ኢትዮጲስ — ከአረንጓዴ ወደ ቢጫ መብራት ( ከጋዜጠኛ ወሰንሰገድ መርሻ)

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን  ዶክተር አብይ ስልጣኑን ከአቶ ኃይለ ማርያም  ከተረከቡ ጊዜ አንስቶ ከታዩ ለውጦች መካከል ከተዘጉ ድህረ ገጾችና ብሎጎች በተጨማሪ ለበርካታ አመታት ከገቢያ ውጪ የነበረችው የነፃው ፕሬስ  ፈር ቀዳጅ የሆነችው የ«ኢትዮጲስ» ጋዜጣ አዘጋጅና ባለቤት መፈታትና ጋዜጣው የመጀመሩ ሁኔታ ይገኛል  ።  የጋዜጣው ባለቤትና አዘጋጅ  የሆነው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ለበርካታ አመታት በእስር ሲማቅቅ ከቆየ በኋላ ከእስር ተፈቶ ጋዜጣውን ከጀመረ 36  እትሞችን ለተደራሲዮና አቅርቧል ።ይህም በወራት ሲሰላ  ጋዜጣው 9 ወራትን አስቆጥሯል።  «ኢትዮጲስ» የነፃው ፕሬስ ፈር ቀዳጅ በመሆኗም ትታወቃለች።ዛሬ ጋዜጣዋ እዚ ደረጃ የደረሰችው እስክንድርን ጨምሮ በርካታ ጋዜጠኞች መስዋትነት ከፍለው ነው።በተለይም ነፍሳቸውን ይማረውና ዛሬ በሕይወት የሌሉት ወዳጆቼ ጋዜጠኛ ተፈራ አስማረና ጋዜጠኛ ወርቁ አለማየሁ ዋናና ምክትል አዘጋጅ ሆነው፤ጋዜጠኛ ጌታመሳይ ገመስቀል(ኩሹ) ደግሞ ጋዜጣውን በማከፋፈል (በርካታ ተዋቂ መጽሔትና ጋዜጣ አከፋፋዮችን ፍቃዱን((ባሪያውን) ፤መኮንንን ወዘተ.ያፈራ ጭምር ነው) ከእስክንድር ጋር በመሆን ትልቅ አስተዋጾ በወቅቱ አድርገዋል።

  እነዚህ የሞቱ የ«ኢትዮጲስ» ባለውለተኞች እንደ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ጥሩ ወዳጆቼ ብቻ ሳይሆን ጥሩ ቀረቤታ እስከ ቤተሰብ  ጭምር ድረስ ነበረን ። አራት ኪሎ ከመፈራረሱ በፊት።ከተፈራ አስማረና ከጌታመሳይ (ኩሹ) ጋር አንድ አካባቢና አንድ ቀበሌ ውስጥ መኖር ብቻ አይደለም የሰፊ ሰፈርና የቀበሌ 07 ዕድር ውስጥ በቤተሰብ ደረጃ በሐዘንም በደስታም ተካፋይ አብረን ነበር ከተፈራ አስማረ ወንድሞች ከሞቱት ከአምባውና ከቴዲ ከሌሎቹ እህቶቹ ጋር ቀረቤታ ነበረኝ ከዚህ ሌላ ከአባቱ   ከአቶ አስማረ ጋር ነፍሱን ይማረውና የአባቴ ጓደኛና የሰፊሰፈር ዕድር ሰብሳቢ ሽባቱ ስለነበሩ በደንብ እግባባ ነበር።ከጌታ መሳይ(ከኩሹ) ጋር አብሮ አደጌ ብቻ ሳይሆን አብረን ብሔራዊ ውትድርና ከመሄዱ በፊት አንድ ክፍል ውስጥ  ተምረናል። ኩሹ የሚለው ቅፅል የወጣለት በብርቱካን ልጣጭ ክብ ሰርተን በሳንቲም ስንጫወት ሁሌ ይህን ጨዋታ ስለሚወደው በዛው ኩሹ አልነው። ወደ ግሉ ጋዜጣ እንድገባ  ያደረጉኝም የሁለቱም  ወዳጆቼ አስተወጾ አለበት። በተለይም ከደርግ ጊዜ ጀምሮ በሬዲዮና በቴሌቪዥን እንዲሁም በዛሬይቱ ኢትዮጵ ጋሽ አያሌው የሚያዘጋጀው የመስታወት አምድና ሌሎች አምዶች ላይ ፣በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ግርማ የሚያዘጋጀው ለወጣቶችጋሽ ክፍሌ ሙላት የሚያዘጋጀው አድማስና ሌሎችም አምዶች ላይ ።ኢትዮጵያን ሄራልድ ( Just A Few  Point) የሚለው የጋሽ አረፋይኔ  አምድ ላይ ብዙ ስለምጽፍ እውቅናውም ሆነ ችሎታውም ስላለ ቶሎ ነፃው ፕሬስ ውስጥ ለመቀላቀል አልፈጀብኝም ተፈራ አስማረን መጀመሪያ የተዋወኩትም በኢትዮጵያ  ቴሊቪዥን ልጅ ሆኜ «ለ«ወጣቶች» የሚለው ፕሮግራም ላይ ጽሑፎችን እየላኩ በሚቀርብበት ወቅት ነበር።  ከጌታ መሳይ ((ከኩሹ) ጋር እሱም በእራሱ በሚያሳትመውና በሚያዘጋጀው የፖለቲካ ጋዜጣ እኔም በተመሳሳይ በማሳትመው የፖለቲካ ጋዜጣ ከአንድም ሁሉቴ  አዲሱ ገቢያ በሚገኘው ወረዳ 10 ፖሊስ ጣቢያ  በማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ(ደንነት) ቢሮ አማካይነት በተውሶ ለሦስት ወራት ያህል ሳይፈረድብን  ምርመራ ላይ እያለን የተለዩዩ ጥያቄዎች ስንጠየቅ ጨለማና ቀዝቃዛ ቤት ውስጥ  ፀጉራችንን ተሸልተን ኬሻ ላይ አብረን እየተኛን ያሳለፍነውን ጊዜ የዛሬን አያድርገውና ጥሩ ትዝታ ያለው እስር አሳልፈን ነበር።  ነፍሱን ይማረውና ጋዜጠኛ ወርቁ አለማየሁን ደግሞ  «መብረቅ» የተሰኘውን ጋዜጣን ከመጀመሩ በፊት «ኢትዮጲስ» ላይ ምክትል ሆኖ የሰራ ነበር። ከዛ በፊት ግን ከወርቁ ጋር የምንተወወቀው የቀድሞ ብስራተ ወንጌል (ዓለም አቀፍ ሬዲዮ) ላይ ነው።እሱ የስፖርት አዘጋጅ ሆኖ እኔ ደግሞ የቅዳሜ የመዝናኛ ፕሮግራም ላይ በወቅቱ አዘጋጅ የነበሩት የጀርመን ጋዜጠኛ የሆነችው ሂሩት መለሰ፤ የአቡነ ጴጥሮስ የጋዜጠኞች አስተማሪ የነበሩት አስፋው ገረመውና አማኑኤል በሚያዘጋጁት ከአንድ ሰዓት ያነሰ ጣፋጭ ፕሮግራም ላይ  ተሳታፊ ሆኜ በተለይም በየ15 ቀን አንዴ በድምፅ የማቀርበው ቋሚ ፕሮግራም ስለነበረኝ እሱን ለማቅረብ ስሄድ ነው የተዋወቅነው።በወቅቱ ተማሪ ብሆንም ስፖርቱ ውስጥ አማተር ሆኜ በርካታ ስፖርቶች ላይ እንቀሳቀስ ስለንበር የወርቁ በሬዲዮ ላይ  ስፖርት ማዘጋጀት የእኔ ስፖርቱ ውስጥ መሳተፍ ይበልጥ እንድንቀራረብ አድርጎን የሀገር ውስጥ የስፖርት ወሬዎችን ለወርቁ በማቀበል  ከመዝናኛው ፕሮግራም ባሻገር ስፖርቱ ላይ በመሳተፍ ይበልጥ ትውውቃችን  ከወርቁ ጋር እንዲቀጥል አድርጎታል።ወርቁ የስፖርት ጋዜጠኝነቱን የከተበኝ እሱ ነው ማለት እችላለሁ።   እንዚህ በሞት የተለዩን ሦስት ጋዜጠኞች ከ«ኢትዮጲስ» ጋዜጣ ጀርባ የነበሩ በመሆናቸው የጋዜጣው ስም ሲነሳ አብረው ሊነሱ የሚገቡ ናቸው።   እስካሁን በኢትዮጵያ የነፃ ፕሬስ ታሪክ ከመቶ ሺህ በላይ የታተመ ጋዜጣ፤አንድ ጋዜጣ እንደዛሬ 10 ብር ከመግባቱ በፊት አንድ ብር የነበረው ዋጋ እስከ 100 ብር በጥቁር ገቢያ ያውም በደላላ እስከ መሸጥ የበቃ ጋዜጥ «ኢትዮጲስ» ጋዜጣ ብቻ ነበር ብል የተሳሳትኩ አይመስለኝም።   በ«ኢትዮጲስ» ጋዜጣ ብቻ ሳይሆን በምኒልክ፣በአስኳል፣በሳተናው፥በአበሻና በሌሎችም በአማርኝና የእንግሊዘኛ ጋዜጣ ላይ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የከፈለው መስዋዕትነት የከፈለ የፕሬሱ የቁርጥ ቀን ልጅ ነው።እስክንድር  የፖለቲካ ጋዜጣ አቁሜ ስፖርት ስጀምር «ሳንጆርጅ» የሚለውን የጋዜጣዬን ስያሜ ያወጣልኝ እሱ ነበር።እስክንድርንም እንደ ሞቱት ሦስት ጋዜጠኞች በደንብ አውቀዋለሁ ።ለቆመበት አላማ ወደ ኋላ የማይል ፤ደፋር ፤ሚዛናዊ አድርጎ ለመስራት የሚጥር፤ሰውን ለመርዳት ወደ ኋላ የማይል ፤ከራሱ ይልቅ ለሰው ሲል እራሱን መስዋዕት የሚያደርግ ፤ኅይማኖተኛ፤በሥራው ላይ ካልመሰለው ፊት ለፊት ሁኔታውን ተናግሮ ጥሎ የሚሄድ፤ሰውን ማስቀየም የማይፈልግ ፤ሰውን አክባሪ ጋዜጠኛ ነው። እስክንድርን ከውጪ ከመጣው በኋላ ሁለት ጊዜ አግኝቼዋለሁ  አሁንም ያው ነው አልተለወጠም አሁንም «ኢትዮጲስን» ጋዜጣ ለመስራት  ደከመኝ ሰለቸኝን አይልም፤ ጋዜጣው እንደሌሎቹ የፖለቲካ፡የስፖርት ጋዜጦችና መጽሔቶች ማስታወቂያ ወይንም ስፖንሰር የሚያደርገው አካል ሳይኖረው ነው ጋዜጣውን ያለማቋረጥ የሚሰራው። አንዳንድ ጋዜጦች በየሳምንቱ 500 እና 700 ጋዜጣ በኪሳራ እያሳተሙ ገቢያ ላይ ያሉ ጋዜጦች እንዳሉ አውቃለው፤በየቢሮ የሚሰራጩ ጋዜጦችም ልክ አንድ አዲስ ዘመን የሚሰራጩም ጋዜጦች አሉ። የእስክንድር ነጋ ግን «ኢትዮጲስ» ከዚህ በተቃራኒ ነው። ያውም የኅትመት ዋጋ በየጊዜው በሚጨምርበት በኢትዮጵያ ያውም ብርሀንና ሰላም ማተቢያ ቤት ነው   አንድም ማስታወቂያ ሳይኖረው ጋዜጣውን እያሳተመ የሚገኘው።ያለምንም ድጎማ ከእስር ከተፈታ በኋላ ለዘጠኝ ወራት መዝለቁ የጋዜጠኛን እስክንድር ነጋን ጉብዝናንና ጥንካሬውን የሚያሳይ ነው።   ባለፈው ቅዳሜ ግንቦት 17 ቀን 2011 ዓ/ ም በወጣው አዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ «የኢትዮጲስ ጋዜጠኛ በፖሊስ ድብደባ እንደተፈፀመበት ገለፀ» ይህን  የ“ኢትዮጵስ” ጋዜጠኛ በፖሊስ ድብደባ እንደተፈፀመበት ገለፀ –

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s