የአማራ ብሔርተኝነት ትኩረቶች!

✍ፍፁም አየነው

በሀገራችን ኢትዮጵያ የተለያዩ የህዝብ አስተዳደሮችም ሆነ የተለያዩ አደረጃጀት ተፈጥረዋል፡፡በእነዚህ ውስጥ አንዱ የብሔረሰብ አደረጃጀት ነው፡፡ዘርን መሰረት በማድረግ ሀገራችን ውስጥ ካሉ ብሔረሰብ ያልተደራጀ የለም ማለት ይቻላል፡፡በፓለቲካ ድርጅትነት ያልተደራጀ ቢኖር እንኳን በማህበር ተሰባስቧል፡፡ከእነዚህ ውስጥ በዕድሜ አጭሩ ነገር ግን በፍጥነቱ አስደማሚ የአማራ ብሔርተኝነት ነው፡፡የአማራ ብሔርነትነት ታዲያ ከሌላው ብሔርተኞች የሚለየው አንድን ህዝብ ጠላት አድርጎ አለመነሳቱ እና በበደል ግፊት የተፈጠረ መሆኑ ነው፡፡አብዛኛዎቹ ሌሎቹ ብሔርተኝነት በስርዓት ላይ ተመርኩዘሁ መሆኑ ቀርቶ አንድን ህዝብ(አማራን) ባልዋለበት በፈጠራ መታገያና በጠላትነት ፈርጀው ነው የተመሰረቱት፡፡ ከአንድነት አደረጃጀት ውስጥም በዚህ አይነት መልኩ የተደራጁ ከሩቆቹ እስከ ቅርብ ጊዜዎቹ ማንሳት ይቻላል፡፡ለአሁን ዋናው ትኩረቴ የአማራ ብሔርተኝነት ግንባታ ላይ ነው፡፡ይህ ብሔርተኝነት ፋሽን ሆኖ የተጀመረ አይደለም በመራራ ዋጋ እንዲጀመር የተገደደ እዚህ ለመድረስም ትልቅ መሰዋዕነት የተከፈለበት የአማራው የዘሩ መቀጠያ ድልድይ ነው፡፡


የአማራ ብሔርተኝነት ትግል የአማራ ነው ሌላው ሊያስጨንቀው አይገባም ጠላቱ ሆኖ እስካልተሰለፈ ድረስ ፤ለዛውም እኔ አማራ ነኝ የሚል ወገን የፈጠረው ነገር ግን ሁሉንም አማራን የሚታደግ ትግል ነው፡፡
ይህ አደረጃጀት በጥርጣሬ እና በፍርሀት የሚመለከቱ መልካም እይታ እና ወገናዊነት ከተሰማቸው ሊረዳቸው ሊያምኑበት ይችላላሉ፡፡ትግሉም ጨለምተኛም አይደለም፡፡

የአማራ ብሔርተኝነት የአማራ ህዝብ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቱ ሳይጠበቅ መልስ አግኝቷል ማለት አይቻልም፡፡በድህረ ወያኔም የአማራ ህዝብን ዘለቄታዊ የአንድነት ትስስር የመረዳጃ የትግል መስመርም ይሆናል፡፡እንደ እኔ እይታ ይህ የትግል አደረጃጀት ካሉበት እንቅፋቶችና የስኬት ፍጥነት አንፃር ለሚጎትቱት በእነዚህ በተረዘርኳቸው ነጥቦች ላይ አመርቂ ውጤት ሊኖረው ይገባል፡፡

፩ኛ – ብቃት ያላቸው መሪዎችን መፍጠር
-ይህ መሰረታዊና የትግሉ ቁልፍ አካል ሲሆን አሁን ካለው በላይ በሁለገብ ሙያዎች የታቀፈ የአማራ ምሁራን ተሳትፎ በህብዑም ሆነ በግልፅ በቅርቡ ባለ አደረጃጀት ውስጥ መታቀፍ አለበት፡፡ያለ ቁርጠኝነትና ብቁ አመራር ትግሉ ስምረት አይኖረውም፡፡በዚህ ሂደት ውስጥ የግለሰቦቹ ተነሳሽነት ብቻ ሳይሆን አሁን ባሉ አደረጃጀቶች ግፊትና እንቅስቃሴ ጉልህ አስተዋፅኦ ሊኖረው ይገባል፡፡ጠንካራ አደረጃጀቶች ብቁ መሪዎችን ፤ብቁ መሪዎች ደግሞ አደረጃጀቶችን ማጠንከር መሰረታዊ ተግባራቸው መሆን ይኖርበታል፡፡መሰዋዕነትነት ለመክፈል የተዘጋጀ፤ ሃላፊነትን የሚቀበል መሪ መፍጠር ይገባል ያለ እነዚህ ስኬት አይመጣም፡፡

፪ኛ- የስነ ልቦና ጥገናና ዝግጁነት
– አማራ በዕሴቶቹ ስነ ልቦናውን ሚገነባባቸው ባህላዊ የሆኑ ልምዶቹን(ጃሎ ፣ስለላ ፤ቀረርቶ ፣ፉከራ) እንዳሉ ሆነው ያሉ አደረጃጀቶች ሁሉ ህዝቡ ላይ ስርዓቱ የነዛቸውን የማሸማቀቂያ እና የሞራል ድቀቶች በማህበረሰቡ ላይ የማንቃት ስራ መስራት ይኖርባቸዋል፡፡ለዚህ ያሉ የሚባሉ አማራጮች ከማህበራዊ መገናኛ ዘርፎች እስከ ኤሌክትሮ ሚዲያዎች በመጠቀም መስራት ይቻላል፡፡በተለይ ከአማራ ጥንተ ግዛቶች ውጭ የሚገኙ አማራዎች እና በሰፊው ወያኔ በአማራ ላይ ማህበራዊ ምህንድስና የሰራበት የሸዋ ክፍለ ሀገር ዋነኛው የትኩረት ነጥብ ነው፡፡ዛሬ በምናካሂደው የአማራ ብሔርተኝነት ከፍተኛ ትኩረት ያልተሰጣቸው ከአማራው አካባቢ ውጭ ያሉ አማራዎች እና የአማራ ደም ያለባቸው ነገር ግን ከአማራ አካባቢ ውጭ የተወለዱ ባህሉንም ቋንቋውም ሳያውቁ አማራነት ብቻ ሚሳደዱ ወገኖች ናቸው፡፡በእነዚህ አይነት ወገኖቻችን ላይ የደረሰውን ጉዳት ለመረዳት ወይ እነሱን ሆኖ መገኘት አልያም ጉዳት መረዳትና መስራት ያስፈልጋል፡፡በአንድ ጀንበር ያልተጎዳ ህዝብ በአንድ ጀንበር ከችግሩ አይላቀቅም፡፡በማንኛውም አማራጮች በትኛውም አደረጃጀት የዚህ ብሔርተኝነት አቀንቃኝ ከጠላቱ የተሻለ የስነ ልቦና የበላይነት መያዝ አለበት፡፡

፫ኛ -ፓለቲካዊ ንቃት ብሔርተኝነቱን በተመለከተ
– የፓለቲካ ንቃት በእየጊዜው ሊዳብርና ሊሻሻል እንደሚችል ሁሉ በዚህ ብሔርተኝነት ምህዋር ውስጥ የሚንቀሳቀስ ሁሉ ወጥና ተቀራራቢ ንቃት ሊኖረው ይገባል ስለሚታገለው ትግል፡፡ዘመናዊ ትምህርት ከተባው እስከ መለኮታዊ አተምሮ የተጠበበው ብሎም በመካከለኛ የትምህርት ደረጃ የሚገኘውም ሆነ ያልተማረው አርሶ አደሩ ስለሚታገለው ትግል መነሻ እና መድረሻ ጠንቅቆ ሊያውቅ ይገባል፡፡አለበዚያ ግን የዕውቀት ክፍተት የትግል ክፍተት ይፈጥራል፡፡በሙሁራን በኩል በዚህ ዘርፍ ከሌላው በተለየ መሬት የመረደ እንቅስቃሴ በማድረግ ክፍተቶችን በመድፈን አናፂ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡በሚታገሉት ትግል አደረጃጀት የሚኮሩ ፣የማይሸማቀቁ የሚታገሉለትን ህዝብና ጥቅም የሚያስከብሩ መሆን መቻል አለባቸው፡፡
በየትኛውም መንገድ ስለ እዚህ እውነተኛ ትግል ማስረዳት የሚችል ግንዛቤ መኖር አለበት፡፡

፬ኛ ጠንካራ የሰራዊት ግንባታ
– ብቁ መሪ ፣የስነ ልቦና ዝግጁት እና በተገነባ የፓለቲካ ንቃት መሰረት እና መመዘን የሚችል በአንድ ዕዝ የሚመራ ሰራዊት የትግሉ ዋስትና ነው፡፡ተቆርቋሪ እና ተከላካይ የሌለው ህዝብ ከጥፋት ሊከላከልተለት የሚችል መንገድ የለም፡፡የአማራ አደረጃጀት ሁሉ ትኩረት ሊያደርግበት የሚገባ የከበረ ጉዳይ ነው፡፡ጉልበት የሌለበት ፓለቲካ ምን ቢሆን ለድል ሩቅ ነው ፤እንደ አማራ ህዝብ ትግል ደግሞ ሰፊ ጉዳት ይኖረዋል፡፡ሚተኩስ ጠላት ይዞ በባዶ እጅ መታገል የዋህነት ከመሆን አልፎ ከአማራ የጥፋት ዘመኖች ውስጥ ሊመደብ የሚችል ትልቅ ጥፋት ያመጣል፡፡ ብቁና ሁለገብ ሰራዊት እና በአንድ የመስመር ፍሰት የሚወርድ የመረጃ እና ደህንነት አሰራር ሊኖረው ይገባል፡፡በዚህ ነጥብ ወደ ፊት በደንብ በሰፊው እመጣበታለው፡፡

፭ኛ ህዝባዊ ድጋፍ
– ከላይ በተጠቀሱት ነጥቦች ላይ የወረደ ትግል ለድል ለህዝብ ቅርብ ነው፡፡የህዝብን ጥያቄን የሚመልስ ትግል የህዝብ ድጋፍን ያገኛል፡፡የህዝብ ድጋፍ ያለው ትግል ደግሞ ያሸንፋል፡፡አንባገነን የሆነ ስርዓት የመጀመሪያው ውድቀት የምሁራንን ተቀባይነት ማጣትና ተቃውሞ እና የህዝብ ድጋፍ ማጣት ነው፡፡

የህዝብ ትግል ሁሌም ትክክል ሁሌም አሸናፊ ነው!!!

ለኢህአዴግ ግዜ ምኑ ነው? – ከተማ ዋቅጅራ

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ኢህአዴግ ከሚባል ድርጅት መጣ እንጂ በህዝብ ምርጫ አልመጣም። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ህውአት ሲጨንቀው አነገሰው እንጂ ህዝብ ፈቅዶ አልሾመውም። ባልተለመደ መልኩ የሚፈልጉትን አውርደው የማይፈልጉትን የመሾሙ ምስጢር ለአገርና ለህዝብ ታስቦ ሳይሆን በአገርና በውጪ የተነሳባቸውን የለውጥ ማእበል በዚህ መልኩ እናልፋለን ከሚል እሳቤ ነው። ዶክተር አብይ ከህዝብና ከአገር ክብር የድርጅቱን ክብር አስበልጦ ድርጅቴን እታደጋለው የሚል ከሆነ ድርጅት ሆኖ ይቀራል አልያም ለአገርና ለህዝብ ከሰራ ግን ህዝብ በክብር ማማ ላይ ያስቀምጠዋል። ዋናው ቁምነገር ኢህአዴግ ሊያውቁት የሚገባው በጥገናዊ ለውጥ የሚመለጥበት ግዜ ማለፉን ነው።
ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ በመጀመሪያ የሹመት ቀን ላይ በፓርላማው ንግግር አድርገዋል። ሲቀጥል በኦጋዴን፣ በአንቦ፣ በትግራይ፣ በጎንደር፣ በባህር ዳር፣ በአዋሳ እንዲሁም ከባለሃብቶች ጋርም ንግግር አድርጓል። አሁን የሚቀረው ከሙሁራን፣ ከሐይማኖት አባቶችና ከአገር ሽማግሌዎች ፣ ከውጪ ከሚኖሩ ኢትዮጵያኖች እና ከጋዜጠኞች ጋር ነው። ከነዚህ አካላት ጋር እንደሚወያይ ተስፋ አደርጋለው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፓርላማው ጀምሮ በሁሉም አካባቢ የተለያየ ይዞታዎች ነበሩት። በፓርላማው የሰማነው ንግግር ድንቅ ንግግር ነበር። በኢህአዴግአዊ ተቋም በ27 አመት ውስጥ ሰምተነው የማናውቀውን ኢትዮጵያዊነትን የሰማንበት እና ኢህአዴግአዊ  መዋቅር የፈረሰበት ኢህአዴግአዊ ምሽግ የተጣሰበት እውነተኛ ለህዝብና ለአገር የሚያስብ መሪ መናገር ያለበትን ንግግር ነበር የሰማነው።
ጠቅላይ ሚንስትሩ በመቀጠል በኡጋዴን የተጣላን እንታረቅ እኛ ስንዋደድ ጠላት ይሸነፋል በሚል እሳቤ የሱማሌ፣ የአማራ ፣ የኦሮሞ እና ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ እጅ ለእጅ በመያያዝ ፍቅራቸውን የገለጽበት።
በአንቦ የኦሮሞ ህዝብ ፍቅር እደሆነና የኢትዮጵያ ዋልታ እንደሆነ በመግለጽ ህዝቡ መሪውን ከቦ ፎቶ በመነሳት ለህዝብ ያለውን ፍቅር የገለጸበት እንደሆነ ተመልክተናል።
በትግራይ ያደረጉት ብስለት ያለው ንግግር ቢሆንም ትግራይን አመሰግናለው ብለው የአማራ ማህበረሰብን ያስቀየሙበት ህውአትን ለማስደሰት ብለው እውነትን የደፈጠጡበት በመሆኑ በትግራይ ያደረጉት ንግግር ሲጠቃለል ተለማማጭነትን ያሳዩበት አድር ባይነት የተንጸባረቀበት ክህውአቶች ውዳሴ ከንቱ የፈለጉበት ንግግር አድርገዋል።
በጎንደር ላጠፉት ጥፋት ይቅርታ ለመጠየቅ የሚችሉ መሪ መሆናቸውን እና ጥፋት ካለ ተቆንጥጠው አልያም ተመክረው መመለስ እንደሚችሉ ያሳዩበት ነበር።
በባህር ዳር ኢትዮጵያ ውስጥ መጠነ ሰፊ ችግር እንዳለ የተረዱበት እና ህዝቡ መከራው ከመብዛቱ የተነሳ ፍራቻን አስወግዶ ለመብቱ ፊለፊት በመጋፈጥ ሞትን እንኳን መፍራት ያቆበት ሰአት እንደሆነ የተረዱበት ሆኖ መጠነ ሰፊ ችግር እንዳለ አምነው ነገር ግን ችግሮቹ በአንዴ መፈታት ስለማይቻል ለመፍቴው ህዝቡ አብሮ እንዲሰራ ያመላከቱበ ነበር።
ከባለሃብቶች ጋር ያደረገው ንግግር ባለሃብቶቹ ወደስራ እንዲገቡና በውጭ ያሉትም መጥተው እንዲሰሩ የተናገሩ ሲሆን ከአገር ውጭ የተቀመጡ ዶላሮች ወደ አገር በማስገባት ሊሰሩባቸው እንደሚገባ ጠቅሰዋል። በአገሪቱ የዶላር እጥረት በከፍተኛ መከሰቱንም ጠቅሰዋል።
በአዋሳ ከፖለቲካው አለም ወጣ በማለት ሰባኪ ሆነው የተገኙበትንም ክስተት አይተናል። ነገ ደግሞ ከሙሁራኑ ጋር፣ ውጭ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጋር፣ እንዲሁም ከሐይማኖት አባቶችና ከአገር ሽማግሌዎች ጋር እንደሚወያዩ ተስፋ አደርጋለው።
ጠቅላይ ሚንስትሩ በተወሰኑ የኢትዮጵያ ክፍሎች በመዘዋወር ያደረጉት ንግግር ከህዝብ ጋር ለመቀራረብ ይጥቅማቸዋል እንጂ በራሱ የመፍቴ ሃሳብ ሊሆን ግን ከቶውን አይችልም። ኢትዮጵያውስጥ ያለው ችግር እንዲህ በቀላሉ የሚፈታ አይደለም ህውአት ስልጣኑን ለማቆየት ብለው የሰሩት ስህተት እራሳቸውን ጨምሮ በአገር ላይ ከፍተኛ አደጋ ጋርጠዋል። ስለዚህ በኢትዮጵያ በሁሉም አካባቢ አፋጣኝ የፖለቲካ መልሶች የሚሹ ወሳኝና አፋጣኝ እርምጃዎች መወሰድ አለባቸው።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በጣም የተጣበበ እና ግዜ የማይሰጥበት የመጨረሻው ምእራፍ ላይ ቢመጡም ቆራጥና ጀግና ከሆኑ ትልቅ የታሪክ እድል አግኝተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለአገርና ለህዝብ ታማኝ በመሆን እውነተኛ መሪነታቸውን ካሳዩ 100 ሚሊዮን ህዝብ ከጎኖ የሚያሰልፉበት በተገላቢጦሽ በመቆም አገርንና ህዝብን ክደው ህውአትን አገለግላለው የሚሉ ከሆነ 100 ሚሊዮን ህዝብን በእርሶላይ የሚያምጽበት ግዜ ነውና በሚወስዱት ፈጣንና ወሳኝ እርምጃዎች ህዝብና እገርን የመታደጉ ስራን በመስራት የሚፈተኑበት የመጨረሻው ግዜ ላይ ኖት። ግዜ የማይሰጣቸው ግን ደግሞ በጣም ወሳኝ የሚባሉትን ውሳኔዎችን ጠቆም አድርጌ ልለፍ። ውሳኔዋችን በአፋጣኝ ባለመውሰዶ ህዝብ ውስጥ የተዳፈነው እሳት ከፈነዳ ያኔ የእርሶም ታሪክ የመስሪያ ግዜ ያበቃለታል በጥልቀት ማሰብና በፍጥነት የሚሰራበት ሰአት ለይ ነው። አፋጣኝ ውሳኔዎች ከሚያስፈልጋቸ የመጀመሪያዎቹ እና ግዜ የማይሰጣቸው…….
1. ኢትዮጵያ ውስጥ ከጠቅላይ ሚንስትሩ ትእዛዝ ውጪ ማንም እየተነሳ ህዝብን የሚያስርና ህዝብን የሚገድሉ አካላቶችን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአዋጅ በማስቆም በግለሰብ ደረጃ ወታደርና እስር ቤት ያላቸውን አካላቶች ምንም አይነት በህዝብና በአገር የሚያደርሱትን ጥፋት በማስቆም ለህዝባችን ዋስትና መስጠት። ወንጀል የሰሩት በሙሉ በህግ እንዲጠየቁ ማድረግ።
2. ኮማንድ ፖስት የሚባለው አካል የህዝብንና የአገር ደንነት ለመጠበቅ የተቋቋመ ሳይሆን በስልጣን ላይ ያሉትን ግለሰብን እና ፖርቲያቸውን ለመታደግ የታለመ ስለሆነ ለአገር ደህንነትና ለህዝብ ሰላም የሚያስቡ ከሆነ በአዋጅ እንደጸደቀው በአዋጅ መሻር አለበት። ከእንግዲህም በኋላ ህዝብንና አገርን ለአደጋ የሚያጋልጡ የሞት አዎጆች እንደማይታወጁ ለህዝብ ዋስትና መስጠት።
3. በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት ባንኮች በሙሉ ላልተወሰነ ግዜ ብድር እንዳይሰጡ በአዋጅ መከልከል። ገቢና ወጪአቸውን በማስላት ለመንግስት እንዲያሳውቁ ማድረግ። በአገር ቤት የታተሙ ሃሰተኛ ብሮችን ከትክክለኛው በመለየት እንዲሰበሰቡ ማድረግ። ህዝቡምን በሃሰተኛ የብር ኖቶች ንብረቱን ተታሎ እንዳይሸጥ መግለጫ በማውጣት የተበላሸውን የባንክ አሰራር በማጥራት ወደትክክለኛው የባንክ አሰራር በመመለስ አስተማማኝ የባንክ አሰራር እንዲኖር ማድረግ።
4. ደንነቱን፣ መከላከያውን ፣ የመገናኛ አውታኖችን፣ የእገር ውስጥና የውጭ ንግድ እንቅስቃሴን፣ ከዝቅተኛ እስከ ከፍተኛ የመንግስ ተቋማት የመሳሰሉት በሙሉ ለቦታው የሚመጥንና ለአገርና ለህዝ አሳቢ የሆኑትን በአፋጣኝ መሾም ያስፈልጋል። ይህ ትክክለኛ ሹመት ከሆነ የህዝብን  ቁጣ ሊያስታግስ ይችላል። ካለበለዛ ግን ግዜው ያበቃና መቀልበሻው ያጥሮታል።
ሳጠቃልለው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ እየተዘዋወሩ ንግግር ማድረግና የህዝቡን ሃሳብ መስማት ጥሩ ቢሆንም ይሄ ግን የመፍቴው አካል አይደለም። መፍቴ ሊሆን የሚችለው ችግሮችን በፍጥነት መፍታት ብቻ ነው። ስለዚህ ለኢአዴግ የሚሰጥ ግዜ የለም።
ከተማ ዋቅጅራ
29.04.2018

ግልጽ ደብዳቤ – ክቡር ዶ/ር አቢይ አሕመድ (ትብብር)

ይድረስ ለኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር

ክቡር ዶ/ር አቢይ አሕመድ

ትብብር የተሰኘው የ ፳፮ የኢትዮጵያ ማኅበረ-ሰባዊ ድርጅቶች ማዕከል፤ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትርነትን ቦታ በመያዝዎ የደስታ መልዕክቱን ያስተላልፋል።

የጠቅላይ ሚኒስቴር ስልጣን በተረከቡበት ዕለት በንግግርዎ “ዲሞክራሲ ያለነጻነት አይታሰብም” ማለትዎን፤ በጽንሰ-ሃሳብ ደረጃም ቢሆን፤ አቀራረብዎ ለዘመናት የኢትዮጵያ ሕዝብ ሲመኝ የነበረውን የነጻነት ተስፋ ጭላንጭል የሚከፍት ሆኖ አግኝተነዋል።

በነጻነት መኖርን በመፈለግ፤ በሺ የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ተሰደዋል፤ ታስረዋል፤ ተሰውተዋል እንዲሁም በመላው አለም ተበታትነዋል። ከሚሊየን በላይ የሚገመቱ ወገኖቻችን ከቀያቸው ተፈናቅለዋል። ቁጥራቸው በቅጡ ባይታወቅም፤ በየቀኑ ብዙ ወጣቶች ከአገራቸው መሰደዳቸው ቀጥሏል።

“ዲሞክራሲ የለነጻነት አይታሰብም” ብለው ያስቀመጡት አቢይ አነጋገር፤ በተግባር ሊፈጸም ይችል ዘንድ የአስተዳደርዎ ተቀዳሚ መርህ እንደሚሆን ተስፋ እናደርጋለን። ወደ ዲሞከራሲ የሚደረገው ጉዞም የሚከተሉትን ተግባራት ሊያጠቃልል ይገባል ብለን እናምናለን፤–

1. በኢትዮጵያውያን ላይ የተደነገገውን ጊዜያዊ አዋጅ በፍጥነት ማንሳት
2. ሁሉንም የፖለቲካ እስረኞች ያለ ቅደመ-ሁኔታ መፍታት
3. ከዚህ ቀደም “ሽብርተኞችን መከላከል” በሚል ሽፋን፤ በጋዜጠኞች፤ በበጎ አድራጎት ድርጅቶች እና በሰላማዊ ተቃዋሚዎች ላይ የተጫኑትን “ሕግጋት” በአስቸኳይ መሻር
4. በግፍ ሰላማዊውን ሕዝብ የገደሉ፤ ያቆሰሉ እና ያፈናቀሉ ግለሰቦችንም ሆነ ተቋሞችን ለፍርድ በማቅረብ ከፍትሕ ጎን መቆም
5. በመላው ኢትዮጵያ፤ ኢትዮጵያውያን በግለሰብም ሆነ በድርጅት በነጻነት በመንቀሳቀስ ብሔራዊ ውይይት የሚያደርጉበትን ጎዳና መጥረግ፤ መድረኩንም ማምቻቸትና ሕዝቡ የፖለቲካ ሥልጣኑ ባለቤት እንዲሆን ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ እንዲካሄድ ሁኔታዎችን ማመቻቸት።

ከዚህ በላይ ያሉት ከብዙው ጥቂቶቹ አሰራሮች ተአመኔታ ከመስጠት ባሻገር ለሃገራችን ዲምክራሲያዊ ግንባታ አስተዋጽዖ ያደርጋሉ ብለን እናምናለን። ከዚህ ባነሰ የሚደረጉ ጥገናዊ እርምጃዎች፤ በንግግርዎ ያቀረቡትን ፅንሰ-ሃሳብ ግብር-አልባ ከማድረጉ ሌላ የኢትዮጵያን ሕዝብ ትግል ላማጨንገፍ እና ያለውን ስርአት እድሜ በሌላ አቀራረብ እንዲቀጥል ለማድረግ የታሰብ ዕኩይ እርምጃ ያስመስለዋል።

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር

ለእርስዎ የጠቅላይ ሚኒስቴር ቦታ ማግኘት፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ትግል፤ በተለይ የወጣቱ ትውልድ መስዋዕትነት፤ አስተዋፅዖ እና ውጤት ነው ብለን እናምናለን። ጥንካሬዎ ሊገነባ የሚችለው በኢትዮጵያ ሕዝብ ድጋፍና መልካም ፈቃድ መሆኑን በማመን አገልግሎትዎ ከልብ የሕዝብን ጥቅም ያማከለ ብቻ ሊሆን እንደሚገባው እናሳስባለን።

የኢትዮጵያ ሕዝብ በአንክሮ የዕለት በዕለት እርምጃዎን በማየት ላይ ነው። ፊትዎን እንደማያጥፉበት ተስፋ እናደርጋለን።

እግዚአብሔር ከርስዎ ጋር ይሁን

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይጠብቅ

በትሩ ገብረእግዚአብሔር፤
የትብብር ሊቀመንበር፤

ዶናልድ ያማማቶ ከዶ/ር መረራ ጉዲና፣ በቀለ ገርባ፣ አንዱአለም አራጌ፣ እስክንድር ነጋ ጋር ሰፊ ውይይት አደረጉ

በኢትዮጵያ ጉብኝት እያደረጉ ያሉት በስቴት ዲፓርትመንት የአፍሪካ ጉዳይ ሃላፊ ዶላንድ ያማማቶ ስለሀገሪቱ ወቅታዊ ፖለቲካ እንዲሁም ዲሞክራሲ ዕውን እንዲሆን ምን መደረግ አለበት? በሚለው ዙሪያ ከዶ/ር መረራ ጉዲና ፣ኦቦ በቀለ ገርባ ፣አንዱአለም አራጌ፣ እስክንድር ነጋ ጋር ሰፊ ውይይት ማድረጋቸውን ጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል ምንጮቿን ጠቅሳ ዘግባለች።

አምባሳደሩ በቀጣይ ከጠ/ሚ/ር ዶ/ር አብይ ጋር እንደሚነጋገሩ ለማወቅ ተችሏል።በስብሰባው ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ የአሜሪካ አምባሳደር የሆኑት ማይክ ሬነር ተገኝተው ነበር።

ስለውይይቱ ተጨማሪ መረጃዎች እንደደረሱን ይዘን እንቀርባለን::

“EFFORTን” መውረስ የኢኮኖሚውን ጥገኛ ተውሳክ እንደማስወገድ ነው!

ስዩም ተሾመ

ትላንት በፌስቡክ ገፄ ላይ የትእምት (EFFORT) ድርጅቶች በመንግስት መወርስ እንዳለባቸው ለመጠቆም ሞክሬ ነበር። ለዚህ ያቀረብኳቸው ምክንያቶችና ማስረጃዎች እንዳሉ ሆነው እነዚህን ድርጅቶች መውረስና ወደ ግል እንዲዘዋወሩ ማድረግ ምን ፋይዳ አለው?፣ በሀገሪቱ ፖለቲካና ኢኮኖሚ ላይ ምን ዓይነት አሉታዊ ሆነ አዎንታዊ ተፅዕኖ ሊፈጥር ይችላል? እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን በዝርዝር መመልከት ያስፈልጋል። በቅድሚያ ግን ስለ ትእምት (EFFORT) ድርጅቶች አጠቃላይ ባህሪ የተወሰነ ግንዛቤ ሊኖረን ይገባል። ለዚህ ደግሞ ከትእምት (EFFORT) ድርጅቶች የሞሶቦ ሲሚንቶ ፋብሪካን እንደ ማሳያ በመውሰድ እንመልከት።

በመቐለ ዩኒቨርሲቲ በቢዝነስ አመራር ሙያ (Business Administration) የሁለተኛ ድግሪ ትምህርት በምማርበት ወቅት “Operation Management” የሚባለውን ኮርስ ያስተማረኝ አንድ የውቅሮ ተወላጅ የሆነ መምህር ነው። ይህ ስሙን የማልጠቅሰው መምህር የሞሶቦ ሲሚንቶ የገበያ ስትራቴጂን እንደ ምሳሌ በመጥቀስ የተናገረው ነገር መቼም ከአዕምሮዬ አይጠፋም። ነገሩ እንዲህ ነው፤ የሞሶቦ ሲሚንቶ በመቐለ ከተማ የሚሸጥበት ዋጋ በአዲስ አበባ ከሚሸጥበት ዋጋ በሁለት ብር ይበልጣል። በዚህ መሰረት የሞሶቦ ሲሚንቶ መቐለ ላይ 300 ብር የሚሸጥ ከሆነ ከፋብሪካው 700 ኪ.ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው አዲስ አበባ ደግሞ 298 ብር ይሸጣል። ይህ “dumping” እንደሚባልና ሕገ-ወጥ ተግባር መሆኑን ስናገር መምህሩና የአከባቢው ተወላጅ የሆኑ ተማሪዎች በሙሉ ¨No” በማለት በአንድ ድምፅ ተቃወሙኝ። ቀጠልኩና “እሺ.. የመቐለ ከተማ ሲሚንቶ ተጠቃሚዎች ያለ አግባብ በድርጅቱ እየተበዘበዙ ነው” ስላቸው አሁንም በአንድ ተቃወሙኝ። በመጨረሻም መምህሩ ያነሳሁትን ጥያቄ ሆነ ሃሳብ በሚያጣጥል መልኩ “ይህ የሞሶቦ ሲሚንቶ የገበያ ስልት (Market Strategy) ነው” በማለት በተግሳፅ ተናገረኝ።

በመሰረቱ የሲሚንቶ ፋብሪካ ምርቱን የሚሸጥበት ገበያ ከ300 ከ.ሜትር በላይ የሚርቅ መሆን እንደሌለበት የዘርፉ ምሁራን ይገልፃሉ። ምክንያቱም ሲሚንቶ በባህሪው ከባድ (Bulky) ምርት ስለሆነ ከ300 ኪ.ሜ በላይ በትራንስፖርት አጓጉዞ መሸጥ ለከፍተኛ የትራንስፖርት ወጪ ይዳርጋል። ሞሶቦ ሲሚንቶ ግን ምርቱን በመኪና 700 ከ.ሜ ርቀት ላይ ወደምትገኘው አዲስ አበባ አምጥቶ መቐለ ላይ ከሚሸጥበት ዋጋ የሁለት ቅናሽ አድርጎ ይሸጣል። በዚህ መሰረት፣ አንደኛ፡- ሞሶቦ ሲሚንቶ ምርቱን አዲስ አበባ ድረስ ወስዶ የትራንስፖርት ወጪውን ሳይጨምር በሁለት ብር ቅናሽ መሸጡ በሕገ-ወጥ ተግባር እንደተሰማራ ያሳያል፣ ሁለተኛ፡- መቐለ ላይ ያለው የሞሶቦ ሲሚንቶ መሸጫ ዋጋ ከአዲስ አበባው የመሸጫ ዋጋ በሁለት ብር የሚበልጥ ከሆነ ድርጅቱ የከተማዋን ነዋሪዎች ያለአግባብ እየበዘበዘ መሆኑን ያሳያል።

ከላይ በተጠቀሰው መሰረት፣ ሞሶቦ ሲሚንቶ የሚከተለው የገበያ ስልት (Market Strategy) ከሕግም ሆነ ከቢዝነስ አንፃር ፍፁም የተሳሳተ ነው። ከሕግ አንፃር የሞሶቦ የገበያ ስልት ሌሎች የሰሚንቶ ፋብሪካዎችን ቀስ በቀስ ከገበያ በማስወጣት የምርቱን ገበያ በበላይነት ለመቆጣጠር ያለመ ነው። ከዚህ በተጨማሪ፣ በአከባቢው ማህብረሰብ ላይ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ በማድረግ ይበዘብዛል። እንዲህ ያለ የገበያ ስልት የድርጅቱን ተወዳዳሪነት ከማሳደግ ይልቅ ለኪሳራ ይዳርገዋል። ይሁን እንጂ ነባር የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ከገበያ ከመውጣት ይልቅ ብዛት ያላቸው አዳዲስ ፋብሪካዎች ተከፈቱ። የሞሶቦ ሲሚንቶ ፋብሪካም በሚፈለገው ደረጃ ተወዳዳሪ ባይሆንም እንኳን በኪሳራ ምክንያት ከገበያ አልወጣም። ለምን?

አስታውሳለሁ… ደርባ ሲሚንቶ ወደ ገበያ በገባበት ወቅት በሀገራችን ከፍተኛ የሆነ የሲሚንቶ ምርት እጥረት ተከስቶ ነበር። በተመሳሳይ በመቐለ ከተማ ነዋሪዎች የሲሚንቶ ምርት ለመግዛት ለብዙ ቀናት ወረፋ የሚጠብቁበት ወቅት ነበር። በዚህ ወቅት ነው እንግዲህ ደርባ ሲሚንቶ ምርቱን በራሱ ትራንስፖርት ለመቐለ ከተማ ተጠቃሚዎች እንደሚያቀርብ ያስታወቀው። ይህን ተከትሎ አብዛኞቹ ሲሚንቶ ፈላጊዎች ከድርባ ሲሚንቶ ጋር የግዢ ስምምነት ማድረግ የጀመሩት። በዚህ ምክንያት በወረፋና በሰልፍ ሲንያንገላታቸው የነበረውን ሞሶቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ ዞር ብሎ የሚያየው ጠፋ።

ሞሶቦ የትእምት (EFFORT) አባል ድርጅት እንደመሆኑ መጠን ዋና ስራ አስኪያጁ ከፍተኛ የህወሓት ባለስልጣን ነው። ይህ ባለስልጣን ለኢትዮጲያ ንግድ ባንክ መቐለ ቅርጫፍ ዋና ስራ አስኪያጅ ቀጭን ትዕዛዝ አስተላለፈ። ትዕዛዙም “በሞሶቦ ሲሚንቶ ላይ ፊታቸውን በማዞር ከደርባ ሲሚንቶ የግዢ ውል ለሚገቡ የመቐለ ከተማ ነዋሪዎች የባንክ ሲፒኦ (CPO) እንዳይሰጣቸው” የሚል ነበር። በዚህ መልኩ በህወሓት ከፍተኛ ባለስልጣናት ጣልቃ-ገብነት ምክንያት ሞሶቦ ሲሚንቶ የተሳሳተና ሕገ ወጥ የሆነ የገበያ ስልቱን ይዞ እንዲቀጥል ያደርጉታል።

ስለዚህ እንደ ሞሶቦ ሲሚንቶ ያሉ የትእምት (EFFORT) ድርጅቶችን መውረስና ወደ ግል እንዲዘዋወሩ ማድረግ ምን ፋይዳ አለው?

  • 1ኛ፡- የትእምት (EFFORT) ድርጅቶች የሀገሪቱን ኢኮኖሚ በበላይነት ለመቆጣጠር በሚከተሉት ስልት ምክንያት በተለያዩ የቢዝነስ ዘርፎች የሚያሳድሩትን አሉታዊ ተፅዕኖ ማስወገድ ይቻላል። በዘርፉ የሚታየውን የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት ያስቀራል። በመሆኑም በዘርፉ አዳዲስ የቢዝነስ ተቋማት እንዲሰማሩ ያስችላል። እንዲሁም የሀገር ውስጥና የውጪ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ምቹ ሁኔታ ይፈጠራል። 
  • 2ኛ፡- ድርጅቶቹ ወደ ግል ሲዘዋወሩ በምርት ዋጋና ጥራት ተወዳዳሪ የሚያደርጋቸውን የገበያ ስልት ይቀይሳሉ። በመሆኑም ምርቶቻቸውን ለአከባቢው ማህብረሰብ በተመጣጣኝ ዋጋ ያቀርባሉ። ከዚህ በተጨማሪ፣ በገበያው ውስጥ ተወዳዳሪና ትርፋማ ስለሚሆኑ ለአከባቢው ማህብረሰብ ሆነ ለሀገሪቱ አሁን ካለው በተሻለ ሁኔታ ተጨማሪ የሥራ እድል ይፈጥራሉ።  
  • 3ኛ፡- የትእምት (EFFORT) ድርጅቶችን ወደ ግል በማዘዋወር መንግስት ገንዘብ ያገኛል። በዚህ መሰረት፣ በመሰረተ-ልማት ግንባታ አስተዋፅ ከማበርከቱ በተጨማሪ ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍልን ከማረጋገጥ አንፃር የራሱ የሆነ ሚና ይኖረዋል። 

ከላይ በተገለፀው መሰረት፣ መንግስት የትእምት (EFFORT) ድርጅቶችን በመውረስ ወደ ግል ባለሃብቶች ማዘዋወሩ የህወሓት ባለስልጣኖች እያገኙት ያለውን ያልተገባ ጥቅም ያስቀራል። እነዚህ ድርጅቶች ቢወረሱ የሚጎዱት የተወሰኑ የህወሓት አመራሮች እና አባላት ናቸው፡፡ ከዚያ በተረፈ ግን እንደ ክልል የትግራይ ሕዝብ ይጠቀማል፡፡ እንደ ሀገር ደግሞ ለኢትዮጲያ የተሻለ ነገር ይዞ ይመጣል። ሌላው ቢቀር የህወሓትን አድሏዊ ድጋፍ፥ ማጭበርበርና ኪራይ ሰብሳቢነት ያስቀራል፡፡ በአጠቃላይ “EFFORTን” መውረስ ከሀገሪቱ ኢንዱስትሪ ውስጥ ጥገኛ ተውሳክን እንደማስወገድ ነው፡፡ እነዚህ ድርጅቶች እስካሁን ባሉበት ሁኔታ በኢኮኖሚው ውስጥ ከጥገኛ ተውሳክ የተለየ ሚና የላቸውም፡፡

በመጨረሻም፣ አንዳንድ የትግራይ ልሂቃን “የትእምት (EFFORT) ድርጅቶች የሚወረሱት በእኛ መቃብር ላይ ነው” የሚል አቋም የሚያራምዱበትን በተመለከተ ቀደም ሲል የጠቀስኩትን መምህርና ተማሪዎች ማስታወስ ይበቃል። እንኳን የትግራይ ሕዝብን ጥቅምና ተጠቃሚነት የሚማሩትን ሆነ የሚያስተምሩትን ፅንሰ-ሃሳብ መገንዘብ የተሳናቸው ስለመሆናቸው ጥርጥር የለውም።

ይድረስ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ

~”በእስር ቤት አንድም ቀን አሳልፈው ስለማያውቁ የእስር ቤት ሕይወት ይገባዎታል ብለን አንደፍርም። በማንነታቸው………በማያምኑበትና ባልፈፀሙት ታስረው፣ በምርመራ ወቅት አሰቃቂ ግፍ ደርሶባቸው፣ አካላቸው ጎድሎ፣ የዘር ፍረያቸውን እየተኮላሸ መሃን የሆኑ፣ ወገባቸው፣ እጅና እግራቸው ተሰብሮ፣ አካለ ስንኩል የተደረጉ ያለ ማስረጃ በሀሰት ምስክር እየቀረበባቸው በእስር ላይ ይገኛሉ። አይጥ፣ ትኋንና ቁንጫ ጋር ተገደው ዝምድና ፈጥረው በእስር አስከፊ ሕይወት ይመራሉ።

~”ይህ የተማረረ ሕዝብ በንግግር እና “ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ተደርጓል” ስለተባለ የሚሸነገል ከመሰለዎት ከፍተኛ ስህተት ውስጥ እየተዘፈቁ እንደሆነ ግልፅ ነው። በአንፃሩ በአስቸኳይ ወደ ተግባር ከገቡ ተስፋ ያደረገብዎት ሕዝብ ከጎንዎት እንደሚቆም አያጠራጥርም።”

~”………በአንድ ወር ውስጥ መፍታት አለመቻልዎት ለምን ይሆን? የጥያቄዎቹን አንጋብጋቢነት አልተረዱትም ይሆን? እየዞሩ በሚያደርጓቸው ስብሰባዎች ምክንያት ጊዜ አጡ? እርስዎ ሳይሆኑ፣ የድሮዎቹ አሳሪና ፈችዎች አሁንም አሳሪና ፈችዎች ናቸው? አሁንም እርስዎ ሳይሆኑ አዛዦቹ እነ ጌታቸው አሰፋ ናቸው?”

(ከህሊና እስረኞች የተላከ)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ ሆይ!

የእርስዎም ሆነ በአካባቢዎ ያሉ ግለሰቦችን ሚና ባይናቅም አሁን ለተቀመጡበት ወንበር ያበቃዎት ሕይወታቸውንና አካላቸውን ያጡ፣ በእስር ላይ የሚገኙ፣ ለሀገራቸው ሲሉ በሰው ሀገር የሚንከራተቱት ኢትዮጵያውያን የከፈሉት መስዋዕትነት መሆኑ የሚዘነጋ አይደለም። ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ያደረጓቸው አንዳንዶቹ ንግግሮች ሕዝብ ተስፋ እንዲጥልብዎ አድርገዋል። ነገር ግን ትዝብት ውስጥ የሚከትቱ ጉዳዮችም አሉ። ለምሳሌ:-

1) የኢህአዴግ መንግስት ስለ ዲሞክራሲ ሲያወራ 27 አመቱ በጣም ጥቂት ጊዜ ስለሆነ ገና ታዳጊና እየተለማመድን ስለሆንን በትግስት ተጠባበቁ የሚባለው

2) 10 የስኳር ፋብሪካዎች እና ሌሎች ትልልቅ ፕሮጀክቶች ለብረታብረትና ኢንጅነሪንግ ኮርፖረሽን (ሜቴክ) ተሰጥቶት ነበር። ብዙ ሚሊዮን ዶላር ከስሯል። ነገር ግን ማንም ተጠያቂ አይደለም ብለው በፓርላማ ተናግረዋል።
3) ደረቅ ሕግ ያለ ፍትሕ ሊሰራ እንደማይችል ደጋግመው ተናግረዋል። በፍትህ እጦት ሕዝብ ተቸግሯል። አስቸኳይ ፍትሕ ያስፈልጋል ብለዋል። ሆኖም የብዙ ሀገራት መሪዎች ለውጥ ሲያደርጉ አስቸኳይ ውሳኔዎችን ያስተላልፋሉ።

እርስዎ በእስር ቤት አንድም ቀን አሳልፈው ስለማያውቁ የእስር ቤት ሕይወት ይገባዎታል ብለን አንደፍርም። ዛሬ በማንነታቸው፣ በአመኑበት ሕጋዊ የፖለቲካ አቋም፣ በማያምኑበትና ባልፈፀሙት ታስረው፣ በምርመራ ወቅት አሰቃቂ ግፍ ደርሶባቸው፣ አካላቸው ጎድሎ፣ የዘር ፍረያቸውን እየተኮላሸ መሃን የሆኑ፣ ወገባቸው፣ እጅና እግራቸው ተሰብሮ፣ አካለ ስንኩል የተደረጉ ያለ ማስረጃ በሀሰት ምስክር እየቀረበባቸው በእስር ላይ ይገኛሉ። አይጥ፣ ትኋንና ቁንጫ ጋር ተገደው ዝምድና ፈጥረው በእስር አስከፊ ሕይወት ይመራሉ።

በኢህአደግ ስራ አስፈላሚ ስብሰባ የህሊና እስረኞ እንዲፈቱ መስማማታችሁ ተገልፆ ነበር። በውሳኔው መሰረት ይህ ጉዳይ በሁለት ወር ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ ነበር። እስካሁን ለምን ሁሉም የህሊና እስረኞች አልተፈቱም? የህሊና እስረኞችን ለመፍታት እና ጊዜያዊ አዋጁን ለማንሳት አንድ ቀጭን ትዕዛዝ በቂ መሆኑ ግልፅ ነው። ታዲያ ሕዝባችን አንገብጋቢ ብሎ ያስቀመጠውን ችግር በአንድ ወር ውስጥ መፍታት አለመቻልዎት ለምን ይሆን? የጥያቄዎቹን አንጋብጋቢነት አልተረዱትም ይሆን? እየዞሩ በሚያደርጓቸው ስብሰባዎች ምክንያት ጊዜ አጡ? እርስዎ ሳይሆኑ፣ የድሮዎቹ አሳሪና ፈችዎች አሁንም አሳሪና ፈችዎች ናቸው? አሁንም እርስዎ ሳይሆኑ አዛዦቹ እነ ጌታቸው አሰፋ ናቸው? ወይንስ እርስዎም ከሚናገሩት በተቃራኒ ያልተቀየረው ኢህአዴግ ነዎት?

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ ሆይ፣ ስርዓቱ እንዳልተቀየረና የመቀየር ምልክትም እንዳላሳየ አንዳንድ ማሳያዎችን እንጥቀስ:_
1ኛ ፍርድ ቤቶች አሁንም፣ አቃቤ ሕግ ምስክር አልመጣልኝም ስላለ ብቻ በተደጋጋሚ ቀጠሮ እየሰጡ የህሊና እስረኞችን እያመላለሱ ነው። አቃቤ ሕግ ምስክር አላገኘሁም እያለና በሌሎች ሰበቦች ፍርድ ቤት በ101 ጊዜ ቀጠሮ የሰጠውና እየተመላለሰ ያለ እስረኛ ቂሊንጦ ውስጥ ይገኛል። ከ15 እስከ 25 ጊዜ መቀጠር የተለመደ ነው።

2ኛ ተከሳሾች ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ለማረሚያ ቤት ተደውሎ “ተከሳሾችን ዛሬ እንዳታቀርቧቸው፣ ቀጠሯቸውን በጉዳይ አስፈፃሚ እንልካለን” ይባላል። ለአብነት ያህልም በቂሊንጦ ቃጠሎ ሰበብ የተከሰሱት 38ቱ ተከሳሾች ለመጨረሻ ጊዜ በሚል ለሚያዝያ 16 ቀጠሮ ተሰጥቶ ቤተሰቦቻቸውና ጠበቆቻቸው በፍርድ ቤት ተገኝተው ተከሳሾች አልተገኙም። ፍርድ ቤቱ ብይኑን ሰርተን አልጨረስንም በሚል ለሚያዝያ 30 ባልተገኙበት ቀጠሮ ሰጥቷል።

ዶ/ር አብይ ሆይ!

በአምቦ የተደረገው ሰልፍ፣ በጎንደር የተሰማው ጉምጉምታን በአንክሮ አይተው ትምህርት ካልወሰዱ ከእርስዎ ቀድመው የነበሩት ላይ የደረሰው እርስዎም ላይ ገና ወንበሩ ሳይደምቅ እንደሚደገም እንዳይጠራጠሩ። ይህ የተማረረ ሕዝብ በንግግር እና “ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ተደርጓል” ስለተባለ የሚሸነገል ከመሰለዎት ከፍተኛ ስህተት ውስጥ እየተዘፈቁ እንደሆነ ግልፅ ነው። በአንፃሩ በአስቸኳይ ወደ ተግባር ከገቡ ተስፋ ያደረገብዎት ሕዝብ ከጎንዎት እንደሚቆም አያጠራጥርም።

ማስታዋሻ ቁጥር 2፡ ሕዝብን ለሚያዳምጡ መልካም መሪዎች እውነትን እንዴት መናገር እንደሚቻል

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

Memorandum No. 2

የጸሐፊው ማስታዋሻ፣ ላለፉት ጥቂት ሳምንታት በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ላይ የተሰነዘሩ አሳማኝ ያልሆኑ እና ኃላፊነት የጎደላቸውን ትችቶች ሳነብ እና ስሰማ ቆይቻለሁ፡፡ አብዛኞቹ በእርሳቸው ላይ ትችት የሚያቀርቡት እ.ኤ.አ በ1970ቹ በወጣትነት ጊዚያቸው ተጣብቀውበት ከነበረው የበከተ የፖለቲካ አስተሳሰብ እና ምንም ዓይነት ዴሞክራሲያዊ የለውጥ አስተሳሰብ የሌላቸው የሻገተ አስተሳሰብ በማራመድ ተቸክለው የቀሩ እንደ እኔ ያሉ የጉማሬው (የቀድሞው ትውልድ) አባላት ናቸው፡፡

እነዚህ ከግጭቱ ተርፈው በመኖር ላይ ያሉት ጥቂቶች ጉማሬዎች ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ደስታ በተቀላቀለበት መልኩ እየደገፍኩ መሆኔን እንድተው ይመክሩኛል፡፡ ቀጣይነት ባለው ሁኔታ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን እየደገፍኩ መሆኔ እስከ አሁን ድረስ በአንባቢዎቸ ልብ ውስጥ ገንብቸው የነበረውን የታማኝነትን መንፈስ ላጣው እንደምችል ይናገራሉ፡፡

እነዚህ ውንጀላዎች የተለመዱ እየሆኑ መጥተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የህወሀት ሰው እና አሻንጉሊት ነው ይላሉ፡፡ አገዛዙ በስልጣን ላይ እንደ መዥገር ተጣብቆ ለመቆየት እንዲችል የሚያደርግ የህወሀት ድብቅ መሳሪያ ነው ይላሉ፡፡ ህወሀት ጠንካራ እና አይበገሬ ሆኖ እንደገና እስኪመለስ ድረስ ጊዜ ለመሸመት እና ወንበር እያሟሟቀ የሚቆይ ሰው ነው ይላሉ፡፡ እንዲያውም አንድ ሰው ከዚህም ባለፈ መልኩ በእነዚህ ባለፉት አስርት ዓመታት ሰምቸው የማላውቀው ቃል “የውጭ ሰላይ” ነው በሚል ይገልጸዋል፡፡ ሰውን ማሳመን የሚችል አንደበተ ርትኡ እና አስመሳይ ነው ይላሉ፡፡

የእነዚህን አባባሎች እውነትነት በማስረጃ ለማስደገፍ እንዲቻል ጥያቄ በማቀርብበት ጊዜ ምንም ነገር የለም፡፡ ዝም ብለው በደፈናው “ወያኔዎች ምን ያህል አታላዮች እና ብልጦች እንደሆኑ አንተ አታውቅም፡፡ እነርሱ ሰይጣኖች ናቸው እያሉ ይነግሩኛል”፡፡

በህወሀት ላይ ያሉኝ አመለካከቶች በሚገባ የሚታወቁ ናቸው፡፡ ሆኖም ግን በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ እና በኦቦ ለማ መገርሳ አዎንታዊ እና አነሳሳሽ መልዕክቶች ምክንያት ሃሳቤን ቀይሪያለሁ፡፡ ስለህወሀትም ቢሆን፡፡ ሁላችንም መልካም ሰዎች እና ሰይጣኖች ነን፡፡ ዶ/ር ማርቲን ሉተር እንዲህ በሚል አሳስበዋል “በመጥፎዎቻችን መካከል ጥቂት መልካም ሰዎች ይኖራሉ፡፡ እንደዚሁም ሁሉ መልካም በሆንን ሰዎች መካከል ጥቂት ሰይጣኖች ይኖራሉ“ ነበር ያሉት፡፡ ይህንን እውነታ በምንገነዘብበት ጊዜ ጠላቶቻችንን መጥላትን እንቀንሳለን፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ኃጢያቶች ዝም ብሎ በደፈናው ጥፋተኛ ናቸው የሚል ነው፡፡ በአገዛዙ ውስጥ ሆነው በወታደራዊ እና በሲቪል የኃላፊነት የስራ መደቦች የማገልገላቸው እውነታ በፖለቲካ አገልግሎት ዘላለማዊ ኃጢያተኛ አድርጎ አስፈርጇቸዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ያዋቀሩት ካቢኔ የእርሳቸውን የውድቀት ዕጣ ፈንታ የሚያመላክት ምልክት ነው ይላሉ፡፡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ማንሳት አለባቸው ይላሉ፡፡ ሆኖም ግን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ቢያነሱት ደግሞ ውሸት ነው ይህ ለታዕይታ ነው ይላሉ፡፡ የሚቀጥለው ሀገር አቀፍ ምርጫ ነጻ፣ ፍትሀዊ እና ተወዳዳሪነትን ያካተተ ይሆናል ብለው ሲናገሩ ደግሞ ለማታለል ነው በማለት ጨለምተኛ አስተሳሰባቸውን ያቀርባሉ፡፡ ገና በመጀመሪያዎቹ ጥቂት ሳምንታት የስልጣን ዘመናቸው ስለወደፊቱ የኢትዮጵያ ዕጣ ፈንታ አስደማሚ በሆነ ሁኔታ ሲናገሩ በተግባር የማይገለጽ ባዶ ንግግር ነው ይላሉ፡፡

እርሳቸው ማሸነፍ እንዳይችሉ እና ለውድቀት እንዲዳረጉ ሆነው ነው በአስቸጋሪ ሁኔታ ላይ በስልጣን እንዲቀመጡ የተደረጉት፡፡ ቢሰሩም ይወገዛሉ ባይሰሩም ይወገዛሉ፡፡

ሆኖም ግን ለማንኛውም የስህተት ድርጊት የእርሳቸው የግል ጥፋት ምንድን ነው? ባገዛዙ ውስጥ ባላቸው ስልጣን ምንድን ስህተት ነው የሰሩት?

በአሁኑ ጊዜ በተቃዋሚዎች መካከል ከአገዛዙ ጋር እጅ እና ጓንት ሆነው የሚሰሩ በርካታዎች የሉምን? ወይም ደግሞ ካላቸው ቀረቤታ አንጻር ከአገዛዙ ጋር እየተሞዳሞዱ በሕዝብ ሀብት ላይ ተጠቃሚ የሆኑ አይደሉምን? እነዚህስ ብቃትየለሽ ተብለው መወገዝ የለባቸውም ወይ? እስኪ ለመሆኑ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ላይ የመጀመሪያዋን ጠጠር ለመወርወር ዝግጁ የሆነ ማን ነው?

እውነታው ግልጥልጥ ብሎ ሲታይ ግን ፖለቲካ እንግዳ የሆነ የአልጋ ተጋሪነትን ይጠይቃል፡፡ ማንዴላ ዴሞክራሲን በደቡብ አፍሪካ ውስጥ ተግባራዊ ለማድረግ ከዴክለርክ ጋር ተቀራርበው መስራት ነበረባቸው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ እያንዳንዱን ሰው እንደማያስደስቱ ወይም የእያንዳንዱን ሰው ፍላጎት እንደማያሟሉ አውቃለሁ፡፡ በእኔ አመለካከት እርሳቸው ድንግተኛ ጠቅላይ ሚኒስትር ናቸው፡፡ በታሪካዊ ኃይሎች ለታሪካዊ ሚና የተገኙ ኢትዮጵያ ካፈራቻቸው ባለብሩህ ተስፋ ወጣቶች መካከል አንዱ ናቸው፡፡ እንደማንኛውም ሰው ያለምንም ጥርጥር ሊወድቁ ወይም ደግሞ ስኬታማ ላይሆኑ ይችላሉ፡፡ ማንዴላ እንዲህ ብለው ነበር፣ “በህይወት ውጣ ውረድ ውስጥ ታላቁ ስኬት በፍጹም ያለመውደቅ አይደለም ሆኖም ግን ታላቁ ስኬት በእያንዳንዱ በወደቅንበት ጊዜ ሁሉ ፈጥነን የመነሳት ችሎታ ማዳበር ነው፡፡ ለማዘግየት ስኬታማዎች ልትሆኑ ትችሉ ይሆናል ሆኖም ግን ደቡብ አፍሪካን ወደ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት  ለማሸጋገር የሚደረገውን ተልዕኮ በፍጹም ልታጨናግፉት አትችሉም“ ነበር ያሉት፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ለበርካታ ጊዜ ይወድቃሉ እናም በየጊዜው እንደገና እየተነሱ ኢትዮጵያን ወደ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንደሚያሸጋግሯት አምናለሁ፡፡

ሆኖም ግን ከእርሳቸው ጋር እንዴት ነው ተቀናጅተን መስራት ያለብን?

ለእያንዳንዷ ለሚሰሯት ስህተት ሁሉ ውግዘት እና ትችትን ማጉረፍ ወይስ ደግሞ እርሳቸውን በመልካም ሁኔታ በመገንዘብ ወንድማዊ ፍቅርን እና ጓዳዊ ትብብርን በመስጠት ወደ ታለመው ግብ መገስገስ?

ለእያንዳንዱ ሰይጣናዊ ድርጊት ሁሉ እርሳቸውን ተጠያቂ ማድረግ ይኖርብናልን? ወይስ ደግሞ እርሳቸው የሚፈልጓቸውን ሁሉንም ዕድሎች ሁሉ ለእርሳቸው በመስጠት ስኬታማ እንዲሆኑ እና በድል አድራጊነት እንዲወጡት ማገዝ ይኖርብናል?

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ መጠነሰፊ የሆነ ሕዝባዊ ድጋፍ በተለይም ደግሞ ሰባ አምስት በመቶ የሚሆነውን የህብረተሰብ ክፍል በሚወክለው በወጣቱ ትውልድ እንዳላቸው የሚያጠያይቅ አይደለም፡፡ በአሁኑ ጊዜ በየከተሞች እየተገኙ ከሕዝብ ጋር የሚያደርጓቸው ውይይቶች ስኬታማነታቸውን በማረጋገጥ ላይ የሚገኙ ናቸው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ እና ለማ መገርሳ በዘረመል የትውልድ ህዋሶቻችን ውስጥ ኢትዮጵያዊነትን ያነቃቁ እና ወንድማዊ ፍቅርን ለማስፈን የሚታትሩ የማይናወጥ ጽኑ እምነት ባለቤቶች ናቸው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ እና ለማ አብረን እንቆማለን ወይም ደግሞ አብረን እንወድቃለን ይላሉ፡፡ ዕጣ ፈንታችን በአንድነት የተገመደ ነው፡፡ ማንም ብቻውን አይቆምም፡፡ ኢትዮጵያዊነት ማለት እንግዲህ እንደዚህ ነው ይሉናል፡፡

በዚህ አሁን እየጻፍኩት ባለው ማስታዋሻየ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ላይ እያራመዷቸው ያሉትን የተጠናከረ ተጠራጣሪነታቸውን፣ ጨለምተኛነታቸውን የአሸናፊነት መንፈሳቸውን እና አሉታዊ አስተሳሰቦቻቸውን እርግፍ አድርገው በመተው ጨለምተኛና የተቃርኖ አመለካከቶቻቸውን ወደ አዎንታዊ አመለካከቶች፣ የብቸኝነት እና የእራስ ወዳድነት ስሜትን ወደ ጋርዮሽ እና አብሮነት፣ ውስጣዊ ጥላቻዎቻቸውን  ወደ ፍቅር እና ብሄራዊነት አስተሳሰቦች፣ ቀኖናዊ ግትርነታቸውን፣ ስሜታዊነታቸውን እና አድሏዊነታቸውን ወደ ምሁራዊነት፣ ተራማጅ እና መርህን መሰረት ያደረጉ አስተሳሰቦች፣ የቡድናዊ እና ጎሳዊ አስተሳሰቦችን ወደ ኢትዮጵያዊነት፣ ሰብአዊነት፣ ሀሳባዊነት እና ትክክለኛነት እንዲቀይሩ ለእኔ ጓደኞች የጉማሬው ትውልዶች (አሮጌው ትውልድ)  ተማጽዕኖዬን አቀርባለሁ፡፡

አሁን በእጃችን ያለው አንገብጋቢው ተግባር ኢትዮጵያን ወደፊት እንዴት ማስኬድ እንደምንችል እና ይህንንም መልካም አስተሳሰብ እንዴት ማቆየት እንደምንችል ትኩረት ማድረግ ላይ ነው፡፡ ለአንድ የጋራ ዓላማ ወደ ነጻነት፣ ዴሞክራሲ እና የሰብአዊ መብት መከበር አንድ አቅጣጫ መጓዝ አለብን፡፡

በተዛባ መልኩ እንዳትገነዘቡኝ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የኢትዮጵያ አዳኝ ወይም ደግሞ መለኮታዊ ኃይል ናቸው ብየ አላስብም፡፡ እርሳቸው ወጣት ሰው ናቸው፡፡ አብዛኞቻችን በእርሳቸው የእድሜ ክልል ያሉ ልጆች አሉን፡፡ እንደማንኛውም ወጣት ሰው እርሳቸውም ብዙ የሚማሯቸው ነገሮች አሏቸው፡፡ አብዛኞቻችን በወርቃማው የእድሜ ክልላችን ልንማራቸው የሚገቡን በተለይም ስለእውነት እና እርቅ በርካታ ቁምነገሮች አሉን በማለት ደፍሬ ለመናገር እችላለሁ፡፡

ግልጽ የሆነው ነገር ፍጹም በሆነች ዓለም ውስጥ አንኖርም፡፡ ለዚህም ነው ምጡቅ አስተሳሰብ ማሰብ ያለብን እና ትችን ማውገዝ ያለብን፡፡ ይህንንም በማድረግ አስደማሚ የሆኑ መፍትሄዎችን ይዘን በቅ እንላለን፡፡

በአሁኑ ጊዜ ቅድመ ማስረጃዎች እንደሚያሳዩን በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አመራርነት ኢትዮጵያ በቀጥተኛው መንገድ እና በትክክለኛው መስመር ላይ ወደፊት በመጓዝ ላይ ትገኛለች፡፡ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጋራ በመሰለፍ ኢትዮጵያ በትክክለኛው መስመር ላይ እንድትቆይ እና በፈጣን ሁኔታ እንድትራመድ የበኩላችንን ማድረግ አለብን፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ሩህሩህ፣ መልካም አሳቢ ፍቅርን የተላበሱ እና የኢትዮጵያን ወጣቶች እና ሀገሪቱን በሰላም፣ በአንድነት እና በእርቀ ሰላም ወደፊት እንድትጓዝ ማድረግ የሚችል ችሎታ ያላቸው ወጣት መሪ ሆነው ይታዩኛል፡፡

ለእኔ አሮጌ የጉማሬ ትውልድ እህት እና ወንድሞቸ የነጻነት ባቡሩ መነሻ ጣቢያውን ለቅቋል ተነስቷል በማለት ልነግራቸው እፈልጋለሁ፡፡ ሆኖም ግን አሁንም ቢሆን ለመሳፈር የሚፈልጉ ከሆነ ባቡሩን በቀጣዩ ጣቢያ ለመያዝ ይችላሉ፡፡

በወጣትነት ዘመኔ በጣም የምወደው መዝሙር ነበር፡፡ ይህም መዝሙር “እልም አለ ባቡሩ ወጣት ይዞ በሙሉ“ ይባል ነበር፡፡

የአቦሸማኔው ትውልድ አባላት በባቡሩ ተሳፈሩ:: አብይ አህመድ ባቡሩን በመሾፈር ላይ ናቸው፡፡

ወደ ዋናው ርዕሴ ከመግባቴ በፊት ባለፈው ሳምንት በሰማኋቸው አንዳንድ ዜናዎች ላይ አስተያየቴን መስጠት እፈልጋለሁ፡፡

“ይቅርታ እጠይቃለሁ…” የሚለው ቃል የመፈወስ ኃይል ያለው እና ለወጣቱ ጠቅላይ ሚኒስትር እና ለእኛ ታላቅ ትምህርት ትቶ ያለፈ ክስተት ነው፡፡

በውይይቱ ወቅት ቀርቦ ለነበረ ጥያቄ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጡት ምላሽ ላይ ጥቂት ኢትዮጵያውያንን ጨለምተኛ እንዲሆኑ ያደረገ ስለነበር እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር በተሳሳተ መንገድ ግንዛቤ በመወሰዱ ይቅርታ እጠይቃለሁ በማለታቸው እኔ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ላይ ያለኝ ክብር እጅግ በጣም አየጨመረ መጥቷል፡፡

ባለፈው ሳምንት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለብዙ ጊዜ አወዛጋቢ ሆኖ የቆየውን የወልቃይት ጉዳይ እንደ ቀላል ነገር በመውሰድ የወልቃይት ጉዳይ የልማት ችግር ነው፣ የመሰረተ ልማት እና የማህበራዊ አገልግሎቶች ያለመሟላት ችግር ነው በማለት የንቀት ንግግር አድርገዋል በሚል የማህበራዊ ሜዲያዎች ውንጀላዎችን አቅርበው ነበር፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የዘመናት የኢትዮጵያ መሪዎችን መጥፎ ባህል በሚያስደንቅ እና ባልተጠበቀ ሁኔታ አሽቀንጥረው በመጣል ይቅርታ ጠይቀዋል፡፡ አስደናቂው ነገር ይቅርታ መጠየቃቸው ብቻ ሳይሆን የእርሳቸውን ሀሳብ ሌሎች ሰዎች እንዴት እንደተገነዘቡ የሰጡበት ምላሽም ጭምር ነበር፡፡ ከዚያም በመቀጠል ከወልቃይት የአማራ ማንነት ኮሚቴ አመራር አባላት እና ከሌሎች በደርዘን ከሚቆጠሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ተገናኝተዋል፡፡ ስለሁኔታውም ተገቢውን ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ሩህሩህነትን በሚያሳይ መልኩ ሰከን ብለው ስለጉዳዩ ጥልቅ ስሜት እንደተሰማቸው እና ከዚህም ተገቢ የሆነ ልምድ ወስደዋል፡፡

በከተማው ተደርጎ በነበረው ሀዘን የተንጸባረቀበት ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ስለወልቃይት ጉዳይ ተናግረውት በነበረው ንግግር ምክንያት ሕዝቡ ቅር በመሰኘቱ ወደ ጎንደር እንዳይሄዱ ተነግሯቸው እንደነበር ተናግረዋል፡፡ ሆኖም ግን ይህንን ነገር ወደ ጎን በመተው ወደ ጎንደር ለመሄድ ወሰኑ ምክንያቱም እርሳቸው ስህተት ሰርተው ከሆነ የጎንደር ሕዝብ ትንሽ ቁንጥጫ እንደሚሰጣቸው እና እንደሚያስተምራቸው ተናግረዋል፡፡ በሌላ አባባል እርሳቸው ማለት የፈለጉት እርሳቸው ወጣት ስለሆኑ ስህተት መስራት እንደሚችሉ ወይም ደግሞ በተሳሳተ መንገድ ግንዛቤ ሊወሰድባቸው እንደሚችል ግልጽ ማድረጋቸው ነው፡፡ ሆኖም ግን እርሳቸው የጎንደር ሕዝብ ልጅ ናቸው፡፡ ስህተት ከሰሩ ወይም ከተናገሩ ሕዝቡ እንደ ልጆቻቸው በማየት አርሞ ያስተካክላቸዋል፡፡

እንደዚህ ያለ ጨዋ እና ሩህሩህነትን የተላበሰ የሀገር መሪ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ተሰምቶ አያውቅም፡፡ ለሚሰራቸው ስራዎች እራሱ ኃላፊነትን የሚወስድ መሪ ሙገሳ እንጅ ውግዘት አይፈልግም፡፡ ለዚህም ነው ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ገንቢ እና አዎንታዊ የሆኑ ትችቶችን መስጠት አለብን የምለው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አስተያየትን ይቀበላሉ፣ ከዚህም ትምህርት ይወስዳሉ እናም በሂደት ልምድ እየወሰዱ የበለጠ ጠንካራ እና ውጤታማ መሪ ይሆናሉ፡፡

የኢትዮጵያ መሪ የሆነ እና ላደረገው እና ለተናገረው ስህተት ድርጊት ይቅርታ በመጠየቅ ከሕዝብ ጋር ሆኖ በመስራት ቅሬታዎችን ለማስወገድ እና መፍትሄዎችን ለማምጣት የሞከረ በየትኛውም ጊዜ አላውቅም ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በሹመት በዓል ንግግራቸው ዕለት ባሰሙት ንግግር በሰላማዊ አማጺዎች ላይ በወታደር እና ደህንነት ኃይሎች ለተፈጸሙ ግድያዎች እና ለደረሱ ጉዳቶች ይቅርታ የጠየቁ ብርቅየ እና ልዩ ሰው መሆናቸውን አውቃለሁ፡፡ ለእኔ ያ ማለት ብዙ ነገር ነው ምክንያቱም ከሕግ አግባብ ውጭ በዘፈቀደ በንጹሀን ኢትዮጵያውያን ላይ ግድያ መፈጸም ነው እኔን በመጀመሪያ ደረጃ ወደ ሰብአዊ መብት ተሟጓችነት ትግሉ ዘው ብየ እንድገባ ያደረገኝ፡፡

ይቅርታ ለመጠየቅ ድፍረቱ እና ስብዕናው ያለው መሪ ሩህሩህ፣ አእምሮው ግልጽነትን የተላበሰ፣ ልቡ ክፍት የሆነ እና በእራስ የመተማመን ስሜት ያለው መሪ ነው፡፡ እንደዚህ ዓይነቱ መሪ ለእኛ ለኢትዮጵያውን ስልጣን ለሕዝብ አገልግሎት ብቻ መዋል እንዳለበት ያረጋግጥልናል፡፡ እንዲህ በማለት ይነግረናል፣ “እኔ ሰው ነኝ እንደማንኛውም ሰው ስህተት ልሰራ እችላለሁ፡፡ እኔ የሕዝብ አገልጋይ የመሆንን ከባድ ኃላፊነት ከመሸከም የዘለለ ሌላ ልዩ ነገር የለም“ ይላሉ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከሕዝብ ጋር  ንስሀ የመግባት እና ዕርቀ ሰላም የማውረድን ዋጋ ምሳሌ በመሆን ያስተምሩናል፡፡

እ.ኤ.አ ሰኔ 2010 አቅርቤው በነበረው ትችቴ መሪዎችን ከሕዝብ ጋር ለማቆራኘት ንስሀ መግባት አስፈላጊ እንደሆነ ጽፌ ነበር፡፡ አሁን በስልጣን ኮርቻ ላይ ተፈናጥጠው ያሉ እና ተቃዋሚዎች ለኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲህ ማለት አለባቸው፣ “አምታተናችኋል፣ ግራ አጋብተናችኋል፡፡ ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡ ወደፊት ከስህተቶቻችን እንማራለን ለሁለተኛ ጊዜ አንደግመውም፡፡“  እንደ አጋጣሚ ሆኖ ብዙዎቻችን ከስህተት ላይ እንወድቃለን እናም ስህተት ትክክል ነው እያልን ለብዙ ጊዜ ይህንኑ ስናራምድ እንቆያለን፡፡

ይቅርታ የመጠየቅ ኃይል ምህረትን እና ይቅርታን የመጠየቅ ኃይል ነው፡፡ ቅንነት ያለው ይቅርታ ብልህነት ነው፡፡ ንዴትን እና ጥላቻን ያስወግዳል፡፡ ፍቅርን፣ መግባባትን እና ዕርቅን ያጠናክራል፡፡

ጋንዲ እንዲህ ብለው ነበር፣ “ደካሞች በፍጹም ምህረት ሊያደርጉ አይችሉም፡፡ ምህረት  የጠንካሮች እሴት ነው“ ብለዋል፡፡

እኔ ደግሞ እንዲህ የሚል እጨምራሁ፣ “ደካሞች በፍጹም ይቅርታ ሊጠይቁ አይችሉም፡፡ ይቅርታ የጠንካሮች እሴት ነው“ እላለሁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ታላቅ ትምህርትን አስተምረውኛል ምክንያቱም እራሴ ታላቅ ይቅርታ የማድረግ ጉድለት አለብኝ፡፡ ሆኖም በዚህ ላይ እራሴን ለማሻሻል እየሰራሁ ነው፡፡

ከወጣቱ ትውልድ ለመማር ጊዜው እሩቅ አይደለም፡፡ እኔ ለእራሴ እውነትን እናገራለሁ!

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የቆሰሉትን ለመፈወስ ሲሉ በሚያሰሟቸው ቃላት እና ለሚያሳዩት መልካም ባህሪ፣ ደግነት፣ ሩህሩህነት እና ፍቅር አመሰግናቸዋለሁ፡፡ ቃላት ለመፈወስና ለማውደም ኃይል አላቸው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ልቦቻቸው በተናገሯቸው ቃላት ተሰብረው የቆዩትን በርካታዎቹን ኢትዮጵያውያን በተሳሳተ መንገድ ስለተገነዘባችሁኝ ነው ይቅርታ በማለት ቃሎቻቸውን ለፈውስ አገልግሎት እንዲውሉ አድርገዋል፡፡

ኢትዮጵያዊ ጀግና እስክንድር ነጋን በከፋፋይ ፖለቲካ ለማጥቃት መሞከር፣

ቅዱሱ መጽሐፍ እንዲህ ይላል፣ “ሰይጣናዊ ድርጊትን ካልሰሩ ስለማያርፉ ሰውን ለማጥቃት ሲሉ እንቅልፋቸውን አጥተዋል“  ይላል፡፡ በሌላ አባባል ሰይጣኖች በፍጹም አይተኙም፡፡

ከጥቂት ቀናት በፊት ኢትዮጵያዊው አርበኛ እና ጀግና እንዲሁም ዓለም አቀፋዊ እውቅናን የተጎናጸፈው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የአምነስቲ ኢንተርናሽናልን የወርቅ ኢዮ ቤልዩ በዓል ለማክበር ተጋብዞ ወደ ኔዘርላንድ እንዳይበር ክልከላ ተደርጎበት ነበር፡፡ ፓስፖርቱን በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ የኢሜግሬሽን የመቆጣጠሪ ጣቢያ ከተነጠቀ በኋላ ወደ ውጭ መጓዝ እንዳይችል የጉዞ ማዕቀብ የተጠለበት መሆኑን ተነግሮታል፡፡

ፓስፖርቱን እንደነጠቁት እስክንድር ለኢሚግሬሽን ባለስልጣኖች ጉዳዩን ለከፍተኛ ባለስልጣኖች በማቅረብ ይረጋገጥ ምክንያቱም አላስፈላጊ የሆነ ትችትን በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አስተዳደር ላይ መስጠትን አልፈለገም፡፡ ፓስፖርቱን እንዲነጠቅ ትዕዛዙ የመጣው ከከፍተኛው ባለስልጣን እንደሆነ ተነግሮት ነበር፡፡ እንዳጋጣሚ በሰዓታት ጊዜ ውስጥ ለመሄድ ነጻ መሆኑ ተዘግቦ ነበር፡፡

እስክንድር እ.ኤ.አ የካቲት 2018 ነበር ከእስር የተፈታው እናም እንደገና ባለፈው ወር መጀመሪያ አካባቢ በአንድ የግለሰብ ቤት ውስጥ ሲደረግ በነበረ ዝግጅት ላይ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሰንደቅ ዓላማ አሳይተሀል በማለት ከሌሎች የፖለቲካ እስረኞች ጋር እንደገና ወደ እስር ቤት እንዲገባ ተደርጎ ነበር፡፡

“ከፍተኛ የሆኑ ባለስልጣኖች” እገዳውን በማድረግ ወደ ውጭ አገር እንዳይወጣ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል የሚለውን እስክንድር ነጋ የሰብአዊ መብት ክብረ በዓልን ለማክበር ከሀገር ወደ ውጭ እንዳይወጣ የከለከሉት ለምንድን ነው?“ የሚል ነበር፡፡ ከሁሉም በላይ ከሁለት ሳምንታት በፊት ገደማ ከእስር ቤት ለቀውታል፡፡

አንድ ሀሳብ በአእምሮዬ ላይ ውልብ አለብኝ፡፡ ኢትዮጵያ እስክንድር ነጋን የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የወርቅ ኢዮ ቤልዩ በዓል ላይ የክብር እንግዳ ሆኖ እንዳይገኝ እንደገና በመከልከል “የዓለም ውራጅ” መሆን ይኖርባታልን?

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከእስክንድር ነጋ ጋር ጠብ የላቸውም፡፡ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በፊት የነበረው ጠቅላይ ሚኒስትር እስክንድር ነጋ እና ሌሎች በርካታዎቹ በእርግጥ “የፖለቲካ እስረኞች” ናቸው ብሏል፡፡

በእርግጥ ለእኔ ይህንን ሁኔታ ለማወቅ ጊዜ አልወሰደብኝም፡፡

ምን ዓይነት ጨዋታ እየተጫወቱ እንዳለ እና ይህን ጨዋታ የሚጫወተው ማን እንደሆነ በእርግጠኝነት አውቃለሁ፡፡ ቀደም ሲል ሲጫወቱት አይቻለሁ፡፡

እ.ኤ.አ ግንቦት 2016 በዞን ዘጠኝ ጦማሪዎች ላይ ተመሳሳይ ሸፍጥን ሰርተዋል፡፡ የዘላለም ክብረትን እና የሌሎችን አምስት ጦማሪዎችን ፓስፖርት በአውሮፕላን ማረፊያው ቅጥር ግቢ ውስጥ ወስደዋል፡፡ ዘላለም እ.ኤ.አ በሰኔ 2016 የኦባማን ወጣት የአፍሪካ መሪዎች ጉባኤን እንዲካፈል ይጠበቅ ነበር፡፡ በዚያ ጊዜ የመንግስት ከሙኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር ጌታቸው ረዳ እንዲህ በማለት ገልጾ ነበር፣ “ድርጊቱ የተፈጸመው ከስልጣናቸው ገደብ በላይ አልፈው በዳኞች እና በኢሚግሬሽን ባለስልጣኖች ነበር፡፡ ለማስተካከል ወራትን ወይም ዓመታትን የሚፈጅ ስህተት ሊሰሩ ይችላሉ“ ነበር ያለው፡፡

በእስክንድር ላይ የተፈጸመውም እንዲዚያ ዓይነት ነገር ነውን? በዳኞች እና በእረፍት የለሽ የኢሚግሬሽን ባለስልጣኖች ነውን?

ያንን ጨዋታ እናውቀዋለን፡፡ በስልጣን ላይ ያሉ እና እስክንድርን ለማዋረድ እና ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን ለማበሳጨት የሚፈልጉ አንዳንድ አድሀሪ ግለሰቦች እንደዚህ ያለ ድብቅ አጀንዳ አላቸው፡፡

እስክንድርን የመውጫ ቪዛ በመከልከል የሚከተሉትን ዓላማ ለማሳካት ጥረት አድርገዋል፡

የጠቅላይ ሚኒስትር አብይን ተቀባይነት እና ክብር ለማዋረድ እና ለማበሳጨት፣

በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ እና በዲያስፖራው ማህበረሰብ መካከል አጥር ለማጠር፣

ዝናው አየናኘ በመጣበት ወቅት ታላቁን እስክንድር ነጋን ለማዋረድ፣

እስከ አሁንም ድረስ በስልጣን ላይ ናቸው እናም የፈለጉትን ነገር ሁሉ ማድረግ ይችላሉ የሚል መልዕከት ለማስተላለፍ፣

ዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን እንደገና ወደ ክስ እንዲገቡ እና ሀሳቦቻቸውን ለማስቀየስ፣

ወደ ጨለማው ክፍል ሊመልሱን ስለሚፈልጉ ነው፡፡

ሆኖም ግን እኛ ከእንግዲህ ወዲያ ወደ ጨለማው አንሄድም ምክንያቱም ኃይሉ ያለው ከእኛ ጋር ነው!

ከእንግዲህ ወዲያ በኢትዮጵያ ውስጥ እና በዲያስፖራው ማህበረሰብ ውስጥ ያሉ ኢትዮጵያውያን እንደዚያ ያለውን ያረጀ እና ያፈጀ ጨዋታ አይጫወቱም፡፡

ለዓመታት በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ያሉ ባለስልጣናት ዲያስፖራ ኢትዮጵያውያንን በደመ ነብስ፣ በስሜታዊነት እና በብስጭት ምላሽ እንዲሰጡ በማድረግ ሲጫወቷቸው የነበሩባቸውን አጋጣሚዎች ሁሉ እያስጠነቀቅሁ ስጽፍባቸው ቆይቻለሁ፡፡ ወደ ኋላ መለስ ብለን ስንመለከት የማይጠቅም እርባና ቢስ የሆኑ ነገሮችን ሲሰሩ እናያለን፡፡ ሆን ብለው አስበውበት የዲያስፖራውን ማህበረሰብ ሀሳብ ለማስቀየስ አሳፋሪ የሆነ ነገር ይናገራሉ፡፡  ከዚያም የዲያስፖራው ማህበረሰብ ለዚያ ምላሽ ለመስጠት ቆላ ከደጋ በማለት በመዋተት ሌላ ሀሳብን የሚያስቀይስ ነገር እስኪመጣ ድረስ እና እንደገና በአዲስ እስኪጀመር ድረስ ጊዜውን ያባክናል፡፡

አሁን ዳንሱ ያለቀ መሆኑን ሊገነዘቡ ይገባል፡፡ ጨዋታው ተጠናቅቋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ ፍቅር፣ እውነት እና ዕርቅ የሰፈነባትን ኢትዮጵያ ለመገንባት በመንቀሳቀስ ላይ እንገኛለን፡፡

ለእነርሱ እንዲህ የሚል ቀላል መልዕክት አለኝ፣

“እንደዚህ ዓይነት ሰይጣናዊ ድርጊት ስትፈጽሙ የቆያችሁ ሁሉ አሁን ጊዚያችሁ ያለፈ መሆኑን እወቁ፡፡ የጨለማ ዘመን ተጠናቅቋል፡፡ አሁን የጨዋነት፣ የመግባባት እና የእርቅ ዘመን  ነው፡፡ በመጨረሻው ሰዓት የእናንተ ጨዋታ በጫካ ውስጥ በመሆን በአንድ እጅ ማጨብጨብ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው፡፡ በሕዝቦች መካከል ግጭት እና ጥላቻን ለመፍጠር እንቅልፍ የለሽ ምሽቶችን ማሳለፍ ትችላላችሁ፡፡ ሆኖም ግን እኛ ወደፊት ተንቀሳቅሰናል፡፡ ለእናንተ ቫይረስ ጸር የሆነውን እና ኢትዮጵያዊነት እየተባለ የሚጠራውን መድሀኒት በመርፌ ተወግተናል፡፡ እንደፈለጋችሁ ሞክሩ ሆኖም ግን በመከፋፈል ለመግዛት የምታደርጉት ጥረት ስኬታማ አይሆንም፡፡ ከዚህ በኋላ በፍጹም!“

ስለወንድሜ ስለእስክንድርና… እስቲ ልናገር…

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በሹመት በዓል የመክፈቻ ንግግራቸው እንዲህ ብለው ነበር፣ “በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና በሀገር ውስጥ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን መካከል ከልብ በመነጨ ሁኔታ ይቅር ልንባባል ይገባል፡፡ በውጭ ያሉ ኢትዮጵያውያን እውቀታቸውን፣ ሀብቶቻቸውን እና ልምዶቻቸውን በመያዝ ሀገራቸውን በመገንባቱ ጥረት የእራሳቸውን ድርሻ እንዲወጡ እጆቻችንን ዘርግተን እንቀበላቸዋለን“ ነበር ያሉት፡፡

የእርሳቸውን የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግሮች በሙሉ ልቤ አደንቃቸዋለሁ፡፡

የእኔ ህልም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ እጆቻቸውን በመዘርጋት ዲያስፖራ ኢትየጵያውያንን ከመቀበላቸው በፊት የኢትዮጵያን የሀገር ውስጥ ጀግኖች ወንዶች እና ሴቶች ልጆች ለመልካም ነገር እና ለዴሞክራሲ ማበብ፣ ለሰብአዊ መብት መከበር እና ለሕግ ልዕልና ሲታገሉ የቆዩትን እና ምንም ዓይነት ወንጀል እንዳልሰሩ ፊት ለፊት በመናገር እቅፍ አድርገው ይሳሟቸው፡፡

ይንገሯቸዉም “እዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ተቀራርበን ልብ ለልብ ይቅር እንድንባባል እንፈልጋለን፡፡”

በግድግዳ ላይ ያለ ዝንብ በመሆን የእስክንድር ነጋን፣ የአንዷለም አራጌን፣ የፕሮፌሰር በቀለ ገርባን፣ የውብሸት ታዬን፣ የፕሮፌሰር መረራ ጉዲናን፣ የአበበ ቀስቶን፣ የኦልባና ሌሊሳን፣ የእማዋይሽ ዓለሙን፣ የዘላለም ወርቅ አገኘሁን፣ የማህሌት ፋንታሁንን፣ የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎችን፣ የአህመዲን ጀበሊን፣ የንግስት ይርጋን፣ የአቡ በካር አህመድን፣ የኦኬሎ ኦኳይ ኦቻላን፣ የኮ/ል ደመቀ ዘውዱን፣ የዶ/ር ፍቅሩ ማሩን፣ የናትናኤል መኮንንን፣ የማሙሸት አማረን…እንዲህ የሚሉትን ቃላት ሲሰሙ ማየት እወዳለሁ፣ “በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ ከውስጥ ልባችን በመነጨ መልኩ እርስ በእርሳችን ይቅር መባባል ያስፈልገናል፡፡“

ምን ዓይነት ወርቃማ አጋጣሚ ይሆን!

በሀገር ውስጥ ሆነው አምባገነኑን አገዛዝ ሲፋለሙ ለቆዩት ወጣት ኢትዮጵያውያን ምን ያህል ክብር እና አድናቆት እንዳለኝ አንባቢዎቸ ትገነዘባላችሁ ብዬ አምናለሁ፡፡ እንግሊዝ በናዚ ላይ መልሶ የማጥቃት እርምጃ ከመውሰዷ ከአንድ ወር በፊት ዊንስተን ቸርችል ጥቂት ለታጠቁት የአውሮፕላን አብራሪዎቻቸው እንዲህ የሚል የሙገሳ ንግግር አሰምተው ነበር፣ “እነዚህ ጥቂት ጀግኖች ያደረጉት መስተዋፆ ጠቅላላው ህዝባችን ዉለታዉን መመለስ አይችልም” ነበር ያሉት፡፡

እንደዚሁም ሁሉ በኢትዮጵያ ታሪክ በተደረገው የሰብአዊ መብት ትግል ውስጥ የኢትዮጵያ ህዝብ የነዚህን ጥቂት ወጣቶች ዉለታና መስዋእትነት መከፈል ያዳግተዋል፡፡

ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ፣ ለነጻነት እና ለሰብአዊ መብት መከበር ብዙ ከተሰቃዩት ከእነዚህ ጀግኖች ጋር የሚደረገው ዕርቀ ሰላም በኢትዮጵያ ውስጥ ለእውነት እና እርቀ ሰላም መስፈን እውነተኛ ማረጋገጫ ነው፡፡

አልጠራጠርም ይህ ድርጊት ይፈጸማል፡፡ የጊዜ ሁኔታ ብቻ ነው፡፡ 

ሕዝባቸውን ለሚያዳምጡ መልካም መሪዎች እውነትን መናገር፣

እኔ በስልጣን ላይ ላሉት እውነትን የምናገር በመሆኔ ኩራት ይሰማኛል፡፡ ይህም መፈክር በድረ ገጼ መግቢያ ላይ እንዲህ በሚል ተጽፎ ይገኛል፣ “ሰብአዊ መብት ይከበር፡፡ በስልጣን ላይ ላሉት እውነትን መናገር፡፡“

ወደ ኋላ መለስ በማለት እ.ኤ.አ በ2006 ስለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት መጠበቅ ገና በመጀመሪያ ጊዜ መስበክ በጀመርኩበት ጊዜ ዓላማዬን ለማሳካት እንዲህ የሚሉትን የጋንዲን ቃላት ተውሻለሁ፣ “መጀመሪያ ይተውሀል፣ ከዚያም ይስቁብሀል፣ ከዚያም በመቀጠል ይታገሉሀል፣ ከዚያ በኋላም አሸናፊ ትሆናለህ“፡፡

ላለፉት አስራ ሶስት ዓመታት ጆሯቸውን ለዘጉብኝ፣ ዓይናቸውን ለጨፈኑብኝ እና ለተሳለቁብኝ በስልጣን ላይ እንደ መዥገር ተጣብቀው ለሚገኙት እውነቱን ስናገር ቆይቻለሁ፡፡

በእርግጥ በስልጣን ላይ ላሉት እውነትን በመናገር ሳቀርባቸው የቆየሁት ሳምንታዊ ሰበካዎቸ በጋንዲ የትግል ስልት አጠራር መሰረት በግለሰቦች የሚደረጉ ሕዝባዊ እምቢተኝነቶች ናቸው፡፡

በአምባገነኖች ላይ  ሰላማዊ ትግል፣ ሕዝባዊ እምቢተኝነት፣ ከጨቋኞች ጋር ያለመተባበር እና በመንግስት ላይ የብዙሀን ተቃውሞ በማድረግ መታገል “እውነተኛ ኃይል” መሆናቸውን ጋንዲ አስተምረዋል፡፡ የጋንዲ የእውነት ኃይሎች አስተምሮ በጨቋኞች ልብ እና አእምሮ ውስጥ ያለ ጥላቻ እንደሚያጠፋቸው እና ብቸኛው ጽድቅ እራስን፣ ማህበረሰቡን እና ሀገሪቱን መውደድ እንደሚሆን ያሳምናቸዋል፡፡

በኢትዮጵያ ውስጥ ከመጀመሪያ ጊዜ ጀምሮ ቀስ በቀስ በስልጣን ላይ ላሉት እውነትን በመናገር ቆይቻለሁ በማለት መናገር እችላለሁ፡፡ ሆኖም ግን እ.ኤ.አ እስከ 2006 ዓ.ም ድረስ ሰላሜን ይዠ ቆይቻለሁ፡፡

እ.ኤ.አ ሰኔ 10 ቀን 1991 ዓ.ም በጊዜው በኢትዮጵያ ቀደምት መጽሄት በነበረው በኢትዮጵያን ሪቪው የደርግ ዘመን ፍጻሜ እና በኢትዮጵያ ሁሉም ወገኖች አዲስ የሰላም እና የብልጽግና ምዕራፍ እንዲከፍቱ እና ይህን መልካም ዕድል እንድንጠቀምበት ወይም ደግሞ ይህችን ዕድለ ቢስ ሀገር በተሳሳቱ ምርጫዎች እና ስሌቶች ወደ ስቃይ እና መከራ እንዳትገባ የሚል ትንታኔ እና ነብያዊ ትንበያ ሰጥቸ ነበር፡፡

እ.ኤ.አ ሀምሌ 1 ቀን 1991 ዓ.ም አቅርቤው በነበረው የግል አስተያየት ጽሁፍ ኢሀአዴግ ስልጣንን ከያዘ ወዲህ ተደቅነውበት በሚገኙት ተግዳሮቶች ላይ ትንታኔ በመስጠት አሳታፊነት፣ ቅንነነት እና አንድነት እንዲኖር ተማጽእኖ አቅርቤ ነበር፡፡ ከእውነተኛ ዴሞክራሲ ውጭ ምርጫው ወደ መጥፎ ነገር የሚሄድ እና ኢትዮጵያ ደህና ሰንብች ይሆናል በማለት አስጠንቅቄ ነበር፡፡

እነዚያ ቃላት ነብያዊ መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡ እናም እ.ኤ.አ በሚያዝያ 2018 እውነትን በስልጣን ላይ ላሉት በአደባባይ በመናገር አባ ገዳ በየነ ሰንበቶ እንዲህ በማለት እውነታውን ፍርጥርጥ አድርገው ተናግረዋል፣

“አንድ ነገር ልንገራችሁ፡፡ አሁን በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ለመምረጥ እንደዚህ ያለ ነገር ነበር፡፡ ሰላማዊ የጠቅላይ ሚኒስትር ሽግግር አልተካሄደም ነበር፡፡ እውነታውን ልናገር፣ ሁሉም የሀገሪቱ ሕዝቦች ይስሙት፡፡ ሀገሪቱ በከፍተኛ አደጋ ውስጥ ነበረች፡፡ እግዚአብሄር ምስክሬ ነው፡፡ እያንዳንዱ ሰው ቢላዋውን በመሳል ተዘጋጅቶ ይጠብቅ ነበር፡፡ ምን እንደሚደረግ እናያለን እያሉ ነበር፡፡ ሆኖም እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይጠብቃታል፡፡ እናም የመንግስት አካላት ትክክለኛውን ነገር አደረጉ፡፡ እናም ከጭንቅ ገላገሉ፡፡ ያ ሳይሆን ቢቀር ኖሮ አንድ ሺ የኮማንድ ፖስት ወታደሮች አንድ ሚሊዮን የሚሆነውን ሕዝብ አምቀው ለመያዝ አይችሉም ነበር፣ በፍጹም አይችሉም…“ ነው ያሉት፡፡

አባገዳ በየነ ትክክል ናቸው፡፡ እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይጠብቃታል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ጥይቱን እና ቢላዋውን አስወግደናል፡፡

ከስምንት ዓመታት ገደማ በፊት በሁፊንግተን ፖስት “በስልጣን ላይ ላሉት እውነትን መናገር …“ በሚል ርዕስ ተከታታይ ጽሁፎችን ጽፌ ነበር፡፡ በእነዚህ ተከታታይ ጽሁፎች ለእንግዳዎች (ለዓለም አቀፍ ለጋሽ እና አበዳሪ ድርጅቶች) እውነቱን መናገር፣ እንደዚሁም ደግሞ ለእውነት ፈላጊዎች (ለኢትዮጵያ ልሂቃን) እና በኢትዮጵያ ወጣቶች እና ሴቶች በኩል በመሆን ጽፌ ነበር፡፡ እርባና ቢስ የሆነ ንግግር ለሚያደርጉት ሁሉ እውነትን ተናግሪያለሁ፡፡ ምንም ኃይል ለሌላቸው ሁሉ ድምጽ በመሆን ተናግሬላቸዋለሁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን እንሞግት፡ የዲያስፖራ ኢትዮጵያውየንን አጀንዳ (ዎች) እንስጣቸው፣

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በሹመት በዓል የመክፍቻ ንግግራቸው እንዲህ ብለዋል፣ “በውጭ ያላችሁ ኢትዮጵያውያን ሁሉ እውቀታችሁን፣ ሀብቶቻችሁን እና ልምዶቻችሁን በመያዝ ወደ ሀገራችሁ ብትመጡ እና በሀገር ግንባታው የበኩላችሁን አስተዋጽኦ ለማድረግ ብትዘጋጁ እጆቻችንን ዘርግተን እንቀበላችኋለን“ ነበር ያሉት፡፡

በተመሳሳይ መልኩ እ.ኤ.አ ህዳር 2017 ለማ መገርሳ እንዲህ በማለት አጽንኦ ሰጥተዋል፣ “መማር እና ሀገርን ማገልገል የአካደሚክ የምርምር ወረቀት ማዘጋጀትን አይጠይቅም፡፡ ይህም ማለት ሀገርህን ለመጠበቅ፣ የተለያዩ መንገዶችን መፈለግ፣ ገንቢ የሆኑ ሀሳቦችን ይዞ መምጣት እና እንደነዚህ ያሉ ሀሳቦችን ማሰራጨት ነው፡፡ ይህ ነው እንግዲህ ከምንም በላይ ከእኛ ምሁራን የሚጠበቀው፡፡ እኔ እንደዚህ ነው የማስበው“ ነበር ያሉት፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ እና ለማ ሁላችንንም እየሞገቱን ነው፡፡

እኔ በግሌ የእነርሱን መልዕክት ወስጃለሁ፡፡ ለእኔ እንደዚህ የሚል መልዕክት ነው የሰጡኝ፣ “የተናገርከውን አድርግ አለዚያም መናገርህን አቁም፡፡“

ለዚህም ነው በህዳር እና አሁን የቀረበውን መገዳደር ወዲያውኑ የተቀበልኩት፡፡ አደርጋለሁ!

ሌሎችም ይጋሩታል ብየ የማስበው የእኔ የዲያስፖራ አጀንዳ፣

የማይለወጥ እና አንድ ዓይነት ስብስብ አይደለም፡፡ በአንድ ከበሮ መች ስር የሚሰባሰብ አይደለም፡፡ በብዙ መልኩ ብዝሀነት የሚታይበት ስብስብ ነው፡፡ የተለያዩ ጉዳዮችን እና ፍላጎቶችን ያካተተ አጀንዳ ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ሊቀርባለቸው ይገባል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

የእኔ የወጣቶች እና የሰብአዊ መብቶች አጀንዳ ጉዳይ በየሳምንቱ ሁልጊዜ የምሰብከው ስለሆነ በደህና ሁኔታ የሚታወቅ ነው፡፡

የ21ኛው ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያ በጣም አንገብጋቢው ችግር የኢትዮጵያ ወጣቶች ችግር እንደሆነ ከብዙ ጊዜ ጀምሬ አምናለሁ፡፡ በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ላይ የተለየ ትኩረት በመስጠት በስፋት ስጽፍበት ቆይቻለሁ፡፡ እንደዚሁም ሁሉ በኢትዮጵያ ውስጥ የሰብአዊ መብቶች እንዲሻሻሉ በተለያዩ መድረኮች ተከራክሪያለሁ እንዲሁም ሰፊ ስብከት አድርጊያለሁ፡፡

ስለወጣቶች እና ስለሰብአዊ መብቶች መከበር ጉዳይ የሚጋሩኝ በርካታ የዲያስፖራ ማህበረሰብ አባላት እንዳሉ እርግጠኛ ነኝ፡፡ ስለሆነም አንዱ ክፍል የሆነውን “የወጣቶች እና የሰብአዊ መብቶች አጀንዳ” በአንድ ላይ ሆነን ረቂቅ እናዘጋጅ እና ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ እንላክላቸው፡፡

በወጣቶቻችን ላይ ያለው ሁኔታ የሚያስፈራ ነው፡፡

እንደ ዩኤስ የሕዝብ ቆጠራ ቢሮ ዘገባ በሶስት አስርት ዓመታት ውስጥ የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር ከሶስት ጊዜ በላይ እጥፍ በማደግ 278 ሚሊዮን በመሆን ሀገሪቱን ከ10 ከፍተኛ የሕዝብ ብዛት ከሚኖራቸው ሀገሮች መካከል አንዷ ያደርጋታል፡፡

የኢትዮጵያ የሕዝብ ብዛት ለበርካታ አስርት ዓመታት በከፍተኛ ሁኔታ ወደላይ እያደገ ነው፡፡ እ.ኤ.አ በ1967 ዓ.ም የሕዝቡ ብዛት 23.5 ሚሊዮን ነበር፡፡ እ.ኤ.አ በ1990 ወደ 51 ሚሊዮን እና በ2003 ዓ.ም ወደ 68 ሚሊዮን አደገ፡፡ እ.ኤ.አ በ2008 ዓ.ም ቁጥሩ ወደ 80 ሚሊዮን አደገ፡፡ እ.ኤ.አ በ2013 የኢትዮጵያ ሕዝብ ብዛት ከ94 ሚሊዮን በላይ እንደሚሆን ይገመታል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ወደ 70 በመቶ (66 ሚሊዮን) የሚሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ እድሜው ከ35 ዓመት በታች ነው፡፡ እ.ኤ.አ ከ1995 ዓ.ም ጀምሮ ዓመታዊ ዓማካይ የሕዝብ እድገት መጣኔው ከ3 በመቶ በላይ ሆኖ ቀጥሏል፡፡

እ.ኤ.አ በ2014 ዓ.ም 45 በመቶ የሚሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ እድሜው ከ15 ዓመት በታች ሲሆን 71 በመቶ የሚሆነው ሕዝብ ደግሞ እድሜው ከ30 ዓመት በታች ነው፡፡ እ.ኤ.አ በ2018 የዚህ ዓይነት የሕዝብ ኮሆርት ግምት ከ75 በመቶ እንደሚበልጥ ጥርጥር የለውም፡፡

ስኢትዮጵያ ወጣቶች ችግሮች በርካታ ጥናቶች ተደርገዋል፡፡ እ.ኤ.አ በ2012 ዓ.ም በዩኤስኤአይዲ በተደረገ ጥናት ኢትዮጵያ ከፍተኛ የሆነ የከተማ ስራ አጥነት የተንሰራፋባት እና እስከ 50 በመቶ ስራ አጥ እንደሆነ እና 85 በመቶ የሚሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ በሚኖርበት በገጠሩ ደግሞ ስውር የሆነ ስራ አጥነት ተንሰራፍቶ እንደሚገኝ ይፋ አድርጓል፡፡ እንደዚሁም ደግሞ እ.ኤ.አ በ2012 በዓለም አቀፍ የእድገት ማዕከል (International Growth Centre) በተባለ ዓለም አቀፋዊ ድርጅት በወጣቶች ስራ አጥነት ላይ በተደረገ ሌላ ጥናት እ.ኤ.አ ከ2010 – 2015 የሚተገበረው የዕድገት እና ትራንስፎርሽን ዕቅድ የወጣቶችን ስራ አጥነት በቀጥታ አያካትትም፡፡

እ.ኤ.አ በ2012 ኢትዮጵያ ከዓለም ከትምህርት ገበታ ውጭ ከሆኑ ሀገሮች ሕዝቦች መካከል በሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡

ከኢትዮጵያ ወጣቶች ውስጥ ስራ አጥ የመሆናቸው ችግር ብቻ ሳይሆን ስራውም ቢገኝ ተቀጥረው ለመስራት የሚያስችል በቂ የሆነ መሰረታዊ የእውቀት ክህሎት የላቸውም፡፡ ወጣቶች በመንግስት ስራዎች ላይ ተወዳድረው ስራ ለማግኘት በስልጠና እና በክህሎት በብቃት እና በፍትሀዊ ውድድር ላይ በመመስረት ብቻ አይደለም የሚገቡት፡፡ ሆኖም ግን ከዚህም ባሻገር የፖለቲካ እና የማህበራዊ ግንኙነት ትስስር እና የፓርቲ አባልነት እንደ መስፈርት ይወሰዳል፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለ ማንኛውም ወጣት በስራ እና በትክክለኛው መንገድ ከሚያገኘው ዲግሪ እና ዲፕሎማ ይልቅ የገዥው ፓርቲ አባል መሆን የበለጠ ጠቃሚ ነው፡፡ ከዚህም በላይ የገጠር ወጣቶች መሬት አልባነት መሆን ከገጠር ወደ ከተማ የሚደረገውን ፍልሰት በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ እንዲሄድ እና ብጥብጥ፣ ስራ አጥነት እና ተስፋየለሽነት እየተንሰራፋ ያለበት ሁኔታን አስከትሏል፡፡

እ.ኤ.አ ጥቅምት 2017 ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ እንዲህ ብለው ነበር፣ “ወጣት ኢንተርፕሪነሮችን ለማፍራት እና የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ለመንባት የ400 ሚሊዮን ተዘዋዋሪ ፈንድ ኢንቨስትመንት በማድረግ በየዓመቱ በመቶዎች እና በሺዎች ለሚቆጠሩ አዲስ ተመራቂ ወጣቶች የስራ እድል የሚፈጠር እና የወጣቱን ስራ የማግኘት እድል ለማሳለጥ ለግል ዘርፉ እገዛ ይደረጋል“ የሚል ንግግር አድርገው ነበር፡፡

በተጨባጭ በመሬት ላይ የሚታየው ግን ኢንቨስትመንቱም አልተተገበረም ወጣቶችም በሕዝባዊ እምቢተኝነት አምጸዋል፡፡ እናም አሁን ያለው ሁኔታ በተጨባጭ ይህን ይመስላል፡፡

እ.ኤ.አ በ2004 በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው አገዛዝ “ብሄራዊ የወጣቶች ፖሊሲ” የሚል ፖሊሲ በማውጣት ከ44 በመቶ በላይ የሚሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከፍጹማዊ ድህነት ወለል በታች እንደሆነ ግልጽ አድርጓል፡፡ የዚህ ዓይነት ድህነት በተንሰራፋበት ሁኔታ ወጣቱ በከፍተኛ ሁኔታ የችግሩ ሰለባ የሚሆን የህብረተሰቡ ክፍል ነው፡፡ ከዚህም በላይ ያ ፖሊሲ ወጣቶች ስራ ለማግኘት የአገዛዙ እና የገዥው ፓርቲ ደጋፊዎች እንዲሆኑ በማስገደድ ባዶ ሰነድ ሆኖ ሸረሪት አድርቶበት እና አቧራ ተኝቶበት ቀርቷል፡፡

እ.ኤ.አ ከ2006 ጀምሮ የኢትዮጵያ የሕግ ባለሞያዎችን በማሰባሰብ ስኬታማ ባይሆንም የሕግ ጥበቃ ፈንድ ለማቋቋም ጥረት አድርጊያለሁ፡፡

እ.ኤ.አ በ2011 ይፋ ያልሆነ የፐብሊክ ፖሊሲ (ህዝብ መምሪያ) የምሁራን ቡድን ለማቋቋም እንዲያግዝ ለበጎ ፈቃደኞች ጥሪ አቅርቢያለሁ፡፡

ለዚህ ጥረት ስኬታማነት ለበርካታ ዓመታት ብዙ ጥያቄዎችን በማቅረብ ጥረት አድርጊያለሁ፡፡ ይህንን ሀሳብ ለተቃዋሚ ቡድኖች ሳይቀር አቅርቤው ነበር ምላሹ ጆሮ ዳባ ቢሆንም፡፡

ሌሎች የተለያዩ ትብብራዊ ጥረቶችን ሞክሪያለሁ ሆኖም ግን ጉዳዩን በውል በመያዝ ስራዬ ብለው አልወሰዱትም፡፡ የእኔ ጥረቶች ለምን እንደወደቁ በርካታ የሆኑ ምክንያቶችን መዘርዘር ይቻላል፡፡ የረዥም ጊዜ ስራ እና የሰብአዊ መብት ትግሉን የእራስ ህይወት አድርጎ መውሰድ ለእያንዳንዱ ሰው ሊከብደው ይችላል፡፡

በኢትዮጵያ ውስጥ የሰብአዊ መብት ጥበቃን ለማሻሻል ሊሰሩ የሚችሉ በርካታ ነገሮች አሉ፡፡ አጠቃላይ የሆነ የዲያስፖራ ሰብአዊ መብት ጥበቃ አጀንዳ ምንም ዓይነት የተለየ ከባድ ችግርን የሚያስከትል አይደለም፡፡

ወደፊት ለመጓዝ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጋር የሚደረጉ ትብብሮች ምን መሆን አለባቸው?

ዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጋር ወደፊት እንዴት መራመድ ይችላሉ? እርሳቸው ከእኛ ጋር በምን ዓይነት ስምምነት ነው መስራት የሚችሉት?

እ.ኤ.አ በ2010 አሁን ላለንበት ሁኔታ ጠቃሚ የሆኑ የተወሰኑ አብሮ የመስራት የስምምነት ሃሳቦችን አቅርቤ ነበር፡፡

በተወሰኑ ጥቂት መሰረታዊ በሆኑ አብሮ የመስራት ሃሳቦች ስምምነት ካደረግን ውጤታማ የሆነ እና የመከባበር ግንኙነት ማድረግ እንደምንችል አምናለሁ፡፡

መረጃን መሰረት ያደረገ እሳቤን እናዳብር፣ ግምትን አሉ ባሌ መሰረት ያደረገን እሳቤ እናስወግድ፣

በእኔ አመላካከት በርካታ ነገሮችን የሚያነሱ እና በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ላይ አሉታዊ የሆነ አመላከከት ያላቸው ሰዎች ግምትን አሉ ባሌን መሰረት ባደረገ መረጃ ላይ ይመሰረታሉ፡፡ ያለምንም ማስረጃ ትችት ያቀርባሉ፡፡ በተጨባጭ መረጃ ላይ በመመስረት እና ስልታዊ የሆነ ጥናት ሳያደርጉ መሰረት በሌላቸው እና በተደጋጋሚ በሚደረጉ ታሳቢዎች እና ግምቶች ላይ በመመስረት ይተነብያሉ፡፡ ታሳቢዎቻቸውን እንደገና ለመመርመር ፈቃደኞች አይደሉም እንዲሁም አዲስ መረጃዎችን ለመጠቀም ከእራሳቸው እሳቤዎች ጋር ቅራኔ ውስጥ ይገባሉ፡፡ ፎርሙላ የመሰለ እሳቤን የመውደድ ዝንባሌ ያሳያሉ፡፡ እናም ነገሮችን ሁሉ ለመስራት አንድ ዓይነት መንገድ ብቻ አለ ወደሚል ዝንባሌ ያመራሉ፡፡

አንድ የቀድሞ አባባል እንዲህ ይላል፣ “እያንዳንዱ ሰው ለእራሱ ሀሳብ ብቻ ነው የሚገዛው ነገር ግን ለእራሱ እውነታዎች ተገዥ አይደለም፡፡“

የእራሳችንን አመለካከቶች እና ሀሳቦች ከተለያዩ ምንጮች ከተሰባሰቡ መረጃዎች በአንክሮ በመገምገም መሰረት አድርጎ መወሰን አለብን፡፡ አድሏዊነታችንን ማስወገድ አለብን፡፡ ክፍት የሆነ አእምሮን ለመያዝ ፈቃደኛ መሆን እና ለረዥም ጊዜ በቆዩ እና ወጥነት በሌላቸው አመለካከቶች እና ታሳቢዎች ላይ ሳንመሰረት ትክክለኛውን መንገድ ተከትለን መጓዝ አለብን፡፡

በዓለም ላይ ለማየት የምንፈልገውን ለውጥ እንሁን፣

የቀድሞ አባባል እንደሚለው አመልካች ጣታችንን በአንድ ሰው ላይ በምንቀስርበት ጊዜ ሶስቱ ጣቶቻችን ወደ እኛው ያመለክታሉ፡፡

ሆኖም ግን ለውጥ በሰው ላይ ይጀምራል፡፡ ጆርጅ በርናርድ ሻው እንዲህ ብለው ነበር፣ “ያለለውጥ መሻሻል አይቻልም፡፡ እናም አስተሳሰባቸውን የማይለውጡ ምንም ዓይነት ነገር ሊለውጡ አይችሉም፡፡“

ብዙዎቻችን እራሳችንን ሳይሆን ዓለምን ለመለወጥ እንፈልጋለን፡፡ በአሳዛኝ ሁኔታ በውስጣችን ያለውን ተቃርኖ አናስተውለውም፡፡

ዓለምን ለመለወጥ ከመቻላችን በፊት የምንለውጥበትን የአስተሳሰብ መንገድ መለወጥ አለብን፡፡

ጋንዲ እንዲህ በማለት አስተምረውናል፣ “በዓለም ላይ ሆኖ ለማየት የምትፈልገውን ለውጥ ሁን፡፡ ያ ለውጥ የሚመጣው ከአእምሮ እና ከልብ ነው፡፡ በመቀጠልም እንዲህ አሉ “እምነቶችህ ሀሳቦችህ ይሆናሉ፣ ሀሳቦችህ ቃላቶችህ ይሆናሉ፣ ቃላቶችህ ተግባሮችህ ይሆናሉ፣ ተግባሮችህ ደግሞ ልማዶችህ ይሆናሉ፡፡ ልማዶችህም እሴቶችህ ይሆናሉ፣ እሴቶችህ ዕጣ ፈንታዎችህ ይሆናሉ“ ነበር ያሉት፡፡

ወኔ ያለው ተናጋሪ ለመሆን ብዬ የመስበክ ወይም የማስመሰል ዓላማ የለኝም፡፡ ሆኖም ግን አብዛኞቻችን ግልጹን ነገር እንረሳዋለን፡፡

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!   

ሚያዝያ 17 ቀን 2010 ዓ.ም

የእስክንድር ነጋ የውጪ ሃገር ጉዞ!

( ይድነቃቸው ከበደ )

ከዛሬ 12 ዓመት በፊት በህወሃት መራሹ የኢህአዴግ “መንግስት” የደህንነት ተቋም አንድ አስገራሚ ገጠመኝ በቦሌ ሃየር መንገድ ተከስቶ ነበር ፤ ነገሩ እንዲህ ነው የደህንነት ተቋሙ ከያዘው ጥቁር መዝገብ ውስጥ “እስክንድር ነጋ” የሚል ስም ተጽፎ ይገኛል ።በወቅቱ የደህንነት መስሪያ ቤት አለኝ ባለው መረጃ “እስክንድ ነጋ” ያሳፈረው አውሮፕላን ጉዞውን ለማቅናት ማኮብኮቢያውን ለቆ ሃየር ላይ መሆኑ ይደረስበታል፤ በወቅቱ ተሳፋሪ የጫነው አውሮፕላን በአስቸኳይ ወደነበረት መሬት እንዲያርፍ በደህንነት ሰዎች በሬዲዮ ግንኙነት ይገደዳል ፤ “እስክንድር ነጋ” ያሳፈረው አውሮፕላን በተሰጠው ቀጭን ትእዛዝ ወደ ነበረበት ይመለሳል ።

በወቅቱ በተሳፋሪዎቹ ዘንድ ድንጋጤ እና ወከባ ይፈጠራል፤ እነዚያ “ጎበዝ” የደህንነት ሰዎች በመጣደፍ መሳሪያቸውን አቀባብለው ፣ የሬዲዮ ግንኙነት እያደረጉ በከፍተኛ የጀብደኝነት ሰሜት በአውሮፕላን ውስጥ “እስክንድር ነጋ” ፍለጋ ይጀምራሉ ጊዜም አልፈጀ ወዲያውኑ በእነኚሁ “ጎበዝ” የደህንነት ሰዎች ተፈላጊው ሰው መያዝ እሁን ይሆናል ። በተደረገው ጥብቅ ፍተሻ እና ክትትል ” እስክንድር ነጋ” ሳይሆን ‘እስከዳር ነጋ” የተባለች ሴት ተጓዥ ሆና ትገኛለች ። የቸኮለች አፍሳ ለቀመች አለ የሃገሬ ሰው መባሉ ለምን ሆነና ?! የእለቱ በረራ በዚህ ምክንያት ተስተጓጉሎ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው። የዚህ ጽሁፍ አንባቢያን ይህ ከላይ የተገለጸው ምናባዊ ተረት እንዳይመስላችሁ በሃገሬ እሁን የሆነ ክስተት እንጂ ።

ጋዜጠኛ እና የሰብዓዊ መበት አቀንቃኝ የሆነዉ እስክንድር ነጋ ! በአገዛዙ ስርዓት በተደጋጋሚ ለእስር እና ለከፍተኛ እንግልት የተዳረገ ብርቱ አገር ወዳድ ዜጋ ነው። በዚያው ልክ ተደጋጋሚ አሰቃቂ የእስር ጊዜ አሳልፎ የደረሰበት በደል እና መከራ ወደ ጎን በመተው “ከእኛ የሚጠበቀው በትግላችን ጽናት ፣ በአካሄዳችን መቻቻል፣ በመንፈሳችን ፍቅር፣ በአስተሳሰባችን ሚዛናዊነትና በተግባራችን ሠላምን ይዘን ወደፊት መጓዝን ነው ” በማለት በቅርብ ከእስር መፈታቱን አስመልክቶ ባስተላለፈው መልእክት አጽኖት በመስጠት ፤ መቻቻልን ፣ ፍቅርን፣ እና ሰላምን እንዲሁም ይቅር ባይነት እየሰበከ ይገኛል ። ከእስር ከተፈታ በኋላ በተገኘው አጋጣሚ ይህን ሃሳቡን በተደጋጋሚ ከመግለጽ ወደኋላ ብሎ አያቅም ።

ይሁን እንጂ ለሰላም ፣ለፍቅር እና ለይቅር-ባይነት እጅን የዘረጋው ጋዜጠኛ እና የሰብዓዊ መብት አቀንቃኝ እስክንድር ነጋ ፤ በአገዛዙ ስርዓት በኩል አሁንም የተሰጠው ምላሽ ከወትሮው የተለየ አይደለም ። ” ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳም ” እንደሚባለው በዶ/ር አብይ አህመድ “የሚመራው” መንግት አሁንም የዜጎች የመንቀሳቀስ እና ከሃገር ወደ ሃገር የመዘዋር መብት እየገታ ይገኛል። ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ አስፈላጊውን የውጪ ሃገር ጉዞ ሕጋዊ ሰነድ ያሟላ ቢሆንም ከሃገር እንዳይወጣ ታግቷል ፤ ይህ ደግሞ መንግስታዊ ውንብድና ነው ። እርግጥ ነው የዚህ አይነት መሰል መንግስታዊ አሻጥር ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ በሌሎች ሰዎችም ላይ ደርሶ እንደነበር የሚታወቅ ነው።

ነገሩን ይበልጥ አስገራሚ የሚያደርገው ለዜጎች መብት መከበር ጠንክሬ እሰራለው የሚሉት ዶ/ር አብይ አህመድ ፤ እሳቸው የሚመሩት የሚንስትሮች ምክር ቤት አቶ አባዱላ ገመዳ የብሔራዊ ደህንነት ጉዳዮች አማካሪ አድርጎ በሾመ ማግስት ፤ የብሔራዊ ደህንነት ተቋም የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የውጪ ሃገር ጉዞ በማስተጓጎል ሥራውን እንደቀድሞ በይበልጥ አጠናክሮ ቀጥሏል ። ይህም የደህንነት ተቋሙ የሚመራው ወይም እየተመራ ያለው በማን እንደሆነ የሚያመላክት ከመሆኑ ባሻገር ፣ ተቋሙ አሁንም የዜጎችን ደህንነት እና የአገር ሉዓላዊነት ከመጠበቅ ይልቅ ፤ ከአገዛዙ ስርዓት በፖለቲካ አመለካከት ብቻ የተለዩ የሰብዓዊ እና የዲሞክራሲ መብት ተሟጋቾች እንዲሁም አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ሰላማዊ እና ሕጋዊ የእለት ከእለት እንቅስቃሴ ማወክ ዋንኛ ሥራው እንደሆነ የሚያመላክት ጭምር ነው ።

” ድል ለዲሞክራሲ !! ”
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !!!

ጎንደር አብይን እንዴት ተቀበለችው? (ጌታቸው ሺፈራው)

ጌታቸው ሺፈራው

PM Dr. Abiy Ahmed visiting Gondar.

ጠዋት 1:30 አካባቢ በመኪና እየዞሩ እየለፈፉ ነው። ሕዝብ ጠቅላይ ሚኒስትሩን እንዲቀበል። ሆኖም ሰሞኑን ለመቀበል የሚገቡት ሰዎች ተለይተው እንደታወቁ፣ ወረቀትም እንደደረሳቸው ሕዝቡ ሰምቷል። ካድሬ ነው የሚሰበሰበው ተብሏል። ስለዚህ ለመሄድ ፈቃደኛ አይደለም።

ወደ ፋሲለደስ ስቴዲየም ከመግባቴ በፊት ቡና ልጠጣ ተቀምጫለሁ። ሁለት ወጣቶች ቡና እየጠጡ ያወራሉ። “በሙሉ ካድሬ ነውኮ የሚገባው” ይላል አንዱ።

“እኔ ለምሳሌ ለመታዘብ ልገባ ነው፣ ለምን አትገቡም?” አልኩት። “ምን ላረግ? የተለየ ነገር አይመጣም ባክህ። ያው ነው! ሕዝቡም መረረው መሰለኝ ከማሾፍ ውጭ ሌላ ነገር አያደርግም።” አለኝ። ጓደኛው ዶ/ር አብይ ስለ ወልቃይት በተናገረው እንደበሸቀበት አወራኝ።

እነሱን ተሰናብቼ ወደ ስቴዲዬሙ ሳቀና መሃል ላይ ባጃጅ አገኘሁ። ዝግ ስለሆነ የተወሰነ ርቀት ብቻ ነው የሚሰሩት።

“ስቴዲዬም ልሄድ ፈልጌ ነው። የት ድረስ ትወስደኛለህ?”

“እስከ አውቶፓርኩ አደርስሃለሁ”

“አንተ አትገባም እንዴ?”

“ምን ያደርግልኛል? ለወጣቱ ብድር ያመጣል?”

“እኔ እንጃ! የሚባለውን ከሰማህ ብየ ነው።”

“የሚባለው ምን ያደርግልኛል?”

ምንም ሳልመልስለት ወርጄ ወደስታዲዬም።

የመጀመርያውን የፍተሻ መስመር አለፍኩ!

ሁለተኛው የፍተሻ መስመር ላይ ስደርስ በርካታ ሰልፎች አሉ። ሰልፈኞቹ ፊት ለፊት በርካታ አማራ ክልል ልዩ ኃይል አለ። ከእነሱ ቀጥሎ ፈደራል ፖሊስ ይታያል።

እንደመጀመርያው ፍተሻ መስመር መስሎኝ በተናጠል ላልፍ ስል “ተሰለፍ” ተባልኩ። ተማሪዎች በየ ትምህርት ቤታቸው ተሰልፈዋል። ገበሬዎች በየ ወረዳቸው ተሰልፈዋል። “አርማጭሆ፣ ወገራ፣ ደንቢያ… ወደዚህ!” ይባላሉ። የጥቃቅንና ሌሎች አደረጃጀቶች አሉ።

ፖሊሱን “እኔ በግል ነው የመጣሁት። ማን ጋር ልሰለፍ አልኩት?”

ከፖሊሱ ጎን ሆኖ ተሰላፊውን በየ ወረዳው የሚጠራ ካድሬ “እንዴት በግል?” ብሎ ጠየቀኝ።

“የከተማው ነዋሪ በግሉ መጥቶ መከታታል አይችልም?” አልኩት። ግራ ገባው! “ሰው ግን ምን ነክቶት ነው የማይደራጀው?” ብሎ መሰለኝ። የካድሬ ነገር።

ፖሊሱም በቡድን ነው ሲያሰልፍ የቆየው። እንደኔ ብቻቸውን የመጡ የተወሰኑ ሰዎች ከኋላየ ቆመዋል። ፖሊሱ በቡድን አሰልፍ ስለተባለ “በቃ ከአንዱ ቡድን ግባ! ብቻህን ማለፍ አትችልም” አለኝ።

ወደ ግራዬ ሳይ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ተሰልፈዋል። በቀኝ በኩል አርሶ አደሮች ተሰልፈዋል። ህፃናት ጋር መሰለፉ ትንሽ ከበደኝ። ግራር መስየ ልታይ ሆነ። ፖሊሱም ጭንቀቴ ገባው መሰለኝ።

“በቃ ከአርማጭሆ ጋር ተሰለፍ! የአርማጭሆ ወረዳ ነህ” ብሎ ሳቀብኝ። በአይሱዙ ተጭነው ከመጡት የአርማጭሆ ገበሬዎች ጋር ተሰልፌ ገብቻለሁ።

ወደ ስቴዲዬሙ ስገባ ከውጭ ካየሁት በባሰ በተማሪዎች፣ በእናቶችና ገበሬዎች ተሞልቷል። ከጥላ ፎቁ ጎን ያለው አንድ አካባቢ በሙሉ ተማሪ ነው። ትንሽ እንደተቀመጥን ሙዚቃ ተከፈተ።

ማረሻው ምንሽር መጎልጎያው ጓንዴ፣

የእነ ስበር ሀገር ወልቃይት ጠገዴ!

ወዲያውኑ ደህና ሲሰራ የነበረውን ሞንታርቮ ነካክተው አጠፉት። በድንጋጤ አበላሹት መሰለኝ። ተሰብሳቢው ገብቶታል። ሙዚቃው መቋረጥ የለበትም ብሎ አፏጨ።

የተቀባን፣ የገዱንም የአብይንም ንግግር በደንብ ማዳመጥ አልተቻለም። ሰው አብይ ተናግሮ ሳይጨርስ መውጣት ጀመረ። ዶ/ር አብይ ተገድዶ ነው የመጣው። ትግራይ ክልል ያደረገው ንግግር ብዙ ሰው አላስደሰተም። ብአዴን ተጨንቆ ሰንብቷል። የወልቃይት ጥያቄ እንዳይነሳበት። ይች ጥያቄ በአለቆቹ ታስኮረኩመዋለች። ስለዚህ አደራጅቶ ማስገባት አለበት። ተማሪ፣ ጥቃቅንና አነስተኛ፣ ገበሬ…። ተደራጅቶ የሚገባውን ለማመላለስ የጎንደር መኪና ባለሀብቶች ግዴታ ተጥሎባቸዋል። የአሽከርካሪ ማሰልጠኛዎችም እንዲሁ።

ይህ ግን በቂ አልነበረም። ትናንት ከሰዓት የከተማው ባለስልጣናት የቅማንት ጥያቄ የሚያነሱትን ሰብስበው ነበር። ዛሬ የወልቃይት ጥያቄ በባነር ያሰሩ ወጣቶች እንዳይገቡ ሲከለከሉ፣ የቅማንት ተፈቅዷል። ለወልቃይት ጥያቄ አፀፋ መሆኑ ነው። በዚህ ላይ የአማራ አክቲቪስት ነኝ የሚለው ሁሉ አጋጣሚውን እንዴት መጠቀም እንዳለበት ጠንቅቆ ያወቀ አይመስለኝም። አብይ “አዲስ አበባ የኦሮሚያ አይደለችም” ብሎ ተናግሮ አምቦ ላይ ስብሰባ ቢያደርግ እነ ጃዋር ካድሬውን ሳይቀር ያስጮሁታል። ወደዚህ ሰፈር ግን ቁሞ ቀርነት እየበዛ መሰለኝ። (ስለ አማራ አክቲቪስቶች ጉዳይ ሌላ ጊዜ በስፋት ብመጣ ይሻላል) ብአዴን አብይን ሹልክ አድርጎ ከስቴዲየም ይዞት ወደ ጎሃ አቅንቷል። በመጠኑም ቢሆን ለአብይ ጥሩ ሆኖለታል። ንግግሩን ሳይጨርስ ከወጣው ሕዝብ ውጭ የበረታ ተቃውሞ አልገጠመውም። ግን ከሕዝብ ጋር ተወያየሁ ለማለት አያስችለውም። የብአዴን ጉዳይ እንደሁሌው አሳፋሪ ነው። የ9 እና የ10 አመት ህፃናትን ሳይቀር ሰብስቦ አብይን ተቀብሎታል።ይህን ካወቀ አብይም የሚገረም ይመስለኛል! ያም ሆነ ይህ በአማራ ክልል፣ የአብይ ካድሬዎቹ የብአዴን ካድሬዎች ናቸው። አብይን የተቀበሉት ድሮ መለስን በየ ስቴዲየሙ ሲቀበሉት የነበሩት አደረጃጀቶች ናቸው። ከሕዝብ ጋር ተወያየሁ ማለት አይችልም።

“የወልቃይት ጉዳይ እና የኤርትራ ጉዳይ” (ኤርሚያስ ለገሰ)

(ማስታወሻ – ይሄ መጣጥፍ የተዘጋጀው የዛሬ ሁለት አመት ጥቅምት 2016 ነበር። ያቀረብኩት ደግሞበሂውስተን ቴክሳስ ለህዝብ በተዘጋጀ መድረክ ላይ ነው ከአሁኑ ወቅታዊ ሁኔታ ጋር ይሄዳል ብዬ ስላሰብኩበፌስቡኬ ላይ ለጥፌዋለሁ። ከዚህ በተጨማሪ ይህ ፅሁፍ ከራሴ ውጭ የማንንም አቋም አያንፀባርቅም።)

“Wolqayit Factor! & Eritrean-Factor!”

ኤርሚያስ ለገሰ

ላለፉት ሩብ ክፍለ ዘመናት ህዉሃት በብሔር ብሔረሰቦች ዲሞክራሲያዊ መብቶች እየማለና እየተገዛተ ዝህቡን ለማታለል ብሎም ለመለያየት ቢሞክርም ያሰበውን አላማ ሊያሳካ አልቻለም። ለሁሉም ግልጽ እንደሆነው በአገራችን የሰላም እጦት ከጫፍ እስከ ጫፍ እየታየ ነው። የስርአት ለውጥና የነፃነት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት የተለያዩ የትግል ስልቶች ተቀርፀው ወደ ትግባር ተቀይረዋል። እየተደረጉ ያሉት ትግሎች አስተሳስረን ስንመረምር አሁን ኢትዮጵያ ያለችበት ሁኔታ ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ወደ መቃብር የወረደበት ሆኖ እናገኘዋለን። ከዚህ በኋላ ህዉሃት መንግስታዊ የበላይነትን ባገኘበት ሁኔታ የምርጫ ፖለቲካ አጀንዳው ተዘግቷል። የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች እንዳሉት በምርጫ ፖለቲካ መቃብር ላይ ጥቁር አበባ ተቀምጦበታል። መቃብር ፈንቅሎ ትንሳኤ ይፈፀም ይሆን ለወደፊት የምናየው ይሆናል።

Ermias Legesse, author and ESAT TV and Radio contributor

ተስፋ አለኝ።

ህዉሃት መራሹ ድርጅት በየጊዜው የሚሰጠው ድርጅታዊ መግለጫና እሱን ተከትሎ እየተወሰደ ያለው እርምጃ ተስፋ የሚያስቆርጠው የአገሬው ህዝብና የአለም መንግስታትን ብቻ አይደለም። የስርአቱ መስራችና ባለቤት የነበሩ እንዲሁም በተለያየ ከፍተኛ የፖለቲካና ወታደራዊ ስልጣን ላይ የነበሩትን ጭምር ነው። በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ የሚገኙ የኢትዮጵያ ሚዲያዎችን ያጨናነቁት ጄኔራል አበበ እና ጄኔራል ፃድቃን በስርአቱ ምላሽ ላይ ምን ያህል ተስፋ እንደ ቆረጡ መገመት ይቻላል። “የስርአት ችግር ስላለ፣ ኢህአዴግ የተቀባይነት ችግር ስላጋጠመው የስርአት ለውጥ መምጣት አለብት!” ብሎ የተናገረው አንደበታቸውና የከተበው ብዕራቸው ዞር ብለው ሲመለከቱ ማፈራቸው የሚቀር አይደለም። እነ ፃድቃን “ሀገሪቷ የመበታተን አደጋ ሊያጋጥማት ይችላል” ቢሉም የቀድሞ የትግል ጓዶቻቸውና የስልጣኑ ባለቤቶች “ህገ-መንግስታዊና ዲሞክራሲያዊ የፖለቲካ ስርአት በጽኑ መሰረት ላይ ተገንብቷል” የሚል ዲስኩር ያሰማሉ።

እነ ጆቤ “ህዝቡ በተስፋ እጦት ውስጥ ገብቷል” ብለው ሲፅፉ በተቃራኒው እነ አባይ ፀሀዬ “የአገራችን ህዝቦች በኢትዮጵያ የፈነጠቀውን የልማትና የዲሞክራሲ ጮራ ተማምነው በለመለመ ተስፋ ወደፊት ይመለከታሉ” የሚል ዘመን ተሻጋሪ ማብራሪያ ይሰጣሉ።  እነ ፃድቃን በቀኝ ሆነው የመቶ ፐርሰንት ምርጫ በህዝብ ማላገጥ ነው” በማለት ብዕራቸውን ሲያነሱ በግራ የተሰለፉት እነ በረከት “ኢህአዴግ ስራ በምርጫ ካርድ የተሰጠውን ሃላፊነት አደራ ለመወጣት ቆርጦ ተነስቷል” ይሉናሉ። አራንባና ቆቦ!!

እዚህ ላይ በሁለቱ የቀድሞ የጦር አዛዦችና የህዉሃት መራሹ መንግስት ሃይሎች መካከል በሁሉም ጉዳይ ተቃርኖ ውስጥ እንደገቡ የሚያስብ ካለ በደንብ ተሸውዷል። ሁለቱም ሃይሎች የህዉሃትን ብሎም የትግራይ ህዝብ ጥቅም ይነካል ብለው በገመቱት ጉዳይ ላይ ተመሳሳይ አቋም አላቸው። ከዚህ አንፃር በቅድሚያ ሊነሳ የሚችለው በቀድሞ በትግራይ አስተዳደር ስር ያልነበሩና ዛሬ የተካለሉት ወልቃይትን የመሳሰሉ ቦታዎች ናቸው። የጦር አዛዦቹም ሆነ የህዉሃት ታጋይ ባለስልጣናት መጀመሪያ ሰሞን የወልቃይትና ተመሳሳይ ቦታዎች ፈጽሞ አንዳይነሱ፤ የሚዲያ ትኩረት እንዳያገኙ አድርገው ነበር። በጽሑፎቻቸውም ሆነ በመግለጫዎቻቸው በየትኛውም ቦታ ከመግለጥ ተቆጥበው ነበር። የቅማንትን ጉዳይ አጉልቶ የገለጠው “ጆቤ” ወልቃይት ላይ ሲደርስ የብዕሩ ቀለም በሚያስፎግር ሁኔታ አልቆበት ነበር። በኦሮሚያ ጥያቄዎች ላይ በምናቡ ከፈጠራቸው የኦሮሞ ልጆች ጋር ማውራቱን ሊነግረን የፈለገው ጄነራል አበበ ጠገዴና ጠለምት ፀለምት(ጨለማ) ሆነውበት ግድግዳ ተስታኮና ተንፏቆ ሲያልፋቸው ተመልክተናል።

ሁኔታዎች እየገፋ ሲመጡና የትግሉ ማዕከሉ “ወልቃይት” መሆኑ ሲረጋገጥ እየተንፏቀቁም ቢሆን የወልቃይትን አጀንዳ ማንሳት ጀመሩ። ለምን ከዚህ በፊት ልታነሡት አልሞከራችሁም ሲባሉ “ይሔ ትልቅ ጉዳይ አይደለም:” የሚል ምላሽ ሰጡ። ቁምነገሩ እዚህ ጋር ነው። ለእነ ጄነራል ፃድቃን የቅማንት ጉዳይ ትልቅ እንደሆነ አድርገው ሊያገኑት ሲሞክሩ የማያቋርጥ የህዝብ ደም እየፈሰሰበት ያለውን ወልቃይት ንቀው እንደተውት ሊያሳዩ ሞከሩ። እነዚህ ሰዎች ይህን ምላሽ ሲሠጡ ወልቃይት “የትግል ማዕከል” እና “የኢፍትሃዊነት ማሳያ” መሆኑን ጠፍቷቸው አይደለም። ልክ አቶ መለስ በኢትዮ- ኤርትራ ጦርነት ወቅት ካድሬዎች “ለምን ባድመን ለመሰለ ቁራሽ መሬት የ10ሺዎች ደም ይፈሳል?” ብለን ሥንጠይቀው እጁን እየጠበጠበ “ባድመ የትግላችን ማዕከል የሆነችው የኢፍትሐዊነት ማሳያ ስለሆነች ነው” በማለት የንዴት ምላሽ ሰጥቷል። በመሆኑም ባድመ የኤርትራ መንግስት በሃይል ስለወሰዳት መጀመሪያ ወደቀድሞው ቦታዋ ትመለስና ህጋዊ ውሳኔ ይሰጥባት እንደተባለ ሁሉ የወልቃይትም ተመሳሳይ ነው። ወልቃይት “ኢፍትሃዊነት ማሳያ” ስለሆነች መጀመሪያ ወደቀድሞው ታሪካዊ ባለቤቷ ትመለስና ሌሎች የህዝብ ጥያቄዎች ቂም በቀል በማይፈጥሩና የጋራ ድል (Win_Win) በሚያረጋግጡ መልኩ ይፈቱ ማለት የአባት ነው። ይገባልም። ይህ ካልሆነ ግን ምንአልባት ከባድመው ባልተናነሰ በ100ሺዎች የሚጠጋ ህይወት የሚወድቅበትና ደም መቃባቱ የሚያባራ ሊሆን ይችላል።

በመቶ ሺዎች ሊገደሉ ይችላሉ የሚለውም ተራ ማስፈራራት አይደለም። ህዉሃት በተለይም የአማራ ተወላጆች ላይ የቋጠረው የቂም ቋጠሮ ከዚህ በላይ ሊገድል እንደሚችል ፍንጭ የሚሰጥ ነው። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር አሰፋ አቢዩ ከሳምንታት በፊት በሰጠው መግለጫ “99 ፐርሰንት ንፁህ ናቸው። እርምጃ የምንወስደው በተቀሩት ላይ ነው” በማለት ይፋ አድርጓል። አሁን ባለው የአማራ ክልል ንቅናቄ ከ5 ሚሊዮን የአማራ ተወላጆች በቀጥተኛ እየተሳተፉ እንደሆነ ዝቅተኛ ግምት ቢወሰድ እንኳን በኮሚሽነር አሰፋ ስሌት መሠረት ከ50 ሺህ በላይ ሠዎች እርምጃ ይወሰድባቸዋል። ህዝባዊ ማዕበሉ እየሰፋ ሲሄድ በአስቸኳይ የስርአት ለውጥ ካልመጣ እርምጃ የሚወሰድበት የአማራ ተወላጅ ሁለትና ሶስት እጥፍ ይሆናል። ለህዉሃት “የትግል ማዕከል” የሆኑትን ቦታዎች አሳልፎ መስጠት መቃብሩን በጥልቀት የመቆፈር ያህል ስለሚመለከተው በጅምላ ከመግደል የሚመለስ አይሆንም።

በእኔ እምነት ኢትዮጵያ ውስጥ የተቀጣጠለው ህዝባዊ ማዕበል ከህዉሃት ህልውና አንጻር በርካታ ዋልታዎች (Multi- Polar) ያሉት ቢሆንም፣ የዋልታዎቹ ምሰሶ ወልቃይት (Wolqayit Factor) ተደርጎ የሚወሰድ ነው። የኦሮሚያ፣ ጋምቤላ፣ ኮንሶ የተነሱት እምቢተኝነቶች ትላልቅ ዋልታዎች ቢሆኑም ህዉሃት ልቦና ገዝቶ በህይወት መቆየት ከፈለገ ወደ ምሶሶነት ሳያድጉ በተራዘመ ሂደት ሊያዳፍናቸው ይችላል። ለምሳሌ ህዉሃት ኤርትራ ላይ የሚያስበው (Eritrian-Factor፡ ኤርትራ በጦርነት ማሸነፍና አስመራ ላይ አሻንጉሊት መንግስት መመስረት)ከተሳካና ህዉሃት ኢትዮጵያን መምራት ከተነሳው የኦሮሚያን ጥያቄ እስከ ጫፍ ሊወስደው ይችላል። ይህም በኦሮሞ ጉዳይ የተደራጁ የፖለቲካ ፓርቲዎችንና አክቲቪስቶችን የመከፋፈል እድሉ ሰፊ መሆኑ አይቀርም። ህዉሃት እስከ ጫፍ የሚወስደውን ፍላጎት ለመቀበል አዳዲስ ሃይሎች (Emerging Powers) የሚፈልቁበት ሁኔታ ይፈጠራል። በመሆኑም ህዉሃት በሚቀደው ሀገር የማፍረስ ቦይ የሚፈሱ ቁጥራቸው ቀላል ያልሆኑ ሰዎች ይኖራሉ።

እንደ እውነቱ ከሆነ ሁለቱ የህዉሃት የቀድሞ ጦር አዛዦች በተለይም ሌ/ጄነራል ፃድቃን ወልቃይትና ሌሎች “የኢፍትሐዊነት ማሳያ” ቦታዎችና “የትግል ማዕከሎች” በተመለከተ ያስቀመጡት ምላሽ ህዝባዊ እምቢተኝነቱን የበለጠ ነዳጅ የሚጨምር ነው። ጄነራል ፃድቃን መጀመሪያ አካባቢ ባቀረባቸው ጽሁፎች በብልጣብልጥነት ሊያልፈው ቢፈልግም ቦታዎች ይበልጥ “የትግሉ ማዕከሎች” መሆናቸውን በህዝባዊ ማዕበሉ ሲመለከት ከድርቅና በተሻገረ አይን አውጣነት ለአዲስ አድማስ ጋዜጣ እርስ በራስ የተምታታ ምላሽ ሰጠ። ይህ የጦር መኮንኑ ምላሽ የአማራ ህዝብ ትግልና መነቃቃት ከደረሰበት ደረጃ ጋር ፍፁም የማይመጥን ነው። የአሁኑ የአማራ ትግል የደረሰበት ደረጃ ፍልሚያው ተጧጡፎ አድማሱን በመስፋት ቅኝቱ ሙሉ ለሙሉ ተቀይሯል። ከአስር አመት በፊት ሃሰን ዑመር አብደላ በመጣጥፋቸው እንደገለጡት ቅኝትና ምቱ ከተቀየረ እስክታውም መቀየር አለበት። በመሃመድ አህመድ የትዝታ ቅኝትና ምት ጥላሁን ገሠሠን “አንቺን ነው! ሰማሽ ወይ” የሚለው አይደነስም። በ “እምበር ተጋዳላይ” አጨፋፈር ስልት የይሁኔ “ሰከን በል” አይጨፈርም። እንደዚህ ከሆነ በአራዳ ቋንቋ ሽወዳ ይሆናል። አሁን ትግሉ በደረሰበት ደረጃ ደግሞ ውሽልሽል ምክንያት ሸውዶ ማለፍ የሚችልበት ወቅት ላይ አይደለንም። አለበለዚያም እውነት መድፈር ካልተቻለና የሚያስፈራ ከሆነ (ኮንስቲትወንሲያቸውን እንደሚያጡ ይገባኛል) ምላሽ አለመስጠት ይቻል ነበር። ፃድቃን ሊጠቀምበት የፈለገው “የሽወዳ ፖለቲካ” ህዝባዊ እምቢተኝነቱን አቀጣጥሎ መስዋዕትነቱን ከመጨመሩ ባሻገር በሌሎች ያቀረባቸው የመፍትሄ ሃሳቦችም ላይ በጥርጣሬ እንዲታይ ያደረገ ነው።

ለማንኛውም ሌ/ጀነራል ፃድቃን ገ/ትንሳይ “የትግሉ ማዕከል” በሆነው ወልቃይት ዙሪያ ለአዲስ አድማሱ ጋዜጣ የሰጠውን መግለጫ በመመልከት ፍርዱን እንስጥ። አዲስ አድማስ ጋዜጣ “በሰሜን ጎንደር አካባቢ ያለው ተቃውሞ በተለይ ከ “ወልቃይት አማራነት” ጋር የተያያዘ ነው። የወልቃይት የማንነት ጥያቄ ጉዳይ በምን አግባብ ነው መፈታት ያለበት?” ለሚለው ጥያቄ የሚከተለውን ምላሽ ሰጥቷል።

“እኔ የወልቃይት ጉዳይ ለአንዳንድ ፖለቲካዊ አላማዎች ሽፋን ነው ብዬ ነው የማምነው። እንዴት ነው የሚፈታው ላልከው እኔ የሚታየኝ ህገ- መንግስቱን መሠረት አድርጎ ነው። በመጀመሪያ ደረጃ ይሔ ትልቅ ጉዳይ መደረግ አልነበረበትም። ህዉሃትና ብአኤን ተመካክረው መፍታት የሚችሉበት ደረጃ ላይ መድረስ ነበረባቸው።…. በህጋዊ መንገድ ስንሄድም ህገ-መንግስቱን መሰረት አድርጎ መፍታት ያስፈልጋል ነገር ግን ክልሎች በሚወሰኑበት ወቅት ከፍተኛ የፖለቲካ ውሳኔ ሰጪ አካል ውስጥ ነበርኩ። በወቅቱ ቋንቋና የህዝብ አሰፋፈርን መሰረት አድርገን እንወሰን በሚል ነው የወሰነው። በዚህ መሰረት ደግሞ የተወሰነው ተወስኗል።”

አዲስ አድማስ ጋዜጣ ቀጥሎ የጠየቀው “በወቅቱ ወልቃይት እንዴት ነው ወደ ትግራይ የተላከው?” በማለት ነበር። ሌ/ጄነራሉ እንዲህ በማለት አስገራሚ፣ አሳዛኝና እርስ በራሱ የሚደባደብ ምላሽ ሰጠ።

“አሁን እየጠየከኝ ያለኸው መረጃ ነው። ይሄን መረጃ አሁን አላስታውሰውም። እንደዚህ  ሆኖ ነበር ብዬ ለማለት አልችልም። የተጠቀምንበት አቅጣጫ ግን የፌደራሊዝሙን መነሻ ነው። የህዝቦች ቋንቋና ባህልን መነሻ አድርገን ነው የከለከልነው። እኔ እስከማውቀው ድረስ እዚያ አካባቢ ያለው አብዛኛው ህዝብ ትግርኛ ተናጋሪ ነው። ባህሉ የትግራይ ነው። በትግራይ ውስጥ ሊካተት የሚችል ህዝብ ነው። የሆነውም በዚህ አግባብ ነው።”

በመሆኑም እነዚህ የህዉሃት ጦር ጄነራሎች “ህዉሃት አደጋ ላይ መውደቁን ሲያዩ ሊታደጉት መጡ” የሚለውን አባባል ለጊዜው እንተወውና የጎደላቸውን ነገር በጨዋ ቋንቋ እንንገራቸው።

ከጄኔራል ፃድቃን አስተያየት ሳልወጣ አድናቆቴን መግለጽ የምፈልግበት አንድ አረፍተ ነገር አለ። ጄኔራሉ በሌሎች የህዉሃት ታጋዮች ባልተለመደ መልኩ አሁን ያለውን ሁኔታ ሲገመግሙ “የትግራይ ህዝብ በተለይም በከተሞች አካባቢ በሌሎች ማህበረሰቦች የመገለል ሁኔታ አጋጥሞታል። መተማመኛውንም የስልጣን የበላይነት አስጠብቆ ማቆየትና በመከላከያና ሌሎች የፀጥታ ሃይሎች ተከልሎ መኖር” እንደሆነ ገልጧል። ይሄንን ግምገማ ሙሉ በሙሉ የምቀበለው ነው። ለረጅም ጊዜያቶች ይሄ ችግር እየመጣ እንደሆነ ደጋግመን ስንለፈልፍ በህዉሃት ጎራ ያሉ ሰዎች “ዘረኞች” የሚል ታፔላ ተለጥፎልን ነበር። ዛሬ የጦር መኮንኑ በግላጭ ሲያወጣው በህዉሃት መንደር የተፈጠረ ብዙም መንጫጫት አይታይም። ታዲያ! ጄኔራል ፃድቃን በዚህ ጉዳይ ላይ ይሄን ያህል ርቀት መጓዝ ከቻለ ከጥያቄው ጋር አብረው ለሚነሱት ሌሎች ጥያቄዎች ምላሽ ቢሰጥበት እኛንም ከስድብና ውርጅብኝ ያድነናል። ጥያቄው የትግራይ ህዝብ በተለይ በከተሞች ውስጥ በሌላው ማህበረሰብ እየተገለለ መሄዱ እውነት ሆኖ ሲያበቃ፤ የመገለሉ መንስ ኤና መሰረታዊ ምክንያት ምንድነው? መገለሉስ ከመቼ ጀምሮ የተፈጠረ ነው? ተጠያቂው ማነው?…. ወዘተ የሚሉ ናቸው። ይህንን ቁልፍ ጉዳይ መመለስ ከተቻለ ወደ ቁልፍ መፍትሄው የምንሄድበት መንገድ አልጋ በአልግስ ይሆናል።

የትግራይ ኤሊቶች፣ የህዉሃት የቀድሞ የጦር ጄኔራሎችም ሆነ የቀድሞ ታጋይ ባላስልጣናት ከህዉሃት በፍጥነት ተፋተው ለአዲስ የስርአት ለውጥ ዝግጁ የማይሆኑባቸው ሌሎች ተጨማሪ መሰረታዊ ምክንያቶች አሏቸው። ከዚህ ውስጥ የቅድሚያ መስመር የምትይዘው ኤርትራ ናት (Eriteria-Factor)። ህዉሃት ከኢርትራ ጋር የገባበት ጦርነት ፍፃሜ የረጅም ጊዜ የመጠባበቂያ ህልሙን ያጨለመ ነው። ለሁሉም ግልጽ እንደሆነው ከጦርነቱ በፊት ከኤርትራ መንግስት ጋር ለአመታት የተካሄደው ድርድርም ሆነ የጦርነት ውሳኔ የተወሰነው በህውሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ ነው። ወደ ጦርነት ከተገባም በኋላ የመሪነቱን ሚና የጨበጡት ህዉሃቶች ናቸው። በጦርነቱ ምክንያት የአገሪቱ ካዝና በተራገፈና ሙጥጥ ባለ ሰዓት መንግስት ከሶስት ቢሊዮን ብር ያላነሰ የተበደረው ከህዉሃት የኢኮኖሚ ኢምፓወ ከሆነው ኤፈርት (ትእምት) ነበር። ለጦርነቱ የሚሆነውን የጦር መሳሪያ (ታንክ፣ ሮኬት፣ ሚሳየል፣ የውጊያ አውሮፕላኖች……) በየአህጉራቱ የተሽከረከሩ የሚገዙት የህዉሃት አመራሮችና የጦር አዛዦች ናቸው።

(በነገራችን ላይ በአውሮፕላን ግዢ ላይ ከፍተኛ ተሳትፎ ከነበራቸው የጦር አዛዦች ግንባር ቀደሙን የሚይዘው የቀድሞ አየር ሃይል አዛዥ የነበረው ሜ/ጄኔራል አበበ ተ/ሃይማኖት ነው። አበበ የክፍፍሉ መጀመሪያ ወቅት እንቡር እንቡር ቢልም የአንጃዎቹ መጨረሻ ኩምሽሽ አድርጎታል። “አይተነው ጊዜ ወደሚያደላው” አይነት ባህሪ ያለው አበበ ገልብጦ የመለስን ቡድን ይቅርታ ቢጠይቅም የመለስን የቃሪያ ጥፊ ከማግኘት አልታቀበም። ከአዛዥነቱ በንፋስ ፍጥነት ተባረረ። ከዛ በኋላ ጆቦ በሚሊዮን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ከኪሱ በማውጣት አሜሪካን ሀገር ተማረ። በትምህርቱም “የአሰብ ኢትዮጵያዊነት” ተገለጠለት። መገለጡ ቀልብ ይስባልና በኢትዮጵያ አየር ሃይል ላይ በተነው። ጆቤ! ዛሬ በወር 150ሺህ ብር የሚከራይ ቪላ አለው። ያውም በአዱገነት እምብርት! ለ100 አመት ይዞ ቢቆይና ከደሞዙ ሰባራ ሳንቲም ባያወጣ አሁን ያለውን ሀብት ሩብ አይኖረውም። እርግጥ ከርቀት እንደሰማነው ባለቤቱ ብቸኛዋ ሴት ጄኔራል ሆናለች።)

እዚህ ላይ የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ውጤት ለህዉሃት የበላይነት መምጣትና የትግራይ ተጠቃሚነት ዋስትና የፈጠረው አደጋ ለህዉሃት መሰንጠቅ መሰረታዊ ምክንያት ቢሆንም ሌሎች ተጨማሪ ምክንያቶች አሉት። እነዚህ አደጋዎች ከህዉሃት አፈጣጠር፣ የዘረጋው ስርአት ባህሪና ውስጠ- ድርጅት ሁኔታ ጋር የተያያዘ ነው። ህውሃት የበላይነቱን ያረጋገጠባት ኢትዮጵያ ካልቀጠለችና የአገር መበተን ካጋጠመ “የትግራይ ሪፐብሊክ” ነፃ ሀገር ፈጥሮ መኖር እንደ መጨረሻ ግብ ያስቀመጠ ቢሆንም ከኤርትራ ጋር የገባበት ቁርሾና ደም መፋሰስ ይህን ፍላጎቱን ከሞላ ጎደል ዝግ አድርጎታል። Eriteria-Factor የተባለው አንዱ ገፅታ ይሄ ነው። የጎንደር፣ አፋር፣ ወሎ ህዝብ ከታች ኤርትራ ከላይ ሆነው ትግራይን ሳንድዊች የሚያደርጉበት ሁኔታ ስለሚፈጠር ከዚህ በኋላ “የትግራይ ሪፐብሊክ” ከህልም የዘለለ አይሆንም። ትግራይን ገንጥለን በሰላም እንኖራለን የሚባል ህልም ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ጠለምት፣……ወዘተ ወደ ትግራይ የተከለሉ ሰአትና የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት በተነሳ ሰአት ወደ መቃብር ወርዷል።

የኢትዮ- ኤርትራ ጦርነት አጨራረስ በአንድ በኩል ነፃ ሀገር ለመመስረት ህልም የነበረችውን የህዉሃት አመራሮች ወሽመጥ የቆረጠ ሲሆን፤ በሌላ በኩል ኢትዮጵያዊነቱን አጥብቆ ለሚፈልገው የትግራይ ህዝብ ትልቅ ብስራት ተደርጎ ሊወሰድ የሚችል ነው። በአጭሩ ኢትዮጵያን ወዳድ ለሆነው የትግራይ ህዝብ የጦርነቱ አጨራረስ በመጥፎ ሁኔታ ውስጥ የሚፈጠር ጥሩ አጋጣሚ ነው። Blessing in disguise!!

የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት አጨራረስ ህዉሃትን ለሁለት ሰንጥቋል የሚባልበት መሰረታዊ ምክንያት ይሄ ነው። የስዬ አብርሃ ቡድን የኢትዮጵያን ህዝብ ሀብትና ደም መከታ አድርጎ ኤርትራ በመደምሰስ አሻንጉሊት መንግስት ለመመስረት ሲያስብ ሌሎች አላማዎችን ለማሳካትም ጭምር ነበር። ህዳጣኑ ህዉሃት ከትግራይ ውጭ ያለው የኢትዮጵያ ህዝብ መግዛት ካቃተውና ህዝባዊ ማዕበሉ ካናወጠው ያለ ኤርትራ ስጋት “ነፃ የትግራይ ሪፐብሊክ” መመስረት ይችላል። የስዬ ቡድን ኤርትራ ላይ ለራሱ ተጠሪ የሆነ አሻንጉሊት መንግስት መመስረት አለመቻሉ በክፉ ጊዜ መጠጊያ የምትሆነውን “ሪፐብሊክ ትግራይ” የመመስረት ራዕይ ተጨናገፈበት። በተለይ በአሁን ሰዓት የኢትዮጵያ ህዝብ ልጆቹን በመገብሩ ቁጭት ላይ የወደቀ መሆኑና ከዚህ በኋላ ጋሻነቱ ባከተመበት ሁኔታ ከኤርትራ ጋር ጦርነት መግጠም ማለት የህዉሃት ፍፃሜ መሆኑ አይቀርም።

በሌላ በኩል ጓድ መለስ በስልጣን ለመቆየት ካለው ጥማት በመነሳት ጦርነቱ ሊገፋበት አለመቻሉ እዛው ሳለ የትግራይን ነፃ መንግስት ህልም ባጭሩ የቀጨ ሆኗል። ይህ በመሆኑ ምክንያት በህዉሃት/ኤህአዴግ ህገ-መንግስት ውስጥ የሰፈረው አንቀጽ 39 ከህዉሃትና ትግራይ ህዝብ አኳያ ከወረቀት አንበሳነት የዘለለ አይሆንም። የህዉሃት አፈጣጠር መነሻ የሆነው “የትግራይ ነፃ ሪፐብሊክ” መመስረት እውን ሊሆን የሚችለው ሁለት መሰረታዊ ጉዳዮች ሲሟሉ ብቻ ነው። አንደኛው ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ጠለምት….. የመሳሰሉ መሬቶችን ለባለቤታቸው ሲመልሱ ይሆናል። ሁለተኛው ኤርትራ ላይ (Eriteria-Factor) ዳግም ጦርነት በመክፈትና ኤርትራን ወደ ዳግም ሱማሊያ መውሰድ፤ ከተቻለም ለህዉሃት ተጠሪ የሆነ አሻንጉሊት መንግስት በመመስረት በተራዘመ ጊዜ በኮንፌደሬሽን መዋሃድ። የወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ጠለምትና ሌሎች ቀድሞ በትግራይ ክልል ያልነበሩ ቦታዎች ወደ ቀድሞ ቦታቸው ይመለሳል የሚለው ጥያቄ “በህዉሃት መቃብር” ላይ ብቻ የሚፈፀም ነው። ለዚህም ነው ከየትኛውም የኢትዮጵያ ቦታዎች በበለጠ ሁኔታ እነዚህ አካባቢዎች “የትግሉ  ማዕከል” ናቸው የተባለበት ምክንያት። ኤርትራን በጦር ገጥሞ ለህዉሃት ተገዢ የሆነ አሻንጉሊት መንግስት በአስመራ እናቋቁማለን የሚለውም ፍላጎት ያለቀና የደቀቀ ተደርጎ ባይወሰድም ወደ ዜሮ የቀረበ እድል (Probability) ተደርጎ ሊወሰድ የሚችል ነው።

እርግጥ ሌሎች ህዉሃትን ለሁለት የሰነጠቁ እንጭፍጫፊ ምክንያቶች እዚህ ላይ ሊጨመሩ የሚችሉበት ሁኔታ መኖሩ እሙን ነው። የህዉሃት የፍጥረቱ የመጨረሻ ግብ ከመኮላሸቱ ጎ ለጎን የዘረጋው ስርአት ባህሪና የውስጠ- ድርጅቱ ሁኔታ ለመሰነጣጠቁ ምክንያት ነው። ህውሃት የዘረጋው ስርአት የፓርቲውን የበላይነትና የትግራይን የተለየ ተጠቃሚነት ዝርፊያ (ሙስና) አንዱ መለያ ባህሪው ነው። መንግስት እንደመሆኑ መጠን ወረራና ዝርፊያው “መንግስታዊ” መሆኑ አይቀርም። “መንግስታዊ ሌብነት”…. “መንግስታዊ ዝርፊያ”…. “መንግስታዊ ሙስና”…. “መንግስታዊ ውንብድና!”…. በመሆኑም የህዉሃት አንዱ መሰረታዊ መለያ ባህሪ በአዋጅ፣ በህግ፣ በመመሪያ የሚፈፅም የቡድን ዝርፊያ (“መንግስታዊ ሙስና”) ነው። ህዉሃት ገና ከጠዋቱ ቁልፍ ቁልፍ የሆኑ የመንግስትና ድርጅታዊ የስልጣን ቦታዎችን በቁጥጥር ስር ያዋለው በዚህ ምክንያት ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትር፣ ውጭ ጉዳይ፣ መከላከያ፣ ደህንነት፣ ፖሊስ፣ ሚዲያ፣ የድርጅት ቢሮ፣ የክልሎች ሞግዚት በመሆን አይናቸውን በጨው ያጠቡት ለዚህ ነው።

ይህም ሆኖ የህዉሃት ስርአት በትግራይ ህዝብና ልሂቃን ዘንድ ያለው አረዳድ ከሌላው አካባቢ ጋር ተመሳሳይ አይደለም። አሁን ባለው ነባራዊ እውነታ ከትግራይ ህዝብ የወጡት ህዉሓቶች በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ፈላጭ ቆራጭ በሆኑበት፤ ገዳዩ አሳሪው ገራፊውና መርማሪው እነሱ በሆኑበት፤ የመንግስት ስልጣንን በመጠቀም ከፍተኛ የኢኮኖሚ አቅም በገነቡበት፤ በትግራይ ውስጥ ታይቶ በማይታወቅና ኢ-ፍትሃዊ በሆነ መንገድ እልፍ አእላፍ ፋብሪካና የኢኮኖሚ አውታሮች በተገነቡበት፤ በጠብታ ኢኮኖሚ መልኩ በትግራይ ክልል የተገነቡት፤ መሰረተ ልማቶችና ማህበራዊ ፍትህ ማምጫ ተቋማት….. ወዘተ በፍጥነት ወደ ህዝባዊ እምቢተኝነቱ ሊቀላቀላቸው አይችልም። ራሳችንን ማምሸት ካልፈለግን በስተቀር የትግራይ ህዝብ በህዉሃት አገዛዝና አፈና ተማሮ ሊሆን ይችላል እንጂ “አዲስ ስርአት” ለመቀበል ዝግጁነቱ አይታይም። የህዉሃት አገዛዝ በፓርቲ መዋቅሩ አማካኝነት የሚፈጥረው ጭቆና፣ የዘመድ አዝማድ አድሎአዊ አሰራር፣ ኋላቀርነት፣ “አህያ ቢራገጥ” የሚመስል አይነት ቂም በቀል፣… አሰልቺ ስብሰባዎች እና መዋጮ….. ወዘተ የትግራይን ህዝብ ሊያስመረምረው ይዝል ይሆናል እንጂ ለስር-ነቀል ለውጥ የተዘጋጀ አይደለም። ግፋ ቢል ከአጭር ጊዜ አኳያ “ላም እሳት ወለደች” ከሚለው ብሂል የሚርቅ አይደለም። ይህ የብዙሃኑ የትግራይ ተወላጅ ፍላጎት አድርገን ልንወስደው የምንችል ነው።