ቅዱስ ሲኖዶስ የሦስት ቀናት ጸሎት እና ምሕላ ዐወጀ

 • አገሪቱን ለከፍተኛ ጥፋት እና ድህነት የሚዳርግ እጅግ አሳሳቢ ግጭት እየተስፋፋ ነው፤
 • የጸጥታ ኀይሎች ቅድመ ግጭትን መሠረት ላደረገ መከላከል ትኩረት እንዲሰጡ ጠየቀ፤
 • ሐሰተኛ ትርክቶች ለግጭት መንሥኤ ናቸው፤ ምሁራን የድርሻቸውን ሊወጡ ይገባል፤
 • ሶሻል ሚዲያውን ለሰላም፣ አንድነትና ተግባቦት በመጠቀም ኹሉም የበኩሉን ይወጣ፤

***

በአገራችን እንኳንስ ሊደረጉ ቀርቶ ሊታሰቡ የማይገባቸው ጎሣንና ሃይማኖትን መሠረት ያደረጉ መጠነ ሰፊ ግጭቶች በተለያዩ ክልሎች እየተስፋፉ መኾኑ በእጅጉ ያሳሰበው ቅዱስ ሲኖዶስ፣ ከዛሬ ጥቅምት 13 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ ለሦስት ቀናት ጸሎት እና ምሕላ እንዲደረግ ዐዋጀ፤ ከመንግሥት የጸጥታ ኀይሎች አንሥቶ ኹሉም አካላት እና ዜጎች በየድርሻቸው ለአገራዊ ሰላም፣ አንድነት እና ተግባቦት የድርሻቸውን እንዲወጡ የሰላም ጥሪ አስተላለፈ፡፡

ወቀተወ መገለጨ

የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም፡ የምልአተ ጉባኤውን የጸሎተ ምሕላ ዐዋጅ እና አስቸኳይ የሰላም ጥሪ መግለጫ በንባብ ሲያሰሙ

ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባውን በማካሔድ ላይ የሚገኘው ምልአተ ጉባኤው፣ የምሕላ ዐዋጁንና የሰላም ጥሪውን ያስተላለፈው፣ ዛሬ ኀሙስ፣ ጥቅምት 13 ቀን 2012 ዓ.ም. ረፋድ፣ “ተገሐሥ እምዕኵይ ወግበር ሠናየ፤ ከክፉ ነገር ራቅ፤ ሰላምን ፈልጋት” (መዝ.33፥12) በሚል ርእስ በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ በሰጠው አስቸኳይ መግለጫው ነው፡፡

የበርካቶች ሕይወት ከጠፋባቸውና ንብረት ከወደመባቸው፣ ዜጎች ለከፋ እንግልትና እርዛት ከተዳረጉባቸው የቀደሙ ግጭቶች ባለመማር፣ አሁንም በኦሮሚያ ክልልና በአዲስ አበባ ዙሪያ ከተሞች እንዲሁም በሌሎችም ክልሎች፣ በአገራችን ላይ ከፍተኛ ጥፋትና ድህነት የሚያደርሱ መጠነ ሰፊ ግጭቶች መበራከታቸው በእጅጉ እንዳሳሰበው ቅዱስ ሲኖዶሱ ገልጿል፡፡

የአማራ እና የቅማንት፣ የአማራ እና የጉሙዝ፣ የአማራ እና የትግራይ፣ የሶማሌ እና የአፋር፣ የኦሮሞ እና የአማራ፣ የሲዳሞ እና የወላይታ እየተባሉ የተደረጉ ግጭቶች ኹሉ፣ “ምክንያታዊ ባልኾኑ ጉዳዮች መነሻነት” የተከሠቱ እንደ ኾኑ ምልአተ ጉባኤው በመግለጫው አስፍሯል፡፡

ከእውነታ የራቁ፣ የሕዝቡን የአንድነት እና የአብሮነት ባህል የሚጎዱ፣ ታሪክን የሚያፋልሱ ሐሰተኛ ትርክቶች ለግጭቶች መንሥኤ እንደኾኑ ጠቅሶአል፤ የፖለቲካ ኀይሎች፣ የብዙኀን መገናኛዎች፣ የሶሻል ሚዲያው ተጠቃሚዎች እንዲሁም ምሁራንና የመንግሥት የሥራ ሓላፊዎች፣ ብሔርንና ሃይማኖትን መሠረት ካደረጉ የትንኮሳ ቃላት ተቆጥበው፣ ከልዩነትና ግጭት ይልቅ ለሀገራዊ አንድነትና ተግባቦት የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪውን አስተላልፏአል፡፡

የጸጥታ እና የፍትሕ አካላት፣ ግጭቶች እና አለመግባባቶች ከመከሠታቸው በፊት፣ ቅድመ መከላከልን መሠረት ያደረገ የጸጥታ ሥራን በመተግበር፣ የሰው ሕይወት መጥፋትንና የንብረት ውድመትን በማስቀረት የተጣለባቸውን ሓላፊነት እንዲወጡ ቅዱስ ሲኖዶሱ በአስቸኳይ መግለጫው ጠይቋል፡፡

73495093_1703173283152293_4840485604959453184_n
73125467_1703173246485630_8801642536566259712_n

ያለሀገር ሰላም እና አንድነት እንዲሁም ፍቅር እና ተግባቦት መኖር የማይቻል በመኾኑ፣ ኹሉም እንደየእምነቱ እና የሃይማኖቱ ሥርዐቱ፣ ከዛሬ ጥቅምት 13 ቀን ጀምሮ ለሦስት ቀናት ያህል በጸሎት እና በሐዘን፣ ስለ ሀገር ሰላም በአንድነት ልመናውን ለፈጣሪ ያቀርብ ዘንድ፣ ጸሎት እና ምሕላ እንዲያደርግ ማወጁን ምልአተ ጉባኤው በአስቸኳይ መግለጫው አስታውቋል፡፡

‡‡‡‡‡‡‡‡‡‡‡‡‡

የሀገራችንን ወቅታዊ ጉዳይ አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የተላለፈ የሰላም ጥሪ

“ተገሐሥ እምዕኲይ ወግበር ሠናየ = ከክፉ ነገር ራቅ ሰላምን ፈልጋት” (መዝ.3312)

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መሥራቿና አምላኳ የሰላም አባትና አለቃ የሆነው ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደመሆኑ በጸሎቷና በአገልግሎቷ ስለ ሀገር ሰላም፣ ስለ ሕዝቦቿና ስለ መላው ዓለም ሰላም ዘወትር ወደአምላኳ ስታማጽንና ስትማልድ የኖረች ያለችና ወደፊትም የምትኖር የሀገር ባለውለታና የሁሉም እናት መሆኗ ይታወቃል፡፡

ይሁን እንጂ በሀገራችን በተለያዩ ክልሎች ልዩ ልዩ ምክንያቶች የአማራና የቅማንት፣ የሱማሌና የአፋር፣ የአማራና የትግራይ፣ የኦሮሞና የአማራ፣ የጉምዝና የአማራ፣ የሲዳሞና የወላይታ በሚል ብሔርና ሃይማኖትን እንዲሁም ቋንቋን መሠረት ያደረገ በኢትዮጵያ ሀገራችን እንኳንስ ሊደረጉ ይቅርና ሊታሰቡ የማይገባቸው መጠነ ሰፊ ግጭቶች በመከሠታቸው የሰው ሕይወት ጠፍቷል፤ በርካታ ንብረት ወድሟል፤ ዜጎች ከቀዬአቸው አለአግባብ እየተፈናቀሉ ለከፋ እንግልትና እርዛት ተዳርገዋል፡፡

እስከ አሁን ድረስ በግጭቶች እየደረሱ ካሉት የሰው ሕይወት ጥፋትና የንብረት ውድመት ልንማር ባለመቻላችን በያዝነው ሳምንት ችግሩ ቀጥሎ በአዲስ አበባ፣ በኦሮምያ ክልልና በሌሎችም ክልሎች እየተሠከተ ያለው ግጭት እጅግ አሳሳቢ ከመኾኑም በላይ ጊዜ የማይሰጥና ሁሉም ኢትዮጵያውያን በአንድነትና በሕብረት ችግሩን ካልቀረፍነው መጠነ ሰፊ ጉዳትን የሚያስከትል ከመሆኑም በላይ በሀገራችን ያሉ ጅምር የልማትና የእድገት ጉዞዎችን በመግታት ሀገሪቱን ለከፍተኛ ጥፋትና ድህነት የሚዳርግ እጅግ አሳሳቢ ጉዳይ በመሆኑ ዓመታዊ ስብሰባውን በማካሄድ ላይ የሚገኘው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ስለ ሀገር ሰላም ቅድሚያ በመስጠትና ከሌሎች የመወያያ አጀንዳዎች በማስቀደም በጉዳዩ ላይ በስፋት ከተወያየ በኋላ ተከታዩን አስቸኳይ የአቋም መግለጫና የሰላም ጥሪ አስተላልፏል፡፡

1. ማንኛውም የተለየ ሐሳብና አመለካከት ያለው ወገን ቢኖር ሐሳቡን በሠለጠነና በሰከነ መንገድ ሀገራዊ አንድነትን ማእከል ባደረገ ኹኔታ በክብ ጠረጴዛ በመወያየት ችግሮቹ እንዲፈቱና የአሠራር ግድፈቶች ካሉም እንዲታረሙ እንዲደረግ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ያሳስባል፤

2. የሀገር ተረካቢ የኾናችሁ መላው የኢትዮጵያ ወጣቶች፣ ሀገራችኁ ኢትዮጵያ ከዛሬ ይልቅ ነገ በእናንተ ተተኪነትና በምታከናውኑት የማይተካ የላቀ አስተዋፅኦ ወደ ላቀ የዕድገት ደረጃ ደርሳ እናንተም ኾናችኁ መላው ወገናችሁ ተጠቃሚ የሚኾንባት የበለጸገች ኢትዮጵያን ለመገንባትና እውን ለማድረግ የሀገሪቱ ሙሉ ተስፋ በእናንተ በወጣት ልጆቻችን ትከሻ ላይ የተጣለ መኾኑ ይታወቃል፤ በመኾኑም በወቅታዊና ሚዛናዊ ባልኾነ አንዳንድ ከሕግ ማሕቀፍ የወጡ አካሔዶችን በሰከነ አእምሮ ትኩረት በመመልከት ሀገራችን ኢትዮጵያን ከጥፋትና ካልተገባ ግጭት ትታደጓት ዘንድ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከአደራ ጋር በአጽንኦት ለእናንተ ለልጆቿ ጥሪዋን ታስተላልፋለች፤

3. በሀገራችን ኢትዮጵያ የተፈጠረውን የመድበለ ፓርቲ ሥርዓት ተከትሎ ለሀገራችሁ የሚሆን ልዩ ልዩ አማራጭ ሐሳቦችን በማመንጨት ሕጋዊ እውቅና አግኝታችሁ በመንቀሳቀስ ላይ የምትገኙ ሁላችሁም የፖለቲካ ፓርቲዎች በሙሉ ፖሊሲ ቀርጻችሁና ያመናችሁበትን ርዕዮተ ዓለም አቅዳችሁ የምትንቀሳቀሱት ሀገራችሁ ኢትዮጵያ ወደተሻለ የእድገት ደረጃ እንድትደርስ የበኩላችሁን ድርሻ ለመወጣት መሆኑ አያጠያይቅም፡፡ ከዚህ አንጻር በየጊዜው ዘር፣ ብሔርና ሃይማኖትን መሠረት አድርገው እየተከሰቱ ያሉ ግጭቶችን ከጅምሩ በአንድነት ማስቆም ካልተቻለ ነገ የምትረከቧትና የምታስተዳድሯት ሀገር ልትኖር ስለማትችል በቅድሚያ የፖለቲካ አመለካከት ልዩነት ሳይገድባችሁ ለሀገር ሰላምና አንድነት በሕብረት ዘብ በመቆም የበኩላችሁን ኃላፊነት ትወጡ ዘንድ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪውን ያስተላልፋል፤

4. ለመንግሥታችሁና ለሕዝባችሁ ሞያዊ ትንታኔን መሠረት ያደረገ አማራጭ ሐሳቦችን በግብዓትነት በማበርከት የሀገራችንን እድገትና የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ወደተሻለ ደረጃ እንዲደርስ የበኩላችሁን አስተዋፅኦ ለማበርከት በማሰብ ልዩ ልዩ ጽሑፎችንና ዘገባዎችን በመገናኛ በዙኃንና በማኅበራዊ ሚዲያ የምታቀርቡና የምታስተላልፉ የፖለቲካ ተንታኞችና አክቲቪስቶች ከስሜት፣ ከብሔር፣ ከቋንቋና ከሃይማኖት ልዩነት በጸዳ ሁኔታ እናት ሀገራችሁን ማዕከል በማድረግ ለተሻለ ሰላምና አንድነት የበኩላችሁን ድርሻ ከማበርከት ባለፈ ሕዝብን ከሕዝብ የሚያጋጩና አንዳንድ ያልተገቡ ትርክቶችን አላግባብ ከማሰራጨት በመቆጠብ ሀገራዊ ግዴታችሁን እንድትወጡ እናሳስባለን፤

5. የመንግሥትም ኾነ የግል የመገናኛ ብዙኃን ድርጅቶች ከተቋቋማችሁበት መሠረታዊ ተልዕኮና ዓላማ አንጻር በተቻለ አቅም ዘርን፣ ቀለምን፣ ብሔርንና ሃይማኖትን መሠረት ካደረጉ የትንኮሳ ቃላቶች በመራቅና ሚዛናዊ የሆኑ መረጃዎችን ለሕዝባችን በማድረስ ለሀገራችን ኢትዮጵያ ሰላምና አንድነት የበኩላችሁን ኃላፊነት እንድትወጡ አደራ እንላለን፤

6. የማኅበራዊ ሚዲያ መሠረታዊ ዓላማው ዜጎች በእውነታ ላይ የተመሠረቱ ወቅታዊ መረጃዎችን በተሻለ ፍጥነት እንዲያገኙ ታስቦ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ግን በሀገራችን ኢትዮጵያ እየታየ ያለው እውነታ ከዚህ በተለየ መልኩ ሕዝብን ከሕዝብ፣ ብሔርን ከብሔር፣ ጎሳን ከጎሳ ሃይማኖትን ከሃይማኖት የሚያጋጩና ከእውነት የራቁ ግጭት ቀስቃሽ ሐሰተኛ መረጃዎችን በማሠራጨት ሀገራችን ኢትዮጵያ የቆየ የአብሮነትና የአንድነት ባህሏን በሚያጎድፍ መልኩ ላልተገባ ዓላማ እየዋለ መሆኑ አጠያያቂ አይደለም፤ ከዚህ አንጻር ዛሬ በሌሎች ላይ የሚደርሰው የሰው ሕይወት መጥፋትና የንብረት ውድመት ነገ በየአንዳንዱ ቤት ሲያንኳኳ ሁሉም የጉዳቱ ሰለባ እንደሚሆን በመረዳት በተቻለ አቅም የማህበራዊ ሚዲያውን ለሀገራዊ ሰላምና አንድነት በመጠቀም ሁሉም የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚው ሕዝባችን የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ እንጠይቃለን፤

7. ሀገር በእውቀት እና በተሻለ ሐሳብ የምታድግና የምትመራ መሆኑ አጠያያቂ አይደለም፡፡ ከዚህ አንጻር የሀገራችን ምሁራን ያላቸው ድርሻ በቀላሉ ሊገመት የማይችል ሲሆን በአሁኑ ወቅት ግን አንዳንድ ምሁራን የሚያስተላልፏቸው የኢትዮጵያን ታሪክ መሠረት ያላደረጉ ትርክቶች ለሀገራችን የግጭትና ያለመግባባት መንሥኤ ሲሆኑ ይስተዋላሉ፡፡ በመኾኑም የሀገራችን ምሁራን በተቻለ አቅም ከልዩነትና ከግጭት ይልቅ ለሀገራዊ አንድነት እና ሰላም ሓላፊነታችሁን እንድትወጡ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፤

8. በየደረጃው ያላችሁ የመንግሥት የሥራ ሓላፊዎች መላው ሕዝባችን ትመሩትና ታስተዳድሩት ዘንድ የሰጣችሁን ይኹንታና ሀገራዊ ሓላፊነት ከግምት ውስጥ ባስገባና በታላቅ ሀገራዊ ሓላፊነት ስሜት በተቻለ መጠን ግጭቶችና አለመግባባቶች ከመከሠታቸው በፊት ልዩ ልዩ የውይይት መድረኮችን ለመላው ሕዝባችሁ በማዘጋጀት እና በውይይት መድረኩ የሚገኙትን ግብአት የዕቅዳችሁ አካል አድርጋችሁ በመተግበር ሓላፊነታችሁን ከቀድሞው በተሻለና በላቀ ሁኔታ በመፈጸም ለሀገራችን ሰላምና አንድነት ዕድገትና ብልጽግና የድርሻችሁን እንድትወጡ እንጠይቃለን፤

9. በየደረጃው ያላችሁ የፀጥታና የፍትሕ አካላት ሁሉ በተለያዩ ቦታዎች ግጭቶችና አለመግባባቶች ከመከሠታቸው በፊት ቅድመ መከላከልን መሠረት ያደረገ የፀጥታ ሥራን በመተግበር እየተከሠቱ ያሉ ግጭቶችንና የሰው ሕይወት መጥፋትን እንዲሁም የንብረት ውድመትን በመከላከል የተጣለባችሁን ሓላፊነት እንድትወጡ እናሳስባለን፤

10. መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ! እስከ አሁን ድረስ የኢትዮጵያን ሰላም በማይወዱ አካላት የሚከሠቱ ልዩ ልዩ አፍራሽና ግጭት ቀስቃሽ አጀንዳዎችን ወደ ጎን በመተውና በአርቆ አሳቢነትና በሀገር ባለቤትነት መጠነ ሰፊ ትዕግሥት የተሞላበት ሀገራዊ አንድነትና ኅብረት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ላበረከታችሁት የማይተካ ሚናና ታሪክ የማይረሳው ውለታ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በቤተ ክርስቲያኒቱ ስም እያመሰገነ እንደ አሁን ቀደሙ ሁሉ ለሀገራችን ሰላምና አንድነት ዘር፣ ብሔርና ሃይማኖት ሳይለያያችሁ እጅ ለእጅ በመያያዝ የበኩላችሁን የማይተካ ድርሻ እንድትወጡ የአደራ መልእክታችንን እናስተላልፋለን፤

11. በሀገራችን ኢትዮጵያ የምትገኙ የሁሉም የሃይማኖት ተቋማት ሀገራችን ኢትዮጵያ በሃይማኖት ብዝኀነትና ተቻችሎና ተከባብሮ በመኖር አስደናቂ ባሕሏ ሌሎች ሀገራት የሚቀኑባትና በአርኣያነትም የሚጠቅሷት ሀገር መሆኗ ይታወቃል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ይህን አኩሪና አርኣያ የሆነ ታሪኳን በሚያደበዝዝ ሁኔታ ሃይማኖትና ብሔርን መሠረት ያደረጉ ግጭቶች እየተበራከቱ በመሆናቸው ዜጎች ያለምንም መሸማቀቅና ተጽዕኖ እምነታቸውን ለማምለክና ለማስመለክ የማይችሉበት የስጋት አደጋ እየተጋረጠ ከመሆኑ አንጻር ሁሉም ቤተ እምነቶች ለሀገራዊ አንድነትና ለእምነት ነጻነት በአንድነትና በሕብረት ለመላው ሕዝባችን የሰላም ጥሪ በማስተላለፍና ዘወትር በየአስተምህሮአችን ለሕዝባችን የሰላምን ጥሪ ተደራሽ በማድረግ ሀገራዊ ኃላፊነታችንን እንወጣ ዘንድ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፤

12. በመጨረሻም ያለ ሀገር ሰላምና አንድነት እንዲሁም ፍቅርና ዕድገት መኖር ስለማይቻል መላው ሕዝባችን እንደየእምነቱና ሃይማኖቱ ሥርዓት ከዛሬ ጥቅምት 13 ቀን 2012ዓ.ም. ጀምሮ ለ3 ቀን ያህል በጾም፣ በጸሎትና በሐዘን ስለ ሀገር ሰላም በአንድነት ጥሪውን ለፈጣሪውና ለአምላኩ ያቀርብ ዘንድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ጸሎትና ምህላ እንዲደረግ በቤተ ክርስቲያኒቱ ስም ጥሪውን አስተላልፏል፤ መንፈሳዊ ዐዋጁንም ዓውጇል፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤ አሜን፡፡

ጥቅምት 13 ቀን 2012 .

አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ


የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ለመሥዋዕትነት ሞት እንዲዘጋጁ ፓትርያርኩ አሳሰቡ፤ ምልአተ ጉባኤው የጥቃት መከላከል እና የኮሚዩኒኬሽን ኀይለ ግብሮችን እንዲያቋቁም ጠየቁ

የቅዱስ ሲኖዶስ ጥቅምት2012 ምልአተ ጉባኤ የቅዱስነታቸው መክፈቻ ቃለ ምዕዳን
 • “ይህ ጉባኤ በኢትዮጵያ ብቻ ከሰባ ሚሊዮን ያላነሰ ሠራዊት ያለው ጉባኤ እንጂ ብቻውን አይደለም”
 • ቅዱስ ሲኖዶስ፣ የዓመቱን የመጀመሪያ የምልአተ ጉባኤ መደበኛ ስብሰባውን ማካሔድ ጀመረ

***

በቤተ ክርስቲያን ላይ በቀጣይነት እየደረሰ ያለውን ተጽዕኖ እና ጥቃት ለማስቆም፣ የመንጋው እረኞች የኾኑ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ ድምፃቸውን በዓለም ዙሪያ በአንድነት ለማሰማት እና እስከ ሞት ድረስ መሥዋዕት ለመክፈል እንዲዘጋጁ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ አሳሰቡ፡፡

የቅዱስ ሲኖዶስ የመጀመሪያ ዓመታዊ የምልአተ ጉባኤ መደበኛ ስብሰባ፣ ዛሬ ረቡዕ፣ ጥቅምት 12 ቀን 2012 ዓ.ም. ሲጀመር ቅዱስነታቸው ባሰሙት የመክፈቻ ቃለ ምዕዳን እንደገለጹት፣ የመንግሥት የበታች መዋቅር እና ባለሥልጣናት በምእመናን ላይ እያደረሱት የሚገኙት ግፍ ቤተ ክርስቲያን ከምትታገሠው በላይ እየኾነ መጥቷል፡፡

በሕገ መንግሥቱ የተቀመጠውን የእምነት ነፃነት በሚሸረሽሩ የታችኛው መዋቅር ባለሥልጣናት ላይ መንግሥት የማያዳግም የርምጃ ማስተካከያ እንዲያደርግ ቤተ ክርስቲያን ቀደም ሲል ብትጠይቅም፣ አሁንም የአብያተ ክርስቲያን ቃጠሎ፣ የካህናት እና ምእመናን መፈናቀል እና ግድያ ስጋቶች መኖራቸውን፣ ባለፈው ሳምንት በተካሔደው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ 38ኛ ዓመታዊ ስብሰባ በቀረቡ የአህጉረ ስብከት ሪፖርቶች ማረጋገጥ መቻሉን ቅዱስነታቸው ጠቅሰዋል፡፡

“ነባር የቤተ ክርስቲያናችን ይዞታዎች ሥልጣንን መከታ ባደረጉ ወገኖች እየተነጠቁ ነው፤ ምእመናን በሚደርስባቸው የማያባራ ተጽዕኖ እና አድልዎ ከቀዬአቸው እየተፈናቀሉ እና እየተሰደዱ ነው፤” ያሉት ፓትርያርኩ፣ “እንዲህ ዓይነቱ ኢሰብአዊ ድርጊት እስከ መቼ ነው የሚቀጥለው?” በማለት ጠይቀዋል፡፡

72432193_2332270366882688_486723307643600896_n
gubae

የጥቃት እና የተጽዕኖ ድርጊቱን ለማስቆም፣ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ በሙሉ አቅማቸው መሥራት እና በዓለም ዙሪያ መደመጥ በሚችሉበት አኳኋን መነሣሣት እንዳለባቸው፤ ከዚህም አልፈው እስከ ሞት ድረስ መሥዋዕት መኾን እንደሚጠበቅባቸው ቅዱስነታቸው አሳስበዋል፡፡ “ይህ ድርጊት እንዲቆም እስከ ሞት ድረስ መሥዋዕት መኾን ከዚህ ጉባኤ አባላት ይጠበቃል፡፡ ይህ ጉባኤ የኀያሉ የእግዚአብሔር ጉባኤ ነው፤ ይህ ጉባኤ በኢትዮጵያ ብቻ ከሰባ ሚሊዮን ያላነሰ ሠራዊት ያለው ጉባኤ እንጂ ብቻውን አይደለም፤ ይህ ጉባኤ በሙሉ አቅሙ ሥራውን ከሠራ እና ድምፁን ካነሣ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይኾን፣ በዓለም ዙሪያ ሁሉ ሰሚው ብዙ ነው፤” ብለዋል፡፡

መብታችንን ለማስከበር መንግሥትን በተደጋጋሚ ከመጠየቅና የባለሥልጣናቱን የተሳሳቱ አካሔዶች በቅርበት እየተከታተሉ በማያዳግም ርምጃ እንዲያስተካክል ከማድረግ ጋራ፣ ሁሌም በተጎጂው ሕዝብ መካከል እየተገኘን በልዩ ልዩ ግፍ ልባቸው የተሰበረውን የልጆቻችን ኀዘን መቅረፍ ይኖርብናል፤ ችግራቸውንም መጋራት ይጠበቅብናል፤ የተቃጠሉ አብያተ ክርስቲያናትን እንደገና መገንባት አለብን፤ በማለት ቅዱስ ፓትርያርኩ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱን አዘክረዋል፡፡


ከዚህ ጋራ በተያያዘ፣ ቅዱስ ሲኖዶስ ኹለት ኀይለ ግብሮችን እንዲያቋቋም ነው ቅዱስ ፓትርያርኩ በምልአተ ጉባኤው መክፈቻ ቃለ ምዕዳናቸው የጠየቁት፡፡ ይኸውም፣ ዙሪያ መለስ ጥቃቶችንና ተጽዕኖዎችን ለመመከት ብሎም ለማስቆም የሚሠራ የጥቃት መከላከል ኀይለ ግብር እንዲሁም በየአካባቢው የሚሰነዘሩትን ጥቃቶች፣ ወከባዎች፣ ተጽዕኖዎችና አድሎአዊ አሠራሮች እየተከታተለ ትክክለኛ ኢንፎርሜሽን የሚያቀርብ የኮሚዩኒኬሽን ኀይለ ግብር ናቸው፡፡

ትልቁ የእግዚአብሔር ትእዛዝ እና የቤተ ክርስቲያን ተልእኮ፣ የመንጋ ጥበቃ ተግባር በመኾኑ፣ እኒህን ኹለት ኀይለ ግብሮች ቅዱስ ሲኖዶሱ አቋቁሞ፣ ቤተ ክርስቲያንን ከመከራ የመታደግ፤ የሀገርን ሰላም እና የሕዝቡን አንድነት በጽኑ የማስጠበቅ ሓላፊነቱን በንቃት እና በትጋት፣ በሓላፊነት እና በቁጭት እንዲወጣ ቅዱስ ፓትርያርኩ አሳስበዋል፡፡

‡‡‡‡‡‡‡‡‡‡‡‡‡

Holy Synod TIk2012 Patriarck Opening

የጥቅምቱ የቅዱስሲኖዶስምልአተ ጉባኤ መደበኛ ስብሰባ መጀመሩን አስመልክቶ ቅዱስ ፓትርያርኩ የሰጡት የመክፈቻ ቃለ ምዕዳን

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤ አሜን፡፡

 • ብፁዕ አቡነ ያሬድ፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤
 • ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤
 • ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት፣

ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በደሙ የዋጀ ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን ለዓመታዊው የጥቅምቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ አደረሰን አደረሳችኹ፡፡

ወይእዜኒ ረዐዩ ዘሀለዉ ኀቤክሙ መርዔቶ ለክርስቶስ፤ አሁንም በእናንተ ዘንድ ያለውን የእግዚአብሔርን መንጋ ጠብቁ” (፩ኛጴጥ፪፥፮)

እግዚአብሔር አምላካችን የፍጥረታት ሁሉ ፈጣሪ፣ ጠባቂ፣ መጋቢ፣ አስተናባሪ እና አስተዳዳሪ ነው፤ በሰማይ እና በምድር ያለው የሚታየውና የማይታየው ፍጥረታት በአጠቃላይ በእግዚአብሔር ጥበቃ እና አስተዳደር ሥር ነው፤

ፍጡራን ከእርሱ በተገኘ የአእምሮ ነፃነት በሚፈጽሙት ተግባር የራሳቸው ድርሻ እና ሓላፊነት እንዳላቸው ቢታወቅም ያለእርሱ ዕውቅና የሚደረግ እንደሌለ ግን ከቅዱስ መጽሐፍ እንማራለን፡፡

እንግዲህ እርሱ የጠባቂዎች ጠባቂ ኾኖ ሳለ ከፍጡራን ወገን ደግሞ በልዩ ምርጫው እየሾመ መንጋውን ወይም ፍጥረቱን ያስጠብቃል፤ ይህ ከጥንት ጀምሮ የነበረ የእግዚአብሔር አሠራር እንደ ኾነ ቅዱስ ያሬድ ሲገልጽ፣ ኢኃደጋ ለምድር እምቅድመ ዓለም ወእስከ ለዓለም እንበለ ካህናት ወዲያቆናት፤ ዓለም ከመፈጠሩ በፊት አንሥቶ እስከ ዘለዓለሙ ድረስ ምድርን ያለ ካህናት እና ያለ ዲያቆናት አልተዋትም፤›› በማለት ያደረጋግጣል፡፡

ይህ የሚያመለክተን፣ እግዚአብሔር ዓለምን ያለጠባቂ የተወበት ዘመን ካለመኖሩም ሌላ ጠባቂዎቹ ካህናት እና ዲያቆናት መኾናቸው ነው፤ “ካህናት” የሚለው ስያሜ የወል ስም ኹኖ ከቅዱስ ፓትርያርክ ጀምሮ ያለው ውሉደ ክህነት በሙሉ እንደሚያጠቃልል ይታወቃል፡፡

ከዚህ አኳያ፣ ኰኵሐ ሃይማኖት ቅዱስ ጴጥሮስ ከጌታችን በተሰጠው የጥበቃ ሓላፊነት መሠረት እርሱም በክህነት ለወለዳቸው ልጆቹ በፈንታው መንጋውን ጠብቁ” እያለ ምእመናንን ሲያስጠብቅ እናያለን፡፡

ትልቁ የእግዚአብሔር ትእዛዝ እና የቤተ ክርስቲያን ተልእኮም፣ ይህ የጥበቃ ተግባር ነው፡፡

እግዚአብሔር እኛ ካህናትን በሓላፊነት የሾመበት ዋና ዓላማ፣ መንጋውን እንድንጠብቅለት ነው፤ ይህ መንጋ ተብሎ የተገለጸው ወገን፣ የተለየ ሕዝብ እና ጎሳ ሳይኾን፣ ለትዝምደ ሰብእ ወይም የሰው ዘርን በሙሉ ነው፡፡

በራሱ እምቢተኝነት ከሚቀርበት በስተቀር፣ የጌታችን ጥሪ ለትዝምደ ሰብእ በሙሉ እንደኾነ፣ “ሑሩ ወስብኩ ወንጌለ ለኵሉ ፍጥረት፤ ሒዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ በማለት አሳውቆናል፡፡

እንዲሁም ከኾነ ጠብቁ ተብለን የታዘዝነው ያመኑት ወይም የተጠመቁትን ብቻ ሳይኾን፣ ያላመኑትንም፣ ያልተጠመቁትንም በአጠቃላይ እንደ ኾነ ለጥያቄ የሚቀርብ አይደለም፡፡

ከዚህ አንጻር መንጋችንን ስንጠብቅ፣ ያመኑትን በነፍሳቸውም በሥጋቸውም ምንም ዓይነት ጉዳት እንዳይደርስባቸው የተሟላ ጥበቃ እና ክብካቤ በማድረግ፣ ያላመኑትንም በፍቅር በማቅረብ እና ዘመድ ዘመድ በማለት፣ ውሳጣዊ እና መንፈሳዊ ስሜታቸውን በመንፈስ ቅዱስ ኀይል በማነቃቃት እና ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በማምጣት እንደ ኾነ ለሁላችን ግልጽ ነው፡፡

ኾኖም፣ ይህን የጥበቃ ሥራ በአግባቡ ለማሳካት ትልቁ ትጥቃችን ቅዱስ ወንጌል እንደ ኾነ ምንጊዜም መዘንጋት የለብንም፡፡ ቃለ ቅዱስ ወንጌልን ለፍጥረት ሁሉ ለማዳረስ የተለያዩ ዘዴዎችንና አቀራረቦችን፣ ሥልጠናዎችንና አስተምህሮዎችን መጠቀምና በዚህ የባዘነውን በግ ወደ መንጋው የምንመልስበት ታሪካዊ እና ወቅታዊ ሥራ ከፊታችን ይጠብቀናል፡፡

በአሁኑ ጊዜ በየቀኑ የሚባክኑና በተኩላ የሚነጠቁ በጎች በእጅግ እየተበራከቱ ነው፤ ዛሬ ሁሉን ነገር መልካም ነው ብለን የምንዘናጋበት ጊዜ ሳይኾን፣ የጎደለውን ለመሙላት ቃል የምንገባበት ያኑንም በተግባር ፈጽመን በጎቻችንን የምንሰበስብበት ጊዜ ነው፡፡

በዚህ አኳኋን በንቃት እና በትጋት፣ በሓላፊነት እና በቁጭት ከሠራን ከባዘኑት በጎች መካከል ብዙዎችን ወደ መንጋው መመለስ እንደምንችል፣ ያሉትንም ባሉበት ጸንተው እንዲቀጥሉ ማድረግ እንደምንችል ምንም ጥርጥር የለውም፡፡

 • ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት፤

የጥበቃ ተግባራችን፣ ከውጭ ኀይሎች ጣልቃ ገብነት እና ከውስጥ ጥቅመኞች የተነሣ ተደጋጋሚ እንቅፋት በበዛበት በአሁኑ ጊዜ፣ ‹‹በእንቅርት ላይ …›› እንደሚባለው፣ በሀገራችን በተፈጠረው ያለመረጋጋት ክሥተት፡- አብያተ ክርስቲያናት ተቃጥለዋል፣ ካህናት እና ምእመናን ተገድለዋል፤ አሁንም ስጋቱ እንዳለ፣ ከቀረበልን የአህጉረ ስብከት ሪፖርት ሰምተናል፤ በዓይናችንም አይተናል፤ ነባር የቤተ ክርስቲያናችን ይዞታዎች ሥልጣንን መከታ ባደረጉ ወገኖች እየተነጠቁ ነው፤ ምእመናን በሚደርስባቸው የማያባራ ተጽእኖና አድልዎ ከቀያቸው እየተፈናቀሉ እና እየተሰደዱ ነው፡፡

በመኾኑም እንዲህ ዓይነቱ ኢሰብአዊ ድርጊት እስከ መቼ ነው የሚቀጥለው? ይህ ድርጊት እንዲቆም እስከ ሞት ድረስ መሥዋዕት መኾን ከዚህ ጉባኤ አባላት ይጠበቃል፡፡ ይህ ጉባኤ የኀያሉ የእግዚአብሔር ጉባኤ ነው፤ ይህ ጉባኤ በኢትዮጵያ ብቻ ከሰባ ሚሊዮን ያላነሰ ሠራዊት ያለው ጉባኤ እንጂ ብቻውን አይደለም፤ ይህ ጉባኤ በሙሉ አቅሙ ሥራውን ከሠራ እና ድምፁን ካነሣ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይኾን በዓለም ዙሪያ ሁሉ ሰሚው ብዙ ነው፡፡

ስለዚህ በቤተ ክርስቲያናችን ላይ በታችኛውም የመንግሥት መዋቅር እየደረሰብን ያለውን የማንታገሠው ግፍ መንግሥት እንዲያስተካክልን ደጋግመን መጠየቅ ይኖርብናል፡፡ እኛም በጸሎት አምላካችንን ከመማፀን ጋራ ሁሌም በተጎጂው ሕዝባችን መካከል እየተገኘን በልዩ ልዩ ግፍ ልባችን የተሰበረውን የልጆቻችን ኀዘን መቅረፍ ይኖርብናል፤ ችግራቸውንም ማጋራት ይጠበቅብናል፤ የተቃጠሉ አብያተ ክርስቲያናትን እንደገና መገንባት አለብን፤ መንግሥትም በሕገ መንግሥቱ የተቀመጠውን የሃይማኖት ክብር ነፃነት እና እኩልነትን በሚሸረሽሩ የታችኛው መዋቅር ባለሥልጣናት ላይ የማያዳግም የርምጃ ማስተካከያ እንዲያደርግ ጥብቅ ክትትል ማድረግ አለብን፡፡

 • ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የሲኖዶስ አባላት

የመንጋ ጥበቃችን ሥራ እየተሰነካከለ የሚገኘው፣ ከውጭ ኾነው በገንዘብ፣ በፖለቲካ እና በኢኮኖሚ እርስ በርሳችን በመከፋፈል በሚተነኩሱን ኀይሎች ብቻ አይደለም፡፡ በውስጣችን ያለው ያልዘመነ አሠራርም የምእመናንን ልቡና እያቆሰለ የሚገኝ ሌላው የጥበቃችን ዕንቅፋት ነው፤ በመሠረቱ ይህን ችግር ከሥር መሠረቱ ነቅለን በማጽዳት ማስተካከል ካልቻልን ችግራችን በወሳኝ መልኩ ሊቀረፍ አይችልም፡፡

በመኾኑም፣ ቀደም ሲል የተጠኑትን የቤተ ክርስቲያን ኹለንተናዊ ችግር መፍትሔ እና የመሪ ዕቅድ ጥናቶች፣ ይህ ዐቢይ ጉባኤ በወሰነው መሠረት፣ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ በአስቸኳይ ይተገብር ዘንድ ጠበቅ ያለ መመሪያ ሊያስተላልፍ ይገባል፡፡ ከእንግዲህ ወዲህ በብልሹ አሠራር አዙሪት የሚታመስ የቤተ ክርስቲያን አሠራር ሊኖር አይገባም፡፡ በዚህ ዓመት አሠራራችንን ሁሉ አስተካክለን ወደ መንጋ ጥበቃ እና ወደ ልማት ሥራችን በፍጥነት መሸጋገር አለብን፡፡

በመጨረሻም፡

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በቤተ ክርስቲያናችን ላይ በተደጋጋሚ እየደረሰ ያለውን ዙሪያ መለስ ጥቃት ለመመከት እና ለመከላከል ብሎም ለማስቆም፣ አንድ የጥቃት መከላከል ግብረ ኃይል እንዲሁም በየአካባቢው የሚሰነዘሩት ጥቃቶች፣ ወከባዎች፣ ተጽእኖዎችና አድሎአዊ አሠራሮችን እየተከታተልን ትክክለኛ ኢንፎርሜሽንን የሚያቀርብ የኮሙኒኬሽን ግብረ ኃይል በአሁኑ ጉባኤያችን አቋቁመን ቤተ ክርስቲያናችንንና መንጋችንን ከመከራ እንድንታደግ፤ የሀገራችንን ሰላም እና የሕዝባችንን አንድነት በጽኑ እንድናስጠብቅ አባታዊ መልእክታችንን እያስተላለፍን፣ የጥቅምቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በዛሬው ዕለት መከፈቱን እናበሥራለን፡፡

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ፤ ይቀድስ፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን!

አባ ማትያስ ቀዳማዊ

ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ

ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት

ጥቅምት ፲፪ ቀን ፳፻፲፪ .

አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

ጃዋርና የአብይ ኦዴፓ ድራማ እየሰሩ ነው

ካልደፈረሰ አይጠራም !!! ( ድራማ ??? ) ጃዋር በመንግስተ ኮማንዶዎች ተከቧል። ኦዴፓና ጃዋር ትኩሳት ለመለካት ያቀናጁት ድራማ እንዳይሆን ያጠራጥረኛል። ሰውየው ሩሲያ መሄዱን ተከትለው የኦሮሞ ጽንፈኞቹና የውሕደቱ ተቃዋሚዎች መፈንቅለ መንግስት አድርገው ይሆን ብሎ ማሰብም ሌላኛው የፖለቲካ ጥርጣሬ ነው።የሰሞኑን ቄሮ የፈጠረን ሽብርና ወከባ ተከትሎ በመንግስት ላይ የሕዝብ እና የፖለቲከኞች ጫና ስለበዛ በጃዋር አከባቢ ያለውን የተከማቸ ኃይል ለማሳየት ጥያቄ ባበዙት ብዙሃን ላይ ፍራቻ ለመልቀቅ የታቀደ ሴራም ሊሆን ይችላል። መጠራጠር ይበጃል፤ የኢትዮጵያ ፖለቲካ በሴራ የተሞላ ነው። ድራማው ቀጥሏል ።

መንገድ የመዝጋቱ ሂደት አዲስ አበባ ደረሰ በዚህ ሰዓት ከጀሞ ቁጥር ፪ ወደ አዲስ አበባ ያለው መንገድ ተዘግቶ ሕዝቡ የመንግስት ያለህ እያለ ነው። በካራ በኩል ዞረው ለመግባት የሞከሩትን ደግሞ ፖሊስ አስወርዶ እየፈተሸ ነው። አደገኛ አካሔድ እንዳይሆን ጥንቃቄ ያስፈልጋል ! መንግስት እንደሰማንለት እያደረገ ከሆነ በደንብ ተዘጋጅቷል ማለት ነው ። ለአጀንዳና የሕዝብን አፍ ለማስያዝ ከሆነ ግን በስሜት ለሚደርሱ ጥፋቶች መንግስት ተጠያቂ ነው።

ጠባቂዎች  የጅዋርን ጊቢ ለቃቹ ውጡ ተብለዋል። ጃዋር የድረሱልኝ ጥሪ እያሰማ ነው! ራሱ ፌስቡክ ላይ ፅፏል። የስልክ ንግግሮችንም ይፋ አድርጓል።

እንዲህም ሲል ፅፏል ፦ ( ጉዳዩ ለሚመለከተው ሁሉ – በብዛት ወደ መኖሪያዬ እየተሰማራ ያለው የታጠቀ ሀይል ወደኋላ እንዲመለስ በአጽኖት እንጠያቀለን። ማንኛውም ታጥቆ በዚህ ጭለማ ወደግቢ የሚንቀሳቀስ ግለስብም ሆነ ቡድን ላይ ጥበቃው የመከላከል እርምጃ እንደሚወስድ ሊታወቅ ይገባል። ለሚከሰትው ግጭት እና ጉዳት ሙሉ ሀለፊነቱን የሚወስደው ያላንዳች ምክናያት እና ማሳሰቢያ ሀይል ያሰማራው አካል መሆኑን ህዝቡ እንዲያውቅልን እንፈልህጋለን። Jawar Mohammed )

የጃዋር መሐመድ መኖሪያ ቤት አከባቢ ያለው ሁኔታ ይህን Photo ይመስላል። የኦሮሚያ ፖሊስ ከፍተኛ አመራሮች ከጃዋር ጋር አብረው እንዳሉና ለደህንነቱም ጥበቃ ተገቢ እየተደረገለት እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል : ድራማው ቀጥሏል ።

#MinilikSalsawi

አማራ ሆይ! ጉደኛ ዓለምን ለመሻገር ጉደኛን ዓለም ማወቅ ይኖርብሃል! – በላይነህ አባተ

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)

ይህቺ ዓለም ጉደኛ ናት፡፡ ነብርን ፍየል፣ አንበሳንም ድኩላ ሲያባርር አሳይታለች፡፡ የይህ አዴግ ካድሬና ጆሮ ጠቢም የአማራን ህዝብ መደመርንና አንድነትን ሲያስተምር አሳይታለች፡፡ የሚገርመው የፍየሉና የድኩላው የማባረር ሙከራ ወይም የዓይን አውጣው ይህ አድግ ጆሮ ጠቢ ስለመደመርና አንድነት ለማስተማር የሚያደርገው ድፍረት ሳይሆን የነብርና የአንበሳ መባረር የአማራ ህዝብም አፉን ከፍቶ በይህ አዴግ ካድሬ ስለ መደመርና አንድነት ሲማር መታየቱ ነው፡፡

አማራ ሆይ! ይህቺ ዓለም ጉደኛ ናት! “ባህርዳር ቄሱና ሼሁ መጣፍ ቅዱስንና ቁራንን ትተው የጆሮ ጠቢ ጠልሰም ጨብጠው አሳይታለች፡፡ ይህቺ ዓለም ጉድኛ ናት! የይህ አድግ ጀሮ ጠቢ ለአማራ የመደመር መጥሀፍ ሲሸጥ አሳይታለች!

አማራ ሆይ! ይኸንን ምጥ ለናቷ አስተማረች የካድሬ ስብከት ተውና በምድር የሚፈጠምብህን የዘር ማጥፋት ወንጀል አስተውል፡፡ ነፍጠኛና ትምክህተኛ በሚል ምልክት ዘርህ እየተለቀመ መጥፋት ከጀመርክ ግማሽ ክፍለ_ዘመን ሊሞላህ ነው፡፡ ተወልቃይትና ተራያ ተነቅለህ ሳስተሃል፡፡ ተጉራ ፈርዳ ሙሴን እንደተከተሉት እብራውያን ከረጢትህን በትከሻህና በጭንቅላትህ ተሸክመህ ሁለተኛውን ዘጥዐት ፈጥመሃል፡፡

አማራ ሆይ! ዘር እንዳትቀጥል ሴት ልጆችህ በመድሃኒት መክነዋል፤ ወንዶች ልጆችህ በከርቸሌ ተሰልበዋል፡፡ ሊታደጉህ የታገሉት እንደ አስራት ወልደየስ፣ አሰፋ ማሩ፣ ሳሙኤል አወቀ፣ ጎቤ መልኬና ሌሎች ቁጥር ስፍር የሌላቸው ልጆችህ በየጥሻው ተረሽነውብሃል፡፡ ልጆችህ በማጀቴ፣ በባህርዳር፣ በጎንደር፣ በወልድያና በደብረታቦር እንደ አገዳ ተጨፍጭፈዋል፡፡ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ልጆችህ በወህኒ ማቀዋል፡፡ ዛሬም ልጆችህ በሰበብ አስባቡ እየተለቀሙ ከርቼሌውን አጣበውታል፡፡ እርስትህን ተነጥቀሃል፡፡ በባህልህና በቋንቋህ ደባ ተፈጥሟል፡፡ ፊደልህን በላቲን ላፒስ ጠርገውታል፡፡ በባንዲራህ፣ በሃይማኖትህና በቀን አቆጣጠርህም መጥተዋል፡፡

አማራ ሆይ! በቅድመ አያቶችህ ደም በከበሩት በሀረርጌ፣ በባሌ፣ በአርሲ፣ በሲዳሞ፤ በከፋ፣ በኢሉባቦር፣ በወለጋና በሸዋ በጋጠ ወጦች እንደ ዜጋ በክብር የመኖር መብትህ ተናግቷል፡፡ በአዲስ አበባ የመናገርና የመሰብሰብ መብትህ ተገፏል፡፡ ባጠቃላይ በመሰረትካት አገርህ ኑሮህ የሶስተኛ ደረጃ ዜግነት ሆኗል፡፡

አማራ ሆይ! ህልውናህ ተድጡ ወደ ማጡ እየገባ ሄዷል፡፡ ማጥ ውስጥ ተራ በተራ ገብተህ ተማለቅህ በፊት በጋራ መድሀኒት መፍጠር ይኖርብሃል፡፡ “ታሞ ተመማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ!” ወይም “በፊት ነበር እንጅ መጥኖ መደቆስ አሁን ምን ያደርጋል ድስት ጥዶ ማልቀስ!” የሚሉትን ብሂሎችህን እንደ መዝሙር እየዘመርክ ላለመጥፋት መዘጋጀት ይኖርብሃል፡፡ እንደምታውቀው የቋጠሩት ስንቅ ለጉዞ ይሆናል፡፡ ጉዞው ተቀረም ተቤት ይኮመኮማል፡፡ ለችግር ብለው ያስቀመጡት ችግሩ ተመጣ ተሞት ያድናል፤ ችግሩ ታልመጣም እሰየው በጠጋ ላይ ጠጋ ይደርባል፡፡ በቂ ዝግጅት ምንጊዜም አጉሎ እንደማያውቅ ባህልህ ይመሰክራል፡፡

አማራ ሆይ! ሆድ ይፍጀውን አብዝተህ እንጅ ክቡር ግሪጎሪ ስታንተን ከዘረዘሯቸው ስምንት የዘር ማጥፋት ደረጃዎች* ስድስቱ ለሰላሳ ዓመታት በጠረ_ነፍጠኛ ቡድኖች ተፈጥመውብሃል፡፡ ተሰባተኛውና ተስምንተኛው ደረጃ ራስህን አድነህ ሌሎችንም ትታደግ ዘንድ የሚፈጥሙብህን የዘር ማጥፋት ብታጤን እንድትዘጋጅ ፈጣሪህም ይረዳሃል፡፡

አማራ ሆይ! ይህቺን ዓለም ሳጥናኤል እንደወረራት ማወቅ ይኖርብሃል፡፡ እነቅዱስ ማቴዎስ፣ ማርቆስ፣ ጳውሎስ፣ ሉቃስ፣ዮሀንስ ወንጌላቸውን እየተሳደዱ ተዋሻ ውስጥ ሲጥፉ የይህ አድጉ ካድሬ ተቤተ መንግስት ተንፈላሶ ጠልሰሙን በሌላ ሰው አስጥፎ በድግስና በፌስታ ያስመርቃል፡፡ የቅዱሳን መጣህፍት እየታደኑ ሲቃጠሉ የጀሮ ጠቢው ጠልሰም በህዝብ ገንዘብ በሚሊዮን ታትሞ በዓለም ለገበያ ውሏል፡፡ እንደነ ፕላቶ፣ አርስቶትል፣ ስፓይኖዛ፣ ቮልቴር፤ ካፍካ ያሉ ጠሀፊዎች ለፍትህ የጣፉትን ታትሞ ሳያዩት ሲሞቱ ፍትህን ሲያንቅ የኖረው የይህ አድጉን ጆሮ ጠቢ ጠልሰም በተለያዬ ቋንቋ ተርጉመው የሚያሳትሙ ተላላኪዎችና ሹንባሾች አግኝቷል፡፡ ክርስቶስን ከሶስት ሰው በቀር ሁሉም ከድቶት ሲሞት የነፍሰ፟ በላውን ይህ አድግ ድርጅት ቁንጮ ግን ሚሊዮን መንጋ ይከተለዋል፡፡

አማራ ሆይ! ቅዱስ ጴጥሮስና ጳውሎስ ባስተማሩትና በጣፉት እውነት እንደ ሻሸመኔው ዜጋ ተዘቅዝቀው ተሰቅለዋል፡፡ ኢትዮጵያዊው ቅዱስ ጴጥሮስ በተናገሩት የፍትህ ቃል ባብሩድ ተደብድበው አልፈዋል፡፡ አቡነ ጴጥሮስ የሞቱላትን አገር በቋንቋ እሾህ ያጠረው፤ የተሰውለትን ፊደልና ባንዲራ በላቲን ላፒስ የፋቀውና የሰው ልጅ ተዘቅዝቆ የሚሰቀልበትን ሻሸመኔ ያስተዳድር የነበረው የይህ አዴግ ጆሮ ጠቢ ግን ሰው ተእግሩ ይደፋለታል፡፡

አማራ ሆይ! ይህ ሁሉ ዓለም ጉደኛ መሆኗን ያሳያል፡፡ ጉደኛ ዓለምን ለመሻገር ጉደኛን ዓለም ማወቅ ይኖርብሃል!

*8 stages of genocide; Gregory Stanton http://www.genocidewatch.org/aboutgenocide/8stagesofgenocide.html (last accessed in October, 2019)

ጥቅምት ሁለት ሺ አስራ ሁለት ዓ.ም.

ወደ ህወሃት ሽማግሌ የሚልክ ለኢትዮጵያ ህዝብ ምን ይልካል? (በመስከረም አበራ)

በመስከረም አበራ

Ethiopian writer, Meskerem Abera.

መስከረም አበራ

በተለያየ አጋጣሚ ከሚያጋጥሙኝ አስተያየቶች አንዱ አቶ ጃዋር መሃመድን መነጋገሪያችን ማድረጉን እንተው፤ግለሰቡ የሚሰጠንን አጀንዳ አንስተን በመተንተን ሰውየው የሚፈልገውን ክብር በመስጠት ተፅኖ ፈጣሪነት እንዲሰማው አናድርግ የሚል ነው፡፡በግሌ ስራየ ብሎ ሰውን ማጉላትንም ሆነ ሆን ብሎ ሰውን ማሳነስን ብቻ አላማ አድርጎ መጓዙ የብልህ መንገድ አይመስለኝም፡፡ጠቃሚው ነገር የሰው ስራ የሚያመጣው ተፅዕኖ ላይ ትኩረት አድርጎ መነጋገሩ ይመስለኛል፡፡በዚህ ሁኔታ ግባችን ግለሰቦች ሳይሆኑ የግለሰቦች ሃሳብ እና አካሄድ የሚያመጣው በጎ ወይ መጥፎ ተፅዕኖ ነው፡፡በጎ ወይም መጥፎ ተፀዕኖ ያመጣውን የሰዎችን ስራ በተመለከተ ስንነጋገር የሰዎችን ስም ማንሳታችን ደግሞ አይቀርም፡፡በጎውን ስራ ስናወድስ፤መጥፎው ስራ ወደ ባሰ መጥፎ እንዳያድግ ልንነጋገርበት ስናነሳሳው ከግለሰቦች ጋር የተለየ ፀብ ወይም ፍቅር ስላለን አይደለም፡፡

ለዚህ ፅሁፍ መነሻ የሆነኝ ዝም ብሎ ለማለፍ ሞክሬ ያልቻልኩት የአቶ ጃዋር ንግግር ነው፡፡ንግግሩን ሰምቼ ዝም ብሎ ማለፉ ያቃተኝ ደግሞ ግለሰቡ በርካታ ስሜታዊነት የበዛው ተከታይ ያለው ሰው በመሆኑ ንግግሩ የሚያመጣው ተፅዕኖ በጎ ስላልመሰለኝ ነው፡፡የዚህ ንግግር አንድ በጎ ጎን አቶ ጃዋር መስመሩ ከህወሃት ጋር መሆኑን በግልፅ ማሳወቁ ብቻ ነው፡፡ለዛሬው ፅሁፌ መነሻ የሆነኝ የግለሰቡ ንግግር የተደረገው  በኦሮምኛ ቋንቋ “OMN” በተባለው ሚዲያ ላይ ነው፡፡ንግግሩ ከኦሮምኛ ወደ አማርኛ ሲተረጎም ይህን ይመስላል፤

“በደቡብም በምስራቅም ሄጃለሁ፡፡ብዙ ሰዎች ፈርተው አይናሩትም እንጅ አቋማቸው ከህወሃት የተለየ አይደለም፡፡ ፖለቲካ ያስተማሩኝም የብዙ ፓርቲዎች አመራር፣ ምሁራን፣ ወጣቶችም ጭምር በተለያየ ዘዴ አዋርቻቸዋለሁኝ፡፡ በይዘት ህወሃት የሚያራምደውን ፌደራላዊ ፖለቲካ ይደግፋሉ፡፡ እኛም አሁን ከህወሃት ጋር የሚያጣላን የታክቲክም ሆነ የእስትራቴጅ ልዩነት የለም፡፡ ህወሃቶች ፌደራሊስቶች መሆናቸውን በተደጋጋሚ በተግባርም በአቋምም አሳይተዋል፡፡ ድሮ ብዙ ተባብለናል፡፡ ያለፈው አልፏል፡፡ እርግጠኛ ሆኜ የምናገረው ግን በአብይ ዙሪያ ካሉት ሰዎች መካከል አብይን ከልብ የሚደግፉ በጣት የሚቆጠሩ ሰዎች ናቸው፡፡ በስም ሁሉ ልጠራቸው እችልላለሁ፡፡ አሁን ኦሮሞ ማድረግ ያለበት ለእስትራቴጅክ  አጋሮቹ አጋርነቱን ማሳየት ነው፡፡ ሽማግሌም ቢሆን ልከን  ዋናውን እስትራቴጅያዊ ወዳጅ አብሮን እንዲሰራ እንሞክር፡፡ አብይ ብቻውን ነው እየሄደ ያለው፡፡ እንደተናገርኩት በጣት የሚቆጠሩ ናቸው አጠገቡ ያሉት፡፡” (መስመር የእኔ)

ይህን ንግግር በፍጥነት ወደ አማርኛ መልሰው ለህዝብ ይፋ ያደረጉት የተለያዩ የትግራይ ሚዲያዎች ናቸው፡፡ተናጋሪው ወደ  ምስራቅ እና ምዕራብ መጓዙን ሲናገር የተጓዘው ወደ ደቡብ/ምስራቅ ኦሮሚያ ይሁን ወደ ደቡብ/ምስራቅ ኢትዮጵያ ግልፅ አይደለም፡፡ከተናጋሪው የቆየ በሚዲያ ለሚደረግ ንግግር ጥንቃቄ ያለማድረግ፣ተረጋግቶ እና አስቦ ያለማውራት ባህሪ ተነስቶ ለገመገመ ደግሞ ደቡብ/ምስራቅ የሚለው አባባል ደቡብ/ምስራቅ የሚለውን አቅጣጫ ለመጠቆም ሳይሆን  ወደ ብዙ ቦታ ተዘዋውሬ ሰዎች አነጋግሬያለሁ ለማት ሲሆን ይችላል፡፡

ተናጋሪው ኦሮሚያ ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራ ፖለቲከኛ በመሆኑ እያወራ ያለው በኦሮሚያ ስላነጋገራቸው ሰዎች ነው ብለን ብንነሳ እየተባለ ያለው በኦሮሚያ ውስጥ ህወሃት ያራምደው የነበረው የፌደራሊዝም ፖለቲካ በእጅጉ ይወደዳል ነው፡፡ይህ ማለት ኦሮሚያ ክልል በህወሃት ምርጫ ይሰየም የነበረ ርዕሰ መስተዳደር በመናፈቅ እየዋተተች ነው ማለት ነው፡፡የኦሮሞ ፖለቲከኞች የኦሮሚያ ክልል ህወሃት በሚያሰማራቸው ህወሃታዊ ዘራፊዎች መዘረፉ ስለቀረበት አዝናነው ሊሞቱ ነው ማለት ነው፡፡

ምስራቅ የተባለው በምስራቅ ኢትዮጵያ ነው ከተባለ ደግሞ የሶማሌ ክልል ምሁር፣ፖለቲከኛ ወጣት ህወሃት ያደርገው የነበረውን ፌደራላዊ ፖለቲካ ይደግፋል ማለት ነው፡፡ በሌላ አባባል የሶማሌ ምሁር፣ፖለቲከኛ እና ወጣት አብዲ ኢሌ እና ህወሃት እጅ ለእጅ ተያይዘው ያነበሩትን የፌደራሊዝም ፖለቲካ የሚደግፍ ነው ማለት ነው፡፡ይህ ማለት የሶማሌ ፖለቲከኛ፣ወጣት እና ምሁር የጄል ኦጋዴንን ሲኦል በመናፈቅ መዋተት ውስጥ ነው ማለት ነው፡፡የሶማሌ ህዝብ በህወሃት ጀነራሎች የኮንትሮባንድ ንግድ ዘረፋ ናፍቆት እየተቸገረ ነው ማለት ነው፡፡የሶማሌ ሴቶች በቀን በብርሃን በመሃል ከተማ መደፈርን የመሰለን “አክብሮት”ያመጣላቸውን ፌደራሊዝም እየናፈቁ ነው ማለት ነው፡፡

ሕወሃት ያነበረው ፌደራላዊ ፖለቲካ ተናጋሪው እንደሚያስበው የደቡብ/ምስራቅ ጉዳይ ስላልሆነ ሰፋ አድርገን ስናየው በጋንቤላ በህወሃት ጀነራል እና ደራሽ ኢንቨስተር መሬትን መዘረፍ፣የሲጋራ መግዣ የማያክል ገንዘብ ከፍሎ ለሚመጣ የውጭ ኢንቨስተር መሬትን አስረክቦ መፈናቀል፣ህወሃት በሾመው አሻንጉሊት አስተዳዳሪ መተዳደር ባጠቃላይ የህወሃት የገንዘብ ሳጥን መሆን ነው፡፡ለጋንቤላዎች ህወሃት ያነበረው የፌደራል ፖለቲካ ለኑዌር ወግኖ አኙዋክን መቸፍጨፈ፤አለያም ኑዌር እና አኙዋክ ወንድማማችነቱን ረስቶ ለደመኝነት እንዲፈላለግ ማድረግ ነው፡፡

የህወሃት የፌራሊዝም ፖለቲካ በአማራ ክልል ሁኔታ እንየው ከተባለ ለምለም መሬትን ለህወሃት አስረክቦ፣የማልቀሻ እና መዝፈኛ ቋንቋን ሳይቀር ህወሃት የሚመርጥበት የባርነት አለም ውስጥ ቋንጃን ተቆርጦ መንፏቀቅ ነው፡፡የህወሃት ፌደራላዊ ፖለቲካ ለአማራ ህዝብ በረከት ስምኦን በተባለ ኤርትራዊ ገዥ እግር ስር ተደፍቶ ውርደት መጋት አለያም አለምነው መኮንን በተባለ የአሽከር አሽከር አሻንጉሊት አስተዳዳሪ ያልተገራ አፍ መሰደብ ነው፡፡የህወሃት ፌደራሊዝም በአማራ ክልል መዲና ባህርዳር ከተማ ህወሃት በቀለሰው እስርቤት በህወሃት ገራፊ በፌሮ መገረፍ ነው፡፡የህወሃት ፌደራላዊ ፖለቲካ በአማራ ክልል በተቀለሰ እስርቤት አማራ ሱሪውን አወልቆ ራቁቱን እንደቀረ፣አከርካሪው የተሰበሰ ሽባ እንደሆነ እየተነገረው የበላው በአፉ እስኪመጣ በህወሃት መኳንንት ተዘቅዝቆ የሚሰቀልበት ማለትነው፡፡የህወሃት ፌደራላዊ ፖለቲካ ለደቡብ ክልል ፖለቲከኛ በአንድ ህወሃት ቀላጤ ደብዳቤ መሾር፤የህወሃት ባስልጣናትን ዘመድ አዝማድ በአንድ ሌሊት ከበርቴ የሚሆንበትን መንገድ ከፍቶ ዳርቆሞ ማየት ነው፡፡

የህወሃት ፌደራሊዝም ዘጠኙም ክልል ጀግናው ህወሃት በትግርኛ ፅፎ ያሰናዳውን መመሪያ በየቋንቋው ተርጉሞ ህወሃት እንደወደደ ለማስፈፀም ሽር ጉድ ማለት፤ለባርነት መታጠቅ ነው!የህወሃት ፌደራሊዝም ማለት የሶስት አባል እና የአምስት አጋር ፓርቲዎች  ካድሬዎች የህወሃትን መንበር ተሸክመው “አሜን አሜን” ሲሉ ማለት ነው፡፡የህወሃት ፌደራሊዝም ማለት መለስ ዜናዊ የእግዜር ታናሽ ተደርጎ ተቆጥሮ የተናገረው ቃል በዘጠኙም ክልል ካድሬዎች እንደወረደ ሲነገር ማለት ነው፡፡ የህወሃት ፌደራሊዝም ማለት ህወሃት የጠላውን ዜጋ በሌሊት ይሁን በቀን፣በእግር ይሁን በፈረስ ከፈለገው ክልል አምጥቶ ማዕከላዊ አስገብቶ ጥፍሩን ሲነቅል፣በፌሮ ጀርባውን ሲተለትል፣ዘር እንዳይተካ ሲያኮላሽ፣ግብረ ሰዶም ሲፈፅም፣ሴት በርብርብ ስትደፈር ማለት ነው፡፡ህወሃት ፌደራሊስትነቱን በተግባር አስመስክሯል ሲባል “ይህ አረመኔያዊ ተግባር ስሙ የፌደራሊዝም ፖለቲካ ይባላል” ብሎ መናገር ነው፤ይህ ደግሞ ለእብደት መዋሰን ነው! ከህወሃት ጋር ስትራቴጃዊ አጋር ነኝ ማለት የዘረፋ፣የአይን አውጣነት፣የሰብዓ መብት ጥሰት አጋር ነኝ ማለት ነው፡፡

በርግጥ የህዋትን አረመኔነት ለመገንዘብ ከኢትዮጵያ ህዝብ አጠገብ ተቀምጦ ህወሃት ባሳረረው ማሳረረር ሳቢያ ከእትንፋሱ የሚወጣውን የምሬት ጭስ ማየት ይጠይቃል፡፡በህወሃት ዘመን ወደ ኢትዮጵያ ዝር ለማለት ቀርቶ ለማሰብ የማይደፍር ራሱን ጠባቂ “ታጋይ” ህወሃት በኢትዮጵያ ህዝብ አካል እና አእምሮ ውስጥ ስላስቀመጠው የማይሽር ጠባሳ ሊያውቅ አይችልም፡፡እንዲህ ያለው “ታጋይ” ትናንት ህወሃትን ሲታገል የነበረው ከአትላንቲክ ማዶ ነፍሱን በጨርቅ ቋጥሮ በተቀመጠ፣መራራ በደል ባልቀመሰ ማንነቱ ስለነበረ ያለፈውን እንደዋዛ ለመተው አይቸገርም፡፡

በመሆኑም አቶ ጃዋር በምድረ-አሜሪካ ሆኖ ህወሃትን ታገልኩ ባለበት ዘመን ስለ ህወሃት ስላለው ነገር ሁሉ እንደ መፀፀት በሚቃጣው መልኩ እንደ አለፈ ውሃ እንዲተለው ይፈልጋል፡፡እኛ የህወሃትን አረመኔያዊ ገፅታ ሁሉ እዚችው ቁጭ ብለን ያየን ኢትዮጵያዊያን ግን ህወሃትን መታገላችን ከበቂ በላይ በሆነ ምክንያት የተነሳ የተደረገ ነበርና የሚያፀፅተን፣እንደ አለፈ ውሃ እንዲረሳልን የምንፈልገው ታሪክ አይደለም፡፡ይልቅስ ባሰብነው ቁጥር የምንኮራበት የታሪካችን ገፅ ነው! ወደፊትም ህወሃታዊነት የሚያንሰራራ በመሰለን ጊዜ ሁሉ ከቀድሞ በበረታ ጥንካሬ ለመታገል እጅ ለእጅ የምንያያዝ ባለምክንያት እምቢ ባዮች  ነን እንጅ “የትናንቱን እርሱልን እና እንታረቅ” የምንል አጥነተ-ቢስ ልፋጭ ስጋዎች አይደለንም፡፡ትላንት ያለ ምክንያት የጮኽ ብቻ “የትናነትቱን እርሱልኝ” ይላል፤ትናንት በበቂ ምክንያት የታገለ ባለ አእምሮ በታገለው ባላጋራው ፊት አይሽረከረክም፡፡

ከሁሉም በላይ የባላጋራችንን የህዋትን ማንነት አሳምረን  እናውቃለን፡፡ህወሃት ስልጣኑን ካስቀማው ባለጋራው  ጋር  አይደለም አንድ አጭር  የትችት አርቲክል ከፃፈበት ሰው ጋር የእውነት እርቅ አይታረቅም፡፡በህወሃት እልፍኝ የእውነት እርቅ የለም! ህወሃት ከነገሩ ሁሉ አጥንት አለው! ጠላቱ እንታረቅ ባለው ሰዓት ሁሉ የሚታረቅ ደጅ ወጥቶ የተቀመጠ ልብ የለውም፡፡የሆነ ሆኖ የህወሃት እግር ስር ተንከባሎ ማሩኝ ማለት፣አመድ ነስንሶ ማቅ ለብሶ፣ድንጋይም ተሸክሞ  ለእርቅ የህወሃትን ደጅ ማንኳኳት ይቻላል፡፡ መታወቅ ያለበት አበይት ጉዳይ ግን ህወሃት ጥፋቱን አምኖ ለመስተካከል ባልሞከረበት፣ጭራሽ ሃገሪቱን ለባሰ ብጥብጥ ለመዳረግ ታጥቆ በሚሰራበት በዚህ ወቅት  “ሽማግሌ ልኬም ቢሆን ከህወሃት ጋር እታረቃለሁ” ማለት ለኢትዮጵያ ህዝብ የጠብ ደብዳቤ መፃፍ ነው!

ለአማራ ህዝብ ያልቆማችሁት ከስልጣናችሁ መባረርን ፈርታችሁ ነው? – ከአንድ አዴፓ አባል

ባህር ዳር በተካሄደው ሰብሰባ አንድ የአዴፓ አባል ለአዴፓ አመራሮች እናንተ የማን መሪ ናችሁ?

የአዴፓ መሪዎች እንደዚህ ሳምንት ተዋርደው አያውቁም።

የአዴፓ መሪዎች በተቀመጡበት አንድ የአዴፓ አባል የሆነ ለአዴፓ መሪዎች ለመሆኑ እናንተ የማን መሪዎች ናችሁ?

ሁል ጊዜ በቲቪ ለውጡ እንዳይደናቀፍ እያላችሁ በቲቪ መስኮት ትናገራላችሁ ።

ለመሆኑ ስለየትኛው ለውጥ ነው የምትናገሩት?
አማራ እየታሰረ እየተፈናቀለ ነው።
ወልቃይትንና ራያን እናስመልሳለን እያላችሁ ጉራ ስትነፉ አዲስ አበባን አስረከባችሁ ።
በኦሮሞ ክልል አማራ በመሆናቸው ብቻ እየታሰሩ አንድ መልስ እንኳ አትሰጡም ።
የኦሮሞ ፅንፈኞች በክልላቸው አማራን እያሳደዱ ወሎ የእኛ ነው እያሉ በከሚሴ ኦነግን እያደራጁ የእናንተ ልዩ ሃይል አማራን
ማሳደድ ብቻ ነው ስራው ።
ቆይ ግን ችግራችሁ ምንድነው? ለአማራ መብት ያልቆማችሁበት ችግራችሁ ምንድነው?
በእርግጥ አማራ ናችሁ ግን?
እናንተ ለአማራ ምኑ ናችሁ ?
ወይስ ኦሮሞን ወክላችሁ ነው የምትሰሩት?
ለመሆኑ ማንን ነው የምትፈሩት ?

ፍርሀታችሁ ከስራ እንዳትባረሩ ነው? የአማራን ህዝብ የሸጣችሁት፣ የአማራን ህዝብ የከዳችሁት፣ ለአማራ ህዝብ ያልቆማችሁት ከስልጣናችሁ መባረርን ፈርታችሁ ነው?

ወይንስ ከደመቀ መኮንን ብቃትና ራዕይ ማነስ ነው?
እስከሞት መስዋዕት ለመሆን ካልተዘጋጃችሁ ገለል በሉ።

እናንተ በየቀኑ ለ8 ሰአታት ሰራን ስትሉ እንወክለዋለን ላላችሁት የአማራ ህዝብ ለአንዲት ደቂቃ እንኳን ምን ሰራችሁ? ከነበረው ላይ አስወሰዳችሁ እንጂ አንዲት ነገር እስከዛሬ አልጨመራችሁለትም።

በባህር ዳር እስቴዲዮም ተለውጠናል ለአማራ ቁመናል ብላችሁ የተናገራችሁትን ቃላት ምኑ በላው ?
አውቆ የተኛን ቢቀሰቅሱት አይነሳም ማለት እናንተ ናችሁ።

በደመቀ ዘመን አማራ መብቱ ይረገጣል እንጂ ይከበራል ማለት ዘበት ነው።