የተጋሩ ፈተናዎች እና የመፍትሔ ጥቆማዎች (በአቤል ዋበላ)

 

ወያኔ-ህወሓት ለትግራይ ህዝብ (ተጋሩ) በረከት ወይስ መርገም አመጣለት የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ጥልቅ ጥናት የሚያሻው ይመስለኛል፡፡ ይህንን ጥናት ለማካሄድ ቁርጠኝነት ቢኖር እንኳን ጉዳዩ ተጨማሪ ገቢሮችን እያስተናገደ መሄዱ ጉዳዩን የበለጠ ውስብስብ ያደርገዋል፡፡ ይህ ደግሞ ባለአእምሮ የሆነን ሁሉ ያስጨንቃል፡፡ ምክንያቱም ዋጋው ከጥቂት የንጹሐን ደም እስከ ዘር ማጥፋት ድረስ የሚያስከተል አሳሳቢ እና አደገኛ ስለሆነ ነው፡፡ ከደደቢት አንስቶ እስከ አራት ኪሎ(1996-1983 ዓ.ም.) ያለውን ማስላት አጠቃላዩን የቡድኑን ጉዞ እና መጪውን ጊዜ እንደመተንተን አይከብድም ብዬ አስባለው፡፡ የነገው ግን ትልቅ ሸክም ነው፡፡ ይህንን ማድረግ የሚችለው ከስሜት የጸዳ እና አስተዋይ አእምሮ ያለው ሰው ነው፡፡ በዚህ አጭር ጽሑፍ ያንን ሚና የመወጣት ትዕቢት እንደሌለ ከወዲሁ መግለጽ አስፈላጊ ይመስለኛል፡፡ ነገር ግን የብዙ ወገኖቼ ስጋት የኔም ስጋት ነውና ዝም ከማለት አንዳንድ ሐሳቦችን ለመጠቆም ሰለመረጥኩኝ ይህንን ጻፍኩኝ፡፡
ከፈተናዎቹ ልጀምር፡፡ የተደበቀ ነገር ሳይሆን ሁላችንም ያስተዋልነው የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡ ወያኔ አምባገነን የሚያስብሉ ሁሉንም አይነት ዕኩይ ተግባራት ፈጽሟል፡፡ ይህ ለትግራዋይም ሆነ ለሌላው ኢትዮጵያዊ የተሰወረ አይደለም፡፡ ላለፉት ሁለት አስርት አመታት በኢትዮጵያ ያለው ስርዓት ጨቋኝ አይደለም ወይንም ቢያንስ የተወሰነው የትግራይ ተወላጅ የተለየ ጥቅም አላገኘም ብሎ የሚያምን ቢኖር ከዚህ በታች ያለውን በማንበብ እራሱን እንዳያደክም እመክራለው፡፡

ጦማሪ አቤል ዋበላ
ጭቆናን ለዘላለም ተሸክሞ የሚኖር ህዝብ ስለሌለ ጊዜው ሲደርስ በአብዛኛው ሀገሪቱ ክፍል ህዝባዊ እምቢተኝነት ተነስቷል፡፡ ይህንን እምቢተኝነት ለማፈን ስርዓቱ የጭካኔ እርምጃዎች እየወሰደ ደም እያፈሰሰ ነፍስ እየቀጠፈ ነው፡፡ ይህም ህዝቡን ወደ አልሞትባይ ተጋዳይነት እያመራው ነው፡፡ በሞት እና በህይወት መካከል ያለ ሰው ደግሞ የሚታገለው ጨቋኙ በመረጠለት መንገድ ብቻ ነው፡፡ ጨቋኙ የውሸት ዴሞክራሲን እና መከፋፈልን እንደተጠቀመው ሁሉ የትግራይ ህዝብንም እንደመሳሪያነት ተጠቅሟል፡፡ ለአንዳንዶች ደግሞ ጨቋኙ የትግራይ ህዝብ ጉያ ውስጥ የተሸሸገ በትግራይ ህዝብ የሚነግድ ሳይሆን እራሱ የትግራይ ህዝብ ነው፡፡
ወደዚህ ድምዳሜ ላይ ለመድረሳቸው ሁለት ዐብይ ምክንያቶችን ይጠቀሳሉ፡፡ አንደኛው የትግራይ ተወላጆች ለስርዓቱ ያላቸው ስስ ልብ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በጉልህ የሚታየው በሁሉም ዘርፍ ያለ ተጠቃሚነት ነው፡፡ ተጋሩ ስለወያኔያዊው ስርዓት መቆርቆራቸው አንደኛው ምክንያት ተፈጥሮዊ የሆነና በሰውን ልጆች መካከል ያለ የቅርብ ወገንን አብልጦ የመውደድ ስሜት ነጸብራቅ ስለሆነ ጤነኛ እና የሚጠበቅ ነው፡፡ ሁለተኛው ምክንያት የወያኔ ፕሮፓጋንዳ ያዋለደው ነው፡፡ ‘እኛ ነን ከአውሬው የደርግ ስርዓት ነጻ ያወጣናችኹ’ ከሚለው አንስቶ ‘የኢትዮጵያ ህዝብ ከትግራይ ህዝብ ጋር ጠላትነት ውስጥ ገብቷል፤ ስለዚህ እኛን መደገፍ ያለባችኹ ለራሳችሁ ህልውና ስትሉ ነው’ እስከሚለው የሚደርስ ነው፡፡ የትግራይ ተወላጆች ተጠቃሚነት ሁሉንም ዘርፍ ያካለለ ነው፡፡ መደበኛ እና ኢ-መደበኛ የፖለቲካ ስልጣን የበላይነቶች፣ ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚያዊ አብላጫዎች፣ በሠራዊቱ፣ በፖሊስ እና በደህንነቱ ውስጥ ያሉ ፍጹም የበላይነቶች በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
እነዚህን ሁለት ጉዳዮች የሚመለከቱ ተጋሩ ያልሆኑ ኢትዮጵያውያን ህወሓትን ከትግራይ ህዝብ ለመለየት ቢከብዳቸው አይፈረድባቸውም፡፡ ምክንያቱም የትግራይ ህዝብ በሀሳብም በተግባርም የህወሓት አቻ ገጽ ሆኖ ስለተሳለ ነው፡፡ ማደናገሩ መደናገር ሆኖ ቢቀር መልካም ነበር፡፡ ግን አልሆነም፡፡ ከላይ እንደጠቀስኩት ጨቋኙ ለተጨቋኙ የመታገያ መንገድ እየመረጠለት ነው፡፡
ከቀልባቸው ጋር የሆኑ ተጋሩዎች ፈተና ይሄ ነው፡፡ በጠራራ ጸሐይ የሚፈጸመውን በደል ይመለከታሉ፡፡ ይህንን ለማስወገድ የሚደረግ ትግል ተገቢ እና የተቀደሰ እንደሆነ ይገነዘባሉ፡፡ ነገር ግን ይህ ትግል የገዛ ወገናቸውን ዒላማ ሊያደርግ ይችላል፡፡ በሥራው ጥፋት ተመጣጣኝ ቅጣት ቢያገኝ ችግር አይኖረውም ነበር፡፡ ነገር ግን አንድ ሰው ስርዓቱ የፈጠረለትን ኢ-ፍትሓዊ ዕድል ተጠቅሞ አዲስ አበባ ላይ ሰማይ ጠቀስ ፎቅ ቢገነባ ወይም ጋምቤላ ሰፋፊ እርሻዎች ቢኖሩት አልያም ከኦሮሚያ ጫት እና ቡና ወደውጪ ቢልክ ደክሞ ያገኘውን በመተው በዘረፋ የወሰደውን ንብረት እንዲመልስ እና ለተላለፈው ህግ በፍርድ ቤት እንዲጠየቅ ይደረጋል እንጂ ህይወቱን እንዲያጣ መደረግ የለበትም፡፡ ይህ በግለሰብ ደረጃ ያለ ነው፤ ወደጅምላ ጭፍጨፋ ላለማደጉ ግን ምንም ዋስተና የለንም፡፡
ይህንን ያልተመጣጠነ ምላሽ እና የጅምላ ፍረጃ በመስጋት ተጨቋኙን በስርዓቱ ላይ ማመጽን ተው ማለት ተገቢ እንዳልሆነም ሁሉም ይረዳዋል፡፡ በዚህ ምክንያት የትግራይ ተዋላጅ የሆነ ባለአእምሮ ኢትዮጵያዊ ‘የገደለው ባልሽ የሞተው ወንድምሽ ሀዘንሽ ቅጥ አጣ ከቤትሽ አልወጣ’ ሆኖበት ተጨንቆ ይገኛል፡፡ ይህም እጅና እግሩን አስሮ የበይ ተመልካች አድርጎታል፡፡ የችግሩን ስፋት ቢገነዘብም ምንም አይነት ሱታፌ አለማድረጉ ሁሉን ነገር ጊዜ እንዲፈታው የተወ ያስመስልበታል፡፡ ነገር ግን ችግር ሳይፈቱ እንዳለ ቢተውት የበለጠ ውስብስብ ሆኖ ለመፍታት አስቸጋሪ ይሆናል እንጂ ወደ ሰማይ አይተንም፡፡
ከላይ ያነሳነው ዝምታ ለሁላችንም አይበጅም፡፡ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም በትግራይ ተወላጆች ግምባር ቀደም ተነሳሽነት ያልተጀመረ ትግል ሀገርን እንዳማያድን ጽፈዋል፡፡ ስለዚህ ለሁላችንም ሲባል ይህን ዝምታ( እርግጥ ነው ይህ ዝምታ የማይመለከታቸው ከጥቂት ግለሰቦች መኖራቸውን አልክድም) መስበር አስፈላጊ መሆኑን በማመን አንዳንድ ሊደረጉ የሚችሉ ነገሮችን መጠቆም ወደድኩኝ፡፡ ጥቆማዎቹ መሰረት ያደረጉት ይህንን ስርዓት ለመለወጥ ወይም ተገዶ መሰረታዊ ማሻሻሎችን እንዲያደርግ የትግራይ ተወላጆች ሚና ምን ይሁን በሚለው እና ለውጥ ቢመጣ ደግሞ ለውጡ በሰላማዊ ሽግግር የሚጠናቀቅበትን የትኛውም የኢትዮጵያ ማኀበረሰብ የጥቃት ዒላማ እንዳይሆን ማድረግን ነው፡፡
1. የትግራይ ብሔርተኝነት ፈር ማስያዝ:- በስርዓቱ አፈቀላጤዎች ሆን ተብለው የሚቀናበሩ አጀንዳዎችን በጥንቃቄ ማስተዋል ይገባል፡፡ ለምሳሌ አጼ ዮሐንስ በኢትዮጵያ ታሪክ ያላቸውን ድርሻ ማጉላት እንደምሳሌ መጥቀስ ይቻላል፡፡ ንጉሱ እንደሌሎቹ የሀገሪቱ ነገስታት የሚነቀፍ እና የሚያስመሰገን ታሪክ ሰርተው አልፈዋል፡፡ ይህንንም ሁሉም ኢትዮጵያው ይረዳዋል፡፡ ዝርዝሩ ለአካዳሚያዊ ስራዎች የሚተው ነው፡፡ ነገር ግን አጼው ከሌሎች ነገስታት ተነጥለው እንደሚወቀሱ እና በሌሎች ኢትዮጵያውያን ህሊና ተገቢው ቦታ እንደሌላቸው አድርጎ የማቅረብ አባዜ ይስተዋላል፡፡ ይህ የትግራይ ተወላጅ የሆነ ኢትዮጵያዊን በጭፍን ለመንዳት ካልሆነ ምንም ረብ የለውም፡፡ በቅርቡ የሰማኹት ደግሞ “‘ትግሬ’ ብሎ መጥራት አስነዋሪ ነው የትግራይ ተወላጅ ትግሬ ሳይሆን ‘ተጋሩ’ የሚባለው ነው’ የሚል ክርክር ነው፡፡ ይህ ከቀድሞው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ‘…ወርቅ የሆነው…’ ከምትል ንግግር ጋር ሲደመር በናዚ ሰርዓት እንደነበሩት ጀርመናውያን የበላይነት ስሜትን በመቆስቆስ ከሌሎች ጋር በእኩልነት መኖርን አደጋ ውስጥ ይከታል፡፡
2. የኢትየጵያ ህዝብ በተለይ አማራው ጠላትህ ነው የሚለውን ስብከት ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዳይሸጋገር መግታት:- ብዙ በአዲስ አበባ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ከሌላ ብሔር ተወላጆች በእጅጉ በሚሻል መልኩ ልጆች የወላጆቻቸውን ቋንቋ በቤት ውስጥ እንዲማሩ ያደርጋሉ፡፡ ይሄ የሚበረታታ ነው፡፡ ቋንቋ እና ሌሎች መገለጫዎችን ልጆች እንዲማሩ በትጋት መስራት ያስፈልጋል ጠላትነትን ግን በአዲስ ትውልድ አእምሮ ውስጥ አንዝራ፡፡
3. የህወሓት የተጋድሎ ታሪክ ድምጸት ማሰተካከል:- ከደርግ ጋር በተካሄደው ትግል በርካታ የትግራይ ተወላጆች መስዋዕት መሆናቸው ሀቅ ነው፡፡ ይህ ዋጋ ተከፍሎ ስልጣን ላይ ከወጡ በኋላ ደግሞ በብዙዎች ዘንድ እነዚህ ሰዎች ያን ሁሉ ዋጋ የከፈሉት ለምንድን ነበር የሚለው እንዲጠይቁ አድርጓቸዋል፡፡ ይህንን ተረክ አጉልቶ መናገር አሁን በስርዓቱ እየደማ ባለው ዜጋ ቁስል ላይ እንጨት እንደመስደድ ይቆጠራል፡፡ የትጥቅ ትግሉ መሪዎችንም ተጨቋኙ ህዝብ የሚመለከተው በተመሳሳይ መልኩ ነው፡፡ የእነርሱን ምስል ማግነን የጭቆናው ስርዓት ይቀጥል እንደማለት ይቆጠራል፡፡ በእርግጥ ቡድኑ እና የቡድኑ አውራ የነበሩ ግለሰቦች ለሀገር ያበረከቱት አስተዋጽኦ ካለ ታሪክ አይዘነጋቸውም፡፡ ነገር ግን እሬሳን ከመቃብር እያወጡ በእርሱ ተከልለው ዙፋን ላይ መቀመጥ የማያዋጣ የፖለቲካ ታክቲክ ነው፡፡
4. ልማቱን በዝርዝር መፈተሸ፡- ባለፉት ሁለት አስርት አመታት በርካታ የልማት ስራዎች ተከናውነዋል፡፡ ይህ ግን ግርድፍ መረጃ ስለሆነ በዝርዘር መታየት አለበት፡፡ እንደ አስረጅ ሲቀርብ እንደችሮታ መታየት የለበትም ምክንቱም መንግስት ያን ማደረግ ግዴታው ነውና፡፡ የተሰሩ የልማት ሥራዎች በደንብ የተጠኑ ነበሩ? ባለሙያዎች ስለእነዚህ የተሰሩ ፐሮጀክቶች ምን ይላሉ? ህዝቡስ በርግጥ በቂ ነገር አግኝቷል? የልማት ክፍፍሉ ፍትሓዊ ነበር? የህዝብ ሀብት በልማት ሰበብ አልተዘረፈም? ጥራቱስ ምን ያህል አስተማማኝ ነው? ምን ያህል ብር ተበድረን? ለመጪው ትውልድ ምን ያህል ዕዳ አሸጋግረን? የሀገሪቱን የተፈጥሮ ሀብት እና ዕድል በአግባቡ ተጠቀምን? በአለም አቀፍ ደረጃስ ቦታችን የት ነው? የመንግስት ሰነዶች እና ቁጥሮች ምን ያህል ተዓማኒ ናቸው? አለም አቀፍ ተቋማት እና ልዕለ-ኃያል መንግስታት በምን ፍልስፍና ከአምባገነን መንግስት ጋር ያሰራሉ? ስለልማት ስናወራ እነዚህን እና ሌሎች ተገቢ ጥያቀዎች ለመመለስ መሞከራችንን አንርሳ፡፡
5. የትግራይ ተወላጆች ያገኙትን ኢ-ፍትሓዊ ጥቅሞች ማመን፡- በዚህ ስርዓት የትግራይ ተወላጆች ጨርሶ የተለየ ጥቅም አላገኙም ብሎ መካድ በሌሎች ጉዳዮች ላይ ያለንን ታማኝነት ጥያቄ ውስጥ ያስገባዋል፡፡ የትግራይ ተወላጆች በግልጽ የሚታይ አይን ያወጣ ዘረፋ እያካሄዱ ነው፡፡ ከመካድ ይልቅ የሚሻለው የእነዚህ መረጃዎች ምንጭ መሆን ነው፡፡ የትኞቹ የትግራይ ተወላጆች እንዴት በመንግስት ድጋፍ እንደበለጸጉ፣ የህዝብ ሀብት እንደዘረፉ፣ የትኞቹ ባለስልጣናት ምን ያህል የሀብት ክምችት እንዳላቸው እና ከሀገር እንዳሸሹ፣ የትኞቹ የልማት ስራዎች አለአግባብበ ትግራይ ክልል እንደተከናወኑ ማጋለጥ ሌላው ኢትዮጵያዊ በላባቸው ደክመው ሀብት ያደራጁ የትግራይ ተወላጆችን ከሌቦቹ ጋር እንዳይፈርጅ ይረዳዋል፡፡ የትግራይ ህዝብ የትኛው ባለስልጣን ምን እንደዘረፈ እና ማን ዘመዶቹን የሀገር ሀብት ሰርቆ እንዳናጠጠ ያውቃል፡፡ ይህንን በተጨባጭ መረጃ በማራጀት እና ይፋ በማድረግ በደፈናው ሙሉ ተጋሩ ዘርፎ እንደከበረ የሚነገረውን በማስተካከል ወደ እውነታው ማምጣት ያስፈልጋል፡፡
6. የትግራይ ህዝብ በዚህ ስርዓት የደረሰበትን በደል ማጋለጥ፡- በትግራይ ያለው ፖለቲካዊ አፈና ከሌላው የኢትዮጵያ ክልል ቢበረታ እንጂ አያንስም፡፡ ነገር ግን ይህ ለሌላው ኢትዮጵያዊ አስረጅ በሆነ መልኩ ሊገለፅ ይገባዋል፡፡ እርግጥ ነው ጥቂት የአረና ፓርቲ ወጣቶች የተወሰኑ ሙከራዎች እያደረጉ መሆኑ አይዘነጋም፡፡ ነገር ግን በቂ ነው ብዬ አላምንም፡፡ ሶሻል ሚዲያ የዜጎችን ችግር እያንዳንዱ ዜጋ ወደአደባባይ ማውጣት እንዲችል አድርጓል፡፡ ስለዚህ የስርዓቱን አፈናዎች ለማውጣት በሌሎች የሀገሪቱ ክፍል እንዳለው መነሳሳት በትግራይም ሊኖር ይገባል፡፡
7. በትግራይ ያለውን ድህነት በመረጃ ማሳወቅ፡- ምን ያህል የትግራይ ተወላጆች የምግብ እህል ተረጂዎች ናቸው? ምን ያህሉ የትግራይ ገበሬ አርሶ ልጆቹን ማብላት ይችላል? ስንት ወንድም እህቶቻችን ከትግራይ ተሰደዱ? ከሦስት ዓመት በፊት ሳውዲ አረቢያ ካባረረቻቸው ኢትዮጵያውያን መካከል ምን ያህሉ ከትግራይ ናቸው? በትግራይ ከተሞች ጎዳና ተዳዳሪነት እና ልመና እየቀነሰ ነው ወይስ እየጨመረ? ወጣቶች ተምረው በቀላሉ ስራ ያገኛሉ ወይስ እንደ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ወገናቸው ስራአጥ ይሆናሉ? ወይስ ለሆዳቸው ሲሉ በስርዓቱ መዋቅሮች ውስጥ በታማኝ ካድሬነት ያገለግላሉ? እነዚህ መረጃዎች ተዓማኒ ሊባል በሚችል መልኩ ከተደራጁ ትግራይ ተጠቅሟል ወይም አልተጠቀመም የሚል ክርክር ውስጥ ሳንገባ በሀገራችን ፍትሓዊ የሀብት ክፍፍል እንዲኖር የበኩላችንን ለማደረግ ያግዘናል፡፡
8. የሀይማኖት አባቶች ከብሔራቸው ይልቅ ለሃይማኖታዊ መመሪያቸው እንዲታመኑ ማድረግ፡- ትግራይ የእስልምናም የክርስትናም የሀይማኖት አባቶች መፍለቂያ ነች፡፡ በተለይ የዘር ሐረጋቸው ከትግራይ የሚመዘዝ ብዙ ካህናት እና መነኮሳት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡ ነገር ግን ከእነዚህ የሀይማኖት አባቶች መካከል ጥቂት የማይባሉት ከአምላካቸው ይልቅ ለመንግስት ባለስልጣናት ሲያጎበድዱ የሚስተዋሉ ናቸው፡፡ ለእነዚህ አባቶች ከቄሳር ይልቅ ለጌታ እንዲገዙ፣ ድሃ ሲበደል ፍርድ ሲጓደል የሚያዝኑ፣ የሚጸልዩ እና አጥፊውን የሚገስጹ እንዲሆኑ መንገር ይገባል፡፡ በተለይ እርስ በርስ የሚያጠፋፋ፣ ህዝብን በህዝብ ላይ የሚያነሳሳ ነገር ከመከሰቱ በፊት ግንባር ቀደም በመሆን ይህንን አደጋ መመከት የእነርሱ ድርሻ መሆኑን እናሳውቃቸው፡፡ የማይገባውን ለመውሰድ የሚሮጠውን፣ የንጸኀንን ደም ለማፍሰስ የሚቻኮለውን ሁሉ ከተግባሩ እንዲታቀብ እንዲያስጠነቅቁ፣ ህዝቡን ደግሞ የሌላ ሰውን ነጻነት ማክበር ሀይማኖታዊ ግዴታው እንደሆነ እንዲያስተምሩ መንገር ያስፈልጋል፡፡
9. ማኀበረሰባዊ ትስስርን በመጠቀም ግንዛቤ መፍጠር፡- በመኖሪያ ቤት ከቤተሰብ ጋር፣ በትምህርት ቤት ከጓደኞቻችን፣ በመስሪያ ቤት ከባልደረቦቻችን ጋር በመነጋገር እየመጣ ያለውን አደጋ ማስገንዘብ ይገባናል፡፡ በኢትዮጵያ የዘር ግጭት ሊነሳ የሚችልበት ዕድል ዜሮ እንዳልሆነ፣ በኦሮሚያ፣ በአማራ እና በኮንሶ የተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ መንስኤዎች እና በትግራይ ህዝብ ስም እየተፈጸመ ያለውን ወንጀል የውይይት ርዕስ ሊሆን ይገባዋል፡፡ በሠራዊቱ፣ በደህንነት መዋቅሩ እና በመንግስት ስልጣን ላይ ያሉ ዘመዶችን እባካችኹ የዚህ ዕኩይ ተግባር ተሳታፊ አትሁኑ ማለት ይገባል፡፡ የበታች ካድሬ ወገኖቻችን የገዛ ወጋናቸውን በሚጎዳ ተግባር እየተሳተፉ እንደሆነ ማስረዳት ጠቀሜታው የጎላ ነው፡፡
10. የትግራይ ተቃውሞን(#TigrayProtests) ማደራጀት፡- ከላይ ባየናቸው ዝርዝር ጉዳዮች ላይ የሚኖረን ምላሽ ትግራይ ስለራሱ ሲል ማመጽ ወይም አለማመጽ እንዳለበት ይነግረናል፡፡ በደሉ በራሱ ላይ ባይደርስበት እንኳን ስለተጨቆኑ ሌሎች ኢትዮጵያውያን ወገኖቹ ሲል ማመጽ ይገባዋል፡፡ እርግጥ ነው ከላይ እንዳነሳነው መታፈኑ ከሌላው ቢብስ እንጂ ስለማያንስ መሬት ላይ እንቅስቃሴዎች ማድረግ ይከብድ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ቢያንስ በሶሻል ሚዲያ ያንን አመለካከት ማራመድ አያቅትም፡፡
አንዳንዶች አጠቃላይ ችግሮችን ለማስቀረት በኢትዮጵያ ታርጋ ብቻ ነው መቃወም ያለብን የሚል ክርክር ያነሳሉ፡፡ ይህንን ሲሉ ኢትዮጵያዊነት በስርዓቱ ተረጋግጦ እንደወደቀ አልተረዱም፡፡ ኢትዮጵያዊነት በመታገያ ስልትነት የማገልገል እድሉ አናሳ መሆኑን የኢትዮጵያን የፖለቲካ በቅርብ የሚከታተሉ ሁሉ ይገነዘባሉ፡፡ ከዚያ ይልቅ ኢትዮጵያዊነት መፍትሔ ነው፤ ሁላችንም የምናሸንፍበት፣ ከጥፋት የምንድንበት መፍትሔ፡፡ ብቸኛው መፍትሔ ግን አይደለም ሌሎች ሁላችንም የምንሸነፍባቸው ‘የመፍትሔ ሐሳቦች’ አይጠፉም፡፡ አሁን ግን አንድ የትግራይ ተወላጅ ተነስቶ “ኢትዮጵያ ኢትየጵያ፣ አንድነት አንድነት” ቢል ሌላው የሚረዳው ሊያታልለው እየሞከረ እንደሆነ ነው፡፡ ስለዚህ ተጋሩ ያለው አማራጭ ህዝቡ ከስርዓቱ እንደሚለይ ማሳየት ነው፡፡ ይህ ሁለት ዕድሎችን ይዞ ይመጣል፡፡ አንደኛው ተጨማሪ የህዝብ ሀይል ወደ ትግል መድረኩ አምጥቶ ስርዓቱን አዳክሞ የሚውደቅበት ጊዜ ያፋጥናል፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ስርዓቱን ባያዳክም እንኳን በህዝቦች መካከል የጠላትነት መንፈስን አጥፍቶ የትግራይ ህዝብን ወደ ‘የኢትዮጵያ ጭቁን ህዝቦች ህብረት’ ያስገባል፡፡
ዝርዝሩ በዚህ ያበቃል ብዬ አላስብም፡፡ እስኪ ሌሎቻችንም ተጨማሪ መደረግ የሚችሉ ነገሮች ካሉ ጠቁሙን፡፡ ምናልባት አንዳንድ ሰው ከዚህ የተወሰኑ ሐሳቦች ወስዶ የስርዓቱ እድሜ ለማራዘም መጠቀሙ አይቀርም፡፡ ለእንደዚህ አይነቱ ሰው አጭር መልዕክት አለኝ፡፡ በእሳት አትጫወት! አበቃኹኝ፡፡

የብአዴን የበታችነት ያክትም | ከያሬድ ጥበቡ

 

ከባህርዳር የሚወጡት መረጃዎች ሁሉ የሚጠቁሙት የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት የሆነው አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከሥልጣኑ እንደሚነሳ ነው ። ይህ በጣም የሚያሳዝን ፍፃሜና የክልሉን ህዝብ ፍላጎት የሚፃረር ተግባር ነው ። አቶ ገዱ የሚገለለው ምን ጥፋት ስለተገኘበት ነው? በሱ ምትክስ የሚመጣው ሰው ምን አይነት ሰው ይሆን? ይህስ ሹም ሽር ለህዛባዊ እምቢተኝነቱ የሚደነቅረው ችግርም ሆነ፣ የሚያደርገው አስተዋፅኦ ምን ሊሆን ይችላል?
Yared

ባለፉት 25 የወያኔ/ኢህአዴግ አገዛዝ አመታት፣ ከዘጠኙ የክልል ፕሬዚደንቶች፣ እንደ አቶ ገዱ የህዝብ ይሁንታ ያገኘ ገዢ ነበር ማለት የሚቻል አይመስለኝም። ምናልባት ተቀራራቢ ሬከርድ የነበረው የትግራዩ ገብሩ አስራት ነበር ። አቶ ገዱም መልካም ስሙን አግኝቶ የነበረው፣ የአማራ ክልል ህዝብ የተለየ የልማት ተጠቃሚነት ስላገኘ ሳይሆን፣ የወያኔን ቀጥተኛ እዝ ለመቋቋም ፈቃደኛ መስሎ የሚታይ መሪ ሆኖ ስለተገኘ ነበር ። በተለይ የወያኔ ኮማንዶዎች በወልቃይት የአማራ ማንነት ኮሚቴ አባላት ላይ ያልታሰበ ጥቃት በሰነዘሩበት ወቅት፣ ገዱ በእዙ ስር የነበረውን የክልሉን ልዩ ሀይል ለወያኔ ተባባሪ እንዳይሆኑ ከማድረጉም በላይ የጎንደር ህዝብ መሬት አንቀጥቅጥ ትእይንተ ህዝብ ባደረገበት ወቅት፣ ልዩ ሀይሉ ሰላማዊ ጥበቃ ከማድረግ ውጪ፣ ሰላማዊ ሰልፈኛውን እንዳይተነኩስ በማድረግ ጨዋ አመራርን ያሳየ ሰው ነበር ። እነዚህ መልካም ተግባሮቹና፣ የህዝብ ይሁንታ ያገኘ መሆኑ ግን ገዢውን ፓርቲ አላስደሰተውም ።

የሚፈለገው በሁሉም ክልሎች ከህዝብ የተነጠለና በነስዩምና አባይ ፀሀዬ የግል ፈቃድ ላይ የታጠረ ሎሌና ታዛዥ አመራር ብቻ በመሆኑ፣ አቶ ገዱ የሚገለልበት ወቅት ላይ ደርሰናል ። ይህ ግን መሆን አልነበረበትም ። የዞንና ወረዳ አመራሮችና ካድሬዎች “መሪያችንን በወያኔ ፈቃድ አናወርድም” የሚል ፅናት ቢኖራቸው ኖሮ፣ ወያኔ ወይ ተገዶ የብአዴንን አባላት ፍላጎት መቀበል ወይም የሲቪል አስተዳደሩን በትኖ ኦሮሚያ ክልል ላይ እንዳደረገው በወታደራዊ አገዛዝ መተካት ይገደድ ነበር ። ሆኖም ወያኔ የፈለገውን ማድረግ የሚችልበት አደጋ ከፊታችን ተደቅኗል ።

እንደ እውነቱ ከሆነ፣ ከስልጣን መውረድ የነበረበት በጎንደር ከተማ ላይ ያልታሰበ ጥቃት ሰንዝሮ ለብዙ ዜጎች መቁሰልና ሞት ምክንያት የሆነው የትግራይ ክልሉ ፕሬዚዳንት አባይ ወልዱና ከማእከላዊ መንግስቱ የሚተባበሩት ዘረኞች ነበሩ ። አባይ እግሩን አንፈራጦ ተቀምጦ ወያኔ ጥልቅ ተሃድሶ አደረግኩ ብሎ ስብሰባውን ባጠናቀቀበት ሳምንት ብአዴን የህዝብ ይሁንታ ያገኘ መሪውን ለማሰናበት ቢገደድ፣ ሊያፍርበት የሚገባው ውሳኔ ነው ። አሁንም እድል ስላለ ከዚህ አይነት አሳፋሪ ውሳኔ ራሱን ማቀብ ይገባዋል ብዬ ማሳሰብ እወዳለሁ ።

እያንዳንዱ የዞንና የወረዳ ካድሬና አመራር አባል “አባይ በስልጣኑ ተቀምጦ ገዱን ብናወርድ የትግራይ ጠባብ ብሄርተኞችን እብሪትና መሳለቅ እንዴት ልንመክት ነው” ብሎ ሊጨነቅና ሊጠበብ ይገባው ይመስለኛል ። የምፅፈውን እንደምታነቡና፣ አጭር ፅሁፍ ለማንበብ የሚያሰችል ያህል የኔትወርክ ግንኙነት እንዳለ ስለማውቅ፣ “መካሪ አጥተን” ተሳሳትን እንዳትሉም በማሰብ ነው ። እባካችሁ ከዚህ አይነት አሳፋሪ ውሳኔ ታቀቡ ። የህዝባችሁንም ልብ በሃፍረትና በሃዘን አትስበሩ ። ጦርነት የቀሰቀሰውና፣ የድንበር ግፊት የሚያደርገው፣ ወልቃይቶችን የአማርኛ ዘፈን አደመጣችሁ ብሎ የሚያስደበድበው፣ አንዳችም ትንኮሳ ሳይደረግባቸው “በትግሬነታችን የተነሳ የዘር ማጥፋት ታቃጣብን” በሚል የሀሰት ክስ በጎንደርና በጎጃም የሚኖሩ ትግሬዎች ከቤት ንብረታቸው እንዲሰደዱ በማበረታታት አሳፋሪ ተግባር የፈፀመው አባይ ወልዱና ተባባሪዎቹ የሆኑት ስዩም መስፍንና አባይ ፀሀዬ በስልጣን ተቀምጠው እንዴት በሰላማዊ ህዝብ ላይ አንተኩስም ያለ መሪያችሁን አሳልፋችሁ ለጠባብ ብሄርተኞች ትሰጣላችሁ ?
ቢያንስ በህገ መንግስት የተሰጣችሁንስ የክልል መሪውን ራሱ የክልሉ ህዝብ የመምረጥ መብቱንስ እንዴት ተላልፋችሁ፣ የክልሉ ሸንጎ፣ ፕሬዚዳንት አድርጎ የመረጠውን ሰው፣ በካድሬ ስብሰባ ትሽራላችሁ? ያወጣችሁትን ህግ ራሳችሁ እያፈረሳችሁ፣ ነገ ሲከፋችሁ ለናነተስ የሚደርስላችሁ የህግ ከለላ ከየት ሊገኝ ነው? እባካችሁ ተመከሩ ። የወያኔን እዝ የመፈፀም ምንም አስገዳጅ ሁኔታ የለባችሁም ። ይህ ምንጠራ በገዱ ይቆማል ብላችሁ ካሰባችሁም ሞኞች ናችሁ ። እንዲያውም ከገዱ ይልቅ ዋነኛዎቹ ኢላማዎች እናንተ ናችሁ ። ገዱስ ከፕሬዚደንትነት ቢነሳም ወይ አምባሳደር ወይም ምክትል ሚኒስትር ሹመት ለጊዜው ለመደለያ ይሰጠው ይሆናል ። ማወቅ ያለባችሁ ፣ ወያኔ “የዞንና ወረዳ ካድሬዎችና አመራሮች ናቸው ህዝቡን አይዞህ እያሉ ትምክህተኛ ያደረጉት” በሚል ጥርሱን የነከሰው በናንተ ላይ ነው ። በመቶዎች የምትመነጠሩትና መንገድ ዳር የምትወረወሩት እናንተው ናችሁ ። በዚያን ወቅት፣ አሁን ልትሰሩት በምትከጅሉት ገዱን የማባረር ውሳኔ የተነሳ፣ ዛሬ ፍቅር የሚያሳያችሁ ህዝብ ዓይናችሁን ላፈር ይላችኋል ። በረከት ስምኦንና ከበደ ጫኔ እያመሷችሁ እንደሆን እሰማለሁ ። ካስፈለገ “ዘወር በሉ ከፊታችን” ልትሏቸው ይገባል ። ደግሜ ላስጠንቅቃችሁ ፣ ዛሬ በገዱ ላይ እንድትወስኑ የምትጠየቁት ውሳኔ እውነተኛው ሰለባዎች ገዱ ሳይሆን እናንተ ናችሁ ። ጭክን አድርገው ነው የሚቀጠቅጧችሁ ። ለሌላው መማሪያ እንድትሆኑ አድርገው ነው የሚያደኸየሁዋችሁ ። ወሳኙን ትግል ዛሬ አድርጉ ።

የሰማሁት መረጃ እርግጠኛ ከሆነ፣ ወያኔ በገዱ ምትክ እንድትመርጡለት የሚፈልገው ብናልፍ አንዱአለምን ነው ። ይህ ሰው ለስራው ይመጥናልን? ባለፉት አመታት አፍቃሪ ወያኔ ተልእኮዎችን በማስፈፀም ስሙ የተበከለ ሰው አይደለምን? ከህዝቡ ፍላጎትና ስጋት ጋር የሚመጥን የተሻለ ሰው ከመሃላችሁ አይገኝምን? እንደኔ ግን ስለ ለውጥ ባታሰቡና፣ የወያኔ የጎማ ማህተም ባትሆኑና የክልላችሁን ህዝብ እንባ ብታደርቁ ይሻላችሁ ይመስለኛል ። በእኔ እምነት የተሻለው መንገድ በገዱ ዙሪያ ቆማችሁ፣ ትከሻ ለትከሻ ተደጋግፋችሁ “እምቢ ለወያኔ እዝ” ማለት ነው ። ለማንም ብላችሁ ሳይሆን ለራሳችሁ ስትሉ ። ልጆቻችሁን መንገድ ዳር ላለመወርወር ስትሉ ። ስራችሁን ላለማጣት ስትሉ ። ስደትና እስር እንዳያገኛችሁ ስትሉ ። ከሁሉም በላይ ግን ለሰብአዊ ክብራችሁ ስትሉ ።

በገዱ ላይ የምታደርጉት የወንጀል ትብብር፣ እውነተኛው ገፈት ቀማሾች ራሳችሁ መሆናችሁን ለሰከንድ እንኳን አትጠራጠሩ ። የናነተን ፈቃድ ሳይዝ ወያኔ ብቻውን ይህን ማድረግ አይቻለውም ። “የክልሉ ምክርቤት የመረጠውን መሪ እኛ ካድሬዎች ተሰብስበን ማውረድ አንችልም” ማለት መብታችሁ ነው ። ያንን መብታችሁን ተጠቀሙበት ። የክልሉ ምክርቤት ሲሰበሰብ ደግሞ፣ ከክልሉ ህዝብ ፍላጎትና የአስተሳሰብ እድገት ጋር የሚመጥን ውሳኔ ለማድረግ ታገሉ ። ገዱን አለማውረድ ብቻ ሳይሆን፣ ለወያኔ የተላላኪ ሚና ከመጫወት የማይመለሱትን ከሰልፋችሁ የማጥራት፣ በምትካቸው ህዝቡ ይወክሉኛል የሚላቸውን አዳዲስ የክልል ሸንጎ አባላትን በየአካባቢው እንዲመርጥ እስከማድረግ በትግሉ ግፉበት ። በመታገል የምታጡት ነገር የለም፣ ከወያኔ ጋር ከተሳሰራችሁበት የውርደት ካቴና ውጪ።
አዎን የውርደት ካቴና ይሰበር ። በክልላችሁ ይህን በማከናወን፣ ለኢትዮጵያም የተደላደለና የተረጋጋ የሰላማዊ ፖለቲካ ሽግግር እድል ታስጨብጣላችሁ ። ይህን ማድረግ አቅቷችሁ የወያኔን ፍላጎት ብታሰፈፅሙ ግን፣ የውርደት ሰንሰለታችሁ መጥበቅ ብቻ ሳይሆን፣ የመንገድ ተዳዳሪ ትደረጋላችሁ ። ትራባላችሁ፣ ትጠማላችሁ ። ያኔ የሚያዝንላችሁ ከንፈር መጣጭ ስንኳ አታገኙም ። እባካችሁ ለራሳችሁ ስትሉ ተመከሩ ። በገዱ ዙሪያ ቆማችሁ የወያኔን ጠባብ ብሄርተኛ እብሪትና የትንኮሳ ፓለቲካ አምክኑ ። ኢትዮጵያችንንም ከትርምስ ታደጓት ። ዛሬ በማወላወልና በፍርሃት ከወያኔ ጋር ብትቆሙ ግን እንደ ገና ዳቦ፣ ወያኔ ከላይ፣ ህዝባዊ እምቢተኝነቱም ከስር ይለበልቧችኋል ። በማንኛውም ሰው ውስጥ ያለው የፍትህ ብርሃን የናንተንም ውሳኔ እንዲመራው ጥልቅ ምኞቴ ነው ። ፈጣሪያችሁ ቀናውን መንገድ ያሳያችሁ።

ለብአዴን ካድሬዎችና አባላት ይህን መልእክት ማድረስ የምትችሉ ሁሉ ተባበሩ!

ጉዞአችን ወዴት ነው? | ሉሉ ከበደ

 

ፎቶ መግለጫ: በትንቢት ተናጋሪው በሼህ ሁሴን ጅብሪል ምድር በወሎ ወይንም ላኮመልዛ በደሴ ከተማ የመስቀል ደመራ በዓል የአባቶቻችን ሰንደቅ አላማ ከፍ ብሎ ተውለብልቦ በፋሽስት ወያኔ በግፍ ለወደቁት አማሮች ጸሎት ተደርጎ በዚህ መልኩ ተከብሮ ውሏል። (ፎቶ ከአቻምየለህ ታምሩ)

ከሉሉ ከበደ

ዛሬ በመላ ኢትዮጵያ የተቀጣጠለው አብዮታዊ አመጽ ባለቤት እራሱ ህዝቡ ነው። እርግጥ ያኛው ወይም ይህኛው ወገን የቀሰቀሰው ነው የምንለው ሳይሆን እራሱ የትግሬው ነጻ አውጭ ቡድን ፤ ቧጦ፤ ነክሶ፤ ወግቶ አድምቶ አቁስሎ ፤ህዝቡን የመጨረሻው ሞት አፋፍ ላይ ቢወስደው አልሞት ባይ ተጋዳይ ሆኖ ሰዉ ተነሳ።

 

ከልክ ያለፈ ስግብግብነት፤ ቅጥ ያጣ ሌብነት፤ ስርቆት፤የገንዘብ ስርቆት፤ የንብረት ስርቆት፤ የመሬት ስርቆት፤ የታሪክ ስርቆት፤ የተራራ ስርቆት፤ የሀገር ስርቆት፤ የማንነት ስርቆት፤ ህወሀት ህዝቡን አንገፍግፎት በግድ ከተኛበት አስነሳው።ጋዜጠኛም ፖለቲከኛም ቀስቅሶት ሀያአምስት አመት ያልተነሳውን ህዝብ።

የህመምተኞች ስብስብ የሆነው የትግሬው ነጻ አውጭ ቡድን፤ለህዝቡ ቁጣ ማስታገሻ ብሎ ያቀረበው መዳኒት አንድ የሚያውቀውን ነገር ተኩሶ መግደል ብቻ ሆነና የህጻናትን ደም ማፍሰሱን ተያያዘው። ነገር ግን ወደኋላ የሚል ህዝብ ጠፋ። መልካም…. ህዝቡ ለለውጥ ዝግጁ ነው። ዋጋ ሊከፈል ቆርጧል።

ይህን አመጽ አሰባስቦ፤ አስተባብሮ፤አንድ መቋጫ ያለው ግብ ላይ ማድረስ እንደሚገባ የሚያጠያይቅ ነገር የለውም። ይህ መኖር ያለበት የጋራ ግብ እስካሁን አልታየም። አልተሰማም።

ሁለቱ አንጋፋ ክፍለ ህዝቦች አማራውና ኦሮሞው ናቸው የአመጹ ፊት አውራሪዎች። የተቀሩትም ሰማንያው ክፍለ ህዝቦች ሳይውል ሳያድር አመጹን እንደሚቀላቀሉ ምንም አያጠራጥርም። ምክንያቱም ወያኔ በኢትዮጵያ ውስጥ ያላቆሰለው፤ ያላደማው እና ደሙን ያልጠጣው የህብረተሰብ ክፍል የለምና!

እና ?…… ይህ ስራት ከተወገደ በኋላ ስለምናቋቁመው የመንግስት አይነት ከየትኛውም ወገን የሚሰማ ነገር የለም። በሁለቱ አንጋፋ ክፍለ ህዝቦች ውስጥ ትግሉን እንመራለን ብለው ወደፊት የመጡ፤ ከአመጹ ውስጥ የወጡ፤ ወይም ደግሞ ቀደም ብለውም ትግል የጀመሩ አንድ ቦታ ላይ ተገናኝተው የጋራ ግባችን ይህ ነው ማለት ይጠበቅባቸዋል። ባስቸኳይ።

ጉዞው ወደ አንድ ግብ ካልሆነ ወያኔን ጥሎ እርስ በርስ መያያዝ እንዳይመጣ መጠንቀቅ ያስፈልጋል። የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች በለስ እንዳይቀናቸው። ልብ ይሏል የቅርብም የሩቅም ወዳጅ የለንም ጠላት እንጂ።

ይህ አመጽ የኢትዮጵያ ህዝብ አብሮነትን አንድነትን እንደሚፈልግ ባንደበቱ ያረጋገጠበት አጋጣሚም ነው። የኦሮሞ ደም ደሜ ነው ያለው አማራ፤ የአማራ ደም ደሜ ነው ያለው ኦሮሞ፤ ባጠቃላይ ሰማንያአንዱም ጎሳ አብሮ መኖር ያልቻሉበት ዘመን በታሪክ የለም።

ባለፉት ሀያ አምስት አመታት ውስጥ የኢትዮጵያ ህዝብ በጎሳ ፖለቲካ ከሚገባው በላይ ቅጣት አግኝቷል። የእድሜ ልክ ትምህርትም አግኝቶበታል። የዘር ፖለቲካ ልክፍተኞች የሆናችሁ ኢትዮጵያውያን በቶሎ እራሳችሁን አስታሙና ጤነኛ ሁኑ። አለበለዚያ ህዝቡ ወያኔን ከቀበረ በኋላ ወደ ዘር ፖለቲካ እንመልስሀለን ብትሉት ወዮ ለናንተ ። ነጻነት ምናምን መገንጠል የምትሉ ቡድኖችና ግለሰቦች፤ የስልጣን ህልመኞች፤ ሌላ የመተላለቂያ ምእራፍ ልትከፍቱ ማንም አይፈቅድላችሁም።ራሳችሁን እንደ ህዝብ የምትቆጥሩ ተስፈኞች ወያኔ ካደረሰውና ከሚደርስበት አደጋ እንድትማሩ እመክራችኋለሁ።

ስለዚህ፡

የዜግች መብት ሙሉ በሙሉ የሚከበርባት፤

የህግ የበላይነት የሚነግስባት፤

ፍጹም የሆነ እኩልነት የሚሰፍንባት፤

ሀሳብን የመግለጽ ነጻነት እውን የሚሆንባት፤

ዜጎች በሚገባቸው ቋንቋ የሚዳኙባት፤

ህጻናት አፍ በፈቱበት ቁንቋ የሚማሩባት፤

አማርኛና ኦሮምኛ የሀገሪቱ የስራ ቁንቋ የሚሆንባትና መላ የሀገሪቱ ዜጎች የሚማሩባት

በዘር ላይ የተመሰረተ የፖለቲካ ድርጅት በህግ የሚታገድባት፤

የዘር ክልል የማይደገምባት፤

ፓርቲዎች በነጻነት ህዝብ ውስጥ ተንቀሳቅሰው የሚፎካከሩባት

ኢትዮጵያን መፍጠር የዚህ ህዝባዊ አመጽ ግብ እንዲሆን እንደ አንድ ዜጋ ለማመልከት እወዳለሁ።

ኢትዮያ እንዲህ ነች፤ እንዲያ ነች እያላችሁ ሀገራችሁን የምትጠሉ ሰዎች፤ ኢትዮጵያ ማለት ግኡዝ ምድር ነች። ምድር አትጠላም። የሚጠላው፤ ሀገርንም የሚያስጠላው ጨቋኝና አንባገነን ስራት ነው። ሁላችንም አንባገነን ስራት ያስመረረን ህዝቦች ተሰባስበን፤ ተነጋግረን፤ ተመካክረን፤ ለራሳችን የሚስማማንን የሚመቸንን ስራት ከፈጠርን ለምንድነው ሀገራችንን የምንጠላው? ለምንድነው ተለያይተን መንግስት ስለማቆም የምናስበው? የምንዶልተው? ይህን ጥያቄ የሚመልስልኝ ሰው ባገኝ ደስ ይለኛል።

አመሰግናለሁ።

በብር ሸለቆ ወታደራዊ ካምፕ የአማራ እስረኞች በከባድና በተከለከሉ አፍዝ አደንግዝ መርፌ መድኃኒቶች እንደሚሰቃዩ መረጃዎች አመለከቱ

ክሙሉቀን ተስፋው

14522996_1317609571596986_8800174711447287377_nበብር ሸለቆ ወታደራዊ ካምፕ የሚገኙ ወገኖቻችን በከባድና የተከለከሉ አፍዝ አደንግዝ መርፌ መድኃኒቶች እንደሚሰቃዩ መረጃዎች አመለከቱ። ብር ሸለቆ የታሰሩ የዐማራ ወጣቶች በግዴታ በመርፌ እንዲወስዱ የተደረገውን መድኃኒት ምንነት የሚያስረዳ ምስል ትናንት ወጥቷል። በዚሁ መሠረት የዐማራ ሀኪሞች ማኅበር መድኃኒቱን በተመለከተ የሚከተለውን ማብራሪያ ሰጥቷል።

ሁሉም የሰውነት ጡንቻወች እንዲዝሉ ወይም አላግባብ እንዲወጠሩና የፈለጉን አሰቃቂ ድርጊት ለመከወን (አስንፎ ለመምታት፣ ለማንጠልጠል፣ ለመግደል..) የሚያስችሉ አፍዝ አደንግዝ(Sedative Hypnotic) የሆኑትን የመርፊ መድኃኒቶች በግዳጅ እየተውጉ ነው። ዲያዘፓም እና ዲልትያዘም (Diazepam Diltiazem) ጥቂቶቹ ናቸው። እነዚህ መድኃኒቶች ለሚያስፈልገውና በሃኪም ትዛዝ ብቻ የሚሰጡ፡ ከፍተኛ ቁጥጥርና ክትትል የሚያስፈልጋቸው ናቸው። ከመጠን በላይ(Over Dose)ና ለማያስፈልገው ከተወጉ የመናገር ችግር፡ የሰውነት ክፍል መዛል: አለመታዝዝ (Dyskinesias): እረፍት መንሳት(akithsia)፡መደበት(Depression) ጭንቀት እና መተንፈስ ኣለመቻል ያስከትላሉ። በብዛትና በተክታታይ ከሆነ የልብ መድከም፡ የደም ማነስ፡ ሾክ፡የሚጥል(Sezure)፡ ራስን ማሳት(Coma)ና ሞት ያመጣሉ። የሳይኮሎጅ ማስቀየር ‘Psychologic Dislocation’ ና ፍላጎት ማሳጣትም ጉዳቶች ናቸው። ቆዳ ላይ ከፈሰሱ የቆዳ ላይ ቁጣ፡መላላጥ፡ እብጠት፡እንፊክሽን፡የቆዳ ጋንግሪንና ሞት የመጨረሻወቹ ናቸው።
14440933_1079306455516726_783002433903273477_nናዚውና ኢሰብዓዊ ህውሃት ኣካላዊ ስቃይ ንጹሃን ላይ እንደሚያደርስ ለማንም ግልጽ ነው። ኣስደንጋጩ የህክምና ማስቃያ ግን ኣማራው ላይ የመጀመሪያው ሳይሆን ኣይቀርም። የሚያስፈራው የህክምና ሰወች (የናዚ ዶክተሮች) ለዚህ ኦፕሪሽን መሳተፋቸው ነው።ይህ ኢሰባዊነትና አለማቅፋዊ የህክምና ሰነምግባርን የጣሰ ሆኖኣል። ሰውን በግፍ ኣለመጉዳት ’Do Not Harm’ ፡ፍቃደኛ ለሆኑ ብቻ ‘Authonomy’ ፡ የሚጠቅም ሲሆን ብቻ ‘Beneficience ’ ወዘተ የሚሉት ቃለ-ማህላ(Physicians Oath) ተክደው በ’ናዚ ሃኪሞች’ ህዝባችን እየተስቃየ ነው ። የአማራና የኢትዮጵያ ሃኪሞች ይህን ጉዳይ ባስቸኩይ ለ’ Federal Ministry of Health of Ethiopia, FMHACA, UN Human Rights ‘ ማድረስና እልባት ማግኘት ኣለበት።
መረጃውን በጥንቃቄ እየያዝን ተግጅወችን እንርዳ። መልእክቱን ለአለም አናሰራጭ።

– See more at: http://www.satenaw.com/amharic/archives/22111#sthash.YuuDibcF.dpuf

Is VOA acting like kangaroo court to exonerate Woyane offenders?


Is VOA acting like kangaroo court to exonerate Woyane offenders on the expenses of Ethiopian victims?

Woyane will die unceremonious death soon so its sorry Mafia operatives but, unless the political elites’ superficial knowledge dies with it, we Ethiopians will continue to struggle to secure our freedom and liberty.

by Teshome Debalke

False confession, conversion and exoneration of Woyanes to thwart Ethiopian democratic revolution from ending the corrupt ethnic Apartheid rule on make-believe Medias is getting out of hand. In a nation where a Mafia regime is running amok with firearms in the wrong hands to shoot-and-kill our people and gasoline to burn down the country if it doesn’t get its way, the last thing Ethiopians expect from so called Medias is to act as kangaroo courts or a platform to exonerate Mafia offenders on the expenses of the victims instead of being advocates for the truth.VOA Amharic walking a tight rope in Ethiopia

The recent VOA drama playing Kangaroo court presided by reporter Tsion Girma acting as Judge to vindicate Junedin Sado, the Former ‘fake’ (his own word)  Oromyia President of TPLF led Apartheid regime is another debacle of the out of control Media operatives violating their journalistic oath  and mandate.

The staged VOA kangaroo court’s testimony (interview) not only gave the offender a platform to declare his innocence on all crimes against the people of Ethiopia and the nation without his victims presence to confront him but, the charges of promoting a radical Islamic sect his own ‘fake’ regime brought against him – contracting and incriminating himself and his former regime he willingly served for 15 years in both charges.

On the first allegation, he admitted serving ‘fake’ Federal regime playing as Oromo President and in the second, he confess not only receiving fund from the Saudi Embassy cultural attaché but, many of his Muslim compatriots did with the knowledge of the regime – further incriminating the Mafia regime he served for allowing the Saudi government involvement in  expansion of religion sect throughout Ethiopia in direct violation of diplomatic relation and against the law — no interference government let alone a foreign in the religion affair of the nation.

Such explosive allegation from a man that came out of his hiding to spill the beans about the ‘fake’ ethnic Apartheid Federal regime should alarm Ethiopians in general and Muslim followers in particular.  Moreover, VOA’s reporter Tsion Girma and associates’ motive to stage such a drama with a colorful Woyane man coming out of his hiding to tell-tell the extent the ‘fake’ Mafia regime involvement with the Saudi government to finance the expansion of religion should be examined extensively.   Is Tsion Girma VOA and associates implying the Ethiopian Muslims movement for freedom of religion associated with the Saudi regime or is she opening religious front to further polarize Ethiopians to sustain the Mafia regime?

If VOA credential is an indication, there is no question there is something fishy going on that requires every Ethiopian attention. Given VOA reporters on the ground (in Ethiopia) failed to generate a single independent reporting on the ongoing Ethiopian revolution or on the Mafia regime atrocities and corruption in general throughout its reign, there is no surprises in what they do. But, in this particular case, putting up a drama with the long forgotten former Woayne in hiding without his victims that flee from terror of his former regime is not only crime against humanity but, cover up the extent of the Mafia regime crimes against Ethiopians.

Quit honestly, the numbers of Make-believe Media playing as kangaroo courts- platforms with clandestine journalist-operators acting as judges to exonerate offenders of all kinds quadrupled in the recent past and getting out of hand. What they are doing now is the tip of the iceberg to come to undermine the people’s revolution for their democratic rights and justice by trampling on the blood of Ethiopians being spilled by the regime with impunity.

Moreover, by muddying the political water further thus, poisoning the ongoing grassroots revolution; the campaign to sustain the status qua is in full gear. Fanning TPLF made up conflicts and polarizing Ethiopians further to make it look like the sky will fall if the Mafia group masquerading as government bit the dust or if their own twisted agenda not accepted is populating the make-believe Medias in the cyberspace.

It appears, the political elites are not yet done slicing-and-dicing Ethiopians’ rights to be free from dictatorship. Therefore, the long awaited simple solution of sorting out criminals from the innocent in body politics Ethiopian demands is taking an ugly turn again on the make-believe Medias playing kangaroo courts and pseudo journalists acting judges and mediators than the important public service their profession demands.

The same people that were part-and-partial of the problem the Mafia group brought showing up to be part of the solution is unfortunate. But, in their trifling minds, they not only think Ethiopians have no democratic rights to decide our fate or deserve justice for the pain-and-suffering we endured from Mafia group masquerading as government and others but, not capable of sorting out our own problems without recycling the same offenders. Once again, it shows the incompatibility of the elites’ interest with people of Ethiopia.  And, nowhere is it evident than in the make-believe Medias run by clandestine pseudo journalists.  Where is the justice for the people in that?

But again, what we can learn from political elites of our time in general is; the application of their superficial knowledge made them oblivious to what legitimacy means and the mandate that comes with it. Noting exhibits such incompetent and arrogance than VOA reporters/journalists (among them the Former VOA reporter/journalist and the present mouth piece of the Mafia group Mimi Sebhatu) that slice and dice the meaning of legitimacy and the mandate or the responsibility that comes with it.

Speaking of the queen of defamations Mimi Sebhatu’s recent tantrum on the ongoing revolution and on good governance analyzed in her little mind would make any decent person throw up. But, when you think about it; she isn’t the exception but the rule of the elites’ superficial knowledge that drive them to believe; the Ethiopians rights and liberties rotates around it. She happen to have access to trumpet her superficial knowledge because she serve the Mafia group like many to lesser extent that gave her the microphone.

As we witness the make-believe Medias’ clandestine operatives agonize to thwart the ongoing Ethiopian revolution and undermine the patriots of the struggle, we should remember what the humble hero of the struggle Feyisa Lilesa said speaking on behalf of Ethiopians. The moral superiority of the humble young Ethiopian breaking Woyane’s barrier speaks 1000s of words than what all the political elites’ failed to do all these years.

The moral of the story is, just because one have access to magnify superficial knowledge to serve a Mafia regime or any interest group doesn’t earn her-him creditability or the right to own the truth. Woyane will die unceremonious death soon so its sorry Mafia operatives but, unless the political elites’ superficial knowledge dies with it, we Ethiopians will continue to struggle to secure our freedom and liberty. And, the shortest and the easiest way to end the proliferation of superficial knowledge is to end the make-believe Medias’ clandestine operatives from promoting it and defending and supporting real Medias to bury it for good.

After all, Woyane came and remained to cause unimaginable havoc because of the make-believe Medias amplified the political elites’ superficial knowledge not the other way around.  Therefore, the sooner Ethiopians identify the make-believe Medias and their clandestine operators trumpeting superficial knowledge in general and the Mafia group in particular as the root cause of the problem the better Ethiopians will be.

“Alien, hosts and guests” how pseudo-scholars divide Ethiopia

 

 

Can Ethiopia Survive Its Own War on Terror?

by Girma Tefera

The famous African-American minister and activist Dr. Martin Luther King Jr is one of the most successful world leaders of a nonviolent resistance to injustice. During one of his inspiring speeches many decades ago, he once said:

“Darkness cannot drive out darkness: only light can do that. Hate cannot drive out hate: only love can do that.”

In this 21st century, unfortunately, most of our so-called “politicians” and “scholars” from Ethiopia do not seem to comprehend such a simple but principled concept by MLK. Maybe we Ethiopians are better off without these politicians and scholars. Despite these pseudo-scholars instigating hate and division, many Ethiopians have come together- as exemplified by the recent unity & solidarity between “Oromoprotests” and “Amharaprotests.”

But lo and behold, hate always finds a way to lurk back into Ethiopian politics!

This is what we find when we read the latest article titled, “The Special Interest: the affirmation of denial” written by Mr. Tsegaye Ararssa.

Using hateful labels like “aliens,” “hosts,” “settlers” and “guests,” Mr. Tsegaye Ararssa decided to divide our people instead of uniting. It is sad. Those Oromo and Amhara Ethiopian protesters who were shot and massacred by TPLF must be rolling over their graves. It is unfortunate.

Sadly, Our politicians seem to always snatch DEFEAT from the jaws of victory.

Mr. Ararssa should learn from Dr. Martin Luther King Jr that hate will not drive out hate. We can not win against the tyranny in Ethiopia by preaching more hate, bitterness and division.

In his new divisive article disguised as a legal and scholarly piece, Mr. Tsegaye Ararssa presented his wild opinions as indisputable facts. He erratically handed out negative labels of alien and “settlers” to us Amharic speaking Ethiopians. For Mr. Ararssa, we are foreigners who do NoT belong in Addis Ababa. Despite the fact that our ancestors arise from Oromo, Sidama, Welayta or any of 80 other ethnicities, Mr. Tsegaye said we are now “aliens” and “guests” just because we speak Amharic.

Apparently, he is our generous “host.”

According to him, I am supposed to be one of his foreign “guests” so let me introduce myself to you, Mr. Ararssa, the self-proclaimed Oromo owner of Addis Ababa.

I don’t know what village you come from, But I am a proud Ethiopian born and raised in Addis Ababa city. My great-grand parents and ancestors have lived in this area that you now call “finfinne” as well as in Shoa and Wollo for many centuries. Some of them have fought and died in wars to protect our country from the Italians, Turks, Egyptians and other invaders. If it wasn’t for their unity, hard work and bravery; Addis Ababa would not have been the historically and internationally important city that it is now. This Addis Ababa (including your finfinne: the tiny portion of current Addis Ababa where Oromos lived in after 1500s) would have probably remained undeveloped and insignificant if it was not for my patriotic ancestors. My ancestors have built and served this city and our nation in government and as civil servants while some members of my family have also served as critics in opposition with MEISON and MTA, to name a few. No matter which side of history and politics they partook, all of my ancestors belong here in Addis Ababa, whether you like it or not.

My ancestors have many different ethnolinguistic background, including Gurage, Tigre, Oromo and Amara. For example, on my paternal side, my “Oromo” great-grand father willingly married my great grand mother in southern Wollo region. All branches of my ancestors have their own unique history and experience that makes this country special and diverse. And they all belong here….we are not aliens or guests.

But Mr. Ararssa, do you know who else belongs in Addis Ababa? EVERYONE! Every Ethiopian belongs here.

One wonders….If writers and scholars like you continue to alienate and antagonize Ethiopian people against each other; then what exactly makes you any different from the TPLF/EPRDF regime that you protest against?

Thanks to the poisonous politics of the TPLF ruling party, I am sure there are many brainwashed people like Mr. Ararssa who really believe that we Ethiopians are aliens and “guests” in Addis Ababa. The TPLF’s dangerous “ethnic-federalism” system has oversimplified our complex identities in order to divide and put us all in separate boxes. TPLF’s constitution has institutionalized this impractical, tribal and genocidal interpretation of our identities. That is why pseudo-scholars like Mr Tsegaye Ararssa love to obsessively quote the TPLF constitution. In essence, It is their manifesto.

The current constitution is a narrow manifesto to benefit Oromo, Amhara, Tigray and other narrow nationalists at the expense of millions of Ethiopian nationalists. Indeed, until we draft and implement a new all-inclusive constitution to benefit all Ethiopians, we will not have lasting peace. Mr. Ararssa and other ethic nationalists should not waste their time and energy on the useless piece of paper that does not recognize the existence of millions of us Ethiopians of diverse, mixed and complex identities.

For the record, Many of us Ethiopian nationalists in Addis Ababa actually support the right of Oromos to oppose the “Addis Ababa master plan.” We support you because every Ethiopian (including Oromo) should enjoy basic human rights and freedom of speech & assembly. Secondly, instead of being ruled by TPLF puppets like OPDOs, all Ethiopians agree that Oromos should have the right to self-govern in towns and villages where they are the overwhelming majority and where they can democratically elect their own representatives. Thirdly, Oromo and non-Oromo farmers near the city also have a right to protect their interests against improper urbanization. So for many reasons, we support the “#oromoprotests” against the master plan.

But we oppose the idea that any group or tribe is a “guest” or a “host” in Ethiopia. Addis Ababa is not owned exclusively by the Oromo or by any ethnic group. It is for all Ethiopians. Yes, Oromo clans lived in Addis Ababa area for many centuries. But before Oromos, many other ethnolinguistic communities have lived in this land. For example, Gurage people’s southern migration, Muslim sultanates and Christian kingdoms are all part of the whole Shewa region’s history over a thousand years. So Oromos are not the only “natives” of this land. For many reasons, Addis Ababa belongs to every Ethiopian citizen. Unfortunately, some Oromo nationalists like to recklessly throw around “settler” and “colonialist” labels against non-Oromos. That is shameful. Mr. Ararssa even complained about Oromos “material and cultural loss, humiliation, dispossession of land…” But he forgot to mention the same “dispossession” has happened to the Sidama, the Dawaro, the Adal, Damot, Argoba and many others who lost their land and identity at the hands of Oromo warriors. If you are a real scholar, why selectively hide parts of our history? Thanks to the Oromo’s Mogassa and Gudifecha systems and other mass assimilation campaigns by the Oromo, many distinct ethnic communities have lost their past identities, territories and they have “become Oromo.” Despite these historical events, we still might not know every detail of how pieces of our history fit together. What we know for sure is that we are ALL here now in the land that we all call Ethiopia. We are all here in Addis Ababa. Let us move on. Whether we like it or not, we have to find ways to get along and co-exist peacefully.

We can not achieve this goal by attacking and labeling each other.

When scholars & politicians instigate violence using the “us vs them” tactic, or divide people using the “host vs guest” labels, they are playing into the WORST of our emotions and our instincts. Exploiting people’s tribal instincts is very unscholarly and weak. If people like Mr. Ararssa want to show how smart and scholarly they are, they should provide comprehensive solutions to our complex identities and our complicated problems. So please Stop taking the easy way out. It is very easy to preach tribal propaganda to the choir. It is hard to present progressive ideas that break ethnic barriers, and solve the economic, social and political problems of a multiethnic nation. It is very easy to rubber-stamp one-sided historical accounts from the A-to-Z liberation fronts in Ethiopia. It is hard to do a balanced, inclusive and extensive research of our diverse Ethiopian history. As leaders and thinkers of our nation, We can either choose to take the easy path, or we can choose to take the hard but honorable and rewarding path. For the Mr. Ararssas and Mr. Jawars out there, I challenge you to take the honorable path. The crisis in Ethiopia requires an in depth approach and multifaceted solution. Let us shine light into the darkness, because more darkness can not drive out existing darkness.


የፓትርያርኩ ልዩ ጸኃፊ፣ ወይንስ የህውኃት ጉዳይ አስፈጻሚ (ይገረም አለሙ)

ይገረም አለሙ

“በርግጠኝነት ሁልግዜም ችግር የመሪ እንጂ የህዝብ አይደለም፤” አቡነ አብርሀም

“ለጠፋው ህይወት መንግሥትን ብቻ ተጠያቂ ማድረግ አይቻልም” አባ ሰረቀብርሀን

“በትልቅም ቤት የእንጨትና የሸክላ ዕቃ ደግሞ አለ እንጂ የወርቅና የብር ዕቃ ብቻ አይደለም፡፡እኩሌቶቹም ለክብር እኩሌቶቹም ለውርደት ይሆናሉ፡፡እንግዲህ ማንም ራሱን ከእነዚህ ቢያነጻ ለክብርም የሚሆን የተቀደሰም ለጌታውም የሚጠቅም ለበጎ ስራ የተዘጋጀ ዕቃ ይሆናል፡፡”  (ጢሞቲዎስ 2፣2፣20)TPLF cadre in the Ethiopian Orthodox Church Aba Sereke Berhan

መስከረም 16 ቀን 2009 ዓም በእለተ ደመራ ምሽት የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ የአማርኛውን ፕሮግራም እያዳመጥኩ ነው፡፡ በዜና መጽሄት ክፍለ ጊዜ  የአዲስ አበባው ዘጋቢ እስክንድር ፍሬው በስብሰባ መሀል ነው ያነጋገርኩዋቸው ካላቸው  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ  ልዩ ጸሀፊ አባ ሰረቀ ብርሀን ወልደ ስላሴ ጋር ያደረገው አጭር ቃለ ምልልስ ቀረበ፡፡ እስክንድር በኦሮምያና በአማራ የተገደሉ ወጣቶችን ጉዳይ አንስቶ ቤተ ክህነት ምን አለች ምንስ አደረገች በማለት ላነሳቸው ጥያቄዎች  በልዩ ጸሀፊው የተሰጠው ምላሽ እንደ ሰው የሚያሳዝን፣ እንደ ዜጋ የሚያበሳጭ፣ እንደ ኦርቶዶክስ አማኝ የሚያሳፍር ነበር፡፡

አማርኛ ከእንግሊዘኛ እየደባለቁ የሚናገሩት አባ ሰረቀ ብርሀን አንደበታቸው ፈጽሞ የሀይማኖት አባት አይመስልም፡፡ከጠቅላይ ምኒስትሩ ጀምሮ የተለያዩ ባለሥልጣኖች ጥፋቱ የእኛ  የእኛ ነው በማለት ለማታላያም ቢሆን አምነው  ለዚህም ጥልቅ ተሀድሶ ያስፈልገናል በማለት እየተውተረተሩ ባለበት በዚህ ወቅት እኝህ የጳጳሳችን ልዩ ጸሀፊ ግን ከጳጳሱ ቄሱ አንዲሉ ሆነው “ለጠፋው ህይወት መንግስትን ብቻ ተጠያቂ ማድረግ አይቻልም” በማለት በተከላካይነት ቆሙ፡፡ በዛች አጭር ቃለ ምልልስ በተናገሩት ከመንግስት ቃል አቀባዩ አቶ  ጌታቸው ረዳ   ብሰው የተገኙት አባ ሰረቀ ብርሀን  “እየወረወረ በድንጋይ የሚገልም እየተኮሰ የሚገልም..” በማለት የመንግሥትን ግድያ ልክ አንደ ሰብአዊ መብት ኮሚሽነሩ ዶር አዲሱ ተመጣጣኝ ሊያደርጉት ዳዳቸው፡፡ ይህን ሰምቶ የማይናደድ ሰው፣ የማያፍር የእምነቱ ተከታይ ይኖራል፡፡ ነደድሁ አፈርሁ፡፡

አባ ሰረቀ ንግግራቸውም ሆነ የቃላት አጠቃቀማቸው የሀይማኖት ሰው ሳይሆን የፖለቲካ ሰው የሚያስመስላቸው፤ ቅላጼአቸው ደግሞ የትግረኛ ነውና ግብራቸውን በማይገልጽ መጠሪያ የፓትርያርኩ ልዩ ጸሀፊ ከሚባሉ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የህውኃት ጉዳይ ፈጻሚ ቢባሉ የሚገልጻቸው ይመስለኛል፡፡

በሰማሁት ነድጄ በሀይማኖቴ አፍሬ እንዳይነጋ የለም ለሊቱ ነጋ፡፡ ማርፈጃው ላይ ወደ ማህበራዊ ድረ ገጽ ጎራ ስል  ንዴቴን የሚያበርድ ብቻ ሳይሆን በሀሴት የሚሞላ፤ ሀፍረቴን የሚከላ ብቻ ሳይሆን  በኦርቶዶክስ እምነቴ ይበልጥ እንድኮራ ያደረገኝ ንግግር አገኘሁ፡፡ ንግግሩ የተደረገው በባህር ዳር መስቀል አደባባይ የደመራ ክብረ በአል ላይ ሲሆን ተናጋሪው የአካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ አብርሀም ናቸው፡፡ ያገኘሁት ንግግር ከመጀመሪያው የማይጀምር ቢሆንም ከጀመረበት አንስቶ ያለው ግን እውነተኛ የሀይማኖት አባት መሆናቸውን ያረጋገጠ ንግግር ነው፡፡ ሙሉ ንግግራቸው በጽሁፍም በድምጽም ከተቻለ በምስል ጭምር ቢገኝ ለአሁኑ አስተማሪ ለታሪክም ቅርስ ነው፡፡

ለመንግሥት ጥብቅ መልእክት፣ ለእምነቱ ልጆቻቸው አባታዊ ምክር ባስተላለፉበት ንግግራቸው “ የምናገረው ሀይማኖት ነው፤በፖለቲካ ከተረጎመው የራሱ ጉዳይ ነው” በማለት እውነቱን በድፍረት የገለጹት አቡነ አብርሀም  “በርግጠኝነት ሁልግዜም ችግር የመሪ እንጂ የህዝብ አይደለም” በማለት የመንግሥት ሰዎችን መክረዋል ፣አስጠንቅቀዋል፡ጋዜጠኞችንም ወቅሰዋል፡፡ የአቡነ አብርሀምን ይህን ንግግር እያዳመጣችሁ አለያም ይህችን ከመሀል መዝዤ የጠቀስኳትን ችግር የመሪ አንጂ የህዝብ አይደለም የምትለዋን እያብላላችሁ የአባ ሰረቀ ብርሀንን “እየወረወረ በድንጋይ የሚገልም እየተኮሰ የሚገልም..” የሚለውን አገላላጽ አስቡት አነጻጻሩት፡፡ መኩሪያና ማፈሪያ በአንድ ቤት፡፡

በመግቢያ ላይ የጠቀስኩት {በትልቅም ቤት የእንጨትና የሸክላ ዕቃ ደግሞ አለ እንጂ የወርቅና የብር ዕቃ ብቻ አይደለም፡፡እኩሌቶቹም ለክብር እኩሌቶቹም ለውርደት ይሆናሉ፡፡እንግዲህ ማንም ራሱን ከእነዚህ ቢያነጻ ለክብርም የሚሆን የተቀደሰም ለጌታውም የሚጠቅም ለበጎ ስራ የተዘጋጀ ዕቃ ይሆናል፡፡} (ጢሞቲዎስ 2፣2፣20) የሚለው  በስማቸው ሳይሆን በግብራቸው በያዙት የሀላፊነት ቦታ ሳይሆን በፍሬቸው ለተለዩት ለእነዚህ ሁለት አባቶች ጥሩ ገላጭ ሀይለ ቃል ይመስለኛል፡፡

የሚሊዮኖች የእምነት ቤት የሆነችው ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በውስጧ አንደ አቡነ አብርሀም ያሉ ወርቆችንና ብሮችን፣ አንደ እነ አባ ሰረቀ ብርሀን ያሉ የእንጨትና የሸክላ ስሪቶችን የያዘች ለመሆኗ አይደለም በምእምኑ ከእምነቱ ውጪ ላሉትም በግልጽ የሚታይና የሚታወቅ ነው፡፡

የእንጨትና የሸክላ ስሪቶቹ ያለ ቦታቸው መግባታቸው፣ ያለ ደረጃቸው መቀመጣቸው፣ ለምን እንዴት በምን ምክንያትና በማን አንደሆነ የተሰወረ ባለመሆኑ ወርቅ እንዲሆኑ ማድረግም ሆነ ከማይገባቸው ቦታ ማንሳት የማይቻል ስለሆነ የሚቻለውና መሆንም ያለበት “አንግዲህ ማንም ራሱን ከእነዚህ ቢያነጻ” የሚለውን የቅዱስ መጽኃፍ ቃል መፈጸም ነው፡፡

ከብረው ለሚያስከብሩን፣ በእውነተኛ አባትነት በጌታ በእየሱስ ክርስቶስ ቃልና መንገድ ለሚመሩንና ለሚያስታርቁን የአባትነት አክብሮት መስጠት፣ቃላቸውን መስማት ምክራቸውን መቀበል መሪነታቸውን መከተል፡፡ ከዚህ በተቃራኒ ያሉትን ደግሞ አታውቁንም አናውቃችሁም ማለት ያስፈልጋል፡፡ አቅሙ ካለና ሁኔታው ከፈቀደም ከወርቆቹና ከብሮቹ ጋር በመተባበር ቤታችንን ከሸክላና ከእንጨት ማጽዳት፡፡ ቤተ መቀደሴን የሌቦች ዋሻ አደረጋችሁት አይደል ያለው ጌታ እየሱስ፡፡

እነዚህ አለቦታቸው ገብተው የተቀመጡ መንፈሳዊውን ሥልጣን ለአለማዊ ተግባር የሚያውሉ ከእውነተኞቹ አባቶች እየቀደሙ በተገኘው መድረክ ሁሉ እየታደሙ ምእምኑን የሚያሳቱ ናቸውና፤ በዮሐንስ መልእክት (1፣3፣17)  “እንግዲህ እናንተ ወዳጆች ሆይ ይህን አስቀድማችሁ ስለምታውቁ በአመጸኞች ስህተት ተስባችሁ ከራሳችሁ ጽናት አንዳትወድቁ ተጠንቀቁ”፡ተብሎ እንደተጻፈው ሰዎቹን ለይቶ ማወቅ፣አውቆም መጠንነቅ የምእምኑ ተግባር ይሆናል፡፡

“ረጃጅም ልብስ ለብሰው መዞርን በገበያም ሰላምታን፣ በምኩራብም የከበሬታን ወንበር፣ በግብርም የከበሬታን ስፍራ ከሚወዱ ከጻፎች ተጠበቁ” ( የማርቆስ ወንጌል 12፣38/39)

ረዣም እድሜ ከጤና ጋር ለእውነተኛዎቹ የሀይማኖት አባቶች

በዘ-ህወሀት የውሸት ምድር የማወንበጃ መረጃ ዘመቻ፡ ቀጣፊው በኢትዮጵያ ዉሸትን እዉነት ነው እያለ ሲሰብክ?

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

የጸሐፊው ማስታዋሻ፡ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ እየተጠናከረ የመጣውን የዘ-ህወሀት (ዘራፊ ህወሀት) የመረጃ ማወናበጃ ዘመቻ ለማጋለጥ ሲባል በተከታታይ እያቀረብኩ ካለሁት ትችት ይህ ሶስተኛው ክፍል ነው፡፡ እ.ኤ.አ መስከረም 5/2016 አቅርቤው በነበረው ትችት በኢትዮጵያ ውስጥ ተንሰራፍቶ የሚገኘውን የዘ-ህወሀትን የጭቆና አገዛዝ በመቃወም እየተስፋፋ እና እየተጠናከረ የመጣውን ሕዝባዊ የእምቢተኝነት አመጽ አሳንሶ እና አኮስሶ ለማቅረብ በሚል እኩይ ምግባር ዘ-ህወሀት በቅርብ ጊዜ ውስጥ የመረጃ ማወናበጃ ዘመቻውን ይጀምራል በማለት አሳስቤ ነበር፡፡

እ.ኤ.አ መስከረም 18/2016 አቅርቤው በነበረው ሁለተኛው ትችቴ ዘ-ህወሀት በኢትዮጵያ ውስጥ አስፈሪ እና የማይቀር የዘር ማጥፋት ዘመቻ እውን ይሆናል በማለት አቅርቦት የነበረውን የቅጥፈት የመረጃ ማወናበጃ ዘመቻ መሰሪ ፕሮፓጋንዳ ሀሰት እና ተራ ቅጥፈት መሆኑን አጋልጫለሁ፡፡

በመስከረም መጀመሪያዎቹ አካባቢ አቅርቤው የነበረው የዘ-ህወሀት የመረጃ ማወናበጃ ዘመቻ በአሁኑ ጊዜ ተጠናክሮ በመቀጠል ላይ እና በተሟላ ቁመና ላይ ይገኛል፡፡ በዚህ ትችቴ ደግሞ የዘ-ህወሀት ዋና የመረጃ ማወናበጃ ቆሮ/ዋና ኃላፊ (መማቆ) የሆነውን የደብረጽዮን ገብረሚካኤልን የተዛባ እና መሳቂያ የሆነ የቅጥፈት ፕሮፓጋንዳ በማጋለጥ አቀርባለሁ፡፡ “እራሱን በራሱ ዉሸት ካሳመነ ሰው ጋር በፍጹም አትከራከር“ የሚለውን ጥንታዊ አባባል በሚገባ እገነዘባለሁ፡፡ ጭራ የቀራቸዉን ቀጣፊ ውሸታሞች በፍርድ ቤት በፍትሕ አደባባይ በመስቀለኛ ጥያቄ ማፋጠጡን የምመርጥ ቢሆንም ቅሉ ያ የፍትሕ አደባባይ የሚለው ነገር በሀገሪቱ ውስጥ ከቶውንም የሌለ እና ዳብዛው የጠፋ በመሆኑ ምክንያት በዓለም ህዝብ ህሊና ዳኝነት ክርክሬን ቀጥላለሁ።

በእኔ ዘመን ሳሙና የሆኑ አእምሮአቸው በዉሸት የተበከለ ቀጣፊዎችን  አጋጥመዉኛል፡፡ እናም አንድ ቁልጭ ያለ እና በግልጽ የማስታውሰው ነገር ቢኖር እነዚህ አእምሮአቸው የታመመ ቀጣፊዎች እራሳቸዉን  እንጂ ሌላ ሰው ስያታለሉ አላየሁም፡፡ ይልቁንም እነርሱ የቅጥፈት ባለሞያዎች የሆኑት እራሳቸውን በማታለል ነው፡፡ ሆኖም ግን ውሸት በሚነሳበት ጊዜ የመረጃ ማወናበጃ ቆሮ (መማቆ) የሆነው ደብረጽዮን እና ሌሎች የዘ-ህወሀት ወሮበሎች የአንበሳውን ድርሻ ይይዛሉ፡፡ እነዚህ ፍጡሮች የውሸት፣ የቅጥፈት እና የተራ አሀዛዊ ቅጥፈት ቀፍቃፊ ጌቶቸ ናቸው፡፡

መማቆ ደብረጽዮን በኢትዮጵያ ሕዝቦች ላይ ለበርካታ ሳምንታት የመረጃ ማወናበጃ ዘመቻ በመክፈት ማወናበድን በመቀጠል ረገድ 3ኛው ትልቅ ጠብመንጃ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ የዘ-ህወሀትን የጭቆና አገዛዝ በመቃወም እንደ ሰደድ እሳት ተቀጣጥሎ በሚገኘው ሕዝባዊ አመጽ እና መገዳደር ከጥቂት ሳምንታት በፊት አባይ ጸሀይ እና ስዩም መስፍን ከዘ-ህወሀት የአውሬዎች ዋሻ መካከል በድንገት ብቅ ብለው በመውጣት በሕዝብ ላይ የዘር ፍጅት ያወጁ እና የጮኹ ተኩላዎች ናቸው፡፡

የዘ-ህወሀት የመረጃ ማወናበጃ ጨዋታ ግልጽ ይመስላል፡፡ በኢትዮጵያ ሕዝቦች ላይ የቁማርና ካራምቦላ (እያጋጩ  ማለት) ጨዋታ በመጫወት ላይ ይገኛሉ፡፡

አባይ ጸሀይ እና ስዩም መስፍን ፍጹም በሆነ መልኩ ምክንያታዊ ያልሆነ እና እርባናቢስ የሆነ የዘር ማጥፋት ወንጀል ይፈጸማል በማለት ፍርሃት ለመፍጠር ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ “ሰማይ ይወድቃል” እያለ በሕዝብ ላይ ምዕናባዊ ፍርሀት በመልቀቅ እንደሚባለው በተመሳሳይ መልኩ አባይ ጸሀይ እና ስዩም መስፍን በኢትዮጵያ ውስጥ የዘር ማጥፋት ድርጊት ይፈጸማል በማለት ሕዝቡን በማስፈራራት እና በማደናገር ላይ ይገኛሉ፡፡

እንዲያው ለመሆኑ ይህንን አዲስ ነገር አድርገው እንደበቀቀን እየደጋገሙ የሚለፈልፉት ባለፉት 25 ዓመታት ውስጥ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ምን ሲያደርጉ ነው የቆዩት? በአማራው፣ በኦሮሞው፣ በጋምቤላው፣ በሶማሊው፣ በሲዳማው፣ በአፋሩ፣ በቤንሻንጉሉ፣ ወዘተ ሲፈጽሙት የቆዩትን የዘር ማጥፋት ወንጀል እስቲ ዘወር ብለው ይመልከቱት፣ ዘወር ብሎ የሚያይ አንገት ካላቸው፡፡ ምኑ ነው አሁን አዲስ የሚሆነው፡፡ ይልቁንስ አሁን የእነርሱ ማብቂያ እና መውደሚያ መሆኑን ስለተገነዘቡት ይሆናል የአቦን ቅጠል እንደቀመሰች ፍየል በመለፍለፍ ላይ የሚገኙት፡፡

ነው? ወይስ ያብየን ለምዬ?

መማቆ ደብረጽዮን የዘር ማጥፋት ወንጀል አይኖርም ይላል፡፡ በእርግጥ የራሱ ቃላት እንዲህ የሚሉ ሆነው ይገኛሉ፣“በኢትዮጵያ ውስጥ የሕዝብ ለሕዝብ ግጭት (የዘር ማጥፋት ወንጀል) ሊኖር አይችልም፡፡ በጥቂት ወንጀለኞች እና ችግር ፈጣሪዎች ሊቀሰቀሱ የሚችሉ የተነጣጠሉ ሁከቶች እና ግጭቶች (አመጾች ሳይሆኑ) ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ እነዘህ ደግሞ የዘር ማጥፋት ወንጀሎች አይደሉም“ በማለት ሳያውቀው አምኗል፡፡

እንግዲህ ወገኖቼ ከነዚህ ባለመንታ ምላስ እባቦች የትኛውን እንመን? አባይ ጸሀይን፣ ስዩም መስፍንን ወይስ ደግሞ ደብረጽዮን ገብረሚካኤልን?

መማቆ ደብረጽዮን በመጠኑም ቢሆን ተቀባይነት ያለው ለማስመሰል እና እራሱን ከሌሎቹ አስበልጦ እንዲታይ የማድረግ ቁመናን ለመላበስ ሙከራ አድርጓል፡፡ በስተቀኙ በኩል የዘ-ህወሀትን ባለኮከብ እርማ ሰንደቅ ዓላማ በማንጠልጠል የዘ-ህወሀት መልካም አድራጊ መስሎ መቅረብ ሞክሯል። ግን ያለው አስተሳሰብና ያደርገው ድርጊቶች ለኢትዮጵያ ህዝብ  አርሱም ዘ-ህወሀትም  ደንታ እንደሌላቸው አረጋግጧል። መማቆ ደብረጽዮን  የኢትዮጵያ ህዝቦች በዓለም ላይ ታይተው የማያውቁትን ነገሮች ቀይ እና ሰማያዊ ላም እንዲሁም ቀይ ዝሆን አየን እያሉ ይናገራሉ፡፡ ዝም ብለው ይቀባጥራሉ እናም እንዲሁ በፈጠራ ወሬዎች ጭንቅላታቸውን ሞልተው ይገኛሉ ነበር ያለው፡፡

መማቆ ደብረጽዮን ሁሉም ነገር አንዳለ ሳይሆን አንደተመለከቱቱ ነው ይላል። ሲያስረዳም ፣ “አንድ ሰው የጠራውን ቀን ጨለማ ነው  ደጋግሞ ካለ ሕዝቡ ያንን የጠራ ቀን ጨለማ ነው የሚል ሀሳብን ይይዛል ማለት ነው“ ነበር ያለው፡፡

ከዚህ አንጻር በዘፈቀደ አመንኩ፡፡ እጄን ሰጠሁ!

ስለጨለማ እራሱ የጨለማው  ልዑል ከሆነው አስመሳይ ፍጡር በላይ ማን ሊያውቅ ይችላል?

ስለጨለማ የጨለማው ጌታ ከሆነው ከንቱ ፍጡር በላይ ማን የበለጠ ሊያውቅ ይችላል?

ስለጭለማ መማቆ ደብረጽዮንን የመሞገት ችሎታ የለኝም።

ስለጨለማ በብርሀኑ በኩል ያሉት ሰዎች ሳይሆኑ የጨለማው ጌታ የበለጠ ያውቃል።

በሚያስገርም ሁኔታ መማቆ ደብረጽዮን የእርሱን የጨለማ ተመሳስሎ የተዋሰው እንዲህ ከሚለው እና የናዚ ጀርመን የፕሮፓጋንዳ ሚኒስትር ከነበረው ከጆሴፍ ጎቤልስ ነው፣ “ታላቅ ውሸት ከዋሸህ እና ይህንንም ውሸት ደግመህ እና ደጋግመህ ተግባራዊ ካደረግኸው በመጨረሻ ሕዝብ እውነት ብሎ ያምናል፡፡

ሆኖም ግን መማቆ ደብረጽዮን እንዲህ የሚሉትን የጎቤልስን አብረው የነበሩትን ቃላት ሆን ብሎ ዘሏቸዋል፡

“መንግስት ሕዝቡን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና/ወይም ወታደራዊ የሆኑ ውሸቶች ከሚፈጥሯቸው እንቅስቃሴዎች ለመከላከል ሲል ውሸቶች ለእንደዚህ ላለ ጊዜ ብቻ ሊቆዩ ይችላሉ፡፡ በዚህም መሰረት እውነት የሚሞተው የውሸት ጠላት በመሆኑ እና የዚህም ተቀጽላ እውነት የመንግስት ታላቁ ጠላት በመሆኑ መንግስት ሁሉንም ኃይሉን ሰላማዊ ሰዎችን ለመጨቆኛነት የሚጠቀምበት ዋናው አስፈላጊው መሳርያ ነገር ነው፡፡“

እውነት የመንግስት የመረጃ ማወናበጃ ዋና ጠላት ነው፡፡

የመማቆ ደብረጽዮን ቃለመጠይቅ፣

Debre Tsiyon and TPLF lie

በቪዲዮ በተቀረጸው ቃለመጠይቅ መማቆ ደብረጽዮን በበርካታ ጉዳዮች ላይ በተደጋጋሚ ሲደነፋ ( ሲንተባተብ አላልኩም) እና የኢትዮጵያ ሕዝቦች ስለዘ-ህወሀት እውነተኛ ምንነት መግለጽ የማይችሉ ደንቆሮዎች እና ደደቦች መሆናቸውን ተናግሯል፡፡ በቁስል ላይ እንጨት እንዲሉ በውሸት ላይ ያሉ ሕዝቦች በማለት እራሱን ከፍ ከፍ እያደረገ መሰረተቢስ የሆነውን የማታለል ንገግር አድርግዋል ፈጽሟል፡፡ ለመማቆ ደብረጽዮን ኢትዮጵያ ሕዝቦች በምዕናባዊ ሀሳብ እና በእውነት መካከል ያለውን ልዩነት ለይተው የማያውቁ የዋሀን ናቸው፡፡ በእርሱ ድሁር አስተሳሰብ የኢትዮጵያ ሕዝቦች የሚያዩት ነገር በተጨባጭ የሚያዩት እና የሚመለከቱት ነገር አይደለም፡፡ ሆኖም ግን ምንም ዓይነት እውነታነት የሌለው በድድብና የተሞላ ምዕናባዊ ነገር ነው፡፡ እውነታውን እንዲያውቁት እንዲመለከቱት ተደጋጋሚ የሆነ ትምህርት ሊሰጣቸው ይገባል፡፡ ይህንን ትምህርት እንዲሰጥ እና ስራውን እንዲሰራ ለብዙሀን መገናኛ ጥሪ መቅረብ አለበት ነው ያለው መማቆው !

የመማቆ ደብረጽዮን ቃለመጠይቅ እንዲህ የሚሉ በርካታ የሆኑ የፕሮፓግንዳ እና የፖለቲካ ዓላማዎችን ለመጎናጸፍ በግልጽ የተዘየደ ዕቅድ ነው፡

1ኛ) በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ ተቀጣጥሎ የሚገኘው መጠነ ሰፊ ሕዝባዊ ተቃውሞ በጎንደር ላይ ተወስኖ የሚገኝ ትንሽ ነገር ነው፡፡

2ኛ) በጎንደር ውስጥ የተፈጠረው ሁከት ጥቂት የውጭ ኃይሎች እና ወንጀለኞች ስራ ነው፡፡ በጎንደር ውስጥ ወይም ደግሞ በሌላ በማናቸውም ቦታ እና አካባቢ ውስጥ ምንም ዓይነት ሕዝባዊ አመጽ የለም፡፡

3ኛ) በጎንደር የተቀሰቀሰው ሁከት ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ባልተወጡ የስራ ኃላፊዎች እና  በአካባቢው አመራር ብቃትየለሽነት እና የአስተዳደር ጉድለት የተፈጠረ ነው፡፡ ስለዚህ እነዚህ ሰዎች ተወግደው በሌላ መተካት ይኖርባቸዋል፡፡

4ኛ) በኢትዮጵያ ሕዝቦች ፖለቲካ እና ማህበረሰብ ውስጥ የትግራይ የበላይነት የሚለው ነገር አውዳሚ የሆነ የሰዎች የተሳሳተ ምዕናባዊ ሀሳብ ነው፡፡ የትግራይ የበላይነት በልብወለድ ውስጥ ያለ በምዕናባዊ ሀሳብ የሚኖር እንጅ በነባራዊ እውነታ በተጨባጭ የሌለ ነገር ነው፡፡

5ኛ) የኢትዮጵያ ሕዝብ የትግራይ የበላይነት የሌለ መሆኑን እንዲያውቅ ትምህርት ያልተሰጠው በመሆኑ ከግንኙነት ውድቀት የመነጨ ነው፡፡ የእራሳቸው የግንዛቤ ምዕናባዊ እሳቤ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝቦች በብርሀን እና በጨለማ መካከል ያለውን ልዩነት መናገር የማይችሉ እንደዚህ ያለ የትግራይ የበላይነት የሚባል ነገር ያለ መሆኑን መናገር የማይችሉ እና ትምህርት የሚያስፈልጋቸው ደንቆሮዎች ናቸው፡፡

6ኛ) ትግራውያን በኢትዮጵያ ሕዝቦች ላይ የጎሳ የበላይነት እየተገበሩ ላለመሆናቸው ሊያስገነዝብ የሚያስችል የመረጃ የማወናበጃ ዘመቻ ታላቅ የብዙሀን መገናኛ ፍላጎት አለ፡፡

7ኛ) የኢትዮጵያ ፖለቲካ ነባራዊ እውነታ የሚያሳየው ነገር ቢኖር እያንዳንዱ የጎሳ ቡድን በእራሱ ክልል (ባንቱስታን) የበላይ ነው፡፡

8ኛ) ለጎሳ ታላቅነት እና የበላይነት የጎሳ ፌዴራሊዝም የመጨረሻው ጠባቂ ኃይል ነው፡፡

9ኛ) ብቸኛው እውነታ የዘ-ህወሀት እውነታ ብቻ ሲሆን ሌላው ግን ተራ ምዕናባዊ ሀሳብ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ስለኢትዮጵያ ሕዝቦች መልካም ነገር እና ጥቅም ተልዕኮው ተነግሮ ስለማያልቀው ስለዘ-ህወሀት የተሳሳተ ግንዛቤ አለው፡፡

10ኛ) የኢትዮጵያ ሕዝቦች ዘ-ህወሀት ደም የተጠማ ወንጀለኛ የወሮበሎች ስብስብ እንደሆነ አድርገው የሚነግሯቸውን የሚዋሹ ዓይኖቻቸውን እና ጆሮዎቻቸውን ማመን የሚያቆሙ ከሆነ የዘ-ህወሀትን ደግ፣ ጓዳዊ፣ የተረጋጋ፣ ለጋሽ፣ አፍቃሪ እና ሰብአዊ ፍጡርነት ይገነዘባሉ፡፡“

በሰጠው ቃለመጠይቅ መማቆ ደብረጽዮን በቅርቡ በጎንደር የተፈጠረውን ሁከት (ሕዝባዊ አመጽ) እና ትግራውያንን ማፈናቀል እየተባለ የቀረበውን ውንጀላ ጨምሮ የትግራይ የበላይነት የሚለው መሰረተቢስ ውንጀላ እንደሆነ እና የጎሳ ፌዴራሊዝም የኢትዮጵያ የፖለቲካ እና የማህበራዊ ቀውሶች ሁሉ ፈዋሽ መድኃኒት አድርጎ በርካታ ጉዳዮችን እንደሚከተለው አቅርቧል፡

መማቆ ደብረጽዮን አንደተናገረው (ከእንግሊዘኛው አንደተተረጎመ)

“በጎንደር ስለተከሰተው “ግጭት”፣ “ሁከት” ሁኔታ፣

…እንደ ቁንጮ አመራር እኔ ብቻ ስለሁኔታው አውቃለሁ፡፡ የግጭቱን ዝርዝር ሁኔታ የሚያውቁ የተለያዩ አካላት ናቸው፡፡ ያንን ሁኔታ በቅርበት አልከታተልም…በሱዳን እና ከሱዳን በተመለሱት መካከል ግጭት እንዳለ አውቃለሁ፡፡

ይህንን እንዴት መመልከት እንዳለብን፡ በተለየ መልክ እንደተገለጸው ዋናው ነገር ይህ ሁኔታ የሕዝብ ለሕዝብ ጉዳይ (ግጭት) አይደለም፡፡ ከትግራይ ጥቂት የእኛ ሰዎች እና ከሌሎች ቦታዎች በጎንደር ውስጥ በተፈጠረው አመጽ እየተሰቃዩ እና ጉዳት እየደረሰባቸው ይገኛሉ፡፡ የተቀጣጠለውን እሳት (ግጭት) ለማስፋፋት የሚፈልጉ ጥቂት ሰዎች እንዳሉ እንገነዘባለን፡፡ በጎንደር የሚኖሩ የአማራ ሕዝቦች ናቸው፡፡ ሌሎችን (አማራ ያልሆኑትን) እንደሚከላከሉላቸው እና ጉዳት እንደማይደርስባቸው እንገነዘባለን፡፡ የተፈጸሙ በርካታ ድርጊቶች (ወንጀሎች) አሉ፡፡ በጣም ጥቂት የሆኑ ሰዎች በጎንደር በሚኖሩ ትግራውያን ንብረቶች ላይ ጉዳት ለማድረስ ይፈልጋሉ፡፡ ስለሆነም እነዚህ ድርጊቶች የአብዛኛው የጎንደር ሕዝብ ድርጊቶች አይደሉም፡፡ በየትኛውም ቦታ ትግራውያንን ለማጥቃት ተብሎ የሚደረግ እንቅስቃሴ የለም፡፡ ሆኖም ግን በትግራውያን ላይ ወንጀሎችን ለመፈጸም የሚንቀሳቀሱ ጥቂት ሰዎች እንዳሉ እናውቃለን፡፡ ጥቂት ግለሰቦች በትግራውያን ላይ የወንጀል ድርጊቶችን እንደፈጸሙ እናውቃለን፡፡ ይህ ሁኔታ የጥቂቶች ድርጊት እንደሆነ እናውቃለን፡፡ ከእራሳቸው ዓላማ ጋር የሚደረግ እንቅስቃሴ አለ፡፡ የፌዴራል መንግስት እና የክልሉ መንግስት ይህንን ሁኔታ በቅርብ በመከታተል ላይ ይገኛሉ፡፡

ሆኖም ግን ይህ ጥያቄ መጠየቅ ያለበት ጥያቄ አይደለም፡፡ ከትንታኔው መገንዘብ እንደሚቻለው መፍትሄው በግጭቱ (መጋፈጥ) ላይ በማተኮር ብቻ ሊገኝ አይችልም፡፡ በአካባቢው አመራር፣ ለሕዝቦች መልካም አስተዳደር ማቅረብ ያልተቻለበትን፣ ለሚቀርቡት ጥያቄዎች ሁሉ በወቅቱ ምላሽ ያልተሰጠበትን፣ ችግሮች ያሉ መሆናቸውን ያለማስተዋል እና ሌሎችን እንደዚህ ያሉትን ሁኔታዎች ሰፋ ባለ መልኩ መመልከት አለብን፡፡ እናም በዚህ ጉዳይ ዙሪያ እንቅስቃሴዎች ይኖራሉ፡፡ ይህ በእራሱ ችግሮችን ፈጥሯል፣ እናም በዚህ ዙሪያ ያሉትን ችግሮች የምንፈታ ከሆነ ሌሎችን ችግሮችም አብረን እንፈታለን፡፡ ሌሎች አስተዳደራዊ ችግሮችን፣ የልማት ጥያቄዎችን እንፈታለን ማለት ነው፡፡ እንደዚሁም ሁሉ የፖለቲካ ጥያቄዎችን ማንሸራሸር እና መፍታት እንችላለን፡፡ እኛ እንግዲህ የምንመለከተው በዚህ ዓይነት መንገድ ነው፡፡ 

በጎንደር የተከሰተው ግጭት አንድ ውሱን ጉዳይ ነው፡፡ ሁሉንም አጠቃላይ ሁኔታ የሚያሳየን አይደለም፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝቦች በተለያዩ መድረኮች ላይ እየተካሄዱ ባሉት ውይይቶች ላይ በጣም አዝነዋል፡፡ ይህ ኢህአዴግ ያመጣው ነገር አይደለም፡፡ የጎንደር እና የትግራይ ሕዝብ ለበርካታ ጊዚያት አብረው ኖረዋል፡፡ በአንድ ላይ መኖር ብቻ አይደለም ሆኖም ግን እርስ በእርስ በመጋባት እንደ አንድ ቤተሰብ ሆነዋል… ሆኖም ግን ሕዝብ ለሕዝብ ግጭት (የጎሳ ግጭት) ለመፍጠር ዓላማ አድርገው የሚንቀሳቀሱ ጥቂት ሰዎች አሉ፡፡ ይህ ህገወጥ ተግባር ነው፡፡ ጉዳቶች ተፈጥረዋል…እንግዲህ በቅርብ ጊዜ ውስጥ እየተደረገ ያለው ውይይት ስለዚህ ጉዳይ ነው፡፡ 

የሕዝብ ለሕዝብ (የጎሳ) ግጭት ሊኖር አይችልም… በጎንደር ስለተፈጸመው ትንሽ ግጭት የተለየ ልዩ የሆነ መፍትሄ የለንም፡፡ በአንድ በትግራውያን ላይ ለደረሰ ጉዳት መፍትሄ የለም፡፡ ዋናው ነገር ስለሰላም እና መረጋጋት ጉዳይ ነው፡፡ ይኸ ጉዳይ በሚገባ ከተመለሰ ሌላው (የጎሳ ግጭት) ጉዳይ በእራሱ ይፈታል፡፡ 

በኢትዮጵያ ሕዝቦች ላይ ስለትግራይ የበላይነት ሁኔታ፣ 

አልጋ በአልጋ የሚሆን ነገር የለም፡፡ ውጣ ውረድ አለ፡፡ እውነታ የማይመስል አንድ  ምዕናባዊ አስተሳሰብ እውነት ይሆናል፡፡ ለምሳሌም ያህል አሁን በዚህ ክፍል ውስጥ ብርሀን አለ፡፡ ነገር ግን አሁን በዚህ ክፍል ያለው ጨለማ ነው የሚባል እና የሚደገም ከሆነ ሕዝብ ጨለማ ነው ብሎ ያምናል፡፡ ብርሀን መኖሩ የሚታወቅ ቢሆንም እንኳ ጨለማ ነው፡፡ ምዕናባዊው ሀሳብ ወደ ተጨባጭ እውንነት ተለወጠ ማለት ነው፡፡ ይህም የሆነበት ዋና ምክንያት አንድ የተረሳ ነገር አለ ማለት ነው፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት ትክክለኛው ምላሽ ለኢትዮጵያ ሕዝብ አልተሰጠም ማለት ነው፡፡ ከዚህም የተነሳ በብዙሀን መገናኛዎች ውጤታማ የሆነ ስራ አልተሰራም ማለት ነው፡፡ ማንኛውም እውነት ሆኖ ያልተገኘ ነገር ሁሉ (ምክንያቱም ስለትግራይ የበላይነት እየተነገሩ የቆዩ ውሸቶች እስከ አሁን ድረስ ተግዳሮት ስላልገጠማቸው) አሁንም እውነት አይደለም፡፡ 

እውነት በእራሱ አይናገርም፡፡ እውነታውን በተለያዩ መንገዶች በብዙሀን መገናኛ እና በሌሎች መግለጽ ይቻላል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ የመንግስት ሜዲያ ተገቢ የሆነ ስራ መስራት አለበት፡፡ ድክመት፣ እድገት ወይም ደግሞ ወደኋላ የመንሸራተት እና ሌሎችም ጉዳዮች ካሉ የመንግስት ሜዲያ ነው እውነታውን ማቅረብ ያለበት፡፡ ሆኖም ግን ሜዲያው እውነትን ማንጸባረቅ (ማሰራጨት) አለበት፡፡ 

በፌዴራሊዝም መኖር ምክንያት የትግራይ የበላይነት ሊኖር አይችልም፡፡ ፌዴራሊዝም ማለት ሁሉም ሕዝቦች እኩል ናቸው ማለት ነው፡፡ እያንዳንዱ ሕዝብ እራሱን በእራሱ ያስተዳድራል፡፡ አንድ ጎሳ የበላይ ወይም የበታች የሚባል ነገር የለም፡፡ የጎሳ ቡድኖች ትልቅ ወይም ትንሽ አባላት ስለመኖር ጉዳይ አይደለም፡፡ ትግራውያን እራሳቸውን ያስተዳድራሉ፡፡ ኦሮሞዎች እና የደቡብ ሕዝቦች እንዲሁም የሶማሊ ሕዝቦች እራሳቸውን በእራሳቸው ያስተዳድራሉ፡፡ ይህም ማለት የእራሳቸውን መንግስት በባለቤትነት ይይዛሉ ማለት ነው፡፡ መሰረቱ እኩልነት ነው፡፡ ይህ ማለት የእራስህን አስተዳደር አስተዳድር ማለት ነው… 

በአማራ ክልል ውስጥ ትግራውያን አስተዳዳሪዎች ሊሆኑ አይችሉም፡፡ በጋምቤላ ውስጥ አስተዳዳሪው ትግራዊ ሊሆን አይችልም፡፡ እንደዚህ ያለው የጎሳ ፌዴራሊዝም አወቃቀር አንዱ ጎሳ በሌላው ላይ የበላይ እንዲሆን አያደርግም፡፡ አንድ ዓይነት የጎሳ ማንነት ያላቸው እራሳቸውን ያስተዳድራሉ፡፡ ትግራውያን እዚህም እዚያም የበላይ (አለቆች) ናቸው የምትል ከሆነ መሰረትየለሽ ነገር ነው፡፡ ሆኖም ግን በየቦታው እስከ ቀበሌ መዋቅር ድረስ ሁሉም ነገር እውነትነት የሌለው ምዕናባዊ ሀሳብ ነው፡፡ የትግራውያን የበላይነት እውነታነት የለውም፡፡ እንደዚህ ያለ ውንጀላ ማቅረብ መሰረተቢስ ነው፡፡ ብርሀን እየበራ እያለ ባለበት ሁኔታ ጨለማ ነው እንደማለት ያህል ነው፡፡ ሆኖም ግን ይህንን በደጋገምከው ጊዜ ሌሎችም አዎ ጨለማ ነው ሊሉ ይችላሉ፡፡ በፌዴራሊዝም ሀገሪቱ እንዴት መተዳደር እንዳለባት ስለፌዴራሊዝም የኢትዮጵያን ሕዝቦች አላስተማርናቸውም፡፡   

ያ እውነታ ለህዝቡ እንዲተላለፍ አልተደረገም፡፡ ትግራውያን በየቦታው የበላይ ናቸው ማለት እውነታ አይደለም፡፡ ያ ዜሮ ነው፡፡ ዜሮ፡፡ ከትግራይ ክልል ውጭ ትግራውያን ሰው ካለ የመዋዕለ ንዋይ አፍሳሽ ኢንቨስተር ሆኖ እንደማንኛውም ሰው ይኖራል፡፡ ስለሆነም ሕዝቡን ያለማስተማር የግንዛቤ ችግር አለብን፡፡ የትግራይ የበላይነት እውነት አይደለም ሆኖም ግን የእኛ ብዙሀነን መገናኛዎች ጉድለት አለባቸው፡፡ የትግራይ የበላይነት እንደሌለ ብዙሀን መገናኛዎች እውነቱን የማሰራጨት ኃላፊነት አለባቸው…

መማቆ ደብረጽዮን ገብረሚካኤል፡ መንታ ምላስ እና ሁለት ተጻራሪ እምነቶችን በመያዝ የመረጃ ማወናበጃ ዘመቻን ማካሄድ፣

ጆርጅ ኦርዌል “ፖለቲካ እና የእንግሊዝኛ ቋንቋ“ በሚል ርዕስ ባዘጋጀው ድርሰቱ እንዲህ በማለት ጽፏል፡

በእኛ ጊዜ የፖለቲካ ንግግር እና መጻፍ በአብዛኛው መከላከል ለማይደረግላቸው መከላከያዎች ናቸው፡፡ የፖለቲካ ቋንቋ… ውሸቶችን ለመፈብረክ እና እውነት ለማስመሰል የተዘጋጀ እና የተከበሩትን ለመግደል ምንም ዓይነት ጥንካሬ በሌለበት በባዶ ነፋስ ውስጥ ጥንካሬ እንዳለ አድርጎ የማቅረብ ድርጊት ነው…“ ነበር ያለው፡፡

ከደብረጽዮን መንታ ምላስ የሚወጡ ዉሸቶችና እና ተጻራሪ እምነት የሚብሱ ብዙ የሉም፡፡

የአዞ እንባ አንቢው ደብረጽዮን በመንግስት ላይ መንግስት ላዋቀረው እና ማንኛውንም ነገር የሚቆጣጠረው የዘ-ህወሀት ፖለቲካ አጧዛዥ አድራጊ ፈጣሪ ነው፡፡ በዘ-ህወሀት አገዛዝ ውስጥ በርካታ የኃላፊነት ቦታዎችን ይዞ ቆይቷል፡፡ በአሁኑ ጊዜ የኮሙኒኬሽን እና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጅ ሚኒስቴር ኃላፊ (በትክክለኛ አጠራር የመረጃ ማወናበጃ ቆሮ (መማቆ)/ Chief Disinformation Officer (CDO) እና ከሶስቱ የዘ-ህወሀት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮች አንዱ በመሆን በማገልገል ላይ ይገኛል ይባላል፡፡ እንደዚሁም ሁሉ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን የቦርድ ሊቀመንበር እና የቀድሞው የኢትዮጵያ የኢንፎርሜሽን እና ኮሙኒኬሽን ልማት ኤጀንሲ/Ethiopian Information and Communication Development Agency (EICTDA)፣ ቴክኖሎጂ የደረሰበትን የብሮድባንድ ኔትዎርክ ለመገንባት እና የአካዳሚክ እና የምርምር ኔትወርኮችን ለመደገፍ፣ የኢንፍርሜሽን ኮሙኒኬሽን ኔትዎርክ እና ልማትን በማሳደግ  የአካዳሚክ ተቋማትን የግል ዘርፉን ለማሻሻል ተቋቁሞ የነበረው ድርጅት ዳይሬክተር ጀኔራል ነበር ይባላል፡፡

በአዋጅ ቁጥር 691/2010 ድንጋጌ መሰረት የተቋቋመው የኮሙኒኬሽን እና የኢንፎረሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የEICTDA፣ የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒከኬሽን አጀንሲ/ETA እና የዘ-ህወሀት የትራንስፖርት እና ኮሙኒኬሽን ሚኒስቴር ጥምረቶች ነው፡፡

መማቆ ደብረጽዮን የዘ-ህወሀት ተቃዋሚ በሆኑት በኢትዮጵያ ዲያስፖራዎች ላይ ስለላ ለሚያካሂደው እና ከጣሊያን አገር የሳይበር ደህንነት ድርጅት ምርመራ ቡድን/cybersecurity firm Hacking Team የተገዛው ሶፍት ዌር በስለላ ተግባር ላይ እንዲውል እና ለኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲ እና ሰብአዊ መብት ድፍጠጣ ዕኩይ ምግባር ዋና መሀንዲስ ሆኖ ሲያገልግል የነበረ ነው፡፡ እ.ኤ.አ በ2014 የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሬፐብሊክ ከዩኤስ አሜሪካ የቴሌፎን መስመር ጋር በማገናኘት የስለላ ተግባራትን በማካሄድ ሕግን መጣስ የሚል ውንጀላ በዩኤስ ፌዴራል ፍርድ ቤት ተመዝግቦ በፋይል ተያዘ፡፡ በአሁኑ ጊዜ ጉዳዩ በሕግ ማሻሻያ ሂደት ውስጥ ሲሆን በቀጣዮቹ ጥቂት ዓመታት ውስጥ ለዩናይትድ ስቴት አሜሪካ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ይደርሳል፡፡

እንደ አንድ ዘገባ ከሆነ መማቆ ደብረጽዮን በጫካ ውስጥ የዘ-ህወሀት ሬዲዮ ጣቢያ የነበረውን ድምጺ ወያኔን ከመሰረቱ ግለሰቦች መካከል አንዱ ነው ይባላል ፡፡ ሚኒያፖሊስ አም ኤን እየተባለ ከሚጠራው የድረገጽ ዩኒቨርስቲ የዶክትሬት ዲግሪውን እ.ኤ.አ በ2011 እንዳገኘ ተመዝግቦ ይገኛል፡፡ “በኢትዮጵያ ድህነት ላይ የአይሲቲ ማዕከል ተጠቃሚዎችን የአይሲቲ ውጤታማነት መፈተሽ/Exploring the perception of users of community ICT centers on the effectiveness of ICT on poverty in Ethiopia“ በሚል ርዕስ ባዘጋጀው የዶክትሬት ዲግሪው የጥናት መሟያ የመመረቂያ ጽሁፍ ምናልባትም ኢንፎርሜሽን እና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ (አይሲቲ) የልማት መገልገያ መሳሪያ እንደሆነ መርምሮ ይሆናል፡፡ ሆኖም ግን በሚያስገርም ሁኔታ በድህነት ላይ ያለውን የህልዮት ግንዛቤ በተመሳሳይ መልኩ ለፕሮፓጋንዳ እና ለመረጃ ማወናበጃ ዘመቻ ስራ እንደሚውል አድርጎ እምነት ያሳደረ ይመስላል፡፡

መማቆ ደብረጽዮን አሁን በህይወት እንደሌለው እንደ ወሮበላ ዘራፊው መለስ ዜናዊ (ወዘመዜ) ሁሉ የኦርዌልን ባህሪ የተላበሰ ገጽታ ያለው ሰው ነው፡፡ እንደ ወዘመዜ ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ መማቆ በኢትዮጵያ ሕዝቦች፣ በአበዳሪዎች፣ በለጋሽ ድርጅቶች እና በዓለም አቀፍ የድህነት አቃጣሪዎች ላይ የቁማር ጨዋታን መጫወት ይወዳል፡፡

እንደ ታላቅ ወንድሙ እንደ ወዘመዜ ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ መማቆ እርሱ እና የእርሱ ዘ-ህወሀት ወሮበላ ዘራፊዎች በእውነት እና በእውነታዋ ዓለም ላይ የሚኖሩ እና እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ደግሞ በህልም እና በጨለማ ምዕናባዊ ዓለም እንዲሁም በሀሳብ እና በቅዠት ዓለም ውስጥ የሚኖር ነው በማለት ያምናሉ፡፡

በዘ-ህወሀት የኦርዌሊያን ፕላኔት “ጦርነት ሰላም ነው፡፡ ነጻነት ባርነት ነው፡፡ ድንቁርና ጥንካሬ  ነው፡፡ አምባገነንነት ዴሞክራሲ ነው፡፡ የጎሳ ፌዴራሊዝም የጎሳ እኩልነት ነው፡፡ የጎሳ የበላይነት ሕገወጥ ሴራ ነው፡፡ የዘ-ህወሀት ባለሀብቶች አገዛዝ ማለት ሁሉም ሕዝቦች እኩል የፖለቲካ ስልጣን አላቸው ማለት ነው፡፡“

መማቆ ደብረጽዮን የኢትዮጵያን ሕዝቦች እንደሚያታልሏቸው፣ ጆሮዎቻቸው እንደሚዋሹባቸው እንዲያምኑ እና ጉድለት ያለው አእምሮ እንዳላቸው አድርገው እንዲያምኑ ይፈልጋል፡፡

ስለዘ-ህወሀት ፕላኔት መረጃ ማወናበጃ ዘመቻ ከብዙ ጊዜ ጀምሬ ስጽፍ ቆይቻለሁ፡፡

እ.ኤ.አ ወደ 2009 መለስ ብለን ስንቃኝ ከ3.6 ሚሊዮን የአካባቢ ምርጫዎች መቀመጫዎች ባለፈው ዓመት (2008)ከሶስት መቀመጫዎች በስተቀር ሁሉንም ማሸነፍ ፍጹም የሆነ ዴሞክራሲያዊ ነው፣ እናም ዴሞክራሲ ስለሂደት ነው፣ ስለውጤት አይደለም… ሂደቱ ንጹህ ከሆነ ስህተት ዜሮ ነው ነበር ያለው መለስ ዜናዊ ፡፡

ዛሬ መማቆ ደብረጽዮን እንዲህ ይላል፣ “የጎሳ ፌዴራሊዝም እኩልነት ነው፡፡ የዘ-ህወሀት የበላይነት ምንም ዓይደለም ግን ዱለታ ነው፡፡ ትግራውያን በየቦታው የበላይ ናቸው ማለት እውነታን የሚያመላክት አይደለም፡፡ ያ ዜሮ ነው፡፡

የሚያስገርመው ነገር መማቆ እና ወዘመዜ ስለዜሮ አንድ ነገር አላቸው፡፡

ዘሮን በጣም ይወዱታል፡፡ በተለይም የዜሮ ድምር ምርጫ ጨዋታዎችን (ሁልጊዜ ሁሉንም ነገር እንደሚያሸንፉ እና ሌላው እያንዳንዱ ሰው ግን ሁሉንም ነገር እንደሚያጣ እና እንደሚሸነፍ) በጣም ይወዷቸዋል፡፡ ላለፉት 25 ዓመታት ከአንድ የዜሮ ድምር ጨዋታ ሌላ የዜሮ ድምር ጨዋታ እየተገለባበጡ በመጫወት ሁልጊዜ በተከታታይ ሲያሸንፉ ኖረዋል፡፡

እስቲ ጉዳዩን ግልጽ ላድርገው፡፡ እ.ኤ.አ ግንቦት 2015 በዘ-ህወሀት ፓርላማ መቀመጫዎችን መቶ በመቶ ያሸነፈው ማን ነው? ይኸ ነው እንግዲህ የዜሮ ድምር ጨዋታ ማለት!

ቀደም ሲል እ.ኤ.አ በ2008 ተካሂዶ እንደነበረው የአካባቢ ምርጫዎች ወዘመዜ ኢትዮጵያውያን ስለዘ-ህወሀት የተሳሳት ግንዛቤ አላቸው እንዳለው ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ መማቆ ደብረጽዮን ዛሬ እንደዚሁ በማለት ላይ ይገኛል፡፡

ወዘመዜ ኢትዮጵያውያን ስለዴሞክራሲ የተሳሳተ ግንዛቤ አላቸው ብሏል፡፡ ስለምርጫዎች፣ የሕግ የበላይነት፣ መልካም አስተዳደር እና ስለፌዴራሊዝም የተሳሳተ ግንዛቤ አላቸው፡፡

መማቆ ደብረጽዮን ስለዘ-ህወሀት ዴሞክራሲ፣ ፌዴራሊዝም፣ ስለትግራይ የበላይነት፣ ስለልማት፣ ስለመልካም አስተዳደር እና ስለዴሞክራሲ የተሳሳት ግንዛቤ አላቸው ይላል፡፡

መማቆ ደብረጽዮን ኢትዮጵያውያን ከእንቀልፋቸው ተነስተው የፈላዉን ቡና ያሽትቱ ይላል፡፡

በዘ-ህወሀት ፕላኔት ውስጥ የተጻራሪ እምነቶች እና መንታ ምላሶች ውጤት፡ “ጦርነት ሰላም ነው፡፡ ነጻነት ባርነት ነው፡፡ ድንቁርና ጥንካሬ ነው፡፡ አምባገነንነት ዴሞክራሲ ነው፡፡ ድህነት ባለጸግነት ነው፡፡ ረሀብ ጥጋብ ነው፡፡ የመንግስት ስህተቶች የሰብአዊ መብቶች ናቸው፡፡ የተጭበረበሩ እና የተዘረፉ ምርጫዎች የሕዝቦች ምርጫዎች ናቸው፡፡ ሕዝቦችን ማስፈራራት ለእነርሱ የደስታ ምንጭ ነው፡፡ እናም የተደራረቡት የውሸቶች ቁልሎች የእውነት ማዕበሎች ናቸው፡፡“

የዘ-ህወሀት መንታ ምላስ እና ተጻራሪ እምነቶች ምርጫዎች ስለሂደት የሚዘግቡ ናቸው፡፡ የሕግ የበላይነት ማለት በዘፈቀደ የዜጎችን ህይወት የመቅጠፍ፣ የነጻነት እና ንብረት ክልከላ ሂደት ነው፡፡ አስተዳደር ስለተጠያቂነት እና ግልጸኝነት አይደለም፡፡ በላም ጡት ላይ ተጣብቆ እንደሚኖር መዥገር በስልጣን ኮርቻ ላይ ተጣብቆ መኖር ማለት ነው፡፡ ሕገ መንግስት ስለሕግ የበላይነት አይደለም፡፡ ስለሕገወጥ አገዛዝ ነው፡፡ ፌዴራሊዝም ስለግልጽ ሕገመንግስታዊ የስልጣን ክፍፍል አይደለም፡፡ ሆኖም ግን አምባገነናዊ አገዛዝን ለማጠናከር ጥልቅ የሆነ የጎሳ፣ ባህላዊ እና ክልላዊ የጎሳ ፌዴራሊዝም እየተባለ ስለሚጠራው ምዕናባዊ ሂደት ነው፡፡

መንታ ምላስ እና ተጻራሪ እምነቶች እንደ መረጃ ማወናበጃ ስልቶች፣

እ.ኤ.አ በ1984 ኦርዌል እንዲህ በማለት ጽፏል፡

ተጻራሪ እምነት ሁለት ተጻራሪ እምነቶች በአንድ ሰው አእምሮ ውስጥ በአንድ ጊዜ የሚያዙበት እና ሁለቱንም መቀበል ማለት ነው… በቅንነት የሚያምኑበትን ሆን ብሎ ውሸቶችን ለመናገር እና የማይመቹ የሚመስሉትን እንዲረሱ የማድረግ እና አስፈላጊ ከሆነም ብዙ ጊዜ የቆየ እና የተረሳ ቢሆንም ነባራዊውን እውነታው መካድ እና አንድ ሰው የካደውን እንዲይዝ የሚደረግበት ሁኔታ ነው- ይኸ ሁሉ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ተጻራሪ እምነቶች የሚለውን ቃል መጠቀም ቢኖርም ተጻራሪ እምነቶችን መጠቀም አስፈላጊ ነው፡፡ ቃሉን ለመጠቀም አንድ ሰው ከእውነታው ጋር መጋፈጥ ይኖርበታል፡፡ አዲስ በሆኑ ተጻራሪ እምነቶች ይህንን እውቀት ለማጥፋት እና ወሰን በሌለው መልኩ ሁልጊዜ ውሸቱ ከእውነቱ በአንድ እርምጃ ወደፊት ይሄዳል፡፡

 መማቆ ደብረጽዮን እና የእርሱ ዘ-ህወሀት ወሮበላ ዘራፊዎች ሁሉንም ነጻ ጋዜጠኞች በማሰር እና እነርሱን ለመተቸት ድፍረቱ ያላቸውን ፕሬሶች እንዲዘጉ አድርገዋል፡፡ አሁን ደግሞ የመገናኛ ብዙሀኑ የዘ-ህወሀትን እውነተኛ አፈጻጸም ለሕዝቡ በመዘገቡ ረገድ ደካማ አፈጻጸም ነው ያስመዘገቡት በማለት ቅሬታውን በመግለጽ ላይ ይገኛል፡፡ ስለዘ-ህወሀት የብዙህን መገናኛ ደካማ ስራ ቅሬታ የሚያቀርብ ከሆነ የተሳሳተ የአስተሳሰብ መስመርን መከተል ማለት ነው፡፡ አሁን ማንም ኢትዮጵያዊ (ምናልባትም ከዘ-ህወሀት ታዛዥ ሎሌዎች በስተቀር) ለዘ-ህወሀት መገናኛ ብዙሀን ትኩረት አይሰጥም፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝቦች በዘ-ህወሀት ውሸቶች፣ ቅጥፈቶች እና ተራ አሃዛዊ አሀዛዊ ቅጥፈቶች ታመዋል፣ ደክመዋልም!

መማቆ ደብረጽዮን ምንም ዓይነት አዲስ ነገር እየተናገረ አይደለም፡፡ የእርሱ ቀደምት የሆነው አስቂኙ በረከት ስምኦን ማንም ቢሆን የዘ-ህወሀትን ቴሌቪዥን ወይም ሌሎችን መገናኛ ብዙሀን አይመለከትም በማለት በየጊዜው ቅሬታውን ያቀርብ ነበር ፡፡

የኢትዮጵያ ሕዝቦች ከኢሳት ጋር ተጣብቀዋል፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝቦች ከኢሳት ሬዲዮ ጋር እራሳቸውን አዋህደዋል፡፡ በዚህ አጋጣሚ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ኢሳትን በገንዘብ እና በሌላም መደገፍ እንዲችሉ ጥሪዬን አቀርባለሁ፡፡

መማቆ ደብረጽዮን በጎንደር እና በሌሎች ሁከቱ በተቀሰቀሰባቸው አካባቢዎች ያለው ችግር  ስር የሰደደ ሙስና፣ ስልጣንን ከሕግ አግባብ ውጭ የመጠቀም እና ክልሎችን (ባንቱስታን) የሚያስተዳድሩ ባለስልጣኖች የአስተዳደር ጉድለት አለባቸው ይላል፡፡ ከዘ-ህወሀት ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የላቸውም፡፡

እውነታው ፍርጥርጥ ተደርጎ ሲታይ ግን  እንደ እንግሊዝ የቅኝ ግዛት ጌቶች እና እንደ ደቡብ አፍሪካ የጥቂት ነጮች ዘረኛ የአፓርታይድ አገዛዝ ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ ዘ-ህወሀት በክልሎች (ባንቱስታንስ) ውስጣዊ ቅኝ ግዛትን በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ ዘ-ህወሀት ለእርሱ ታማኝ የሆኑ ብቸኛ የክልሉ ኗሪ የክልል ባለስልጣናትን ፈጥሯል፡፡ ዘ-ህወሀት የእርሱን ወኪሎች፣ አሻንጉሊት የአካባቢ መሪዎች በስልጣን ላይ ያስቀምጣል፣ እናም ምዕናባዊ የእራስ ገዝ እና የእራስ አስተዳደር መብት ይሰጣቸዋል፡፡ ሆኖም ግን በክልል መንግስታት ላይ ጥብቅ የሆነ ቁጥጥር ያደርጋል፡፡ የክልል ባለስልጣኖች የእራሳቸውን መንግስት በነጻነት መምራት ይቅር እና ከዘ-ህወሀት ፈቃድ ውጭ ከቢሯቸው እንኳ መንቀሳቀስ አይችሉም፡፡ ሆኖም ግን መማቆ ደብረጽዮን በክልል የሚገኙትን ባለስልጣናት በማባረር ዘ-ህወሀትን ነጻ ሊያደርግ ይፈልጋል፡፡

መማቆ ደብረጽዮን ዘ-ህወሀት በጣም ወሳኝ እና አስፈላጊ በሆኑ የፖለቲካ እና የማህበራዊ ተቋማት ውስጥ ዘ-ህወሀት ትንሽ ወይም ደግሞ ምንም ዓይነት ቁጥጥር እንደማያደርግ ይክዳል፡፡

ይህንን ጉዳይ እንዲህ በማለት በሌላ መንገድ ላስቀምጠው፡ እ.ኤ.አ ግንቦት 2016 ተካሄደ የተባለውን የይስሙላ የፓርላሜንታሪ የቅርጫ ምርጫ መቶ በመቶ ያሸነፈው ማን ነበር? በኢኮኖሚው ላይ የበላይነት ያለው ማን ነው? በወታደራዊ ኃይሉ ሙሉ በሙሉ ቁጥጥር ያለው ማን ነው? በሲቪል ሰርቪሱ ላይ ፍጹም የሆነ ቁጥጥር ያለው ማን ነው? የደህንነት አገልግሎቱን እና የፍትህ ሂደቱን ሙሉ በሙሉ የሚቆጣጠረው ማን ነው? የአበዳሪ እና የእርዳታ ሰጭ ድርጅቶችን እንዲሁም የዓለም አቀፍ የደህንነት አቃጣሪዎችን ሙሉ በሙሉ የሚቆጣጠረው ማን ነው?

ለእነዚህ ጥያቄዎች የሚቀርብ ጥያቄ ቢኖር አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን ለማቅረብ እና በማንኛውም ጊዜ ለመከራከር እርግጠኞች ነን፡፡

በመማቆ ደብረጽዮን የተደረገ አስደናቂ የእምነት ቃል፣

ለአስር ዓመታት ያህል የዘ-ህወሀት የጎሳ ፌዴራሊዝም ስርዓት እና የእርሱ የክልል መንግስታት ሸፍጠኞች እና ስለደቡብ አፍሪካ (ባንቱስታን) ስርዓት የጭብጥ ክርክሬን ሳደርግ እና መረጃዎችን ሳቀርብ ቆይቻለሁ፡፡

በአሁኑ ጊዜ የዘ-ህወሀት ክልል (የጎሳ ፌዴራሊዝም) ስርዓት የአፓርታይድ ባንቱስታን ወይም ደግሞ መኖሪያ ሀገር ስርዓትን በሚመለከት ከደብረጽዮን አፍ ማጠቃለያ ማስረጃ አለ፡፡

አሁን ባለፈው ሚያዝያ “ባንቱስታናይዜሽን (ክልላዊነት) በኢትዮጵያ“ በሚል ርዕስ አቅርቤው በነበረው ትችት በዘ-ህወሀት በኢትዮጵያ ውስጥ የተፈጠረው እና እየተጠበቀ ያለው ስርዓት ከደቡብ አፍሪካ ጥቂት ነጮች ዘረኛ አገዛዝ ጋር እንደሚመሳሰል እና እ.ኤ.አ በ1994 የብዙሀኑን ጥቁር አገዛዝ ከመመስረቱ በፊት ከነበረው ጋር አንድ ዓይነት እንደሆነ ከምንም ጥርጣሬ በላይ አሳይቻለሁ፡፡

መማቆ ደብረጽዮን በቃለ ምልልሱ እንዲህ ብሎ ነበር፡

“በአማራ ክልል ትግራውያን አስተዳዳሪዎች ሊሆኑ አይችሉም፡፡ በጋምቤላ ውስጥ አስተዳዳሪው ትግራውያን ሊሆን አይችልም፡፡ ይህ (የጎሳ ፌዴራሊዝም ስምምነት) ለሌሎች የበላይነት ዕድል አይሰጥም፡፡ አንድ ዓይነት ጎሳ ያላቸው እራሳቸውን በእራሳቸው ያስተዳድራሉ፡፡ ትግራውያን እዚህም እዚያም የበላይ (አለቆች) ናቸው የምትል ከሆነ መሰረተቢስ ነው“ ነበር ያለው፡፡ 

ይኸ ነበር እንግዲህ በአፓርታይድ ባንቱስታን ሀገር በግልጽ የተፈጸመው!

በክዋዙሉ ሀገር ስልጣን የሚይዝ እና የመንግስቱን ስራ ሊያንቀሳቅስ የሚችለው ዙሉስ ሕዝብ ብቻ ነበር፡፡

በሲስኬይ እና በትራንስኬይ ሀገር ስልጣን የሚይዝ እና የመንግስቱን ስራ ሊያንቀሳቅስ የሚችለው የኮሳ ሕዝብ ብቻ ነበር፡፡

በቦትስዋና ሀገር ስልጣን የሚይዝ እና የመንግስቱን ስራ ሊያንቀሳቅስ የሚችለው የትስዋና ሕዝብ ብቻ ነበር፡፡

በሌቦዋ ሀገር ስልጣን የሚይዝ እና የመንግስቱን ስራ ሊያንቀሳቅስ የሚችለው የፔዲ እና የሰሜን ድበሌ ሕዝብ ብቻ ነበር፡፡

በቬንዳ ሀገር ስልጣን የሚይዝ እና የመንግስቱን ስራ ሊያንቀሳቅስ የሚችለው የቬንዳ ሕዝብ ብቻ ነበር፡፡

በጋዛንኩሉ ሀገር ስልጣን የሚይዝ እና የመንግስቱን ስራ ሊያንቀሳቅስ የሚችለው የሻንጋን እና የሶንጋ ሕዝቦች ብቻ ነበሩ፡፡

በክዋ ክዋ ሀገር ስልጣን የሚይዝ እና የመንግስቱን ስራ ሊያንቀሳቅስ የሚችለው የባሶቶስ ሕዝብ ብቻ ነው፡፡

ሆኖም ግን በደቡብ አፍሪካ የመጨረሻውን ስልጣን የያዘው ማን ነው? የጥቂት ነጮች የአፓርታይድ አገዛዝ ነው፡፡

በደቡብ አፍሪካ ያሉ ሕዝቦች ነጻነት ምን ያህል ነጻ ነው?

እንዲያው ለነገሩ ያህል ዘ-ህወሀት ነጻ ናቸው ይላል፡፡

የኢትዮጵያ 9ኙ ባንቱስታንስ ምን ያህል ነጻ ናቸው? ዘ-ህወሀት እንዲያው ለነገሩ ያህል ነጻ ናቸው ይላል፡፡

በእውነተኛ የፌዴራሊዝም ስርዓት ዘር፣ ጎሳ፣ ጾታ፣ ኃይማኖት፣ ርዕዮተ ዓለም፣ ወዘተ የፖለቲካ መብቶችን ከመተግበር ጋር በተያያዘ መልኩ ምንም ዓይነት ጠቀሜታ የላቸውም፡፡

ለምሳሌም ያህል ሂላሪ ክሊንተን ከኒዮርክ የዩኤስ አሜሪካ የምክር ቤት አባል ከመሆኗ በፊት የሞያ ህይወቷን ያሳለፈችው በአርካንሳስ ግዛት ነበር፡፡ ሚት ሮምነይ የተወለደው በሚችጋን ሲሆን የኮሌጅ ትምህርቱን የተከታተለው በኡታህ ሆኖ የማሳቹሴትስ አስተዳዳሪ ሆኗል፡፡ ባራክ ኦባማ የተወለደው በሀዋይ ሲሆን የኮሌጅ ትምህርቱን የተከታተለው ደግሞ በካሊፎርኒያ፣ በኒዮርክ እና በማሳቹሴትስ ሆኖ ከኢሊኖይስ የዩኤስ አሜሪካ የምክር ቤት አባል ለመሆን በቅቷል፡፡

የዘ-ህወሀት የጎሳ ፌዴራሊዝም ስርዓት የቅርብ እና ታላቅ የደቡብ አፍሪካ አፓርታይድ አገዛዝ ተቀጽላ መሆኑን መማቆ ደብረጽዮን ማስተባበል የማይቻል ማስረጃ ያቀረበልኝ ስለሆነ አመሰግነዋለሁ፡፡

ኃይል ያለው ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ነው፡ የዘ-ህወሀት መገዳደር እርባናቢስ ነገር ነው፣

በዘ-ህወሀት አገዛዝ ላይ መጠነ ሰፊ እየሆነ እና እየተስፋፋ የመጣው ሕዝባዊ እምቢተኝነት እና መገዳደር እልቂትን በመፈጸም፣ የተዛባ የማወናበጃ መረጃ በማቅረብ ወይም ደግሞ በሌላ በማንኛውም መንገድ የሚቆም አይደለም፡፡

በአንዲ ዊሊያም የግጥም ስንኞች ጸሀይ ሰማይን ትለቃለች ብሎ መናገር አይቻልም/ህጻንን እንዳያለቅስ መጠየቅ አይቻልም/የውቅያኖስን ማዕበል ወደ ዳርቻው እየገፋ እንዳይመጣ ለማስቆም አይቻልም/

እንደዚሁም ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ የኢትዮጵያ ሕዝቦች የሰብአዊ መብቶቻቸውን እንዳይቀዳጁ እና የሕግ የበላይነት የተረጋገጠባት፣ የማትከፋፈል፣ ነጻነት እና ለሁሉም ፍትህ የሰፈነባት ዴሞክራሲያዊ የሆነች ሀገርን እንዳይመሰርቱ ማስቆም አይቻልም፡፡

የኢትዮጵያን ሕዝብ ማስቆም በፍጹም አይቻልም!!!

ምክንያቱ ደግሞ ግልጽ እና ቀላል ነው፡፡

እ.ኤ.አ በ2008 ዓለም አቀፍ ንቃት የተፈጠረ መሆኑን ዥብግኒው ብርዜንስኪ እንደተናገሩት ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ በአሁኑ ጊዜም በኢትዮጵያ ውስጥ የፖለቲካ መነቃቃት ተፈጥሯል፡፡

ብርዜንስኪ እንዲህ የሚል የመከራከሪያ ጭብጥ አቅርበዋል፡

በሰው ልጆች ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሁሉም የሰው ልጆች ሁሉ የፖለቲካ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ናቸው፣ የፖለቲካ ንቃታቸው ከፍ ብሏል እናም የፖለቲካ ተሳትፏቸው እየጨመረ የመጣበት ሁኔታ ተከስቷል…የዓለም አቀፉ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውጤት በዓለም አቀፍ ደረጃ ለበርካታ ዘመናት በቅኝ ግዛት ትዝታ እና በአገዛዝ የበላይነት ተቀፍድዶ የኖረው ሕዝብ በአሁኑ ጊዜ ለግል ክብር መጨመር፣ ለባህል መከበር እና ለኢኮኖሚ ዕድሎች ጥያቄዎችን በማቅረብ ላይ በመገኘቱ ምክንያት ነው…ለክብር የሚጠየቀው ዓለም አቀፍ ጥያቄ ለዓለም አቀፉ የፖለቲካ መነቃቃት ዋና መሰረታዊ ክስተት ነው…ያ መነቃቃት ማህበራዊ መጠኑ ግዙፍ እና ስር ነቀቀል የፖለታካ ጥያቄ ነው… ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ ዓለም አቀፍ የሬዲዮ፣ ቴሌቪዥን ስርጭት እና እየጨመረ የመጣው የኢንተርኔት አገልግሎት የፖለቲካ ወይም የኃይማኖት ጉዳዮችን መስመር እያስያዘ ለመብቱ እና ለወደፊቱ ብሩህ ተስፋ ሲል የጋራ ግንዛቤ ያለው ማህበረሰብን በመፍጠር ላይ ይገኛል፡፡ እነዚህ ኃይሎች ዓለም አቀፍ ወሰንን በመሻገር በአሁኑ ጊዜ ባሉት መንግስታት እንደዚሁም ባለው ዓለም አቀፍ ተዋረድ ላይ መገዳደሮችን በመፍጠር ላይ ይገኛል… 

የሶስተኛው ዓለም ወጣቶች በተለይ እረፍትየለሽ እና በቀልተኞች ናቸው፡፡ እንደዚሁም ሁሉ አሁን ያሉበት የሕዝብ የመጨመር አብዮትም የፖለቲካ የጊዜ ፈንጂ ቦምብ ነው…የወጣቶቹ የወደፊት አብዮተኞች የመሆንም ሁኔታ በርካታ ተማሪዎች የሶስተኛ ደረጃ የከፍተኛ ትምህርት በታዳጊ ሀገሮች ተከታታይ እና በምሁራን ካምፕ ውስጥም የሚገኙ በመሆናቸው የሁኔታው መከሰት ጎልቶ በመውጣት ላይ ይገኛል… 

የዓለም ዋና ዋና ኃይሎች፣ አዲሶቹ እና የቀድሞዎቹ አስደናቂ ከሆነ እውነታ ጋር ተጋፍጠዋል፡ የጦር ኃይላቸው አደገኛነት ከምንጊዜውም በላይ የበለጠ ሆኖ የሚገኝ ቢሆንም የፖለቲካ መነቃቃት በተፈጠረበት ማህበረሰብ ላይ በመግባት ሁኔታውን ለመቆጣጠር መሞከር በጣም ዝቅተኛ የሆነ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ አቅምን የሚገድብ ስለሆነ ማለት ነው፡፡ ጉዳዩን በግልጽ ለማስቀመጥ በዱሮ ጊዜ አንድ ሚሊዮን ሕዝብ በአካል ከመግደል ይልቅ አንድ ሚሊዮን ሕዝብን መቆጣጠር ይቀል ነበር፡፡ በአሁኑ ጊዜ ግን አንድ ሚሊዮን ሕዝብን ከመቆጣጠር ይልቅ አንድ ሚሊዮን ሕዝብን መግደል መቁጠር ከሚያስችል በላይ ቀላል ነገር ነው፡፡   

ለዘ-ህወሀት የተገኙት ትምህርቶች ቀላል እና እንዲህ የሚሉ ናቸው፡

70 በመቶ ያህሉን የሕዝብ ብዛት የሚይዙት የኢትዮጵያ ወጣቶች ሕዝባዊ የእምቢተኝነት አመጹን እና አብዮቱን የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ መሪዎች እና ሌሎች ቀሪዎች ሳይሆኑ ወጣቶቹ በመምራት ላይ ይገኛሉ፡፡

የኢትዮጵያ ወጣት ሕዝቦች የሰብአዊ ክብር እና ሰብአዊ መብቶች እንዲከበሩ በመጠየቅ ላይ ናቸው፡፡ ይኸ ነገር ምንም ዓይነት ድርድር ሊቀርብበት የሚችል ጉዳይ አይደለም፡፡

የኢትዮጵያ ወጣት ሕዝቦች እረፍትየለሾች እና በቀልተኞች ናቸው፡፡ ምንም ዓይነት ትዕግስት የላቸውም፡፡ እንደ እቃ ሊገዙ ወይም ሊሸጡ አይችሉም፡፡

የኢትዮጵያ ወጣት ሕዝቦች በዘ-ህወሀት የጭቆና አገዛዝ የሁለተኛ ዜግነት ባርነት ተጭኖባቸው የሚገኙ ስለሆነ በዚህ መቅነቢስ ዘረኛ ስርዓት ታመዋል፣ ደክመዋል፡፡

የኢትዮጵያ ወጣት ሕዝቦች የዘ-ህወሀት መሪዎች ባልሰለጠነው አውሪያዊ ምዕናባቸው ከሚስሉት በእጅጉ የበለጠ ስረነቀል ለውጥን ናፋቂ እና ለተግባራዊነቱም ሌት ከቀን የሚታገሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ናቸው፡፡

ዘ-ህወሀት አንድ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንን ከመቆጣጠር ይልቅ አንድ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንን መግደል በእጅጉ ይቀለዋል፡፡

የዘ-ህወሀት ወታደራዊ ኃይል አደጋ ጣይነት ከምንጊዜውም በላይ ከፍተኛ ነው፣ ሆኖም ግን ከኢትዮጵያ ወጣቶች ኃይል ጋር ስናነጻጽረው በአውሎ ነፋስ ዉስጥ አንዳለ የላባ ያህል ነው፡፡

እንግዲህ የዘ-ህወሀት ዕድል እንደዚህ ነው፡፡

ዘ-ህወሀት ባዶ ይሆናል እናም ወደታሪክ ቆሻሻ መጣያ ቅርጫት ይጣላል፡፡

ዘ-ህወሀት ማወቅ ያለበት አንድ የማይሞት እና የማይበገር ሕግ አለ፡፡

ያንን ሕግ ያቀናበሩት ማህተመ ጋንዲ ሲሆኑ ሕጉ እንዲህ የሚል ነው፡

“ጨቋኞች እና ገዳዮች ለጊዜው የማይበገሩ መስለው ይታያሉ፣ ሆኖም ግን በመጨረሻ ሁልጊዜም ቢሆን ይወድቃሉ፣ አስቡት ሁልጊዜ፡፡“

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!  

መስከረም 17 ቀን 2009 ዓ.ም

ከታሪክ መድረክ – ለመሆኑ የብሔር ብሔረሰብ ጭቈና በኢትዮጵያ ነበር ወይ: – ከኀይሌ ላሬቦ

 

ከኀይሌ ላሬቦ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የዘውገኝነትንና[1] የዓለም-አቀፍነትን ያስተዳደር ርእዮተ ዓለም የሚያራምዱ አንጃዎች ኢትዮጵያ የብሔር ብሔረሰቦች መታጐርያ እስር ቤት ናት እያሉ የሚሰብኩት ስብከት ተደማጭነትን ከማግኘት አልፎ፣ ብዙዎችን አገርወዳዶች ሳይቀሩ ጭምር፣ እያወነበደም እየማረከም ነው። የሰባኪዎቹ አቋም የግል ጥቅማቸውን የማራመድ ዕቅድ ካላቸው ይጠቅማቸው ይሆናል እንጂ፣ በኢትዮጵያ ታሪክና በየጊዜው በተፈጸሙት ተጨባጭ የመንግሥት ተግባራትና መመርያዎች አይደገፍም። ለዘመናት በየጊዜው የተነሡት የርስ በርስ ጦርነቶችና የሕዝብ ፍልሰቶች፣ የሃይማኖቶች መስፋፋትና እነዚህም ድርጊቶትች ያስከተሏቸው ግጭቶች፣ በተለያየ ጊዜ የማዕከላዊ መንግሥት መፍረስና መልሶ መቋቋም፣ በብዙ መልክ አገሪቷን የጐዱ ቢሆኑም፣ በሌላው አኳያ ደግሞ የኢትዮጵያን ሕዝብ ከማቀራረብ አልፈው አዋህደዉታል። እነዚህ ክሥተቶች ከንግድ፣ የእምነት ማዕከላትን ለመሳለም በየጊዜው ከሚደረጉት የምዕመናን ንግደቶችና ከጋብቻ ጋር ሁነው፣ የኢትዮጵያን ሕዝብ በታሪክ፣ በደም፣ በቋንቋ፣ በባህል አስተሳስረው እንደሰርገኛ ጤፍ ስለደበላለቁት፣ በዘሩ ጭንጩ የሆነ ዘውግ በርግጥ በኢትዮጵያ ውስጥ አለ ማለት እንደዘበት መቈጠር ይኖርበታል። እውነት ነው እያንዳንዱ ዘውግ ራሱን የሚገልጥበት የተለየ የአካባቢው ቋንቋ አለው። ቢኖረውም ግን ተናጋሪው ሕዝብ ካንድ እንጅላት ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ እንዳልሆነ ግልጽ ነው። ሁሉም ለሚኖርበት መጤ፣ አለበለዚያም ከሌላ አገር ከፈለሰ መጤ ጋር  የተቀላቀለና የተዋሐደ ነው። ስለዚህም የኢትዮጵያ ሕዝብ በጠቅላላ ሲታይ፣ አንዱ የሌላው የሥጋው ቊራጭ፣ የደሙ ፈሳሽ ነው ቢባል መቼም በምንም መልክ የማይካድ ሐቅ ነው።

nat-m-sa

አገሩን የገዛው እያንዳንዱ ተከታታይ ሥርወ መንግሥት የአገሪቷ የመሬት ቈዳ ይጥበብም ይስፋም ሕዝቧን በነፃነት፣ ለማንም ሳያደላ የበላይነትና የበታችነት ስሜት ሳያሳይ በእኩልነት አስተዳደሯል። ከዚያም ሕዝቡ ራሱ ከነጋሹም ክፍል ጋር ሆነ፣ እርስ በርሱ በመጋባትና በመወላለድ ተደባልቆ ተዋሀዷል። ከዚያም አልፎ፣ አንድ የኢትዮጵያውያን የጋርዮሽ ሀብት የሚያሰኝ የራሱን ቋንቋ ለመፍጠር ችሏል። ከነዚህም እሴቶች የተነሣ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከማንም የአፍሪቃ ሕዝብ በላይ የሥነ-ልቡና ኩራትና ከማንአንሼነት መንፈስ ለማዳበር በቅቷል። በዘመናዊ መልክም የተቋቋመችው ኢትዮጵያ ለሁሉም ሕዝቧ የነጻነትና የእኩልነት ማኅደር እንጂ የማንም እስርቤት አልነበረችም። ጨቋኝና ተጨቋኝ ብሔረሰብም ታይቶባት አይታወቅም ማለት ይቻላል።

ኢትዮጵያ ከሌላው የዓለም አህጉራትና ሕዝብ በተለይም ከአፍሪቃዎቹ የምትለይበት አያሌ መሠረታዊ እውነቶች አሉ። አንደኛ፣ አብዛኛው፣ (እውነቱን ለመናገር ሁሉም ማለት ይቀላል) የዛሬ የአፍሪቃ አገሮችና መንግሥታት ህልውናቸውንና ምንነታቸውን ያገኙት በውጭ አገር መጤዎች ሲሆን፣ ኢትዮጵያና የኢትዮጵያ መንግሥት ግን አላንዳች የውጭ እርዳታ ባገሩ ተወላጆች እጅ የተገነቡ ናቸው። የአክሱም ሐውልቶችና ቤተመንግሥቶች፣ እንዲሁም በየጊዜው የተሠሩ ሕንጻዎች፣ የአሁኗ መናገሻዋ አዲስ አበባ፣ ሌሎችም ከተሞችና የግል ሕንጻዎች የታነጹት በራሳቸው በኢትዮጵያውያን እንጂ ከውጭ መጥተው አገሪቷን በያዙ ኀይሎች አይደሉም[2]። ይኸም ማለት የውጭ አገር ሰዎች በሠራተኛነት አልተቀጠሩም አይባልም። ከመሐንዲሶች እስከተራ ሠራተኞች ባገሪቷ ውስጥ ተቀጥረው ሠርተዋል።

 

ይልቅስ ይኸ ራሱ ማለትም ምዕራባውያንንና የሌላውን አገር ዜጋ ቀጥሮ ማሠራት፣ አንድ ራሱን የቻለ የኢትዮጵያና የኢትዮጵያዊነት መለዮ ነው ማለት ይቻላል። ያፍሪቃ አገሮች ነጻነታቸውን እስካገኙበት ጊዜ ድረስ፣ መጤዎቹ የውጭ አገር ሰዎች [ምዕራባውያኑም ሆኑ እስያዉያኑ] ባገሩ ውስጥ ይኖሩ የነበሩት የገዢና ያስተዳዳሪ አለበለዚያም የከበርቴ ክፍል ሁነው ነበር። በነዚህ አገሮች፣ ፈረንጆችን በአዛዥነት ቦታ እንጂ፣ ባገሩ ተወላጅ ሲታዘዙ ማየት ድንቅ ግሩም ስለነበር አይታሰብም፣ አይታለምም ማለቱ ይቀላል። ያገሩ ተወላጅ የተመደበው፣ የጊዜውን አነጋገር ብንጠቀም፣ ለውሃ ቀጂነት፣ ለዕንጨት ለቃሚነትና ፈላጭነት ብቻ ነበር ማለት ይቻላል።  በኢትዮጵያ ግን ፈረንጅ በታዛዥነት እንጂ በአዛዥነት ቦታ ታይቶ አይታወቅም ቢባል ሐሰት አይደለም። ስለዚህም ባንድ የአፍሪቃ ክፍል በሆነ አገር ውስጥ ይኸ የሥልጣን ተገላቢጦሽ መፈጠሩ፣ አገሩን የጐበኙትን ፈረንጆች በጣም እንዳደናገራቸው ግልጽ ነበር።  ጆን ቦይስ የተባለ እንግሊዛዊ ከእንግሊዝ ምሥራቅ አፍሪቃ (ማለትም ከዛሬዋ ኬንያ፣ ኡጋንዳና ታንዛንያ) ወደአዲስ አበባ እንደደረሰ፣ በጣም እንግዳ የሆነብኝ ነገር ቢኖር፣ “አንድ አፍሪቃዊ [ማለትም ጥቊር] የሆነ ሰው ቤቱን እያነፀለት ያለውን ነጩን ሲያዘው” ማየቴ ነበር ይላል። ከአክሱም ሐውልት ጀምሮ አገሪቷን ሆነ፣ የአገሪቷንም ታሪክ ሠሪዎችና ገንቢዎች ኢትዮጵያኑ ራሳቸው ናቸው። ይኸ አባባል በዘመነ መሳፍንት ፈርሳ እንደገና በዘመናዊ መልክ የተገነባችውን የዛሬዪቱን ኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ከገናናው ከአክሱም መንግሥት እስከዘመነ መሳፍንት ድረስ የነበረውን መላውን ያገሩን ታሪክ ሁናቴ ጭምር ይመለከታል።

 

በሁለተኛ ደረጃ የኢትዮጵያ ግንባታና ታሪክ ካንድ ዘውግ ወይንም ካንድ አካባቢ በተወጣጡ ሰዎች የተካሄደ ሳይሆን ከብዙ ነገድና አካባቢ የመጣ ሕዝብ ድርጊት ነው። ታሪኩን በአክሱም መንግሥት ከጀመርን፣ አንደኛ አክሱም የኢትዮጵያ ክፍል መሆኗ በጥያቄ ውስጥ የሚገባ አይደለም። ልክ ሮም የተባለችው ከተማ ከኢምንትነት ተነሥታ የመላው የኢጣልያን ባሕረገብ ምድር የበላይ ሁና እንደተቈጣጠረች ሁሉ፣ አክሱምም በጊዜዋ ከከተማነት አልፋ፣ አብዛኛውን የዛሬዎቹን የኢትዮጵያን ግዛቶች እስከሱማሌ፣ ከዚያም ቀይ ባሕር አልፋ የመንንና ደቡብ ዐረብን፣ በሰሜን ደግሞ እስከግብፅ ወሰን ድረስ ትገዛ እንደነበር የአዱሊስ ዙፋን በሚል ሐውልት ላይ የተቀረፀው ጽሁፍ ይገልጥልናል[3]። ልክ ሮም የሮማዉያን መንግሥት መናገሻ ከተማ እንደነበረች ሁሉ፣ አክሱምም በስሟ የሚጠራው መንግሥት ዋናው ከተማ ስም ነበረች[4]

 

የአክሱም ሥልጣኔና ግዛት የሚነግሩን ግልጥ ነገር ቢኖር በመንግሥታቸው ሥር የነበሩት ነዋሪዎች፣ ልክ እንደሮማው መንግሥት በቋንቋም ሆነ በሥልጣኔ ደረጃ የተለያዩ እንደነበርና፣ ንጉሥም እንደዋና ተልእኮው አድርጎ ይመለከት የነበረው በየቦታው ሰላም ማስፈን፣ ንግድ ማስፋፋት፣ ማንም በሌላው ላይ ግፍ እንዳይፈፅም ከበላይ ሁኖ መቈጣጠር ነበር። ግዛታቸው ሰፊ ከመሆኑ የተነሣ፣ አገሩን በጸጥታና በሥነሥርዐት ስላስተዳደሩ፣ ግፍና ዐመፅ ስላራቁ፣ ንግድ እንዲስፋፋ ጥርጊያውን ስላመቻቹ፣ ከያንዳንዱ ኅብረተ-ሰብ ግብር ይጠብቃሉ። ይኸ ደግሞ በየትም ያለ የዜግነት ግዳጅ ስለሆነ የአክሱሞችን መንግሥት ሆነ፣ በነሱ ምትክ የመጡትን የኋለኞቹን ሥርወመንግሥታት፣ ጨቋኞች ወይንም በዝባዦች አያሰኛቸውም። መንግሥት ነዋሪዎቹ በኢትዮጵዊነታቸው በእኩልነትና በነፃነት [ማለትም በሌላ የውስጥ ኀይል ሳይጨቈኑ በባዕድም ሳይደፈሩ) እንዲኖሩ በማድረግ የዜግነት መብታቸውን እንዳስከበረ ሁሉ፣ ለእነሱም ግብር መክፈል የመንግሥትን ሥልጣን  መቀበላቸውንና ላገሩ ሕግ የሚታዘዙ መሆናቸውን ከሚገልጡበት መሣርያዎች ዋነኛው ነው።

 

የአክሱም ሥልጣኔ በአፍሪቃ ክፍለአገር ከመላው ጥቁር ሕዝብ የሚለይበት ሌላም ነገር አለ። ሥልጣኔው ከራሱ ከአካባቢው ሕዝብ በሂደት የፈለቀና የመነጨ እንጂ ባዕዳን መጤዎች ከፈለሱበት እናት አገራቸው ይዘው የመጡት ወይንም በአክሱም ከሰፈሩ በኋላ የፈጠሩት እንዳልሆነ በእጃችን ያሉት ማስረጃዎች ይገልጡልናል። ይኸንን የሚፃረር አሳብ የሚደግፍ እስካሁን አንድም ማስረጃ የለም። በሌላው አንጻር፣ አክሱሞች ወደሌላው አገር ሂደው ሥልጣኔአቸውን እንዳስፋፉ የተውልን የሕንፃ፣ የጽሑፍ ቅርሶች ይመሰክሩልናል። ሐቁ እንደዚህ ሁኖ እያለ፣ የኢትዮጵያን ታሪክ ጥናት እየተቈጣጠሩት የነበሩት (አሁንም እየተቈጣጠሩ ያሉት ማለት እንችላለን) አውሮጳያን፣ ለጥቁር ሕዝብ ከነበራቸው ንቀት የተነሣ፣ “የአክሱም ሥልጣኔ ከየመንና ከደቡብ ዐረብ ወደኢትዮጵያ ፈልሶ ባገሩ ውስጥ በየጊዜው የሰፈረው ሳባውያን በተባለ ስም የሚጠራው የሴማዊ ሕዝብ ሥልጣኔ እንጂ ካገሩ ነባር ጥቁር ሕዝብ የፈለቀ አይደለም። ይኸም አስገራሚ ሥልጣኔ ሊሞት የበቃው፣ ፈጣሪዎቹ ሴማውያን ከአገሩ ጥቁር ሕዝብ ጋር ከመደበላለቃቸውና ከመወላለዳቸው የተነሣ ነው፤ መጤዎቹ የሰውነታቸው መልክ እየጠቈረ በሄደ ቊጥር፣ አእምሯቸው እየደነዘ፣ የመፍጠር ችሎታቸውም በዚያው ልክ አብሮ ሊደበዝዝና ሊጠፋ ቻለ” ይላሉ። እነዚህ ምሁራን ነን ባዮች፣ ከዚህ ዐይነቱ የተዛባ አስተሳሰብ ተነሥተው የኢትዮጵያን ሕዝብ ሴማውያንንና አፍሪቃውያን እያሉ ለመከፋፈል በቅተዋል። ሴማዉያን ከቀይባሕር ማዶ ከዐረብ አገር የመጡና፣ የአክሱምን ሥልጣኔ የገነቡ ናቸው። ጥቁሮቹን አፍሪቃውያን ደግሞ እነሱ ባወጡት መለኪያ፣ ኩሳውያንና አባይ-ሰሐራውያን ብለው ከፋፍለው ሲያበቃ፣ እነዚህ ለአክሱማውያን ሥልጣኔ ያደረጉት አስተዋፅኦ ኢምንት ነው ይላሉ። በከፍተኛ ዕውቀት የዳበረ የዛሬ ሰው ይኸንን ሲሰማ ነጮችን አምባገነንታቸው ምን ያህል እንዳሳበዳቸው ሊገነዘብና በነገሩ ሊያፌዝበት፣ ካልሆነም ሊስቅበትም ሆነ ሊያዝንበት ይቃጣ ይሆናል። ግን ባገራችን ሌላው ቀርቶ ተምረናል የሚሉትንም እንኳን ሳይቀር አሳምኖ፣ እነርሱም በበኩላቸው ሕዝቡን እስከማወናበድና እርስበርስ እስከማፋጀት አድርሰዋል ማለቱ የለዘበ አነጋገር ይመስለኛል።

 

ሮም በ፬፻፸፮ ዓ. ም. ላይ ስትወድቅ፣ የአውሮጳውያን የሥልጣኔ መሠረት ጥላ ነበር። አክሱምም በ፱፻ ዘመን አካባቢ ላይ ፍጻሜዋን ስታይ ለኢትዮጵያዉያን ያደረገችው ልክ ይኸንኑ ስጦታ ነው። ሁኖም ሮም የግዛቷ አካል ያደረገቻትና የሥልጣኔዋ ዋና ወራሽ የሆነችው ኢጣሊያ ግን፣ ከሮም ውድቀት በኋላ የፈረሰውን አንድነቷን እስከ፲፰፻፸፪ ዓ.ም. ድረስ መልሳ ማቋቋም አልቻለችም። ኢጣሊያን ከሮም ውድቀት በኋላ የተከተላት የብዙዎች ነገዶች[5] ወረራ ሲሆን፣ ውጤቱ አገሩን መከፋፈልና የአካባቢው የኀይለኞች መንግሥታት መፈንጫ ሜዳ ሁና መቅረት ነው። በኢትዮጵያ፣ የአክሱማውያን መውደቅ ያስከተለው የድብልቅልቅና የጨለማ ዘመን የብጥብጥ፣ የሕገ-አልባነትና የሁኬት ጊዜ እንደነበር ቢነገርም፣ በሌላው በኩል ደግሞ ከፍተኛ የሕዝብ እንቅስቃሴ፣ መፈላለስና መዘዋወር የታየበት ወቅት ነበር። ሁናቴው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲደበላለቅና ርስበርሱ እንዲተሳሰር በጣም ረድቷል ቢባል ሐቅ ነው። ቀጥሎም ሥልጣኑን የተረከበው ዛጐ በመባል የሚታወቀው የአገዎች ሥርወ መንግሥትም፣ የአክሱማውያንን ሥልጣኔ እንደባዕድ ሳያይ፣ ልክ የራሱ እንደሆነ አስመስሎ ከመቀጠል አልፎ የግሉን ጨምሯል። አገዎች ግብርናን በማዳበር ረገድ፣ ለመጀመርያ ጊዜ አላምደው ወይንም ከሌላ ጋ አምጥተው ለድፍኑ ዓለም ያበረከቷቸው እንደጤፍ፣ ዘንጋዳ፣ ስንዴ፣ ገብስና ባሕርማሽላ የመሳሰሉ የእህልና የዕፀዋት ዐይነቶች በአፍሪቃ ክፍለአገር ውስጥ በመፍጠር ችሎታቸው ወደር የሌለው ሕዝብ ነው አሰኝቷቸዋል[6]። እንደላሊበላ የመሰሉ የነገሥታቱ ሕንጻም ቢሆን የድፍኑ ዓለም መደነቂያና መገረሚያ ሁኗል። በአዱሊስ ሐውልት ላይ እንደተጻፈው፣ የአገው ምድር የአክሱሙ ንጉሥ ካስገበራቸው አገሮች አንዱ ቢሆንም፣ አገዎች የተረከቡት ግዛት ከአክሱም ያነሰ ነበር። ሰለሞናዊ በተባለው ሥርወ መንግሥት እስከተተኩ ጊዜ ድረስ፣ አገሩን ያስተዳደሩት፣ እንደአክሱሞቹ ሕዝቡን በጐሣና በእምነት ሳይለዩ፣ በፍትሕና በርትዕ ነበር። ንግድ እንዲስፋፋ፣ ሰላም እንዲሰፍን፣ ሌላው ቀርቶ፣ አማኞች ንግደታቸውን አለችግር እንዲወጡ ማመቻቸት[7]ና የበላይ ሁኖ መቈጣጠር እንደዋና ተግባራቸው ያዩ እንደነበር ታሪካቸው ይመሰክራል።

 

የዛጐ መንግሥት በአገዎች እንደተቋቋመ፣ የሰለሞኖች መንግሥት የተመሠረተው ታሪክ እንደሚነግረን ከሆነ አማራ[8] ከተባለው አገር በመጣ ንጉሥ ነው[9]።  አማራ ደግሞ ያነ የሚያመለክተው የተወሰነ አካባቢ ሲሆን፣ ክልሉም በምዕራብ በአባይና በመጋቢው የበሽሎ ወንዝ፣ በሰሜን በአንጎትና ላስታ፣ በደቡብ በወንጭት ወንዝ፣ በምሥራቅ ደግሞ ወደደንከል በረሃ በሚደርሰው ሰፋፊ ገደላንገደል የተከበበውን ምድር ነው። ከዚህ የምንማረው አሁን አማራ ብለን የምንጠራቸውን እንደነጐጃም፣ በጌምድር፣ ሸዋ እንዲሁም የወሎን አንዳንድ ክፍል እንደማያካትት ነው። በዚህ ግዛት ውስጥ በሚኖሩት የአገሩ ተወላጆች [ማለትም የአማሮች] አፈታሪክ መሠረት የአማራ ሕዝብ አሁን ወዳለበት የመጣው በቀጥታ ከአክሱም ነው። የቃሉም ትርጒም “ነፃ ሕዝብ” ማለት እንደሆነ ይነገራል።  ይሁንና አፄዎቹ “ንጉሠ አምሐራ” የሚል ስያሜ ቢኖራቸውም፣ ጐንደር የኢትዮጵያ ቤተመንግሥት ቋሚ መናገሻ ከተማ ሁና እስከተቈረቈረችበት እንደአ.አ. እስከ ፲፮፻፴፪ ዓ. ም. ጊዜ ድረስ፣ ነገሥታቱ ይኖሩት የነበረው ከቦታ ወደቦታ እየተዘዋወሩ፣ አብዛኛውን ጊዜ በደቡብ ባሉት እንደነይፋት፣ ሸዋ፣ ደዋሮና ፈጠጋር በመሳሰሉት አገሮች እንጂ፣ መናገሻቸውን ክልሉን በዘረዘርነው የአማራ አገር አድርገው አያውቁም። ምናልባትም ከመጀመርያዎቹ በስተቀር፣ የአብዛኞቹ ነገሥታት አማራነትም ቢሆን እጅግ በጣም አጠያያቂ ነው ማለት ይቻላል።

 

ከዚህ በተጨማሪ፣ አማርኛ የተባለው ቋንቋው ራሱ ምንጩና መነሻው አማራ ከተባለው ግዛት ውስጥ ይሁን እንጂ፣ ያደገውና የዳበረው ግን በጠቅላላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ባደረገው አስተዋፅኦ ነው። አማርኛ በመባል ከተወለደበት አገር ጋር ተቈራኝቶ ቢቀርም፣ እውነቱ ግን በየአካባቢው የሚገኙትን የተለያዩ ቋንቋዎች ቃላትንም ሆነ ሰዋስዋዊ አገባብ በመከለስና በመደቀል፣ በማዳበልና በማቀያየጥ አዋህዷቸውና አመሳስሏቸው የተውጣጣ የኢትዮጵያውያን የጋርዮሽ ቋንቋ ነው። የቋንቋ ጥናት ምሁራን አነጋገር ብንጠቀም፣ አማርኛ ጥንተ ዘሩ የሴማውያን ቋንቋዎች ከሚባሉት ክፍል ቢሆንም፣ ሐቁ ግን በኩሻውያን ቋንቋዎች ቃላትና ሰዋስዋዊ አገባብ ከሚጠበቀው በላይ ተበርዟል። ስለዚህም ከማንኛውም የኢትዮጵያውያን ቋንቋ ይበልጥ፣ የመላው ያገሪቱ ሕዝብ የትብብር ፍሬ ስለሆነ፣ እውነተኛ የኢትዮጵያውያን የጋራ ሀብት ነው ማለቱ የሚቀል ይመስለኛል። ይኸንንም በመገንዘብ ነው እንግዴህ ቋንቋው ባገሪቷ ውስጥ ያሉትን የልዩ ልዩ ብሔረ-ሰቦችን ድምፅ ለማስተናገድ ሲል ጥንት ከአባቱ ግእዝ በወረሳቸው ፊደላት ላይ አስፈላጊነቱን እያየ ሌሎች አዳዲስ ሊፈጥርና ሊጨምር የበቃው። ስለዚህም አብዛኛው የአማርኛ  ተናጋሪ የሚገኘው ከጥንት ትውልዱ ክልል ውጭ ነው። በላስታ፣ በሸዋ፣ በበጌምድር፣ በወሎና፣ በጐጃም ግዛቶች የኩሳውያንን ቋንቋዎች ተክቶ ይገኛል። ቋንቋዎቻቸው የሴማውያን ነበር በተባሉት  አርጐባና ጋፋት በመባል በሚታወቁት አገሮች ደግሞ የአፍ መክፈቻቸው ሁኖ ቀርቷል።

 

በእነዚህ አገሮች አማርኛ እናት ቋንቋቸው ቢሆንም፣ እንደአ.አ. በ፲፱፻፺ዎቹ ዓ.ም. ላይ፣ አማሮች ናችሁ የሚል ስያሜ በግድ በላያቸው ላይ እስከተለጠፈባቸው ጊዜ ድረስ፣ ራሳቸውን ይጠሩ የነበሩት በሚኖሩበት የአገርና የቦታ ስሞች ጐንደሬ፣ ጐጃሜ፣ ሸዌ፣ መንዜ በመባል እንጂ አሁን በተሰጣቸው አማራ በሚል ብሔረሰብነታቸው አልነበረም። ታሪክም ራሱ የሚያመለክተው ይኸንኑ ነው። ከ፲፬ኛ ዘመነ ምሕረት ጀምሮ እስከ፲፰ኛ ዘመን  ድረስ ባሉት ጊዜ ውስጥ በተጻፉት በታሪከ ነገሥታትም ሆኑ፣ እስከ፲፱ኛ ዘመነ ምሕረት ድረስ በተደረሱት በክርስቲያኖቹና በእስላሞቹ መዛግብት ውስጥ “አማራ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው አሁን ጊዜ በወሎ ግዛት ውስጥ የሚገኘውን የቦታ ስም ብቻ ነው። በምንም መንገድ ካንድ ከተወሰነ ብሔረሰብ ጋር የሚያይዝ ምንጭ የለም።

 

እንዲሁም ከዚሁ ጋር በማያያዝ የምጨምር ነገር ቢኖር፣ ባሁኑ አጠራር ኦሮሞ፣ ድሮ ደግሞ ጋላ በመባል የሚታወቀው ሕዝብ ሁናቴም ልክ ይኸንኑ ይመስላል። የወያኔ መንግሥት በአፄ ምኒልክ ዙፋን እንደተቀመጠ ቦረን፣ ሜጫ፣ ቱለማ፣ ኢቱና ጉጂ በመሳሰሉት ስሞች ራሳቸውን ይጠሩ የነበሩትን ብሔረ-ሰቦች ፣ የፈጠራ ስም ሰጥቷቸው ኦሮሞ በሚባል በጋራ መጠርያ ስም ሥር እንዲካተቱ አስገድዷቸዋል[10]። ይኸ ጥንት ጋላ በአሁኑ መንግሥት አጠራር “ኦሮሞ” የተባለ እረኛ ሕዝብ ለከብቱ ግጦሽ ፍለጋ ሲል፣ በተለመደው አነጋገር “ኢትዮጵያን መውረር” ጀመረ ከተባለ ወደ፭፻ ዓመታት ሊያስቈጥር ነው። ወረራው የጀመረው የእስላሞች ንጉሥ ኢትዮጵያን ሊቈጣጠር ሲል፣ በክርስቲያኖቹ ንጉሠነገሥትና በአገሪቷ ላይ እንደአ.አ. በ፲፭፻፳፱ ዓ.ም. ያወጀው ጦርነት ከ፲፭ ዓመት ከፍተኛ ዕልቂት በኋላ፣ በክርስቲያኖች ድል በተደመደመው ማግሥት ነበር። ጉልበቱ በረጅም ጊዜ ጦርነት ስለተዳከመ፣ በየቦታው የነበሩት የመከላከያ ተቋማትና መዋቅርት ፈራርሰው ስለነበር፣ የኢትዮጵያ ማእከላዊ መንግሥት ወረራውን የመመከትና፣ ሕዝቡንም የመጠበቅ ችሎታው እምብዛም ስላልነበር፣ዘላኖቹ በየሄዱበት በአሬመናዊ ጭካኔአቸው ባደረሱት ለሰማው ሁሉ የሚዘገንን የሰው ዕልቂት፣ የንብረት ውድመት እንደፈጸሙና፣ እግራቸው የረገጠውን አካባቢ በሙሉ ወደጫካና ዱር እስከመለወጥ ደርሰው እንደነበር፣ የጊዜው ሰነዶች አበክረው የሚናገሩት ነገር ነው[11]። ያደረሱትን ጥፋት ባይናቸው ያዩት የውጭም ሆኑ ያገር ውስጥ ጸሓፊዎች፣ ‘ጋላ” ፈጸመ ከሚሉት ግፍና ጭካኔ የተነሣ ድርጊታቸውን አገሪቷን ለመቅጣት ሲባል የተላከ “የእግዚአብሔር መቅሠፍት” ነው በማለት ገልጸውታል።

 

ሁኖም ግን ኦሮሞች ወረራቸውን በጀመሩት ግማሽ ዘመን እንኳን ባልሞላ ጊዜ ውስጥ፣ የኢትዮጵያን ዳር ድንበር ሊጠብቁ ሲሉ በጦር ሜዳ ላይ እንደሌላው እንደቈየው የኢትዮጵያ ሕዝብ ብርቅ ሕይወታቸውን ሲሠውና ሲሞቱ ይታያሉ[12]። ነዋሪውን ገድለው ጨርሰው፣ ወይንም ለገባርነት ዳርገው መሬቱን በጉልበት ወስደው በየሰፈሩበት አካባቢ፣ አብዛኞቹ ኦሮሞች የጥንት የእረኝነት ኑሯቸውንና የዘልማድ እምነታቸውን ትተው፣ በግብርና ሕይወት በመሰማራትና፣ የሰፈሩን እምነት በመቀበል፣ የቀረውን የኢትዮጵያን ሕዝብ መስለዋል። እንደየአሰፋፈራቸው ክርስቲያን ወይንም እስላም ሁነው አብዛኞቹ እንደየእምነታቸው ስማቸውንም እስከመቀየር ደርሰዋል። በኢትዮጵያ መንግሥት ውስጥ ገብተው ልክ እንደሌላው ብሔረሰብ ተወላጆች በሥልጣን ሲሻኰቱ ማየት የተለመደ ገጽታቸው ሁኖም ይታያል። አፄ ሱስንዮስ ተቀናቃኞቹን ሁሉ አሸንፎ ለንጉሥነት የበቃው በኦሮሞች ድጋፍና የነሱን የጦር ስልት በመጠቀም እንደሆነ ታሪከ ነገሥቱ ይገልጥልናል። ሚስቱም ከርስትና ወልድሠዓላ በሚል በክርስቲያን ስም ብትጠራም፣ በትውልዷ የኦሮሞ ብሔረሰብ አባል እንደነበረች ይነገራል። ይኸም ማለት ጐንደርን ከቈረቈረው ከልጇ ፋሲለደስ ጀምሮ እስከ ዘመነ-መሳፍንት ድረስ በኢትዮጵያ ዙፋን ይቀመጡ የነበሩት የሷ ልጆችና የልጅ ልጆቿ እንደነበሩ ነው የሚያሳየው። ዘመነ መሳፍንት ማለት ደግሞ የኦሮሞ ዝርያ ናቸው የተባሉት የየጁ መኳንንት ላንድ መቶ ዓመት ያህል የጐንደርን መንግሥት ሙሉ በሙሉ የተቈጣጠሩበት የኢትዮጵያ ታሪክ ዘመን ነው ማለቱ እውነትን ያንፀባርቃል ብዬ አምናለሁ። የጁዎች በክርስቲያን ቤተመንግሥት ተቀምጠው እስላሞችን ሲያገቡ ያከረስትኗቸው እንደነበረ ሁሉ፣ የወሎዎቹ ሙሐመዶች ደግሞ እስላሞች እንደመሆናቸው ከክርስቲያን ሚስቶቻቸው ይጋቡ የነበሩት እያሰለሟቸው ነበር። ሁለቱም በዝርያቸው ከኦሮሞ ብሔረሰብ እንደመሆናቸው ሁናቴው የሚያሳየው የኢትዮጵያ ሕዝብ በደምና በሥጋ ብቻ ሳይሆን በእምነትና በባሕል ወወራረሱንና መዋሐዱን ነው።

 

ዘመነመሳፍንትን ያከተሙት አፄ ቴዎድሮስ ዳግማዊ የቋራ ብሔረሰብ ተወላጅ ናቸው። ቋራ የአገው እንጂ የብሔረ አማራ ዝርያ አይደለም። በሌላው በኩል ደግሞ፣ ከልክ በላይ የሚወዷት ሚስታቸው የኦሮምኛና የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪ ብሔረሰብ ልጅ እንደነበሩ ምንም አያጠያይቅም። እንዲሁም ከአፄ ዮሐንስ ቀጥለው በኢትዮጵያ ዙፋን በየጊዜው ከነገሡት ነገሥታት በቀጥታ ኦሮሞ ያልሆነ ወይንም የኦሮሞ ደም የሌለው አንድም ገዢ አልነበረም ማለት ይቻላል። በሌላው ጐን ደግሞ ኦሮሞች በወረራቸውም ወቅት ቢሆን፣ ያካባቢውን ሕዝብ ወንድና ሴት፣ ዐዋቂና ሽማግሌ ሳይለዩ በጅምላ ሲገድሉ፣ ብዙውን ጊዜ ሕፃናቱን ማርከው ወስደው እንደሚያሳድጓቸው መታወቅ ይገባል። በዚህ መልክ ከተማረኩት ሕፃናት መካከል አፄ ሱስንዮስ አንዱ ነበሩ። እነዚህ ሕፃናት የብሔረሰቡ አባላት ሁነው ላቅመአዳም ሲደርሱ፣ ከኦሮሞው ጋር ተጋብተው ልጅ መውለዳቸው አይቀሬ ነው። ስለዚህ ከሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ያልተዳቀለ በዘሩ ጭንጩ ኦሮሞ የሆነ ሰው፣ በኢትዮጵያ ምድር ውስጥ አለ ማለት በፍጹም ዘበት ነው። ከኔ ምርምር እንደምረዳው ከሆነ፣ የጠባብ ብሔርተኝነት አስተሳሰብ ያሰከረው ግለሰብ ወይንም ቡድን ብቻ ነው በዚህ ዐይነት ቅዠት የሚጠቃው።

 

ይኸ ሁናቴ ኦሮሞን ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያን ሕዝብ በሙሉ የሚመለከት ነው። የዛጐን ሥርወ መንግሥት የተኩት ሰለሞናውያን ነገሥታት፣ ከቀይባሕር ማዶ ያሉትን የድሮዎቹን የአክሱማውያንን ግዛት መቈጣጠር ባይችሉም፣ እስከዘመነ-መሳፍንት ድረስ በበላይነት ይገዙት የነበረው የኢትዮጵያ የቈዳ ስፋት ከመላጐደል እንደኣ.አ. እስከ፲፱፻፹ ዓ.ም. መጨረሻ ድረስ ያለውን ያጠቃልላል። የእነሱም አስተዳደር የተከተለው ልክ ቀድመው የመጧቸውን የአክሱሞቹንና የዛጐዎቹን ፈር ነበር። በእምነታቸው ክርስቲያን ቢሆኑም፣ ሕዝቡን በዘውጉና በሃይማኖቱ ምክንያት ሳይለዩ፣ በፍትሕና በርትዕ ማስተዳደር፣ ንግድ ማስፋፋት፣ ሰላምና ጸጥታ ማስፈን ዋነኛ ዓላማቸው ነበር። እንደማንኛውም የገዢ ክፍል ሥልጣናቸውን የሚቀናቀን ወይንም የሚደፍር ለነሱ ጠላት ነበር። ይኸንን ሐቅና የኢትዮጵያ ነገሥታት ምን ያህል ለማንም ሳያዳሉ ሁሉንም እምነት በደምብ ማስተናገድ ሥራቸው እንደነበር፣ ታላቁ አፄ ዐምደጽዮን [1314-1344]፣ “እኔ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖር የመላው እስላም ንጉሥ ነኝ” ያሉት ንግግር መርሀቸውን ጥርት አድርጎ ይገልጻል። ይኸም ኢትዮጵያን ከአብዛኛው የክርስቲያን ዓለም በጣም ልዩ አገር ያደርጋታል። ከሳቸው በኋላ ወደመቶ ዓመት ያህል ቈይተው የነገሡት ያውሮጳ ነገሥታት መቻቻልና አብሮ መኖር የሚባለው ሐሳብ በቋንቋቸው ስላልነበር፣ እንኳን እስላም ይቅርና፣ ክርስቲያን የተባለውን ሕዝባቸውን በፀረማርያምና በካቶሊክ ጐራ ለያይተውት አላንዳች ምሕረት ሲጨፈጭፉትና ሲያስጨፋጭፉት፣ ካዘኑለት ደግሞ ከግዛታቸው ሲያባርሩት እናያለን። እውነት ነው በኢትዮጵያም ውስጥ ቢሆን ዘመናዊ አስተዳደር እስከተዘረጋ እስከቅርብ ጊዜ ድረስ፣ ክርስቲያን ሁኖ የእስላምን አገር ማስተዳደር እንደማይቻል ሁሉ፣ እስላም ሁኖ የክርስቲያንን አገር ማስተዳደርም አልተለመደም። ሕዝቡም ቢሆን የሚቀበለው ሥርዐት አይደለም። የኢትዮጵያ ነገሥታት ይኸንን በመረዳት ነው እንግዴህ የመላው ኢትዮጵያ ማለትም የክርስቲያኑም፣ የእስላሙና የባህላዊ እምነቶች ተከታዩም ሕዝብ መሪዎች መሆናቸውን ለማስታወቅ ባፄነታቸው ላይ “ንጉሠ ጽዮን ወንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ[13]” የሚል መፈክር በማኅተማቸው ላይ ያኖሩት የነበረው።

 

አስተዳዳሪዎቹን በተመለክተ፣ ከሰለሞናውያን እስከ ዘመነ መሳፍንት ባሉት ዘመናት ጊዜ ውስጥ በክርስቲያኑ የኢትዮጵያ መንግሥት ውስጥ እከፍተኛ ሥልጣን ላይ የነበሩትን ሰዎች ብሔረሰብነት ለመመርመር ብዙ ሰነዶች የሉንም። በእጃችን ያሉን ጥቂቶቹ የሚያመለክቱት፣ ግለሰቦቹ ከሁሉም ብሔረሰቦች የተወጣጡ መሆናቸውን ብቻ ነው። በነገሥታት ደረጃ፣ ያብዛኞቹ ነገሥታት እናቶቻቸው ከሐድያና ከአካባቢዎቹ ብሔረሰቦች የተወለዱ ነበሩ። በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ወደር የሌለ ሚና ተጫውተዋል ተብለው ከሚደነቁት ሴቶቹም ወንዶቹ መካከል በገናናነትና በስመጥሩነት ስሟ ዘወትር የሚነሣው ንግሥት እሌኒ[1431-1522][14] የሐድያው መሪ የሙሐመድ ወይንም የቦያሞ ልጅ ነበረች። በሥልጣን ሽኩቻ በንጉሥ ሱስንዮስ እጅ የተገደሉት አፄ ያዕቆብም ሆኑ፣ ኋላ ንጉሥነገሥትነቱን በጦር ኀይል የተጐናፀፉት አፄ ሱስንዮስ ራሳቸው ጭምር በእናቶቻቸው ከቤተእሥራኤል ናቸው። የአፄ ሱስንዮስ ታሪክ እንደሚገልጥልን ከሆነ ያነ በጣም ታላቅ ሁኖ የሚታሰበውን የጐጃምን ግዛት፣ “ጐጃም ነጋሽ” የሚለውን ከፍተኛና ክቡር የሆነውን ያገሩን የገዢ ማዕርግ ተጐናፅፎ ለብዙ ዓመታት ያስተዳደረው የጉራጌው ተወላጅ ስልቡ“ጐጃም ነጋሽ ክፍሎ” ነበር። ያፄ ሠርፀድንግልን ሁለት ልጆች አግብቶ፣ አገሩን በበላይነት ይገዛ የነበረው በጊዜው የመንግሥት ፈላጭ-ቈራጩ መኰንን፣ የወለጋው ተወላጅ ራስ ዘሥላሴ[15] ነበር። በ “ዳሞት ጸሓፊላምነት” ማዕርግ፣ የኢትዮጵያን ሕዝብም ሆነ፣ ወሰንና ድንበር ለማስጠበቅ ሲል ብዙ ጦርነት በጀግንነት በመዋጋት፣ ንጉሠነገሥቱን እንደአ.አ. ከ፲፮፻፲፯ እስከ ፲፮፻፳፯ ዓ.ም. በታማኝነት አገልግሎ፣ በመጨረሻም የዳሞት ግዛቱን “ከጋላ ወረራ” ሊከላከል ሲል በጦር ሜዳ ላይ ሕይወቱን የሠዋው ደጃዝማች ቡኮ፣ ከመጀመርያዎቹ የኦሮሞች ታላላቅ ገዢዎች አንዱ ነበር። እንዲሁም ንጉሠነገሥቱ “እንደልቤ ታማኝ” ያሉት፣ ዋናው አማካሪያቸውና፣ ከቁመታቸው ማጠር የተነሣ በኦሮሞኛ ቃል “ጢኖ” በመባል የሚታወቁት፣ ጸሓፈ ትእዛዙ አዛዥ ተክለሥላሴ፣ የኦሮሞ ብሔረሰብ ነበሩ። ጽሑፋቸው እንደሚያመለክተው፣ አዛዥ ጢኖ ከኦሮሞ ቋንቋና ባህል በተጨማሪ፣ አማርኛና ግእዝ አሳምረው የሚያውቁ፣ ቅኔ የሚቀኙ፣ አንደበታቸው የተባ፣ ብዕራቸው የሰላ ጸሓፊ ናቸው። እነዚህ ለእንደዚህ ዐይነት ወግና ማዕርግ ሊበቁ፣ ዕውቀትንም ሊገበዩ የቻሉት፣  “ጋላ” በኢትዮጵያ ፈጸመ የተባለው ወረራ ግማሽ ዘመን ማለት ዐምሳ ዓመት እንኳን ሳይሞላው ሲሆን፣ እስከኛ ጊዜ ድረስ ባሉት ዐራት መቶ ዓመታት ውስጥማ ምን ያኽል መቀራረብና መዋሐድ እንደተካሄደ መገናዘብ የሚያዳግት አይሆንም። እንግዴህ የአክሱማያኑን እንኳን ብንተው፣ ከሰለሞናውያን ሥርወ መንግሥት ጀምረን የኢትዮጵያን መዝገበ ታሪክ፣ በፖለቲካ ጥቅም ተገፍተን ሳይሆን ታሪክ በሚጠይቃቸው በምርምር መስፈርቶች[16] ተመሥርተን ብናሰላስል፣ በመጀመርያ ደረጃ ስለቋንቋ እንጂ ስለብሔርና ብሔረሰብ[17] ልዩነት መናገር አንችልም። ስለዚህ በኢትዮጵያ ውስጥ የቋንቋ እንጂ የዘር ልዩነት ከቶውኑ የለም ማለት የማይካድ ሐቅ ነው ማለት ይቻላል። እንግሊዝኛ የሚናገር የእንግሊዝ ዘር እንዳልሆነ ሁሉ፣ ኦሮሞኛንም የሚናገር ሁሉ የኦሮሞ ዘር አይደለም። ታሪክ የሚያስተምረን ታላቅ ነገር ቢኖር፣ ቋንቋዎች ይጠፋሉ፣ በሌሎች ቋንቋዎች ይተካሉ። የአርጐባ ተወላጆች ነን ባዮች፣ ዛሬ እንደአፍ መክፈቻቸው የሚናገሩት ቋንቋ አርጐበኛ ሳይሆን እንደየአሰፋፈራቸው አካባቢ ልዩነት፣ አማርኛ፣ አፋርኛ፣ ኦሮምኛ፣ ትግርኛ ነው። በምዕራብ ወለጋ የሚኖሩት አንፊሎች ቋንቋቸውን ረስተው አሁን የሚናገሩት ኦሮምኛ ነው።

 

ነገሩ እንደዚህ ከሆነ ታዲያ፣ ኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦች እኩልነትና ነፃነት ተነፍገው የሚኖሩባት እስር ቤት ናት የሚለው አስተሳሰብ ከየት መጣ ብሎ መጠየቁ ተገቢ ይመስለኛል። ባጭሩ ለመመለስ፣ አሳቡ ብቅ ያለው ኢትዮጵያ ኢጣሊያንን በአድዋ ጦርነት ድል አድርጋ ለአውሮጳውያን ከፈጠረችው ውዝግብ ጋር የተያያዘ ነው ማለት ይቻላል። ኢጣሊያም ቢሆን እንደ አ.አ. በ፲፰፻፸፪ ዓ.ም. ዓመት ላይ መልሳ አንድ አገር ስትሆን፣ እንደኢትዮጵያ በብዙ ቋንቋ ተናጋሪዎች የተጥለቀለቀችና የተወጠረች አገር ነበረች። ከኢትዮጵያ በተለየ መልኩ ደግሞ ቋንቋዎቹን ተናጋሪዎች ሕዝቦች ከተለያዩ አገሮች የተሰባሰቡ ጥርቅምቅም ከመሆናቸውም በላይ፣ ገዢዎቻቸውም የተለያዩና እንደየጊዜው ይለዋወጡ ስለነበር፣ ሕዝቦቹ ርስበርሰ ለመደባላለቅ፣ ከቦታ ወደቦታ ለመዘዋወር ዕድል አልገጠማቸውም። ስለዚህም አገሪቷ አንድ እስከሆነችበት ጊዜ ድረስ ለዐራት መቶ ዘመናት[18] ተለያይተው ሲኖሩ፣ አንድ የሚያደርጋቸው ነገር ቢኖር፣ ሁላቸውም የካቶሊክ እምነት ተከታዮች መሆናቸው ብቻ ነው። ኢጣሊያኖች  በኢትዮጵያ ላይ ማትኰር የመረጡት አንድነታቸውን ለማጐልበት፣ ልዩነታቸውን ለማስረሳት ሊረዳ ይችላል ብለው ከተለሙት ጥንስሶች አንዱ ስለነበር ነው። ስለዚህም፣ የሆነ ያልሆነ ምክንያት በመፍጠር፣ እጃቸውን በኢትዮጵያ ላይ ከመቅሰር መቼም ሊቈጠቡ አልቻሉም። የአድዋ ድል ጥሩ ትምህርት አስተምሯቸው ለጊዜው ተወት ቢያደርጉትም፣ ልክ አፄ ምኒልክ እንዳረፉ፣ ወደጥንት አሳባቸው ተመልሰው መጡ። የያኔ መርሃቸው “የዳር ፖሊትካ[19]” በመባል ይታወቃል። ከቅድመ አድዋው ዘዴያቸው የሚለየው፣ ይኸኛው “የሸዋና የትግራይ ፖሊትካ[20]” በመባል ሲታወቅ፣ ዐላማው የትግራይንና ባካባቢዋ ያሉትን የባላባቶችን ግዛቶች ከማእከላዊው የአዲስ አበባው መንግሥት ጋር በማጋጨት፣ ያገሪቷን አንድነት በማናጋትና የርስበርስ አለመግባባት በማጠናከር፣ አገሪቷ ተበታትና በኢጣሊያን እጅ እንድትወድቅ ማዘጋጀት ነበር[21]

 

በኢጣሊያን ባለሥልጣኖች አገላለጽ፣ “የዳር ፖሊትካ”ም ግቡ ይኸው ነበር። ዋና ትኩረቱ ግን ባንድ በኩል የኢትዮጵያን መኳንንት በገንዘብ በመግዛት፣ ተራ ሕዝቡን በሕክምናና በትምህርት ቤቶች ስጦታና በመሳሰሉት ነገሮች ስም በማታለል፣ በሌላ በኩል ደግሞ በአዲስ አበባ ላለው መስተዳድር ወዳጅ በመምሰል፣ ማእከላዊው መንግሥት ያገሩን አንድነት ለማጠንክር የሚያደርገውን እርምጃና ጥረት በተቻለ መጠን በሙሉ ማክሸፍ ይገባል የሚል ነበር። ሁኖም እንደአ..አ. በ፲፱፻፴ ላይ የኢጣሊያን ባለሥልጣናት የጻፉት ዘገባ፣ “ኢጣሊያ እንዳቀደችው ኢትዮጵያ ደካማ ከመሆን ይልቅ”፣ አፄ ኀይለሥላሴ ከተጠበቀው በላይ አገሩን በዘመናዊ መልኩ እንዳዋሃዱትና አንድነቱን እንዳጠናከሩት፣ የኢጣሊያንም መርህ ልክ እንደቅድመ አድዋው መክኖ እንደቀረ ይናገራል[22]

 

አፄ ኀይሌ ሥላሴ ያመጡት ለውጥ ያስተሳሰበው ኢጣሊያንን ብቻ አልነበረም። በኢትዮጵያ ውስጥ ለጥቂት ዓመታት ከሠራ በኋላ ካገር የተባረረው ሮማን ፕሮቻዝካ የተባለ የነምሳ ተወላጅ፣ ሁናቴው የሌሎችም አውሮጳውያን ዋና ሥጋት እንደነበር ይገልጣል። ፕሮቻዝካ አደጋውን ከጅምሩ ለመቅጨት ሲል፣ እንደአ.አ. በ፲፱፻፴፭ ዓ.ም. ላይ “ኢትዮጵያ የባሩድ በርሚል” የሚል መጽሐፍ አሰራጨ። በዚህ ወዲያዉኑ በብዙ ቋንቋ በተተረጐመው መጽሐፍ አባባል፣ የኢትዮጵያ ዕድገትና ልማት፣ እንዲሁም ከአውሮጳ አገሮች ተምረው የተመለሱት ወጣቶች ሥራቸውን በዚህ መልክ ከቀጠሉ፣ ያፍሪቃ ቅኝ ገዢዎች ለሆኑት አውሮጳውያን እጅግ አስጊ ሁናቴ ስለሚፈጠር፣ ኢትዮጵያ እንዲትበታተን፣ ሕዝቦቿን “በነገድ፣ በዘር፣ በቋንቋና በባህል መከፋፈልና” ሁሉም ነገዶች በአምባገነኑ አማራ እየተጨቈኑ እንዳሉ መስበክ ያስፈልጋል[23]”።  ኢጣሊያም አገሩን ወርራ እንደያዘችው፣ ሥራዬ ብላ የለፋችው፣ ኢትዮጵያ የሚል ስም ካለም ካርታ እንዲፋቅ[24]፣ ሕዝቡ በጋራ ቋንቋ አማካይነት ርስበርስ እንዳይገናኝ አማርኛን ማጥፋት፣ የአንድነት መንፈስ እንዳያዳብር አስተዳደሩን በቋንቋና በጐሣ መሠረት አወቃቅሮ መከፋፈል ላይ እንደነበር ሁላችንም የምናውቀው ነገር ስለሚመስለኝ እዚህ ላይ መተንተኑ አስፈላጊ ሁኖ ስለማይታየኝ እዘለዋለሁ። ዋናው ነገር ግን፣ እንዳለፉት ሌሎች ጥንስሶችዋ ሁሉ፣ ይኽንንም በተግባር ሊታውለው አልቻለችም። የኢትዮጵያ አርበኞች የሰነዘሩት የጥቃት ወላፈን እስከአገሯ መጥቆ ደርሶ፣ ኢጣሊያን ራሷን ባለም ጦርነት ውስጥ በመዝፈቅ ለህልውናዋ እስከማስጋት ደረሰ። ፕሮቻዝካም ኢትዮጵያን ለማጥፋት የቀየሰው ንድፍ ከኢጣልያን ሽንፈት ጋር አከተመ። ለኢትዮጵያ የቃጣው ዱላ ለራሱ አገር ለነምሳ ተረፈ[25]

 

ይሁንና እንደአ.አ. በ፲፱፻፷ቹና ሰባዎቹ  ለመጀመርያ ጊዜ ባገር ውስጥ ከፍተኛ ትምህርት በመቅሰም ላይ የነበሩት ተማሪዎች የፕሮቻዝካን ቅያስ ከተቀበረበት አንሥተውት እንደገና ለአዲስ ሕይወት አበቁት። በጊዜው ባለም ደረጃ ደርቶ የነበሩት በወጣቶች ፊታውራሪነት የሚመሩት ፀረቅኝ ግዛትና ፀረ-ቄሳርያዊነት እንቅስቅሴዎች፣ ለኢትዮጵያም ተማሪዎች ተረፉ። እነዚህ ተማሪዎች፣ አገራቸውን ኢትዮጵያን በውጭ አገር ካዩትና በትምህርት ገበታ ከቀሰሙት ፅንሰአሳቦች ላይ በመመሥረት ሲመረምሯት፣ በምጣኔ ሀብት ዕድገት አኳያ በጉልተኛ ባላባት[26] ሥርዐት ደረጃ ያለች ኋላቀር አገር ትሁን እንጂ፣ እሷም ብሔር ብሔረሰቦችን በመጨቈን፣ ቅኝግዛትን በማስፋፋት የነጮች አውሮጳውያን አጋር ነበረች ብለው ደመደሙ። ለነዚህ ብዙውን ጊዜ ከወጣትነት ዕድሜ ጋር አብሮ በሚመጣው በኀልዮ ኑሮ በተበረዘው ጭንቅላታቸው፣ በጥራዘ-ነጠቅነት ላይ የተገነባ ማራኪው የኅብረተሰባዊነት አስተሳሰብ ሲጨመርበት የግንዛቤአቸው ሐቀኝነት እየጐላ እንደሄደ አይካድም። ጊዜው ደግሞ የቀዝቃዛ ጦርነት ወቅት ስለነበር፣ ብዙዎቹ የፖሊትካ ጥቅማቸውን የሚያራምዱ ኀይሎችና ግለሰቦቻቸው ሰለባ እንደነበሩ አይካድም[27]። ዋናው ነገር ግን የተራማጅነት ጨንበል አጥልቀው በሰላቢ ድምጻቸው፣ በኢትዮጵያም ሆነ በሌላው ለከፍተኛ ትምህርት ሲሉ በተሰማሩበት ዓለም ውስጥ ይንጫጩ የነበሩት ሁሉ፣ ባይን ዐዋጅ ተመርተው ያዩትን አሜን ብሎ ከመቀበልና በለብለብ ዕውቀታቸው ላይ ከመመሠረት ውጭ፣ ያገሩን ሁነኛ ታሪክና ባህል፣ የምጣኔውንና የማኅበራዊውን ዕድገት ደረጃና መጠን ባገናዘበ በረቀቀ ጥናትና በጠለቀ ምርምር የተመረኰዘ አልነበረም። እውነት ነው እንቅስቃሴዎቹ በርከት ላሉት መሪዎቻቸው ባገርና በዓለም ደረጃ ጐልተው እንዲታዩ፣ ዕድልና ምቹ መድረክ ሰጥቶዉአቸዋል። በጥራዘ-ነጠቅነታቸው በየቦታው እየሄዱ የነበነቡት ግራዘመም ስብከታቸው ግን፣ አገሪቷን ህልውናዋን እስከመፈታተን ድረስ ለታላቅ መከራና ሥቃይ ዳርጓታል። የጥፋት አደጋው አሁንም ቢሆን እላይዋ ላይ እያንዣበበ እንዳለ ሁላችንም ስለምናውቅ እዚህ ላይ በማተት ላሰለቻችሁ ምኞቴ አይደለም።

 

የኢትዮጵያ ተማሪዎች ትልቁ ችግር ኢትዮጵያ አንድ ከመሆኗ በፊት ባገሩ ውስጥ የነበረውን ያገዛዝ ሥርዐትና ሁናቴ አለማመዛዘናችውና በዙርያዋም ይካሄዱ ከነበሩት ከአውሮጳውያን ተግባራት ጋር አለማያያዛቸው ነው። ካንድነት በፊት አገሪቷን ከጫፍ እስከጫፍ ይገዙ የነበሩት፣ በተለያየ የማዕርግ ስም ይጠሩ የነበሩት የየአካባቢው ባላባቶች ነበሩ። እነዚህ አገራቸውን ወደርስበርስ ጦርነት እንደቀየሩት፣ ነዋሪዎቹን በለየለት ዐይንባወጣ ብዝበዛና ሥቃይ እያተራምሱ እንደነበርና፣ ሕዝቡ ሰላምና ዕረፍት ከማጣት አልፎ፣ የነበረው ያስተዳደር ሥርዐት ከባርነት የተለየ እንዳልነበረ ተማሪዎቹ የተረዱ አይመስልም። ሁሉንም በየዘርፉና በየቦታው መዘርዘር አስፈላጊም አይደለም። ጊዜም አይፈቅድም። ግን ለምሳሌ ያህል ብቻ ሌላውን ትቼ ሁለት አካባቢ ልጥቀስ። የጋዳን ሥርዐት አድናቂዎች፣ ሩቅም ሳይሄዱ በኦሞ ሸለቆ አካባቢ ቊብ ቊብ ያሉትን የጂማ አባጅፋርን፣ የሊሙ እናርያን፣ የጐማንና የጉማን፣ እንዲሁም የለቃ-ነቀምቴንና የለቃ-ቄለምን መንግሥታት ሊያዩ ይገባል። እነዚህ መንግሥታት አካባቢውን የያዙት፣ ነባሩን ሕዝብ በመፈንቀል፣ ወይንም በመግደልና ለባርነት በመዳረግ መሆኑ መረሳት የለበትም። አልፎ አልፎ አንዳንድ ጥሩ ገጽታ ቢኖራቸውም፣ ከመላጐደል የሚያማዝነው አስቀያሚ ጐናቸው ነበር ቢባል የሚካድ አይደለም። የደሞክራሲ ሥርዐትን ያቀፈ ነው ተብሎ የሚወራውን የጋዳ አገዛዝ አፍርሰው፣ ገዢዎቹ አምባገነኖች ሁነው በዘፈቀደ ይገዙ ነበር። ሕዝባቸውንም ሆነ፣ ከሌላ አካባቢ የሚመጣውን እንደባዕድ የሚቈጥሩትን ሌላውን መጤ መፈንገል ልማዳቸው ነበር። የእስላም ሃይማኖት በግድ ያልተቀበለ አንገቱን ለሳንጃ አሳልፈው ይሰጡ ነበር። አለበለዚያም ለስደትና ለባርነት ይዳረግ ነበር። ድንበር ለማስፋት የሚደረገው ጦርነት መቆሚያ አልነበረውም።

 

ከነዚህ ወጣ ብለን ሌሎችን ብናይ የከፋ እንጂ የተሻለ አስተዳደር አናገኝም። ዎማ ወይንም ንጉሥ በመባል የሚታወቅ የከምባታ ገዢ ለምሳሌ፣ በየጊዜው ባካባቢው ካሉት ሕዝቦችና ባላባቶች ጋር ባካሄዳቸው አስከፊ ጦርነቶች፣ መንግሥቱን እያስፋፋ በሄደ ቊጥር አምባገንነቱም በዚያው ልክ አሻቅቦ ነበር። ኦያታ በመባል ለሚታወቀው የራሱ የገዢው መደብ፣ ኮንቶማ የተባለውን ተራውን ሕዝብ እንዲበዘብዝና እንዲያዋርድ ሥልጣን በሥልጣን ላይ ካበላቸው። ለምሳሌ ያህል፣ ኦያቶች ገደብ የለሽ ሚስቶች ሊያገቡ ሲችሉ፣ ተራው ኮንቶማ ግን ካንድ ሚስት በላይ አይፈቀድለትም ነበር። ኦያታ ምርጥ ምርጥ መሬት እየነጠቀ ከተራው ኮንቶማ ወስዶ ሲያበቃ፣ ኮንቶማውን መሬት አልባ ገባር ማድረግ መብቱ ነው። ከዚያም አልፎ ኮንቶሞች አጥር ማጠር፣ በቅሎ መጋለብ አይፈቀድላቸውም፡፡ ጥሰው ከተገኙ የሚጠብቃቸው ጥቃት ቅጥ ያጣ ነበር። ንጉሡም ሲሞት ከባሮቹ ተመርጠው ቆንጆ ሴቶችና ሀብቱም አብረው ይቀበሩ እንደነበር ይነገራል።

 

አፄ ምኒልክ በጦር ኀይልም ሆነ፣ “ሕዝብ በከንቱ እንዳያልቅ፣ ሀገር እንዳይጠፋ በሰላም ግበር” የሚለውን ጥሪያቸውን ተቀብለው በፍቅር በተዋሀዱት አገሮች፣ ከእነዚህ አስከፊ ገጽታ ካላቸው ያስተዳደር ሥርዐት አብዛኛውን ሽረው፣ ሕዝቡ እፎይ እንዲል አድርገዋል። በቦታቸው የዘረጉትም አስተዳደራቸው መዋቅር ሁለት የተጠማመሩ ግቦችን ያካተተ ነበር ማለት ይቻላል። አንደኛው ሕዝብን በግድ ሳይሆን በፍቅርና በዘዴ መግዛት ሲሆን፣ ለዚህም በሕዝቡ ዘንድ እሱ የለመደውና የሚያውቀው ያገሩ ባላባት ተቀባይነት ይኖረዋል ብለው ስላመኑበት፣ የተማረከዉን ገዢ መልሰው በቦታው ይሾሙ ነበር። ካልሆነም ልጁን ወይንም ሕዝቡ ተሰብስቦ የመረጠውን ያስቀምጡ ነበር። መዋጋትንም ይመርጡት የነበረው ባላባቱ፣ በሰላም ግበር ብለው አስቀድመው ደጋግመው ለላኩት ጥሪ፣ አሻፈረኝ ሲላቸውና፣ ሌላ አማራጭ ሲያጡ ብቻ ነበር።

ሁለተኛው ዓላማ፣ ዘመኑ አውሮጳዉያን፣ ነጭ ያልሆነውን ዓለም የሚቀራመቱበት ወቅት ስለነበር፣ ቅኝ ገዢዎቹ አገሩን ለመያዝ ልባቸው እንዳይዳዳ፣ ንጉሠነገሥቱ በግዙፉ በይፋ ማስታወቅ ነበረባቸው። ለዚህም ሲባል፣ ቅኝገዢዎቹ አገሩ በአፄ ምኒልክ ሥር እንዳለና፣ ቢዳፈሩም ጦርነቱ በቀጥታ ከሳቸው ጋር መሆኑን እንዲረዱ፣ ከማዕከላዊ መንግሥት የተሾመ የታጠቀ የጥበቃ ኀይል በያገሩ ተመደበ። የውስጡ አስተዳደር ሙሉ በሙሉ በባላባቱ እጅ ስለሆነ፣ ሕዝብ ተበደልሁ ካላለ በስተቀር፣ የጥበቃው ክፍል ባስተዳደሩ ጣልቃ አይገባም። ሁኖም ግን የሥልጣን አጠቃቀም ውስብስብነት ስላለው መቼም ቢሆን ችግር እንደሚኖር አይካድም፤ የሚጠበቅም ነው። ይሁንና በዚህ መልክ የተዋቀረው አስተዳደር ራሱን የቻለ እንዲሆን ሲባል፣ እያንዳንዱ ባላባት ዓመታዊ ግብር ይከፍላል። ከዚህም ግብር፣ የጥበቃው ክፍል ለራሱ የሚበቃውን ቀንሶ፣ የቀረውን ለመንግሥት ግምጃ ቤት ያስተላልፈዋል።

ሁኖም ግብሩ የተጣለበት የደቡቡ ሕዝብ ከዉህደቱ በፊት፣ ከዚህ በላይ ራሳቸውን በቻሉ በጥቃቅን የባላባቶች መንግሥታት ቢጤ ሥር ስለነበር፣ እንደሰሜኑ ሕዝብ ለማዕከላዊ መንግሥት ለብዙ ዘመናት ገብሮ አያውቅም። ስለዚህም ትውፊቱ በሌለበት አካባቢ ግብር በመጣሉ፣ እንደግፍ ተቈጥሮ በመተቸት፣ ያፄ ምኒልክን ሥራ በቅኝ-ገዢነት እስከመተርጐም አድርሷል። እንዲህ ዐይነቱ አቃቂር መሠረተ ቢስ ከመሆን አልፎ፣ በታሪክም ቢሆን በምንም መልኩ የማይደገፍ ነው። እንግሊዞች “ግብርና ሞት ሁለት አይቀሬ የመኖር ዕዳ ናቸው” እንደሚሉ ሁሉ፣ አፄ ምኒልክ በግዛታቸው ሰላም ለማስፈር፣ ጸጥታ ለማስከበር፣ የሚወጣውን ወጪ ለመሸፈን፣ እንደማንኛውም መንግሥት ግብር የማያስከፍሉበት ምክንያት የለም። እንደእንግሊዞቹ ባገራችንስ ቢሆን “ግብር ይውጣ፣ የማይቀር ዕዳ” ወይንም “ግብር፣ እስከመቃብር” ይባል የለም።  ይልቅስ ግብሩ፣ ጊዜውንና የሕዝቡን አኗኗርና ችሎታ ያገናዘበ በመሆኑ፣ ንጉሠ ነገሥቱ ምን ያኽል አስተዋይና፣ የአገራቸውንና የሕዝባቸውን የዘለቀታ ጥቅም በደምብ የተረዱ መሆናቸውን ፍርጥ አድርጎ ያመለክታል።

ግብሩ በጠቅላላ ከሕዝቡ ዐቅም ጋር የተመጣጠነ ሁኖ፣ የክልሉን አስተዳደር ወጪ ችሎ፣ ቀሪው ለመንግሥት ግምጃ-ቤት ገቢ ይደረግ ነበር። ይኸም ኢትዮጵያ ከውጭ አገር መንግሥታትና ከዓለም-አቀፍ አበዳሪ ድርጅቶች ገንዘብ ሳትበደር፣ ባላት ገቢዋ ብቻ ተቈጥባ፣ እጅግ በጣም ሰፊ አገር እንድታስተዳድርና፣ አንዳንድ የልማት ሥራዎች እንድታካሄድ አበቅቷታል። አለመበደሯ ለአብዛኞቹ የእስያና የአፍሪቃ ሀገሮች ከደረሰባቸው መጥፎ ጽዋ (በተለይም ግብፅን የገጠማት ዐይነት)፣ ማለትም አበዳሪዎቹ ኪሳራቸውን ለመሸፈን በሚል ሽፋን አገሯን በዋስትና ከመያዝ አድኗታል። አካባቢው የታወቀ የተፈጥሮ ምርት ከሌለው፣ በሰሜኑ ክፍል እንደተለመደውና ከጥንት ይሠራ እንደነበረው፣ መሬቱ ተሸንሽኖ በተወሰነ ሰው ቊጥር ይደለደልና በሰው ልክ ግብር ይጣልበታል። በተራ ቋንቋ ገባር የሚባል ቃል ከዚህ የመነጨ ነው። ትርጒሙም “ግብር የሚከፍል” ማለት ነው።

ባህሉንና አሠራሩን ባልተረዱትና፣ ከአገራቸውና ከራሳቸው ጥቅም አንጻር በሚያዩት የፈረንጅ ጸሓፊዎች ላይ በመመርኰዝና ከታሪክ ሂደት ጋር ካለማገናዘብ የተነሣ ነው እንግዴህ፣ ብዙዎች ተማርን ባዮች ኢትዮጵያውያን ለገባር መጥፎ ትርጒም ይሰጡ የነበሩት። ይባስ ብሎ፣ ከፀጥታ ጥበቃው ክፍል በማያያዝ “የነፍጠኛ ሥርዐት” ብለው የሚጠሩትም አሉ። ታሪክ ማጣመም ካልተፈለገ በስተቀር ትርጒሙ እውነቱን አያንፀባርቅም። ከጊዜው የአገሩ ምጣኔ ሀብትና ከሕዝቡ የዕድገት ደረጃ፣ እንዲሁም ከዓለም ዐቀፍ ሁናቴና ከዘመኑ መንግሥታት ኀይል አሰላለፍ አንጻር ሲታይ፣ ምንም ብንል፣ ያኔ ከገባር የተሻለ አማራጭ ከቶውኑ አልነበረም። ቢኖር ኖሮ፣ አፄ ምኒልክ በደስታ እንደሚቀበሉት በምንም አይጠረጠርም። ለዚህም ያኔ በመጠኑ በሥልጣኔ ደረጃ ከሌላው ክፍለ አገር ሻል ብላ ለሚትገኘው ለድሬዳዋ ከተማ በ፳፰ ሠኔ ፲፰፻፺፰ ዓ.ም. አስተዳደርዋ እንደሌላው አካባቢ በባላባት መሆኑ ቀርቶ በቤተ መማክርት፣ ማለትም በሥራ አስኪያጅ ቡድን እንድትተዳደር ብለው ያወጡት ሕግ እንደማስረጃ ሊጠቀስ ይችላል። እንደዚሁም የወላይታ ባላባቶች በተራው ሕዝብ ላይ በደል ቢያበዙ፣ ሽረውዋቸው ከጥብቅ ማስጠንቀቂያ ጋር በ፪ ሠኔ ፲፱፻ ዓ.ም. ያቋቊሙት የሹማምንቶች መማክርትም ሌላ ምሳሌ ነው5 ።

የገባር ሥሪት ባሕርይ በሰሜንም በደቡብም አንድ ዐይነት ሁኖ ሳለ፣ በኻያኛው ዘመን ላይ በደቡቡ ሥርዐት ሰፊ ለውጥ ታይቷል። ስለዚህም ልዩነቱ በአካባቢው የተከናውኑ የሥራዎች ውጤት እንጂ ከመንግሥት የታወጀ አዋጅ ወይንም የተወሰደ ያስተዳደር እርምጃ ያመጣው አልነበረም። የሰሜኑ ክፍል በሥልጣን ሱስኞች ባላባቶች በመበጥበጡ፣ ምንም ዐይነት የልማት ሥራ ሳይካሄድበት በቁመናው ሲቀር፣ በደቡብ የባቡር ሐዲድ መዘርጋትና የዘመናዊ እርሻ መስፋፋት ያመጡት ሀብትና ድሎት ባላባቱንም ሆነ የማእከላዊ መንግሥት ሹሞችን ስለተፈታተነ፣ ሁለቱ አንዳንዴ በመተባበር፣ አንዳንዴ ደግሞ በተናጠል ተራ ሕዝቡን እያባበሉም ሆነ እያዋከቡ፣ ወይንም ኀይል በመጠቀም መሬቱን እስከመንጠቅና ጥሎላቸው እስከሚሄድ አድርሰዉታል። ለምሳሌ አሩሲዎች ለከብታቸው ግጦሽ እስከሚያጡ ድረስ መሬታቸዉን አጥተዉት ነበር። አፄ ምኒልክና ተከታዮቻቸው ጊዜውና ዐቅማቸው በፈቀደላቸው መጠን ከሕዝቡ ጐን ተሰልፈው፣ አንዳንዴ በአዋጅ፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ባለሥልጣኖቹን ሽረው ሌላ በመተካት፣ ሳይታክቱ እንደተዋጉ ሰፊ ማስረጃዎች አሉ።

 

አንድነትን ከመፍጠራቸው በፊት፣ ከላይ እንዳየነው፣ በየቦታው ይገዛ የነበረው የባላባቶች መንግሥት፣ የራሱን ሕዝብ ከታጐረበት ክልሉ ውስጥ እንዳይወጣ ሲያስገድድ፣ ከሌላው አካባቢ ወደሱ አገር የሚገባውን ደግሞ ብዙውን ጊዜ ለባርነት ስለሚፈልግ ተመልሶ ካገሩ እንዳይወጣ ይከለክል ነበር። አፄ ምኒልክ የኢትዮጵያን ሕዝብ ከዚህ ሁሉ የክልል መንግሥት አሰቃቂ ጭቈናና እሰር ነፃ አስወጥተው፣ በወደደበት እንደፈለገ እንዲኖር አድርገዋል። መጥፎ ልማዳቸውንም አንለቅም ላሉት እንደነጂማ አባጅፋር ዐይነቶቹ ባላባቶች ደግሞ፣ “ማንም ሰው እወደደበት ቦታ ላይ ይኖራል እንጂ … በምንም መልክ ልትይዘው አይገባም፤ ድኻው እወደደው፣ እተመቸው ቦታ ይደር[28]” ብለው የሰጡት ትእዛዝ ማንኛዉም የቅኝ ገዢ ያራምድ ከነበረው መርህ ጋር በጣም ተፃርራሪ ነበር ማለት ይቻላል።

እንግዴህ አፄዎቹ ይልቁንም አፄ ምኒልክ ያደረጉት ታላቅ ሥራ ቢኖር፣ በየቦታው በነዚህ አምባገነን ባላባቶቻቸውና፣ ንጉሥ ነን ባዮች ገዢዎቻቸው ሥር፣ እንደእስረኞች ከጠባቡ ግዛታቸው ውስጥ ታጉረው፣ በሚዘገንን ጭቈና ይማቅቁ የነበሩትን ኅብረተ-ሰቦች ነፃ አውጥተዋቸው፣ የቋንቋና የሃይማኖት ልዩነት ሳይደረግ፣ በኢትዮጵያዊነታቸው ባሰኛቸው ቦታ እንዲኖሩ፣ የመላዋን ኢትዮጵያን ምድር ሀብታቸው ማድረጋቸው ነው። አፄ ምኒልክ ያዋሀዷት ኢትዮጵያ “የኅብረተ-ሰቦች እስር-ቤት ናት” ማለት ታሪክን ካለማወቅ ወይንም ከማጣመም የመነጨ ሲሆን፣ እውነቱ ግን ንጉሠነገሥቱ በባላባቶች ክልል ውስጥ ታስሮ የነበረውን ሕዝብ ነፃነት አቀናጅተውለት፣ በፈለገበት ሄዶ በእኩልነት እንዲኖር፣ በወደደውም የሥራ መስክ እንዲሰማራ አድርገዋል። በዚህም ሥራቸው መደነቅና መከበር ይኖርባቸዋል። በፈጠራ ታሪክ በመመሥረት ስማቸውን ማጒደፍ ደግሞ በታሪክ ያስጠይቃል[29]

ይሁንና በኢትዮጵያ ውስጥ በመንግሥት ደረጃ አንዳንድ ያስተዳደር ጕድለቶች መኖራቸው አይካድም። ቢሆንም ግን ያንድ የተወሰነ ዘውግ ወይንም የዘውግ አባል በመሆኑ ብቻ በይፋ የተንቋሸሸ፣ የተጨቈነና ዜግነቱን የተከለከለ፣ ከሥልጣንም ከዕድገትም የታገደ፣  ግለሰብም ሆነ ብሔርና ብሔረሰብ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የለም። ከዚያም ባሻገር  የኢትዮጵያ ሥልጣኔና መንግሥት ካንድ ብሔረሰብ ወይንም አካባቢ ጋር የተቈራኘ ሁኖም አያውቅም። ሌላው ቀርቶ በዘመነ-መሳፍንት ፈርሶ የነበረው የሕዝቡና ያገሩ አንድነት መልሶ በዘመናዊ መልኩ እንደ አንድ አገረ-ግዛት የተቋቋመው፣ በብዙ ጐን በተለያየ መልክ የተወጣጣና የተሰለፈ ብሔርንና ብሔረሰቦችን ባቀፈ ኀይል እንጂ፣ ካንድ ከተወሰነ አካባቢ ወይንም ጐሣ በመነጨ ጦር አልነበረም። አገሪቷና ሕዝቧም ይመሩ የነበሩት ለማንም ሳያዳላ ገንዘቡና ዐቅሙ በፈቀደው መጠን ሁሉንም በእኩል በሚያስተዳድር መንግሥት ስለነበር፣ አንዱን ዘውግ ከሌላው በተለየ፣ በላቀና በሞለቀቀ መልክ የሚገዛ ሕግም ልምድም ሁናቴም ባገሩ ውስጥ ከቶውኑ አልታየም።

 

ኢትዮጵያ ያቀፈችው አሁንም ቢሆን እንደጥንት የተለያየ ቋንቋ የሚናገርና ሃይማኖት የሚያመልክ የሕዝብ ሙዚዩም” ስትሆን፣ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በበኩሉ የዚሁ ሕዝብ ጒንጒን ነው ማለት ይቻላል። አሁን ለሀገሬ ተቈርቋሪ ነኝ ከሚል ትውልድና ግለሰብ የሚጠበቀው፣ ባለፉት ያስተዳደር ጉድለቶችና በተደረጉት አለመግባብቶች ማትኰርና መወቃቀስ ፋይዳቢስ መሆኑን ዐውቆ፣ የተሻለች ኢትዮጵያን መገንባት ነው። ጃገማ ኬሎ የተባሉት ሰመጥሩ ጄነራል አንዴ እንዳሉት፣ በአስተሳሰብም ሆነ በሙያ ዘርፍ ጠባብ በነበረው በጐሦችና በባላባቶች ዓለም ይኖሩ የነበሩት አባቶች፣ የጀብዱነታቸው መለኪያና ምልክት በሚጥሉት ግዳይ በሚያስቈጥሩት ሚርጋ የተመጠነ ነበር። በዛሬ ዘመን ግን የጀብዱ ሚርጋ የሚቈጠረው እያንዳንዱ ግለሰብ ለአገርና ለኅብረተ-ሰብ ዕድገትና ልማት በሚሠራው ሥራና በሚያበረክተው አስተዋፅዖ ነው። ከዚያም አልፎ በተሰማራው የሙያ ዘርፍ በሚያደርገው ፍልሰፋና ምርምር እኩዮቹን ሲያስከነዳና፣ ለዓለም ሕዝብ በጠቅላላ ጠቃሚ አገልግሎት ሲሰጥ ነው። አፄዎቹ ኢትዮጵያን አንድ አገር በማድረግ፣ ይኸንን ዓላማችን አድርገን ባገር ውስጥም ሆነ በዓለም መድረክ ላይ እንድናበረክት ዕድሉንና በሩን በሰፊው ከፍተዋል። እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ እውድድሩ ሜዳ ውስጥ ገብቶ ድርሻውን ለገዛ አገሩም ለዓለምም መክፈል እንዲችል፣ ነገሥታቱ አመቺ ሁናቴ አደራጅተዋል። አገሩን አደላድለው ካበቁ በኋላ የዘመናዊ ሥልጣኔን መሠረት ጥለው ሜዳውን አመቻችተዋል።

 

ካርል ማርክስ እንዳለው ጐሣነት የበግ ዐይነት ስሜት ነው። በደመነፍስ ብቻ አንዱ ሌላውን ይከተላል። ሰው ግን የመራቀቅና አስፍቶ የማየት ልቡና አለው። እኔ ሁለዬ የሚገርመኝ ነገር ቢኖር፣ የዘውግና የክልል መስተዳድር አራማጆች ስብከታቸውን የሚያቀነቅኑት፣ ብዙዎቹ ወደፈለጉበት ሂደው እንዳሰኛቸው በሚኖሩበትና በሚሠሩበት በምዕራብ ዓለም ተቀምጠው ነው። እንዴት ነው እንደነዚህ ዐይነቶቹ በሰብኣዊ ልቡና የማይመራውን የጐሣንና የባላባቶችን ዓለም የሚያደንቁት። ለኔ እነዚህን ሁለቱን ማድነቅም ሆነ ከሞቱበት ለማንሣት መሞከር ከታሪክ ጋር ግብግብ መያያዝ ነው።  አያዋጣም። እንዲሁም አፄዎቹን ራሳቸውን መውቀስ፣ ከሙት ጋር መሟገት ሰለሆነ ርባን የለዉም። የራስን ድርሻ መወጣትና ከአባቶችና ከፊተኛው ትውልድ የተረከቡትን አሻሽሎ ለመጪው ትውልድ ማስተላለፍ ግን በታሪክ የሚያስጠይቅ የያንዳንዱ ሰው ግዴታው ነው።

 

 

 

[1] . ዘውገኝነት ስል የጎሣ ፖሊትካን፣ በዓለም አቀፍነት ደግሞ የካርል ማርክስንና የቪላድሚር ሌኒንን ር እዮተ ዓለም የሚያተናፍሱትን ነው የማመለክተው። አብዛኞቹ ዛሬ ባገራችን ያሉት ጐሠኞችና ጐጠኞች [ወያኔዎችንና የፓለቲካ አጫፋሪያቸውን ኢሕአደግን ጭምር] የግራዘመም ፖሊትካ አራማጆች ነበሩ ማለት ይቻላል። ወደጠባብ ብሔርተኝነት የፈለሱት የግራው ርእዮተ ዓለማቸው ክሽፎባቸው ሲቀር ነው።

[2] . ይኸንን በመላዋ ጥቁር አፍሪቃ ውስጥ ከታነጹት ከተሞች ጋር ማነጻጻር ነው። ከኤርትራ ከተሞች ጀምሮ በመላዋ አፍሪቃ የተገነቡት ከተሞች በፈረንጆች እጅ ናቸው ማለት ይቻላል።

[3] . ይኸ ከአናቱ ላይ ያለው የንጉሡን ስም የሚገልጸው ወገን ከመግቢያ ተጐምዶ የጠፋበት ጽሑፍ በሦስተኛ ዘመን አካባቢ የተጻፈ ሲሆን፣ ንጉሡ በኻያ ሰባተኛ ዘመነ-መንግሥቱ ስፊ ድል የሰጡlለትን አማልክቱን ማለትም ዜውስን፣ ኤራስ [ጨረቃ]ንና፣ ጳሰይዶስን ሊያመሰግን ሲል ባቆመ ባንድ የዘውድ ቅርጽ ባለው ድንጋይ ላይ የተጻፈ ሐውልት ነው;፡ ንጉሥ አስገበርኋቸው የሚላቸው የአገሮች ዝርዝር በቅርብ ጊዜ ሊቅ ላጲሶ ድሌቦ [የድሮው ጌታሁን ድሌቦ] ለኢሳት ሬድዮ ቴሌቭዥን በሰጡት ቃለምልልስ “የአክሱማያን ግዛት ከዛሬው ትግሬና ኤርትራ ክልል አያልፍም ብለው የተናገሩትን ያስተባብላል።

[4] . ያገሩ ስም አክሱም ይሁን ወይንም ሌላ ስም ይኑረው በግልጥ የሚታወቅ ነገር የለም። ግን በድሮ ዘመን ብዙውን ጊዜ አንዳንድ መንግሥታት የሚጠሩት በሚገዙት አገር ስም ሳይሆን ታዋቂነት ባላቸው መናገሻ ከተሞቻቸው እንደነበር፣ ባሁኑ ጊዜ በሱዳን ስም በሚጠራው ጥንት በግእዝ ካሱ፣ በዕብራይስጡ ኩሽ፣ በጽርዕ ደግሞ ‘ኢትዮጵያ” ከሚባለው አገር ልንገነዘብ እንችላለን። ካሱ በብዛት የሚታወቀው በየጊዜው በተከታታይ ገናናነትን ባተረፉ መናገሻ ከተሞቹ በቄርማ (2400-1570 ዓመተ ዓለም [ዓ.ዓ.)፣ በናጳታ (900-590 ዓ.ዓ.)ና በመርዌ (590 ዓ.ዓ. – 350 ዓመተ ምሕረት [ዓ.ም.] ነበር። የአክሱምም አጠራር ከዚህ ልምድ የተለየ ላይሆን ይችላል የሚለውን ግምት ከንግግሩ ውስጥ ማስገባቱ ተገቢ ይመስለኛል።

 

 

[5] . አረመኔ ጐሣዎች ወራሪዎቹ መካከል ጥቂቶቹን ብቻ ለመጥቀስ ያህል ጀርመናውያን ቭሲጎቶችና ሂሩሎች፣ ሃኖችና ኦስትሮጎቶች፣ ዐረቦች ነበሩ። ወረራዎቹ ገብ እንዳሉ ኢጣሊያ በተለያዩ የየራሳቸው ገዢ ባላቸው ግዛቶች ተከፋፍላ ሕዝቡ አልፎ አልፎ ካልሆነ በስተቀር በሰፊው ለመደበላለቅና ለመወላለድ እስከ፲፰፻፸፪ ዓ. ም. ድረስ ዕድል አልገጠመውም። ስለዚህ አሁንም ቢሆን ይልቁንም የሰሜኑና የደቡቡ ሕዝብ ሃይማኖቱ አንድ ቢሆንም በቋንቋና በባህል ባስተሳሰብ በጣም ይለያል።

[6] . የዱር አህያን ያላመዱት በቅሎንም ያስገኙት አገው ናቸው ተብሎ ይታመናል።

[7] . ጊዜው በፈረንጆች ታሪክ አገላለጽ

[8] . አማራ ለመጀመርያ ጊዜ በኢትዮጵያ ታሪክ ስሙ የሚነሣው ድግናጃን፣ ደጋዛንና ግዳዣን በመባል በተለያየ ስም የሚታወቅ የአክሱም ንጉሥ ከመናገሻው ወደመቶ ዐምሳ ሰባኪዎች ደብተራ ብሎ ከሠየማቸው በኋላ ሕዝቡን ወደክርስትና እምነት እንዲመልሱት ወደ”አማራ” ላከ በሚል ሰነድ ነው።

[9] . አገዎቹን የተካው ሰለሞናዊ ሥርወ-መንግሥት በሥልጣን ላይ በቈየው የዘመን ርዝመት አኳያ ለጊኒስ ቡክ ቢመረጥ የኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን ያለምንም ክብረወሰን እንደሚያሸንፍ እርግጠና ነኝ። ያገዎች መንግሥት በጦር ሜዳ ቢሸነፍም፣ ታሪክ እንደሚነግረን ሥልጣኑን ለሰለሞናዊ ሥርወ መንግሥት የለቀቀው በሽምግልና ተደራርድሮ ነው። ድርድሩም እንደ አ.አ. በሺ ዘጠኝ መቶ ሰባ ዐምስት ዓ. ም. የሰለሞናዊ ሥርወ መንግሥት እስከፈረሰ ድረስ ከመላጐደል ተከብሮ ቈይቷል።

[10] . ከደቡቡም ሕዝብ የወያኔ መንግሥት ይመሳሰላሉ ብሎ ያመናቸውን አንዳንድ ብሔረሰቦችን አጠራቅሞ “ወጋጋዳሶ” የሚል ቋንቋ ፈጥሮ የወል መታወቂያቸውና መጠሪያቸው እንዲሆን ሞክሮ ነበር። ግን ሕዝቡ በከፍተኛ ደረጃ በመቃወሙ ምርጫ አጥቶ ዕቅዱን ለሟሟላት ዐርባ ሚሊዮን ብር ቢያጠፋም ወደኋላ ማፈግፈግና መሰረዝ የግድ ሁኖበታል።

[11] ሊቅ ሙሐመድ ሐሰን በቅርቡ ባወጡት “ኦሮሞና ክርስቲያኑ የኢትዮጵያ መንግሥት፣ 1300-1700.” [Mohammed Hassen, The Oromo & The Christian Kingdom of Ethiopia, 1300-1700] መጽሐፋቸው የኦሮሞ ወረራ የተፈጸመው በሰላማዊ መንገድ ነው። በግራኝ ጦርነት አገሩ ተራቁቶ ስለነበር፣ ኦሮሞች በባዶው መሬት ሰተት ብለው ገቡ ይላሉ። ይሁንና አቋማቸው በጊዜው የነበሩት የውጭም የውስጥም አገር ጸሓፊዎች ከተውት ምስክርነት ጋር በግልጽ ይጋጫል ብቻ ሳይሆን እሳቸውም በተለያዩ በሌሎች ጽሑፎቻቸው እንዳደረጉ ሁሉ አሳማኝ የሆነ ተጨባጭ ማስረጃ አያቀርቡም።

[12] . አፄ ሠርፀድንግል እንደ አ.አ. በ፲፭፻፹ ዓ.ም. ድባርዋን የያዘውን ቱርክ እስተነአካቴው ከኢትዮጵያ ምድር ሊያባርሩት ይዘው ከሄዱት ጦር መካከል “የሰውን ደም ማፍሰስ የጠማው” የጋላ ጦር ነበር። Conti Rossini, trans. Ed., The Chronicle of Emperor Sarsa Dengel [Malak Sagad], p. 129

[13] . ትርጒሙ “የጽዮን ንጉሥና የኢትዮጵያ ነጉሠ-ነገሥት” ማለት ነው። ጽዮን የክርስቲያን እምነት የሚከተለውን የኢትዮጵያን ክፍል ሲያመለክት፣ ኢትዮጵያ ደግሞ የተለያየ እምነት የያዘውን አገር በሙሉ ያካትታል።

[14] . የንግሥ ስሟ አድማስ ሞገሳ የአፄ ዘርዐ-ያዕቆብ ባለቤት ነበሩ

[15] . ጸሓፊው አባቱ ከወረብ፣ እናቱ ከጐናን ምድር ሲሆን የተወለደው በመጤንት በደርኀ ምድር ነው ይላል። አንዳንድ ጸሓፊዎች ቦታዎቹ በወለጋ ውስጥ ይገኛሉ ቢሉም የተረጋገጠ ነገር የለም።

[16] . ገብረሕይወት ባይከዳኝ የማስተዋል ጸጋ የታደላቸው ታላቅ ምሁር ናቸው። ሕይወታቸው ባጭሩ ባይቀጭ ኖሮ፣ ላገራችን ብዙ ዕውቀት ባበረከቱ ነበር። ስለታሪክ ጸሓፊነት አስፈላጊ መስፈርቶች ሲናገሩ፣ ታሪክ መጻፍ በጣም አስቸጋሪ ሙያ ነው ብለው አበክረው ካስገነዘቡ በኋላ፣ መሟላት አለባቸው የሚሉትን ሦስት የሚቀጥሉትን ነገሮች ያማጥናሉ። አንደኛ፣ ድርጊቱን ለማስተዋል አመዛዛኝ ልቡና፤ ሁለተኛ፣ ድርጊቱን ለመፍረድ የማያዳላ አእምሮ፤ ሦስተኛ፣ያመዛዘኑትንና የፈረዱትን ለማስታወቅ የጠራ የቋንቋ አገባብ ናቸው ይላሉ። የሚያሳዝነው ብዙዎቹ የኢትዮጵያ ታሪክ ምሁራን ነን ባዮች የገብረሕይወትን ምክር ለማሟላት ተቸግረዋል።

[17] . በቅርቡ ሊቀማእምራን (ዶር.) ሕዝቅኤል ኢብሳ “Ethiopia: An Oromo Dilemma. The National Question and Democratic Transition” በሚል ርእስ በድረገጾች ያሰራጩት ጽሑፍ በሰገሌ ምድር፣ ባንድ በኩል በልጅ ኢያሱና በአባታቸው ንጉሥ ሚካኤል በሌላው ደግሞ በልጅ ተፈሪና (ኋላ አፄ ኀይለሥላሴ) በደጋፊዎቻቸው መካከል የተካሄደውን የሰገሌ ጦርነት በሚገርም መንገድ በወሎ ኦሮሞችና በሸዋ አማሮች እንደሆነ አድርጎ ያቀርበዋል። በሁለቱም በኩል የሚዋጉት አብዛኞቹ ኦሮሞች ወይንም የኦሮሞ ደም ያላቸው ሲሆን፣ ምሁሩ እንዴት አድርገው እንደዚህ ለመደምደም እንደበቁ አይናገሩም። ሊቁ በጀርመን አገር በታተመው በEncyclopedia Aethiopiaca ይልቁንም በኦሮሞ ታሪክ ዐምድ [vol. 4 O-X] ላይ በተጻፈው ብዙ የተዛባ ግንዛቤና አስተያየት አስቀምጠዋል። ጽሑፎቹ የሚከተሉት እንደነጆን ማርካኪስን [John Markakis] የመሰሉ ያገሩን ባህል ቀርቶ ቋንቋውን በፍጹም የማያውቁ ግራዘመም ምሁራንን ነው። እንደዚህ ዐይነቱ የታሪክ አተረጓጐም ቁልጭ አድርጎ የሚያሳየው የኢትዮጵያ ምሁራን ታሪክን የፖለቲካ ደንገጡር እንዳደረጓትና ምንስ ያህል የባዕዳን ቃል አስተጋቢዎች መሆናቸውን ነው።

[18] . ልክ ለ፲፫፻፹፰ ዓ. ም. ተለያይቶ የኖረ ሕዝብ ነበር ማለት ይቻላል።

[19] በኢጣሊያንኛ  “politica periferica” ይሉታል።

[20] . በኢጣሊያንኛ “politica scioana e politica tigrina” በመባል ይታወቃል።

[21] . በአፄ ምኒልክ ብልሃትና ችሎታ “የትግሬና የሸዋ ፖሊትካ፣” ኢትዮጵያን ከመበታተን ይልቅ ኢጣሊያንን እትልቅ ሽንፈት ላይ ጣላት።

[22] . ዘገባው “ኀይሥላሴ እያካሄዳቸው ያሉት ሥራዎች እጅግ አስደናቂ ከመሆናቸው የተነሣ፣ ሁናቴው በዚህ መልኩ ከቀጠለ እስካሁን የምናውቃት ትላንት በጥንት ባህሏ ተዘፍቃ የነበረችው [ኢትዮጵያ]፣ በጣም አጭር በሆነ ጊዜ ውስጥ ወደከፍተኛ ዘመናዊ ሥልጣኔ ትደርሳለች” ብሎ ከደመደመ በኋላ፣ የዳር ፖሊትካ እንዳልሠራና በትጋት አጠናክሮ በግብር መተርጐም እንዳለበት ይናገራል።

[23] . መጽሐፉ ተሰሚነት ለማግኘት፣ “ኢትዮጵያውያን ግብረ-ገብ የሌላቸው፣ ክብረኅሊና የጐደላቸው፣ ምግባረ ብልሹና በተፈጥሯቸው ብስብስ የሆኑ ሕዝብ ናቸው። … የሚኖሩት በጉልተኛ ባላባት ሥርዐትና በባርያ ፍንገላ ነው። … አማሮች የተለያዩ ነገዶችን በብርቱ በመጨቈን ላይ ይገኛሉ፤ አገሪቷ የብዙ ሕዝቦች እስርቤት ናት” በማለት ኢጣልያኖች ይነዙ የነበሩትን ስብከት ያሰራጫል።

[24] . ሌሎቹ የኢጣሊያን ቅኝ ግዛቶች ባዲሱ መዋቅር ገብተው ከነስማቸው ሲቀጥሉ ኢትዮጵያ የሚለው ስም ጠፍቶ፣ በካርታው ላይ የነበረው ስም የኢጣሊያን ምሥራቅ አፍሪቃ “Africa Orientale Italiana = አፍሪቻ ኦሪየንታሌ ኢታሊያና” ነበር።

[25] . በታሪክ እንደምናውቀው ሒትለር በአውሮጳ ወረራው ከያዛቸው አገሮች መካከል ነምሳ የመጀመርያዪቷ ነበረች።

[26] . “የጒልተኛ ባላባት” ሥርዐት ስል አውሮጳውያን ፊውዳሊዝም [feudalism] የሚሉትን ከሮማውያን ውድቀት ማግሥት ላይ የታየውን ሥርዐት ነው። የተማሪዎቹ ታላቁ ስሕተት አንደኛው የማኅበረሰብን ጥበብ [science] ልክ እንደሌላው የተፈጥሮ ጥበብ መልክ ማየታቸው ነው። ሁለተኛው ደግሞ በመምሰልና በመሆን መካከል ያለውን ልዩነት ባገባቡ አለመገንዘባቸው ነው። የኢትዮጵያ የመሬት ሥሪትና የምጣኔ ሀብት ቅርጽ ባንዳንድ ነገር ከአውሮጳውያኑ የጉልተኛ ባላባት ሥርዐት ይመሳሰላል። ግን በምንም መልኩ አንድ አይደለም። ባገራችን የባርያ ሥርዐት እንዳልነበረ ሁሉ፣ በማርክስ የተዋረድ እርከን ተከታዩ የነበረው የጉልተኛ ባላባት ሥርዐትም ከቶ አልነበረም።

[27] . የአፍሪቃን ቅኝ ገዚዎች የተካችው አሜሪቃ በቀዝቃዛ ጦርነትና በዐረብ-እስራኤል ግጭት ሰበብ ከሺ ዘጠኝ መቶ ስድሳዎቹ መጨረሻ ላይ ጀምሮ የነበራት መምርያ ከድሮው ከአውሮጳውያንን መርህ ብዙም የማይለይ እንደነበር የሚቀጥለው ክሲንጀር ለአሜሪቃ መንግሥት ያቀረበው ዘገባ የተወሰነም ቢሆን ጠቃሚ ፍንጭ ይሰጣል። “ኢትዮጵያ ሰላም ካገኘች፣ ሕዝቧ ሠራተኛና ታትሪ ሰለሆነ፣ በዓለም ብድር ዕዳም እንደሌሎቹ የሦስተኛ ዓለም አገሮች ተዘፍቃ የማታውቅና የኰራች አገር በመሆኗ አንድ ቀን አድጋ ራሷን የቻለች አገር ትሆናለች። ዕድል አግኝታ በዘመናዊ ሥልጣኔ ቢትገፋ፣ የሚትቻል አገር አይደለችም። ስለዚህ ከንጉሥ ኀይሌ ሥላሴ በኋላ ኢትዮጵያን የሚመራ መንግሥት ሰላም እንዳያገኝና፣ አገሪቷም እንደዐረብ አገሮች ተከፋፍላና ተነጣጥላ ካልተበታተነች በስተቀር፣ ለወደፊቱ በቀይ ባሕር ላይ አሜሪቃ የሚትጫወተው ሚና እንዳይመነምን እንዳያድጉ ማደናቀፍ ከሚገባቸው በቀይ ባሕር አዋሳኝ ታዳጊ አገሮች አንዷ ኢትዮጵያ መሆን አለባት። የቀይ ባሕር ወተት የሆነውን የዐረብን ነዳጅ በነፃ አለቀረጥ ማለብ የምንችለው፣ መንግሥታችን ኢትዮጵያን ከጎረቤቷ ከሱማሌ ጋር ብቻ ሳይሆን፣ ክፍለ ሀገሮቿን ራሳቸውን በሰሜንና በደቡብ ከፋፍሎ፣ የደከመውን ወገን በመርዳት፣ ያላመፀውን ጐሣ በማነሣሣት፣ ከዳር ድንበሯ ዘላለም ሁከትና ጦርነት እንዳይለያት በማድረግ፣ ፀረ-መንግሥት ተዋጊዎችን በሲአይኤ በማደራጀት በአገሪቷ ሰላም በመንሣት ብቻ ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ ጠንካራና ብርቱ ቢሆንም ቅሉ፣ በሥልጣን ፍላጎቱ ደካማ ጐን አለው። አንዱ በሌላው ላይ መንገሥ ዋና ምኞቱ ነው። በታሪካቸው ደሞክራሲያዊ መንግሥት መሥርተው አያውቁም። ከጥንት ጀምሮም ቢሆን አንዱ ንጉሥ ሌላውን በመግደል ሥልጣን መቀማትና ማመፅ ባህላቸው፣ ልማዳቸውና ታሪካቸዉም ነውና፣ እኛ ያሳደግነው ውሻም ቢሆን ሊነክሰን ቢሞክር በማስገልበጥ፣ ላንዲት ዘመን እንኳ በኢትዮጵያ ምድር ላይ ሰላም ሳይኖር፣ ሰሜናዊና ደቡባዊ፣ እንዲሁም ኤርትራ፣ ትግሬ፣ አማራ፣ ኦሮሞ እየተባባሉ እርስ በርሳቸው ሳይስማሙ ለረጅም ጊዜ ከኖሩ፣ ቀይ ባሕር ለአሜሪቃ መንግሥት ጠቃሚ በር ሁኖ ይኖራል። ሱማሌና ኢትዮጵያ ሰላም ሁነው አንድ ቀን ከተባበሩ፣ የአሜሪቃ ታላቅነትና ብልፅግና በቀይ ባሕርና በዓለም ላይ አይኖርም። ኢትዮጵያና ሱማሌ እማዶ ካሉት የዐረብ አገሮች ጋር በቀይ ባሕር ጥቅም ላይ ተስማምተው ቢዋዋሉ፣ የአሜሪቃና የአውሮጳ ሕዝብ “ቡፋሎ” ፍለጋ ወደጫካ መሄድ ካልሆነ በስተቀር፣ ጥበባችንን እንኳን ሽጠንና ለውጠን ለመኖር እንችልም። ሊቃውንቶቻችን ወደአፍሪቃ ሲፈልሱ ከሩቁ ማየትና መገንዘብ የኛ ተራ እንደሚሆን አንርሳ።” (ይኸ አሳብ በዶክተር ሔንሪ ክሲንጀር “የቀይ ባሕር ለጦር ሰልት ያለው ጥቅም” በማለት ለመንግሥታቸው ያቀረቡት ጥናት ሲሆን የአሜሪቃ መንግሥት የፓለቲካ መርህ መሆኑን በየጊዜው የወሰዳቸው ርምጃ ይደግፈዋል።)

[28] . በቅኝ ግዛት ባሉት አገሮች ያገሩ ተወላጅ ሕዝብ ወደፈለገበት አካባቢ ሄዶ ለመኖርና ለመሥራት ከፈለገ ልዩ መታወቂያ ያስፈልገዋል።

[29] . እዚህ መነሣት የሚገባው የኦሮሞ ምሁራን ነን ባዮች ዘውገኞች በየቦታው የሚነዙት ስብከት ነው። በቅርቡ ደግሞ እንደነሊቀማእምራን ጌታሁን [ላጲሶ] ድሌቦ የመሰሉት ዐይነቶች ወደዚህ እምነት እንደገቡ ኢሳት በተባለው የብዙኃን መገናኛ በሰጡት አሳፋሪ ቃለመጠይቅ መገንዘብ ይቻላል [Getahun Lapiso Interview on ESAT Radio October 15, 2015]።

 

አቡነ አብርሃም በባህርዳር ያደረጉት ታሪካዊ ንግግር ድምጽ እጃችን ገባ | ይዘነዋል

 

የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ አብርሃም ታሪካዊ መል ዕክት አስተላለፉ:: አቡነ አብርሃም ዛሬ ይህን ከተናገሩ በኋላ በመኪና አልሄድም ብለው በባህር ዳር ጎዳና ላይ ከሕዝብ ጋር አብረው ወደ ማረፊያቸው ሄደዋል:: ንግግራቸውን ሼር ያድርጉት::


አቡነ አብርሃም በባህርዳር ያደረጉት ታሪካዊ ንግግር ድምጽ እጃችን ገባ | ይዘነዋል