በምሥራቅ ወለጋ የተፈጸመው ብሔርን መሠረት ያደረገ ጥቃት እንዳሳሰበው ኢሰመኮ ገለጸ

የኢሰመኮ አርማ

ባለፈው ሳምንት በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ ኪራሙ ወረዳ ውስጥ ታጣቂዎች በነዋሪዎች ላይ ብሔርን መሠረት ያደረገ ጥቃት መፈጸማቸው በእጅጉ እንዳሳሰበው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ገለጸ።

ኮሚሽኑ ባወጣው መግለጫ ላይ እንዳመለከተው ነሐሴ 12/2013 ዓ.ም “ኦነግ ሸኔ” ናቸው በተባሉ ታጣቂዎች በተፈጸመው ጥቃት ከ150 በላይ ነዋሪዎች መገደላቸውን ከአካባቢው ነዋሪዎችና ከሌሎች ሰዎችም መረዳቱን ገልጿል።

በጊዳ ኪራሙ አካባቢ ተሰማርተው የቆዩ የፀጥታ ኃይሎች ማክሰኞ ወደ ሌላ አካባቢ መሄዳቸውን ተከትሎ በነጋታው ረቡዕ ነሐሴ 12/2013 ዓ.ም ታጣቂዎች “ብሔርን መሠረት ያደረገ ጥቃት ማድረሳቸው በከፍተኛ ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑን” ኮሚሽኑ ገልጿል።

ይህንንም ተከትሎ የወረዳው ነዋሪዎች በተለይም ሴቶችና ሕጻናት ወደ አጎራባች አካባቢዎች መሸሻቸውን የሰብአዊ መብት ተቋሙ በመግለጫው ላይ ጠቅሷል።

“በቀጣይ ቀናትም ከነዋሪዎች የተውጣጡ ሰዎች ብሔርን መሠረት ያደረገ የአጸፋ ጥቃት በማድረሳቸው 60 ሰዎች መገደላቸውን፣ ነዋሪዎችም ወደ አማራ ክልልና ወደ ኪራሙ ከተማ መፈናቀላቸውን” ኮሚሽኑ ገልጿል።

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ የፌዴራልና የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ለጥቃቱ መፈፀም ክፍተት የፈጠረው የፀጥታ ኃይሎች ከአካባቢው የወጡበትን ምክንያት እንዲያጣሩ ጥሪ አቅርበዋል።

ጥቃት ተፈጽሞ በርካታ ሰዎች ከተገደሉ በኋላ የፀጥታ ኃይሎች ወደ አካባቢው እንደተመለሱና ጊዳ ኪራሙ ወረዳ ወደ መረጋጋት መመለሱን ነገር ግን በወረዳውና በአጎራባች ወረዳዎች አሁንም የፀጥታ ስጋት እንዳለ ነዋሪዎች እንደተናገሩ ኢሰመኮ አመልክቷል።

የክልሉ የፀጥታ ኃይሎች ከፌዴራል የፀጥታ ኃይሎች ጋር እንዲቀናጁና የአካባቢውን ነዋሪዎች ደኅንነት እንዲያረጋግጡ የጠየቁት ኮሚሽነሩ፤ “በተለይም በአካባቢው ተሰማርተው የነበሩ የፀጥታ ኃይሎች ስምሪት እና እንቅስቃሴን የተመለከተ አሠራር ተገቢው ምርመራ ሊደረግበት ይገባል” ብለዋል።

ኢሰመኮ ጨምሮም ስለ ክስተቱ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር ክትትሉን እንደሚቀጥልና “የአካባቢው ፀጥታ የደረሰበት አስጊ ደረጃ ወደ አጎራባች አካባቢዎች እንዳይዛመትና የበለጠ ሰብአዊ ቀውስ እንዳያደርስ አስቸኳይ እርምጃ መውሰድ አስፈላጊ ነው” በማለት አሳስቧል።

ለታጣቂዎቹ ጥቃት ተጋላጭ የሆኑ አካባቢዎችን ፀጥታ በዘላቂነት ለመጠበቅ የፀጥታ ኃይል እንዲጠናከር የፌዴራል መንግሥት ትኩረት እንዲሰጥ እንዲሁም በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት የፈጸሙ በሕግ ተጠያቂ እንዲሆኑ የፌዴራልና የክልሉ ኃላፊዎች በቅንጅት እንዲሠሩ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ጥሪ አቀርቧል።

በምሥራቅ ወለጋ ውስጥ በሚገኙ አካባቢዎች ተመሳሳይ ጥቃቶች በሰላማዊ ነዋሪዎች ላይ በታጣቂዎች በተደጋጋሚ ሲፈጸም የቆየ ሲሆን፤ በመንግሥት ኦነግ ሸኔ የሚባለውና እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን ጥቃቱን በማድረስ ይከሰሳል።

በአካባቢው እንደሚንቀሳቀስ የሚነገረው ይህ ታጣቂ ቡድን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሽብርተኛ ቡድን ተብሎ የተሰየመ ሲሆን በቅርቡ ከህወሓት ጋር ጥምረት መፍጠሩን ማሳወቁ ይታወል።

ሰዓቱ አሁን ነው! በዓለም አቀፍ ቌንቌ ተምረን ብሄር ተጠየቅን! እናት ሃገራችሁ ትፈልጋችኃለች! – ፀ/ት ፂዮን ዘማርያም(ኢት-ኢኮኖሚ)

ቴዎድሮስ አበባው ያዲስአበባው…ነፍስ ይማር!!! ታላቁ እስክንድር ተደራጁ ….ተደራጁ….ተደራጁ!!! ብሎል፡፡

የኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ አስር ሚሊዮን የፖለቲካ ምላሳዊ ካድሬ ለሃያ ለሠላሳ አመታት በጥገኝነት ደሞዝ እየተሰፈረላቸው፣ መኪና ተሰጥቶቸው፣ ቤት ተሰጥቶቸው፣ መሬት  ከአንድም ሁለት ሶስቴ ተበርክቶላቸው፣እንደ መዥገር ተጣብቀው እናት አገራችንን ህዝቡን ሲበዘብዙ ኖረዋል፡፡ የህክምና ዶክተሮችና የጤና ባለሙያዎች ሥራ አጥተው ሲሰቃዩ ማት ይህ ሥርዓት ከነሰንኮፉ እስካልተወገደ ድረስ የብልፅግናው መንገድ የጨለመ ለመሆኑ አብይን ማማከርና መጽሃፉን መግለጽ አሊባባና አርባዎቹ ሌባዎችን ታሪክ ያስታውስሃል፡፡ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘመን ወጣቶች የህወሓትና የብልጽግናን የሥርዓት እድፍ አጥባችሁ አዲስ ሥርዓት ለመገንባት ከመታገል ሌላ አማራጭ የላችሁም፡፡ ሰዓቱ አሁን ነው! እናት ሃገራችሁ ትፈልጋችኃለች!

አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ/መጋቢት 6 ቀን 2013 ዓ.ም/አዲስ አበባ ሸዋ…ካለፈው አንድ ዓመት ጀምሮ የስራ ምደባ ወይም ቅጥር ባለመሰራቱ እየተጉላሉ ያሉ የህክምና ዶክተሮች በባህርዳር ሊያደርጉት የነበረው ሰላማዊ ሰልፍ ከላይ ታዘናል ባሉ የልዩ ሀይልአባላት እና አድማ በታኞች አማካኝነት ክልከል ገጥሞታል። የመጋቢት 7 ዜናዎች- ወሎ ቤተአምሀራ /በሀኪም እጥረት እናቶች የሚሞቱበትና ስራ አጥ ሀኪሞች የበዙበት ../ በሰኔ 15 ሰበብ የታሰሩ የጦር መኮንኖች ጉዳይ..https://youtu.be/k9gpEz_0PiM  (1)

በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የታክሲ አገልግሎት የሚሰጡ የታክሲ ባለንብረቶችና ሹፌሮች በተደጋጋሚ በሚደርስባቸው ዘረኛና ተረኛ አድሎዊ አሠራርን በመቃወም በቤንዚን ዋጋ መጨመር የተነሳ የታክሲ መሳፈሪ ዋጋ ተመን ጋር የተጣጣመ ባለመሆኑ የተነሳ ሰኛ እለት የሥራ ማቆም አድማ አድርገዋል፡፡ መንግሥት የጣለባቸው የተከማቸ የትራፊክ ቅጣት እንዲነሳላቸውም ጠይቀዋል፡፡  የአዲስ አበባ ህዝብ በዋጋው ጭማሪ የተነሳ በኑሮ ውድነት እየተሰቃየ ይገኛል፣ የታክሲ አገልግሎት ማግኘት ባለመቻሉ በታክሲ ሠልፍ ጥበቃ  ሥራ ተስተጎጉሎል፡፡ መንግሥት ሃምሳ ስድስት የታክሲ ሹፌሮችን አድማውን አስተባብራችኃል በማለት አስሮል፡፡ አድማው ማክስኛም ቀትሎል፡፡

Much of Addis Ababa has been paralysed as taxi drivers on Monday embarked on a strike to protest a revised tariff for city trips, APA can report on Tuesday. (2)

Hundreds of taxi drivers brought the Ethiopian capital to a standstill, saying the revised fare was not proportional to increased fuel prices. The government increased the price of fuel twice in a month after its fuel import from neighboring Sudan was halted due to a border conflict. “We already have much lower fares against increasing prices of fuel,” said the taxi owners and drivers. They also want the government to cancel fines which have been accumulated over the years. Although the authorities increased the peak hour frequency of public transport on Monday, a lot of passengers were affected by the strike. There have been long queues of passengers in Megenagna, Ayat Kolfe and Awtobestera areas.  The strike especially affected those people who live in the outskirts of Addis Ababa where train service is not available.

Addis Ababa City Transport Head Engineer Sitotaw Tekele said the fares were revised based on the paying ability of passengers and increased fuel price. “The government will take stringent measures if the protest continues,” he added.  Police said they have arrested 56 taxi drivers over the protest which they claimed was infiltrated by individuals with political motives. The strike has continued in some parts of the city on Tuesday.

‹‹የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ግንቦት 28 ቀን 2013 ዓ/ም አገራዊ አጠቃላይ ምርጫ ከስድስተኛው አገራዊ ምርጫ፣በ49407 የምርጫ ጣቢያዎች ለሚሠማሩ የምርጫ አስፈፃሚዎች ሁለት ቢሊዮን ብር እንደሚያወጣ ታወቀ፡፡ ለመቶ ኃምሳ ሽህ የምርጫ አስፈፃሚዎች 1.8 ቢሊዮን ብር ይከፈላል፡፡ 182 የዞን አስተባባሪዎችና 2019 የምርጫ ክልል አስተባባሪዎች 105648000 ብር ይከፍላል፡፡  የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም (ዩኤንዲፒ) በዓይነቱ የ 40004000 ዶላር ድጋፍ የሚደረግለት ሲሆን፣ የዚህም ዓላማ ቦርዱን ብቁ፣ ግልጽና የሚታመን ተቆም ለማድረግና አካታች፣ ግልጽና ተዓማኒነት ያለው ምርጫ ማድረግ እንዲችል ለማገዝ ነው፡፡››  (3)

የኦሮሞ ነጻ አውጭ ግንባር (ኦነግ) ዳውድ ኢብሳ ነጻና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ለማካሄድ አስፈላጊ መስፈርቶች ለማሟላት ብልጽግና ፓርቲ ፍላጎት ስለሌለው ከምርጫው ለመውጣት ተገዶል፡፡ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) መሪ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና  በኦሮሚያ የተለያዩ ስፍራዎች የተዘጉ ቢሮዎቻቸው እንዲከፈቱ፣ እንዲሁም ታማኝነት ያለው ምርጫ ለማድረግ የሚያስችል አገራዊ ምክክር እንዲደረግ ጥሪ ሲያቀርብ ነበር። አገራዊ ምርጫ ተገፍቶ ለመውጣት ተገድዷል። የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማፓርቲ በኦሮሚያ ክልል ቢያንስ በ46 (አርባ ስድስት) የምርጫ ወረዳዎች ዕጩዎቹን ማስመዝገብ እንዳልቻለ አስታውቆል፡፡ አሁን እንደምናየው ብልፅግና ኦሮሚያ ላይ ብቻውን ለመወዳደር እየሄደበት ያለው መንገድ አገርንም ጭምር ከፍተኛ ዋጋ ያስከፍላል፡፡›› በኦሮሚያ ክልል፣ የኢዜማ የአድአ ምርጫ ወረዳ 1 ሊቀመንበር የነበሩት አቶ ግርማ በግፍ በጥይት ተገድለዋል፡፡  (3)

ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ፡-ቴዎድሮስ አበባውን በአሰቃቂ ሁኔታ ገድለውታል፡፡ ታላቁ እስክንድር ተደራጁ ….ተደራጁ….ተደራጁ!!! ብሎል፡፡ የአዲስ አበባ ህዝብ ህብረ ብሄር ህዝብ እንኳን ኦነግን የደርግ ኢሠፓንና ህወሓት ኢህአዴግን አሸንፎል፡፡ አዲስ አበባ የሁሉም ብሔር ብሄረስብ፣ የኦሮሞው፣ አማራው፣ ጉራጌው፣ ወላይታው፣ ሱማሌው፣ ጋምቤላው፣ ወዘተ የሁሉም አፍሪካ፣ ዓለም አቀፍ ሜትሮፖሊያን ከተማ ነች፡፡ አዲስ አበባን ከተማ ሜትሮፖሊያን ከተማ ሆና እንድትቀጥል ትግል ይጠይቃል፡፡

የኦሮሞ ነጻ አውጭ ግንባር (ኦነግ) እና የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) በምርጫው ተገድደው በመባረራቸው እጃቸውን አጣጥፈው ይቀመጣሉ ማለት የዋህነት ነው፡፡ ሁለቱም በኦሮሚያ ህዝብ ከፍተኛ ተከታዬች ያሎቸው መሆኑ ፀሐይ የሞቀው ዓለም ያወቀው ጉዳይ ነው፡፡ ኦነግ በተለይ በወለጋና በባሌ እንዲሁም ኦፌኮ በሸዋ፣ በሐረር፣ በአርሲ ከፍተኛ ህዝባዊ ድጋፍ እንዳላቸው ይታመናል፡፡ በስድስተኛው ዙር ምርጫ የማይሳተፉት ኦነግና ኦፌኮ ባላቸው ህዝባዊ ድጋፍ  ምን ሊሰሩ ይችላሉ ብለን ብንመረምር ውስጥ ውስጡን አንደኛ ምርጫው እንዲደናቀፍ  የቄሮ ወጣቶችን ኦነግና ኦፌኮ በጋራ በስድስተኛው ዙር አገር አቀፍና ክልላዊ ምርጫ የትግል ጥሪ ይዘት፣ የቄሮ ወጣቶችን በማሰማራት ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና መሃበረሰባዊ ዉሳኔዎች በማስተላለፍ  የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከግንቦት 28  አስከ  ሰኔ 5 ቀን 2013 ዓ/ም የአዲስ አበባና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምርጫ ሊያደርጉ የሚችሉት የትግል ስልት ከወዲሁ ሊያሴሩ የሚችሉትን መተንበይ ይቻለናል፡፡ የኦሮሞ ነጻ አውጭ ግንባር (ኦነግ)

  • አውራ መንገዶች ዝግ ማድረግ ኦሮሚያን ከሌሎች ክልሎች ጋር የሚያገናኙ፣ የህዝብ ትራንስፖርት፣ የጭነት መኪኖች ወዘተ ማገድ
  • ከኦሮሚያ የሚቀርቡ ምርቶች ሁሉ የግብርና ሌሎች ለገበያ እንዳይቀርቡ በማድረግ ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ ማድረግ
  • ግብር መሰብሰብ አይቻልም ኦሮሚያ ውስጥ የሚገኙ መንግስታዊ መዋቅሮች ግብርና ታክስ እንዳየከፍሉ በማድረግ የኢኮኖሚ አሻጥር ማድረግ
  • የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር የንግድ ሥራ ማቆረጥ የመሳሰሉትን የትግል ስልቶች ሊያከናውኑ ይችላሉ፡፡

ዶክተር ዐቢይ አህመድ ለኦነግ መረጃ አሳልፎ ይሠጥ ነበር፣ ለኦነጉ ለገሠ ወጊ መረጃ ይሰጡት እንደነበረ መስክሮል፡፡

በመሆኑ ይህ በሃገሪቱ ያለው የህገወጥ የመሣሪያ ንግድ ዝውውር ከምርጫው በፊት፣ የመገደያችን ሹጉጦቹ፣ ጠመንጃዎቹ፣ ቦንቦቹ፣ የመታረጃችን ሜንጫው፣ ገጀራው፣ ካራው፣ ቀስቱ ወዘተ ከወዲሁ ያልተያዘው ህገወጥ የጦር መሣሪያዎች እንዲሰበሰብ ምርጫ አስፈፃሚዎች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርዱን ብትጠይቁ ለእራሳችሁና ለህዝብ ፀጥታና ደህንነት ትተርፋላችሁ!!! ካለዛ ግን እንኳን መከላከያ ሠራዊት ወፍ አይደርስላችሁም!!!

ኦነግና ኦዴፓ ብልጽግና ስድስተኛውን ዙር ምርጫ ማሸነፉን ቀድሞ በማወቁ የአዲስ አበባና ድሬዳዋ ከተማን የህዝብ ምርጫ እንደሚሸነፉ ከወዲሁ በማወቃቸው የተነሳ ልዩ ልዩ ሴራ በመንደፍ ላይ ናቸው ፡፡ የቄሮ የትግል ጥሪ ይዘት፣ የቄሮ ፖለቲካዊ, ኢኮኖሚያዊ, እና መሃበረሰባዊ ዉሳኔዎች እና ይዘታቸዉ እንዲሁም የትግራይ ክልል በህወሓት ላይ የታወጀ ጦርነት አጋር በመሆን ስውር ግንኙነት እንደሚያደርጉ ይታመናል፡፡ ኦነግ የኦሮሞ ህዝብ በስብዓዊ ጋሻነት በመያዝ በወለጋ ሆሮ ጉድሩ ውስጥ ኖሪ የሆኑትን የአማራ ተወላጆች ቀያቸውን በሦስት ቀናት ውስጥ ለቀው እንዲወጡ በየቦታው ወረቀት ተለጥፎል ህዝቡም ቀየውን እየለቀቀ ወደ ከተማ በመግባት ላይ ናቸው፡፡ ኦነግና ኦዴፓ ብልጽግና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርዱ አይቶ እንዳላየ ዝምታ መርጦል፡፡ በደቡብ ክልል በጉጂ ታጣቂ ቡድን አማሮ፣ ዲላ፣ አዲስ አበባ አውራ ጎዳና መንገድ ተዘግቶል፡፡ በሌላ በኩል በጉራጌ ዞንና አካባቢው ያለ ችግር ተጠናክሮ ቀጥሎል፡፡ ኦነግና ኦዴፓ ብልጽግና የኢትዮጵያን ህዝብ በፍርኃት ቀንበር ውስጥ ከተው ለመቶ አመት እንገዛለን ብለው ያስባሉ፡፡ ኦነግና ኦዴፓ ብልጽግና ከህወሓት ኢህአዴግ ውድቀት መማር አልቻሉም፡፡

ኦነግና ኦዴፓ ብልጽግና ፓርቲ ክስ ውስጥ፡-

‹‹የኦሮሞ ብሄርተኝነት እንደ አሸባሪነት ተቆጥሮል፣ የዴሞክራሲ ጭላንጭል ጠፍቶል በኦሮሚያ ውስጥ ሰዎች ይገደላሉ፣ ሴቶች ይደፈራሉ፣ በወለጋ፣ በበቆጂ፣ ኦነግ መንግሥት የለም ከመስከረም 25 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ ኦሮሚያ የደም መሬት ሆኖል፣ የብሄር ብሄረሰቦች መንግሥት የነበረው መንግሥት በዶክተር አብይ መንግስት የነፍጠኛ ሥርዓት  አህዊ ሥርዓት ተተክቶል ይላሉ፡፡ የዶክተር አብይ መንግሥት ኦዴፓ ብልፅግና የአራት ኪሎው መንግሥት ህቡዕ ሥርዓት  1.5 ቢሊዮን ብር የሠጡት ባለፀጎች ናቸው፡፡ ኢሳያስ አፈወርቂና ዐብይ አህመድ በህቡዕ ፀረ- ኢትዮጵያ አጀንዳ ያራምዳሉ፣ ጨፌ ኦሮሚያ  የሚያካሂደው ስብሰባና የሚያወጣው ህግ  ኢህገመንግሥታዊ ስለሆኑ ተቀባይነት የላቸውም፣ በዚህም መሠረት ይሄን የሚተካ የሽግግር መንግሥት እንመሠርታለን፡፡ የኦሮሞ እስረኞች በትግላችን እናስለቅቃለን  የአብይ መንግሥት በአባ ቶርቤ ሥም ይገድላል፣ ፍርድ ቤት የለቀቀውን እስረኛ  ፖሊስ አለቅም የሚልበት የአብይ መንግስት ነው፡፡ የአብይ መንግስት የማይቆጣጠረው የትግራይ መንግስት፣ የኦሮሚያ ክልል መንግሥት መንግሥታዊ መዋቅሮች ሠባብረን የሽግሰግር መንግሥት እነናቆቁማለን፣ የምርጫ ቦርድ ምርጫ በኦሮሚያ ምድር የሽግግር መንግሥት ማቆቆም እቅድ አላቸው፡፡›› ክሱ በውሸትና ቅጥፈት ላይ የተመሠረተ ቢሆንም ኦነግና ኦዴፓ ብልጽግና ስውር ግንኙነት እንዳላቸው ይታወቃል፡፡

የኦሮሞ ነጻ አውጭ ግንባር (ኦነግ) በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ጋር ተቀላቅሎል

  • ኦነግ ሸኔ በኦሮሚያ ክልል በዘር ማፅዳት ሥራ ላይ ከተሠማራ ሦስት አመታት ተቆጥሮል፡፡ ከኤርትራ ወደ ሃገር መሣሪያ ሳይፈታ የገባው የኦሮሞ ነጻ አውጭ ግንባር (ኦነግ) ይዞቸው የገባውን ጦር አንድ ሽህ አምስትመቶ የሚሆነውን ከኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ጋር እንዲቀላቀል በማድረግ ከሦስት ሽህ አምስት መቶ የሚገመተውን ከነትጥቁ በኦነግ ሸኜ ስም አንዴ ለአባገዳዎች ተሠጥተዋል ወዘተ ብለው እየቀለዱ ኦነግ ሸኜ በየትምህርት ቤቶቹ ውስጥ ብዙ ሽህ ወጣቶችን በመመልመል፣ ሃያ ሦስት ባንኮች በመዝረፍ፣ የአማራ ተወላጆችን በማረድ፣ በዘር ማጥፋት ሥራ እንዲሠማራ ስምሪቱን ህወሓት፣ኦነግና ኦዴፓ ብልፅግና ሃላፊነቱን ይወስዳሉ፡፡  አነግ ሸኔ ከስድስተኛው ዙር ምርጫ በፊት ከክልሉ ሌላዎቹን ዘር አማራ፣ ጉራጌ፣ ትግሬ ወዘተ በማስወጣት ምርጫውን ለማሸነፍ  የነደፈው የኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ የፖለቲካ ሴራን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ተባባሪ በመሆን ህዝቡን በመሸጥ ከምርጫው በኃላ እንባሣደር ሆነው ለመሾም ቃል ተገብቶላቸዋል፡፡
  • የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በኦሮሚያ ክልል መንግሥት የኦሮሞ ፖሊስ ኮሚሽነር የህዝብን የጸጥታና ደህንነት ሁኔታ በኦነግ ሸኔ አራጅ ብድን የብዙ ንፁሃን ደም እየፈሰሰ እንዳለ የፖሊስ ኮሚሽነሩን ጄኔራል አራርሳ መርዳሳ ‹‹ከኦነግ ሸኔ ጋር አበሩ ባላቸው ከአንድ ሽህ በላይ ፖሊሶች ላይ እርምጃ መውስዱን ገልፀዋል፡፡ በፀጥታና ፖለቲካ መዋቅር ውስጥ ሰርጎ በመግባትና ሰዋችን አደራጅቶ በመያዝ ከጎነግ ሸኔ ጋር  የሚሰሩ አካላት ጨምሮ ከ1000 በላይ የፖሊስ አባላት ላይ የተለያዩ  እርምጃዎች መወሰዱን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቆል፡፡ በቡድኑ የጥፋት ተልእኮ አልፎ አልፎ የሚሳተፉ፣ የሚጠረጠሩ፣ መረጃ የሚሰጡ፣ ከእነርሱ ጋር የሚያብሩ፣ ከጎሰኝነት፤ ከከባቢነትም ተነሰተው ከፀጥታ መዋቅርና አመራር ጋር በሚመሳጠሩት ላይ በየወቅቱ ግምገማዎች እየተካሄደ እርምጃ ይወሰዳልም ሲሉ ኮሚሽነሩ ተናግረዋል፡፡(EPA)›› የሰሜን ዕዝን መከላከያ ሠራዊት ህወሓት/ ወያኔ ሠርጎ በመግባት ሠራዊቱን በመውጋት  ገደሉ፣ አሰሩ፣ አገቱት መጨረሻቸውም የወያኔ መደምሰስ ሆነ፡፡ የኦሮሚያ ክልል መንግሥት፣ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን በኦነግ ሸኔ ድብቅ ቡድን ውስጡ ተቦርቡሮል፣ ከውስጥ መረጃ የሚሰጡ ፖለሶች ስላሉ ኦነግ ሸኔን ማጥፋት አልቻሉም፡፡  የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ከሰሜን ዕዝ መከላከያ ሠራዊት ጥቃት ምን ይማራል?
  • በአዲስ አበባና ድሬዳዋ የከተማ አስተዳደር ሥነ-ህዝብ (Demography) ፕወዛ:- በአዲስ አበባ ከተማ ዙሪያ የሚገኙ የኦሮሚያ ልዩ ዞኖች ንዋሪዎችን የአዲስአበባ የመታወቂያ ካርድ በመስጠት የከተማዋን ሥነ-ህዝብ በመቀየር ስድስተኛውን ዙር ምርጫ ለማሸነፍ የሚደረገውን ህገወጥ ሥራ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በዝምታ አልፎል፡፡ የመታወቂያ ካርድ በአዳነች አቤቤ ትእዛዝ በየአስሩም ክፍለ ከተሞች በተረኞች ይታደላል፡፡ ነፃና እንከን የለሹ ምርጫ፣ ዴሞክራሲ  አፍንጫውን ተሰንጎ ጭር እንዳለች ዶሮ ዝቅዝቅ ተሰቅሎል፡፡ ኦዴፓ ብልፅጋና ፓርቲ በዴሞክራሲ ስም ስንት ግፍ ሠራ!!!
  • የኦሮሙማን ተራኛነትንና ዘረኛነትን በህብረት ከሁሉም ክልሎች (የሱማሌ፣ አፋር፣ ሀረሪ፣ ደቡብ፣ ሲዳማ፣ ጋምቤላ፣ ቢኒሻንጉል) ጋር ሆኖ መታገል አንገብራቢ ጥያቄ ነው፡፡ የፌዴራል መንግሥታዊ መዋቅሮች ሥልጣን፣ የመከላከያ ሠራዊትና የፖሊስ ኃይል ጀነራል መኮንኖች፣ የውጭ ሃገራት አንባሳደሮች፣ ወዘተ ስልጣን የብሄር ተዋፆኦ በግልፅ በዴሞክራሲያዊ መንገድ መፍታት ተረኛነትንና ዘረኛነትን የመከላከያ አንዱ ዘዴ ነው እንላለን፡፡
  • በአገራችን ኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ምሶሶዎች የህግ አውጪ፣ የህግ ተርጎሚ፣ ህግ አስፈፃሚና ሚዲያ ሥር እየሰደዱ እንደ ቆጥኝ እየፀኑ ይሄዳሉ ሲባል በዘመናይ ልጆቾ እየዘመሙና እየተናዱ መሄዳቸው ምስጢር እንቆቅልሽ ሆኖል፡፡ የኢትዮጵያችን ማህፀን በሾተላይ ተጠቃና ውርጃ እጣ ፈንታዋ ሆኖል!!! በሃገሪቱ ዴሞክራሲያዊ መብቶች፣ የአመለካከት እና ሀሳብን በነፃ የመያዝና የመግለፅ መብት በነጠፈበት፣ የፕሬስ ነፃነት በሌለበት የመሰብሰብ፣ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ነጻነትና አቤቱታ የማቅረብ መብት በተነፈገበት፣ የመደራጀት መብት በታቀበበት፣ የመዘዋወር ነፃነት በሌለበት፣ የዜግነት መብቶች መጠበቅ በተሳነበት ወዘተ በተግባር እስኪተገበሩ  ድረስ ስድስተኛ ዙር ምርጫ ይቆየንና በፊት መገደያችን ህገወጥ የጦር መሣሪያዎች ጠመንጃ፣ ሽጉጥና ቦንብ፣ እና መታረጃችን ገጀራ፣ ሜንጫ፣ ጦሩ ተሰብስቦ ምርጫ ቦርድ ሙዚየም ውስጥ ይቀመጥ እንላለን፡፡
  • የጠቅላይ ሚንስትር ፅህፈት ቤት የወጡ ህጎች ውስጥ ማንኛውም የፌዴራል መንግሥት ሹማምንት ከኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ እውቅና ውጪ በአገር ውስጥና ውጭ ሀገር የመንቀሳቀስ መብታቸው ታግዶል
  • በኢትዮጵያ የሚዲያ ነፃነትና የጋዜጠኞች መታሰርና መገደል አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ሲፒጄ አስታውቆል፡፡ ኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ ስልጣን ከጨበጠ ሦስት አመት ሊሞላው ትንሽ ሲቀረው በሃገሪቱ የታሰሩ ጋዜጠኖች ከስልሳ በላይ ሆኖል፡፡  ምንጭ (http:// cpj.org/ Africa/Ethiopia/2020)
  • የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ መሪ እስክንድር ነጋ፣ ስንታየሁ ቸኮል፣ አስቴር ስዩም፣ ወዘተ   እስካሁን በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡ በዚህ ምርጫ ላለመሳተፍ የምርጫ ካርድ እቀባ ለማድረግ እንገደዳለን በማለት ገለታው ዘለቀ  አሳስበዋል፡፡
  • ኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ የመሰብስብና ሰላማዊ ሠልፍ የማድረግ ነፃነትና አቤቱታ የማቅረብ መብት ከ 2011 ዓ/ም ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ታግዶል፡፡ በቅርቡም ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ የጠራው ሰላማዊ ሠልፍ ታግዶል፡፡ በታሪካችን ለመጀመሪያ ጊዜ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመመሥረት ወሳኝ ምዕራፍ በሆነው ቀጣዩ ምርጫ ይለናል ፕሮፌሰረር ብርሃኑ ነጋ!!!
  • የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 5 ቀን 2013 ዓ/ም የአዲስ አበባና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክርቤቶች ምርጫዎች እንደሚፈፀሙ አስታወቆል፡፡ ግንቦት 28 ቀን የመረጡት ዳግም ሰኔ 5 ቀን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ ምርጫ ላይ እንዲመርጡ የተቀናጀ ሴራ ነው ለሚሉት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ምርጫ ቦርድ በተለያዩ ቀናት ምርጫውን ለምን ማድረግ እንደፈለገ የሚሠጠው ምላሽ ውኃ አያነሳም፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተቌማቱ ዝግጁነትና ገለልተኛነት፣ የታዛቢዎችና የምርጫው ሂደት ታዓማኒነት፣ የብሔረሰቦች የማንነት ጥያቄዎችና ከምርጫ ክልል ጋር የሚያያዙ ጥያቄዎች፣እንዲሁም የፖለቲካ ፓርቲዎች ጥያቄዎችና የሚዲያ ሚዛናዊነትና ተዓማኒነት፣ ምርጫው ውጤት ጋር ተያይዘው ሊነሱ የሚችሉ ጉዳዩች አፈታት በዝርዝር አልቀረበም፡፡
  • የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) ብልጽግና ፓርቲ መሪ ዶክተር ዐቢይ አህመድ በምርጫው ለመሳተፍ በምርጫው ከሚሳተፉት 47 የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል በርካታ ቁጥር ያላቸውን ዕጩዎች በማቅረብ በኩል ገዢው ፓርቲ ብልጽግና 2432 ዕጩዎችን በማስመዝገብ ቀዳሚው መሆኑ በመግለጫው ላይ ተመልክቷል። ከዚህ አንጻር ከብልጽግና በመከተል ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ዕጩዎች በማስመዝገብ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) 1385 ዕጩዎችን እንዲሁም እናት ፓርቲ ደግሞ 573 ዕጩዎችን አስመዝግበዋል። ኦዴፓ ብልጽግና ፓርቲ ካቀረባቸው 2432 ዕጩዎች ብዛት ከወዲሁ አሸናፊ እንደሆነ ትንቢት ተናጋሪ መሆን አይጠይቅም፡፡ ኦዴፓ ብልጽግና ፓርቲ አዲስ አበባ ህዝብ ድምጽ እንደማያሸንፍ ስላወቀ የአዲስ አባባ መታወቂያ ንዋሪ ላልሆኑ ሰዎች በመስጠት አሻጥር በመፈፀም ላይ ይገኛል፡፡
  • በዓለም አቀፍ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት የኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ የዘርና ኃይማኖት ፍጅት መንግሥታዊ ሽብርተኝነት ይዳኛል!!!

ማንኛውም ሰው በህይወት የመኖር መብቱ ይከበር!!!

ያለ ሕግ ልዕልና ዴሞክራሲ አይሰርፅም!!!

ያለ ሠላም፣ ፀጥታና  አስተማማኝ  የህዝብ ደህንነት ምርጫ ግጭት ያስከትላል!!!

ምንጭ

(1) https://youtu.be/k9gpEz_0PiM

(2) Taxi drivers’ strike paralyzes Addis Ababa/ Mar 16, 2021 to 11:36/APA-Addis Ababa (Ethiopia)

(3) የዘንድሮ ምርጫ ለአስፈጻሚዎች ብቻ ሁለት ቢሊዮን ብር ያስወጣል/ሪፖርተር ጋዜጣ /14 March 2021/ብሩክ አብዱ

(4)https://www.bbc.com/amharic/news-5478337

(5)https://www.youtube.com/watch?v=4ulGZQAsayk/የቄሮ አምስተኛ ዙር የትግል ጥሪ ይዘት, የቄሮ ፖለቲካዊ,ኢኮኖሚያዊ,እና መሃበረሰባዊ ዉሳኔዎች እና ይዘታቸዉ እንዲሁም የትግራይ ክልል ላይ እየታወጀ ያለዉ .

መሞቴን ለመናገር ከገዳይ አስገዳዮች ፈቃድ አልጠብቅም (ደሳለኝ ጫኔ ዶ/ር)

1) ሞት ቢደገስ እንኳ አንቀርም፣ የአማራ ልጅ አምባገነኖችን በታሪኩ ፈርቶ አያውቅም፣ ዛሬም በፍፁም አይፈራም!

2) የአባይ ግድብ ለአማራ የመቃብር ስፍራ ማድመቂያ እንዲሆን አስባችሁ እየገነባችሁት ከሆነ ጥሩ ነው። የአባይ ጉዳይ ከወገኖቻችን በህይዎት መኖር በታች ያለ አጀንዳችን እንጂ ከአማራ ነፍስ የሚቀድም ጉዳያችን አይደለም። ለናንተ ለተላላኪዎች ከአማራ ህይዎት በላይ ያለ ቀዳሚ አጀንዳችሁ መሆኑን ግን አሳይታችሁናልና እናመሰግናለን!

3) ሰላማዊ ሰልፉ የክልሉን አለመረጋጋት ለሚፈልጉ ሀይሎች ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል ለተባለው ጉዳይ፣ አንዱ ስራችሁና ግዴታችሁ ህዝቡን ከፀረ ሰላም ሀይሎች መጠበቅ እንደሆነ መገንዘብ አለባችሁ። በክብር ስትጠየቁ ፈቅዳችሁ፣ አስፈላጊውንና የሚገባውን ጥበቃ ብታደርጉ እናንተም ቢያንስ ከ2008ቱ አጥፊ ስህተታችሁ መማራችሁን ታሳዩ ነበር። የአማራ ወጣት እናንተ ከልክላችሁት ሰልፍ ከቀረ ገዳዮችን አበጃችሁ ብሎ እንደሸለመ እንቆጥረዋለን።

4) በ2008 አንገራግራችሁንም ሆነ ገድላችሁን ፈርተን እንዳልተመለስን አስታውሱ። በወቅቱ አማራው ሆ ብሎ ወጥቶ «ወልቃይት ሆይ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ»፣ «ኮሎኔል ደመቀ የነፃነት ታጋይ እንጂ አሸባሪ አይፈለም»፣ «በኦሮሞ ክልል የሚፈሰው የወገናችን ደም የኛም ደም ነው» ብለን የአማራን ጥያቄ ስናስተጋባ እናንተ ተላላኪዎች መለስን ስታመልኩና፣ ታግሎ ነፃ ላወጣን ትህነግ እንኳን ወልቃይትን ጎጃምን ብንሰጠው ምን ችግር አለ ስትሉ ነበር።

ዛሬ የአማራ ደም በየቦታው እንደጎርፍ እየወረደ ከ2008ቱ ጭፍጨፋችሁ በፈጣሪ ተዓምር የተረፍን አማሮች የሀምሌና የነሀሴ 2008 ሰማዕታት ወንድሞቻችን የወደቁለትን ዓላማ ይዘን ለአማራ ህዝብ ጥያቄዎች መመለስ የምንችለውን ካላደረግንና፣ በየቦታው የሚፈሰው የአማራ ደም ባስቸኳይ ይቁም ብለን ካልወጣን ከሞቱት በታች ሆነናል ማለት ነው።

5) በሌላችሁ ስልጣን ሰላማዊ ሰልፍ መከልከል ውስጥ ከገባችሁ ከህዝብና ከአምባገነኖች የማንኛው የበላይ እንደሆነ፤ ከህዝብና ከተላላኪዎችም ማን ፈሪ እንደሆነም እናያለን።

6) ጥበቃ እንድታደርጉለት ጥያቄ ባቀረብንባቸው በነዚህ ሰልፎች ላይ አንድ አማራ አንድ ነገር ቢሆን ትግላችን ወደምን እንደሚያመራ እናንተም አይጠፋችሁም!

አማራ በልጆቹ ትግል ይከበራል!

ለመስከረም 12 በዕለተ ማክሰኞ ….የዋስተና መብት ይሰጥ ወይስ ይቅር የሚለውን ለመወሰን ተቀጥሯል።ግን በችሎቱ እነ እስኬ ምን አሉ

…. !#ስንታየሁ …ታከለን በማስጨነ…ቅ ተብሎ የቀረበብን ክስ አስቂኝ ነው። ***” ታከለ በመንግስት ስልጣን ተቀምጦ ሲባልግ ማስጨነቅ ስራችን ነው”። የድሃ ኮንዶሚኒየም ሲዘረፍ ..መሬት ሲወረር ….ታሪካዊ ቅርስ ሲፈርስ….ድሃ ሲፈናቀል ታከለን ማስጨነቅ ስራችን ነዉ።””ፍትህ የሚገኘው በቅድሚያ ከፈጣሪ ነው።” ቀጥሎ ከጭቁኑ ህዝብ……ከዛም የፖለቲካ ጫና እንዳለባችሁ እያወቅን በናንተም ተስፋ አንቆርጥም።#አስቴር …..” የዚህ አገር ፍትህ የተለየ ነው። ፍትህ ተብሎ የሚፈፀመው ወንጀለኞችን ሸሽጎ በእኛ በንፁሃን ላይ ነው።”#እስክንድር …..” እኛን አስሮ ሊደረግ የሚታሰብ ምርጫ የባሰ የቁልቁለት መንገድን የሚወስድ እንጅ …እነሱ የሚሉትን ፍትህና ሰላም እኩለነት የሚያመጣ አይደለም።”#አስካለ …..” እኔ የመንግስት ሰራተኛ ነኝ የታሰርኩት ለምን የባልደራስ አመራር ሆንሽ ተብየ ነው።የሴቶች እኩልነትን አራምዳለሁ የሚል መንግስት ሴቶችን ወደ መድረክ እንዲመጡ የሚፈቅደው የራሱ ደጋፊና አባል ሲኮን ብቻ ነው ወይ ? “በወግደረስ ጤናው!

ትእግስቱ የማያልቅበት ጨዋ ሕዝብ – መስፍን ወልደ ማርያም

የሚሰሙኝ ከሆነ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ለዶር. ዓቢይ አሕመድ፣ ለአዲስ አበባ ከንቲባም፣ ለወይዘሮ ሙፈሪያት የሰላም ሚኒስትር፣ ምናልባት ሌሎች መኖሪያ ቤት መፍረስ የተጠናወታቸው ባለሥልጣኖች ካሉ ለነሱም የኅሊናዬን ጩኸት አስሰማለሁ፤የሚያዩኝና የሚያዝኑልኝ ከሆነም ተንበርክኬ እለምናቸዋለሁ!በዚህ የክረምት ወቅት፣ በዚህ የማትታይ ጉድ ዓለምን በሙሉ አንበርክካ በየዕለቱ ሰዎችን በምትጨርስበት ዘመን፣ በዚህ ዘመን እጃችሁን ቶሎ-ቶሎ ታጠቡ፤ አፍና አፍንጫችሁን ሸፍኑ፣ ስትገናኙ ተራራቁ በተባለበት ዘመን፣ በዚህ ሰው ሁሉ ሥራ ፈትቶ በቦዘነበት ዘመን፣ በዓባይ ጉዳይ ከግብጽ ጋር በተፋጠጥንበት ዘመን፣ የድሆችን ቤት በጉልበት ማፍረስና ድሆችን ማስለቀስ አቤቱታቸው የላይኛው ጌታ ዘንድ እንደሚደርስ ባለማወቅ ነው? ወይስ ኮሮና በቂ አልሆነምና ነው? እግዚአብሔር እንደሆነ ከኮሮና የባሰ ለመልቀቅ ችግር የለበትም፡፡ዶር. ዓቢይ ስለይቅርታ የሚናገረው ስለነዚህ ደሀዎች አይሠራም? ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ትልልቅ ዓላማዎች አንዱም እነዚህን እንባቸው የእግዚአብሔርን ደጃፍ የሚያጨቀይ ደሀዎችን አይነካም?በመጨረሻም እነዚህን ደሀዎቸ እግዚአብሔር አያያቸውም ብላችሁ ተስባላችሁ? ወይስ አይቶ መልስ ሳይሰጥ ይቀራል ብላችሁ ታምናላችሁ?እግዚአብሔር ነገን ይግለጥላችሁ!

መክሸፍ እንደኦሮሚያ፤ የከሸፈ ክልል እና የምስኪኖች ሰቆቃ – ተtክለሚካኤል አበበ፤ ቶሮንቶ ካናዳ

ሀምሌ፤ 2012/2020

እንደመግቢያ፤ ነፍጠኛው ተነሳ፤ ሞቶ፤ ርቆ ከተቀበረበት፤

ልጅ ተክሌ

ይህ ጽሁፍ፤ ቀደም ሲል የነገሌ አርሲው ተወላጅ፤ ወንደወሰን ተሾመ ከጻፈው ጽሁፍ[1] የቀጠለና በዘዚያ ጽሁፍ የተነሳሳ ነው፡፡ የሀጫሉን ሞት ተከትሎ በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች የደረሰውን ጥፋት ሳስብ፤ በእውኑ የኦሮሚያ መንግስት፤ ክልል መምራት ይችላል ወይንስ ከሸፈ የሚል ጥያቄና ክርክር አጭሮብኛል፡፡ የኦሮሞ ልሂቃን፤ ክልል አሉ፤ ክልል አገኙ፡፡ ቋንቋ አሉ፤ እሱንም አገኙ፡፡ በአገራችን፤ አባቶቻችንና እናቶቻችን በገነቡት አገር ላይ ባይተዋርና ባእዶች ተደረግን፡፡ በቱርጁማን መኖርን፤ በአስተርጓሚ መነገድን፤ መዳኘትን ለመድን፡፡ እንደሚባለው፤ አያት ቅድመአያቶቻችን፤ ሰፋሪዎች፤ ቅኝ ገዢዎች፤ ጡት ቆራጮች ቢሆኑ እንኳን፤ በእውኑ እኛ የአያቶቻችን የልጅ ልጆች የምንሳደድበት አመክንዮም ሞራልም እንደሌለ ጠፍቶን አይደለም፡፡ ግን ይሁን አልን፡፡ ተሸንፈን፤ ይሄን ብለንም ግን፤ ነፍጠኛውን ላይመለስ አርቀን ቀብረነዋል ካሉን፤ ከ30 አመታት በኋላም ያፈራነው፤ ክልላቸውን በሀላፊነትና በብቃት የሚመሩ መሪዎችን ሳይሆን፤ ዜጎችን የሚገድሉ፤ የሚያስገድሉ፤ ንብረት የሚያቃጥሉ፤ የሚያስቃጥሉ፤ ሽብርተኞችን ነው፡፡ ጀግኖችን አይደለም፡፡ በኦሮሚያ ውስጥ ለደረሰው ጥፋት፤ የፌደራሉም የክልሉም መንግስት ተጠያቂዎች ናቸው፡፡

ካለፈው ስንቀጥል፤

ኦሮሞ ደግ፤ ቅን፤ በጦርነት እንኳን የማረካቸውን እንደልጅ የሚያሳድግ እንደ ሚስት  የሚጠብቅ፤ አደንና ግድያ ለይቶ የሚያውቅ ህዝብ ነው፡፡ ኦሮሞ፤ ጫካ እንጂ ከተማ አደን አይወጣም፡፡ ኦሮሞ ሰው ዘቅዝቆ የሚሰቅልም አይደለም፡፡ እነዚህ ነገሌና ሌሎች የኦሮሚያ ከተሞ ውስጥ፤ ሰው በገጀራ የቆራረጡ፤ ሰው ዝቅዝቀው የሰቀሉና ከግዳያቸው አጠገብ ፎቶ የሚነሱ ሰዎች፤ ይሄን ሰው ማረድና መቆራረጥ ከየት አመጡት? የኢትዮጵያ ባህል ነው እንዴ? ልብወለድ አምነው፤ ጡት በመቁረጥና በመስለብ በሚያሙት ንጉስ ምኒሊክ ለተቆረጡ ጡቶች፤ የአኖሌ ሀውልት መታሰቢያ ያቆሙ ሰዎች፤ ባለፈው ሰኔ 23 ያደረጉት የሚወገዝ ድርጊት ነው፡፡ ሰው እንዴት ከ150 በፊት ተፈጸመ የተባለን ልብወለድ እያመነዠከ፤ በ21ኛው ክ/ዘ፤ ከዚያ የከፋ ግፍ ይፈጽማል? ሰው እንዴት፤ አርሲ ነገሌ ከተማን የገነቡ፤ ለዚህች ከተማ እድገት መስዋእትነት የከፈሉ፤ አረቄ አውጥተው፤ ከብት አደልበው፤ እርሻ አርሰው ይህቺን ከተማና አገር የገነቡ፤ እኛና፤ ወንድም እህቶቻችንን ያስተማሩ፤ ለትምህርት እድገት አስተዋጽኦ ያደረጉ ሰዎች ንብረት ያወድማል?

ባለፈው እንደተገለጸው፤ የነገሌ አርሲ የረጅም ግዜ ነዋሪው፤ አቶ ፈቃደ ደጀኔ፤ ባንድ ወገን ኦሮሞ ነው፡፡ አማራ ኦሮሞ ሳይል፤ ከ40 አመታት በላይ ትውልድ ያሰተማረና፤ ባለፈው አመት በበጎ ሰው ሽልማት የታጨ ሰው ነው፡፡ የዛሬ አመት ከ7 ወር፤ ህዳር 2010 ላይ፤ ማቃጠል የጀመሩትን ትምህርትቤት፤ በዚህኛው ዙር ጨረሱት፡፡ ሕዳር 2010 የተቃጠሉት ላብራቶሪና መዝገብ ቤቶች ነበሩ፡፡ በወቅቱ፤ የአካባቢው ሕዝብ ቃጠሎውን ሊያጠፋ ሲሞክር፤ የከተማው ፖሊሶች ሕዝቡን እሳቱን እንዳያጠፋ ያባርሩ እንደነበር ማስረጃ አለ፡፡ በኋላም፤ በምርመራው ወቅት፤ ፖሊስ ጣቢያ አካባቢ፤ አንዳንድ ፖሊሶች፤ ለምን የተቀረውንስ አልጨረሳችሁትም እንዳሉ ማስረጃ አለን፡፡ ሰው እንዴት ትምህርት ቤትና ክሊኒክ፤ ያቃጥላል? መንግስት ያኔ ያልቀጣቸው፤ እንደውም ለማባበል የሾማቸው፤ ኦሮሞ ያልሆኑ ኦሮሞዎች ናቸው እነሆ ዛሬ ይሄንን ይፈጸሙት፡፡

እንደተባለው፤ እንደተመኙት፤ ነፍጠኛም ይሁን የተቀረው ሕዝብ ከተማዎቹን ጥሎ ቢወጣ እኮ፤ ጅልነት እንጂ፤ ሕንጻውና ተቋማቱ ቢተርፉ ለቀሪው የኦሮሞ ሕዝብ እድገት ያስፈልጋሉ፡፡ ጉዳዩ ትግል ነው እንዳንል፤ የነበረው ዘረፋ ጉዳዩ ትግል ብቻ እነዳልነበረ ያሳብቃል፡፡ የዘረፋው ሰለባ ከሆኑት ሰዎች እንዱ ሲነግረኝ፤ አንዳንድ ሰዎች ሽብሩ እንደተጀመረ፤ ከዘረፋው ለመቋደስ፤ የማዳበሪያ ቀረጢታቸውን ይዘው ይተሙ ነበር፡፡ ቡቲኮችና የንግድ መደብሮች ተዘርፈው፤ አንድ ዙር በማዳበሪያቸው ይዘው የመጡትን ዝርፊያ ቤታቸው ዘርግፈው፤ እንደገና ልጆቻቸውን ማዳበሪያ አስይዘው አስከትለው ለሁለት፤ ሶሰት ዙር ዝርፊያ የተመላለሱም እንዳሉ ሰምተናል፡፡ በዝረፊያ ብቻ በማሯቸው፡፡ ማቃጠል፤ ማንደድ፤ ማውደም፤ መግደል ምን ይባላል፤ ይሄ ኢትዮጵያዊም፤ ኦሮሟዊም ምግባር አይደለም? የኦሮሚያን መስተዳድር ክሽፈት የሚያሳይ ድርጊት እንጂ፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ፤ ወንድወሰን እንዳለው ከ29 አመታት በኋላም፤ ለአቅመ አዳም/ሄዋን ያልደረሱ፤ ከፕሮፌሰር መሰፍን ቃል ስዋስ ደግሞ፤ የከሸፉ ክልሎች አሉ፡፡ ኦሮሚያ አንዱና ዋንኛው ነው፡፡

የቅዱስ ጊዮርጊስ እለት፤ በቅዱስ ጊዮርጊስ ደብር፤ ይህ ህዝብ ምን አደረገ፤

ለረጅም ግዜ፤ የነገሌ ከተማ ብቸኛ ታቦት፤ ቅዱስ ጊዮርጊስ ነበር፡፡ ባለፉት 20 አመታት ግን፤ ሌሎች ተጨማሪ አብያተ ክርስቲያናት ተተክለዋል፡፡ ቅዱ ጊዮርጊስ ግን፤ የጥንቱ ነው፡፡ የጠዋቱ፡፡ ማክሰኞ፤ ሰኔ 23፤ የቅዱስ ጊዮርጊ እለት፤ በመዘረፍ ብቻ መዳን ምኞት ነው፡፡ ቅንጦት፡፡ መሞትም አለና፡፡ የሚዘርፉት ደግሞ፤ ሰነፎችና ዱላ ይዘው መዞር የሚወዱ፤ ሰው በሰራውና በላቡ በገነባው ህንጻ አይናቸው ደም የሚለብስ፤ በከተማው መስተዳደር የሚታገዙ ቀናተኞችና ምቀኞች ናቸው፡፡ ምናልባት፤ በደም እንጂ፤ በባህርይ ኦሮሞዎች አይደሉም፡፡ ከመስተዳድሩ አባላት የወጣ ሊሆን የሚችል ስም ዝርዝር ተይዞ፤ የእከሌ ቤት ይዘረፍ፤ የነእከሌን ቤት ተዉት እየተባለ እንደሆነ የሚያሳዩ የሰዎች ምስክሮች/ማስረጃዎች አሉን፡፡ ሽብርተኞቹ ሽብራቸውን ተረጋግተውና ሰኣታት ወስደው ነው ያካሄዱት፡፡ አንዳንዶች ባሀብቶች፤ የአያት የቅድመአያቶቻቸውን ስም እየጠሩ፤  በዘራቸውና በገንዘብ ተደራድረውና ተከራክረው ንብረታቸውንም ሕይወታቸውንም ከአሸባሪዎቹ አድነዋል፡፡ አንዳንድ የሸዋ ኦሮሞዎች ንብረትም ተቃጥሏል፡፡ ተጠቂው ሁሉም ነው፡፡ አማራው፤ ጉራጌው፤ ስልጤው፤ ጎንደሬው፤ ሸዌው፤ ደቡቡ፡፡

ይሄ ህዝብ ምን አደረገ? የእኩል እርሻ አረሰ፤ ንግድ አስፋፋ፤ ስራ ፈጠረ፤ ጸጥ ብሎ አደረ፤ ተገዛ፤ መብቱን ሲነጠቅ፤ አሜን ብሎ ተቀበለ፤ በኖረበት፤ በተወለደበት፤ ባደገበት፤ ግብር በሚከፍልበት ቀዬ እንደሁለተኛ ዜጋ ሲታይ ይሁን ብሎ አደረ፡፡ ሁሉም ነገር ተወሰዶበት በኖረ፤ እንደገና ወሮና ከቦ ሕይወትን መንጠቅ ምን ይባላል? ሕዝቡ ቻይ ስለሆነ፤ ከድንቁራና ጋር አልዳረቅም፤ ችግሩን ጊዜ ይፈታዋል ብሎ እንጂ እኮ፤ እስካሁን በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የሚደረገው ሁሉ ሕገመንግስታዊ አይደለም፡፡ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስት ሕገመንግስት፤ አንዱን ብሄር ባንደኛው ላይ አያነግስም፡፡ ይሄ ሀይ ባይ ያጡ፤ ያልተወከሉ የብሄር ወኪሎች ለብሄራቸው የጫኑት ኢ-ሕገመንግስታዊ ስልጣን እንጂ፤ ሕገመንግስቱ፤ ኦሮሞዎችን የኦሮሚያ አንደኛ፤ ሌሎችን ሁለተኛ አያደርግም፡፡ ይሄ ሁሉ ሲሆን፤ የፌደራል መንግስት የትነበር? ዘግይቶ ደርሷል፡፡ አብይ አሕመድ፤ በሁሉም አቅጣጫ፤ የቀረውን እንጥፍጣፊ ተቀባይነት እያጣ ነው፡፡ ሁሉንም አስደስታለሁ ሲል፤ ሁሉንም አያጣ ነው፡፡

የአብይ ቸልተኝነት፤ ዋጋ እያስከፈለን ነው፤

ይሄ ደም መፋሰስ እንደሚከሰት፤ አብይ ሁለት ሶስት ፍንጮች ነበሩት፡፡ የማንቂያ ክስተቶች፡፡ ላለፉት ሁለት አመታት ሰዎች ሲገደሉ፤ አብያተ ክርስቲያናትና መስጆዶች ሲቃጠሉ፤ ዝም አለ ወይም የማያዳግም እርምጃ አልወሰደም፡፡ እንደውም ባለፈው ጥቅምት፤ ከ86 በላይ ሰዎች ሲደገሉ፤ አብይ ከቀናት በኋላ ነው ሚዲያ ላይ ወጥቶ የተናገረው፡፡ ለዚያውም በዚያ ጉዳይ ላይ፤ እርሙን ሊናገር ቢወጣ፤ የሟቾችን ቁጥር በብሄር ከፋፍሎ መጣ፡፡ 50 ኦሮሞ፤ 30 አማራ፤ 10 ጉራጌ እያለ ይቀጥላል፡፡ ሬሳ ብሄር የለውም፡፡ በዚያን ግዜው ጥቃት፤ በዶዶላ፤ ከ10 ሰዎች በላይ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል፡፡ እንዲያውም ቤተክርስቲያን ውስጥ ሁሉ ጥቃቱ እንደተፈጸመ ማስረጃ አለ፡፡፡ ለዚያውም ቢሆን፤ ድርጊቱን የፈጸሙ ሰዎች ለፍርድ አልቀረቡም፡፡ ዝም ተባለ፡፡ እንዚያ በእቁላለሉ ግዜ ያልተቀጡ ሰዎች ናቸው፤ አሁን ግመል መስረቅ ውስጥ የገቡት፡፡

አብይ ስልጣን ሲይዝ፤ መንግስት ወደድሮው የሀይል አገዛዝ ዘዴ ላለመለስ ቃል ኪዳን ነበረውና፤ በተወሰነ መልኩ የወቅቱን የአብይ ትእግስት መረዳት ይቻላል፡፡ ግን ተደጋገመ፡፡ በዛ፡፡ ሴቶች፤ አራሶች፤ ቄሶች፤ አረጋዊያን፤ ቤተሰቦች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለው፤ አስከሬናቸው በምድር ተጎተተ፤ ተቃጠለ፤ ተሰቀለ፤ ከሰለ፡፡ ያ በቂ ምልክት ነበር፡፡ የአካባቢ ሁቱዎች ሲፋፉ እየተመለከተ፤ መንግስት እንዝህላልነቱን ቀጠለ፡፡ በመንግስት እንዝህላልነት ምክንያት፤ ምስኪን ቱትሲዎች ዋጋ ከፈሉ፡፡ በዚህ ረገድ፤ የፌደራሉም፤ የክልሉም መንግስት ከድተውናል፡፡ ሀላፊነታቸውን አልተወጡም፡፡

ልክ ሰኞ ማት፤ ሰኔ 22፤ ሀጫሉ ተገደለ ሲባል፤ በማግስቱ ሊመጣ ያለውን መኣት፤ እንኳንስ የሙሉ ግዜ ስራው ሰላምና ጸጥታ ማስከበር የሆነው መንግስት፤ ማንም ተራ ሰው መገመት ይችላል፡፡ ሞቱ በተነገረ በሰኣታት ግዜ ውስጥ፤ መንግስት፤ ከሚኒሶታ ጀምሮ ከኢትዮጵያ ተከትሎ የሚተላለፈውን የዘር ማጥፋት ጥሪ ዝም ብሎ ኮሞኮመ፡፡ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሲተላለፍ ካየሁት ቪዲዮ እንደተረዳሁት፤ በነገሌው ኬዝ፤ አንዲት ሴት፤ የነገሌን መንገድ መግቢያና መውጫ ብትዘጉት፤ መንዜ መሄጃ የለውም ስትል ተሰተምታለች፡፡ አንዳንዶች ሀጫሉን የገደለው ነፍጠኛው ነው ሲሉ ሁሉ ተደምጠዋል፡፡ የተማሩትም ጭምር፡፡ መንግስት ሰራዊቱንና ፖሊስ በተጠንቀቅ ማቆምና ስጋት ባለባቸው ቦታዎች ማሰማራት ሲገባው፤ ያን ባለማድረጉ ምክንያት፤ ምስኪን ኢትዮጵያዊያን በብዙ የኦሮሚያ ከተሞች ታረዱ፡፡ ንብረት ወደመ፡፡ መንግስት ባለበት አገር፡፡ ይህ የሆነው፤ መንግስት የአመጥ እንቅስቃሴ ወይም የትጥቅ ትግል አለባቸው ባለባቸው አካባቢዎች ብቻ ቢሆን ኖሮ አይገርመኝም ነበር፡፡ ሰላማዊ በመሰሉ ከተሞች፤ ሻሸመኔና ነገሌ፤ ዝዋይ፤ አሳሳ፤ ደም ፈሰሰ፡፡ በመሀል አገር ይህ ከሆነ፤ በዳር አገር የሚሆነውንማ አስቡት፡፡

መንግስት ለምኔ፤ እና ሕግመንግስቱ፤

መንግስት የተቋቋመው፤ እንደአውሬ ከመሆን እንዲታደገን ነው፡፡ ከሰየጠነ የተፈጥሮ አገዛዝ ወደሰለጠነ የስምምነት አስተዳደር እንዲመልሰን ነው፡፡ መንግስት ያስፈለገው፤  ወደ State of Nature (ወደአውሬነት) ከመመለስ እንዲቤዠን ነው፡፡ ያንን ካላደረገ፤ የመንግስት የመኖሩ አስፈላጊነት ያበቃል፡፡ ሕዝብን ስራው እንዲያወጣው መተው ነው፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ አንዱ ላንዱ አያንስም፡፡ ነገሌ እንደዚያ ነው የሆነው፡፡ ቁስቋምና አንዳንድ ሰፈሮች እስከምሽቱ 11 ሰዓት ድረስ በዱላ ብቻ ተፋልመው ራሳቸውንና ቤተሰባቸውን ጠብቀዋል፡፡ ብዙዎቹ ሽብርተኞች በክላሽ ጩከት አይደለም፤ በቆመጥ ብቻ የሚበተኑ ፈሪዎች ናቸው፡፡ ሕዝቡ ያልተደራጀው፤ ፖሊስና ልዩ ሀይልን፤ ብልጽግናን ፍራቻ ነው፡፡ ሕዝቡ ሲደራጅና ሲጠነክር፤ ልዩ ሀይል/ፖሊስ ከነፍሰገዳዮቹ ጎን ይሰለፋል፡፡ እንጂ፤ ሕዝቡ ራሱን እንዲከላከል ቢተው፤ በደንብ ይመክታል፡፡ የአካባቢው ባለስልጣናት ግን፤ ሕዝብን ያጠቃሉ፡፡ ያስጠቃሉ፡፡ ለምሳሌ፤ በግድያው ማታና በማግስቱም፤ አላገግባብ የታሰሩ ሰዎች እንዳሉ፡፡ ስላልሞቱ፡፡ ስለተረፉ፡፡ ሰውን ለምን ተረፍክ ብሎ ማሰር የጤና ነው? ከግድያው ቀደም ባሉት ቀናት፤ የአንዳንድ አማራዎች ቤቶች መሳሪያ ደብቃችኋል በሚል ሰበብ ይፈተሸ እንደነበርም ሰምተናል፡፡ ከዚህ በፊት ራሳቸውን ለመከላከል፤ ሊያጠቃቸው በከበባቸው ቡድን ላይ መሳሪያ ወደሰማይ የተኮሱ ሰዎች እንደታሰሩም ምስክሮች ተናግረዋል፡፡ ለዚህ ነው በዚህ ጥቃት ውስጥ፤ የከተማው መስተዳደር፤ የአካባቢው መንግስት ባለስልጣናት እጅ አለበት የምንለው፡፡

ችግሩ ግን ከሕገመንግስቱ አፈጻጸም/አተረጓጎም/አረዳድም ጭምር ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕገ-መንገስት ዘረኝነትን ስለሚያስፋፋና ስለሚያፋፋ፤ ቶሎ ይሻሻል ወይም ይቀየር ወይም ይጣል ከሚሉት ውስጥ አይደለሁም፡፡ ብዙ ችግሮች ቢኖሩበትም፤ ይህ ሕገመንግስት በመርህ ደረጃ፤ የዜጎችን የእኩልነት መብት ያረጋግጣል፡፡ አንቀጽ 25 ማናቸውም ኢትዮጵያዊ በዘሩ፤ በእምነቱ፤ በጾታው በሌሎችም ምክንያቶች ልዩነት/መድልዎ አይደረግበትም ይላል፡፡ አንቀጽ 10፤ የዜጎችና የህዝቦች ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ይከበራል ይላል፡፡ አንቀጽ 13፤ የፌደራሉም የክልልም መንግስታት በምእራፍ 3 የተዘረዘሩትን መሰረታዊ መብቶች ማክበር ማስከበር አለባቸው ይላል፡፡ ሕገ መንግስቱ ሰብአዊ መብትን ለመጠበቅ  በቂ አንቀጾች አሉት፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ የጠፋው ሕገመንግስታዊነት ነው፡፡ የምንገዛው፤ ሕገመንግስታዊነት ባልገባቸው የእውቀት ጨዋዎች ነው፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ፤ የግለሰቦች መብት ወደክልል ሲወርድ ይሸራረፋል፡፡ የክልሎችን ስልጣንና ባለቤትነት በተመለከተ፤ ክልሎች አብላጫ የብሄሮች ቋንቋ በሚናገሩት ሰዎች ቢሰይምም፤ የዚያ ክልል ባለቤት ያ ብሄር ብቻ ነው ማለት አይደለም፡፡ የፌደራሉ ሕገመንግስት ውስጥ ክልሎችን ለብሄሮች በባለቤትነት የሚሰጥ አንቀጽ የለም፡፡ ኦሮሚያ በኦሮሚያ ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ እንጂ የኦሮሞዎች ብቻ አይደለችም፡፡ ኦሮሞና ኦሮሚያ አንድ አይደሉም፡፡ ኦሮሚያ፤ በክልሉ ውስጥ የሚኖሩ፤ ወደፊትም መጥተው መኖር የሚፈልጉ ሁሉ ነች፡፡ ሌላም ቦታ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን መጥተው መኖር፤ የክልሉ ባለቤት መሆን ይችላሉ፡፡ የኦሮሚያ ሕገመንግስት የክልሉን ባለቤትነት ስልጣን ለአንድ ብሄር ሰጠ ማለት፤ ያ ትክክል ነው ማለት አይደለም፡፡ በዚህ ረገድ፤ የኦሮሚያ ሕገመንግስት የፌደራል ሕገ-መንገስቱን ይጥሳል፡፡ ማናቸውም ሕጎች፤ ልማዶች፤ አሰራሮች ከፌደራል ሕገመንግስቱ ጋር መጋጨት የለባቸውም፡፡ ሕገ-መንግስቱን ሳይሆን፤ ይሄንን የተንሻፈፈና የተዛባ፤ ሌሎች ኢትዮጵያዊያንን የባለቤትነት ስልጣን የሚያሳጣ ትርጉም፤ ልማድና አሰራር ነው ባስቸኳይ ማስወገድ ያለብን፡፡

የክልል ሕገ-መንግስት፤ የክልል ክሽፈት፤  

የኦሮሚያ ሕገ-መንግስት፤[2] እኛ ኦሮሞዎች ብሎ ይጀምርና፤ አንቀጽ 8፤ የክልሉን ሉአላዊነትና የመንግስት የስልጣን ባለቤትነት፤ ለኦሮሞ ሕዝብ ብቻ ይሰጣል፡፡ በኦሮሚያ ውስጥ የሚኖሩ ሌሎች አናሳ ብሄሮች የባለቤትነት ቦታ የላቸውም፡፡ ሰፋሪዎች እንጂ፡፡ አንቀጽ 14(6)፤ ኦሮሞነትን ሲተረጉም፤ የኦሮሞ ቋንቋ የማይናገረውን፤ ከትርጉሙ ውጪ ያደርገዋል፡፡ አናሳ ህዝቦች ወይንም ኦሮሞ ያልሆኑ ሰዎች፤ በኦሮሚያ ሕገመንግስታዊ ጥበቃ የላቸውም፡፡ የራስን እድል በራሳቸው የመወሰን መብት የላቸውም፡፡ የኢትዮጵያ ሕገመንግስት አንቀጽ 13(1)፤ የፌደራልና የክልል ባለስልጣናት፤ በምእራፍ 3 የተቀመጡትን ድንጋጌዎች፤ መሰረታዊ መብቶችና ነጻነቶች የማክበር/የማስከበር ግዴታ ቢጥልባቸውም፤ የኦሮሚያ መንግስት፤ እነዚህን መብቶች ማክበርም ማስከበርም አልቻለም፡፡ ባለቤትነት ይቅር፤ የኦሮሚያም የፌደራሉም ሕገመንግስት፤ ሌሎች ዜጎች፤ በኦሮሚያ ውስጥ፤ ሀብት የማፍራትና የመኖር መብት አላቸው ቢልም፤ ያለፈው የሰኔ 23ቱ ድርጊት የሚያሳየው፤ ያ መብት ባዶ እንደሆነ ነው፡፡

ይህ የሰኔ 23ቱ አይነት ክስተት ሲከሰት፤ ማለትም የክልል መንግስታት፤ የዜጎች መሰረታዊ መብትና ነፃነትን የሚፃረር ተግባር ከፈፀሙ፤ የእርምት እርምጃ እንዲወስዱ በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት መመሪያ ይሰጣል፡፡ ይህንንም አክበረው ካልተገበሩ የፌደራል መንግስት የፀጥታ ሃይል ጣልቃ የመግባት ህገ መንግስታዊ ገዴታ ተጥሎበታል።    በአጠቃላይ፤ የኦሮሚያ መንግስት እንደመንግስት፤ ከሽፏል፡፡ እንደ ህዝብስ? በክልሉ ውስጥ አብዛኛኛው ኦሮሞ የሆነ ማህበረሰብ (የጋራ ታሪክ፣ ማህበራዊ ኑሮ፣ ልማድ እና ሌሎች የሚየስተሳስሩ ነገሮች እንዳሉ ሆነው) እንዴት ይህ ሰብአዊ ግፍ ተደጋግሞ ሲከስት ማስቆም/መግታት ተሳነው? ይህ እጅግ በጣም አሳሳቢና በሚገባ ልንወያይበት የሚገባ ጉዳይ ነው። መንግስት ከሸፈ፡፡ እንደ ህዝብ፤ ኦሮሞ እንዳይከሽፍ መጠንቀቅ አለበት፡፡ የባለፈው ማክሰኞ ክስተት ሲደጋገም ስትመለከቱ፤ የኦሮሚያ መክሸፍ እንደደረሰ እወቁ፡፡

ሕገ-መንግስቱ ያሰራል፤ ግን ይሰራበት፤ የተንሻፈፈው ትርጉሙ ይቃና

ይሄንን ሕገመንግስት ቀዶ ለመጣል ያሰፈሰፉ ብዙ ሀይሎች አሉ፡፡ እሱ አያዋጣም፡፡ አሁንም ለዚህ ህገመንገስት የሚሞቱ አሉ፡፡ ይሄ ሕመንግስት ለብዙዎች አሁንም ድረስ ትኩስ ነው፡፡ ሕያው ነው፡፡ ከምንምነት ክልል፤ ከዞንንት ክልል የሆኑበትና ለመሆን የሚሰናዱበት፤ አገር ለመሆንም የቋመጡበት አሉ፡፡ ይሄንን ሕገመንግስት መቀልበስ ከባድ ነው፡፡ 25 አመት አዝልቆናል፡፡ ባንዴ ለመናድ መሞከር አገሪቱን መናድ ሊሆን ይችላል፡፡ ኢህአዴግን አፍርሶ ብልጽግናን መመስረት፤ አብይንና ለማን እንደለያያቸው፤ የኦሮሞና የትግራይ ብሄርተኞችን እንኳን በአብይ ላይ እንዴት እንደቀሰቀሳቸው እያየን ነው፡፡ ትናንት አይንና ናጫ፤ ገራፊና ተገራፊ የነበሩ ሀይሎች ሁሉ አብረው ሲቆሙ እያየን ነው፡፡ የብልጽግና ምስረታ፤ ፍጥጫውን አብሶታል፡፡ ወደአሃዳዊነት የመመለስ ፍራቻ የቀድሞ ባላንጣዎችን ሁሉ በአንድነት ያቆማል፡፡ ስለዚህ ለጊዜው መታገል ያለብን፤ ሕገመንግስቱን ለመቀየር ሳይሆን፤ ሕገመንግስታዊነትን ለማስፈን ነው፡፡ ሕገመንገስታዊነት ከሰፈነ፤ ይሄ ሕመንግስት፤ ሌላ ክፍለዘመን ሊያኖረን ይችላል፡፡ ከሕገመንግስቱ ጋር ቀጥታ መላተም አያስፈልግም፡፡ በዚሁ ሕገመንግስት የዜግነት መብታችን ይከበርልን፡፡ ኦሮሚያ፤ የኦሮሞ ብቻ ተደርጋ የተሳለችበትና የተተረጎመችበት አግባብ ይቃና፡፡ ያ የትርጉም ስህተት ነው፡፡ ኦሮሚያ፤ በጣም ከጠበበ በውስጧ የሚኖሩ ሁሉ፤ ከለጠጥነው የሁላችንም ናት፡፡ ሁላችንም እናስፈልጋለን፡፡ ሁላችንም የመንግስት ጥበቃም ያስፈልገናል፡፡ የኦሮሚያ መንግስት፤ ጠንካራ የሕዳጣን/አናሳዎች መብት ጥበቃ መዋቅር ካላበጀ፤ የከሸፈ ክልል መሆኑን ይቀጥላል፡፡ ምናልባት ይሄ አማራውና ጉራጌው፤ ስለጤውና ሀድያው ላይ ብቻ የሚያቆም ከመሰለን፤ ተሳስተናል፡፡ በአርሲዎች ዘንድ፤ ጉጂዎችም አናሳ ናቸው፡፡ በጉጂዎች ዘንድ፤ ሜጫና ቱለማም አናሳ ነው፡፡ የጭቆና ሰንሰለት፤ ጫፍ የለውም፡፡

አሻጋሪው አብይና፤ አስገድዶ ደፋሪው ባል

አብይ ይሄን ስልጣን የያዘው ወዶ ነው፡፡ በግድ አሻግራችኋለሁ፤ እንደውም እግዚአብሄር ኢትዮጵያን አድን ዘንድ የቀባኝ ነኝ ሁሉ ብሎ የሚያምን ይመስለኛል፡፡ እኛም እንደመጣ ንግግሩንና ስብከቱን፤ የወሰዳቸውንም አንዳንድ አዎንታዊ እርምጃዎች አይተን ይሄ ሰው በርግጥም በእግዚአብሄር የተቀባ ይሆን እንዴ ብለን ነበር፡፡ ትእግስቱ መብዛቱን፤ አንዴ ስንወቅስ፤ አንዴ ስናወድስ፤ ሌላ ግዜ ስንከልስ እዚህ ደረስን፡፡ አብይ በውዴታ ሀላፊነት ከወሰደ፤ ያንን ሀላፊነት በብቃት መወጣት አለበት፡፡ ሀላፊነትን ላለመወጣት ምንም ሰበብ የለም፡፡ ስራ እንጂ፡፡ የሚገደለው እኮ፤ ሰው ነው፡፡ ዝንብ አይደለም፡፡ ዛሬ የምስኪኖችን አስከሬን የጎተቱ ሰዎች፤ ነገ የሱን አስከሬን እንደማይጎትቱ ዋስትና የለም፡፡ ካንቀላፋ፤ ይቀድሙታል፡፡ ማንቀላፋቱ፤ እንደፖለቲካዊ ስትራቴጂም፤ እንደሕገመንግስታዊ ጉዳይም አያስኬድም፡፡

አብይ፤ በቀጥታም ይሁን 28 አመት ተሰጥቶት ይህቺን አገር መለወጥ ያልቻለ ፓርቲ ራስ ነው፡፡ ያ ፓርቲ፤ ስም ለውጦ ብልጽግና መጣ፡፡ እኛ የስም ለውጥ አይደለም የምንፈልገው፡፡ የባሕርይ እንጂ፡፡ ኢህአዴግም እንበለው ብልጽግና፤ 29 አመት ይህቺን አገር አስገድደው ደፈሩ፡፡ ይሄንን የፌደራል ስርአት ወለዱ፡፡ መቼስ በአስገድዶ መደፈር ቢወለድም፤ ልጅ፤ ልጅ ነው፤ አገር ነው ብለን ተቀብለን ኖርን፡፡ ልጅ ልጅ ነው፤ ዱርዬም ይሁን ጨዋ፤ ወንጀለኛም ይሁን ሰላማዊ፤ ዲቃላም ይወለድ በትዳር፤ ልጅ ልጅ ነው፡፡ ግን ልጅ ማደግ አለበት፡፡ የተፈጥሮ ጉድለት፤ በሽታ፤ እንከን ከሌለበት በስተቀር፤ ልጅ 18 አመት ከሞላው ልጅ አይደለም፡፡ አዋቂ ነው፡፡ ሙሉ ሰው፡፡ ክልሎች፤ በዚህ ሕገመንገስት ከተወለድን 25 አመት ሞላን እኮ፡፡ ከሽግግር መንግሰቱ ጋር 29፡፡ ይሄ ስርአት እኮ ለ30 አንድ ፈሪ ነው፡፡ እንደግ እንጂ፡፡ ምንድነው አድሮ ጥጃ፡፡ ይሄንን ስርአት በኢትዮጵያ ላይ ለማሳደግና ለአቅመ አዳም/ሄዋን ለማድረስ 30 አመት ካልበቃ፤ ችግር አለ፡፡

የክሽፈት ትርክት፤

የሀጫሉን ሞት ተከትሎ በኦሮሚያ በኢትዮጵያዊያን ላይ የተፈጸመው ግፍ፤ የኦሮሙማ ተቃራኒ ነው፡፡ ኢትዮጵያ የአማራም፤ የኦሮሞም፤ የትግሬም፤ የወላይታም፤ የሌሎችም ጀግኖች ነበሯት፡፡ ሴትና ሕጻናት፤ ሽማግሌዎችና ካህናት፤ ያልታጠቁ ሰላማዊ ዜጎችን መግደል ግን፤ ጀግንነት አይደለም፡፡ ትግልም አይደለም፡፡ ለአቅመ አዳም አለመድረስና አገር ወይም ክልል ማስተዳደር አለመቻል ነው፡፡ በውስጣቸው የሚኖሩትን ዜጎች ሕይወትና ንብረት መጠበቅ ካልቻሉ፤ ክልሎች ለአቅመ ክልልነት አልደረሱም፡፡ የአብይና ሽመልስ መንግስት፤ የዚህን ጥፋት ምንጭ ከስር ከመሰረቱ ካልመረመሩና እርምጃ ካልወሰዱ፤ የክልሉ መክሸፍ እውነት ይሆናል፡፡

[1] የምስኪኖች ሰቆቃ እና የነገሌ ግፍ || ልጅ ወንድወሰን ተሾመ (ኢጆሌ ነገሌ-ከዲሲ) July 3, 2020, https://ethiopianege.com/archives/13640

[2] http://www.ethcriminalawnetwork.com/system/files/Lak_1_Bara_1987%5B1%5D.pdf

“ለስልጣን ሲባል ኢትዮጵያዊነታችን ተወስዶ ማንነታችን ብሔር እንዲሆን ተደርጓል”ኦባንግ ሜቶ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች

አዲስ አበባ፡- ለስልጣን ሲባል ኢትዮጵያዊነታችን ተወስዶ ማንነታችን ብሔር እንዲሆን ተደርጓል ሲሉ የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ አቶ ኦባንግ ሜቶ ገለጹ ።አሁን መገዳደል ላይ የተደረሰው በውሸት ማንነት እንደሆነም አስታወቁ።አቶ ኦባንግ ሜቶ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳመለከቱት፣ ጥቂት ሰዎች ተበድለናል ብለው ተነስተው ጫካ ገቡ። ከጫካ ሲወጡ እና ስልጣን ለመያዝ ስትራቴጂ ሲነድፉ ህዝቡን መከፋፋል ላይ አተኮሩ። የጋራ የሚባል ነገር ሁሉ የእነርሱ ጠላት መሆኑን አስቀመጡ። እኩልነት፣ ኢትዮጵያዊነት፣ ጥሩዎቹ የአብሮነት ታሪኮች ተሰወሩ። ትልቁን ነገር የኢትዮጵያውያንን ማንነት ከህዝቡ ነጠቁ።“ፖለቲካ ጨዋታ ነው። ጨዋታው ደግሞ ከማሸነፍ ጋር የተያያዘ ነው። ነገር ግን ማሸነፍ ሲታሰብ አገር እና ትውልድን ከመጉዳት አንፃር መሆን አልነበረበትም” ያሉት አቶ ኦባንግ፣ በኢትዮጵያ ግን ለማሸነፍ ሲባል አገር የምትፈርስበት እና ትውልድ የሚጎዳበት መንገድ መመረጡን አስታውቀዋል።የምንገዳደልበት የተሰጠንን የውሸት ማንነት ተቀብለን ነው። እውነቱ ግን ከዚህ የራቀ ነው ያሉት አቶ ኦባንግ፣ አያቶቻችን ብሔርን ሳያስቡ በፍቅር ተጋብተዋል። የሰውን ብሔር ሳያውቁ ሰው በመሆኑ ብቻ አግብተው ልጅ መውለዳቸውን አመልክተዋል። በፊት ዕቁብ፣ ዕድር፣ ቡና መጣጣት፣ በአንድ ትሪ ያለምንም ድንበር መብላትነበር። ሁሉም ከሰውነት አንፃር ይታይ ነበር። አሁን ይሄን ማንነት ተነጥቀናል። እከሌ ያንተ ጠላት ነው። እከሌ ይሄንን በደል ፈፅሞብሃል መባሉ በብዙዎች ውስጥ ገብቶ የአብሮነት ስጋት መፍጠሩን አስታውቀዋል።“ፈጣሪ ሰውን ፈጥሯል። ሰው ያለሰው መኖር አይችልም። ዝሆን ስትወልድ ብትሞት፤ የተወለደው የዝሆን ግልገል ያለማንም ድጋፍ ወዲያው መሄድ እና ማደግ ይችላል። የተወለደው የዝሆን ልጅ ራሱን ለመመገብ አያዳግተውም። ሰው ግን ተወልዶ ቢጣል ያለሰው ማደግ አይችልም። ቆሞ ከመሄዱ በፊት መታቀፍ አለበት። መብላት እስከሚጀምር የሚያጎርሰው ይፈልጋል። ሰው ያለሰው አይሆንም። ሰው ከእንስሳት የተለየ ፍጥረት ነው። ሰው ዕውቀት፣ ኃይል እና ኃላፊነት ያለው ፍጥረት ነው። ሰው እንደ ሰው ሊታሰብ ይገባል” ብለዋል።

ለፖለቲካ ፍጆታ ሲባል ብቻ የሚደረጉ አይን ያወጡ የግፍ ግድያዎችን እናወግዛለን !

ሀገራችን ኢትዮጵያ የተለያየዩ ቋንቋዎች የሚነገሩባት በርካታና ውብ ባህሎች የሚታዩባት ጥንታዊ ታሪክ ካላቸው ጥቂት ሀገሮች አንዷ ነች። የኢትዮጵያ ሕዝብ በጋራ ባለፈባቸው የታሪክ መስተጋብሮች፣ የሀገሩን አንድነትና ሉአላዊነት ላለማስደፈር ከውጭ ወራሪ ኃይሎች ጋር ባሳለፋቸው የተጋድሎ የታሪክ ጊዜያቶች፣ በሀገሩ ውስጥ ከቦታ ቦታ በመዘዋወር በመኖር በመጋባትና በመዋለድ በፈጠረው ጠንካራ ማህበራዊ ትስስርና ግንኙነት፣ በቆይታም በሀይማኖትና በባህል መወራረስ በቋንቋ አጠቃቀም የኢትዮጵያዊነትን የጋራ ስነልቦና እንዲፈጠርና ብዝሃነት እንዲያብብ አድርጎታል። ይህም ብዝሃነትና ህብረብሄራዊ ቀለም ለሀገራችን ዉበታችን ሆኖ ደምቀን እንድንታይና ተሳስረንም እንድንኖር አስችሎናል። ይህን አንድነቱን የውጭ ወራሪዎች እና የሀገር ውስጥ የስልጣን ጥመኞች በተቻላቸው ሁሉ አለመግባባትን ሊፈጥሩ ይችላሉ ያሏቸውን ያልነበሩና ያልተሰሩ በታሪክ የማይታወቁ የፈጠራ ትርክቶችን በመፈብረክ ሊከፋፍሉት ሞክረዋል። ሆኖም በዋዛ የማይነጣጠል ለመነጣጠል ውል የማይገኝለት በጥብቅ የተሸመነ እና አብሮ በመኖር ታሪክ የተገመደ ታሪካዊ ትስስር ስላለው ከቶውንም ትላንትም አልተሳካላቸው። ዛሬም ሆነ ነገ አይሳካላቸውም።

——[ሙሉውን መግለጫ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]——

የዘማሪ ዶ/ር #Dereje Kebede

“ኢትዮጵያ አትፈርስም የሚሉ ህልመኞች ስትፈርስ አፍጥጠው እያዩዋት ነው” !ከሁሉም ከሁሉም የሚያስሳስቡኝ እነኝህ ችግር እያለ የለም የሚሉ ህዝብ እያለቀ ነገ የተሻለ ይሆናል የሚሉ ናቸው። የወደፊቱን የተሻለ ለማድረግ ወይም ዘለቄታ ያለው ሰላም በኢትዮጵያ እንዲሰፍን ወይም ብሄሮች እርስበርስ ሳይጫረሱ በአንድ አገር መኖር እንዲችሉ የሚያመቻች የህገመንግስት፣ የመዋቅርና የመረሆ ለውጥ ሳይደረግ እንዲያው በምኞት ብቻ ኢትዮጵያ አትፈርስም የሚሉ ያሳስቡኛል። ምክንያቱም ኢትዮጵያ አትፈርስም እያሉ ኢትዮጵያ ስትፈርስ አፋቸውን ዘግተው አሁንም እያዩዋት ነው። አንድ የምእራባውያን ፊልም ላይ አንድ የሆነ ሰው በጥይት እየደበደቡት አልሞትኩም (I Am still Alive) አልሞትኩም አልሞትኩም እንዳለ የሞተበት ትዝ ይለኛል። ወኔው ለጊዜው ይደነቃል ነገር ግን ከሞት ያማያድን ባዶ ወኔ ነበር። በሃገራችን የዘር ማጥፋት ወንጀል እየተገበረ ነው ። አማራው በግላጭ ከወያኔ ጊዜ ጀምሮ እንዲጠፋ በተፈረደበት መሰረት ለ 27 አመታት ከዛም ለዶ/ር አቢይ ስርአቱ ተላልፎ የአማራው ግድያ በተጡዋጡዋፈ መልኩ ቀጥሎአል። ይህንን ሃቅ ማድበስበስና እንዳላዩ ለመሆን ማስመሰል ትልቅ ዋጋ ያስከፍላል። ሃገር እየተሸራረፈች ይህንን ሂደት እንደማስቆም የአቢይ ደጋፊዎች አቢይ ያሻግረናል ይላሉ። ወዴት ነው የምትሻገሩት? ሃገር እኮ በምኞት ወይም በአስማት ከመበታተን አትድንም። ብሄር በብሄር ላይ እንዲነሳና እንዲጨካከን ያደረገው ምንድነው? ብሎ ሰው ለምን አይጠይቅም? ከኦሮሞ ክልል ውጡ እየተባሉ የተጨፈጨፉት፣ እሬሳቸው ጎዳና ላይ የተጎተተው አማራዎችና ጉራጌዎች ጉዳይ እውን አይደለም እንዴ? ደግ መመኘት ከተግባር ጋር ካልተዋሃደ እንዲያው ፈረንጆች “Wishful thinking” እንደሚሉት ምኞት ሆኖ ይቀራል። አሁን ኢንተርኔት ተዘግቶ የተፈፅመውን ጭካኔ ምንም አላየንም ማለት ይቻላል። ኢትዮጵያ በአቢይ አስተዳደር ወደ ለየለት የዘር ማጥፋት ተግባር በይፋ ገብታለች። ምናልባት በሩዋንዳው ደረጃ መቶ በመቶ እልፈነዳም (Fullblown scale) ይባል ይሆናል እንጅ ጄኖሳይዱ ከተጀመረ ቆይቶአል። ልብ ብላችሁ ከሆነ ደግሞ ለምሳሌ የቅርብ ጊዜ ምሳሌ ብንወስድ ባለፉት ጥቂት ወራቶች የተፈፀመው በጃዋር የተከብቤአለሁ ለቅሶ ሳቢይ የተፈፀመው ዘርን መሰረት ያደረገው ቄሮዎች ያካሄዱት ጭፍጨፋ በስኬሉና በመጠኑ ወይም ያዳረሰው አካባቢ ስፋትና ቁጥር ከአሁነኛው ያነሰ ነበር። በዚህ በአሁነኛው፣ መንግስትን ከበስተሁዋላው ባደረገ፣ የቄሪዎችና የኦነጎች ጥቃት ወደ 300 ሰዎች ተገድለዋል ቢባልም እውነታውን ፈጣሪ ይወቀው። እንደሚታወቀው መንግስት ከወቀሳ ለመዳን ጥፋቶችንና የሙዋቾችን ቁጥር እጅግ በጣም አሳንሶ እንደሚያወራ ማንም ያውቀዋል። በጀዋር ሳቢያ 80 ሰዎች ተገደሉ የተባለውም የመንግስት ሚዲያዎች በሉ የተባሉት ነው እንጅ በግል ታዛቢዎች የሙዋቾቹ ቁጥር አልተቆጠረም። መንግስትም አይፈቅድም። ቁም ነገሩ የሃገራችን ነገር በየጊዜው እየባሰበት የተገዳዮችም ቁጥር እየጨመረ ነው የሚሄደው እንጅ የተሻለ ጊዜ አይመጣም ። ምክንያቱም አስተዳደሩ የችግሩን መሰረት (Root cause) ሊነካው ፈቃደኛ ስለአይደለ ነው። ያም በብሄርና በቁዋንቁዋ ላይ የመሰረቱት ክልል የሚሉት ሴይጣናዊ መዋቅር ነው። በነገራችን ላይ የፌዴራሊዝምና የኤትኒክ ፌዴራሊዝም ልዩነት ጠንቅቀን ማወቅ ይገባናል ምክንያቱም ሁለቱ ስርአቶች የብርሃንና የጨለማን ያህል ልዩነት አላቸው። በፌዴራሊዝም ስርአት የሴንታራሉ መንግስት ስልጣን ከሁሉ የበላይ ነው። በኢትዮጵያ የምናየው ግን ብሄር ዜግነትን ደፍጥጦት፣ የክልል ስልጣን ከማእከላዊው አስተዳደር ስልጣን መቶ እጥፍ በልጦ ያለበት ሁኔታ ነው። ብሄርና ቁዋንቁዋን ያማከለ ፌዴራሊዝም ግን ለጠላታችንም የማንመኘው መቅሰፍት ነው። ወደ ዋናው ጉዳዬ ስገባ አሁን እያየነውና እየሰማነው ያለው እልቂት ከበስተሁዋላው የመንግስት እጅ አለበት የምንልበት ምክንያት ህዝቡ ቄሮን ለመመከት በተነሳበት አካባቢ ሁሉ የአቢይ ወታደሮች ከገዳዮቹ ጋር በመተባበትር ወይም ገዳዮቹን በመደገፍ ራሱን ለማዳን የወጣውን ህዝብ ሲያዋክቡ፣ሲደበድቡና ሲያስሩ እንደነበር መረጃዎች በብዛት እየወጡ ነው። ባለፉትም የቄሮዎች ጥቃት የመንግስት ሰራዊቶች ተጠቂዎችን እያሰሩ አጥቂዎችን እያጀቡ ያሉበት የምስልና የድምፅ ማስረጃዎች አሉ። እንግዲህ የመንግስቱ ደጋፊዎች የሆናችሁ ይህንን እንዴት ነው የምትገልፁልን??/መንግስት የዜጎችን ደህንነት መጠበቅና ማስጠበቅ ሲገባው እጆቹን አጣጥፎ እያየ ባለበት ክፉ ሁኔታ ውስጥ፣ ዜጎችም ዝም ብለን የቆንጨራ እራት አንሆንም ብለው ለመከላከል ያላቸውን መሳሪያ ይዘው ሲወጡ፣ የመንግስት ሰራዊት ጥቃት ፈፃሚዎቹን ትቶ ተጠቂዎቹን ማጥቃቱ ከቶ ምን ይባላል????የመንግስት እጅ ባይኖርበትማ ኖሮ ፖሊሱ፣ሚሊሻው፣ልዩ ሃይሉ፣ ባጠቃላይ በመንግስት እዝ ስር ያለው ወደ 500 000 የታጠቀ ሃይል አሽባሪዎቹን በግማሽ ቀን በቁጥጥሩ ስር አድርጎ የሙዋቾቹን ህይወት ባዳነ ነበር። እዚህ ላይ መታወቅ ያለበት ነገር የዶ/ር አቢይ ሃይል የኦነግ፣ የቄሮ፣ የትህነግና የህወሃት ጦሮች ተደምረው እንኩዋን ከሚኖራቸው ሃይል የበለጠ እንደሆነ ነው። በዚያ ላይ ዶ/ር አቢይ የኤርትራው መሪ የኢሳያስ ሙሉ ድጋፍ እንዳለው ይታወቃል። ታዲያ በዚህ ሁሉ አቅም ለምንድነው ዶ/ር አቢይ ህዝቡን የማያድነው? ለምንድነው ገዳዮችን የሚወዳጀው? ለምንድነው የገዳዮችን ቤተሰቦች እግዜር ያፅናችሁ እንኩዋን የማይለው?? ለምሳሌ ያህል ባለፈው በጃዋር ለቅሶ ህዝብን የጨፈጨፉት (አማራውንም፣ ኦሮሞ ኦርቶዶክሶችን፣ ጉራጌውን፣ጋማውን የገደሉት) ገዳዮች ምነው አንዳቸውም ወደፍርድ አልመጡም?? ምነው በግድያቸው አልተጠየቁም? አያችሁ ወገኖቼ ምነው በእንቁላሉ ጊዜ በቀጣሽኝ እንደሚባል ቄሮዎች ገና ከጠዋቱ ከተማ ሲያሸብሩ ቆንጠጥ የሚያደርጋቸው መሪ ቢኖረን ኖሮ ይህንን ያህል ጥፋት ባላመጡ ነበር። በህግ የሚጠይቃቸው ቢኖር አርፈው በሰላም ይቀመጡ ነበር። ነገር ግን እውነት ለመናገር ጠ/ሚኒስትሩ ቄሮንና ኦነግን ካጠቃሁ የኦሮሞዎችን ድምፅ አጥቼ ከስልጣኔ እሰናበታለሁ በሚል ፍራቻ ባይያዝ ኖሮ ሃገሪቱን ከአሸባሪዎች ለማዳን አቅም ባልቸገረው ነበር። እንደእውነቱ ከሆነ በእኔ ግምት የኢትዮጵያ ነገር አክትሞለታል። ትንቢት ፈጣሪዎቹ የዘመኑ ሃዋሪያትና ነቢያት የሚናገሩትን “የብልፅግና ዘመን ይሆንልናል” “የመጎብኘት ዘመን ፊታችን አለ” የሚሉት ከኪሳቸው የሚተነብዩት ትንቢት አያታላችሁ። ፊታችን ያለው ዘመን የመበታተን፣ የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ፣ የእሬሳ ክምር፣ የሙሾ አውራጆች ዘመን ነው የሚሆነው። የምናገረው ትንቢት አይደለም፣ ተንባይም ባለራእይም አይደለሁም። መሬት ያሉትን አሰራሮች በማየት ጭንቅላቴን ተጠቅሜ ነው የምናገረው። ኢትዮጵያን የምትቀጥለዋ ዩጎዝላቪያ፣ ሶማልያና ሶሪያ የሚያደርጋት ብቻ ሳይሆን ከዛም በባሰ መልኩ የማንም መሳለቂያ እንድትሆን የሚያደርጋት ዘመን በደጅ ነው። ዶ/ር አቢይ የብሄርና የቁዋንቁዋን ድንበር እስካልገረሰሰ ድረስ፣ በአማራው ላይ የተጣለው ቅጥ ያጣ ጥላቻ ውንጀላና ግድያ እስካልቆመ ድረስ፣ ሃገሪቱዋ የእልቂት ቀጠና ነው የምትሆነው። ምክንያቱም አማራውና ጉራጌው፣ጋሞው ወዘተ የቄሮዎችን የኦነጎችንና የህወሃትን ጥይት ፣ሜንጫና ገጀራ ተንጋለው የሚቀበሉበት ጊዜ ማክተሚያው ሩቅ አይደለም። እነኝህ የጥቃት ታርጌቶች በተለይም አማራው፣ ብረትን በብረት፣ ሜንጫን በሜንጫ፣ ዱላን በዱላ እንዲመክቱ የሚያስገድዳቸው መገፋትና ጥቃት መፍለቅለቂያው ግለት ላይ ደርሶአል። ይህ እንዳይሆን መንግስት ከወንጀለኞች ጋር ማበሩን ትቶ ሃይሉን ተጠቅሞ ፀጥታን ያስከብር። ዶ/ር አቢይ በእጅህ ያለውን ሃይል ተጠቀምበት አለበለዛ ህዝቡም ሃገሪቱዋም አንተም በፊታችሁ ቀና ጊዜ አይሆንላችሁም!!!!!

የተቀነባበረው ኢትዮጵያን የማፈራረስ ሴራና የአንድነት ኃይሎች ድክመት

የምንተባበርበት ጊዜ ለአንድነት እንጅ፤ ለለቅሶ አይሁን—

Map of Ethiopia

አክሎግ ቢራራ (ዶር)

ኢትዮጵያ ሃገራችን በአሁኑ ወቅት፤ ከመቸውም ጊዜ በባሰ ሁኔታና ደረጃ፤ በውስጥ ተደራጅተው፤ በውጭ ኃይል በገንዘብ፤ በቴክኒክ፤ በመረጃ፤ በመሳሪያና በሌሎች ግብአቶች ተደግፈው፤ ጠባብ ብሄርተኞች፤ ጽንፈኞች፤ ሽብርተኞች፤ ቅጥረኞች፤ ከሃዲዎችና በተደጋጋሚ የፈፀሟቸውና አሁንም በንፁሃን እናቶቻችንና እህቶቻችን ላይ በተቀነባበረ ደረጃ የሚያካሂዱቸው የተቀነባበሩሩ የዘውግ ዘውግና ኃይማኖት ተኮር እልቂቶች፤ አገራችን ኢትዮጵያንም ወደ ጥፋት አፋፍ እያሸጋገሯት ነው።

በ 10/23/2016 “የአማራው ሕዝብ ህልውና” በሚል እርእስ” በጻፍኩት ማሳሰቢብያ፤ ፀረ-ኢትዮጵያና ፀረ-ኢትዮጵያዊነት ሴረኛው ህወሓት በማኒፌስቶው በጸነሰው አቅድ መሰረት በመሰብሰብ ሽብርተኞች አደጋውን እንደሚያስፋፉትና ለሕዝቡ ብቻ ሳይሆን ለኣገራችንም ህልውና ጭምር አደጋው እንደሚያሰጋት ጠቁሜ ነበር።

ዛሬ ሰፋ አድርጌ ስመለከተው፤ የትግሉ ጎራ ግልጽ ነው። በአንድ በኩል ቀና ደፋ የሚለው፤ ግን ገና አስተሳሰቡን፤ ኃይሉንና አቅሙን፤ ከኢትዮጵያ ፍላጎት ጋር ያላመጣጠነው ክፍል፤ በሌላ በኩል ባለፉት አርባና አምሳ አመታት ዘውግንና ኃይማኖትን ለይቶ ሲንቀሳቀስ የቆየው፤ ግዙፍ የውጭ ድጋፍ ያለው፤ ጠባብ ብሄርተኛነትን፤ ዘረኛነትን፤ ጽንፈኛነትን፤ “እኛና እናንተ” ባይነትን፤ “ክልላዊነትን” ባጭሩ፤ ፀረ-ኢትዮጵያና ፀረ-ኢትዮጵያዊነትን መለያው ያደረገው የብሄርተኞች ስብስብ ተዘጋጅቶ፤ ታጥቆ የተደራጀና የተቀነባበረ እልቂትና አገራችንን የማፍረስ ስራዎች በማካሄድ ላይ ይገኛል።

የመጀመሪያውን ክፍል ለምንደግፍ አገር ወዳዶች፤ ይህን ፈተና እንደ ወሳኝ እድል አይተን ተበታትኖና ሳይናበቡ ከመጨነቅ አለማችን ወጥተን ወደ ብሄራዊ አንድነት ከመሰብሰብ ውጭ ሌላ አማራጭ እንደሌላን ለማሳሰብ እፈልጋለሁ። ይህን ካደረግን፤ ረዢምና አስደናቂ ታሪክ ያላት፤ ለጥቁር ሕዝቦች ሁሉ የነጻነት ተምሳሌት የሆነችው፤ በፍጥነት ለማደግ የመቻል እድሏ ሰፊ የሆነችው፤ የአፍሪካ መዲና ኢትዮጵያ በምንም አትጠፋም እላለሁ። ይኼ ግን በምኞች ብቻ እንደማይሳካ ካለፉት ዓመታት ታሪካችን ልንማር እንችላለን። ኢትዮጵያን ለመታደግ የምንችለው በኢትዮጵና በኢትዮጵያዊነት የምናምነው ብቻ ነን። ፈረንጆችን ባናምናቸው እመርጣለሁ። በቅርቡ የሚያስተጋቧቸውን ሁኔታዎች ብቻ መመራመሩና መመልከቱ በቂ ነው።

እንደገና ላሰምርበት የምገፈልገው፤ የአማራው ሕዝብ ህልውና ከኢትዮጵያ ህልውና ጋር የተያያዘ መሆኑን ነው።

በሁለተኛው ክፍል ያስቀመጥኳቸው ኃይሎች ከውጭ መንግሥት (መንግሥታት ጋር) ተቀናጅተው፤ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን  በማያሻማ ደረጃ በማፈራረስ ላይ ይገኛሉ። ዝግጅታቸውና አቀነባበራቸው ስር-ነቀል ለውጥን ስኬታማ ለማድረግ መሆኑ በግልጽ ይታያል። “አገር ሲፈርስ ጃርት ያበቅላል” እንዲሉ፤ ሌላው ቀርቶ፤ በነጻነቷ ኮርታና ተከብራ በምትታወቀው አገራችን በኢትዮጵያ የግብፅን ባንዲራ ይዘው ሰልፍ የወጡ ግለሰቦች የሚታዩባት አገር ሆናለች። መለያችን ግብፅ ናት የሚሉ ግለሰቦች ጦርነት ቢካሄድ፤ ግብፅን ደግፈው ኢትዮጵያዊያንን ለመግደል ዝግጁ ናቸው ማለት ነው። እነዚህ ፀረ-ኢትዮጵያና ፀረ-ኢትዮጵያዊነት መመሪያቸው የሆኑት ግለሰቦች ኢትዮጵያን ጠልተው ግብፅን የሚያፈቅሩ ከሆነ የምመክራቸው ወደ ካይሮ ይሂዱና የተሻለ ኑሮ ትስጣቸው እላለሁ። ታሪካችንና እሴቶቻችን ሙሉ የክብርንና የነጻነትን እሴቶች የያዙ መሆናቸውን የሚያዩት ይህን ሲያደርጉ ብቻ ነው።

ለነዚህና ተመሳሳይ አመለካከት ላላቸው ሁሉ የምመክረው፤ ቅጥረኛና ሎሌ ሆኖ ከመኖር በድህነትና በነጻነት መኖርን እንመርጣለን ብሎ መስዋእት የሆነውን የኢትዮጵያን ጀግኖች ታሪክ ማወቅ ይበጅ ነበር የሚል ነው። ይህን እሴትና ፈለግ የሚከተለው ትውልድ ብቻ ነው ኢትዮጵያንና ኢትዮጵዊነትን ሊታደግ የሚችለው። ህብረትንና አንድነትን እንምረጥ፤ ለብሄርተኝነት፤ ለዘረኝነት ቦታ አንስጥ የምለው ለዚህ ነው።

ኢትዮጵያን ከድህነትና ከኋላ ቀርነት አሮንቃም ነጻ የሚያወጣት ይህ የማህበረሰብ ክፍል ብቻ ነው። ህብረት ይኑረን የምለው ለዚህ ነው። ግብፅን ተቃውሞ የሕዳሴን ግድብ ስኬታማ ለማድረግ የሚችለው ኃይልም ይኼው ነው። ህብረት ይኑረን የምለው ለዚህ ነው። ተራው ኢትዮጵያዊ ካለችው ገንዘብ እያወጣ ህዳሴን ለመገንባት የቻለው ህብረት ስላለው ነው። ከሃዲዎችና ቅጥረኞች እንኳን ይህን ለማጤንና ለማድረግ ቀርቶ ሰብአዊ ፍጥረት ምን እንደሆነም አያውቁም። የሚተባበሩት ለጥፋት እንጅ የተራውን ሕዝብ ኑሮ ለማሻሻል አይደለም።

ቢሆንማ በሻሸመኔ ሆነ በሌላው ክፍል ታታሪዎች አርባ ዓመት ጥረው ግረው የመሰረቱትን የኢኮኖሚ ተቋም፤ ለብዙ ድሃዎች የስራ እድል የፈጠረውን ብሄር እየለዩ አያወድሙትም ነበር።

የዘውግ ጥላቻ ውድመት ነው።

የህወሓት ቡድን መለያው በማኒፌስቶው ላይ “የአማራውን ሕዝብ የትግራይ ሕዝብ ጠላት ነው” ብሎ በመበየን፤ ይህን ታላቅ ሕዝብ ለአደጋ አጋልጦት ወደ መቀሌ መግባቱ ነው። የኢትዮጵያን ሕዝብ ከቋንቋ ውጭ ለመለየት አይቻልም። አማራውና ትግሬው፤ አማራውና ኦሮሞው፤ ኦሮሞውና ሌላው ወንድማማች ሕዝብ ነው። ሰማንያ በመቶ የሚሆነው ድብልቅ ነው። ከቋንቋው ውጭ ይህን ታላቅ ሕዝብ እንዴት ለመለየት ይቻላል? አይቻልም። የሚለዩት ልሂቃን፤ ጽንፈኞች፤ ጠባብ ብሄርተኞችና የኢትዮጵያን አንድነት የማይፈልጉ ፈረንጆች ናቸው። የሚለዩት ግብጾች ናቸው። ለምን? ለራሳቸው ጅዖፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ብቻ። የግብፅ ዋና ዓላማ አባይን በበላይነት መቆጣጠር ነው። ይህን ለማድረግ የምትችለው የኢትዮጵያን ሕዝብ በመከፋፈል፤ አገራችን ደክማና ኋላ ቀር ሆና እንድትቆይ በማድረግ ብቻ ነው።

ግብፅ የውክልና ጦርነት እድምታካሂድ በተደደጋጋሚ እኔ ብቻ ሳልሆን የታወቁ ተመራማሪዎችና የታሪክ ምሁራን ዘግበውታል። ወደ አገር ውስጥ የሥልጣን ግብግብና እልቂት ስሄድ፤ ለኢትዮጵያ ደህንነትና ብልጽግና የሚመኝ ኃይል አንዱን ዘውግ ወይንም ኃይማኖት ከሌላው እየለየና ድጋፍ እየሰጠ እርስ በርሳችሁ ተፋጁ አይልም። ይህን ሲያደርግ የሚያገልግለው የኢትዮጵያን ጠላት መንግሥታት፤ በተለይ ግብፅጽን ነው። የውጭ ጠላት፤ ቅጥረኞችን እየመለመለ፤ በገንዘብ እያባበለ፤ የውጭ መገናኛ መሳሪያ እየሰጠ እልቂት እንዲያካሄድ ማድርገጉ ባያስደንቅም፤ የሚያስደንቀው በተከታታይ፤ የውስጥ አርበኞችን ለማደራጀት፤ ለማስታጠቅ፤ ለማስልጠን ተቀባይነት የሚያገኝበት ምቹ ሁኔታ ማግኘቱ ነው። ማን አመቻቸው? ይህን ለሌላ ጊዜና ለሌሎች ልተወው።

የተቀነባበረው አመጽና እልቂት ገጽታ ምን ይመስላል?

የዝነኛው አርቲስት የኃጫሎ ሁንዴሳ አስቃቄና ኢ-ሰብ አዊ ግድያ ታስቦበት፤ ታቅዶበት የተፈጸመ ወይንጀል ነው። ገዳዮቹ ምህረት ሊደረግላቸው አይገባም። ይህ ግድያ ብቻውን ሊታይ አይገባም። በተከታታይ የተካሄዱ የፖለቲካ የግድያ ሙከራዎችና ግድያዎች ሊጠቀሱ ይገባል። እነዚህን በጅምላ “የሰኔ ግድያዎች” ልበላቸው።

  1. በጠቅላይ ሚንስትር ዶር ዐብይ አህመድ ላይ የተደረገውን የነፍስ ግድያ ሙከራ ማን አደረገውና ለምን?
  2. ከአንድ ዓመት በፊት በሰኔ በነ ዶር አምባቸው መኮነንና ጓዶቹ፤ ብርጋዴር ጀኔራል አሳምነው እና በኢትዮጵያዊው የጦር መኮነን እና ኢታ ማጆር ሹም ሳእረ ላይ የተካሄደውን ጭካኔ የተሞላበት ግድያ ማን ጠነሰሰውና ማና አካሄደው?
  3. ለሶስተኛ ጊዜ በሰኔው ወር፤ በኃጫሎ ላይ የተካሄደውን የነፍስ ግድያስ ማን ጠነሰሰው፤ ማን አቀነባበረው፤ ማን ፈጸመውና ለምን?

እነዚህና ሌሎች ተመሳሳይ የፖለቲካ ግድያዎች ለፖለቲካ ሥልጣን ዓላማ የተቀናጁ እንጅ የግል የቂም በቀል ግድያዎች አይደሉም። ቸልተኛነት ያስበላል የምለው ለዚህ ነው። በመጀመሪይው የግድያ ሙከራ ላይ ፈጣንና የማያሻማ እርምጃ ቢወሰድ ኖሮ ተደጋጋሚነት ሙሉ በሙሉ ይጠፋል ለማለት ባልችልም፤ ይቀንሳል። የሕግ የበላይነት ትርጉም ይኖረዋል። ሌሎችም ግድያዎች፤ ለምሳሌ፤ ዘውግን ወይንም ኃይማኖትን ኢላማ ያደረጉ በቀላሉ ከታለፉ፤ የተመለመዱ ይሆኑና  ግድያዎቹ ተከታታይ ይሆናሉ።

ለማንኛውም፤ የኢትዮጵያ መሰረታዊ ጠንቅና ችግር የውስጥ መሆኑ በተከታታይ ይታያል ። ተራው ሕዝብ አይደለም። የኢትዮጵያ እናቶችና ወጣት ሴቶች እንጨት እየተሸከሙ ግብፅን እንደግፋለን፤ ዓባይን መገደብ አያስፈልግም የሚሉ ግለሰቦችና ስብስቦች አሁንም የሚኖሩባት አገር የምታሳየቸው ግድፈቶችና ክፍተቶች አሉ። ብሄርን ከብሄር፤ ኃይማኖትን ከኃይማኖት ጋር የሚጋጩ ግለሰቦች፤ ስብስቦች፤ በየክልሉ ደሞዝ እየተከፈላቸው ለአጥፊዎች ተገንና ሽፋን የሚሰጡ ባለሥልጣናት ያሉባት ክፍተትና እደጋ የተሸመከች  አገር መሆኗን ያሳያል። ጠብ ጫሪዎች፤ ሕዝብን ከሕዝብ ጋር አጣልተው የሚሸሹ ወይንም የሚደበቁ፤ በውጭ ሆነው ያለምንም ስጋት ራሳቸው በነጻ አገር እየኖሩ ለተራው ድሃ ህዝብ ደንታ የሌላቸው ከሳት ላይ ቤንዚን የሚነሰንሱን ግለስቦች በቸልተኛነት ስትመለከት የቆየች አገር ናት ኢትዮጵያ። ዘውግና ኃይማኖት እየለዩ ብቻ እናቶቻችን፤ አክስቶቻችን፤ በአገራቸው የስራ እድል ሲያጡ፤ በርሀና ባህር ተሻግረው አሰቃቄ በሆነ ደረጃ በመካከለኛው ምስራቅ ተሰደው የቀን ሰራተኛ እንደሆኑ እያየዩ በአገራቸው የተሻለ የስራ እድል በመፍጠር ፋንታ ብሄርተኞችና ጽንፈኞች ልዩነቶችን ያበረታታሉ። ግጭቶችን ይፈጥራሉ፤ ንጹሃንን በዘውግ እየለዩ ይገድላሉ። ለግብጽ አገግጋይ እንሁን ይላሉ።

የፖለቲካ ልሂቃንም፤ በአብዝኛው ገንቢ የሆኑ አማራጮችን ሲያቀርቡ አላይም። በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊነት እናምናለን የሚሉትም ቢሆኑ እስካሁን ድረስ በአንድነት ለአንድ አገር ብሄራዊ አላማና ልማት አማራጮችን ለሕዝብ ሲያያቀርቡ አላየሁም። በተጻራሪው ክፍል የተሰብሰበቡት አፍራሽ ስብስቦች፤ ማለትም፤ ጠባብ ብሄርተኞች፤ የብሄር አክራሪዎችና ትምክህተኞች፤ የእነዚህ ኃይሎች የውጭ ደጋፊዎችና አቅም ገንቢዎች፤ ጦር አቀባዮች፤ የማህበረሰብ ሜድያ አርበኞች ወዘተ የችግሩ ዋናው አካል ናቸው። ጥላቻንና እልቂትን የሚያካሂዱት እነዚህ ናቸው።

ድሃው ተራ ሕዝብ ለጎረቤቱ ጠላት ሆኖ አያውቅም። ዛሬም እንዳለፉት የኢህአዴግ አመታት፤ የዘውግ ጥላቻን ጽንሠ ሃሳብ ማን መሰረተው፤ ማን ያራግበዋል፤ ማን እንደ መርዝ አስራጨው፤ ማን ይጠቀምበታል፤ ማንን ይጎዳል? ብለን መጠየቅ ተገቢ ነው። ምክንያቱም ችግሩን በሚገባ ተረድተን መፍትሄ ካልፈለግንለት፤ ጥላቻው ለንጹሃን ሞትና ለግዙፍ ንብረት ውድመት ጠንቅ ከመሆኑ ባሻገር፤ አገርንም ያጠፋል። አሁን ያለንበት ደረጃ ይኼው ነው።

የኢህአዴግ መንግሥት ሲመሰረት፤ ህወሓት መራሹ ቡድን የኢትዮጵያዊያንን ብሄራዊ አንድነት (እኛ ኢትዮጵያዊያን በሚል ስያሜ) መሰረት በማድረግ ፋንታ “የብሄር፤ ብሄርሰብና ሕዝቦችን” መለያ አድርጎ ያዋቀረው ሕገ መንግሥትና የክልል አስተዳደር ልዩነቶች እንዲሰፉና እየተካረሩ እንዲሄዱ  ገደብ የሌለበት ማንነትን እያመረተ ቆይቷል። የዜግነት መብት ተቀዳሚ አለመሆኑ በየክልሉ ለተፈለፈሉ የፖለቲካ ልሂቃን ኑሮ አመች ሁኔታን ከመፍጠሩ በስተቀር ለነዋሪው ሕዝብ ያስገኘው መብትና ጥቅም የተወሰነ ነው። የክልሉ አስተዳደር ያስከተለው አሉታዊ ውጤት ግዙፍ ነው።

በዘውግ የተዋቀረና በዘውግ ርእይቱ የሚያምን ቡድን፤ ይህን  ሕዝብን የሚያጨራርስ፤ አገርን የሚያጠፋ ጠንቅ ፈጥሮ ሊፈታው አልቻለም። ስር ነቀል መፍትሄ በመፈለግ ፋንታ፤ ችግሩን ሲያስታምመው ቆይቷል። በሳቱ ላይ ቤንዚን የሚረጩቱን አጥፊዎች በእንዝህላልነት ቸል ብሏቸው ወይንም ትቷቸው ቆይቷል። አጥፊዎቹ ይጠብቁት የነበረው እድል እስከሚፈጠር ድረስ ነበር። እድሉን ራሳቸው ፈጥረዋል፤ የውጭ ኃይሎችም፤ በተለይ ግብጽ ፈጥራላቸዋለች። ይህን የህዳሴ ግድብና የአባይ ወንዝ መዘዝ ልበለው።

ግብፅ ኢትዮጵያን ለማጥቃት ከጥንት ጀምራ ልዩ ልዩ ዘዴዎችን ተጠቅማለች። ከእነዚህ መካከል የአገር ውስጥ “አርበኞችን” መመልመልና በገንዘብ ደጉሞ ማሰማራት አንዱ ዘዴዋ ነው። በሃይማኖት ስም፤ በፖለቲካ ስም፤ ወዘተ። ዘዴው ብዙ ነው። ስንት ትከፍላለች? አባይ ወንዝ በገንዘብ አይተመንም። ዓባይ የህልውናና የብሄራዊ ደህንነት፤ የኑሯችን መሰረት ጉዳይ ነው። ግብፅ የአባይን ወንዝ በበላይነት ለመቆጣጠር መቶ ሚሊየን ዶላር በአንድ ጊዜ ፈሰስ ብታደርግ አልደነቅም። አስር ሽህዎች ንጹህ ኢትዮጵያዊያን ቢሞቱ ግብፅ ደንታ የላትም። የኢትዮጵያ መንግሥት ፈርሶ አገራችን መንግሥት አልባ ብትሆን ትመርጣለች። ለዚህ ነው፤ ግብፅ ኢትዮጵያን በቀጥታ በጦርነት ለመዋጋት አቅም ባይኖራትም የውክልናውን ጦርነት በምንም ደረጃ አታቆምም የምለው።

የእንግሊዙ መገናኛ ቴሌግራም ዩኬ July 4, 2020, ባቀረበው ዘገባ፤ አንድ የግብፅ አውሮፕላን ከግብጽ ተነሰቶ በብዙ ሽይዎች የሚገመት ካላሽንኮብ፣ ሮኬትና ሌሎች ልዩ ልዩ መሳሪያዎች ጭኖ ወደ ሞቃዲሾ፤ ሶማልያ በረረ። የሶማልያ መንግሥት ይህን መሳሪያ መልሱት እንጂ ከጎረቤት አገር ከኢትዮጵያ ጋር ለመጋጨት አነፈልግም ብሎ ወደ ካይሮ እንዲመለስ ያደረገው በቂ ምሳሌ ነው።

ግብጽ ኢትዮጵያን በቀጥታ ለመዋጋት ሞክራ በተደጋጋሚ ተሸንፋለች። ያላት ሌላ አማራጭ የውክልና ጦርነት ማካሄድ ነው። ለዚህ ደግሞ እድል አላት፤ ቅጥረኞችን ማባበል፤ ገንዘብ ብቻ ሳይሆን መሳሪያም እያቀበለች ኢትዮጵያን ማዳከም ነው። የርስ በርስ ጦርነት እንዲካሄድ ታመቻቻለች ማለት ነው። በሰሜን ህወሕት መራሹ ቡድን “የእርስ በእርስ ጦነት አዋጅ አውጇል” እየተባለ ይወራል። በምስራቅና በደቡብ፤ በአዲስ አበባና በዙሪያዋ፤ የሽኔ ኦነግ፤ የአል-ሸባብ፤ የቄሮና ሌሎች አክራሪዎችና አመጸኞች ንጹሃንን እየገደሉ “የነፍጠኛውን መንግሥት” ማንበርከክ አላማችን ነው ብለው ቅንብሩን የሚያካሂዱት። ቀደም ብለን ስራ አለመስራታችን አደጋውን አባብሶታል።

ለማጠቃለል፤ ቅጥረኞች ዘውግንና ኃይማኖትን እየለዩ በተከታታይ እልቂት ማካሄድ የተለመደ የሆነው ህወሓት መራሹ ኢህአዴግ ሥልጣን ከያዘበት ወዲህ መሆኑ የታወቀና በመረጃዎች የተደገፈ ነው። ስርዓት ወለድ ነው የምልበት መሰረታዊ ምክንያት ይኼው ነው።

የዘውግ ተኮሩ ሕገ-መንግሥትና የክልሉ አስተዳደር መለያዎች ጭካኔ፤ አንዱን ብሄር ከሌላው እየለዩ ማሳደድ፤ መግደል፤ ኃብትና ንብረቱን፤ እሴቱን፤ ተቋሙን፤ ምልክቱን ማፈራረስና በስነልቦናው ላይ ተከታታይ ዘመቻዎችን ማካሄድ የተለመደ ሆኖ ቆይቷል።

ይህ ተከታታይ የማውደምና የማጥፋት ዘመቻ ትኩረት የተደረገበት የብሄር ማጥቃት ሰቆቃና የጭካኔው መጠን በመረጃዎች ተደግፎ ይፋ እየሆነ ሲሄድ፤ አረመኔነትን፤ ኢ-ሰብ አዊነትን፤ አውሬነትን፤ “ከኔ ዘውግና ከኔ እምነት ውጭ” መኖር የለብህም፤ የለባትም የሚል እብሪተኛነትን የሚንጸባርቅበ እልቂትን የሚያሳይ ገጽታ ይታያል።

ኢትዮጵያ ገና ሩዋንዳ ከደረሰችበት ደረጃ ላይ አልደረሰችም ለማለት አልችልም፤ ከደረሰች ብዙ አመታት አልፈዋል።  የሩዋንዳ አይነት እልቂት ደሩሷል የምንለው ስንት ንጹህ አማራዎች፤ ወላይታዎች፤ ጉራጌዎችና ሌሎች ንጹህ ወገኖቻችን ሲሞቱ ነው? ብዙ ወገኖቻችን ታርደዋል፤ ሞተው ያልተቀብሩም አሉ፡፡ ይህ ጭፍጨፋ ሩዋንዳ፤ ኮሶቮና ሌሎች የዘውግ እልቂቶች የተካሄዱባቸውን አገሮች ታሪክ የሚሳይ ኢ-ሰብ አዊ ተግባር ነው፡፡ ወንጀል ነው፡፡ ጾታ፤ እድሜ፤ የገቢ መጠን፤ እናት፤ ህጻን፤ ሽማግሌ፤ እርጉዝ ሴት፤ ወንድ፤ ቦታ ወዘተ በማይለይ ብሄር ተኮር ግድያ በተደጋጋሚ ተካሂዷል ማለቴ ነው። ኢላማው በተለይ አማራውን እየለየና ስም እየሰጠ፤ “ነፍጠኛ ነህ” እያለ፤ ኢላማ የሆነውን ለይቶና አስቀድሞ ጠቁሞ፤ ግድያዎችና አካሂዶበታል፡፡ በቅርቡ፤ በወላይታው፤ በጉራጌውና በሌሎች ብሄር አባላት ላይም ጭካኔ የሞላበት ጭፍጨፋ ተካሂዷል። ግለሰሰቦችና ቤተሰቦች ጥረው ግረው ከሰላሳ እሰከ አርባ ዓመታት በፈጀ ጊዜ ያካበቱትን መዋእለንዋይ ኢላማ ተደርጎ እንዲወድም ሆኗል። ይህ ለወገኖቻቸው የስራ እድል፤ የገቢ እድል፤ የኑሮ መሻሻል እድል ውድመት፤ የኢኮኖሚ ወንጀል ነው።

ለማጥዕቃለ፤ ምን ለማድረግ እንችላለን?

የትግሉን ጎራ ለይቸ ለማሳየት ችያለሁ የሚል እምነት አለኝ። ባጠቃላይ ስመለከተው፤ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊነት ላይ እምነትን ያለን ሁሉ ያለን አማራጭ አንድ ብቻ ነው። በአንድነት ተሰብስቦ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን መታደግ ወሳኝ ነው። ዘውግና ኃይማኖት ተኮር ግድያዎችን ሁሉ ማውገዝ አለብን።

ችግሩ እየተባባሰ ሂዷል የሚሉ ብዙ ታዛቢዎች አሉ፡፡ ለምሳሌ፤ በሰሜን፤ ህወሓት የኢትዮጵያን ሕዝብ ለክተት አዋጅ የሚቀስቅስ አዋጅ አውጇል። ይህ አዋጅ የትግራይን ሕዝብ ይወክላል የሚል እምነት የለኝም። ሰፊው የትግራይ ሕዝብ ከሌላው ወንድሙ ጋር ወደ እልቂት ለመሄድ አይፈልግም። የህወሃትን አጥፊነትና አገር አፍራሽነት የሚቀበሉ ሁሉ በአንድ ላይ ሆነው ይህን ሽብርተኛና የውጭ ጠላት አጋር ቡድን መታገል አለባቸው፡፡ በተጨማሪ፤

  1. አንደኛ፤ ህወሓት የወገነውና የዶሎተው፤ በውጭ ከግብፅ ጋር ነው። በውስጥ ደግሞ አጋሬ ነው ከሚለው ከሽኔ ኦነግና ከቄሮ ጋር ነው። ለምሳሌ ዘውግን ለይቶ እልቂት ከሚያካሂደው ከሽኔ ኦነግና ከቄሮ ጋር ሆኖ ግፍና ጭካኔ በሚያሳይ ወንጀለኛነነት ከሚያንጸባርቀው ጨካኙ ወንጀለኛ ጋር የተቀናጀ ግፍና እልቂት በሻሸመኔ፤ በሃረር፤ በድሪዳዋ፤ በባሌ ይካሄዳል። እነዚኅ ግፎችና እልቂቶች በድምራቸው ስገመግማቸው የጀኖሳይድይ ወች መስራችና መሪ ዶር ግሬገሪ ሃንተን ያወጧቸውን አስርት መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆናቸውን የሚያሳይ ሁኔታ ይታያል። SAGE ያቀረበውን ትንተና እጋራለሁ፤ እደግፋለሁ።
  2. የህወሓት ረዥም ክንድ በነዚህና በሌሎች እልቂቶች በደም የተቀባ መሆኑን ለማሳየት የሚቻልበትን መረጃ ለመሰብሰብና ለዓለም የወንጀል ተቋማት ለማቀረብ የሚቻልበት ሁኔታና እድል እለ። ይህን ለማድረግ የሚችሉ የህግ ባለሞያዎችን መሰብሰብና በገንዘብ መርዳት ወሳኝ ነው።
  3. በተጨማሪ ቅድሚያ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው ብሄራዊና አስኳል ጉዳይ ህወሓት፤ ሽኔ ኦነግና ቄሮ በአሁኑ ወሳኝ ወቅት ከግብፅ ጋር ወግነው፤ የሕዳሴ ግድብ ሙሌት እንዲኮላሽ ለማድረግ የሚያደርጉትን ሴራ፤ በሁሉም ዘርፎች ድምጻችንና አቤቱታችን ማሰማት ብሄራዊ ግዴታችን ነው። ይህን ከሃዲ ተግባር አወግዛለሁ።
  4. ይህ ሴራ ስኬታማ እንዳይሆን ከፈለግን፤ ኢትዮጵያ መሪዎችና መንግሥት አልባ እንዳትሆን አግባብ ያለው አቋም መውሰድና በማያወላውል ደረጃ ድጋፋችን የምናሳይበት ወቅት ዛሬ መሆኑን ለማሳሰብ እፈልጋለሁ።
  5. እኢትዮጵያና እኢትዮጵያዊነት ኩራታችን፤ ክብራችን፤ መለያችን፤ የአቅም መንስ ኤያችን ናቸው፡፡ ከመሳሪያና ክምችት ይልቅ፤ ለኢትዮጵያ ሃገራችን ዋና መከታችን፤ ክንዳችን፤ ሃይላችን፤ መከታችን፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ስርጭትና ብሄርዊ አንድነትና ጀግናነት ነው፡፡
  6. በመጨረሻ፤ ግዙፉ የኢትዮጵያ ምሁራንና ልሂቃን ጥቃቅን ልዩነቶችን ወደ ጎን ትቶ ለብሄራዊ አላማ እየተናበበ የሚሰራበት ወቅት አሁን ነው;፡

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!! ብሄር ተኮር እልቂትን ባስቸኳይ እናስቁም!!፤ የኢትዮጵያዊያንን አንድነት እንደግፍ!!

July 10, 2020