው አራዊትም ቅኝ-ገዥዎችንና ተስፋፊዎችን አንድ ለአምስት የሚገጥሙ ጀግኖችን እንደ ብርቱካን እያንዠረገገ ሲያፈራ ኖሯል፡፡ ከባህሩ ባፈነገጠባቸው ግማሽ ክፍለ-ዘመናት ወዲህ ግን በክብሩ ብቻ ሳይሆን በህልውናውም አደጋ ተጋርጦበት ይገኛል፡፡

ወጣት ሆይ! ስንዴ ጉዛም እስተ ሆድ ዕቃው በርቅሶ ታረሰው ለም መሬት ተዘርቶና ታርሞ እንደሚያፈራው ጀግናም በጀግንነት መንፈስ ከለማ የባህል ማሳ ሲተከልና ሲኮተኮት ፍሬው ይጎመራል፡፡ ጠላትን እንደ ፍልጥ ተርክከውና እንደ ማገዶ አንድደው ድል ስልነሱ የምትዘፍንላቸውና የምትኮራባቸው አርበኞችህ በተፈጥሯቸው ሰዎች ነበሩ፡፡ እነዚህን ሰዎች ከአላህ በቀር ማንንም የማይፈሩ ጀግኖች ያደረጋቸው ሲወለዱ የተነቀሩበት በጀግንነት ባህል የታሸ ቅቤ ሲያድጉም የበሉት በጀግንነት መንፈስ የተቦካ የባህል እንጀራ ነበር፡፡

በጀግንነት ባህል የተቦካ እንጀራን ጀግና አፍሪነት የተገነዘቡ ምዕራባውያን ከአምስቱ ዘመን ዳግም ሽንፈታቸው በኋላ ባህልህን በተለያዬ መንገድ ማጥቃት ጀመሩ፡፡ ብፁእ ቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ  እንዳሉት ያገራቸው ባህልና ታሪክ ያልተቀዳበትን የጭንቅላት ቶፋ ይዘው ወደ ምዕራብ የተላኩትን ተማሪዎች በምዕራባውያን ርዕዮተ ዓለም እያጠመቁ የራሳቸውን ባህል እንደ አተላ እንዲደፉት አደረጉ፡፡ እነዚህ የራሳቸውን ባህል እንደ አተላ የደፉ “ስልጡን” ተማሪዎችም ጠጉራቸውን እንደ ጫጉላ ሙሽራ እየከፈከፉ በባህላቸውና በሃይማኖታቸው ዘመቱ፡፡ ጀግና እንደ ደን የሚያፋፉ ቀረርቶዎችና ፉከራዎችን እንደ አልሰለጠነ ባህል ቆጥረው “ዘመናዊ” በሚሉት የምዕራባውያን ዳንስ እንደ ጋማ ከብት መራገጥ ጀመሩ፤ እርግጫቸውን ለሌሎችም አስተማሩ፡፡

እነዚህ የዳንስ እርግጫ ወረርሽኝ ተጠቂዎች ቅረርቶንና ፉከራን በዳንስ ኮቴ ስብርብር ከማድረግም አልፈው የቅኔን ፍልስፍና ማስተማሪያ የሆኑትን የባህል ዘፈኖች እያጠፉ የምዕራባውያንን ሙዚቃና ሲኒማ አስፋፉ፡፡ በእነዚህ ወራሪ ሙዚቃዎችና ሲኒማዎች ወጣቱን እያነፈዙ ለአገሩ ባህል ባይተዋር አደረጉ፡፡ በዚህም ምክንያት የቆንጆ ወንድ መለኪያው ጀግንነት መሆኑ ቀረና ሱሪን ከጪን ታጥቆ መዥገር እንደ ሸበባት ግታም ላም እየተውለደለዱ መራመድ ሆነና አረፈው፡፡

ይህ ጀግና አምራች ባህል ከአምስቱ ዘመን ድል ማግስት ጀምሮ በምዕራባውያን የባህል ጎርፍ እንደ ዓባይ ሸለቆ ዳገት መሸርሸር ቢጀምርም ጭራሹን የተጠረገው አማራን በጠላትነት የፈረጀ የወንበዴዎች አገዛዝ ከመጣበት ሶስት አስርተ ዓመታት ወዲህ ነው፡፡ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ቀረርቶና ፉከራ በሬዲዮና በቴሌቪዥን ብቻ ሳይሆን በሰፈርና በመንደርም እንዳይሸለል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ተከለከለ፡፡ በዚህ ክልከላ ምክንያትም ይህ ጀግናን እንደ አሳ ገንዳ የሚያራባው ባህር እንደ ጣና በእምቦጭ ተመጦ እንዲደርቅ ትልቅ ሴራ ተሸረበ፡፡ በዚህ ሴራም አዲሱ ትውልድ በቀረርቶና በፉከራ አይምሮንን በጀግነት እንዳያንፅ በምዕራባውያን አጉል ሱስ ተጠምዶ በባህል ሸቀን እንዲቆሽሽ ተደረገ፡፡

ወጣቱ እንደ አያቶቹ በጀግንነት እንዲታነፅ ይህ የባህል ቆሻሻ በሕዝባዊ ዘመቻ መጠረግ ይኖርበታል፡፡ የባህል ቆሻሻው በበረኪና ታጥቦ ወጣቱ በራሱ የባህል ባህር መዋኘት ሲጀምር እንደ አያቶቹ እንኳን ራሱን ሌሎችንም ኢትዮጵያውያን በጎርፍ ከመጠረግ ያድናል፡፡ ከሸረኞች ደባ የፀዳ ባህል እንደ አያቶችህ ቆራጥ፣ ታማኝና ሩህሩህ ጀግኖችን ያፈራል፡፡ ባህልህ ከቆሻሻ ሲፀዳ በእግዚአብሔር ሚዛን የሚፈርዱ ሽማግሌዎችና ዳኞችን ይፈጥራል፡፡ ከተንኮለኞች ሸቀን የፀዳ ባህል ሲኖርህ እንደ ጥንቱ ለቆባቸው የሚያድሩ ሼሆችና መነኩሴዎች ይኖሩሃል፡፡ ከባህል እድፍ የፀዳ ባህል ሲኖር የሰው የማይነካ የራሱንም የማይሰጥ ኩሩና ሙሉ ትውልድ ይገነባል፡፡

ወጣት ሆይ! ስለዚህ ለህልውናህም ሆነ ለክብርህ ወደ ባህልህ መመለስ ይኖርብሃል፡፡ ሱሪህን ከጪንህ ከፍ አድርገህ ከወገብህ በቀበቶ ማጥበቅ ይጠበቅብሃል፡፡  በባዕዳን ዳንስ እንደ ማይክል ጃክሰን እንደ ጥንዚዛ መፈናጠሩን ትተህ እንደ ሞላ ሰጥአርጌ በሽለላና በፉከራ መንጎራደድ ይኖርብሃል፡፡

ወጣት ሆይ! ወደ ባህልህ ተመልሰህ የቅድመ አያቶችህን ዱካ ስትከተል የማትወጣው ተራራና የማትሻገረው ባህር አይኖርም፡፡ ከፊትህ የተገተረው ተራራ ከኦቶማን ኢምፓየዬር ወይም ከአውሮጳውያን ቅኝ ገዥዎች አጠገብ የሚደርስ አይደለም፡፡ ይኸንን ዳገት ሜዳ ማድረግ አቅቶህ ሕዝብህንም ሆነ ቅርሶችህን ማስፈጀት አይኖርብህም፡፡ ዓለም በሚያንቀላፋበት ዘመን ቅደመ-አያቶችህ የጠበቡትን ላሊበላን ማደስ አቅቶህ እንደ አይምሮ በሽተኛ ፈረንሳይን እየለመንክ ክብርህን እንደ ድሪቶ መጣል የለብህም፡፡ እሳት ማጥፋት አቅቶህ በአያቶችህ እርዳታ ትናንት ነፃ የወጡትን ደቡብ አፍሪካውያን እንደ ዕድ-አልባ

“በእይነተ- ስመዓለማርያም” እያልክ የዓለም መሳቂያ መሆን አይኖርብህም፡፡ የሙሴ ጽላት ለስምንት መቶ ዓመታት የተጠለለበት፣ የብዙ የሃይማኖትና ፍልስፍና መዛግብት የሚገኙበትና የእልፍ አእላፍ ፍጥረታት መኖሪያ የሆነው ጣና ሲደርቅ እንደ ባዕድ ቆመህ ማየት የለብህም፡፡

ወጣት ሆይ ህልውናህም ሆነ ክብርህ ያለው ከባህልህ ነውና ለህልውናህና ለክብርህ  ወደ ባህልህ! አመሰግናለሁ፡፡

ሚያዚያ ሁለት ሺ አስራ አንድ ዓ.ም.

ቄሮ ሳይፈጠር ፣ አዲስ አበቤ የህወሃትን ስናይፐር እየተጋፈጠ ፣ ደሙን ሲያፈስ ፣ ቄሮ የት ነበር?

ለቄሮ ትግል ያስተማረው ፣ ማን ሆነና ነው?

በ1997 በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ ፣ የፈሰሰው ደም የማነውና ነው?

=====================

ይህንን ሚያዝያ 30/1997 ዓም የተደረገው ሰላማዊ  ሰልፍ በተመለከተ:
1/ ይህ የአንድነታችን ታሪክ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው።ይህንን ታሪክ ማደብዘዝ በእራሱ አደጋ ነው።የፌስ ቡክ ባለቤቶች በሙሉ በመለጠፍ ትውልዱን ኢትዮጵያዊነት አለመሞቱን በዘመናችን ይህ ታሪክ ከሆነ ገና 11 ዓመቱ ነው አይዞን ማለት ተገቢ ነው ኢትዮጵያ አለች።ለዘላለምም ትኖራለች።
2/  ይህ ሁሉ ሰልፈኛ በ11 ዓመታት ውስጥ ካለፉት ከጥቂቶቹ በቀር ሌላው አሁንም ከእዚህ የለውጥ ፍላጎት አንዳች ስንዝር ወደኃላ እንዳላለ ለማወቅ ሳይንቲስት መሆን አያስፈልግም።
3/ በሚልዮን የሚቆጠር ሕዝብ ሰልፍ ወጥቶ አንዳች የዘረፋ ወይንም ንብረት መውደም ተግባር ሳይፈፀም በሰላም የገባ ሕዝብ ነው።አስደናቂ እና ታሪካዊ ሰልፍ።