Nigerian election: Opposition leader Muhammadu Buhari wins

Opposition leader Muhammadu Buhari has swept to victory in the Nigerian general election, inflicting the first defeat of an incumbent government in the history of Africa’s biggest democracy.

Opposition leader Muhammadu Buhari

With 35 of Nigeria’s 36 states declaring results, Buhari had polled 14,951,378 votes to sitting president Goodluck Jonathan’s 12,827, 522 – a lead of more than 2m votes.

Jonathan called Buhari to concede, a spokesman for Buhari’s All Progressives Congress (APC) told Reuters.

The outcome, following a highly competitive, expensive and at times vicious campaign, was hailed by analysts as a milestone for the advance of democracy on the continent. It marks the first time in Nigeria’s history that an opposition party has democratically taken control of the country from the ruling party.

The APC spokesman praised Jonathan for conceding. “There had always been this fear that he might not want to concede but he will remain a hero for this move. The tension will go down dramatically,” said Lai Mohammed.

“Anyone who tries to foment trouble on the account that they have lost the election will be doing so purely on his own.”

Buhari, 72, first tasted power a generation ago as a military dictator, only to be ousted after 20 months and jailed. The former army general has campaigned as a born-again democrat intent on cleaning up the corrupt politics of the continent’s largest economy and most populous nation.

It was his fourth run at the presidency since 1999. His chances were boosted by frustration over endemic corruption, criticism over Jonathan’s handling of Boko Haram’s six-year uprising and a well-organised opposition.

Tensions mounted as both voting and the collation of results had to be extended by a day each. The second day of vote-counting got off to a dramatic start when a member of the governing party disrupted proceedings to accuse the electoral chief of bias.

The logistics of transporting results from around the country to the national nerve centre Abuja slowed the counting process. Prof Akin Oyebode, an academic, noted that Nigeria lacks high-speed trains while flights are often delayed. “We have to remember we are a third-world country, not a first-world country,” he said.

Source: The Guardian

The TPLF Secret Deal: “The Dam is Owned by Egypt, Sudan and Ethiopia”

At a news conference Oct. 7, Ethiopian Prime Minister Hailemariam Desalegn announced that his country welcomes the participation of Egypt and Sudan in the construction of the dam and stressed that his government considers the dam to be jointly owned by Sudan, Ethiopia and Egypt.

The following article was posted on Ethiopian government owned “Walta Information Center” website and removed later.

Addis Ababa, 22 October 2013 (WIC) – Cairo and Addis Ababa may soon reach a truce to calm their dispute over the construction of the Renaissance Dam on the Blue Nile in Ethiopia. Both countries have recently shown good faith and agreed to negotiate about the project. Egypt has even agreed to take part in building the dam, though without declaring its conditions for doing so.Ethiopias Millennium dam

At a news conference Oct. 7, Ethiopian Prime Minister Hailemariam Desalegn announced that his country welcomes the participation of Egypt and Sudan in the construction of the dam and stressed that his government considers the dam to be jointly owned by Sudan, Ethiopia and Egypt. Cairo viewed his statement as a positive step toward reaching a consensus on the project, despite its earlier sharp criticism of it.

In a telephone conversation Oct. 17, Egyptian Minister of Water Resources and Irrigation Mohamed Abdul Muttalib told Al-Monitor: “Egypt doesn’t mind joining the Ethiopian government in building the dam for the service and development of the Ethiopian people. But we must agree on a number of items in a clear way to prevent any damage to Egypt as a result of the dam construction. The Egyptian government always opts for cooperation and participation. … During the coming negotiations with Ethiopia over the dam, we will clarify our position regarding the policy and method of operating the dam, the size of the storage lake attached to it, and how to fill it with water in times of flood and drought.” He stressed, “Egypt will definitely not participate in the construction unless these policies are agreed upon and agreements regarding them are signed.”

On Oct. 8, Ethiopian Minister of Water Alemayehu Tegenu had tweeted, “Great Ethiopian Renaissance Dam never be slowed down for a second[.] We can pay any cost for it … [sic].”

Egypt gets 55.5 billion cubic meters of Nile water annually in accordance with the 1959 agreement signed between Egypt and Sudan. About 85% of that share comes from the Ethiopian plateau, in particular from the Blue Nile tributary, on which Ethiopia intends to build the Renaissance Dam to store 63 billion cubic meters of water in and generate 6,000 megawatts of electricity. The Ethiopian, Sudanese and Egyptian water ministers are expected to meet Oct. 20-23 in Khartoum to discuss the May report of the Tripartite Commission on the repercussions of the dam and how to implement the report’s recommendations for avoiding harm to any of the Nile states.

On Oct. 8, Egyptian Prime Minister Hazem el-Biblawi met with the Supreme Committee for the Nile Water to agree on negotiating mechanisms for dealing with Ethiopia. The gathering ended with approval for Egypt taking part in the dam’s construction.

An official Egyptian source following the Nile issue who asked to remain anonymous, told Al-Monitor on Oct. 16, “The government has prepared a new paper to negotiate with Ethiopia regarding the Renaissance Dam. Technical and legal teams have been tasked with studying the Egyptian [negotiating] items, which are expected to be presented to the Ethiopian side at the next meeting. … The Egyptian offer includes full participation in the construction, management and operation of the dam, by dispatching Egyptian engineers who specialize in the field of dam construction; the signing of an agreement with the Ethiopian side on sending [to Ethiopia] a permanent Egyptian water mission [that will be stationed] at the dam; and [Egypt’s] participation in the funding and working as an intermediary to obtain aid and international loans and grants to finance dam construction.”

The final report of the Tripartite Commission contained several technical remarks regarding how the dam might harm Egypt. Some experts therefore have reservations about the Egyptian government’s sudden decision to participate in the project, especially if it is without considering the full consequences of such a decision.

Al-Monitor obtained a copy of the report prepared by the Egyptian government on the Tripartite Commission’s final report. The Egyptian document states that building and operating the Renaissance Dam according to the current specifications is not in the interest of downstream countries — Egypt and Sudan — and will enable Ethiopia to fully control the flow of the Blue Nile. Moreover, the time required to initially fill the dam reservoir, three years, will negatively affect Egypt.

The report pointed out that the study of existing designs showed a defect in the safety features concerning the secondary Saddle Dam. This, in turn, has the potential to affect the safety of the High Dam in Egypt. Most studies submitted by Ethiopia are preliminary and not meant for implementation purposes. In addition, no environmental and social impact assessments on downstream countries have been conducted.

A diplomatic source involved in the negotiations among Cairo, Khartoum, and Addis Ababa told Al-Monitor, “The sudden announcement of Egypt’s participation in the dam construction is linked to a number of factors that govern its relationship with Ethiopia. Egypt’s decision doesn’t mean compromising its water rights, but Egypt needs special capabilities in the next phase to negotiate and to hold on to its cards for pressure to not accept the dam if it harms [Egypt]. … The political administration in Egypt is aware of the serious [threat] the dam poses to Egypt’s water security. So first, we must agree on the construction and operation policies before signing any agreement to participate in the dam. [We must also] complete the technical and environmental studies to make sure that there is no harm to Egypt or Sudan. … The situation Cairo is now faced with is very complex, and the negotiating options are limited. Our position is the weakest because we are the most in need of water and because of our weak position on the African Horn after the freezing of Egyptian activity in the African Union. We have no choice but to accept the establishment of the dam.”

On the other side of the equation, the Ethiopian government announced in September that it had completed 30% of the engineering and technical preparations at the dam site and is ready to start building the main body of the dam. Sudan expressed its satisfaction with the project and asserted that the dam would protect Sudan from the floods it faces every year.

Egypt is still trying to make the best of the situation and to secure its share of annual water from the Nile as it awaits the negotiations with Ethiopia and Sudan. Egypt fears that its demands will not be met at a time when the country is experiencing internal unrest, ongoing since the July ouster of President Mohammed Morsi and affecting Egypt’s relations with neighboring African countries.

The Dam Dammed by Cash Flow? (by Alemayehu G. Mariam)

ኦቦ በቀለ ገርባ ዛሬ ተፈተው እንደገና ዛሬ ታስረው ሞጆ ላይ ተለቀቁ

አቶ በቀለ ገርባ የ እስር ጊዜያቸውን ጨርሰው መፈታታቸው ተሰማ::  አቶ በቀለ ዛሬ ተፈተው እቤታቸው ከገቡ በኋላም እንደገና ደህንነቶች “ያልተጣራ ነገር” አለ ብለው እንደገና ወስደው ለሰዓታት ካሰሯቸው በኋላ መልሰው ሞጆ ላይ ለቀዋቸዋል::

የኢሳት ራድዮ ጋዜጠኛ ካሳሁን ይልማ “የአቶ በቀለ አፈታት ድራማ” በሚል በዘገበው ዘገባው ላይ የሚከተለውን ጽፏል::

*ዛሬ መጋቢት 21 2007 ዓም አቶ በቀለ የእስር ጊዜያቸውን ጨርሰው የሚፈቱበት ቀን ነው።
*ጠዋት ላይ ባለቤታቸው ወይዘሮ ሀናን ጨምሮ የአቶ በቀለ መፈታትን ለማየት ወደ ዝዋይ እስር ቤት አቀኑ
*አቶ በቀለ ተፈቱ:: ቤተሰባቸውን በእቅፋቸው አድርገው በደስታ እንባ ታጅበው መነፋፈቃቸውን ገለጹ። ከዚያ ጉዞ ወደ ቤት…
*በድንገት የህወሓት ፖሊሶች ወደ አቶ በቀለ መጡና “መጣራት ያለበት ጉዳይ ስላለ ወደ ቃሊቲ እስር ቤት ይወሰዳሉ” አሉ::   ቤተሰብም አቶ በቀለም ቀልባቸው ተገፈፈ:: ደስታቸው ብን ብሎ ጠፋ!
*በደንጋጤ የተዋጡት ወይዘሮ ሀና ይህንን ጉዳይ ለኦፌኮ አመራሮች አሳወቁ። የኦፌኮ አመራሮች በፍጥነት አቶ በቀለ ይሄዳሉ ወደተባሉበት ቃሊቲ እስር ቤት ተጓዙ።
*ሆኖም ቢጠበቅ-ቢጠበቅ አቶ በቀለ ብቅ ሳይሉ ቀሩ
*አቶ በቀለን ይዘው የነበሩት ጠባቂዎች ታሳሪውን ይዘው ሞጆ አካባቢ ለቀቋቸው።

ውዥንብሩ ለምን እንደተፈጠረ ባይታወቅም ዋናው ደስታው ነውናን ቤተሰባቸው አቶ በቀለ ገርባን ይዞ ወደ አዳማ ናዝሬት ይዞ ሄደ። አቶ በቀለና ሴት ልጃቸው ቦንቱን ኢሳት በስልክ አግኝቶ አነጋግሯቸዋል::

በካንጋሮው የሕወሓት ፍርድ ቤት “በሽብርተኝነት” ክስ ጥፋተኛ ተብለው 3 ዓመት ከ7 ወር የተፈረደባቸው አቶ በቀለ በመጀመሪያ ስምንት ዓመት ቢፈረድባቸውም ተከራክረው ወደ 5 ዓመት ማስደረጋቸው ይታወቃል:: በየኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ም/ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ የ3 ዓመት ከ7 ወር የእስር ጊዜያቸውን እንደጨረሱ በኣመክሮ መለቀቅ የነበረባቸው ቢሆንም መከልከላቸው ይታወሳል:: እስር ቤትም ህክምናም ሳያገኙ ብዙ ተሰቃይተዋል:: አቶ በቀለ ገርባ የ 3 ዓመት ከ 7 ወር የእስር ጊዜያቸውን ኣጠናቀው መለቀቅ የነበረባቸው ባለፈው ጥር 11 ቀን ነበር::

ኢትዮጵያ አንድነት ፈተናዎች – ከአበበ ከበደ

የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ሃገር ኢትዮጵያ በቀደሙት ዘመናት ክፉ ነገሮችን የምትከላከል፣ የደጋጎችና የቅን ሰዎች መኖርያ እንደነበረች ታሪክ ያስረዳናል። የኢትዮጵያ ሕዝብ “ሃገሬን አትንኩ” ይል እንደሆን እንጂ ከማንም ጋር በልቶ፣ ጠጥቶ ከመሸበት የሚያድር የዋህ ፈሪሃ አምላክን የተላበሰ ሕዝብ ነው። ኢትዮጵያ ሕዝቡን በፍትህና በጥበብ የሚያስተዳድር ጀግና መሪንም የምታገኘው ከእግዚአብሄር ነበር። ኢትዮጵያ ሃገሯና ሊወር የመጣን ጠላት ድባቅ የምትመታው እግዚአብሄር ከፊት ቀድሞ ስለሚዋጋላት እንጂ ከሌሎች የበለጠ የፈረጠመ ጡንቻ ኖሯትም አልነበረም። ይህ ሁሉ ታሪክ ምስቅልቅሉ የወጣው ኢጣልያ ዳግም ኢትዮጵያን ከወረረች በኋላ ነው። ራሷ ኢጣልያ በኤርትራ የቆየችበት ዓመታትም ዋናውን የአንድነቱን ማብከኝያ መርዝ በቅርብ ሆና ለመቀመም የቻለችበት ኢትዮጵያን የጎዳ ዘመን ነበር። የኤርትራ ጉዳይ እንደመዥገር ሆኖ ከኢትዮጵያ ገላ ላይ አልላቀቅ ያለውም ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ነው። የኤርትራ ከእናት ሀገሯ ጋር የተደበላቀችበት ጥበባዊ ሥራ በምእራብያውያኖች፣ በመካከለኝው ምሥራቅ ፖለቲካ መዘዝ፣ በግራ ክንፉ የሥልጣን ትንቅንቅ ሳብያና በፖለቲካ መሪዎቹ አናሳ ብስለት ምክንያት ተጨናገፈ። የግራው ክንፍ ፖለቲካም ከኢጣልያ መሠሪ አሰራር ልምዱን ባገኙ ኤርትራዉያን ፖለቲከኞች ሲመራ ቆይቷል። ሻዕቢያ የፊትና የኋላውን መመርመር ያልቻሉትን ግለሰቦች በመደለል፣ የነቁትን በማግለል፣ ላንዳንዱ ደግሞ ሥልጣን መዳረሻ የሚሏቸውን የሃሰት ሥልቶች አስታቅፈው፣ ሲቻል እያፋጇቸው ሳይቻል እያነታረኳቸው፣ ዓላማቸውን ከንቱ ለሆነውና እርባና ቢሱ የኤርትራ ግንጠላ አዋሉት። ኤርትራም በከንቱ ተገንጥላለመከራናስደት ስትዳረግ ኢትዮጵያና የዋህ ሕዝቧ በቆሸሸው ፖለቲካ ውስጥ ተነከሩ።

የኢትዮጵያ ችግር በአብዛኛው መንፈሳዊ ነው። ፀሎት ሥጋዊ ሆኗል፣ ፖለቲካው አስመሳይ ሆኗል። ድህነቱ አዋራጅ ሆኗል። አብዛኛው ሰው ከደረሰበት ችግር ለመላቀቅ የእግዚአብሄርን መንገድ ትቶ ለምእራቡ ዓለም ሰግዷል። ለንዋይ መምበርከኩ ታቦትና ጽላት እስከመሸጥ ድረስ ደፋር አድርጓል። ስደቱ ማንነቱን ከመለወጡ አንስቶ ወደ ሌላ አሳፋሪ ድርጊት ተሸጋግሯል። አሁን ግን አምላክ በቃ እንዲለን ከዚህ በታች የምዘረዝራቸውን የመፍትሄ ሃሳቦች ሳላንዛዛ ባጭሩ ለማቅረብ እሞክራለሁ። ይህ ከዚህ ቀደም ብዙ ቢባልለትም እኔ ለማስታወስ ያህል እንደገና እንዲህ አድርጌ አቀርበዋለሁና በጥሞና አስተውሉት።

ኢትዮጵያ ማነች? ኢትዮጵያዊስ

ኢትዮጵያ ከሰባት ሺህ አምስት መቶ ዓመታት በኅልውና የቆየች እግዚአብሄር አላማውን ለመፈጸም ሲል ከሚታይና ከማይታይ መከራ እየከለለ ያቆያት የዋህና ጀግኖች ሕዝቦችን ያቀፈች በአፍሪካ ቀንድ አሕጉር የምትገኝ ሃገር ነች። ኢትዮጵያ የጽላቱና የታቦቱ ምስጢር የተገለጠባት፣ ጥንታዊ የሆነ የራሷ ጽሑፍ ያላት፣ ከእግዚአብሄር ምልክቷ ይሆን ዘንድ ልዩ ባንዲራን የለበሰች በአምላክ ልዩ ጸጋ የምትደዳደር ሃገር ነች። ነብር ዥንጉርጉርነቱን ኢትዮጵያዊ መልኩን መቀየር አይቻለውም። ኢትዮጵያዊ ድህነት፣ ችግርና መከራ ተንበርካኪ የማያደርጉት ጀግና ነው።

ቅናት ምንድነው?

ከእግዚአብሄር ልዩ ጸጋን የታደለ ሃገርም ይሁን ግለሰብ አርፎ አይተኛም። ቀናተኛው ዲያቢሎስ ይግደራደራቸዋል። የቃል ኪዳኑ ታቦት ቤት የሆነችው ኢትዮጵያም ከቀናተኞች ዓይነጥላ አትሰወርም። የእግዚአብሄር ቃል ኪዳን መፈጸምያዋ እስራዔልም ብትሆን ችግሮች ተፈራርቀውባታል። ዲያቢሎስ እስራኤልንም ኢትዮጵያንም ፋታ አይሰጣቸውም። “እናንተ እሥራኤሎች ለእኔ እንደ ኢትዮጵያ አይደላችሁም” የሚለው የእግዚአብሄር ቃልም እሥራኤል በኢትዮጵያ ላይ ፊቷን እንድታዞር ያደርጋታል። መንፈሳዊ ቅናት ተፈጥሯዊ ነው፣ መጠኑ የበዛ ሥጋዊ ቅናት ግን የሰይጣን ነው። ያእቆብ በልጆቹ መካከል ያደረገው ልዩነት ነው ቅናትን አሳድጎ ታናሽ ወንድማቸውን ዮሴፍን ወደ ጉድጓድ እንዲወረውሩ የገፋፋቸው። ኢትዮጵያውያኖች ቀድሞ በግዕዝ ቋንቋ ይጠቀሙ ነበር። የኋላ ኋላ እስከዛሬ ድረስ የመንግሥቱ መጠቀምያ የሆነው ቃንቋ አማርኛ ግዕዙን ተካ። በአማርኛ ቋንቋ ላይም ቅናት ተበራከተ። ኢትዮጵያ ሁሉንም ታላላቅ ኃይማኖቶች ማለትም ክርስትናን፣ እስልምናንና የአይሁድ ኃይማኖትን አካታለች። ሶስቱ ኃይማኖቶች በመሃላቸው የቀኖና ልዩነት አላቸው። ልዩነት ውበት መሆኑ ቀርቶ ውዝግብ የሚያደርገው ቅናት ነው። ዮዲት ጉዲት በአይሁድ ኃይማኖት ሥር ለማካተት እልቂትን ስታመጣ ግራኝ መሃመድም ወደ እስልምናው ለመጠቅለል ለአስራ ሰባት ዓመታት በኢትዮጵያ ቤተ ክርስትያን ላይ አውዳሚ ዘመቻ አወጀባት። ቅናት ከብልሹ ስሜት ይመነጫል። አንዳንድ ጊዜ ከፍርሃት አንዳንድ ጊዜ ደግሞ የፍላጎት መጠን መንዛዛት የቅናትን ስሜቶች ያሳድጋሉ። ኢትዮጵያ ዙርያዋን በከበቧት ቅናቶች ሳብያ ዘወትር ትመሰቃቀላለች፣ ትቦረቦራለች፣ ትከሳለች። ከእጇ የጎረሱት፣ ውሃዋን የተጎነጩት እንኳን ተረከዛቸውን ያነሱባታል። በገዳማቱ ባሉ እውነተኞች አባቶችና እናቶች ጸሎት ይኸው በኅልውና አለች።

ቅናት በዘመናዊ ፖለቲካ ሲቀመም

ከኢጣልያ ዳግም ወረራ በኋላ ኢትዮጵያን የሚያጠፋው መርዘኛው ፖለቲካ በቅኝ ግዛት በተያዘችው በኤርትራ ውስጥ ይቀመም ጀመር። ኢትዮጵያ ብሄረሰቦች የሚጨቆኑባት ሃገር ነች አሉ። አማርኛ ቋንቋን መጨቆና መሣርያ አድርጎ ለማሳየት ከቅኝ ግዛት አስተዳደሩ ውክልናን ያገኙ ሰዎች ከማርክሲዝም ሌኒኒዝም ቀኖና ጋር ለውሰው የቀድሞ ቅናታቸውን አነባብረው “አማራው ሌሎች ብሔረሰቦችን በጭቆና ይገዛል” የሚል አጥፊ ሃሳብ ፈበረኩ። ተከታታይ የነበረውን የኢትዮጵያ መልካም አስተዳደር ላንዴና ለመጨረሻ ለመናድ ከ ሀ እስከ ፐ ያለውን አማርኛ ፊደልንና አማራ ሕዝብን ጨቋን ጭራቅ አድርጎ የመሳሉ ተልዕኮ፣ የኢትዮጵያን ሕዝብ ማህበራዊ አኗኗርንና የዋህነቱን በሚገባ ለሚረዱት ሠርጎ ገብ አጥፊዎች የቤት ሥራ ተደርጎ ተሰጠ። በዚሁ መሠረት የሻዕቢያ ተላላኪዎች በተማሪው እንቅስቃሴ ኋላም በተለያዩ ጊዜዓት በተመሰረቱት የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ በደርግም ጭምር፣ ሠርገው በመግባት ሌሎች ኢትዮጵያ በሚጠሉ ሃገሮች እየታገዙ ለኤርትራ ግንጠላና አዋሉት። ስለዚህ ጉዳይ ብዙ ስለተባለ ይህን ብቻ ባጭሩ አስቀምታለሁኝ። ሻዕቢያ በዲያቢሎስ ቅናት ተገፋፍቶ አማራን ጭራቅ አድርጎ ስሎ ሲያበቃ ጥቂት ግለሰቦችን በማሰባሰን ፀረ አማራውን ኦነግን መሠረተ። ይህ ትልቁ መሠርያዊ ተግባር ለጊዜው ተሳክቶለት ራሱ ሻዕቢያ ኤርትራን ሲያስገነጥል፣ ማለሊት ኋላም ሕወሃት ለስልጣን በቅቶ ሻዕቢያ ሠራሹን ኦነግን እንደ ጉም በተነ። እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ስለሚጠብቅ ቋንቋቸውን አደበላልቆ በሻዕቢያና ሕወሃት መካከል ያለውን ስምምነት በብረት መጋረጃ ጋረደው። ሆኖም ግን ሕወሃት ከወንድሙ ሻዕቢያ በተማረው መሠረት አማራን ይበልጥ ጭራቅ አድርጎ ስሎ በርካታ ዘርን ማዕከል ያደረጉ ድርጅቶችን ፈጠረ። “አማራ ሊመጣባችሁ ነው ራሳችሁን ጠብቁ” እያለ እያሞኛቸው በስልጣን ወንበሩ ላይ ለረዥም ዓመታት ተቀመጠ።

መፍትሄ ያመጣሉ ብዬ የገመትኳቸው ሃሳቦች

አንደኛ፣ እኛ ኢትዮጵያውያኖች ዘመናዊው ዘመነ መሳፍንት ውስጥ ሳናውቀው ድንገት ተዘፍቀናል። በመሆኑም በአጼ ቴዎድሮስ፣ አጼ ዮሃንስና አጼ ሚኒልክ ዘመን የነበረውን የቀደመውን ፍቅርና አንድነትና ጀግንነት ዳግም መመለስ ይገባቸዋል። ሶስቱም ነገሥታት አማርኛ ቋንቋን የመንግሥት ቋንቋ አድርገው ይጠቀሙበት ነበር እንጂ አማራን ጨቋኝ አድርገው አልሳሉም። ራዕያቸውም ሆነ የነጋ ጠባ ምኞታቸው ኢትዮጵያን አንድ ማድረግና ከውጭ ጠላቶቿ መጠበቅ ነበር። አጼ ቴዎድሮስ ራዕያቸው አንድነት በመሆኑ ነው ሃሳባቸውን የተቃወሟዋቸውን የራሳቸውን ዘመዶች ሳይቀር ያስወገዱት። አጼ ዮሃንስ አማራን ቢጠሉ ኖሮ አማርኛን አስወግደው በትግሬኛ ቋንቋ ለመተካት ሙከራ ያደርጉ ነበር። አጼ ሚኒልክ በዘር ቢያስቡ ኖሮ ራስ ጎበናን፣ ፊታውራሪ ኃብተጊዮርጊስ ወይም ደጃዝማች ባልቻን ለትልቅ ሥልጣን አያበቋቸውም ነበር። እኛ ኢትዮጵያውያኖች ይህን መልካም መንፈስ ዳግም እንድንላበስ ማስተዋላችንን ዳግም ማደስና “ለመሆኑ ወዴት እየተጓዝን ነው?” ስንል መጠየቅ እንዲሁም መፍትሄ ማፈላለግ ይኖርብናል።

ሁለተኛ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን አባቶች በቤተ ክርስትያኗ መሃከል የተፈጠረውን ክፍፍል ለመቅረፍ መንፈሳዊ መላ ማፈላለግ የሚኖርባቸው ይመስለኛል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ኃያል የነበረውን የቅኝ ግዛት ወረራርን ለመቋቋም ከጀግኖች አባቶቻችን ጋር አብራ መዝመቷን ከታሪክ ተምረናል። በግራኝም ሆነ በኢጣልያ ፋሺስት ወረራ ዘመን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን በዱር በገደሉ ተሰዳ እየጸለየች እስከዛሬ ገድላቸው ምሳሌና ጥንካሬ የሆነልንን እንደነ አቡነ ተክለሃይማኖትንና አቡነ ጴጥሮስን የመሳሰሉ መስዋዕቶችን አፍርታለች። ዛሬ በስደት የሚኖሩት ወገኖች ለሁለት ተከፈለው ከፖለቲካ ጉዳይ በባሰ ሁኔተ የሚነታረኩትና አንዱ ባንደኛው ላይ እጁን የሚቀስረው በሃገር ቤትና በውጭ ሁለት ሲኖዶሶች በመኖራቸው ሳብያ ነው። ተሳስቼ ከሆነ እርማቱን ለመቀበልና ለመማር ዝግጁ ነኝ። ቤተ ክርስትያኗ ለሁለት መከፈሏ ለጠላት እንዲሁም ኢትዮጵያን ለሚጠሉት ሁሉ አመቺ ሆኗል። እውነትን ደፍሮ የሚናገር ራሱን በንሥሃ አድሶ በቅዱስ ቁርባን አጽድቆ የሚተጋ፣ ለሌሎች ምስክርነቱን በተግባር የሚያሳይ፣ ግዳጁ በሥራ የሚታይ ጠፋ። ስነምግባር ተወላግዶ ግብረገብነት ተሰውሮ፣ ኃይማኖት ተንቃ፣ የሚፈራ የሚከበር ተዉ የሚል ዳኛ ጠፍቶ ሁሉም አንደኛውን ተገን አድርጎ እንዳሻው ይናገራል። ዲያቆኑ ቄስ፣ አስመሳዩ ዳኛ፣ ጉልበተኛው አገልጋይ፣ አዝማሪው ዘማሪ፣ ባለገንዘቡ ፈላጭ ቆራጭ ሆነው እስኪቀርቡ ድረስ ታሪካዊዋ ቤተክርስትያናችን ህልውናዋ ደበዘዘ። ስለዚህ ጉዳይ በጥልቀት ለመናገር በቂ እውቀት የለኝም ነገር ግን የቤተክርስትያኗ ዋናው ሲኖዶስ መንበረ ፓትርያርክ ሃገር ውስጥ እግዚአብሄር እመረጣት ቅድስት ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲቆይ በሃገርም በውጭም የሚገኙ መንፈሳዊ አባቶች እርቀ ሠላምን ፈጥረው፣ እግዚአብሄርን በጽኑ ተመርኩዘው በመጾም፣ በመጸለይና በእምነተ ተግባር በመንደርደር መንፈሳዊው ትግሉን በማጎልበት ኅያውን ቅርስ ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲያስተላልፉ ስል ተንበርክኬ ልመናዬን አቀርባለሁ። ማንም ለእግዚአብሄር ሲል ቢሸነፍ በሰማዩ አባታችን እግዚአብሄር ዘንድ ትልቅ ሥፍራን ይጎናጸፋል። የምድር ነገሥታት ወይም ተጻራሪ አቋም ያላቸው ድርጅቶች እንኳን በዲፕልማሲው ስልት እየተግባቡ ጦርነትንና መናቆርን ያስቀራሉ እንኳንስ የእግዚአብሄርን አደራ የተሸከሙ ታላላቆቹ አባቶች ይቅርና። ቤተክርስትያናችን አንድነቷ ሲመለስ የሃገሪቱ መንፈሳው ችግር ይቀረፋል።

ሶስተኛ፣ ቢቻል የተማረው፣ የተመራመረው በውጭ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ወደ ሃገሩ መመለስ ይገባዋል። ለሃገሪቱ ሙያዊ አስተዋጾ ማቅረብ የሚችሉት ሃኪሞች፣ ማምህራን፣ መተርጉማን፣ ደራስያን፣ መሃንዲሶች፣ የተግባረ ዕድ ባለሙያዎችና የማህበራዊ ሣይንስና ወታደራዊ ጠበብት ባጠቃላይም በችግሯ ጊዜ አብረዋት ሆነው አይዞሽ ሊሏት የሚገባቸውና በሰላማዊ ትግሉ የሚሳተፉ ደፋሮች ሁሉ ቢመለሱ ሃገሪቱ አሁን ከተዘፈቀችበት መከራ ትገላገላለች የሚል እምነት አለኝ። የተማረው ሁሉ ከተሰደደ የሥራ ዕድል እንዴት ይፈጠር? ሠብሎችንና ንጥረነገሮች ተቀምመው ለምርት ውጤት እንዴት ይብቁ? ሃገሪቱን ከውጭ ጠላት ማን ይጠብቅ? በአሜሪካና አውሮፓ ላሉት ስደት ትልቅ የገቢ ምንጭ ወይም የድሎት ቤት መሆኑ ቢታወቅም እንኳን በሌላ በኩል ደግሞ ስደት የቅድስቲቱ ኢትዮጵያን ስም ማጉደፉን ልንገነዘብ ይገባናል። ስደት ኢትዮጵያዊና እስራኤላዊ ላይ አያምርም። ዜግነት በመለወጡ ከኢትዮጵያዊነት ቀለም ማምለጥ አይቻልም። ሠበባ ሠበብን ከምረው ራሳቸውን በማታለሉ ስልት የሚኖሩ ሁሉ እርካታ በሌለበት ሕይወት የሰባውን፣ የላመውን፣ የጣመውን እየበሉ መኖር ብቻ ነው ትርፋቸው። ኢትዮጵያዊነትን ለመለወጥ የሚያበቃ ኅሊና የማይታዘበው እውነተኛ ሠበብ ከቶም የለም።

አራተኛ፣ አማራው ጭራቅ አለመሆኑን የሚያሳይ አዲስ በቅን መንፈስ ላይ የተመሠረተ የቃል ኪዳን ማህበር ሊመሰረት ይገባል። የዚህ ማህበር አባል ሊሆኑ የሚገባቸው እውነተኞችና ራሳቸውን ለሃገሪቱ ሲሉ መሰዋዕት ለማድረግ የተዘጋጁ ከበቀልና ጥላቻ የራቁ ማስተዋልን የተላበሱ እንዲሁም ራስን በንሥሃ አንጸው ለኢትዮጵያዊነት የሚበቁ ደጋጎች ሊሆኑ ይገባል። አባላቱ ኢትዮጵያዊ የሆኑ፣ በውጭ ሲኖሩ ዜግነታቸውን ያለወጡ፣ በማንነቱ ቀውስ (identity crisis) ያልተበከሉ ወይም የለወጡትን ኢትዮጵያዊ ዜግነታቸውን ሊያስመልሱ የተዘጋጁ ሊሆኑ ይገባል። አታክልትን ውሃ እንጂ ማር ቢያጠጡት አይበቅልም። ሃቀኛና ለመስዋትነት ያልተዘጋጁ ሰዎችን አባል ማድረግ ድርጅትን በቁጥር ብዛት ማሳደግ እንጂ በዓላማ፣ ተግባርና ጥራት አያጸናም። እውነተኞችና ደፋሮች ጥቂት ሊሆኑ ይችላሉ። ጥቂት እውነተኞች ግን ኃይላቸው ጠንካራ ነው። ቆራጥ ዓላማ የጽናት ድምር እንጂ የሰዎች ብዛት ብቻውን ቁጥር ነው። ዛሬ በተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች ምክንያት በዘፈቀድ ወደ ቤተክርስትያን የሚመላለሱትንም ሆነ ለማህበራዊ ጥቅም ሲሉ ልዩ ልዩ ድርጅቶችን የተቀላቀሉትን ወገኖች በማስተማር ወደ ትክክለኛ አስተሳሰብና እውነት እንዲመለሱ ለማድረግ የተማሩት፣ የተመራመሩት ሁሉ የማስተማር ግዴታ ቢኖርባቸውም የኃይማኖት አባቶች ደግሞ ከእግዚአብሄር የተቀበሉት ልዩ አደራ አለባቸው።

አምስተኛ፣ እንደ ግንቦት ሰባት ያሉት የፖለቲካ ድርጅቶች ከሻዕቢያ ጋር ያሰሩትን የቃል ኪዳን ቀለበት እንዲያወልቁ በቅጡ መገሰጽ ያስፈልጋል። ሻዕቢያ እንኳንስ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ይቅርና አቅፈው ደግፈው፣ ገንዘብ አዋጥተው ሰልለውና አሰልለው ለስልጣን ላበቁት ወገኖቹም እንኳን በጎ አልሆነም። “ሻዕቢያን መፍትሄ ያመጣልናል” ብለው ያሰቡት ትላልቆቹ ሰዎች ቀድሞ በትምህርት ቤት ሲማሩ “አይጥ ሞቷን ስትሻ ስታበዛ ሩጫ፣ ሄዳ ታሸታለች የድመት አፍንጫ” የተባለውን የታሪክና ምሳሌ መጽሔትን ምሳሌያዊ አነጋገር አላነበቡም አይባልም። ህወሐትን ለመጣል ሻዕቢያን የመጠጋቱ ስልት “እማዬ፣ ድመት የኛን የመሰለ ለስላሳ ቆዳ አለው የቀይ ስጋ ቁንጮ ራሱ ላይ ያለው ዶሮ ነው የሚያስጠላው” በማለት እናቷን ልታደናግር እንደሞከረችው የትንሽቱ አይጥን ተላላ ሃሳብ የመከተል ዓይነት ስልት ነው። ሻዕቢያን የጋረደው ራሱ እግዚአብሄር ነው። ይህ ሊገባን እንዲችል አድርጎ አምላክ ብዙ ቅድመ ሁኔታዎችን ፈጽሟል። መገንጠሉ ባዶ ፖለቲካ ከመሆኑ አንስቶ ኢትዮጵያን መጠበቁ ራሱ ዋነኛ ምልክቶች ናቸው። አቶ ኢሳያስ ይህን እውነት አልተረዱም አይባልም ግን ሕዝቡን ይቅርታ ለመጠየቅ ባህርያቸው ገና አልፈቀደላቸውም። ኢሳት ባቀረበላቸው ቃለ መጠይቅ ላይ በግራው ፖለቲካ ላይ ያካበቱት ችሎታቸውን በእብሪት መልክ እንደገና ሊያስረዱን ሞክረዋል። አቶ ኢሳያስ ብዙ ምልክቶችን አይተዋል፣ ኢትዮጵያ የእግዚአብሄር የቃል ኪዳን ሃገር መሆኗንም ተረድተዋል ነገር ግን የኢትዮጵያን ቅድስትነትና የታሪኳን ገናናነት ገና አልተቀበሉም። ሻዕቢያ ቀድሞውንም ቢሆን እንደነ ፕሮፌሰር ጌታቸው፣ዶክተር ታዬ ወልደሠማያት፣ ዶክተር አሰፋ ነጋሽ የመሳሰሉት ደፋሮቹንና ሃቀኞችን የፖለቲካና ታሪክ አዋቂዎች እንዲገለሉ የሚያስደርገው ኢትዮጵያን የማዳከሙ ዓላማ እንዲመቻችለት ነው። ሻዕቢያ እውነተኛ ኢትዮጵያዉያን ድርጅቶችንና ማህበሮችን እንዳይጠጉ ለማድረግ እንደ ፈረስ በሚጋልብባቸው ተላሎች፣ ወረተኞችና ጥቅመኞች ይታገዛል።

ስድስተኛ፣ ቀድሞ እሽቅድምድሙ የኢትዮጵያ አንድነትን ማጎልበትና ልዕልናዋን ማስጠበቁ ላይ እንጂ ለስልጣን መራወጡ እንዲህ እንዳሁኑ አሳፋሪ አልነበረም። የቀደመውን እንኳን ትተን የቅርቡን አንስተን ብንወያይ በንጉሡም በድርግም ዘመን“ችሎታ” እንጂ “ዘር” ለስልጣን ክህሎቱ የሚያበቃ መስፈርት አልነበረም። ይህ የተበላሸው በግራው ፖለቲካ አስተሳሰብ ከአልቤንያ ኮሙኒስቶች ካባ የለበሰው ህወሐት ስልጣኑን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ ነው። ሥልጣን የአንድነቱ ማስጠበቅያ መሳርያ መሆኑ ቀረ። ህወሐት በአናሳ ብሄረሰቦች ስም ሳይቀር የዘር ድርጅት መስርቶ መሳለቅያ አደረጋቸው። በመሆኑም ይህን የተሳሳተ ምግባር ለመቀየር ሁሉም ዘሩ ኢትዮጵያዊ መሆኑን ማስረዳት ያስፈልጋል። ኢትዮጵያዊነት ኃይማኖት፣ ጀግንነትና አንድነት ነው። ዛሬ አስፈሪ ሆኖ የሚታየውን በሻዕቢያ የሚታገዙትን የአልሻባብንና ኦነግን የሽብር ዛቻ ለመቋቋም ኢትዮጵያዊነትን ይበልጥ ማጎልበት ያስፈልጋል። ኢትዮጵያ የታላላቆቹ ኃይማኖቶች እስልምናና ክርስትና የጋራ መሰባሰብያ ቤት ነች። ይህ ሃገራዊ ጉዳይ ልል እንዲሆን የሚያደናግሩትን እውስጣችን የተሸሸጉትን የሻዕቢያ ጉዳይ ፈጻሚ ተላላኪዎችን ልንነቃባቸው ይገባል። ሌላው ቀርቶ ትግራይዋን ወገኖችን በማስጠላትና በማስገለል ድርጊቶቻቸውና ቅስቀሳቸው ላይም ቢሆን መተባበር የለብንም። ትግራይ የሚኖረው ወገናችንም ቢሆን እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ በደሎች የሚፈራረቁበት ሕዝብ ነው።

ሰባተኛ፣ ባዶ ስሜት ሊወገድ ይገባል። ባዶ ስሜት ሙያን ገደል። ባዶ ስሜት ጋዜጠኛ ሆነ። ባዶ ስሜት ፖለቲከኛ ሆነ። ባዶ ስሜት ጦረኛ ሆነ። ባዶ ስሜት ፓስተር፣ ቄስ ሼህ ሆነ። ከንቱ ስሜት እንደስካር ነው፣ እመስዋትነቱ መንደር ጫፍ ላይ ሳያደርስ ድንገት ይበናል። ልበ ደንዳናነት፤ ለጥቅመ ጥቅሞች ማነፍነፍ ወይም ፍርሃት ባዶ ስሜትን ያመነጫል። ልባቸው ያልተለወጠውን፣ ድፍረት ያለበሱትን፣ ሃቅን ያልተመረኮዙትንና ያልተማሩትን ያልተመራመሩትን ማሰለፉ ሽንፈትን ይጋብዛል። ለጥቅም በተሰለፉ ሰዎች ብዛት ድርጅት ቢፈላ ጠብ የሚላ ነገር የለም። ባዶ ስሜተኞች በዝተው እውነተኞች ካህናት የተናቁባትና ኃይማኖታዊ ምግባርን የማይተገብሩ ሰዎች የበዙባት ቤተክርስትያን መንፈሳዊነቷ ደካማ ነው፣ አታስተምርም፣ በቅዱስ ኪዳኑ ኃይማኖት አታፀናም፣ ፍቅር አታላብስም፣ ይቅር ባይ ልብ አትፈጥርም፣ ፍሪ አታፈራም፣ ቅንነት አታጎለብትም፣ ምዕመናን ያልተንዛዛ የኑሮ ሥርዓት እንዲከተሉ ወይም ሕይወትን በመልካምነት እንዲመሩ አታደርግም። ባዶ ስሜተኞች የበዙባት የፖለቲካ ድርጅትም መካን ነች። ለሥጋዊ ጥቅሙ የሚያደላና ለዕለት ኑሮው የሚጨነቅ ግለሰብ ለኃይማኖቱ፣ ለኢትዮጵያዊነቱም ሆነ ለወገኑ ደንታም የለውም። ደንታ ያለው እንዲመስል በባዶ ስሜት ይወራጫል፣ ያዙኝ ልቀቁኝ ይላል። ሲለቁት ደግሞ ተግባር የለም።

እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይጠብቃል።

“የትግራይ ተወላጆች ታጥቀናል” ሲለኝ – ደነገጥኩ

tplf-gun-holders-e1427778426754-620x310

ህወሃት – የመርዝ ገበሬ፤ ጥይት ማጭዱ!!

“የትግራይ ተወላጆች ታጥቀናል ሲለኝ – ደነገጥኩ” የሚል አስተያየት የሰጠው ኳስ አፍቃሪ ከጎልጉል የአዲስ አበባ ወኪል ጋር የተገናኘው አዲስ አበባ ስታዲየም ነበር። ጉዳዩ ለሚዲያ ግብዓት እንደሚውል ባይረዳም ገጠመኙን ለመናገር የተገደደው ስለ ምርጫ አንስተው ሲወያዩ ነው። ድንገት ተገናኝተው ቆሎ በመገባበዝ የጀመሩት ጨዋታ ዘጋቢውን ወደ 1997 ምርጫ ትዝታ ወረወረው። ተግባብተው አወጉና ተለያዩ። የትግራይ ተወላጆች ታጥቀናል!! ለምን? መርዝ ዘርቶ በጥይት ለማጨድ?

የስታዲየሙ ሰው የመኪና ማስጌጫ ለመግዛትና ለማስገጠም ሰባራ ባቡር እንደሄደ ይናገራል። እዛም እንደ ደረሰ የሚፈልገውን ገዝቶ እያስገጠመ ሳለ አንድ ጎረምሳ ቢጤ ይጠጋቸውና ወሬ ይጀምራል። ጎረምሳው የትግራይ ተወላጅ ነው። አንዳንድ ማስጌጫዎች የሚፈልግ ከሆነ እሱ ዘንድ በርካሽ እንደሚያገኝ እየነገረው ቃላት መለዋወጥ ጀመሩ። በዛው የተጀመረው ጨዋታ ስር እየሰደደ ሄደና ስለምርጫ ማውጋት ጀመሩ።

“ተቃዋሚዎች የትግራይ ህዝብን የመበቀል አጀንዳ እንጂ ሌላ ምንም ዓላማ የላቸውም። ያስጠሉኛል። ልማት አይወዱም። ከዚህ በላይ ምን እንዲደረግ ይፈልጋሉ? የትግራይ ህዝብ ነጻ አወጣቸው …” ወዘተ እንደ ሰውየው ገለጻ ጎረምሳው ብዙ ተናግሯል። በመሃሉ “አንተ ትፈራለህ እንዴ? እኔ ለምሳሌ ካንተ ጋር በፍቅር እያወራሁ ነው” ሲል ሰውየው በመካከል ጥያቄ አነሳበት። ጎረምሳው እየሳቀ ማብራሪያ ሲሰጥ ድንገት የ1997ቱን ምርጫ አነሳና ቤተሰቦቹና ታላላቅ የአገሩ ተወላጆች የነገሩትን አወሳ።

“ከ1997ቱ ምርጫ በኋላ ያልታጠቅነው ሁሉ ታጥቀናል” አለ። እሱ መሳሪያ እንዳለው ሰውየው ጠየቀው? “አዎ!! ምን ችግር አለው ጠይቀህ መውሰድ ትችላለህ” ሲል እንዴትና ከነማን መሳሪያ እንደሚወስድ ተናገረ። “መሳሪያው ምን ያደርግልሃል? ምን ልታደርግበት” ሰውየው እየሳቀ “አሁን እኔን ትገለኛለህ” ሲል ጠየቀው።

ጎረምሳው ብዙ ብዙ ተናገረ። ከተለያዩ በኋላ ሰውየው ድንጋጤ ውስጥ ስለወደቀ የሰማውን ለማሰላሰል አንድ ጥግ ይዞ ተቀመጠ። “ምን እየሆነ ነው?” ሲል አሰበ። የትግራይ ተወላጆችን ለይቶ ማስታጠቅ፣ ጠላት እንዳላቸው በስውር በማስተማር ማደራጀት፣ ከመደበኛ ስራቸው ውጪም ቢሆን ባልደረቦቻቸውን እንዲሰልሉና ተጠራጣሪ ሆነው እንዲኖሩ ማድረግ፣ በቀልን እያሰቡ ውለው በቀልን እያሰቡ እንዲተኙ ማድረግ፣ ከትልቅ እስከ ትንሽ ያሉት ሁሉ ቂምና በቀል እየጋቱ ሌሎች ህዝቦች ሁሉ የትግራይ ህዝብ ጠላትና ቀን ጠባቂ እንደሆኑ በመሳመን የጥይት ስንቅ ማስያዝ … ለምን? ለምን? እስከመቼ? እንዲህና እንዲያ እያሰበ ተምታቶበት እንደከረመ ለጎልጉል ዘጋቢው አወጋው።

በ1997 ቅድመ ምርጫ የመጨረሻ ሰላማዊ ሰልፍ ወቅት የቅንጅት ሱናሚ አዲስ አበባን የዋጣት ዕለት፣ ሱናሚው አዲስ አበባን አጥለቅልቆ ኢህአዴግን በተለይም ህወሃትን ጣር ውስጥ በከተተበት ወቅት ምንም ነገር ማድረግ ይቻል ነበር። ቤተ መንግስት ገብቶ ሁሉንም የጨዋታ ህጎች መደፍጠጥ ይቻል ነበር። የጎጥም ይሁን የጎሳ ችግር የበቀል አራራ ቢኖር ኖሮ ከዚያን ጊዜ በላይ አመቺ ወቅት አልነበረም። ባድሜ ስትወረር የተመመው የኢትዮጵያ ህዝብ፣ ደጀን የነበረው የኢትዮጵያ ህዝብ ጉዳዩ የትግራይና የተወላጆቿ ነው ብሎ አልተቀመጠም። ፈንጂ ላይ እየሮጠ፣ ፈንጂ ላይ “እናት አገር ወይም ሞት” በማለት እየደነሰ ያለቀው ይህ ትውልድ በእውነት ቂመኛ ነው? የዘጋቢው ጥያቄ ነው!!

በርግጥ የኢትዮጵያ ህዝብ ኢህአዴግ ላይ ቢያቄምስ ይፈረድበታል? ይኮነናል? ሃጢአት ተደርጎ ይወሰድበታል? በሰላም ከሚኖርበት ቀዬ የሚፈናቀል ህዝብ ቢያቄም ኩነኔ ነው? “ከክልላችን ውጣ” ተብሎ ደብዳቤ የተጻፈለት የ1ኛ ክፍል ተማሪ ቂም አርግዞ ቂምን ቢገላገላት ይወቀሳል? በዘሩ ምክንያት በደል የሚፈጸምነት ህዝብ ግፍ በዝቶበት “ቢያስታውከው” በተነፈሱ ቁጥር “አሸባሪ” እየተባሉ እስር ቤት የሚጣሉ ወገኖች በቂም ቢመረቅዙ እንዴት “ተው” ይባላሉ? የአገሪቱን ሃብት ውስን ሰዎችና ድርጅታቸው ሲቀራመቱት በገሃድ እየታየ ሰዎች እልህ ቢጋቡ፣ ጸሎት/ዱዓ ለማድረግና ቤተ እምነትን በነጻነት ማቆም ሲከለከል ዝም ማለት ይቻላል? ጥቂቶች ህንጻ እየገነቡ ሲንፈላሰሱ ቀልባቸው የሚቆጣባቸውን “ልክ አይደላችሁም” ማለት ማን ይቻለዋል? … ዘጋቢውና ሰውየው ካነሷቸው ጥያቄዎች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው።

ፕ/ር መስፍን ወልደ-ማርያም “የወያኔ የጥላቻ ፍሬ” በሚል ርዕስ የዛሬ ዓመት አካባቢ ባወጡት ጽሁፍ ላይ እንደጠቆሙት ግፍ ማብቂያ አለው፡- “ወያኔ ከሀያ ዓመታት በላይ አፍንጫ እየያዘ ያስከፈለውን የሚመልስበት ጊዜ እየተቃረበ ነው፤ ጥያቄው ወያኔ እንዲመልስ የሚገደደው እንዴት ነው? የሚል ነው፤ ጥላቻ ወደ ንዴት፣ ንዴት ወደ ቁጣ ተለውጦ ሲገነፍል ምጽዓት ደረሰ ማለት ነው፤ ሁሉም ሰው ራቁቱን ይሆናል፤ አንደአውሬ ከጥፍሩና ከጥርሱ በቀር ሌላ መሣሪያ አይኖረውም፤ ሰው ሁሉ በክፋት ወደ አውሬነት ይለወጣል፤ ጠመንጃና ቦምብ አያገለግሉም፤ ሕንጻው ምሽግ አይሆንም፤ መኪናው፣ ባቡሩ፣ ታንኩ ከቆመበት አይነቃነቅም፤ የትም አያደርስም፤ ጭፍራ ሁሉ በየራሱ ፍዳ ታንቆ እንኳን ለሌላ ሊተርፍ ለራሱም የማይበቃ ይሆናል፤ ለነገሩ ጌታና ሎሌም የለም፤ ሁሉም በአውሬ እኩልነት የተፋጠጠ ነው፤ ርኅራኄ ተሟጦ፣ መግል ያዘለ ልብ ፈርጦ፣ ውይይትና ክርክር አብቅቶ፣ ጥርሱን ያገጠጠና ጥፍሩን የሳለ መንጋ በደም የሚራጭበት ሁኔታ ነው።”

ስለዚህ አካሄድን በማሳመርና ሚዛን የጠበቀ አስተዳደር በማስፈን አገዛዝን ወደ ህዝባዊ መንግሥት በመቀየር ወግ ነው። ተስማምቶ መኖር እየተቻለ ወገን እየለዩ ማስታጠቅና ባምስትና በአስር ሰዎች የተመደበ የቀድሞ መከላከል፣ የቀድሞ ማጥቃት፣ ካልተቻለም የሚቻለውን አድርጎ የሚሆነውን ማየት በሚል እሳቤ  መንጎድ የትኛውንም ወገን እንደማይጠቅም መረዳት ግድ ይላል። በተለያዩ ወቅቶች አስተያየት የሰጡ እንደሚሉት ህወሃት እንዲህ ካለው አጉል አካሄድ ራሱን በማረቅ ብቸኛ አማራጭ ወደ ሆነው እርቅ ፊቱን እንዲያዞር የሚመለከታቸው ሁሉ ሊያሳስቡት ይገባል።

ኢህአዴግ ዙሪያ ያሉ ድቃይ ድርጅቶችም በዚህ ጉዳይ ላይ በወጉ ሊመክሩና ከወዲሁ የሚበጀውን መንገድ በመከተል ቂምና ምሱን ለማክሰም መንቀሳቀስ እንደሚገባቸው ብዙዎች ይመክራሉ። ለህሊና ዋጋ በመስጠት የመርዝ እርሻን ማክሰም የጊዜው የከረመ ጥያቄ ነውና ሁሉም ልብ ሊሉት እንደሚገባ በተደጋጋሚ መዘገቡም አይዘነጋም። መርዝ እየዘሩ በጥይት አጭዶ ለመከመር መደራጀት ሌላውን ከሚያስፈራው ይልቅ የበደሉንና የቂሙን ቁስል ይበልጥ የሚያመረቅዝ ይሆናልና ህወሃት ልብ ሊገዛ እንደሚገባ የሚመክሩ ጥቂት አይደሉም። ህወሃት “ንፋስ ዘርቶ አውሎ ነፋስ አላጭድም” ማለት አይችልም – ቀን ጎዶሎ ነውና!!

Source-  ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

በአየር ድብደባው በየመን46 ኢትዮጵያኖች ሞተዋል

አውቀው ነው ስደተኞቹን የደበደቡት
ለሞቱት 46 ኢትዮጵያዊያ ሳዑዲ ተጠያቂ ናት…መደብደቧን
አመነች ትላንት ንጋት ላይ በሰሜናዊ ምስራቅ የመን ሀጃ አካባቢ
በተደረገ የአየር ድብደባ አየር የ International
Organization for Migration (IOM) ካምፕ ላይ ጥቃት
ያደረሱት የሳዑዲ አረቢያ የቶር ጀቶች መሆናቸው ታወቀ፡፡
የሳዑዲ መንግስት ባለስልጣናትም ድብደባው በእነሱ ጀት
መፈጸሙን አምነዋል፡፡ ድብደባው ግን ሆነጅ ተብሎ የተፈጸመ
እንደሆነ የሚያሳይ ፍንጭ አለ፡፡ ቦታው የ UNHCR ካምፕ
መሆኑ የታወቀ ነው፡፡ የ UNHCR አርማ ያለበት ድንኳን
የተጣለበት መሆኑ እና የ UNHCR አርማ እየተውለበለበ ያለበት
ሁኔታ ነው ያለው፡፡ በእስከ አሁን ሁኔታ በጨለማ ሲደበድቡ
ቅንጣት ስህተት አልነበረም፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ አርማውን አላየንም አይባል ድብደባው
የተፈጸው ንጋት ላይ ነው፡፡ አንዴ ሳይሆን በተደጋጋሚ ነው
እየተመላለሱ የመቱት፡፡ ይሄ ምን ያሳያል እስኪ መንግስት ካለን
መብታችንን የሚጠይቅልን ከሆነ ይሄን ይጠይቅ…..እባካችሁ
ወገን እያለው ወገን እንደሌለው ሀገር እያለው ሀገር እንደሌለው
የትም እየረገፈ ላለው ኢትዮጵያዊ ወገኖቻችን ድምጽ እናሰማ፡፡
እባካችሁ የተኙትም ይንቁ ጠግበው ተገልብጠው እያደሩ ወገን
እነሱ ባንኮራፉ ቁጥር እየረገፈ መሆኑን ይወቁት ይህን የሰው
ልጅ ላይ የደረሰ አሰቃቂ እልቂት ያላየ ይይ ሼር
አድርጉ……..በሁኑ ሰዓት የአየር ጥቃቱ ከወታደራዊ ተቋም ወደ
ሲቪሉ ህዝብ እየወረደ ነው፡፡ በርካታ ሲቪሎች እየሞቱ ነው፡፡
‪#‎girum_teklehaimanot‬

Tilaye Tarekegn ZE Ethiopia's photo.
Tilaye Tarekegn ZE Ethiopia's photo.
Tilaye Tarekegn ZE Ethiopia's photo.
Tilaye Tarekegn ZE Ethiopia's photo.
Tilaye Tarekegn ZE Ethiopia's photo.

የማለዳ ወግ …” ልዩነት መልካም ነገር ነው! ” አንጀሊና * ዘሐራ ጥቁር አልማዝ ሆና ነጯን እናት ስታደምቅ -ነቢዩ ሲራክ

11030318_10206560045025805_7158802905229137827_n

ለማፍቀር መፈቀር ፣ ሰው ለመርዳት ሰው መሆን ግድ ይላል ! ይህ ተፈጥሯዊ ህግ ሆኖ በሁላችንም ላይ ባይሰረጽም የታደሉት ሲሆኑትና ሲታደርጉት ከማየት አልፎ የድካማቸው ፍሬ አፍርቶ ሲያዩት ምስክር እማኝ መሆን መታደል ነው ። መልካም መስራት ለራስ ነው እንዲሉ ውስጥን ከሚሰጠው እርካታ ባሻገር የታደሉት የዘሩት አሽቶ መልካም ስራቸው በስኬት ጎዳና ሲታይና በውጤት ስኬቱ ሲደምቁ ማየት ከምንም በላይ ያስደስታል ። በአንጻሩ መልካም ሰርተው እጃቸው ” አመድ አፋሽ ” የሆኑንም አለማችን ከማስተናገድ አልቦዘነችም ። የአማድ አፋሽነቱ ህመም ጥልቆ ቢያመም የሰሩት ለውስጥ እርካታ ነውና ሁሉምም የሚያየው አንድ ፈጣሪ ፍርድ ይሰጣልና ህመሙ ህመም አይባልም ። አድርጎ “አመድ አፋሽ ” መሆን ክሽፈት ነው ከተባለ ምድራዊ ጊዜያዊ ክሽፈትነት ፈቀቅ አይልም ፣ የመልካምነት ሰማያዊ ጸጋቸው ሰፊ ነውና እኒህም የታደሉ ናቸው !

11113558_10206560045465816_5724276787710087968_nየዛሬዋን አጠር ያለች የማለዳ ወጌን እንድሞነጫጭር ምክንያት የሆነኝ ትናንት መጋቢት 20 ቀን 2007 የልጆች ምርጫ Nickelodeon’s 28th Annual Kids’ Choice የተሰኘውን አመታዊ የሽልማት ስነ ስርአት አዋርድ በማሸነፍ ተሸላሚ የሆነችው የኦስካር አሸናፊዋ ድንቅ ተዋናይት አንጀሊና ጆሊ ሽልማት አይደለም። ሰብዕናዋ ፈቅዶ የዘራችው አጎምርቶ ለደስታዋ ድርብ ደስታ መሆኑን በማየቴ እንጅ …ቅዱስ መጽሐፉ ” የዘራቸውን ታጭዳላችሁ! ” እንዳለው ከመከራው ኑሮ አቅፋ ደግፋ ያሳደገቻቸው ልጆቿ በአሳዳጊ እናታቸው አንጀሊና ጆሊ ማሸነፍ እየፈነደቁ ሲያቅፉና ሲስሟት የተሰማኝ የደስታ ስሜት ለመግለጽ ያህል ነበር ብዕሩን መጨበጤ …

የተጨበጨበላት ድንቋ የፊልም ተዋናኝ ፣ ደራሲና በጎ አድራጊዋ አንጀሊና ጆሊ ሽልማቷን ስትቀበል ባሰማችው ንግግር ” ልዩነት መልካም ነገር ነው! ” ነበር ያለችው … አዎ ልዪነተ መልካም ነገር ነው ! አንጀሊና እንዳለችው ልዩነት መልካም ነገር ነው ፣ ልዩነት ጌጥ መሆኑን አምኖ በሚያስማማው ነገር ተስማምቶ መኖር ይቻላል ።

አንጀሊና እንደ ፈረንጆቹ ዘመን አቆጣጠር በ2005 ወደ ኢትዮጵያ መጥታ በጉዲፈቻ ወስዳ ያሳደገቻት ዘሐራ ተለውጣለች ። እነሆ አሳዳጊ እናቷ ስትሸለም ከእቅፍ ወርዳ ከጎኗ ተቀምጣ ደስታዋን የምትጋራ የጥቁር አልማዝ ሆና ነጯን እናት አድምቃታለች ” ልዩነት መልካም ነገር ነው! ” እኔም እላለሁ በፍቅር እንድትዋጅ ፍቅርን ስጥ … ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው ” ልዩነት መልካም ነገር ነው! ”

ደስ ሲል: )

ነቢዩ ሲራክ
መጋቢት 21 ቀን 2007 ዓም

satenaw

ግብጽ የዓባይን ወንዝ የመጠቀም ታሪካዊ መብቴ የምትለውን የቅኝ ግዛቱን ውል ወያኔን አስፈረመች! – ሠዓሊ አምሳሉ ገብረኪዳን አርጋው

Amsalu

ያሉን ታሪካዊ መዛግብት እንደሚያመላክቱት የዐባይ ወንዝ ከግብጽ ጋር በነበረን ግንኙነት ለውዝግብ ምክንያት መሆን የጀመረው ከሽህ ዓመታት ወዲህ እንደሆን ያስረዳሉ፡፡ እንዲያ እንዲያ እያለ መጥቶ በዐፄ ምኒልክ ዳግማዊ ዘመን እንግሊዝ ግብጽንና ሱዳንን ቅኝ ትገዛ በነበረበት ወቅት ለምትገዛው አካባቢ የዐባይን ወንዝ የውኃ ምንጭነት አስተማማኝ ለማድረግ በማሰብ የሀገራችን መንግሥት ሁለንተናዊ አቅም በዘመነ መሳፍንት የገጠመውን ስብራትና መዳከምን መልካም አጋጣሚ በመጠቀም የዐፄ ምኒልክ ዳግማዊን መንግሥት በመጫን እ.ኤ.አ. 1902ዓ.ም. አሳሪ ውል ለማስፈረም ጥረት አድርጋ ነበር፡፡ ይህ ውል እጅግ አወዛጋቢና በቀጥታም ከውጫሌው ውል ጋር ተመሳሳይ ይዘትና ቅኝት ያለው የተጭበረበረ ሰነድ ነው፡፡ የውሉ አንቀጽ የሚከተለውን ይል ነበር፡-

“His Majesty the Emperor Menilik II, King of Kings of Ethiopia, engages himself towards the Government of His Britannic Majesty not to construct or allow to be constructed any work across the Blue Nile, Lake Tana, or the Sobat, which would arrest the flow of their waters except in agreement with His Britannic Majesty’s Government and the Government of Sudan” “ከብሪታኒያ መንግሥትና ከሱዳን መንግሥት ጋር ከሚደረግ ስምምነት ውጭ በዐባይ በጣናና በባሮ ላይ ምንም ዐይነት ውኃውን ሊያቅብ የሚችል ግንባታ ላይደረግ” የሚል ነው፡፡ አማርኛው የውሉ ቅጅ የሚለው ደግሞ “የዐባይን ወንዝ ተፈጥሯዊ የፍሰት አቅጣጫ በመቀየር ወደሌላ አቅጣጫ እንዲፈስ ላይደረግ” የሚል ሆኖ ከእንግሊዝኛው ጋር ፍጹም የተራራቀ ትርጉም ያለው ነው፡፡

ይህ የቅኝ ግዛት ውል ሊሠራ የማይችልባቸው አራት ዐበይት ምክንያች አሉ እነሱም፡-

  1. ውሉ ከአንድ በሕግና ሥነ-ሥርዓት እተዳደራለሁ ከሚል መንግሥት ፍጹም በማይጠበቅና ሥነምግባር በጎደለው መልኩ በማጭበርበር በማታለል በማወናበድ የተሞላ በመሆኑ በሕግ ፊት እንኳን ተቀባይነት ኖሮት ገዥ ሊሆን ይቅርና ለማጭበርበር ለማታለል ለማወናበድ የሞከረውን አካል ፊርማና ማኅተም ያረፈባቸውን የእንግሊዝኛውንና የአማርኛውን ትርጉም በማናበብ ከሰነዱ መረዳት እንደሚቻለውና በግልጽ እንደሚያረጋግጠው ለማጭበርበር ለማታለል ለማወናበድ የሞከው አካል እንዲህ ዓይነት ነውረኛ ወንጀል ለመፈጸም በመሞከሩ ቅጣት የሚጠብቀው በመሆኑና የተጭበረበረ ሰነድ በሕግ ፊት ተቀባይነት የሌለው በመሆኑ፡፡
  2. ይህ ውል ሲፈረም በወቅቱ የነበረው ሁኔታ ማለትም በውሉ ላይ የተጠቀሰችው ሀገር ሱዳን ለዘለዓለም የእንግሊዝ ቅኝ ግዛት እንደሆነች እንደምትኖር ግንዛቤ ውስጥ ያስገባ በመሆኑና ይህ ሁኔታ ግን ዛሬ ላይ የሌለ የተሻረ የፈረሰ የተንኮታኮተ በመሆኑ ዛሬ ላይ ባለ መብት ነኝ የምትለዋ እንግሊዝ በቦታው የወሳኝነት ሥልጣን የሌላት በመሆኑ፡፡
  3. እንግሊዞች ሊያደርት የሞከሩት ስምምነት ሙሉ ለሙሉ ከፍትሐዊነት የወጣ በመሆኑ፡፡
  4. በአማርኛው የውሉ ቅጅ ላይ በግልጽ እንደሰፈረው “የዐባይን ወንዝ ተፈጥሯዊ የፍሰት አቅጣጫ በመቀየር ወደሌላ አቅጣጫ እንዲፈስ ላይደረግ” ይላል እንጅ በእንግሊዝኛው ላይ እንደሰፈረው “ከብሪታኒያ መንግሥትና ከሱዳን መንግሥት ጋር ከሚደረግ ስምምነት ውጭ በዐባይ በጣናና በባሮ ላይ ምንም ዐይነት ውኃውን ሊያቅብ የሚችል ግንባታ ላይደረግ” የሚል ባለመሆኑ፡፡ በእነዚህ አራት ዐበይት ምክንያቶች እ.ኤ.አ. 1902ዓ.ም. ከእንግሊዝ መንግሥትና ሱዳንን ይገዛ ከነበረው አሥተዳደሯ ጋር የተደረገው የተጭበረበረ የስምምነት ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም ማለት ነው፡፡ ለነገሩ እነሱም ይሄንን በመረዳት ይመስላል ሲጨንቃቸው ካልሆነ በስተቀር ብዙም ሲጠቅሱት አይሰሙም፡፡

ይህ ውል ግብጽን የሚያካትት አልነበረም፡፡ ግብጽ ደግሞ በበኩሏ የዐባይ ወንዝ ባለመብት ነኝ ለማለት “ግብጽ የዐባይ ስጦታ ናት ወይም ዐባይ የግብጽ ስጦታ ነው፣ ዐባይን የመጠቀም ታሪካዊ መብት አለን” ይላሉ፡፡ ይህ ምን ማለት እንደሆነና ታሪካዊ መብቱንና ዐባይንም በስጦታ ማን መቸ እንደሰጣቸው ተናገሩ ሲባሉ ግን ሊገልጽት የሚችሉት የሚጨበጥ ነገር የላቸውም፡፡ ከጭንቀታቸው የተነሣ ሀገራችን ዐባይን በተመለከተ እንዳትገዳደር ጥያቄ እንዳታነሣ ለመከላከል ያመነጩት ባዶና መሠረት የሌለው ቃል ነው፡፡ ቃሉን ለመጀመሪያ ጊዜ የተናገረው ሄሮዱቶስ ነው፡፡ ይሄንን ያለበት ምክንያትም ግብጽን በጎበኘበት ጊዜ የሥልጣኔዋ መሠረት የሕይወቷ እስትንፋስ ዐባይ መሆኑን በመረዳቱ እንደፈላስፋነቱ ይሄንን ሁኔታ በአጭር ቃል ልግለጸው ሲል የጠቀሰው ቃል ነው፡፡ ግብጾችም ከዚያ በኋላ ይህችን ቃል ይዘው ልክ እግዚአብሔር እንደተናገረው እያስመሰሉ ቋሚ መፈክር አድርገው ይዘውታል፡፡ ዐባይ ወደ ግብጽ የሚፈሰው የግብጽ ስጦታ ስለሆነ ሳይሆን ውኃ ቁልቁል መፍሰስ ተፈጥሯዊ ባሕርይው ስለሆነ ነው፡፡ ይህ አባባላቸው ትክክል ሊሆን ይችል የነበረው ዐባይን የፍሰት አቅጣጫውን አስቀይረነው ወዳስቀየርነው አቅጣጫ ፍሰስ ስንለው ወደ ግብጽ ካልሆነ አልፈስም የሚል ቢሆን ኖሮ ነበር፡፡

ግብጽ ከዚህ ተጨባጭነት ከሌለው ቅዠት ነክ አባባል በተጨማሪ ሀገራችን ዐባይን ገድባ ውኃውን እንዳትጠቀም ለማድረግ ከተቻለ ሀገሪቱን እስላማዊ አድርጎ በእስላማዊ ቃልኪዳን ማሰርና ለእነሱ ታማኝ እንድትሆን ማድረግ፡፡ ካልተቻለ ደግሞ ኢትዮጵያን ያልተረጋጋችና አንድነቷ ያልተጠበቀ አድርጎ አዳክሞ የማስቀረት ስልት (ስትራቴጂ) ነበር ዕድሜ ልካቸውን ሲጠቀሙብን የኖሩት፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ግብጽና ሱዳን ከሀገራችን ውኃ እንዳያጡ እስካሁን ሲጠቀሙት የኖሩት ስልት የሚያዋጣና ተቀባይነት ያለውም አልነበረም ሕገ ወጥ ወንጀልና በሕግ ፊትም የሚያስጠይቃቸው ነው፡፡ ይህ ሕዝብ የሰቆቃና የመከራ ኑሮ እንዲገፋ ምክንያት ሆነዋልና ዋጋም ያስከፍላቸዋል፡፡ ግብጽና ሱዳን እኛን እየተማጸኑ እየለመኑ እየተለማመጡ ውኃ ከማግኘት ባለፈ እስከዛሬ ሲያደርጉት ከነበረው ግፈኛ ስልትና ድርጊታቸው አንዱንም እንኳ በእኛ ላይ እንዲያደርጉ እኛንም እንዲጫኑ እንዲያስገድዱ የሚደግፍ በዓለማ አቀፋዊው የመንግሥታቱ ድርጅት ማኅበርም ሆነ በሌላ የዓለም ሀገራት በአስገዳጅ መልኩ እንዲተዳደሩበት በተደነገገ ሕግ ምንም ዓይነት መብትና ሥልጣን የላቸውም ሊኖራቸውም አይችልም፡፡ እንደ ግብጽና ሱዳን ሁሉ ሆድ የባሳቸው የተፋሰሶች የታሕታይ ሀገራት በመሰባሰብ የዓለም ሀገራት እንዲተዳደሩበት በመፈለግ “የወሰን ተሸጋሪ ወንዞችና የተፋሰስ ሀገራት የመተዳደሪያ ደንብ” ወይም ሕግ ብለው ማንም ሥልጣኑን ሳይሰጣቸው በራሳቸው ተነሣሽነት ያወጡት አንድ ሰነድ አለ፡፡ ይሁንና ይሄ በዓለም ሀገራትም ሆነ በመንግሥታቱ ድርጅት ተቀባይነት አግኝቶ እየተሠራበት ያለ ሕግ ባለመሆኑ ማንም በዚህ ሕግ የመተዳደር ግዴታ የለበትም ኖሮበትም አያውቅም ወደፊትም ይኖርበታል ብየ አላስብም፡፡ ምክንያቱም በተላያዩ አህጉራት ያሉ የላዕላይ ተፋሰስ ሀገራት ነገሩን መበተሳሰብ መፍታትን ይመርጣሉ እንጅ በአንዳች ዓይነት አሳሪ ወል ወይም ሕግ መታሰርና በዚያም ላይ መፈረም ፈጽሞ የሚፈልጉ ባለመሆናቸው ነው፡፡ እነኝህ ሀገራት በዚህ ጉዳይ ላይ የጸና አቋም ነው ያላቸው፡፡ እንግዲህ ያለው ዓለማቀፋዊ ሁኔታ እንዲህ በሆነበት ማለትም እንደሌሎቹ ሁሉ በፈቃደኝነት በመተሳሰብ ካልሆነ በስተቀር አስገዳጅ ሕግና ደንብ በሌለበት ሁኔታ ነው ወያኔ አሳሪና 100% ከዐባይ ውኃ ሀገራችን እንዳትጠቀም የሚያስር ውል ሊፈርም የቻለው፡፡

ሰሞኑን ሱዳን ውስጥ እንደተፈረመ ተደርጎ የተወራ ነገር ግን በሰነዱ ራስጌ ላይ የተጠቀሰው ቀን እንደሚያሳየው ተፈረመ ከተባለበት ሃያ ቀናት በፊት እንደተፈረመ በሚገልጠው ውል ላይ ግብጽ ሱዳንና ወያኔ የዐባይን ግድብና የዐባይን ውኃ በተመለከተ እንደተፈራረሙ ሰምታቹሀል፡፡ እስካሁን እንዳየሁት በዚህ በተፈረመው ውል ወያኔ ምን ያህል በዚህች ሀገር ላይ ዛሬም የሀገር ክህደት እንደፈጸመ፣ ሀገሪቱ ምን ያህል እንደተጎዳችና ልትጎዳም መሆኗን፣ ሉዓላዊነቷ መደፈሩን፣ ብሔራዊ ጥቅሟን መነጠቋን፣ መቀመጫዋ ላይ ተጨማሪ ፈንጅ መቅበሩን የተረዳን የገባል አልመሰለኝም፡፡

እኔ በግሌ የዐባይ ግድብ ግንባታ ሥራ ሲጀምር ከባድ ሥጋት ከጣለብኝና ግድቡ በወያኔ እጅ መገደቡን እንዳልወደው እንዳልቀበለው ካደረጉኝ ታች አምና በጻፍኩት ጽሑፍ ላይ ከጠቀስኳቸው ስድስት ነጥቦች አንዱ ግብጽና ሱዳን ከባድ ተቃውሞ ማንሣታቸው ስለማይቀርና በዓለም ዓቀፉ ማኅበረሰብ ግፊትና ጫና ወደ ድርድር መገባቱ ስለማይቀር ድርድር ከተደረገ ደግሞ ወያኔ በዓለማችን በተለያዩ አህጉራት እንዳሉት የላዕላይ ተፋሰስ ሀገራት ጠንካራ አቋም ይዞ በብልህነት በጥሩ የዲፕሎማቲክ (የአቅንኦተ ግንኙነት) ብቃትና ችሎታ የሀገራችንን ጥቅም የማስጠበቅ ሞራላዊ (ቅስማዊ) ፖለቲካዊ (እምነተ-አሥተዳደራዊ) ኢኮኖሚያዊ (ምጣኔ ሀብታዊ) ጥንካሬ አቅም ጽናትና ቁርጠኝነት የሌለው ከመሆኑ አንጻር እንደለመደው የቡድኑን ጥቅም በማስቀደም የሀገራችንን ጥቅም አሳልፎ ይሰጥብንና የሀገር ክህደት ይፈጽምብናል፣ የሀገሪቱን ጥቅም መቆመሪያ ያደርገዋል፣ ሀገሪቱን ለትውልድ የሚተላለፍ ችግር ላይ ይጥላታል የሚለው ሥጋቴ ከፍተኛ ስለሆነ ነበረ፡፡

“የፈሩት ይደርሳል የጠሉት ይወርሳ” ሆነና ነገሩ ምንጊዜም ምንም ነገር ቢሆን ከራሱ ጥቅም አንጻር ብቻ እንጅ ከሀገርና ሕዝብ ጥቅም አንጻር ወይም ሀገርና ሕዝብ ሊገጥማቸው የሚችለውን ችግርና አደጋ ከመከላከል አንጻር ዐይቶ የማያውቀው ማየትም የማይፈልገው የሀገር ጥቅምን የማስቀደምም የሞራል (የቅስም) አቅም ወኔ ብቃትና ቁርጠኝነት ጨርሶ የሌለው የጥፋት ቡድን ወያኔ የሀገራችንን ብሔራዊ ጥቅም ብቻ ሳይሆን ሉዓላዊነቷንም ጭምር ባስደፈረ መልኩ ታሪካዊ ክህደት በመፈጸም ውል ተፈራረመ፡፡ በዚህ ውል መፈረም የግብጽና ሱዳን ደስታ ገደብ አልነበረውም፡፡ እውነት እውነት መስሎም ሊታያቸው ካለመቻሉ የተነሣ ውሉ የሰጣቸውን ጥቅም ያህል መደሰት ጮቤ መርገጥ አቅቷቸዋል፡፡ ምክንያቱም ይህ የተፈረመው ውል ግብጽና ሱዳን እ.ኤ.አ. 1959ዓ.ም. የዐባይን ውኃ ክፍፍል ባደረጉበት ጊዜ ለግብጽ 55.5 ቢሊየን (ብልፍ) ለሱዳን ደግሞ 18.5 ቢሊየን (ብልፍ) ኪዩቢክ ሜትር ውኃ በመከፋፈል ያደረጉትን ውል ባከበረ በጠበቀ በተስማማ መልኩ የዐባይ ውኃ ሙሉ በሙሉ 100% ባለመብትና ባለቤት መሆናቸውን በማረጋገጥ ነው ወያኔ የፈረመላቸው፡፡ ለዚህ ነው የተፈረመው በዚህ በአዲሱ ውል ግብጽና ሱዳን እ.ኤ.አ. 1959ዓ.ም. ስለተፈራረሙት የቀድሞው ኢፍትሐዊ ውል በዚህ አዲስ ውል ስለ መሻሩ ወይም መተካቱ የሚገልጸው ምንም ነገር እንዳይኖር ተደርጎ የተረቀቀው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ አላወቀውም እንጅ ይህ ዜና ሁሉንም በየቤቱ መርዶ የሚያስቀምጥ ክፉ ዜና ነበር፡፡

ይሄንን ስል ውሉን ያነበባቹህ ወገኖች ሳትቀሩ “እንዴ! እንዴት ሆኖ? ውሉ ይሄንን ነው እንዴ የሚለው?” ብላቹህ ደንገጥ ማለታቹህ የሚቀር አይመስለኝም፡፡ እንዴት እንደሆነ ላስረዳ፡- ወያኔ ሱዳን ላይ ፈረምኩ የሚለው ውል “የግድቡ ተግባር” በሚለው አንቀጽ ስር እንደተገለጸው የዐባይን ግድብ ውኃ ወይም የዐባይን ወንዝ ከኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫነት በስተቀር ለመስኖም ሆነ ለሌላ ውኃን ለሚጠቀም ለሚቀንስ ለሚያጎድል ምንም ዓይነት አገልግሎት መጠቀም እንዳይችል የሚያስር ውል ላይ ነው ፊርማውን ያስቀመጠው፡፡ በዚህም መሠረት ከእንግዲህ ሀገራችን ከዐባይ ግድብም ሆነ እግዚአብሔር ከሰጣት ታላቅ ሀብቷና ጸጋዋ ከዐባይ ወንዝ ውኃ አንድ ስኒ ውኃም እንኳን ቢሆን መቅዳት መጠቀም አትችልም፡፡ ከዚህ በኋላ ሀገራችን ኢትዮጵያ ከላይ እንደገለጽኩት ሁሉ ሕጋዊ መሠረት የሌለው ቢሆንም ስለ ፍትሐዊ የውኃ ክፍፍል ጉዳይ እንዳታነሣ ታስራለች፡፡ ጥያቄውን የማንሣት መብት እንዳይኖራት ተደርጎ በብልጣብልጦቹና ዐይነ ደረቆቹ ግብጻዊያንና ሱዳናዊያን የዲፕሎማቲክ (የአቅንኦተ ግንኙነት) ቡድኖች ብቃታቸውን በሚገባ ባሳዩበት ውል ታስራለች፡፡ በውሉ ላይ በአንቀጽ 3 “ፍትሐዊ ክፍፍል” የሚል ቃል ቢሰፍርም ውሉ ፍትሐዊ ክፍፍል የሚለውን ሐሳብ የኢትዮጵያ ድርሻ ወንዙን ለኃይል ማመንጫነት መጠቀም ብቻ እንደሆነ ብልሀት ባለው ቅንብር አስፍረውታል፡፡ አንቀጽ 4 ላይ ደግሞ “ሌላውን ያለመጉዳት መርሕ” በሚለው አንቀጽ ደግሞ “በወንዙ አጠቃቀም ላይ ዓይነተኛ አደጋ አለመሆን” የሚለውን ቃል ውኃውን ለመስኖና ተመሳሳይ ተግባራት አለመጠቀም ማለት እንደሆነ በሚያስገነዝብ መልኩ ሰፍሯል፡፡ ባጠቃላይ ውሉ እንደሚያረጋግጠው የዐባይ ውኃ በዐባይ ግድብ ተገድቦ ተያዘም አልተያዘ ግብጽና ሱዳን እንደሚያምኑት ሁሉ የዐባይ ውኃ የእነሱ ብቻ መሆኑን ነው፡፡ ውሉ ይሄንን በማረጋገጡ ውኃው ለኤሌክትሪክ ማመንጫነት ብቻ ግድቡን ለመሙላት በግድቡ ታቁሮ መያዙ ግብጽንና ሱዳንን የሚያሳስብ ሆኖ አላገኙትም፡፡ ምክንያቱም ውኃው በኢትዮጵያ ግዛት በኢትዮጵያ ግድብ ውስጥ ቢሆንም አንድ ስኒ እንኳን ሳይቀነስ ኃይል አመንጭቶ ወደ እነሱው እንደሚላክ ወያኔን በፊርማው እንዲያረጋግጥ አድርገዋልና ነው፡፡ ውሉ ከዚህም አልፎ ግብጽንና ሱዳንን “ግድባችን” የሚል ቃል በመጠቀምና በግድቡ የምህንድስና ሥራ ላይ ሁሉ ማለመብት አደድርጓቸዋል፡፡

በርካታ ሰዎች ይህ የተፈረመው ውል በአሻሚና ውሎ አድሮም ለውዝግብ በሚዳርጉ ግልጽ ባልሆኑ ቃላት የተሞላ ነው ይላሉ፡፡ ነገር ግን ይምሰላቸው እንጅ ውሉን በግብጽና ሱዳን በኩል ቆሞ ለሚያየው ውሉ ምንም የሚያሻማ ነገር የሌለበት ጥርት ያለ ነው፡፡ ውሉ በአሻሚ ቃላት የተሞላ ሆኖ የሚታየው በእኛ በኩል ሆነን ስናየው ብቻ ነው፡፡ ይህ ውል ከፍተኛ የማታለል ብቃት ባላቸው ዲፕሎማቶች (አቅናኤ ግንኙነቶች) በሚገባ ታስቦበት እንደተዘጋጀ መገንዘብ ይቻላል፡፡ የውሉ መሠረታዊ የአጻጻፍ ስልት A=B=C \ A=C የሚለውን የአተካኮ (substitution) አመክንዮን (logic) መሠረት ያደረገ ነው፡፡ ወያኔ እንደደንቆሮነቱ በዚህ ስልት ወይም ቀመር የተቀናበረው ውል ምኑም አልገባው ሊገባውም አይችልም የሚያስረዳው ኖሮ አስረድተውት ቢገባውም ውሉ የሀገርን ጥቅም እንጅ ይዚህን የጥፋት የእርግማን ኃይል ቡድን ጥቅም የሚጎዳ ባለመሆኑ ግድ የለውም አይጸጸትምም፡፡

ቀድሞውንም ቢሆን ወያኔ ሥልጣን ከያዘ ማግስት 1985ዓ.ም. ጀምሮ ግብጽ ድረስ በመሔድ ምንነቱ ያልታወቀ ለሕዝብ ያልተገለጸና የተደበቀ ውል አቶ መለስ ከሆስኒ ሙባረክ ጋር ተፈራርሞ እንደነበር ይታወቃል፡፡ ከዚያም ተከትሎ “ዐባይን የማልማት የጋራ እንቅስቃሴ” (Nile basin initiative) እያለ ሲጠራው ከነበረው እንቅስቃሴ ጀምሮ ይንቀሳቀስ የነበረው በተለይ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ለአፉ “የቅኝ ግዛትን ውል አንቀበልም፣ ፍትሐዊ የውኃ ክፍፍል ያስፈልገናል” ይበል እንጅ እንቅስቃሴውን ያደርግ የነበረው ግን ልክ ያ የቅኝ ግዛት ውል ይል እንደነበረው ሁሉ ግብጽንና ሱዳንን የዐባይ ወንዝ ባለመብትና ባለቤት እንደሆኑ አድርጎ በቆጠረ ግንዛቤ እባካቹህ እኔም እንድጠቀም ፍቀዱልኝ በሚል የልመናና የልምምጥ መንፈስ ነበር ያንን ሁሉ ዓመታት በገዛ ሀብታችን ባዕዳንን ደጅ ሲጠና የቆየው፡፡ በዚህም ወያኔ እራሱ ከማዋረዱ ባሻገር ውርደቱ ለሀገራችንም ተርፏል፡፡ እነሱንም የልብ ልብ እንዲሰማቸውና ይሄንን ያህል አብጠው እንዲታበዩ  አድርጓል፡፡ ወያኔ እንዲህ እራሱንም ሀገሪቱንም ባዋረደ መልኩ ይለማመጥ የነበረው በትጥቅ ትግሉ ወቅት ግብጽ “ኢትዮጵያን በማዳከምና የተረጋጋች እንዳትሆን ማድረግ” በሚለው መርሕ መሠረት ወያኔን በከፍተኛ ደረጃ ስትረዳ ስለነበረና ወያኔም የዐባይን ውኃ በተመለከተ ለግብጽ የገባላት ቃል ስለነበረ ነው፡፡ ስለሆነም ወያኔ እጅ የሰጠውና ክህደት የፈጸመብን አሁን ሳይሆን ገና ከድሮውም ጀምሮ ነበር፡፡

ሲናገረው የነበረው ነገር ሁሉም ሲተውንብንና ሕዝብ የሱን የክፋት የክህደት የጠላትነት ተግባሩንና ማንነቱን ዐውቆበት እንዳያምፅበት ተቆርቋሪ መስሎ ለመታየት የግብጽንና የሱዳንን ስምምነት “የቅኝ ግዛት ውል ነው አልቀበልም፣ ፍትሐዊ የውኃ ክፍፍል መኖር አለበት” ምንትስ ይበል እንጅ ይህ አሁን የፈረመው ውል ከዚህ ቀደም በዚህች ሀገር ላይ ክህደት እየፈጸመ እንዳደረጋቸው በርካታ ክህደቶች ሁሉ ይህችን ሀገር መቀመቅ ለማውረድ አሲሮ እንደፈጸማቸው ክህደቶች ሁሉ ይሄንንም ውል የፈረመው ሳይገባው ሳያውቀው ቀርቶ ሳይሆን ተረድቶት አውቆት አምኖበት እንደሆነ ማረጋገጥ ይቻላል፡፡ ከዚህ ቀደም የዐባይን ወንዝ በተመለከተ ይናገራቸው የነበሩት ቃላቶች የማስመሰልና የመደለያ እንደሆነ የሚያረጋግጠው ሲለው የነበረውን ሁሉ ገደል የከተተ ውል ሰሞኑን መፈረሙ ነው፡፡ ጉዳዩ የሦስትዮሽ መሆኑና በተለይም የግብጽ ሕዝብ ምን እየተካሔደ እንደሆነ በንቃት ስለሚከታተልና በግልጽ የማወቅ ፍላጎት ስላለው የግብጽ ባለሥልጣናትም ለወደፊቱ እማኝ እንዲሆናቸው ጉዳዩን የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እንዲያውቅላቸው ስለፈለጉ ጉዳዩን መደበቅ አልተቻለም እንጅ እንደወያኔ ሐሳብና ፍላጎት ቢሆን ኖሮ ከዚህ ቀደም ከኢትዮጵያ ሕዝብ ዕይታና ይሁንታ ውጭ በድብቅ እንደፈረማቸው የክህደት ውሎች ሁሉ ይሄንንም ማንም ሳይሰማና ሳያይ በስውር ፈርሞ ቁጭ ሊል ነበር ፍላጎቱ አልሆነም እንጅ፡፡

እንደኔ እምነት አሁንም ቢሆን ማለትም ፊርማው ቢፈረምም ወያኔ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ በኃይል የተጫነ እንጅ በኢትዮጵያ ሕዝብ ይሁንታና ምርጫ ሥልጣን የያዘ አካል ባለመሆኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ ወያኔ በፈረማቸው ስምምነቶች ሁሉ የመገዛት ግዴታ አይኖርበትም፡፡ ይሄንን ማድረግ የምንችለው ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ በዚህ በተፈረመው ውል ላይ ተቃውሞውን ማሰማት የቻለ እንደሆነ ብቻ ነው፡፡ አሁን ይሄንን ማድረግ ካልቻልን ግን በውሉ እንደተስማማን ተደርጎ ተቆጥሮ ወደፊት የሚመጣው መንግሥት “ውሉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ይሁንታን ያገኘ አይደለም አልገዛበትም የሀገሬን ጥቅም አስከብራለሁ” ብሎ ለማለት እንዳይችል ያደርገዋል ወይም ይሄንን የማለት መብት ያሳጣዋል፡፡ መጪው በሕዝብ ተመርጦ ሥልጣን የሚይዘው የኢትዮጵያ መንግሥት ይሄንን የማለት መብት እንዲኖረው ማድረግ የምንችልው አሁን እኛ ይሄንን የክህደት ውል ተቃውመን የወጣን እንደሆን ብቻ ነው፡፡

ግብጽንና ሱዳንን በተመለከተ ሀገራችን ኢትዮጵያ ያለባት ግዴታ ቢኖር በሌሎች አህጉራት እንዳሉት እንደማንኛውም የላዕላይ የተፋሰስ ሀገራት ሁሉ ሰብአዊና ሞራላዊ (ቅስማዊ) እንጅ ሕጋዊ አይደለም ሊሆንም አይችልም፡፡ ሰብአዊውና ቅስማዊው ግዴታም ቢሆን የራስን ጥቅም ለአደጋ ባልዳረገ መልኩ እንጅ የራስን ጥቅም ለአደጋ ከመዳረግም አልፎ ሙሉ ለሙሉ 100% አሳልፎ እስከመስጠት አይደለም፡፡ “ፍትሐዊ የውኃ ክፍፍል” የሚለው ቃል ራሱ ትክክለኛ ያልሆነና ሱዳንና ግብጽ በእ.ኤ.አ. 1959ዓ.ም. እንዳደረጉት ውል ሁሉ የግብጽንና የሱዳንን ባለመብትነት ያከበረ የተቀበለ ቃል ነው፡፡ እየተጠቀሰ ያለውም በእኛ ላይ ብቻ ነው፡፡ በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጫና ኢፍትሐዊ በሆነ መንገድ ክፍፍሉት ተቀበሉ ከተባለም ሀገራችን ለዐባይ ውኃ የምታበረክተው 86% በመሆኑ በቀረው 14% የነጭ ዐባይ መጠንም የባሮ ወንዝ ድርሻ ያለው በመሆኑና በቀጥታ አይሁን እንጅ መሬት ውስጥ በመስረግ የኦሞ፣ የማጎ፣ የጎጀብ፣ የጊቤ ወንዞችም ድርሻ ያላቸው በመሆኑ ከዚህ ግዙፍ አስተዋጽኦዋ አኳያ የውኃው ክፍፍል ፍትሐዊ የሚሆነው ምን ያህሉ ድርሻ የኢትዮጵያ ቢሆን ነው ክፍፍሉ ፍትሐዊ የሚሆነው የሚለውምው ነገር መጤን ያለበት ዐቢይ ጉዳይ ነው፡፡

እንደኔ እንደኔ ግን በዐባይ ወንዝ ጉዳይ ላይ በሌሎች አህጉራት እንዳሉት እንደ ሌሎቹ የላዕላይ ተፋሰስ ሀገራት ሁሉ ነገሩን ከሰብአዊነትና ከሞራል አንጻር ዕያየን በመተሳሰብ እያስተናገድን በመቀጠል ምንም ዓይነት ውል ላለመፈራረም የጸና አቋም መያዝ አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆን አለበት ባይ ነኝ፡፡ ምክንያቱም “መፈራረም መዋዋል” የሚባለው ጉዳይ እንደምናስበው ቀላል ያልሆነ ከጥቅም አንጻር ብቻ ሳይሆን ብዙ እጅግ የተወሳሰበና የሉዓላዊነት የነጻነትም ጉዳይ ያለበት ውስብስብ ጉዳይ ነውና፡፡ ይህ ወያኔ የፈጸመብን ክህደት በዓለም ታሪክ የማንም ሀገር ምንግሥት አድርጎት አያውቅም ወያኔ የመጀመሪያው ነው፡፡ ከወያኔ ባለሥልጣናት አንደበት እንደሰማቹህት አሁን ወያኔ ከዚህ ውል አገኘው እያለን ያለው ጥቅም ልክ ውኃው የሚፈሰው ከግብጽ ወደ ኢትዮጵያ ይመስል ለሰማው ሁሉ እጅግ አሳፋሪ በሆነ መልኩ “ግብጽ ውኃውን እንድንጠቀም ፈቀደች፣ በውኃው የመጠቀም መብት እንዳለን እውቅና ሰጠች፣ የዐባይ ግድብ እንዲሠራ ፈቀደች ተስማማች” በማለት ነው ነገር ግን “የመጠቀም” እያለ የሚገልጸው መብት የመብራት ኃይልን ለማመንጫነት ብቻ እንደሆነ በፍጹም ሊገልጽ አልፈለገም፡፡

ግብጽና ሱዳን ጉዳዩን እንደራሳቸው አድርገው ሊያዩት ይገባል፡፡ በሰው እጅ ያለን ንብረት የራሴ ነው ብሎ ማፍጠጥ ዐይን ያወጣ ሌብነት ነው፡፡ ሱዳንን እንደ ነዳጅ ዘይቷ አድርጋ እንድታየው ሊነገራት ይገባል፡፡ ሱዳን የነዳጅ ዘይትም እንደ ዓባይ ውኃ ሁሉ የተፈጥሮ ሀብት ነው ብላ በነጻ ስትሰጥ ስታድል አላየንም፡፡ ግብጽም ብትሆን የዐባይን ውኃ ለመካከለኛው ምሥራቅ ሀገራት በቧንቧ በማስተላለፍ ለመሸጥ ፕሮጀክት (የሥራ አቅድ) ነድፋ ስትንቀሳቀስ ውኃ የተፈጥሮ ሀብት ነው እኔም ያገኘሁት በነጻ ነውና በነጻ እንዳገኘሁት ሁሉ ውኃ ለቸገራቸው የመካከለኛው ምሥራቅ ሀገራት በነጻ ልስጥ አላለችም፡፡

እንግዲህ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ! ካለህ ወያኔ እንደሚመለከትህም ተንቀሳቃሽ ሬሳ ካልሆንክና ነፍስህ ካለ ሀገሬ የምትል ከሆነ ዛሬ ነገ ሳትል ይሄንን የተፈጸመብህን ከፍተኛ ክህደት በኃይለኛ ንዴትና ቁጣ በመቃወም ወያኔ የፈረመው ውል አንተን እንደማይገዛ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በማሳወቅ በማረጋገጥ ከልዑል እግዚአብሔር የተሰጠህን የታላቁን ወንዝ የግዮንን የባለቤትነት መብት መልሰህ በእጅህ እንድታስገባ ሀገር አጥብቃ ትጠይቃለች፡፡ በሀገር ውስጥና ውጭ ያላቹህ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ሕዝባዊ ማኅበራትና የሃይማኖት ተቋማት እንደሕዝብ አካልነታቹህ ይሄንን ሕዝባዊ ተቃውሞ በማስተባበርና በተሳካ ሁኔታ ተፈጻሚ በማድረግ የሚጠበቅባቹህን ታሪካዊ ኃላፊነት እንድትወጡ እንደ አንድ ዜጋ አሳስባለሁ፡፡

ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!! ወያኔ ይውደም!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገብረኪዳን አርጋው፡፡

satenaw

**ድንቄም ምርጫ** – ነብሮ

ፍትሕ በተረገጠበትና የዴሞክራሲታዊ ሥርዓት በኃይል በታፈነበት አገር ሕዝብ መሪውን መምረጥ አይችልም።

              EPRDF Election1የምርጫ ጉዳይ ሲነሳ ወደ ኋላ ሄደን የዘመነ ኃይለሥላሴን፤የደርግን የምርጫ ሂደቶች ብናስብ ከዚህ በሰለጠነው ዓለም ከሚካሄደው ምርጫ ጋር በምንም ሁኔታ ሊመሳሰል እንደማይችል ሁላችንም ግልጽ የምንሆን ይመስለኛል።አድሎአዊና ሕዝብን ያላሳተፈ የገዥው መደብ የሚፈልጋቸውን እጩዎች መልምሎ በማቅረብ ሕዝቡን አስገድዶ እንዲመርጣቸው ማድረግ አይነተኛ ባሕሪው መሆኑን መጠራጠር አይኖርብንም።

የባሰ አለ እንዲሉ ከአንድ መንደር የተሰባሰቡና በዘረኝነት በሽታ የተመረዙት (ጎሰኞች) የአሁኖቹ ገዥዎቻችን ከ1997 ምርጫ በፊት ከምርጫው በፊትና በምርጫ ወቅት ሲፈጸም የነበረውን ሤራ በሚገባ የማውቀው ሲሆን የተቃዋሚ ኃይሎች(ድርጅቶች)ውስብስቡን የካድሬ መሰናክል አልፈው በፓርላማው ውስጥ ጥቂት አባሎቻቸውን በፓርላማ ውስጥ እንዲገቡ ያደርጉ ነበር።በፓርላማው ውስጥ ሃሳባቸውን የመግለጽና የማራመድ እድላቸው የጠበበ ቢሆንም የፓርላማውን ውሳኔ የሚነቅፍ የተቃውሞ ድምጽና የተአቅቦ ድምጽ ማስቆጠር ችለው ነበር።ከ1997 ምርጫ በኋላ ግን ዘረኝነት መራሹ ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ(ህወሃት)ከኢትዮጵያ ሕዝብ ተነጥሎ እንደቆመ ተንሳፎ የሚገኝ መሆኑን ሕዝብ በምርጫ ካርዱ ፍርዱን ሲሰጥ የበረገገው ገዥ ቡድን ረጅም እጁን የምርጫ ኮሮጆ ዘረፋ ውስጥ አስገባ ያልተመረጠውን ተመርጫለሁ አለ።ሰርቀሃል ድምጻችን መልስ ሲባል ደግሞ ግድያ፤እስራት፤ስብሰባ መከልከል፤ሰላማዊ ሰልፍ የማይደረግ መሆኑን አወጀ በግብርም ውሎ አየነው።ከዚያ በኋላ የዚህን ትውልድ አምክን ዘረኛ አገዛዝ እድሜ ለማስረዘም የደህንነት፤የመከላከያ፤የፖሊስና የልዩ ፖሊስ የክልል ፈጥኖ ደራሽ፤የካድሬው መዋቅር ትኩረት ተሰጥቶ እንዲጠናከር ተደረገ።አፈናው ግድያው ተስፋፍቶ ኢትዮጵያውያን በየጎዳናው ወድቀው የሚገኙበት ሁኔታ ተፈጠረ።

woyaneይህ የምታዩት የህወሃት መለያ ሲሆን ከብጫው ላይ የተቀመጠው ዓርማ የጀርመን ናዚ ልዩ ምልክት የነበረ ሲሆን ዛሬ ኢትዮጵያውያን ህወሃትን ሲያነሱ የጀርመን ናዚን የጀርመን ናዚን ሲያነሱ ህወሃትን የሚያስታውሱበት ምክንያት ህወሃትና የጀርመን ናዚ በቆዳ ቀለም ቢለያዩም በተግባር አንድ ናቸው ብለው ስለሚያምኑ ነው። እኔ የዚህ ጹሑፍ አቅራቢም ህወሃትን ከጣሊያንና ጀርመን ፋሽስቶች ለይቸ አይደለም የምመለከተው።ለዚህ ጹሑፌ መነሻ የሆነኝ የፊታችን ግንቦት ለሚካሄደው ብሔራዊ ምርጫ የህወሃትን ሥርአት በሰላማዊ መንገድ ታግለን በምርጫ አቸንፈን ሥልጣን እንጨብጣለን ብለው በተነሱ ኃይሎች ላይ የህወሃት የምርጫ ቦርድ የፈጸመውን አሳፋሪ ድርጊት ተመልክቸ ሲሆን በምንም አይነት መስፈርያ ይሁን የተቃዋሚ ኃይሎች ለምርጫ ውድድር የሚያቀርቡትን እጩ ራሳቸው ወስነው ያቀርባሉ እንጅ የምርጫ ቦርድ ይህ ይመረጥ ይኸኛው አይመረጥ ብሎ የመወሰን ሞራሉም ሆነ ብቃት የለውም።ለዚያውም በእጣ! የምርጫ ኮሮጆ ገልብጦ ያልተመረጠውንና ሕዝብ አንቅሮ የተፈውን ተመርጠሃል ሕዝብ ይሆነኛል ያለውን በምርጫ ያቸነፈውን አልተመረጥክም ብሎ የሚቀጥፍ የአንድ ሥርአት አገልጋይና ተቋም አምኖ ምን አይነት ምርጫ እንደሚካሄድ ከወዲሁ መተንበዩ ነብይ የሚያሰኝ አይደለም።ለሥርአቱ አስጊ የሆኑ የተቃዋሚ ድርጅቶችን አንድነትና መኢአድን በኃይል አፍርሶ የየድርጅችን ንብረት ዘርፎ በሌሎቹ የተቃዋሚ ኃይሎች ጉያም ለመግባት ረጅሙን ዘራፊ እጁን ለማስገባት እያሴረ ያለው ህወሃትና ጉዳይ አስፈጻሚው የምርጫ ቦርድ ሕገ-መንግሥቱን እየናዱ መሆኑን ሊያጤኑ ይገባቸዋል።

ህወሃት መሠረታዊ ችግሩ ድህነት ከሆነ በትግራይ ሕዝብም ይህ ችግር እንደ ዋነኛ ተደርጎ ከተወሰደ ሌሎችስ ብሎ ማሰብ የሚችል ተፈጥሮ በህወሃት ቤት እንዳማይኖር ቢታወቅም በትግራይ ለተፈጠረው የኢኮኖሚ መዳከምም ሆነ የንዋይ ጥማት የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚጠየቅበት አንዳችም ምክንያት ሊኖር አይገባውም የህወሃት መራሹ ቡድን በፈጠራ ውሸት የቆጥ የባጡን በመቀባጠር የሕዝብ እልቂት እንዲፈጠር በማድረግ በውንድብድና የካሄደው ዘረፋ፤ዜጎችን በተለይም ምሁሩንና አምራቹን ኃይል ከሀገር መንቀልና የመራሹ ቡድን እንባ ጠባቂዎችና ቤተሰቦች አገሪቱን ተስፋፍተው እንዲይዙና ሌላው ዜጋ በዘመናዊ ባርነት መቀጠል ወይም በሌሎች ላይ የደረሰው ጽዋ ሞልቶ እንዲፈስበት ማድረጉ የሚያስከትለውን መዘዝ መገንዘብ ባለመቻል የተፈፀመ ስለሆነ የዛሬው እዩኝ እዩኝ ነገ ሸሽጉኝ ሸሽጉኝን እንደሚያስከትል በድፍረት መናገር ይቻላል።

በአንድ ወቅት የህወሃቱ ፊታውራሪ ስብሃት ነጋ ከጋዜጠኛ ለቀረበለት ጥያቄ ሲመልስ፡) እንዲህ ብሎ ነበር-ጋዜጠኛ አቶ ስብሃት ድሮ የሃብታምና የባለሥልጣን ልጅ ነበር ስኮላር ሽፕና የውጭ ትምህርት እድል ያገኝ የነበረው ዛሬ ደግሞ የእናንተ ልጆች የሚማሩት ወደ ውጭ አገር ሄደው ነው ሲባል(፡ አቶ ስብሃት ታዲያ እነሱ ያደረጉትን እኛ ብናደርገው ነውሩ ከምኑ ላይ ነው ብሎ ነበር በአራት ነጥብ የዘጋው።እንግዲህ ህወሃት እንዲህ ያሉትን ውዳቂዎችንና ፀረ-ሕዝቦችን አቅፎ ነው ኢትዮጵያን በኃይል አንበርክከን እንገዛታለን ካልሆነልን ደግሞ እናፈራርሳታልን የሚሉን።ከዚህ ወዲያ እብደት የለም እንዲህ ያሉት እብዶች የተሰባሰቡበት ህወሃት ነው ዛሬ በትረ ሥልጣኑን ጨብጦ እየገዛ ያለው።

አንዱ በአንዱ ላይ እምነት እንዳያሳድርና በጥርጣሬ እንዲተያይ ጦርነት ውስጥ እንዲገባ፤አንተ የዚህ አንተኛው ደግሞ የዚህኛው ዘር ነህ በማለት በዘር በማናከስ የሕዝብ ሰላም እንዲደፈርስ ያደረገው ህወሃት ነው። ሰሞኑን ደግሞ አንድ አስገራሚ ድርጊት ተፈፀመ ይህኸውም(ጥቂት ህወሃት የመለመላቸው የቅማንት  ተወላጆች ) በአማራ ገዥ መደብ እስከ ዛሬ ተገዝተናል አሁን በቃን ጐንደር የቅማንት አገር ስለሆነ ራሳችን በራሳችን ለማስተዳደር እንድንችል የራስ ገዝ አስተዳደር ይገባናል በሚል ሲንቀሳቀሱ ቆይተው አሁን የነአቶ በረከትና አዲሱ ለገሠን ይሁንታ አግኝተው ያልተጻፈ የታሪክ ድሪቶ አንግበው በደምና በስጋ የተቀላቀላቸው ወገናቸው ጋር ደም የሚያፋሥስ መንገድ መጀመራቸው ቀልጥፈው ተግባራቸው እኩይ ተግባር መሆኑን አውቀው እንዲያቆሙት ለማስገንዘብ ነው ይህን ጹሑፍ ያዘጋጀሁት። በዚህ ተግባር ግንባር ቀደም ሆነው የሚያራምዱትን በአካል ስለማውቃቸውም ጭምር ወንድማዊ ምክሬን ሊሰሙ እንደሚችሉ በማመን ነው። ህወሃትና የአማራውን ህዝብ ጋንጃ እየመታ የሚገኘውን ብ.አ.ዴ.ንን አምኖ ወደዚህ አጣብቂኝ ጉዳይ መግባት በፍጹም ስህተት ነው።የቅማንት ተወላጅ ለህወሃት የምርጫ ፍጆታ መዋል የለበትም፦የህወሃት ሥርዓትና የሥርአቱ አራማጆች መቀበሪያቸውን ቆፍረው ከመቃብር አፋፍ ላይ በሚገኙበት ወቅት መልካም ታሪክን ማጉደፍ አይገባም።ይህ ስርዓት ወዳቂ ነው በሀገር ጥፋትና እጁን በደም የነከረ ሁሉ በሰፈረው እንደሚሰፈርም ግልጽ ነው።ነገ የዛሬዎቹ ዳኞችና እኛ ፊት ለፊት እንገናኛለን፤ ነገ እኛና ይህወሃት ካድሬ እንገናኛለን፤ነገ የምርጫ ቦርድና እኛ እንገናኛለን፤ነገ የፌደራል ፖሊስና እኛ እንገናኛለን፤ነገ እኛና ፖሊስ እንገናኛለን፤ነገ የአጋዚ ሠራዊትና እኛ እንገናኛለን፤ነገ እኛና የክልል ፈጥኖ ደራሽ እንገናኛለን፤ለዘመናዊ ባርነት ወደ ዐረብ አገር የተላኩ እምቦቃቅላ ሴትና ወንድ ወጣቶችን መዝግበናል፤አገር ጥለው እንዲወጡ የተገደዱ ሙራንና ጋዜጠኞችን ዝርዝር ይዘናል፤ወህኒ ቤት ወርደው ሌትና ቀን እንደ እባብ እየተቀጠቀጡ የሚገኙትን ወጣት ጋዜጠኞችና የፖለቲካ ድርጅት አመራሮችን እናውቃቸዋለን፤በመላ ኢትዮጵያ የመኖርና ሠርቶ የመብላት መብት የተነፈገው ዘሩ በመድሃኒት እንዲመክን የተደረገውን የአማራ ነገድ ሕዝብ ጉዳይ በሚገባ ተመዝግቦ እንዲቀመጥ ተደርጓል፤ከወሎና ጎንደር ተነጥቆ ወደ ትግራይ የሄደውን መሬት በሚገባ እናውቀዋለን ይህን ሁሉ ህወሃትና መንገድ መሪዎቹ የሚከፍሉት እዳ እንደሆነ ሊያውቁት ይገባል። በዚህ አጋጣሚ አቶ በየነ አስማረና አበበ ንጋቱን አመስግኘ ማለፍ እወዳለሁ።« በወደቀ ግንድ ምሳር ይበዛበታል እንዲሉ » ጣሊያን ጎንደር ሲገባ የተጠቀመበትን ፕሮፓጋንዳ ያነገበው የህወሃት ቡድን ኢትዮጵያን ለመበታተን ሲል የሚያራምደውን የጎሳ ፖለቲካ የተጋቱ አውቆ አጥፊ የቅማንት ተወላጆችንና ሌሎች የተለያዩ በአማራው ነገድ ህዝብ ክልል የሚኖሩ ጎሳዎችን በማነሳሳት በጎሳ መራሹ ቡድን ጣቱን የቀሰረውን ሕዝብ አስተሳሰብና አመለካከት አቅጣጫውን እንዲስት ለማድረግ የሚጠቀምበትን ሕዝብን በሕዝብ የማናከስ ሤራ እያራመዱ ይገኛሉ።

24 ዓመት በመድፈን ላይ የሚገኘው የህወሃት አገዛዝ በሚያካሂዳቸው ምርጫዎች አንድም ቀን ፍትሃዊነት ያልታየበትና የተጭበረበረ መሆኑ እንዳለ ሆኖ በምርጫ ወቅት ለሕዝብ የሚገባቸውን ቃሎች ከመካዱ አልፎ በተቃራኒው እንደሚተገብራቸው ይታወቃል።የዘንድሮ ደግሞ በጣም የለየለትና አውሬነቱን በግልጽ የሳየበት ሁኔታ ላይ ደርሷል ሁላችንም የምግባባበት አንድ መሠረታዊ ጉዳይ ህወሃት ለአፍታም ቢሆን ሥልጣን ከእጁ ካፈተለከ የሚደርስበትንና የሚከፍለውን ዋጋ ስለሚያውቅ በሰላማዊ መንገድ ሥልጣን ያስረክባል ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው። ዋናው አነጋጋሪ ጉዳይ ሕዝብ ካለፈው ተመክሮ የማያገኘውና አልመርጥም የማይልበት ምክንያት ምንድን ነው የሚለው ይሆናል።የሚያሰድድን፤የሚገድልን፤አስሮ የሚያሰቃይን፤ዘር በማጥፋት ላይ የተሰማራን ነብሰ-ገዳይ ቡድንን መርጦ በሥልጣን ላይ ማስቀመጥ አገርን ከመገደል የከፋ ወንጀል ነው።ስለዚህ ሕዝቡ የዘንድሮውን ምርጫ በእምብይታ ሊያስተናግደው ይገባል።

ነብሮ ነኝ ከሰ/አሜሪካ

Zehabesha.com

በየመን ኢትዮጵያውያኖች በጭንቅ ላይ ናቸው

ISIS_organs

ግሩም ተ/ሀይማኖት (ከየመን)
ረቡዕ ሌሊት 8፡30 ላይ የተጀመረው የአየር ድብደባ አሁንም እንደቀጠለ ነው፡፡ የመን ነዋሪ የሆነ ሁሉ በፍርሃት ርዷል፡፡ በተለይ በትላንትናው ሌሊት የነበረው የአየር ድብደባ ከፍተኛ ስለሆነ ህዝቡ ላይ የጣለው ፍርሃት ከወትሮው የተለየ ነው፡፡ “በሁቲይን አማጽያን ሚሊሻ ላይ የተጀመረው የአየርጥቃት አሁንም በድርድሩ ካልተስማሙ ወይ ሰነዓ ከተማን ለቀው እስካወጡ አያቆምም!” ሲሉ የሳዑዲ አረቢያ ንጉስ ሰልማን ቢን አብድልአዚዝ ገልጸዋል፡፡ ይህን አባባላቸውን ተከትሎ እግረኛ ሰራዊትም ሊንቀሳቀስ መሆኑ እየተገለጸ ነው፡፡ 20.000 እግረኛ ወታደር ተዘጋጅቶ ድንበር ላይ መሆኑን የየመን መገናኛ ብዙሀን እየዘገቡ ነው፡፡ ከዚያ በፊት ተጀምሮ የነበረውን ድርድር እንዲቀበሉ ለሁቲይን አማጺዎች ከትላንት ወዲያ የ3 ቀን እድሜ ቢሰጣቸውም አልተቀበሉትም፡፡
በሳዑዲ ሰብሳቢነት የአረብ ሊግ ሀገራት መንግስታት በየመን ጉዳይ ለመመከር ግብጽ ሻርማ ሸኸ ተሰብስበው ነው ያሉት። በዚህ ስብሰባ ላይ የአየር ጥቃቱ የዘመቻ መሪ ሀገር የሳዑዲ አረቢ ንጉስ ሰልማን ሀቲይን የተባሉት አማጽያን ለቀው እስኪወጡና የመን እስክትረጋጋ ድረስ የተጀመረው ጥቃት ቀጣይ እንደሆነ ገልጸዋል በማለት የየመኑ ቶውራ ጋዜጣ ዘግቧል፡፡ በዚህ ስብሰባ ላይ የየመኑ መሪ አብድረቡ መንሱር ሀዴ ተገኝተዋል፡፡ ህዝቡ ግን ሀገራችንን እያስደበደበ ያለው ፕሬዘዳንታችን ነው በማለት ጥስ እየነከሰባቸው ነው፡፡ የቀድሞው ፕሬዘዳንት አሊ አብደላ ሳላ ድርድሩን እንደሚቀበሉ ቢገልጹም ተቀባይነት ያገኙ አይመስልም፡፡
ዛሬ ሌሊት በሳውዲ የተመራው የአስሩ ሀገራት ህብረት ጦር በሰንዓ ፈጂ አጣን የተባለው ቦታ ጋራ ላይ የሚገኘው ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ ያለ የብላስቲክ ሚሳየል ክምችት ማውደሙ ታውቋል፡፡ ይህ የመሳሪያ ክምችት በተመታበት ወቅት መላ ከተማው የተርገደገደበት የመሬት መንቀጥቀጥ አይነት ሁኔታ ነበር፡፡ አንዳንድ ህንጻዎች መስታዎታቸው ሁሉ ርግፏል፡፡ ነዋሪው ሲነጋ እንቅልፍ አጥቶ መደሩ ዋነኛው ርዕስ ነበር፡፡ በተለይ ስደተኛ ኢትዮጵያዊን ከፍተኛ ፍርሃት ተውጠን እንዳለን በርካታ ያናገርኳቸው ወገኖቼ ገልጸውልኛል፡፡ በእርግጥ ሌላውስ ወገን የመን ያሉ ኢትዮጵያዊያንን እንዴት እያሰባቸው ይሆን?
የተመታው ካምፕ ላይ የሚቃጠለው መሳሪያ ፍንዳታም ከፍተኛ ነበር፡፡ ከሌሊቱ 8፡20 ጀምሮ ጠዋት ድረስ እሳቱን ለማጥፋት ርብርብ ነበር፡፡ የሁቲይን አማጺያን ድብደባውን በዝምታ እያዩት አይደለም፡፡ ከየአቅጣጫው በአየር መቃወሚያ ምላሽ ይሰጣሉ፡፡ እንደ አባባላቸው ከሆነ የአየር ጥቃቱን ከሚያደርሱት ጀቶች እስካሁን ሁለት መምታታቸውን ተናግረዋል፡፡ በዛሬው ሌሊት ሰነዓ ላይ ድብደባው ቀነስ ቢልም ሁዴዳና ሌሎች ደቡባዊ የመን ላይ ጠንከር ያለ እንደነበር መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ሁቲይኖቹም ከየአቅጣጫው የሚደረገውን ጥቃት ለመከላከል ሙከራቸው በዛሬው ሌሊት ቀንሶ ታይቷል፡፡ ሰነዓ ያለ ኢትዮጵያዊ በጭንቅ ውስጥ ሲሆን አደን የተባለው ሁለተኛ ከተማ ውስጥ ያሉ ኢትዮጵያዊን በከፍተኛ ሁኔታ እያነቡ ነው፡፡