ሰዓቱ አሁን ነው! በዓለም አቀፍ ቌንቌ ተምረን ብሄር ተጠየቅን! እናት ሃገራችሁ ትፈልጋችኃለች! – ፀ/ት ፂዮን ዘማርያም(ኢት-ኢኮኖሚ)

ቴዎድሮስ አበባው ያዲስአበባው…ነፍስ ይማር!!! ታላቁ እስክንድር ተደራጁ ….ተደራጁ….ተደራጁ!!! ብሎል፡፡

የኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ አስር ሚሊዮን የፖለቲካ ምላሳዊ ካድሬ ለሃያ ለሠላሳ አመታት በጥገኝነት ደሞዝ እየተሰፈረላቸው፣ መኪና ተሰጥቶቸው፣ ቤት ተሰጥቶቸው፣ መሬት  ከአንድም ሁለት ሶስቴ ተበርክቶላቸው፣እንደ መዥገር ተጣብቀው እናት አገራችንን ህዝቡን ሲበዘብዙ ኖረዋል፡፡ የህክምና ዶክተሮችና የጤና ባለሙያዎች ሥራ አጥተው ሲሰቃዩ ማት ይህ ሥርዓት ከነሰንኮፉ እስካልተወገደ ድረስ የብልፅግናው መንገድ የጨለመ ለመሆኑ አብይን ማማከርና መጽሃፉን መግለጽ አሊባባና አርባዎቹ ሌባዎችን ታሪክ ያስታውስሃል፡፡ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘመን ወጣቶች የህወሓትና የብልጽግናን የሥርዓት እድፍ አጥባችሁ አዲስ ሥርዓት ለመገንባት ከመታገል ሌላ አማራጭ የላችሁም፡፡ ሰዓቱ አሁን ነው! እናት ሃገራችሁ ትፈልጋችኃለች!

አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ/መጋቢት 6 ቀን 2013 ዓ.ም/አዲስ አበባ ሸዋ…ካለፈው አንድ ዓመት ጀምሮ የስራ ምደባ ወይም ቅጥር ባለመሰራቱ እየተጉላሉ ያሉ የህክምና ዶክተሮች በባህርዳር ሊያደርጉት የነበረው ሰላማዊ ሰልፍ ከላይ ታዘናል ባሉ የልዩ ሀይልአባላት እና አድማ በታኞች አማካኝነት ክልከል ገጥሞታል። የመጋቢት 7 ዜናዎች- ወሎ ቤተአምሀራ /በሀኪም እጥረት እናቶች የሚሞቱበትና ስራ አጥ ሀኪሞች የበዙበት ../ በሰኔ 15 ሰበብ የታሰሩ የጦር መኮንኖች ጉዳይ..https://youtu.be/k9gpEz_0PiM  (1)

በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የታክሲ አገልግሎት የሚሰጡ የታክሲ ባለንብረቶችና ሹፌሮች በተደጋጋሚ በሚደርስባቸው ዘረኛና ተረኛ አድሎዊ አሠራርን በመቃወም በቤንዚን ዋጋ መጨመር የተነሳ የታክሲ መሳፈሪ ዋጋ ተመን ጋር የተጣጣመ ባለመሆኑ የተነሳ ሰኛ እለት የሥራ ማቆም አድማ አድርገዋል፡፡ መንግሥት የጣለባቸው የተከማቸ የትራፊክ ቅጣት እንዲነሳላቸውም ጠይቀዋል፡፡  የአዲስ አበባ ህዝብ በዋጋው ጭማሪ የተነሳ በኑሮ ውድነት እየተሰቃየ ይገኛል፣ የታክሲ አገልግሎት ማግኘት ባለመቻሉ በታክሲ ሠልፍ ጥበቃ  ሥራ ተስተጎጉሎል፡፡ መንግሥት ሃምሳ ስድስት የታክሲ ሹፌሮችን አድማውን አስተባብራችኃል በማለት አስሮል፡፡ አድማው ማክስኛም ቀትሎል፡፡

Much of Addis Ababa has been paralysed as taxi drivers on Monday embarked on a strike to protest a revised tariff for city trips, APA can report on Tuesday. (2)

Hundreds of taxi drivers brought the Ethiopian capital to a standstill, saying the revised fare was not proportional to increased fuel prices. The government increased the price of fuel twice in a month after its fuel import from neighboring Sudan was halted due to a border conflict. “We already have much lower fares against increasing prices of fuel,” said the taxi owners and drivers. They also want the government to cancel fines which have been accumulated over the years. Although the authorities increased the peak hour frequency of public transport on Monday, a lot of passengers were affected by the strike. There have been long queues of passengers in Megenagna, Ayat Kolfe and Awtobestera areas.  The strike especially affected those people who live in the outskirts of Addis Ababa where train service is not available.

Addis Ababa City Transport Head Engineer Sitotaw Tekele said the fares were revised based on the paying ability of passengers and increased fuel price. “The government will take stringent measures if the protest continues,” he added.  Police said they have arrested 56 taxi drivers over the protest which they claimed was infiltrated by individuals with political motives. The strike has continued in some parts of the city on Tuesday.

‹‹የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ግንቦት 28 ቀን 2013 ዓ/ም አገራዊ አጠቃላይ ምርጫ ከስድስተኛው አገራዊ ምርጫ፣በ49407 የምርጫ ጣቢያዎች ለሚሠማሩ የምርጫ አስፈፃሚዎች ሁለት ቢሊዮን ብር እንደሚያወጣ ታወቀ፡፡ ለመቶ ኃምሳ ሽህ የምርጫ አስፈፃሚዎች 1.8 ቢሊዮን ብር ይከፈላል፡፡ 182 የዞን አስተባባሪዎችና 2019 የምርጫ ክልል አስተባባሪዎች 105648000 ብር ይከፍላል፡፡  የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም (ዩኤንዲፒ) በዓይነቱ የ 40004000 ዶላር ድጋፍ የሚደረግለት ሲሆን፣ የዚህም ዓላማ ቦርዱን ብቁ፣ ግልጽና የሚታመን ተቆም ለማድረግና አካታች፣ ግልጽና ተዓማኒነት ያለው ምርጫ ማድረግ እንዲችል ለማገዝ ነው፡፡››  (3)

የኦሮሞ ነጻ አውጭ ግንባር (ኦነግ) ዳውድ ኢብሳ ነጻና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ለማካሄድ አስፈላጊ መስፈርቶች ለማሟላት ብልጽግና ፓርቲ ፍላጎት ስለሌለው ከምርጫው ለመውጣት ተገዶል፡፡ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) መሪ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና  በኦሮሚያ የተለያዩ ስፍራዎች የተዘጉ ቢሮዎቻቸው እንዲከፈቱ፣ እንዲሁም ታማኝነት ያለው ምርጫ ለማድረግ የሚያስችል አገራዊ ምክክር እንዲደረግ ጥሪ ሲያቀርብ ነበር። አገራዊ ምርጫ ተገፍቶ ለመውጣት ተገድዷል። የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማፓርቲ በኦሮሚያ ክልል ቢያንስ በ46 (አርባ ስድስት) የምርጫ ወረዳዎች ዕጩዎቹን ማስመዝገብ እንዳልቻለ አስታውቆል፡፡ አሁን እንደምናየው ብልፅግና ኦሮሚያ ላይ ብቻውን ለመወዳደር እየሄደበት ያለው መንገድ አገርንም ጭምር ከፍተኛ ዋጋ ያስከፍላል፡፡›› በኦሮሚያ ክልል፣ የኢዜማ የአድአ ምርጫ ወረዳ 1 ሊቀመንበር የነበሩት አቶ ግርማ በግፍ በጥይት ተገድለዋል፡፡  (3)

ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ፡-ቴዎድሮስ አበባውን በአሰቃቂ ሁኔታ ገድለውታል፡፡ ታላቁ እስክንድር ተደራጁ ….ተደራጁ….ተደራጁ!!! ብሎል፡፡ የአዲስ አበባ ህዝብ ህብረ ብሄር ህዝብ እንኳን ኦነግን የደርግ ኢሠፓንና ህወሓት ኢህአዴግን አሸንፎል፡፡ አዲስ አበባ የሁሉም ብሔር ብሄረስብ፣ የኦሮሞው፣ አማራው፣ ጉራጌው፣ ወላይታው፣ ሱማሌው፣ ጋምቤላው፣ ወዘተ የሁሉም አፍሪካ፣ ዓለም አቀፍ ሜትሮፖሊያን ከተማ ነች፡፡ አዲስ አበባን ከተማ ሜትሮፖሊያን ከተማ ሆና እንድትቀጥል ትግል ይጠይቃል፡፡

የኦሮሞ ነጻ አውጭ ግንባር (ኦነግ) እና የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) በምርጫው ተገድደው በመባረራቸው እጃቸውን አጣጥፈው ይቀመጣሉ ማለት የዋህነት ነው፡፡ ሁለቱም በኦሮሚያ ህዝብ ከፍተኛ ተከታዬች ያሎቸው መሆኑ ፀሐይ የሞቀው ዓለም ያወቀው ጉዳይ ነው፡፡ ኦነግ በተለይ በወለጋና በባሌ እንዲሁም ኦፌኮ በሸዋ፣ በሐረር፣ በአርሲ ከፍተኛ ህዝባዊ ድጋፍ እንዳላቸው ይታመናል፡፡ በስድስተኛው ዙር ምርጫ የማይሳተፉት ኦነግና ኦፌኮ ባላቸው ህዝባዊ ድጋፍ  ምን ሊሰሩ ይችላሉ ብለን ብንመረምር ውስጥ ውስጡን አንደኛ ምርጫው እንዲደናቀፍ  የቄሮ ወጣቶችን ኦነግና ኦፌኮ በጋራ በስድስተኛው ዙር አገር አቀፍና ክልላዊ ምርጫ የትግል ጥሪ ይዘት፣ የቄሮ ወጣቶችን በማሰማራት ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና መሃበረሰባዊ ዉሳኔዎች በማስተላለፍ  የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከግንቦት 28  አስከ  ሰኔ 5 ቀን 2013 ዓ/ም የአዲስ አበባና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምርጫ ሊያደርጉ የሚችሉት የትግል ስልት ከወዲሁ ሊያሴሩ የሚችሉትን መተንበይ ይቻለናል፡፡ የኦሮሞ ነጻ አውጭ ግንባር (ኦነግ)

  • አውራ መንገዶች ዝግ ማድረግ ኦሮሚያን ከሌሎች ክልሎች ጋር የሚያገናኙ፣ የህዝብ ትራንስፖርት፣ የጭነት መኪኖች ወዘተ ማገድ
  • ከኦሮሚያ የሚቀርቡ ምርቶች ሁሉ የግብርና ሌሎች ለገበያ እንዳይቀርቡ በማድረግ ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ ማድረግ
  • ግብር መሰብሰብ አይቻልም ኦሮሚያ ውስጥ የሚገኙ መንግስታዊ መዋቅሮች ግብርና ታክስ እንዳየከፍሉ በማድረግ የኢኮኖሚ አሻጥር ማድረግ
  • የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር የንግድ ሥራ ማቆረጥ የመሳሰሉትን የትግል ስልቶች ሊያከናውኑ ይችላሉ፡፡

ዶክተር ዐቢይ አህመድ ለኦነግ መረጃ አሳልፎ ይሠጥ ነበር፣ ለኦነጉ ለገሠ ወጊ መረጃ ይሰጡት እንደነበረ መስክሮል፡፡

በመሆኑ ይህ በሃገሪቱ ያለው የህገወጥ የመሣሪያ ንግድ ዝውውር ከምርጫው በፊት፣ የመገደያችን ሹጉጦቹ፣ ጠመንጃዎቹ፣ ቦንቦቹ፣ የመታረጃችን ሜንጫው፣ ገጀራው፣ ካራው፣ ቀስቱ ወዘተ ከወዲሁ ያልተያዘው ህገወጥ የጦር መሣሪያዎች እንዲሰበሰብ ምርጫ አስፈፃሚዎች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርዱን ብትጠይቁ ለእራሳችሁና ለህዝብ ፀጥታና ደህንነት ትተርፋላችሁ!!! ካለዛ ግን እንኳን መከላከያ ሠራዊት ወፍ አይደርስላችሁም!!!

ኦነግና ኦዴፓ ብልጽግና ስድስተኛውን ዙር ምርጫ ማሸነፉን ቀድሞ በማወቁ የአዲስ አበባና ድሬዳዋ ከተማን የህዝብ ምርጫ እንደሚሸነፉ ከወዲሁ በማወቃቸው የተነሳ ልዩ ልዩ ሴራ በመንደፍ ላይ ናቸው ፡፡ የቄሮ የትግል ጥሪ ይዘት፣ የቄሮ ፖለቲካዊ, ኢኮኖሚያዊ, እና መሃበረሰባዊ ዉሳኔዎች እና ይዘታቸዉ እንዲሁም የትግራይ ክልል በህወሓት ላይ የታወጀ ጦርነት አጋር በመሆን ስውር ግንኙነት እንደሚያደርጉ ይታመናል፡፡ ኦነግ የኦሮሞ ህዝብ በስብዓዊ ጋሻነት በመያዝ በወለጋ ሆሮ ጉድሩ ውስጥ ኖሪ የሆኑትን የአማራ ተወላጆች ቀያቸውን በሦስት ቀናት ውስጥ ለቀው እንዲወጡ በየቦታው ወረቀት ተለጥፎል ህዝቡም ቀየውን እየለቀቀ ወደ ከተማ በመግባት ላይ ናቸው፡፡ ኦነግና ኦዴፓ ብልጽግና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርዱ አይቶ እንዳላየ ዝምታ መርጦል፡፡ በደቡብ ክልል በጉጂ ታጣቂ ቡድን አማሮ፣ ዲላ፣ አዲስ አበባ አውራ ጎዳና መንገድ ተዘግቶል፡፡ በሌላ በኩል በጉራጌ ዞንና አካባቢው ያለ ችግር ተጠናክሮ ቀጥሎል፡፡ ኦነግና ኦዴፓ ብልጽግና የኢትዮጵያን ህዝብ በፍርኃት ቀንበር ውስጥ ከተው ለመቶ አመት እንገዛለን ብለው ያስባሉ፡፡ ኦነግና ኦዴፓ ብልጽግና ከህወሓት ኢህአዴግ ውድቀት መማር አልቻሉም፡፡

ኦነግና ኦዴፓ ብልጽግና ፓርቲ ክስ ውስጥ፡-

‹‹የኦሮሞ ብሄርተኝነት እንደ አሸባሪነት ተቆጥሮል፣ የዴሞክራሲ ጭላንጭል ጠፍቶል በኦሮሚያ ውስጥ ሰዎች ይገደላሉ፣ ሴቶች ይደፈራሉ፣ በወለጋ፣ በበቆጂ፣ ኦነግ መንግሥት የለም ከመስከረም 25 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ ኦሮሚያ የደም መሬት ሆኖል፣ የብሄር ብሄረሰቦች መንግሥት የነበረው መንግሥት በዶክተር አብይ መንግስት የነፍጠኛ ሥርዓት  አህዊ ሥርዓት ተተክቶል ይላሉ፡፡ የዶክተር አብይ መንግሥት ኦዴፓ ብልፅግና የአራት ኪሎው መንግሥት ህቡዕ ሥርዓት  1.5 ቢሊዮን ብር የሠጡት ባለፀጎች ናቸው፡፡ ኢሳያስ አፈወርቂና ዐብይ አህመድ በህቡዕ ፀረ- ኢትዮጵያ አጀንዳ ያራምዳሉ፣ ጨፌ ኦሮሚያ  የሚያካሂደው ስብሰባና የሚያወጣው ህግ  ኢህገመንግሥታዊ ስለሆኑ ተቀባይነት የላቸውም፣ በዚህም መሠረት ይሄን የሚተካ የሽግግር መንግሥት እንመሠርታለን፡፡ የኦሮሞ እስረኞች በትግላችን እናስለቅቃለን  የአብይ መንግሥት በአባ ቶርቤ ሥም ይገድላል፣ ፍርድ ቤት የለቀቀውን እስረኛ  ፖሊስ አለቅም የሚልበት የአብይ መንግስት ነው፡፡ የአብይ መንግስት የማይቆጣጠረው የትግራይ መንግስት፣ የኦሮሚያ ክልል መንግሥት መንግሥታዊ መዋቅሮች ሠባብረን የሽግሰግር መንግሥት እነናቆቁማለን፣ የምርጫ ቦርድ ምርጫ በኦሮሚያ ምድር የሽግግር መንግሥት ማቆቆም እቅድ አላቸው፡፡›› ክሱ በውሸትና ቅጥፈት ላይ የተመሠረተ ቢሆንም ኦነግና ኦዴፓ ብልጽግና ስውር ግንኙነት እንዳላቸው ይታወቃል፡፡

የኦሮሞ ነጻ አውጭ ግንባር (ኦነግ) በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ጋር ተቀላቅሎል

  • ኦነግ ሸኔ በኦሮሚያ ክልል በዘር ማፅዳት ሥራ ላይ ከተሠማራ ሦስት አመታት ተቆጥሮል፡፡ ከኤርትራ ወደ ሃገር መሣሪያ ሳይፈታ የገባው የኦሮሞ ነጻ አውጭ ግንባር (ኦነግ) ይዞቸው የገባውን ጦር አንድ ሽህ አምስትመቶ የሚሆነውን ከኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ጋር እንዲቀላቀል በማድረግ ከሦስት ሽህ አምስት መቶ የሚገመተውን ከነትጥቁ በኦነግ ሸኜ ስም አንዴ ለአባገዳዎች ተሠጥተዋል ወዘተ ብለው እየቀለዱ ኦነግ ሸኜ በየትምህርት ቤቶቹ ውስጥ ብዙ ሽህ ወጣቶችን በመመልመል፣ ሃያ ሦስት ባንኮች በመዝረፍ፣ የአማራ ተወላጆችን በማረድ፣ በዘር ማጥፋት ሥራ እንዲሠማራ ስምሪቱን ህወሓት፣ኦነግና ኦዴፓ ብልፅግና ሃላፊነቱን ይወስዳሉ፡፡  አነግ ሸኔ ከስድስተኛው ዙር ምርጫ በፊት ከክልሉ ሌላዎቹን ዘር አማራ፣ ጉራጌ፣ ትግሬ ወዘተ በማስወጣት ምርጫውን ለማሸነፍ  የነደፈው የኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ የፖለቲካ ሴራን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ተባባሪ በመሆን ህዝቡን በመሸጥ ከምርጫው በኃላ እንባሣደር ሆነው ለመሾም ቃል ተገብቶላቸዋል፡፡
  • የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በኦሮሚያ ክልል መንግሥት የኦሮሞ ፖሊስ ኮሚሽነር የህዝብን የጸጥታና ደህንነት ሁኔታ በኦነግ ሸኔ አራጅ ብድን የብዙ ንፁሃን ደም እየፈሰሰ እንዳለ የፖሊስ ኮሚሽነሩን ጄኔራል አራርሳ መርዳሳ ‹‹ከኦነግ ሸኔ ጋር አበሩ ባላቸው ከአንድ ሽህ በላይ ፖሊሶች ላይ እርምጃ መውስዱን ገልፀዋል፡፡ በፀጥታና ፖለቲካ መዋቅር ውስጥ ሰርጎ በመግባትና ሰዋችን አደራጅቶ በመያዝ ከጎነግ ሸኔ ጋር  የሚሰሩ አካላት ጨምሮ ከ1000 በላይ የፖሊስ አባላት ላይ የተለያዩ  እርምጃዎች መወሰዱን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቆል፡፡ በቡድኑ የጥፋት ተልእኮ አልፎ አልፎ የሚሳተፉ፣ የሚጠረጠሩ፣ መረጃ የሚሰጡ፣ ከእነርሱ ጋር የሚያብሩ፣ ከጎሰኝነት፤ ከከባቢነትም ተነሰተው ከፀጥታ መዋቅርና አመራር ጋር በሚመሳጠሩት ላይ በየወቅቱ ግምገማዎች እየተካሄደ እርምጃ ይወሰዳልም ሲሉ ኮሚሽነሩ ተናግረዋል፡፡(EPA)›› የሰሜን ዕዝን መከላከያ ሠራዊት ህወሓት/ ወያኔ ሠርጎ በመግባት ሠራዊቱን በመውጋት  ገደሉ፣ አሰሩ፣ አገቱት መጨረሻቸውም የወያኔ መደምሰስ ሆነ፡፡ የኦሮሚያ ክልል መንግሥት፣ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን በኦነግ ሸኔ ድብቅ ቡድን ውስጡ ተቦርቡሮል፣ ከውስጥ መረጃ የሚሰጡ ፖለሶች ስላሉ ኦነግ ሸኔን ማጥፋት አልቻሉም፡፡  የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ከሰሜን ዕዝ መከላከያ ሠራዊት ጥቃት ምን ይማራል?
  • በአዲስ አበባና ድሬዳዋ የከተማ አስተዳደር ሥነ-ህዝብ (Demography) ፕወዛ:- በአዲስ አበባ ከተማ ዙሪያ የሚገኙ የኦሮሚያ ልዩ ዞኖች ንዋሪዎችን የአዲስአበባ የመታወቂያ ካርድ በመስጠት የከተማዋን ሥነ-ህዝብ በመቀየር ስድስተኛውን ዙር ምርጫ ለማሸነፍ የሚደረገውን ህገወጥ ሥራ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በዝምታ አልፎል፡፡ የመታወቂያ ካርድ በአዳነች አቤቤ ትእዛዝ በየአስሩም ክፍለ ከተሞች በተረኞች ይታደላል፡፡ ነፃና እንከን የለሹ ምርጫ፣ ዴሞክራሲ  አፍንጫውን ተሰንጎ ጭር እንዳለች ዶሮ ዝቅዝቅ ተሰቅሎል፡፡ ኦዴፓ ብልፅጋና ፓርቲ በዴሞክራሲ ስም ስንት ግፍ ሠራ!!!
  • የኦሮሙማን ተራኛነትንና ዘረኛነትን በህብረት ከሁሉም ክልሎች (የሱማሌ፣ አፋር፣ ሀረሪ፣ ደቡብ፣ ሲዳማ፣ ጋምቤላ፣ ቢኒሻንጉል) ጋር ሆኖ መታገል አንገብራቢ ጥያቄ ነው፡፡ የፌዴራል መንግሥታዊ መዋቅሮች ሥልጣን፣ የመከላከያ ሠራዊትና የፖሊስ ኃይል ጀነራል መኮንኖች፣ የውጭ ሃገራት አንባሳደሮች፣ ወዘተ ስልጣን የብሄር ተዋፆኦ በግልፅ በዴሞክራሲያዊ መንገድ መፍታት ተረኛነትንና ዘረኛነትን የመከላከያ አንዱ ዘዴ ነው እንላለን፡፡
  • በአገራችን ኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ምሶሶዎች የህግ አውጪ፣ የህግ ተርጎሚ፣ ህግ አስፈፃሚና ሚዲያ ሥር እየሰደዱ እንደ ቆጥኝ እየፀኑ ይሄዳሉ ሲባል በዘመናይ ልጆቾ እየዘመሙና እየተናዱ መሄዳቸው ምስጢር እንቆቅልሽ ሆኖል፡፡ የኢትዮጵያችን ማህፀን በሾተላይ ተጠቃና ውርጃ እጣ ፈንታዋ ሆኖል!!! በሃገሪቱ ዴሞክራሲያዊ መብቶች፣ የአመለካከት እና ሀሳብን በነፃ የመያዝና የመግለፅ መብት በነጠፈበት፣ የፕሬስ ነፃነት በሌለበት የመሰብሰብ፣ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ነጻነትና አቤቱታ የማቅረብ መብት በተነፈገበት፣ የመደራጀት መብት በታቀበበት፣ የመዘዋወር ነፃነት በሌለበት፣ የዜግነት መብቶች መጠበቅ በተሳነበት ወዘተ በተግባር እስኪተገበሩ  ድረስ ስድስተኛ ዙር ምርጫ ይቆየንና በፊት መገደያችን ህገወጥ የጦር መሣሪያዎች ጠመንጃ፣ ሽጉጥና ቦንብ፣ እና መታረጃችን ገጀራ፣ ሜንጫ፣ ጦሩ ተሰብስቦ ምርጫ ቦርድ ሙዚየም ውስጥ ይቀመጥ እንላለን፡፡
  • የጠቅላይ ሚንስትር ፅህፈት ቤት የወጡ ህጎች ውስጥ ማንኛውም የፌዴራል መንግሥት ሹማምንት ከኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ እውቅና ውጪ በአገር ውስጥና ውጭ ሀገር የመንቀሳቀስ መብታቸው ታግዶል
  • በኢትዮጵያ የሚዲያ ነፃነትና የጋዜጠኞች መታሰርና መገደል አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ሲፒጄ አስታውቆል፡፡ ኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ ስልጣን ከጨበጠ ሦስት አመት ሊሞላው ትንሽ ሲቀረው በሃገሪቱ የታሰሩ ጋዜጠኖች ከስልሳ በላይ ሆኖል፡፡  ምንጭ (http:// cpj.org/ Africa/Ethiopia/2020)
  • የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ መሪ እስክንድር ነጋ፣ ስንታየሁ ቸኮል፣ አስቴር ስዩም፣ ወዘተ   እስካሁን በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡ በዚህ ምርጫ ላለመሳተፍ የምርጫ ካርድ እቀባ ለማድረግ እንገደዳለን በማለት ገለታው ዘለቀ  አሳስበዋል፡፡
  • ኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ የመሰብስብና ሰላማዊ ሠልፍ የማድረግ ነፃነትና አቤቱታ የማቅረብ መብት ከ 2011 ዓ/ም ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ታግዶል፡፡ በቅርቡም ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ የጠራው ሰላማዊ ሠልፍ ታግዶል፡፡ በታሪካችን ለመጀመሪያ ጊዜ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመመሥረት ወሳኝ ምዕራፍ በሆነው ቀጣዩ ምርጫ ይለናል ፕሮፌሰረር ብርሃኑ ነጋ!!!
  • የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 5 ቀን 2013 ዓ/ም የአዲስ አበባና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክርቤቶች ምርጫዎች እንደሚፈፀሙ አስታወቆል፡፡ ግንቦት 28 ቀን የመረጡት ዳግም ሰኔ 5 ቀን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ ምርጫ ላይ እንዲመርጡ የተቀናጀ ሴራ ነው ለሚሉት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ምርጫ ቦርድ በተለያዩ ቀናት ምርጫውን ለምን ማድረግ እንደፈለገ የሚሠጠው ምላሽ ውኃ አያነሳም፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተቌማቱ ዝግጁነትና ገለልተኛነት፣ የታዛቢዎችና የምርጫው ሂደት ታዓማኒነት፣ የብሔረሰቦች የማንነት ጥያቄዎችና ከምርጫ ክልል ጋር የሚያያዙ ጥያቄዎች፣እንዲሁም የፖለቲካ ፓርቲዎች ጥያቄዎችና የሚዲያ ሚዛናዊነትና ተዓማኒነት፣ ምርጫው ውጤት ጋር ተያይዘው ሊነሱ የሚችሉ ጉዳዩች አፈታት በዝርዝር አልቀረበም፡፡
  • የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) ብልጽግና ፓርቲ መሪ ዶክተር ዐቢይ አህመድ በምርጫው ለመሳተፍ በምርጫው ከሚሳተፉት 47 የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል በርካታ ቁጥር ያላቸውን ዕጩዎች በማቅረብ በኩል ገዢው ፓርቲ ብልጽግና 2432 ዕጩዎችን በማስመዝገብ ቀዳሚው መሆኑ በመግለጫው ላይ ተመልክቷል። ከዚህ አንጻር ከብልጽግና በመከተል ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ዕጩዎች በማስመዝገብ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) 1385 ዕጩዎችን እንዲሁም እናት ፓርቲ ደግሞ 573 ዕጩዎችን አስመዝግበዋል። ኦዴፓ ብልጽግና ፓርቲ ካቀረባቸው 2432 ዕጩዎች ብዛት ከወዲሁ አሸናፊ እንደሆነ ትንቢት ተናጋሪ መሆን አይጠይቅም፡፡ ኦዴፓ ብልጽግና ፓርቲ አዲስ አበባ ህዝብ ድምጽ እንደማያሸንፍ ስላወቀ የአዲስ አባባ መታወቂያ ንዋሪ ላልሆኑ ሰዎች በመስጠት አሻጥር በመፈፀም ላይ ይገኛል፡፡
  • በዓለም አቀፍ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት የኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ የዘርና ኃይማኖት ፍጅት መንግሥታዊ ሽብርተኝነት ይዳኛል!!!

ማንኛውም ሰው በህይወት የመኖር መብቱ ይከበር!!!

ያለ ሕግ ልዕልና ዴሞክራሲ አይሰርፅም!!!

ያለ ሠላም፣ ፀጥታና  አስተማማኝ  የህዝብ ደህንነት ምርጫ ግጭት ያስከትላል!!!

ምንጭ

(1) https://youtu.be/k9gpEz_0PiM

(2) Taxi drivers’ strike paralyzes Addis Ababa/ Mar 16, 2021 to 11:36/APA-Addis Ababa (Ethiopia)

(3) የዘንድሮ ምርጫ ለአስፈጻሚዎች ብቻ ሁለት ቢሊዮን ብር ያስወጣል/ሪፖርተር ጋዜጣ /14 March 2021/ብሩክ አብዱ

(4)https://www.bbc.com/amharic/news-5478337

(5)https://www.youtube.com/watch?v=4ulGZQAsayk/የቄሮ አምስተኛ ዙር የትግል ጥሪ ይዘት, የቄሮ ፖለቲካዊ,ኢኮኖሚያዊ,እና መሃበረሰባዊ ዉሳኔዎች እና ይዘታቸዉ እንዲሁም የትግራይ ክልል ላይ እየታወጀ ያለዉ .