እነእስክንድር ነጋ ኮማንድ ፖስቱ ካልወሰነ አይፈቱም ።

የእነእስክንድር ቁርጣቸው ታውቋል

ከዚህ በኅላ የሚመለከተው የኮማንድ ፖስት አካል የሚወስንበት ነው

* የተያዙት በሁለት ምክያንቶች ነው

* በኮማንድ ፖስቱ ያልተፈቀደ ስብሰባ አካሂደዋል

*በህግ የተከለከለ ሰንደቅ ዓላማ ተጠቅመዋል…..ይህንን በማስረጃ አጣርተን ጨርሰናል

*ከዚህ በኅላ እነዚህ ታሳሪዎች ወይ መለቀቅ ወይም መደበኛ ክስ መመስረት ወይም በተለየ ሁኔታ ታስረው ይቆዩ የሚለውን ውሳኔ የኮማንድ ፖስቱ ስልጣን ነው!!

ጠበቃ አማሃ መኮንን ከንፋስልክ ፖሊስ መምሪያ ኮማንደር በኩል ተገልፆልኛል ብለው ለቪኤኤ የተናገሩት ነው።

ለ ዶ/ር አብይ አህመድ፤ አቅጣጫ ማሳያ ወሳኝ ማስታወሻ! (ከሙሉቀን ገበየው)

ከሙሉቀን ገበየው

Dr. Abiy Ahmed, Oromia region of Ethiopia official.

የገዢው ፓርቲ የኢሕአዴግ ሊቀመንበር ሆነው መጋቢት 18፣ 2010 በመምረጦው እንኳን ደስ አለዎት።  በአሰራር ደንባችሁ መሰረት በቅርብ ቀን ደግሞ የኢትዮጲያ መንግስት ጠቅላይ ሚኒስቴር ይሆናሉ። እርሶዎ ስልጣን ላይ የመጡበት ግዜ  በአገራችን ታሪክ እጅግ ወሳኝ  ሰአት ላይ ነው። ኢትዮጲያ መስቀለኛ መንገድ ላይ ናት። እጅግ ፈታኝና የተወሳሰበ ስራ ይጠብቆታል።

በልጅንትዎ ገና 15 ወይም 16 አመት ወጣት ሁነው  በ1980ዎቹ መጀመርያ በወታደርነት የተቀላቀሉት  ወያኔ መራሹ ኢሕአዴግ ወስጥ አደገው፣ ጎልመሰው፣ ከተራ ታጋይነት እስክ ሌትና ኮሎኔል ማእርግ የበቁ አዋቂ ሰው ሆነዋል። በታማኝነትዎ፣ በልጅነት ቅልጥፍናዎ፣ እንዲሁም ለማደግ በሚያድርጉት ጥርትዎና የቤሄር ተዋጾ  ተጭምሮ በተለይም ተወልደው ባደጉበት የሁሉ ሃይማኖትና ጎሳ አስተናግጅና በቡና ንግድ በከበርችው አጋሮና ጅማ ከተማ ቀምስ መሆኖው ጠቅሞታል። በትምህርትዎ መጎብዘውና  መትጋቶት የከተማን ኑሮ ቀምሰው ቀልጠው በቀሩ የጫካና የበርሃ ታጋዮች መካከል እርሶን ጎላ ብለው ለእድግት  እንዲበቁ እድል ገጥሞታል።

ባጋጥሚም ይሁን የእድል ጉዳይ ሆኖ በ1999 አ.ም. ከውትድርና  ተሰናብተወ  የፖለቲካ ሰው  በመሆን የሲቪሉን ኑሮ ቢጀምሩም በቀላሉ በኦህዲድ አመራር የስልጣን እርከን  ተመቻችቶለታል።

እርሶው ከሌሎቹ የቀድሞ በዋናው ስልጣን ወንበር ላይ ከተቀመጡ  ጓደኞቾዎ በተለየ፣ ለዚህ ስልጣን ብቁ የሚያደርጎት ዝግጁነት አሎዎት። በተለይም እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገር በወታደሩ ሞያ  የነብሮት ልምድና አሁን ደግሞ በሲቭል የፖለቲካ ስልጣን ከክልል እስከ ፌድራል ሚኒስቴር ማእርግ ደርሰው ቢሮክራሲውን በደንብ ማወቆው ለሚገጥሞት ፈትና ዝግጁ ያደርጎታል። መቼም ለዚህ ስልጣን የበቁት ድርጅቶውና ገዢው ፓርቲ ወዶ ፈቀዶ እንዳይመስሎት፤ ይልቅስ በመላ አገሪትዋ የተቀጣጠለው ተቃውም ሰልፈና አመጽ ነው። አንዳንድ ወገኖች የርሶው ስልጣን አወጣጥ ወያኔ ህዝቡን ለማድናገር የሰራው ቲያትር ነው ብለው የሚያምኑ ቢኖሩም፤ ብዞዎቻችን ግን ተስፋ ሰንቀን እንመለኮቶታለን።

አሁን ሊያስተርዳድርዋት  የተዘጋቸችው ኢትዮጲያ፡ ያኔ እርሶ ልጅ ሁነው ወያኔ ሕወሃት መራሹ ኢሕአዴግ ስልጣን ሲቆጣጠር 1980ቹ መጀምርያ  ከነብረው ግዜ ፍጹም የተለይች ናት። እርሶ የንጉሳዊው ስርአትን ገፍትሮ ከጣለው ታላቁ  የ1966  አብዮት ቦኋላ ከተወለዱ ትውልድ መካከል ኖት። ከመቶ ሚሊዮን ሀዝብ በላይ በዲሞክራሲያዊ መብት ረገጣ ፍጹም አስከፊ በሆነ ለ 27 አመታት ሲገዛ  የኖረ፤ በ ጎሳ፣በሃይማኖት ና በተበላሸ ፖለቲካ የተወጠርች አገር ናት። በከፋፍልሀ ግዛው መርሆ ሲሰቃይ የከረመ ትውልድ፤ የጭቆና አገዛዝ አንገፈገፎት ነጻነት ወይም ሞት ብሎ በሰላማዊ መንገድ ህይወቱን ለመሰአውት ያቀረበበት ዘመን ነው።

ስለ እርሶው አመራር ተስፈኞች ሁነን መስተዳደሮትን እንጠብቃለን። ታድያ ፈትና የበዛበት፣ ውስብስብና የተጠላለፈ ስራ እንድሚገጥሞው እናወቃለን። አይወጡትም  ይሆን  የሚል ጥርጣሬ ቢያድርብንም ተስፋ ግን ሰንቀናል። ምን ያህል ከወያኔ (ህወሃት) ተጽኖ ውጪ ነጻ ሰው እንድሆኑ  ማወቅ ባንችልም፡ ወያኔ ሕወሃት  ግን ከአሰበው የህልውናና ዋና ተጽኖ ፈጣሪ መንገዱ ዝንፍ እንዳይሉ የሚቻለውን ሁሉ እንደሚያደርግ  እውን ነው። ሆኖም ግን ስራውን ሳይጀምሩ በርሶዎ ተስፋ እንቆርጥም። የቀድሞው ሲቭየት መሪ የነበሩት ጎርቫቾቭ  አባል ከነበሩበት  ከሚጠላው ኮሚኒስት ፓርቲ ተነሰተው ነበር ግልጽነት እና እኪኦኖሚያዊ ጥገና ለውጥ በሚል መሪ መፈክር ትልቅ ሙከራ ያደርጉት። ታድያ ከሳቸው የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ ምኞታችን ነው። መቼም ጎርቫቾቭ  ያን አለም ሁሉ ሲያስድነግጥ የነበርወን የቀዝቃዝው ጦርነትን ቢያስቀሩም  አገራቸውን ሶቪየትን ግን ከመገንጣጠል ሳያድኑ ቀርተዋል።

የኢትዮጲያ ህዝብ በተለይም ወጣቱ በርሶዎ ተስፋ አድርጎል፤ ብዙም ይጠብቆበታል። ዋናው ግልጽ እንዲሆንሎት የሚገባው ወሳኝ ነገር ግን ሰላማዊ በሆነ መንግድ ከአስቃቂ አገዛዝ ወደ ዲሞከራሳዊ አስተዳድር የሚያደርጉት ለውጥ ብቻ ነው ሀገሩቱን፣ ክልሎችን  ህዝቡን አቅፎ ሊይዝ የሚችለው።

በኢትዮጲያ ውስጥ ካሉ ጎሳዎች ሁሉ፣ የተለያየ የፖለቲካ አመለካከት ያላቸውን ወገኖችን  ቀርበው ማየት ማነጋገር ይኖርቦታል። ይህም በህዝብ አመኔታንና ክብርን እንዲሁም ከወያኔው (ሕወሃት) ለሚሰነዘርቦት ተንኮልና መሰሪ የሚከላከሎት የሚጠብቆት ወሳኝ የጀርባ አጥንት ድጋፍ ይሆኖታል። ወያኔ ሕወሃት ስልጣኑን በቀላሉ አሳልፎ  ይሰጥል ብሎ መጠበቅ የዋህነት ሲሆን  የህዝብን ብሶት የሚያስተካከል መንገድ ከመርጡ  ይልቁንስ መሰሪ ተግባሩን የረቀቀ ተንኮሉን ተጠቅሞ ሊያከሽፈው እንደሚሞከር ግልጽ ነው። እርሶም በስራእቱ ውስጥ በነበሩበት ወቅት  በጸጥታና መርጃ ስራ ልምዶው የወያኔውን ተንኮል ይስቱታል አይባለም። ዋናው ማርከሻውን መድሃኒት አስቀድሞ ማዘጋጀት አለቦት። በሻርክ የተሞላ ባህር ላይ የሚቀዝፉትን ጀልባ አስተማማኝ ወደብ ላይ የሚያደርሶትን  አቅጣጫ ማሳያ (ኮምፓስ) መጠቀም ይገባዎታል።  ከዚህ ዝንፍ ብለው የወያኔው አሻንጉሊት ጠቅላይ ሚንስቴር መሆኑን ከመርጡ ግን በህዝብ ተንቀው፣ እጣ ፈንታዎ ዳግማዊ ሐይለማርያም ደሳለኝ ወይም ከዚያ የባሰ ነው የሚሆነው።

ይህን አደገኛ ባህር በሰላም ይሻግሩት ዘንድ፤ ህዝባችንንም ከመሪር አገዛዝ ተገላግሎ ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ጅምሬ እንዲገባ የሚረዳ፣  አቅጣቻ ማሳያ የሚጠቁሞት (ኮምፓስ) ፍሬ ሃሳብን   ከታች ስዘርዘር  ቅድሚያ እንዲሰጡት በማሳሰብ ነው፡

  1. በሀገርችን ኢትዮጲያ ያሉትን ጎሳዎች ሁሉ፤ የተለያየ የፖለቲካ አመለካከት ያላቸውን፣በእድሜ፣በጾታ፤ በሀይማኖት፣በአካል ጉዳት በመሳሰለው ሳይመርጡ ያቅርቡ፣ያነጋገሩ። ይኄም አላማዎን ሊቀለብስ የሚነሳውን ማንኝወንም ሃይል ወይም የወያኔ ሴራ ይቋቋሙሎታል።
  2. እጅግ ግልጽና ጎላ ባለ መልክ  ሊፈጽሙት ያሰቡትን መንግስታዊና ፖለቲካዊ ለውጦች በቅርብ ቀናት ለአትዮጲያ ህዝብም ለጠላቶችዎም ያሳወቁ፤
  3. ለዲሞክራሲያዊ አስተዳድርና ለለውጥ የተዘጋጁ በትምህርትም፣ በችሎታም እንዲሁም ለለውጥ የተነቃቁ ባለሞያዎች፣ የፖለቲካ ሰዎችና  መልካም ዜጎች  በአማካሪነት  ይሰብሰቡ/ይቅጠሩ።
  4. አገር አቀፍ  ምክክርና መግባባትን እንዲሁም የህዝብ-ለሀዝብ መልካም ግንኙነቶችን  ያጠናከሩ ያበረታቱ።
  5. በኢቲዮጲያ እንዲሁም በውጭ ሀገር ያሉ የፖለቲካ ደርጅቶችን የታገዱትን  ሁሉ ጨምሮ በሰላም በሀገራችወ እንዲንቀሳቀሱ ጥሪ ያደርጉ፣ ያበረታቱ።
  6. በህገ-መንግስት በተሰጦው ስልጣን መሰረት በተለይ የጸጥታውና መርጃ  እንዲሁም ወታደራዊ ክፍሉን የመቆጣጠር ስልጣኖን ያረጋግጡ። ሊይስፈጽሙ ያሰቡትን ለውጥ እንቀው ሊይዙ የሚችሉትን የአሁኑን የነዚህ ከፍል አመራሮችን ለመቀየር ይሞክሩ፤
  7. በወያኔ የበላይነት በተመራው የህዝብ መሬት ነጠቃና ዝርፊያ ላይ፣እንዲሁም ኤፈርት በሚባል በሚታወቀው የወያኔ ንግድ ድርጅት ህገ-ወጥ ተጽኖ የኢኮኖሚውን ዘርፈን ማላቀቅና በአገዛዙ የተደርጉ የኢኮኖሚ ምዝበራና ዝርፍያ፣ እርስ በርስ መጠቃቀሚያና የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት  ያላቅቁ። ይህን የሚመርመር ኮሚሽን ይመስርቱ።
  8. የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶችን፤ታዋቂ ሙሁራኖችን እንዲሁም የአገር ሽማግሌዎችን ያካተተ የምርጫ ቦርድን ገለልትኛነት የሚያረጋግጥ ተግባር ይፈጽሙ።
  9. ነጻ ሃሳብ መግልጫ  መድርኮችን ( የህትመት፣ የድምጽ ና ምስል የህዝብ መገንኛ ) እንዲስፋፉ ያበርታቱ፤
  10. የፍትህ አካሉን፣ የፖሊስና የአገር መክላከያ ሰራዊትን ከፖለቲካ ተጽኖ ወጪ ለማድርግ አጥብቀው ይስሩ። ይህ እጅግ አስቸግሪ ስራ እንድሚሆን ይታወቃል። ገዢው ድርጅት ለለውጥ ካልተዘጋጀ የሚፈጸም አይሆንም።
  11. ሁሉንም የፖለቲካ እስርኞች ይፍቱ። የማሰቃያ እስር ቤቶችን እንዲዘጉና ሙዚየም እንድሆን ያበርታቱ፤
  12. የሚቻል ከሆነ ( አገዛዙ መቼም አይፈቀደወም) ሁሉን የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ታዋቂ ሙሁራንና የአገር ሽማግሌውችን፣እንዲሁም ሲቪክ መሃበሮችን ያቀፈ ጊዛያዊ  ምክር ቤት ተቋቁሞ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ቢደረግና፤ ይህም ምክር ቤት እውነተኛ ህገ-መንግስትና ምርጭ በሁለት አመት እንዲያዘጋጅ ቢያበርታቱ፤
  13.  ቁጥር 12 የማይቻል ከሆነ፣ የሚቀጥለው ምርጫ ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች በሰልማዊና ፍታሃዊ መንገድ የሚወዳድሩበት መድርክ ተዘጋጅቶ በአለምአቀፈ  ታዛቢዎች የሚገኙበት ከ 1997 አ.ም  ምርጫ የተሻለ እንድሆን መጣር፤
  14. በየሳምንቱ  በራድዮ ፣ቴሌቪዥን እንዲሁም ማህበራዊ ሚዲያ እየቀርቡ ያቀዱትን ፣የተልሙትን የፈጸሙትን እንዲሁም የገጥሞትን ፈትና ለህዝብ  ቢያቅርቡ፤ ዘመኑ የመረጃ ዘመን መሆኑን አይዘነጉትም።
  15. ሊያመጡ ላሰቡት ፖለቲካዊ ለውጦች ያግዞት ዘንድ የአለም ሃያላን ከሆኑ እንዲሁም ተጽኖ ፈጣሪ ከሆኑ አገሮች ጋ መልካም ግንኙነት ይፈጥሩ።

ነገ ምን ይዘው እንደሚመጡ  የማያወቀው ብዙሃኑ ህዝብ በርሶ መመርጥ ታላቅ መነቃቃትና ተስፋ ማሳደሩ ህዝቡ ምን ያህል ለወጥ ነፍቆት እንደነበር ያሳያል።

ያሰቡትን መልካም ነገር ያሳክሎት ዘንድ መልካም ምኞቴን እየገልጽኩ፤ ነገር ግን ዋናው ጉዳይ አገራችንና ህዝባችንን ሰርንቆ ለያዘን እኩይ አግዛዝ፣ መብት ረገጣ መፍቴሄው ሰላምዊ ዲሞክራስያዊ ስርአትን መገንባት ብቻ መሆኑን ሳልጠቁሞት አላልፍም።

እግዚሓቤር  አገራችን ኢትዮጲያንና  ህዝባችን ላይ ከወረደው መከራ እንድናወጣ ይረዳን!!

ተስፋና ስጋት በጠቅላይ ሚኒስቴሩ ሹመት (ከሳዲቅ አህመድ)

“ከቃለ-መሓላ በሗላ ተራምደው ወደ አራት ኪሎ የሚገቡበት ቀይ ምንጣፍ በመላው አገሪቱ የፈሰሰው የሰማእታት ደም መሆኑ መዘንጋት የለበትም!”

Dr. Abiy elected as PM of Ethiopia.

ከሳዲቅ አህመድ

ልክ ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ ሲሞቱ በኢትዮጵያዉያን ዘንድ የነበረው ተስፋ አሁን ናኝቷል። ጠቅላዩ ቢሞቱም ተጠቅላዩ ሐይለማሪያም መጡና ሐይል-አልባ መሆናቸውን አሳዩ። የመለስ ሞት በዙፋኑ ላይ ያፈናጠጣቸው ሐይለማሪያም ደሳለኝ ፈልገውትም ይሁን በህወሃት አለቆቻቸው ታዘው እነደሆነ ዉሉ ባለየ መልኩ «ስራዬን በገዛ ፈቃዴ ለቅቅያለሁ» አሉ። ሁናቴው በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ግዜ የተከሰተ ተብሎ ቢወደስም፤ በዙፋኑ ላይ ለመፈናጠጥም ይሁን ለመንጠልጠል ይደረግ የነበረው ሙከራ ቀላል አልነበረም።

ዶክተር አቢይ አህመድን አስወንጭፎ አራት ኪሎ ለማስገባት የተቀናጀ የበይነመረብ ዘመቻ ሲጀመር ለማስተዋል ችዬ ነበር። ጉዳዩን መሬት ላይ ያሉ ምንጮች እንዴት እየተከታተሉት እንደሆነ ስጠይቅ «ዶክተሩ አራት ኪሎ እንደሚገቡ ከሶስት ወራት በፊት (አሁን አራት ወር ሞልቶታል) ጥረት እንዳለ እናዉቅ ነበር» የሚል ምላሽ አገኘሁ። ዶከተር አቢይ አህመድ በግለሰብ ደረጃ ያላቸው ብቃት ሚዛን የሚደፋ ቢሆንም፤ ከበስተጀርባቸው የሚኖረውን ሐይል ተቋቁመው እንደምን የተሳካላት ጠቅላይ ሚኒስቴር ይሆናሉ? የሚለው ሐሳብ ጉዳዩን በጥንቃቄ እንድመለከተው የሚያደርግ ነው።

አገራዊ ተግዳሮት

ዶክተር አቢይ አሀመድ በህወሃት መዳፍ ስር ያለውን የመከላከያ ሰራዊት፣የደህንነት መዋቅር፣የመዋእለንዋይ ፍሰትና አቅም፣ የመገናኛ ብዙሗን በህወሃት ቁጥጥር ስር መሆን፣የተንሰራፋዉን የአንድ ብሔር የበላይነት አሸንፈው ብሔራዊ መግባባትን ይፈጥራሉን? ለቀጣዩ ምርጫ የሚደርስ የተዋጣለት የሽግግር መንግስትን ማዋቀር ይችላሉን? መሰል ጥያቄዎች በተገቢው መልኩ ተፈትሸዋልን? ደረጃ በደረጃ ሒደቱ ደረጃ በደረጃ ሳይቃኝ፤ የስርዓት ለዉጥ ሳይሆን የግለሰብ ለዉጥ በመምጣቱ፤ ከመጠን ያለፈ ፈንጠዚያና ተስፋ (expectation) መኖሩን በጥንቃቄ ልንመለከተው የሚገባ ጉዳይ ነው።

ረጃጅም የውጭ እጆች

ዶክተር አቢይን ለማስወንጨፍ የውጭ ሐይል አሰፍስፏል። ምሁሩ ፖለቲከኛ ጥምር የዘርና የእምነት ማንነት ያላቸው በመሆናቸው እርሳቸውን «ኢትዮጵያዊ ኦባማ» አስመስሎ ለማስረጽ የሚደረገው ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል። አፍሪካን በቅኝ በመግዛት፣በተለያዩ የአለም ክፍሎች እምነት አዘል በሆነ ተልእኮ በስልጣን ማማ ላይ በወጡ አገዛዞችና አመራሮችን በመጠቀም፣በአለማችን የፖለቲካና የዲፕሎማሲ ለዉጦች ላይ በመጠቅለል ጥቅምን ለማስረጽ ከሚጥረው የዉጭ ሐይል የአገርን ሉዓላዊነት እንደምን መጠበቅ ይቻላል? በዚህ ረገድ የመቶ ሚሊዮን ህዝብ መሪ መሆን ከባድ መሆኑ አሌ-አይባልምና የዶክተር አቢይ ፈተና ከባድ ነው።

መለስ የጀመሩት የዉጭ ሐይልን የማስገባት ሴራ የቀድሞው የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ዶክተር ሺፈራው ተክለማርያም ለማስፈጸም መጣራቸውን ልብ ይሏል።ከቴክሳስ እስከ ኮሎራዶ ከዚያም እስከ አዉሮፓ ትላልቅ ከተሞች ያሉ ልዩ ጥቅም አስከባሪ ሐይላት (special interest groups) ኢትዮጵያ ዉስጥ ዘልቀው ለመግባትና ጥቅማቸውን ለማስከበር እምነትን መሰረት ያደረጉ ረጃጅም እጆቻቸውን መዘርጋታቸው አይቀርም።የዉጭ እጆች ጥቅምን ለማስከበር ሲዘረጉ የዜጎች ህልዉናና ሰላም አደጋ ላይ እንዳይወድቅ መከላከሉ ተገቢ ነዉና የዶክተር አቢይ ታሪካዊ ሚና በአይነ-ቁራኛ የሚጠበቅ ነው።

ሹመቱ በህዝብ ትግል የመጣ ነው

ዶከተር አቢይ ዛሬ አራት ኪሎ ቤተ-መንግስት እንዲገቡ ላለፉት ስድስት አመታት አያሌ መስዋእትነት ተከፍሏል።ህዝቡ የከፈለው መስዋእትነት በአቶ ለማ መገርሳ የሚመራው ቡድን እንዲፈጠር አድርጓል።ከለማ ቡድን መካከል ዶክተር አቢይ የህዝብን አደራ የመሽከም ሐላፊነት ተጥሎባቸው ያሉበት ደረጃ ላይ ደርሰዋል።

ያለ ኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች «የድምጻችን ይሰማ» ትግል ዶክተር አቢይ ያሉበት ደረጃ ላይ አልደረሱም።ያለ ሰማያዊና አንድነት ፓርቲ የዉስጥና የጎዳና ላይ ሰላማዊ ትግል ዛሬ ዶክተር አቢይን ባላወቅን ነበር። በጎንደርና በጎጃም ያሉ ኢትዮጵያዉያን ለመሰዋእትነት ተዘጋጅተው አደባባይ ባይወጡና በስርዓቱ ላይ ባያምጹ ኖሮ ዶክተር አቢይ ጠቅላይ ሚኒስቴር መሆን ባልቻሉ ነበር።አገር አንቀጥቅጥና ህወሃትን የሚነቀንቅ የቄሮ ትግል ባይኖር ኖሮ ዶክተር አቢይ ወደ አራት ኪሎ ባላቀኑ ነበር። ህወሃት መራሹን መንግስት በጦር እንጥላለን ብለው ጫካ የገቡ ኢትዮጵያዉያን መኖራቸው ለዶከተር አብይ መከሰት ምክንያት አልሆነም ማለት አይቻልም።

ባህር ማዶ ያለው ኢትዮጵያዊና ትዉልደ-ኢትዮጵያዊ ግዜውንና ገንዘቡን ሰጥቷል።ሚዲያዎች እየታፈኑና ከሳተላይት እንዲወርዱ እየተደረገ ለዉጥን ለማምጣት ሰርተዋል።ጋዜጠኞች፣ አክቲቪስቶችና ለዉጥ ፈላጊዎች በአሜሪካና በአዉሮፓ ጎዳኖች ላይ በጸሃይ-በሐሩር-በበረዶ ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ ብዙ ጥረዋል።አያሌ ስብሰባዎች፣የግብንዛቤ ማስጨበጫ ዝግጅቶች፣የማግባባት (lobbying) እና በህወሃት መራሹ ቡድን ላይ ዲፕሎማሲያዊ ጫና የማሳደር ጥረቶች ተደርገዋል።

ተስፋ የተጣለበትን ድህረ-የስርዓት ለዉጥ ለማየት በዝጉም ይሁን በክፍቱ የህወሃት እስርቤቶች ብዙዎች ታስረዋል፣ተገርፈዋል፣ሴቶችም-ወንዶችም በጾታዊ ጥቃት ቶርቸር ተደርገዋል፣ነፍስን ለማዳን አገርን ጥለው የጠፉ በርካታ ናቸው።ከሁሉም በላይ መተኪያ የሌለውን ህይወት በመስጠት መስዋእት የሆኑ ብዙ አገር ወዳድ ዜጎች የሚዘነጉ አይሆኑም።አጋዚ በሚባለው የህወሃት ቅልብ ጦር ልጅ ተገድሎባቸው ለምድራዊ ስቃይ የተጋለጡ እናቶች፣አባቶች፣እህቶች፣ወንድሞች፣ቤተሰቦች፣ወዳጅ-ዘመዶችና ጎረቤቶች ብዙ ናቸው። ዶክተር አቢይ ወደ አራት ኪሎ ቤተመንግስት ሲያመሩ በክብር ቀይ ምንጣፍ ሳይሆን ህወሃት ለ40 አመታት ሲያፈሰው በነበረው የሰማእታት ደም ላይ መሆኑ አትኩሮት ያሻዋል።

የክብር ቀይ ምንጣፉ የሰማእታት ደም ነው

ከሚሰማው የደስታ ድምጽ ባሽገር ስጋት አለ።ስጋቱ በብዙዎች ዘንድ እየተዥጎደጎደ ባለው የምስራች ላይ ሟርትን ለመቸለስ አይደለም።የዶከተር አቢይ መመረጥን ወደ ሌላ እርከን አሳድጎ ለዉጡ የሰው ለዉጥ ሳይሆን የስርዓት ለዉጥ እንዲሆን መትጋት አለብን የሚል ምልከታ (reservation) ዉስጥን በእጅጉ ይሞግታል ።ስለዚህ ያለውን ነባራዊ ሁናቴ በሚገባ አጢነን ህዝባችን የሚሻውን ወሳኝ ለውጥ ከግብ እናድርስ የሚል ጥሪ ሳቀርብ ዶክተር አቢይ ከቃለ-መሓላ በሗላ ተራምደው ወደ አራት ኪሎ የሚገቡበት ቀይ ምንጣፍ በመላው አገሪቱ የፈሰሰው የሰማእታት ደም መሆኑ መዘንጋት የለበትምና ልብ ያለው ልብ ይበል።

አብይ ጉዳይ! ይፈቱ! ይፈቱ! ይፈቱ! ጌታቸው ሽፈራው

ጌታቸው ሽፈራው

ጋዜጠኛ እስክንድርን ጨምሮ መጋቢት 17/2010 ዓም 30 ሰላማዊ ሰዎች ታስረዋል። እነ እስክንድር አዲስ አበባ ላይ ለእስረኞች ምስጋና የተዘጋጀ ፕሮግራም ላይ ነው የታሰሩት። ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ አራት ቀን ሞላቸው፣ ባለፉት ሁለት ቀናት የእስር ቆይታቸው የተሻለ ነበር። ዛሬ ደግሞ አስከፊ ወደሆነው የእስር ክፍል መልሰዋቸዋል። “የኮማንድ ፖስቱን ውሳኔ እየጠበቅን ነው” እየተባለ እነሱ በአስከፊ እስር ላይ ናቸው።

ባህርዳር ላይ የታሰሩት ወጣቶች ሕጋዊ የፓርቲ ምስረታ ሰነድ ይዘው ነው። እነሱም በተመሳሳይ እስር ሁኔታ ላይ ይገኛሉ! አብዩ ጉዳይ የእነዚህ ንፁሃን መሆን አለበት!

ይፈቱ!

መጋቢት 17/2010 ዓም ከታሰሩት ጋዜጠኞች፣ ጦማሪያን፣ ፖለቲከኞች፣ እና ምሁራን መካከል:_

አዲስ አበባ

1) ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ

2)ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

3) አቶ አንዱዓለም አራጌ

4) አቶ አዲሱ ጌታነህ

5) ጦማሪ ዘላለም ወርቅ አገኘሁ

6) ጦማሪ ማህሌት ፋንታሁን
7) ጦማሪና ጋዜጠኛ በፍቃዱ ኃይሉ
8) ወይንሸት ሞላ
9) አቶ ይድነቃቸው አዲስ

10) አቶ ስንታየሁ ቸኮል

11) አቶ ተፈራ ተስፋዬ

ባህርዳር

12) ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ (ባ/ዳር ዩንቨርሲቲ መምህርና የጣና ደህንነትና የአካባቢ ጥበቃ ማህበር ፕሬዚደንት እና ተመራማሪ፣ ረዳት ፕሮፊሰር)

13) ጋሻው መርሻ (የአንጸባቂው ኮከብ መጽኃፍ ከታቢ፤ አዲስ አበባ በማስተማር ሙያ ላይ ይገኛል))
14) የሱፍ ኢብራሂም (ወሎ ዩኒቨርሲቲ መምህር የነበረና በአሁንኑ ወቅት ጠበቃ)

15) ተመስገን ተሰማ (ወሎ ዩኒቨርሲቲ መምህር፤የወሎ ዩኒቨርስቲ የህግ ትምህርት ቤት መስራች፣ ረዳት ፕሮፊሰር እና አማራ ነን የሚለው መዝሙርም ገጣሚ)

16) በለጠ ሞላ ( ተባባሪ ፕሮፊሰር ፡አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሌክቸረር)
17) ጋዜጠኛ ንጋቱ አስረስ (የአማራ ቴሌቪዥን ጋዜጠኛ(አርታኢ)፤ከ1997 እስከ 1999 የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአማራ ተማሪዎች ማህበር ፕሬዜዳት፤)

18) ጋዜጠኛ በለጠ ካሳ (የቀለም ቀንድ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ የነበረ)

19)አቶ ሲሳይ አልታሰብ( ሲቪል ኢንጅነር)

20) አቶ ዳንኤል አበባው

21) አቶ መንግስቴ ተገኔ

22) አቶ ቦጋለ አራጌ

23) አቶ ካሱ ኃይሉ (የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ
መምህር፡የማህበረሰብ ሳይንስ ተመራማሪ)

24) አቶ ተሰማ ካሳሁን

25)አቶ ድርሳን ብርሃኔ

26) አቶ በሪሁን አሰፋ

27)አቶ ፍቅሩ ካሳው

28) አዲሱ መለሰ (ደ/ታቦር ዩኒቨርሲቲ መምህር)

29) አቶ ተመስገን ብርሃኑ

30) አንድ በስም ያልተጠቀሰ ግለሰብ ይገኝበታል!

ይፈቱ! ይፈቱ!

የታሰሩት የዋልድባ መነኰሳት: በሕግ ፊት እኩል ኾኖ የመታየት መብታቸው ተጥሷል – ጠበቃው

FB_IMG_1522057967519

  • የ32ቱ ክሥ የተቋረጠበትና የ3ቱ ተከሣሾች ሳቋርጥ የቀረበት የሕግ ምክንያት አልተገለጸም፤
  • የሥነ ሥርዐት ሕጎች ተለጥጠው ከተተረጎሙ በተከሠሡት ላይ የማይመለስ ጉዳት ያስከትላል፤
  • በተለይም በታሰሩ ሰዎች ላይ፣አለ የተባለ ማስረጃ በሰዓቱ ቀርቦ የተፋጠነ ፍትሕ ይሰጣቸው፤
  • በፍርድ ሒደት ነጻ ቢባሉም እንኳ፣ጉዳታቸው የበዛ እንዳይኾን ዐቃቤ ሕግ ሓላፊነቱን ይወጣ፤
  • በቂ ማስረጃ ባልቀረበበት ኹኔታ ፍ/ቤቱ፥“ለትክክለኛ ፍትሕ አሰጣጥ”ያለው ሊያነጋግር ይችላል፤
  • ከሣሹ አካል፥በሕግ ፊት የተከሠሡ ሰዎች እኩል መኾናቸውን ለማረጋገጥ፣ትልቅ ዋጋ በመስጠት ከተለዋጩ ቀጠሮ በፊት የሚወስነው ውሳኔ ካለ እንጠብቃለን፡፡

†††

(የአሜሪካ ድምፅ ራድዮ፤ መለስካቸው አምኃ፣ መጋቢት 18 ቀን 2010 ዓ.ም.)

እነተሻገር ወልደ ሚካኤል በሚል የክሥ መዝገብ የ”ሽብር ወንጀል” ክሥ የተመሠረተባቸው የዋልድባ ገዳም መነኰሳት አባ ገብረ ኢየሱስ ኪዳነ ማርያም እና አባ ወልደ ሥላሴ ወልደ ሃይማኖት እንዲሁም አቶ ነጋ ዘላለም ላይ ዐቃቤ ሕግ ቆጥሬአቸዋለኹ ያላቸውን ምስክሮች ዛሬ ሳያቀርብ ቀረ፡፡

መዝገቡ ቀደም ሲል የተቀጠረው፣ ምስክሮቹን በዛሬ ዕለት አቅርቦ እንዲያሰማ የነበረ ቢኾንም፣ ዐቃቤ ሕግ ሊያስረዳ ባልቻለው ምክንያት የቆጠራቸው ሦስቱ ምስክሮች አልቀረቡም፤ ብሏል፡፡ ዐቃቤ ሕግ ከወትሮው በተለየ ኹኔታ ፖሊስ እነዚኽን ምስክሮች እንዴት ሊያቀርባቸው እንዳልቻለ እንኳ ለፍ/ቤቱ ለማስረዳት አልኾነለትም፡፡

ፍ/ቤቱ ቀደም ሲል በነበሩ ቀጠሮዎች፣ ዐቃቤ ሕግ በጥንቃቄና ሳይዘነጋ ምስክሮቹን በቀነ ቀጠሮው እንዲያቀርብ ሲያስጠነቅቀው ቆይቶ የነበረ ቢኾንም፣ እንደ ትእዛዙ አልተፈጸመም፡፡ ይኹንና ዐቃቤ ሕግ፣ አንድ ተጨማሪ ቀጠሮ ተሰጥቶት ምስክሮቹን እንዲያቀርብ ፍ/ቤቱን ጠይቋል፡፡

የተከሣሽ ጠበቆች፣ የዐቃቤ ሕግን ጥያቄ ተቃውመዋል፡፡ “ደንበኞቻችን ከታሰሩ አንድ ዓመት ከሦስት ወር አልፏቸዋል፡፡ ስለኾነም ዐቃቤ ሕግ በማናቸውም በከሠሣቸው ሰዎች በተለይም በታሰሩ ሰዎች ላይ አለኝ ያለውን ማስረጃ በሰዓቱ በማቅረብ የታሰሩ ሰዎች የተፋጠነ ፍትሕ እንዲያገኙ፣ ምናልባት በፍርድ ሒደት ነጻ ቢባሉም እንኳ የሚደርስባቸው ጉዳት የበዛ እንዳይኾን ሓላፊነቱን መወጣት ሲኖርበት ይህን አላደረገም፤” ሲሉ ተከራክረዋል፡፡

አክለውም፣ ፍ/ቤቱ ያልተቀበለው ቢኾንም እኒህ ሰዎች ተከሣሾች፣ ክሣቸው ተቋርጦ ከተፈቱት 32 ተከሣሾች ጋራ በአንድ መዝገብ የተከሠሡ መኾናቸውን ለፍ/ቤቱ አስታውሰዋል፡፡ ከጠበቆች መካከል አቶ አምኃ መኰንን ይህን ነጥብ ለአድማጮች ይበልጥ እንዲያብራሩ ጠይቀናቸው ነበር፡-

በእኛ በኩል እስከ አኹንም ድረስ፣ የ32ቱን ክሥ ያቋረጠበትን መስፈርት(ምክንያት) እና የእኒህን የሦስት ተከሣሾች ሳያቋርጥ የቀረበት ግልጽ የሕግ ምክንያት የተነገረ ነገር የለም፤ እኛም የምናየው ነገር የለም፡፡ ከዚህ አንጻር ተከሣሾቹ በሕግ ፊት እኩል ኾኖ የመታየት መብታቸው ተጥሷል፤ የሚል እምነት ነው ያለን፡፡ ይህንንም ለፍ/ቤቱ ገልጸናል፡፡ በርግጥ ፍ/ቤቱ፣ ይህ ነጥብ ፍ/ቤቱን የሚመለከት አይደለም፤ በሚል አልተቀበለውም፡፡


Lawyer Amha Mekonen

ከዚህም በተረፈ ዐቃቤ ሕግ በተደጋጋሚ ምስክሮቹን በታዘዘበት ጊዜ እንዲያቀርብ ተነግሮት ያልፈጸመ ስለኾነ የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች ታልፈው በሰነድ ማስረጃዎች ለደንበኞቻቸው ብይን እንዲሰጥ የተከሣሽ ጠበቆች ጠይቀዋል፡፡ ፍ/ቤቱ የኹለቱን ወገን ክርክር ካዳመጠ በኋላ የዐቃቤ ሕግን ክርክር ውድቅ ማድረጉን ለችሎት ገልጿል፡፡ የተከሣሽ ጠበቆችን ክርክር ሕጋዊነት እንደተቀበለ ገልጾ፣ ለትክክለኛ ፍትሕ አሰጣጥ ሲባል ለዐቃቤ ሕግ አንድ ተጨማሪ ዕድል በመስጠት፣ ሚያዝያ 18 ቀን 2010 ዓ.ም. ምስክሮቹን እንዲያሰማ ቀጠሮ ቆርጧል፡፡

አቶ አምኃ መኰንን በፍ/ቤቱ ውሳኔም ያላቸውን አስተያየት አካፍለውናል፡-

በእኔ በኩል የሥነ ሥርዐት ሕጉ ግልጽ ነው፡፡ በተለይም በወንጀል ጉዳይ የሥነ ሥርዐት ሕጎች በጣም በጥንቃቄና በጠባቡ መተርጎም አለባቸው፡፡ ተለጥጠው የሚተረጎሙበት ኹኔታ ካለ በተከሠሡና በተለይ በታሰሩ ሰዎች ላይ የማይመለስ ጉዳት ያስከትላል፡፡ ዐቃቤ ሕግ በቂ ምክንያት አላቀረበም፡፡ ፍ/ቤቱም ይህን አረጋግጧል፤ ተቀብሏል፡፡ እንግዲህ ከዚያ በኋላ ደግሞ ፍ/ቤቱ በራሱ መንገድ ለትክክለኛ ፍትሕ ሲባል ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ በቂ ማስረጃ ባልቀረበበት ኹኔታ ትክክለኛ ፍትሕ ምን ማለት ነው የሚለው ሊያነጋግር ይችላል፡፡ ይኼ የፍ/ቤቱ አቋም ስለኾነ በጸጋ ተቀብለን የሚቀጥለው ቀጠሮ ላይ ምስክሮች የሚቀርቡ ካሉ ወይም ከዚያ በፊት በከሣሹ አካል፣ በሕግ ፊት የተከሠሡ ሰዎች እኩል መኾናቸውን ለማረጋገጥ፣ ትልቅ ዋጋ በመስጠት ከዚያ በፊት የሚወስነው ውሳኔ ካለ እንጠብቃለን፡፡


ዐቃቤ ሕግ፣ ሰኔ 13 ቀን 2009 ዓ.ም.፣ እነተሻገር ወልደ ሚካኤል በሚል መዝገብ፣ አባ ገብረ ኢየሱስ ኪዳነ ማርያምን፣ አባ ወልደ ሥላሴ ወልደ ሃይማኖትንና አቶ ነጋ ዘላለምን ጨምሮ በ35 ሰዎች ላይ በሽብር ወንጀል ክሥ እንደመሠረተባቸው አይዘነጋም፡፡ በአኹኑ ወቅት ከሦስቱ ተከሣሾች በስተቀር የ32ቱ ተከሣሾች ክሥ ተቋርጦ መፈታታቸው ታውቋል፡

ዶ/ር አብይ አህመድ ዓሊ (መሳይ መኮንን)

መሳይ መኮንን

Mesay Mekonnen, ESAT journalist

ህወሀቶች ተሰልፈው ገብተው ነበር። ነባሮቹ አመራሮች፡ ያለቦታቸው፡ ያለስልጣናቸው ተያይዘው የገቡበት የሞት ሽረት ያህል የተወስደው ስብሰባ መጨረሻው ለህወሀቶች መልካም ዜና አላመጣም። ለሁለት ቀናት የታሰበው ሁለት ሳምንት ወስዷል። መሰረታዊ በሆኑ ጉዳዮች ጫፍና ጫፍ የረገጡ ተቃራኒ አቋሞች የተንጸባረቁበት እንደነበረ መረጃዎች ያመለክታሉ። በተለይም በኦህዴድና በህወሀት መሀል መስመር የለየ ፍጥጫ ተከስቷል።

በረከት ስምዖን የህወሀቶችን ጥቅምና ፍላጎት ለማስከበር የሄደበት ርቀት እነገዱ አንዳርጋቸው ሰልፋቸውን ይበልጥ ከለማ ኦህዴድ ጋር እንዲያደርጉ ምክንያት እንደሆናቸውም ከብአዴን አከባቢ የተገኘው መረጃ ያመለክታል። በረከት የያዘው መስመር ህወሀትን ዋጋ አስከፍሏል። ህወሀትን ለማዳን ወይም የህወሀት ሎሌ የሆነ ሊቀመንበር እንዲመረጥ በበረከት በኩል የነበረው ሩጫ ድምሩ ዜሮ ሆኖ ቀርቷል። ህወሀት ደጋፊ እንዲያጣ በማድረግ በመጨረሻም ህወሀት ባልፈለገው ውጤት ስብሰባው እንዲጠናቀቅ አድርጎታልም ይባላል። ድሮም በረከትን ውሽማውን እንደቀማው ደመኛ የሚጠላው ስብሃት ነጋ ይሄኔ የበረከትን ጭንቅላት በሽጉጥ ቢበረቅሰው የሚፈልግ ይመስላል። ገደል ይዞአቸው ገብቷልናል።

የሊቀመንበር ድምጽ አሰጣጡ ከመከናወኑ በፊት በቀረቡት እጩዎች ላይ የተደረገው ክርክር አስገራሚ ነበር። በተለይ ህወሀቶች ዶ/ር አብይ ላይ የውሸት ዶሴ ከፍተው ስሙን በሚያጎድፉ ውንጀላዎች ሲያብጠለጥሉት እንደነበር ውስጥ ከነበረ አንድ ሰው የተገኘ መረጃ አመልክቷል። ሌላው ቀርቶ የቀድሞ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት አቶ ዓለማየሁ አቶምሳ አሟሟት የዶ/ር አብይ እጅ አለበት የሚል ክስ በህወሀቶች ተነስቶ እንደነበርም ተሰምቷል። ህዝበኝነት፡ ከድርጅት መስመር ማፈንገጥ፡ በግል ተወዳጅነት የሰከረ የፖለቲካ እንቅስቃሴ መጠመድ የሚሉ ስድብ ቀረሽ ውርጅብኝ ከህወሀቶች በየተራ ሲጎርፍም ነበር ተብሏል። አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በፓርላማ ድምጽ በቀረበበት ዕለት ሆን ብሎ ጠፍቷል በሚልም ከእነበረከት ሳይቀር የውግዘት መዓት መቅረቡም ተሰምቷል። በመጨረሻው ስድስት ሰዓታት ህወሀቶች የዶ/ር አብይን መመረጥ ለማጨናገፍና ለማስቀረት ከፍተኛ ተጋድሎ አድርገዋል። የብአዴንና የደኢህዴንን አባላት በቡድናና በተናጠል እየተጠሩ ድምጻቸውን ለሽፈራው ሽጉጤ እንዲሰጡ በህወሀቶች በኩል የተደረገው ብርቱ ጫናና ማስፈራራት ያልተጠበቀ ውጤት ማስከተሉ አልቀረም።

ያደፈጠው ብአዴንና ያልተጠበቀው ደኢህዴን

ኦህዴድ ጀመረው። ደኢህዴን አጀበው። ብአዴን ዙሩን አከረረው። በመጨረሻም ኦህዴድ ገመዱን በጥሶ ገባ። ህወሀት በባዶ አጨብጭቦ ወጣ። የሰሞኑ ስብሰባ በአጭሩ ከተገለጸ ከዚህ አያልፍም። እውነት ለመናገር የሰሞኑ ስብሰባ ኮከብ ተጫዋች ብአዴን፡ ኮከብ ጎል አግቢ ደኢህዴን፡ ሻምፒዮን በመሆን ዋንጫውን የወሰደው ደግሞ ኦህዴድ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም። ህወሀት የጸባይ ዋንጫ እንኳን ተነፍጎት ጨዋታውን አጠናቋል። የገዱ ብአዴን ከለማ ኦህዴድ ጋር የጀመረውና ህውሀቶችን በጥፍራቸው ያስቆመው ወዳጅነት በመሀል የቀዘቀዘ መስሎ ነበር። በሰሞኑ ስብሰባ ዳግም አንሰራርቶ ህወሀትን ጉድ ሰርቷል። ብአዴን በዶ/ር አብይ መመረጥ ላይ የተጫወተው ሚና አስገራሚ ነበር። ህወሀቶች በቀላሉ የብአዴኖችን ድምጽ ወደ ሽፈራው ሽጉጤ እናደርገዋለን የሚለው ተስፋቸው ውሃ በልቶት ቀርቷል። ድምጽ የነፈጉት የገዛ ፓርቲቸው ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረጺዮን ሁለት ድምጽ ብቻ ማግኘቱ የህወሀቶችን ሽንፈት ቅስም ሰባሪ ያደርገዋል።

ያደፈጠው ብአዴን ሙሉ ለሙሉ በሚያሰኝ መልኩ ድምጹን ለዶ/ር አብይ ሰጥቷል። ያልተጠበቀው ደኢህዴንም ህወሀትን አውላላ ሜዳ ላይ ጥሎታል። ቀላል የማይባል የደኢህዴን ድምጽ ለዶ/ር አብይ ተደምሯል። አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ያገኙት አብዛኛው ድምጽ ከደኢህዴን ይልቅ የህወሀትን ነው። ህወሀቶች ድምጻቸውን በሙሉ ለሽፈራው ቢሰጡም የሽጉጤን ልጅ ከሚኒሊክ ቤተመንግስት የሚያስገባላቸው አልሆነም። ሌላው ምርጫቸው የነበረው ደመቀ መኮንንም በምክትልነት የያዘውን ቦታ በመቀጠሉ ቀድሞውኑ ውድድሩ ውስጥ አለመግባቱ ታውቋል። እናም ህወሀቶች ከስብሰባው ሲወጡ በንዴት ጦፈው፡ ተኮራርፈው፡ እየተወራጩ እንደነበረ ከውስጥ የተገኘ መረጃ አመልክቷል።

ብአዴንና ደኢህዴን የያዙት አቋምና ለዶ/ር አብይ መመረጥ የነበራቸው አስተዋጽኦ የህወሀቶችን የበላይነት ያፈራረሰው ይመስላል። በአብዮታዊ ዲሞክራሲ እያሳበቡ፡ ከመስመር ወጥታችሁ በሚል የቃላት ዱላ እየደበደቡ የበላይነታቸውን ለማስጠበቅ በሚል አባል ድርጅቶችን እንደፈረስ ሲጋልቡ የሰነበቱት ህወሀቶች በሰሞንኛው ስብሰባ የገጠማቸው ዱብ እዳ ነበር። የኦህዴድ ማፈንገጥ እያለ ብአዴንና ደኢህዴንም ቋንቋቸውን መቀየራቸው ለህውሀት ከባድ መርዶ ነው። የመጨረሻውን መጀመሪያ በቁማቸው አዩት። ሞታቸውን አሸተቱት።

አዎን! ህወሀቶች ክፉኛ ቆስለዋል። ላለፉት 27 ዓመታት በቀጭን የስልክ መልዕክት ያሻቸውን፡ የፈለጉትን መሪ ሲመርጡ፡ ሲያስመርጡ፡ ሲሽሩ፡ ሲያባርሩ የለመዱት አሁን ጊዜ ከድቷቸው በአንድ አዳራሽ ውስጥ ተሰብስበው የፈቀዱትን መምረጥ እንኳን ሳይችሉ ቀርተዋል። ከእንግዲህ ምን ሊያደርጉ ይችላሉ? የሚቀለብሱት ውጤት አይደለም። እያቃራቸውም ቢሆን ከመቀበል ውጪ ምርጫ የላቸውም። ለኦሮሞ ተወላጅ ወንበሩን ሰጥታችሁ እጃችሁን አጣጥፋችሁ ተቀመጣችሁ የሚለውን የደጋፊዎቻቸውን አስፈሪ ተቃውሞ የሚመክቱበት ትከሻቸው ከዛለ መጪው ጊዜ ከባድ ይሆንባቸዋል።

በመቀሌ ከ2500 በላይ ሰዎች የሚሳትፉበት ጉባዔ የጠሩት አንድም ይህን ጉዳይ ለደጋፊዎቻቸው ሊያረዷቸውና ሊያጽናኗቸው ይሆናል። አይዟአቹሁ፡ መልሰን እናገኘዋለን ብለው በተስፋ ሊያጠግቧቸው ተዘጋጅተውም ይሆናል። ለጊዜው በህወሀቶች ሁኔታ ደጋፊዎቻቸው ግራ ተጋብተዋል። የ60ሺህ ትግራዋይ ህይወት የተገበረለትን ስልጣን አንዲት ብልቃጥ ደም ላላፈሰሱት የለማ ቡድን አባላት አስረከባችሁ የሚለው ተቃውሞ ከወዲሁ አስፈርቷቸዋል። በማህበራዊ ሚዲያ የሚታየው የትግራይ ተወላጆች ቁጭት ለህወሀቶች ጥሩ ምልክት አይደለም። ከወዲሁ አዲስ የትግራይ ፓርቲ እንዲመሰረት ጥያቄ ማቅረብ ጀምረዋል።

ዶ/ር አብይ ስጋት ወይስ ተስፋ?

የዶ/ር አብይ መመረጥ በነጻነትና ዲሞክራሲ ናፋቂው ጎራ በኩል የተለያዩ ስሜቶችን ፈጥሯል። ስጋታቸውን የሚያንጸባርቁ በርካቶች ናቸው። ተስፋን የሰነቁም ቁጥራቸው ቀላል የሚባል አይደለም። ከሁለቱ ሌላ ፍጹም ደስታ ያሰከራቸው፡ በአንጻሩ ደግሞ ጨለማው ብቻ የሚታያቸውም አሉ። የአንዳንድ የዲሞክራሲና የነጻነት ታጋዮችና አክቲቪስቶች በደስታ ስካር አቅል የመስታቸው ሁኔታ የሚያስፈራ ነው። ከአዲስ አባብ ኢህአዴግ የስብሰባ አዳራሽ ዜናው በጭምጭምታ ከተሰማበት ጊዜ አንስቶ ኢትዮጵያ ነጻ የወጣች እስኪመስል በደስታ የተንሳፈፉ ሰዎች ሁኔታ በእርግጥም የጤና አይመስልም። መርህ የሌለው በትንሽ ድል የሚተነፍስ ታጋይ ወይም የነጻነት አቀንቃኝ ራሱን ቢፈትሽ ጥሩ ነው። ተስፋ ማድረጉ ባልከፋ። ነገን መልካም እንዲሆን መመኘቱም ይሁን። ነገር ግን መዘንጋት የሌለብን አሁንም ከቤተመንግስት ያለው ህወሀት መሆኑን ነው። መከላከያው በእጁ ነው። ደህንነቱን የነጠቀው ሌላ አካል እስከአሁን የለም። በኢኮኖሚው ረገድ አሁንም ጡንቻው አልሟሸሸም።

የዶ/ሩን መመረጥ በጨለመው ጎኑ ብቻ የሚመለከቱትም አካሄዳቸውን ቢመረምሩት መልካም ነው። የዶ/ሩ መመረጥ በህወሀቶች የተቀነባበረና የኢትዮጵያውያንን ትግል ለመደፍለቅ የተቀመመ መርዝ ነው የሚሉት ወገኖች ህወሀትን እያጀገኑ፡ የሌለውን ጉልበት እየሰጡት፡ ሌላውን አቅም ያጣ ሁሌም ተላላኪ አድርጎ የመደምደም አደገኛ አዝማሚያ መሆኑን ያወቁት አይመስለኝም ። አቶ ለማ መገርሳና ዶ/ር አብይ አህመድ ነጥረው ከወጡበትና በኢትዮጵያውያን ዘንድ ተሰሚነትን እያገኙ ከመጡበት ጊዜ አንስቶ ልባቸውን ጥርቅም አድርገው የዘጉት እነዚህ ወገኖች የአብይን መመረጥ ለኢትዮጵያ ከበጎነቱ ይልቅ ይበልጥ የከፋ ጊዜ ያመጣባታል ብለው በባዶ ሜዳ የሚደነብሩና ነገን የሚያጨልሙትን ፈጣሪ ይርዳችሁ ከማለት ውጪ ምን ይባላል? እነዚህ ወገኖች ማወቅ ያለባቸው ከየትኛውም ፓርቲና ግለሰብ በላይ ኢትዮጵያ ላይ ሃያል ጉልበት የሆነው የህዝብ እምቢተኝነት የለውጣችን ዋልታና ማገር፡ የነጻነታችን ምርኩዝና መሰላል መሆኑን ነው። የህወሀት ድራማ የማያንበረክከበው፡ የትኛውም ማስመሰያ ቲያትር የማያዘናጋው የማያዳክመው የህዝብ ማዕበል።

ህወሀት በእርግጥ ተዳክሟል። እንደበፊቱ ረግጦና ጨፍልቆ የመግዛት አቅም ከድቶታል። እየሰመጠ ያለ መርከብ ነው። ግን ደግሞ እንደህወሀት ያለ አገዛዝ በቀላሉ የሚላቀቁትም አይደለም። እድሉ ጠባብ ቢሆንም አፈር ልሶ አይነሳም ማለትም አይቻልም። ዘረኛ፡ ወንጀለኛ፡ ማፊያ፡ ፍጹም ጨካኝና አውሬ በሆኑ ሰዎች የሚመራ በመሆኑ ፈራርሶ፡ ወላልቆ፡ ከሩቅ ጉድጓድ ካልተቀበረ በቀር ለኢትዮጵያ ለውጥ ማሰብ እጅግ አስቸጋሪ ነው። ምንም እንኳን ህወሀት ከእንግዲህ እንደጠንካራ ድርጅት ቆሞ መሄድ የማይችል ቢሆንም እያነከሰም የእኛን ምጥ ማራዘምና ስቃያችንን መቆሚያ የሌለው በማድረግ ረገድ አቅም የሚያንሰው አይሆንም። ከእንግዲህ ህወሀት ያለልኩ ያጠለቀውን የመንግስትነት ካባ አውልቆ እልም ያለ የጥፋት ሃይል ወደ መሆን ይሸጋገራል። በተስፋ መቁረጥ ባህር ውስጥ የተነከረ በመሆኑ አጥፍቶ ከመጥፋት ውሳኔ ላይ ሊደርስ ይችላል። የዶ/ር አብይ አንዱ ፈተናም ተስፋ ከቆረጠ አረመኔ አገዛዝ ስልጣኑን በሰላም የመረከቡን እድል እንዴት ያገኛል የሚለው ነው።

በለማ ቡድን አዲስ አቅጣጫ ቀልብና ስሜቱ የተማረከ ኢትዮጵያዊ የዶ/ር አብይን መመረጥ በይሁንታ ተቀብሎታል ማለት ይቻላል። በዚህም ህዝቡ በሰፊው እየጠበቀ ነው። ዶ/ር አብይ በቃል የነገሩትን፡ ኢትዮጵያዊነትን ከፍ አድርገው ከሰቀሉት የክብር ማማ ሀገራቸውን ማየት የሚፈልጉት ኢትዮጵያውያን ከአዲሱ መሪ ቢያንስ የተወሰኑ እርምጃዎችን እንዲወስዱ ከወዲሁ መጠየቅ ጀምረዋል። ለዶ/ር አብይ ትልቁና ዋናው ፈተናም ይህኛው ነው። በመጀመሪያዎቹ ቀናት ህዝቡ የሚጠብቃቸው እርምጃዎች ላይ ተመሳሳይ አቋሞች እየተንጸባረቁ ነው። ሶስት ነገሮችን በመጥቀስ ዶ/ር አብይ ተፈጻሚ እንዲያደርጓቸው ሀሳቡን በመሰንዘር ላይ ነው። ለሁሉም የተቃዋሚ ድርጅቶች ሀገራዊ ጉባዔ እንዲጠሩ፡ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ጨምሮ የቀሩ የፖለቲካና የህሊና እስረኞችን እንዲለቁ፡ ህዝብ ላይ የተጫነውን አስችኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲያነሱ የሚሉት ሀሳቦች ተነቅሰው በመጀመሪያዎቹ የዶ/ር አብይ የስልጣን ቀናት ተግባራዊ እንዲደረጉ በበርካቶች ዘንድ ስምምነት ያገኙ ይመስላሉ። እንግዲህ የእኔም ሆነ የአንዳንዶች ስጋት የሚጀምረው እዚህ ጋ ነው።

ህውሀት ቢዳከምም መከላከያው ውስጥ የበላይነቱ እንዳለ ነው። በደህንነቱም እንደዚያው። እነዚህን ሁለት ቁልፍ የስልጣን ማስጠበቂያ ተቋማትን እንዴት ከህወሀቶች እጅ ፈልቅቆ መውሰድ ይቻላል? እስከአሁን ምንም ምልክት የለም። እነዶ/ር አብይ ውስጥ ለውስጥ ስራ ሰርተው ከሆነ እሰየው ነው። ህወሀቶች በመከላከያና በደህንነቱ ላይ የበላይነታቸው ከተገፈፈ ጨዋታው እንደሚያበቃ ያውቁታል። ያንን በመቃብራቸው ላይ ካልሆነ በቀር የሚፈቅዱት እንደማይሆን ይታመናል፡፡ ይህ ዋናው መሰረታዊ ጉዳይ ነው። በእነዚህ ተቋማት ላይ መዋቅራዊ ለውጥ ስለመኖሩ ፍንጭ ባልታየበት ሁኔታ የዶ/ር አብይ ጠቅላይ ሚኒስትርነት ከአቶ ሃይለማርያም ይሻላል ብሎ መጠበቅ የዋህነት ነው።

ህወሀት አፈገፈገ ወይስ ሸሸ?

አልሸሸም። አፈግፍጓል። የረባሽነት ሚና የመጫወት ስትራቴጂ መንደፉ ይጠበቃል። ከወዲሁ ለአዲሱ መሪ እሾህና አሜኬላ ከፊት ለፊቱ እየተከለ ነው። የአዲሰ አበባ ጉዳይን በእነአባዱላ ገመዳ በኩል ወደፊት በማምጣት ዶ/ር አብይ ጠረጴዛ ላይ ማኖር አንዱ የመበጥበጥ ስትራቴጂው ነው። ዶ/ር አብይን ቅርቃር ውስጥ ይከቱታል ተብለው ከሚታመኑ ጉዳዮች አንዱ የኦሮሚያ ልዩ ጥቅም በአዲስ አበባ የሚለው አጀንዳ ነው። በሚቀጥሉት ሁለት ሶስት ወራት ውስጥ የአዲስ አበባን ጉዳይ ውሳኔ እንዲሰጥበት ከፍተኛ ጫና ለማድረግ ህወሀት ተዘጋጅቷል። ከኦሮሞ ብሄርተኞችና ከተቀረው የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም ከአዲስ አበባ ነዋሪ ጋር የሚያላትመውን ይህን አጀንዳ ወደፊት በመግፋት መንገዱ ለዶ/ር አብይ አባጣ ጎርባጣ እንዲሆን በህወሀት በኩል በማፈግፈጉ ስትራቴጂ የተያዘ ቀዳሚ ተግባር እንዲሆን የተፈለገ ይመስላል።

ሌላው የአብዲ ኢሌ ካርድ ነው። የሶማሌውን አጋር ፓርቲ ወደ ኢህአዴግ አባልነት ለማምጣት የተዋደቀው ህወሀት በእነለማና ገዱ የተባበረ ሃይል ከሽፎበታ። ቀጣዩ ስትራቴጂ አብዲ ኢሌን በመጠቀም የአዲሱን መሪ ስራ ማወክ ነው። ከወዲሁ በጭምጭምታ እንደሚሰማውም የህወሀት የጦር ጄነራሎች ከአብዲ ኢሌ ጋር እየመከሩ ነው። ዶ/ር አብይ የተዛባውን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለማስተካከልና የህወሀትን ዘረፋ ለማስቆም እርምጃ የሚወስድ ከሆነ የአብዲ ኢሌ ልዩ ሃይል ጦር አከባቢውን ለማተራመስ እንዲዘጋጅ፡ ህወሀቶችም ቀውሱን ለማረጋጋት በሚል መፈንቅለ መንግስት አድርገው ዳግም ስልጣኑን መጨበጥ እንደስትራቴጂ ከኋላ ኪስ ተውሽቋል።

ህወሀት የዶ/ር አብይ ስልጣን ቀውስ የበዛበት ሆኖ የኢትዮጵያ ህዝብ ስጋት ውስጥ በመግባት በዶ/ር አብይ ላይ ፊቱን እንዲያዞር ማድረግ በማፈግፈግ ዕቅዱ የሚያከናውናቸው ተግባራት ውጤት እንዲሆን ፈልጓል። የትግራይ ተወላጆችንም ይበልጥ በጎኑ ለማሰለፍ በአንዳንድ አከባቢዎች ትግራዋይ ላይ ያነጣጠረ ጥቃት እንዲፈጸም ሊያደርግም ይችላል። ህወሀት አርፎ አይቀመጥም። ለማ እና ገዱ ድባቅ መትተው የ27 ዓመቱን መርዝ ያረከሱበትን የኦሮሞ-አማራ ጉዳይ ወደ ኋላ በመመለስ ዳግም ግጭት ለመፍጠር መፍጨርጨሩ የማይቀርም ነው። ያዳቆነ ሴይጣን ሳያቀስ መች ይለቃል?

ዶ/ር አብይ ውስብስብ የሆነውን የኢትዮጵያ የፖለቲካ ባቡር መሪ ጨብጠዋል። ፈተናው ብዙ ነው። ከያአቅጣጫው ነው። የህወሀትን አከርካሪ የሰበረው ህዝባዊ ትግሉም ተንጠልጥሏል። ዶ/ር አብይን ለመሪነት እንዲበቁ ነዳጅ የሆነው ህዝባዊ እምቢተኝነቱ መንታ መገድ ላይ ቆሟል። ይህ በጣም አደገኛ ነገር ነው። ዶ/ር አብይም ከህወሀት ጥቃት የሚተርፈው ይህ ትግል ሳይቀዘቅዝ እንደጋለ መቀጠል ከቻለ ብቻ ነው። ዶ/ሩ ሌላ ምን ጉልበት አላቸው?

በተረፈ ዶ/ር አብይ ህዝብ ተስፋ ያደረገውን ለውጥ እንዲያመጡ በግሌ እመኛለሁ። ህዝባዊ ትግሉ ግን ለአፍታም መቆም የሌለበት መሆኑን አድምቄ ለማስመር እፈልጋለሁ። አሁንስ ተስፋዬ ማን ነው?……. ህዝባዊ ትግሉ አይደለምን?!!!

“ሰይፍህን  ወደ ሰገባው መልስ” (ከታምራት ይገዙ)

ህጻን ዩሴፍ እሸቱን

በአሁን ሰዓት የአግራችን የኢትዮጵያ አየር በህጻናት ደም እየታወደ ይገኛል:: ልጅ እያለን እናቶቻችን በህዳር  ወር ላይ ወረርሽኝን ለማጥፋት በሚል ሰበብ  በየጎራችን ቆሻሻ እየሰበሰቡና እያቃጠሉ ያውዱን ነበር:: በኢሀዼግ/ህወሀት ዘምን በተለይ ባለፉት ወራቶች የ13 ዓመት ህጻን ዩሴፍ እሸቱን በመሳሰሉት የህጻናት ደም አገራችን እየታወደች ትገኛለች:: እንዲሁም በሞያሌ  በኩል በአስቸኮይ ሰዓቱ ስም የተበከለ የህዝብ ደም ይጮሃል የወገን ያለህ ይላል:: በተለይ የሚገርመው ነገር በኢህኣዴግ/ህወሀት በኩል አሁንም የማስፈራሪያው: የጉራውና የማስጠንቀቅያው ጫጫታ ከምንግዜውም በላይ ይሰማል:: ቅጥፈትና ባዶ ፕሮፓጋንዳው ውጪ ባላሉት የህወሐት ደጋፊዎችና በትግራይ ህዝብ ደም የሚነግዱ የትግራይ ተወላጆ ሙህራኖችና ባለሃብቶች  ይስተጋባል:: በዚህ ትንኮሳ በዚህ ማስፈራሪያና ድፍረት የተኛው አንበሳ ማግሳት ቢጀምር በግ ሕብረተሰባችን ወደ ተኩላነት ቢለወጥ ለማነው ኪሳራው? በኢህኣዴግ/ ህወሀት መሪዎች በሚያፈሱት የንጹሃን ደም አእምሮቸው በጥፋተኝነትና በተጠያቂነት እያሳቀያቸው ይገኛል <<ጥፋተኛ አእምሮ ባለቤቱን ያሰቃያል>> ብሎ የለ” ቾውሰር”::

በሰይፍ ማመን አግባብ አይደለም:: በሰይፍ የሚያምኑ ሁሉ በመጨረሻ የሚሞቱት (የሚያልቁት) በሰይፍ ነውና:: በዓለማችን በህዝባቸው ላይ ሰይፍ አሊያም የጦር መሳሪያ የመዘዙ እብሪተኞችና ቀጣፊዎች እስከ መንገዱ ጫፍ ድረስ ተጉዘው አያውቁም ይህንን ለማስተዋል የሰው ህይወት የሚቀጥፉት የህወሀት መሪዎችና  ደጋፊዎቻቸው የትግራይ ተወላጆች ታሪክ ማንበብ አሊያም እሩቅ መሄድ የለባቸውም ባለፉት ሶስትና አራት አመታት በሊቢያው መሪና በግብጹ መሪ ላይ የደረሰን ማስታወስ ከበቂ በላይ ማስረጃ ነው::

ዛሬ የህወሃት/ኢህኣዴግ ገዥዎች በቤቱ ላይ እሳት በእሱ ላይ ጥይት የሚለቁበት ሕዝብ በግድ ወደ ነብርነት ወደ አንበሳነትና ወደ ተኩላነት ሊለወጥ እንደሚችል የማያውቁ ከሆኑ ሂሊናቸው በስልጣን የናወዘ መሆኑን ነው የሚያስረዳው ሌሎቹም የህወሓት ደጋፊዎች የሆኑ የትግራይም ሆኑ የሌሎች ቤሄረሰብ ተወላጆች ይህ ካልተረዱ ጊዛዊ ጥቅም ምን ያህል ሂሊናቸውን አንደሸበበው ነው የሚያሳየው:: ህወሐቶች በሚገዙበት አገር እንደ በግ ዝም ማለት ራስን ምንኛ ለጥቃት ማጋለጥ ማዋረድ መሆኑን እነሆ ከሃያ አምስት አመት የውጣ ውረድ ጉዞ  ብንቆይም አሁን የተረዳን ይመስለኛል:: የሰፈራችን ድንጋይ ፈላጭ ቀበና ያለውን ድንጋይ ሲፈረካክሰው የተመለከት መንገደኛ <<ድንጋዩም መጎለቱን አብዝቶት ነበር>> አለ ይባላል::

የኢትዮጵያም ህዝብም ህወሃቶች ነገ ከስተታቸው ተምረው ይመለሳሉ ሲሉ ይህው ግዜው ነጎደ እነሱም አልተማሩም በመጨረሻም በነሱ አገዛዝ ዘመን ተወልደው ያደጉ ቄሮ አርበኞችና ፋኖ አርበኞች እምቢ ለአገራችን እምቢ ለህዝባችን በማለት በአራቱም የአገራችን መዓዘናት እየተነሱ ይገኛል :: እነዚህ የዘመናችን አርበኞች የሚሞቱበት አላማ እንጂ የሚገሉበት ተልኮ የሌላቸው በመሆኑ በየሚሄዱበት ሰላማዊ ሰልፍ ሁሉ እጃቸው ላይ ምንም የመሳሪያ አይነት የማይታየው:: የነሱ እምነት  በሰላማዊ መንገድ መንግስትን ማንንበረከክ ነው እየታየ ያለው እውነታውም ይሄው ነው:: << ዋ! ለህወሃቶች ዋ! ለደገፊዎቻቸው እኔን አያርግርኝ ሰዓቱ ሲደርስ ጽዋው ሲሞላ:: መሬት እንኮን ተከፍታ ብትውጣቸው ከነዚህ የዘመኑ አርበኞች ማምለጥ አይችሉም::

ህወሃቶችም ሆኑ የትግራይ ደጋፊዎቻቸው ክፉና አጥፊ ራዕይን ተከትለው የሚመጡ መሆናቸውን የማያውቅ ያለ አይመስለኝም:: ዘወትር ግድያ በሚፈጸምበትና ሕይወት ዋዛ በሆነበት አገር ይልቁንም መንግስታዊ ሽብር በነገሰበት ሥፍራ የኮማንድ ፖስቱ የግድያ ራዕይ ፍንትው ብሎ ይታያል:: የህጻናትን ደም ካፈሰሱ ቦሓላ እንኮ እንደ ገና ተመሳሳይ የበለጥ እልቂት ለማካሄድ በሚፎከርበትና ሰአት በዊጪ ያሉ የህወሃት ደጋፊ የሆኑ የትግራይ ተወላጆች ስብሰባ ተሰብስበው የሰራችሁትና ልትሰሩ ያሰባችሁት ትክክል ስለሆነ እንደግፋችዋለን የሚል መግለጫ ሲያወጡ ለጥቅማቸውና ለሆዳቸው ሲሉ ምን ያህል የትግራይን ህዝብ እንደጠሉ ነው የሚያሳየው::  የህወሃት መንግስት የበለጥ እልቂት ለማካሄድ በሚፎክርበትና ማስጠንቀቅያ በሚያጎርፍበት አገር ከደም ጥማት ይልቅ የደም ስካር እንዳለም ግልጽ በሆነበት ሰዓት ለዚህ ክፉ ራዕይ እየተባበራቹ ያላችሁት የትግራይ ተወላጆች ከህዝባችሁና ከወላጆቻችሁ ከእህት ከወንድሞቻችሁ ከትግራይ ተወላጆች በላይ ጥቅማችሁንና ሆዳችሁ በማስቀደማቹ  የነገሰባችሁን  የደም ጥማትና የደም ስካር በስሙ መጥራት እየፈራችሁ ባለባችሁበት  ሰዓት ነው አሜሪካኖችና አውሮፓዊያኖች ወጥተው ያወገዙት ከማውግውዝም ያለፈ የአሜሪካኑ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ወደ ኢትዮጵያ የተጎዙት::

እነዚህ የህወሓት መሪዮችና በጥቅማ ጥቅም እጃቸው በደም የተለወሰው የትግራይ ሙህራኖችና በላጸጋዎች ከንግግራቸውና ክተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያቸው እንደምንረዳው በኮማንዶ ፖስቱና በህወሃት መሪዎች አእምሮ ውስጥ የመሸገው ጥላቻና ንቀት በየሰበቡ እየፈነዳ በአገራችን ወደ ፊት የበለጠ የሰው ህይወት እንደ ቅጠል እንደሚቀጠፍ ለመናገር የግድ ነብይ መሆን አይጠበቅብንም::  በአሁኑ ሰዓት የኢትዮጵያን ጉዳይ የሚከታተሉ የምእራባዊያን መሪዎችም ሆኑ ግለሰቦች  የህወሃት መሪዎችና ኮማንዶ ፖስቱ እንዲሁም በውጪ ያሉ የህወሃት ደጋፊ የሆኑ የትግራይ ተወላጆች በደም የተጨማለቁና በደም የሰከሩ መሆናቸውን ጥንቅቀው እየተረዱ ይገኛሉ::

በአገራችን በኢትዮጵያ የጀግናም የፈሪም የሰላማዊውም የታጋዩም ሆነ የማናቸውም ዜጋ ሕይወት መንግስትታዊ ጥበቃና ዋስትና እንደሌለው ከማናቸውም የህወሓት/ኢሃዴግ መሪ ጋር መከራከር ይቻላል:: ሕይወት በማይከበርበትና ዋጋም ባጣበት አገር ደግሞ ሳይታሰብ የእነዚያም ሕይወት የተበዳዮች ኢላማ ይሆናል:: ሕይወት የማያከብሩ ህወሓቶችም ሆኑ የነሱ አጋር የሆኑ የትግራይ ተወላጆችም ሆኑ ሌሎቹ ከሰባዊነት ጋር በጠላትነት የሚቆሙ ወገኖችና ደጋፊዎቻቻው መዘንጋት የሌለባቸው የነሱም ሕይወት በዒላማ ክልል ውስጥ እንደሚገባ ነው::  ጊዜ ይፍጅ እንጂ መግደል ስትጀምሩ ሞት ወደ እናንተም ያነጣጥራል:: በእኔ እምነት በስልጣን ላይ ያሉት የህወሓት አመራሮችም ሆኑ የህወሓት ደጋፊዎች የሆኑ የትግራይ ሙህራኖችና ባለ ሀብቶች ማየትና ማስተዋል የተሳናቸው ከፊት ለፊታቸው እየመጣ ያለውን አደጋ አለማስተዋላቸው ነው::

እርግጥ ነው ይህን የህወሓት መሰሪ ተግባር በትግራይ አባቶቻችንና እናቶቻችን አሊያም በትግራይ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ላይ እያንዣበበ የለውን ክፉ ቀን የተገነዘቡ የትግራይ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ከተቀረው ኢትዮጵያዊ ጋር መቆም ጀምረዋል ምሳሌም ለመጥቀስ ወይዘሮ አብርህት ኪሮስ አርያ ትውልደ ትግራይ ሲሆኑ በኢሳት ቴሌቭዥን ቀርበው እንባ እየተናናቃቸው ነበር ቃለ ምልልስ ያደርጉ የነበሩት:: ሌላው ደሞ ወንድማችን አቶ አምባሳደር አለፎም ናቸው  እኝህ ሰው አገር ቤት በነበሩበት ጊዜ የየካ ክፍለ ከተማ የመሬት ልማት አስተዳዳሪ የነበሩ ሲሆኑ  እኝህ ወንድማችን በኦሮሞ ሚዲያ ቴሌቭዥን ላይ ቃለ መጠይቅ ሲደረግላቸው በትግራይ ውስጥ የሚኖሩት የትግራይ እናቶቻችንና አባቶቻችን እንዲሁም ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በምን ዓይነት መጥፎ አገዛዝ ስር እንዳሉ በማያሻማ ሁኔታ ግልጸውታል:: ሌላው ደሞ በውጭ የሚገኙት የአርና ትግራይ ደጋፊዎች ሰሞኑን የህወሃትን አገዛዝ በማውገዝ መግለጫ እያወጡ ይገኛሉ እንደነዚህ አይነቶቹ ግለሰቦችም ሆኑ የደርጅት ተወካዮች የትግራይ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ሊበረታቱ ይገባል:: ከዚህ በፊት ቀደም ብዪ ባወጣሁት ጹሁፊ  እንዳልኩት ሁሉ ዛሬም የምለው <<  የትግራይ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ለምን አይነሱም ማለት ሳይሆን ጥያቄው መሆን ያለበት ያልተነሱበት ምክንያት ከአብራካቸው የወጡት የእንግዴ ልጆች የሆኑት የህወሓት መሪዎችና ተከተዮቻቸው ምን ያህል ተጽኖ ቢያደርጉባቸው ነው ሊነሱ ያልቻሉት? ምን ዓይነት ትብብር ቢደረግላቸው ነው ከዚህ ጨቆኝ መንግስትና ከአብራካቸው ከተፈጠረው ከህወሀት ሊላቀቁ የሚችሉት የሚል ጥያቄ ነው  መቅደም ያለበት እላለው::

በሌላ በኩል ደሞ ተቃዋሚ ኃይሎችም ሆኑ ሁላችንም የምናቀርበው ጥያቄ <<ወንጀሉን የፈጸሙት ሰዎች ከፍርድ ፊት ይቅረቡ>> ከሚል የዘለለ አይደለም በዓሁኑ ሰዓት አንድ ሰራዊት የሚንቀሳቀሰው ወይ ትዕዛዝ የሚቀበለው ከአንድ የበላይ አዛዡ ከህወሀቶች አሊያም ከኮማድ ፖስቱ ነው:: <<አህያውን ፈርቶ ዳውላውን>> እንደሚባለው ዙሪያውን ከመሸከርከር የሁላችንም ጣቶች ወደ ትክክለኛው ተጠያቂ ወደ ሆኑት ወደ ህወሃት መሪዎችና አቶ ስዩም መስፍን; ወደ አቶ ደብረ ጺዮን ገ/ማርያም; አቶ ስባሐት ነጋ; አቶ በረከት ስመዖን; አቶ አቦይ ጸሃዪ; እና ወደ ኮማድ ፖስቱ ወደ ሲራጅ ፈርጌሳ ማመልከት አለባቸው ባይ ነኝ::

በሌላ በኩል ለኢትዮጵያ የጣር ሰራዊትም ሆነ የፀጥታ  አስከባሪ ፖሊሶች ይህንን ቅዱስ ቃል ከዚህ በፊት ሰምታችሁት ብታውቆም በድጋሚ ላስታውሳችሁ ” ስምዖን ጴጥሮስም ሰይፍ ሰለ ነበረው መዘዘው የሊቀ ካህናቱንም ባርያ መትቶ ቀኝ ጆሮውን ቆረጠ የባሪያውም ስም ማልኮስ ነበር:: ኢየሱስም ጴጥሮስን እንዲህ አለው ሰይፍ የሚያነሱ ሁሉ በሰይፍ ይጠፋሉና ሰይፍህን   ወደ ሰገባው  መልስ አለው :: <<የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 26: ከ51-53>> ስለሆነም እናንት  የጦርና  የፖሊስ ሠራዊት የሆናችሁ ሁሉ ህዝቡ ላይ አንተኩስም እናት አባቴን እህት ወንድሞቼን አልገድልም በማለት ከዚህ አይነት የታሪክ ውርደት ራሳችሁ የምታወጡበት ሰዓቱ አሁን ነው:: ለህዝብ ደህንነትና እንክብካቤ የቆምክኝ በአገሪቱ ዳር ድንበር ላይ ለመሞት የተዘጋጀው የክፉ ቀን የኢትዮጵያ የጦር ሠራዊት ነኝ ብላችሁ ፍርሃትን ሳትፈሩ ለህወሃት መሪዎች ቁርጡን መናገር ይጠበቅባችዎል ያን ግዜ ነው ከታሪክ ተወቃሽነት የምታመልጡት::  

በተጨማሪ እናንት የጦር ሰራዊት የሆናችሁና የፖሊስ ሰራዊ የሆናችሁ የኢትዮጵያውያን ብርቅዪ ልጃች እስቲ እራሳችሁንጠይቁት ከተራ ወታደር አስከ ሻለቃ ባሻ በውስጣቹ የትግራይ ተወላጅ ሆኖ የህወሓት ታዛዥ ምን ያህል አለበኔ ግምትአንድ እጅ:: ከምክትል መቶ አላቃ እስከ ሻለቃ ምን ያህል የትግራይ ተወላጅ የህወሓት ቅጥረኛ አለሁለት ሦስት እጅ:: ከሌተና / እስከ መጨረሻው እርከን ያሉ የትግራይ ተወላጆችና የህወሓት ቅጥረኞች ምን ያህሉ ናቸው ምናልባትአምስት እጅ:: ታዲያ አሥር እጅ የማይሞሉ የትግራይ ተወላጆች የህወሓት ደጋፊ ወታደሮች እንዴት ነው መሳሪያ የታጠቀንዘጠና እጅ የሚሆነውን ኢትዮጵያዊ ወታደርን ሊመሩት አሊያም ሊያሸንፉት የሚችሉት:: በእኔ እምነት እናንት የጦርሰራዊቶችና የፖሊስ ሰራዊት የሆናችሁ ሁሉ ከዘመኑ አርበኞች ከቄሮዎችና ከፋኖዎች ጋር በመሆን እናንተንም መላውንየኢትዮጵያዊ ከህወሀት አገዛዝ መታደግ የምትችሉበት ሰዓቱ አሁን ነውና የያዛችሁትን መሳሪያ አፈ ሙዙን ወደ ህዝብሳይሆን እናንተንም ቤተሰቦቻችሁንና መላውን ህዝብ ወደ ሚያሰቃዩት ወደ ህወሀት መሪዎች መሆኑን ለነንተ መንገርማለት << ለቀባሪው አረዱት>> እንደማለት ነው::

ደል ለዘመኑ አርበኞች ቄሮዎችፋኖዎችና ለጦር ሰራዊታችንና ለፖሊስ ሰራዊቶቻችን:: 

ኦህዴድ ሆይ ለምሳ ታስበሃልና ለራስህ ስትል እወቅበት። (መኮንን ሀብተጊዮርጊስ ብሩ (ዶ/ር))

በመጀመሪያ የዶ/ር አብይ አህመድ ጠ/ሚንስትር ተብሎ መሰየምም ሆነ መመረጥ የሕዝብ ትግል ዉጤት ነዉ ብዬ አምናለሁ። ስለዚህም መስዋህትነት እየከፈለ ያለዉን ሕዝብ ማመስገንም ማበረታታትም እፈልጋለሁ። ሁሉም ወገን በደንብ ሊያዉቀዉ የሚገባ ቁም ነገር ግን የወጣቱ ሙሁር በቦታዉ መሰየም የመጨረሻዉ መጀመሪያ ደዉል ብቻ ሳይሆን የሶስትዬሽ የትርፍ ሰዓት የጥሎ ማለፍ ጫወታ ጅማሬመሆኑን ነዉ።

ቡድን አንድ ኦህዴድ እና በተወሰነ መልኩ ብአዴን

የፕሬዘዳንት ለማ መገርሳ ኦህዴድ የመጨረሻዎቹን የትርፍ ሰዓት የጫወታ ጊዜያት በድል ለማጠናቀቅ የሚያስችል ብስለት የለዉም ብዬ ለመናገር አልደፍርም። ከአዉሬዉ ጋር በትህግስት ብዙ ዘመናት የኖሩ በመሆናቸዉም ከመቁሰሉ በፊትም  ሆነ ከቆሰለ በኋላም ያለበትን ደካማ ጎንና አሁንም ያለዉን የጣር ሰዓት ኀይል ጠንቅቀዉ ያዉቃሉ። ይህም መረዳታቸዉ ነዉ ከሕዝቡ ትግል ጋር ተዳምሮ እዚህ ያደረሳቸዉ። ይህም መረዳታቸዉ ህወኣትን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ይቀብሩት ዘንድ ሊያበቃቸዉ ይችላል። በእርግጥ ነፃነት ለራበዉና ለጠማዉ ሕዝብ የቡድን አንድ ድል አዝጋሚ ይሆናል።

ይህን የትርፍ ሰዓት ሹኩቻ ኦህዴድና የብአዴን ተራማጆች ከሕዝባቸዉ ጋር የበለጠ ለመናበብ ከሞከሩበትና መለስተኛና ከፍተኛ የክልሉ መሪዎቻቸዉ የስልጣናቸዉ ባለቤት ማድረግ ከቻሉ፤ በተጨማሪም ጠንካራ ቄሮና ፋኖ እንዲኖር ከፈቀዱ ብቻ ሳይሆን መዋቅሩ እንዲጠነክር ተግተዉ ከተንቀሳቀሱ፣ በኢዮትጲያ ሕዝብ ልብ ዉስጥ ከሞተ የሰነባበተዉን ህወኣትን መመከት ብቻ ሳይሆን መቅበር ይችላሉ። ቀድሞ እንደተገለፀዉ የዚህ አቅጣጫ ሂደት አዝጋሚ ቢመስልም ጉዞዉ የበርካታ   ትናንሽ ድሎች ስብስብ በመሆኑ ነፃነት የጠማዉን ሕዝብ አቅጣጫ እያመላከቱ ይታገስ ዘንድ ማድረግ ይቻላል።

ይህ ጉዞና መዳረሻዉ ለአዉሬዎቹም የሚበጅ ነዉ። ቢያንስ ቢያንስ ጥቂቶቹ ከተጠያቂነት ሊያመልጡ ይችላሉ።  ወይም የያዙትን ይዘዉ ወይ መቀሌ አልያም ቤጅንግ ሊከትሙ በቂ ጊዜ ሊያገኙ ይችላሉ። ምንም ይሁን ግን ከእንግዲህ ከኢትዬጲያዊያን ጋር የደስታ መሃድ ይቋደሳሉ ብዬ  ተስፋ አላደርግም። ደም የተቃባ ሕዝብ አድርገዉናል።

ቡድን ሁለት ህወኣት

በዚህ ትርፍ ሰዓት ህወኣት የሚንቀሳቀሰዉ ወይም ሊቀምም የሚሞክረዉ መርዝ የኦህዴድንና ብሃዴንን መዋቀር ለመበጣጠስ የሚያስችለዉን ብቻ ሳይሆን ከሕዝቡም ለመነጠል ነዉ። ስለዚህም የመጀመሪያ እርምጃቸዉ መለሳለስ ሆናል። ሴይጣን መልሃክ መስሎ የሚመጣዉ ያህል ሊሆኑም ይችላሉ። አዲስ ጅማሬ በሚል ነጠላ ዜማ ጥቂት ሊያዳምቁ የሚችሉ ተቃዋሚ ተብዬዎችንም ይዘዉ በመምጣት ዳግም ሊያላምዱን መሞከራቸዉ አይቀርም። እርግጠኛ ነኝ ጥቂት የማይባሉም አባዱላዎች አሁንም   በቴሌቪዥን መስኮት ብቅ ብለዉ የትንሳኤ ማግስት የሆነ እስኪመስለን ማደንቆራቸዉን እንጠብቅ። ይህ ግን የመጨረሻዉ የወያኔ ካርድ በመሆኑ ለአፍታም መዘናጋት የለብንም። እባብ ሁሌም እባብ ነዉ። አበቃ!! ህወኣት ትናንትም ዛሬም እስኪቀበር ድረስም ኢትዮጲያ ለምትባል ሀገርና ኢትዮጲያዊ ለሚባል ሕዝብና ዘይቤ ጠላት ነዉ። ከመፈጠሯ ጀምሮ እጆቿን ወደ አምላኴ ዘርግታ ያለችዉ ይህ ቀድሞዉኑ ታይቷት ይሆን?  አዎን!!  አምላክ ደግሞ የለመኑትን የሚነሳ አይደለምና ጠሏቷ ከእግሯ ስር የመሆኛ ጊዜዉ ተቃርቧል።

ቡድን ሶስት ለነፃነቱ ተፋላሚዉ ሕዝብ

ቄሮም ፋኖም ዘርማም ግንቦት ሰባትም ሌላኛዉም የዉስጥም ይሁን የዉጭ አርበኛ ጥያቄዉ ነፃነት በመሆኑ መልሱም ነፃነት ብቻ ነው። አለመታደል ሆኖ ፍልሚያዉ በአመለካከትም ይሁን በባህሪ ሰዉን ከማይመስሉ ኋላቀሮች ጋር በመሆኑ በዚህ ዘመን ነፃነቴን ብለን መጠየቁ በራሱ አፋሪ ቢመስልም እንደ እንሰሳ መኖና የራሳቸዉ ቀንድ  ብቻ የሚታያቸዉ ዘረኞች ጋር ነዉና ትግሉ መደማማቱ ይቀጥላል።

ይህ ቡድን ተወደደም ተጠላም፣ ጊዜው ይርዘም ወይም ይጠርም  አሸናፊ መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነዉ፤ ምክንያቱም ሕዝብ እንደ ሕዝብ ተሸናፊ ሆኖ ሊቀር አይችልም። የእነ ለማና ዶ/ር አብይም ጥንካሬ ይህዉ ብቻ ነዉ። ወያኔም ከሕዝብ ሊነጥላቸዉ የሚንቀሳቀሰዉ ለዚሁ ነዉ። ስለዚህ ይህ ቡድን ኦህዴድንና ጠ/ሚ አብይን ለጊዜዉም ቢሆን ይቀበላል ወይም ታግሶ ጊዜ ሊሰጥ። ቢሆንም ግን በቋፍ ላይ እንዳለ ኦህዴድ ከዘነጋ ከነፃነት ዉጪ ማንም የማያነሳዉ ሰደድ እሳት ይነሳል። እሳቱም የህወኣትን ሬሳ ብቻ ሳይሆን ሌሎቹንም ይበላል። ስለዚህ ኦህዴድ ሆይ ለምሳ ታስበሃልና ለራስህ ስትል እወቅበት።

 

ኢትዮጲያ ለዘላለም ትኑር። አሜን

ለመረጃ ያህል – የጠቅላይ ሚኒስቴር ምርጫ ድምጽ አሰጣጥና ቆጠራ ውጤት

#ገዱና ለማ ህወሀትን ነጥብ አስጥለዋል!
በ 27 አመት ውስጥ #ብአዴንን ማደንቅበት 1 ነጥብ አገኘሁ። ህወሀትን በጠረባ መቶ ቲም ለማ ጋ ማበሩ!
እንደ ታማኝ ምንጫችን የለማና ገዱ መቀናጀትና መናበብ ህወሀት ላይ ጆከር በሞንቴ አስጥሏል።
በእውነት የብአዴኑ ደመቀ መኮንን በመጨረሻ ስዓት ውድድሩን አልፈልግም ብሎ መተው ብአዴን የፖለቲካ ጨዋታ ይችላል እንድንል ያስገድዳል።
ስለሆነም ብአዴን ለዶ/ር አብይ አህመድ መመረጥ የአንበሳውን ድርሻ እንደተወጣ አይሸሸግም። እንዲ ነው ለምሳ ያሰቡትን ህወሀት ቁርስ ማድረግ!!!
ከ180 መራጮች ውስጥ፦

– ዶ/ር አብይ – 108 ድምጽ
– ሽፈራው ሽጉጤ – 59 ድምጽ
– ደብረጽዮን – 2 ድምጽ

ያገኙ ሲሆን ከብአዴን አቶ ደመቀ መኮንን ባለመወዳደር ለኦህዴድ አቫንስ ሰጥቶ ምክትል ጉልትነቱን አስጠብቋል።
ምርጫውን ተከቶሎ የትግራይና የህወሃት ደጋፊዎች በጣም የተደናገጡ ይመስላል
አያሌ መንበር ዳንኤል ብርሃኔ የሚባል ቀንደኛ የህወሃት ፕሮፖጋንዲስት በፌስ ቡክ ገጹ ምርጫንው አስመልክቶ የተናገረውን የሚከተለውን ጽፏል።
ምንጭ – Leaked News አፈትላኪ ዜናዎች

*****************

እኛን አይሞቀንም አይበርደንም ቻሉት!!! ትግሬዎች ግን እያለቃቀሱ ነው።
እንዲህ ይላሉ፦ *ደብረጽዮንን 2 ሰው ብቻ ስለመረጠው የተሰጠ አስተያየት ነው)
ዳንኤል ብርሃኔ በትግርኛ የጻፈው እንዲህ ይላል፡-
“ለሁላችሁም ትግሬዎች ወንድሞቼ
በዛሬው ዜና በተወሰነ መልኩ ግራ የገባችሁ ትመስላላችሁ። አሁን በቂ መረጃ የለኝም። ሆኖም ግን ለግዜው የሚያስፈራ ነገር የለም።በቀጣይ ግዜዎች የሚፈጠሩ ሁኔታዎች ደግሞ እናያለን። ከዚህ ግን ትልቅ ትምህርት ልንወስድ ይገባል። በውጭ አገር የምትኖሩ ባለሃብትና ምሁራን ትግሬዎች አሁን ካለው የቤተሰብ ስብስብ የሆነ ስርዓት ወጥታችሁ የራሳችሁ የሆነ ድርጅትና እንቅስቃሴ መፍጠር እንደሚያስፈልግ ማወቅ አለባችሁ። የትግሬዎች መጭው እድል ለአንድ ድርጅት መተው ወንጀል ነው።”

ምንጭ – ወልቃይት

የሴት ቀን የወንድ ዓለም (በመስከረም አበራ)

አላማችን ወደ ምዕራብ ጋደል ብላ  እንደምትሽከረከር ከአንደኛ ደረጃ ትምህርቴ ሰምቻለሁ፡፡ አድጌ የአለምን ማህበራዊ መስተጋብር መመርመር ስጀምር ደግሞ  ማጋደሏ ወደ ወንዴ ፆታ እንጅ የአንደኛ ደረጃ መምህሬ እንደነገሩኝ  ወደ ምዕራብ እንዳልሆነ በየቀኑ፣ በየሠዓቱ፣ በየሰበቡ እገነዘባለሁ፡፡ ማጋደሉ ሲጀመር ወንድነት የመደመጥ ሴትነት የመታየት መንስኤ ሆኖ ተቀምጧል፡፡ በሌላ አባባል ሴቷ ልታሻሽለው በማትችለው፣ወዳ ፈቅዳ  ባልሆነችው ገፅታዋ ስትተረጎም ወንዱ ጥሮ ግሮ ሊያሻሽለው በሚችለው የአእምሮው ይዘት፣የኪሱ ክብደት  ይመዘናል፡፡በዚህ የተነሳ ሴት ወደ ውበቷ ወንድ ወደ እውቀቱ ይተጋሉ፡፡ሴቷ እጅግም የማታሻሽለውን ገፅታዋን የተሻለ ለማድረግ ስትለፋ፣ በእዛው ላይ ቀልቧን ስትጥል ቁምነገሩ ያልፋታል፤ከእውቀት ማዕድ ትጎድላለች፡፡ሆኖም በመኳኳሏ ትዘለፋለች ትምህርት የማይዘልቃት በመሆኗም ትብጠለጠላለች፡፡በመልኳ ሲመዝናት የኖረው ራሱ ማህበረሰብ መልኳን ለአይኑ እንዲመች ለማድረግ በመልፋቷ መልሶ ይወቅሳታል፤ከሊፒስቲክ እና ቻፕስቲክ በቀር ዓለም የሌላት ድርጎ ሚዛኗን ያቀለዋል፡፡

እድል ቀንቷት ራመድ ካለ ቤተሰብ ተፈጥራ ማህበረሰቡ ከመደበላት የመታየት እጣ ፋንታ አፈንግጣ እውቀትን ከሻተች፣እሱም የተሳካላት እንደሆነም መሰናክል አያጣትም፡፡ከመሰናክሎቿ አንዱ ይካድ ዘንድ የማይቻለውን ስኬቷን አሳንሶ ማየት፣እውቅና አለመስጠት ነው፡፡ ሰለጠንኩ በሚለው ዓለም ጭምር ሴት የዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰሮች ከወንድ ጓዶቻቸው እኩል እየሰሩ እኩል የማይከፈልበት ሃገር እስከዛሬ አለ፡፡ የፊውዳሉ ስርዓት ከዓለማችን ሲወገድ ሁሉም የሰው ልጆች መሪዎቻቸውን የመምረጥ መብት ይኑራቸው ሲባል የዚህን መብት እፍታ ያጣጣሙት ወንዶች ነበሩ፡፡ሴቶች ከወንድ እኩል መሪዎቻቸውን ለመምረጥ ሌላ ሴታዊ ትግል ማድረግ ነበረባቸው፡፡ በዚህ በኩል ሃገሬ ኢትዮጵያ አትታማም- ሴትን ምርጫ እንዳትመርጥ የሚከለክል ህግ አልነበረምና! በመንግስት ፔሮልም የሴት እና የወንድ ደሞዝ ብፌ በታሪክ አልተመዘገብ፡፡

ሆኖም በግል አሰሪዎች ዘንድ እንዲህ አይነት የሴት ሰራተኛን ክፍያ የማሳነስ አካሄድ የለም ማለት አይደለም፡፡ በደንብ አለ! ሴቶችን በአምስት ብርም ሆነ በአስር ብር አሳንሶ መክፈል የሚጎዳው ኪስን ሳይሆን አእምሮን ነው፡፡ በተግባር እንደማታንሰው ልቦናው እያወቀ፣የምታበረክተውም ከወንድ ቅጥሮቹ ያነሰ እንዳልሆነ ልቦናው እየነገረው የሴቷን ክፍያ በሽራፊ ሳንቲም አሳንሶ እሱና የጾታ መሰሎቹ እንደሚበልጧት ምስክር ሊያደርግ የሚሞክር አሰሪ ራሴ ገጥሞኝ አይቻለሁ፡፡ ይህ ለምን ይሆናል ብየ ሙግት መግጠሜ አልቀረም፤ ማን ነገሬ ቢለኝ! ጭራሽ በሰው በምጠላው ገንዘብ ወዳድነት ተከስሼ ቁጭ ….! እንዲህ ያለው የድንጋይ ዘመን አስተሳሰብ ያለው ሰው የአደባባይ ስሙ “የሰብዐዊ መብት ተሟጋች” ሆኖ ስሰማ ከሳቄ ጋር ያታግለኛል!

ሌላው ሴቶችን የማሳነሻ ዘዴ ለስራቸው በከፊል ወይም በሙሉ እውቅናን መንፈግ ነው፡፡ ይህ እንደ ጠለፋ እና አስገድዶ መድፈር የህግ አንቀፅ ጠቅሰውለት  በወንጄል የማይከሱት ወንዳወንዱ አለም የሴቶችን ችሎታ የሚያዳፍንበት ረቂቅ ልማድ ነው፡፡ ይህን የሚያደርጉት ወንዶች ብቻ አይደሉም ሴቶችም ጭምር እንጅ! እንዴውም ሴት ለሴት ያለውን ችግር ቢፅፉትም የሚያልቅ አይመስለኝ፡፡ ወንዶች ሁሉ የሴት ሥራ ያዳፍናሉ ማለትም አይደለም፡፡ ስልጣኔ ከፀጉራቸው እና ከልብስ ጫማቸው አልፎ ልቦናቸውንም የጎበኘው፣ በጥልቅ ያነበቡ፣ ከመጠምጠም እውቀት ያስቀደሙ፣ከማወቃቸው የተነሳ ራመድ ያሉቱ ወንዶችም ሆኑ ሴቶች ለጥሩ ስራ ሁሉ እውቅና ይሰጣሉ፡፡የሰራችው ሴት ስትሆን ደግሞ ስንቱን መሰናክል አልፋ እዚህ እንደ ደረሰች ያውቃሉና ለስራው ያላቸው ክብር ይጨምር ይሆናል እንጅ አይቀንስም፡፡ እንዲህ ያሉ በርካታ  የሃገሬ ሰዎች እንዳሉ በጣም አውቃለሁ፡፡ እነዚህ ያረጄውን አስተሳሰብ ለማሸነፍ የሞራል ስንቆችም ጭምር ናቸው፡፡

ወደ አዳፋኞቹ ስንመጣ ያልሰለጠነው ጭንቅላታቸው ከሴት የማይጠብቀውን  ስኬት ሴት ልጅ ስታስመዘግብ ካዩ የሚያዩዋትን እሷን ትተው ከጀርባዋ ለስራው ባለቤት የሚሆን ስውር ወንድ ይፈልጋሉ – እከሌ ሰርቶላት ነው፣ እንቶኔ አግዟት ነው፣ እንትና አስገብቷት ነው ሲሉ የወንድ ሞግዚትነት ያማትራሉ፡፡ ግፋ ሲልም በግልፅ እንደማትችል ይነገራታል፡፡ በዚህ አንፃር በግሌ የገጠመኝን ሁሉ ባነሳ  ወርዶ ያወርደኛልና አንዱን ብቻ እንደማሳያ ላንሳ፡፡ ከሶስት አመት በፊት ስልኬ የማላውቀውን ሰው ስልክ ቁጥር እያመላከተኝ  ሲያቃጭል አፈፍ አድርጌ “አቤት” ስል እኔ ወደምኖርበት ከተማ ከጓደኞቹ ጋር መምጣቱን እና ሊያገኙኝ እንደሚፈልጉ አንድ የወንድ ድምፅ ሲነግረኝ “ስልኬን ከየት …” ብየ ሳልጨርስ “ስልክሽን የሰጠን እንትና አጠገባችን ደውሎልሽ ነበር ረሳሽ?” ሲለኝ “እሽ ይቅርታ! አስታዎስኩ በቃ ነገ ይሻላል” ብየ በማግስቱ አገኘሁዋቸው፡፡ ስለሃገራችን ፖለቲካ አውርተን ፣አንዳንዴ የምጫጭራቸውን ነገሮችም እንደሚያነቡ ነግረውኝ፣በርቺ ግን ተጠንቀቂ የሚል የበጎ ሰው ምክር ሰጥተውኝ ተለያየን፡፡

ከአንድ ሁለት አመት በኋላ ከመሃላቸው አንዱን በሆነ አጋጣሚ አግኝቸው ስንጨዋወት እኔ አምደኛ ሆኜ ከምፅፍበት መፅሄት ውስጥ የሚጽፉ ሰዎች እየጠራልኝ የምንስማማባቸውን አብረን ስናደንቅ በማልስማማባቸው ልዩነቴን እየገለፅኩ ስንጫወት ቆየንና በስተመጨረሻ የሁሉንም አምደኞች ፅሁፍ ሲያነብ የኔን ፅሁፍ ነገሬ ብሎ ተመልክቶት እንደማያውቅ ነገረኝ፡፡ እኔም “እኔኮ የምፅፈው እንደ አንተ መርጠው ለማያነቡ፣ ጊዜ ለተረፋቸው አሰሱንም ገሰሱንም ለማያልፉ ነው፡፡አንተማ መቼ አዳርሶህ የእኔን ዝባዝንኬ ታነባለህ” ብየ መከፋቴን ለማየት ፊቴ ላይ የሚሯሯጡ አይኖቹን ደስታ ነፈግኳቸው፡፡ ነገሬ ቀልድ እንዳልሆነ ሁለታችንም ብናውቅም ቀልድ አስመስለን ሳቅንበት እና ወደ ሌላ ጨዋታ አለፍን፡፡ በጨዋታ መሃል “ባለፈው ሳምንት የፃፍሽው ፅሁፍ ግን ሴት የፃፈው አይመስልም” ሲል መልሶ ወደማዳፈን ስራው ገባ:: አሁንስ በዛ ! “ፅሁፌን አንብበህ እንደማታውቅ ነግረኽኝ ነበር፤ነው ያነበበ ነገረህ?” ብየ በነገር ወጋ አደረኩትና “ሴት የፃፈው መልኩ ምን አይነት ነው?!” አልኩት ንቀቴን መደበቅ እያቃተኝ፡፡ እሱ ድንግጥ እኔ ፈርጠም …. ! ሌላ ረዥም ሳቅ ! “አንች አትቻይም ከሚያዋሩሽ ፅሁፍሽን ማንበብ ይሻላል” ሲለኝ፤ የአፉን ሳይጨርስ “አዎ ሲያሳንሱኝ አልወድም!” አልኩኝ ሳቄን አባርሬ እውነተኛ ስሜቴን እየገለፅኩ፡፡በዚሁ ተለያየን፤ከዛ በኋላ ተገናኝተን አናውቅም፤ ወደፊትም የምንገናኝ አይመስለኝም በኔ በኩል፡፡

ይህ ወዳጄ እንዲህ የሚቸገረው በግሉ ክፉ ሰው ስለሆነ ላይሆን ይችላል፡፡ ይልቅስ እሱ የለመደው የወንድ ቦታ ላይ ሴት የተቀመጠ ስለመሰለው የሆነ “የተዛባ” ነገር ይታየዋል፡፡የተዛባው ነገር እረፍት ነስቶታል፡፡ ይህ ሁሉ የመጣው ደግሞ ከኖርንበት ስርዓት ነው፡፡ የኖርንበት ስርዓት የተገመደው ደግሞ ሴትን ማየት ወንድን መስማት ከመውደድ ነው፡፡ መታየት አለባት ተብላ የምትታሰበዋ ሴት መናገር ከጀመረች መሰማት ያለበትን ወንድ ቦታ ያጣበበች፣ ህግ ያፈረሰች የሚመስለው ብዙ ነው፡፡ በዚህ ምክንያት መፈንቅለ-ፆታ  የተደረገበት ይመስለውና በወንበሩ የተቀመጠች ለመሰለችው ሴት በጎ እይታ አይኖረውም፡፡ በቀላሉ የምትወድቅ አይነት ከሆነች በንቀቱ፣በማሳነሱ እና በማዳፈኑ አጣድፎ ሊጥላት መመኘቱም መሞከሩም አይቀርም፡፡ ይህን ስሜት ያልሰለጠኑ ወንዶች ሁሉ ይጋሩታል፡፡ በነገራችን ላይ ያልሰለጠኑ ወንዶች ማለት ዲግሪ ያልደራረቡ ማለት አይደለም፡፡ ተምረው ያልሰለጠኑ በርካታ ናቸው፡፡ ሳይማሩ የሰለጠኑም እንደዛው፡፡ እና ጉዳዩ የመማር ያለመማር ነገር አይደለም፡፡ ያልሰለጠኑ ወንዶች የሴቶችን ስራ ለማዳፈን ሲተጋገዙ ቢጤዎቻቸው ሴቶችም ያግዟቸዋል እንጅ “ነግ በኔ” ብለው ላለመውደቅ ከምትታገለዋ ሴት ጎን አይቆሙም፡፡ይህ ብዙ ያልተወራለት የሴቶች ፈተና ነው!