ከአድዋ ድል ማግስት፤ አጼ ምኒልክ እና ኤርትራ (ከ ሙሉጌታ ገዛኸኝ)

 

የአድዋውን ጦርነት ድባብ በርካታ የውጭ ጸሓፍት በስፍራው ተገኝተው የዘገቡት ቢሆንም ከአገሬው ዐይን እማኝ ታዳሚዎች መካከል የአጼ ምኒልክ መዋእለ ዜና አሰናጁ ጸሐፌ ትዕዛዝ ገብረ ሥላሤ ወልደአረጋይ ለዛ ባለው አገላለፅ ሲፅፉት ያስደምማል፡-« እንዲህም እስኪሆን ድረስ  ከሌሊቱ በ11 ሰዓት የጀመረ እስከ 4 ሰዓት ድረስ ተኩስ አላባራም፣ ድምፁም እንደ ሐምሌ ዝናብ እንደያማባራው ነበረ፤ በኖኅ ሰማዩ ተነድሎ መሬቱን አጠፋው እንደሚባለው እንደዚያ ይመስላል እንጅ በሰው እጅ የተተኮሰ አይመስልም፡፡ መድፉም ሲተኮስ ጢሱ የቤት ቃጠሎ መስሎ ይወጣ ነበር፡፡… ነገር ግን ከብዙ በጥቂቱ ጻፍን እንጅ የአድዋን ጦርነት በዐይናችን እንዳየነው በጆሯችን እንደሰማነው መጻፍ አይቻለንም፡፡» በማለት ከትበዋል፡፡

በጦርነቱ ስለወደቁ ጀግኖች አርበኞችም እጅግ አጥብቆ ኅዘን ሆነ፡፡ ከአድዋው ጦርነት ላይ የሚሞተው ይህ ሁሉ ሰው ለአገርና ለንጉሱ ፍቅር ሲያልቅ ያዩት አጤ ምኒልክ ልባቸው በእጅጉ ተነክቶ አዘኑ፡፡ እቴጌይቱም ስለአሽከሮቻቸው፣ ስለወዳጆጃቸው ማለቅ (ስለ ዘማቹ አርበኛ መስዋዕትነት) መሪር ኀዘን አዘኑ፡፡ ብርሃን የመሰለ ፊታቸው አጥላስ እስኪመስል አለቀሱ፡፡ ነገር ግን እንደተኩሱ ብዛት እንደቀኑ ርዝመት የሞተው ሰው ኀዘን መሪር ቢሆንም ስለቆመው ባንዲራና አገር ሲሉ ተፅናኑ፡፡ በማለት ጸሐፌ ትዕዛዝ ገብረ ሥላሤ ያወሳሉ፡፡

ለመሆኑ ከአድዋው ድል የምንማረው በጎ ነገር ምንድነው? ኢትዮጵያውን በጋራ አንድነትና ኅብረት ብረታት ፍቅርን ተላብሰው የውጭ ጠላትን ለመመከት በጀግንነት ወላፈን መተባበራቸውን እንጅ በጥላቻና በዘር የመከፋፈል አባዜን አይደለም፡፡

አሜሪካኖች በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የተቃጣባቸውን ጥቃት ለመከላከልና ኅብረት ለመፍጠር የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን “United we stand/strong divided we fall” በሚገባ እንዳጤኑት ልብ ይሏል፡፡ «እርስ በርሷ የምትለያይ መንግሥት ሁላ ትጠፋለች፤ እርስ በርሱ የሚለያይ ከተማም ሁሉ ወይም ቤት አይቆምም፡፡»ማቴ 12፡ 25 «መንግሥትም እርስ በርሷ ከተለያየች ያች መንግሥት ልትቆም አትችልም፤ ቤትም እርስ በርሱ ከተለያየ ቤት ሆኖ ሊቆም አይችልም፡፡»ማር 3፡25 ፡፡

ስለመረብ ምላሽ የኢትዮጵያ አካል ለጊዜው ተቆርጦ መቅረት ንጉሠ ነገሥቱ ቁጭት ያሳደረባቸው መሆኑን ልዩ ልዩ የሰነድ ማስረጃዎች ይገኛሉ፡፡ ከዚህ በተቃራኒ በአንዳንድ ፀሐፍት ዘንድ ከሚቀርቡት ትችቶች መካከል አጼ ምኒልክ ኤርትራ በኢጣልያ እጅ እንድትቆይ ሆነ ብለው የፈፀሙት ደባ ነው የሚለው አስተሳሰብ ተጠቃሽ ነው፡፡ ምክንያቱን ሲብራሩ ደግሞ ኢጣልያ የመረብ ምላሽ ግዛትን “ኤሪትሪያ” ብላ ሰይማ ቅኝ የምትገዛውንም ህዝብ ከቀሪው የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲነጠል በፀረ-ኢትዮጵያዊነት ጥላቻ ፕሮፖጋንዳ እንዲፈጠለፍ በማድረጓና ኤርትራውያንም በዚሁ ቅሬታ ውስጥ በመቆየታቸውን ንጉሠ ነገሥት ምኒልክ ማረጋገጣቸው ነው ይላሉ፡፡ ይህ አተያይ እውነታው ግልፅ ቢመስልም አጼ ምኒልክ ወደ ፊት ገፍተው እንዳይሄዱ አጣብቂኝ ውስጥ የከተታቸው የስንቅና ውሀ ተያያዥ ችግሮች ያላቸውን የሰው ሀይል አቅም ለጊዜው በመፈታተኑ ምክንያት ብቻ እንደሆነ አያጠራጥርም፡፡ ጥንት ኢትዮጵያ የነበራትን የሰሜኑን የባሕር በር ስትራቴጂያዊ ይዞታ ጠቀሜታውን አብጠርጥረው የሚያውቁት ዳግማዊ ምኒልክ ይቅርና በማናቸውም ዜጋ ህሊና ዘንድ የማይዘነጋ ነው፡፡ የአድዋ ጦርነት የተቋጨው ንጉሠ ነገሥቱ የመረብ ምላሽ ግዛታቸውን ከወራሪው ኢጣልያ ጦር መንጋጋ ለማስለቀቅ ከፍተኛ ቁጭት እንዳዘሉ መሆኑን በቀላሉ ለመረዳት አያዳግትም፡፡

ጦርነቱ በተጠናቀቀ በነጋታው አጼ ምኒልክ ከሰኞ እስከ ሀሙስ ውሎ አድርገው የሞቱትን ሲያስቀብሩና የቆሰለውንም እያነሱ በአድዋና አክሱም ሲያመሩ፣ መድፉን ነፍጡን የመድፉን አረር ሲያሰባስቡ ሰንብተው በ28 ቀን ሐማሴን ለመሻገር ወደ እንትጮ ተጓዙ፡፡ እንትጮ ሰፍረው ወደ ሐማሴን የሚያስከደውን መንገድ ሲያሰልሉ መሰንበቻ ሆነ፡፡ እዚያም ላይ እንደሰፈሩ የኢጣልያ ሹም በጦርነቱ ያለቁትን ኢጣልኖች ልቅበር ብሎ አጼ ምኒልክን ለማስፈቀድ መጣ፡፡ ወደ ንጉሠ ነገሥቱ ቀርቦ የኢጣልያ መንግስት ከግርማዊነትዎ ጋር እርቅ ወዷልና ከንጉስ ኡምቤርቶ ዘንድ ባለማኅተም ደብዳቤ እስኪመጣ ድረስ ወደ ሐማሴን አይሻገሩ ጦርዎን ያስቁሙልን ብሎ ለመነ፡፡ እሳቸውም እስከዚያው ድረስ ጦርነት ማድረግ እንዲቆይ ሲሉ ፈቃዳቸው ሆነ፡፡

ሆኖም አጼ ምኒልክ ኢጣልያኖችን ተዋግተው አድዋ ላይ አስደናቂ ድል ተቀዳጅተው ወቅቱ በፈቀደው የሞራል ብርታት አዲኳላን ተሻግረው እንዲሰፍሩና እዚያው እንዲቆዩአቸው የትግሬውን ገዥ ልዑል ራስ መንገሻን፣ የሐረርጌውን ገዥ ልዑል ራስ መኰንን፣ ፊታውራሪ ተክሌን፣ ሊቀመኳስ አድነውን እንዲሁም ሌሎችን ሰደዷቸው፡፡ እነሱም በታዘዙት መሰረት ወደ አዲኳላ ተሻግረው ቢወርዱም የመረብ ወንዝ ውሀ ደርቆ ስላገኙት እንኳን አካባቢው የአጼ ምኒልክን ጦር ሊያሰፍር ቀርቶ  ጥቂቱን ጋሻ ጃግሬ እንኳ በውሀ ጥም ተጨንቆ መክረሙን አሳወቋቸው፡፡ ንጉሠ ነገሥቱም የወንዙን ውሀ መድረቅ ቢሰሙ የእግዚአብሄር ፈቃድ ባሆን ነውና ተመለሱ ብለው ላኩባቸው፡፡ ከዚህም በኋላ አጼ ምኒልክም ወደ ሐማሴን ለመሻገር እያሰላሰሉ ከገንደብታ ተጉዘው አባገሪማ ጉልት ላይ ሰፍረው ሰነባበቱ፡፡ እዚያም ረቡዕና ሐሙስን ሲመክሩ ቆይተው ኢጣልያ ከያዘችው የመረብ ምላሽ አቅጫጫ ብትወጣም ባትወጣም ወደ ሐማሴን እንጓዝ ተብሎ በመኳንንቱ ዘንድ ቁርጥ ምክር ተመከረ፡፡  በሌላ በኩል ጆርጅ በርክሌይ ይህንኑ አስመልክቶ የአድዋ ዘመቻና የአጼ ምኒልክ አነሳስ በሚል በተተረጎመው መጽሐፉ ሲብራራ ከሁለቱም ወገን በጦርነቱ ያለቀው ሰው ቁጥር ቀላል ስላልነበረ አጼ ምኒልክም ለሠራዊታቸው የሚቀርቡት ስንቅ መመናመን እንዲሁም ኢጣልያ ተጨማሪ ሀይል ለማሰለፍ ብታደርግ በነበረው ሙከራ ከመረብ ወዲያ ያለውን ግዛታቸውን ለማስመለስ ለጊዜው ዘመቻው ፈታኝ መሆኑን አስቀድመው የተገነዘቡት ይመስላል፡፡  ቸር ይግጠመን!!!

ትልቅ አደጋ ከፊታችን ተደቅኗል (መሳይ መኮንን)

መሳይ መኮንን

Mesay Mekonnen, ESAT journalist

ትልቅ አደጋ ከፊታችን ተደቅኗል። የፊታችን ዓርብ የሚሰበሰበው ፓርላማ አስቸኳይ አዋጁ ላይ የሚሰጠው ውሳኔ የኢትዮጵያ ሀገራችንን ቀጣይ ቀናት፡ ሳምንታትና ወራት የሚለይለት ያደርገዋል። ይህ አስቸኳይ አዋጅ ካልተስረዘ አደጋው ከባድ ነው። ምናልባትም ወደ ከፍተኛ የእርስ በእርስ ግጭት ውስጥ ሊከተን ይችላል። ምንም እንኳን የለማ ቡድን በትግራዩ አገዛዝ የተበተነውን የዘር መርዝ በማምከኑ በተወሰነ ድረጃ ስጋቱን የቀረፈ ቢሆንም አሁንም ግዙፍ ዕልቂትን ሊያስከትሉ የሚችሉ ጉዳዮች እንደተወሳሰቡ ናቸው። የትግራዩ አገዛዝ ዓይኑን ጨፍኖ ”የአጥፍቶ መጥፋት” መስመር ላይ ወጥቶ ሽምጥ እየጋለበ ነው።

አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለኢትዮጵያ ህዝብ የሚያስገኘው አንዳችም ሰላምና መረጋጋት አይኖርም። አዋጁ የትግራዩን አገዛዝ ዕድሜ በጉልበት ለማስቀጠል የተወሰደ እርምጃ ነው። የህወሀት ባለሀብቶችና ከስርዓቱ ጋር የተጣበቁ ሰዎችን ንብረት ለመጠበቅ በሚል የታወጀ እንደሆነም ይታመናል። ይህ አዋጅ ኢትዮጵያውያን ላይ የተሰነዘረ የዕልቂት በትር ነው። መንግስት በሚባል አካል ህዝብ ላይ የታወጀ ጦርነት ነው። ነቀምት ላይ ተጀምሯል። ደምቢዶሎ ላይ ተፈጻሚ ሆኗል። በእርግጥ ለነጻነቱ ቁርጠኛ ውሳኔ ላይ የደረሰ ህዝብን ወደኋላ የሚመልሰው ምንም ሃይል አይኖርም። አዋጁን ህዝቡ አልተቀበለውም። ጥሶታል። በየቦታው የህዝብ ንቅናቄ የሚቆም አልሆነም።

አስቸኳይ አዋጁ በምክር ቤት አባላት አብላጫ ድምጽ ውድቅ ካልተደረገ ነገሩ አደገኛ ይሆናል። ለመሞት የቆረጠ ህዝብና ለመግደል የተዘጋጀው የትግራዩ አገዝዝ ተፋጠዋል። ህዝቡም ከመሞት፡ አገዛዙም ከመግደል የሚመለሱ አይደሉም። ይህ ደግሞ ወደ ህዝብ ለህዝብ ጦርነት የማምራት ዕድሉ ሰፊ ነው። የትግራዩ አገዛዝ ሃላፊነት የጎደለው በመሆኑ ይህን ከማድረግ የሚመለስ አይደለም። አጥፍቶ ለመጥፋት ወስኗል። አሁን ኳሷ ያለችው በፓርላማ አባላት እግር ስር ነው። ኢትዮጵያ ወደ ዕልቂት እንዳታመራ ማድረግ ይችላሉ። በፓርላማው ማዕቀፍ ስር በአስቸኳይ አዋጅ ስም ህዝብ ላይ የተጠራውን የሞት ድግስ ማስቀረት ካልቻሉ ታላቅ ታሪካዊ ጥፋት ሆኖ ይመዘገባል።

ዓርብ ወሳኝ ቀን ነው። የፓርላማ አባላት ከህዝባቸውና ከጨቋኙ አገዛዝ አንዱን ለመመረጥ ይሰየማሉ። ከወዲሁ ከትግራዩ አገዛዝ ጫናና ማስፈራሪያ እያደረሰባቸው ነው። ግን ከህዝብ የሚበልጥ ነገር የለም። በስልጣን ካልቆየሁ አጠፋችኋለሁ ብሎ የተነሳን የዘመኑን ጎልያድ በመፍራት ህዝብ ላይ የታወጀውን ጦርነት ይሁንታ ሰጥተው ያጸድቁታል ብዬ አልጠብቅም።ለ27 ዓመታት የትግራይ አገዛዝ አዳማቂ መሆናቸው በራሱ ትልቅ ወንጀል ነው። እናም ታሪካዊ ውሳኔ በእጃቸው ላይ ወድቋል። ዓርብ ዕለት።

ኦህዴድ እና ብአዴን፡ ህወሓት ቃሊቲ ሊስገባቸው ሲያስብ እነሱ የገቡትን ያስወጡት እንዴት ነው?

ባለፉት ጥቂት አመታት በኦሮሚያ ክልል እና በኦህዴድ ውስጥ የተካሄደው ለውጥ እንቅስቃሴ በዘፈቀደ የመጣ አይደለም። ከዚያ ይልቅ፣ በ2005 ዓ.ም አከባቢ በተወሰኑ የኦህዴድ አመራሮች እና የኦሮሞ ልሂቃን ተግባራዊ እቅድ ተዘጋጅቶለት የተጀመረ ሕዝባዊ ንቅናቄ ነው። የኦህዴድ አመራሮች ከውስጥ፣ የኦሮሞ ልሂቃን ደግሞ ከሀገር ወይም ከድርጅቱ ውጪ በመሆን የጀመሩት ንቅናቄ በ2006 ዓ.ም የአዲስ አበባ ማስተር ፕላንን በመቃወም በአምቦና ጊንጪ ከተሞች ተጀመረ። ከዚያ በመቀጠል በ2008 ዓ.ም የአማራ ክልል እና የተወሰኑ የብአዴን መሪዎችን በማሳተፍ ህዝባዊ ንቅናቄው በሀገር አቀፍ ደረጃ እንዲስፋፋ አደረጉ። ከአምስት አመት በኋላ ዛሬ ያለንበት ደረጃ ላይ ደረስን።

የአማራ ክልል ፕረዜዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው እና የኦሮሚያ ክልል ፕረዜዳንት ኦቦ ለማ መገርሳ

የንቅናቄው መሪዎች “የኢትዮጲያ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር መንግስታዊ ስርዓቱ የህወሓትን የስልጣን የበላይነት እና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ የተመሰረተ ከመሆኑ የመነጨ እንደሆነ ፅኑ እምነት አላቸው። በዚህ መሰረት፣ ሀገሪቱ ከገባችበት ግጭትና አለመረጋጋት እንድትወጣ ከብዙሃኑ የሕብረተሰብ ክፍል የሚነሱ የዴሞክራሲያዊ መብትና ነፃነት እንዲሁም የፍትሃዊ ተጠቃሚነት ጥያቄዎች በአግባቡ ምላሽ ማግኘት አለባቸው። በዚህ መልኩ የብዙሃኑን መብትና ነፃነት እንዲሁም ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የሚቻለው በእኩልነት መርህ የሚመራ ዴሞክራሲያዊ መንግስት ሲኖር ነው።

በዚህ መሰረት የኦሮሞና አማራ ሕዝቦችን እኩልነት እና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የሚቻለው የህወሓትን የስልጣን የበላይነት እና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት በማስወገድ ነው። በሌላ በኩል የኦህዴድ እና ብአዴን ሕልውና የተመሰረተው የሚወክሉትን የህዝብ እያነሳ ላለው የዴሞክራሲያዊ መብትና ነፃነት እንዲሁም ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ጥያቄዎች ተገቢና ተጨባጭ የሆነ ምላሽ መስጠት ሲችሉ ነው። በኦሮሚያ ከ2005 ዓ.ም፣ በአማራ ደግሞ ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ እየተካሄደና በፍጥነት ወደ ሌሎች የሀገሪቱ አከባቢዎች እየተስፋፋ ያለው ሕዝባዊ ንቅናቄና ተቃውሞ በሁለቱ የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ላይ የህልውና አደጋ ጋርጧል።

ቀደም ሲል ለመግለፅ እንደተሞከረው፣ የህወሓት አባላት እና አመራሮች ከሦስት አመታት በፊት የተዛባ አመለካከት እና የፈጠራ ወሬ ሲሉት እንዳልነበር ዛሬ ላይ “የህወሓት የበላይነት እና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት” መኖሩን አምነው ተቀብለዋል። ሕዝባዊ ንቅናቄው የተጀመረው በኦሮሚያ ክልል እንደመሆኑ ብዛት ያላቸው የኦሮሞ ልሂቃን የሕዝቡን የእኩልነት እና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ጥያቄዎች በማስተጋባት ላይ ይገኛሉ። የሕዝቡን ጥያቄ ተቀብሎ ለማስተናገድ ተነሳሽነትና ቁርጠኝነት ያላቸው የኦህዴድ አባላት ወደ አመራርነት መጥተዋል።

በአማራ ክልል ሕዝባዊ ንቅናቄው ዘግይቶ የተጀመረ ቢሆንም ባለፉት ሦስት አመታት ውስጥ ብቻ ብዛት ያላቸው የአማራ ልሂቃን የክልሉን ሕዝብ ጥያቄ ማስተጋባት ጀምረዋል። የክልሉ ሕዝብ ለሚነሳው የእኩልነት እና ተጠቃሚነት ጥያቄ የድጋፍ አዝማሚያ ያላቸው የብአዴን አመራሮች በድርጅቱ ውስጥ የበላይነት እየያዙ መጥተዋል። በእርግጥ የብአዴን አመራር ልክ እንደ ኦህዴዶች የአመራርነት ሚናውን ሙሉ በሙሉ አልተቆጣጠሩም። ነገር ግን፣ በክልሉ ፕረዜዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው እና በኮሚዩኒኬሽን ፅ/ቤት ኃላፊው አቶ ንጉሱ ጥላሁን ላይ ከሚያካሂዱት የውሸት ፕሮፓጋንዳ እና የስም ማጥፋት ዘመቻ የትኛው ቡድን ብአዴን ውስጥ የበላይነት እያገኘ እንደመጣ ይጠቁማል።

ባለፉት ጥቂት አመታት የታየው ሕዝባዊ አመጽና ተቃውሞ ኦህዴድ እና ብአዴንን “የመኖር ወይም የመጥፋት” አማራጭ ውስጥ ከትቷዋል። በዚህ መሰረት፣ ዛሬ ላይ ኦህዴድ እና ብአዴን ያላቸው ብቸኛ አማራጭ “የሚወክሉት ሕዝብ ለሚያነሳቸው የእኩልነት እና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ጥያቄዎች ተገቢ ምላሽ በመስጠት መኖር” ወይም “የህወሓት የበላይነት እና ተጠቃሚነት እንዲቀጥል በመፍቀድ ከህወሓቶች ጋራ አብሮ መጥፋት” ናቸው። ከሁለቱ አማራጮች ሌላ ሦስተኛ አማራጭ የለም። ምክንያቱም የህወሓት የበላይነት እና ተጠቃሚነት እስካለ ድረስ የኦሮሞና አማራ ሕዝቦ እኩልነት እና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት አይረጋገጥም።

በሌላ በኩል የሁለቱ ሕዝቦች እኩልነት እና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ከተረጋገጠ የህወሓቶች የበላይነት እና ተጠቃሚነት ያከትማል።   የህወሓትን የበላይነት እና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን ማስቀጠል የሚሹ አመራሮችና ልሂቃን ያላቸው አማራጭ መንግስታዊ ስርዓቱን ማስቀጠል ወይም ማፍረስ ነው። በዚህ መሰረት ቀንደኛ የህወሓት አመራሮችና ደጋፊዎች መንግስታዊ ስርዓቱን ለማስቀጠል የአማራና ኦሮሞ ሕዝብ ለሚያነሱት ጥያቄ የድጋፍ አዝማሚያ ያላቸውን የኦህዴድና ብአዴን አመራሮችን መወገድ እንዳለባቸው በይፋ አሳውቀዋል። በዚህ ረገድ ጥቅምት 21/2010 ዓ.ም አንድ የህወሓት ክፍተኛ አመራር “የኢህአዴግ የመፍረስ አደጋና የኢትዮጲያ ቀጣይ እጣ ፋንታ” በሚል ርዕስ ባወጡት ፅሁፍ የህወሓትን አቋም እንደሚከተለው ገልፀዋል፡-

 “… ኢህአዴግ ለህዝቡና ለዓላማው የሚቆረቆር ከሆነ ለግለ-ሰዎች ዝና መበገር የለበትም። ህዝበኞች እንደሆነ የአንድ ሳምንት አጀንዳ ከመሆን አያልፉም፡፡ ስለሆነም በተጨባጭ መረጃ የተገኘባቸው በቀጥታ ወደ ቃሊቲ እንዲወርዱ ማድረግ የተለያየ የፖለቲካ ሴራ የፈፀሙ ግን ደግሞ ተጨባጭ መረጃ ከሌለ መረጃ እስከሚመጣ መጠበቅ ሳይሆን ፖለቲካዊ እርምጃ መውሰድ፡፡ ሂደቱ እንደተለመደው ላይ ላላ ብሎ ታች መጠንከር ሳይሆን ድርጅቱ እንደ አሳ ከጭንቅላቱ እየሸተተ ስለሆነ ከበላይ አመራር መጀመር አለበት፡፡ ከበላይ አመራር የሚጀመረው አበል መጨመር ብቻ ሳይሆን ቅጣትም ከበላይ አመራር መጀመር አለበት፡፡ ይሄ ተጠናክሮ በሚሄድበት ይህን ስርዓት ማስቀጠል የሚፈልግ ህዝብና አገር ወዳድ በርካታ ስለሆነ ከነዚህ ሆዳሞችና ከሃዲዎች በኋላ የሚፈጠር ስጋት አይኖርም።”

ከላይ በፅሁፉ በተገለፀው መሰረት የኦህዴድና ብአዴን አመራሮችን ወደ ቃሊቲ እስር ከማውረድ ይልቅ በቃሊቲና ሌሎች እስር ቤቶች የሚገኙ የፖለቲካ እስረኞች መፈታታቸው ይታወሳል። በዚህ መሰረት፣ የህወሓት በኦህዴድና ብአዴን ጥምረት መሸነፉን መረዳት ይቻላል። ሆኖም ግን፣ ሰሞኑን የታወጀው የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ጨምሮ ህወሓት የሚከተለው አቅጣጫ ከላይ በተጠቀሰው ፅሁፍ በተገለፀው መሰረት እንደሆነ መገንዘብ ይቻላል። ስለዚህ የድርጅቱ አመራሮችና ልሂቃን የህወሓትን የበላይነትና ተጠቃሚነት ከማስቀጠል በዘለለ ምንም ዓይነት ለውጥ እንዲካሄድ አይፈልጉም።

በተቃራኒው ኦህዴድና ብአዴን ሰሞኑን ያካሄዱትን ስብሰባ ተከትሎ ባወጡት ድርጅታዊ መግለጫ መሰረት፣ መንግስታዊ ስርዓቱን ለመታደግ ፍትሃዊ የስልጣንና የሃብት ክፍፍል ሊኖር እንደሚገባ በግልፅ አስቀምጠዋል። የኦህዴድና ብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ በየፊናቸው ባወጡት ድርጅታዊ መግለጫ መሰረት ህወሓት በመንግስታዊ ስርዓቱ ውስጥ ያለውን የበላይነት እና ተጠቃሚነት ለመጋፈጥ መወሰናቸውን እንደሚከተለው ገልፀዋል፡-
ከኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) ማዕከላዊ ኮሚቴ የተሰጠ ድርጅታዊ መግለጫ፡- 

“የፌዴራላዊ ስርዓታችንን አደጋ ላይ የጣሉ ሙስናና ብልሹ አሰራሮችን፣ ሕዝቡ በመሪ ድርጅቱ ላይ እንዲያምጽ ያስቻሉ የመልካም አስተዳደር እጦቶችን፤ ስልጣን ህዝብን ማገልገያ መሳሪያ መሆኑን በመዘንጋት በርስትነት ይዞ ለግል ምቾትና ጥቅም ቅድሚያ መስጠትን፣ በነጻነት ተዘዋውሮ የመስራት መብትን ነፍጎ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ሕዝቦችን እስከማፈናቀል የደረሰ ድርጊትን፤ በኢንቨስትመንት ስም የመንግስትና የህዝብ መሬት መመዝበሩን፤ እንዲሁም የሕዝቦች ሰላምና ጸጥታ መደፍረሱን እና የመሳሰሉትን እየተፈጸሙ ያሉ አደገኛ ድርጊቶችን ሕዝቡን ባሳተፈ መልኩ አምርሮ በመታገል የሀገራችንን ሕልውና መታደግ ልዩ ትኩረት የሚሹ አበይት ጉዳዮች መሆናቸውን በዝርዝር ተመክሮባቸዋል፡፡” ከኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ የተሰጠ ድርጅታዊ መግለጫ፥ ጥር 29/2010 ዓ.ም

የብሄረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) ማዕከላዊ ኮሚቴ የሰጠው ድርጅታዊ መግለጫ፡- 

 “የፌደራል ስርዓታችንን አደጋ ላይ የሚጥሉ እና የህዝባችንን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት የሚጐዱ ማናቸውንም ዝንባሌዎችና ተግባራት ያለምንም ማመንታት መታገል እንደሚገባ አፅንኦት ሠጥቶ ተወያይቷል፡፡ በፌደራል ስርዓታችን  ውስጥ የፍትሃዊነት መጓደል የሚታይባቸውን ማናቸውም ዘርፎች የማስተካከል ስራ እንዲሠራና ለወደፊቱም ጥርጣሬ የሚያነግሱ መሰል ተግባራት  እንዲታረሙ ተገቢ ትግል እንዲደረግ ስምምነት ላይ ደርሷል፡፡ የፌደራል ተቋማት የሰው ሃይል አደረጃጀት ብቃትንና ብሄራዊ ተዋጽኦን ማእከል በማድረግ እንዲደራጅ እና የሚታዩ ክፍተቶችን ለማረም ተቋማቱን ሪፎርም የማድረግ ስራ እንዲሰራም የበኩሉን ሚና መጫወት እንደሚገባው ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡” የብአዴን ማእከላዊ ኮሚቴ፥ ባህር ዳር፡ የካቲት 16/2010 ዓ/ም

ሆኖም ግን፣ እንደ አቶ አባይ ፀሃየ ያሉ የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች የህወሓትን የበላይነት እና ተጠቃሚነት የሚጋፋ ማንኛውም ዓይነት ለውጥን ለመቀበል ፋቃደኛ አለመሆናቸውን ገልፀዋል። አቶ አባይ ፀሃየ ወቅታዊ የሀገራችን ፖለቲካዊ ሁኔታን ኣስመልክተው በትግሪኛ በሰጡት አስተያየት “ቁጥር የሚጠቅመው ለፖለቲካ ሳይሆን አራቱን የሂሳብ ስሌቶች ለመለማመድ ነው” ማለታቸው ተገልጿል። በዚህ መሰረት አብላጫ ድምፅ ያላቸው የኦሮሞና አማራ ሕዝቦችን እኩልነት እና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚደረግ ማንኛውም እንቅስቃሴ ተቀባይነት እንደሌለው አስታውቀዋል። በሌላ በኩል የኦህዴድና ብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ የክልላቸውን ሕዝብ እኩልነትና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ምርጫና አማራጭ የሌለው የህልውና ጉዳይ መሆኑን በይፋ አስታውቀዋል። “በሁለቱ የለውጥ እና ፀረ-ለውጥ ኃይሎች መካከል ያለው ፍጥጫ ሀገራችንን ወዴየት ይወስዳት ይሆን?” የሚለው በቀጣይ ክፍል እንመለከታለን።

” ቆራጣው ዮሀንስን ” ፍለጋ [ ቬሮኒካ መላኩ]

እኔ ከፌስ ቡክ ከተወገድኩ በኋላ በኢትዮጵያ ሰማይ ስር ብዙ ነገሮች ተከስተው አለፉ። 
ምስኪኑ ጠቅላይ ሚ/ር ሀይለማሪያም ደሳለኝ ከስልጣኑ ተወገደ ወይም ራሱን አስወገደ ።

ታላቁ የግሪክ ፈላስፋ አርሲጣጢለስ፤ “የሰው ልጅ ፖለቲካዊ እንስሳ ነው” ብሎ ያኖረው ዘመን ተሻጋሪን ምልከታ እውን ይሆን ዘንድ “ፖለቲካ አልወድም ” ሲል የከረመው ኢትዮጵያዊ ሁሉ ቀጣዩን ጠቅላይ ሚኒስቴር በመተንበይና በጉዳዩ ላይ በመተንተን ተጠምዶ ከረመ ።



እርግጥ ስለመሪዎች ከዚህም የበለጠ መወራት አለበት የሚል እምነት አለኝ ። ግለሰብ መሪዎች የአንድን አገር እጣፋንታና የሚሊዮኖችን እድል የመወሰን እድላቸው ከፍተኛ ነው። አፄ ሀይለስላሴ ለአምባሳደር ብርሃኑ ድንቄ እንደነገሩት ” ህዝብ መምራት የበግ መንጋ አሰማርቶ እንደ መጠበቅ ቀላል አይደለም ።” በዚህም የተነሳ ኢትዮጵያውያን ” ቀጣዩ ጠቅላይ ሚኒስትር ማን ይሆን ?” እያሉ ቢብሰለሰሉ ትክክል ናቸው።

የሮማን ኢምፓየርን ዋና ከተማ ሮምን እሳት ለኩሶ ከተማይቱን ስትጋይና አመድ ስትለብስ እየሳቀ ሲዝናና የነበረው ፣ በሮማ ኮሎስየም ህዝቦችን ለቀናት ለተራቡ አንበሳና ነብር ወርውሮ ከትዳር ጓደኛዋ ጋር ወይኑን እየተዝናና ይጎነጭ የነበረው ፣። ” ምነው ይሄ በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ህዝብ አንድ አንገት በኖረውና በሰይፍ በቀላሁት ። ” እያለ የተመኘውና ሮምን የሽብርና የቅዤት ከተማ ያደረጋት ኔሮ አንድ ግለሰብ ነበር።


ጀርመንን አዋህዶ ታላቅ ያደረጋት ኦቶ ቫን ቢስማርክም ሆነ ጀርመንን ወደ የሰው ልጅ መታረጃ ቄራና ምድጃ የቀየራት ሂትለር ሁለቱም ግለሰቦች ናቸው።
ኢትዮጵያን የአፍሪካ የነፃነት ጉልላትና የአለም ጥቁር ህዝቦች ምልክት ያደረጋት እምዬ ምኒልክም ሆነ ኢትዮጵያን ገነጣጥሎ የዜጎች መቀቀያ ድስት ያደረገው መለስ ዜናዊ አንድ ግለሰብ ናቸው። ግለሰብ መሪዎች በአንድ አገርና ህዝብ እድል ላይ በአዎንታዊውም ሆነ በአሉታዊ መልኩ ተፅእኗቸው ከፍተኛ ስለሆነ በጉዳዩ ላይ መወያየቱ ትክክል ነው።

አሁን ወደ ተጨባጩ የአገራችን ሁኔታ ስንመለስ ህውሃት ሀይለማሪያምን የሚተካ “ቆራጣው ዮሀንስን” ፍለጋ በር ዘግቶ እያሴረ ይመስላል። እዚህ ላይ ስለ 70 አመት አዛውንቱና እጄ ቆራጣው ዮሀንስ ለማውራት ጊዜ ባይኖረኝም ቆራጣው ዮሀንስ ማለት በ17ኛው ክዘ የሰሜን ጎርፍ አምጥቶ ጎንደር ላይ የጣለው ሚካኤል ስሁል የሚባል ወንበዴ ከወህኒ አምባ ደካሞችን እየመረጠ ዙፋን ላይ ወዝፎ እንደ አሻንጉሊት ከተጫወተባቸው ንጉሶች መካከል የመጨረሻው ንጉስ ነበር።

በእኔ አመለካከት የመጨረሻው ” ቆራጣው ዮሀንስ” ሀይለማሪያም ደሳለኝ ይሆናል ብዬ አስቤ ነበር ነገር ግን ደመቀ መኮንን ሽፈራው ሽጉጤና አቢይ አህመድ የሚባሉ ተራ ይዘው ተኮልኩለው እየጠበቁ ነው።


ሽፈራው ወይም ደመቀ መኮንን የጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ስልጣን የሚይዙ ከሆነ የአቦይ ስብሃት የሽንት ጨርቅ ቀያሪ ከመሆን የዘለለ ሚና አይኖራቸውም ። በአቢይ አህመድም ቢሆን መተማመን ያስቸግራል።

እርግጥ የኦሮሞ አክቲቪስቶች አቢይ አህመድ የሚባል “ነቢይ ” እየመጣ እንደሆነ በመስበክ
ዳረጎቱን ህዝቡ አሜን ብሎ እንዲቀበል እውነታውን በማጥበረበር ወይም “ፎልስ ኮንሸስነስ” መፍጠር የፕሮፓጋንዳቸው ተቀዳሚ ሥራ ሆኗል።

ከነዚህ ሶስት ሰዎች የተሻለውን ለመምረጥ
በቅድሚያ በአገራችንን የናኘውን ውስብስብ ነባራዊ የፖለቲካ ሁኔታ መመርመር ያስፈልጋል። አሁንም ህውሃት የተባለው ቡድን የሚናከስበት አብዛኛው ጥርሱ ወላልቆ በድዱ ቢቀርም አሁንም መከላከያና ደህንነት የሚባሉ ሁለት ጥርሶች ቀርተውታል ። ቀጣዩ ጠቅላይ ሚኒስትር በህግ በተሰጠው ስልጣን ተጠቅሞ እነዚህን ሁለት ጥርሶች መንግሎ የሚጥል ከሆነ ታሪክ ይሰራል።

አሜሪካኖች እንደሚሉት ” ትላልቅ ችግሮች ታላላቅ መሪዎችን ይወልዳሉ ።”

ሁለተኛው

የአለም ጦርነት ዌንስተን ችርችልንና ሩዝቬልትን ወልዷል። በእኛም አገር ዘመነ መሳፍንት የሚባለው የችግርና የፈተና ወቅት አፄ ቴዎድሮስን የሚያክል ታላቅ መሪ ወልዶልናል ።
ዛሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ችግር ውስጥ ነች ። ነገር ግን ዛሬም ኢትዮጵያ የወላድ መካን አይደለችም ። ከወያኔ ውስጥ መሪ የሚሆን ቢጠፋም ከተቃዋሚው ጎራ ውስጥ ታላላቅ መሪዎች ተፈጥረዋል። ኮለኔል ደመቀ ዘውዴ ፣ እስክንድር ነጋ ፣መረራ ጉዲና ፣ በቀለ ገርባ አንዱአለም አራጌ እና ሌሎችን ታላላቅ ሰዎች ወልዳለች።

አሁን በተጨባጭ እንደምንመለከተው ወያኔ እንደ ሀይለማሪያም ደሳለኝ የሚዘውረው ባለተራ ” ቆራጣው ዮሀንስ ” ከመፈለግ ለአንድትም ሰከንድ አያርፍም።።
ስሁል ሚካኤል በ17ኛው ክዘ እሱ ራሱ ንጉስ ሆኖ መግዛት ስለማይችልና የነጋሲነት ዘር ስላልነበረው ደካሞችን አየፈለገ በእጅ አዙር ለመግዛት ሞክሮ ነበር ።
ዛሬም ህውሃት የጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ቦታ እንደማታገኝ ስታውቅ በእጅ አዙር “ጡል ጡል ” እያለ የሚላላካትን አሻንጉሊት ጠቅላይ ሚኒስትር ፍለጋ ላይ ነች ። ሽፈራውሽፈራው ሽጉጤ በመላላክ ከሀይለማሪያም ቢበልጥ እንጅ የሚያንስ አይደለም። ደመቀ መኮንንም “የጎባጣ አሽከር ” የሚባለው አይነት ነው ። ብዙ ተስፋ የተጣለበት አቢይ አህመድ ነው ። አቢይንም ቢሆን ከጣሪያ በላይ የሚሰማው ያልተገራና ያልበሰለ የቄሮ ጫጫታ አደንቁሮት ሊሆን ስለሚችል አስተማማኝ አይደለም ። በዚህ ሁሉ ፍትጊያ ቀጣዩ ” ቆራጣው ዮሀንስ ” ማነው ካላችሁኝ ደመቀ መኮንን ይመስለኛል።የዚህን ግምታዊ ስሌት ለማወቅ በጣም ቀላል ነው። ህውሃት ከኦህደዱ እጩ አቢይ አህመድ ይልቅ የብአዴኑን ደመቀን ይመርጣል ። ሌላው ድርጅት ዴኢህዴን የህውሃት የጓሮ እርሻና የአትክልት ቦታ ስለሆነ በህውሃት የታዘዘውን መሪ እንድመርጥ ይደረጋል ። አቢይ አህመድ የሚያገኘው ድምፅ የኦህዴድን እና ትንሽ የብአዴንን እጆች ብቻ ነው። በዚህ ስሌት መሰረት ቀጣዩ “ቆራጣው ዮሀንስ ” የገደል ስባሪ የሚያክለው ደመቀ መኮንን ይሆናል ማለት ነው።

ለማንኛውም ለእኛ ኢትዮጵያውያን ሁነኛ መፍትሄው ሀይለማሪያም የተባለ ጉልቻ በአቢይ ወይም በደመቀ መቀየር ሳይሆን ስርነቀል ለውጥ ነው። ማንኛውም ስርዓት እንደ ሰው ይወለዳል፤ ያረጃል ይሞታል ። ወያኔ ከማረጀትም አልፎ አርጧል ። ከዚህ በኋላ ወያኔ ላባውን በማራገፍ ንስር መሆን አይችልም። በዚህም መሰረት ከልሂቃኑ የሚጠበቀው ለውጡ አስፈላጊ መሆኑን በመረዳት፤ ከለውጡ ቅኝት ጋር ተስማሚ የሚሆን አቋም በመያዝ፤ ለለውጥ ፈላጊው ህብረተሰብ ጥያቄ ምላሽ የሚሰጥ የሚመጥን ስርአት ይመጣ ዘንድ ትግሉን መቀጠል ብቻ ነው።

ብአዴን፤ ህወሃት፤ በረከትና ሌሎችም

ከሚኪ አማራ

የሃይለማሪያም ስልጣን መልቀቅ የበረከትና የአባዱላ ጥምረት ግፊት መሆኑ ታዉቋል፡፡ ሀወሃት በጉዳዩ ላይ ሲያመነታ እንደነበርና እንዲሁም የእነ አባዱላን ዉሳኔ ተከትሎ የእልክ በሚመስል መልኩ ፈጥኖ ወደ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንደሄደም ተነግሯል፡፡ በኢህአዴጉ የ 17 ቀን ስብሰባ አባዱላ ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ላይ ጄኔራሎችን መቆጣጠር አልቻለም የሚል ክስ አቅርቦበት ነበር፡፡ በረከትም አልቻልክም የአመራር ክፍተት ተፈጥሯል በዚህም ምክንያት ድርጅቱና አገሪቱ አደጋ ላይ ወድቀዋል የሚል ትችት ሰንዝሮ ነበር፡፡ ሀወሃት ሃይለማሪያምን ቢደግፍም ዉሎ አድሮ ግን ለድርጅቱ ህይወት አስጊ መሆኑን በመረዳቱ ከመደገፍ ይልቅ ለዘብተኛ አቋሙን አንጸባርቋል፡፡


በረከት ቀጣይ ሚሽኑ የነበረዉ በስመ ሪፎርም ከአለምነዉ መኮነን፤አዲሱና ከበደ ጫኔ ጋር በመሆን ገዱን ጨምሮ አሁን የማልጠቅሳቸዉ ሌሎች በመጠኑም ቢሆን የህወሃትን ረዥም እጅ እንዲያጥር የሚከራከሩ የማእከላዊ ኮሚቴ ሰወችን ለማባረር ወስነዉ ነበር፡፡ ነገሩ ግን ወዲህ ነዉ ስብሰባዉ እየተጋመሰ ሲመጣ ያልጠበቁት resistance ከሌሎች የብአዴን አባሎች ጠበቃቸዉ፡፡ ወዲያዉም አለምነዉ ህዝቡ ለዉጥ ይፈልጋል የእኛን ዉሳኔ እየጠበቀ ነዉ ብሎ ለመከራከር እንዲያመቸዉ ከስብሰባዉ አቋርጦ በመዉጣት ለህወሃት ደጋፊዉ ለሪፖርተር ጋዜጣ ትልልቅ ዉሳኔዎችና ለዉጦችን ይዘን እንመጣለን በማለት መግለጫ ሰጠ፡፡ ይሄም የማእከላዊ ኮሚቴዉን ህዝቡ እራሱ እየጠበቀን ነዉ፡ ለህዝብ ቃል ገብተናል መባረር ያለበት አመራር ይባረራል መጠየቅ ያለበትም ይጠየቃል የሚል ክርክር ይዞ መጣ፡፡ ነገር ግን አልተሳካም፡፡

የገዱን መዉረድም አጥብቀዉ ፈልገዉ የነበሩ ቢሆንም አብዛኛዉ የማእከላዊ ኮሚቴዉ ከገዱ ጎን በመቆሙ ሳይሳካ ይቀራል፡፡ ህወሃትም ማእከላዊ ኮሚቴዉ ገዱን ለማዉረድ እንደማይፈለግ ሲያዉቁ በተለያየ መንገድ ጫና ለማድረግ ሞክሯል፡፡ ለምሳሌ በህወሃት ደጋፊዎች አማካኝነት ገዱ ወርዶ በሌላ ተተክቷል የሚል ዜና ሰሩ፡፡ ይሄም ታስቦ የነበረዉ እኛ በዉጭ ብናራግበዉ ስብሰባዉ ዉስጥ ያሉትን የብአዴን አባላትን አነሳስቶ በገዱ ላይ እርምጃ ይወስዳሉ ብሎ በማሰብ ነበር፡፡ ከወረደም የአንባሳደርነት ሚና እንሰጠዋለን የሚል ገዱንም ሆነ ደጋፊወችን reassure የማድረግ ፕሮፖጋንዳም ተሰርቷል፡፡ በዚህ መሃል ግን ጭራሽ ነገሩ ተገልብጦ አለምነዉ ተገምጋሚ ሁኖ ቁጭ አለ፡፡ በግምገማዉም ባህርዳር መሃል ከተማ ላይ ይሄን ትልቅ ቤት የት አምጥተህ ሰራህ፡፡ በወር ከ20ሺህ ብር በላይ እያከራየህ የምትኖዉ የመንግስት ደሞዝህ ይሄን ያሰራል ወይ የሚል ጥያቄወች የቀረቡበት ሲሆን፡፡ ቤቱ ያለቀዉ መጽሀፍ ሽጨ ነዉ፤ የተለያዩ ድርጅቶች የቦርድ አባል ነኝ እሱን እሱን ሰብስቤ ነዉ ቢልም ሰሚ አላገኘም፡፡ የስልጣን ጥም አለብህ፤ እኔ ብቻ ነኝ ለክልሉ የማዉቅለት ትላለህ፤ ሌሎችን ታሳንሳለህ፤ ቡድን ዘርግተሃል የሚሉ ግምገማወች ቀርበዉበታል፡፡ በክልሉ ህዝብ ተቀባይነት እንዴለለዉና ለምሳሌ ያህል በቆቦ የተፈጠረዉን ችግር እኔ ነኝ የምፈታዉ ብሎ ቢሄድም እንኳን ሊፈታ አባብሶ ነዉ የመጣዉ የሚል ወቀሳ ሁሉ ቀርቦበታል፡፡

ገዱ ወደ ስልጣን ሲመጣ አለምነዉ የገዱ ቡድን የነበረ ሲሆን አሁን ተገልብጦ ገዱን ክልል አትመራም አንተም ሆነ እኔ አንመራም እንዳለ ተሰምቷል፡፡ አለምነዉ ቡድን በመመስረትና የእሱን ሃሳብ የማይቀበሉትን በተደራጀ ሁኔታ በማባረርና ከክልሉ ቢሮወችና ከድርጅቱ በማራቅ ይታወቃል፡፡ በዚህኛዉ ስብሰባ ግን የአለምነዉና የበረከት ቡድን ተሸናፊ ሁኖ ወቷል፡፡ ጭራሽ አለምነዉ ባላሰበዉ መንገድ ከክልሉ ስልጣን የመራቅ ሁኔታ አንዣቦበታል፡፡የተባለዉ ሪፎረምም በሽኩቻ ምክንያት ምንም ነገር ሳይካሄድ ቀርቷል፡፡ በመግለጫ አጻጻፍ ጉዳይ እንኳን ሌላ ንትርክ አንስተዉ ነበር፡፡

ስለዚህም ለሶስተኛ ግዜ የስልጣን ማዉረድ ሙከራ ህወሃት በገዱ ላይ ቢሞክርም ሳይሳካ ቀርቷል፡፡ ነገር ግን የብአዴን መአከላዊ ኮሚቴ ገዱን አላስነካም ቢልም ደመቀ መኮነንን ግን ማዉረድ አልቻለም፡፡ ማእከላዊ ኮሚቴዉ ገዱን የብአዴን ሊቀመንበር እንዲሆን ቢፈልግም የበረከት ቡድን የደመቀ መኮነን ደጋፊ በመሆኑ ሁለቱም ቡድን ሳይጎዳዳ (compromise አድርገዉ) የየራሱን ሰዉ ባለበት አስቀምጦ ወቷል፡፡ በዚህ ሽኩቻ ማህል ግን ምናልባትም ለአማራ ህዝብ ሊጠቅሙ የሚችሉ ዉሳኔወች ባለመካሄዳቸዉ ተጎጅዉ ያዉ ህዝቡ ይሆናል ማለት ነዉ፡፡

ሌላዉ ግልጽ የሆነዉ ነገር የአማራ ክልል ምክር ቤት 100% የገዱ ደጋፊ ሲሆን የብአዴን ማእከላዊ ኮሚቴ ከ 95% በላይ ገዱን ይደግፋል፡፡ ስለዚህም ገዱን እንኳን ህወሃት ብአዴን እራሱ ላዉርድ ቢል አሁን ባለዉ ሁኔታ ማዉረድ አይችልም፡፡ ገዱ ከዚህ በኋላ የሚወርደዉ ኢሀዴግ ሲወርድ ይመስላል፡፡ በራሱ ፍላጎት እንኳን ለመዉረድ ደጋፊዎቹ የሚፈቅዱለት አይሆንም፡፡ ህወሃት የገዱን መዉረድ አጥብቆ የሚፈልገዉ ገዱ ይጎዳኛል ብሎ አይደለም፡፡ የገዱ መዉረድ ለህወሃት symbolic value ስለአለዉ ነዉ፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ የብአዴን ሰወች ገዱ ከማንም የተሻለ ነዉ ብለዉ ሳይሆን የገዱ መኖር ለነሱም symbolic value ስላለዉ ነዉ፡፡

ሀወሃት የደህዴንን ማእከላዊ ኮሚቴ አስገድዶም ቢሆን ሁለት ለህዋሀት በታማኝነት የሚያገለግሉ ሃላፊዎቹን አስመርጧል፡፡ በኦህዴድና በብአዴን ሰወች ከቀን ወደ ቀን እምነት እያጣ በመምጣቱ ቢያንስ አንድ ጠንከራ ቡድን እንደሚያስፈልገዉ ስለተረዳ ደህዴንን መጀመሪያ የመረጡትን ምርጫ አንስተዉ እደገና ሌላ ዉሳኔ አንዲያካሂዱ በማስገደድ ሁለት የራሱን ሰወች ወደ ፊት በማምጣት ትንሽ ትንፋሽ ገዝቷል፡፡

በረከት ከበስተጀርባ ሁኖ ኢህአዴግን እንደገና ተረክቧል፡፡ ህዋሀት ከ crisis መዉጫ ሃሳብ ማመንጨት ባለመቻሉ ለጊዜዉ በረከትን ነጻነት በመስጠት የችግር መዉጫ ስትራቴጅና የፖሊሲ አቅጣጫ እንዲነድፍ ተደርጓል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ብአዴንን የማጥራት ስራ እንዲሰራ ቢደረግም በሰሞኑ ስብሰባ ግን ያን ማድረግ አልቻለም፡፡ ለጊዜዉ ባይሳካለትም፡ ሰዉየዉ ግን በረከት በመሆኑ ነገ በፈለገዉ መንገድ ማጽዳቱ አይቀርም፡፡ በረከት ትልቁ ችግሩ ኢትዮጵያ ዉስጥ በመጥፎም ሆነ በጥሩ ጎኑ የራሱ ስም ብቻ እንዲናኝ ይፈልጋል፡፡ ሰዉየዉ በህክምናዉ ዘንድ Narcissistic personality disorder የምንለዉ በሽታ ተጠቂ ነዉ፡፡ ገዱን በተደጋጋሚ የሚከሰዉ ስምህ ከድርጅት በላይ ገኗል የሚል ነዉ፡፡ እኛ ለድርጅት እየታገልን እንደ ጭራቅ እንታያለን እናንት ስማችሁን ትገነባላችሁ ይላል፡፡ በበረከት አይን ለማ መገርሳም ሆነ ዶ/ር አብይ በዚሁ ስሌት የሚታዩ ይሆናሉ ማለት ኑዉ፡፡ ስንተረጉመዉ ለደ/ር አብይ ጠቅላይነት የበረከት ይሁንታ ወሳኝ ነዉ ማለት ነዉ፡፡ እንግዲህ አባዱላ ካላሳመነዉ በቀር በረከት ከላይ ከተባለዉ የተለየ አመለካከት አይኖረዉም፡፡ በዛ ላይ በኢህአዴግ ዉስጥ ህዝባዊነት የሚያጠቃዉ ሰዉ ካለ በማንኛዉም መንገድ ዋጋ ይከፍላል፡፡ ይህ የድርጅቱ መርህ ነዉ፡፡

ሁሉም ኢትዮጵያዊ ይህን ያዳምጥ | እኛን በማዘናጋት እየተሰሩ ያሉ ሴራዎች | ዶ/ር ዲማ ነገዎ፣ ሻለቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስና ዶ/ር ጌታቸው በጋሻውን ይስሟቸው


ሁሉም ኢትዮጵያዊ ይህን ያዳምጥ | እኛን በማዘናጋት እየተሰሩ ያሉ ሴራዎች | ዶ/ር ዲማ ነገዎ፣ ሻለቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስና ዶ/ር ጌታቸው በጋሻውን ይስሟቸው

በውጭ ምንዛሪ እጥረት ሳቢያ የነፍስ አድን መድኃኒቶች ጥቁር ገበያ ደርቷል

  • እንደሞባይል በግመል ተጭነው ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ መድኃኒቶች ተበራክተዋል
  • ዜጎች መድኃኒት ፍለጋ እየተንከራተቱ ነው

ዋዜማ ራዲዮ- ከውጭ ምንዛሬ ጋር በተያያዘ አገሪቱ አጣብቂኝ ውስጥ መግባቷን የሚያሳብቁ ምልክቶች መታየት ከጀመሩ ሰንበትበት ብሏል፡፡ የውጭ ምንዛሬ መሳሳትን ተከትሎ አገር ውስጥ የግንባታ ዕቃዎች የዋጋ ንረት መፈጠሩን በዘገብን በሳምንታት ውስጥ ችግሩ ከብረታ ብረት የግንባታ ዕቃ ወደ ነፍስ አድን መድኃኒቶች መዛመቱ የአገሪቱ ፈተና ስለመብዛቱ አመላካች ሆኗል፡፡
የዋዜማ ዘጋቢዎቻችን በተዘዋወሩባቸው ፋርማሲዎች ባለፉት ዐስርተ ዓመታት ተከስቶ የማያውቅ የመድኃኒቶች እጥረት መታየቱን ለማረጋገጥ ችለዋል፡፡ ሁነኛ መድኃኒቶችን ጨምሮ ጤናን ለመጠበቅ ተብለው የሚታዘዙ አልሚ ንጥረ ነገሮችም ከገበያ ተሰውረዋል፡፡
ወተትና ሌሎች ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችን የያዘውና ለምታጠባ እናትና ለእርጉዝ ሴት ተዘውትሮ የሚታዘዘው “ሊብቶማማ” አንዱ ጣሳ ከመንፈቅ በፊት 100 ብር ይሸጥ ነበር፡፡ አሁን ዋጋው ወደ 300 ብር አሻቅቧል፡፡ ዋጋው ማሻቀቡ ብቻ አይደለም ችግሩ፡፡ ቀደም ባሉ ጊዜያት ከፋርማሲም አልፎ በየሱፐርማርኬት እንደልብ ይገኝ እንደበረና አሁን ግን “ሊብቶማማን” ያለበትን አውቃለሁ የሚል ጠፍቷል፡፡
“በፍለጋ እግሬ ቀጠነ፤ ‘ምናልባት የእናቶችና ሕጻናት ሆስፒታሎች ውስጥ ጠይቅ’ ተብዬ በስንት ውጣ ዉረድ እዚህ ጌታሁን በሻህ ጋ ሁለት ጣሳ በስድስት መቶ ብር ገዛሁ፤ ለዚያውም በስንት መከራ…” ብሎናል ባለቤቱ ነፍሰጡር እንደሆነች የነገረን ግለሰብ፡፡ በመጨረሻ ሊብቶማማን ማግኘት የቻለው ከሴማህ የእናቶችና ሕጻናት ክሊኒክ ነው፡፡ ሊብቶማማ አልሚ ምግብ የሱፐርማርኬት ሸቀጥ ከመሆን አልፎ በጥቁር ገበያ የሚታደን መሆኑ የችግሩን ስፋት የሚያመላክት ነው፡፡

የግመል መድኃኒት
በአሁኑ ጊዜ በመድሀኒት አስተዳደርና ቁጥጥር ባለ ስልጣን ከዋና ዋና የመድኃኒት ዝርዝር ውስጥ የተካተቱና ኾኖም ግን ከገበያ ፈጽሞ የተሰወሩ መድኃኒቶች ቁጥር ከ20 እንደማያንስ የሚናገሩ የመድኃኒት ቅመማ ባለሞያዎች ታካሚዎች ከጥቁር ገበያ ወይም ውጭ ከሚኖሩ ዘመዶቻቸው ብቻ ማግኘት የሚችሏቸውንና በመደበኛ ግብይት የማይገኙ መድኃኒቶች ዝርዝር በከፊል ነግረውናል፡፡

ለካልሺየም እጥረት በመርፌ መልክ የሚታዘዘው ካልሺየም ግሉኮኔት፣ ለልብ ህመም የሚታዘዘው ፕሮፕራኖሎል ከገበያ ከጠፉ ሰነባብተዋል፡፡ የደም መርጋትን ለማስወገድ በመርፌ የሚታዘዘው ሄፓሪንና ኢኖክዛፓሪን አንድ መርፌ በጥቁር ገበያ 300 ብር መድረሱንም ሰምተናል፡፡ የአፍንጫ መታፈንን ተከትሎ የሚታዘዘው ስዊዘርላንድ ሠራሹ ኦትሪቪን ናሳል ድሮፕ ቀደም ሲል ከመቶ ብር ጀምሮ ገበያ ላይ እንደልብ ይገኝ እንደነበረና አሁን ግን ፈጽሞ ማግኘት እንዳልተቻለም ታውቋል፡፡

በ”አር ኤች ፋክተር” መለያየት ጽንስ ያለጊዜው እንዳይወርድ የሚያግዘውና በተለምዶ ሾተላይ ለሚባለው ችግር የሚታዘዘው አንቲ-ሮ-ዲ-ኢሚኖግሎቢን (Anti RHO-D Immunoglobulin) በጥቁር ገበያ ከ3ሺህ እስከ 5ሺህ ብር በድርድር እየተሸጠ መሆኑም ተነግሮናል፡፡
ተፈላጊነታቸው እምብዛምም ሆኖ ነገር ግን ብዙ ፈላጊ ስለሌላቸው ብቻ በብዛት የማይመረቱ መድኃኒቶችም በዶላር ምክንያት ወደ አገር ቤት ስለማይገቡ በጥቁር ገበያ እየተቸበቸቡ እንደሆነ ይነገራል፡፡ “አንቲ ሎክሲን ዝገት የነካው ብረት ሲወጋን የሚታዘዘ መድኃኒት ነው፡፡ በፍሪጅ መቀመጥ ያለበት መድኃኒት ቢሆንም በበረሃ ተንገላቶ እየገባ ለገበያ እየቀረበ ነው” ይላል ዋዜማ የነጋገረችው የፋርማሲ ባለሞያና የመድኃኒት ደላላ፡፡

ለደም ግፊት የሚታዘዙ ሀይድራላዚንም ከገበያ ከተሠወሩት አንዱ ነው፡፡ ለደም ማነስ የሚታዘዘው ሀይማፕ ሲራፕ (HAEM UP SYRUP) አገር በቀሉ ካዲላ ብቻ የሚያመርተው ሲሆን በውጭ ምንዛሬ እጥረት ምክንያት አሁን በበቂ ማምረት እንዳልቻለ ሰምቻለሁ ይላል ይኸው የመድኃኒት ባለሞያ፡፡

ለጨጓራ በሽታ የሚታዘዙት ስዊዘርላንድ ሰራሹ ኔክሲየም (በስሪት ስሙ ኢሶመፐራዞል) (Esomeprazole) 14 ፍሬዎችን አልፎ አልፎ በግል የመድኃኒት መደብሮች እስከ 3መቶ ብር ከፍሎ ማግኘት ቢቻልም አሁን አሁን ግን እንደልብ ለማግኘት ወደ ጥቁር ገበያ መዝለቅ አስፈላጊ ሆኗል፡፡
ቲንየም አንቲባዮቲክ በሐኪም ጥብቅ ትዕዛዝ ብቻ በማኅተምና ፊርማ ወጪ ተደርጎ የሚገኝ፣ በጥንቃቄ የሚወሰድ መድኃኒት ሲሆን አንዱ ቫይል በ400 ብር በጥቁር ገበያ መሸጥ ተጀምሯል፡፡ ይህ መድኃኒት ሱስ የማስያዝ እድሉ እጅግ ከፍተኛ በመሆኑ ወደ ጥቁር ገበያ መቀላቀሉ እንደ አገር አሳሳቢ ነው ይላሉ ባለሞያዎች፡፡
ከላይ ከተዘረዘሩት መድኃኒቶች በተጨማሪ ለሚለበልብ ስሜት የሚታዘዘው ፈሌክሲካም፣ ለሳል የሚታዘዘው ሜዶቨንት ሽሮፕ፣ ለደም ግፊት የሚታዘዘው ፉሪዴንክ፣ ለሕመም ማስታገሻ የሚታዘዘው ግሮፌናክ በሙሉ አገር ውስጥ ባሉ ፋርማሲዎች ማግኘት ዘበት እየሆነ መምጣቱም ተነግሯል፡፡
“ጣፊያ ኢንሱሊን አያመርትም፤ አገር ኢንሱሊን አታስገባም”
ሕይወት አድን ከሚባሉ መድኃኒቶች የሚመደበው ኢንሱሊን ከ2 ሚሊዮን የሚልቁ ኢትዮጵያዊ የስኳር ሕመምተኞችንና ቤተሰቦቻቸውን ክፉኛ እያስጨነቀ ነው፡፡ የመድኃኒት ፈንድና አቅርቦት ኤጀንሲ ‹‹አታስቡ! በቂ ክምችት አለኝ›› ቢልም ለጊዜው የሚያምነው ማግኘት አልቻለም፡፡
ሸገር ሬዲዮ፣ ኢቢሲ እና ፋና ቲሌቪዥን ጣቢያዎች በቅርቡ በሠሯቸው ተደጋጋሚ ዘገባዎች የስኳር ሕሙማን ኢንሱሊን እጥረት እንዳጋጠማቸውና በተለይም ከገጠሪቱ ኢትዮጵያ ለሕክምና ወደ ከተማ የመጡ ታካሚዎች እንደወትሮው ለሦስት ወራት የሚሆን ኢንሱሊን ሸምተው ወደ አገራቸው መመለስ እንዳልቻሉ መስክረዋል፡፡ አንዳንድ ታካሚዎች ኢንሱሊን እስከናካቴው ሊጠፋ ይችላል በሚል እሳቤ በቀን መውሰድ ያለባቸውን የኢንሱሊን መጠን ቀንሰው እየተወጉ እንደሆነም ለተጠቀሱት የመገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል፡፡

በመንግሥት ሆስፒታሎችና በሕዝብ የመድኃኒት መደብሮች አካባቢ ሁኔታውን ለማጣራት ከሁለት ሳምንት በፊት ባደረግነው ሙከራ ኢንሱሊን ከገበያ አለመጥፋቱንና ሆኖም ግን ክምችቱ እየተመናመነ መሆኑን በመረዳት ሥጋት የገባቸው ፋርማሲዎች ታማሚዎች ከሚጠይቁት መጠን ግማሹን ብቻ መስጠት ጀምረው እንደነበረ ለማረዳት ችለናል፡፡ ካለፈው ሳምንት ወዲህ ግን የመድኃኒት ፈንድ አገሪቱ ለ11 ወራት የሚሆን በቂ የኢንሱሊን ክምችት እንዳላት በመግለጹ ሁኔታዎች መሻሻልን አሳይተዋል፡፡

“ዜጎች መንግሥትን የማያምኑበት ደረጃ ላይ ደርሰዋል፡፡ በቂ ክምችት አለ እያልናቸው በቻሉት አቅም ሁሉ በርከትከት አድርገው ነው እየገዙ ያሉት፡፡ እነሱ ሲያከማቹ ደግሞ እጥረት ይፈጠራል” ትላለች በፒያሳ ከነማ ፋርማሲ ውስጥ የምትሠራ የመድኃኒት ባለሞያ፡፡
የኢንሱሊን ከገበያ ጠፍቷል የሚለው የሚዲያ ጩኸት ገፍቶ ቢመጣም በመድኃኒት ፈንድና አቅርቦት ኤጀንሲ ተቀባይነት ሊያገኝ አልቻለም፡፡ ከመንግሥት በኩል ሁሌም እንደሚሰማው ‹‹እጥረት የለም፣ እጥረቱን የፈጠረው የፍላጎት መጨመር ነው፤ እጥረቱ ጊዝያዊ ነው፤ እጥረቱን የፈጠሩት ስግብግብ የመድኃኒት ነጋዴዎች ናቸው›› የሚሉ እርስበርሳቸው የሚምታቱ መግለጫዎች ዛሬም እየተሰሙ ይለኛሉ፡፡
የንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ ባለሥልጣን ከሁለት ወራት በፊት ስምንት የመድኃኒት አስመጪዎችን መድኃኒት መጋዘን በማጎር እጥረት እንዲፈጠር አደርጋችኋል፣ ለዋጋ ንረትም ምክንያት ሆናችኋል ብሎ ፍርድ ቤት የገተራቸው የዛሬ ሁለት ወር ገደማ ነበር፡፡ ጉዳያቸው ዛሬም አልተቋጨም፡፡

በቀናት ልዩነት የተከሳሽ መድኃኒት አቅራቢዎችን ቁጥር ወደ 19 ከፍ ብሎም ነበር፡፡ ከነዚህ ተከሳሾች ውስጥ አንድም የአገር ውስጥ መድኃኒት አምራች የለበትም፡፡ በኢትዮጵያ በዜጎችና በውጭ ካምፓኒዎች ሽርክና የተቋቋሙ 22 አገር በቀል የመድኃኒት አምራቾች በአሁኑ ጊዜ በሥራ ላይ ይገኛሉ፡፡ በ20 ሚሊዮን ዶላር ወጪ በቻይና ባለሐብቶች የተቋቋመው ሂውማንዌል ፋርማሱቲካል በአማራ ክልል፣ ሀገረማርያም ተመርቆ ሥራ የጀመረው ከጥቂት ወራት በፊት ነበር፡፡

“ተከሳሾቹ መድኃኒት መደበቅ ብቻም ሳይሆን ከአንድ መድኃኒት እስከ መቶ ፐርሰንት ጭማሪ አድርጎ በመሸጥም ተወንጅለው ነበር፡፡ ከተከሳሾቹ መሐል ሀየላ፣ ማክ፣ በከር፣ አምባ፣ አፍሪ ሜድና ጄኔቲክ ፋርማሱቲካል ይገኙበታል፡፡
ከስኳር ታማሚዎች ቁጥር የተነሳ አሁን የሚዲያዎችን ትኩረት የሳበው የኢንሱሊን መድኃኒት መሰወር ይሁን እንጂ በየሆስፒታሉ በርካታ የመድኃኒት ዝርያዎች ከጠፉ ሰነባብተዋል፡፡ ነገር ግን የኢንሱሊንን ያህል አነጋገሪ መሆን አልቻሉም፡፡
“እኔ እስከማውቀው ኢንሱሊን አልጠፋም፤ እንደውም ከሌላው መድኃኒት ይልቅ በሽ…በሽ ነው፤ ሰው መድኃኒቶቹን ‘በብራንድ ኔም’ ስለሚያውቃቸው ነው የጠፋ የመሰለው፡፡” የሚለው ዋዜማ ያነጋገረችው ፋርማሲስት “ብዙ ሰው “ኢንሱላታርድ” ካልሰጠከው “ጁስሊን” ብትሰጠው እሺ አይልም፡፡ የተለያየ ንግድ ስም ያላቸው አንድ አይነት መድኃኒቶች እንደሆነ ብታስረዳቸውም አይሰሙህም፡፡” ይላል፡፡
“ኢንሱሊን በከነማ፣ በቀይ መስቀል እና በሁሉም ሆስፒታሎች በአንድ ወር ብቻ 410ሺ ቫይል ተሠራጭቷል፡፡ ኾኖም ታካሚዎች መድኃኒቱ ይጠፋል በሚል ከሚያስፈልጋቸው በላይ ይገዛሉ፡፡ የግል ፋርማሲዎችም መድኃኒቱ ሲጠፋ ጠብቀው በጥቁር ገበያ ለመሸጥ ሆን ብለው ያከማቻሉ፡፡ እጥረቱ የሚፈጠረው በዚህ ምክንያት ይመስለኛል፡፡” ይላል ዋዜማ በዚህ ርዕሰ ጉዳይ በስፋት ያነጋገረችው፤ በፋርማሲ በዲግሪ ከግል ኮሌጅ ተመርቆ በመድኃኒት ማሻሻጥና ድለላ ሥራ የተሠማራ ባለሞያ፡፡ ይኸው ባለሞያ እንደነገረን ከሆነ ብዙ ለማጠራቀምና እጥረት ሲፈጠር አውጥቶ ለመሸጥ በሚሞክሩ ሰዎች የተማረረው ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል “ከራሴ ሆስፒታል ላልተመረመሩ መድኃኒቱን አልሸጥም” የሚል ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

የመድኃኒት የገበያ ሠንሠለት
የመድኃኒት ሥራ የትርፍ ሕዳግ ከ15 እስከ 20 በመቶ ብቻ ነው፡፡ አንድ ኩባንያ ራሱ አስመጥቶ፣ ራሱ ጅምላ አከፋፍሎ፣ ራሱ ካልቸረቸረው መንግሥት ይሁንታ በሰጠው የትርፍ ሕዳግ ብቻ ሠርቶ የሚያመረቃ ትርፍ ማግኘት አይችልም ይላሉ በዘርፉ የሚውተረተሩ ደላሎች፡፡ ፋርማሲዎች የተወሰኑ መድኃኒቶችን ከመድኃኒት ፈንድና አቅርቦት ኤጀንሲ በወረፋ መግዛት ይችላሉ፡፡ ኾኖም አብዛኛው ግብይታቸው የሚዘወረው የመድኃኒት አስመጪዎች በሚያሰማሯቸው በዘርፉ የሰለጠኑ ደላሎች ነው፡፡

“አዲስ ብራንድ መድኃኒት ለማስተዋወቅ ለሐኪሞች ብዙ ብር መክፈል ያስገልጋል፡፡ በፋርማሲ የተመረቁ ደላሎች በየፋርማሲው እየሄዱ ማስተዋወቅ አለባቸው፡፡ ሥራው የሚሠራውም በዱቤ በማከፋፈል ነው፡፡” የሚለው የመድኃኒት የሽያጭ ባለሞያ፣ አሁን በቁጥር በብዛት የተከፈቱ ፋርማሲዎች ሁሉም የዱቤ ተጠቃሚዎች ካልሆኑ መድኃኒት ለመረከብ ፍቃደኞች አይሆኑም ሲል ያብራራል፡፡

እነዚህ ሁኔታዎች መድኃኒት ደብቆ እጥረት ሲፈጠር ብቻ አውጥቶ በመሸጥ ሞቅ ያለ ትርፍ ለማግኘት የሚደረገውን ሙከራ እንዲስፋፋ አድርገውታል፡፡ የግል መድኃኒት ቤት የሚሠሩ ፋርማሲስቶች አንድን መድኃኒት ‹‹የለም›› ካሉ በኋላ የደንበኛውን አቅም ገምግመው ‹‹እስኪ ከውጭ የሚያመጡ ሆስተሶች ስላሉ ምናልባት ልሞክርዎ፤ ስልክዎትን ይስጡኝ›› ይላሉ፡፡ ይህ የሚደረገው መድኃኒቱን ከጥቁር ገበያ አምጥቶ በውድ ለመቸብቸብ እንደሆነ ይነገራል፡፡
ዋዜማ ያናገረችው ባለሞያ የመድኃኒት ሽያጭ ሰንሰለቱ ክትትል እንደማይደረግበት ጠቅሶ በተለይም ሥነምግባር የጎደላቸው የሕክምና ባለሞያዎች ጄኔሪክ ኔም ከመጻፍ ይልቅ ብራንድ ኔም በመጻፍ ታካሚዎችን ለእንግልት ይዳርጋሉ ይላል፡፡ “አንድ ታካሚ ሐኪሙ ካዘዘለት የመድኃኒት ስም ውጭ ልስጥህ ብትለው የምታጭበረብረው ነው የሚመስለው፡፡” ሲል ያብራራል፡፡ የዴንማርኩ ኢንሱላታርድ በጠፋበት ወቅት የሆነውን በማስታወስ፡፡ ሐኪሞች በብራንድ ስም መድኃኒት እንዳያዙ ቢደረግ የሚል አስተያየትም ይሰጣል፡፡
የግል ጤና ተቋማት መድኃኒት የሚያገኙት ከግል አስመጪዎች ነው፡፡ የመድኃኒት ፈንድና አቅርቦት ኤጀንሲ መድኃኒት የሚያከፋፍለው ለመንግሥትን የሕዝብ ጤና ተቋማት ብቻ ነው፡፡ አንዳንድ የተመረጡ መድኃኒቶችን ብቻ ለግል ያቀርባል፡፡ የግል አስመጪዎች እንደበፊቱ ዶላር ስለማያገኙ በበቂ መጠን መድኃኒት አያስገቡም፡፡ የሚገቡ መድኃኒቶች ውስን ስለሆኑ የግል ፋርማሲዎች እጥረት እንዲፈጠር ያሏቸውን መድኃኒቶች ይደብቋቸዋል፡፡ ሰው መድኃኒቱን ሲያጣ ግራ ስለሚገባው፣ የሕይወት ጉዳይም ስለሚሆንበት የተጠየቀውን ገንዘብ ይከፍላል፡፡ የዶላር እጥረቱ ጥቁር ገበያው ሁነኛ የመድኃኒት አቅርቦት መስመር እንዲሆን አግዞታል፡፡

አንዳንድ የጠፉ መድኃኒቶች በደላሎች እጅ እንዴት ሊገቡ የሚችሉባቸውን መንገዶች ያነጋገርነው የመድኃኒት ባለሞያ ሲያብራራ፤ ” አንደኛው ከመንግሥት ሆስፒታልና ፋርማሲ በድብቅ በማውጣት ሲሆን፣ ሁለተኛው መድኃኒቶቹን በድንበር በኩል በግመል በማስመጣት” እንደሆነ ያብራራል፡፡ በግመል የሚገቡት ለጤና አደገኛ እንደሚሆኑም አልሸሸገም፡፡

“አብዛኛው መድኃኒት ፀሐይ ከነካው ፈዋሽነቱ ይጠፋል፤ ፍሪጅ ውስጥ መቀመጥ የነበረበት መድኃኒት በግመል ጀርባ በበረሃ መጥቶ በውድ ሲሸጥ ምን ሊከሰት እንደሚችል አስበው፡፡ ታማሚዎች መድኃኒቱን ማግኘታቸውን እንጂ እንዴት እንደገባ አያውቁም፡፡” ሲል ያብራራል፡፡ እነዚህ መድኃኒቶች “ዳካ” ሳይመዘግባቸው፣ ዱካቸው ሳይታወቅ አገር ውስጥ ስለሚገቡ ፎርጅድ የሕንድ መድኃኒት የሚሆኑበት አጋጣሚም ብዙ ነው፡፡
በፓኬጂንግ እና ሌብሊንግ ላይ የተጠመዱ ፋብሪካዎች
መንግሥት በገቢ ንግድ ከጨከነ ሰንብቷል፡፡ በራሱ ሜጋ ፕሮጀክቶች መጨከን ከጀመረ ወራት ተቆጥረዋል፡፡ በመድኃኒት ግን ጨክኖ አያውቅም፡፡ አንዲት አገር መድኃኒት ማስገቢያ የውጭ ምንዛሬ ላይ መሰሰት ከጀመረች የዛች አገር ጥርስ ተነቃንቋል ማለት ነው፡፡ ሰሞኑን እየታየ ያለውም ይኸው ነው፡፡

አገሪቱ ከሚያስፈልጋት የመድኃኒት ፍላጎት 80 ከመቶውን የምታሟላው አንጡራ የውጭ ምንዛሬዋን ከስክሳ ከውጭ በማስገባት ነው፡፡ ከ15 እስከ 20 በመቶ የሚሆነውን የመድኃኒት አቅርቦት አገር ውስጥ በማምረት ላይ የሚገኙት ዘጠኝ ፋብሪካዎችም ቢሆኑ አብዛኛውን የመድኃኒቱን ግብአት ለመሸፈን የውጭ ምንዛሬን ይሻሉ፡፡

ማንኛውም መድኃኒት የብዙ ንጥረ ነገር ድምር ነው፡፡ በድምሩ Active እና inactive ንጥረ ነገሮች ingredient ውህድ ተደርጎ ነው የሚመረተው፡፡ ከፈዋሹ ንጥረ ነገር ባሻገር መድኃኒቱ ሆድ ውስጥ ከገባ በኋላ ቶሎ እንዲበተን የሚያደርጉ ንጥረ ነገሮች (Disintegrant)፣ የፈዋሹ መድኃኒት ማቀፊያዎች (bulking agent)፣ ለጣዕም የሚጨመሩ ንጥረ ነገሮች (sweetening agent)፣ ሳይበላሸሽ እንዲቆይ (reservative) ወዘተ መድኃኒቱን ለማምረት አስፈላጊ ናቸው፡፡ እነዚህ ሁሉ ከውጭ የሚገቡ መሆኑ የምንዛሬን አስፈላጊነት ያጎላዋል፡፡

በዚህም ምክንያት ዛፍ፣ ሜድቴክ፣ አዲግራት፣ ጁልፋር፣ ካዲላ፣ አዲስ ፋርም፣ ፋርማ፣ ሜድ ሶል ሁሉም የዶላር ያለህ እያሉ ነው፡፡ ገዘፍ ያሉ የአገር ውስጥ የመድኃኒት አምራቾች በቁጥር ዘጠኝ ብቻ ሲሆኑ ከዓመታዊ የመድኃኒት ፍጆታ በነዚህ አምራቾች መሸፈን የቻለው ከ20 በመቶ አይዘልም፡፡ እነዚህ ፋብሪካዎች ከ380 እጅግ ወሳኝ የሆኑ የመድኃኒቶች ዝርዝር ውስጥ በአገር ውስጥ መመረት የሚችሉት 65ቱ ብቻ ናቸው፡፡ አብዛኛዎቹ መድኃኒት አምራች ናቸው ለማለት የሚከብደውም ለዚሁ ነው፡፡ ባይሆን በፓኬጂንግና ሌብሊንግ የተጠመዱ ብንላቸው ይቀላል፡፡

በአንጻሩ መንግሥት በየዓመቱ ለመድኃኒት የሚያወጣው ወጭ በከፍተኛ ሁኔታ እየናረ ሲሆን ባለፈው ዓመት ብቻ የስድስት ቢሊዮን ብር የመድኃኒት ግዢ አከናውኗል፡፡ የዓለም ጤና ድርጅትን ከመሰሉ አጋር ድርጅቶች ከዚህ ገንዘብ የማይተናነስ የመድኃኒት ድጎማም ተደርጎለታል፡፡ በድምሩ የከ15 ቢሊየን ብር በላይ ለመድኃኒት ተከስክሷል፡፡ ይህ ሁሉ ሆኖም ፍላጎት አልተሟላም፡፡

በአሁኑ ወቅት ከሦስት መቶ የማያንሱ የተመዘገቡ ጅምላ መድኃኒት አቅራቢዎች በአገሪቱ ይገኛሉ፡፡ የመድኃኒት አቅርቦት በየዓመቱ በ20 በመቶ ቢጨምርም አሁንም ፍላጎት ሊሟላ አልቻለም፡፡ አንዱ ምክንያት በአገሪቱ በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋ የመጣው ተላላፊ ያልሆኑ ደዌ ነው የሚሉ ባለሞያዎች አሉ፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥት የውጭ ምንዛሬ ጭንቀቱን በዘላቂነት ለማስወገድ እንደ ጨርቃ ጨርቅ ኢንደስትሪው ሁሉ የፋማሱቲካል ኢንደስትሪ ፓርክ ለማቋቋም ወስኖ በፍጥነት ወደ ተግባር መግባቱ ይታወሳል፡፡ በኢትዮጵ ኢንቨስትመንት ኮሚሽንና በዶክተር አርከበ እቁባይ አመራር ቂሊንጦ አቅራቢያ በ5.5 ቢሊዮን ብር በቻይናው ሲቲሲኢ እየተገነባ ያለው የመድኃኒት ፓርክ ታይቶ በማይታወቅ ፍጥነት እየተገነባ ይገኛል፡፡ ፍሬ እስኪያፈራ ግን ረዥም ዓመታትን መፈለጉ አይቀርም፡፡
የውጭ ምንዛሬ- አዙሮ የሚጥል በሽታ
መድኃኒት ፋብሪካ የሚገነቡ ባለሐብቶች ማሽን መቶ በመቶ ከቀረጥ ነጻ ያስገባሉ፣ የታክስ እፎይታ ይሰጣቸዋል፤ 70 በመቶ ያለ ማስያዣ ብድር ያገኛሉ፡፡ በጨረታ ጊዜ የተወዳዳሪነት የዋጋ ድጋፍ ይደረግላቸዋል፡፡ 50 በመቶ ምርታቸውን ለወጪ ንግድ ካቀረቡ የ3 ዓመት ግብር ነጻ ይደረጋሉ፡፡ ያም ሆኖ ብዙ ፋብሪካዎች የኢትዮጵያ ነገር አይማርካቸውም፡፡ የሁሉም ምክንያት ተመሳሳይ ነው፡፡ ‹‹ርካሽ ጉልበት አለ፤ አልሰለጠነም፤ ሰፊ ገበያ አለ፤ ዶላር ግን የለም›› ይላሉ በአንድ ድምጽ፡፡
እውነት አላቸው፡፡
በኢትዮጵያ የተሠማሩ በርካታ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች በሕግ የተፈቀደላቸውን የትርፍ ገንዘብ በዶላር ከብሔራዊ ባንክ ለመውሰድ እንዳልቻሉ ይታወቃል፡፡ ከነዚህም መካከል አንዱ ዳንጎቴ ሲሚንቶ ነው፡፡ በተመሳሳይ በአገሪቱ ግዙፉ የቢራ ጠማቂ ሃይኒከን በዓመታት ውስጥ ያተረፈውን ገንዘብ በዶላር ከአገር ለማውጣት አለመቻሉ ሲነገር ቆይቷል፡፡ መንግሥት የችግሩን አሳሳቢነት በመረዳት ከቢራ ጠማቂው አመራሮች ጋር ባደረገው ድርድር ከአገር ለማውጣት ያልቻሉትን ግዙፍ የዶላር ክምችት ለፋብሪካው ማስፋፊያ እንዲውል፣ ይህንኑ ለማሳለጥም ንግድ ባንክን ጨምሮ ሁሉም የግል ባንኮች ያላቸውን ጥሪት ቆነጣጥረው በመዋጮ 40 ሚሊዮን ዩሮ ለሃይኒከን ኤል ሲ መክፈቻ እንዲያውሉ ከብሔራዊ ባንክ መመሪያ እንደተሰጣቸው፣ ይኸው መመሪያም ከዶክተር አርከበ እቁባይ እንደተላለፈ ሳምንታዊው ፎርቹን ጋዜጣ በጃንዋሪ 30 ዕትሙ ጽፎ ነበር፡፡
የኋላ ኋላ ‹‹እኔ ትዕዛዝ አልሰጠሁም፤ ሥልጣኑ የብሔራዊ ባንክ ነው›› የሚል ማስተባበያ ከአርከበ እቁባይ እንደደረሰውም ይኸው ጋዜጣ ጽፏል፡፡ ከዚህ የዶላር መዋጮ ነጻ እንዲሆን የተደረገው ደቡብ ግሎባል ባንክ ብቻ ሲሆን አዋሽ ባንክ ትልቁን መዋጮ እንዲሰጥ ግዳጅ ተጥሎበት ነበር፡፡ ‹‹ለመድኃኒት የሌለውን ዶላር ለቢራ ጠማቂ አምጡ ተባልን!›› ሲል መገረሙን የገለጸው የዚሁ ዘገባ አካል የተደረገ አንድ የባንክ ሠራተኛ የምንዛሬ እጥረቱ መንግሥትን እንዳሰከረው የሚጠቁም ሐሳብ አንጸባርቋል፡፡
ባንኮች ዶላር አዋጡ የሚል መመሪያ ሲደርሳቸው በአንድ ዓመት ውስጥ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ እንደሆነም ተዘግቧል፡፡ ከወራት በፊት ለኢትዮጵያ ንግድ መርከብ ደርጅት ተመሳሳይ የዶላር ክፍያ መዋጮ የግል ባንኮች የውዴታ ግዴታ መመሪያ ተላልፎላቸው ነበር፡፡

የመድኃኒት ፈንድና አቅርቦት ኤጀንሲ አገሪቱ የሚያስፈልጓትን የመድኃኒት ዝርዝር መዝግቦ ግዢ ፈጽሞ ያቀርባል፡፡ ኾኖም ሁሉም መድኃኒቶች በዚህ መሥሪያ ቤት በኩል አያልፉም፡፡ ሁሉንም መድኃኒት የማቅረብ አቅሙም የለውም፡፡ በመሆኑም ኤጀንሲው በአገሪቱ ዋና ዋና የጤና ችግሮችን መሠረት ያደረገ ግዢ ይፈጽማል፡፡ የመድኃኒት ግዢው የሚካሄደው የጤና ተቋማት ለዚህ መሥሪያ ቤት በሚያቀርቡት የፍላጎት ዝርዝር መሠረት ነው፡፡

ኤጀንሲነው በሚቻለው ሁሉ 17 ቅርንጫፎችን ተጠቅሞ መድኃኒት ግዢ ኮማንድ ፖስት አቋቁሞ የሚቻለውን ሁሉ ሞክሮ ባይሞላለት “የኅብረተሰቡ መድኃኒት የመጠቀም ልምድ መጨመር ነው እጥረት እየፈጠረ ያለው” እስከማለት ደርሶ ያውቃል፡፡ ኤጀንሲው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በጀመረው ዘመናዊ አሰራር በየጊዜው የግዢ ጨረታ ከማውጣት ይልቅ አንድ የመድኃኒት አቅራቢ ለሦስት ዓመት እንዲፈራረም በማድረግ በጨረታ ሂደት የሚባክነውን ጊዜ ለማሳጠር እየሞከረ ይገኛል፡፡ ኾኖም መድረስ የሚችለው የሕዝብና የመንግሥት የጤና ተቋማትን ብቻ በመሆኑ ጥረቱ ግመሽ ጎዶሎ አደርጎበታል፡፡
“በቅርብ ጊዜ ውስጥ ለቀዶ ጥገና የሚውሉ ክሮች ጠፍተዋል እንዳንባል እሰጋለሁ” የሚለው የራስ ደስታ ዳምጠው ሆስታል ሀኪም “እንደልብ የሚገኙ የሐኪም ጓንት፣ አንቲ ፔይን፣ አንቲ ባዮቲክ አንቲ ኤነፌክሽን፣ የባክቴሪያ ኤንፌክሽን ለማከም የሚውሉ የመርፌ ሜሮፔኔም፣ ቫንኮማይሲን ስንጠይቅ ጠብቁ እየመጣ ነው መባል ተጀምሯል፤ ያስፈራኛል” ይላል፡፡
“አስበው እንግዲህ፤ ኢትዮጵያ ከሰሐራ በታች በስኳር ሕመምተኞች ብዛት አንደኛ ናት፡፡ ከ2 ሚሊዮን በላይ የስኳር ህመመትኛ ያለባት አገር መሆኗ ይታወቃል፡፡ መንግሥት ኢንሱሊን በምንዛሬ ምክንያት ጠፋ ካለ ዜጎችን በጅምላ ጨራሽ መሣሪያ ከመግደል በምን ይተናነሳል” ሲልም ይጠይቃል፡፡

ሀገር የሌለዉና ኢትዮጵያዊነቱን የተነጠቀ ህዝብ ከመሆንም የከፋዉ የጋራ መጻኢ ራዕይ የሌለዉ ህዝብ መሆን ነዉ ! (ሸንቁጥ አየለ)

አንተ ኦሮሞ ነህ: አንተ ትግሬ ነህ: አንተ አማራ ነህ: አንተ ከምባታ ነህ: አንተ ሲዳማ ነህ አንተ ደግሞ ከዚህ ወይ ከዚያ ብሄር ነህ በማለት ቀዳሚ ማንነትህ ብሄርህ እንጅ ኢትዮጵያዊነትህ አይደልም ስለዚህ የምትይዘዉ መታወቂያ ኢትዮጵያዊነት የተፋቀበት : የብሄር ማንነትህ የተለጠፈበት ነዉ ሲል በዘረኝነት: በአምባገነነትና በማንነት ቀዉስ ዉስጥ የገባዉ ወያኔ አወጀ::

የብሄር ማንነት ሰጠሁህ ተብሎ በግድ የጎሳ ፖለቲካ አስተሳሰብ የተጫነበት ህዝብ ግን ማንነትም : ሀገርም ብሎም መጻኢ እድልም የሌለዉ ሆነና ቁጭ አለ:: ኢትዮጵያዊነቱን ነጥቀዉ የጎሳ ማንነት ሰጠንህም ቢሉትም እዉነታዉ የጎሳ ማንነትም ሆነ ሀገራዊ ማንነት የሌለዉ ህዝብ እንዲሆን ተመቻችቶ ተቀመጠ::

ከ87 ብሄረሰቦች በላይ ያሉባት ኢትዮጵያ በሰባት ብሄረሰቦች ስም በክልል ተሸንሽና እንደ ቀልድ ከ80 በላይ የሚሆነዉ ብሄረሰብ ሀገርም: ክልልም ማንንነትም የሌለዉ ፍጡር ሆነ:: እንዴት ቢሉ ጋምቤላ ክልል የሚኖር አገዉ አገሩ ኢትዮጵያም ወይም ጋምቤላም አይደለም:: ኦሮሚያ ክልል የሚኖር አማራ ሀገሩ ኦሮሚያም ወይም ኢትዮጵያም አይደለም:: ደቡብ ክልል የሚኖር ጉራጌ ሀገሩ ኢትዮጵያም ደቡብም አይደለም:: እንዲህ እያለ ሲቆጠር ከኢትዮጵያዊነትም ከብሄር ክልሉም ተቆርጦ የተነጠለዉ ኢትዮጵያዊ እጅግ ብዙ ሆኖ ይገኛል::

ክልል በተባለዉ ዉስጥ ደግሞ መብት የለዉም:: የክልል ዜጋም አይደልም:: የሀገር ዜጋም አይደለም:: የሀገር ዜጋ ላለመሆኑ ማረጋገጫዉ በፈለጉ ሰዓት የክክል ባለቤት ነን የሚሉ ወንድሞቹ ገፍተዉ ያባርሩታ:: የክልል ባለቤት ላለመሆኑ ማረጋገጫዉ ደግሞ ከስሙ እስከ ህገመንግስታዊ መብቱ ብሎም ሰበአዊ መብቱ በዚያ ክልል ዉስጥ የተነፈገ ነዉ::

ክልል አለን የሚሉት አማራ : ኦሮሚያ : ሶማሊያ : አፋር ክልሎች ደግሞ ክልሉ ለለበጣ እና ለፖለቲካ ፕሮፖጋንዳ በስማቸዉ ተለጠፈላቸዉ እንጅ በክልሉ ህግ ዉስጥ የሚያበጁት ወይም የሚፈጽሙት ጉዳይ የለም:: ህግ ያልሆነ ህግ እንደ ደራሽ ዉሃ ከወያኔ ምስለኔዎች ይፈስላቸዋል እንጅ::

ከዚህም የከፋና የከረፋዉ ነገር ደግሞ ትልልቅ ቁጥር ያላቸዉ ማህበረሰቦች መላዉ ኢትዮጵያን በታላቅ ክብርና ፍቅር መምራትና ኢትዮጵያዉያንን አንድ ማድረግ ሲችሉ በትንንሽ ክልል ስር ታስረዉ እጎሳ ከረጢት ዉስጥ እንዲከረቸሙ ተደረጉ:: አዕምሮአቸዉን ከኢትዮጵያዊነት በመነጠል እትንሽ ቋት ዉስጥ በመጨመር በመጨረሻም ኢትዮጵያዊነታቸዉን አዉልቀዉ ጎሳዊ ማንነታቸዉን እንዲለብሱ ከፍተኛ ፕሮፖጋንዳ እንዲሁም ተቋማዊ ስራ ተሰራባቸዉ:: አብዝቶ የሚያሳዝነዉ ታዲያ ጎሳዊ ማንነታቸዉን ሊለብሱ ሲሞክሩ የየማህበረሰቡ ቁመት ከጎሳዊ ማንነቱ እጅግ የገዘፈና ትልቅ በመሆኑ የማንነት ቀዉስና የስነልቦና መዋለል ይስተዋል ጀመረ::

እናም መደምደሚያዉ ምን ሆነ?በመጨረሻም ህዝባችን ሀገር የሌለዉና ኢትዮጵያዊነቱን የተነጠቀ ሆነ ማለት ነዉ!

ይሄን እዉነታ በሚለተሉት የዜጎች የኑሮ ገጠመኝ እና ኩነቶች ዉስጥ ተመልከቱት::

ኩነት አንድ:-
————-
ሀጎስ ከሀይለስላሴ ጀምሮ ሀብት በጥረታቸዉ ካፈሩ ዜጎች የተገኘ ታታሪ ነጋዴ ነዉ:: ነዋሪነቱም አዉሮፓ ነዉ:: ኢትዮጵያ ሄዶ በመላ ሀገሪቱ ኢንቨስት ማድረግ ይፈልጋል:: ግን የሚፈራዉ ነገር አለ:: ትግሬ ስለሆንኩ ከወያኔ ጋር ተሞዳሙጄ ያፈራሁት ሀብት ስለሚመስላቸዉ በሌሎች ክልል ያሉ ኢትዮጵያዉያን ቀን ዘንበል ያለ እንደሆነ ሀብቴንም እኔንም ያጠፉኛል ብሎ ያስባል::

ኩነት ሁለት:-
—————
ሀያልሰዉ በትንሿ የሀረሪ ክልል ብዙ ሀብት አፍርቶ ነበር:: የሀረሪ ክልል ባለስልጣናት ሀረሪ የሚለዉን የቀልድ ክልል ብቻቸዉን እንድ ትንሽ ጀልባ ሊቆጣጠሩት አስበዋልና ሀረሪ ያልሆኑ ኢትዮጵያዉያንን ሀብት እንዲሁም ንግድ ደጋግመዉ ሲያቃጥሉ ሀያልሰዉ ያፈራዉ ሀብት ሁሉ ደጋግሞ ስለወደመበት ካሁን ብኋላ የትኛዉም የኢትዮጵያ ክልል ዉስጥ ንግድ ላለመስራት አስቦ ነበር:: አንዳንድ ሰዎች ግን አማራ ስለሆንክ አማራ ክልል ይሻልሃል ቢሉት አማራ ክልል የተሻለ ይሆናል ብሎ አማራ ክልል ኢንቨስት ያደረገዉ ሀብትም በሚገርም ፍጥነት አንዴ የቅሪት ፊዉዳል : አንዴ የኢሰፓ: አንዴ የመዓህድ ሌላ ጊዜ ደግሞ የቅንጅት አመለካከት አለዉ ተብሎ እንዲከስር ተደርጓል::

ኩነት ሶስት:-
————–
ደቻሳ ኢትዮጵያን ለመምራት የሚያስችለዉን የስነልቦና እና የእዉቀት ዝግጅት አድርጎ የጨረሰ ሰዉ ነበር:: ደቻሳ የሚያነሳቸዉ ዲሞክራሲያዊ አመለካከቶችን ግን ማንም ኢትዮጵያዊ ፖለቲከኛ ከምር አድርጎ ለመዉሰድ ሲቸገሩ ያስተዉላል:: “ምን ሆናችኋል?” ሲላቸዉ “ያዉ ዞረህ ዞረህ ኦሮሚያ ይገንጠል የምትል ይመስለናል” ይሉታል:: እሱም ይመልሳል:: “አማራ ክልል: ደቡብ ክልል እና ሶማሌ ክልል ዉስጥ ያለዉን በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ኦሮሞ የት ትቼ ነዉ የምገነጠለዉ:: ከዚያም በላይ ከብዙ ሚሊዮን ኢትዮጵያዉያን ጋር የተዋሃደዉን ዉህድ ኦሮሞ ለማን ትቼ ነዉ የምገነጠለዉ ? የኦሮሞ ማንነት ከኦሮሚያ የገዘፈ ነዉ::” ደቻሳ ለማስረዳት ይሞክራል:: ግን የሚያምነዉ የለም:: ወያኔ ኦሮሞዉን ጥሩ አድርጎ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ቆርጦታል::

ኩነት አራት:-
———-
ሰብሉ በደርግም በወያኔም ሰዎችን እየወነጀለ እና እያቃጠረ የሚኖር ሰዉ ነዉ:: ሰብሉ እምነት የለዉም:: ሰዉ አይወድም::ሌባ ነዉ:: በቀን ዉስጥ አስር አይነት ባህሪያትን ማሳዬት ይቻላል:: ባለስልጣን ሲያገኝ በፍጥነት መመሰልና መሆን ይችላል:: የዘር ሀረጉ የተመዘዘበትን ጎሳ አጠገቡ ካለዉ ባለስልጣን ጋር በፍጥነት የማመሳሰል ተሰጥዖው ልዩ ነዉ::ማንንም አይወድም:: ማንንም አያምንም:: የሰዉ ሀብት አጭበርብሮ እና ከባለስልጣናት ተሞዳሙዶ መንጠቅ ይችላል:: እግዜርንም ሆነ ሰይጣንን አይፈራም:: እግዜርም ሆነ ዲያቢሎስ አምላኩ አይደለም:: እግዜር መጥቶ ጌታህ ነኝ ቢለዉ ግን በፍጥነት እሽ ይላል:: እግዜር ዞር ሲል ዲያቢሎስ መጥቶ ጌታህ ነኝ ቢለዉም በፍጥነት ተገልብጦ እሽ ባሪያህ ነኝ ይላል::

በጣም ፈሪ ስለሆነ የማንንም አመለካከት መጋፋት እና እዉነት ነዉ ስለሚለዉ ነገር መቆም አያዉቅም:: ግን አድብቶ ማጥቃት ያዉቅበታል:: በተለይ ገንዘብ የሚያስገኝ ከሆነ ሁሉንም ተንኮሎች ማጠንጠን ይችላል:: ምላሱ ጤፍ ይቆላል:: እናም ይሄ ሰዉ በደርግም ጊዜ በወያኔም ጊዜ በሀገሪቱ ዉስጥ ሀብታም ሆኖ የቀጠለ ነዉ::

ኩነት አምስት:-
—————-
በወጣት ስሜት የተሞሉት መሃመድ: ንጹህ: አሊ: ግዞ: ሰማኝ: ደበላ: ምህረት እና አበራ ሆነዉ “አሃመነስ ቴክኖ ግሩ” የሚል ኢትዮጵያን መሰረት አድርጎ መላዉ አፍሪካ የሚያዳርስ ቴክኖሎጅ ፈጠራ እና ንግድ ላይ የሚሰራ ድርጅት መስረትዉ ነበር:: የድርጅታቸዉን ስም አሃመነስ ያሉትም ከክርስቶስ ልደተ አለም በፊት በ1900 ዓመተ አለም (ዓ.ዓ) አሃመነስ የተባለ ኢትዮጵያዊ የጠፈር ተመራማሪ በህዋ ዉስጥ 16 ፕላኔቶች አሉ ሲል የደረሰበትን የምርምር ምጥቀት ለማስታወስ እንዲሁም የባለዐእምሮ ህዝብ መሰረት ላይ የቆሙ ወጣት መሆናቸዉን እና እነሱም ለትዉልዳችዉ የሚያበረክቱት ነገር እንዳላቸዉ ለማጠዬቅ አስበዉ ነበር::

ሆኖም የሚያገኙት የወያኔ ባለስልጣን ሁሉ የሚጠይቃቸዉ ተደጋጋሚ ጥያቄ ቁጭ ብለዉ በጋራ እንዲያነቡ አድርጓቸዋል:: “ብሄራችሁ ምንድን ነዉ? የሱ ብሄርስ ? የእርሷ ብሄርስ? ከጀርባችሁ ማን ነዉ ያለዉ? የአማራ የነፍጠኛ እና ትምክህተኛ ስሜት እመሃላችሁ አለ? የኦሮሞ የጠባብነት ስሜት እመሃላችሁ አለ? የጉራጌ አድርባይ ሀይል እናንተ መሃል አለ? የእስላም አክራሪነት ስሜት ያለዉ ሰዉ እመሃላችሁ አለ ?” ጥያቄዉ ማለቂያ የለዉም::

የመላዉ አለም ወጣቶች በዚህ የቴክኖሎጅ ዘመን ስለ ቴክኖሎጅ ምርምር : ስለህዋ ምጥቀት: ስለ ታላላቅ ፈጠራዎች በጋራ ይሰራሉ:: አዕምሯቸዉን አስፍተዉም ይጨነቃሉ:: እንኳን በአንድ ሀገር ዉስጥ ያሉ ዜጎች በመላዉ አለም ያሉ ዜጎች ስለጋራ ቢዝነስ ይጠበባሉ:: ስለጋራ ፈጠራ እና ስለጋራ ታላላቅ የአለም ንግዶች ተባብረዉ ይሰራሉ::

የኢትዮጵያዉያን ወጣቶች ግን ወያኔ በቀዬሰዉ የጎሳ ፖለቲካ አስተሳሰብ ታንቀዉ ገና ወደ ድንጋይ ዘመን ይንሸራተታሉ:: “እከሌ ጎሳ ቡዳ ነዉ:: እከሌ ጎሳ ከብት ነዉ:: እከሌ ጎሳ ካንሰር ነው:: እከሌ ጎሳ ሰዉ አይደለም::እከሌ ጎሳ ዝንጆሮ ነዉ:: እከሌ ጎሳ ከምድረ ገጽ መጥፋት አለበት::” ሲባባሉ እና ሲተቻቹ ሲሰዳደቡ ይዉላሉ::

ኢትዮጵያ በአለም ላይ ካሉ ሀገሮች ብዙ ሰፊ የሚባል የቆዳ ስፋት የላትም:: ቢሆንም ቀላል የሚባልም አይደለም:: በህዝብ ቁጥር ከአለም ሀገራት 13ኛ ደረጃ አላት:: በኢኮኖሚ ህዝቧ ገና ሌት ከቀን መስራት እና ወደፊት መራመድ አለበት:: ህዝቡ ብዙ ዉህድ ነገሮች ያሉት ዉህድ ህዝብ ነዉ::የወያኔ የጎሳ ፖለቲካ ግን ታላቅ ገበያ ያለዉ ኢትዮጵያዊ ዉህድ ማህበረሰብ አብሮ እንዳይኖር እና አብሮ የኢኮኖሚ ግስጋሴ እንዳያደርግ ሁሉንም ነገር ተረት ተረት አድርጎታል:: ዛሬ ስለኢትዮጵያ ህዝብ ዉህድነት መናገር ልክ ተረት ተረት እንደ መተረክ ይቆጠራል::

ስለ ጋራ ብልጽግና ሳይሆን ስለ እርስ በእርስ መጠፋፋት ወጣቱ ሌት ከቀን እንዲያልም የጥላቻ ቋንቋዎች በስፋት ተዘርተዋል:: ዲሞክራሲያዊ የሀሳብ ልዉዉጥ ኢትዮጵያዉያን ወጣቶች መሃከል የሚታሰብ አይደለም:: ስለብልጽግና መነጋገር ተረት ተረት ነዉ:: ስለ ጋራ ቢዝነስና ታላላቅ ፈጠራዎች ማዉራት ተራ እና ከንቱ ነገር ኢንዲሆን ተደርጓል::

በኢትዮጵያዉያን ወጣቶች መሃከል ሀገራዊ አጀንዳ እንዲጠፋ ወያኔ ሁሉንም ወጥመዶች አጥምዳ ጨርሳለች:: በወያኔ የጎሳ ፖለቲካ የተነሳ የኢትዮጵያዉያን ወጣቶች በድንጋይ ዘመን እንዲኖሩ ታላላቅ አዕምሮ ፈሶበት የተፈጠረዉ ማህበራዊ ሚዲያ እና ልዩ ልዩ ለሰዉ ልጅ ብልጽግና የሚዉል የሚዲያ ቴክኖሎጅ ሁሉ ኢትዮጵያዊ ማህበረሰቦችን ማጠላሊያ : ማራራቂያና ማጠፋፊያ እንዲሆን ሆኗል:: ኢትዮጵያም የማንም ያልሆነች ሀገር እንድትሆን ተደርጓል::ኢትዮጵያም የኔ የሚላት ዜጋ የላት::ዜጎቿም ሀገር የላቸዉም:: ከሁሉም የከፋዉ ደግሞ የነገ የጋራ ተስፋቸዉን ሁሉ ተነጥቀዋል::

በጎሳ ፖለቲካ ህሳቤ መሰረት ኢትዮጵያዊነት በቂ አይደለም:: እንዲያዉም ምንም ዋጋ የለዉም:: ወጣቶቹን የወያኔ ባለስልጣናት ሊገመግሟቸው እና ዉጤታማ እንዳይሆኑ እንቅፋት የሚያስቀምጡላቸዉ ብሄራቸዉን : ሀይማኖታቸዉ እና አመለካከታቸዉን እየለኩ ነዉ::በጎሳ ፖለቲካ ዉስጥ ሰዉነት ከጎሳ ማንነት ያነሰ ነዉ:: ኢትዮጵያዊነትም ከቀበሌ ማንነት እጅግ ዝቅ ያለ ነዉ::

እናም በመጨረሻ “አሃመነስ ቴክኖ ግሩ” የመሰረቱትም ወጣቶችም: ሀጎስም : ሀያልሰዉም: ደቻሳም ለየብቻ ቁጭ ብለዉ ይቆዝማሉ:: ስለክልል ሲያስቡ ክልል የላቸዉም::ስለማንነታቸዉ ሲያስቡ እዉነተኛ ማንነታቸዉ ከጎሳ ማንነታቸዉ በላይ ነዉ:: ማንነታቸዉን በሀገራቸዉ ልክ እንዳያደርጉት ደግሞ ስለ ሀገር ሲያስቡ ሀገር የላቸዉም:: እነሱም ሊሞቱላት የሚያስቡት እንዲሁም የሚኮሩባት ሀገር እንደሌላቸዉ አምነዉ ኢትዮጵያ የሚለዉን ቃል ገፍተዉታል:: ኢትዮጵያ ዉስጥ ሰርቶ የመለወጥ ተስፋቸዉ ተሟጧልና የሆነ ሌላ ሀገር በመሄድ በሌላ ሀገር ዉስጥ ጠንክረዉ ሰርተዉ ሀብታም ስለመሆን እያንሰላሰሉ ነዉ:: በደምሳሳዉ ሲታሰብ ሀገር የሌለዉ ህዝብ : ኢትዮጵያዊነቱን የተነጠቀ ህዝብ ምንም ነገር ቢያስብ ወይም ተስፋ በልቡ ባይቋጥር የሚደንቅም ላይሆን ይችላል::

ሀገር የሌለዉና ኢትዮጵያዊነቱን የተነጠቀ ህዝብ ከመሆንም የከፋዉ መጻኢ ራዕይዉ የተነጠቀ ህዝብ መሆን ነዉና የኢትዮጵያ ህዝብ ምንም የጋራ ራዕይ የሌለዉ ድንግዝግዝ ጨለማ ዉስጥ የገባ ህዝብ ሆኖ በወንዝና በጎሳ ማንነት ቀለበት ዉስጥ ገብቶ የሚዳክር በእርስ በእርስ ጥላቻ መሰረት ላይ ተደላድሎ እንዲቆም ተደርጓል:: ሀገር የሌለዉና ኢትዮጵያዊነቱን የተነጠቀ ህዝብ ከመሆንም የከፋዉ የጋራ መጻኢ ራዕይ የሌለዉ ህዝብ መሆን ነዉ !

እናም እድገትና ብልጽግና ሰላም እንዲሁም የሁሉ ወገን ፍቅር የናፈቃቸዉ ሰዉ ናቸዉና በዬልባቸዉ ያነባሉ:: አንድኛቸዉም ግን ኢትዮጵያዊነትን ነጥቆ ሀገር አልባ ያደረጋቸዉን ነገር ምን እንደሆነ ደፍረዉ ተነጋግረዉ አያዉቁም:: በዉስጣቸዉ ግን ያዉቁታል:: የወያኔ የጎሳ ፖለቲካ ህዝባችንን ኢትዮጵያዊነቱን ነጥቆ እንዴት ሀገር አልባ እንዳደረገዉ ገብቷቸዋል::

እዉቀታቸዉ ግን ግማሽ ነዉ:: አሁን የገጠማቸዉ እዉነታ እንዲለወጥ ይፈልጋሉ እንጅ ይሄን ሁኔታ ሊለዉጡ የሚፈልጉትን ወገኖች ደግሞ ሲነቅፉ ይገኛሉ::ይባስ ብለዉም ህዝቡ በተገቢዉ መልክ ስላልደገፋቸዉ በቀጨጨና በመነመነ መሰረት ላይ የቆሙትን ተቃዋሚዎች እንዲህ አላደረጉ እንዲያ አላደረጉ እያሉ ሲተቹና ሲያንቋሽሹ ይዉላሉ:: በለዉጡ ሂደቱ ዉስጥ የኛ ሚና ምን ይሁን ብለዉ ግን ጠይቀዉ አያዉቁም:: ወይም አንድም ቀን ተቃዋሚዎች ምን ሊደገፉ ይገባል ሲሉ ጠይቀዉ አያዉቁም:: የትኛዉ ተቃዋሚ ነዉ ኢትዮጵያን ወደ ከፍታ ማማ ሊያወጣት የሚችለዉ የሚለዉን ጥያቄ አንስተዉ አያዉቁም:: ተቃዋሚዎች በራዕይ : በጉልበት: በተቋማዊ አወቃቀር እና በሌሎች ነገሮች ሁሉ ለምን አቅመቢስ እንደሆኑም አስበዉም አያዉቁም::

አንድ ነገር እንዲለዉጥ ከፈለግህ ማወቅ ብቻዉን በቂ አይደለም:: ለለዉጡ መሳካት ተነስተህ መስራት አለብህ::ሌሎች እንዲህ አላደረጉ ወይም እንዲያ አላደረጉ እያሉ ማንንም መክሰስና መዉቀስ አይቻልም::

ሀገር ያለዉ ህዝብ ለመሆን ኢትዮጵያዊነትም ከስብርባሪ የወንዝ ማንነቶች በላይ ገዝፎና እሚያስከብር ማንነት እንዲሆን ብሎም ለዜጎች ሁሉ የሚመች እንዲሆን ለማድረግ በእያንዳንዱ ዜጋ መከፈል ያለበት ዋጋ አለ:: እያንዳንዱ ዜጋ ይሄን ዋጋ እስካልከፈለ ድረስ የግለሰቦች ትግል እና ጥረት ምንም የሚያመጣዉ መሰረታዊ ለዉጥ የለም:: ብዙዉ ኢትዮጵያዊ ይሄን ሀቅ አላምጦ እስቂዉጠዉ ብሎም ለተግባራዊ ለዉጥ እስኪነሳ ድረስ ኢትዮጵያዊነት ወደ ከፍታ ማማ ላይ ወጥቶ ለማዬት መናፈቅ ብቻ ወደ ተፈለገዉ ግብ የሚያደርስ አይሆንም::

የሆነ ሆኖ ግን ኢትዮጵያዊነትን ወደ ከፍታ ማማ ላይ ለማዉጣት ከመስራት የተሻለ የመጻኢ ጊዜ አማራጭ የሌለዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ይሄን የፈጠጠ እዉነት የሚያስተዉልበት ጊዜ ብሎም ለተግባራዊ ለዉጥ በጋራ የሚነሳበት ወቅት እሩቅ እንደማይሆን እሙን ነዉ::

የአንቡላ ቃርምያ! (ሥርጉተ ሥላሴ የሳተናው አምደኛ)

ከሥርጉተ ሥላሴ 26.02.2018 (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)

„ሳትናገር አስቀድምህ ነገሩን ተረዳ። በሃጢያት ሳትታመም ንሰሃ ግባ።“ (መጸሐፈ ሲራክ ምዕራፍ ፲፰ ቁጥር ፲፰)

ጤና ይስጥልን ብለናል እኔ እና እመቤት ብዕሬ ለጎንደር ባለጣውንት አቦይ በረከት ስምዖን። ግን እንዴት ነው ትንሽ አሰርውሃ ነገር ጠፋ መሰል? ከቶ የሴራው ቸረቸራ በሽሁራር ተዋጠ ይሆን?

በመጋቢት 24.2015 አንድርያስ ሉቢስ (Andreas Lubitz) የሚባል የጀርመን ዊንግ ረዳት አውሮፕላን ወጣት አብራሪ አቅዶ እራሱን ጨምሮ ወደ 149 ሰው ከተራራ ጋር አጋጭቶ አሰቃቂ እልቂት ፈጸመ። ሰቆቃው እጅግ አስከፊ ነበር። እሬሳው ከተለቀመ በኋዋላ ታች ላሉት ኤሊኮፍተር ይመጣላቸዋል፤ ገመድ ሲላክላቸው ሬሳውን እንደታቀፉ በኤልኮፍተር ተንጠልጥለው በብዙ ገመድ ታስረው ሬሳ ተሽከመው አዬር ላይ በወጀብ እዬተናጡ ነበር የሚጓጓዙት። ያን ጊዜ እንቅልፍ አልነበረኝም፤ እህል ውሃም ትንፋሽ ለማሳደር ያህል ነበር። ታስተውሱ ከሆነ የካቲት ላይ ደግሞ የእኔ ጀግና ረዳት አውሮፕላን አብራሪ ሐይለመድህን አበራ ያ ብርቱና ሃላፊነት የሚሰማው ጠንቃቃ፤ ብልህ ወጣት ሰውንም ንብረትንም ካተረፈበት የተቀደሰ ቅኑ ዕለት ብዙም ሳይርቅ ነበር። ከዛ በኋዋላ ሰማይ ማንጋጠጥ ልማዴ ሆነ። በአውሮፕላን ለሚጓጓዙ ሁሉ ጭንቀታም ሆንኩኝ። ጀግናዬ በሰላም ሲዊዝ ጄኔባ ላይ አርፎ ግን አስከ አሁን ድረስ ሳስበው ይሰቀጥጠኛል። በዚህ በጭንቀት በሰመጥኩበት ማግስት ነበር ይህ ደግሞ የተደረበው። እጅግ አሰቃቂ ነበር። ለሶስት ሳምንት የዘለቀ ዘመቻ ነበር። ሥራው ፈታኝ ነበር። ጀርመን፤ ስፔን እና ፈረንሳይ በጥምረት ነበር ፈተናውን በወል የተወጡት።

  • ተፈጥሮን ስለማሰብ።

ስለምን ይሄ ወጣት እንዲህ ክፉ ነገር አሰበ በማለት አንድርያስ ሉቢስ የህሊናዬ አብይ አጀንዳ ሆነ። ልጆች የህጻናት ማሳዲጊያ ከሚገቡበት ዕለት ጀምሮ በሰው ልጆች ተፈጥሯዊ ፍቅር ላይ ያተኮረ ሥርዐተ ትምህርት ሊማሩ ይገባል ብዬ በግሌ ወሰንኩኝ። ፍቅር ሰውን ያድናል። ግን በተለምዶ ሳይሆን ሙያዊ መሆን አለበት። የሚማሩት፤ የሚመረቁበት፤ ምርምር የሚካሄድበት ወዘተ …

ሃሳቤንም ለሚመለካታቸው ዓለም ዓቅፍ አካላት ላኩኝ። ከዛ በኋዋላ ዓመቱን ሙሉ የስሜት ንክኪ ነገሮች ላይ የተለያዩ ሁኔታዎችን ማጥናቴን ቀጠልኩኝ። „ስሜት“ የሰውነትን ሰራዊት ጄኒራል ነው። ቁጡነት፤ ብስጩነት ወዘተ … በዚህ ዙሪያ ዓለም ምን እዬሰራች ነው? ብዬ ሳስ የተለያዩ መረጃዎችን አገኘሁኝ። በተለይ „ሜዲቴሽን“ በሚመለከት ያለው ውጤት ጥሩ ፍንጪ ነበር። በዚህ ፍንጭ ተጓጉዤ አሜሪካን ሐገር እንደ ገናም ጀርመን ሐገር በዚህ ዙሪያ ብስጩነትን የማስታገሻ መንገዶችን ተከትሎ የተሠሩ ተግባራት እና የተገኙ ውጤቶችን ተከታተልኩኝ። የትውልድ ነገር ስለሚያስጨንቀኝም በመደበኛ የጀርመን፤ የኦስትራሺን እና የሲዊዝን የወጣቶችን የተለያዩ ውድድሮች እከታተላለሁኝ። ዓለም አስፈሪ እዬሆነች ስለመጣች። በጋራ የውድድር ቆይታ የአብሮ መኖር ዕድል ሲገጥማቸው ከቡድኑ ውስጥ የእስያ ደም ያለባቸው፤ ከሌሎች በተለዬ መልኩ አብዛኛውን ጊዜ ልዩ የሆነ ሰብዕና አይባቸዋለሁኝ። ስለምን ይሆን ብዬ ደግሞ ወደ እስያ በስሜት ጎራ ተፈተሽ እስያ ስል፤ የእስያ ልጆች እብዛኞቹ ጤናማ እና የተረጋጋ መንፈስ አላቸው። ምክንያቱ ምን እንደሆነ ስከታተለው ያው ከሜድቴሽን፤ ከዮጋ አደረሰኝ። ፈተንኩት። በራሴ ላይ ሠራሁበት።

ከዛ ቀጥዬ እማማ አፍሪካስ ምን እየሰራች ይሆን ብዬ ስኳትን ነው የኛውን ድንቅ ዶር ምህረት ደበበን ያገኘኋዋቸው። ያን ቀን ደስታዬ ወደር አልነበረውም። እሳቸውን ሳገኝ የሳቸውን ቃለ መጠይቅ፤ የሠሯቸውን ተግባራት፤ ያቋቋሙትን ፕሮጀክት ስመረምር ነበር የዶር አብይን አህመድን ጉዳይ ያገኘሁት። ይህ መልካም ጅምር በነበረበት ጊዜ ለአቦይ በረከት  ስምዖን ዶር አብይ አህመድ ስጋት አልነበሩም። የሳይስንስና ቴክኖሎጂ ሚር/ በነበሩበት ጊዜ ከእርምጃ ወደ ሩጫ“ ሞቶ ላይ ስብሰቡ ከድንቅ በላይ ነበር። የስበስቡ አመራረጥ የደረጀ እና ዓላማውን በዘለቄታ ለመሳካት ከጉልቱ የተነሳ ነበር። … ቀደምቶችን ፈላስፋዎቻችን ተወት አድርጌ ግን በወጣቶች ላይ የነበረው አትኩሮት ሳበኝ … ተተኪ ትውልድ ማፍራት ለዶር አብይ አህመድ የነፍስ ያህል ነው። ተከታታይነት ብሩህ አጀንዳ ነው። ተንታኞቹ በዬተሰጣቸው እርአስ ጉዳይ  ዶር. ምህረት ደበበ፤ ወ/ሮ ጽዮን ተክሉ፤ ዶር ብሩክ ለምቢሶ ሙሉ ዕድሜ ላይ ያሉ፤ አቶ ዮናስ ደስታ  ወዘተ ነበሩ ። ሃሳቡ ከተነሳ አንድ ለአቦይ በረከት ሲለጥቅም ፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂን የሚነስት ወይንም በእንቅጥጠቅጥ የሚሰለቅጥ ክኒን ልግለጥ።

  • እንደ እሸት ቅመሱ፤

… አቶ ዮናስ ደስታ ካሉት … ከስማርት ፎን ፍልስፍና በፊት ኢትዮጵያ የቀደመችበት አብይ ጉዳይ አለ ይሉናል። „የመጀመሪያው ስልጣኔ ሊሆን የሚችለው የሰው ልጅ ከአካባቢው እራሱን ፊድ ለማድረግ የተጠቀማባቸው ስቶን ቱሎች ናቸው። the most papleshed stone ይሏታል ያቺ ስቶን ቱል ጎና የሚባል ኢትዮጵያ ወደ ደቡብ ላይ ያለ የተገኘች ድንጋይ ስትሆን 2.6 አንድ ሚሊዮን ዓመት ዕድሜ ያላት ናት። ከዛች የድንጋይ መሳሪያ በፊት የተገኜ ቴክኖሎጂ ስሌላ ስማርት ፎን … ወዘተ … መነሻው የእኛ ነው።“  ስለ እጽዋት ፕ/ ሰብስቤ ደምሴ ደግሞ እንዲህ ይላሉ „ብዙ እማናውቃት የህብነት የሚባል በሱማሌ /ኢትዮ/ ክልል ውስጥ balanced (diet) የሆነ ምግብ ስለመሆኑ ተመስክሮለታል።“  አንደ ሽፈራው ቅጠል ማለት ነው። እና ከእነ ቁጭበሉ ጋር ይህን የሊቃውንት ጉባኤ ያደራጀ፤ የመራ፤ ስለ እናቱ በጥልቀት ሊመራመር የፈቀደ … የእናቱ ቀደምትነት እና ኋላቀርነት አለመመጣጠን ሩሁ አድርጎ ለያዘ ቅን፤ ሩህሩህ፤ አዛኝ፤ ለማወቅ ጉጉት ያደረበት፤ ራሱን ዝቅ ያደረገ ለእናቱ መታመንን የሸለመ መንፈስ ጋር እንዴት ከነአለቅት ጋር … ጋዳ ነው …

  • የትቅማጡ መነሻ በጥቂቱ።
  1. አቦይ በረከት ስምዖን በቀጥታ ሥራ ፈት ይሆናሉ። የብዕር ቅርሻቸው የሽሁራር ማራገፊያ ይመክናል። „የአፍሪካ ነብርነት“ ፉከራ ¡እንዲህና እንዲያ … ቀልድ ስምጥ።
  2. በኤርትራ መንግሥት የተሰጣቸው ስውር የስለላ ልዩ ተልዕኮ፤ ሃላፊነት እና ግዴታ ወደ መቃብር ይወርዳል።
  3. እንደ ተፈለገ ቢሮ ሆነ ቤት ተገብቶ ካሜራ ገጥሞ፤ ድምጽ መቅጃ ገጣጥሞ መሰለል ያከትማል። ዕውቀቱ ከነሙሉ ቁመናው መዳፍ ላይ ስለሚኖር የስላለ ሰላላን እሞክረዋለሁ ቢል ግጥግጡ መላላጥ ብቻ ነው የሚሆነው።
  4. የስለላው ውጤት ሁለመናዋን ቀጤማ አድርጎ ለጥቃት ማጋለጥ ወዘተ … ግባዕተ መሬት …
  5. ጣልቃ እዬገቡ መንጨቧረቅ ሆነ ወጥ እንጨት መሆን ይቀራል። በተዘዋዋሪም ቢሆን የሚቻል አይሆንም። በፍጹም የታመኑባቸው ጉዳዩች በመርህ እና ለወቅቱ በሚያገለግለው ህግ ብቻ ይከወናል። ከህግ በላይም ከህግ በታችም መወዛወዝ መንገዱን ጨርቅ ያድርግልህ ይባላል። ክልሎችን መነሰተም መልክ ይይዛል።
  6. ተጠያቂነት እና ሚዛናዊነት ከዝቅተኛዋ ሐገራዊ ጉዳይ እስከ ከፍተኛው ድረስ ባለቤቱ ውስጥነት ይሆናል። ጥምና፤ ቅልውጥ ይሰናበታል። በሐገር መደራደር … አከርካሪው ወጌሻ አልቦሽ ይሆናል።
  7. ከረባት እያንጠለጠሉ የውሸት ቁጥር መደርደር ያከትማል። ችግሩ በልኩ ይጠናል። የመፍትሄው ዘለቄታ መለኪያው ጭንቅላት ስለሆነ በዛም የሰራበታል።
  8. ትልቅ ሐገራዊ ፕሮጀክት አቅዶ በስብሰባ በዛብኝ ሰበብ ቀልድና ቁም ነገር ግብዕቱ ይፈጸማል። አላግባብ የጊዜ፤ የህሊና፤ የመዋለ ንዋይ፤ የታሪክ ብክነት በአግባቡ ይመራል።
  9. ተዘርፎ በድልቂያ የሚራወጣው የዳንኪራ ዲስኮ ቤቱ ይከረቸማል።
  10. ርህራሄ፤ ሰዋዊነት፤ ተፈጣሯዊነት ይነግሳሉ።
  11. ማድመጥ፤ ማዬት፤ ማጥናት፤ አዲስ ሃሳብ ዕውቅና ይሰጣቸዋል፤ ይከበራሉ፤ ቀን ይወጣላቸዋል።
  12. ባለቤት አልባ ሁነቶች ከከርሰ ምድር በታች ያሉ የኢትዮጵያ አንቱ ጥሪቶች ሳይቀሩ ለብቃት አቅም የሚሆኑበት ሁኔታ ይመቻቻል። በትጋትና በተከታታይነት ይሰራበታል።
  13. የግል አንባገነንነት ተጥሶ የወል አመራር በግል ሃላፊነት ድርሻ ይሰክናል። እያንዳንዱ በግል ሁሉም በጋራ ይጣመራሉ። ግንኙነቱ መርሃዊ እንጂ ጎናዊ፤ ወይንም ዲያጎናላዊ አይሁንም።
  14. ሃላፊነት በአግባቡ መወጣት የመጀመሪያው ረድፈኛ ሞቶ ይሆናል።
  15. የኢትዮጵያ ሁልአቀፍ ችግር በሰከነ ጥናት፤ በታቀደ ተደሞ አድማጭ ያገኛል። መንገዱም ይጠረጋል።
  16. „ድሃ፤ ለማኝ፤“ የምንባለበት ዘመን ለመቀየር የመነሻ ነገሮች ይሠራባቸዋል። ለምሳሌ የካቢኒ አባላት ብቃት፤ ጥራት፤ ችሎታ በፓርቲ፤ በዞግ፤ በሌላም ሌላም ሳይሆን በጭንቅላት እና በተጨበጠ የማድረግ ሙሉ አቅም፤ ከሙሉ ጨዋ ስብዕና ጋር ይሆናል።
  17. ለዬዘርፉ ተተኪ ማፍራት ዋናው አናት ጉዳይ ይሆናል።
  18. በጠ/ሚር በዓለም አቀፍ መድረክ ሳይቀር መሳቂያና መሳለቂያ የሆንበት ዘመን ያከትማል። አንገት አንደፋም። አናፍርም። ወቀሳ አይኖርም ማለት ግን አይደለም። ሁሉን ሰው ማስደሰት ስለማይችል። ኔጌቲብ የሚያስቡ ሰዎችን የመቀነስ ተግባር ተመጣጣኝ ለማድረግ ይሰራበታል። ጥሞና የሚጠይቁ ውስብስብ የተከመሩ የዘመናት ችግሮችም ስላሉብን ግን ሸክሙ ግዙፍ ነው። ተጋድሎውም ግዙፍ ነው። ለዛውም ሀገር ምድሩ ቁጡ በሆነበት ሰዓት። ትእግስት ከእዮብ መሸመት ግን ግድ ይላል። ልቡ ከኖረን። የሚታዬው ግን ዕድሉ የጨበራ ተዝካር ሆኖ ባክኖ እንዲቀር የታደመበት ይመስላል። ሴሪሞኒያዊ ሩጫው ደርቷል። ቀውስ ለመፍጠርም እየተሰራበት ነው። ለኢትዮጵያ እናት ምን ሲቸግር ለኢጎ ብርንዶ ለዛውም የሰው ሳታክት ታቀርባለች። የትውልድ ብክንት ስለመሆኑ ከቁጥር አይገባም። ስከነት ተሰደደ …
  19. ኢትዮጵያን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የሚመኟት ሁሉ ልካቸውን ይዘው፤ በመከባባር እና በእኩልነት ላይ ግንኙነቱን እንዲያደርጉ መንገድ ይጀመራል። የውስጥ አርበኛ ሰላዮቹን ጨምሮ ትኩረቱ ከውስጥነት ይሆናል።
  20. ዘመን ጠገቡ የኤርትራውያን ገብተው የማነኮር አዚም ለመጀመሪያ ጊዜ ያከትማል። ኢትዮጵያ በማህጸኗ ፍሬዎች በተቆርቋሪነት ጣዝማ እንደ ተፈጣሯዋ ውሰጧ በፍሬ ዘር ይለመልማል። ወዘተ ወዘተ ወዘተ ገራሚው ነገር አንድ አብይ ብቻ አይደለም ብዙ ናቸው፤ የገድአንባው መንፈስ የተከደነ ሲሳይ ነው።
  • አንጎል።

ሌላው አቦይ በረከት ስምዖን ደህና መዳራቸውን ባላውቅም ጨርቃቸውን ጥለው የሚያሳብዳችው ነገር ተከስቷል። የኔዎቹ — ታስታውሳላችሁ አይደል? በባህርዳሩ ኮንፈረስ ላይ ትውር አላሉም የኦሮሞ እና የአማራ የመንፈስ ተደሞ ላይ። ከጎንደሩ ላይ ግን ሙሉ የወያኔ ሃርነት ማንፌሰቶ ባላንባራሶች ተገኝተው ነበር። ግን ለምን? ስለምን? ወፊት ትጠዬቅ …

  • የጎንደሪት ሙሉቀን።

በዚህ OBN በሠራው የዶር አብይ አህመድ ዶክመንተሪ ፊልም ላይ ቀደም ብዬ እንደ ገለጽኩት ጨርቃቸውን ጥለው አለማበዳቸውም እሳቸው ሆነው ነው – አቦይ በረከት ስምዖን። እንዴት በሉኝ? እንዴት ማለት ጥሩ ነው። የማከብራችሁ „የጎንደር መከራ የጠራው አንድ ታላቅ መንፈስ ደግሞ ተከሰተ“ ተመስገን ትበል ጎንደር። ይህም አቦይ በረከት ብቻ ሳይሆን ባለፈው ዓመት ያን መከረኛ ህዝብ ያደረገውን ተጋድሎ እንደ ጎርፍ፤ የሆያ ሆዬ ነገር፤ እዛውም ሊያልፍ የማይችል የመንደርዮሽ ጉዳይ አድርገው ያጣጠሉት የጸሐፊ አቶ አስራት አብርሃንም መንፈስንም ልክ አስይዞ የሚቀጣ ይመስለኛል። ግን ስለምን ይመስለኛል አልኩኝ። ነው እንጂ። በአማራ ማንነት የህልውና ተጋድሎ ምክንያት ወገኖቻችን የቀራንዮ መከራ ተቀብለውበታል። ይህ ለእነሱ ምንም ነው። የሆነ ሆኖ ያ የ43 ዓመት የዕንባ ዶፍ ይመስለኛል ምክንያት ፈልጎ ፈጣሪ እያናገራ ያለው ቅዱሳኑን። የሞራል አባቱ አቦ በቀለ ገርባ እና የግልጥነት የኔታው አቦ ደረጃ ጣፋ „አማራና ኦሮሞ እስር ቤት ነው ያሉት ከአማራም አብሶ ከጎንደር“ ውጪ ሰው የቀረ አይመስልም ነው። የዛን ህዝብ መከራ – ከውስጣቸው ነው የተጋሩት – ቅዱሳኑ። አሁን ደግሞ ከሰሞኒት አንድ የኢትዮጵያ አዱኛ ድንቅ የሃይማኖት አባት „ለጎንደር ማን አለው?“ አሉ ሊቁ ኡስታዝ አባ ራይ አባመጫ። በቴሌቪዥን እኮ ነው እንዲህ ያሉት። ጉድ በል ጎንደርስ አሁን ነው። ይሄን ያክል ከውስጣቸው ገብቷል የነገረ – ጎንደር አሳር እና ፍዳ። ደም መላሽ! የልቤ መሠረት የሆኑ የሃይማኖት አባት። አደራ ይጠንቀቁ! እነዚህ ሰላቢዎች አይታመኑም። አላህ ጨምሮ ጨምሮ ክብሩን፤ ሞገሱን፤ ግርማውን ይስጥልን። እጅግ የማከብረውት ኡስታዝ አባ ራይ አባመጫ የ43 ዓመቷ ጥቁር ለባሽ፤ የዘመኑ ማገዶ፤ እሰረኛ ጎንደርን በቃሽ እንዲላት፤ ይህ ዘመን የመከራዋ መጨረሻ እንዲሆን እባከዎት የተለዬ ድዋ ያሰደርጉላት? አደራ! ከታችም የለጠፍኩትን ሰቆቃ እባከዎት ያደማጡት። እግዚ አብሄር ይስጥልን። ይኑሩልን። https://www.youtube.com/watch?v=TyzkK6btxRM Ethiopia: OBN Documentary – ዶ/ር አብይ አህመድ ማን ናቸው? : Who is Dr Abiy Ahmed? | February 2018፤ የአማራ ተጋድሎ መከራውን ለማድመጥ ላልፈቀደ ሁሉ ፈጣሪ „በአንድም በሌላም እያናገረ ነው።“ ይሄ ነው አቦይ በረከትን የሸረከታቸው፤ የገረደፋቸው፤ የሾከሸካቸው፤ የሰለቃቸው፤ የወቃቸው፤ የለነቆጣቸው። „ለጎንደር ማን አለው?“ ይገርማል። ተመስገን። እናት ሆዲት ጎንደር ምንም እንኳን መከራሽ ባያልቅም እንደ እናት አንጀቱ የጎጃም ህዝብ ፈጣሪ አምላክ ድንበር፤ ሃይማኖት፤ ብሄረሰብ፤ ጾታ ሳይለይ መከራሽን እዬተጋራ ነው ወገንሽ። አይዞሽ እናትዓለም።

  • አቅመ ልሙጥነት። ጭንቁ በጨርቁ።

የአቦይ በረከት ስምዖን መንፈስ አማራነትን መሸከም አይችልም። በፍጹም! ጭንቅ ነው። ቁመናው ልፍስፍስ ነው። አማራነት ፖሰተር አይደል አይለጠፍ ነገር። ቀለም አይደል አይቀባ ነገር። ወይ ቀዳዳ አይደል ማንነት አይወታተፍ። አማራነት የጥርስ መጥቆሪያ አይደል አይጠቆሩት ነገር። ኤርትራዊ በምን ሂሳብ አማራ፤ የአማራ ወኪል አራጊ ፈጣሪ ሊሆን ይችላል? አይሸመት አይሸቀጥ ነገር ደም። ግን ግን አቦይ በረከት ለመሆኑ ደህና አድረው ይሆን? የቀበር ጉድጓድ!

  • እንጂ ….

እኔ „መባቻን“ „መቋሚያን“ „ጣና ኬኛ የቄሮ ወጣቶችን 2 መቶወቹ የአብቹ አርበኛች“ „ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ የጸጋዬ ትንሳኤ መሆኑን ስጽፍ፤ በኋዋላም ጥቃቱ ሲበዛ „አብይ ኬኛ ከክፍል አንድ አስከ ስድስት ስጽፍ“ በመጨረሻም ጉግሱ በፈረቃ ሲጠናከር „ህሊናን“ ስኮልም አቦይ በረከት ስምዖን ነገረ አብይ ከዚህ ይደርሳል ብለው አልገመቱም ነበር። ተስፋቸውን ጥለው የተደላደሉበት ነገር ነበር።

  • የሚገርመኝ፤

እኔ ስለ ዶር. አብይ ፎቶ ስመርጥ ጉግል ላይ 500 አይሞላም ነበር፤ ከዛ ወደ 87 ሺህ ከፍ አለ፤ በሰሞኑ አጀንዳ ደግሞ ወደ 114,000 የሚደርሱ ውጤቶች (0.44 ሴኮንድ) በንግግራቸው ላይም ለማገናዘቢያ ስሰራ በእያንዳንዱ ላይ ከ300 – 1500 ነበር ዛሬ ሳዬው 175,379 views ልብ የሚነካ አስገራሚ ንግግር Dr abiy ahmed # mind set

ይህ ማለት እንግዲህ የተለያዬ ሰው ነው በተለያዩ ዩቱቦች የሚለጥፈው፤ በዚህ ስሌት ቁጥሩ የትዬሌለ ነው። በዬቀኑ ነው የምቆጣጠረው። ዊክሊ በዚህ ሳምንት ብቻ ለሦስት ጊዜ ያህል የህይወት ታሪካቸውን በሚመለከት በማጠናከሪያ አስተካክሎታል። ይህ አቅም ኤርትራን ራድ ያልስያዘ ማንን? ትንቀጥቀጥ። ትንዘፍዘፍ!

  • ከእውነተኛው ዴሞክራሲ ልቆ የሄደ ሰብዕና።

እዮር ሰማይ ላይ ብቻ ሳይሆን በዚህ ቅዱስ መንፈስ ውስጥ አየሁ። ለዛውም ስለእኔ። ተመስገን።

https://www.youtube.com/watch?v=8Z6HexcMHGU „Ethiopia – Dr Abiy ከላይ ስትሆኑ በዛ መነጽር ብቻ ታች አትመልከቱ“ አጠቃላይ የዕድምታውን ጭብጥ ነው እኔ እማነሳው። ሃዘኑ ከውስጣቸው ሲገባ፤ ተቆርቋሪነታቸው ሲያል፤ እዩት ክብረቶቼ የቻላችሁ አዳምጡት። እስቲ የትኛው አለቃ ነው ሃላፊዎችን ሰብስቦ „ አለቃ ስንሆን ሰርቢስ ማምለጡን ረስተነዋል። አስተውሰነው አናውቅም። ብዙ ጉድ አለ ቤት ውስጥ የልጆች ጉዳይ አለባት፤ ፖርሳዋ ገንዘብ ላይኖረው ይችላል፤ በእግሯ ኳትና ስትመጣ …“ ጨርሱት። „ሌላዋ ደግሞሞ ልጇ ታሞባት ልጄ ታሟል ብላ ፈቃድ ስትጠይቅ የተለያዬ መልስ እንሰጣለን፤ የሃኪም ወረቅት ይዘሽ ነይ ወዘተ … ይሄ ቁስ ነው። ልጅ ታመመብኝ እኮ ነው ያለችው። ሰርግ ልሂድ አይደለም። መደንገጥ አለብን ምን ሆነብሽ? ሰርቢስ አለሽ? ገንዘብ አለሽ? እኔ ላድርስሽ ካልልን ምን አለቃ ሆነው? በዬዕለቱ ሰራተኛ በጉንፋን የሚይዘው መጸዳጃው ቤቱ ንጹህ ባለመሆኑ ነው። ግን አለቆች ሄዳችሁ አይታችሁት ታውቃላችሁን?“ ይሄ ለእኔ ከእውነተኛው ዴሞክራሲ በላይ ነው። እራሱ ዕውነተኛው ዴሞክራሲ ይህን ቅድስና አይችለውም። ምክንያቱም አሸናፊው ድምጽ ትክክልም ትክክልም ላይሆን ስለሚችል፤ ተሸናፊው ትክክል ከነበረ ሊጎዳ ስለሚችል። አሸናፊው ትክክል ቢሆንም ተሸናፊውን ሃሳብ አመጣጥኖ ዕውቅና አይሰጠውም። ስለዚህ ተባደግ ነው ለእኔ በግል። የሰዋዊነት የተፈጥሯዊነት ከሆነ ግን ተሸናፊውም እኩል እንክብካቤ እና ክትትል ይደረግለታል። አቋጣሪው አሸናፊው ሃሳብ እራሱ ይሆናል። ብቻ የዶር. አብይ አህመድ ሰብዕና  ደረጃ እና ጥልቀቱ እንዲህ አይነቱን አንጀት አርስ ርህርና የመሸከም አቅም፤ አቅልም የለውም የአቦይ በረከት ሽሁራር የበላው አይዲወሎጂ ሶሻሊዝም። የወረቀት ነበር ነው። ጭካኔ፤ በቀል፤ ቂም፤ መጠፋፋት፤ ኢጎ፤ ሰላም መንሳት፤ አሉታ፤ ማጥድ፤ ማግለል፤ መቧደን፤ ማህበራዊ ኑሮን ማቃጠል ወዘተ ….።

  • ቅንነት በቅኔነት።

ሌላው ሊቀ ሊቃውነቱ የአቶ ለማ መግርሳ ምጡቅ የግንዛቤ አድማስ ልቅና ብስለት ደግሞ የድርጅቱን ቅኔ እንድናጠናው፤ አንድንማረው ግድ ይላል። አይተነውም፤ ጠብቀነውም የማናውቅ አዲስ ዓለም ነው ትዕግስቱን ከሰጠን። ሥራ አስፈጻሚው ብቻ አይደለም፤ የማዕከላዊ ምክር ቤቱ አባላትም የምርጥ አቅም ወጥ ህሊና ነው እኔ እያዬሁት ያለሁት። ግን „7 ዓመት ታውራ የኖረች ዓይን አንድ ቀን እደሪ ብትባል እንደምን ብዬ አለች“ ይባላል። የአቅል አቅም አነሰን። አዜኔታ አጣን። የታሰረ ለማስፍታት ስንት ጭንቅ እያለ አዲስ ታሳሪ እንማርታለን። አዲስ ለቅሶ እንደራጃለን። አንተላለፋለን። ወጀብ ሲኖር ተግ ብሎ ማሳለፍ ማንን ይገዳል። ጫና አበዛንባቸው። ሁልጊዜ ጥሬ። ግን እኛ ምን ጉዶች ነን?

  • አረስርስ።

ትውልድ የማይተካቸው አርቲሰት ዶር አሊ ቢራ ደግሞ „ለተጨቆነው ህዝባችን መዳሃኒት መሆን አለብን“ ይላሉ። እሰቡት ጥልቀቱን „ለተጨቆነው ህዝባችን“ ነው። ነጻነት አልነበረንም ነው። ጥልቅ ነው ይሄ በጣም። የውሸቱ የሶሻሊዝም ቅርናታዊ ኑሮ አክትሞ እውነተኛ ነፃነት የአብይለማ መንፈስ ያመጣል ነው የሚሉት። መታመን! እና ስለእኛዊነት መልካም ማለም …  እና የኔዎቹ አቦይ በረከትን ቃርሚያ ይሄ ያላሳበደ ማን ይበድ? የደከመች፤ የሰነፈች፤ ኢትዮጵያን ለማዬት ጎንደርን አከርካሪውን መስበር ህልሙ ሆኖ ላደገ የጥላቻ ጥቅርሻ መንፈስ ተዚህ የሚለጥቀው እብደት ወይንም ስደት ….

  • ጀባ።

በተረፈ ለጥቃችሁ ይህችን ታደምጡ ዘንድ በቅኒት መንፈስ ሰጥቼ ሽው ልብል። ግን ግን ዛሬ ደግሞ አዲስ ሙዚቃም ወጥቶላቸዋል። ግን አስፈራኝ ምን ይሆኑ ብዬ? ምንስ ይነጥቀን ብዬ። በዚህ ነፍስ ውስጥ ቅኖችን ሁሉ አሰብኳቸው። ፈሪ ነኝ እኔ … ኤርትራን ያህል ደመኛ ተሸክመን ፈሪ መሆን ግድ ይላል። ሌላ ሐገር አያሰጋም። ደጋግሜ አንደምጽፈው ኤርትራ እና በረከት ግን አይተኙላቸውም። በፍጹም። መግቢያቸው አይታወቅም። በዬዘመኑ ሚስጢራትን ገብረናል። ሌላ ምን ነበር? አዲስ ነገር ያገኘሁት መረጃ … ትግረኛ ቋንቋ ደግሞ ይችላሉ። ይህም ማለፊያ የምስራች ነው። ቋንቋ ሙያ ነው። ተጨማሪ ዕውቀት። የልብ ለልብ ሃዲድ መዘርጊያ። ቋንቋ ፍቅርና መታመንም!

  • ክወና።

በዝግታ መራመድ ያስፈልጋል። የቅንጅትን የመንፈስ ዲታነትን ቀብረን፤ ኪሳራውን አስከጓዙ መከረኛው የኢትዮጵያ ህዝብ ተሸከመ። ይሄኛው ከቅንጅትም በላይ የ አቅም ጥሪት ብቻ ሳይሆን የመምራት አቅም በጥበብ የተቀለመ ነው። ድርጁ ነው።  የብልህነት ጥልፍ። አሁን ደግሞ የተደላደለውን ዲታነት አንዳናሾልክ እንጠንቀቅ። ረጋ እንበል። አደብ እንግዛ። ልብ ይስጠን መድሃኒትዓለም አባቴ።

  • የልባዊነት ምርኩዝ።

Ethiopia Dr abiy ahmed በመጀመሪያ ካፖርትህን አዉልቅ

https://www.youtube.com/watch?v=qD9EeCFEraA&t=87s

stic news

Ethiopia Dr abiy ahmed በመጀመሪያ ካፖርትህን አዉልቅ

Ethiopia – New Dr Abiy – አንድ ሰዉ ብቻዉን መለወጥ ይችላል!

Dr. Abiy Ahmed – አዲሱ ትውልድ ምን አድርጓል?

https://www.youtube.com/watch?v=i7i9hDTCFdo

Abiy Zema – New music Video 2018 – Dedicated to Dr. Abiy Ahmed Ali

  • የእንባ መንኩሲያዋ ጎንደር።

http://www.satenaw.com/amharic/%E1%8C%80%E1%8C%8D%E1%8A%95%E1%8A%90%E1%89%Bጀግንነት አይሰማኝም፤ ጀግና የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው፡፡” (ወይዘሮ እማዋይሽ

ዓለሙ)https://www.youtube.com/watch?v=AmKRrs_rO_o

Must Listen Nigist Yerga With Ayalew Menber 2018

https://www.youtube.com/watch?v=vPwm9rE6cSk

VOA Exclusive Interview with Bekele Gerba & Dejene Tafa | Special Report | Ethiopia | Oromo | Amhara

“ታሪክ ራሱን ቧልት በሆነ መንገድ ሲደግም!”

ኤርሚያስ ለገሰ

Ermias Legesse, author and ESAT TV and Radio contributor

አንድ safegurding Tegaru lives በሚል ስያሜ የሚጠራ  ካድሬ ” ደኢህዴን ከኃይለማርያም ወደ ሽፈራው ሽጉጤ ያደረገው ለውጥ የጥልቅ ተሃድሶ እድገት ነው፣ ወይንስ ከድጡ ወደ ማጡ ነው?” በሚል ያነሳሁት ጥያቄ ላይ አስተያየት ሊሰጥ ወደ ገፄ መጥቶ ነበር።  ከላይ ከተጠቀሰው ኮካ በተጨማሪ በለውጥ ሀይል ዙሪያ ያሉ ወገኖች ” ሲራጅ ፈርጌሳ የደኢህዴን ሊቀመንበር ሆነ ብለህ ነበር!” የሚል ጥያቄ ስላነሳችሁልኝ ሁኔታውን ትንሽ ልበልበት። በትግራይ ነፃ አውጪ ደጃፍ ታሪክ እራሱን ስለሚደጋግሞ መለስ እያሉ ማስታወሱ ሳይበጅ አይቀርም። ከላይ የተጠቀሰው አይነት ሾርት ሜሞሪ ያላቸውን ኮተታም ካድሬዎች አፍ ማዘጋት የሚቻለው በዚህ መልኩ ነው። በሚያገኙት መረጃ ወደ ሰው ይመለሳሉ ብሎ ተስፋ ማድረግ ታማኝ እንዳለው ” እባብ ለመደ ተብሎ በኪስ አይያዝም!” ቢሆንም እባብነታቸውን እንዳይረሱ ያደርጋቸዋል። እናም እንደሰሞኑ በጅምላ ግድያ በርሜላቸውን እስኪሞሉ አድብተው እንዲቀመጡ ያደርጋቸዋል።

ወደ ገደለው ስመለስ ጠዋት ከእንቅልፌ ነቅቼ መረጃዎች ሳነፈንፍ የኃይለማርያም ድርጅት (ደኢህዴን) ፌስቡክ ድረገፅ ፊትለፊቴ መጣ። የድረ ገፁን ትክክለኛነቱን ለማረጋገጥ ከታች እስከ ላይ ወረድኩበት። ያለምንም ጥርጥር የድርጅቱ መሆኑን አረጋገጥኩ። በፓርቲው ማህበራዊ ድረገፅ ዘገባ መሰረት ሲራጅ ፈጌሳ ሊቀመንበር ሆኖ መመረጡን ያበስራል። አስቀድሞ የተወራ ስለነበር ብዙም አልገረመኝም። ከአራት ቀን በፊት በደቡብ ክልላዊ መንግስት ሬዲዬ የሚሰራ ጋዜጠኛ ” ወዲ ሽጉጤን ተገላገልነው!” በሚል በፌስቡኩ የፃፈውን ተመልክቼ ነበር። ዋሽንግተን ዲሲ ከሚኖሩ የኃይለማርያም እጅግ የቅርብ ዘመዶች በተዘዋዋሪ በደረሰኝ መረጃ መሰረት ሽፈራው ሽጉጤ የሙስና ችግር በሰፊው እንደተነሳበት ጠቁመዋል። ወደ ኃላ ተኪዶ በቡና እርሻ መሬት አሰጣጥ ላይ ከፓስተር ባደግ በቀለ ጋር በሼር የጀመረው ኢንቨስትመንት በአውጫጪኝ እንደቀረበበት መረጃው ደርሶናል። እቤት ውስጥ ተቀምጠው የነበሩ የ70 አመት ሽማግሌ አባቱ ፓስተር ባደግ በወር 50ሺህ ብር እየከፈለ ለቡና እርሻው ስራ አስኪያጅ ማድረጉም በሂስ መቅረቡን ሰምተናል።

ለማስታወስ ያህል ፓስተር ባደግ ለሁሉም ባለስልጣናት እና ጄኔራሎች የማስተርስ ዲግሪ በ30ሺህ ዶላር የሸጠላቸው ሰው ነው። ለምሳሌ አቶ በረከት ስምኦን ከ11ኛ ክፍል በቀጥታ ማስተርሱን እንዲወስድ አድርጐታል። በፓርላማ መለስ ሲያሾመው እየሳቀ ” አቶ በረከት ስምኦን የትምህርት ዝግጅት ማስትሬት ዲግሪ በተቋማዊ አመራር” በማለት አስጨብጭቦለታል። ራሱም አንጨብጭቧል። አንዳንድ የዋሆች ( የዋህነቱ በመርፌ ቀዳዳ የመሹለክ ያህል ከሆነ እኔንም ይጨምራል) እንደዚህ አይነቱን ” ተወዳጅ ፓርላማ!” የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ይሽረዋል ብለን ተስፋ እናደርጋለን።

ወደ ተነሳሁበት ልመለስ እና የኃይለማሪያም ፓርቲ ድረገፅ ላይ የወጣው የሲራጅ ፈጌሳ ሊቀመንበር መመረጥ በአንድ ጊዜ ተሰራጨ። የለማ መገርሳ ድርጅት የሆነው ኦህዴድ በድረገፁ ተቀብሎ አስተጋባው። ከዚህ በላይ መተማመኛ ለማግኘት መሄድ አስፈላጊ አልነበረም። ከበቂ በላይ ነው። በሌላ በኩል እስከ ቀትር ድረስ ደኢህዴን ማስተባበያ ባለመስጠቱ የኢሳት ኢዲቶሪያልም የፓርቲውን ድረገፅ ዋቢ በማድረግ ዜናውን አሰራጨ። ደኢህዴንን የበላው ጅብ አልጮህ አለ። ሁኔታዎች ወደ አልተፈለገ መሄዳቸውን የተገነዘበው የስለላው ቢሮ ( የሽማግሌው ስብሃት ነጋ ቡድን በተለይም ቀጣዩ ስውር ጠቅላይ ሚኒስትር የምትሆነው ፈትለወርቅ ሞንጆሪኖ) ማስተባበያውን በተከፋይ የህውሓት ፌስቡክ የኮካ አለቆች አማካኝነት ማሰራጨት ቻሉ ። የፌስቡክ የኮካ አለቆቹ ከማስተባበያው ባልተናነሰ የለማ ቡድንን መረጃ ተቀብሎ በፍጥነት ማሰራጨቱን ደቂቃና ሰከንድ እየመተሩ ለመሳለቅ ሙከራ አደረጉ። እነዚህ አለቆች አዙረው መመልከት ቢችሉ ኖሮ መጠየቅ የሚኖርባቸው ” የደኢህዴንን የውስጥ ግምገማ እንዴት እኛ የትግራይ ነፃ አውጪ ሰራዊቶች ቀድመን እናወጣለን? ነውር አይደለም ወይ? ደኢህዴን ተላላኪ ነው የሚለውን ምስክርነት እየሰጠን አይደለም ወይ?” ይሉ ነበር።

እናም በሰፊው የተሰራጨውን የሲራጅ ፈጌሳ ወደ ደኢህዴግ ሊቀመንበርነት መምጣት ተመርኩዤ የህውሓት ጨዋታ ( Game theory) ምን ሊሆን እንደሚችል የቢሆን መላምቶች መስራት ጀመርኩ። የጨዋታውን መመዘኛዎች ከሶስቱ እጩዎች( ዶክተር አቢይ፣ ደመቀ መኮንን እና ሲራጅ ፈጌሳ) ጋር በማጐዳኘት ነጥብ መስጠት ጀመርኩ። ሲናሪዬዎቹ በማቲማቲክስ እና ማይክሮ ኢኮኖሚክስ ኮርስ ስወስድ ከተማርኩት እና መልሼ መላልሼ ካነበብኩት የእስረኞች ወለፈንዲ ( prisoner dilemma) ከሚባለው ጨዋታ ጋር ተመሳሰለብኝ። (የዘርፋ ሙያተኞች በሁለት ኮርስ ያገኘሁትን ሚጢጢ እውቀት ወደ ተግባር ለመቀየር ላሳየሁት ተገቢ ድፍረት ይቅርታዬ ከወዲሁ ይድረሳችሁ።) ለማንኛውም በጨዋታው ህግ መሰረት ህውሓት ብአዴንና ደኢህዴንን ባህርዳር እና ሐዋሳ ጨለማ ቤት እንዳይገናኙ አድርጐ አስሮ የለማ ቡድንን ሊጫወትበት ሲሞክር በልበ ህሊናዬ ወከክ ብሎ ታየኝ። ጨዋታውን በእያንዳንዱ መመዘኛ (የስልጣን መወጣጫ መስፈርት) አብጠርጥሬ ተመለከትኩ።

ህውሓት ሌሎችን ከስልጣን ለማግለል የሚጠቀምባቸው ስትራቴጂና ታክቲኮች አሁንም አልተቀየሩም። በመሰረቱ በሁለት ከፍለን ልናያቸው እንችላለን። ከእነዚህ ስትራቴጂዎች አንዱ ኢህአዴግን መሰረቱ የተባሉት አራቱ ድርጅቶች በስራ አስፈፃሚም (እያንዳንዱ ዘጠኝ) ሆነ በኢህአዴግ ምክርቤት (እያንዳንዱ 45) እኩል ውክልናና ድምፅ እንዲኖራቸው መደረጉ ነው። ይሄ መሆኑ ህውሓትን ቢጠቅመውም በሶስቱ ድርጅት ካድሬዎች እና አባላት ዘንድ የቆየ ቅሬታ እና ቁጭት የፈጠረ ነው። በዘውጌ ድርጅቶቹ ጉባኤ ላይ ዘወትር የሚነሳና ቢያንስ በፓርላማ ወንበር ቀመር መሰረት የፓርቲዎቹ ቀመር ይስተካከል በሚል የሚገለፅ ነው። ዛሬ ሁኔታዎች ወደ ህዝብ ወርደው  ቢያንስ በኦሮሞና አማራ ህዝብ) የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ እና ምክርቤት ቁጥር በሕዝብ ብዛት ይሰራ መባል ተጀምሯል። የለማ ቡድን ደግሞ በህልምም በውንም ሊታሰብ የማይችል ከሶስቱ ድርጅቶች ሊለያየው የሚችል አዲስ የአይዲኦሎጂ ለውጥ ማድረጉ ” ኢህአዴግ ውስጥ ምን ያደርጋል?” የሚል ጥያቄ በሕዝቡ ዘንድ እየተጠየቀ ነው። እርግጥም ” ጨቋኝ ተጨቋኝ” ተረት ተረት እና ” አብዬታዊ ዲሞክራሲ” የሚባል እንቶፈንቶ እንጮቆረር የወረወረው የለማ ቡድን የኢህአዴግ የውሸት ዣንጥላ ውስጥ መቆየቱ ከፍተኛ ኪሳራ ላይ ሊጥለው ይችላል። ህጉ በሚፈቅድለት መሰረት በፍጥነት ፍቺውን ካልፈፀመ የሞት መንገዱን ያፋጥናል። ህውሓት ጊዜ ባገኘ ቁጥር መርዙን አጠራቅሞ በመርጨት ወደ ፍፃሜ ይወስደዋል።

ሕውሓት ባህርዳር እና ሐዋሳ ጨለማ ቤት አስሮ የለማ ቡድንን ከጨዋታ ውጭ የሚያወጣው ” የፓርቲው የስልጣን አተያይ እና መያዣ መንገዶች” የሚለውን ድርጅታዊ መመሪያ ፊት ለፊት በመደንቀር ይሆናል። የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ( ከእያንዳንዳቸው 9 አባላት) ወደ ምክርቤት ከመሄዱ በፊት የድርጅት ሊቀመንበርና ጠቅላይ/ ተጠቅላይ ሚኒስትር በሚኮንበት መስፈርቶች ላይ በመወያየት አስቀድሞ አቋም ይወስዳል።

እነዚህ መስፈርቶች አብዬታዊነት፣ ብቃት፣ ስነ ምግባር ዋናዎቹ ናቸው። ከ40 በመቶ በላይ የሚይዘው አብዬታዊነት ( አብዬታዊ ዲሞክራሲን ማመን እና መጠመቅ፣ የጨቋኝ ተጨቋኝ ትርክትንና አንቀፅ 39 በፅናት ማመን፣ ማእከላዊነትን ሳያንገራግሩ መቀበል፣ ድርጅቱ የመደበውን ቦታ መቀበል፣ ከግለሰብ ክብር ይልቅ ለድርጅቱ ክብር መጨነቅ) በመስፈርትነት ያስቀምጣል። የኢህአዴግ ባለስልጣናት ” ድርጅቴ ሊስትሮ ሁን ካለኝ እሆናለሁ” ሲሉ የሚደመጡት በዚህ ምክንያት ነው። በነገራችን ላይ በዚህ መመዘኛ 40/40 የሚያገኙት ከጫካ ድረስ የመጡት የህውሓት ካድሬዎች ብቻ ናቸው።

የብቃት መለኪያ ተደርጐ የሚወሰደውም የአብዬታዊ ዲሞክራሲ አስተሳሰቦችን በሙሉ ተረድቶ በፓሊሲው መሰረት የማስፈፀም አቅም ነው። ” ገበሬም ቢሆን የድርጅቱን ፓሊሲ ማስፈፀም እስከቻለ ድረስ ከበቂ በላይ ነው” ተብሎ በተደጋጋሚ ሲነገር የምንሰማው በዚህ ምክንያት ነው። ትልቅ አገር፣ የታሪክ አቅጣጫ፣ብሔራዊ አላማና ሕልም የሚባል ነገር የለም። ከዚህ ይልቅ ሁሉንም ነገር አጥቦና በጐሳ መነፅር ማየት መቻል የተሻለ ተመራጭነትና ትልቅ ነጥብ የሚያስቆጥር ነው።

የትምህርት ዝግጅትን በተመለከተ በኢህአዴግ ” የአመራር ምደባ ፓሊሲ” ውስጥ የተቀመጠው እጅግ በጣም የሚያስደነግጥ ነው። ብዙ ሰዎች ህውሓት/ ኢህዴግ የመሐይማን ጥርቅም መሆኑ በጣም እየገረማቸው ሲናገሩ ይሰማል። ይሄ ግን ሆን ተብሎ በታቀደ መልኩ የሚፈፀም ነው። በህውሓት ውስጥ ትምህርት እና ከፍተኛ ስልጣን ተቃራኒ ተዛምዶ (Inversely related) ናቸው። ጥቂት አብዬታዉያን ብቻ ናቸው የአካዳሚያዊ ትምህርት የመጨረሻው እርከን ( ዶክተር ልበለው) እንዲደርሱ የሚፈቀድላቸው።

ይሄን በማስመልከት ” የመለስ ትሩፋት: ባለቤት አልባ ከተማ” በሚለው መፅሐፍ ላይ በገፅ 309 ላይ፣

የኢህአዴግ የውስጠ ድርጅት መመሪያ ከፍተኛ ምሁራንን በሁለት ጐኑ የተሳሉ ቢላዋ በማለት በንዑስ ከበርቴነት ጐራ ይመድባቸዋል። በጀማሪ ካፒታሊዝም ውስጥ የምሁራን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መሰረት ለጥገኛ ዝቅጠት የተመቸ እንደሆነና ከፍተኛ መደላድል እንደሚፈጥር ያሳስባል። በመሆኑም የምሁራን አሰላለፍ በንዑስ ከበርቴ ደረጃ በመሆኑ በህዝቡ ውስጥ የሚካሄድ ትግል ሲፋፋም በመጀመሪያው የንቅናቄው መስመር በመሰለፍ ግንባራቸውን ለጥይት እንደሚሰጡ፣ ትግሉ ሲቀዛቀዝ ደግሞ ከሌላው የበለጠ ተስፋ የሚቆርጡና የሚያስቆርጡ፣ ይባስ ብሎም ለግል ጥቅማቸው የሚሯሯጡ ሆዳሞች ይሆናሉ ይላሉ። በመሆኑም ድርጅቱን የሚቀላቀሉ ምሁራን አብዬቱን የመምራት ሃላፊነት ስለሚሸከሙ በመርፌ ቀዳዳ ማለፍ የሚችሉ ሆነው ከአጠቃላይ ተመልማዬች ከ1 በመቶ መብለጥ የለባቸውም በማለት ይገልፃል” ይላል።

እንግዲህ ህውሓት ስልጣንን እንደ ርስት ለመያዝ የሚጠቀምባቸውን መስፈርቶች በመመልከት የለማ ቡድን ወደ ድርድር መምጣት ካልቻለ ቢያንስ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን መቀበል) ሲራጅ ፈጌሳ ሊቀመንበር እና ተጠቅላይ ሚኒስትር ሊሆን እንደሚችል የትንበያ ለውጥ አደረኩ። ከእኩለ ቀን በኃላ የደኢህዴን እና የለማ ቡድን ደረገፆች ባይቀየሩም የህውሓት ኮተታም ካድሬ አለቆች ከሚከፍላቸው ስለላው መስሪያቤት ( የስብሃት ነጋ ገዥ መደብ በበላይነት ሞንጆሪኖ) ከሲራጅ ፈጌሳ ወደ ” ወዲ ሽጉጤ!” መቀየሩን ይፋ አደረጉ። መጀመሪያ ስሰማ በጣም ተገርሜ ነበር። የጥልቅ ተሐድሶው ለውጥ ከድጡ ወደ ማጡ መሆኑን በቀጥታ ማረጋገጣቸው እጅጉን አስደነቀኝ። በውስጤ ኃይሌንና ሽጉጤን ሚዛን ላይ እያስቀመጥኩ ኃይለማርያም በምን ጣዕሙ አልኩኝ። የጀርመኗ የአገልግል ዶሮ ወጥ በአይኔ ላይ ሄደች። ለመወሰን መረጃ የለኝም የሚለው ንግግሩ ትውስ አለኝ። ዲሊቨሮሎጂ በእጄ ላይ ተንከባለለ። ጄኔራል ሳሞራ በህዝቡ በጥፊ ስለተመታው ወታደር የተረከለትን አስታወስኩ። የግመል ቁመት የማያውቀው የቻይና መሐንዲስ ቤጂንግ ድረስ በትውስታ ወሰደኝ። ለኃይሌ እናንተ ኢትዬጲያውያን መኪና ትበላላችሁ እንዴ? በማለት የጠየቀው ፈረንጅ የየት አገር ዜጋ ሊሆን እንደሚችል ግምቴን አስቀመጥኩ። የመብራት ፓል እየገጨ አዲሳአባን በጨለማ የሚያውላት ሰካራም ስሙ ማን ሊሆን እንደሚችል ጠረጠርኩ። ኸረ ወዲያ! ኸረ ወዲያ! አሁን እውነት ከህውሓቶች ውጭ ከኃይለማርያም የሚብስ ሰው ይመጣል ብሎ የሚጠብቅ አለ?

የሆነው ሆኖ ከሲራጅ ፈጌሳ ወደ ” ወዲ ሽጉጤ!” ከመቅፅበት የተቀየረው ድራማ አንዲት ነገር አስታወሰኝ። ታሪክ ራሱን በቧልት መልኩ ይደግማል ያልኩት በዚህ ምክንያት ነው። ታሪኩ ፎርቹን በሚባለው ጋዜጣ ላይ ወጥቶ ስለነበር እንዲሁም ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና በተደጋጋሚ የሚያነሳው በመሆኑ በብዙዎች ጭንቅላት ውስጥ እንደሚኖር እገምታለሁ። የመጀመሪያው ታሪክ ባለቤት ሟቹ መለስ ዜናዊ ሲሆን ተጨዋቾቹ አባዱላ ገመዳና ሟቹ አለማየሁ አቶምሳ ናቸው። የዛሬዎቹ ቧልተኛች ጄኔራል ሳሞራ ( ሲራጅ) እና ጌታቸው አሰፋ ( ሽፈራው ሽጉጤ) ናቸው። ታሪኮቹ ተመሳሳይ ስለሆኑ የሟቹ መለስ ዜናዊን ላጫውታችሁ እና መጣጥፌን ልቋጭ።

እንዲህ ነበር የሆነው፣

የኦህዴድ ማእከላዊ ኮሚቴ በአዳማ ይሰበሰባል። አጀንዳው የድርጅት ሊቀመንበር ምርጫ በመሆኑ አባዱላ ኔትወርኩን ተጠቅሞ በሙሉ ድምፅ ራሱን ሊቀመንበር ያስመርጣል። አባዱላ ራሱን ማስመረጡ ያበሳጨው መለስ ዜናዊ አባዱላ ስብሰባውን አቋርጦ ወደ አዲሳባ እንዲመጣ ያደርገዋል።በማስፈራራት አለማየሁ አቶምሳን በአስቸኳይ እንዲተካ ይነግረዋል። ውሃ የገባ ፀጉራም ውሻ የሆነው አባዱላ በውስጡ ቂም ቋጥሮወደ አዳማ በመመለስ ” ራሴን አግልያለሁ አለማየሁ አቶምሳ ሊቀመንበር እንዲሆን አቅርቤያለሁ!” ይላል።ለጥቂት ሰአታት የማእከላዊ ኮሚቴው የብርጭቆ ማዕበል አስነስተው ድምፅ እንስጥ ይባባላሉ። ከአንድ ሰው በስተቀር አባዱላ ተሽሮ አለማየሁ አቶምሳ ይተካ በሚለው ላይ ይስማማሉ። በነገራችን ላይ አባዱላ በውጭ ተፅእኖ መቀየር የለበትም ብሎ ድምፅ የሰጠው የዛሬው የኦሮሚያ ሊቀመንበር ለማ መገርሳ ነበር። የዛሬው የቲም ለማ ቡድን መሪ።እነሆ! አለማየሁ አቶምሳ ብዙም ሳይቆይ የተመረዘ ውሃ እንዲጠጣ በማድረግ የቂም ቋጠሮው ፍቺ አገኘ። ፀረ ሌባው አለማየሁ አቶምሳ ለዘላለም አሸለበ።ለማ መገርሳ የአለማየሁ እጣ እንዳይደርሰው የእግዜር መላእክት ክንፋቸውን ይዘርጉለት።