ለፖለቲካ ፍጆታ ሲባል ብቻ የሚደረጉ አይን ያወጡ የግፍ ግድያዎችን እናወግዛለን !

ሀገራችን ኢትዮጵያ የተለያየዩ ቋንቋዎች የሚነገሩባት በርካታና ውብ ባህሎች የሚታዩባት ጥንታዊ ታሪክ ካላቸው ጥቂት ሀገሮች አንዷ ነች። የኢትዮጵያ ሕዝብ በጋራ ባለፈባቸው የታሪክ መስተጋብሮች፣ የሀገሩን አንድነትና ሉአላዊነት ላለማስደፈር ከውጭ ወራሪ ኃይሎች ጋር ባሳለፋቸው የተጋድሎ የታሪክ ጊዜያቶች፣ በሀገሩ ውስጥ ከቦታ ቦታ በመዘዋወር በመኖር በመጋባትና በመዋለድ በፈጠረው ጠንካራ ማህበራዊ ትስስርና ግንኙነት፣ በቆይታም በሀይማኖትና በባህል መወራረስ በቋንቋ አጠቃቀም የኢትዮጵያዊነትን የጋራ ስነልቦና እንዲፈጠርና ብዝሃነት እንዲያብብ አድርጎታል። ይህም ብዝሃነትና ህብረብሄራዊ ቀለም ለሀገራችን ዉበታችን ሆኖ ደምቀን እንድንታይና ተሳስረንም እንድንኖር አስችሎናል። ይህን አንድነቱን የውጭ ወራሪዎች እና የሀገር ውስጥ የስልጣን ጥመኞች በተቻላቸው ሁሉ አለመግባባትን ሊፈጥሩ ይችላሉ ያሏቸውን ያልነበሩና ያልተሰሩ በታሪክ የማይታወቁ የፈጠራ ትርክቶችን በመፈብረክ ሊከፋፍሉት ሞክረዋል። ሆኖም በዋዛ የማይነጣጠል ለመነጣጠል ውል የማይገኝለት በጥብቅ የተሸመነ እና አብሮ በመኖር ታሪክ የተገመደ ታሪካዊ ትስስር ስላለው ከቶውንም ትላንትም አልተሳካላቸው። ዛሬም ሆነ ነገ አይሳካላቸውም።

——[ሙሉውን መግለጫ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]——

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s