ሚስማር ባለው ዱላ እየተገረፈ ጥፍሩን ሳይቀር እየተነቃቀለ በእስር ቤት ስቃይ ላይ የሚገኘው አግባው ሰጠኝ | ሊሰሙት የሚገባው ታሪክ


ሚስማር ባለው ዱላ እየተገረፈ ጥፍሩን ሳይቀር እየተነቃቀለ በእስር ቤት ስቃይ ላይ የሚገኘው አግባው ሰጠኝ | ሊሰሙት የሚገባው ታሪክ | Brana Radio

አርቲስት ተስፋዬ ሳህሉ(አባባ ተስፋዬ) ለዚህ አለም በሞት 94 ዓመታቸው ተለዩ -ነፍስ ይማር!!!!

አርቲስት ተስፋዬ ሳህሉ(አባባ ተስፋዬ)

ጤና ይስጥልኝ ልጆች የዛሬ አበባዎች የነገ ፍሬዎች እንደምን አላችሁ ልጆች አያችሁ ልጆች የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የልጆች ክፍለ ጊዜ ዝግጅት እናንተን ለማስደሰት ልክ በሰአቱ ይገኛል አባባ ደሞ የልጆች ሰአት እንዳያልፍባቸው በሩጫ ዲ ዲ ዲ ከተፍ እናንተ ደግሞ ቆማችኃል ይሄ በጣም ጥሩ ነው ልጆች አንድ አባት ሲመጣ በአክብሮት መነሳት አስፈላጊ ነው 
***
ደህና ሁኑ ልጆች! …
ደህና ሁኑ ልጆች!
ደህና ሁኑ ልጆች!

ነፍስ ይማር

Tiss Abay Genji

ትናንሾቹን ዓሳዎች እኛ እንይዛቸዋለን፤ ትላልቆቹ እርስ በርስ ይበላላሉ

አንድ የሩሲያ ተረት እንዲህ ይላል፡-
ባልና ሚስት ዓሳ ሊያጠምዱ ወደ አንድ ሀይቅ ይወርዳሉ፡፡ ገና መንገድ ሳሉ፤
ሚስት፤
“የሚያዙት ዓሳዎች ግማሾቹ ለልጆቻችን ምግብ ይሆናሉ፡፡ ግማሾቹን ደግሞ ወደ ገበያ ወስደን እንሸጣቸውና፤ ሌሎቹ ኑሯችንን ማሟያ ገንዘብ ያመጣሉ፡፡” ትላለች
ባል፤
“እስቲ መጀመሪያ ዓሳዎቹ ይገኙ፡፡ ከዚያ ደግሞ መረባችን የሚይዘውን ብዛት እንይ፡፡ የዛሬ ዓሳዎች እኮ እንደ ድሮዎቹ ዓሳዎች በማንኛውም መረብ ውስጥ ተንደርድረው ጥልቅ አይሉም”
ሚስት፤
“ዓሳ ዓሳ ነው፤ ብርብራ ካየ ዘሎ ጥልቅ ማለቱ አይቀሬ ነው”
ባል፤
“አይምሰልሽ፤ እኛ ያለን የዱሮ መረብ ነው፡፡ ዓሳዎቹ የአሁን ጊዜ ናቸው፡፡ የዱሮ መረብ በቶሎ ይበጣጠሳል፡፡ ወይ መረቡ በአዲስ ክር መሰራት አለበት፤ አሊያም ሙሉ በሙሉ ተለውጦ አዲስ መሆን አለበት፡፡ እንጂ የዛሬን ዓሶች ችሎ አፍኖ አያስቀምጥም”
ሚስት፤
“ግዴለህም ባሌ፤ አታስብ፡፡ ሀይቁም ያው የዱሮው የምናውቀው ሀይቅ ነው፡፡ ዓሳዎቹም የዱሮዎቹ ዓሳዎች ናቸው፡፡ ድንገት ተነስተው ብልጥ ዓሳዎች ሊሆኑ አይችሉም፡፡ እኛ ተጃጅለን፤ ቅልጥፍና አንሶን የማምለጥ እድል ካልሰጠናቸው ባንድ አፍታ እጃችን እናስገባቸዋለን”
ባል፤
“እስቲ ይቅናን! ወዳጄ”
ተያይዘው እሀይቁ ዳርቻ ደረሱ፡፡ መረቡን ዘረጉት፡፡ የተያዙት ግን በጣም ደቃቃ ደቃቃ ዓሳዎች ብቻ ናቸው፡፡
ሚስት፤ በጣም ገረማትና፤
“ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል፤ መረቡ ትናንሽ ዓሳዎችን ብቻ እየመረጠ ነው እንዴ የሚይዘው?” ስትል ባሏን ጠየቀችው፡፡
ባሏም፤
“ይሄውልሽ ጊዜው እንደዚህ ሆኗል፡፡ ትናንሾችን ዓሳዎች እኛ እንይዛቸዋለን፤ትላልቆቹ እርስ በርስ ይበላላሉ!!”
*       *      *
ዘመኑ እንደዚህ ነው! ትላልቆቹ ሌቦች አይነኩም፡፡ ትናንሾቹ ብቻ ይጠመዳሉ፡፡ ባለ ከፍተኛ ንግድና ሀብት ባለቤቶች የሚነካቸው የለም፡፡ ትናንሾቹ ጉልት ቸርቻሪዎች፣ ከገቢ ገማች እስከ ወንጀል መርማሪ ይፈራረቅባቸዋል፡፡ ይህንን ዕውነታ መለወጥ የትራንስፎርሜሽን ያህል ከባድ ነው፡፡ ምነው ቢሉ፣ ከባድ ከባድ፣ ንክኪ በሥሩ አለ፡፡ አብ ሲነካ ወልድ ይነካ ነው!
ስለሆነም የላይኞቹ ክፉኛ ይጮሀሉ!! የታችኞቹ ወንጀሉ የዓለም መጨረሻ እንደሆነ አድርገው ያወራሉ፤ ይጮሃሉ! ባለ ፎቆቹ፣ ባለ ቪላዎቹ፤ ባለ ብዙ ኤከር መሬት ባለቤቶቹ፤ ንፁሀን ሆነው ቁጭ ይላሉ! በየሸንጎውም ላይ ጨዋዎቹ እነዚህ ባለፀጎች ይሆኑና የክብር እንግዶች ተብለው ክብር ትሪቡን ውስጥ ይቀመጣሉ፡፡ አዳዲስ ተቋም ሲመረቅ መድረኩን ይሞላሉ፤ ግንባር ግንባር ቦታውን ያጣብባሉ! በደህና ጊዜ የአባትህ ቤት ሲዘረፍ አብረህ ዝረፍ እያሉ፣ የአንበሳውን ድርሻ ሲቀራመቱ የነበሩ ናቸው፡፡
በሌላ ወገን፤ ዝቅተኛው መደብ፣ ሱቁ ሲመዘበር፣ ያልሆነ ዋጋ ሲተመንበት፣ ሰሚ ያጣ ጩኸት ሲጮህና የአገር ያለህ፣ የመንግሥት ያለህ ሲል፤ “ስህተት ያለ ነገር ነው፤ ለቅሬታ ሰሚ አመልክት እንጂ ምን ታካብዳለህ” ይሆናል የምላሹ ዘይቤ! ሱቃቸውን ዘግተው የጠፉ፣ ዕቃቸውን ያሸሹ፣ ንብረት አናስገምትም ያሉት ዕውን ከግንዛቤ ማነስ ነውን? ግንዛቤ እንዲጨብጡ ተደርጎስ፣ ወደ ሰላማዊ ኑሮአቸው ተመልሰዋል ማለት ዕውን ነባራዊው ሀቅ ነውን? መሬትና ሰማይን ያነካካ ገመታ፣ የምስኪኑ ችርቻሮ ነጋዴ ደስታ ሊሆን ይችላልን? ግልፁ ጨዋታ ሌባው በወርቅ አልጋ፣ በእርግብ ላባ ላይ፣ ከዝሆን ጥርስ በተሰራ ፎቅ ውስጥ መኖሩ ነው! ማን ይንካው? የማይታረቁ ግጭቶች ተፋጠው ይገኛሉ!! የማይታረቁ ግጭቶችን ለመፍታት ቢያንስ ገጣሚና ፀሐፌ – ተውኔት መንግሥቱ ለማ፤ በባ‘ለ ካባና በባለዳባ’ ተውኔታቸው ውስጥ፡-
“ቀማኛን መቀማት፣ ከሌባ መስረቅ ……….. (‘ቅ’ ይጠብቃል)
ከማቅለል ከሆነ፣ የድሆችን ጭንቅ ………….. ( ‘ቅ’ ይጠብቃል)
በእኔ ቤት፣ ፅድቅ ነው፣ አንድ ሰው ይሙት …………(‘ሙት’ ይጠብቃል)
አንድ መቶ ሺ ሰው፣ ኪኖር በምፅዋት!!” …..…………(‘ዋት’ ይጠብቃል)
ያሉትን ማስታወስ ግድ ይሆናል!!
“እገሌ የእኛ ወገን ነው አይነካም”፤ “እገሌ የሌላ ወገን ነው፤ በለው!”፤ “እገሌ የማንም አይደለም ጊዜውን ይጠብቅ” …. “እነ እገሌን ተውዋቸው የኛ ናቸው” … “እነገሌን ግፏቸው ጠላት ናቸው” … ዓይነት አካሄድ፤ ቢያንስ ‹ከልጅ ልጅ ቢለዩ ዓመትም አይቆዩ› አለማወቅ ይሆናልና ልብና ልቦና ይስጠን!!
የሀገራችን አንድ ፈታኝ የሆነ ችግር፣ “ህዝቡ አያውቅም” የሚለው መላምታዊ ድንቁርና ነው፡፡ የነቃው፣ ህዝቡን በትግሉ ሲያግዝ የኖረው፣ በቀውጢው ሰዓት ታጋዮችን ከክልል ክልል ሲያሳልፍ የከረመው፤ ትልቅ አድናቆት ሲቸረው የኖረ ህዝብ፤ ድንገት ድንቁር ሊል ፈፅሞ አይችልም፡፡ እንደ ሁልጊዜው የግምት ስህተት አለ!! “ይሄን ስናሰላ፣ እንዲህ እንዲህ ያለ ችግር ነበረብን” የምንለውን እንኳ ዛሬ ስለተውነው፤ ከስህተት መታረም የሚለው ቁም – ነገር ጨርሶ ጠፍቷል፡፡ ከዚህ ይሰውረን!!
ትናንሾቹን ዓሳዎች አሳዶ የሚበላቸው አይጠፋም – አቅም የላቸውምና! ትላልቆቹ ግን እርስ በርስ እስኪበላሉ መጠበቅ ነው! ከዚህም ያውጣን!!

ምንጭ – አዲስ አድማስ

ግብር በአምባገነን አገዛዝ – ታደሰ ብሩ ከርሴሞ

ስለ አምባገነን አገዛዝና ግብር ሲነሳ መጥቀስ የምወደው የእውቁ ኢኮኖክስ ማንኩር ኦልሰን Dictatorship, Democracy, and Development ነው። ከዚህ ጽሁፍ በዛ አድርጌ ልጥቀስ።
ዘላን ወንበዴዎች /roving bandits/ ነጥቀው ይሮጣሉ፤ መቼ እንደሚመለሱ አይታወቅም። እነዚህ ወንበዴዎች ነጥቀው በሮጡ ቁጥር የማኅበረሰቡ ሀብት የማፍራት ፍላጎት ስለሚዳከም በሚቀጥለው ዙር የሚዘርፉት ነገር እያነሰባቸው ይመጣል። ቀን ባለፈ መጠን ነጥቆ መሮጥ ራሳቸውን እንደሚጎዳቸው ይገነዘቡና ከተዘዋዋሪ ወንበዴነት ወደ ቋሚ ወንበዴነት /stationary bandit/ ይቀየራሉ። ለንጥቂያቸውም ሥርዓትና ልክ ያበጁለታል፤ ስሙን “ግብር” ይሉታል። ማኅበረሰቡንም፣ ራሳቸውንም ከሌሎች ተዘዋዋሪ ወንበዴዎች ይከላከላሉ። ይህ ሥርዓት ከሥርዓተ አልበኝነት የተሻለ፣ የቅሚያውም መጠንም አስቀድሞ የሚታወቅ ከመሆኑ ጋር ማኅበረሰቡ ለሚከፍለው ተመጣጣኝ ባይሆንም የሚያገኘው ጥቅም (ሰላምና ሌሎችም ማኅበራዊ ምርቶች) ስላሉ ምርት ይጨምራል፣ ዕድገትም ይኖራል።

ይሁን እንጂ አምባገነን ሰፋሪዎች በተደላደሉ መጠን ፍጆታቸው እየናረ መሄዱ ፈጽሞ የማይቀር ነው። ለጦር ሠራዊቱ፣ ለቤተመንግሥቱ፣ ለማሰልጠኛው፣ ለመታሰቢያ ሀውልቶች ግንባታ፣ ለአዳራሾች ግንባታ፣ ለአምባገነኖች፣ ለተከታዮቻቸውና ቤተሰቦቻቸው የክብር ልብሶችና ጌጣጌጦች፣ “ለመጠባበቂያ“፣ ….. የሚያስፈልገው ወጪ በጨመረ ቁጥር ሕዝቡ በግብር አሊያም በሌላ መንገድ እንዲከፍል ስለሚገደድ ሥርዓት በመስፈኑ ምክንያት አንሰራርቶ የነበረው የሥራ ፍላጎት እንደገና ያሽቆለቁላል። የሰፋሪ ወንበዴዎችን የሀብት ማጋበስ፣ ምቾትና እዩልኝ ፍላጎቶችን ማርካት አይቻልም።

==

በማንኩር ኦልሰን ላይ የምጨምረው የለኝም፤ ሁሉንም ብሎታል። ሙሉውን ማንበብ ለምትፈልጉ የመጣጥፉን ጠቋሚ አያይዣለሁ።

ወንበዴዎች ሕዝብን ለማስገበር ሁለት ነገሮች ያስፈልጓቸዋል። አንዱ ጉልበት ነው። ሞኝ ሽፍታ ዘርፎ ይሮጣል፤ ብልጣብልጥ ሽፍታ ደግሞ ቁጭ ብሎ መዝረፍ ያምረዋል። ብልጣ ብልጥ ሽፍታ ራሱን በመንግሥትነት ሰይሞ ለዘረፋው “የመንግሥት ግብር “ የሚል ስያሜ ሰጥቶ ተዘራፊን አሰልፎ ደረሰኝ እየሰጠ ይዘርፋል።

ቁጭ ብሎ ደረሰኝ እየሰጡ ለመዝረፍ ግን ከጉልበት በተጨማሪ ለዘረፋ ሰበብ የሚሆኑ ማኅበራዊ ምርቶች (public goods) ማምረት ያስፈልጋል። ካድሬዎች ሕዝቡን “ግብር የምትከፍለው ለመንገድ፣ ለጤና አገልግሎት፣ ለትምህርት …” ብለው መቀስቀስ አለባቸው። ግብር ግዴታ መሆኑ ቢታወቅም ምክንያታዊ እንደሆነ ማብራራት መቻል አለባቸው። በአምባገነን ሥርዓት ውስጥ ከተሰበሰበው ግብር ምን ያህሉ ወደ ማኅበራዊ ምርት፤ ምን ያህሉ ደግሞ ወደ ባለሥልጣናቱ ኪስ እንደሄደ የሚጠይቅ የለም። መንገዱም ሆነ ሕንፃው ቢሰራ ለማን፣ ለምን ብሎ የሚሞግት የለም። ሕዝቡ አምፆ እስካላስቀረው ድረስ ደረሰኝ እየተቀበለ ይዘረፋል።

በህወሓት/ኢሕአዴግ አገዛዝ አገራችን የምትገኝበት ሁኔታ ይህ ነው። የህወሓት ሠፋሪ ወንበዴዎች በግብር ስም እያስራቆቱን ነው። ህወሓት የዘረጋው የግብር ሥርዓት ወንበዴው ቁጭ ብሎ ለፍቶ አዳሪውን የሚመጥበት፤ ድሀው ሀብታሙን የሚደጉምበት ነው። እንዲህ እንዳሁኑ አንዳንዴ የሙስና ዜና ሲኖር ነው በግብር የተሰበሰበው ገንዘብ የት እንደተከማቸ በወሬ ወሬ የምንሰማው።

ሌላም ላነሳው የምሻ ጉዳይ አለ: “ግንዛቤ ማስጨበጥ” የሚሉት።

አገራችን ውስጥ የወር ደመወዝ ተከፋይ ምንም ከግብር ማምለጫ ቀዳዳ የሌለው በመሆኑ ከሁሉ በላይ ተበዳይ እንደሆነ ስለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ መጠነኛ እውቀት ያለው ሁሉ የሚያውቀው ሀቅ ነው። የግብር ዕዳን ለማስተካከል ሲባል “ነጋዴ ላይ ግብር መጫን የወር ደመወዝተኛው ኑሮ ያሻሽላል” የሚል “ግንዛቤ ማስጨበጥ” “እኔ ብጎዳም ያንተ ከኔ ይበልጥ መሰቃየት ያስደስተኛል” ዓይነት ሰይጣናዊ አመክኖ ነው። በነጋዴ ላይ የሚጫን ግብር ውሎ አድሮ በሙሉ ወይም በከፊል ወደ ሸቀጦች ዋጋ መተላለፉ አይቀርም። ይህንን ሽግግር የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅም አያስቀረውም። እናም የወር ደመወዝ ተከፋዩ የሚጠቀመው በለፍቶ አዳሪው ላይ የግብር ዕዳ በመጫኑ አይደለም። የወር ደመወዝተኛው የሚጠቀመው በለፍቶ አዳሪው ብቻ ሳይሆን በሱም ላይ የተጫነው የግብር ዕዳ ሲቀንስ ነው።

ላጠቃለው።

ወገኞቼ፤ ለህወሓት/ኢሕአዴግ አገዛዝ ግብር አልከፍልም ማለት ተገቢ ነው። ለአንባገነን ሥርዓት አልገብርም ማለት ከሥነ ምግባር አንፃር ተቀባይነት ያለው የጽድቅ ሥራ ነው። ለህወሓት አንገብርም ማለት የሚኖርባቸው ነጋዴዎች ብቻ ሳይሆኑ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው።

“ለኢህአዴግ ነገሮች እየከበዱ ነው” – ኦባንግ

“እነሱ (ምዕራባውያን) ገፍተው የገደል አፋፍ ላይ ቢያስቀምጡህ እንኳ ክፉ ቃል አይጠቀሙም። በተግባር ግን ያሳያሉ። በጀት ሲቀንሱ ምልክት ነው። የጦር ካምፓቸውን ሲያነሱ ምልክት ነው። ፊት ሲነሱ ምልክት ነው። ከሶማሌ እንዳትወጣ እያሉ ሲለምኑና ዶላር ሲያፈሱ ኖረው የራስህ ጉዳይ ካሉህ ትልቅ ምልክት ነው። መከርንህ፣ ነገርንህ አሁን የራስህ ጉዳይ ነው፣ ለራስህ እወቅ፣ ሁሉም ነገር ባንተ እጅ ነው ሲሉህ ምልክት ነው። ከዚህም በላይ አሁን ኢትዮጵያ እየሄደች ያለችበት መንገድ ወዴት እንደሚያደርሳት ጠንቅቀው ያውቃሉ። ወያኔዎቹ በዘላቂነት ምስራቅ አፍሪቃ እና አካባቢው ላይ ያላቸውን ፍላጎት የማስጠበቅ አቅማቸው መዛሉን ያውቃሉ። ከውስጥ የተነሳው ችግርና አገዛዙ የገባበት የቀውስ ገደል መጨረሻ ከማንም በላይ ይታያቸዋል። ተወደደም ተጠላም አሁን ነገሮች እየከበዱ ነው። እነሱ እንዳሉት ምርጫው በባለስልጣኖቹ እጅ ላይ ነው።” ኦባንግ ሜቶ ሰሞኑን የህወሃት/ኢህአዴግን የሰብዓዊ መብቶች ይዞታና አጠቃላይ አስተዳደርን የሚወቅስ የህግ ረቂቅ በዩናይትድ ስቴትስ የሕግ መምሪያ የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ ፊት ቀርቦ በሙሉ ስምምነት ክጸደቀ በኋላ ከዛጎል ጋር ካደረጉት ቃለምልልስ የተቀነጨበ። ሙሉው ቃለምልልስ ከዚህ በታች ቀርቧል።

ዛጎል፡- ተደስተሃል?

ኦባንግ ፡- በምኑ? ለምን? ምን አዲስ ነገር አለና?

ዛጎል፡- ኢህአዴግን የሰብዓዊ መብቶች ይዞታና አጠቃላይ አስተዳድሩን የሚወቅስ የህግ ረቂቅ ዛሬ በመጽደቁ፤

ኦባንግ፡- ጥሩ እርምጃ ነው። ግን አስቀድሜ ስለማውቀው ብዙም አልገረመኝም። አሜሪካኖቹ እንዲህ ወዳለው ድምዳሜ እንደሚመጡ ይገባኝ ነበር። እዚህ መድረሱ ትልቅ ጉዳይ ቢሆንም ብዙ ርቀት መሄድ ያስፈልጋል። ገና ብዙ ይቀረናል።

ዛጎል፡- ከኢህአዴግ ወገን ያሉ ወሳኔው አያሳስብም እያሉ ነው። ትስማማለህ ማለት ነው?

ኦባንግ፡- ምን ማለትህ ነው?

ዛጎል፡- ገና ብዙ መንገድ ይቀረናል እያልክ መሰለኝ፤

ኦባንግ፡- አልተግባባንም። በየትኛውም መስፈርት ይህን የህግ ረቂቅ ቀላል አድርጎ የሚወስድ አካል ካለ ከመገረም ውጪ የምለው ነገር የለም። ግን ሥራው አልተጠናቀቀም እና ገና ብዙ ይቀራናል ለማለት ነው። ሥራው አላለቀም።

ዛጎል፡- አስቀድሜ አውቀው ነበር አለከኝ? እንዴት? አንተ ማን ነህ?

ኦባንግ፡- እኔ ኦባንግ ነኝ። (ይስቃል …) ሥራው ሲሰራ ነበርኩ ለማለት ነው። ረቂቁ ከመቅረቡ ቀናት በፊት ስለ ጉዳዩ በቂ እውቀት ነበረኝ። አብረንም …. ብቻ ይህ ጠቃሚ አይመስለኝም። ሌሎች ጉዳዮች ላይ እንነጋገር።

ዛጎል፡- ታዲያ አስቀድመህ ለምን አልገለጽከውም?

ኦባንግ፡- ማውራቱ ምን ይጠቅማል? ቀጣዩ ሥራ ላይ ትኩረት ማድረጉ ነው የሚጠቅመው።

ዛጎል፡- እና ቀጣዩ ጉዳይ ምንድን ነው?

ኦባንግ፡- በተቀናቃኝ ፓርቲዎች ዙሪያ ያለው ግብግብ ሊቆም ይገባል። የጋር ግብና ራዕይ አስፈላጊ ነው።

ዛጎል፡- አንግባባም፤ እንደየ እምነታችን እንጓዛለን ካሉስ?

ኦባንግ፡- አዩት እኮ!! እንደዚህ አይነቱ ሩጫ የትም አላደረሰም። በሄየድንበት ቦታ ሁሉ የምንጠየቀው አገራዊ ራዕይና ጥልቀት የላችሁም የሚለውን ወሳኝ ጥያቄ ነው።

ዛጎል፡- የጋራ ዓላማና ራዕይ ሊይዙ ያልቻሉበትን ምክንያት ታውቀዋለህ? ወይም ደርስህበታል?

ኦባንግ፡- ምርምር የሚያስፈለገው ጉዳይ አይመስለኝም። አገርን፣ ሕዝብን፣ መጪ ትውልድን የሚያስቡ አካላት የጋራ ራዕይ ለመቅረጽ አይቸገሩም። ይህንን ለማድረግ አገላጋይና ሸምጋይ አያስፈልግም። ስለ አገር፣ ስለ ሕዝብ፣ ስለ መጪ ትውልድ በቃል ሳይሆን በተግባር የማያስቡ ስለ ምን እንደሚያስቡ መናገሩ አሰስፈላጊ አይመስለኝም፤ ግልጽ ነው። ስለዚህ በመከፋፈል፤ በመበጣጠስ የትም አይደረስም። ስትበጣጠስ ታንሳለህ። ስትበጣጠስ ሳታስበው ሳይከፈልህ የምትታገለውን ድርጅት እያገዝክ ነው ማለት ነው። በግልጽ ቋንቋ ለኢህአዴግ እና ለወያኔ ትሠራለህ፣ ታገለግላለህ፣ ትገዛለህ፣ ትኖራለህ … ማለት ነው። በዛው ነጻ ሰው የመሆን እድል ሳይገጥምህ ታልፋለህ ማለት ነው።

ዛጎል፡- ኢህአዴግ መንግሥት ነው። ለምን ወያኔ ትላለህ? በመንግሥት ደረጃ እያነሳን ብንነጋገር፤

ኦባንግ፡- ችግር የለብኝም። ግን ስማቸው እኮ ነው። እነሱ እንዲጠሩበት የሚወዱትን ስም እኔ ምን አግብቶኝ እቀይረዋለሁ? ያውም አገር የሚገዙበት ስማቸው እኮ ነው፤ ተገንጣይ ቡድን አይደል የሚባለው፤ … ለማንኛውም እነሱ ሲቀየሩት ያኔ እኔም በአዲሱ ስማቸው እጠራቸዋለሁ። ብዙ ጊዜ በዚህ ጉዳይ የሚነሳ ክርክር ይገርመኛል። እኔ ኦባንግ ነኝ ። ሌላ ሰው ተነስቶ እንዴት ኦባንግ ትለዋልህ ቢልህ መልስህ ምንድን ነው? የሰውየውን ጤንነት አትጠራጠርም? አንድን አካል በስሙ መጥራት ግድ ነው። ክብርም ነው። አንተ መንግሥት ነው ትላለህ፤ እነሱ አሁን አገር እየገዙ ያሉት በውሸት ስም አይደል? ወይ የንግሥና ስም አይደል! በነገርህ ላይ ይህ የሰብዕና (ፐርሰናሊቲ) ችግር ያመጣል፤ ለምሳሌ መለስ ማነው? መለስ ነው? ወይስ ለገሠ? ስሙ ደግሞ የተቀየረው ሲጠቀምበት ቆይቶ ካደገ በኋላ ነው፤ በልጅነቱ እንኳን አይደለም፤ ስምና ማንነት የተያያዘ ነው፤ ብቻ ተወው ወደ ሌላ ርዕስ ይወስደናል፤

ዛጎል፡- ወደ ተነሳንበት እንመለስ፤ ስለዚህ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ችግራቸው የስልጣን ጥማት ነው እያልክ ነው?

ኦባንግ ፡- ሕዝብን ለመታደግ፣ አገርን ለመታደግ፣ የወደፊቱ ትውልድ ነጻና ተስፋ ያለው እንዲሆን ካሰብክ እንዴት የጋራ ራዕይና ግብ እንዲኖርህ አትስማማም? ተበጣጥሶ የመደራጀቱ ጣጣ ያው ለስልጣን ያለ ጉጉት እንጂ አገርና ህዝብን የሚጠቅም አይደለም።

ዛጎል፡- በብሔር መደራጀት ግድ ነው? አሁን በብሔራዊ ደረጃ ታግሎ ውጤት ማምጣት አይቻልም የሚሉ አሉ፤ እነዚህ ክፍሎች የትግሉ ደረጃ በብሔር ተቧድኖ ወደ መደራጀት አድጓል ባይ ናቸው፤

ኦባንግ፡- ውጤቱ መጨረሻ ላይ ምን ይሆናል? ይህንን ጥያቄ ይመልሱታል? ለምንስ እሳካሁን ውጤት ሳያመጡ ቀሩ? አሸንፈው በተራቸው ሌላውን ለመጫን ነው የሚመኙት? እኔ የምመራው ድርጅት “ሁላችንም ነጻ ካልወጣን ማንም ብቻውን ነጻ አይወጣም” የሚለው ያለምክንያት አይደለም፤ የተበደሉት ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ናቸው። የተገፉትና የሚሰቃዩት ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ናቸው። ታዲያ ሁሉም የሚበደሉ ከሆነ ሁሉም ለምን ነጻ እንዲወጡ አይደረግም። በኢትዮጵያ ማዕቀፍ ውስጥ ይህንን ማድረግ የሚቀል ሆኖ ሳለ ወደፊት የማይቀረፍ ችግር ለመትከል መምረጥ ለኔ አግባብ ሆኖ አይታየኝም። ህዝብንም ይጎዳል። የህዝብም ፍላጎት አይመስለኝም።

ዛጎል፡- የምታነሳው ሃሳብ በጣም ቀላልና ግልጽ ነው፤

ኦባንግ፡- ቀና ስትሆን ቀላልና ግልጽ ነገር ታስባለህ። በቀናነት መንገድ ውስጥ ውስብስብ ነገር የለም። እኔ ይህን የምናገረው ተመራማሪ ሆኜ አይደለም። ሁልጊዜ ነገሮችን በቀናነት የመመልከት እምነትና ፍላጎት ስላለኝ ብቻ ነው። የክፋት ፖለቲካ ለማራመድ የሚወስን ልብና እምነት ቢኖረኝ በአኙዋክ ወንድሞቼ ላይ ዕልቂት በተፈጸመ ማግስት አውሬ መሆን እችል ነበር። ግን የትም አያደርስም። ሁሉም ኢትዮጵያዊ ወግኖቼ ነጻ የሚወጡበትን መንገድ ማሰቡ ነው የቀለለኝ። ብዙ ማለት ይቻላል…

ዛጎል፡- ታዲያ ለማቀራረብ ሞክረሃል? ወይስ ታስባለህ? ወይስ …

ኦባንግ፡- ሞክሬ ነበር የሚሰማ አልተገኘም። ካሁን በኋላ አልሞክረውም። እኔ በፕሮፓጋንዳ አላምንም። ለመተማመን ቅድሚያ እርስ በርስ እንነጋገር ብዬ ጥሪ አስተላልፌ አይቸዋለሁ። እኔ የማምነው በመነጋገር ነው። ቅድሚያ አንዱ ከሌላው ጋር ሩቅ ሳይሄድ መነጋገር ሲጀምር ነገሩ ሁሉ ያለ ፕሮፓጋንዳ ይሆናል። አሁን ወያኔዎቹ ብቻቸውን ቲቪ፣ ራዲዮ፣ ጋዜጣ … ሁሉን ይዘው የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ያደርጋሉ። በተግባር የሚታየው ግን ብቻቸውን ተጠቃሚ ሲሆኑ፣ ራሳቸው ብቻ ሲበለጽጉ፣ ሌላውን ሲገድሉ፣ ሲያሳድዱና ሲያፈናቅሉ፣ ሲያስሩ፣ … ወዘተ ነው። ተመሳሳይ ነገር መድገም አልፈልግም። ሊሆንም አይገባም። ሰው ሁሉም ክቡር። ሁሉም ክቡር ከሆኑ በታማኝነትና በከበረ ስብዕና ሁሉም ነጻ እንዲወጡ ለማሰብ አንዱ ለሌላው ቀሰቃሽና ሰባኪ ሊሆን አይገባም። ተለይቶ ነጻ የሚወጣና ተለይቶ ቀንበር የሚጫንበት ሰው ሊኖር አይገባም። የሁሉንም ጥያቄ በኢትዮጵያ ማዕቀፍ ውስጥ መመለስ ይቻላል። ይህ ሲሆን ማየት ከስልጣንም፣ ከግል ዝናም፣ ከሁሉም ዓይነት ፍላጎት በላይ ነው። ይህ ሲሆንና ሕዝብ ሲከበር፣ ቀናነት ሲታከልበት የግል ጉዳዮች፣ ተከታይ ለማግኘት የሚደረግ ሩጫ፤ የጎሳና የዘር መቧደን ይቀራል። ለምን? ምክንያቱም ከትግሉም ሆነ ከድሉ ህዝብ የሚያገኘውን እፎይታ በማየት ከእርካታ የዘለለ የምትፈልገው ነገር የለምና፤

ዛጎል፡- አሜሪካና ኢህአዴግ አሁን በመልካም ግንኙነት ላይ ያሉ ይመስለሃል?

ኦባንግ፡- በአጭሩ አይመስለኝም።

ዛጎል፡- እንዴት? ሁሌም አሜሪካኖቹ አጋራችን ነው የሚሉት፤

ኦባንግ፡- እነሱ ገፍተው የገደል አፋፍ ላይ ቢያስቀምጡህ እንኳ ክፉ ቃል አይጠቀሙም። በተግባር ግን ያሳያሉ። በጀት ሲቀንሱ ምልክት ነው። የጦር ካምፓቸውን ሲያነሱ ምልክት ነው። ፊት ሲነሱ ምልክት ነው። ከሶማሌ እንዳትወጣ እያሉ ሲለምኑና ዶላር ሲያፈሱ ኖረው የራስህ ጉዳይ ካሉህ ትልቅ ምልክት ነው። መከርንህ፣ ነገርንህ አሁን የራስህ ጉዳይ ነው፣ ለራስህ እወቅ፣ ሁሉም ነገር ባንተ እጅ ነው ሲሉህ ምልክት ነው። ከዚህም በላይ አሁን ኢትዮጵያ እየሄደች ያለችበት መንገድ ወዴት እንደሚያደርሳት ጠንቅቀው ያውቃሉ። ወያኔዎቹ በዘላቂነት ምስራቅ አፍሪቃ እና አካባቢው ላይ ያላቸውን ፍላጎት የማስጠበቅ አቅማቸው መዛሉን ያውቃሉ። ከውስጥ የተነሳው ችግርና አገዛዙ የገባበት የቀውስ ገደል መጨረሻ ከማንም በላይ ይታያቸዋል። ተወደደም ተጠላም አሁን ነገሮች እየከበዱ ነው። እነሱ እንዳሉት ምርጫው በባለስልጣኖቹ እጅ ላይ ነው።

ዛጎል፡- አዲሱ ረቂቅ ህግ የሚጠይቀውን አንቀበልም ቢሉስ?

ኦባንግ፡- አይመስለኝም።

ዛጎል፡- እንደ ቀድሞው ረቂቅ HR 2003 ቢያስገለብጡትስ? ያንን የማድረግ አቅም እንዳላቸው የሚናገሩ አሉ፤

ኦባንግ፡- በዛሬው ሁኔታ፣ በቅርብ እንደማውቀውና በግል እንደማምነው አዲሱን ረቂቅ በሎቢ ማስቀየር የሚቻል አይመስለኝም። ተራ ቀልድ ነው የሚሆነው። የተስማሙት ሁለቱም ፓርቲዎች ናቸው። በኢትዮጵያ ያለው የሰብዓዊ መብት አያያዝና ስርዓቱ የገባበት ውድቀት ከልክ በላይ ሆኗል። በአራቱም ማዕዘናት የሚታየው ሁሉ አያምርም። ወያኔዎቹም ቢሆኑ በራሳቸው ሚዲያ ሆን ብለው ይሁን ሳያውቁ የሚያቀርቡት ዘገባና ዜና ይህንኑ የሚያረጋግጥ ነው። አንዳንድ የመፍትሄ ርምጃ በሚል የሚወሰዱት ሁሉ የመደናበር ምልክት ነው። እናም በዚህ መልኩ የሚቀጥል ነገር አይኖርም።

ዛጎል፡- እና ህጉ በሙሉው ምክርቤት (በኮንግረስ) ቀርቦ ተግባራዊ ይሆናል እያልክ ነው?

ኦባንግ፡- በመጀመሪያ የአድቮኬሲ ስራ የትም አያደርስም ለሚሉ ወገኖች ይህ ትልቅ ትምህርት መሆኑንን መግለጽ እወዳለሁ። ከሌሎች ችግሮች ጋር ተዳምሮ የአድቮኬሲ ስራ ፍሬ አፍርቶ በማየቴ ደስተኛ ነኝ። ጉዳዩ ብዙ የተደከመበት ነው። እንዲሁ ወደዚህ ሃሳብ አልተደረሰም። እናም አሁን ባለው ሁኔታ ህጉ በኮንግረንስ ጸድቆ ተግባራዊ ይሆናል። አስቀድሜ እንዳልኩት አድርጉ የሚባሉትን አናደርግም ካሉ ተፈጻሚ የሚሆን ዓለምዓቀፍ ህግ አለ። ህጉ ኢትዮጵያውያንን በማሰቃየትና በመግደል፣ እንዲሁም የሰብዓዊ መብቶቻቸውን በመርገጥ ተግባር የተሳተፉ ለመሆናቸው የተመዘገቡ የስርዓቱ ባለስልጣኖችና ተባባሪዎች የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር  ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር በመቆራኘት በዓለምአቀፍ ሕግና ደንቦች መሠረት ዕቀባ እንዲያደርግባቸው በረቂቅ ሕጉ ተቀምጧል። በዚህ መነሻ ለአሜሪካ የለውጥ ዕቅድ አሻፈረኝ የሚሉ ከሆነ የአገዛዙ ሹሞችና ቤተሰቦቻቸው ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ ማዕቀብ ይጣልባቸዋል፥ ሃብታቸው እንዳይነቃነቅ ይታገዳል። ሌሎችም ተመሳሳይ ደንቦችና ህጎች ተግባራዊ ይሆኑባቸዋል። ይህ ግድ ነው። ነገሮች ወደ መራራነት እየተቀየሩ ነው ያልኩት በዚህ መነሻ ነው። ይህ እንደሚመጣ አስቀድመው ሊያውቁትና እንመራዋለን የሚሉትን ህዝብ ሊያከብሩት በተገባ ነበር። ይህንን ስል ግን በእኛ በኩል ስራው የሚቀጥል …

ዛጎል፡- ቤተሰቦቻቸው ለምን?

ኦባንግ፡- የወያኔ ባለስልጣናት አገሪቱ ላይ የሚፈጽሙትን ወንጀልና ግፍ ቤተሰቦቻቸው አያውቁም? ለምንስ አይቃወሙም? ለምን ሌላውም ሰው ልክ እንደ እነሱ ክብር እንደሚያስፈልገው በማመን አይከራከሩም? ለምን የሌላው ስቃይ ስቃያቸው አይሆንም? አንድ የባለስልጣን ልጅ በንጹሃን ላይ የሚደርሰውን ግፍ በመመልከት የተቃወመ አለ? ስለዚህ ክሬሙን ብቻ ሳይሆን መከራውንም ሆነ ችግሩን አብሮ መጋራት ግድ ነው። ይህንን ስል ግን ጊዜ አለ። ህዝብ መሃሪ ነው። ህዝብ ይቅር ይላል። ሁልጊዜም እንደምለው እርቅ የአገራችንን ችግር የሚፈታው ብቸኛ መንገድ ነው። ወደዚያ ማምራት ከተቻለ ነገሮች ይቀላሉ። እነሱም አሁን የተባለውን ሁሉ ማድረግ ነው። ሰላም መፍጠርና ሁሉም ዜጎች እኩል ሆነው በመረጡት እንዲተዳደሩ ማድረግ … ለዚህ ተግባራዊነት ደጋፊ፣ ተቃዋሚ፣ ቤተሰብ ሳይባለ ሁሉም ከሰራ ችግሩን መቀነስና ወደ ሚፈለገው ግብ መድረስ ይቻላል።

ዛጎል፡- የኢትዮጵያ ጉዳይ ከእነ ሄዝቦላ፣ ሰሜን ኮሪያና ቬኒዙዌላ ከመሳሰሉት አገሮች ጋር በአንድነት ለወሳኔ መቅረቡን እንዴት አየኸው?

ኦባንግ፡- ሰዎቹ አስቀድሜ እንዳልኩት እንዴት እንደሚሰሩ ያውቃሉ። ይህ በራሱ ልዩ ትርጉም አለው። ከማንም በላይ ለወያኔዎቹ ይገባቸዋል። እነሱን ማግኘት ብትችልና መከራከሪያቸውን ብንሰማ…

ዛጎል፡- ረዥም ጉዞ ከፊት ለፊት አለ ብለህ ነበር፤

ኦባንግ፡- አዎ! የአሁኑ ትልቅ ድል ነው። ግን ድሉን እውን አላደረግነውም። ድሉ እውን እንዲደረግ በውጪ ያለው ሃይል ግፊቱን መቀጠል አለበት። ይበልጥ መግፋት አለበት። ዛሬ የተደረሰበት ደረጃ የሚያኮራና ደረት የሚያስነፋ ተደርጎ መታየት የለበትም። ተግባራዊ ሲሆን ለማየት ተቃዋሚ ፓርቲዎች በአስቸኳይ የጋራ ራዕይ ሊያበጁና አስተማማኝ አማራጭ መሆናቸውን ሊያሳዩ ይገባል። በሁሉም ዘርፍ ይበልጥ እንድንሰራ የሚያበረታታ ወቅት ላይ በመሆናችን ይበልጥ ጠንክረን ልንሰራ ይገባል።

ዛጎል፡- የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ በተለይ የሚያደርገው ነገር ይኖራል?

ኦባንግ፡- ከሂውማን ራይትስ ዎች፣ ከአምነስቲና ሰብአዊ መብት ላይ ከሚሰሩ ተቋማት ጋር ብዙ ሰርተናል። ዝርዝር ውስጥ መግባትና ይህንን አደረግን የሚለውን ጉዳይ እዚህ ላይ አልፈዋለሁ። ሆኖም ግን ስራው እንደሚቀጥል አውቃለሁ። ድርጅታችን በመርህ ላይ ተመስርቶ የሚሰራ፣ ሲሞቅና ሲበርድ የሚቀያየር፣ እንደ ወቅቱ ከፍና ዝቅ የሚል ግብ አስቀምጦ የሚሰራ ባለመሆኑ በአስቀመጠው ግብ መሰረት ከአጋሮቹ ጋር ይሰራል። ጫና መፍጠር ከሚችሉ ብዙ ድርጅቶች ጋር ሰርተናል። እየሰራን ነው። አሁንም እንሰራለን። አዲስ ነገር የለም። አዲስ ነገር የሚፈጠረው ዓላማችን ሲሳካ ብቻ ነው።

ዛጎል፡- ኢህአዴግ ቻይናን በአማራጭ በመያዙ የአሜሪካንን ጫና ወይም ማዕቀብ ሊቋቋም እንደሚችል፣ እንደውም ለማስፈራሪያነት እንደሚጠቀም የሚናገሩ አሉ፤

ኦባንግ፡- ቻይና እንደ አሜሪካ በጀት እየበጀተች፣ ሰፊ ድጋፍ እየሰጠች፣ እየደጎመች የምትገፋ አይመስለኝም። እንዲህ ያለው መላምት ለጊዜው ቀልድ ነው ብሎ ከማለፍ የዘለለ ምላሽ የለኝም።

ዛጎል፡- አሁን በአገር ቤት ተቃዋሚ የሚባሉት የፖለቲካ ድርጅቶች እየተደራደሩ መሆኑ ሰምተሃል?

ኦባንግ፡- አዎ! እንዴት አልሰማም?

ዛጎል፡- እንዴት አየኸው? አንድ ትልቅ እርምጃ ነው የሚሉ አሉ፤

ኦባንግ፡- መነጋገር ጥሩ ነው። ካለመነጋገር የተሻለ ነው። ለመነጋገር ግን የምታናገረው ሌላ፣ የተለየ አቋም ያለው አካል ያስፈልጋል። እስከሚገባኝ አሁን አሁን የሚካሄደው ድርድር አይደለም። በሺህ የሚቆጠሩ ዜጎች፣ ፖለቲከኞች፣ የፓርቲ መሪዎች፣ ጋዜጠኞች፣ ወዘተ እስር ቤት ታሽገው ምን አይነት ንግግር ነው የሚደረገው። ስለማንስ ነው ለመነጋገር የሚቀመጡት? ማንን ነው የሚወክሉት? እነዚህ ጥያቄዎች ሲመለሱ በሚነጋገሩት አካላት መካከል ልዩነት አይታይም። ልዩነት ከጠፋ ድርድር የለም ማለት ነው። እያሰርክ፣ እየገረፍክ፣ ቶርቸር እያደረክ፣ ያሻህን እያደረክ እንደራደር ብሎ ነገር ያለ አይመስለኝም። ካለ ምን አልባትም ይህ በታሪክ የመጀመሪያ ነው። ቅድም ያልኩት ጉዳይ እዚህ ላይ ይነሳል።

ዛጎል፡- ምኑ?

ኦባንግ፡- የመንፈስ ልዕልና፣ የህሊና ጉዳይ፣ ከሁሉም በላይ ስልጣን የመመኘት አዝማሚያ። አሁን ኢትዮጵያ ባለችበት ሁኔታ ስለ ስልጣን ማሰብ፣ አቋራጭ መንገድ መመኘት፣ የጋራ አገራዊ አጀንዳ እንዳይኖረን የሚያደርጉ አደገኛ በሽታዎች ናቸው። በዚህ ችግር ውስጥ እስካለን ድረስ የወያኔ አገልጋይ እንጂ የህዝብ ወኪል ልንሆን አንችልም። ኢትዮጵያ ብሄራዊ ችግር እንጂ የጎሳ፣ የብሄርና የተበጣጠሱ ጎሳዎች ድርጅት ችግር የለባትም። ብሄራዊ ችግር የሚፈታውና መፍትሄ የሚያገኘው በብሄራዊ አጀንዳ ነው። ብሄራዊ አጀንዳ ደግሞ ወደ ጋር ግብ ያደርሳል። የጋራ ግባችን ራስን ጨምሮ ሁሉንም ነጻ ማውጣት ከሆነ የማንም አገልጋይና ተገዢ መሆን የለም። ለማንም እንደማይገዛና እንደማያጎበድድ የተረዳ ሰው የሚያደርገውን ሁሉ በነጻነት ያደርጋል። ያንን ዘመን ለማየት ራዕይ ሰንቆ መጓዝ በታሪክም በትውልድም ፊት ታላቅ ዕልናን ያቀዳጃል። የፍቅርና የቀናነት ምሳሌ ያደርጋል። አሁን የራበን ይህ ነው።

ታክስ ከፋይ ነኝ – ተዎልደ ግርማ

በነጮቹ ሀገር ዜጎች አስተዳደራዊ በደል ሲደርስባቸው እንዲሁም ከመንግስት የሚገባቸውን አገልግሎት ሳያገኙ ሲቀሩ እኔ “ታክስ ከፋይ ነኝ (I am a tax payer)” በማለት በደላቸውን ሲገልፁ ይስተዋላሉ፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ህዝባዊ ተቆርቋሪነት የሚሰማቸው መሪዎችም አግባብነት የጎደለው የመንግስት ወጪን እና ብክነት ሲመለከቱ “ይህ የታክስ ከፋዩ ገንዘብ ነው” በማለት ፈፃሚ አካላትን እንዲሁም ተቋማትን ሲኮንኑ ይስተዋላሉ፡፡ በመሆኑም ባደጉ ሀገራት ታክስን መሰወርም ሆነ ማጭበርበር እንዲሁም የህዝብ ገንዘብን አግባብነት በጎደለው መልኩ ማባከን ትልቅ የህግ ቅጣትን ያስከትላል፡፡ ለአብነት ያክል በአህጉረ አሜሪካ አንድ ታክስ የሰወረ ዜጋ የግለሰብ ህይወት ካጠፋ ዜጋ ባላይ የህግ ቅጣት ይጣልበታል ምክንቱም ታክስ የሰወረው ግለሰብ በመላው የአሜሪካ ህዝብ ላይ የግድያ ቅጣት እንደሞከረ ይቆጠራል እና ፡፡ በመሆኑም ባደጉ ሀገራት ምንም እንኳ ታክስ ማጭበርበር እና መሰወር የለም ባይባልም መጠኑ ዝቅተኛ ሲሆን ዜጎቻቸውም ታክስ በመክፈላቸው አንፃራዊ ኩራት ይሰማቸዋል፡፡ በየጊዜው በሚያኪሂዱት ሀገራዊ ምርጫም በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍል ላይ ለመጣል የሚያቅዱት የታክስ መጠን እና አይነት የዜጎቻቸውን ቀልብ ሲስብ ይስተዋላል፡፡

ወደ ሀገራችን ኢትዮጵያ ስመለስ ሰመኑን በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች እንዲሁም በመዲናይቱ አዲስ አበባ ከታከስ ጋር ቁርኘት ያላቸው ህዝባዊ አድማዎች እየተስተናገዱ ነው ፡፡ አልፎ አልፎም የንግድ ቤቶቻቸውን ክርችም አድርጎ በመዝጋት ቅሬታቸውን የገለፁ ከተሞችም አልጠፉም፡፡ እናማ እኔም ከታች የተዘረዘሩ ጥያቄዎችን መሰረት በማድረግ ሃሳቤን መግለፅ ፍለኩ፡፡ ለመሆኑ በሀገራችን ኢትዮጵያ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍል የሚሰበሰበው የታክስ መጠን እንደተባለው አውን የስራ ፍላጎትን የሚጎዳ ነው (cannon of productivity) ወይስ የፍታሃዊነት(cannon of equality) ችግር አለበት? ለምንስ ህዝባችን ስለ ሚከፍለው ታክስ ኩራት አይሰማውም? የሚሉ ጥያቄዎች ላይ አስታየቴን ለማንፀባረቅ እሞክራለው፡፡

የሀገራችን ኢኮኖሚ የሚያመነጨው የታክስ መጠን የስራ ፍላጎት እና ተነሳሽነት ላይ ያለውን ተፅኖ ለመለየት የሌሎች ሀገራትን ተምከሮ መመልከት ተገቢ ነው፡፡ የበለፀጉ ሐገራት የሰለጠነ የሰው ሀይል እና በቂ የሆነ ተቋማዊ እና ቴክኖሎጂካዊ አቅም ስላላቸው በአማካኝ 34 ፕርሰንት የሚሆነውን የአመታዊ ሐገራዊ ምርታቸውን በታክስ መልክ ይሰበስባሉ (In developed country on average tax revenue accounts for 34 of their GDP) ፡፡ ለአብነት ያክል ታክስ በታላቋ አሜሪካ በአመታዊ ሀገራዊ ምርት ሲለካ 26 ፕርሰንት የሚደርስ ሲሆን በዴንማርክ እስከ 48 ፕርሰንት ይደርሳል፡፡ በሀገራችን ኢትዮጵያ ከታክስ የሚሰበሰበው ገንዘብ በአመታዊ ሀገራዊ ምርት ሲለካ ከ 13 ፕርሰንት ያነሰ ነው፡፡ ይህም ኢኮኖሚው በሚያመነጨው ገቢ መጠን ታክስ እየተሰበሰበ አለመሆኑን የሚያሳይ ሲሆን እንደ አኔ አመላከከት በአጣቃላይ በሀገራችን የታክስ ትልቅነት የስራ ፍላጎትን የመጉዳት ደረጃ ላይ ደርሷል የሚል እምነት የለኝም፡፡ ይህም ማለት ግን ከአቅማቸው በላይ ታክስ እንዲከፍሉ የተገደዱ ዜጎች የሉም ማለት ግን አይደለም ምክንያቱም የታክስ አጣጣል ስርዓቱ ግምታዊ እና በመረጃ የተደገፈ ባለመሆኑ፡፡

በመቀጠልም የታክስ ግዴታው/Burden በተግባር ትልቅ ሃብት ካለው የህብረተሰብ ክፍል ይልቅ ትንሽ ገቢ ባላው የህበረሰተስብ ክፍል ላይ ይበረታል በተጨማሪም ፍትሃዊነት ይጎድለዋል፡፡ በአማካኝ ከ80-85 ፕርሰንት የሚሆነው የመንግስት ገቢ በታክስ አማክኘት የሚገኝ ሲሆን ከ37 እስከ 40ፕርሰንቱ ከውጭ በሚገቡ እቃዎች ላይ በሚጣል ቀረጥ፤ ከ26-32 ፕርሰንቱ በሰራተኛው ገቢ እና በንግዱ ማህበረሰብ ትርፍ ላይ በሚጣል ቀጥተኛ ቀረጥ እንዲሁም ከ19-26 ፕርሰንቱ በሽያጭ እቃዎች አና አገልግሎት ላይ በሚጣል ኢ-ቀጥተኛ(Indirect tax) ቀረጥ አማካኝነት የሚሰበሰብ ነው፡፡ ከውጭ በሚገቡ እቃዎች ላይ የሚጣል ታክስ (import duties)(37-40%) እንዲሁም በሽጣያጭ እቃዎች አና አገልግሎት ላይ የሚጣል(19-26%)ታክስ የሚሰበሰቡበት ከነጋዴው ማህበረሰብ ቢሆንም የሚከፍለው ግን ሸማቹ ህብረተሰብ ነው(Ultimately the bearer of the indirect tax burden is the consumer, not the seller)፡፡

በመሆኑም እንደኔ አመለካከት የታክስ ግዴታውን በአግባቢ እየተወጣ ነው ብዩ የማስበው የህብረተሰብ ክፍል የመንግስት ሰራተኛው/ሲቪል ሰርቫንቱ/ሸማቹ ብቻ ነው፡፡ “ለምሳሌ አንድ በማስተርስ ደረጃ ያለ የዩኒቨርሲቲ መምህር ገቢውን መደበቅ ስለማይችል በወር 2881.5 ብር ወይም በአመት ከሚያገኘው125,250 ብር 34,578 (27.7 ፕርሰንቱን) በታክስ መልክ ይከፍላል (የድርጅት መዋጮ ፣የአባይ ግድብ፣ የወላይታ ልማት ማህበር ምናመን ሳይታሰብ/ሴተረስ ፓሪብስ ማለቴ ነው)” ፡፡ በመሁኑም የንግዱ ማህበረሰብ(በተለይ የደረጃ “ሀ” እና “ለ” ግብር ከፋዮች) የሚያሰሙትን ቅሬታ የምመለከተው ከተጣለባቸው የታክስ ግዴታ ትልቅነት አንፃር ሳይሆን እኩለነትን በማስፈን ረገድ ፍታሃዊነት ይጎድለዋል በሚል እሳቤ ነው፡፡ እኔ እና አንተ ተመሳሳይ ቢዝነስ ኖሮን አንተ እጅህ በመርዘሙ ትንሽ ታክስ ትከፍላል፤ አንተ ለመንግስት መክፈል የሚገባህን ቀንሰህ ለኢዲተር በማካፈልህ እኔ ከገቢያ ስወጣ አንተ ተሸላሚ ባለሃብት ትባላለህ፡፡

በመጨረሻም እኔን ጨምሮ አብዛኛው የህብረሰተስብ ክፍል ስለሚከፍለው ታክስ ኩራት ሲሰማው አይስተዋልም፡፡ ለዚህም እንደ ምክንያትነት ከሚጠቀሰው ችግሮች መካከል ዜጎች በሚክፍሉት ታክስ ልክ ተጠቃሚ አለመሆን እና የሚከፍሉት ታክስ በመንግስት ተቋማት አማካኘነት አለአግባብ ሲባክን መመልከት ዋናዎቹ ናቸው፡፡ለመሆኑ ከቀበሌ መታወቂያ ለማግኘት የሚንገላታ ህብረተሰብ፤ ዘርፈ ብዙ የልማት ፕሮጀክቶች ተጀምረው መጠናቀቅ ሲሳናቸው የተመለከተ ህብረተሰብ፤ የተጠናቀቁ የቤት እና የመንገድ ፕሮጀክቶች ደብዛቸው ጠፋ ሲባል የሚስማ ህበረተሰብ፤ በቢሊየን የሚቆጠር ገንዘብ ህጋዊ ስርዓት ሳይከተል ስለመከፈሉ የሚያውቅ ትውልድ እና ህብረሰተሰብ ታክስ አልከፍልም፤ እረ ከበደኝ ቢል ምን ይደንቃል፡፡ አይደንቅም፤ ግን ወዳጄ እንደ ነጮቹ “እኔ ታክስ ከፋይ ነኝ” እንደማትል ተስፋ አድርጋለው ምክንያቱም እኔ ጥይት ያዥ ነኝ ይሉሃል፡፡

የነጋድያኑን አድማ ወደ ዐመፅ ቀይሮ ወያኔን ካለማስወገድ ሌላ መፍትሔ የለም! – ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

ወያኔ የነጋድያኑ አድማ እየተባባሰ የሚሔድ እንጅ የማይቀዘቅዝ መሆኑን ሲያውቅ ይፋዊ ባልሆነ መንገድ ማስተካከያ እንደሚያደርግ ቃል እየገባና እየለፈፈ ይገኛል፡፡ ነጋዴው ኅብረተሰብ ይሄንን የወያኔን የመደለያ ቃል አምኖ የተያያዘውን አድማ ወደ ዐመፅ ከመቀየር መታቀብ እንደሌለበትና ብቸኛው መፍትሔ ይሄው መሆኑን ጠንቅቆ ማወቅ ይኖርበታል፡፡ ምክንያቱም ወያኔ ግብር የጨመረው አማራጭ ስላጣ እንጅ ተጨማሪ ገቢ ለማግኘት አስቦ አይደለምና ነው፡፡ ወያኔ አማራጭ ቢኖረው ኖሮ እንዲህ ሕዝብ ጥርሱን በነከሰበት፣ ከሕዝብ ጋር በተፋጠጠበት ሰዓት ቢችል እንዲያውም ግብር ይቀንስ ሌላም ሌላም የማባበያ የመደለያ እርምጃዎችን ይወስድ ነበር እንጅ ጭራሽ እንዲህ ሕዝብን በጣም በሚያስቆጣ መልኩ ግብር እየቆለለ አያሸክምም ነበረ፡፡

ከሚገርማቹህ ነገር ነጋዴው “የተጣለብን ግብር ፈጽሞ የመክፈል አቅማችንንና ገቢያችንን ያገናገበ አይደለም!” ይበለው እንጅ የወያኔ ፍላጎት ግን ጭራሽ ከዚህም በላይ የሆነ ግብር በነጋዴው ላይ መጫን ነበር ፍላጎቱ፡፡ ነገር ግን አሁን ካለበት አሳሳቢ ሁኔታ አኳያ ይሄንን ቢያደርግ “በገዛ እጀ በአንገቴ ላይ ገመድ ማጥለቅ ማለት ነው!” ብሎ በማሰቡ “ተመጣጣኝ ነው!” ያለውን ነገር ግን ከነጋዴው ኅብረተሰብ የመክፈል አቅምና ገቢ አንጻር ፈጽሞ ተመጣጣኝ ያልሆነውን ግብር ሊጭን ችሏል፡፡

በነገራችን ላይ ወያኔ ግብር ብቻ አይደለም የሚጨምረው፡፡ ሁሉንም በተመሳሳይ ሰዓት ማድረጉ “ችግር ይፈጥርብኛል!” ብሎ ስላሰበ ነው እንጅ ቀረጥንም ከእጥፍ በላይ ለመጨመር አስቧል፡፡ የሸቀጦች ዋጋ አሁን ያለበትን ደረጃ እያያቹህት ነው፡፡ ሁሉም ነገር ጣሪያ ነክቷል፡፡ ይሄ ዋጋ ከእጥፍ በላይ ሲጨምር ደግሞ እንዴት ሊሆን እንደሚችል አስቡት! እስትንፋስ ያለውን ሁሉ ጸጥ ነው የሚያደርገው፡፡ ወያኔ ኃላፊነትና ተጠያቂነት የሚሰማው አካል ቢሆን ኖሮ እንዲህ ዓይነት ችግር ሲፈጠር እጅ ሰጥቶ “ተረከቡኝ! እኔ አልቻልኩም! ያዋጣል ብየ የያዝኩት መመሪያና የአሥተዳደሬ ሥርዓት እንዲህ ዓይነት ችግሮችን ፈጥሯል፣ ወድቄያለሁ (ፌይል አድርጌያለሁ) ላይሆን ነገር ይሄንን ችግር እቀርፋለሁ ብየ ሕዝብን በከፍተኛ ግብርና ቀረጥ ማስጨነቅ ማሰቃየት የለብኝምና ይችላል ችግራችንን ይቀርፍልናል የምትሉትን አካል ምረጡና አስቀምጡ!” ብሎ ሥልጣኑን ያስረክብ ነበረ፡፡ ነገር ግን ወያኔ እንደምታውቁት ፍጹም ኃላፊነትና ተጠያቂነት የሚባል ነገር የማይሰማውና የአስተሳሰቡ መሠረት “እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል!” የሚለው የአህያ አስተሳሰብ በመሆኑ ይዞን መቀመቅ ለመውረድ ያስባል እንጅ ሥልጣንን የማስረከብ ፍላጎት የለውም፡፡

ወያኔ ይሄንን እጅግ ከፍተኛ የሆነን ግብርና ቀረጥን ሳይፈልግ ለመጫንና ለመጣል የተገደደበት ምክንያት ከዚህ ቀደም ከምዕራባውያን ለጋሾች ያገኘው የነበረው ቀጥተኛ የባጀት (የገንዘብ መደብ) ድጋፍና እርዳታ በከፍተኛ ደረጃ ስለቀነሰበትና መልሶ ለማግኘትም ዕድሉ እንደሌለው ስለተረዳ ነው፡፡ ወያኔ አምና የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብት ተቋም “የሰብአዊ መብት ጥሰት ተፈጽሞ መሆን አለመሆኑን ገብቸ አጣራለሁ!” ብሎ ያቀረበውን ጥያቄ ውድቅ ካደረገ ወዲህ ምዕራባውያኑ ለጋሾች እንደከዚህ ቀደሙ እንኳንና ለቀጥተኛ ባጀት ድጋፍና እርዳታ ሊያደርጉ ይቅርና እንደ ድርቅ ላሉ የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ ጥሪ እንኳ በጎ ምላሽ የማይሰጡ ሆነዋል፡፡ እንደ US Aid (የአሜሪካ የእርዳታ ድርጅት) ያሉ ከፍተኛ የእርዳታ ድርጅቶች ዘግተው እየወጡ ነው፡፡ በዚህ ምክንያት ወያኔ ባጀቱ (የገንዘብ መደቡ) ተቃውሶበት ለከፍተኛ የባጀት (የገንዘብ መደብ) ጉድለት ተዳርጓል፡፡

በየዓመቱ ከሚመደበው የመንግሥት ወጪ (ባጀት) ባለሥልጣናቱ እየዘረፉ ወደየግል ጋዝናቸው የሚያግዙት ከፍተኛ መጠንም ለባጀቱ መቃወስ ትልቁ መንስኤ መሆኑን ልብ በሉ፡፡ ኃላፊነትና ተጠያቂነት የማይሰማው አገዛዝ ባለበት ሁኔታ እንኳን ሙስናን ዋነኛ የአገዛዝ ሥርዓቱ መሣሪያ አድርጎ እየተጠቀመ ይቅርና ከሙስና የፀዳ ቢሆን ኖሮ እንኳ የተረጋጋ የምጣኔ ሀብት ሥርዓትን መዘርጋት መቻሉ የሚታሰብ አይደለም፡፡ በነኝህ ምክንያቶች ያጋጠመው የባጀት ጉድለት እጅግ በጣም ከፍተኛ ነው፡፡ ነጋዴው የተጣለበትን ከፍተኛ ግብር የሚከፍል ቢሆንም እንኳ ወያኔ የገጠመውን ጉድለት መሙላት አይችልም፡፡ ስለሆነም ወያኔ ከቆየ ይሄንን የቁርጥ ግብር ተመን ካላመደ በኋላ ሩቅ ባልሆነ ጊዜ ፈርቶ የተወውን የመጀመሪያውን የግብር ተመን በነጋዴው ላይ እንደሚጭን መገመት ይቻላል፡፡ በመሆኑም “የተጣለብን ገቢን ያላገናዘበው ግብር ይስተካከልልናል!” ብሎ ተስፋ የሚያደርግ ነጋዴ ካለ ሲበዛ የዋህ መሆኑን ልነግረው እወዳለሁ፡፡

ወያኔ ዜጎች መዋዕለ ንዋይን ለማፍሰስ፣ ሥራ ለመሥራት የራሱ ደጋፊ መሆናቸውን ግዴታ ሳያደርገው ዜጎችን ከሀገር ውጭ ያለውን የተማረውንና ሀብት ያካበተውን ጨምሮ በፖለቲካ (በእምነተ አሥተዳደር) አቋም አስተሳሰባቸው ምክንያት ሳያገል፣ ዕድል ሳይነፍግ በሀገራቸው በነጻነት መዋዕለ ንዋያቸውን ማፍሰስ፣ መሥራት፣ መንቀሳቀስ የሚችሉበት ሁኔታ ቢኖርና ለባዕዳንም ለሀገር ውስጥም መዋዕለ ንዋይ አፍሳሾች አደጋ፣ እንቅፋትና ሥጋት የሆኑት የንግድ ድርጅቶቹ ባይኖሩ ኖሮ ሀገሪቱ የእርዳታና ብድር ጥገኛ ሳትሆን፣ በነጋድያንም ላይ አሰቃቂ ግብርና ቀረጥ መጫን ሳያስፈልግ ከየትኛውም ሀገር በተሻለ የማደግ የመበልጸግ ዕድልና አቅም ነበራት፡፡ ይህችን ሀገር የእርዳታና ብድር ጥገኛ ያደረጋት፣ ያላትን አቅምና ዕድል ያህል ተጠቃሚ ሆና እንዳታድግ እንዳትበለጽግ ያደረጋት የወያኔ ያልተጻፈው አግላይ ፖሊሲ (መመሪያ) እና ውንብድና የተሞላበት የንግድ ድርጅቶቹ እንቅስቃሴ ነው፡፡

ይሄ አሁን የተፈጠረው ሁኔታ ግን ይሄንን ሁሉ ውጥንቅጥ መቋጫ የሚያበጅለት ይመስለኛል፡፡ ከዚህ ቀደም ነጋዴው ኅብረተሰብ የወያኔን በርካታ ግፎች ችሎ አሳልፏል፡፡ ትናንትና ወያኔ ለወገኖቹ ለትግሮች ሹክ ብሎ የንግድ ሱቆችን አማላይ ዋጋ እየከፈሉ የመንግሥትን ቤት ከተከራዩት ላይ እንዲከራዩ ካደረገ በኋላ የተከራይ አከራይ አዋጅን አውጆ አብዛኛውን የንግድ ሱቆች ወገኖቹ ትግሮች ወርሰው እንዲቀሩ ማድረጉን የንግዱ ማኅበረሰቡ ችሎ አሳልፏል፡፡ ነጋዴው ማኅበረሰብ እነኝሁ ሱቆችን እንዲወርሱ የተደረጉት ትግሮች ያለቀረጥና ግብር እየነገዱ ለከፍተኛ ኪሳራ ዳርገው ከጨዋታ ውጭ ሲያደርጉት አሁንም ችሎ አሳልፏል ወይም ለመቻል እየተንገዳገደ ይገኛል፡፡ ይሄንን የግብር ጫና ግን የንግዱ ማኅበረሰብ ወያኔን በመፍራት ችየ ላሳልፍ ቢል እንኳ ጉሮሮውን ተይዟልና የሚችል አይሆንም፡፡ ምክንያቱም ግብሩ ገቢውንና የመክፈል አቅሙን ያገናዘበ ባለመሆኑ ከየትም አምጥቶ ሊከፍል አይችልምና፡፡ በልቶ ለማደር ደግሞ የግድ መሥራት ስለሚኖርበትና “ሱቄን ዘግቸ እቀመጣለሁ!” የሚለው አባባል የሚያዋጣ ስለማይሆን የንግድ ማኅበረሰቡ የግዱን ጨክኖ መውጣቱና ወያኔን “በቃኸኝ!” ማለቱ የማይቀር ይሆናል፡፡

ስሙ የንግዱ ማኅበረሰብ ተባለ እንጅ ይህ ችግር የማይነካው የኅብረተሰብ ክፍል አይኖርም፡፡ ተጽዕኖው የሸቀጦች ዋጋ ላይ ጎልቶ መታየቱ አይቀርምና፡፡ አንዳንዶች ይህ የግብር ጫና ያተኮረው የቁርጥ ግብር ከፋይ ነጋዴዎች ላይ ስለሆነ ችግሩ የእነሱ ብቻ ሆኖ የሚቀር ይመስላቸዋል፡፡ ነገር ግን የቁርጥ ግብር ከፋዩ መሥራት ካልቻለ የደረጃ ሀ ግብር ከፋይ ትላልቅ ነጋዴዎች የሚያስመጡትን ሸቀጥ ማን ይወስድላቸዋል? ስለሆነም ከቁርጥ ግብር ከፋይ ውጭ ያለው ነጋዴም በዚህ ችግር ምክንያት ቀጥተኛ ተጎጂ ይሆናል ማለት ነው፡፡ በዚህ ችግር ምክንያት የሸቀጥ ዋጋ ሰማይን ሊቧጥጥ ነውና አጠቃላይ ሕዝቡም ቀጥተኛ ተጎጂ ሊሆን ነው ማለት ነው፡፡ ስለሆነም ችግሩ የሁላችንም ነውና በራሱ ችግር ምክንያት ይህችን ሀገርና ይሄንን ሕዝብ እንዲህ ባለ ምስቅልቅል ውስጥ ያሰጠመንን ወያኔን የግድ ከልተን፣ ነቅለን፣ አስወግደን ከችግር መላቀቅ ይኖርብናልና ለራሳችን ብንል እያንዳንዳችን ለዚህ ቆርጠን እንነሣ!!!

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
amsalugkidan@gmail.com

‹‹በሴትነቴና በማንነቴ ላይ ተመስርተው ስድብና ማንቋሸሽ ፈጽመውብኛል›› ቀለብ ስዩም


#Ethiopia #HumanRights #KelebSeyoum

ስም፡- ቀለብ ስዩም
ዕድሜ፡- 28
አድራሻ፡- አማራ ክልል፣ ሰሜን ጎንደር ዞን፣ ምዕራብ አርማጭሆ
አሁን በእስር የምገኝበት ቦታ፡- በአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት፣ ቃሊቲ እስር ቤት
ለእስር የተዳረግሁበት ምክንያት፡- በሽብር ወንጀል ተጠርጥረሻል ተብዬ ነው የታሰርሁት
በይፋ የተመሰረተብኝ የክስ አይነት፡- አርበኞች ግንቦት ሰባት ከተባለ የሽብር ድርጅት አመራሮች ጋር ግንኙነት በማድረግ ድርጅቱን ለመቀላቀል ልትጓዝ ነበር በሚል የጸረ-ሽብርተኝነት አዋጁን አንቀጽ 7(1) በመተላለፍ በማናቸውም መልኩ በሽብርተኛ ድርጅት ውስጥ መሳተፍ የሚል ክስ ነው የፌደራል አቃቤ ህግ ያቀረበብኝ፡፡

በእስር በምገኝበት ወቅት የሚከተሉት የመብት ጥሰቶች ተፈጽመውብኛል:
1. ለእስር ሲዳርጉኝ የፍ/ቤት ማሰሪያ ትዕዛዝ አላሳዩኝም፡፡
2. ማዕከላዊ ፌደራል ወንጀል ምርመራ ካሰሩኝ በኋላ ለቤተሰቤ ያለሁበትን ሁኔታ ለማሳወቅ ተከልክያለሁ፡፡
3. ቤተሰቦቼ መታሰሬን ከሰሙም በኋላ ለአንድ ወር ያህል በፍጹም እንዳላገኛቸው/እንዳይጠይቁኝ ተደርጌያለሁ፡፡
4. በመርማሪዎቼ ድብደባ ተፈጽሞብኛል፡፡
5. በሴትነቴና በማንነቴ ላይ ተመስርተው ስድብና ማንቋሸሽ ፈጽመውብኛል፡፡
6. በግዳጅ ቃል እንድሰጥ አድርገውኛል፡፡
7. በይፋ ክስ ተመስርቶብኝ ቃሊቲ እስር ቤት ካዛወሩኝ በኋላም የጠያቂ ገደብ ተጥሎብኛል፡፡ እኔን መጠየቅ የፈለገ ሰው ሁሉ እንዲጠይቀኝ አይፈቀድም፤ ቀድሞ ስማቸው በእስር ቤት አስተዳደሩ ከተመዘገቡት ውጭ አይፈቀድም፡፡
8. የመጠየቂያ ሰዓት ገደብም ተጥሎብኛል፡፡ እኔ መጠየቅ የሚፈቀድልኝ ከ6፡00-6፡30 ለሰላሳ ደቂቃዎች ብቻ ነው፡፡
ለእስር የተዳረግሁት ልክ የዛሬ ሁለት አመት ነው፡፡ ለስራ ፍለጋ ከጎንደር ወደ አዲስ አበባ በመጣሁበት ወቅት ነው ተይዤ የታሰርሁት፡፡ ወደ አዲስ አበባ የመጣሁት ደካማ እናቴንና የስምንት ወር ህጻን ልጄን ትቼ ነበር፡፡ ምክንያቴ ደግሞ እራሴንም ቤተሰቦቼንም ለመርዳት የሚያስችል ስራ አገኝ ይሆናል በሚል ነበር፡፡ በዚህ ሁኔታ ባላሰብሁት መንገድ ታሰርሁ፡፡ አሁን ላይ በተከሰስሁበት ክስ የአራት አመት እስር ቅጣት ተፈርዶብኝ ቃሊቲ እገኛለሁ፡፡
ትምህርት እስከማስተርስ ዲግሪ ተምሬያለሁ፤ ማስተርሴን ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ነው የሰራሁት፡፡ ጎንደር አርማጭሆ በመንግስት መስሪያ ቤት የሴቶች ጉዳይ ቢሮ ውስጥ እሰራ ነበር፡፡ ሆኖም በፖለቲካ አመለካከት ልዩነቴ ምክንያት ተባርሬያለሁ፡፡ የአንድነት ለፍትህና ዴሞክራሲ ፓርቲ አባል ነበርሁ፡፡

ሐምሌ ፭ ፪፼፰ (July 11 2016)! – “የታገልኩት አምባገነን ስርዓት ለማስወገድ እንጅ ማንኔትን ቀይሬ ትግሬ ለመሆን አይደለም።” ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ

(ቬሮኒካ መላኩ)

• “የታገልኩት አምባገነን ስርአት ለማስወገድ እንጅ ትግሬ ለመሆን አይደለም።” ኮሌኔል ደመቀ ዘውዱ

• “እኛ አማራነታችን በማመልከቻ ለማምጣት አይደለም የምንታገለው”  አታላይ ዛፌ

• “አማሮች ምንም እንኳን ለጊዜው ያመኑ ቢመስሉም አመች ጊዜ መርጠው ለማጥቃት አድብተው ይጠባበቃሉ።” ሩዶልፎ ግራዚያኒ

• “በማይቆጣጠሩት የፍጥነት ደረጃ እያደገና እየጨመረ የመጣውን አማራ የሚባለውን ብሄር ገስጋሴ እኛ አውሮፓውያን ፖሊሲ አውጥተን በአጭር ካልቀጨነው አፍሪካን አልፎ ለአውሮፓውያን መስፋፋት ትልቅ እንቅፋትና ተጋዳሮት እንደሚሆን አትጠራጠሩ።” Baron Roman Prochazka.

መሬት እንደ ንብረት ተቆርሶ አይወሰድ፣
ወልቃይት አማራ ነው ሁሌም የትም አይሄድ።

ዛሬ ብትወስዱት ነገ ይመለሳል፣
ታሪኩን ተነጥቆ ማንስ ይቀመጣል።

ከጥንት እስከ ዛሬ ከቀን እስከማታ፣
አማራ በወልቃይት አይወጣም ጡረታ።

ገና መች ገባችሁ የአማራ ማንነት፣
ክብር እንደሆነው ለመብቱ መሰዋት።

የተብላላው ገነፈለ ። የተናፈቀው ደረሰ ።ጎንደር አመፁን ባረከው። የአማራ አርሶአደር የሀምሌ ጎርፍ ሆነ።ግምባር ለግምባር ከአጋዚ ጋር ገጠመ። ደመቀ የሚባል አብሪ ኮኮብ የፌደራል ፖሊስ መለዮ ከነጭንቅላታቸው ቀነጠሰው ። ቦደሰው። ሀምሌ 5 ቀን 2008 አም የነፃነት ጉዞ መጀመሪያው ችቦው ተለኮሰ።

አንድ ህብረተሰብ ባላሰበውና ባልጠበቀው አይነት ከአንድ መራራ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የሶሻል ቀውስና ክስረት ውስጥ ድንገት በተዘፈቀ ጊዜ በግለሰቦችም ሆነ በማሀበረሰብ ላይ ብዙ አሳዛኝና አስቀያሚ ድርጊቶች ይፈፀማሉ። ድህረ ግንቦት 20 ኰድኩዶ ካስወለደው የቀውስ ዱብ ዕዳዎች አንዱ ባለፉት 25 አመታት በአማራ ላይ የደረሰው ዱብዳ ነው። አማራ ተከዜን አሻግሮ አራት ኪሎ ባደረሳቸው ለምድ የለበሱ የተኩላ መንጋ ባለፉት አመታት ሲነከስና ሲዘነጠል ኖሯል። አማራ በእነዚህ አመታት የደረሰበት ቀውስና ክስረት ምን ያህል የሚጎመዝዝ መራራ ሰፍነግ መሆኑን እኛ ከአማራ ከአብራኩ የወጣን ልጆቹ በደንብ እንገነዘባለን።

ይህን ሁሉ ስቃይ ሲቀበል የኖረ የአማራ ሕዝብ፣ የውስጡን ረመጥ በአደባባይ ለማሰማት በአገኘው አጋጣሚ ሲያጉረመርም ነበር ።

አማሮች በጭቆና ብዛት ገመምተኛ የሆነውን ስሜታቸውን ለማስታመም በውጭም በውስጥም እስከ ሀምሌ 5 መባቻ ድረስ በየፊናቸው እንጉርጉሮ ማሰማት ጀመሩ። ሀምሌ 5 ሌሊት ለአመታት ሲበስል እና ሲንተከተክ የነበረው የአማራ ህዝብ አመፅ እንደ እሳተ ገሞራ ፈነዳ ። በዚች ታሪካዊ ቀን አማራ የመጨረሻውን መጀመሪያ የትግል ጉዞ ጀመረ።

የአማራ የፀረ ወያኔ አገዛዝ ትግልና የነፃነት ገድል ተመዝግቦ በሚገኝበት ምእራፍ ውስጥ ሀምሌ 5 ልዩና ሰፊ ምዕራፍ ይዛለች። ባለፉት አመታት አማራ ብዙ ጊዜ ወድቆ ተነስቷል።አለቀለት ሲባል አገግሟል። ጠላቶቹ ቀብረነዋል ሲሉ ነፍስ ዘርቷል። ያን ሁሉ ዘመን አልፎም ዛሬ የነፃነት መንገድ ይዞ ለሌሎች መሰሎቿ በአርአያነት የሚጠቀስ የጀግንነት ተምሳሌት ሆኗል።

ነጻነት በገንዘብ የማይተምኑት፣ በስጦታ የማይደልሉለት የሰው ልጅ ፍላጎት መሆኑን አማራ ይረዳል። ድህነት፣ ማጣት፣ ችግርና የመሰለው ምንም አይነት መከራ ቢመጣ የአማራ ህዝብ ነጻነትን ለድርድር እንዲያቀርቡ አያደርጋቸውም። ነጻነት ክብር ነው፤ ክብር ደግሞ በምድር ላይ ለሰው ልጅ የተሰጠ ጸጋ ነው። ይህን ደግሞ ከምንም ከማንም በላይ አማሮች ያውቁታል።

ሚስማር ሲመቱት እንዲጠነክር ባለፉት አመታት በአማራ ህዝብ ላይ የደረሰው በደል እርሾ ሆኖ የህዝቡን ወኔ ይባስ ቀሰቀሰው እንጂ ወደኋላ አልመለሰውም። ተስፋ ሊያስቆርጡ የሚችሉ እጅግ በርካታ ምክንያቶች ቢደረደሩም ክብርና ነጻነትን ማቆየት ግን ከሁሉ በልጠው አመዘኑ።

ቋንቋ ያልተደባለቀባቸው፣ ቀለማቸው ያልደበዘዘ ባቸው፣ ባህል ያልተሰወረባቸው፣ ውበታቸው ያልተበረዘባቸው የራሳቸው ማንነት ያልጠፋቸው ልጆቻቸው ያለአንዳች ሃፍረት አንገታቸውን አቅንተው በኩራት እንዲቆሙ አደረጋቸው።

እነዛ ብርቱ የአማራ አርበኞች የህዝባቸው መልክ ይቀየር ዘንድ ለጠላት እጅ አልሰጡም፤ አልፈቀዱምና። አማራ ዛሬ ትጥቁን አልፈታም የጠመንጃው አፈሙዝ የጠላትን ፋሽስታዊ ጠረን እያነፈነፈ በመቅጣት ላይ ነው።

በጣም አስቸጋሪ በሆነ ሰአት አካላዊ ጥንካሬና የሞራል ሀቀኝነት በማሳየት ለሚያምኑበት ነገር እድላቸውንና ህይወታቸውን ለህዝባቸው አሳልፈው የሚሰጡ ሰዎች “ሄሮ ” ወይም ጀግና ይባላሉ ። አማራ በአለፈው ታሪኩ እልፍ አእላፍ ጀግኖችን ያፈራ ህዝብ ነው። ስለሁሉም የአማራ ጀግኖች ለመፃፍ መሞከር አባይን በጭልፋ ቀድቶ አለመጨረስ መሞከር ነውና ለጊዜው የዛሬዋን ቀን ስለሚያስታውሰው አንዱን ጀግና እንዘክራለን። ይህ የአማራ ጀግና ኮሌኔል ደመቀ ዘውዴ ይባላል።

የደመቀ ዘውዴን ክብር ስብእናና ግሑስ ባህርይ አሟልቶ ለመግለፅ እጅግ በጣም ያስቸግራል ። ምንም አይነት የብዕር ሀይል ሊገልፀው የማይችል ሆኖ ይሰማኛል። ኮለኔሉ የነጠረ የጀግና አበጋዝ ነው።

የደመቀ ዘውዴ ምድራዊ ህላዌ ግብ የተነደፈው ለህዝቡ የነፃነት ዋስትና መስጠት ነው። በዚህም ምክንያት የራሱ ግለኛ ኑሮና ህይወት ዶጋመድ ቢሆንና አፈር ድሜ ቢግጥ ጨርሶ ደንታው አይደለም ። ለግሉ ጥቅምም ሆነ ዝና ለራሱ ምቾትም ሆነ ብልፅግና በፍፁም አያልምም። ደመቀ ዘውዴ ነፃ አእምሮና ወታደራዊ ጥበብ ያጣመረ ለሚያምንበት ግንባሩን የማያጥፍ ጀግና ነው።

ኮሌኔል ደመቀ ዘውዴ የወልቃይት አማራ ህዝብ በገዛ መሬቱ በገዛ ወንዙ በመጤዎች የሚደርስበትን ግፍ እና ስቃይ አንገሽግሾት ይሄን ጭቆና አሽቀንጥሮ ጥሎ ለህዝቡ የነፃነት ሻማ ለመለኮስ የተጋ የዚህ ታሪካዊ ቀን አስጀማሪ አብሪ ኮኮብ ነው። ሀምሌ 5 ስትነሳ ደመቀ ዘውዴ ፣አታላይ ዛፌ እና እልፍ አእላፍ ጀግና አማሮች አብረው ይታወሳሉ።

የኮሌኔል ደመቀና ጓደኞቹ መንፈስ ዛሬም ከህውሃት ማጎሪያ አዘቅጥ ውስጥ ሆኖም አማሮችን ይመራል። የወልቃይት፣ የአርማጭሆ ተራራዎች ድምፁን እየተቀባበሉ ያንቆረቁሩታል። ድል አይቀሬ መሆኑን ይዘምሩለታል።