ዩቶፒያ ኢትዮጵያ (መስፍን ማሞ ተሰማ)

“ብዙ ህልም ባለበት ዘንድ እንዲሁም ብዙ ቃል ባለበት ሥፍራ በዚያ ብዙ ከንቱ ነገር አለ።” መፅሐፈ መክብብ ምዕ፤ 5 ቁ፤ 7

**************************************

ቀባሪው የነገ ሞቱን በሟች ሞት እያየው፤ ዛሬን ሞቶ ባያድርም ሟችን ቀብሮት አሟሟቱንም አይቶታልና – ለዚህ ነበር እኒያ “አያልቅባቸው” አብናቶቻችን “አሟሟቴን አሳምረው” ማለታቸው። በሞታቸው ቋሚው እረፍት እንዳይነሳቸው፤ ሠላም እንዲሰጣቸው። ‘ኖረና ተሞተ’ን እንዳይተርትባቸው . . . አላስ! . . . ኦሮማይ!

እነሆ በዩቶፒያ ኢትዮጵያ ግና ‘ኖረና ተሞተ’ ተረት ሳይሆን ዕለት ተዕለት ዓመት ተዓመት ‘ለልማታዊው መንግሥት’ የሚከፈል ግብር ሆኗል። የምናብ ዓለሟን – ዩቶፒያ ኢትዮጵያ – የገነባው የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር ገዢ በበኩሉ ‘ሁሉ በእጄ ሁሉ በደጄ ሆኗል ፤ አሥራ አንድ በመቶ ሮኬታዊ ዕድገት ተመዝግቧል፤ ያለ ወደብ ማደግ መመንደግ ሲቻል ወደባችን ይመለስ እያላችሁ የቁራ ጩኸት አታብዙ፤ ሀብቱን በመቶ ሳይሆን በሚሊዮን የሚቆጥር ገበሬ ተፈጥሯል ፤ የንግድ መነሻ ካፒታል የፈለገ ሠፌዱን ይዞ ወርቅ ካለበት ሄዶ ማፈስ ይችላል፤ ኢኮኖሚያችን አስተማማኝ በመሆኑ እርዳታ ለጋሾች ሳይቀሩ ከኢትዮጵያ ላይ የርጥባን እጃቸውን ሰብስበዋል፤ በሀገረ ኢትዮጵያ በፖለቲካ አመለካከቱ የተነሳ ወህኒ የወረደ እስረኛ የለንም፤ በምድረ ኢትዮጵያ በብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች አንድነት ፤ ፍቅርና እኩልነት ላይ የተገነባ ፌዴራሊዝም መስርተናል፤ እና ወዘተርፈዎችንም ሁሉ ይላል።

ቅዠትና ዕውነት በዩቶፒያ ኢትዮጵያ ተደባልቀዋል። ዕውነቱ ቅዠት ሲባል ቅዠቱ ዕውነት ሆኗል። ሚሊዮን ወሚሊዮናት ሲራቡ ጥቂቶች ቁንጣን ያቁነጠንጣቸዋል። አእላፍ ታዛ ሲያጡ ጥቂቶች በፈጠሩዋት ዩቶፒያ ኢትዮጵያ በተንጣለለ ቪላ በተንቆጠቆጠ ‘ማንሽን’ ውስጥ ይኖራሉ። ባይሆንማ ኖሮ በዩቶፒያዋ ኢትዮጵያ እኒያ ሁሉ ግፉዐን በቆሼ ሱናሚ ታፍነው አያልቁም ነበር። ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የህወሃት/ኢህአዴጓ ዩቶፒያ ኢትዮጵያ ተምሳሌ ናት፤ መስተዋት። በዕውኗ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የህይወት መናኸሪያ ተምሳሌ። የቆሼ ተምሳሌነቱ በድፍን ኢትዮጵያ ውስጥ ቢሆንም ቅሉ በተለይ እና በአስከፊ መልኩ ግን በትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር አፈሙዝ በምርኮ የወደቀው ህዝብ ህይወት ገፅታ ይንፀባረቅበታልና ወይንም ተንፀባርቆበታልና። (ፎቶው በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የቆሼ ነዋሪዎች መኖሪያ ሰፈር ነው፤ ወይም ነበር)

እነሆ ደግሞ ቀጣዩ በዩቶፒያ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩት ዘመነኞች መኖሪያ እንጂ በሆሊ ዉድ ፊልሞች ወይም ለትንግርት የሚታዮት የናጠጡ ቢሊየነሮች መኖሪያ አይደለም፤ የሚገኘውም በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍል ከተማ መሆኑን ልብ ይሏል። በአንድ ክፍለ ከተማ የሁለት ዓለም ነዋሪዎች ገፅታ !! * (ፎቶ 1)

እነሆ በዕውኗ አትዮጵያ ውስጥ የግፍና የሥቃዩ፤ የድህነቱና የዘር መድልዖው፤ የእስሩና የቶርቹ ፤ የምዝበራውና የፍንገላው ፤ የእናቶች ዋይታና የወጣቶች ሰቆቃ ጠርዙና ገደቡ ለፅሁፍም ሆነ ለስሚ ወይም ለንግግር ወደማይቻልበት ደረጃ ተሸጋግሯል። በተለይ በማዕከላዊ እስር ቤት ከአራቱም ማዕዘናት በታፈኑ ኢትዮጵያውያን ላይ እየደረሰ ያለው የበደል የሥቃይና የግፍ ጣራ ሰው የመሆንን ተፈጥሯዊ መለኪያዎች ሁሉ የጣሰ በመሆኑ አንደበትን ከፍቶ ለመግለፅ እንኳን አልተቻለም። ለዩቶፒያ ኢትዮጵያ ገዢዎች ግና ይህ ሁሉ የህልውናቸው ዘፈን ፤ የግዛት ዘመናቸው ግብር ፤ የጀግንነታቸው ኒሻን መሆኑ እንጂ ሌላ ትርጉም አይሰጣቸውም።

የዩቶፒያ ኢትዮጵያ አጋፋሪው የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር (ህወሃት) ስብሰብ ሰው ከመሆን የሰብዕና ተፈጥሮ መለኪያዎች ጠቅልሎ የወጣ የሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ያፈራቸው ሰዋዊ አውሬዎች ስብስብ ነው። የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር (ህወሃት) ባለሟሎች በዋናነት የተገኙትም – ከአማራው አብራክ የብሄረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን)፤ ከኦሮሞው አብራክ  የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ)፤ ከደቡብ ብሄረሰቦች አብራክ የደቡብ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ደህዴግ) – ሲሆኑ እነሆ አጋፋሪያቸው ሲያስነጥስ እነርሱን እያሳላቸው፤ አጋፋሪያቸው ሆዱን ሲቆርጠው እነርሱን እያስቀመጣቸው፤ አጋፋሪያቸው ሲያዛጋ ከያብራካቸው የወጡትን ወጣቶች ግብር እያቀረቡ … ይኸው የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር (ህወሃት) ምሶሶ ሆነውና እንኮኮ ተሸክመውት ሩብ ምዕተ ዓመት አኑረውታል። በኢትዮጵያ ውስጥ ለተፈጠረው እልቂት ፤ ግፍ ፤ ሰቆቃ ፤ ቶርች ፤ የዘር ማፅዳት ፤ የሀገር ንብረት ዘረፋ እና ወዘተርፈዎች ሁሉ እኒህ የህወሃት ሎሌዎች ከህወሃት እኩል ተጠያቂዎች ናቸው። የቆሼው ዕልቂትም የህወሃትና የባለሟሉቹ ውጤት ነው።

በዚያ ቀነ ጎደሎ – ቅዳሜ መጋቢት 2 ፤ 2009 ዓ/ም ሌሊት – (መቼም ቢሆን ባለፈው ሩብ ምዕተ ዓመት ለኢትዪጵያውያን ሞልቶ አያውቅም) በዚያ የቆሼ ናዳ ታፍነው በሲቃ ያለቁትን ህፃናት፤ እናቶች፤ አረጋውያንና ወጣቶች ጣዕር እንደው ለሚሊ ሰከንድ እንኳ ሰቆቃውን በእዝነ ህሊና ለማየት የሚቻል ከሆነ እነሆ አንባቢ ሆይ ይህንን ታደርግ ዘንዳ እጠይቅኻለሁ……..አፍህን ግጠም አፍንጫህንም በሁለት ጣቶችህ ግጥም አድርገህ ያዝ እና ቆይ ……. ለምን ያህል ሰከንድ ቆየህ? ምን ተሰማህ? ልብህ ከደረትህ ልትፈነቀል ስትንደፋደፍ  ደምህ ወዳናትህ ሲምዘገዘገ አልተሰማህም? ጭንቅ ጥብብ አላለህም? እንግዲህ በዚያ ድቅድቅ ጨለማ እንደጨለማ የጠቆረ ቆሼ አፍኗቸው መሪር በሆነ ሲቃና ጣዕር ታፍነው ያለቁትን ወገኖቻችንን ሞት እንደምን “ሞት” የሚለው ቃል  ሊገልፅላቸው ይችላል?! አዎ ቀደምቶቻችንን መስማት ካቆምንና ታሪካቸውን ክደን ማዋረድ ከጀመርን አምስት አሥርታትን አስቆጠርንና አንጂ እነሱስ “አሟሟቴን አሳምረው” ብለው ነበር። ደግሞም እስከዛሬ ምሥጢሩ ያልሰረፀብንን ዘመን አይሽሬ ፍልስፍና እንዲህ በማለት አስተምረውን ነበር – እናት አባት ቢሞት በሀገር ይለቀሳል / እህት ወንድም ቢሞት በሀገር ይለቀሳል / ሀገር የሞተ’ለት ወዴት ይደረሳል?! – ለመሆኑ ያለ ምክንያት ይሆን እንዴ የተረቱት? “ኖረና ተሞት” መባሉስ ምሥጢሩ እስከምን ገብቶናል? ለመሆኑ እኛ ኢትዮጵያውያን (በተለይም በዚህ ዘመን) ኖረን እምንሞተው መቼ ነው?!

ዕውነት ነው የዕውኗ ኢትዮጵያውያን “ከሞቱት በላይ ከቆሙት በታች” (አበው እንዳሉት) ሆነን መኖር የጀመርነው በተለይና በዋናነት ዩቶፒያ ኢትዮጵያ ከተመሰረተችበት ዘመን አንስቶ ነው ፤ 1983 ዓ/ም። እነሆ ባሳለፍናቸው ሁለት ዓሥርታት ተኩል ቆሼ በህወሃት/ኢህአዴግ ዘመነ አገዛዝ የምንገኝበትን አኗኗራችንን እና አሟሟታችንን ማሳያ ሐውልታችን ሆኗልና ከቶም ሌላ ምሳሌ አናነሳም።  ቆሼ ለታሪክ ነጋሪ ካበቃቻቸው አንዱ አሸናፊ እንዳለ የተባለ ወጣት ነው። እርሱ ያንን የቆሼን የሰቆቃ ህይወት ኖሮታል ፤ የቆሼን ቁጣ ግን አምልጧል። ቆሼ ተወልዶ ቆሼ መኖር ምን እንደሆን ለጋዜጠኛ ጌጡ ተመስገን እንዲህ ብሎታል።

ክፉ ነው ደሃ መሆን (ለቆሼ ሠፈር ልጆች) የችግሩ ጥግ ቆሻሻ ላይ የላስቲክ ቤት ያሰራሃል፡፡ መሠረት ስለሌለህየሚያውቅህ የሚያስብልህ መንግስት አይኖርህም፡፡ ጥሩ መልበስ ንፁህ መብላት ያንተ የልብ መሻቶች አይሆኑም፡፡አንገትህን ደፍተህ ነገን ትናፍቃለህ፡፡ ተፈጥሮ ፊቷን አዙራብህ ስትፍጨረጨር ሠዎች በፈጠሯቸው ተልካሻ ምክንያቶችሕይወትህ ያልፉል፡፡ ቤትህ ተንዶ ማቅ ላይ ብትሆን እንኳን ጩኸትህን የሚሰማ አምቡላንስ እንጂ የሚያድን ወገንየለህም፡፡ ምክንያቱም አንተ ደሃ ነህ! ‹‹ምስኪን›› (ትርፍራፊ) እየበላህ ያደክ የተማርክ ደሃ ! ይሄ ነው የኔና የሠፈሬልጆች ኑሮ፡፡ ይሄም ኑሮ ሆኖ ይሄ ሁሉ ሃዘን ታዲያ ስለምን? … ዳሩ አንድ ቀን እንደ ሠው የምንታይበትና የምንኖርበትቀን ይመጣል፡፡ የሟቾቹ ቁጥር ከፍና ዝቅ ማለት አይጠቅመንም፡፡ … ለሞቱት ነፍስ ይማርልን ! … በጣር ላይ ላሉትምእግዚአብሔር ይሁናቸው፡፡ ወይ ቆሼ ምግባችንም፤ ሞታችንም አንተው ትሆን ! …›› *(2)

 

ይሀ አንጀት የሚበላው ገለፃ የቆሼ ህይወት ገፅታ ነው። ይህ ደግሞ የሚሊዮናት ኢትዮጵያውያንም ህይወት ነፀብራቅ ነው። የዩቶፒያ ኢትዮጵያ ገዢዎችና ዝርያዎቻቸው ግን ይህንን ህይወት አያቀውቁትም። ለእነርሱና ለዝርያዎቻቸው የማይገባውን እንዲህ ያለ አኗኗርና አሟሟት መኖሩን ሰምተው ለሞቱት የሀዘን ቀን ቢያውጁም ሀዘኑ ተሰምቷቸው ኑሮውም ገብቷቸው ግን አይደለም። እነርሱ የሚኖሩት በዩቶፒያ ኢትዮጵያ ነውና!!

ቆሼ በዩቶፒያ ኢትዮጵያ ለሩብ ምዕተ ዓመት የሰፈነው የኢፍትሃዊው ዘረኛ አገዛዝ ውጤት ነው። በቆሼው ዕልቂት እንደ ሀገር እና እንደ ህዝብ ቅስማችን ተሰብሯል። ኢትዮጵያ ከዚህ የከፋ ቅስም ሰባሪ ሀዘን ሊገጥማት አይችልም። በዩቶፒያ ኢትዮጵያ የሰፈነው አግላይና ጨቋኝ፤ ግፈኛና ዘራፊ፤ እኩይና ጨካኝ ፤ ፀረ ኢትዮጵያና ፀረ ኢትዮጵያውያን … የጥፋቶችና የክፉ ተግባራት ሁሉ ቁንጮ የሆነ ሥርዐት ነው – የህወሃት/ኢህአዴግ ሥርዐት።

ይህ ሥርዐት ከወልቃይት እስከ ቦረና ከጋምቤላ እስከ ሐረር ሲገድል ሲያስገድል ሲያስር ሲያሳድድ ሲያፈናቅል ሲዘርፍ ሲያዘርፍ በንፁሀን ደም እየዋኘ በእናቶች እንባ እየታጠበ ሩብ ምዕተ ዐመት ጨርግዶ እነሆ ደግሞ ለሁለተኛው ሩብ ምዕተ ዓመት ሀሌታ ደርሷል። እነሆ ደግሞ የቆሼ ደም ይጣራል ፤ የሆራ ቢሾፍቱ ደም ይጣራል ፤ የወልቃይት ፀገዴ ደም ይጣራል ፤ የአኝዋኹ ደም ይጣራል ፤ የኮንሶው ደም ይጣራል … እንግዲህስ አይበቃንም እንዴ?! ወይስ ሰቆቃችን ገና ይቀጥላል ?!

*****************************

ተፃፈ ሚያዚያ 2009 ዓ/ም

ኤፕሪል 2017

ሲድኒ አውስትራሊያ

mmtessema@gmail.com

ማጣቀሻ

*(ፎቶ1) – ከጎልጉል ድረገፅ ጋዜጣ ፎቶ ከነማብራሪያው የተወሰደ ፤ http://www.goolgule.com/regardless-of-tplfs-cover-up-the-drought-is-escalating-and-schools-are-closing/

*(2) ከጋዜጠኛ ጌጡ ተመስገን ፌስ ቡክ የተገኘ፤

https://www.facebook.com/getu26/posts/1544759092230993

* ቁጥር ያልተሰጣቸው ፎቶዎች በቆሼ ሱናሚ ካለቁት ጥቂቶቹና የህዝቡ ሀዘን ከታየባቸው – ከሶሻል ሚዲያዎች የተገኙ ናቸው።

ሪቻርድ ፓንክረስት የታሪካችን ጎልጉል (አገሬ አዲስ)

በአገራችን ታሪክ ላይ ብዙ መጽሃፍት የተጻፉ ቢሆንም በዘመናዊ ጥናትና ምርምር ከቀረቡት ውስጥ በ1927 ዓም እአአ በእንግሊዝ አገር ውድፎርድ በተባለው ቦታ የተወለዱት የፕሮፌሶር ሪቻርድ ፓንክረስት ስራዎች ትልቁን ድርሻ ይይዛሉ።እኝህ የታሪክ ምሁር ለኢትዮጵያ ታሪክ ትኩረት የሰጡት ገና በወጣትነት ሳሉ ከወላጅ እናታቸው ከወረሱት አፍቅሮ ኢትዮጵያ በመነሳት ነው።እናታቸው ወ/ሮ ሲልቪያ ፓንክረስት ኢትዮጵያ በጣልያኖች በተወረረችበት ጊዜ ከአጼ ሃይለስላሴ ጎን በመሆን የኢትዮጵያን ጉዳይ በእንግሊዞች አእምሮ ውስጥ ሰርጾ እንዲገባና ለነጻነት ትግሉ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱ የቁርጥ ቀን የኢትዮጵያ ወዳጅ ናቸው።በዚህ የኢትዮጵያ ፍቅር የተጠመቀው ልጃቸው ሪቻርድም የእናቱን ፈለግ ተከትሎ ለኢትዮጵያ ያለውን ፍቅር እስከመጨረሻው ባለው የብእር መሳሪያ ታሪኳን እየጎለጎለ/እያወደሰ ሲከላከልና ለተተኪው ትውልድ ሲያስተምር ፣ልጆቹንም ሄለንና አሉላ በማለት በስምና በግብር ከኢትዮጵያ ጋር አስተሳስሮ እንደሱ በአፍቅሮ ኢትዮጵያ የተራቸውን እንዲወጡ ያደረገ ትልቅ ምሁርና የኢትዮጵያ ባለውለታ ነው።ይህ ታላቅ የታሪክ ሰው በተወለደ በሰማንያ ዘጠኝ ዓመቱ ….….[ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ] ——

ሞት ላይቀር- ተጠላልቶ መኖር፤ – ይገረም አለሙ

 

የአቶ አሰፋን ነፍስ ይማር በጥላቻ ለምንኖር የይቅርታ ልብ ይስጠን፡

                                                      የት አባቱ ሞትም ይሙት

እባካችሁ ዘመዶቼ ስሞት ሞትም አብሮኝ ይሙት

በሳቅ በደስታ ግደሉት

በሀሴት በእልልታ ውገሩት

ከአጥንት በታች ቅበሩት

እባካችሁ ለሞት የልብ ልብ አትስጡት

ናቁት አጥላሉት አውግዙት

በሙሾ ግነን አትበሉት

በሞቴ አታስደስቱት፣

(ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን)

የሰው መጨረሻው ሞት እንደመሆኑ ሞት በራሱ አያሳዝንም፣አሟሟቱ እንጂ፤ያለ ግዜው መቀጨት፣በአሳቃቂ ሁኔታ መሞት፣እውቀቱን ፣ልምዱን ችሎታውን ለሀገር ጥቅም ሳያውል ወይንም ጀምሮ ሳይጨርስ መሞት ወዘተ የሳዝናል ያስቆጫል፡፡ ሟች በህይወት በነበረበት ግዜ ለቤተሰቡ ምሰሶ ከሆነ ቤተሰቡ ለአንድ ሰሞንም ቢሆን ያዝናል፡፡ለሀገር ለወገን ጠቃሚ የነበረ ከሆነ  ህዝብ ያዝናል፡፡ በእኛ ባህል ደግሞ  ሰው ሲሞት ክፉው ደግ፣ ጨካኙ ሩህሩህ፣  ንፉጉ ቸር፣ ፈሪው ጀግና ተደርጎ ይነገርለታል የህይወት ታሪክ ተብሎ ይነበብለታል፡፡ ምን መጥፎ ቢሆን ሙት አይወቀስም፡፡ ሙት ወቃሽ አታርገኝ ይላሉ አበው ፡፡

የአቶ አሰፋ ጫቦ ሞት መርዶ የደረሰን ህመማቸውን ሳንሰማ መሆኑ አስደንጋጭ ነበር፣ ገለጥለጥ  በሚል ርዕስ January 12, 2017  በጻፉት ጽሁፍ ያጋራ ቤታችንን  ጨርሼ 10 ቀን ውስጥ አደባባይ አዋጣለሁ። አማራና ኦሮሞየሚመለከት ነው የሚል  Facebook  ላይና ሌላም ቦታ ጠቃቀስኩ። ይህ እርግማንና ዘለፋ የተጀመረው ገናባልታየ፤ባልተነበበ ጹሁፍና አስተያየት ላይ ነበር።ያ ነው ይበልጥ የገረመኝ። ከማንውቀው ይሰውረን ማለት ይሆን ?ከምናውቀው ግን ከሸሸነው እውነት ሰውረን ነው? አውቀን የካንደነውን እውነት አታስታውሰን ማለት ይሆንይህንንደህና ያጧጧፍነውን ሥራና ገበያ ይሻማብናል ማለት ይሆን? ሥራ ያሰኘኝ በተለየ አንዳንድ ዲያስፖራው ኗዋሪዎችመተደዳደሪያም ወደ መሆን የተቃረበ የሚያስመስል ፍንጭ ስለሚታይ ነው። በተፈጠረው የሕዝብ አመጽ ሳቢያ ታዋቂሆነን፤አገር አውቆን ፣ፀሐይ ሞቆን፤ አንቱ የተባልንበትን ልታፈርስብን ነው  የሚል ስጋት ፈጥሮ ይሆን? የሚል መላ ምትይፈጥራል። ”  ብለውን ስለነበር 10 ቀኑ አልፎ ወራቶች በመቆጠራቸው አቶ አሰፋ የነገሩንን ምነው አዘገዩት የሚል ጥያቄ ለመሰነዝር ዛሬ ነገ እያልኩ  ባለሁበት ሰአት ነበርና ሞታቸውን የሰማሁት በጣም ነው የደነገጥኩት፡፡

ከአቶ አሰፋ ጋር ያስተዋወቀችን ጦቢይ መጽሄት ከአስር አመት በፊት ሞተች፣ እነሆ ዛሬ ደግሞ በጦቢያ ያወኩት ያለፈበትን በድፍረት ይነግረን በጽሁፉ እንደ የፊልምና የትያትር  ያህል ነገሮች በአይነ ህሊናችን ለማየት ያስችለን የነበረው ሰው የብእሩ ቀለም ሳያልቅ ሳይነጥፍ ብእር የሚጨብጠው  እጁ በሞት ተሸነፈ፡፡ ቋሚ የእርሱም ወር ተራ እስኪደርስ ሟችን ሸኝቶ ነብስ ይማር፣ቤተሰብና ወዳጅ ዘመድን አግዚአብሄር ያጥናችሁ ማለት ነውና ወግ ልማዱ  ነብስ ይማር!

የአቶ አሰፋ ጫቦ ሞት ዜና ከናኘ በኋላ ኢሳት ያነጋገራቸው አቶ ያሬድ ጥበቡ የተናገሩት ደግሞ በሁለት መንገድ በጣሙን የሚያሳዝንና በኢትዮጵያዊነት የሚያሳፍር ሆኖ ተሰማኝ፡፡ አንደኛው አቶ አሰፋ ታመው ሆስፒታል ተኝተው የሚጠይቃቸው ቀርቶ ታመው መተኛታቸውን ለወዳጅ ዘመድ የሚነግር ሰው መጥፋቱ ሲሆን፣ ሁለተኛውና ይበልጥ አሳዛኝና አሳፋሪው ነገር ለዚህ ምክንያት የሆነው እንደ አቶ ያሬድ ጥበቡ አገላለጽ የፖለቲካ አመለካከት ልዩነት መሆኑ ነው፡፡ አንደኛ የፖለቲካ አመለካከት ልዩነት የአንድ ሀገር ልጆችን እዚህ ደረጃ ማደረሱ ሁለተኛ ደግሞ ከአርባ አመት በላይ ቆይቶ አለማርጀቱ ያ ትውልድን የሚያስወቅስ መድረኩ ቢገኝም የሚያጠያቅ ይመስለኛል፡፡

አቶ ያሬድ እንደነገሩ አቶ አሰፋ የተኙበት ሆስፒታል በሚገኝበት ከተማ የሚኖሩት በአብዛኛው ኢህአፓ የነበሩ ሰዎች ናቸው፣ እግዜር ይማርህ ባይሉዋቸውም የሞታቸው ዜና የተነገረው በእነዚሁ ኢህአፓዎች ነው፡፡ አቶ አሰፋ ኢጭአት እንደነበሩ ነው የሚታወቀው፡፡ ሁለቱም በግዜው ሥልጣን ላይ የነበረው ደርግ ተቀዋሚዎች ነበሩ፡፡ ዛሬ  ሲቃወሙት የነበረውም ደርግ እነርሱ የተሰለፉባቸው ፓርቲዎችም (ኢህአፓም፣ኢጭአትም፣መኢሶንም፣ወዝ ሊግም፣ ማልሬድም) የለሙ፣ ነገር ግን ሰዎቹ ቢያረጁም የጥላቻ ስሜታቸው አላራጅ ብሎ  እስከ ሞት አብሮአቸው ይኖራል፡፡ በሁለት የተቀዋሚ ፓርቲ አባላት መካከል እዚህ ደረጃ የደረሰ እድሜ የማይሽረው ጥላቻ ከተፈጠረ በወያኔና በተቀዋሚዎች መካከል ያለው ሁኔታ ሊደንቀንም ሊያስገርመንም አይችልም፡፡ ግን የሳዝናል ያሳፍራል፡፡ ለመሆኑ ይህ መጠላላት ፋይዳው ምንድን ነው? ለማነውስ የሚጠቅመው? ምንድስ ነው ጥቅሙ? መስዋዕትነት ከፍለንለታል ለሚሉት በነበር ለሚያስታውሱት ዓላማቸውም ሆነ ምን አልባት ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ይመኙ ያስቡ ከሆነ ለዛ የሚያበረክተው አስተዋጽኦስ አለ?

ከወያኔ ጋር እርቅ እያሉ ከማላዘን ይህን እንደ መልካም ነገር ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተሸጋገረ ያለ እርጅና የማያስረጀው ስደት የማያስቀረው የአንድ ሀገር ልጆችን ለክፎ መድሀኒት ያልተገኘለት መጥፎ በሽታ ጸብና ቁርሾ ማስወገዱ ነበር ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ የሚሻለውም፡፡ ከእነ ጥላቻችሁ ወደ ሞት ከምትሄዱ በመጨረሻው ሰአትም ቢሆን ይቅር ተባባሉ፡፡

 

ከተክሌ የሻዉ ይልቅ ኢሳያስ አፈወርቂን እመኑ እያሉ የሚያላዝኑ ሰዎችን ምን እንበላቸዉ? – ሸንቁጥ አየለ

ለኢሳያስ አፈወርቄ እድሜ መራዘም ጸሎት የያዙ ሰዎች ተክሌ የሻዉ እንዲሞት ጸሎት መያዛቸዉን በአደባያይ እየደሰኮሩ ነዉ::ሳያፍሩ እና ቅር ሳይላቸዉ ተክሌ የሻዉ ደጋግሞ እንዲሞት በአደባባይ እየሰበኩ ነዉ:: ስለ ኢትዮጵያ እቆረቆራለሁ የሚል ቡድን የፖለቲካ ስራዉን ትቶ በአደባባይ ወጥቶ እክሌ ይሙትልኝ ይላል? በእግዚአብሄር ስራ ገብቶ እንዲህ ይፈተፍታል? ምን አይነት ጥላቻ ነዉ? ምን አይነት ስር የሰደደ ነቀርሳ ነዉ?

ጥላቻቸዉ እንዲህ ተራራ ተነካ ምናልባትም ተክሌ የሻዉን ሊገሉት አቅደዉ ይሆን እንዴ? እንዲህ በአደባባይ ተክሌ የሻዉ ካልሞተልን የሚሉት?

ሻቢያ የኢትዮጵያን ተቃዉሞ ለመቆጣጠር የማይፈነቅለዉ ድንጋይ አይኖርም::በኢትዮጵያ ተቃዉሞ ዉስጥ ጎላ ያለ ሰዉ ካዬ ከምድረ ገጽ አጥፍቶ እርሱ የጠፈጠፋቸዉን እና እርሱ የሚቆጣጠራቸዉ ሀይሎች ብቻ ገነዉ እንዲወጡ የማይሰራዉ ደባ የለም::እናም አሁን ተክሌ የሻዉ ጥቂት እየጎላ መጣ መሰለኝ:: እናም መጀመሪያ ተክሌ የሻዉ ይሙት የሚል ጸሎት በአደባባይ ተይዟል::

ከተክሌ የሻዉ ይልቅ ኢሳያስ አፈወርቂ ለኢትዮጵያ ህዝብ ይጨነቃል ይሉሃል::

ተክሌ የሻዉን አናምነዉም::ኢሳያስ አፈወርቂን ግን እናምነዋለን ይሉሃል:: ተክሌ የሻዉ ደርግ ስለ ነበረ አናምነዉም ይሉህና::የኢትዮጵያን ክብር አዋርዶ ኢትዮጵያን ብትንትኗን ያወጣትን ኢሳያስ አፈወርቂን ግን የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ ነዉና እመኑት ይሉሃል::ባንዳ ከባህሪዉ ሁሉ የሚያስጠላዉ እፍረትም የለዉምና ሳያፍሩ የኢሳያስን ሬሳ በአደባባይ ይዘዉ እየዞሩ እዉነተኛ ኢትዮጵያዉያንን ግን ይሙቱልን : ይጥፉልን ይሉሃል:: እዉነተኛ ኢትዮጵያዉያንን በደርግነት ይከሷቸዋል::

ደርግ ለኢትዮጵያ አንድነት ሲጋደል የወደቀ መንግስት ብሎም ወያኔን እና ሻቢያን ልክ ለማስገባት መከራዉን ያዬ የኢትዮጵያ ልጅ እንጅ የኢትዮጵያ ጠላት አይደለም::ደርግ ስህተት ቢሰራም ስህተቶቹን የሰራቸዉ ኢትዮጵያዊ ሆኖ ነዉ እንጅ እንደ ወያኔ እና እንደ ሻቢያ ኢትዮጵያን ለምጥፋት ብሎ አይደለም::

ኢሳያስ አፈወርቂ ለኢትዮጵያ አንድነት ሲጨነቅ ዉሎ ሲጨነቅ ያድራል ይሉሃል::ለኢሳያስ አፈወርቂ እድሜ መራዘም ጸሎት ያዙ::ለተክሌ የሻዉ ቶሎ መሞት ደግሞ እኛ እያሟረትን ነዉ ብለዉህ ቁጭ:: ጉድ እኮ ነዉ::

ለምደዋላ::እነዋለልኝን መልምሎ እና አሰማርቶ የአማራን ህዝብ እና የኢትዮጵያን ህዝብ ሆድና ጀርባ አድርጎ እስከዛሬ ድረስ መርዛማ ጽንሰ ሀሳብን በኢትዮጵያ ፖለቲከኞች አዕምሮ የጠቀጠቀዉን እና ወያኔን ጭንቅላታን ላይ ያስቀመጠብንን ኢሳያስ አፈወርቂን ሲማልዱ ዉለዉ ሲማልዱ የሚያድሩት ጸረ ኢትዮጵያዉያን ሀይላት እራሳቸዉን በኢትዮጵያ አንድነት ስም ጠርዘዉ ኢሳያስ አፈወርቂን እመኑት ተክሌ የሻዉን ግን አትመኑት የሚል ለቅሶ ያላዝናሉ::ኢሳያስ አፈወርቂ ለምዷል::እዉነተኛ ኢትዮጵያዉያንን ከኢትዮጵያ ተቃዉሞ በማስወጣት የኢትዮጵያን ፖለቲካ በምናምንቴዎች ቁጥጥር ስር እንዲሆን ማድረግ ለምዶበታል::አሁንም እንደዚያ ማድረግ የሚቻል እየመሰላቸዉ ዘጥ ዘጥ የሚሉ ሀይሎች አሁንም አፍርቷል::

ከስንቱ አስመሳይ እና ባንዳ ጋር እንዋጋ ጃል? ጠላት ላለማብዛት ብዙ ዝም ስንል እያንዳንዱን የሻቢያን ደባ የማናዉቅ መስሏቸዋል:: ለኢሳያስ አፈወርቂ እድሜ መራዘም ጾሎት ይዘዉ ተክሌ የሻዉ ግን ይሙት የሚል መዝሙራቸዉን በአደባባይ ለቀዋል::

ምድረ ጸረ ኢትዮጵያዊነት እና ጸረ አማራ ከህዝባችን እራስ ላይ አልወርድ አሉ እኮ::

ከተክሌ የሻዉ ይልቅ ኢሳያስ አፈወርቂን እመኑት አሉ?….

ሆይ ሆይ….

የኢትዮጵያን ህዝብ በተለይም ደግሞ የአማራን ህዝብ እንዴት ቢንቁት ነዉ ግን ከተክሌ የሻዉ ይልቅ ኢሳያስ አፈወርቂን እመኑት እያሉ ሳያፍሩ ልሃጫቸዉን የሚያዘሩት?

ብንከባበር መልካም ነዉ

ከትህትና እና እና ፍቅር በቀር ማንንም የመፍራት መንፈስ የለንም:: እናም እዉነተኛ ኢትዮጵያዊ ወገኖቻችን አትንኩ::

እዚያዉ ለኢሳያሳችሁ እድሜ መራዘም ጸሎታችሁን ያዙ::እርሱን የከለከላችሁም አታድርጉ ያላችሁም የለም::ከተክሌ የሻዉ እራስ ላይ ግን ዉረዱ::

መከባበሩ ይሻላል !

ልባችን በብዙ ጥቃት የቆሰለ ኢትዮጵያዉያን ነን እና ሌላ ህመም አትጨምሩልን::

ኃይሌ ገ/ስላሴ ከመጋረጃው ጀርባ የሚሰራውን ምን ያህል ያውቃሉ? ( ቆንጅት ስጦታው)

ኃይሌን በአደባባይ የምናውቀው በእግሮቹ ፍጥነት ነው፡፡ ከአደባባይ በመለስ ከመጋረጃው ጀርባ የሚሰራውን ምን ያህል ያውቃሉ?

ኃይሌ በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኘውን ጤፍ (The Ethiopian endemic crop) ከወንድሙ ጋር በመሆን እና ከሆላንድ ባለሀብቶች ጋር በመመሳጠር ባለቤትነቱ በሆላንዳዊያን አንዲ መዘገብ አድርጓል፡፡ሀይሌ እና ወንድሙ ከሆላንድ ባለሀብቶች ጋር በፈጠሩት ሽርክና ጤፍን ከኢትዮጵያ ውጭ በማምረት እና በማሰራጨት ሀገሪቱ በዚህ ብርቅየ አዝዕርት ማግኘት የነበረባትን ጥቅም አሳጥቷታል፡፡

ኃይሌ በወቅቱ ስለዚህ ጉዳይ የወያኔውን ሪፖርተር ጋዜጣን ጨምሮ የተለያዩ ሚዲያዎች ጥያቄን ቢያቀርቡለትም መልስ ለመስጠት ፍቃደኛ አልነበረም፡፡ “የኢትዮጵያ የዘረመልህ ባንክ” የሚባለው ተቋም የስራ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች የኃይሌን ተግባር ቢቃወሙም፤ የህወሓት የዘረፋ ሸሪክ በመሆኑ ምንም የተባለው የለም፡፡ እንዲያውም ይህ ጉዳይ በVOA ቀርቧል፡፡

የኢትዮጵያ አንጡራ የተፈጥሮ ፀጋን የዘረፈው እና ያዘረፈው ኃይሌ፤ እንደ መደኃኔት በአለም አቀፍ ደረጃ ከሚሸጠው ጤፍ ላይ ሀብት እያካበተ ነው፡፡ በአለም አቀፍ ደረጃ አንድ ሀገር በብቸኝነት ላላት የተፈጥሮ ፀጋ ልዩ መብት የሚሰጥ የባለቤትነት መብት አለ፡፡ ኃይሌ ኢትዮጵያ ያሳጣት ይህንን ልዩ መብት ነው፡፡ የማምረት እና የመሸጥ ፍቃድ በመስጠት ብቻ ኢትዮጵያ በአመት ሚሊዮን ዶላርሮችን ማግኘት የምትችልበትን መብት ነው ያሳጣት፡፡

ሌላኛው የኃይሌ እና የወያኔ የንግድ ሽርክና “ማራቶን ሞተርስ” ነው፡፡ ይህ የኮሪያን ቅንጡ ተሽከርካሪዎችን የሚያስመጣው ተቋም ዋንኛ ሸማቾች የወያኔ መከላከያ ሚንስቴር መስሪያ ቤት ነው፡፡ ሌሎችም የወያኔ የመንግስታዊ ተቋማት ሸማቾች ናቸው፡፡ኃይሌ በአንድ ወቅት የመኪና ንግድ በወራት በመቶ ሚሊዮኖች የሚታፈስበት ነው ብሏል ለሪፖርተር ጋዜጣ፡፡ በመቶ ሚሊዮኖች የሚታፈሰው ለኢትዮጵያ ህዝብ ሸጦ ሳይሆን ለመንግስታዊ ተቋማት በተመቻቸለት የልዩ ተጠቃሚነት መብት ነው፡፡ በኢትዮጵያ አንደኛ የመኪና ሻማቾች የመንግስት ተቋም ተብየዎች መሆናቸው ግልፅ ነው፡፡

ኃይሌ ከሩጫ የተሸለመው ጥቂት ምሊዮኖች ነው፡፡ ከስፖንሰር የሚያገኘውም ቢሆን እዚህ ግባ የሚባል አይደለም ምክነያቱም ስፖንሰር የሚያደርጉት አለማከፍ ኩባንያዎች ኢትዮጵያ ውስጥ የሚያጓጓ የገብያ ድርሻም የላቸውም፤ ምርታቸውም ለአብዛኛዎቹ ተጠቃሚዎች የሚቀመስ ዋጋ አይደለም፡፡ የኃይሌ ሀብት ግን በቢሊዮኖች የኢትዮጵያ ብር ነው፡፡

ስለዚህ የኃይሌ የሀብት ምንጭ ከወያኔዎች ጋር የሚደረግ የዝርፊያ ሽርክና ነው፡፡

ሌላው የሀይሌ ገራሚ ነገር ለአፍሪካውያን በተለይም ለኢትዮጵያውያን ያለው የተዛባ አመለካከት ነው፡፡ ይህንንም በBBC ላይ ለአፍሪካውያን ዲሞክራሲ አያስፈልግም ብሏል፡፡ ምክነያት እሱ ከጨቋኞች እና ከዘራፊዎች ጋር መሞዳሞድ ስለሚችል ነው፡፡

Ethiopia: ዉድ የአማራ ልጆች (ዶ/ር አቤል ጆሴፍ)

ከፌስ ቡክ እንድለይ ያስገደደኝ ነገር ክብሬ ስለተነካ ወይም ፎቶዬን ጥቂት ወረበሎች ለጥፈዉ ስም ለማጥፋት ስለሞከሩ አይደለም፤ እንደዛማ ቢሆን ኑሮ የግንቦት ሰባትና የወያኔ ቡችሎች ፎቶዬን ለጥፈዉ ለማሸማቀቅ በሞከሩ ጊዜ ነበር ከፌስ ቡክ ሆነ ከትግል አለም የምሰናበተዉ።ለማታዉቁኝ ጎንደሬ ነኝ፤ ከጎንደርም ከጀግናዉ የቆላ ወገራ ጸለምትና ሰሜን ጃናሞራ ህዝብ ለራበዉ እንጀራ ለጠገበዉ ጥይት ከሚሰጥዉ የተወለድኩ፤ በአማራነቴ ሆነ በኢትዮጵያዊነቴ የምኮራ ግለሰብ ነኝ።

እኔ አንድ ተራ ሰዉ ነኝ፤ ከኔ ክብር ይልቅ የአማራ ህዝብ ደህንነት በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚበልጥ እረዳለሁ፤ ይሁንና ከሁሉም ነገር ያሳሰበኝና ተስፋ ወደ መቁረጥ አዝማሚያ የወሰደኝ፤ የአማራዉ የራስ አድን እንቅስቃሴ፤ አማራን ከወያኔ መዳፍ ለማዳንና የራሱን ህልዉና ሆነ ጥቅም ለማስጠበቅ እንደሆነ ሳይሆን፤ ሆነ ተብሎ አማራዉ ኢትዮጵያን አፈራርሶ የራሱን መንግስት ለመመስረት ተደርጎ ሲቀርብ በመመልከቴና፤ ይህን ተግባር የሚያራምዱት በግንባር ቀደምት አማራ ነን ባዮች መሆናቸው ነዉ።

እንደሚታወቀዉ የአማራዉ ትግል በትግራይ ፋሽሽቶች ከተደቀነበት የጅምላ ጭፍጭፋ እራሱን ማዳን ትግል እንጅ ወያኔና የኦሮሞ ጽንፈኞች እንደሚፈልጉት ኢትዮጵያን አፈራርስ ትንንሽ ሃገሮች ለማቋቋም አይደለም። ሃ እራስን ማዳን ነዉ እንዲሉ አማራዉ መጀመሪያ እራሱን ከጥቃት መከላከል፤ ከዛም እንደሁኔታዎች በሂደት መስመር የሚያስዛቸውን ነገሮች የራሱን ጥቅምና ህልዉና በማይጋፋ ሁኔታ ማስያዝ ነዉ የሚሆነዉ።

በዚህም ሂደት ዉስጥ ከሌሎች ኢትዮጵያኖች ወገኞቹ ጋር በሰላምና ጥቅሙን በማይጋፋ ሁኔታ የጋር መንግስት መስርቶና ሁሉም በየመጠኑ ተወካይ የሚኖርበት፤ የህዝብ ድምጽ የተከበረበትና ሰዉ ሳይሆን ህግ ወይም ህገ መንግስት ንጉስ የሆነበት ስርአት መስርቶ መኖር የሚችልበት ሁኔታ ይኖራል፤ ያ ካልሆንነና አብሮ የመኖር በሩ ተዘግቶ፤የሁሉም ህዝብ ፋልጎት ተነጣጥሎ መኖርና የየራሱን ትንንሽ ሃገር መስርቶ መኖር ከሆነ ደግሞ አማራዉ የራሱን ሃገር መስርቶ ይኖራል።

የአማራን የራስ አድን ትግል ኢትዮጵያን አፍራሽ ትግል አድርጎ ማቅረብ፥

ይህ ሁኔታ ወያኔ የከፈፍለህ ግዛዉ ተግባሩን ለማጠናከር የሚጠቀምበትና አማራዉ መሬትንህን ነጥቆ የራሱን ሃገር ሊገነባ ነዉ በማለት አማራ መንግስት እንመሰርታለን ባዮች በካርታቸው ባጠቃለሉት ህዝብ ላይ ከፈተኛ ቅስቀሳ እንዲያደርገና የነሱን ጸረ አማራ ድጋፍ ለማግኘት የሚጠቀምበት ነዉ፤ ስለዚህ እንደዚህ አይነት ሁኔታዎች እንዲኖሩና አማራዉ ኢትዮጵያን አፍርሽ ተብሎ እንዲቀርብ እየተደርገና ሌሎች የኢትዮጵያ ብሄሮች ከነበራቸው በላይ ከፍተኛ የሆነ ጥላቻ እንዲያሳድሩና; አማራ መጣብህ አይነት ማስፈራሪያ ወያኔ እንዲጠቀም እየተደረገ ነዉ።

የአማራዉን ስብስብ የወሮበላ ስብስብ ማስመሰል፥

በዚህ ላይ ወያኔ ካድሬዎችን በማሰለፍ አማራ መስለዉ እንዲሳደቡና በተለይም ከአማራ ህዝብ የማይጠበቁ ጸያፍና አሳፋሪ ቃላቶችን በመጠቀም የአማራዉ ስብስብ ተራ የወሮበላ ስብስብና በሌሎች አስተዋይ አማራዎች ድጋፍ እንደሌለዉ አድርጎ ለማቅረብ ከፈተኛ ዘመቻ እያደረገ ነዉ፤ ለዚህም ተግባሩ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ብዙ የአማራ ልጆች የስድብ ባለሙያወች ሆነዉ ወጥተዋል፤ በተለይም የአማራ ምሁራንና በሳል ሰዎች ወደ ትግሉ ጎራ እንዳይቀላቀሉ ሆን ተብሎ የሚሰራ ተንኮል ነዉ።

የአማራ ጸንፈኞች መኖር ሌሎች ጽንፈኞችን ማሰፈራሪያ ይሆናል፤

ይህ የተሳሳተ ግንዛቤ ነዉ ምክንያቱም ጽንፈኞችን የሚፈራዉ በሌላ ጎራ ያለው ጽንፈኞ ሳይሆን፤ አብሮ የመኖር ፍላጎት ያለዉ ህዝብ ነዉ። በሌላ ጎራ ያለዉ ጽነፈኛማ የመገንጠል አላማ ስላለዉና አብሮ የመኖሩን ሰንሰለት የሚበጣጥስለት ከሌላዉ ጎራ ጽንፈኛ መኖሩ የራሱን ፍላጎት ያጎለብትለታል፤ ደስም ይለዋል፤ ህዝቦችን ለዘመናት አስተሳስሮ የኖረዉን መረብ ሌላ መጋዝ ይዞ የሚቆርጥለት ሲያገኝ እንዴት ነዉ የሚፈራ፤ ድግስ በድግስ ይሆናል እንጅ።

ወያኔ ሆነ ሌሎች አምባገነኖችን የሚያስፈራቸው በህዝቦች መካከል የሚኖረዉ የጠነከረ ግንኙነት ነዉ፤ ለዛም ነዉ ወያኔ ሁሌ በርግጠኝነት በአማራን በኦሮሞ ህዝብ መካከል ያለዉ ግንኙነት ምንም አይነት ጥንካሬ እንዳይኖረዉ በከፍተኛ ሁኔታ የሚሰራዉ፤ ምክንያቱም ሁለቱ ህዝቦች በጋር ጠላት ላይ ቢነሱ፤ የወያኔ ቀን ቁጥር እንደሚሆን ያዉቀዋል።

ለጽፈኞች መልሱ ጽንፈኝነት ሳይሆን፤ ጽንፈኝነትን ያጋለጠና የራስን ፍላጎት ያስጠበቀ ህዝባዊ ድጋፍ ያለዉ አቋም መያዝ ነዉ፤ ሁለት ተቃራኒ ሃሳብ ያላቸው መሳሳብ አይችሉም፤ ስለዚህ ይህ የጽንፈኛ አቋም ወያኔም ሆነ የ ኦሮሞ ጽንፎኞች የሚያስቡት ኢትዮጵያን አፈራርሶ ትንንሽ መንግስት መመስረት ህልም እዉን እንዲያደርጉ የሚረዳና ጽንፈኛ ተግባራቸውን በ አማራዉ ህዝብ ህጋዊነት እንዲያገኝ የሚረዳ አካሄድ ነዉ። እናነተም ተገንጠሉ እኛም እንገነጠላለን ነዉ ነገሩ።

ዋናዉ ቁም ነገር ግን ትንንሽ ሃገራት መመስረቱ ሳይሆን እንደ ኢትዮጵያ አይነት ክልሎች በዉል ያልታወቁበትና ህዝቦች ተሰባጥረዉ በሚኖሩበት ምድር ሃገር ምስረታዉ ቀጣይ የእርስ በእርስ ጦርነት እንደሚያስከትልና ሃብስ (Hobbes- war of all agisnt all) እንዳለዉ ጦርነቱ ሁሉም ከሁሉም ጋር የሚዋጋበት ይሆናል፤ ማለትም ቀጣይና የማያባራ ጦረንት ይገጥመናል።

የአማራ ድርጅት መኖር፤

የ ኢትዮጵያ የፖሊትካ ትግል ዉስብስብ የሆነ ስለሆነ፤ በርግጥ የሚኖረዉ አማራጭ ሁለት ነዉ፤ አብሮ መኖር ወይም ያዉ ትንንሽ ሃገሮችን መስርቶ መኖር።

አብሮ የመኖር ሁኔታ በርግጥ በ አብዛኛዉ የሚደገፍና በተለይም እንደ ኢትዮጵያ አይነት ድሃ ሃገር ህዝቦች አብሮ መኖሩ ከመበታተኑ ጠቀሜታ ይኖረዋል፤ ለዚህም ሁሉም ብሄሮች ተስማምተዉ የሁሉንም ጥቅም ማስጠበቅ የሚችልና አድል ኦ የሌለዉ፤ ሁሉም የየራሳቸው ተወካይ የሚኖርበት፤ አንዱ የ አንዱን ጥቅም የምያጋፋበት የጋር መንግስት መመስረቱ ወሳኝ ነዉ።

በዚህም የጋር መንግስት ምስረታ አማራዉ የራሱን ድርጅት ኑሮት ከሌሎች ጋር በወንድማማችነት የራሱን ጥቅም በማስጠበቅ የሚቀጥለበት ሁኔታ ይኖራል፤ ለዛም ነዉ አማራዉ በ አማራነት ተደርጅቶ የ አማራዉን ህዝብ ፍላጎት ማስጠበቅና አማራዉ ከጥቃት መከላከል የግድ የሚለዉ።

እንደ ኢትዮጵያ አይነት በብሄር የተከፋፈለ ሃገር የግድ የብሄር ድርጅቶች መኖር ያስፈልጋል፤ ያ ማለት ግን ህብረ ብሄር ድርጅቶች አይኖሩም ማለት አይሆንም።

ይሁንና የ አማራዉ የብሄር ድርጅት መኖር የግድ የሚልና አማራዉ ከሌሎች ጋር በሚፈጥረዉ የጋር መንግስት የራሱን ድርሻ የሚወጣበትና ጥቅሙን የሚያስጠብቅበት ስለሆነ፤ የ አማራ ድርጅት መኖሩ ክርክር ዉስጥ የሚገባ አይሆንም።

ሃገር ምስረታ

ለተቀማጭ ሰማይ ቅርቡ ነዉ አበዉ ሲሉ ምን ለማለት ፈልገዉ ነዉ፤ አንድ ነገር ስትሞክረዉ ነዉ እንጅ ሳትሞክረዉ ቀላል ነዉ የሚመስልህ ለማላት ፈልገዉ ነዉ።

አንዳንዶች ሃገር መመስረት እንደ ኬክ መቁረስ አቃልለዉ ሲያዩት እንመለክታለን፤ ይህ የተሳሳተ አመለካከት ብቻ ስያሆን፤ ግንዛቤ የጎደለዉ አ እሞሮ የሚያፈልቀዉ ቅዥት ነዉ።

ሃገር ምስረታ በተለይ ከስለጣኔ አለም ለተጣላዉ አፍሪካ ከባድ መሆኑን መረዳትና ሃገር መሰረትን ያሉት ኤርትራያኖች ለምን የ አዉሮፓንና የ አርብን መንገዶች እንዳጣበቡና፤ በሜድትራንያንና በቀይ ባህር ስንቶቹ ህየወታቸው እንዳለፈ መወቅ የግድ ይላል።

ሃገር ምሰረታ ብዙ ቅድመ ባንዴራ ማዉለበልብ ወይም መዝሙር መዘመር አይደለም፤ ነገር ግን ቅድመ ሁኔታዎች ያስፈልጉታል፤ ህዝቦች እራሳቸውን የሚያስችል ነገሮች መኖራቸውንና በተለይም አሁን አለም በካፒታሊስቱ ማርኬት ቁጥጥር ስር ባለችበት ሁኔታ፤ ከባርነት ሊያላቅ የሚችለ የሰዉ ሃይል ማለትም አምራችና ፈጣሪ የሆነ፤ ብሎም ብቁ የሆነ አንጡራ ሃብት ያስፈልጋል፤ ይህ በሌለበት ሁኔታ ሃገር ለመመስረት መሞክር በራስ ላይ ገመድ እንደ ማስገባት ይቆጠራል።

ወያኔ በ አማራዉ ትግል ሰርጎ ገብትዋል፥

ወያኔ አማራዉን ጭራቅና ሰይጣን አድርጎ ላለፉት አርባ አመታት የሰራበትና አሁን ደግሞ አማራዉን እንደ ጸረ ኢትዮጵያን ኢትዮጵያን አፍራሽ አድርጎ በማቅረብ የሌሎችን ብሄሮች ድጋፍ ለማግኘትና አማራዉን ነጥሎ ለመምታት ትልቅ ስራ እየሰራ ነዉ።

ለዚህም ስራዉ ሆድ አደር አማራዎችን መግዛትና በ አማራዉ ትግል ሰርገዉ እንዲገቡ ማድረግ ነዉ።

ጎቤን ከመግደል ጀሞሮ የ አማራ ታጋዮችን እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር ታጋይ አስመስሎ በበርሃም ሆነ በከተማ እንዲሁም በዉጩ አለም ያሰማራቸው ደሞዝተኞች ሞልተዉታል።

ዛሬ የ አማራ ገበሬዎች የሚያደርጉት እንቅስቋሴ በራሱ በገበሬው ማለትም ታጋይ መስሎ በሚቀርበዉ እንዲገታና፤ ግንኙነታቸው እንዲሰናከል እየተደረገ ነዉ።

ለምሳሌ ከወልቃይትና ከጠገዴ ተንቀሳቀሰዉ በዳበት አልፈዉ በለሳ የሚሄዱ የነበሩት ግንኙነታቸው እንዲቋረጥና ሳይታሰብ አደጋ እንዲደርሳባቸው እየተደረገ ነዉ።

ከጃንወራና ከቦዛ በደባርቅ አልፈዉ ጃናሞራ ብሎም ጸለምት እየተንቀሳቀሱ የነበሩት ከፋኞች እንዲሁ እንቅስቃሴ አቸው ተገትትዋል።

በከተማም ሆነ በዉጩ አለም፤ እንዲሁ የ አማራዉን ትግል ለመከፋፈልና አማራን መጥፎ ስም ለማሰጠት ወያኔ ቅጥረኞቹን አሰማርትዋል።

ባጠቃላይ ወያኔ ባለዉ የገንዘብ ጉልበት እየተጠቀመና፤ ሆድ አደር አማራዎችን እየተጠቀመ የ አማራዉ ትግል ከፌስ ቡክ እንዳያልፍ እያደርገው ነዉ።

ለምሳሌ አንዳንድ የ አማራ ድርጅቶች ጎንደር ቦንብ የሚያፈነዱ እነሱ እንደሆኑ ይናገራሉ፤ እዉነቱ ግን ቦንቡን የሚያፈነዳዉ እራሱ ወያኔ ነዉ።

ባጠቃላይ የአማራዉን ትግል ለማኮላሽትና አማራዉን ለመነጠል ወያኔ በከፍተኛ ሁኔታ እየሰራ ስለሆነ፤ ለ አማራ ህዝብ እናስባለን የምንል ከስሜት በወጣ ሁኔታ ነገሩን በ አበክሮ መመልከትና፤ በተለይም አስተዋይ ሰዎች ያለዉን ሻጥር ከመጋረጃዉ በስተጀርባ መመልክት ጥሩ ነዉ።

ፖሊቲካ ሳይንስ መሆኑንና አስተዋይ ጭንቅላት የሚፈልግ እንጅ እንዲህ በዘፈቀደ አካኪ ዘራፍ በማለት የሚካሄድ አይደለም።

ዶ/ር አቤል ጆሴፍ

አሰፋ ጫቦ ተገደለ ወይስ ሞተ? [ቬሮኒካ መላኩ]

የመጨረሻው መጀመሪያ

ባለፈው ወር አካባቢ የቦርከና ድረ ገፅ ባለቤት የእለት ስራውን እያከናወነ እያለ ከሌላኛው የአለም ጫፍ ከወደ አውስትራሊያ አንድ አጠር ያለች መልእክት ትደርሰዋለች ። ይች መልእክት ቦርከና የመልእክት ሳጥን ውስጥ በገባችበት ሰአት በሌላኛው የአለም ጫፍ አንድ በሙሉ ጤንነት ላይ የሚገኝ ሰው ዳላስ ውስጥ ምናልባት ራሱ ያፈላውን ቡና ከሲጃራው ጋር እያወራረደ ይሆናል ወይም ደሞ ብዙውን ጊዜውን የሚያዘወትርበት ቤተ መፅሃፍት ቤት ውስጥ ይሆናል ። ሁለቱንም ልማዶቹን በጣም ይወዳቸዋል ። ይህ ሰው በሙሉ ጤንነት ይገኝ የነበረው አሰፋ ጫቦ ነበር ።

መልእክቷ ምን ትላለች?

የቦርከናው ድረ ገፅ ባለቤት መልእክቷን ሲከፍታት እንደዚህ ትላለች :

” ሰላም ጠና ይስጥልኝ ። ስሜ ግሪጎሪ ማኬንዚ ይባላል ። አቶ አሰፋ ጫቦ ጋር እንተዋወቃለን ። ሁለታችንም በዓለም በቃኝ እስር ቤት ጓደኛ ነበርን ። እባክህ የአቶ አሰፋ ጫቦን የኢሜይል አድራሻ ላክልኝ። ከምኖርበት አውስትራሊያ ወደ አሜሪካ ስለምጓዝ አሰፋን ማግኘት እፈልጋለሁኝ ። ሁለታችንም ስላረጀን የመጨረሻ እድሌ ሊሆን ይችላል ። ” ይላል

ይች አጭር መልእክት የደረሰችው የቦርከናው ድሜጥሮስ ብርቁ ወድያውኑ ለአቶ አሰፋ በፌስ ቡክ ሜሴጂ በኩል የሚከተለውን መልእክት ይልካል :

” ጋሼ አሰፋ ሰላም ነዎት ወይ? አንድ ግሪጎሪ ማኬንዚ የሚባል ሰው ከወደ አውስትሪሊያ ኢሜሎትን ጠየቀኝ ። ሰውየው በአለም በቃኝ እስር ቤት አብረን አሳልፈናል እያለ ነው ። ጓደኛየ ነበሩ ብሏል ። ግለሰቡን ያውቁታል ወይ ? ” በማለት ይፅፍላቸዋል ።

አሰፋ ጫቦም ስሙን በማስታወስ ” አዎን ! በማእከላዊ እስር ቤት ካገኘኋቸው አዋቂ የምላቸው ሰዎች አንዱ ነው ፤ ኢሜይሌን ስጠው ” ብለው መለሱ።

የአቶ አሰፋን መልስ ያገኘው የቦርከናው ድረ ገፅ ባለቤት አቶ አሰፋ የሰጡትን የኢሜይል አድራሻ ለግሪጎሪ ማኬንዚ ይልክለታል ።
ከቀናት በኋላም አቶ አሰፋ ወደ ቦርከና በላኩት መልእክት ” ግሪጎሪ ማኬንዚ በስልክ እንዳገኛቸው እና ወደ አሜሪካ ሲመጣ ዳላስ ቴክሳስ ለመገናኘት እንደተቀጣጠሩ ይነግሩትና ። ” ምስጋና ጨምረው ይፅፉለታል ።

ቀድሞ በተያዘው ቀጠሮ መሰረት አቶ አሰፋ ጫቦ እና “ሊጎበኛቸው” ዳላስ ድረስ የሄደው ግሪጎር ማኬንዚ ማርች 27 ቀን ዳላስ (ዳውን ታውን) ተገናኙ።
በወቅቱ ሁለቱ ግለሰቦች ሲገናኙ አቶ አሰፋ ጫቦ ምንም አይነት የህመምም ሆነ የድካም ምልክት ያልነበራቸው እና እንዲያውም ለእድሜያቸው በጣም ጠንካራ የሚባል ሁኔታ ላይ እንደነበሩ ነበሩ ።
ይሄንም የሚያረጋግጥ ምናልባት ከራት ሰዓት በፊት በሚመስል ሁኔታ አብረው የተነሱትንም ፎቶ ግራፍ አለ።
ሶስት ሰዓት በዘለቀው ቆይታቸው ፤ በእራት ሰዓት በአንድ የጣሊያን ሬስቶራንት ራት በልተው ፤ እንደገና ለመገናኘት ቀጠሮ ይዘው ተለያዮ።

በማግስቱ አቶ አሰፋ ጨቦ ታመው ሆስፒታል ሄዱ። አቶ አሰፋ ጫቦ የመጨረሻዋን ኤሜይል ለግሪጎሪ ፃፉ “በምግብ መመረዝ” ። እንደታመሙ እና ስለህመማቸው ስሜት በዝርዝር ከፃፉለት በኋላ ዳግም ሊያገኙት ያልቻሉበትን ምክንያት ሆስፒታል መግባታቸው እንደሆነ ገለፁለት ። ”

ከአውስትሪሊያ ወደ አሜሪካ አቶ አሰፋን ጫቦን ለማግኘት ብዙ ሺህዎች ማይል አቋርጦ ዳላስ የደረሰውና አብሮአቸው ራት የበላው ግሪጎር ማኬንዚ ምንም የሆነው ነገር የለም።
ከዚያ በኋላ አቶ አሰፋ ከሆስፒታል አልተመለሱም። የግሪጎሪ ማኬንዚን እራት ተከትሎ ወደ ሆስፒታል የገቡት አቶ አሰፋ ከሆስፒታሉ ድነው ሳይሆን የወጡት ህይወታቸው አልፎ ነበር ።
እንቆቅልሹ የሚጀምረው እዚህ ላይ ነው ።

ለአለፉት 40 አመታት አቶ አሰፋ ጫቦ ከተለያዩ የፖለቲካ ሃይሎች ጋር ግልፅና ስውር ሽኩቻ ሲያደርግ ቆይቷል ። ዋጋም ከፍሎበታል ። ኢትዮጵያ ውስጥ እና በአካባቢው ያሉ የፖለቲካ ሃይሎች ወያኔ ፣ ኦነግ ፣ሸአቢያ ፣ ኢህአፓ እና መኢሶኖች አሰፋ ጫቦ ላይ ብዙ ክሶችን ፅፈውበታል ። እሱም የሚያውቀውን የድርጅቶችን ገበና ሳያቅማማ ሲፅፍ ነበር ። እነዚህ ፓርቲዎች በግለሰብ ደረጃ እንደ አሰፋ ጫቦ በእጅጉ የሚፈሩት አልነበረም፡፡ የሸአቢያን ፣ የወያኔንና የኦነግን ሴራ የሚያጋልጠው ፅሁፉ ፅፎ ካሰራጨና በመላው አለም መነጋገሪያ ከሆነ እንኳን ሁለት ወር አይሞላውም ነበር ።
አሰፋ ጫቦ በብሩህ አዕምሮውና በላቀ የእውቀት ደረጃው ብዙዎቹን ፖለቲከኞች በእጥፍ ድርቡ ያስከነዳቸው ነበር ፡፡ በዚህ የተነሳም አሰፋ ጫቦን ለአመታት ሲሰሩት የነበረውን ድብቅ ሴራ አውጥቶብናል ገና ወደፊትም ያወጣብናል እያሉ አጥብቀው ይፈሩትና አምርረው ይጠሉት ነበር ።

አሰፋ ጫቦ ጠንቃቃና የማስታወስ ችሎታ የነበረው አዛውንት ስለነበር በኢትዮጵያ ውስጥ እና በኢትዮጵያ ላይ የተሰሩ የድብቅ ሴራዎችን በጥንቃቄ ይዟቸው ኖሮ እያወጣ መጎልጎል ጀመረ ።
በመለስ ዜናዊ የውሸት ክስ ሀገር የተባረረው አሰፋ ጫቦ በአሜሪካ አገር በስደት መኖር ጀመረ፡፡ የተለያዩ የፖለቲካ ሃይሎች ግን በብዙ ሺ ኪሎ ሜትሮች ርቆ በሰው ሀገር የሚኖር ቢሆንም የአሰፋ ጫቦ ነገር እንቅልፍ ሊሰጣቸው እንዳልቻለ ብዙ ጠቋሚ ምክንያቶች ነበሩ ።፡ አቶ አሰፋ ጫቦ በተለያዬ ጊዜ በሚፅፋቸውና በሚያጋልጣቸው ድብቅ ሴራዎች “የቀን ቅዠት ሆኖ እያባነነና እያስበረገጋቸው እንደነበር ይታወቃል። ሌሎቹንም የተደበቁ ሴራዎች እየፃፈ እንደነበር ተናግሯል ።

የአቶ አሰፋ ጫቦ የማስታወሻ ደብተር ብዙ ጉዳዮችን አጭቂ የያዘ እንደነበር መገመት አይከብድም ። የኢትዮጵያ ፖለቲካ
እንደ ቆሰለ ጅብ የመበላላት አባዜ የተጠናወተው ነው ። ሸፍጡን እና ሴራውን ለመደበቅ አንዱን ገድሎ ስልጣኑን ማደላደል የተለመደ ነው ። ይሄ ለአመታት የተለመደ መርዘኛ ሂደቱን ቀጥሏል ። ከአንድ ሰሞን ከንፈር መምጠጥ ባለፈ “ ይሄ ሰው እንደት ሞተ? “ለምን ተገደለ?” በማን ተገደለ? ገዳዩ ለፍርድ ይቅረብ ወዘተ” የሚል ባህል የለንም ።

የአሰፋ ጫቦ ጉዳይ ገዳይ ተገዳይ ድራማ ያለበት መስሎ ይሰማኛል ፡፡ በዚህ የገዳይ ተገዳይ ድራማ ውስጥ ብዙ ተሳታፊዎችን መጥቀስ ይቻላል ። አሰፋ ጫቦ በብእሩ ጫፍ ያቆሰላቸው ብዙ ናቸው ። “የትዝታ ፈለግ ” በሚለው መፅሃፉ CIA ኢትዮጵያን ለማፍረስ ሱዳን ካርቱም ላይ መሰርቶት የነበረውን ጣቢያ አጋልጧል ።
“የተሰነይ ጉባኤ ” በሚለው ፅሁፉ ወያኔ ፣ሸአቢያ እና ኦነግ በኢትዮጵያ ላይ የሰሩትን ሴራ ለህዝቡ አሳውቋል ። ለወደፊቱም የሚያጋልጣቸው ብዙ ሚስጥሮች እንዳሉት እና እያዘጋጃቸው እንደነበር ነግሮናል ።

ስታሊን ከአባት ሀገር ያባረረውን ሊዮን ትሮትስኪ በብዙ ሺ ኪሎ ሜትሮች ርቆ በሰው ሀገር ሜክሲኮ የሚኖር ቢሆንም የሊዮን ትሮትስኪ ነገር እንቅልፍ ሊሰጠው ስላልቻለ በመጥረቢያ አስፈልጦ አስገደለው ። ወያኔ በኬኒያ እና በሱዳን የሚኖሩ ተራ ስደተኞች እረፍት ሲነሷት ወደ አገሮቹ ጎራ በማለት እንደምትገድል ይታወቃል ። CIA ም ቢሆን ጠላቴ ትንሽ ነው ብሎ አይንቅም ። ኦነግም አቶ አሰፋ ጫቦ በሚፅፋቸው መራራ ሃቆች ሲቆስል ኖሯል ። ዛሬ አሰፋ ጫቦን አጥተነዋል ነገር ግን ስለአሟሟቱ እንድንጠይቅ የሚያስገድዱ ብዙ ጥርጣሬዎች አሉ ። አሰፋ ጫቦ ተገደለ ወይስ ” ሞተ? ” ። ይሄ እንቆቅልሽ ይፈታ ዘንድ ሁላችንም መጠየቅ እና ትክክለኛውን መልስ ማግኘት አለብን ።

ጋሼ አሰፋን “ያገኘነውም፣ ያጣነውም አብረን ነው” እንላለን

ታዋቂው ጸሐፊ እና የአደባባይ ሰው(ጋሼ)አሰፋ ጫቦ አረፈ። ጋሼ አሰፋ ያረፈው ትናንት እሑድ ሚያዝያ 15 ቀን 2009 ዓም፣ በስደት በሚኖርባት አሜሪካ ዳላስ ከተማ ነው። ከ1960ዎቹ ጀምሮ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ምህዳር ከታዩት ትጉህ ተዋንያን አንዱ ተደርጎ የሚቆጠረው ጋሼ አሰፋ፣ በዘመነ ደርግ ለ11 ዓመታት በግፍ ታስሮ ነበር። በዘመኑ ኢጭአት የሚባለውን ፓርቲ ካደራጁትና ካዋለዱት አንዱ እርሱ ነበር። የእስሩ ምክንያትም ከዚሁ የራቀ አልነበረም። በዘመነ ኢህአዴግ መጀመሪያ ላይ የሽግግር ምክር ቤቱ አባል ሆኖ አዲሶቹ ገዢዎች ዴሞክራሲን የምር ይቀበሉ እንደሆነ የበኩሉን ለማበርከት ሞክሯል። የዚህ ተሳትፎው ውጤት ግን ለብዙ እንግልት እና እንደወጣ ለቀረበት ስደት ዳርጎታል።

ጋሼ አሰፋ በትምህርቱ የሕግ ባለሞያ ነው። ሆኖም የአደባባይ ሕይወቱን ያለጽሑፍ ማሰብም ማኖርም የሚችል አይመስልም። በ1956 ዓ ም ለሥራ ከሔደበት ባህር ዳር ከተማ “ለፖሊስና እርምጃው” ጋዜጣ በላካት ጽሑፍ የተጀመረው የጋሼ አሰፋ የጽሑፍ ጉዞ የተቋረጠው በሁለት አጋጣሚዎች ብቻ ነበር። የመጀመሪያው በደርግ ታስሮ በቆየባቸው ዓመታት ነበር። ሆኖም በነዚህ ዓመታት ባይጽፍም ብዙ አንብቦና ተምሮ መመለሱን ይናገራል። ሁለተኛው የጸጥታ ወቅት አሜሪካ ከገባ በኋላ ለራሱ ባወጀውና “ሱባኤ ብጤ” ባለው የጽሞና ጊዜው ነበር።

ጋሼ አሰፋ በአማርኛ ሥነ ጽሑፍ የኢልቦለድ አጻጻፍ ታሪክ በአጻጻፍ ስልታቸው ድንቅ ሊባሉ ከሚችሉት ጥቂቶች አንዱ ነው ማለት ማጋነን አይሆንም። በሚያነሳቸው ቁም ነገሮችም ጋሼ አሰፋ፣ አባባይና ጎንታይ፣ አሰላሳይ እና ጋባዥ ጸሐፊ ነበር። በጋዜጦችና በመጽሔቶች ያሳተማቸው በርካታ መጣጥፎች አሉ። 28 የሚሆኑ መጣጥፎች የተሰባሰቡበት “የትዝታ ፈለግ” የተሰኘው መጽሐፉ ሚያዝያ 2008፣ ልክ ከዓመት በፊት፣ ታትሟል። በተጨማሪም ጋሼ አሰፋ በሕይወት ታሪኩ ላይ የተመሠረተ ሌላ መጽሐፍ በማዘጋጀት ላይ እንደነበር ለወዳጆቹ ይናገር ነበር።

ቀድሞ በጋዜጦችና በመጽሔቶች ተወስኖ የነበረው ጋሼ አሰፋ በቅርቡ በማኅበራዊ ሚዲያ በተለይም በፌስቡክ ጭምር ንቁ ተሳታፊ ሆኖ ነበር። ባለፉት ጥቂት ዓመታት በብሔረሰብ ተኮር (ዘውጌ) ፖለቲካ፣ በኢትዮጵያዊነት እና በሕዝቦቿ የጋራ እጣ ፋንታ ላይ በሬዲዮና በቴሌቪዥን በሚሰጣቸው ትንተናዎች አዲስ የመወያያና የክርክር ገበታ ዘርግቶ ነበር። “ኢትዮጵያዊነቴና ጋሞነቴ አይጣሉብኝም” በሚለው ማዕከላዊ እምነቱ የተቃኘው የፖለቲካ ትንተናው አሰባባሳቢ ምህዳር ለመፍጠር የሞከረበት የመጨረሻው ምእራፍ ይመስላል። አንዳንድ የታሪክ ትንተናዎቹ ግን አነጋጋሪዎች ነበሩ፤ በተለይ በአክራሪ የዘውጌ ብሔረተኞች አልተወደዱለትም ነበር። ሆኖም ክርክርና ውይይትን ከመጋበዝ ተቆጥቦ አልታየም። ለኢትዮጵያ እና ለልጆቿ ያለው ፍቅር እንዳልተናወጠ በጉልህ ይታይ ነበር።

በሕይወቱ ማለዳ ወደእርሱ ዓለም የመጡት ቀኝ አዝማች ኢልታሞ ኢቻ፣ ከጋሞ ባህልና ታሪክ፣ ከሕዝብ አገልግሎት እና ከመንግሥት ቢሮክራሲ ጋራ አስተዋውቀውታል። ገና የ13 ወይም 14 ዓመት ልጅ እያለ። በዚህ ውለታው የተነሳም ይመስላል በቀብራቸው ላይ ባለመገኘቱ ከሚቆጭባቸው አጋጣሚዎች አንዱ የኢልታሞ ቀብር መሆኑን ጽፏል። “የትዝታ ፈለግ” በሚል ርእስ በታተመው መጽሐፉ ራሱን እድለ ቢስ ይለዋል። ምክንያቱ ደሞ የሚያፈቅራቸውን ሰዎች ሌላው ቢቀር በቀብራቸው ተገኝቶ እርሙን አሉማውጣቱ ነው። “የማይታደሉ አሉ። እኔ በለቅሶ ጉዳይ እንደዚያ ነኝ። እስከ ዛሬ ድረስ ዘመድ ቆሜ አስቀብሬ አላውቅም። አፈር ሲመለስ አለማየቱ በሕይወት ላይ ክፍት ቦታ የሚተው ይመስለኛል። መሞታቸው የወሬ ወሬ እንጂ አይዘነጋም። ትዝ የሚለው ሞተዋል ተብሎ የተነገረው ሳይሆን በመጨረሻ በሕይወት የተለያዩት ነው። ለኔ እንደዚያ ነው።” ብሎ ነበር።

ጋሼ አሰፋ፣ ለባለውለታው ለቀኝ አዝማች ኢልታሞ ኢቻ የጻፈው ለራሱም ሊባልለት የሚገባና የሚቻል ነው። “ኢልታሞ የሠራውን ለመሥራት የሚያስችል ብዙ አመቺ እድል አልነበረውም። የሌለውን ዕድል ወይም የተገኘችውን ውሱን ዕድል ለታላቅ ሥራ አዋለው። ይህ ከታላቅ ሰዎች መለኪያ አንደኛና ዋነኛ ነው። የቅርብ ቤተሰቡን ይህ የጋራ ኀዘናችን ነውና በመንፈስ እዚያው ከእናንተው ጋራ ነኝ እላለሁ። ኢልታሞን ያገኘነውም፣ ያጣነውም አብረን ነው እላለሁ። የማይሞት ሥራው ግን ከእኛ ጋራ ይኖራል! በሥራው ይዳኝ!!”

ጋሼ አሰፋ አገሩን አጥብቆ ይናፍቅ ነበር። “ሕልም ባየሁ ቁጥር፣ ሰመመን ባየሁ ቁጥር የኢትዮጵያ መሬት፣ የኢትዮጵያውያን ፊት ብቻ ነው የሚታየኝ” ብሎ ጽፏል። ይህም ሞቱን የመለጠ አሳዛኝ ያደርገዋል። ይህ የገፋፋቸው ወዳጆቹና ጓደኞቹ ቢያንስ ቀብሩን በኢትዮጵያ መሬት ለማድረግ በጎ ፈንድ ገንዘብ ማሰባሰብ ጀምረዋል።

ዶ/ር መረራ ጉዲና በከሳሽ አቃቤ ህግ የተመሰረተባቸውን ክስ ለመቃወም ባለ 11 ገፅ የክስ መቃወሚያ አቀረቡ

ዶ/ር መረራ ጉዲና, ኢትዮጵያ እና የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ሊቀመንበር በማድረግ ረገድ ግንባር ቀደም የተቃዋሚ ቁጥር, እሱ በሽብርተኝነት እና ሌሎች የወንጀል ክስ ላይ የሙከራ ቆሞ ባለበት የፌዴራል ፍርድ ቤት መቅደም የተቃውሞ አቅርቧል.

ጉዲና ሁለት ሌሎች ሰዎች, ጃዋር መሐመድ, አንድ ታዋቂ የኦሮሞ ተሟጋች, እና በኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ዋና ዳሬክተር እና ብርሃኑ ነጋ ጋር ክስ ነበር. ክሶቹ የካቲት 23, 2017 ላይ ይታወቅ ነበር.

የአዲስ መደበኛ ዜና መተላለፊያውን በአሁኑ የተቃውሞ ጉዲና ያነሳው ጋር ዓቃብያነ ወደ የተቃውሞ ምላሽ ለመስጠት ያህል, ጉዳዩ ቅደም ግንቦት 4 ድረስ ከተበተነ ዘግቧል.

ዶክተር መረራ ፍርድ ቤት ወረቀቶች መሠረት ቤልጂየም እና የአውሮፓ ፓርላማ አድራሻ የሚያደርገውን ጉዞ የእርሱ ቀጠለ በእስር ምክንያቶች መሆን የለበትም በማለት ይከራከራሉ. እሱም ጉዞ ዓቃብያነ እጨነቃለሁ ሊሆን ክሶች አንዱ የሆነውን የአስቸኳይ ሁኔታ, በደል ጋር ምንም ግንኙነት ነበረው መሆኑን ታክሏል.

በተጨማሪም እርሱ restive ክልሎች ውስጥ ተቃውሞዎች ውስጥ መጨመር ለምን ነበር መሠረት የሆነውን መካከል ፀረ-መንግስት ማሰራጫዎች, ወደ ቃለ ለስፔን claimes ተከልክሏል.

ባለፈው ዓመት ታህሳስ ውስጥ የአውሮፓ ጉብኝት ጀምሮ ሲመለስ ላይ ተይዞ የነበረው የትምህርት እሱ ቀደም ሲል የአስቸኳይ ደንቦች ሁኔታ መመሪያችሁን ምክንያት ተካሄደ እንኳ በሽብርተኝነት ክስ ነበር.

እርሱ በጣም ለሕዝብ ተሳትፎ ብራሰልስ ውስጥ የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ ላይ አንድ አድራሻ የመላኪያ ባይሆንም እንኳ ጉብኝት ወቅት ፀረ-ሰላም አባሎች ጋር ተገናኝቶ ሊሆን ይነገራል. እሱም አቃብያነ ማስረጃ ለመሰብሰብ ስንቀጥል ጊዜ በርካታ የዋስ ተከልክሏል.

ወደ አገር በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች ውስጥ ፀረ-መንግስት ተቃውሞ ለማስቆም ወደ ባለፈው ዓመት ጥቅምት ላይ እላፊ የተደረጉ.

የ እላፊ መስጠትን ትእዛዙ ፖስት አንጻራዊ ሰላም አገር ተመልሶ ሆኗል ይላል. ፓርላማ በቅርቡ ጥቅምት 2016 ውሳኔ ጋር የመጡትን ገደቦች በአብዛኛው ዘና በኋላ የአስቸኳይ ሁኔታ ይዘልቃል.

በተጨማሪም አገር አብዛኛዎቹ ክፍሎች ውስጥ የዘገየ ኢንተርኔት ጋር ግንኙነት መዳረሻ ዙሪያ ጉዳዮች አሉ. በአንዳንድ የአውሮፓ አገሮች ጋር ኢትዮጵያ ያላቸውን የጉዞ ምክር ከፍ ባደረጋችሁት ‘ሰላም መመለስ.’

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የ2017 የዓለም የፕሬስ ነፃነት ጀግና ሆኖ ተመረጠ (ዋዜማ)

ዋዜማ ራዲዮ- ዛሬ ሚያዚያ 17 ቀን 2009 ዓ.ም አለም አቀፍ ፕሬስ ኢንስቲትዩት ከቪየና በወጣው መግለጫ መሰረት እስክንድር ነጋ የግል ህይወታቸውን መስዋዕት በማድረግ ለንግግር ነፃነት የጎላ አሰተዋፅዎ ያበረከቱ ጋዜጠኞችን ለማክበር እና ለማወደሰ በየአመቱ የሚሰጠውን የዓለም የፕሬስ ነፃነት ጀግና ሽልማት እንዲሰጠው ተወስኗል። የሸልማቱ ሰነስርዓት በግንቦት 10 ቀን 2009ዓ.ም በጀርመን አገር ሃምቡርግ ከተማ ይከናወናል።

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ተደላድሎ የጋዜጠኝነት ስራውን ከሰራባቸው አመታት ይልቅ የታሰረባቸው አመታቶች ይልቃሉ፡፡መንግስት ብቻውን ማሰር አልበቃ፣ አላጠግብ ሲልው ከነመላው ቤተሰቡ አስሮታል በ1997ዓ.ም።

እስክንድር ነጋ ብቸኛ ልጁንም ወልዶ ለመሳም እንድ ማንኛውም ዜጋ የታደለ አልነበረም፡፡ በአዲስ አበባ ቃሊቲ ማርሚያ ቤት ከማዶ በተለምዶ “የእምጫት” ቤት ተብሎ በሚጠራው የሴት እስረኞች ክልል ባለቤቱ ሰታምጥጥ እስክንድር ቀበቶውን ፈቶ አብሯት አላማጠም። ለብቻዋ እስር ቤት ውስጥ አምጣ እንድትወልድ የተገደደችው ባለቤቱ ጋዜጠኛ ሰርክዓለም ፋሲል በሰላም መገላገልን በወሬ ወሬ በሶሰተኛ ወገን ስማ እንጂ።

ልጁንም ክርስትና ለማስነሳት የሚያሰችል ወግ እና ማዕረግም አልደረሰው፡፡ ተወልዶ በአይኑ ያላየውን በእጁ ለማቀፍ የጓጓውን ልጁን ናፍቆት ብሎ የስየመውም ለዚሁ ነበር፡፡ ኢትዮጲያ ውስጥ በጋዜጠኝነት ሙያ እና ለንግግር ነፃነት መከበር ለሚደርስ በደል፣ ግፍ፣ መከራና ኢፍታዊነት የመጨረሻውን ፅዋ በትዕግስት በትህትና እንዲሁም በልዕልና ዜጎች የሚከፍሉትን የህይወት ዘመን ዋጋ እንድ ማሳያ ከሚሆኑ በርካታ ጋዜጠኞች መካከል አንዱና ዋንኛው ነው እስክንድር ነጋ፡፡

መስከረም ሶስት ቀን 2004 ዓ.ም ልጁን ናፈቆት ከትምህርት ቤት ወደ ቤት እያመጣ ሳለ በማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ፖሊሶች ከልጁ ፊት ተይዞ ለእስር የተዳረገው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ከታሰረ 2 ሺህ 35 ቀናቶች ተቆጥረዋል፡፡ የህግ ጠበቃ፣ የሃይማኖት አባት፣ ቤተስብ እንዲሁም ወዳጅ ዘመድ መንገደኛ እንዳይጠይቀው እገዳም ተጥሎበታል፡፡

በአሁኑ ሰዓት በአዲስ አበባ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት እስኪርቢቶ፣ ወረቀት እና መፀሃፍ በጭራሽ እንዳይዝ የተከለከለው ጋዜጠኛ እስክንድር፣ ቃሊቲ አብረውት የከረሙ ሁሉ ስለመልካም ትህትናው፣ ለሰላማዊ ትግል ሰላለው ቆራጥነት እንዲሁም ከፍተኛ የፍትህ ጥማት በአንድ ቃል የሚመሰክሩ ቢሆንም መንግስት ግን እስክንድርን በሽብር ክስ ከመክሰስ ወደ ኃላ አላስቀረውም።

ጦማሪ እና ጋዜጠኛው እስክንድር ነጋ የሽብር ቡድን ተበሎ በፓላማ ከተሰየመው የግንቦት ሰባት ከፍተኛ አመራሮች ጋር በህቡዕ ግንኙነት በማደርግ፣ ሁከትና ብጥብጥ ለመፍጠር በማሰብ እና ቀሰቃሽ ፁሁፎቹን በመፃፍና በማሰራጨት የሚል ክስ በመንግስት ይመስረትበት እንጂ ወደ እስር ቤት እንዲገባ ዋንኛ መነሾ የሆነው የፀረ ሸብር አዋጁን መንግስት የተለየ ድምፆችን ለማፈን እንድሚጠቀምበት እስክንድር በተደጋጋሚ በመተቸቱ ነበር።

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የቀደሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የፀረ ሸብር አዋጁን አላግባብ በመጠቀም ጋዜጠኞችን እና ተቃዋሚዎችን ድምፅ ለማፈን እየተጠቀሙበት ሰለመሆኑ፤ ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ፣ ርዕዮት አለሙ እንዲሁም የኢትዮጲያ መንግስት ያሰራቸው ሁለቱ የስዊዲን ጋዜጠኞች ማርቲን ሽብዬ እና ጆሃን ፐርሰን የፀረ ሽብር አዋጁ ተገን በማደረግ መንግስት የንግግር ነፃነታቸውን ተጠቅመው በመፃፋቸው ለእስር እንደዳረጋቸው በተደጋጋሚ ተችትና አሰተያየት መሰነዘሩን ተከትሎ እርሱም ለእስር ተዳርጓል።

የጋዜጠኞቹን መታሰር አሰመልክቶ እስክንድር በጊዜው ለአለም አቀፍ ፕሬስ ኢንስቲትዩት “የጋዜጠኞቹ መታሰር የፍራቻን ዘር ለመዝራት በስሌት የተደረገ እስራት ነው፡፡ አምባገነኖች የሚተማመኑበት መቋሚያቸው በህዝባቸው ውስጥ ፍርሃትን መንዛት ነው” ብሎ ነበር።

ጋዜጠኛ ውበሸት ታዬ በከፍተኛው ፍርድ ቤት የ14 ዓመት እስራት ሲፈረድበት፣ ሁለቱ የሲውዲን ጋዜጠኞች ማርቲን ሽብዬ እና ጆሃን ፐርሰን ድግሞ አስራ አንድ አመት ተፈረዶባቸው ነበር፤ እስክንድር ነጋ ከሁሉም ከፍተኛ የሆነውን የአስራ ስምንት አመት ፍርድ ተሸክሟል።

የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት እስክንድር ላይ በ 2004 ዓ.ም የአስራ ስምንት ዓመት ፅኑ እስራት እና የአምስት አመታት ህዝባዊ መብቶች እግድ ቢጥለበትም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የዘፈቀደ እሰራቶችን የሚመለከተው ክፍል የጋዜጠኛ እስክንድር እሰራት ዓለም አቀፍ ህግጋቶችን የሚፃረር እንድሆነ በመገለፅ እስራቱን ኮንኗል

የፍርድ ቤቱ አሰራር ከፍትህ የአሰራር ስርዓት ውጪ በአሰፈፃሚው ኢህአዴግ እንድሚዘወር ለማንም ሰው ግልፅ ቢሆንም ሁለቱ የሲውዲን ጋዜጠኞች ማርቲን ሽብዬ እና ጆሃን ፐርሰን በይቅርታ እንዲፈቱ ገዢው መንግስት ሲፈቅድ ጋዜጠኛ ውበሸት ታዬ እና እስክንድር ነጋ ግን በዝዋይ እና በቃሊቲ እስር ቤቶች መንግስትን  በፅኑ በመተቸታቸው ብቻ አመታትን ይቆጥራሉ።

“አምባገነኖች ፊት ለንግግር እና ለሃሳብ ነፃነት ሲል ያለፍርሃት በእውነት በመቆሙ እና ለዓላማው ፅናት ፣ የኢትዮጲያ መንግስት የፀረ ሽብር አዋጁን ተቃዋሚዎችን እና የተለየ አተያይ ያላቸውን ወገኖች ለማፈን እየተጠቀመበት ስለመሆኑ በድፍረት በመናገሩ ለዚህም ላሳየው ትጋት ተሸልሟል፡፡” ብለዋል በመገለጫቸው የአለም አቀፍ ፕሬስ ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ባርባራ ትሪዊኒፊ።

ሽልማቱ የእስክንድር ነጋ ጀግንነትን ለማሰብ፣ መንግስት በተደጋጋሚ የሚያደርስበትን ጫናና ጭቆና እንዲያቆም ለመጠየቅ እንዲሁም መንግስት እስክንድር ነጋን እና ሌሎች እንደ እርሱ ሃሳባቸውን በነፃነት በመግለፃቸው ብቻ የታሰሩ ጋዜጠኞችን እንዲፈታ ለማሳሰብ እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ኢትዮጲያ ለሰብዓዊ መብቶች መከበር የገባችውን ቃልኪዳን እንድታከብር ጥሪ እንዲያቀርብ ለማስታወስ ያለመ ነው።

የእስክንድር ነጋ ባለቤት ጋዜጠኛ ሰርክዓለም ፋሲል በበኩሏ እስክንድር የተሸለመውን ሽልማት አሰምልክታ በመግለጫው “ለመናገር ነፃነት የከፈለው ከፍተኛ ዋጋ በአለም አቀፍ መደረኮች ትኩረት ሰላገኘ እጅግ በጣም ደስ ብሎኛል። የሚከፈለው መሰዋዕትነት እንደሁ በከንቱ አልቀረም። “

“እርሱ በእስር ቤት የሚከፍለው ዋጋ እና መሰዋዕትነት ምንም እንኳን ለእኔ እጅግ አሰቸጋሪ ቢሆንም ሌሎችን ስለሚያበረታ እና ተከታዬችንም ሰለሚያፈራ ያሰደሰተኛል። ይህም ሽልማት የእርሱን ነፃነት የሚያፋጥን እና ለረጅም እስሩ መቋጫ እንድሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ።”ብላለች።

ለንግግር ነፃነት መከበር ዝብ ለቆሙ  በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚሰጡ ከፍተኛ ሽልማቶችን ሁሉ በየዓመቱ የሚሸለመው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ መንግስት ለስምንተኛ ጊዜ ሲያሰረው በተቃራኒው በ2004ዓ.ም ፔን አሜሪካ ከተባለ አለማቀፍ ድርጅት በአደገኛ የመገናኛ ብዙሐሓን ድባብ ውስጥ ሆኖ በመፃፍ ላደረገው አስተዋፅዎ “የመፃፍ ነፃነት ሽልማትን” ስጥቶታል

በድጋሚ በዚሁ 2004 ዓ.ም አለማቀፉ የሰብዓዊ መብት ተማጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል እስክንድር ነጋ የህሊና እስረኛ ስለመሆኑ አውጇል፡፡

በታህሳስ 2005ዓ.ም ደግሞ የሂውማን ራይትስ ዎች የነፃ ንግግር ሽልማት አሸናፊ ነውበ36ተኛው አለማቀፍ የፀሃፊዎች ፌስቲቫል ላይም እስክንድር ነጋ የፔን ካናዳ “የአንድ ስብዓዊነት ሽልማት” አሸናፊ ነው

አለም አቀፍ ጋዜጦች እና ዜና አታሚዎች ማህበር በበኩሉ  በጥር ወር 2006 ዓ.ም የጎለደን ፔን ፍሪደም ሽልማትን ለእስክንድር ሸልሟል።

የአርባ ስምንት አመት ጎልማሳው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በመሰከረም ወር 2004 ሲታሰር አብሮት የታሰረው እና በጋራ ክስ የተመሰረተባቸው የቀደሞ አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበርና የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አንዱዓለም አራጌም የእድሜ ልክ እስራቱን በአዲስ አበባ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት እየገፋ ይገኛል