“እኛን ውሰዱና እህቶቻችን መልሱልን!” – ሥርጉተ©ሥላሴ

„ከግፍ ብዛት የተነሳ ሰዎች ይጮኃሉ፤
ከኃያልን ክንድ የተነሳ ለእርዳታ ይጣራሉ።“

ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
26.01.2020
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።

ይህን ዘመን እናልፈው ይሆን? ለካንስ ፌስ ቡክ እንዲህ ህይወት ነው። እንዴት ፈርቼው እኖር መሰላችሁ ውዶቼ። ” እኛን ውሰዱና እህቶቻችን መልሱ!” ዘመንን አናጋሪ፤ ዘመንን መካሪ፤ ዘመንን ገሳጭ፤ ዘመንን መርማሪ፤ ዘመንን ተርጓሚ፤ ዘመንን አናባቢ፤ ዘመንን ተነባቢ ያደረገ ጉልበታም አመክንዮ ነው። ሰለዚህም ነው ወደ ሌላውን የጹሑፍ እርማቴ መሄዱን ትቼ ይህን ከቶውንም የማይገኝ የውስጥነት ቅኔ ላጋራችሁ ብዬ የወሰንኩት። የትውልድ የርህርህና ሥጦታ እንዲህ ባለ የመሆን ውስጥነት ነው ሃዲዱ መዘርጋት አለበት። ብዬ አምናለሁኝ። እራስን ፈቅዶ መስጠት። እራስን ወዶ ለስቃይ አሳልፎ ማስረከብ። እንደምን ያለ ድንቅነት ነው? ዕውነት እንዲህ በፍጡራን ሲገኝ እንዴትስ አያጽናና። ብሩክ የሆነ መልዕክት። አደራንም ያወጣ። ትውፊትም መሆን የሚችል። የበቃ! 

ለክርስትና እምነት ተከታዮች የጌታችን መዳህኒታችን የእዬሱስ ክርስቶስን ጽዋ የተቀበለ መልዕክት ነው። ጌታችን መዳህኒታችን እዬሱስ ክርስቶስ ለእኛ ሃጢያት ሲል ነው ሞትን የቀመሰው፤ የተገረፈው፤ የተሰቀለው፤ የተንገላታው። እህቶቻችን ሆይ! ስቃያችሁን ሁሉ ለመቀበል ዝግጁ ነን ነው መልዕክቱ። ውስጥን እንዴት የሚመረምር ነው። በፍጽምና ሩህን የሚፈትሽ ኃያል መልዕክት አለው። እንዲህ ዓይነት ሰብዕናም አለ በኢትዮጵያዊነት ውስጥ። ይህ መልዕክት ለየኢትዮጵያዊነት ልዩ ማህደረ – ማዕረጉ ነው።

እንደምንስ ያለ ልብ የሚነካ፣ የሚፈትን፣ ውስጥን የሚጠይቅ እኛዊነት ነው። የእርህራሄው መጠን አጥንት ድረስ ይሰማል። እናት አንጀት የሚባሉ ተባእትን ሁሉ እነኝህ ወጣቶች ይወክላሉ። እንደምንስ አይነት ከተባረከ ማህፀን ነው የወጣችሁት? ከእንደምንስ ያለ አብራክ ይሆን የተገኛችሁት። ብሩክ ቅዱስ ሁኑ። አሜን! መቼም ዘንድሮ በሁሉም ነገር ሆድ ብሶኛል፤ እያነበብኩኝም እዬጻፍኩም ዕንባዬን መቆጣጠር በፍጹም አልቻልኩም። የመልዕክቱ ትህትና ቃለ ወንጌል ነው። ህይወት።

ሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያ የማያቸው ንጹህ ተሳትፎዎች ስድብ የለባቸውም፤ ቂም የለባቸው፤ ጥላቻ የለባቸው፤ መተላለፍ ብዙም የለባቸውም። ሰዋዊነት ባመዛኙ ጎልቶ እና ጎምርቶ በጉልበታም መልዕክቶች፤ በጠንካር የኪነ ጥበብ ብቃት የተቀመሩ ፖስተሮች ናቸው እኛና እኛን እትብታዊነት በአንድ የዕንባ ማዕዶት ላይ ያገናኜን። መከራችን መገናኛ ሰራ። ከዚህ የዕንባ ማዕድ ያፈነገጡ ሊኖሩ ቢችሉም ነገር ግን ያለው ተሳትፎ እጅግ የሚደንቅም የሚገርም ብቁ ነው። ከልጅ እስከ አዋቂ ድረስ ሁሉም ውስጡን እያስጎበኜ ነው።

በሁሉም ብመሰጥም የእናት ጋዜጠኛ እዬሩሳሌም ተ/ፃድቅ ፕሮግራም እዬመራች ዕንባዋን መቆጣጠር አለመቻል፤ የልጆች ተሳትፎ እና  የእነዚህ ሦስት ወጣቶች ውስጥነት እጅግ ነፍሴን የገዛው ሁኔታ ነው። በሌላ በኩል የውጭ ዜጎችም ዕንባችን መጋራታቸው ብሩክ ዜና፤

ልልፈውም፤ ልተውውም፤ ቸል ልበለውም ሊባል የማይችል ነገር ነው። በዚህ ማህል ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ ደግሞ ወደ ኤርትራ እንዳቀኑ እዬተደመጠ ነው። ምን ነካቸው ያሰኛል። በቃ እንዲህ ዓይነት የጭንቅ ቀን ሲመጣ ሹልክ ይላሉ። እንግዲህ መግለጫው ሊሰጥ ከታሰብ እሳቸው በሌሉበት የተፈጸመ እንዲባልላቸው ይሆን?

የሆነ ሆኖ ልዑል እግዚአብሄር እረኛ ለዚህ ዕንባ ይስጥ። ልዑል እግዚአብሄር ካዘኑት ጋር የሚዝን እረኛ ይስጥ። ልዑል እግዚአብሄር ከተጨነቁት ጋር የሚጨነቅ ሙሴ ይስጥ። ልዑል እግዚአብሄር ከተሰቃዩት ህዝቦቹ ጋር አብሮ የሚሰቃይ የእኛነት አለቃ ይስጥ። አሜን! ሁሉም ነገር ሆድ ያስብሳል። ሁሉ ነገር ያባባል። ሁሉ ነገር ይጨንቃል። ዘመኑም ከጨለማ በላይ ይጨልማል። ዘመነ የመቃብር ሥፍራ!

Related

ክፉነት ነግሶ ርህርህና ተሳደድ። ጭካኔ ነግሶ ደግነት ተገለለ። አረመኔነት ገዝፎ ሰዋዊነት መጠጊያ አጣ። ህዝብ ባለቤት አጣ። ግርባው ብአዴን የተጎጂ ቤተሰቦች ሄደው ሲያነጋግራቸው እንክብካቤ ማድረግ ሲገባው „የፖለቲካ መጠቀሚያ አደረጋችሁት“ ብሎ  እንዳሰናበታቸው አዳምጫለሁኝ። አርዮሳዊነት! ከቶ ከሰው ዘር ይሆን የተፈጠሩትን?

የልጅ አድራሻ በምን ሁኔታ ላላወቀ ወላጅ ይህ መልስ ነውን? አደራ የተሰጠው እኮ ለመንግሥት ነው። መንግሥት የሚያስጨንቀው  እሱ ዝብርቅ፤ ብርቅርቅ አመራር ወይንስ የእነዚያ ተስፋቸው የጨለመ ስቃይ ውስጥ ያሉ ልጆች? የትኛው ነው የሚቀድመው? የታመመ በሽተኛ ዕሳቤ። ሁለመናው ድውይ ሆነ። የዳነ የተረፈ ነገር ጠፋ።

  • ክውና።

ሁሉን አይደለም ያቀርብኩት ጥቂቱን ነው። ይህን ንጽህና አማላካችን ይጠብቅልን። ይህን ርህርህና ያለምልምን። እንዲህ የምንተዛዝንበት የድንግልና ዘመን ያምጣልን። አሜን!

ቸር ወሬ ያሰማን አምላካችን። አሜን።

የኔዎቹ ኑሩልኝ።

መሸቢያ ጊዜ።

የሌለው “ጭንብላችን” ቢገለጥ ምን ይመጣል? መስከረም አበራ

ሃገራችን ሩብ ምዕተ-ዓመት በቆየችበት ህወሃት-መር የጎጠኝነት ፖለቲካ እንደ አማራው ግራ የተጋባ ህዝብ/ልሂቅ የለም፡፡ አማራው ከጎጥ ፖለቲካው ጋር መላመዱ አልሆን ብሎት እስካሁን በገዛ ሃገሩ እንደ መፃተኛ ሆኗል፡፡ በጎጥ መደራጀቱ እንደ የማይገለጥ ምስጢር የሆነበት የአማራ ልሂቅ መገፋት ገፍቶት የመሰረተው መአድ የተባለው ፓርቲ ግማሽ ጎኑ አፍታም ሳይቆይ ወደ ህብረብሄራዊ ፓርቲነት ሲቀየር መቀየሩን ያልወደደው ቅሪቱ መአድ እንደ ሲኒ ውሃ እያደር ተመናምኖ ወዳለመኖር የተጠጋ ሁኔታ ላይ ነው፡፡ መአድ የተባለው ፓርቲ መኢአድ ወደሚባል ህብረ ብሄራዊ ፓርቲ የተቀየረው መለስ ዜናዊ አማራውን የሚያሳድድበትን በትር፣ የሚያሳርድበትን ቢለዋ ወደ ሰገባው ሳይመልስ ነው፡፡ ይህ ሁሉ የሆነው አማራው በጎጥ መደራጀቱን ስለማያውቅበት ነው፡፡ይህ የዘመኑን ፋሽን ያለመከተል የአማራው ግርታ ያደረሰበት ጉዳት መጠነ ሰፊ ነው፡፡

አማራን ሁሉ ባላንጣ አድርገው የሚያስቡ ኦነጋዊ የኦሮሞ ብሄርተኞች የአማራ ልሂቃንን ለዘውግ ፖለቲካ ባይትዋርነት “አማራው የብሄር ፖለቲካው አልገባ ብሎት ሲደናገር ሩብ ምዕተ አመት ሞላው፤ ይህ ለኦሮሞ መካልም ነው” ሲሉ በመሳለቅ ይገልፁታል፡፡ እነዚህ ቡድኖች አማራው ሲሞትም፣ ሲፈናቀልም፣ ሲንጓጠጥም ሲገደለም ዝም ማለቱ ብቻ ይስማማቸዋል፡፡ አማራው መናገር ሲጀምር ኦነጋዊ የኦሮሞ ብሄርተኞች እና ህወሃታዊ ትግራዊያን የሚናገረው ሁሉ ያስበረግጋቸዋል፡፡ አማራው በዘውጉ የሚደርስበትን ሁሉ ችሎ የለመደውን ኢትዮጵያዊነት ሲያጠብቅ በኢትዮጵያዊነት ስም ፍላጎቱን በብሄረሰቦች ላይ የሚጭን ጨቋኝ ሲሉ ኢትዮጵያን በማለቱ በድንጋይ መወገር የሚገባው ሃጢያተኛ አድርገው ያቀርቡታል፡፡ እነሱው በየደረሱበት በሚሰኩት የአማራ ጥላቻ ሳቢያ በአማራነቱ መሞቱ ተሰምቶት ኢትዮጵያዊነቱን ሳይጥል አማራነቱ እያስገደለው እንደሆነ ከተናገረ ደግሞ በጭብላምነት ያብጠለጠሉታል፡፡ አማራውም ይጥለው ዘንድ የማይችለውን ኢትዮጵያዊነት በደሙ ውስጥ ይዞ የተጋረጠበትን የህልውና አደጋም ለመከላከል ቢጣጣርም አማራነቱን ማጠባበቁ ከኢትዮጵያዊነቱ የሚጋጭ እየመሰለው በፈራተባ ውስጥ ይኖራል፡፡

የአማራው ዘመን አመጣሹን የጎጥ ፖለቲካ ፋሽን ተረድቶ ራሱን ከዘመኑ ጋር ማራመድ አለመቻሉ (በባላንጣዎቹ ንግግር “ግራ መጋባት”) ቋጥኝ የሚያክል ፈተና ያንዣበበትን የአማራውን ህዝብ ያለጠበቃ አስቀርቷል፡፡ የጎጥ ፖለቲካውን መላመድ ድሮ ቀርቶ ዛሬ ያልሆነላቸው የአማራ ምሁራን በአማራ ብሄርተኝነት መስመር ተሰልፈው ሌሎች እንደሚያደርጉት ለህዝባቸው መሞገት አለመቻላቸው ለኦነግ ግርፍ የኦሮሞ ብሄርተኞች እና ህወሃት ቀመስ ትግራዊያን የአባት ገዳይን በግላጭ እንደማግኘት ያለ ሰርግ እና ምላሽ ነበር፡፡ ሆኖም በአማራው ላይ የሚወርደው ዱላ የተኛ ቀርቶ ሙት የሚቀሰቅስ እየሆነ ሲመጣ ዛሬ ላይ የአማራ ምሁራንም ከእንቅልፋቸው መንቃት ጀመሩ፡፡ ይህ ደግሞ ለኦነጋዊ የኦሮሞ ብሄርተኞች እና ለህወሃቶች መልካም አዝማሚያ አይደለም፡፡ ለእነሱ መልካም የሚሆነው ባፈው ሃያ ሰባት አመት እንደሆነው አማራው ከሞት በበረታ ዝምታ ውስጥ ሆኖ ግድያውንም፣ መንጓጠጡንም፣ መፈናቀሉንም፣ መገደሉንም አጎንብሶ ሲቀበልነው፡፡

ይህ ሁለት ጥቅም አለው፡፡ አንደኛው አማራው “በሰራው ታሪካዊ ወንጀል” የሚሸማቀቅ በደለኛ እንጅ ስልጣን የሚጋራ የፖለቲካ ሃይል አለመሆኑ ለኦሮሞ ብሄርተኛ ሁለተኛውን ግዙፍ ዘውግ ከስልጣን ተገዳዳሪነት ይቀንስለታል፡፡ ሁለተኛው ጥቅም በታሪክ በድሎናል የሚሉትን ህዝብ በማሸማቀቅ የሚያገኙት ስሜት በቀለኝነት የሚጋልበውን የስነ-ልቦና ቀውሳቸውን ተንፈስ ያደርጋል፡፡ ስለዚህ አሁን አሁን ከበደል ብዛት የተነሳ እያቆጠቆጠ ያለውን የአማራ ብሄርተኝነት አይወዱትም፡፡ ምክንያቱም የአማራው ብሄርተኝነት ካቆጠቆጠ አማራው ያለ ስራው የተለጠፈበትን የበደለኝነት ተረክ የሚያፈርስ መልስ መስጠት ይጀምራል፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ አማራውን ጭራቅ አድርገው የሚያቀርቡበትን ተረክ ብቻቸውን እያወሩ፣ ያወሩትም እንደእውነት እየተቆጠረ ወደስልጣን ማዝም አይቻልም፡፡ አማራውን የማይስተሰረይ ሃጢያት የሰራ በደለኛ አድርጎ ማሸማቀቅም አይቻልም፡፡ ስለዚህ አማራው በደሉ እንዲሰማው አይፈለግም! በአይን የሚታየውን በአማራ ህዝብ ላይ ያንዣበበ አደጋም ሆነ በዚህ ህዝብ ላይ በወያኔ እና ኦነግ የተደረገውን ግፍ አንስቶ የሚሞግት አማራም ሆነ ሌላ የሰው ዘር አይፈለግም፡፡

ከወያኔ ወደ ስልጣን መምጣት ወዲህ በአማራ ህዝብ ላይ በርካታ በደል የተፈፀመ፣ አሁንም ይህ ህዝብ በሃገሪቱ ባሉ የዘውግ ፖለቲከኞች ሁሉ በክፉ አይን የመታየት ፈተና ውስጥ ያለ ቢሆንም የአማራ ምሁራን እና ልሂቃን ኢትዮጵያዊ ብሄርተኝነታቸውን የሚቀማቸው የሚመስላቸውን የአማራ ብሄርተኝነት መልበስ አይፈልጉም፡፡ በአንፃሩ የወጡበት ህዝብ ያለበት ፈተናም ያሳስባቸዋል፡፡ ስለዚህ ኢትዮጵያዊ ብሄርተኝነታቸውን ሳይጥሉ ስለ አማራው ህዝብ እንግልትም ይሟገታሉ፡፡ የአማራ ህዝብ ሁሉ ባላንጋራቸው የሚመስላቸው ኦነጋዊ የኦሮሞ ብሄርተኞች ደግሞ መለስ ዜናዊ እንዳደረገው የአማራን ህዝብ ያለ አንዳች ጠበቃ መቅጣት ስለሚፈልጉ ይህን ነገር አምርረው ይጠላሉ፡፡ኢትዮጵያዊነትን ሳይጥል የአማራ ህዝብ ለምን በገዛ ሃገሩ እንዲህ ይደረጋል የሚል የሚል የአማራ ልሂቅ ሲገጥማቸው ሌባ እጅ ከፍንጅ እንደያዘ ሰው ባለድልነት ይሰማቸዋል፡፡

ለአማራ ልሂቃን/ምሁራን ኢትዮጵያዊነት የክብር ልብስ እንጅ ጭንብል አይደለም!ኢትዮጵያዊነት ጭንብላችን ቢሆን ኖሮ በአማራ ህዝብ ላይ ከመለስ ዜናዊ እስከ ጃዋር መሃመድ ነጋሪት ጎሳሚነት የደረሰው በደል ጭንብል ቀርቶ ቆዳ የሚያስወልቅ ክፉ ነውና “ጭንብል” ወርውሮ ጎጠኛ መሆን አስቸጋሪ ሆኖ አይደለም፡፡ ኢትዮጵያዊነት በአማራ ህዝብ/ልሂቅ/ምሁር ዘንድ በደም ውስጥ የሚሮጥ ልክፍት እንጅ ጭንቅላት ላይ ለይምሰል ሸብ የሚደረግ ቡቱቶ ጨንብል አይደለም፡፡ የአማራ ልሂቃንን በጭንብላምነት የሚከሱ የኦሮሞ ብሄርተኞች ኢትዮጵያ እንደኩንታል አናታቸው ላይ ተጭና የምትከብዳቸው ሸክማቸው እንደሆነች የፈረንጅ ጋዜጠኛ እጅ እየመቱ የሚምሉ፣ ኦሮሚያ የምትባል ሃገር ናፍቆተኞች ናቸው፡፡ ስለዚህ ሁሉም እንደነሱ ይመስላቸዋል፡፡ ኢትዮጵያን ማለት ትርጉም ስለማይሰጣቸው ሁሉም እንደእነሱ ኢትዮጵያን በጭንብሉ፤መንደሩን ሃገር አሳክሎ በልቡ ተሸክሞ የሚጓዝ የማነስ ልክፍተኛ ይመስላቸዋል፡፡ ስለዚህ የሌለ ጭንብል ይፈልጋሉ፡፡

ለማንኛውም እነሱ ጭንብል የሚሉት ነገር ለአማራው ማን እንደጣለበት የማያውቀው፣ በደሉን እንኳን እንዳይቆጥር የሚያደርግ ኢትዮጵያን የሚያስብለው ከደሙ ጋር በመላ ሰውነቱ የሚዞር ልክፍቱ እንጅ አናቱ ላይ የተንከረፈፈ ጭንብሉ አይደለም፡፡ ይህ ልክፍቱ ነው ኢትዮጵያን ካለ ጋር ሁሉ የሚያዛምደው፡፡ አማራው ኢትዮጵያን ይላል ማለት ግን ስሟ በተጠራበት ልገኝ በሚልላት ሃገሩ አማራነቱ ወንጀል ሆኖ ሲያስገድለው ዘላለም የማይገባው ነፈዝ ነው ማለት አይደለም፡፡ ኢትዮጵያዊ ሆኖም በአማራነቴ አትግደሉኝ ማለትን የሚከለክል ፍርደ-ገምድል ህግ የለም! “ኢትዮጵያዊ ነኝ ካልክ አማራ ነህ ብየ ስገድልህ አመጣጤ አይግባህ” የሚባል አካሄድ ድሮ ቀርቷል፡፡ ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚለውን ሰው አማራ ነህ ብሎ ገድሎ ያስገደለህን ምክንያት ስሙን አትጥራ ማለት የሞኝ ብልጠት ነው፡፡ ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚለውን ሰው አማራ ነህ ብሎ የሚያስገድለው አባዜ ሁለቱንም የመጥላቱ በሽታ መሆኑን ማን ያጣዋል?

ለማንኛውም አማራው አጠለቀው የተባለው የኢትዮጵያዊነት ጭንብል የኢትዮጵያዊነቱን ከፍታም ሳይለቅ በአማራነቱ ሚመጣበትን ፍላፃም ለመከላከልም የመሞከሩ የሚዛናዊነቱ ምልክት ነው፡፡ አማራውን ኢትዮጵያዊ ነኝ በል እያሉ ግን በአማራነቱ የሚገድሉት አዳኞች ደግሞ ይህን አይወዱምና ኢትዮጵያዊነት ከአማራው ላይ እንደማይወልቅም፣ ጭምብል እንዳልሆነም እያወቁ “ጭንብልህን አውልቅ” ይላሉ፡፡

አይሆንም እንጅ አማራው ችሎ ኢትዮጵያዊነቱን እንደተንከረፈፈ ጭንብል ቢያወልቅ ለኢትዮጵያ መልካም አይሆንም፡፡ አማራው ኢትዮጵያዊነቱን አወለቀ ማለት ትልቁ የኢትዮጵያ አእማድ ፈረሰ ማለት ነው፡፡ ይሄኔ ኢትዮጵያዊነት በአማራነት ይተካል፤ ከተተካ ደግሞ የጎጥ ፖለቲካ መለያ የሆነው “ሁሉ ኬኛ” የሚባለው አባዜ አማራውንም ይዋሃደውና የቱ የአማራ የቱ የኦሮሞ ግዛት እንደሆነ የመነጋገሪያ ፋታ የለም! ያኔ መናጋገሪያው ጡጫ ይሆናል፡፡ አንዴ ወደ ቁልቁለት ከተወረደ ደግሞ ጡጫ የማይጨብጥ እጅ ያለው የለም፤ በአንድ እጅ አስር ጡጫ የሚጨብጥ ባለ ዘጠኝ ሱሪም የለም!

ማቆሚያ የሌለው የኦሮሞ ጽንፈኞች ሽብር – ግርማ ካሳ

በኦነግ የኦሮሞ ታጣቂዎች የታገቱ ተማሪወች ስም ዝርዝር እንደሚከተለው ነው፡፡ ተማሪዎች ይኑሩ፣ ይሞሩ ፣ በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ የሚታወቅ ነገር የለም፡፡ ሕገና ስርዓት ማስጠበቅ ሳይሆን እንደውም ሕግና ስርዓት የሚጥሱትን የሕግ ከለላ የሚሰጠው የኦሮሞ ክልል መንግስት አፉን ዘግቶ ቁጭ ብሏል፡፡ እንደውም አንዳንድ አመራሮቹ በክልላቸው የሆነው ነገር እኛ ምንም የምናውቀው ነገር የለም እያሉን ነው፡፡

የፌዴራል መንግስቱ ውሸትንና ዝምታን ነው የመረጠው፡፡ ተማሪዎች ከአንድ ወር በላይ ታግተው ደንታም የተሰማቸው አይመስልም፡፡

ተማሪዎቹ የመጡበት የአማራ ክል መስተዳደር ሁኔታማ ማሳዘን ብቻ ሳይሆን በሕዝቡ ላይ የተፈጸመ እጅግ በጣም ትልቅ ክህደት ነው፡፡ በዚህ አይነት ከነ በረከት ስምኦን በምን እንደሚሻሉ ቢነግሩን ጥሩ ነበር፡፡

1, በላይነሽ መኮንን ደምለዉ (Auto Economics 1st year ) ከጎንደር
2, ሳምራዊት ቀሬ አስረስ (Journalist 2nd year ) ከጎጃም
3, ዘዉዴ ግርማዉ ፈጠነ ( Auto Economics 3rd) ከጎንደር
4, ሙሉ ዘዉዴ አዳነ (Sociology 2nd year) ከጎጃም
5, ግርማቸዉ የኔነህ አዱኛ (Biotechnology 3rd year) ከጎንደር
6, ስርጉት ጌቴ ጥበቡ (Natural science 1st year) ከጎንደር
7, ትግስት መሳይ መዝገቡ (የ12 ፕሪፕ ተማሪ) ከቄለም ወለጋ ጨነቃ
8, መሰለች ከፍያለዉ ሞላ ( Natural science 3rd year) ከወሎ
9, ዘመድ ብርሃን ደሴ (Natural science 3rd year) ከወሎ
10, ሞነሞን በላይ አበበ (journalist 2nd year) ከ ጎጃም
11, ጤናለም ሙላቴ ከበደ (Agro Economics 2nd
year) ከጎጃም
12, እስካለሁ ቸኮል ተገኝ (Chemistry 3rd year ) ከጎንደር
13, አሳቤ አየለ አለም (Plant science 3rd year ) ከጎጃም
14,ቢተዉልኝ አጥናፉ አለሙ (Computer science 3rd year) ከጎንደር
15, ግርማዉ ሀብቴ እመኘዉ (Mechanical Engineering 3rd year) ከጎንደር
16, አታለለኝ ጌትነት ደረሰ (Natural science 1st year ) ከጎንደር
17, ክንድዬ ሞላ ገበየሁ ( Natural science 1st year) ከጎንደር ናቸዉ።