“ለስልጣን ሲባል ኢትዮጵያዊነታችን ተወስዶ ማንነታችን ብሔር እንዲሆን ተደርጓል”ኦባንግ ሜቶ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች

አዲስ አበባ፡- ለስልጣን ሲባል ኢትዮጵያዊነታችን ተወስዶ ማንነታችን ብሔር እንዲሆን ተደርጓል ሲሉ የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ አቶ ኦባንግ ሜቶ ገለጹ ።አሁን መገዳደል ላይ የተደረሰው በውሸት ማንነት እንደሆነም አስታወቁ።አቶ ኦባንግ ሜቶ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳመለከቱት፣ ጥቂት ሰዎች ተበድለናል ብለው ተነስተው ጫካ ገቡ። ከጫካ ሲወጡ እና ስልጣን ለመያዝ ስትራቴጂ ሲነድፉ ህዝቡን መከፋፋል ላይ አተኮሩ። የጋራ የሚባል ነገር ሁሉ የእነርሱ ጠላት መሆኑን አስቀመጡ። እኩልነት፣ ኢትዮጵያዊነት፣ ጥሩዎቹ የአብሮነት ታሪኮች ተሰወሩ። ትልቁን ነገር የኢትዮጵያውያንን ማንነት ከህዝቡ ነጠቁ።“ፖለቲካ ጨዋታ ነው። ጨዋታው ደግሞ ከማሸነፍ ጋር የተያያዘ ነው። ነገር ግን ማሸነፍ ሲታሰብ አገር እና ትውልድን ከመጉዳት አንፃር መሆን አልነበረበትም” ያሉት አቶ ኦባንግ፣ በኢትዮጵያ ግን ለማሸነፍ ሲባል አገር የምትፈርስበት እና ትውልድ የሚጎዳበት መንገድ መመረጡን አስታውቀዋል።የምንገዳደልበት የተሰጠንን የውሸት ማንነት ተቀብለን ነው። እውነቱ ግን ከዚህ የራቀ ነው ያሉት አቶ ኦባንግ፣ አያቶቻችን ብሔርን ሳያስቡ በፍቅር ተጋብተዋል። የሰውን ብሔር ሳያውቁ ሰው በመሆኑ ብቻ አግብተው ልጅ መውለዳቸውን አመልክተዋል። በፊት ዕቁብ፣ ዕድር፣ ቡና መጣጣት፣ በአንድ ትሪ ያለምንም ድንበር መብላትነበር። ሁሉም ከሰውነት አንፃር ይታይ ነበር። አሁን ይሄን ማንነት ተነጥቀናል። እከሌ ያንተ ጠላት ነው። እከሌ ይሄንን በደል ፈፅሞብሃል መባሉ በብዙዎች ውስጥ ገብቶ የአብሮነት ስጋት መፍጠሩን አስታውቀዋል።“ፈጣሪ ሰውን ፈጥሯል። ሰው ያለሰው መኖር አይችልም። ዝሆን ስትወልድ ብትሞት፤ የተወለደው የዝሆን ግልገል ያለማንም ድጋፍ ወዲያው መሄድ እና ማደግ ይችላል። የተወለደው የዝሆን ልጅ ራሱን ለመመገብ አያዳግተውም። ሰው ግን ተወልዶ ቢጣል ያለሰው ማደግ አይችልም። ቆሞ ከመሄዱ በፊት መታቀፍ አለበት። መብላት እስከሚጀምር የሚያጎርሰው ይፈልጋል። ሰው ያለሰው አይሆንም። ሰው ከእንስሳት የተለየ ፍጥረት ነው። ሰው ዕውቀት፣ ኃይል እና ኃላፊነት ያለው ፍጥረት ነው። ሰው እንደ ሰው ሊታሰብ ይገባል” ብለዋል።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s