ሱዳን ከአማራ ክልል ጋር በምትዋሰንበት በኩል የሚገኘውንና ሶስት ወንዞች የሚያቋርጡትን የ250ካሬ ኪ.ሜ የቆዳስፋት መሬት እንደገና ይካለል ዘንድ ለኢትዮጵያ መንግስት ጥሪ አደረገች (አዋዜ)

Ethiopia-Sudan-Border-Protest1

የሱዳን ገዳሪፍ ግዛት ሀገረ ገዢ ሜርጋኔ ሳሌህ በኢትዮጵያና በሰዳን መካከል አለ ብለው የሚያምኑት የረጅም ግዜ የድንበር ውዝግብ ይፈታ ዘንድ ድንበሩ እንዲካለል መጠየቃቸው ተሰማ፡፡ ሄራል ትርቢውን የተሰኘው ጋዜጣ ትላንት እንደዘገበው ሱዳን በምስራቃዊ ግዛቴ ገዳሪፍ ደቡብ ምስራቅ አል-ፍልሻጋ በተባለው አከባቢ ይገኛል የምትለውና የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች መሬታችው መሆኑን ሚናገሩለትን ይህን ምሬት ጉዳይ ከቀ/ጠ/ሚ/ አቶ/መለሰ ዜናዊ ግዜ ተጀምሮ እሳቸው ድንገት በመሞታቸው መቋረጡን ያስታውሳል ጋዜጣው፡፡ እናም አሁን ‹‹የኢትዮጵያና ሱዳን መንግስታት ድንበሩን እንደገና ለማካለል በተስማሙት መሰረት ይፈጸምና ድንበር ውዝግቡ ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ይፈታ››› ብለዋል ገዳሪፍ ሀገረ ገዢ፡፡

የሱዳኑ ሄራልድ ትርቢውን የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ‹‹ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ የኢትዮጵያን ምድር ለሱዳን አሳልፎ ትቶለታል በማላት ይከሳሉ›› ሲል ጋዜጣው ጽፏል፡፡ በባለፈው የፈረንጆች አመት ህዳር ወር የሱዳኑ አል-በሽርና የኢትዮጵያው ጠ/ሚ ሀይለማሪያም ደሳለኝ በቀ/ጠ/ሚ/ አቶ/መለሰ ዜናዊ ሞት የተነሳ የተቋረጠውን ድንበሩን እንደገና የማካለል ስራ የሚጀመርበትን አዲስ ቀን እንዲወስኑ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሮቻቸው መመሪያ ማስተላለፍቸውን ጋዜጣው ጠቅሷል፡፡

አዲስ ይደረጋል በተባለው ማካለል ጉዳይ ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀው መሬት 250 የ250 ካሬ ኪ.ሜ ነው ምናልባት የአዲስ አበባን ጠቅላላ ስፋት ከግማሽ በላይ የሚሆን መሬት ማለት ነው፡፡ በውስጡ ደግሞ ለእርሻ እጅግ ተስማሚ መሬት የሆነ 6 መቶ ሺ ሄክታር 6 መቶ ሺ የእግር ኳስ ሜዳ የሚያክል ለም መሬት አለው፡፡

የሱዳኑ ሄራልድ ትርቢውን እንደተነተነው ይህን ለም መሬት ደግሞ አጥባር ሲቲት ባዝላን የሰተሠኙ ወንዞች አቋርጠውት የሚያልፉ በመስኖ ሊለማና በአመት ሁለት ግዜ ሊመግብ የሚችል በጠራ ቋንቋ ጮማ መሬት ነው የሱዳን ገዳሪፍና ብሉ ናይል ግዛቶች ከአማራ ክልል ጋር የሚዋሰኑ ናቸው፡፡

ምንጭ ፤- አዋዜ

– See more at: http://satenaw.com/amharic/archives/10034#sthash.CwU6WdaE.dpuf

ከዊሃ እስከ ኦምሃጀር – አንድ ሰሞን ከአርበኞች ጋር (ኤፍሬም ማዴቦ)

በኤፍሬም ማዴቦ

ቃል የዕምነት ዕዳ ነዉ። አዎ! ማተቡን ላጠበቀና በአምላኩ ለሚታመን በእርግጥ ቃል የዕምነት ዕዳ ነዉ። ሰዉ ነኝና እንደ ፈጣሪ ቃሌ ሁሉ እዉነት ነዉ ብዬ አለተፈጥሮዬ አላብጥም። ግን ሰዉ ብሆንም ፈጣሪዬን የምፈራ ሰዉ ነኝና ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ስል ልቦናዬ እያወቀዉ እንደነ ጋሼ እንደልቡ ዉሸት ደርድሬ ለአንባቢ የማቀርብበት ምንም ምክንያት የለም። ከዚህ ቀጥሎ የማስነብባችሁ እያንዳንዱ ቃል እንደ ዳያስፖራ ተረተኞች የምተርተዉ ‘ሰዉ ሰዉ’ የማይሸተት ተረት ሳይሆን ኢትዮጵያ ድንበር ላይ በየግንባሩ የተሰለፉትንና በስልጠና ላይ የሚገኙትን የኢትዮጵያ አርበኞች ስጎበኝ በአይኔ ያየሁትንና በጆሮዬ የሰማሁትን ቃል ነዉ።Ephrem Madebo with Patriotic Ginbot 7 fighters

ቨርጂኒያ ወደሚገኘዉ “Dulles” አዉሮፕላን ማረፊያ የሄድኩት ከልጄ ጋር ነበር። ከቤቴ Dulles የግማሽ ሰዐት መንገድ ነዉ። ያቺን ግማሽ ሰዐትና አዉሮፕላን ማረፊያ ደርሼ ሻንጣዬን እስካስጭን ድረስ አይኔ እያንዳንዷን ደቂቃ ከልጄ ከቢኒያም አልተለየም። መለየቱን ስላልወደደዉ ልቤ ደንግጧል። ከወያኔ ጋር ለመፋለም በረሃ የሚጓዘዉ ኤፍሬም ከአንድ ልጁ መለየት አቃተዉ። ምነዉ ብዬ እራሴን ጠየኩት- እኔዉ መልሼ ምንም አልኩ። ልጄን አቀፍኩት፤ አሁንም ደግሜ ደጋግሜ አቀፍኩት። እምባ ፊቴን ሞላዉ። ቀና ብሎ ተመለከተኝና ሲከፋዉ ታየኝ። ሁለተኛ ዙር እምባ ፊቴን ሞላዉ። “Son I don’t want to do this, but I have to do it” አልኩ በሁለት እጄ አቅፌ እንደያዝኩት። ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ አባት ሆይ ፈቃድህ ከሆነች ይቺ ጽዋ ከኔ ትለፍ ብሎ የጸለየዉ ፀሎት ትዝ አለኝ። እኛ ሰዎች የዳንነዉ ይህ ፀሎት ባለመመለሱ መሆኑ ትዉስ ሲለኝ ልቤ በሀሳቡ ጸና። አባባ Come on . . . be strong. I promise I will be the son that you raised- you will be proud of me” አለኝ ቢኒያም በዚያ 17 አመት ሙሉ በማዉቀዉ ቆንጆ ድምጹ። የተናገራቸዉ ቃላት ዉስጤ ገብተዉ ኃይል ሲሆኑኝ ተሰማኝ። ጠነከርኩ። ተሰናብቼዉ ወደኋላ እያየሁት ወደ ዉስጥ ገባሁ። ወደ ፍተሻዉ ቦታ ስሄድ ልቤን ከፍተኛ የመለየት ኃዘን እንደ ግግር በረዶ ሲጫነዉ ተሰማኝ፤ መሸከም አቃተኝና እንደ ህፃን ልጅ እያነባሁ ፍተሻዉ መስመር ላይ ገብቼ ወረፋ ያዝኩ።

እንደፈረንጆቹ ዘመን አቆጣጠር ረቡዕ ኦጎስት 5 ቀን ከሌሊቱ 9 ሰዐት የተሳፈርኩበት አዉሮፕላን አስመራ አለም አቀፍ አዉሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ አይኔ ላይ ዉል ዉል እያለ ልቤን የሰቀለዉ የሚጠብቀኝ የትግል ዉጣ ዉረድ ሳይሆን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተመርቄ በ22 አመቴ ስራ የጀመርኩባት ዉቧ የአስመራ ከተማ ምን ትመስል ይሆን የሚል የሀሳብ ዉጣ ዉረድ ነበር። ሆኖም አካልም መንፈስም እየከዳ ምንም ነገር ማሰብ አይቻልምና ወደ ግዜያዊ ማረፊያ ቦታዬ እንደወሰዱኝ ለሁለት ቀን ከግማሽ የተጠራቀመ እንቅልፍ ይዞኝ ጭልጥ አለ።

ረቡዕ ከቀኑ አንድ ሰዐት አካባቢ “እባክህ ተነሳና ምሳ እንብላ” የሚል የሁለት ሰዎች ድምጽ ተራ በተራ ጆሮዬ ዉስጥ ገባና እንቅልፌን ሰለበዉ. . . መነሳት ባልፈልግም በልቤ ትግሉ ተጀመረ አልኩና ከተጋደምኩበት ቀና አልኩ። ፊት ለፊቴ ቆመዉ ተነስ እያሉ የሚጨቀጭቁኝ የትግል ጓደኞቼ ነአምን ዘለቀና ብርሀኑ ነጋ ነበሩ። ምሳ ላይ ተቀምጠን እነሱ የሚያወሩት ወደ ኤርትራ በረሃዎች ሰለሚደረገዉ ጉዞ ሲሆን እኔ ደግሞ በወጣትነቴ ስለማዉቃት የአስመራ ከተማ ነበር። አስመራን ትቼ ከነሱ ጋር እንደነሱ ማሰብ ሞከርኩ . . . አሁንም አሁንም ሞከርኩና ሲያቅተኝ ተዉኩት። በተለይ ምሳ የበላንበት ካራቨል ሬስቶራንት ዉስጥ በወጣትነቴ ብዙ ትዝታዎች ነበሩኝና ጭራሽ ምግቡን ትቼ በምናብ ወደ ወጣትነቴ ሽምጥ ጋለብኩ። ባር ኡጎ፤ ባር ቱኔል፤ ባር ፀአዳ ፈርስ፤ ባር እምባባና የባቢሎን ጋጋታ እንዳለ ፊቴ ላይ እየመጡ ተደቀኑ። ቀና ስል ነአምንና ብርሀኑ . . . አትበላም እንዴ አሉኝ። ወደ ኋላ ሽምጥ ያስጋለበኝን ፈረሴን ልጓም ያዝ አደረኩና ካሁን በኋላ ወደፊት ብቻ ብዬ ከሁለቱ ጓደኞቼ ጋር በአካልም በመንፈስም ተቀላቀልኩ።

የአስመራ ከረን መንገድ ከተነጠፈ አስፋልት ዉጭ ሌላ ምንም አይቶ ለማያዉቅ ለእንደኔ አይነቱ የዳያስፖራ ‘በለስ’ ቀርቶ ደጋግሞ የተጓዘበትንም ሰዉ ልብ ይሰልባል። አስመራን ይዞ፤ አዲአቤቶንና እምባደርሆን ይዞ በአዲተከለዛን፤ በኢላበርዕድ፤ በከረንና በሀጋዝ አድርጎ አቆርደት ድረስ የሚዘልቀዉ መንገድ የአለም ተራራዎች ስብሰባ ተጠራርተዉ ወደየመጡበት ላለመመለስ ተማምለዉ የመሸጉበት ቦታ ይመስላል። አንዱን ተራራ ሽቅብ ወጥተንና ቁልቁል ወርደን እፎይ ብለን ሳንጨርስ ሌላዉ ከተፍ ይላል። በስተቀኛችን ያለዉን ተራራ አይተን ወይ ጉድ ስንል በግራችን ያለዉ ድንቄም ጉድ እያለ ያሾፍብናል። እልፍ ስንል ተራራ፤ ከዚያም ተራራ፤ተራራ፤ ተራራ ብቻ ነዉ። ፊት ለፊቴ የማያቸዉ ተራራዎች ተፈጥሮ የቆለለዉ የዲንጋይ ክምር ሳይሆን አዋቂ በዉኃ ልክ እየጠረበ የደረደረዉ ሾጣጣ ኃዉልት ይመስላሉ። አንኳን ለሰዉ ልጅ ለገደሉ ንጉስ ለዝንጀሮም አይመቹም። ባጠቃላይ የአስመራ አቆርደትን መንገድ ሲመለከቱት እንደ አጥር ከተሰለፉት ተራራዎች ባሻገር አገር ያለ አይመስልም። አላማና ጽናት ላለዉ ሰዉ ግን ከተራራዉ ወዲያ አገር ከአገርም ወዲያ ሌላ. . . ሌላ ወያኔ የቀማን አገር አለ።

አላማ የሌለዉ፤ ሆዱ ያልቆረጠ፤ ፈሪ፤ ወኔ የከዳዉና አይኑን ተራራዎቹ ላይ ብቻ ያሳረፈ ሰዉ ከአስመራ ተነስቶ በከረን በኩል አቆርደትን አቋርጦ የጀግኖቹ መንደር ሀሬና የሚደርስ አይመስለዉም። ለዚህ ነዉ ሁሉን የሚችል እግዚአብሄር አይዞህ ብሎ የላከዉ የብሉይ ኪዳኑ ነቢዩ ኤልያስ ኤልዛቤልን ፈርቶ እንደሸሸ ሁሉ የኛም ዘመን ጋዜጠኛ ነን ባዮች፤ ዘፋኞችና አርበኛ ነን ባይ የሀሰት ነቢያት ገና ከረን ሳይደርሱ ተራራዉን እየፈሩ በኤርትራ በኩል ምንም ነገር መስራት አይቻልም እያሉ እንደ ግመል ሽንት የኋሊት የሚጓዙት። ድንቄም ጋዜጠኛ! ጋዜጠኛ ታሪክ ሸራርፎ በሰጠዉ ግዜ እየኖረ ያየዉንና የሰማዉን ለትዉልድ እያስተላለፈ ለራሱ የማይኖር ልዩ ፍጡር ነዉ። የኛዎቹ “ጋዜጠኛ” ነን ባዮች ግን እራሳቸዉ ለራሳቸዉ በሰጡት ግዜ እየኖሩ የራሳቸዉን ግሳንግስ የፈጠራ ታሪክ የሚነግሩን ከህያዉ በታችና ከሙታን በላይ ባለዉ ባዶ ቦታ የሚኖሩ ባዶዎች ናቸዉ። አምላክ በምህረቱ ወደ ላይ ይሳባቸዉና ከህያዋን ጋር ይቀላቅላቸዉ።

ምድረ የወሬ ቋቶች ይግባችሁ! የኢትዮጵያ ህዝብ ዉኃ ዉኃ የሚያሰኝ የእሳት ጉድጓድ ዉስጥ ነዉ ያለዉ፤እሱ ከጉድጓዱ ባስቸኳይ መዉጣት እንጂ እንደናንተ በኤርትራ በኩል ከሆነ ይቅርብኝ ብሎ የሚጃጃልበት ግዜዉም ትዕግስቱም የለዉም። ለነገሩ እነዚህ የወሬ አርበኞች ተራራ ወጥተዉ፤ በረሃ አቋርጠዉና ወንዝ ተሻግረዉ ከወያኔ ጋር ሳንጃ ሊማዘዙ ቀርቶ የገዛ ልጆቻቸውን የልደት ኬክ ደፍረዉ በቢላዋ የማይቆርጡ የ”ዳዉን ታዉን” ቅምጦልች ናቸዉና ከነወሬያቸዉ እዚያዉ “ዳዉን ታወን” ብንተዋቸዉ የሚበጅ ይመስለኛል። አይደል?

ወሬና ስራ ለየቅል ናቸዉ፤ ለወሬ የሚያስፈልገዉ ሹል አፍ ብቻ ነዉ። ለስራ ግን አፍ፤ እጅ፤ አግር፤ አይን፤ ጆሮና የሚያስብ አዕምሮ ያስፈልጋል። ወረኛና ለስራ ያልተፈጠረ ሰዉ የተራራዉ ከፍታ እየታየዉ “በዚህ በኩል እንዴት ተደርጎ” እያለ የወሬ ቱማታዉን መደርደር ይጀምራል። የሚሰራ ሰዉ ግን ግቡ ከተራራዉ ባሻገር ከተከዜ ማዶ ነዉና ተራራዉን ሽቅብ ወጥቶና ከጠመዝማዛዉ መንገድ ጋር እኩል ተጠማዝዞ ወዳለመዉ ግብ ይጓዛል። አንባቢ ሆይ! ሠራተኛ በለኝ አትበለኝ እሱ ያንተ ጉዳይ ነዉ፤ መዳረሻዬ ከተከዜና ከመረብ ወንዞች ባሻገር መሆኑንና አላማዬም ፍትህና ነጻነት መሆኑን ግን እኔዉ እራሴ አብጠርጥሬ ልነግርህ እችላለሁ። የምወደዉን አንድ ልጄንና ጥሩ ስራዬን ደህና ሁኑ ብዬ በረሃ የገባሁት እናት አገሬ ዉስጥ ፍትህ፤ ነጻነት፤ እኩልነትና ዲሞክራሲ አብበዉ ለማየት ነዉ እንጂ የኤርትራ በረሃና ተራራ ናፍቆኝ አይደለም። የናፈቀኝ ተራራና በረሃ ቢሆን ኖሮ አሪዞናና ኮሎራዶ ይቀርቡኝ ነበር።

ዉቧን የአቆርደት ከተማና ቀዳማዊ ኃ/ሥላሤ ያሰሩትን ግዙፍ መስጊድ በስተቀኝ እያየን ወደ ባሬንቱ ስናመራ ያ ከአስመራ ጀምሮ የተከተለን የተራራ መንጋ ፀሐይ እንደገላመጠዉ በረዶ እየሟሸሸ ሄዶ ገና ሀይኮታ ሳንደርስ ሜዳ ሆኖ አረፈዉ። የበረሃዉ ሙቀት እንዳለ ቢሆንም ባሬንቱ ስንደረስ የሚነፍሰዉ ቀዝቃዛ አየር ሙቀቱን አለዝቦታል። ባሬንቱን ለቅቀን ወደ ተሰነይ ስናመራ መሬቱ ሜዳ፤ ሰማዩ ደመናማ፤ አየሩ ነፋሻማ እየሆነ ይመጣል። ትናንሽ ልጆች እዚህም እዚያም ይዘልላሉ፤ ትራክተሩ ያርሳል፤ ግረደሩ ይዳምጣል፤ እንደኔ አይነቱ ጠመዝማዛዉ መንገድ ቀልቡን የሰለበዉና ፀሐዩ ያቀለጠዉ ምስኪን ደግሞ ወላዲት አምላክ ምን በደልኩሽ እያለ ያምጣል። ባሬንቱ ያኔ እኔ ሳዉቃት የጋሽና ሰቲት አዉራጃ ዋና ከተማ ነበረች፤ ዛሬ ከሃያ ስምንት አመት በኋላ ያየኋት ባሬንቱ ግን ከፍተኛ የንግድና የእርሻ እንቅስቃሴ ይታይባታል፤ ዉብትም ስፋቷም በእጥፍ ጨምሯል ፤ደግሞም የዛሬዋ ባሬንቱ የጋሽ ባርካ ዞን ዋና ከተማ ናት።

ከባሬንቱ ወደ ተሰነይ ሲወጣ ግራና ቀኝ አዉራጎዳናዉን ይዞ ኢትዮጵያና ሱዳን ጠረፍ ድረስ የተንጣለለዉ መሬት የኤርትራ የእህል መቀነት ነዉ። አካባቢዉ ከፍተኛ የልማት እንቅስቃሴ ይታይበታል። የኤርትራን ልማትና የኤኮኖሚ እንቅስቃሴ ማየት የፈለገ ሰዉ ከአስመራና ከሌሎች ትላልቅ ከተማዎች ወጥቶ ገጠር መግባት አለበት። ግድቡ፤ እርሻዉ፤ የጤና ተቋሙና ሌላም ሌላ የመሠረተ ልማት ምልክቶች በጉልህ የሚታዩት ገጠሪቱ ኤርትራ ዉስጥ ነዉ።

ከተሰነይ ወጥተን ጥቂት እንደተጓዝን መኪናችን አስፋልቱን ለቅቃ ኮረኮንቹ መንገድ ዉስጥ ገብታ ስትንገጫገጭ ከእንቅልፌ ነቃሁና እንደመንጠራራት ብዬ . . . ደረስን እንዴ አልኩ … የመኪናችንን ሾፌር። ገና ነዉ ትንሽ ይቀራል አሉ ወደኋላ ዞር ብለዉ። እንዳዉ ለነገሩ ነዉ እንጂ ሰዉዬዉ ዬት እንሄዳለን፤ መቼ አንሄዳለን ወይም መቼ እንመለሳለን ለሚሉ ጥያቄዎች በፍጹም መልስ አይሰጡም። ወያኔ የማይሰማን ሁሉንም ነገር ሆዳችን ዉስጥ ከያዝነዉ ብቻ ነዉ የሚል ፈሊጥ አላቸዉ። ዋናዉን መንገድ ለቅቀን ኮረኮንቹን ከተያያዝነዉ በግምት ከ20 ደቂቃ በኋላ አርበኞች መንደር ቁጥር አንድ ደርስን። ዘፈኑ፤ ጭፈራዉ፤ ሆታዉና ዕልልታዉ ቀለጠ። አርበኛዉ ጠመንጃዉን እንደታቀፈ እየዘለለና እየፎከረ እንኳን ደህና መጣህልን እያለ መሪዉ ላይ ተጠቀለለ። “የወያኔ ዘረኞችና አንዳንድ ተላላዎች አንተንና ጓዶችህን ትኩስ ሀምበርገር እየበላችሁ ወጣቱን በረሃ ዉስጥ ታስጨርሳላችሁ” እያሉ አርበኛዉንና መሪዉን ለመለያየት ብዙ ጥረዋል። እናንተ ግን የሞቀ ኑሯችሁን ትታችሁ ታግላችሁ ልታታግሉን በረሃዉ ድረስ መጥታችሁ ተቀላቅላችሁናል . . . እሴይ የኢትዮጵያ አምላክ! . . . ወያኔ የተሸነፈዉ ዛሬ ነዉ እየለ አርበኛዉ በሆታና በዕልልታ ከዉስጥ የመነጨ ደስታዉን ገልጸ። ብቻ ምን አለፋችሁ ጀግኖቹን ያሉበት ቦታ ድረስ ልናይ ሄደን የጀግና አቀባበል ተደረገልን። እንደ አንድ ታጋይ ድል አፋፍ ላይ ልድረስ አልድረስ አላዉቅም፤ ማሸነፋችንን ግን አረጋገጥኩ።

የነፍስ ወከፍ ጠመንጃዉን እንዳቀፈ ሰላም ሊለኝ ሲመጣ ትኩር ብዬ አየሁት። ወጣት ነዉ፤ ጽናቱና ቁርጠኝነቱ ፊቱ ላይ ይነበባል። በፈገግታ የታጀበዉ የዋህ ፊቱ ልጅነቱን በአዋጅ ይናገራል። ዕድሜዉ ከሃያ አይበልጥም። ተቃቅፈን ሰላም ስንባባል እጅብ እጅብ ብሎ የተጎነጎነ ፀጉሩን በእጄ እያሻሸሁ “እቺን ነገር ታበድረኛለህ” አልኩት ፀጉር እየከዳዉ ያስቸገረኝን እራሴን እያሳየሁት። ችግር የለም አለኝ። “ችግር የለም” በአርበኞቹ ሠፈር የተለመደ አባባል ነዉ። የበረሃዉ ንዳድ፤ የዉኃዉ ጥማት፤ የምግብ ችግር፤ ክብደት ተሸክሞ ተራራዉን ሽቅብ መዉጣትና ባጠቃላይ ወያኔንና ዘረኛ ስርዐቱን ማስወገድ ለአርበኛዉ ችግር አይደለም። አርበኛዉ ለእንደነዚሀ አይነት ችግሮች ተዘጋጅቶ ስለመጣ እንደችግር አይመለከታቸዉም።

ድንኳን ዉስጥ ገብተን ቁጭ እንዳልን . . . . እዚህ አካባቢ ችግራቸሁ ምንድነዉ አልኩት። ይምጡ አለኝና ከድንኳኑ ይዞኝ ወጥቶ ገዢ መሬት ይዘዉ የመሸጉትን የተለያዩ ካምፖች አሳየኝና የእያንዳንዳቸዉን ስም ነገረኝ። ሁላችንም የመጣነዉ ከኢትዮጵያ ነዉ፤ ሁላችንም የምንታገለዉ ወያኔን ነዉ፤ ደግሞም የሁላችንም ጥያቄ ፍትህ፤ ነጻነትት፤ እኩልነትና ዲሞክራሲ ነዉ. . . .. ግን አንድ ላይ አንታገልም። እስከመቼ ነዉ የአንድ አገር አርበኞች ከአገራችን ወጥተን፤ የተለያየ ድንኳን ተክለን፤ በተናጠል የጋራ ጠላታችንን የምንዋጋዉ? እባካችሁ ገላግሉን ብሎኝ ቀና ሲል አይኑ ካይኔ ገጠመ። በአፉ ከነገረኝ በአይኑ የነገረኝ በለጠብኝ። እንዲህ አይነቱን ብስለት የተሞላዉ ንግግር የሰማሁት ከልጄ ብዙም ከማይበልጥ ኢትዮጵያዊ ወጣት መሆኑ ሲሰማኝ እራሴን ታዘብኩት፤ ኢትዮጵያዊነቴን ግን ከወደድኩት በላይ ወደድኩት። አዎ አሁንም አሁንም አትዮጵያዊነቴን ከነችግሩ ወደድኩት። ደግሞስ ዬኔ ስራ ችግር መፍታት ነዉ እንጂ የአገሬ ችግር ፊቴ ላይ በተደቀነ ቁጥር ኢትዮጵያዊነቴን ጥያቄ ዉስጥ ማስገባት አይደለም።በነገራችን ላይ በተናጠል የሚደረገዉ ትግል አያዋጣምና “እባካችሁ አንድ አድርጉን” የሚለዉ ጥያቄ የአንድ አርበኛ ጥያቄ ሳይሆን በየሄድኩበት ካምፕ፤ ግምባርና ምሽግ ዉስጥ ከአብዛኛዉ አርበኛ አፍ የሚወጣ ጥያቄ ነዉ።

ቀኝ እጄን ወጣቱ አርበኛ ግራ ትከሻ ላይ አሳረፍኩና በሌባ ጣቴ በርቀት የሚታዩትን ካምፖች እያሳየሁት… አንዱጋ መሄድ እንችላለን አልኩት። አይ ጋሼ አሁን መሽቷል አለኝ። ሰዐቱ ገና ከቀኑ 9 ሰዐት ቢሆንም ሰፈሩ የአርበኞች ስለሆነ በነሱ ህግ መተዳደር አለብኝ ብዬ እሺ አልኩት። አይዞት እናንተ አስተባብራችሁ አንድ አድርጉን እንጂ ሌላ ሌላዉ ችግር የለዉም አለኝ። እኔም እንደ ወጣቱ አርበኛ በድፍረት “ችግር የለም” ለማለት ባልደፍርም . . . አይዞህ ትብብርን በተመለከተ በቅርብ ግዜ ሁላችንንም የሚያስደስት ዜና አብረን እንሰማለን አልኩት። ፈገግ አለና እሱን ከጨረሳችሁልን ሌላዉን ለኛ ተዉት አለኝና ይዞኝ ወደ ድንኳኑ ገባ።

ሐሙስ ነኃሴ 13 ቀን ጎህ ሳይቀድ ከእንቅልፌ ተነሳሁና ትንሽ ዞር ዞር ብዬ አልጋዬ ላይ ተመልሼ መጽሐፌን ማንበብ ጀመርኩ። ሁለት ምዕራፍ ጨርሼ ሦስተኛዉን ልጀምር ስል ከሩቁ ቡና ቡና ሸተተኝ። ቀና ብዬ ስመለከት ፍረወይኒ የቆላችዉን ቡና እስከነማንከሽከሻዉ ተሸክማ ልታስሸትተኝ ስትመጣ አየኋት፤ ከተቀመጥኩበት ተነስቼ ቁርስ ደረሰ እንዴ ብዬ ማንከሽከሺያዉ ላይ የሚንቦገቦገዉን ጭስ በእጄ ደጋግሜ ወደ አፍንጫዬ ሳብኩት። ‘ኡወ ቁርሲ ደሪሱ’ ብላ ፍረወይኒ የተቆላዉን ቡና ይዛ ወደ መጣችበት ተመለሰች።

ከጧቱ አንድ ሰዐት ከመሆኑ በፊት ቁርስ ተበልቶ አለቀና ሁላችንም ወደየተመደብንበት መኪና እንድንገባ ተነገረን። የሚጸዳዳዉ ተጸዳድቶ ሲጋራ የሚያጤሰዉም ሲጋራዉን ለምጦ ጉዞ ተጀመረ። ዬት እንደምንሄድ ወይም ለምን እንደምንሄድ የጠየቀም የተናገረም አልነበረም። . . . ዋ! ትንፍንሽ ብትሉ የተባለ ይመስል ሁሉም አፉን ዘግቶ ወደማያዉቀዉ ቦታ ጉዞዉን ቀጠለ። አንድ ሰዐት ያክል እንደተጓዝን . . . “እነዚያ ቤቶች ይታዩሃል” የሚል ድምጽ መኪናዉ ዉስጥ የሰፈነዉን የዝምታ ጽላሎት ሰበረዉ።አዎ ይታየኛል . . . ምን የምትባል ከተማ ናት ብዬ ቀና ስል ትልቅ ወንዝ አየሁ፤ ግን ወንዙንም ከተማዉንም ስለማላዉቃቸዉ ምንም አልተሰማኝም። እንድያዉም ፀሐይ ያጋለዉን ሰዉነቴን ለማቀዝቀዝ ወደ ወንዙ እንሂድ አልኳቸዉ። “ይቅርብህ እንደቀዘቀዝክ ትቀራለህ” አለኝ ከአጃቢያችን አንዱ።

ከተማዉ ኦምሀጀር፤ ወንዙ ተከዜ፤ ከወንዙ ባሻገር የሚታየዉ ከተማ ደግሞ ሁመራ መሆኑ ሲነገረኝ . . . የምን ወንዝ መዉረድ እዚያዉ ቀዝቅዤ ቀረሁ። አደራ ቦቅቧቃ እንዳትሉኝ . . . አልፈራሁም አልደነገጥኩም። በእርግጥ እንኳን እንደዚያ ቀርቤዉ ከሩቅ ከባህር ማዶም ጠልፎ ሊወስደኝ የሚፈልግ ሰላቢ የነገሰበትን ምድር ሳላዉቀዉ እንደዚያ በድንገት መቅረቤ ትንሽም ቢሆን አሳስቦኛል። ይልቅ እንደዚያ ያፈዘዘኝና ገና ወንዙ ዉስጥ ሳልገባ ያቀዘቀዘኝ እናት አገሬን ኢትዮጵያን በ25 አመት ለመጀመሪያ ግዜ ማየት መቻሌ ወይም የእናት ኢትዮጵያ ናፍቆት ነዉ። ለነገሩ አገርም ሰዉም የሚናፍቀዉ ርቀዉ ሲሄዱ ነዉ። ዬኔ ናፍቆት ግን ልዩ ጭራሽ ልዩ ነዉ። አጠገቧ ቆሜ አገሬ ናፈቀችኝ። አዎ! መግቢያዬ ቀረበ መሰለኝ ኢትዮጵያ ስቀርባት ይበልጥ ናፈቀችኝ።

በቃ አንሂድ አለ ይዞን የመጣዉ የበላይ መኮንን . . . አዎ እንሂድ እንጂ ከዚህ በላይ መቆየት ለወያኔ ካልሆነ ለሌላ ለማንም አይበጅም አሉ ሌላዉ በዕድሜ ጠና ያሉ የበላይ መኮንን። እኚህ ሰዉ የወያኔ ስም ሲነሳ ደማቸዉ ይፈላል ፤ እሳቸዉ እራሳቸዉ እንደ ዳዊት ሲደጋግሙት ግን ምንም አይሰማቸዉም። ከሰዐት በኋላ ረፋዱ ላይ ሁላችንም ወደየመኪናችን ገብተን ኦምሀጀርን ለቅቀን ወደ ጀግኖቹ አገር ወደ ሀሬና አቀናን። ሀሬና አርበኞች ግንቦት 7ን፤የጋምቤላ ህዝብ ነጻነት ንቅናቄን፤ የአማራ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄን፤ የቤንሻንጉል ህዝብ ነጻነት ድርጅትንና ደምህትን ወላድ ማህፀንዋ ዉስጥ አምቃ የያዘች እርጉዝ ምድር ናት። እርግጠኛ ነኝ በቅርቡ ትወልዳለች።

የአስመራ ምፅዋ መንገድ እንደ ጥምጥም እየተጠመጠመ እየቀናና እየጠመመ ለረጂም ሰዐት የሚዘልቅ ያዋቂንም የልጅንም ቀልብ የሚሰልብ ሰላቢ መንገድ ነዉ። እግዚኦ . . . የከረን መንገድ በስንት መልኩ! ከአስመራ ምፅዋ መሄድ ማለት ከ2500 ሜትር ተራራ ላይ ቁልቁል ወርዶ ባህር ወለል መድረስ ማለት ነዉ። ትንፋሼን ቋጥሬ በቀኜ ገደሉን በግራዬ ተራራዉን እያየሁ ለሰዐታት ቁልቁለቱን ከተያያዝኩት በኋላ የቋጠርኩትን ትንፋሽ አዉጥቼ እፎይ ማለት የጀመርኩት ማይ አጣል ስደርስ ነዉ። ከማይ አጣል በኋላ ምፅዋ ድረስ መንገዱ ሜዳ ነዉ።

ምፅዋ ልንደርስ ትንሽ ሲቀረን ሆዴን ባር ባር አለዉ። የደስታ ይሁን የሀዘን ወይም የሲቃ አላዉቅም ብቻ ልቤ ሌላ ሌላዉን ሰዉነቴን ትቶ ደረቴ ዉስጥ ብቻዉን ይዘላል። “ዉስጥ እጄን ይበላኛል” ምን ሊያሳየኝ ይሆን . . . ይል ነበር የልጅነት ጓደኛዬ። ምነዉ እኔም እንደሱ ሆኜ ዉስጥ እጄን በበላኝ . . . ልቤ ደረቴን ጥሶ የሚወጣ እሰኪመስል ድረስ ደረቴ ዉስጥ ከሚዘል። አይፎኔን አወጣሁና ግራና ቀኙን አይኔ ያረፈበትን ቦታ ሁሉ ፎቶ አነሳሁ። ቦታዉ ዶጋሌ ይባላል. . . አዎ! ዶጋሌ . . . ጀግናዉ ራስ አሉላ 500 የጣሊያን ወታደሮችን ዶጋ አመድ ያደረጉበት የድል ቦታ። ለካስ ልቤ አለምክንያት አልዘለለም! ጣሊያን ዋና ከተማ ሮም ዉስጥ የአምስት መቶዎቹ አደባባይ የሚባል ቦታ አለ (ፒያዛ ዴ ቺንኮ ቼንቶ)። እመኑኝ እኛም አገር አይቀርም! ባንዳ ባንዳዉንና ልክ ልኩ ሲነገረዉ ደንግጦ የሞተዉን ምናምንቴ ሁሉ ትተን ሞተዉ ህይወት የሆኑልንን የትናንትናና የዛሬ ጀግኖቻችንን እናስታዉሳለን።

ምፅዋ ሁለት ቀን ብቻ ነዉ ያደርኩት – ቅዳሜና እሁድን። በጦርነቱ የፈራረሱ ህንጻዎች አሁንም አልፎ አልፎ ይታያሉ፤ ያም ሆኖ ምፅዋ ዉብ ከተማ ናት፤ ደግሞም አያሌ አዳዲስ ህንጻዎች ተሰርተዉባታል። የቀድሞዉ የኢትዮጵያ ባህር ኃይል ጠ/መምሪያ የነበረዉ ማዕከል ግን በጦርነቱ እንደፈረሰ ነዉ፤ ያየዉም የነካዉም ያለ አይመስልም።

እሁድ ነኃሴ 16 ቀን ከምፅዋ ተነስተን 45 ደቂቃ ከነዳን በኋላ ዊሃ ደርስን። ዊሃ ሌላዉ የአርበኞች መንደር ነዉ። ዊሃ ያለዉ አርበኛ እንዴት እንደተቀበልን ለመግለጽ አማርኛ ቋንቋ እንደገና “ሀ” ብዬ መጀመር የሚኖርብኝ ይመስለኛል። በዚያ የወፍ ማረፊያ በሌለበትና በየሴኮንዱ ዉኃ ዉኃ በሚያሰኝበት ንዳድ ዉስጥ ወታደራዊ ሥልጠና መዉሰድ ቀርቶ አንድ ሜትር መራመድም እጅግ በጣም ይከብዳል። እንግዲህ ይታያችሁ የኛዎቹ ጀግኖች እንደዚህ የምድር ሲኦል በመሰለ ቦታ ነዉ ወገኖቻቸዉን ከወያኔ መንጋጋ ነፃ ለማዉጣት እልህ አስጨራሽ የሆነ ወታደራዊ ሥልጠና የሚወስዱት። እኔም የኢትዮጵያን ህዝብ ከወያኔ ዘረኞች ለማላቀቅ እንደወያኔ 17 አመት ጫካ ለጫካ መንፏቀቅ እንደሌለብን ቁልጭ ብሎ የታየኝ ዊሃ ሄጄ እነዚህን የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ስመለከት ነዉ።

ሰኞ ነኃሴ 17 ቀን በጧት ተነስተን ጉርጉሱም ሄድን። ጉርጉሱም ቀይ ባህር ዳርቻ ላይ የሚገኝ ቆንጆ የመዋኛ ቦታ ነዉ። ቁርስ አዝዘን ሳንጨርስ የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ መሪ አቶ ሞላ አስገዶም ከተፍ አለ። ታጋይ ሞላ በድንገት አልነበረም የመጣዉ፤ ልክ በቀጠሮዉ ሰዐት ነበር የደረሰዉ። አብሮን ቁርስ በላና እኛ ቀይ ባህር ዉስጥ ገብተን ስንምቦጫረቅ እሱ ማይ አጣል እንገናኝ ብሎ መኪናዉን አስነስቶ ከነፈ።

ከጥዋቱ 11፡30 ሲሆን ዋናችንን ጨርሰን የምፅዋ አስመራን መንገድ ተያያዝነዉ። ከምፅዋ አስመራ ጉዞ ማለት ሽቅብ ወደሰማይ የሚደረግ ጉዞ ማለት ነዉ፤ እንደኔ አይነቱ የዋህ ሰዉ ሰማዩን ደርሶ በእጁ የሚነካ ይመስለዋል ፤ ግን ሰማዩም ሞኝ አይደለም ደረስኩብህ ሲሉት ይሸሻል። ከቀኑ 12፡30 ሲሆን ማይ አጣል ደረስንና አስፋልቱን ትተን ወደ ደምህቶች ካምፕ የሚወስደዉን የኮረኮንች መንገድ ተያያዝነዉ። ወደ ካምፑ ስንደርስ ዊሃን፤ ሄሬናን፤ አምሀጀርንና ሌሎቹንም የአርበኞች ግንቦት 7 ካምፖች ስንጎበኝ ያየነዉ ፍጹም ኢትዮጵያዊ የሆነ የእንግዳ አቀባበል ተደረገልን። በነገራችን ላይ የደምህቶችን ካምፕ ስንጎበኝ ይህ የመጀመሪያችን አይደለም። ለእግራችን ዉኋ ቀረበልንና ነጠላ ጫማ ያደረገዉ ሁሉ እግሩን በቀዝቃዛ ዉኃ አራሰዉ። ቀዝቃዛ ዉኋ ለእግር ማቅረብ በሁሉም አርበኞች ካምፕና በበረሃዉ የኤርትራ ክፍል የተለመደ ባህል ነዉ። ከቀኑ እንድ ሰዐት ሲሆን ምሳ ቀርቦ እየተበላ ቡና ይፈላ ጀመር። ረከቦቱ፤ጀበናዉ፤ ማቶቱ፤ የከሰል ምድጃዉ፤ ፈንዲሻዉና የተደረደረዉ ስኒ በቀጥታ ወደ አደኩበት ሠፈሬ ፒያሳ ወሰደኝ። አዎ! ፒያሳ… የአዲስ አበባዉ ሳይሆን የአዋሳዉ ፒያሳ።

ቡናዉ እየተጠጣ ጨዋታዉ ሞቅ ሲል ቆየት ካሉት የጥላሁን ገሠሠ ሙዚቃዎች አንዱ ከሩቅ በለሆሳስ ተሰማኝ። በዉኔ ነዉ በህልሜ ብዬ ቀና ስል ነአምን ዘለቀ ጥላሁንን ከቴፑ ጋር አብሮ ይጫወታል። በህልሜ አለመሆኔን አወቅኩት። በሞት የተለዩን ድምጻዉያን የኛዎቹም የዉጮቹም ከላይ ከሰማይ ቢጫወቱልን እርገጠኛ ነኝ ጋላክሲዉንና ናሳ “Black Hole” እያለ የሚነግረንን ዬትየለሌ ክስተት አቋርጦ ከፀሐይ ብርሐን ቀድሞ እኛጋ የሚደርሰዉ ዘመን አይሽሬዉ የጥላሁን ገሠሠ ድምፅ ብቻ ነዉ። ይህንን ስሜት የሚኮረኩር፤ ጅማት የሚወጥርና አዕምሮን ሰብስቦ በትዝታ የሚያስዋኝ ዉብ ቃና ነበር ደምህቶች ሲያሰሙን የዋሉት። ብቻ ምን ልበላችሁ. . . ወበቅ የተቀላቀለዉ የምፅዋ ንዳድ ሳይቀር ለጥላሁን ገሠሠ ሙዚቃ ቦታዉን ለቀቀ። እኛም ወታደራዊ ትዕዛዝ የተሰጠን ይመስል የሁላችንም አፍ ተዘግቶ የሚንቀሳቀሰዉ እግራችን፤ ትከሻችንና ጭንቅላታችን ብቻ ሆነ።

“አልማዝን አይቼ እልማዝን ሳያት”፤ “እንጉዳዬ ነሺ” “አመልካች ጣት” “መሳቁን ያስቃል” . . . ብቻ ምን አለፋችሁ የጥላሁን ሙዚቃ ተዥጎደጎደ። ጥላሁን ገሠሠ አስመራ ላይ የሚጠብቀንን ቀጠሮ ብቻ ሳይሆን ጭራሽ እኛነታችንን አስረሳን። ቢበዛ አንድ ሰዐት ብለን የመጣን ሰዎች ከሦስት ሰዐት በላይ ከደምህት ጓዶቻችን ጋር ቆየን። በመጨረሻ የጉዟችን መሪ “አንድ ለመንገድ” ብሎ ከተቀመጠበት ተነሳ። እሱ ሲነሳ “እንክርዳድ እንክርዳድ የተንከረደደ፤ ስንዴ መስሎ ገብቶ ስንቱን አሳበደ” የሚለዉ ዘፈን እያለቀ ነበር። ነአምን. . . ነአምን ብዬ ስጣራ . . . “One for the road” ይቀረናልኮ አለ ነአምን . . . እንሂድ የምለዉ መስሎት። ይህንን ሙዚቃ እንደ እንክርዳድ ተቀላቅሎን ለሚያሳብደን የዳያስፖራ ቱልቱላ መርጫለሁ አልኩት። ሳቅ አለና ከቴፑ ጋር መጫወቱን ቀጠለ። እርግጠኛ ነኝ ተቦርነ በየነ ወይም መሳይ መኮንን አንድ ቀን “እንክርዳድ እንክርዳድን” በኢሳት ያሰሙናል። አይደል ተቦርነ?

በመጨረሻ የኛም መሄጃ የሙዚቃዉም መገባደጃ ደረሰ። “One for the road” የተባለለት ሙዚቃ (ዘፈን) ገና ሲጀምር ሰማሁና ኢችንማ አምላክ ነዉ የመረጠልን አልኩ በልቤ። ያ በቁሙ “አጥንቴም ይከስከስ” ብሎ ያስተባበረን ጥላሁን ገሠሠ አሁንም ከላይ ከሰማይ ቤት “ቃልሽ አይለወጥ እባክሺ….ን” እያለ ቃል እንድንገባባ አደረገን። ተራ በተራ ከአርበኛ ሞላ አስገዶም ጋር እየተቃቀፍን “ቃልሽ- አይለወጥ- አባክሽን” ብለን ተለያየን። ቃል የዕምነት ዕዳ ነዉ ብዬ ነበር የጀመርኳችሁ፤ አሁንም ቃሌ ይሄዉ ነዉ። ቃላችን አይለወጥ! ቸር ይግጠመን።

ኤፍሬም ነኝ ከአርበኞች መንደር

ebini23@yahoo.com

መልዕክት በድሆች ድህነት ለመክበር መሯሯጥ ላይ ላሉ የዲያስፓራ ማኅበረሰብ አባላት!!

arbegnoch-ginbot7-300x300

 

መልዕክት በድሆች ድህነት ለመክበር መሯሯጥ ላይ ላሉ የዲያስፓራ ማኅበረሰብ አባላት!!

የግል ኑሮን ለማደላደል ሲባል የወያኔ አባል መሆን “ወይን ለመኖር” የሚል ስያሜ ከተሰጠው ዓመታት ተቆጥሯል። “ወይን ለመኖር” ዜጎች ነፃነታቸውን ለጥቅም አሳልፈው የሚሸጡበት፤ የሰው ልጅ ክብር የሚዋረድበት ገበያ ነው።

በወይን ለመኖር “የገበያ ህግ” መሠረት እያንዳንዱ ዜጋ ሊያገኘው መብቱ የሆነውን አገልግሎት እንዲያገኝ የህወሓት፣ የብአዴን፣ የኦህዴግ፣ የደህዴግ፣ የአብዴፓ፣ የቤጉህዴፓ፣ የጋህአዴን፣ የሀብሊ ወይም የኢሶዴፓ አባል መሆን፤ አልያም መደገፍ ግዴታ ነው። እነዚህ ሁሉ ድርጅቶች የህወሓት ተቀጽላ ወያኔዎች ናቸው። የእነዚህ ድርጅቶች አባል ወይም ደጋፊ ያልሆነ እንኳስ የመንግሥት አገልግሎት ሊያገኝ ጥሮ ግሮ ያፈራውንም ይነጠቃል።
በዚህም ምክንያት፣ በገጠር ያለው አርሶ አደር ቁራጭ የእርሻ መሬት፣ የግብርና ባለሙያዎች የምክር እገዛ፣ የማዳበሪያና ዘር ግዢ፣ ብድር ወይም እርዳታ ለማግኘት በአካባቢው ባለ የወያኔ ድርጅት አባልነት መመዝገብ፤ አንድ ለአምስት መደራጀት እና የወያኔን የስልጣን እድሜ የሚያራዝሙ ነገሮችን መሥራት ይጠበቅበታል። በከተሞች ውስጥም ሥራ ለመቀጠር፣ ለደረጃ እድገት፣ የመኖሪያ ቤት (ኮንዶሚንየም) ለመግዛት ሲባል መወየን አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታ ሆኗል:: በንግዱም ዘርፍ የንግድ ፈቃድ፣ የሥራ ቦታ እና የባንክ ብድር ለማግኝት፣ የመንግሥት ጨረታዎችን ለማሸነፍ፣ ከጉምሩክ እቃ ለማስለቀቅ፣ የውጭ ምንዛሪ ለማግኘት መወየን ግዴታ ነው።
“ወይን ለመኖር” የኢትዮጵያን ሕዝብ ያዋረደ፤ ለትውልድ የሚተርፍ የማኅበራዊ ስነልቦና ኪሳራ ያደረሰ እና ደካማውን ወያኔን ጠንካራ በማስመሰል በሕዝብ የትግል መንፈስ ውስጥ ፍርሃትን የረጨ መሆኑ ግንዛቤ እየዳበረ በመጣ መጠን እየቀነሰ የመጣ ክስተት ነው። በአሁኑ ሰዓት ከቀድሞው እጅግ በተሻለ ኢትዮጵያ ውስጥ የምንገኝ ኢትዮጵያዊያን ራሳችንን ከህወሓት ባርነት እያላቀቅን ምሬታችንን በግልጽ መናገር የጀመርንበት ወቅት ነው፤ ከዚያም አልፎ የህቡዕ ተግባራዊ የትግል እንቅስቃዎችን ማድረግ ደረጃ ላይ ደርሰናል።

አገር ውስጥ እየተዋረደ የመጣው “ወይን ለመኖር” በአገዛዙ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አማካይነት በውጭ አገራት ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን (ዲያስፓራ) መካከል ነፃነታቸውን በጥቅም የሚለውጡ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያንን ፍለጋ ተሠማርቷል። አገዛዙ ተስፋ ያደረገው ያህል ባይሆንም ጥረቱ የተወሰነ ውጤት እያስገኘለት ነው። በጥቅማ ጥቅም እየደለለ ካመጣቸው ውስጥ በስርዓቱ ብልሹነት ያዘኑና የተሰማቸውን በግልጽ የተናገሩ መኖራቸው የሚያስደስትና የሚያበረታታ ቢሆንም ከመንደር ካድሬዎች ባነሰ ተለማማጮችና አጎብዳጆች በማየታችን ተሸማቀናል። ኢትዮጵያ ውስጥ ካለነው አብዛኛው ሕዝብ አንፃር ሲታይ በተሻለ የኑሮ ደረጃ ላይ ከሚገኙት ዲያስፓራዎች መካከልም ነፃነታቸውን በጥቅም ለመለወጥ የሚፈቅዱ መገኘታቸው አሳዛኝ ነው። እነዚህ ክብራቸውን በጥቅም የለወጡ ዲያስፓራዎች ዓለም ባንክንና የዓለም የገንዘብ ድርጅትን (IMF) ተክተው ህወሓት ስላስገኘው ፈጣን እድገት በአገዛዙ ራድዮ እና ቴሌቪዥን ሲነግሩን መስማት ያሳፍራል። የህወሓት አገዛዝ “ፍትህን፣ መልካም አስተዳርንና ዲሞክራሲን አስፍኗል፤ ይህንንም መጥተን በዓይኖቻችን ተመልክተናል” እያሉ የግፉን ገፈት እየቀመስን ላለነው ሲነግሩን መስማት ያማል።

እነዚህ ወገኖቻችን ህወሓትን በማሞካሸት የሚያገኙት መሬት ብዙ ድሆች የተፈናቀለቡት፤ ለእነሱ በብላሽ የተሰጠው ብድር በረሃብ ለሚጠቃ ወገን የተላከ እርዳታ መሆኑ ማሳሰብ ይገባል። ከህወሓትና አጫፋሪዎቹ ጋር ተስማምተው ባገኙት ገንዘብ የሚቆርሱት እያንዳንዱ እንጀራ የብዙ ወገኖቻችን ደምና እንባ የፈሰሰበት መሆኑ ማስገንዘብ ያሻል። ከህወሓት ጋር በማበር በወገኖቻችን ድህነትና ችጋር እየከበሩ ያሉ የዲያስፓራ ማኅበረሰብ አባላት ከዚህ እኩይ ሥራቸው እንዲታቀቡ ማስጠንቀቅ ይገባል። እኚህ ወገኖች የራሳቸው ክብር ማጉዳፋቸውን ብቻ ሳይሆን የልጅ ልጆቻቸውም የሚያፍሩባቸው መሆኑን ማስታወስ ይገባል። ከዚህም አልፎ የዛሬ ተግባራቸው ነገ በህግ የሚያስጠይቃቸው መሆኑን ሊያውቁ ይገባል።
አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ለግል ጥቅማቸው ሲሉ የአገዛዙን እድሜ በማራዘም ላይ የተሰማሩ፤ በድሆች ድህነት ለመክበር በመሯሯጥ ላይ ያሉ፤ ለግል ጥቅማቸው ሲሉ ለአገዛዙ ጥብቅና የቆሙ የዲያስፓራ አባላት ከዚህ ተግባራቸው እንዲታቀቡ ያሳስባል።
አርበኞች ግንቦት 7 “ከህወሓት ውድቀት በኋላ ያለው ጊዜ ለእናንተም ከዛሬው የተሻለ ይሆናል። ዛሬ ከህወሓት ጋር ያላችሁን ሽርክና አቋርጡ። ለነፃነት የሚደረገውን ትግል እርዱ፤ መርዳት ባትችሉ እንቅፋት አትሁኑ፤ አለበለዚያ ግን ከተጠያቂነት የማታመልጡ መሆኑን እወቁ” ይላል።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!

– See more at: http://satenaw.com/amharic/archives/9984#sthash.h6pcIhaq.dpuf

የፓርቲዎቹ ጉባኤዎች (ይገረም አለሙ)

ይገረም አለሙ

ሰሞኑን ህውኃትና የፈጠራው ድርጅቶች ጠቅላላ ጉባኤያቸውን አካሂደዋል፡፡ የህውኃት ጭንብል የሆነው ኢህአዴግ ጉባኤም ይቀጥላል፡ከእነዚህ ጉባኤዎች የሚጠበቅ አዲስ ነገር ባለመኖሩ መነጋገሩ አስፈላጊ አይመስለኝም፡፡ ስለሆነም እኔ በዚህች ጽሁፍ የማነሰው የሀገራችንን የዴሞክራሲ ተስፋ በማጨለሙ በታሪክ ሲጠቀስ ሊኖር የሚችለው ምርጫ 2007 ማግስት ስለተካሄዱ የአራት ተቀዋሚ ፓርቲዎች (በሀገር ውስጥና በውጪ) ጉባኤ ነው፡፡

ጠቅላላ ገባኤ የፓርቲ የመጨረሻው የሥልጣን አካል እንደመሆኑ ሲሰበሰብ ያለፈን ገምግሞ የወቅቱን ሁኔታ ፈትሾ ወዴትና አንዴት እንደሚኬድ አቅጣጫ አመላክቶ ውሳኔዎች እንዲያሳልፍ ይጠበቃል፡፡ ነገር ግን ከሁሉም ጉባኤዎች ፍጻሜ በኋላ ያነበብነውም ሆነ የሰማነው እንደስከዛሬው ሁሉ ጉባኤ አካሄድን ከሚለው የፕሮፐጋንዳ ፍጆታ የዘለለ ቁም ነገር አለመከናወኑን ነው፡፡ ጉባኤ በመተዳደሪያ ደንብ ላይ በይህን ያህል ግዜ ይካሄዳል ስለተባለ ብቻ የሚከናወን ከሆነ ለጉባኤው ማካሄጃ የሚወጣውን ገንዘብ ያህል እንኳን ቁም ነገር የሚሰራ አይሆንም፡፡ በመሆኑም የአራቱም ፓርቲዎች ጉባኤዎች መሬቱ የሚፈልገውን ትቶ አራሹ ያሻውን ዘራ ይሉ አይነት ስራ ነው የተሰራባቸው፡፡ እስቲ በትንሽ በትንሹ በተናጠል አንያቸው፡፡

የኢህፓ ጉባኤ ፤በዚህ ጉባኤ አንድ ታላቅ ቁም ነገር ተከናውኗል፤ተበታትነው ግን በአንድ ኢህአፓ ስም ይጠሩ የነበሩ ፓርቲዎችን ወደ አንድ በማምጣት ኢህአፓ አንድነት በሚል ስም ለመንቀሳቀስ የተደረሰበት ስምምነት በጎ ተግባር ነው፡፡ለመለያየት ምክንያት የሆኑ ነገሮች ተመርምረው ዳግም ያ መለያየት መቼምና በማንም እንዳይከሰት የሚያስችል መተማመን ተፈጥሮ የተፈጸመ ከሆነ ይህ ምስጢር አይደለምና ቢገለጽ የእንቧይ ካብ እየሆነ ለሚያስቸግረው ለፓርቲዎች እየተባበሩ መለያየት እየተገነቡ መፍረስ ትምህርት በሆነ ነበር፡፡

ጉባዔው የኢትዮጵያን አጠቃላይ ፖለቲካዊ፤ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ሁኔታዎችን በጥልቀት ከገመገመ በኋላበማለት የዘረዘራቸው 15 የሚደርሱ ጉዳዮች በሙሉ ወያኔ በኢትዮጵያውያን ላይ ያደረሳቸው በደሎች ናቸው፤ እነዚህ ከቃላት በላይ በቀን ከቀን ህይወታችን የምናያቸው በመሆናቸው አዲስ አይደሉም፡፡ ነገር ግን ኢህአፓ በአንድ ወቅት የትግሉ ግንባር ቀደም ተሰላፊ የነበረና የከተማውንም የጫካውንም ትግል የሞከረ ከአርባ አመት ለሚበልጥ ግዜም በሂደቱ ውስጥ ያለ እንደመሆኑ በተለይ ባለፉት ሀያ አራት አመታት ከወያኔ ጋር የተደረጉ ትግሎች መስዋእትነት እንጂ ውጤት ማስገኘት ያልቻሉበትን ምክንያት መርምሮ ችግሮችን ማሳየት መፍትሄውንም ማመላከት ከወያኔ አገዛዝ የመላቀቂያውን ስልትና መንገድም መጠቆም በቻለ ነበር፡፡ የወያኔን ድርጊትማ በተግባር እያየነው ነው፡፡

ጉባኤው ስለ ቀጣይ ሁኔታ ሲገልጽም ጉባዔው የወያኔ/ኢህአዴግ አገዛዝ ሀገር አፍራሽና አጥፊ ፖሊሲዎቹን በጥብቅ አውግዟል። ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን ለመመሥረት፣ የወያኔ/ኢህአዴግን አገዛዝ ማስወገድ እንደሚገባ አረጋግጦ የበለጠ ተጠናክሮ መታገል እንደሚገባ በድጋሚ አረጋግጧል። ይላል፡፡ ይህ ማንኛውም የወያኔ አገዛዝ የአንገሸገሸው ኢትዮጵያዊ የሚለው ነው፡፡ ከአንድ ያውም የረዥም ግዜ ልምድ ካለው ፓርቲ ጉባኤ መወጣት የነበረበት በሀያ አራት አመታት ትግል የወያኔን አገዛዝ ማስወገድ ያልተቻለው በእነዚህ ምክንያቶች ነው፤እነዚህን ችግሮች ለማስወገድ ይህን ይህን ማድረግ ያስፈልጋል፤ እንዲህ ካደረግን በዚህ ስልትና መንገድ መጓዝ ከቻልን ለድል እንበቃለን፤ይህን ለማድረግም ፓርቲያችን የሚችለውን ሁሉ ያደርጋል፣ወዘተ የሚል መሆን ነበረበት አልሆነም፡፡ በመሆኑም የተበታተኑትን ማሰባሰብ ችሎ ካልሆነ በስተቀር ከጉባኤው የሰማነው አንዳችም አዲስ ነገር ባለመኖሩ ተስፋ አልሰነቀብንም፡፡

ሸንጎ፣ ሸንጎው ከጉባኤው በኋላ ባወጣው መግለጫ ለመመስረት ምክንያት የሆነውን ጉዳይ ሲገልጽ …. ሸንጎ እንዲመሰረት ያስገደደው ዋና የፖለቲካ አደረጃጀትና የአመራር ክፍተት የተበታተነውና እርስ በእርሱ የሚጠላለፈው አገር ወዳድ ተቃዋሚ ኃይል ተባብሮ፤ ተመካክሮ፤ ተናቦ፤ ተደራጅቶ፤ ብቁነት ያለው አመራር መስርቶና የጋራ ሰነድ አዘጋጅቶ በተከታታይ ትውልድና ታሪክ ሊጠቀስ የሚችል አስተዋፆ ለማድረግ ሲችል ብቻ ነው የሚል እምነት ስላለው ነው። ብሏል፡፡ ነገር ግን ይህን ለመመስረቱ ምክንያት የሆነውን ጉዳይ ምን ያህል እንዳሳካ ፣ምን ተግዳሮት እንደገጠመው፣ በሂደት ከተገነዘበው ተነስቶ ምን መደረግ እንዳለበት አላሳየም፡፡

በስልጣን ላይ የሚገኘው የህወሓት/ኢህአደግ አገዛዝ ለዴሞክራሲ መስፈን፤ ለእርጋታ፤ ለሰላም፤ ለዘላቂና ፍትሃዊ እድገት እንቅፋት የሆነ ስርዓት በመሆኑ መወገድ እንዳለበት መቀበልና ያልተቆጠበ ጥረትና አስተዋፆ ማድረግ ናቸው። የሚልም በመግለጫው ወስጥ ተጽፎአል፡፡ የወያኔን ማንነትና ምንነት በመናገር ረገድ ችግርም ልዩነትም የለም፡፡መወገድ ያለበት በመሆኑም እንደዚሁ፡፡ እንዴትና በምን ሁናቴ የሚለውና በተለይም ከቃል ይልቅ ተግባር ላይ መገኘቱ ነው ችግሩ፡፡ ወያኔን የሚያል 17 አመት ገሎና ሞቶ በጠመንጃ ሥልጣን የያዘና ሀያ አራት አመታት በምርጫ እያጭበረበረ በጠምንጃ ሥልጣኑን አስከብሮ የኖረ ሀይል በጥረትና በአስተዋጽኦ ከቤተ መንግሥት ይወጣል ተብሎ አይታሰብም፡፡ ጥረት ሳይሆን ትግል፣ አስተዋጽኦ ሳይሆን መስዋዕትነት ይጠይቃል፡፡ በመሆኑም ነው በሸንጎ ጉባኤ መግለጫ ላይ የሰፈሩት ለለውጥ ሊታገል ከተደራጀ ወይንም የተደራጁ ኃይሎችን ካሰባሰበ ድርጅት ጉባኤ የወጡ ያልመሰሉት፡፡

የሸንጎ ጉባኤ ያለፉትን ትግሎች አደረጃጀት ስልትና ተግባራዊነት ገምግሞ ውጤት አልባ ያደረጋቸውን ምክንያት ተረድቶ መፍትሄ ማመላከት የትግል አይነትና ስልት መንደፍና የተግባር መንገድ ማሳየት ነበረበት፡፡

መድረክ፤ መድረክ በዚህ ስሙ ሁለት ምርጫዎች የተወዳደረ ለ99.6 እና ለመቶ በመቶ ውጤት ባለድርሻ እንደመሆኑ፤በተናጠልም አንዳንዶቹ በተቀዋሚነት የወያኔን የሥልጣን እድሜ ያህል የቆዩ እንደመሆናቸው በዚህ ወቅት የተጠራው ጉባኤ በሰማነው መልኩ የምናውቀውን የወያኔን ድርጊት ነግሮን የተለመደውን ውግዘት አሰምቶን መጠናቀቅ አልነበረበትም፡፡ ለመሆኑ መቼ ይሆን ራስን ማየት የምንደፍረው፡፡

ወያኔ መቶ በመቶ አሸነፍኩ ለማለት የበቃው አጭበርብሮ ቢሆን ተወዳድሮ ነው፡፡ ዋንኛ ተፎካካሪ እየተባለ ሲገለጽ የነበረው ደግሞ መድረክ ነውና ለተገኘው ውጤት ባለድርሻ ነው፡፡ ስለሆነም በጥቅሉ መድረክ በተናጠል አባል ድርጅቶች በምርጫው ወቅት የነበራቸው ድክመትና ጉድለት በጉባኤው በድፍረት መፈተሽ ነበረባቸው፡፡ የ2002 የ99.6 ሽንፈት ሳይፈተሸና ትምህርት ተወስዶ ዝግጅት ሳይደረግ በዘልማድ ጉዞ ምርጫ ለ2007 ተገባና የመቶ በመቶ ሽንፈት መጣ፡፡ አሁንም በተድበሰበሰ ሁኔታ በሰላማዊ ትግሉ እንቀጥላለን በማለት የሚያደርጉት ጉዞ ምንም ተስፋ የሚሰጥ አይደለም፡፡ ድክመት ሳይታወቅ እንዴት መሻሻል ይመጣል፡፡

መድረክ እንደ ስሙ ስራው የገነነ አለመሆኑን ባቀረባቸው እጩዎች ብዛት አይተናል፡፡የፓርላማውን ወንበር ግማሽ እንኳን የሚሆን ዕጩ ማቅረብ ያልቻለው ለምንድን ነው? በዚህ ቁጥርስ እናሸንፋለን የተባለው እንዴት ነው? ምርጫ ቦርድ ትክክለኛውን የመድረክ ዕጩዎች ብዛት ሳይናገር በደፈናው ከኢህአዴግ ቀጥሎ ዕጩዎችን ያቀረበ እያለ ሲያሞካሸው የነበረው ለማባበል ወይንስ ለማማለል፡?( መድረክ ያቀረባቸው የዕጩዎች ብዛት እንደዚህ የሚያስብል አልነበረምና) ኢህአዴግ ምርጫ ቦርድንና ጠመንጃውን ካልጣለ አይሸነፍም ከተባለና እንዳልጣለ ከታወቀ በምርጫ የመሳተፉ ፋይዳ ምንድን ነው? ጫናው አባላትን ከማሰር አልፎ ወደ መግደል ሲደርስ በምርጫው መቀጠል ነበረብን ውይ? ሰላማዊ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ለመባሉ የእኛ አጃቢነት አስተዋጽኦ አላደረገም ወይ?ወደ ፊት የምንቀጥለው እስካሁን በመጣንበት አኳኋንና መንገድ ነው ወይ? ወዘተ እነዚህና መሰል ጥያቄዎች የጉባኤው መነጋገሪያ ሊሆኑ በተገባ ነበር፡፡

ይህም ብቻ አይደለም በመድረክ ስም ተሰባስበው ያሉ ፖለቲከኞች በርግጥ ለለውጥ ከሆነ የሚታገሉት በዚህ መልክ የምንፈልገውን ለውት ማምጣት እንደማይችል ከመቼውም ግዜ በበለጠ ዛሬ ተረድተናል ስለሆነም በዚህ ጉባኤ ውህደት ፈጥረናል፡ በአንድነትና በጽናት ለለውጥ ለመታገል ቆርጠን ተነስተናል ብለው ማወጅ በቻሉ ነበር፡፡ ነገር ግን ከሀገራዊ ለውጥ በላይ የእነርሱ የፓርቲ መሪነት ያሳስባቸዋልና እስሚቀጥለው ጉባኤ ድረስ እንመክራለን ገና አንደራደራለን አሉ፡፡ አሳዛኝ፡፡ ሌላም ታዝበናል፡፡መድረክ ከምስረታው ጀምሮ ከተጣባው የቁጥር በሽታ ዛሬም አልተላቀቅም፡፡ በዚሁ ጉባኤ ዘገባ ላይ አንዴ የአምስት ፓርቲዎች ሌላ ግዜ የሰባት ፓርቲዎች ስብስብ ተብሎ ሲገለጽ ሰምተናል፡፡ ቁም ነገሩ ብዛቱ አይደለም ሆኖ መገኘቱ ነው፡፡መድረክ ግን የቁጥር ጨዋታ ይወዳል፡፡

ሰማያዊ፤ ይህኛው ፓርቲ ምርጫ ሲወዳደር የመጀመሪያው ነው፡፡ የምርጫ ቦርድ የግዜ ሰሌዳ ባወጣ ሰሞን ነጻነት ለፍትሀዊ ምርጫ የሚል ዘመቻ የጀመረው ሰማያዊ ወደ ምርጫ የገባው ነጻነት መኖሩን አረጋግጦ ነው ማለት አይቻልም፡፡ እናም ወደ ምርጫ የገባው አለምንም ዝግጅት በመሆኑ ምርጫ የገባበት ምክንያት ወዶ ይሁን ተገዶ ግልጽ አይደለም::

ሰማያዊ ያወዳደራቸው እጩዎች ከመቶ የዘለሉ አልነበሩም፡፡ (ትክክኛውን ቁጥር እነርሱም ም/ቦርድም አልተናገሩ) ከእነዚህም አብዛኛዎቹ አንድነት ሲፈርስ ወደ ሰማያዊ የሄዱ ናቸው፡፡ታዲያ በቂ ዝግጅት ሳይደረግ ምርጫ ውስጥ የተገባው ለምንድን ነው? የአንድነት አባላት ወደ ሰማያዊ መሄድ በፓርቲው በኩል የአቋም ለውጥ አስከትሏል ወይ ? ምርጫ ቦርድ ከመቶ በላይ ዕጩዎቻችንን አልመዘግብ አለን ፤ለቅስቀሳ የምንጽፈው ሳንሱር ይደረግብናል፤አባላቶቻችን ወከባ እየደረሰባቸው ፣እየታሰሩ ነው ወዘተ ከተባለ በዚህ አይነቱ ሂደት እስከመጨረሻው አጃቢ ሆኖ መዝለቅ ለምን አስፈለገ? ሰላማዊና ዴሞካራሲያዊ ምርጫ ለመባሉ የእኛ አስተዋጽኦ የለም ወይ? ወዘተ እነዚህና መሰል ጉዳዮችን አንስቶ የሰማያዊ ጉባኤ ሊመክርና ስለ ቀጣዩ የትግል ሂደት ምንነትና እንዴትነት ላይ ውሳኔ ሊያሳልፍ በተገባ ነበር፡፡የወጣቶች እየተባለ የሚነገርለት ፓርቲ በአስተሳሰብም ሆነ በአሰራር ከተለመደው መንገድ ያልወጣ መሆኑን በዚህ ጉባኤው አረጋገጠ፡፡ሳይድግ ያረጀ እንዳይሆንም ያሰጋል፡፡

ብዙ ከሚጠበቅበት ጉባኤ ከጉባኤው ጉልቶ የወጣው ዜና ኢ/ር ይልቃል በድጋሚ ተመረጡ የሚለው ነው፡፡ ይህ ደግሞ የሥልጣን ሽኩቻ ነበር እንዴ የሚል ጥያቄ ያስነሳል፡፡ፓርቲዎችን ሁሉ እግር ከወርች እያሰረ በዳዴ የሚያስኬዳቸው የሥልጣን ጉዳይ ነው፡፡ብዙ ምለው ተገዝተው ከወንበሩ ሲቀመጡ በአንዴ ይለወጡና አጠገቤ አትድረሱ ይላሉ፡፡

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ችግር አዲስ ፓርቲ በመመስረት ወይንም አዲስ ሰው ወደ መሪነት በማምጣት የሚፈታ አይደለም፡፡ወጣት ሽማግሌ ሳይል፣በፖለቲካው ውስጥ የኖረ ወይንም አዲስ የመጣ ብሎ ሳይለያይ ሁሉንም ያጠቃና ስር የሰደደ የአስተሳሰብ በሽታ አለ፡፡ስለሆነም መጀመሪያ የአስተሳሰብ ለውጥ ያስፈልገናል፡፡ራስን ሳይለውጡ ለውጥ ማምጣት አይቻልምና፡፡ ከአራቱም ጉባኤዎች አዲስ ነገር ማየት ያልቻልነውም በዚሁ በሽታ ምክንያት ነው፡፡

አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በአትሌቶች ላይ የሚሰራው በደል እየተሸፈነ ማለፍ ይቁም!!! (ከተማ ዋቅጅራ)

9973910113-large

 

በአትሌቶች ላይ የሚሰራው በደል እውነቱ ይወጣ ዘንድ ይገባል።

በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ውስጥ ያለው ችግር ቢዘረዘር ዘርፈ ብዙ ችግር እንዳለበት ይታወቃል። በቦታው ላይ የተቀመጡት ሰዎች እራሳቸው ችግር እስከሚመስሉ ድረስ በምስኪኑ አትሌቶች ላይ ከፍተኛ በደል ፈጻሚ እና ችግር አምጪ ናቸው። በአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ቢሮ ሰዎች  ያልተሰደበ፣ ያልተገፋ፣ ያልተንቋሸሸ፣ ያልተንገላታ፣ አትሌት የለም። አትሌቶቹ በዚህ ቢሮ ሰዎች ከሚደርስባቸው ያለአግባብ በደልና ግፍ ያላለቀሰ አትሌት አለ ብዬ ለመናገር ይከብደኛል። በዚህ ቢሮ  ውስጥ የሚሰሩ ሰዎች አትሌቶችን ለማገልገል ሳይሆን በደል ለመፈጸም የተቀመጡ ይመስለኛል። አትሌቶቹ በፌዴሬሽኑ ላይ በየግዜው ቅሬታቸውን ቢያቀርቡም ሰሚ ባለማግኘታቸው በደል ፈጻሚዎችም በስልጣን ላይ ስልጣን ሲሰጣቸው ሲመለከቱ አንገቱን ደፍቶ እየተሰደበ እና እየተናቀ የተሻለ ቀን ይመጣል እያሉ በደላቸውን በሆዳቸው ይዘው ተቀምጠዋል። የተወሰኑት አትሌቶች ዜግነት ቀይረው ሌላ አገር ወክለው መሮጥ የተጀመረውም ፌዴሬሽኑ በሚያደርስባቸው በደል ነው።

Ethiopian-Athletes-Association

ኃይሌ ገብረ ስላሴ የፌዴሬሽኑ ሰዎች የተሰጠው ዘለፋ <<አንተ አርጅተኸል ከእንግዲ ወዲያ ምንም አታመጣም>> ብለው ሲተቹት የማራቶንን ሪከር ሰብሮ  አሳፍሯቸዋል።

ቀነኒሳ በቀለ ታዋቂ ከመሆኑ በፊት ወደ ትራክ ትሬኒግ ለመስራት ሲመጣ እግሩ ወፍራም ስለነበረ የተሰጠው ዘለፋ<< ይሄንን እግር ይዘህ ልትሮጥ ነው የመጣኸው? አንተ እሯጭ አትሆንም ይልቅስ ሂድና አገርህ ገብተህ እርሻህን እረስ>> የሚል ነበረ።

ብርሃኔ አደሬ በአንድ ወቅት በፊት ከነበራት ብቃቷ ትቀንሳለች የተሰጣት ትችት ግን ልብ የሚያደማ ነው። <<ከአሁን በኋላ አንቺ መሮጥ አትችይም ሂጂና ኩበትሽን ጠፍጥፊ>> የሚል ነበረ። ብርሃኔ በጣም እልኽኛ ስለነበረች ብቃቷን መልሳ እስከ አለም ሻንፒዮና ድረስ ለመሳተፍ በቅታለች።

ፀጋዬ ከበደ የመጀመሪያውን የውጪ ጥሪ መቶለት ከፌዴሬሽኑ ወረቀት ሊያጽፍ ሲሄድ <<አንተ አጭር አሁን አንተ ማራቶን እሯጭ ነኝ ብለህ ነው የመጣኸው>> እያሉ ይቀልዱበት ነበረ  ፀጋዬ ግን እኔ ምንም የለኝም እባካችሁ እድሌን አታስመልጡብኝ እያለ ሲለምናቸው እነሱ ግን ይሳለቁበት ነበረ።

ተፈሪ የሚባል አንድ አትሌት ከክፍለ ሃገር መቶ ማራቶን ይወዳደራል ያደረገው ቁምጣ የእግር ኳስ ተጫዋች ቁምጣ ነው። በዚህ ውድድር ላይ ሰባተኛ ይወጣና ውድድሩን ይጨርሳል በኋላ ላይ ቁጥር ሊቀበል ሲሄድ አመናጭቀው አባረሩት በኋላለይም ፌዴሬሽን ሄዶ ሲያናግራቸው <<ሂድ አንተ ዝም ብለህ ከመንገድ መተህ ማራቶን እሯጭ ነኝ ትላለህ ሂድ ውጣ>> ብለው አመነጫጭቀውት ሲናገሩት ተፈሪ ግን አንድ ነገር ብሎአቸው ነበረ የወጣው ትሰማላችሁ አላቸው የሚቀጥለውን ማራቶን ውድድር ሳሸንፍ ምን እንደምትሉኝ አያለው ብሎ ይወጣል። በሌላ የማራቶን ውድድር ላይ በዛው ቁምጣ እሮጦ ሁለተኛ በመውጣት ውድድሩን ይጨርሳል ያላቸው ነገር ቢኖር ዛሬስ ቁጥሩን አትሰጡኝም ዛሬስ ከመንገድ ነው የመጣሁት ትሉኝ ይሆን? ብሎአቸው ብቃቱን አሳይቷል።

ከላይ እንደገለጽኩት እነዚህን ታላላቅ እና ብርቅዬ አትሌቶቻችንን ለምሳሌነት ጠቀስኳቸው እንጂ በፌደሬሽኑ  ሰዎች  በደል ያልደረሰበት እና ያላለቀሰ  አትሌት አለ ብዬ ለመናገር ይከብደኛል።

አንድ አትሌት በክለብ ታቅፎ መስራት ከጀመረ በክለቡ ውስጥ ጥሩ ተፎካካሪ ከሆነ ኢንተርናሽናል ውድድር እንዳይወዳደር የሚከለክለው ህግ እስከሌለ ድረስ የውጪ ውድድሮችን የመጋበዝ እድሉን ካገኘ ፌዴሬሽኑ አትሌቱ በፌዴርሽኑ ስር ታቅፈው ከሚሰሩት ክለብ ውስጥ መሆኑን ጠቅሶ በሚጻፍ ፋንታ ወረቀት በመከልከል የአትሌቶቻችንን እድገት እየቀጩት ይገኛሉ። አትሌቶቹም እራሳቸውን ችለው ለአገርም እንዳይጠቅሙ አድርጎ በማምከን አዳዲስ አትሌቶች እንዳይወጡ እያደረገ ነው። አዲስ አትሌት ከማየት ይልቅ በኛ አገር የተለመደው ሁለት ወይም ሶስት አትሌቶች ላይ ትኩረት በማድረግ የአትሌቲክስ አገር የነበረችውን አገራችንን ምንጩን  እያደረቁት ይገኛሉ። ለዚህም ደግሞ ትክክለኛው መፍትሄው በአትሌቶቹ ላይ  በደል  በመስራት ያሉትን ወንጀለኞች በህግ ተጠይቀው መጪው ፌዴሬሽኑን የሚረከበው አካል በንጹ አዕምሮ  እና ተጠያቂነት ባለው ስራ እንዲሰራ ማድረግ ሲቻል ሊጠፋ የተቃረበው አትሌታችንን ማዳን ይቻላል።

በዚህ አጋጣሚ አንድ ነገር ጠቆም አድርጌ ልለፍ

በፌዴሬሽኑ ህጋዊ እውቅና ተሰጥቶአቸው አትሌቶችን በመመልመል በማናጀር ስር በማቀፍ የሚያሰሩ ግለሰቦች አሉ። እነዚህ ግለሰቦች ከፌዴሬሽን ሶዎች ጋር ጥብቅ ሚስጢራዊ ስራ  አላቸው ያም ህገ ወጥ አሰራር ነው ። ለዛሬ በዚህ ጉዳይ ላይ ጥቂት ልበል ወደፊት ግን በሰፊው እመለስበታለው።

በፌዴሬሽኑ በኩል እና  በፌዴሬሽኑ እውቅና በተሰጣቸው እንዚህ ማናጀሮች ተብለው ሚጠሩት እየተሰራ ያለው ስራ አሳፋሪ እና መንግስትም ሆነ ህብረተሰቡ በአትክሮት ሊያየው የሚገባ ጉዳይ ነው። በፌዴሬሽኑ ወይም በማናጀሮች በኩል ወደተለያዩ  አገራት ውድድር ለማድረግ በስራቸው የሚሰለጥኑትን አትሌቶች ይልካሉ። ይሄ የሚደገፍ እና የሚያበረታታ ጥሩ ስራ ነው ወደ ውጪ ወጥቶ  ለመወዳደር ጥሩ አጋጣሚ ነውና። ችግሩ ያለው በአትሌቶች ስም የሚደረገው ወንጀል ነው። ፌዴሬሽኑ ወይም ማናጀሮች ከተለያየ አገራት ለአትሌቶች የውድድር ግብዛ ጥሪ ማስመጣት ይችላሉ በዚህ መሃል ለምሳሌ አምስት አገር በአንድ ወር ውስጥ ቢያስመጡ ለዚህ ውድድር የሚሆኑ እሯጮች አንድ አገር ላይ አራት ሰው ቢልኩ ለአምስቱ አገር ሃያ እሯጮችን መላክ ይችላሉ። ለሁሉም አትሌቶች እኩል የሆነ አገልግሎት በመስጠት የውጪ የመወዳደር እድላቸው የተዘጋ ባይሆን ከበቂ በላይ አትሌቶችን ማፍራት እንደሚቻል ይታወቃል። ነገር ግን በጠበበው የውጪ እድል ላይ በአትሌቶች ስም ፌዴሬሽኑ እና ማናጀሮች የሚሰሩት ቢዝነስ ከአምስት አገር ሊልኳቸው ከታሰቡት ሃያ አትሌቶች መካከል ከግማሽ የሚበልጠው እሯጭ ያልሆኑ ሰዎች ዳጎስ ያለ ገንዘብ ከፍለው የሚሄዱ አልያም የፌዴሬሽኑ ወይም የማናጄሩ ዘመድ የሆኑት በህገ ወጥ መንገድ  በአትሌቶቹ ስም የሚሰራ ወንጀል ነው። አትሌቶቹ ሲመለሱ እነዛ ግን በዛው የሚቀሩ ናቸው። እውነተኛው እና ደሃው አትሌት ጥሪ አስመጥቶ  አልያም ጥሪ የሚያስመጣለት አጥቶ በፌዴሬሽን ቢሮ በራፍ ላይ እና ማናጀሮቹ ላይ ሲያለቅሱ የሚያጥላላ ስድብ ከመስደብ በተጨማሪ በስፖርቱ ተስፋ እንዲቆርጡ የሚያደርግ ድርጊትን ሲያደርጉ እስከዛሬ ድረስ ዝም መባላቸው ኢትዮጵያውስጥ ህግ እንደሌለ የሚያሳይ ጉዳይ ነው። አትሌቶቹ ላይ የሚደርሰውን በደል ለማወቅ የሚፈልግ ማንኘውም አካል ከጀማሪው አትሌት እስከ ታዋቂዎች አትሌቶችን ጠይቆ እውነቱን መረዳት ይቻላል።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ከሞሞቱ በፊት ፌዴሬሽን ያሉት ኮሚቴዎችን በአትሌቶቹ ላይ ለሚሰሩት ስህተት ተጠይቀው አትሌቲክሱን የሚያሳድጉ በቦታው ሊይዙት ይገባል እላለው።

ከተማ ዋቅጂራ

Email- waqjirak@yahoo.com

– See more at: http://satenaw.com/amharic/archives/9975#sthash.CTXIG1uc.dpuf

ኢትዮጵያውያን ጦማርያን በዝንጀሮ ችሎት

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

የወያኔ ኢፍትሐዊነት በዝንጀሮው ፍርድ ቤት፣

ባለፈው ሳምንት በጥቅል ስማቸው “የዞን 9 ጦማሪያን” (ከዋና መዲናይቱ እምብርት በስተደቡብ ምስራቅ አቅጣጫ በጥቂት ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ ከሚገኛው እና ንጹሀን ዜጎችን በማሰቃየት በአስከፊነቱ ከሚታወቀው ከአምባገነኑ የመለስ ዜናዊ የማጎሪያ እስር ቤት 8ኛ ህንጻ/Block ቀጥሎ የተገነባው ህንጻ) እየተባሉ የሚጠሩት ወጣት ኢትዮጵያውያን ጦማሪያን እ.ኤ.አ ሚያዝያ 2014 በቁጥጥር ስር ከዋሉበት ጊዜ ጀምሮ 33 ጊዜ እራሱን ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) እያለ ለሚጠራው ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ስርዓት የዝንጀሮው ፍርድ ቤት ችሎት ቀርበው ነበር፡፡Ethiopian Bloggers in Kangaroo (Monkey) court

(ፖሊስ በጥርጣሬ የሚታይን ሰው በቁጥጥር ስር በማዋል እና በወንጀል የተጠረጠረን ሰው በእስር ቤት ካሰረ በኋላ ተጠርጣሪው ፈጽሟቸዋል ለተባሉት የውንጀላ ጥፋቶች መረጃዎችን ለመፈለግ እና ለማሰባሰብ በሚል ከሕግ አግባብ ውጭ ለሆነ ድርጊት ለወራት ከዚያም አልፎ ለዓመታት በእስር ቤት በማማቀቅ የሚያቆይ ሀገር አለ ከተባለ ብቸኛይቱ ሀገር ኢትዮጵያ ናት!)

የዘገዬ ፍርድ እንደተነፈገ ይቆጠራል፡፡ 33 ጊዜ የተንዛዛ የችሎት የጊዜ ቀጠሮ በመስጠት የዘገዬ ፍርድ 33 ጊዜፍትሕ እንደተነፈገ ይቆጠራል፡፡

ወጣት ጦማሪያኑ ለፍትህ አካል ከመቅረባቸው በፊት ለበርካታ ጊዚያት በእስር ቤት ታጉረው እየማቀቁ፣ ዋስትና ተከልክለው፣ ውጤታማ የሆነ የሕግ የምክር አገልግሎት እንዳያገኙ ተነፍገው፣ ፈጣን የሆነ የፍትሕ አገልግሎት ማግኘት አለመቻላቸው፣ ከአድልኦ የጸዳ እውነት አፈላላጊ አካል አለመመደብ እና ለ33 ጊዜ የተንዛዛ የችሎት የጊዜ ቀጠሮ መስጠት በፍትሕ አካል ላይ እንደመቀለድ እና እንደተነፈገ ፍትሕ ይቆጠራል፡፡

ባለፈው ሐምሌ 2015 ባራክ ኦባማ ኢትዮጵያን እንደሚጎበኝ በመገመት የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ሁለት ጦማሪያንን እና ሶስት ጋዜጠኞችን ከማጎሪያው እስር ቤት ባልተሰበ እና ባልተጠበቀ ሁኔታ ለቋቸዋል፡፡ ለማድለብ እንደተዘጋጀ ሰንጋ ሲፈልግ የሚያስር ሲፈልግ የሚፈታ እንደዚህ ያለ አምባገነን ስርዓት በኢትዮጵያ ካልሆነ ሌላ በየትኛው ሀገር ይገኛል!

እ.ኤ.አ ከ2006 ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ስለወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ስርዓት የዝንጀሮ ፍርድ ቤት ትችቶችን ስጽፍ እና ሳቀርብ ቆይቻለሁ፡፡

“የዘበት ፖሊሶች፣ አቃቤ ሕጎች እና ዳኞች ሚና በፖሊስ መንግስት” በሚል ርዕስ እ.ኤ.አ ታህሳስ 2006 የመጀመሪያውን ትችቴን አቅርቤ ነበር፡፡ ያ ትችት እ.ኤ.አ የ2005 ሀገር አቀፍ ምርጫን ተከትሎ ተከስቶ በነበረው ሁከት ሳቢያ በአሁኑ ጊዜ በህይወት በሌለው በአምባገነኑ በመለስ ዜናዊ ትዕዛዝ በቃሊቲ የማጎሪያ እስር ቤት ታስረው በነበሩት “የቃላቲ ተከላካዮች” (የተቃዋሚ የፖለቲካ መሪዎች) ላይ እየተካሄደ ባለው የችሎት ሂደት ላይ ምርመራ የሚያደርግ ነበር፡፡

እ.ኤ.አ ታህሳስ 2007 “የጦጣ የፍትሕ ችሎት በዝንጀሮው ፍርድ ቤት“ በሚል ርዕስ በዚያን ጊዜ የአክሽን ኤይድ ዓለም አቀፍ በኢትዮጵያ ማኔጀር/Manager of Action Aid International in Ethiopia በነበሩትና በአሁኑ ጊዜ ደግሞ በሂዩማን ራይትስ ዎች የአፍሪካ ዴስክ ዋና ክፍል ኃላፊ /Executive Director of the African Division of Human Rights Watch ሆነው ባማገልገል ላይ ባሉት በአቶ ዳንኤል በቀለ እና የማሕበራዊ ፍትሕ በኢትዮጵያ ድርጅት/Organization for Social Justice in Ethiopia መሰራች እና አመራር ሰጭ በነበሩት በአቶ ነጻነት ደምሴ ላይ ላይ ተመስርቶ የነበረውን የፍትሕ ሂደት የሚመረምር ትችት አቅርቤ ነበር፡፡ የእነርሱን የፍትሕ ሂደት የፍራንዝ ካፍካን የፍርድ ሂደት ከሚዘግበው የጆሴፍ ኬ.ን አስቀያሚ እና ተስፋ አስቆራጭ ልብወለድ የፍትሕ ታሪክ ጋር በማነጻጸር አቅርቤ ነበር፡፡

ለበርካታ ዓመታት ስለወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የተሰበጣጠረ መንግስት እና በአብዛኛው ግን በውጭ የገንዘብ ድጋፍ እርዳታ ላይ ተንጠልጥሎ ስለሚገኘው አምባገነን ስርዓት እንዲሁም ስለዝንጀሮው የፍርድ ስርዓቱ ብዙ ትችቶችን ስጽፍ ቆይቻለሁ፡፡

እ.ኤ.አ ሰኔ 2014 “የኢትዮጵያን ጦማሪያን ማን ይፈራቸዋል?“ በሚል ርዕስ በዞን 9 ጦማሪያን ላይ እየተፈጸመ ያለውን የሕግ ሸፍጥ የሚያጋልጥ ትችት አቅርቤ ነበር፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብን የይስሙላ ኢፍትሐዊ ስርዓት ለመግለጽ ከተንኮል በመነጫ ሳይሆን ከገለጻትክክለኛነት ፍላጎት አንጻር የዝንጀሮ እና የጦጣ ፍርድ ቤት የሚሉ ተመሳስሎዎችን እጠቀማለሁ፡፡

“የዝንጀሮ (ካንጋሮ ) ፍርድ ቤት” የሚለው ሀረግ የአውስትራሊያ አጥቢ እንስሳት ከሆኑት ማርሱፒያል ካንጋሮዎች ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የለውም፡፡

ይህ ሀረግ በ19ኛው ክፍለ ዘመን በምዕራብ አሜሪካ እራሳቸውን የሾሙ የሸፍጥ፣ ሀፍረተቢስ እና አታላይ የፍትሕ ሂደትን ያራምዱ የነበሩ ሰዎችን ለመግለጽ በስራ ላይ የዋለ ነው እየተባለ ይነገርለታል፡፡

ይህ ሀረግ አብዛኛውን ጊዜ ከሚከተሉት ጋር አንድ ዓይነት ትርጉም እንዳለው ሆኖ ሲገለጽ ቆይቷል፣

1ኛ) የሕግ እና የፍትሕ መርሆዎች ወደ ጎን የተጣሉበት ወይም ደግሞ የተዛቡበት አስመሳይ የፍርድ ችሎት፣

2ኛ) ዓይን ባወጣ መልኩ እና ሆን ብሎ ታስቦበት ዕውቅና ያላቸውን የሕግ ወይም ደግሞ የፍትህ መርሆዎችን እና መስፈርቶችን ወደ ጎን ገሸሽ አድርጎ መተው፣

3ኛ) የፍርድ ቤቱን ሕጋዊ ወይም ደግሞ የስነምግባር ግዴታዎችን ሆን ብሎ ወደ ጎን የሚተው ሕጋዊ የፍትሕ ስልጣን ያለው ፍርድ ቤት፣ እና

4ኛ) የፍርድ ውሳኔው በእርግጠኝነት የፍርድ ችሎቱ ሂደት ከመጀመሩ በፊት የተወሰነ እና የታወቀ ቢሆንም እንኳ “የፍርድ ሂደቱ ለሕዝብ ፍትሐዊ እና ትክክለኛ ቅርጽ ያለው እንዲመስል” እየተነበዬ የሚሰራ ፍርድ ቤት የሚሉት ናቸው፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የፍርድ ሂደት ስርዓት ከዚህ በላይ ከተገለጹት ሁሉም ትርጉሞች ጋር መሳለመሳ ነው፡፡

ይህ ሀረግ በዩናይትድ ስቴትስ የሕግ ታሪክ ውስጥ በጣም ጠቃሚ እንደምታ ካላቸው የወንጀል የሕገ መንግስት ጉዳዮች መካከል የእራሱን መንገድ አግኝቷል፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት “ፖሊሶች ጉዳዮችን በእራሳቸው እጆች የሚይዙበትን ሁኔታ፣ የጥቃት ሰለባዎችን የሚይዙበትን መንገድ፣ የጥቃት ሰለባዎች በግድ የእምነት ቃል እስኪሰጡ ድረስ የሚደበድቡበትን እና በኃይል የሚመቱበትን ጥንታዊ የሆኑ የሕግ ጉዳዮች አወገዘ፡፡ ክስ የቀረበበት ማንኛውም ሰው ጉዳዩ በይስሙላ የዝንጀሮ ፍርድ ቤት ሳይሆን ሕጋዊ በሆነ የፍትህ አካል የመታየት እና የመዳኘት መብት አለው፡፡”

እንግዲህ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የይስሙላ የዝንጀሮ ፍርድ ቤቶች ዋና መለያ ባህሪ ይኸው ነው፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ወሮበላ ዘራፊ ፖሊሶች በፖለቲካ ወንጀል የሚጠረጥሯቸውን ንጹሀን ዜጎች በፖለቲካ ኃላፊ ጌቶቻቸው ትዕዛዝ መሰረት በቁጥጥር ስር ያውላሉ፣ ጭካኔ በተመላበት ሁኔታ ድብደባ በመፈጸም በግድ የእምነት ቃል እንዲሰጡ ያደርጋሉ፣ ክስ ሳይመሰረት በእስር ቤት ታጉረው እንዲቆዩ ያደርጋሉ፣ የሕግ የምክር አገልግሎት እንዳያገኙ ያደርጋሉ፣ እንዲሁም በወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የሚሾሙ ሸፍጠኞች የይስሙላ የፍርድ ሂደቱን እስከሚጀምሩ ድረስ እስረኞችን ከወዲያ ወዲህ እያመላለሱ ያሰቃያሉ፣ ፈጣን የሆነ የፍትሕ አገልግሎት እንዳያገኙ ያደርጋሉ፣ አይጦችና ቅማል ቱሃን ሌላም ተውሳክ  በሚተራመሱበት እና ጽዳቱ ባልተጠበቀ ክፍል (በረት ማለቱ ይቀላላ) ውስጥ ለወራት ወይም ደግሞ ለዓመታት በእስራት እንዲማቅቁ ያደርጋሉ፡፡ ይህ ሁሉ ህግን ያልተከተለ ድርጊት የሚፈጸመው ሸፍጠኛ የሆኑ እና ለርካሽ ጥቅም ሲሉ ለስርዓት ያጎበደዱ ዳኞች አቃብያነ ሕግ ተብዬዎች የቆሸሸ የስብዕና ድሪቶ መንፈሳቸውን በመጠቀም በንጹህን ተጠርጣሪዎች ላይ የሀሰት ማስረጃዎችን ፈብርከው እስከሚያጠናቅቁ ድረስ መጨረሻ የሌለው የጊዜ ቀጠሮ እየሰጡ እጅ እና ጓንት ሆነው ፍትህን በመደፍጠጥ በንጹሀን ዜጎች ላይ ደባን እና ሸፍጥን ስለሚሰሩ ነው፡፡

በወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ፕላኔት (ዓለም) ላይ የይስሙላ የዝንጀሮ/የጦጣ ፍርድ ቤቶች ይኖራሉ፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ኢፍትሐዊ ስርዓት የዝንጀሮ/የካንጋሩ ችሎት በማለት ለትዮጵያውያን አንባቢዎቼ ተመሳስሏቸውን ለመግለጽ እጠቀማለሁ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የዝንጀሮ የፍርድ ስርዓት የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራሮች እና አባላት ተቀናቃኞቻቸውን ለማጥቂያነት የሚጠቀሙባቸው መሳሪያዎቻቸው መሆናቸውን ላሰምርበት እፈልጋለሁ፡፡

በዞን 9 ጦማሪያን የፍርድ ሂደት ላይ እንደዚህ ያለ የማስመሰል የፍትሕ ሸፍጥ እየተካሄደ በመሆኑ ምክንያት ነው በአሁኑ ጊዜ ዋና ዋና የሆኑት ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች እኩይ ድርጊቱን በማውገዝ ላይ የሚገኙት፡፡

በእርግጥ ከፖለቲካ እና ትክክለኛ ከመሆን አንጻር ማናቸውም ቢሆኑ ስርዓቱን የበቀል መወጫ መሳሪያ የዝንጀሮ ፍርድ ቤት ወይም ደግሞ የጦጣ ፍርድ ቤት ብለው ለመጥራት ድፍረቱ የላቸውም፡፡

ሆኖም ግን የዘንጀሮ/የጦጣ ፍርድ ቤት በየትኛውም በሌላ ስያሜ ቢሰየምም ያው የዝንጀሮ/ጦጣ ፍርድ ቤት ከመሆን የሚለየው ነገር በፍጹም የለም፡፡ በሌላ አባባል ለመቆንጀት ሲባል ፉንጋዋ ዓሳማ የከንፈር ቀለም ብትቀባም እንኳ በዕለቱ መጨረሻ የከንፈር ቀለሙ ያው ፉንጋ ዓሳማነቷን አይቀይረውም፡፡

ሂዩማን ራይትስ ዎች የተባለው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የዝንጀሮ/የጦጣን ፍርድ ቤት ስርዓት የፖለቲካ ተቀናቃኞቹን ለማጥቃት የሚጠቀምበት መሳሪያ ነው በማለት ገልጾታል፡፡ ሂዩማን ራይትስ ዎች የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ላይ እንዲህ በማለት ተቃውሞውን አቅርቦበታል፣ “ጋዜጠኝነት ወንጀል አይደለም፡፡“

የጋዜጠኞች ተከላካይ ኮሚቴ (ጋተኮ) ሽብርተኝነትን ከጋዜጠኝነት ጋራ በማቀላቀል በመንግስት እየተደረገ ያለውን ሰላማዊ ዜጎችን የማሰቃየት የፍርድ ሂደቱን አውግዟል፡፡

ፍሪደም ሀውስ/Freedom House የተባለው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት በጦማሪያን ላይ የተመሰረተው የክስ ጉዳይ በእውነታ ላይ ያልተመሰረተ ቅንነት የጎደለው ነው፣ መንግስት የግንቦቱ ምርጫ እየተቃረበ በሚመጣበት ወቅት በዴሞክራሲ ወትዋቾ ላይ ፖለቲካዊ እንደምታ ያለው የሀሰት ክስን በመፈብረክ ጥቃት በመሰንዘር ላይ ይገኛል፡፡ ስለሆነም ይህንን ኢፍትሐዊ የሆነ ድርጊት ለማስቆም ለጋሽ ድርጅቶች በመንግስት ላይ ጫና በመፍጠር ድርጊቱን ማስቆም ይኖርባቸዋል ብሎ ነበር፡፡

እ.ኤ.አ ጥር 2015 የአሜሪካ መንግስት መምሪያ በ6 ጦማሪያን እና በ3 ጋዜጠኞች ላይ በወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የተሰጠው የፍርድ ውሳኔ ላይ የጸረ ሽብር አዋጁ እየተተገበረ መሆኑ አሳስቦኛል በማለት ስጋቱን ገልጾ ነበር፡፡

መምሪያው እንዲህ በማለት አውጆ ነበር፣ ውሳኔው ነጻ እና ለሁሉም ክፍት የሆነ የሜዲያ ከባቢ አየር እንዳይሰፍንየሚያደርግ፣ .. ግንቦት 2015 በኢትዮጵያ ታማዕኒነት ያለው እና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ እንዳይካሄድያደርጋል፡፡

እ.ኤ.አ ሰኔ 2015 የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በግንቦት የተካሄደውን ሀገር አቀፍ ምርጫ መቶ በመቶ አሸንፊያለሁ በማለት አወጀ፡፡

እ.ኤ.አ ሀምሌ 2015 ባራክ ኦባማ ኢትዮጵያ ከደረሰ በኋላ “በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠው የኢትዮጵያ መንግስት“ በማለት ስምምነቱን ገልጿል፡፡ (ኦባማ ይህንን ነገር የተናገረ የአታላይነቱን ጉብዝና ለማሳየት ፈልጎ ነውን?)

በወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ፕላኔት ውስጥ የመጦመር ወንጀለኝነት፣

በወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የዝንጀሮ/ጦጣ ፍርድ ቤት የሸፍጥ ክስ የተመሰረተባቸው ተከላካይ ጦማሪያን የሚከተሉትን ያካትታል፡ በፈቃዱ ኃይሉ ተጫኔ፣ ናትናኤል ፈለቀ አበራ፣ ማህሌት ፋንታሁን ተፈራ፣ አጥናፍ ብርሀኔ አያሌው፣ ዘላለም ክብረት ቤዛ፣ አቤል ዋቤላ ሱጌቦ፣ አስማማው ኃይለጊዮርጊስ ግዛው፣ ኤዶም ካሳዬ ገላን፣ ተስፋለም ወልደዬስ አራጌ እና (በሌለበት የሸፍጥ ክስ የተመሰረተበት ሶሊያና ሽመልስ ገብረማርያም) ናቸው፡፡

ተከላካይ ጦማሪዎች በኢትዮጵያ የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ እና በወያኔ ጸረ ሽብር ሕጉ አዋጅ ቁጥር 652/2009 በሁለት ክሶች በአንድ ላይ ከስ ተመስርቶባቸዋል፡፡

በአንደኛው ክስ “ዋና ወንጀለኞች” ወይም ደግሞ በወንጀለኛ ሕጉ አንቀጽ 32 በተራ ቁጥር 1 እና 2 ላይ የተጠቀሰውን በመተላለፍ ዋና ወንጀል የመፈጸም ሙከራ የሚል ክስ ተመስርቶባቸዋል፡፡

በሁለተኛው ክስ ላይ ደግሞ ተከላካዮቹ በወንወጀለኛ መቅጫ ሕጉ በአንቀጽ 27 በተራ ቁጥር (1 እና 2) የተጠቀሱትን በመተላለፍ (ወንጀል የመፈጸም ሙከራ)፣ በአንቀጽ 38 በተራ ቁጥር (1) በሕገ መንግስቱ ወይም ደግሞ በመንግስት ላይ የተፈጸሙ ወንጀሎች የሚሉ ክሶች ተመስርተውባቸዋል፡፡

የውንጀላ ክሶቹ እንደማስረጃ ሊሆኑ የሚችሉ በርካታ ገጾች ያሏቸውን የእምነት መግለጫዎች ፈርመዋል ተብሏል፡፡ የገጾቹ ብዛትም እንደተከላካዮቹ ፊርማ እንደሚከተለው ቀርበዋል፡ በፈቃዱ ኃይሉ ተጫኔ (31 ገጾች)፣ ናትናኤል ፈለቀ አበራ (27 ገጾች)፣ ማህሌት ፋንታሁን ተፈራ (12 ገጾች)፣ አጥናፍ ብርሀኔ አያሌው (16 ገጾች)፣ ዘላለም ክብረት ቤዛ (16 ገጾች)፣ አቤል ዋቤላ ሱጌቦ (12 ገጾች)፣ አስማማው ኃይለጊዮርጊስ ግዛው (13 ገጾች)፣ ኤዶም ካሳዬ ገላን (10 ገጾች) እና ተስፋለም ወልደዬስ አራጌ (13 ገጾች፣ እና በሌለበት ክስ የተመሰረተበት ሶሊያና ሽመልስ ገብረማርያም ናቸው፡፡)

ተከላካዮቹ በውንጀላ የእምነት ቃል እንዲሰጡ በሚደረግበት ጊዜ የሕግ ምክር አገልግሎት እንዳያገኙተከልክለዋል። 

ለሕዝብ የህሊና ዳኝነት ክፍት ለማድረግ እንዲቻል በማሰብ በወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የሸፍጥ ውንጀላ የተከሰሱት ጦማሪያን በዝርዝር እና የቀረቡባቸው የጽሁፍ እና የቁስ ማስረጃዎች እንደሚከተለው ቀርበዋል፡

1) በፈቃዱ ኃይሉ ተጫኔ፡ የተመሰረተበት ክስ “የሀገር ውስጥ የሚስጥር የሽብር ድርጅት ማቋቋም“ እና “ለአባላቱ ዕቅድ ማውጣት እና የሚከናወኑ ተግባሮችን እና ኃላፊነቶችን ለአባላቱ መመደብ“ የሚሉ ናቸው፡፡ በፍቃዱ መንግስትን በኃይል ለማስወገድ በማሰብ “የሳጥን ደህንነት ” እየተባሉ የሚጠሩትን ጽሁፎችን ወደ ኮድ የሚለውጡ መሳሪያዎችን እና የግንኙነት ስልጠናዎችን በመውሰድ ግንቦት 7 እየተባለ የሚጠራውን “አሸባሪ” ድርጅት ለማገዝ ስትራቴጂ በመንደፍ ድጋፍ አድርጓል የሚል ነው፡፡

በበፈቃዱ ላይ የቀረበው የሰነድ ማስረጃ የሚከተሉትን ያካትታል፡ 31 ገጽ የእምነት ቃል እና ከእራሱ ላፕቶፕኮምፒውተር እና ከቤቱ የተሰበሰበ መረጃ፡ “ለለውጥ ፈላጊዎች እና ለጀግኖች” በሚል ርዕስ የተጻፈ ጽሁፍ እና “ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ለትግራይ እንዴት ሕጋዊ እንደሆነ”፣ “80 ሚሊዮን እስከምንሆን ድረስ እንዋጋለን“፣ “እኛ ህብረት ከፈጠርን አምባገነኖች ምንድን ሊሆኑ ይችላሉ“፣ “በድረ ገጾች የሚለቀቁ ጽሁፎችን የመመርመር ዘመቻ ይቁም“፣  “ዋኤል ጎኒም ኢትዮጵያዊ ቢሆን ኖሮ የሚል (ከግብጽ ምዕናባዊ የኢንተርኔት አክቲቪስት ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ-18 ገጾች“፣ “የሲቪል ነጻነቶች ተሟጋቾች የስልጠና ሰነድ“፣ “መንግስት አለን? ወይም ደግሞ መንግስት የማን ነው? እና ምን ዓይነት ነው? -10 ገጾች“፣ “የኢሕአዴግ አባል ያልሆነ ዳኛ ይኖራልን?”፣ “የቴሌኮም የሸፍጥ ሕግ ሀሳብን የመግለጽ ነጻነትን ለመሸበብ የወጣ መሳሪያ – 12 ገጾች“፣ “የተሰበሰበ የሕዝብ አስተያየት እና የድረ ገጽ ዘመቻ ዕቅድ – 3 ገጾች“፣ እና “ለዘጋቢ ፊልም ዝግጅት በኢትዮጵያ ሀሳብን በነጻ በመግለጽ ሁኔታ ላይ ያተኮሩ በእጅ የተጻፉ ቃለመጠይቆች ዝርዝር“ በሚሉ የተለያዩ ርዕሶች የተዘጋጁ ጽሁፎች ናቸው፡፡

2) ናትናኤል ፈለቀ አበራ፡ የአሸባሪ ቡድኑ ዋና አቀነባባሪ የሚል የውንጀላ ክስ ተመስርቶበታል፡፡ “በሀገር ውስጥ የሚስጥር የሽብር ድርጅት ማቋቋም“ እና “ሁሉንም የሽብር ቡድኑን እንቅስቃሴዎች ማስተባበር“፣ “ናትናኤል ከግንቦት 7 ጋር በመተባበር ሕብረተሰቡ የአመጽ ድርጊት እንዲጀምር በርካታ ስልጠናዎችን ለመስጠት ተነሳሽነትን በማሳየት ማደራጀት፣ ሙሉ ተሳታፊ መሆን፣ ስራዎችን ሁሉ ማሳለጥ” የሚሉ ውንጀላዎች ቀርበውበታል፡፡

የጽሁፍ ማስረጃ ተብለው የቀረቡት የሚከተሉትን ያካትታል፡ የእምነት ቃል የተሰጠባቸው 27 ገጾች፣ “ከላፕቶፕ ኮምፒውተሩ የተሰበሰቡ እና ከኢሜይል ድረ ገጽ የወረዱ/download የተደረጉ ጽሁፎች“፣ ሌሎች ሰነዶች ማለትም በሚከተሉት ርዕሶች የተዘጋጁ፣ “ዋኤል ጎኒም ኢትዮጵያዊ ቢሆን ኖሮ የሚል (ከግብጽ ምዕናባዊ የኢንተርኔት አክቲቪስት ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ-18 ገጾች – በበፈቃዱ ኃይሉ የተጻፈ“፣ “ዳቦ እና ነጻነት በሚል፣ ለጽሁፍ ምርመራ ይቁም ዘመቻ የተጻፈ“፣ “የጽሁፍ ምርመራ ዋጋ – 8 ገጾች ጽሁፍ“፣ “አሁን በህይወት የሌለውን መለስ ዜናዊን የሚተች የግንቦት 7 ደብዳቤ – 4 ገጾች“፣ “ከቢዝነስ እና ኮንስትራክሽን ባንክ ገንዘብ የተቀበለበት ደረሰኝ“፣ “በኢንተርኔት የደህንነት ጉዳይን በማስመልከት ከሶሊያና ሽመልስ ፓስፖርት ጋር በተያያዘ የተደረገ የኢንተርኔት መልዕክት ልውውጥ – 26 ገጾች“፣ “ስለኢትዮጵያ በናትናኤል ፈለቀ በእጅ ጽሁፍ የተዘጋጀ ግጥም እና ከቤቱ የተሰበሰበ – 1 ገጽ“ በሚሉ ርዕሶች የተዘጋጁ ናቸው፡፡

3) ማህሌት ፋንታሁን ተፈራ፡ “የግንቦት 7ን አሸባሪ ቡድን ዓላማዎች ለማስፈጸም በርካታ የሚስጥር መረብ በመዘርጋት ተባባሪ ሆና መገኘት”፣ “በርካታ የሆኑ የአመጽ እና የሽብር ስልጠናዎችን በማዘጋጀት እና በመሳተፍ ትብብር አድርጋለች“ የሚሉ ውንጀላዎች ቀርበውባታል፡፡

በማህሌት ላይ የቀረቡባት የጽሁፍ ማስረጃዎች የሚከተሉትን ያካተተ ነው፡ “የእምነት ቃል እንድትሰጥ የተደረገችበት – 12 ገጾች”፣ እንደዚሁም ሌሎች ማስረጃዎች “ከኮምፒውተር የተሰበሰቡ ሰነዶች“፣ “የኃይል አመጽ ለመቀስቀስ መንቀሳቀስ እና የምጣኔ ሀብት ዕድገቱን ዕውቅና ያለመስጠት የሚሉ ጹሁፎችን ያካተተ – 2 ገጾች“፣ እና “ከሲዲ እንዲታተም የተደረገ የኦነግ የፖለቲካ ፕሮግራም – 22 ገጾች“ የሚሉ የውንጀላ ክሶች ናቸው፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ባልታሰበ እና ባልተጠበቀ ሁኔታ ክሱ እንዲቋረጥ ተደርጎ .. ሀምሌ 9/2015 ከማጎሪያውእስር እንድትለቀቅ ተደርጓል፡፡

4) አጥናፍ ብርሀኔ አያሌው፡ ሆን ብሎ እያወቀ በሚስጥር ከሚንቀሳቀሰው የግንቦት 7 አሸባሪ ቡድን ጋር በሚድብቅ ተሳትፎ አድርጓል“፣ “የመንግስት የደህንነት ኃይሎችን እንዴት አድርጎ መቀስቀስ እንደሚቻል እና በመካከላቸው የጎሳ ክፍፍልን በመፍጠር ሁከት ለማስነሳት እና እራስን እንዴት አድርጎ ፊትን በመሸፈን፣ሄልሜቶችን በእራስ ላይ በማድረግ ከአደጋ መከላከል እንደሚቻል፣ የሚፈነዱ ነገሮችን እና ድንጋይን እንዴትመጠቀም እንደሚቻል ስልጠና ወስዷል፡፡“ (አጽንኦ ተጨምሯል፡፡)

በአጥናፍ ላይ የቀረቡት የጽሁፍ ማስረጃዎች የሚከተሉትን ያካትታል፡ “የእምነት ቃል እንዲሰጥ የተደረገበት – 16 ገጾች”፣ እና ሌሎች ሰነዶች ማለትም “ነጻነት በኢትዮጵያ – 34 ገጾች“፣ “ስለኢንተርኔት ደህንነት የስልጠና ሰነድ“፣ “በእጅ ጽሁፍ የተዘጋጀ የሚስጥር የአመጽ ቅደምተከተል ሰነድ – 61 ገጾች“፣ “በፍላሽ ላይ ያለ ስለደህንነት ቅደምተከተል የተዘጋጀ ሰነድ“፣ “በገጠሪቱ ኢትዮጵያ ስለነጻነት ሊታዩ የሚችሉ አጫጭር ፊልሞችን ለማዘጋጀት የቀረበ ንድፈ ሀሳብ – 7 ገጾች“፣ “ለሚመጣው ምርጫ ዓላማ ሊውል የሚችል የኢንተርኔት አድራሻ ስያሜ ለመግዛት ዕቅድ መያዝ – 8 ገጾች“፣ “እ.ኤ.አ በ2015 በኢትዮጵያ ስለሚካሄደው ሀገር አቀፍ ምርጫ የማህበራዊ ድረ ገጽ ሚና- 9 ገጾች“፣ “የጽሁፍ ምርመራን እንዴት ማስቀረት እንደሚቻል በሲቪል መብቶች ተሟጋች ድርጅቶች አስተባባሪነት የተዘጋጀ የስልጠና ሰነድ“፣ “በኢንተርኔት የመጠቀሚያ የሚስጥር ኮዶችን እና ፓስወርዶችን የመለወጥ ዘዴ – 129 ገጾች“፣ “የዲጂታል የደህንነት ስልጠና ለመውሰድ ለእርሱ የተላለፈ የግብዣ ደብዳቤ“፣ “የጉዞ ዕቅድ እና ቲኬት – 18 ገጾች“ የውንጀላ ክሶች ቀርበውበታል፡፡

5) ዘላለም ክብረት ቤዛ፡ “የሀገር ውስጥ የሚስጥር የሽብር ድርጅት ማቋቋም“ እና ሆን ብሎ እያወቀ በሚስጥር ከሚንቀሳቀሰው የግንቦት 7 አሸባሪ ቡድን ጋር በሚስጥር የግነኙነት መረብ ዘርግቷል“፣ “ህዝቡን ለማነሳሳት አመጽ እንዲጀመር ለማድረግ እንዲቻል በሀገር ውስጥ እና ከኢትዮጵያ ውጭ በርካታ ስልጠናዎች እንዲዘጋጁ አድርጓል፣ ተሳትፏል፣ እንዲሳለጡም አድርጓል፡፡“

በዘላለም ላይ የቀረቡት የጽሁፍ ሰነድ ማስረጃዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ፡ “የእምነት ቃል እንዲሰጥ የተደረገበት – 16 ገጾች“፣ እና ሌሎች የተሰበሰቡ ሰነዶች ማለትም “ከውጭ ሀርድ ዲስክ ጭቆና እና የሰብአዊ ልማት ጽሁፍ“ የሚል ያለበት፣ “ዋኤል ጎኒም ኢትዮጵያዊ ቢሆን ኖሮ የሚል (ከግብጽ ምዕናባዊ የኢንተርኔት አክቲቪስት ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ-18 ገጾች – በበፈቃዱ ኃይሉ የተጻፈ“፣ “የጽሁፍ ምርመራ ዋጋ“፣ “ድምጻችን ከሚዘረፍ እንዲሰማ ማድረግ“፣ “በገጠሪቱ ኢትዮጵያ ስለነጻነት ሊታዩ የሚችሉ አጫጭር ፊልሞችን ለማዘጋጀት የቀረበ ንድፈ ሀሳብ“፣ “የመለስ ዜናዊ ራዕይ እና ትሩፋት – 4 ገጾች“፣ “የሞተው ፓርላማ – 22 ገጾች“ የሚሉ ውንጀላዎች ቀርበውበታል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ባልታሰባ እና ባልተጠበቀ ሁኔታ ክሱ እንዲቋረጥ ተደርጎ .. ሀምሌ 9/2015 ከማጎሪያውእስር እንዲለቀቅ ተደርጓል፡፡

6) አቤል ዋቤላ ሱጌቦ፡ የተመሰረተበት ክስ “የሀገር ውስጥ የሚስጥር የሽብር ድርጅት ማቋቋም“፣ “ከግንቦት 7 ጋር በመተባበር ህዝቡን ለአመጽ ለማነሳሳት፣ አመጽ እንዲጀመር ለማድረግ እንዲቻል በሀገር ውስጥ እና ከኢትዮጵያ ውጭ በርካታ ስልጠናዎች እንዲዘጋጁ አድርጓል፣ ተሳትፏል፣ እንዲሳለጡም አድርጓል፡፡“

በአቤል ላይ የቀረቡት የጽሁፍ ሰነድ ማስረጃዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ፡ “የእምነት ቃል የተሰጠበት – 12 ገጾች“፣ እና ሌሎች ሰነዶች ማለትም “ለሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ዲጂታል የደህንነት ሰነድ – 18 ገጾች“፣ “በእርሱ ቤት ውስጥ የተመደቡ የቡድን አባላት ሚናዎች እና ኃላፊነቶች – 26 ገጾች“፣ “ለሚመጣው ምርጫ ዓላማ ሊውል የሚችል የኢንተርኔት አድራሻ ስያሜ ለመግዛት ዕቅድ መያዝ – 8 ገጾች“ የሚሉ ውንጀላዎች ቀርበውበት ነበር፡፡

7)  አስማማው ኃይለጊዮርጊስ ግዛው፡ የተመሰረተበት የክስ ውንጃላ “የሀገር ውስጥ የሚስጥር የሽብር ድርጅት ማቋቋም“፣ “አስቦበት እና ሆን ብሎ እያወቀ ግንቦት 7 እየተባለ ከሚጠራው “አሸባሪ” ድርጅት ጋር ግንኙነት ፈጥሯል፡፡“ የሚል ነው፡፡

በአስማማው ላይ የቀረቡት የጽሁፍ ማስረጃዎች የሚከተሉትን ያካትታል፡ “የእምነት ቃል የሰጠበት – 13 ገጾች“፣ እና ሌሎች የተሰበሰቡ ሰነዶች ማለትም “ከምግብ በፊት ፍትሕ እና ሰላም”፣ “ሙስሊሞች በኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ ተሳትፎ ማድረግ መጀመር አለባቸው – 6 ገጾች“፣ “የሁሉም ንቅናቄ ተከሳሾች የምርመራ ውጤት በኢትዮጵያ የመረጃ ደህንነት ተመዝግቦ እንደተያዘ- 31 ገጾች“፣ “በኢትዮጵያ የፌዴራል የመረጃ ደህንነት አገልግሎት የተጻፈ ደብዳቤ   56 ገጾች“፣ “የዲጂታል ደህንነት ለጋዜጠኖች“፣ “በኢትዮጵያ መንግስት ሀሳብን በነጻ የመግለጽ መብትን የሚነጥቅባቸው መንገዶች“፣ “በዳሽን ባንክ የተጻፈ ደብዳቤ – 31 ገጾች“፣ “የተከሳሹ የፓስፖርት ፎቶኮፒ ቅጅዎች ለተከሳሹ ውንጀላ ማጠናከሪያ እንዲመጡ ተደርጓል፡፡“ የሚሉት ናቸው፡፡        

ይህ በእንዲህ እንዳለ ባልታሰባ እና ባልተጠበቀ ሁኔታ ክሱ እንዲቋረጥ ተደርጎ .. ሀምሌ 9/2015 ከማጎሪያውእስር እንዲለቀቅ ተደርጓል፡፡

8) ኤዶም ከሳዬ ገላን፡ የተመሰረተባት የክስ ውንጀላ “ሆን ተብሎ ታስቦበት እና እያወቀች የግንቦት 7 አሸባሪ ቡድንን ስትራቴጂዎች ባካተተ መልኩ ለተፈጻሚነታቸው ተሳትፎ አድርጋለች“፣ “ከግንቦት 7 ጋር በመተባበር ህዝቡን ለአመጽ ለማነሳሳት እና አመጽ እንዲጀመር ለማድረግ እንዲቻል በሀገር ውስጥ እና ከኢትዮጵያ ውጭ በርካታ ስልጠናዎች እንዲዘጋጁ አድርጋለች፣ ተሳትፋለች፣ እንዲሳለጡም አድርጋለች“ የሚሉ ናቸው፡፡

በኤዶም ላይ የጽሁፍ ሰነድ ማስረጃ ምንም ዓይነት ዝርዝር አልቀረበም! 

ይህ በእንዲህ እንዳለ ባልታሰበ እና ባልተጠበቀ ሁኔታ ክሱ እንዲቋረጥ ተደርጎ .. ሀምሌ 9/2015 ከማጎሪያውእስር እንድትለቀቅ ተደርጓል፡፡ 

9) ተስፋለም ወልደዬስ:  የተመሰረተበት የክስ ውንጀላ “ሆን ተብሎ ታስቦበት እና እያወቀ የግንቦት 7 አሸባሪ ቡድንን ስትራቴጂዎች ባካተተ መልኩ ለተፈጻሚነታቸው ተሳትፎ አድርጓል“፣ “ከግንቦት 7 ጋር በመተባበር ህዝቡን ለአመጽ ለማነሳሳት እና አመጽ እንዲጀመር ለማድረግ እንዲቻል በሀገር ውስጥ እና ከኢትዮጵያ ውጭ በርካታ ስልጠናዎች እንዲዘጋጁ አድርጓል፣ ተሳትፏል፣ እንዲሳለጡም አድርጓል“ የሚል ነው፡፡

በተስፋለም ላይ የጽሁፍ ሰነድ ማስረጃ ምንም ዓይነት ዝርዝር አልቀረበም! 

ይህ በእንዲህ እንዳለ ባልታሰበ እና ባልተጠበቀ ሁኔታ ክሱ እንዲቋረጥ ተደርጎ .. ሀምሌ 9/2015 ከማጎሪያውእስር እንዲለቀቅ ተደርጓል፡፡ 

የአሸባሪነት ቁሳዊ ማስረጃዎች፣ 

የውንጀላ ክስ የተመሰረተባቸው የቁስ አካል ማስረጃዎች የሚከተሉትን ያካትታል፡ 2 ቶሽባ  ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች፣ 3 ሳምሰንግ ተንቀሳቃሽ ስልኮች ከ2 ሲምካርዶች ጋር፣ 1 አሰስ ላፕቶፕ ኮምፒውተር፣ 1 ቴክኖሞባይል ተንቀሳቃሽ ስልክ ከ2 ሲምካርዶች ጋር፣ 1 ሳምሰንግ ተንቀሳቃሽ ስልክ፣ 2 የመቅጃ ፍላሾች፣ 1 ተች ሰክሪን ተንቀሳቃሽ ስልክ፣ 2 በሳጥን ውስጥ ያሌ የደህንነት መጽሐፎች፣ 3 ኖኪያ ተንቀሳቀሽ ስልኮች፣ 1 ዴል ላፕቶፕ ኮምፒውተር፣ 1 አፕል ላፕቶፕ ኮምፒውተር፣ 1 ሁአዌ ተንቀሳቃሽ ስልክ ከ3 ሲም ካርዶች ጋር፣ 12 የቪዲዮ ማጫዎቻ ሲዲዎች ናቸው፡፡

በኃይል በማስገደድ የተገኘ የእምነት ቃል እና በሕገወጥ መልክ ኃይልን በመጠቀም የሕግ የምክር አገልግሎትእንዳያገኙ በማድረግ የተገኘ የአሸባሪነት ማስረጃ ሆኖ ሊቀርብ ይችላልን? 

የሚከተሉትን ሁሉንም ወይም ደግሞ አንደኛቸውን ነገሮች እንደበቂ ማስረጃዎች በመያዝ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስርበማዋል የሽብር ድርጊት ፈጽመዋል ወይም ደግሞ የሽብር ድርጊት ሙከራ አድርገዋል በማለት በችሎት በማቅረብየሕግ ሂደት ስርዓት ማከናወን ይቻላልን?:

“ለለውጥ ፈላጊዎች እና ለጀግኖች የተጻፈ ጽሁፍ” በሚል ርዕስ የተጻፈ ጽሁፍ ይዞ መገኘት፣

“ህወሀት ለትግራይ ህዝብ እንዴት ያለ ህጋዊ ድርጅት ሊሆን እንደሚችል የሚጠይቅ ጽሁፍ” በሚል ርዕስ ተዘጋጀ ሰነድ ይዞ መገኘት፣

“80 ሚሊዮን እስከምንሆን ድረስ እንዋጋለን” በሚል ርዕስ የተጻፈ ጽሁፍ ይዞ መገኘት፣

“እኛ ህብረት ከፈጠርን አምባገነኖች ምንድን ሊሆኑ ይችላሉ?“ በሚል ርዕስ የተጻፈ ጽሁፍ ይዞ መገኘት፣

“በድረገ ገጽ በሚወጣ ጽሁፍ ላይ የሚደረግ የጽሁፍ ምርመራ ዘመቻ ይቁም” በሚል ርዕስ የተጻፈ ጽሁፍ ይዞ መገኘት፣

“ዋኤል ጎኒም ኢትዮጵያዊ ቢሆን ኖሮ (ከግብጽ ምዕናባዊ የኢንተርኔት አክቲቪስት ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ – 18 ገጾች“ በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ጽሁፍ ይዞ መገኘት፣

“ለሲቪል ነጻነት ተሟጋቾች የስልጠና ሰነድ” በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ሰነድ ይዞ መገኘት፣

“መንግስት አለን? ወይም ደግሞ መንግስት የማን ነው? ምንስ ዓይነት ነው? – 10 ገጾች” በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ጽሁፍ ይዞ መገኘት፣

“የኢህአዴግ አባል ያልሆነ ዳኛ ሊኖር ይችላልን?“ በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ጽሁፍ ይዞ መገኘት፣

“የቴሌኮም የሸፍጥ ሕግ ሀሳብን የመግለጽ ነጻነትን ለመሸበብ የወጣ መሳሪያ – 12 ገጾች“ በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ጽሁፍ ይዞ መገኘት፣

“የተሰበሰበ የሕዝብ አስተያየት እና በደረ ገጽ ላይ የሚደረግ ዘመቻ ዕቅድ“ በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ጽሁፍ ይዞ መገኘት፣

“ለዘጋቢ ፊልም ዝግጅት በኢትዮጵያ ሀሳብን በነጻ በመግለጽ ሁኔታ ላይ ያተኮሩ በእጅ የተጻፉ ቃለመጠይቆች ዝርዝር“ በሚል ርዕስ በእጅ የተጻፈ ጽሁፍ ይዞ መገኘት፣

“ዳቦ እና ነጻነት፣ ለጽሁፍ ምርመራ ይቁም ዘመቻ“ በሚል ርዕስ የተጻፈ ጽሁፍ ይዞ መገኘት፣

“የጽሁፍ ምርመራ ዋጋ – 8 ገጾች“ በሚል ርዕስ የተጻፈ ጽሁፍ ይዞ መገኘት፣

“አሁን በህይወት የሌለውን መለስ ዜናዊን የሚተች የግንቦት 7 ደብዳቤ – 4 ገጾች“ የተጻፈ ትችት ይዞ መገኘት፣

“ከቢዝነስ እና ኮንስትራክሽን ባንክ ገንዘብ የተቀበለበት ደረሰኝ“ በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ደረሰኝ ይዞ መገኘት፣

“በኢንተርኔት የደህንነት ጉዳይን በማስመልከት ከሶሊያና ሽመልስ ፓስፖርት ጋር በተያያዘ የተደረገ የኢንተርኔት መልዕክት ልውውጥ – 26 ገጾች” በሚል ርዕስ የተጻፈ የመልዕክት ልውውጥ ይዞ መገኘት፣

“ስለኢትዮጵያ በናትናኤል ፈለቀ በእጅ ጽሁፍ የተዘጋጀ ግጥም እና ከቤቱ የተሰበሰበ – 1 ገጽ“ በሚል ርዕስ የተጻፈ ጽሁፍ ይዞ መገኘት፣

“የኃይል አመጽ ለመቀስቀስ መንቀሳቀስ እና የምጣኔ ሀብት ዕድገቱን ዕውቅና ያለመስጠት የሚሉ ጹሁፎችን ያካተተ – 2 ገጾች” በሚል ርዕስ የተጻፈ ጽሁፍ ይዞ መገኘት፣

“ከሲዲ የታተመ የኦነግ የፖለቲካ ፕሮግራም – 22 ገጾች“ በሚል ርዕስ የቀረበ ጽሁፍ ይዞ መገኘት፣

“ነጻነት በኢትዮጵያ – 34 ገጾች“ በሚል ርዕስ የተጻፈ ጽሁፍ ይዞ መገኘት፣

“ስለኢንተርኔት ደህንነት የስልጠና ሰነድ“ በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ሰነድ ይዞ መገኘት፣

“በእጅ ጽሁፍ የተዘጋጅ የሚስጥር የአመጽ ቅደምተከተል ሰነድ – 61 ገጾች“ በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ጽሁፍ ይዞ መገኘት፣

“በመቅጃ ፍላሽ ላይ ያለ ስለደህንነት ቅደምተከተል የተዘጋጀ ሰነድ“ በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ጽሁፍ ይዞ መገኘት፣

“በገጠሪቱ ኢትዮጵያ ስለነጻነት ሊታዩ የሚችሉ አጫጭር ፊልሞችን ለማዘጋጀት የቀረበ ንድፈ ሀሳብ – 7 ገጾች“ በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ጽሁፍ ይዞ መገኘት፣

“ለሚመጣው ምርጫ ዓላማ ሊውል የሚችል የኢንተርኔት አድራሻ ስያሜ ለመግዛት ዕቅድ መያዝ – 8 ገጾች“ በሚል ርዕስ የተዘጋጅ ጽሁፍ ይዞ መገኘት፣

“እ.ኤ.አ በ2015 በኢትዮጵያ ስለሚካሄደው ሀገር አቀፍ ምርጫ የማህበራዊ ድረ ገጽ ሚና- 9 ገጾች“ በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ጽሁፍ ይዞ መገኘት፣

“የጽሁፍ ምርመራን እንዴት ማስቀረት እንደሚቻል በሲቪል መብት ተሟጋች ድርጅቶች አስተባባሪነት የተዘጋጀ የስልጠና ሰነድ“፣

“በኢንተርኔት የመጠቀሚያ የሚስጥር ኮዶችን እና ቁልፎችን የመለወጥ ዘዴ – 129 ገጾች“፣ በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ጽሁፍ ይዞ መገኘት፣

“የዲጂታል የደህንነት ስልጠና ለመውሰድ ለእርሱ የተላለፈ የግብዣ ደብዳቤ“ “የጉዞ ዕቅድ እና ቲኬት – 18 ገጾች“ በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ጽሁፍ ይዞ መገኘት፣

“የጉዞ ዕቅድ እና ቲኬት – 18 ገጾች“ በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ሰነድ ይዞ መገኘት፣

“ከውጭ ሀርድ ዲስክ ጭቆና እና የሰብአዊ ልማት ጽሁፍ“፣ በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ጽሁፍ ይዞ መገኘት፣

“ዋኤል ጎኒም ኢትዮጵያዊ ቢሆን ኖሮ የሚል (ከግብጽ ምዕናባዊ የኢንተርኔት አክቲቪስት ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ-18 ገጾች – በበፈቃዱ ኃይሉ የተጻፈ“ ሰነድ ይዞ መገኘት፣

“የጽሁፍ ምርመራ ዋጋ“ በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ጽሁፍ ይዞ መገኘት፣

“ድምጻችን ከሚዘረፍ እንዲሰማ ማድረግ“ በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ጽሁፍ ይዞ መገኘት፣

“በገጠሪቱ ኢትዮጵያ ስለነጻነት ሊታዩ የሚችሉ አጫጭር ፊልሞችን ለማዘጋጀት የቀረበ ንድፈ ሀሳብ“ በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ጽሁፍ ይዞ መገኘት፣

“የመለስ ዜናዊ ራዕይ እና ትሩፋት – 4 ገጾች“ በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ጽሁፍ ይዞ መገኘት፣

“የሞተው ፓርላማ – 22 ገጾች“ በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ጽሁፍ ይዞ መገኘት፣

“ለሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ዲጂታል የደህንነት ሰነድ – 18 ገጾች“ በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ሰነድ ይዞ መገኘት፣

“በእርሱ ቤት ውስጥ የተመደቡ የቡድን አባላት ሚናዎች እና ኃላፊነቶች – 26 ገጾች“ በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ጽሁፍ ይዞ መገኘት፣

“ለሚመጣው ምርጫ ዓላማ ሊውል የሚችል የኢንተርኔት አድራሻ ስያሜ ለመግዛት ዕቅድ መያዝ – 8 ገጾች“ በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ጽሁፍ ይዞ መገኘት፣

“ከምግብ በፊት ፍትሕ እና ሰላም” በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ጽሁፍ ይዞ መገኘት፣

“ሙስሊሞች በኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ ተሳትፎ ማድረግ መጀመር አለባቸው – 6 ገጾች“ በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ጽሁፍ ይዞ መገኘት፣

“የሁሉም ንቅናቄ ተከሳሾች የምርመራ ውጤት በኢትዮጵያ የመረጃ ደህንነት ተመዝግቦ እንደተያዘ – 31 ገጾች“ በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ጽሁፍ ይዞ መገኘት፣

“በኢትዮጵያ የፌዴራል የመረጃ ደህንነት አገልግሎት የተጻፈ ደብዳቤ 56 ገጾች“ በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ጽሁፍ ይዞ መገኘት፣

“የዲጂታል ደህንነት ለጋዜጠኖች“ በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ጽሁፍ ይዞ መገኘት፣

“የሁሉም ንቅናቄ ተከሳሾች የምርመራ ውጤት በኢትዮጵያ የመረጃ ደህንነት ተመዝግቦ እንደተያዘ – 31 ገጾች“ በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ጽሁፍ ይዞ መገኘት፣

“በኢትዮጵያ የፌዴራል የመረጃ ደህንነት አገልግሎት የተጻፈ ደብዳቤ – 56 ገጾች“ በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ጽሁፍ ይዞ መገኘት፣

“የዲጂታል ደህንነት ለጋዜጠኖች“ በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ጽሁፍ ይዞ መገኘት፣

“በኢትዮጵያ መንግስት ሀሳብን በነጻ መግለጽ መብትን የሚነጥቅባቸው መንገዶች“ በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ጽሁፍ ይዞ መገኘት፣

“በዳሽን ባንክ የተጻፈ ደብዳቤ – 31 ገጾች“ በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ደብዳቤ ይዞ መገኘት፣

“የተከሳሹ የፓስፖርት ፎቶኮፒ ቅጅዎች ለተከሳሹ ውንጀላ ማጠናከሪያ እንዲመጡ ተደርጓል” በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ሰነድ ይዞ መገኘት የሚሉ ናቸው፡፡

የሚከተሉት ቁሶች በአሸባሪነት የሕዝብ ዕልቂትን ሊያስከትሉ የሚችሉ ተመራጭ መሳሪዎች ናቸውን? 

2 ቶሽባ ላፕቶፖች፣ 3 ሳምሰንግ ተንቀሳቃሽ ስልኮች ከ2 ሳም ካርዶች ጋር፣ 1 አሰስ ላፕቶፕ ኮምፒውተር፣ 1 ቴክኖሞባይል ተንቀሳቃሽ ስልክ ከ2 ሲም ካርዶች ጋር፣ 1 ሳምሰንግ ተንቀሳቃሽ ስልክ፣ 2 የመቅጃ ፍላሾች፣ 1 ተች ስክሪን ተንቀሳቃሽ ስልክ፣ 2 በሳጥን ውስጥ ያሉ የደህንነት መጽሐፎች፣ 3 ኖኪያ ተንቀሳቃሽ ስልኮች፣ 1 ዴል ላፕቶፕ ኮምፒውተር፣ 1 አፕል ላፕቶፕ ኮምፒውተር፣ 1 ሁአዌ ተንቀሳቃሽ ስልክ ከ3 ሲምካርዶች ጋር፣ 12 የቪዲዮ ማጫዎቻ ሲዲዎች የሚሉ ናቸው፡፡

ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች ከAK 47 ጋር እኩል ናቸውን?

ተንቀሳቃሽ ስልኮች ከእጀ ቦምቦች ጋር እኩል ናቸውን?

የመቅጃ ፍላሽ ድራይቮች ከፍላሽ ቦምቦች ጋር እኩል ናቸውን?

በሳጥን ውስጥ ያሉ የደህንነት መጽሐፍት የተሻሻሉ የፍንዳታ መሳሪዎች ናቸውን?

የቪዲዮ ማጫዎች ሲዲዎች ከአርፒጂዎች/RPGs (ፈንጂ መተኮሻ ) እኩል ናቸውን?

ሲም ካርዶች ከጥይቶች ጋር እኩል ናቸውን?

በአጠቃላይ ከዞን 9 ጦማሪያን ጉዳይ ጋር በተያያዘ መልኩ እነዚህ ጦማሪያን የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ግንቦት 7 የተባለውን ድርጅት አሸባሪ ብሎ የሰየመው የነጻነት ንቅናቄ ድርጅት አባላት ናቸው በማለት በምዕናቡ ፈጥሮ የሚያራምደው እና የሚያናፍሰው እኩይ ምግባር ነው፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እነዚህ ለመብቶቻቸው በጽናት በመቆም ሰላማዊ ትግል የሚያካሂዱ እና ለሀገራቸው ለውጥ በሰላማዊ መንገድ ይመጣል በማለት እምነታቸውን የሚያራምዱ ትንታግ ወጣት ጦማሪያን ለግንቦት 7 ይቅር እና ለሌላ ለየትኛውም ድርጅት አባል ስለመሆናቸው ቅንጣት ታህል ማስረጃ የለውም፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እራሱ በፈጠረው ባዶ ምዕናቡ በመመራት በእነዚህ ጦማሪያን ላይ የደቦክስ በመመስረት ጥፋተኛ እንዲባሉለት ይፈልጋል፡፡

የዞን 9 ጦማሪያን ምንም ዓይነት የሰሩት ወንጀል የለም፡፡ በወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ወንጀል ተብሎ የተያዘባቸው ሀሳባቸውን የመግለጽ መብታቸውን በመጠቀማቸው ብቻ ነው!

ይልቁንም የዞን 9 ጦማሪያን እራሳቸው የወንጀል እና የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የሽብር ሰለባዎች ናቸው፡፡

እንዲያው ለመሆኑ እትብታቸው በተቀበረችበት በእራሳቸው ሀገር ዘመኑ ያፈራቸውን የግንኙነት ቴክኖሎጂዎች በመጠቀም የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ሀሳብን በነጻ የመግለጽ መብት የተከበረባት ሀገር አድርጊያታለሁ እያለ ሌት ከቀን እንደበቀቀን ከሚለፈልፍባት ሀገር ሆነው ሀሳባቸውን የመግለጽ መብታቸውን በመጠቀም ሰላማዊ እና የምሁራዊ አንደበት ክህሎታቸውን በማከል ግንኙነት ማድረጋቸው በየትኛው መለኪያ እና መስፈርት እንዲሁም የሕግ አንቀጽ ነው ሽብረተኞች ተብለው ከሕግ አግባብ ውጭ በእስር ቤት እየማቀቁ እንዲኖሩ የሚደረገው?

ምን ዓይነት የፍትሕ አካል ቢኖርስ ነው ለእንደዚህ ያለው የሸፍጥ መንግስታዊ ውንብድና እኩይ ምግባር ተባባሪ ሆኖ በዜጎቹ ላይ እንደዚህ ያለ ግፍ እየሰራ የአምባገነኖች ተባባሪ ሊሆን የሚችለው?

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ፕላኔት የዝንጀሮዎች ፕላኔት አፈታሪክ ቢሆን ኖሮ የዞን 9 ጦማሪያን እጅግ በጣም ጥሩ የሆነ የማምለጫ ዕድል ይኖራቸው ነበር፡፡

የመከላክል ጥረቱ በምንም ዓይነት መንገድ ለወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ቡድን አያጎበድድም፡፡

ሆኖም ግን ጉዳዬን በወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ፕላኔት ላይ ላለው የዝንጀሮ/ጦጣ ችሎት ትቻለሁ!

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!

ነሐሴ 20 ቀን 2007 .

በመተካካት ተሸኝተው የነበሩት የሕወሓት ነባር አመራሮች ተመለሱ

በመተካካት ተሸኝተው የነበሩት የሕወሓት ነባር አመራሮች ተመለሱ

– ሦስቱ አባል ድርጅቶችም ጉባዔያቸውን አካሂደዋል

ከነሐሴ 16 ቀን 2007 ዓ.ም. ጀምሮ በመቐለ ሰማዕታት አዳራሽ እየተደረገ ባለው 12ኛው የሕወሓት ጉባዔ፣ በመተካካት ተሸኝተው የነበሩ የሕወሓት አመራሮች በጉባዔው እንዲመረጡና እንዲመርጡ ተወሰነ፡፡ አዘጋጅ ኮሚቴው የጋበዛቸው ያለ ድምፅ እንዲሳተፉ ነበር፡፡

ከ1,650 በላይ ጉባዔተኞች በታደሙበት ጉባዔ የተገኙ አንድ ተሳታፊ ከዚህ ቀደም ተገፍተው የወጡ ያሏቸው ነበር አመራሮች በድምፅ እንዲሳተፉ ጥያቄ ካቀረቡ በኋላ፣ በጉዳዩ ላይ የመከረው ጉባዔ በጭብጨባ በሙሉ ድምፅ ጥያቄውን ተቀብሎታል፡፡ በዚህም መሠረት ዶ/ር አርከበ እቁባይ፣ አቶ ስብሃት ነጋ (አቦይ)፣አምባሳደር ሥዩም መስፍን፣ አምባሳደር ብርሃነ ገብረ ክርስቶስ፣ አቶ ፀጋዬ በርኼን ጨምሮ 17 ነባር አባላት ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

ጉባዔው በእስካሁኑ ቆይታው በአንደኛው የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ፣ በመልካም አስተዳደርና በመተካካት ላይ ተወያይቷል፡፡ በመልካም አስተዳደር እጦት ክልሉ እየተጠቃ እንደሆነ በርካታ አስተያየቶች ተሰጥተዋል፡፡ በተለይ በአንድ የሃይማኖት አባት የቀረበው የመልካም አስተዳደር እጦት ትኩረት የሳበ ነበር፡፡ የሕወሓት አመራሮች ድርጅቱ ቀድሞ አንግተውት የነበረውን ዓላማ እንደረሱ በአጽንኦት ገልጸው፣ ፍትሕ በገንዘብ እየተገዛ የክልሉ ሕዝብ የማያውቀው አዲስ ባህል በመጎልበቱ ይህንንም እንደሚዋጉት አመልክተዋል፡፡ ‹‹እሳት ያልፈራ ሕዝብ እናንተን የሚፈራ ይመስላችኋል?›› ሲሉም ጥያቄአቸውን አቅርበዋል፡፡ መተካካትን በተመለከተም ወደ መገፋፋት በመቀየሩ ያለ ዕድሜና አቅም ማነስ ዶ/ር አርከበና አምባሳደር ብርሃነ እንዲወጡ መደረጉን ተችተዋል፡፡ እንደ ድሮው መገማገምና አንዱ አንዱን ተጠያቂ ማድረግ በመሸፋፈንና በመጠባበቅ መቀየሩም ተገልጿል፡፡

የሕወሓት ሊቀመንበርና የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ዓባይ ወልዱ የቀረበውን ቅሬታ ተቀብለው፣ የተሠራ ነገር ቢኖርም ትልቅ ዳገት እንደሚጠብቅ ገልጸዋል፡፡ የአመራር አባላት ራሳቸውን ማጥራትና ወደ ራሳቸው መመልከት እንደሚኖርባቸው አሳስበዋል፡፡

ዶ/ር አርከበ በጉባዔው ንቁ ተሳትፎ ያደረጉ ሲሆን፣ ሕዝቡ ቅሬታ እያቀረበ ያለው በፍትሕ አካላትና በፓርቲው አባላት መሆኑ አሳሳቢ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ጉባዔው ዛሬ የሚጠናቀቅ ሲሆን፣ የሥራ አስፈጻሚና የማዕከላዊ ኮሚቴ እንዲሁም የቁጥጥር ኮሚሽን አባላትን ይመርጣል፡፡

11ኛው የብአዴን ድርጅታዊ ጉባዔ በባህር ዳር በድርጅቱ ሪፖርት ላይ ተወያይቷል፡፡ ጉባዔው በክልሉ የተመዘገበውን የኢኮኖሚና ዕድገትና የግብር ምርት ውጤታማነት የገመገመ ሲሆን፣ ኢኮኖሚያዊ ዕድገቱ 10.4 በመቶ በመድረሱ የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ መቻሉ ተገልጿል፡፡ የመጀመርያው የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ፣ የመሠረተ ልማት ግንባታዎች፣ መልካም አስተዳደር፣ ትምህርት፣ ጤናና ሌሎች መስኮችም በግምገማው ተካተዋል፡፡

መልካም አስተዳደርን በተመለከተና በሥራ ፈጠራ ጉድለቶች መኖራቸውን የገመገመው ጉባዔው፣ የክልል ከፍተኛ አመራሮችም ለችግሩ ከፍተኛውን ድርሻ እንደሚይዙ አውስቷል፡፡ የድርጅቱ ጉባዔ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት፣ የብአዴንና የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትን፣ የድርጅቱን ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበር በመምረጥ ማክሰኞ ምሽት ተጠናቋል፡፡ ማክሰኞ ምሽት የተመረጡት እነማን እንደሆኑ ግን አልታወቀም ነበር፡፡

ኢሕዴድ በአዳማ ከተማ 8ኛ ጉባዔው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቷል፡፡ በጉባዔው በክልሉ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ መሠረታዊ ለውጥ ለማምጣት የሚያስችሉ አቅጣጫዎችን ለማምጣት የሚችሉ አዳዲስ ሐሳቦች እንደ ግብዓት ሲሰባሰቡ እንደነበር ተገልጿል፡፡ በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን በክልሉ የ11.2 በመቶ ዕድገት ለማስመዝገብና የኢኮኖሚውን መዋቅራዊ ሽግግር ለማፋጠን የሚያስችሉ ውሳኔዎች ይተላለፋሉ ተብሏል፡፡

የኦሕዴድን ድርጅታዊ ህልውና ይፈታተናሉ የተባሉት ትምክህትና ጠባብነት፣ ኪራይ ሰብሳቢነት፣ የተንዛዙ አሠራሮችና ፍትሐዊነት የጎደላቸው አመራሮች በጉባዔው ወቅት መነሳታቸው ታውቋል፡፡ ላለፉት ሦስት ቀናት ሲካሄድ የነበረው የኦሕዴድ ጉባዔ ማክሰኞ ምሽት ማተሚያ ቤት እስከገባንበት ጊዜ ድረስ ይጠናቀቃል ተብሎ እየተጠበቀ ነበር፡፡

የደኢሕዴን ጉባዔ በሐዋሳ ማክሰኞ ነሐሴ 19 ቀን 2007 ዓ.ም. ተጠናቋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ሊቀመንበር ሆነው እንዲቀጥሉ ሲመረጡ፣ የትምህርት ሚኒስትሩ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ለምክትል ሊቀመንበርነት ተመርጠዋል፡፡ ጉባው በሦስተኛ ቀን ውሎው የመጀመርያውን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ገምግሞ፣ በምግብ እህል ራስን መቻል ላይ አበረታች ውጤት መገኘቱን ተወያይቶበታል፡፡

አበረታች የተባሉ ስኬቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ፣ ይቀራቸዋል የተባሉት ላይ ደግሞ በተጠናከረ ሁኔታ ርብርብ እንዲረደረግ ውሳኔ ተላልፏል፡፡ የጤናና የትምህርት ዘርፍ ተደራሽነታቸው መልካም መሆኑ ተወስቶ፣ የጥራት ጉዳይ ግን እንዲታሰብበት ማሳሰቢያ ተሰጥቷል፡፡ በተጨማሪም ጠባብነት፣ ብልሹ አሠራርና ሙስና በድርጅቱ ውስጥ ቦታ እንደማይኖራቸው ውሳኔ ላይ መደረሱ በውይይቱ ወቅት ተነስቷል፡፡ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት፣ የደኢሕዴንና የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ አባላትም ተመርጠዋል፡፡ የተሟላ ዝርዝር ግን ማግኘት አልተቻለም፡፡

በተያያዘ ዜና የብአዴን ነባር ታጋይና ከፍተኛ አመራር የነበሩት አቶ አዲሱ ለገሠ በክብር መሰናበታቸው የተገለጸ ሲሆን፣ አቶ ዮሴፍ ረታም እንዲሁ ተሰናብተዋል፡፡ የደኢሕአዴን ሊቀመንበር፣ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል በመሆን ያገለገሉት ዶ/ር ካሱ ኢላላ እንዲሁ ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት በክብር መሰናበታቸው ተገልጿል፡