ፓርላማው በሕወሓት የሚመራው ቡድን እየፈጸመ ያለውን ዝርፊያ አበረታታ

የገዥው መደብ ፓርላማ፣ ሜቴክ የተባለው ድርጅት እየሰራ ያለው ስራ የሚደነቅ መሆኑን ገለጸ፡፡ በኦሮሚያ ክልል የሚገኘውን እና ያዮ የተባለውን የማዳበሪያ ፋብሪካ እየገነባ የሚገኘው በህወሓት ጄኔራሎች የሚመራው ብረታ ብረት እና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ሲሆን፣ ፋብሪካውን ለመገንባትም በቢሊዬን የሚቆጠር ገንዘብ ወጪ ተደርጎበታል፡፡ ሆኖም እስካሁን ድረስ ፋብሪካው ተጨማሪ ገንዘብ ከማስወጣት ውጪ ሊጠናቀቅ አልቻለም፡፡

የፋብሪካው ግንባታ የተጀመረው ከዓመታት በፊት ቢሆንም፣ እስካሁን ግን ስራው ከ46 በመቶ ከፍ ሊል አልቻለም፡፡ በኦዲት ሪፖርት ላይ እንደተጠቀሰው፣ ሜቴክ ፋብሪካውን ገንብቶ ሳይጨርስ ተጫማሪ ቢሊዬን ብሮችን የጠየቀ ሲሆን፣ ገንዘቡ ይፈቀድለት አይፈቀድለት እስካሁን የታወቀ ነገር የለም፡፡ የተጠየቀው ገንዘብም፣ ገና ላልተሰራ ስራ መሆኑ የድርጅቱ ውንብድና ምን ያህል ከፍ እንዳለ አመላካች ነበር፡፡ ፓርላማው ስራ በመጓተቱ ድርጅቱን ሊወቅስና ሊገስጽ ሲገባ፣ ጭራሽ ተደናንቀው መለያየታቸው ድርጅቱ በመከላከያ ሚኒስቴር ስር ይሁን እንጂ፣ የህወሓት ሰዎች እንደፈለጉት የሚጋልቡበት መሆኑን እንዳስመሰከረ ታዛቢዎች ይናገራሉ፡፡

ሜቴክ ያለ ጨረታ ከተረከባቸው የግንባታ ስራዎች መካከል ስኳር ፋብሪካዎች የሚጠቀሱ ሲሆን፣ አንድ የስኳር ፋብሪካ ለመገንባትም ከስምንት ዓመታት በላይ እየፈጀበት ይገኛል፡፡ ይህ እየታወቀ በጉዳዩ ላይ ተወያየው ያለው ፓርላማ፡- ‹‹ኮርፖሬሽኑ በርካታ ሀገራዊ ፕሮጀክቶችን እየገነባ በመሆኑ፣ አብዛኞቹ የተሻለ አፈጻጸም ላይ ይገኛሉ፡፡›› ብሏል፡፡

ያዮ የተባለው የማዳበሪያ ፋብሪካ እየተገነባ ያለው በ530 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ሲሆን፣ ገና ግንባታው ከ46 በመቶ ከፍ ሳይል ሜቴክ የ60 በመቶ ክፍያ ጠይቋል፡፡ ድርጅቱን በዋና ዳይሬክተርነት የሚመሩት የህወሓቱ ሰው ሜ/ጄ/ል ክንፈ ዳኘው፣ ለስራው መጓተት የሰጡት ምላሽ የውጭ ምንዛሪ እጥረት ነው ቢሉም፣ ምክንያታቸው የማያሳምን ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ድርጅቱ ካለው እንዝላልነት እና ዘራፊነት የተነሳ፣ የሀገር ሀብት በማባከን ላይ መሆኑ፣ ከፍተኛው ችግሩ እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በግንቦት ወር ላይ ዋና ኦዲተር፣ ፓርላማ ቀርቦ ሜቴክ ገንዘብ እያባከነና ላልሰራውም ስራ ተጨማሪ ገንዘብ እየጠየቀ መሆኑን ለፓርላማው አባላት አስረድቶ ነበር፡፡ ሆኖም በትላንትናው የፓርላማ ውሎ፣ አባላቱ ይህን ጉዳዩ አንስተው የድርጅቱን ስራ አስኪያጅ ከመጠየቅ ይልቅ፣ ጭራሽ እየተሰራ ያለው ስራ አበረታች መሆኑን መግለጻቸው አስገራሚ ሆኗል፡፡

 

የዜናው ምንጭ ቢቢኤን ራድዮ ነው

ግራ የገባው ህወሓት ኦሮሚያ ውስጥ ለመደበቅ እየሞከረ ነው ተባለ


BBN news  በመላ ሀገሪቱ ከፍተኛ ተቃውሞ ያጋጠመው የህወሓት መንግስት ሰሞኑን ኦሮሚያ ኦሮሚያ ለመጫወት ደፋ ቀና እያለ መሆኑ ተገለጸ፡፡ አምባገነኑ የህወሓት መንግስት እየመጣበት ካለው ህዝባዊ መዓት ለማምለጥ ይረዳኛል ያለውን ዕቅድ ሁሉ ይዞ ብቅ እያለ ሲሆን፣ የተቃውሞ ወጀቡንም ኦሮሚያ ውስጥ ተደብቆ ለማምለጥ መፈለጉን ታዛቢዎች ይናገራሉ፡፡ የለውጥ ጥያቄ የተነሳው በመላ ሀገሪቱ ቢሆንም፣ ህወሓት ግን አንድን ብሔር ነጥሎ በመያዝ፣ ቅራኔ ለመፍጠር መከጀሉን አስተያየት ሰጪዎች በመግለጽ ላይ ናቸው፡፡
በኢትዮጵያ የተነሳው ተቃውሞ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አለመቀልበሱን የተረዳው ህወሓት፣ አሁን ደግሞ አንድን ብሔር ከሌላው ብሔር በዓይነ ቁራኛ እንዲተያይ ለማድረግ ጥርጣሬ የሚፈጥሩ እንቅስቃሴዎችን መጀመሩ በአደባባይ እየታየ ነው ተብሏል፡፡ ከሶስት ቀናት በፊት ይፋ የተደረገው የአዲስ አበባ ኦሮሚያ ዞን ልዩ ጥቅም አንደኛው የመጫወቻ ካርድ ሲሆን፣ ሌሎች የመጫወቻ ካርዶችም እየተሳቡ መሆኑ ተመልክቷል፡፡ ህወሓት ሙሉ በሙሉ ፊቱን ወደ ኦሮሚያ ክልል በማዞር የጀመረው አዲስ እንቅስቃሴ፣ የክልሉን ህዝብ በጥቅማ ጥቅም ለመደለል ማሰቡን እንደሚያሳብቅበት ታዛቢዎች ያስረዳሉ፡፡

አዲሱ ሰነድ ይፋ በተደረገበት ሶስት ቀናት ውስጥ ብቻ ኦሮሚያን የተመለከቱ የተለያዩ ዜናዎች ሊደመጡ ችለዋል፡፡ አንደኛው ዜና አወዛጋቢው ሰነድ ሲሆን፣ ‹‹በአርሲ ዞን ዶዶታ ወረዳ በ400 ሚሊዬን ብር ለሚገነባው የመስኖ ልማት ፕሮጀክት የመሰረተ ድንጋይ ተቀመጠ፡፡›› የሚለው ዜና ደግሞ ሌላኛው የሕወሓት እንቅስቃሴ ነው፡፡ እንቅስቃሴው ይቀጥልና ‹‹ከ2 ዓመት በፊት የመሰረት ድንጋይ የተቀመጠለት የነቀምቴ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ተጀመረ፡፡›› ይላል፡፡
በዚህ ያልተገደበው የህወሓት አዲስ ኦሮሚያ ተኮር ዘመቻ፣ ‹‹የአዲስ አበባ አስተዳደር ለኦሮሚያ ልዩ ዞን ከተሞች ንፁህ ውኃ ለማቅረብ ፕሮጀክት ነደፈ፡፡›› ይላል፡፡ እስከዛሬ ተኝቶ የከረመው ህወሓት መጪው የህዝብ ማዕበል ሲያባንነው፣ ድንገት ተነስቶ ኦሮሚያ ውስጥ ለመደበቅ መሞከሩ፣ ሊመጣ ካለው ማዕበል እንደማያድነው አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ፡፡ ሰሞነኛውን ዜማ ኦሮሚያ በማድረግ፣ በሌላው የህብረተሰብ ክፍል ላይ ጥርጣሬ በመፍጠር አንዱን ከሌላው ጋር በዓይነ ቁራኛ ለማስተያየት እየተደረገ ያለው ጥረት የትም እንደማያደርስ የሚገልጹት ታዛቢዎች፣ ህወሓት ለኦሮሞም ሆነ ለአማራ፣ ለጉራጌም ሆነ ለደቡብ ህዝበ እንዲሁም ለሌሎቹ የሀገሪቱ ህዝቦች የማይጠቅም መንግስት መሆኑን ታዛቢዎቹ ያሰምሩበታል፡፡

የቁልቁለት መንገድ አዲስ አበባ ገደል ስትገባ!! – አገሬ አዲስ

በየትኛውም ዓለም ከተማ ውስጥ የሌለና ያልታዬ ታሪክ በአገራችን ዋና ከተማ በሆነችው አደስ አበባ ውስጥ ለበለጠ የህዝብ ልዩነትና  አገራዊ ቀውስ የሚዳርግ እቅድ ሰሞኑን በወያኔ ካቢኔ በህግ ጸድቆ ይፋ ወጥቷል።ህጉን ምክርቤት ተብየው የወያኔ ሆድ አደር መንጋ ካሳለፈው ለዘመናት ኢትዮጵያውያን በደምና በአጥንታቸው፣በእውቀትና በሃብታቸው የገነቡትን የጋራ ከተማ የሚንድና የአዲስ አበባን ሁልንተናዊነት አጥፍቶና ንዶ የጠበበች፣ የግጭትና የልዩነት አውድማ አድርጎ የሚያደራጅ ነው።የወያኔ ዘላቂ ዓላማ ኢትዮጵያን በታትኖ የራሱን ጠባብ ክልል አገር አድርጎ ለመፍጠር እንደሆነ ምርምር አያሻውም።በዚያው አኳያ በኢትዮጵያዊነት የተሰሩትንና የተገነቡትን እየናደ፣የሚያስተሳስረውን ድርና ክር እየመዘዘ ማዳከም ለዘላቂው ዓላማው መጀመሪያው እርምጃ ነው።ባይሆንልን ብትንትኗን አውጥተን እንመለሳለን ከሚለው ነባር ዓላማ ጋር የተያያዘ መሆኑ ሊዘነጋ አይገባውም።

የወያኔ መራሹ የጎሰኞች ስብስብ አገር አቀፍ ህዝባዊ ተቃውሞ ዓላማውን እንደሚያጨናግፍበት በመረዳት  የትግሉን ትስስር ለመበጠስና ለማዳከም የተካነበትን የማለያየት ስልት፣አንዱን የጠቀመና መብቱን ያስከበረለት በመምሰል ሁሉንም የሚጎዳና ለበለጠ ግጭት የሚዳርግ ስልቱን  ሰሞኑን በአዲስ አበባ አስተዳደር ዙሪያ በመጀመር ይፋ አድርጓል።በዚህ ይፋ ባደረገው አዲስ የህገመንግስት አንቀጹ አዲስ አበባ የሁሉም ከተማ መሆኗ ቀርቶ የአንድ ማህበረሰብ ከተማ እደሆነች በማመን ዘርና ጎሳን ተንተርሶ ያልወጣላት ስሟም የኦሮሞ ተገንጣዮች በሚጠሯት ስም  ፊንፊኔ በሚለው ጭማሪ እንድትጠራ(ይህ እራሱን የቻለ ውዥንብር የሚፈጥር ነው፤የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በየትኛው ለመጥራት ግራ ይጋባል፤ከተማዋም ለሚኖራት ግንኙነት ሁሉ እንቅፋት ይፈጥራል)።ሁሉም ነዋሪ የሚጠቀምበትና የሚግባባበት ቋንቋ ቀርቶ አንድ ማህበረሰብ ብቻ የሚናገረው የኦሮሞ ቋንቋ የአስተዳደሩ ተጨማሪ የስራ ቋንቋ  ለማድረግ የሚያስችል ቅድመ ዝግጅቱን ጨርሶ ህጋዊ ሽፋን ሰጥቶት መወሰኑን ባወጣው መንግስታዊ መግለጫ ይፋ አድርጓል።ይህ ተንኮል ግን ኦሮሞውን ለመጥቀም ሳይሆን የተነሳበትን ተቃውሞ ለጊዜው ለማብረድና በስፋት የያዘውን የዘረፋ ዕድሜ ለማራዘም ሆን ተብሎ የተተመነ ስልት ነው።የኦሮሞም ሆነ የሌላው ማህበረሰብ  ተወላጅ ጥያቄው ቋንቋየን እየተናገርኩ ከሌላው ተነጥዬ ልረገጥ ሳይሆን የሰብአዊና የዜግነት መብቴ ይጠበቅ፣ከድህነትና ከዃላቀርነት የሚገላግለኝ የጋራ ስርዓት ይመስረት፣የዴሞክራሲ መብቶች ይከበሩ፣በጎሳ ማንነት መጠቀምና መጎዳት ይቅር ለወደፊቱም አይኑር፣ከትውልድ የወረስኩት መሬቴን  እየተቀማሁ አልፈናቀል… የሚል ነው።

አዲስ አበባ የአገራችን የፖለቲካና የዓለም አቀፍ ግንኙነት መዲና ፣የአገሪቱም የኤኮኖሚ እምብርት መሆኗ እየታወቀ የአንድ ነጠላ ማህበረሰብ ጥቅም ብቻ የሚከበርበት አንቀጽ  ህጋዊ መመሪያ አድርጎ መደንገግ፣በከተማዋም ሁለገብ ህይወትና በነዋሪው እጣፈንታ ላይ የአንድ ማህበረሰብ የበላይነት ማስፈን  ፍትሃዊና ለሰላማዊ ኑሮና ለህዝብ ጤናማ ግንኙነት የሚረዳ አይደለም።የከተማዋ እድገትና ህይወት ሁሉም የኢትዮጵያ ክፍለሃገሮችና የተለያዩ ማህበረሰቦች ተወላጆች ያበረከቱት ድርሻ ውጤት ነው።ከተማዋ የተገነባችው ከሁሉም ያገሪቱ ክፍሎች በሚሰበሰበው የግብርና የእውቀት መዋጮ ነው።ስለሆነም ሁሉም እኩል የባለቤትነት ድርሻ ሊኖረው ይገባል።ኦሮሞኛ ለሚናገረው ቅድሚያና ብልጫ ጥቅም ይሰጠዋል፣መብቱም ይከበርለታል ማለት በዘረኛው አፓርታይድ ስር  እንደ ቀድሞዋ ደቡብ አፍሪካና ከሚሊዮን ህዝብ በላይ በጎሳ ውዝግብ እንደተጨፈጨፈባት ሩዋንዳ ከባሰ ቀውስ ውስጥ የሚከት ነው።ለመሆኑ ኦሮሞኛ የማይናገረው አዲስ አበባ ውስጥ ተወልዶ ያደገው የኦሮሞ ልጅ ምን ይውጠው ይሆን?ኦሮሞኛ የሚናገረውስ የሌላው ማህበረሰብ ተወላጅ የጥቅሙ ተካፋይ ይሆን ይሆን?ወይስ የጀርባ አጥንቱ እየታዬ ለጥቃቱ ሰለባ ይሆናል?

በሌሎቹስ ክፍላተ ሃገሮች ውስጥ የተቋቋሙትና የተፈጥሮ ሃብት ምንጭ የሆኑት አካባቢ ህዝብ ተመሳሳይ መብትና ጥቅም ያገኛልን? የኤሌክትሪክ ምንጭ፣የወርቅና የተለያዩ ማዕድኖች ቁፋሮ የሚካሄድባቸው አካባቢዎች ህዝብ የጥቅሙ ተካፋይ የሚሆንበት አሰራርና ህግ መቼ ተፈጠረለት?የበይ ተመልካች ከመሆን ያለፈ ዕድል መች አገኘ?

ይህ እንደ አዲስ የወጣ የማጠናከሪያ ደንብና መመሪያ ምናልባት የኦሮሞውን ማህበረሰብ የሚጠቅም ሊመስል ይችል ይሆናል።አርቆ ለሚያስብ የኦሮሞ ተወላጅ ግን ተቃውሞውን ለመግታትና አገራችንን ለመበታተኑ ሂደት የመጀመሪያው መንደርደሪያ እንደሆነ፤ ብቻውን ነጥሎ የሚያስመታውና የሚያስጠቃው የወያኔ ሰይጣናዊ ብልሃት መሆኑንም ሳይረዳው አይቀርም።

የዘፈን ዳርዳሩ እስክስታ ነው እንዲሉ ወያኔ ስልጣን ከመያዙ በፊት ከአጋሩ ከኦነግ ጋር ሆኖ በጀርመን አገር ውስጥ በተካሄደው ስብሰባ ላይ ከፈረንጆቹ በኩል « ኦነግ ተሳክቶለት ስልጣን ላይ ቢወጣ በአዲስ አበባ ውስጥ የሚኖረው ከሁሉም ክፍለሃገር የተውጣጣ ህዝብ ምን ዕድል ይገጥመዋል?» ተብሎ ለቀረበለት ጥያቄ የኦነጉ መሪ የዛን ጊዜው አቶ የአሁኑ ዶክተር ዲማ ነገዎ(ዩሃንስ ነገዎ) የሰጠው መልስ «ለኦሮሚያ የሚጠቅመው መኖሪያ ፈቃዱን እያሳደሰ ሲኖር የማይጠቅመው ደግሞ ወደ መጣበት እንዲመለስ ቀዳዳ መንገድ(safe corridor) ይከፈትለታል» ብሎ ነበር።ይህንን ባለ በስድስት ወሩ ሻእብያ፣ወያኔና ኦነግ ከሌሎቹ በአማራው ስም ከተደራጁት አሽከሮቹ ጋር ስልጣኑንc ጨበጡ።ይህንን የተናገረው ዲማ ነገዎ(ዩሃንስ ነገዎ)የማስታወቂያ ሚኒስቴር ሆነና በውጭ አገር በመዘዋወር ስለተመሰረተው አገዛዝ መብራሪያ ለመስጠት በውጭ አገር እየተዘዋወረ በየስብሰባው መድረክ ላይ ብቅ አለ። በስብሰባ ላይ ያንን ቀድሞ ጀርመን የተናገረውን በአካል ካዳመጥነው ውስጥ አንዱ ቢጠይቀው« አይኔን ግንባር ያድርገው!፣እንዲህ ያለ ቃል ካፌ ወጥቶ አያውቅም» ሲል ሸመጠጠ።ይባስ ብሎም በጠያቂው  ላይ በስብሰባው የተሳተፉት አብዛኛዎቹ የወያኔና የሻእብያ ደጋፊዎች እንዲዛበቱበት የግለሰቡን  አስተያየት አጣጥሎ ለማቅረብ ሞከረ።

እውነትና ጀንበር እያደር ይጠራል! ነውና የኸው ዛሬ ከሃያ ሰባት ዓመት በዃላ የዚያ አስተሳሰብ እንቁላል ተፈልፍሎ በአደባባይ ይፋ ወጣ።

የአዲስ አበባ ከተማ በሸዋ ክፍለሃገር የምትገኝ እንጂ ኦሮሞ የሚል ክፍለሃገር እንዳልነበረና በዚያ  ክፍለሃገር ውስጥ የምትገኝ ከተማ እንዳልነበረች ሁሉም ያውቃል።የሸዋ ክፍለሃገር ደግሞ ኦሮሞውን ብቻ ሳይሆን አማራውና  የተለያዩ ማህበረሰቦች የሚኖሩበት ክፍለሃገር ነው።ስለሆነም  የባለቤትነቱ ጥቅም ይከበርለት ቢባል እንኳን የዚያው የሸዋ ጠ/ግዛት ህዝብ ይሆናል እንጂ የአንዱ ማህበረሰብ ብቻ ሊሆን አይገባውም።

የከተማውንም አስተዳደር በሚመለከተው የአንድ ከተማ አስተዳደር የሚዋቀረው በነዋሪው ብዛትና አኳያ ሊሆን ይገባዋል።አዲስ አበባ በክፍለ ከተማ ና ወረዳ እንዲሁም ቀበሌና መንደር የተዋቀረች በመሆኗ፤በነዚህም የከተማዋ እርከኖች  ውስጥ ከተለያዩ ማህበረሰቦች የፈለቀና የተዋለደ ህዝብ ስለሚኖር አስተዳደሩም(ማዘጋጃቤቱም)የነዋሪውን ገጽና ስብጥር የሚያካትት ሊሆን ይገባዋል።የሚጠቀምበትም የስራ ቋንቋ የከተማው ህዝብ የሚግባባበትና በአገሪቱ ህግ የጸደቀው የአማርኛ ቋንቋ ሊሆን ይገባዋል።ይህ ማለት ግን በከተማዋ ውስጥ ብሎም በአገር አቀፍ ደረጃ ተጨማሪ ቋንቋዎች አይነገሩ ማለት አይደለም።ማንኛውም ዜጋ ከጎሳው አባል ጋር እርስ በርሱ ሊግባባበት የሚችለውን ቋንቋ መናገሩ በህግ ብቻ የሚጸድቅ ሳይሆን ከቤተሰብና  በትውልዱ ያገኘው ችሎታና መብቱ ነው።ኦሮሞው ከኦሮሞው ጋር ለመግባባት ኦሮምኛ ይቀለዋል፤እንደዚህም ያለው ግንኙነት ለዘመናት የቆየና ያለፉት ስርዓቶችም የከለከሉት አሰራር አልነበረም፤በወያኔ መራሹ ስርዓት  ብቻም እውቅና የተሰጠውም አይደለም።ሰው ከሌላው ጋር ለመግባባት የሚመርጠው ቋንቋ ከሁኔታው ጋር የሚያየውና በግላዊ ውሳኔው የሚወስደው እንጂ በህግ ተገዶ የሚከተለው መሆን የለበትም።ብዙ ማህበረሰብ በሚኖርበት አገር ውስጥ የአንድ ማህበረሰብ ተወላጅ የሆነ ዜጋ በራሱ የጎሳ ቋንቋ ቢናገር ከጎሳው ተወላጅ በስተቀር ከሌላው ጋር ሊግባባ አይችልም፤ስለሆነም የሚግባባበት የጋራ ቋንቋ መኖሩ ችግሩን ያቃልልለታል።በታሪክ አጋጣሚ የሁላችን ቋንቋ የሆነው አማርኛ በሌሎቹ ማህበረሰብ ተወላጆች ላይ በግድ የተጫነ ሳይሆን በህብረተሰቡ ቅልቅልና መስተጋብር ሂደት ቃላት እየወረሰ ያደገና የተስፋፋ ቋንቋ ነው።

በኦሮሞ ማህበረሰብ ውስጥ የተወለደ የየትኛውም ማህበረሰብ ተወላጅ ኦሮምኛ ለመናገር ዕድሉ ከፍ ያለ ነው።ይናገረዋልም።የሌላውም በሌላውም ቦታ እንዲሁ ነው።የሁሉም ቅልቅል በሚኖርባትም የአዲስ አበባ ከተማ ኑዋሪ በሚያግባባው የጋራ ቋንቋ በአማርኛ መናገሩ ሊሻርና ሊገደብ አይገባውም።በአዲስ አበባ ብቻም ሳይሆን በተቀሩት ክፍለሃገር ውስጥ የሚኖረው ህዝብ ከየማህበረሰቡ የተውጣጣ በመሆኑ አንድ ቋንቋ አማርኛ መናገራቸው ከነጠላ ጎሰኝነት አጥር ውስጥ ፈልቅቆ ሊያወጣቸው ችሏል ለወደፊቱም ይችላል።የከባቢ ቋንቋ ብቻ ይነገር ከተባለ ከሰማንያ በላይ የሚሆኑት የኢትዮጵያ ማህበረሰቦች ሳይግባቡ ይኑሩ ብሎም በቋንቋቸው ተዋረድ የየራሳቸውን ክልልና መንግስት አቋቁመው እርስ በርሳቸው እየተጋጩና እየተዋጉ ይለቁ ብሎ መፍረድ ይሆናል።አዲስ አበባም ውስጥ የሚኖሩት  አማራና ኦሮሞ ብቻ ስላልሆኑ ሁሉም የማህበረሰብ አባል የጎሳዬ ቋንቋ የአስተዳደሩ ቋንቋ ይሁንልኝ የማለት ጥያቄ እንዲያቀርብ በር ይከፍታል። ወያኔና ግብረአበሮቹም  የሚወጡት የሚወርዱት በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ብሎም በአጠቃላይ በአገራችን ኢትዮጵያ በዚህ አይነቱ ዘዴ ትርምስምስ እንዲመጣ ለማድረግ ነው።በትርምሱ የሚያልቀው የፈረደበት ህዝብ ነው።እነሱ ቤተሰባቸውን ይዘው ቀድሞ ወዳዘጋጁት አገር ይሾልካሉ፤ቀድመውም የሾለኩና ያሾለኩ ብዙ ናቸው።።የደርግ መሪዎች የመጨረሻው ታሪክ ትዝ ሊለን ይገባል።የወያኔና ተባባሪዎቹ ገንዘብና ንብረት በውጭ አገር ማካበታቸው የሚታበል አይደለም።ህዝቡን ኦሮምኛ፣ትግርኛ… ተማር፣ተናገር እያሉ ሲያስጨንቁት ልጆቻቸውን ግን በሚሸሹበት አገር ችግር እንዳይገጥማቸው በከፍተኛ ወጭ በቤትና በውጭ አገር ት/ቤቶች ቋንቋ ያስተምራሉ። ሁለትና ሶስት የውጭ አገር ቋንቋ የማይናገር የባለስልጣን ልጅ ተፈልጎ አይገኝም።

የኦሮሞን ተወላጅ ጥቅም ለማስከበርና ለተጎዳው ካሳ መክፈል የሚለው የማታለያ ስልት ዕድሜን ከማራዘም ሌላ ትርጉም የለውም።በአዲስ አበባ መሬቱን የተነጠቀውና የተፈናቀለው ኦሮሞው ብቻ አይደለም።ከተማዋ ከተቆረቆረችበት ጀምሮ ለብዙ ዓመታት ከአያት ቅድመአያት ሲወርስ ሲወራረስና ገዝቶ ቤት ሰርቶ የኖረውም ኦሮሞ ያልሆነው ዜጋ የጥቃቱ ሰለባ ሆኗል።ወያኔና የሱ ባለሟል የሆነው የከተማዋን አስተዳደር በመያዝ መሬቱን እየነጠቀ ለከበርቴዎች በመሸጥ የባለስልጣኖች የገቢ ምንጭ ያደረገው ኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት( ኦፒዲኦ) የተባለው በኦሮሞ ህዝብ ስም ስልጣን ይዞ መልሶ ኦሮሞውን የሚያጠቃውና የሚያስጠቃው ቡድን ነው።ካሳ መክፈልም ያለበት ይኸው ድርጅትና የገበያው ሸሪኮቹ ናቸው። ካሳ ይከፈል ከተባለ ደግሞ መሬቱን የተነጠቀውና ቤቱ የፈረሰበት፣መጠለያ አጥቶ ለመከራ የተጋለጠውንና ጥቂት የገንዘብ መደለያ እንዲቀበል ተገዶና ተታሎ መሬቱ ለከፍተኛ ዋጋ የተሸጠበት ያዲስ አበባ ኑዋሪ ሁሉ ይመለከተዋል።በሌሎቹም ያገሪቱ ከተማዎች ተመሳሳይ ግፍ የተፈጸመ ሲሆን የካሳ ጉዳይ ከተነሳ በተመሳሳይ መንገድ ተግባራዊ ሊሆን ይገባዋል።

ቋንቋን በተመለከተ  ኦሮምኛም ሆነ የሌሎቹ ቋንቋዎች ማደግ ተገቢ ነው ።ሌላው ቀርቶ የውጭ አገር ቋንቋዎች የሚሰጡበት ትምህርት ቤት በተከፈተበት ከተማ የኦሮምኛም ሆነ የሌሎቹ አገር በቀል ቋንቋዎች ትምህርት ቤት መክፈቱ ለቀና ዓላማ እስከሆነ ድረስ ጉዳት የለውም።የፈለገ ሰው  ጎሳው ሳይታይ  ሊከታተለው ይችላል።ለአማራውም ሆነ ለሌላው ኦሮሞ ላልሆነውም ቢሆን አማርኛ ከማይችለው ኦሮሞ ወገኑ ጋር የሚግባባበትን ዕድል ከፍ ያደርግለታል።ጥንቃቄ የሚያሻው ነገር የተገንጣዮች ዓላማ መሳሪያ እንዳይሆን መከላከሉ ነው።እውነት ለኦሮሞ ህዝብ የሚያስቡለትና የአፍላቂነት ችሎታ ቢኖራቸው ኖሮ ከነጮችም  ተጽእኖ እንዲድን ቢፈልጉ ኖሮ የላቲን ፊደላትን አምጥተው ባልጫኑበት ነበር። ለኦሮሞ ህዝብ አዲስ የፊደል ባለቤት ባደረጉትና ሁላችንም ኢትዮጵያኖች የምንኮራበት ተጨማሪ እሴት እንዲኖረን ባደረጉ ነበር።የጠባብ ጎሳ ምሁራን ግን ቆምንለት ያሉትን ወገናቸውን ለውጭ አገር ባዕዳን ተጽእኖ በቋንቋው ጀርባ አሳልፈው ሰጥተውታል።እነሱ ግን አማርኛን ከአማራው በላይ እየተናገሩ በስልጣኑ ላይ የተቀመጡ ነበሩ፤ናቸውም።የቀና ልብ ባለቤቶች ቢሆኑማ ኖሮ  ልዩነትን የሚፈጥሩ ነገሮችን እያጠፋ አንድነትን በሚያመጡት ላይ ማተኮር በቻሉ ነበር።የዓለም ህዝብ ሊግባባ የሚችልበትን ቋንቋ በፍላጎቱ እየተማረ ካገሩ ወጥቶ እየተግባባ ሲኖር የአንድ አገር ህዝብ የሚግባባበትን ቋንቋ  እንዲጠላና በጎሳው ቋንቋ እየተናገረ እንዳይግባባ ማድረግ ጸረ አገር  ብቻ ሳይሆን ጸረ ህዝብ አሰራር ነው።

የአዲስ አበባን አስተዳደር በሚመለከተው ዙሪያ የወጣውን መመሪያ ከሌሎቹ የሰለጠኑ የዓለም ከተማዎች አሰራር ጋር ሲነጻጸር የሌሎቹ በጎሳ ዙሪያ የተቀነባበረና የተዘጋጀ ሳይሆን የከተማው ነዋሪ የሚሳተፍበትና  ብሎም የአገሪቱ ዜጋ ሁሉ የሚጠቀምበት ሁኔታን ከግምት ውስጥ ያስገባ ነው።አስተዳደሩም የሚመሰረተው ከጎሳ አንጻር ሳይሆን የፖለቲካ ድርጅቶች በፍልስፍና ላይ በተመሰረተ መርሃ ግብር አኳያ በምርጫ ወቅት ባገኙት የህዝብ ድምጽ መጠን አንዱ ብቻውን  ወይም ከሌሎቹ ጋር በጥምር ሁሉም የሚካፈልበትና የሚጠቀምበት አስተዳደር ይቋቋማል እንጂ አንዱን ነጠላ የጎሳ ማህበረሰብ ብቻ በሚጠቅም ሌላውን  በሚጎዳ፣ባይተዋርና ባዳ በሚያደርግ  እኩይ ጽንሰሃሳብ የሚመራ አስተዳደር አይመሰረትም።

በጣም የሚያስፈራውና የሚያሳስበው ነገር አዲስ አበባ የኦሮሞም ዋና ከተማና የአገሪቱም ዋና ከተማ  እርስ በርሱ በሚቃረን በክልላዊነትና በአገር አቀፍነት መልክ ሆና መቅረቧ በሁለት የተለያዩ አስተዳደሮች በጥቅም ፍጥጫና ግጭት ለመፈራረስ በሚያስችል ተንኮል እንድትዋቀር ማድረጉ ነው። ይህንን አደገኛ በማር የተጠቀለለ መርዝ  በኢትዮጵያዊነቱ የሚያምነውና የሚኮራው፣ለኢትዮጵያም አንድነት ህይወቱን ለመስጠት ወደ ዃላ የማይለው፣የጎሳን ፖለቲካ አንቅሮ የተፋውና የሚቃወመው  የኦሮሞ ማህበረሰብ  ተወላጅ ከሌላው ማህበረሰብ ተወላጅ ጋር ተባብሮ ሊከላከለው ይገባል።በህብረት የመሰረታትን አገሩን ኢትዮጵያን ለማፈራረስ  በቅድሚያ ምሰሶ የሆነችው አዲስ አበባ በጎሰኞች የተቀነባበረ ሴራ ለመፈራረስ ስትዘጋጅ በዝምታ ሊያየውና ሊያልፈው አይገባም።አሁን በተለያዩት  በሰሜኑና መካከለኛው ያገሪቱ ክፍለሃገራት በተለይም በጎንደርና አካባቢው የተቀጣጠለውን ህዝባዊ ትግል ለመቅጨትና የአማራውን ማህበረሰብ ለማጥፋት የታቀደውን ዘመቻ ከኦሮሞው ኢትዮጵያዊው በኩል ተቃውሞና ከህዝቡ ትግል ጋር ተሳትፎ እንዳይኖረው ለማድረግ የተሸረበ ሴራ ነው።

«ከጠላት የጎረሱት በሶ ይወጣል ደም ጎርሶ» ነውና ወያኔና ግብረአበሮቹ የሚወረውሩት አሳሳች የጥቅም ፍርፋሪ የኦሮሞን ማህበረሰብ ከኢትዮጵያዊነት የሚነጥልና የሚያስጠቃ፣ተባብሮ በመታገል የእድገትና የእኩልነት  ባለቤት ሊሆኑ ከሚችሉበት ሰልፍ ውስጥ የሚነጥል ስለሆነ« እኛም  አውቀናል ጉድጓድ ምሰናል» እንዳለችው አስተዋይ ጥንቸል የማዘናጊያውን መርዝና አደጋውን ተባብሮ ማክሸፍ ይኖርበታል።

ሌላው የአዋጁ አስፈላጊነት ወያኔና ግብረአበሮቹ ለገጠማቸው ውጥረት ማስተንፈሻና ምናልባትም በውጩ ግፊት ለውይይት  ከተገደዱ ከጠንካራ አክራሪ አቋም(from a strong position) በመነሳት ቀድሞ ወደ ነበሩበት ቦታ ለመመለስ የሚረዳቸው ስልት አድርገው ሊጠቀሙበት በማሰብ ይሆናልና ከወያኔ ጋር ተደራድረን ለውጥ እናመጣለን ብለው የሚያስቡ ከወዲሁ ምኞታቸውን እንዲያጤኑት ያስፈልጋል።ወያኔ ቀለሙን እንጂ ውስጣዊ ምንነቱን የማይቀይር እስስት መሆኑን ሊያውቁት ይገባል።

በተቃዋሚውም ጎራ ከወያኔ ጋር ለመደራደር የሚሹ እንዳሉ አይካድም።ከነዚያም ውስጥ የኦነግ መሪዎች ለተመሳሳይ ዓላማ ስማቸውን ቀይረው በተመሳሳይ የጎሳ ስብስብ መልክ ተደራጅተው የመጡ ስለሆነ ለዳግመኛ የስቃይ ኑሮ ላለመዳረግ የኢትዮጵያ ህዝብ ከጸረ ወያኔ ከሚያደርገው ትግል ጋር የነዚህንም ስብስብ ሊታገለው ይገባል።ወያኔን ተሸክመው አምጥተው  ላለፉት 27 ዓመታት የስቃይና የመከራ ስርዓት እንዳሰፈኑት ሁሉ ለሌላ 27 ዓመታት ተመሳሳይ ስርዓት እንዳይጭኑበት  ተባብሮ  ወግዱ ሊላቸው ይገባል።የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው የሚሉት ፈሊጥ አሁን አገራችን ባለችበት ሁኔታ ላይ አይሰራም።ትግሉ አገር የማዳን ስለሆነ አደጋውም በጎሰኞች ምክንያት የመጣ ስለሆነ ከነሱ ጋር ምንም አይነት የዓላማ አንድነት አይኖርም። ዓላማችንና ተልእኳችን ኢትዮጵያዊነትንና ኢትዮጵያን የማዳን ሊሆን ይገባዋል።ያ ደግሞ በጎሳ  ለተደራጀ ድርጅት አለርጅኩ ነው። በኢትዮጵያዊነታቸው የማያወላውል አቋምና ታሪክ ያላቸው ብዙሃን ስለሆኑ ድሉ የማታ ማታ የነሱ ይሆናል። እንደዚያማ ባይሆን ኖሮ ኢትዮጵያ የምትባል አገር አትኖርም ነበር።

የወያኔንና የግብረአበሮቹን አደገኛ ስልት ተባብረን እናክሽፍ።

አገሬ አዲስ

 

አዲስ አበባንና አካባቢዋን ከኦሮሞ የማጽዳት አዋጅ – ሰርጸ ደስታ      

እኔ ብዙ ጊዜ ብዬዋለሁ የዛሬውን ብዙ የኦሮሞ ትውልድ ወያኔ በራሱ ስለሰራችው እንደፈለገች እንደምትዘውረው ታውቃለች፡፡ ከወያኔ ጋር የኦሮሞን ሕዝብ ልጆች ለማምከን ብዙ በኦሮሞ ሥም የተንቀሳቀሱ ድርጅቶች አሉ፡፡ በዋናነት ግን ኦነግ ከፍተኛውን ድርሻ ይወስዳል፡፡ ቁጥሩ አነሰም በዛም ዛሬ ላይ ድምጹ ከፍ ብሎ የሚሰማው ይሄው ወያኔ የሰራችው ትውልድ ድምጽ ነው፡፡ መቼም ይህን ከሚያክል ሕዝብ የተወሰነም ቢሆን የሚያስተውል ይጠፋል ብዬ አላስብም፡፡ እነ መረራና የሱ አጋሮች ዛሬ ላይ መናገር አይችሉም፡፡ ግን ቢያንስ የእነ መረራን መርህ የሚከተል ትንሽም ቢሆን ይገባዋል የሚል እምነት አለኝ፡፡ የኦሮሞ ሕዝብ ከመጀመሪያው ጀምሮ በዋናነት አማራ ከሚባለው ሕዝብ ጋር ልዩ ጥላቻ እንዲያድርበት በፖሊሲ ጭምር ታግዞ ሲሰራበት ነው የቆየው፡፡ ዛሬ ላለው ኦሮሞ እየገደለው ያለው ወያኔ ምኑም አደለ፡፡ ዋና ጠላት አድርጎ የሚያስበው የኦሮሞ ክብርና ልዕልና ከፍ ያለበትን የሚኒሊክ ታሪክ ነው፡፡ ይህን እውነት እስከሚገባው ድረስ ኦሮሞ ከክብር እየወረደ እንደሚሄድ አትጠራጠሩ፡፡ ኦሮሞ በኦሮሞ ሥም በሚኒሊክ ዘመን ያለው ታሪክ ሁሉ በውሸት የተቀናበረለት አኖሌ ብቻ ነው፡፡ ሲያሰኘውም ጨለንቆን ይጨምራል፡፡ ልብ በሉ አሁን እየተነገረ ያለው የአኖሌ ታሪከ ፍፁም ውሸት ሲሆን በአርሲ የነበረው ጦርነት ግን ብዙ ጥፋት እንደነበረው የራሳቸው የሚኒሊክ መዋዕለ ዜናም መዝግቦት ይነበባል፡፡ ጨለንቆን ካሰባችሁ ከእነ ጭርሱም ከኦሮሞ ጋር የተደረገ ጦርነት አልነበረም፡፡ ከሀረሪው ገዥ ጋር ነበር እንጂ፡፡ ዛሬ ዘጠና ከመቶ በላይ የሚሆነው  ኦሮሞ ጨለንቆን ከኦሮሞ ጋር የተደረገ ጦርነት እንደሆነ ነው የሚያውቀው፡፡ ዛሬ የሚነገረው የአኖሌውንም የጨለንጦውንም የውሸት ታሪክ አስተውላችሁት እንደሆን እየተቀነቀነ ያለው በሙስሊም አክራሪዎች ነው፡፡ ኦሮሞን በሙሉ በሙስሊም አክራሪ ሴራ ውስጥ እየተጠቀሙበት ነው፡፡ በተቃራኒው ታላላቅ ዝናና ገድልን የፈጸሙ የኦሮሞ ጀግኖች ታሪክ እንዲዋረድ ተደርጓል፡፡ ጀግኖቹ በአብዛኛው ከክርስቲያን ኦሮሞ ስለነበሩ ይህን ሆን ተብሎ ነበር ዘመቻው የተካሄደው፡፡ ጀግኖቹን አለም ሳይቀር መዝግቧቸዋል የኦሮሞ ሕዝብ ግን የገዛ ጀግኖቹንና ታሪኩን አጥቶ ምልከት የሌለው የመከነና ተቅበዝባዥ ወኔው የከዳው ሆኗል፡፡ ጎበናን ያቃልላል ያልታወቀ የሰፈር ሽፍታ እያመጡ ጀግና ይሰይሙለታል፡፡ ገበየሁ ጎራን፣ ባልቻ ሳፎን፣ እና እልቆ መሳፍርት የኦሮሞ ጀግኖች በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ የሉም፡፡ እና ምን ባዶ ምልክት የሌለው ሕዝብ ምን ወኔና አቅም ይኖረዋል እንደፈለጉ ለሚዘውሩት ራሱን ሰጥቶ፡፡ ከዚህ ነበር የጀመረው የኦሮሞ ሕዝብ ውድቀት፡፡

በኃይለሥላሴም በደርግም ኦሮሞ እንደማኝኛውም ዜጋ የራሱ ድርሻ ነበረው፡፡ ይህ የኦሮሞ ትውልድ ግን ድርሻ አልነበረኝም ይላል፡፡ ዛሬ ግን አስተውሉ አሮሞ ምንም ውስጥ የለም፡፡ ሲስተማቲካል ሙልጭ ብሎ ከኢትዮጵያ ተሳትፎ ውስጥ ወጥቷል፡፡ ኦሮሞ በንግድ ውስጥ የለም፣ በስልጣን የለም፣ በትልልቅ ተቋማት የለም፣ ድሮ በሚታወቅበት በመከላከያ ሰራዊት መሪነት ውስጥ እንኳን ባዶ እንዲሆን ነው የተደረገው፡፡ ብልጦቹን የኦሮሞ ልጆች ሲስተማቲካሊ በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት እንዳይኖራቸው ተደረገ፡፡ አሮሞን ዛሬ ብታዩት ምንም የለውም፡፡ ባለሀብት ጥሩ! ባለስልጣን ጥሩ! ኦሮሞ ምንም ውስጥ የለም፡፡ ኦሮሞ ኦሮሚያ የምትባል የቅዠት አገር ውስጥ ነው የሚኖረው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ዛሬ አሮሞ የለም፡፡ ይሄው ዛሬ 26 ዓመት አለፈው አሁንም አልነቃ ብሏል፡፡ ቋንቋ፣ ከተማ፣ የቦታ ሥያሜ ምናምን እያሉ ይደልሉታል፡፡ መሠረታዊ ማንነቱንና በአገሪቱ ያለውን ኢኮኖሚያዊም በሉት ማህበራዊና ፖለቲካዊ ድርሻ ግን እንዳይኖረው ተደርጎ ተጠርንፏል፡፡ ናዝሬት አዳማ፣ ደብረዘይት ቢሾፍቱ፣ ዝዋይ ባቱ፣ ተባሉ መልካም፡፡ ግን ለኦሮሞ ምን ጠቀመው;   ኦሮሞ በእንደነዚህ አይነት መደለያዎች እንደሚዘወር ስለተረዱት ታሪክም እውነትም መጠበቅ አያስፈልግም ብቻ ኦሮምኛ በማድረግ ኦሮሞን አፉን መዝጋት እንደሚቻል ሰዎቹ ተማምተናዋል፡፡ አዳማ በትክክልም ታሪካዊ ሥያሜዋን እንዳገኘች አልጠራጠርም መልካም ይህ ለኦሮሞ ሳይሆን ሌላውም ይጋራዋል፡፡ ዝዋይን ባቱ ብሎ መሠየም ግን ኦሮሞን ለመደለል ከተከደበትም አካሄድ በላይ ታሪካዊ ስህተትና የሌሎችን ታሪክ የሚጋፋ ነበር፡፡ ይህ ቦታ ከጥንት ጅምሮ ከዜይ ሕዝብ ጋር የተገናኘ ነው፡፡ ከኦሮሞም ሕዝብ በፊት የዜይ ሕዝብ በዚህ ቦታ ይኖር ነበር፡፡ ሀይቁ በእነዚሁ በዜይ ሕዝቦች ስም ዝዋይ ተባለ ከተማው ደግሞ ከሀይቁ ሥያሜውን አገኘ፡፡ ይህ ሁሉ እየሆነ ያለው በወያኔና ኦሮሞን ከኢትዮጵያዊነት ቦታ ድራሹን ያጠፉት በቅዠት አገር በሚያኖሩት ነው፡፡ ኦሮሞን የከበበው ሕዝብ ሁሉ ኦሮሚያ የምትባለው አገር እውን ብትሆን ኦሮሞ ዋና ጠላታቸው እንደሆነ ያውቃሉ፡፡ ለአለፉት 26 ዓመት የኦሮሞ ሕዝብ ያልተጋጨው አዋሳኝ የለም፡፡ ምክነያቱም በኦሮሞነት ሌላውን እንዲጠላ በመደረጉ ነው፡፡  እናም ዛሬ ኦሮሞ ሲባል የትኛውም ሕዝብ በበጎ አያይውም፡፡ እንደውም አማራ ከተባለው ጋር በተወሰነም ቢሆን መግባባቱ አለ፡፡

አሁን አዲስ አበባን ለኦሮሞ ጥቅም ማስከበር በሚል የተደረገው ይሄው ለዘመናት በኦሮሞ ሕዝብ ላይ ሲቆመር የነበረው አሰራር ነው፡፡ አሮሞ በሌሎች ሕዝቦች እንዲጠላ ማድረግ የበለጠ ባዶ እንዲሆን የበለጠ እንዲምታታ ማድረግ፡፡ ኦሮሞ ከአልታገለ ወያኔ ብዙ እድሜ እንዳላት ታውቃለች፡፡ የወያኔ መጥፊያዋ ኦሮሞ ከሌሎች ሕዝቦች ጋር የተባበረ ዕለት ነው፡፡ በወሳኝነት ቦታ እንዲሳተፍ አይፈለግም፡፡ ምክነያቱም በራስ መተማመን እንዳያመጣ፡፡ እንዲሁ የተወናበደ በራሱ የማይተማመን ኦሮሞ ነህ በሚል እየተደለለ እንዲኖር ነው በዋናነት እየተሰራበት ያለው፡፡ አስቂኙ የኦሮምን ጥቅም ያስጠብቃል የተባለው የአዲስ አባባ ከተማ አዋጅ ፍፁም ሕገ ወጥ ከመሆኑም በላይ ዳግም አሮሞን ከሌሎች ሕዝቦች ጋር ሕብረት እንዳይኖረው የሚያደርግ፣ ግን ምንም አይነት ትቅም እንዳይኖረው የተቆለፈበት ነው፡፡ በግልፅ ግን የኦሮሞ ገበሬዎች በስፋት እንደሚፈናቀሉ ደንግጓል፡፡ አላማውም መሬቱን ከኦሮሞ ማጽዳት ነው፡፡ ልብ በሉ ዛሬ ሰዎቹ ገንዘብ ስላላቸው መሬቱን ሊገዙት ይችላሉ፡፡ ለኦሮሞ ገበሬውም በቂ ገንዘብ ሊሰጡት ይችላሉ፡፡ በዚህ ሂደት አዲስ አበባና ዙሪያዋ ከኦሮሞ የጸዳች  አካባቢ ይሆናል፡፡ ቀመሩ ይህ ነው፡፡

ለኦሮሞ ወጣቶች ሥራ እንሰጣለን የሚለው ሌላው አሳዛኝ ንቀት ነው፡፡ የኦሮሞ ወጣት የሀብት ባለቤት ሳይሆን የሚሆነው ተቀጣሪ ባሪያ ነው፡፡ ሀብቱ ውስጥ መቼም እድል እንዳይኖረው ሰርተውበታል፡፡ የእነሱን ፋብሪካዎችና ድርጅቶች ለማንቀሳቀስ ኦሮሞ ያስፈልጋል፡፡ ድሮስ የጉልበት ሠራተኛ የሚሆነው ማን ነው; ይህ አሳዛኙ ነገር አንዱ ነው፡፡ በአጠቃላይ ይህ አዋጅ አሮሞን በቀጣይም ከተሳትፎ በማራቅ በራስ መተማመኑን ሁሉ በማጥፋት የተገዥነት እውነታውን አሜን ብሎ እንዲቀበል የተደረገ ነው፡፡ አዲስ አበባን የሚሟገተው ኦሮሞ መላው ኦሮሚያ የተባለውን አገሩን ራሱ እንዳጣ አያውቅም፡፡ በዚህ አዋጅ ብዙዎች ጮቤ ረግጠዋል፡፡ ይህ ይጠበቅ ነበር፡፡ ይህንንም ታስቦ ነበር አዋጁ፡፡ አዋጁ የኦሮሞን ሕዝብ ዝም ለማሰኘት ታስቦ የወጣ እንጂ ወያኔ የደረሰችውን ሕገመንግስቷ አንቀጽ49/5 የሚለው ጋር ምንም አይገናኝም፡፡ አዋጁ አዲስ አበባ በኦሮሚያ እምብርት ላይ በመሆኗ እያለ በተደጋጋሚ ይናገራል፡፡ ይህ ማሳከር ነበር፡፡ አንቀጽ ተብዬው የሚለው አዲስ አበባ በኦሮሚያ ክልል መሀል ስለሚገኝ ነው የሚለው፡፡ መሀል ማለት አካለ ነው ማለት አደለም፡፡ ራሱን የቻለ አስተዳደርም አለው፡፡ አዲስ አበባ የራሱ መስተዳደር እንዲኖረው የሆነበት ብዙ ምክነያቶች ይዘረዝራል፡፡ አዲስ አበባ ከሥያሜዋ ጀምሮ ሕገ ምንግስት ተብዬው ያጸደቀው ነው፡፡ አሁን ፊንፊኔ ምናምን ኦሮሞን ለማስደሰት ነው፡፡ የኢስ አባባ መንገዶችና ሰፈሮች እንደአስፈላጊነቱ በኦሮምኛ ይሰየማሉ ይላል፡፡ ይህም ያው አሮሞን ለመደለል ነው፡፡ በእንደእነዚህ ያ ነገሮች እንደሚረካ እናውቃለን ብለው ስለሚያስቡ፡፡ ሲጀምር የአዲስ አበባ መንደሮች የኦሮምኛን ሥያሜያቸውን አጥፍተውም አያውቁም፡፡ አሁንም ቢሆን ፒያሳና መርካቶን እንቀይር ካልተባለ የኦሮምኛ ሥያሜዎች እንዳሉ ናቸው፡፡ ከጊንፊሌ፣ ቀበና፣ የካ፣ ቦሌ፣ ጉለሌ፣ ምናም፡፡ እንግዲህ 7ኛ አብነት ምናምን የሚባሉትን ኦሮሞ እንደሚያስበው አማራ አልሰየማቸውም፡፡ ለቡ፣ አቃቂ፣ ቃሊቲ፣ ለመሆኑ ግን አማርኛው የት ነው፡፡ ምን አልባት መገናኛ፡፡ ኮተቤም አማርኛ አደለም፡፡ መንገዶቹም አሁን ተሰይመው ያሉት በአብዛኛው በሌሎች ሕዝቦች ነው፡፡ መቼም ኦሮሞ ነፍጠኛ የሚላቸው አንዱንም መንገድ በሥማቸው አልሰየሙም፡፡ እንዲህ ነው በኦሮሞ ላይ እየተሰራ ያለው ድራማ፡፡ ኦሮሞ በዚህ ከቀጠለ በቁጥርም አናሳ እንደሚሆን ይሰማኛል፡፡ በአለፉት 26 ዓመት ከምንም ነገር ውስጥ እንዳይታይ ተደርጎ በፖለቲካ ውዥንብር ውስጥ ከሌሎች ጋር እንዲቃርን ሲደረግ ነው የኖረው፡፡ አሁንም ብዙው አልነቃም፡፡

ሰሞኑን አቶ ለማንና ቡድናቸውን የሚያወድስ ጽሁፍ ጽፌ ነበር፡፡ እርግጥ ትንሽ ማየት እንዳለብን ተናግሬም ነበር፡፡ እስከዛሬ እየመጡበት በአለው ነበር ለገመግም የሞከርኩት፡፡ በዚች በአዲስ አበባዋ አዋጅ ዋና ጮቤ ረጋጭ እንደሆኑ ሳይ ግን እስካሁንም ለካ ሕዝብን በእነሱ ቀለበት ውስጥ ለመክተት ነው የሚል ጥርጣሬ አደረብኝ፡፡ ከጥርጣሬም በላይ እነለማ የኦሮሞን ሕዝብ ለቀጣይ አመታት ለሽያጭ እንዳቀረቡት ተሰማኝ፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ይህ አዋጅ ዛሬ መምጣቱ ብቻ ሳይሆን አዋጁን ራሳቸው እንደሚፈልጉት አዘጋጅተው የተወሰነ በተለያዬ ሚዲያዎች ሕዝብ ምን ይላል የሚለውን ለማወቅ ሲለቁና አይ እኛ አናውቀውም ሲሉ ከርመው ያው አሁን ያወጁት በዛ መሠረት ነበር፡፡ እነ ለማ አሳምረው ያውቁ ነበር፡፡ በሕግም በሞራልም፣ በምንም ዋስትና የሌለውን አዋጅ በኦሮሞ ሕዝብ ሥም አውጀው እነሱ ዋጋ ተቀበሉበት፡፡ በዚህ አዝናለሁ፡፡ አቶ ለማን መስሎኝ መጀመሪያ ሥራዎ የታሰሩ የሕዝብ ልጆች እንዲለቀቁ ማድረግ ነው የሚል ምክርም ሞክሬ ነበር፡፡ ለነገሩ ብዙ ሌሎች የኦሮሞ ልጆችም አቶ ለማን በዚህ ጉዳይ ትኩረት እንዲሰጡ መክረዋል፡፡ አሁን ግን ሳይ ገና የተናገሩት እንኳን ከሰው ጆሮ ገብቶ ሳይደመጥ የኦሮሞን ሕዝብ የገበያ ማቅረባቸው አሳዝኖኛል፡፡ እንደእኔ ይህን አዋጅ የአቶ ለማ ቡድን መቀበል አልነበረበትም ብቻ ሳይሆን በዚህ ወቅት ምንም አይነት ነገር በዚህ ጉዳይ ላይ ተባባሪ መሆን አልነበረበትም፡፡ ይህ 23ዓመት ሥራ ላይ ያልዋለ አዋጅ ዛሬ ሕዝቡ ፍጹም ከዚህ የተለየ ጥያቄ እየጠየቀ በአለበት ወቅት ነው ለማ የ23 ዓመት ሻጋታ ሕዝብ ትዝ የማይለውን ጉዳይ ያነሱት፡፡ እሱም የኦሮሞን ሕዝብ ጥያቄ ለለስኩልህና አርፈህ ተቀመጥ ለማለት፡፡

በአጠቃላይ የኦሮሞ ሕዝብ ወደነበረበት ማንነቱ ከአልተመለሰ እንዲሁ ይቀጥላል፡፡ አሁን አማራውንም እንደኦሮሞው ከታሪክና ማንነት ለማምከን ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ነው፡፡ ኦሮሞን በተሳካ ሁኔታ እንዳመከኑት የተረዱት አሁን አማራውን ብሄረተኛ በሚል እያጦዙት ነው፡፡ ልብ በሉ በወያኔ የዘወር የነበረው የኦነግን እንቅስቃሴ ኢትዮጵያን በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ ሲኦል ማድረግ ነበር፡፡ 26 ዓመት ሕዝቡን ከኢትዮጵያዊነቱ አመከነው፡፡ ጀግኖች አባቶቹን አስጣለው ዛሬ ወኔ የሌለውና አላቃሻ አናሳ ከሚባሉትም በታች አቅም የሌለው ሆነ፡፡ ለዘመናት እየተገደለም እየታሰረም ቢሆን አማራ የተባለው ወያኔን ሲፈታተናት ነበር፡፡ ይህም ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚለው እምነቱ ጽኑ በመኆኑ ነው፡፡ አሁን ወያኔ ኦሮሞን እንዴት እንዳመከነቸው የሰራላትን ሥልት በአማራው ላይ በከፍተኛ ትኩረት እየሰራችበት ነው፡፡ ዛሬ አማራ የሚባለው እንደ አሸን የበዙ ድርጅቶች አሉት ሁሉም ይነታረካሉ፡፡ ብዙ ትውልድ ቤተ አማራ የተባለ የወያኔ ተላላኪ ተከታይ ሆኖ ገደል እየገባ ነው፡፡ አማራ በአማራነቱ አደለም ታሪክ ያለው፡፡ በኢትዮጵያዊነቱ እንጂ፡፡ ኢትዮጵያዊነት ከሌለ ጉልበት፣ ወኔ፣ ኣላማ የለም፡፡ አማራ በጊዜ ከአልነቃ በኦሮሞ የሆነው መምከን እንደሚመጣበት አትጠራጠሩ፡፡ ዛሬ ኦሮሞ የሰፈረበት ምድር የሌሎች ሆኖ ቢሆን ወያኔ አዲስ አበባ ላይ አደለም ደደቢት ቦታ ባልኖራት፡፡   አማራን ነፍጠኛ ሲሉት ያጣጣሉት መስሏቸው ነበር፡፡ ግን አዎ ነፍጠኛ ነኝ እኮራለሁ በዚህ ሲል ጭራሽ  ወኔና ጉልበት እንደሆነው ገብቷቸዋል፡፡ አሁን የሚያዋጣው አማራን ተበዳይ ነህ በሚል የበታችነት ስሜት እንዲኖረው ማድረግና እንደኦሮሞ ከታሪክም፣ ከወኔም ማምከን ነው፡፡ ኦሮሞም ተጨቁነሀል እየተባለ ነው የክብር ታሪኩንና ጀግኖች አባቶቹን ጥሎ ዛሬ ከምንም የሌለ መካን የሆነው፡፡  አንዴ ከታሪክና ከማንነቱ ከወጣላቸው የሚያደርጉትን እነሱ ያውቃሉ፡፡ ቤተ አማራ አማራውን ከታሪክና ከማንነት ለማምከን ኦነግ የተባለው የኦሮሞ ኮፒ በአማራ እንደሆነ ሰው ልብ ሊል ይገባዋል፡፡ ኦሮሞን ይሄው ዛሬ መላውን ኦሮሚያን ነጠቀውት አዲስ አባባንም ሰጠንህ ሲሉት እየተደሰተ ነው፡፡ ጊዜ በአገኙ ቁጥር ከቁጥሩም ያሳንሱታል፡፡ እነሱ በአዲስ አበባ ብቻ አደለም በሌላውም ዋና ዋና የኦሮሞ ግዛቶች ይስፋፋሉ፡፡

አመሰግናለሁ

ልዑል እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይጠብቅ!

አሜን!

ሰርጸ ደስታ

የኦሮሞ ህዝብ እኩልነት እንጂ ልዩ ጥቅም ፈላጊ አይደለም (ገለታው ዘለቀ)

» የኦሮሞ ህዝብ እኩልነት እንጂ ልዩ ጥቅም ፈላጊ አይደለም (ገ

ገለታው ዘለቀ

Bishoftu, Irreecha massacre

የኦሮሞ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ሌሎች የኢትዮጵያ ብሄሮችም ሆኑ ዜጎች በጋራ ከመሰረቱት ሃገር ልዩ ጥቅም ፈላጊዎች አይደሉም። ኢትዮጵያውያን በመሬት ዙሪያ በኢኮኖሚ ዙሪያ ለየቡድናቸው ልዩ ጥቅም (special interest)  ይዘው በአንድ የፓለቲካ ጠገግ ዘንድ ለማረፍ አይስማሙም። አልተስማሙም። ኢትዮጵያውያን ለእንደዚህ ዓይነት ራስ ወዳድ ስምምነት ሃይማኖታዊም ባህላዊም መሰረት የላቸውም። ለእንግዳ እንኳን ቅድሚያ የሚሰጥ ባህል ነው ያላቸው።  ለነገሩ ኢትዮጵያ ብቻ ሳትሆን እጅግ ብዙ የዓለም ሃገራትም ቢሆኑ በመሬትና በኢኮኖሚ አካባቢ “ልዩ ጥቅም” የሚል ስምምነት በህገ-መንግስታቸው ላይ አያሰፍሩም። ልዩ ጥቅም የሚለው ፅንሰ ሃሳብ ራሱ ከፍትህ ምንጭ አይቀዳም። ራስን ያስቀደመ ስግብግብ ፍልስፍና በመሆኑ የሰው ልጆች ፓለቲካዊ ጠገግ ሲሰሩ  “በልዩ ጥቅም” አይስማሙም። ቡድኖች አገር ሲመሰርቱና ጠገጉን ሲሰሩ አንዱ ትልቁ ኪዳናቸው የጋራ እኩልነት፣ ፍትህ ነፃነት ናቸው። በጋራ የሚያቆሙት ይህንን ነው።  መንግስትም ዘብ ቆሞ ይህንን እሴት  እንዲጠብቅላቸው ይሻሉ። ይሁን እንጂ በታሪክ አጋጣሚ ብሄርን ለይቶ በኢኮኖሚ ወይም በማህበራዊ ጉዳይ ያልተመጣጠነ እድገት ካለ እነዚህ በአንድ ላይ የሚኖሩት ህዝባች ቀደም ብለው ለፍትህና ለእኩልነት በህገ መንግስታቸው ላይ ቃል በገቡት ጠቅላላ የፍትህ ሥርዓት መሰረት እንደየ ሁኔታው የተለያዩ ካሳዎች (affirmative actions) እየተጠቀሙ ለእኩልነት ሊሮጡ ይችላሉ።  ይህ ማለት ግን ልዩ ጥቅም በሚል ሃብትን መሬትን ለመቀራመት ሳይሆን  እኩልነትን በፍጥነት ለማረጋገጥ የሚወሰድ የማስተካከያ ርምጃ  ነው።

አሁን በቅርቡ በኢትዮጵያ ሚንስትሮች ምክር ቤት የወጣው መግለጫ ይዘት ካሳ ወይም afirmative action ሳይሆን ከብሄር ፌደራሊዝሙ አስተሳሰብ የመነጨ ከተፈጥሮ ሃብትና የመሬት የብሄሮች ቅርምት የመጣ ዶክትሪን ነው። ይህ አስተሳሰብ ደግሞ አደገኛ ነው። ይህ የብሄር ፓለቲካን መሰረት ያደረገ ፓሊሲ በሃገሪቱ የተፈጥሮ ሃብት አጠቃቀም በኢኮኖሚ ክፍፍል ላይ ብዙ የሚያተራምሱ ችግሮችን የያዘ ነው። ለምሳሌ ህገ-መንግስቱ አዲስ አበባ አካባቢ የኦሮሚያን ልዩ ጥቅም ያነሳል። ይህ ስሜት ግን ብዙ ጥያቄዎችን ይለምናል። ራስን በራስ ማስተዳደርና የራስን እድል በራስ መወሰን ዋና መመሪያችን ከሆነ ቡድኖች ሰብሰብ ብለው በሚኖሩባቸው ከተማዎች ሁሉ የልዩ ጥቅም ጉዳይ ይነሳባቸዋል።  ለምሳሌ አዋሳን እናንሳ። አዋሳ የደቡብ ክልል ዋና ከተማ ስትሆን ነገር ግን የሲዳማ ህዝብ በአዋሳ ላይ ልዩ ጥቅም ሊጠይቅ ይችላል ማለት ነው። ምክንያቱም የክልሉ ርእሰ ከተማ ሲዳማ እምብርት ላይ ስለምትገኝ።  አዋሳ ብቻ ሳትሆን አሶሳም፣ ጋምቤላም ይህንን ጥያቄ ያነሳሉ። የሚገርመው ይህ ችግር እስከ ዞን ከተሞችም ሊወርድ ይችላል። ብሄሮች ሰብሰብ ብለው  በሚገኙበት ከተማ አካባቢ የልዩ ጥቅም ጉዳይ ሊነሳ ይችላል። ውሎ እያደር ማለት ነው።  ይህ የሚያሳየው ልዩ ጥቅም የሚባለው ነገር  እንዴት የፍትህ ስርዓታችንን እስከ ታች እንደሚያበላሽብን ነው።  ይህ ጥይቄ ከፍ ሲል እንዳልኩት የተበደለን ለመካስ ሳይሆን የመሬትና የተፈጥሮ ሃብት ቅርምትን መሰረት ያደረገ በመሆኑ ከፍትህ የተጣላ እርስ በርስ የሚያናቁር ነገር ነው። በመርህ ደረጃ ያለውን ችግር ማንሳቴ ነው። ወደ  ተግባራዊ ጉዳዮች እንግባ ካልን ደግሞ በርግጥ የኢትዮጵያ መንግስት ለኦሮሞ ህዝብ ልዩ ጥቅም በዚህ አዋጅ አምጥቷል ወይ? ብለን መገምገምም አለብን።   በመግለጫው ላይ የተጠቀሰውን አንዳንዱን እናንሳ። የትምህርትን ጉዳይ እናንሳ። አንዱ የኦሮምያ ልዩ ጥቅም ማሳያ በአፍ መፍቻ ቋንቋ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ይከፈታል የሚል ነው። ይሄ ልዩ ጥቅም ሳይሆን መብት ነው። ኦሮሞው ብቻ ሳይሆን ጉራጌም፣ ትግሬም ሊፈቀድላቸው ይገባል። የንፁህ መጠጥ ውሃ ጉዳይም እንደ ልዩ ጥቅም አይታይም። የግድ በማናቸውም መልኩ ይህ ህዝብ ንፁህ ውሃ ማግኘት አለበት። እስካሁን አለማግኘቱም ይገርማል። የቋንቋ ጉዳይ ሲነሳ መታየት ያለበት ጉዳይ ዲሞ ግራፊው ነው። በዛ ያለ አንድ ቋንቋ ተናጋሪ ባለበት ወረዳ ወይም የታችኛው የስልጣን ርከን አካባቢ የዚያ ቋንቋ ተናጋሪዎች ቋንቌቸው ኦፊሽያል ሊሆን ይገባል።  ሁሉንም  ቋንቋዎችም በዚህ መንገድ ኦፊሺያል በማድረግ ፍትህን ማውረድ ይቻላል። ኦሮምኛ የስራ ቋንቋ መሆኑ ሲነገር መልካም ነው። ታዲያ ከኦሮሞ ቀጥሎ በቁጥር ብዙም የማያንሰው የጉራጌ ብሄርስ? ስለዚህ ዓላማው  የተጎዳን የመካስ ጉዳይ ከሆነ ቋንቋዎች ሁሉ አሰራራቸው ተቀይሮ ለተጠቃሚው አገልግሎት እንዲሰጡ መደረግ አለበት። መግለጫው ፊንፊኔ የሚለውን ስያሜ ህጋዊ አድርጎታል። መልካም ነው። ሸገር፣ ፊንፊኔ፣ አዲስ አበባ እየተባለች ብትጠራ የሚከፋ አይኖርም። በተለይ ፊንፊኔ የሚለውን መጠሪያ ብዙ ሰው ከወደደው ይህ ስም እውቅና ቢሰጠው የሚደገፍ ነው።  ይልቅ ሌላው በመግለጫው ውስጥ የተቀመጠው አስገራሚ ነገር የመሬት አቅርቦትን የሚመለከተው ነው። የኦሮምያ መንግስት ለህዝብ ጥቅም የሚሆኑ ህንፃዎችን ለመስራት ሲያስብ ከሊዝ ነፃ ይሆናል ይላል። ይሄ በውነት ያሳዝናል።ይሄ አይደለም እኮ የኦሮሞ ጥያቄ። ለመሆኑ የኦሮምያ መንግስት የሊዝ ክፍያ የማይከፍል ከሆነ ማን ነው እንዲከፍል የተፈረደበት? ለምሳሌ የአማራ መንግስት ለህዝብ ጥቅም የሚሆን የሙዚየም ህንፃ አዲስ አበባ ለመገንባት ቢያስብ ይከፍላል ማለት ነው? ትግራዩ ቢያስብ ይከፍላል ማለት ነው? ጋምቤላ ቢያስብ ይከፍላል ማለት ነው? ለመሆኑ ኦሮሞስ በዚህ ይደሰታል? ይሄ አይሰራም። ወይ ሁሉም ይከፍላል። ወይ ሁሉም አይከፍልም። አለቀ። የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ አዲስ አበባ ውስጥ መሬት ለእኔ በነፃ ይሰጥ ሌላው ይክፈል አይደለም። የእኩልነት ጥያቄ ነው ያነሳው። ከተማዋ ስትስፋፋ ለሚፈናቀለው ገበሬ ተገቢ ካሳ ይሰጥ ነው እንጂ መሬት በነፃ ይሰጠኝ አይደለም።  ሌላው ጉዳይ የሥራ እድል ነው። ከፍ ሲል እንዳልነው  በቡድኖች መካከል ያለን የኢኮኖሚ እድሎች  የትምህርት እድሎች መራራቅ ለማስተካከል ካሳ (affirmative action ) በርግጥ አስፈላጊ ነው። ይሁን እንጂ አዲስ አበባ ከተማ አቅም አግኝታ ካሳ ካሰበች የተጎዱትን ሁሉ ማሰብ አለባት። ኦሮሞን ብቻ ሳይሆን አዲስ አበባን የማያውቁ ብሄሮች አሉ። እነዚህ ብሄሮች ባህላቸውን በከተማዋ እንዲያስተዋውቁ ራሳቸውን እንዲያስተዋውቁ እድሎችን ማስፋት ተገቢ ሊሆን ይችላል። የአካባቢ ስሞችን በሚመለከት እንደየ ሁኔታው በቀድሞ የኦሮምኛ ስም እንዲጠራ ይደረጋል ይላል የሚንስትሮች ምክር ቤት መግለጫ።  ይህ በውነት ሚዛን አይደፋም። ስልቻ ቀልቀሎ ቀልቀሎ ሥልቻ ነው ነገሩ። አዲስ አበባ ውስጥ ፒያሳ የሚለው ስም ተቀይሮ በአንድ የኦሮምኛ ስም ቢተካ ለኦሮሞ ህዝብም ቢሆን ትርጉም ያለው አይመስለኝም። ከተማይቱ ፊንፍኔ እንድትባል ሰዎች አሳብ ሲሰጡ እሰማለሁ። የየሰፈሩ ስም በኦሮምኛ መሆን አለበት የሚል ጥያቄ ግን አይሰማም። የኦሮሞ ህዝብ ስንት ግዙፍ ችግር እያለበት በስም ለውጥ ልቡን ማድረቅ በደል ነው። ይልቅ አንዳንድ አዳዲስ መንገዶች ሲሰሩ መንደሮች ሲሰሩ ስማቸውን በኦሮምኛ ብቻም ሳይሆን በሌሎችም ቋንቋዎች ቢሰየም ደስ ይላል። በአማርኛ በእንግሊዘኛ በጣሊያንኛ የተሰየሙ ቦታዎች እንደገና ቢቀየሩ የሚሰራው ያጣ መንግስት ሥራ ይሆናል ሥራው።  በአማራ ክልል አንዳንድ የኦሮሞ ስያሜ ያላቸው ቦታዎች አሉ፣ በደቡብ አንዳንድ የአማርኛ ስም ያላቸው ቦታዎች አሉ፣ በደቡብ የኦሮምኛ ስም ያላቸው ቦታዎች አሉ ወዘተ. ሃገሪቱ በቦታ ስም ለውጥ መታወክ የለባትም። ይህን ሁሉ እንዴውም የህብረታችን ጌጥ አድርገን ልናይ ነው የሚገባን። ይህን ካልኩ በሁዋላ ትንሽ ስለ ካሳ (Affirmative. Action ) ውይይት ልቀጥል።

በኢትዮጵያ ውስጥ እውነተኛ እኩልነትን ለማምጣት የተጎዳን መካስ በጣም ጥሩ መንገድ ነው። ይህ ጉዳይ ለብሄራዊ እርቅም መሰረት ነው። በርግጥ ሁሉም ቡድን ባለፉት ሥርዓቶች ተጎድቷል። ሁሉንም እንደየ ጉዳቱ መካስ ደግሞ ይቻላል። በአሁኑ ሰዓት ሃገራችን አፌርማቲቭ አክሽንን ተግባራዊ ማድረግ ከሚገባት መስክ አንዱ በኢኮኖሚና ማህበራዊ አገልግሎት አካባቢ ነው። እውነተኛ የአፌርማቲቭ አክሽን ከፈለግን የኢኮኖሚውን ያልተመጣጠነ የቡድን ሃብት ክምችት ነው ማየት ያለብን። እውን ይህ መንግስት ካሳ  ከፈለገ በህወሃት ሃብትና በኦህዴድ ሃብት መካከል ያለውን ልዩነት መመልከት ያስፈልጋል። የኦህዴድ ሃብትና የኤፈርት ሃብት ሲወዳደር ልክ አላሙዲንን አንድ በተለምዶ ሸምሱ ከሚባል ትንሽ ባለ ሱቅ ጋር የማወዳደር ያህል ነው። ግዙፍ የሃብት ልዩነት አለ። ደቡብ ደሞ በጣም ያንሳል፣ አፋር ጋምቤላ ሌሎች ብሄሮች ደግሞ ጨርሶ የላቸውም መሰለኝ።   አልማ ከህወሃት አይወዳደርም።  ይሄ ነው ማስተካከያ የሚሻው። ህወሃት ኦሮሞን ሊክሰው ካሰበ የአዲስ አበባ የሰፈር ስም በኦሮምኛ ሊሆንልህ ነው አይልም። ህወሃት ሌሎቹን ብሄሮች በመጫን ያከማቸውን ሃብት ወደ ብሄራዊ ሃብት ካዛወረ ነው ለኦሮሞ ህዝብ ትልቅ ካሳ። ኢትዮጵያን ከተደቀነባት አደጋ ለመታደግ አንዱ ትልቁ ርምጃ  ኢትዮጵያን ወደ አንድ የኢኮኖሚ ማህበረሰብነት መለወጥ ነው። ይህ በራሱ ብዙ ነገር የሚለውጥ ሲሆን በሂደት የተመጣጠነ የማህበራዊ አገልግሎት ማቅረብ ተገቢ ነው። መንግስት የያዝከው የተከፋፈለ ኢኮኖሚ የሃገርን አንድነት እያናጋ ለግጭት መንስኤ እየሆነ ነው ሲሉት ሽንጡን ገትሮ አንድ የኢኮኖሚና የፓለቲካ ማህበረሰብ ለመፍጠር እየሰራሁ ነው ይላል። አስቸጋሪ ነገር ነው የገጠመን በውነት። በሌላ በኩል    በህገ መንግስቱ ላይ መብታችን እስከመገንጠል ነው ይላል። ልክ የኢትዮጵያ ብሄሮች  እቃቸውን ሸክፈው  አንድ ቀን ብሽ ሲላቸው ለመበተን የተዘጋጁ አድርጎ ያሳያቸዋል። ኧረ ይሄ ነገር ጥሩ አይደለም ዲክተተር ብትሆኑ ይሻላል ይህን እስከ ሃቹ የሚጎዳንን ነገር እባካችሁ ሰርዙ  ሲባሉ አፍጠው መጥተው የአንድነታችን ዋስትና ነው ይላሉ። በጣም አስቸጋሪ ነገር ነው።

ምን ይሻላል?

አሁን ያለንበት የፓለቲካና የኢኮኖሚ ሁኔታ የኢትዮጵያን መስዋእቶች ሁሉ አጭዶ የበላ ነው። አንድ የኢኮኖሚና የፓለቲካ ማህበረሰብ ይፈጠር ዘንድ መሰረታዊው ነገር ቡድኖች ያሏቸውን የተፈጥሮ ሃብትና መሬት ኢኮኖሚ እውቀት ሁሉ ለኢትዮጵያዊነት መስዋእት ማድረግ አለባቸው። ይህን መስዋእት ማድረጋቸውን የሚያሳይ ለትውልድ የሚያሳልፉት አንድ አዲስ ኪዳን መግባትም አለባቸው። ይህ ኪዳን የሚይዘው ዋና ነገር የመስዋእትነት ጉዳይን ሆኖ ይህ ኪዳናቸው አንድ የኢኮኖሚና የፓለቲካ ማህበረሰብ ሆነው ጠንካራ የመኖሪያ አገራዊ ጠገግ እንዲመሰርቱ ያደርጋቸዋል። በመሆኑም የሚነሱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ይህንን የሃገርን የመስዋእት ጉዳይ ከፍ አድርገው ማሳየት አለባቸው። የአሁኑ የብሄር ፌደራሊዝም የሃገርን መስዋእቶች ሁሉ የዘረፈ ነው። የወሰድነውን መስዋእት እንመልስ። የተከፋፈለ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ እየፈጠርን እንደገና ለአንድነት እንሰራለን ማለቱን ትተን በጋራ ለአዲሲቱ የተባበረች ኢትዮጵያ መስራት አለብን። ኢትዮጵያውያን ሁሉ ነፍስ ሳይቀርላቸው ለሃገራቸው ያላቸውን መስዋእት አድርገው ጠንካራ አንድ የኢኮኖሚና የፓለቲካ ማህበረሰብ ለመፍጠር መነቃነቅ ወጣቶች መመካከር አለባቸው። ይህን ስናደርግ ሁላችንን የሚክስ ስርዓት እንፈጥራለን።

እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ

geletawzeleke@gmail.com

ኢትዮጵያ የሁሉም ኢትዮጵያዉያን እኩል ሀገር መሆን እንዲችል:- አዲስ አበባን እንደ ማሳያ – ሸንቁጥ አየለ

አዲስ አበባ ላይ እራሱ የወሰነዉን ዉሳኔ እና ረቂቅ ህግ እያለ የሚያሰራጨዉን ነገር በማራገብ በኢትዮጵያዉያን መካከል የጥላቻ መርዝ እንዲሰራጭ ወያኔ ደፋ ቀና እያለ ነዉ::

አዲስ አበባም ላይ ሆነ እሌሎች ጉዳዮች ላይ ወያኔ እየወሰነ ያለዉ ሆን ብሎ ህዝብን በሚያፋጅ እና ጸረ ኢትዮጵያዊነት በሆነ መልኩ ነዉ::ኢትዮጵያን ወያኔ በቅኝ ግዛት ስለያዛት ቅኝ ገዥነቱን በሚያጠናክር መልክ: ህዝቡን በሚለያይ መልክ እና በመጨረሻም ኢትዮጵያዉያንን እርስ በርሳቸዉ በሚያፋጅ መልክ ነገሮች እንዲሄዱ ይፈልጋል::

ምናልባት ኢትዮጵያ ከእጁ የምትወጣ ከሆነም በሚነሳዉ የርስ በርስ ጦርነት ድምጥማጧ እንዲጠፋ ወያኔ በደንብ አስልቶ የተነሳዉ ዛሬ አይደለም:: በተንኮል አማካሪዎቹ በኩል ወያኔ ህገ መንግስት ሲያረቅ ዛሬ የሚያናፍሰዉን ሁሉ አስልቶ እና አንሰላስሎ አስቀምጦታል::አሁን እያደረገ ያለዉ ነገሮችን ከተንኮል ጎተራዉ እየጎተተ ኢትዮጵያዉያን እርስ በርሳቸዉ እንዲጨራረሱ እና እንዲበጣጠሱ የጥላቻ ሊጡን ማጎብጎብ ነዉ::

ወያኔ ሌላዉ የመዘዘዉ ካርታ ኦህዴድ (ኦሮሞን ወክሎ) እና ብአዴን (አማራን ወክሎ) የአዲስ አበባን ጉዳይ በመወሰን ሂደት ዉስጥ እንዳሉበት ማስመሰል ነዉ:: እናም የወያኔ ካድሬዎች በደንብ አድርገዉ ይሄን ፕሮፖጋንዳ እያናፈሱት ሲሆን አንዳንድ የዋህ ሰዎች ደግሞ እዉነትም ኦህዴድ እና ብአዴን እዚህ ዉሳኔ ዉስጥ ያሉበት እየመሰላቸዉ የነዚህን ድርጅቶች ስም ሲያነሱ እና ሲጥሉ ይስተዋላል:: ሆኖም ኦህዴድ እና ብአዴን የሚባሉ የፈረስ እና የአጋሰስ ስብስቦች አዲስ አበባ እንዲህ ትሁን ወይም እንዲያ ትሁን እሚለዉ ዉሳኔዉ ዉስጥ እንዳሉ የሚመስላችሁ የዋህ ሰዎች እንዳትሸወዱ ማስገንዘብ እወዳለሁ:: ገና ኢትዮጵያን ከተቆጣጠረበት: ህገመንግስት እስከጻፈበት እንዲሁም እስካሁን ድረስ ሁሉንም ዉሳኔዉን እየሰጠ ያለዉ ብቸኛዉ ሀይል ወያኔ/ህዉሃት ብቻ ነዉ::

እናም ሁሉም ወገን ለዉጥ ከፈለገ እንዲሁም እዉነተኛ የህዝቦች ዘላቂ ሰላም ከፈለገ አንድ ነገር ላይ ብቻ ያተኩር::ወያኔን በማባረር እና ስሩን በመንቀል ላይ::ኢትዮጵያን ከወያኔ ቅኝ ተገዥነት ነጻ እማዉጣት ላይ::አዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን ሁሉም የኢትዮጵያ ምድር የሁሉም ኢትዮጵያዉያን እኩል ሀገር መሆን የሚችለዉ ወያኔ ሲነቀል ብቻ ነዉ:: ወያኔ በኢትዮጵያ ፍጅት እና የጎሳዎች እልቂት እንዲመጣ አንዱን አካባቢ የአንዱ ብቻ: አንዱን ቀብሌ የዚያ ንብረት ብቻ እያለ ተንኮል እየጎነጎነ የሚፈጥረዉን ተረት ተረት ተቀብለህ ማንኛህም ወገን አብረህ አትሩጥ:: የቱም አካባቢ የማንም ብቻ አይደለም::ኢትዮጵያ የሁሉም ኢትዮጵያዉያን እኩል ሀብት እና እኩል ሀገር ነች::

ወያኔ ሆን ብሎ ኢትዮጵያን በሰባት ክልል ከልሎ ሰባቱን ክልሎች ለሰባት ብሄረሰቦች አድሎ ሲያበቃ ሰማኒያ የሀገሪቱ ብሄረሰቦችን/ጎሳዎችን/ማህበረሰቦችን ሀገር አልባ አድርጓቸዋል::በወያኔ የሀገር ሽንሸና መሰረት አንድ ክልል ሲከለል ያክልል የአንድ ብሄረሰብ ሀብት እና ንብረት ይሆንን እና በዚያ ክልል የሚኖረዉ ሌላዉ ኢትዮጵያዊ ግን መጤ ወይም ሀገር አልባ ተደርጎ እንዲቆጠር ይደረጋል::በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ ከሚገኙት ሰማኒያ ሰባት ብሄረሰቦች ዉስጥ ክልል ያላቸዉ ሰባት ብቻ ሲሆኑ ሰማኒያ የሚሆኑት የኢትዮጵያ ብሄረሰቦች/ማህበረሰቦች/ጎሳዎች ክልል የላቸዉም::

ይሄም ማለት በወያኔ የደንቆሮ ፍች መሰረት እነዚህ ክልል የሌላቸዉ ሰማኒያ ብሄረሰቦች አገር የላቸዉም::ምክንያቱም በየትኛዉም ክልል ቢሄዱ የሚቆጠሩት መጤ ወይም ሀገር አልባ ተደርገዉ ነዉ::የወያኔ አስተሳሰብ በመሰረታዊነት ታላቅ የተስቦ በሽታ የተጠናወተዉ አስተሳሰብ ነዉ::በርካታ ኢትዮጵያዉያንን እየገደለ ያለ እና በመጨረሻም ኢትዮጵያዊነትን ስሩ እንዲነቀል ተግቶ የተቀመረ አስተሳሰብ ነዉ::

በመሆኑም የመጀመሪያ ተቃዉሞ የሚጀምረዉ የወያኔን ህገመንግስት ብሎም ህግጋት: የወያኔን ክልል: የወያኔን ዉሳኔ እና የወያኔን አስተሳሰብ በሙሉ ዉድቅ ማድረግ ነዉ::ወያኔ የሰራዉን እና የወሰነዉን ሁሉ በልብህ አፍርሰህ መነሳት አለብህ:: ተወደደም ተጠላም ወያኔ የሰራዉ እና የዘራዉ ሁሉ ይፈርሳልም: ይደመሰሳልም::የወያኔ መርዝ እና ካንሰራዊ አስተሳሰብ በሙሉ ይነቀላል::

ኢትዮጵያ የሁሉም ኢትዮጵያዉያን እኩል ሀገር መሆን የሚችለዉ መቼ ነዉ ብለህ መጠዬቅ ከቻልክ ብቻ ይሄን እዉነት ትደርስበታለህ:: ኢትዮጵያ የኢትዮጵያዉያን ሁሉ ሀገር እንድትሆን ወያኔን ንቀል::ከዚያም ሁሉም በጋራ አንዲት ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመስራት ወገብህን ጠበቅ አድርገህ ተነስ::ምርጫ የለም::ያለዉ ምርጫ አንድ ነዉ::ሁሉም እኩል አሸናፊ የሚሆንበትን ስልት እና ስትራቴጅ መንደፍ ነዉ::ይሄም ኢትዮጵያ የሁሉም ኢትዮጵያዉያን እኩል ሀገር መሆን እንዲችል ማድረግ::ለዚህም አንዲት ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመስራት በጋራ መነሳት::

ኢትዮጵያን እግዚአብሄር ይባርካት !

አማራ ወዳጆችን ማብዛት ፤ ባላንጣዎችንም መቀነስ የሚችለው በራሱ ጠንክሮ ሲወጣ ብቻ ነው! (መርከቡ ዘለቀ)

 በወቅቱ ባለው ተጨባጭ ሁኔታ በአማራ ህዝብ ላይ እጣታቸውን የሚቀስሩ ቡድኖች ብዙ  መሆናቸውን እየተመለከትን ነው፡፡ በእርግጥ  ህወሓትና ግብረ አበሮቹ የሀገር  ሀብት እስከ ዳር ደንበሯ እየዘረፉ ባለበት ዘመን ለሀገር ጠበቃ ሆኖ የተገኘ ሁሉ ጠላት  ሊበዛበት የግድ ነው፤ የሚጠበቅም ነው፡፡ ከአማራ ህዝብ ታሪካዊ ጠላቶች (ህወሓት፤ ሻብዕያና ኦነግ) በተጨማሪ የዛሬዎቹ ግንቦት 7 እና  ሀገራዊ ንቅናቂ ተብየው ቡድንም የአማራን ህዝብ የሚወክሉ ድርጅቶችን በአገኙት አጋጣሚ ሁሉ በማውገዝ ላይ ይገኛሉ፡፡

አሁን ግን እጅግ እየገረመንና እየመረረን የመጣው ግንቦት 7 የተባለው ሳያፈራ የጨነገፈው የምውታን ስብስብ የሚፈጥረው የማያባራ ንትርክ ነው፡፡ለዚህም ዋናው ምክንያት የግንቦት7 ከአሳዳሪዎቹ የተሰጠውን የቤት ስራ ለመስራት ሲል  ነው በአማራ ስም የተደራጁ ቡድኖችን በባላንጣነት የፈረጀው፡፡

ስለእውነት ግን  ግንቦት 7 ለምን በአማራ ስም የተደራጁ ቡድኖችን ያወግዛል? ለምን ጸረ-ኢትዮጵያና በኢትዮጵያ አንድነት ላይ የጠራ አቋም ከሌላቸው ቡድኖች ጋር አብሮ ለመስራት እየታተረ በኢትዮጵያ አንድነት ላይ የማይደፈርስ  አቋም ካላቸው የአማራ  ድርጅች ጋር መስማማት/አብሮ መስራት  ተሳነው?

እኔ ግንቦት 7ን  ባለፈው አንድ አመት ውስጥ ከሚያስተላልፋቸው ፕሮፓጋንዳዎች  አንፃር ስመለከተው ራሱን በራሱ እያጠፋ/እየገደለ (ስዊሳይድ እየፈጸመ) ያለ ድርጅት መሆኑን ነው፡፡ ይህ እሳቤ እውነት የሚሆነው ግን ግንበት 7ን እንደ ሀገራዊ ድርጅት አድርገን  ከወሰድነው ነው፡፡ አሁን አሁን ግን ግንቦት 7 አገራዊ ድርጅት መሆኑ ቀርቶ ዘረኛና ጸረ-ኢትዮጵያ ድርጅት መሆኑን እያስመሰከረ ነው፡፡ዘረኛነቱን ባወጣው የድርጅቱ ውስጠ ድንብ(ከአማረኛ በተጨማሪ ሌላ ቋንቋ ማወቅ አስፈላጊ መሆኑን የገለጸበት) በሚገባ ተገለጾ ይገኛል፤ ጸረ-ኢትዮጵያነቱም የሻዕቢያ ተላላኪ በመሆኑና  ከሌሎች ጸረ-ኢትዮጵያ ቡድኖች ጋር በጋራ ኢትዮጵያን ለማፍረስ በሚያደርገው አንቅስቃሴ ይገለጣል፡፡

ግንቦት 7 የህወሓትን መንግስት ማስወገድ(በህልሙ) የሚፈልገው ስልጣን ከህወሓት ወደ ግንቦት 7 ሰዎች በማሸጋገር ሌላ ዘረኛና የጥፋት ሰርአት ለመመሥረት እንጅ ሥር ነቀል  ለውጥ በኢትዮጵያ በማምጣት ሁሉም ዜጎች እኩል የሚስተናገዱባት ሀገር ለመፍጠር አይደለም፡፡ለዚህም ነው የህወሓትን በቋንቋ ላይ የተዋቀር ፌደራሊዝም እንዲቀጥል የሚፈልገው፤ ለዚህ ነው በዘር ላይ የተዋቀሩ ቡድኖችን ሲቀላቀሉ የህወሓትን ዘራኛ እና አግላይ  አስተዳደር የሚቃወሙ ቡድኖችን የሚኮንነው፡፡

ግንቦት 7 በቋንቋ ላይ የተመሠረተውን የወያኔ ክልላዊ አስተዳደር እንዳለ እቀበላለሁ ከሚልባቸው ምክንያቶች አንዱ  የግብረ አበሮቹን ፍላጎት ለማሟላት ሲሆን የእነርሱም ምኞት በህወሓት ዘርኛ መንግስት ከአማራ ህዝብ የነጠቁትን ሰፊ መሬት እንደያዙ በሂደት ለመሸሽ ነው፡፡ ነገር ግን በእውነት የግንቦት 7 ጥረቅሞች የፖለቲካ ሰዎች ናቸው ወይ? አስተማማኝ አጋሩን  አውግዞ  ከመሰናክሉ ጋር የሚዶልቱ፤ በአሜሪካ ውብ ሆቴሎች እየተንፈላሰሱ አረበኞች ነን እያሉ በአረበኛ ስም የሚቀልዱ፤ ስለ ኢትዮጵያ እንታገላለን እያሉ ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ዘንድ የሚሸጎጥ/የሚወተፉ፤ ጦር ሜዳ ሳይውሉ ነውጡን የፈጠርነው  እኛ  ነን እያሉ ያለ ሀፍረት በአደባባይ የሚዋሹ፤ ውጤት በሚስገኝ  ስራ ላይ ከማተኮር ይልቅ በየጊዜው የንትርክ መድረክ ያሚዘጋጁ፤ ስለ ኢትዮጵያ እንታገላለን እያሉ በጀግና ኢትዮጵያውያን ደም እና አጥንት ተለወሶ   የተጻፈውን የኢትዮጵያ ታሪክ  ኢሳት በተባለው ሚዲያቸው የሚያርክሱ ከሆነ  ግንቦት 7 ጤና የጎደላቸው ሰዎች  ስብስብ እንጅ ሌላ ሊሆን አይችልም፡፡ ምክንያቱም ግንቦት 7  የጤነኛ ሰዎች ስብስብ ቢሆን ኑሮ ጸረ-ኢትዮጵያ አቋሙን ለማራመድ እንኳ  አካሄዱን  ከአጋሮቹ ከወያኔ እና ከሻዕብያ ይማር ነበር፡፡ በአርግጥ ከኦነግ ሊማር  አይችልም ምክንያቱም ኦነግም ኢትዮጵያ ውስጥ ገብቶ አንድ ጥይት እንኳ ሳይተኩስ በለንደን ሆቴሎች እየተዝናና ኢትዮጵያን አናፈርሳለን   የሚል መናኛ  ድርጅት በመሆኑ፡፡ ኦነግ መፈክሩ ብቻ ሳይሆ የሚገርመው ህልሙን ለማሳካት የሚጠቀምበት  ስልት/ ስተራቴጅም ከንቱ ነው፡፡

ስለ እውነት ግን  አንድ ጥያቄ አለኝ፡፡ ከዚህ ጸረ-አማራ እና ጸረ-ኢትዮጵያ ከሆነው  ግንቦት 7 ድርጅት  ጋር አሁንም አባል ሁነው የሚደክሙ የአማራ ተወላጆች ካሉ እነርሱም  በእውነት አብደዋል ማለት ነው፡፡ እርግጥ ነው ከአንድ አመት በፊት ብዙዎቻችን ተሸውደን ነበር፡፡ ስለ ኢሳትና ግንቦት 7 በየቀኑ  ወሬ/ዜና  ሳንሰማ ከዋልን አንድ  ትልቅ ነገር እንዳመለጠን  ይሰማን ነበር፤ ስለ ግንቦት 7 ሲወራ የተስፋ ጭላንጭል ይታይን ነበር፡፡ የግንቦት 7ን  ድብቅ አጀንዳ በብዕራቸው ለተፋለሙና ላጋለጡ ውድ ኢትዮጵያን  ምስጋና ይግባቸውና  አሁን በግንቦት 7 ላይ የነበረው ተሰፋና መልካም ስሜት በሀገር ውስጥ ሙሉ በሙሉ በሚባል ሁኔታ  ላይመለስ ሙቶ ተቀብሯል፡፡ የሚቀጥለው ሥራ ግንቦት 7 እንደ ህወሓት ስረ ሰዶ/ገንግኖ ሳያስቸግር  በሁሉም መስክ መፋለምና ማጥፋት  ነው፡፡

የአማራን  ህዝብ ከጥፋት ለመታደግ ከእውነት እየሰሩ ላሉ ቡድኖች የማስተላልፈው መልክት የአማራ ህዝብ  ብዙ ወዳጆች እንዲኖሩትና የባላንጣዎቹም ቁጥር  እንዲቀንስ  ከተፈለገ  ብቸኛው አማራጭ  መንገድ አማራ  በራሱጠንክሮ  መውጣት አለበት የሚል ነው ፡ ባለፈው ሩብ ክፍለ ዘመን ማንም እየተነሳ የአማራን ህዝብ ሲያዋርድ፡ ሲዘርፍ፤ ሲያሳድድ፡ በግፍ ሲገድል ፤ ደም እና አጥነቱን የገበረበትን ታሪካዊ መሬቱን ሲነጥቀው የኖረበት ብቸኛው ምክንያት  አማራ ጠንክሮ ባለመውጣቱ/ባለመደራጀቱ  እንደሆነ ሁላችንም የሚያስማማ  አብይ ጉዳይ ሆኗል፡፡

ለዚህም ነው ተልካሻው ግንቦት 7 እንኳ ሳይቅር ያለ ምንም ሀፍረትና ፍርሀት ከ30 ሚሊዮን በላይ የሚሆነውን  የአማራ ህዝብ  እራስህን ከጥፋት ለመከላከል መደራጅት የለብህም  እያለ እያፌዘ  የሚገኘው፡፡ ይህ ትዕቢት ህወሓትና ሻዕቢያ ከሚያሳዩት ትዕቢትም በላይ ነው፡፡ ምክንያቱም ሁለቱ የአማራና የኢትዮጵያ ጠላቶች የትዕቢታቸው ምንጨ ለረጅም ጊዜ ማንም ሳይነቃ በወታደራዊ ኃይል መዘጋጀታቸው ብቻ ነው፡፡ ግንቦት 7 ግን በአውላላ ሜዳ ላይ የሚጮህ ከንቱ ሲሆን   ሌላውን ሊያጠቃ ይቅርና እራሱን ለመከላከል እንኳ የማይችል ቡድን ነው፡፡

ለመሆኑ ግን ግንቦት 7 በየትኛው አቅሙና ህጋዊ ሰውነቱ ነው የሌሎችን የመደራጀት መብት  ቻሪና ከልካይ የሆነው? ግንቦት 7 ውስጣዊ ማንነቱ ሻዕቢያና ወያኔ መሆኑ እየታወቀ ከግንቦት 7 ጋር አብሮ ለመስራት የሚመኝ የአማራ ድርጅትስ እንዴት ሊኖር ይችላል?  የግንቦት 7ም ሆነ የሀገራዊ ንቅናቄው ኢለማ አማራና ኢትዮጵያ ናቸው ፡፡ ለዚህ ነው ግንቦት 7 በሚያካሂደው  ስብሰባ ላይ ሁሉ በአማራና በኢትዮጵያ ታሪክ  ላይ የሚዘምተው፡፡

ግንቦተ 7 አማራንና ኢትዮጵያን ለማጥቃት ከሚጠቀሙባቸው ስልቶች አንዱ ሰርጸ ደሰታ እንደገለፀው “የወያኔ  የክትሰዎችን” በመጠቀም ነው ፡፡ ለዚህም ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማሪያምን በሲያትል ስብሰባ ተገኝተው ያደርጉትን  የወረደ ንግግር  እንደምሳሌ መውስድ እንችላለን፡፡ ግን ስለ እውነት እንነጋገረ ከተባለ ፕሮፌሰሩ አሁን ኢትዮጵያ በታሪኳ  አይታው የማታውቀው ቀውስ ውስጥ በገባችበት ወቅት  ስለ ኢትዮጵያ አንድነት፤ ስለመተሳሰብና በጋራ  ስለመስራት ነው መስበክ/መናገር ያለባቸው  ወይስ ሊያግባቡ በማይችሉ  ጉዳዮች ላይ? አጼ ቴዎድሮስ ያለ ጊዜያቸው የተፈጠሩ ታላቅ መሪ መሆናቸው እየታወቀ አፄ ቴዎድሮስ ከህዝቡ ጋር አልተግባቡም  ነበር ማለት ከፕሮፌሰሩ የሚጠበቅ የወቅቱ ንግግር ነው ወይ? ኢትዮጵያ  ከሁሉም ብሄር ብሄረሰብ ከተውጣጡ ጀግና እና አረበኛ  ልጆቿ ተከብራ የኖረች ሀገር መሆኗ እየታወቀ ጀግናው በላይ ዘለቀ ጎጃሜ ቢሆንም ማንነቱ ኦሮሞ ነው ማለት በእውነት እንኳስ የፕሮፌሰር ንግግር ሊሆን ቀርቶ ፌደል ያልቆጠረ ሰው  እንኳ ሊናገረው ይገባል ወይ?

ሰረጸ ደስታ  ሰለ ኦረሞ ደጋግሞ እንደገለጸው  አሮሞ እኮ የራሱ ጀግና አላጣም ነበር፤  ችግሩ  ጀግኖቹን ሁሉ የነፍጠኛ ወዳጆች ናቸው ብሎ በመካዱ ባዶ እጅኑ  መቅረቱ ነው ፡፡ እንበልና ጀግናው በላይ ዘለቀ ኦሮሞ ነው ብለን ብንቀበላቸው ፕሮፌሰሩ ምን ይፈጠር ነው የሚሉን? አማራ ጀግና  የለውም ለማለት ከሆነ ፈጽሞ  አያስኬድም፡፡ በእውንት አንድ ስሙን ለጊዜው የማላሰታወሰው ወንድሜ ስለ ፕሮፌሰሩ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በለጠፈው ጽፍ ለጽሁፉ የሰጠው ርዕስ “መገለባበጥ እንደ—— መክሸፍ እንደ ፕሮፌሰር መስፍን” የሚል ነበረ፤ እውነት ነው በጣም ከሽፈዋል ፕሮፌሰሩ፡፡

በነገራችን ላይ ስለ ኮሌኔል መንግስቱ ኃይለማሪያምና የወታደራዊ መንግስት የውድቅት መንስኤዎች በሚያትት መጽሃፍ ላይ እንዳነበብኩት መንግስቱ ኃይለማሪያም እጅግ ካዘነባቸው ምሁራን መካከል ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማሪያምና ደ/ር ኃይሉ አርአያ ይገኙባቸውል፡፡ መንግሰቱ ኃይለማሪያም እንደሚለው ወያኔ 1983ዓ.ም ሰሜን ሸዋ በደረሰበት ወቅት ምሁራኑ ለኢትዮጵያ አዋጭ መንገዶችን ከማቅረብ ይልቅ ለወያኔ አስተዋፆ በሚያደርጉ ጉዳዮች ላይ ማተኮራቸውን በማንሳት በወቅቱ  እንዳዘኑባቸው አንብቢያለው፡፡

ስለዚህ ግንቦት 7 የወያኔን የክፉ ቀን ልጆች ከየቦታው እየመዘዘ ለመጠቀም የሚያደርገው ትርፍ የማያስገኝ አካሄድ ውድቀቱን ከማፋጥን ውጭ  ሌላ ትርፍ አያስገኝለትም ፤ ስልቱ ተነቅቶበታል፤ የክት ሰዎችም እነማን እንደሆኑ  እየታወቀ ነው፡፡

ሌላው ላለፈው 40 ዓመት ሙሉ ኢትዮጵያን ለማፈረስ የሻዕብያና ወያኔ አሽከር ሆኖ ሌት ከቀን ሲሰራ የኖረውና አሁንም ከዚህ ነውረኛ ሰራው ያልታቀበው አቶ ሌንጮ ለታ በሲያትሉ ስበሰባ “ የኢተዮጵያ ጉዳይ ያሳስበኛል” ሲል የምጸት ንግግር እንዳደረገ አነበብን፡፡ ይገርማል!  ስለ አቶ ሌንጮ ለታ  ምንነት አቶ ሰርጸ ደስታ በሚያስደት ሁኔታ የገለጸው ስለሆነ መድገም አያስፈልገም፡፡ ዶ/ር ብረሀኑ ነጋም የአሻንጉሊቶችን ስብስብ (ሀገራዊ ንቅናቄ ተብየውን) ኢትዮጵያን የሚመጥን ድርጅት ነው በሚል ያደረገውን ንግግር እንዲሁ በድረ ገጽ አነበብን ፡፡ በእውነቱ ኢትዮጵያን የሚወክለውና የሚመጥነው ኢትዮጵያን ለማፈረስ ሲጥር የኖረውና አሁንም ኢትዮጵያ ብሎ መጥራት የሚጸፈው፤ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓለማ ሲያይ የሚበረግገው  የሌንጮ ለታ  ድርጅትና የሻዕቢያ ተላላኪ የሆነው  የግንት 7 ድርጅት በአንድ ላይ የመሠረቱት የጥፋት ቡድን እንዴት ነው ኢትዮጵን የሚመጥነው?   ምን አልባትም በውስጥ ወይራ  ንግግር  ደ/ሩ ማለት የፈለገው  ኢትዮጵያን ለማፍረስ አቅም ያለው ጸረ-ኢትዮጵያ ድርጅት መሥረተናል ለማለት ሊሆን ይችላል፡፡ ይኸኛውም  ሀሳብ ቢሆን ሊሳካላቸው  የሚችል አይደለም፡፡

ኢትዮጵያ እጅግ የምትገርም ሀገር ናተ፡፡ በክፉ ቀን ከጎኗ ተሰልፈው መሰዋት የሚከፍሉ እንዳሉ ሁሉ ችግር በገጠማት ቁጥር ከቅጥረኞች ጋር በማበር ያለማንም  ተከላካይ የቡድን ጥቅማቸውን ለማሳካት የሚሮጡ  ብዙ ናቸው፡፡በተለይ በአሁኑ ወቅት ከዘረኛው ህወሓት ትግሬ በተጨማሪ  ኦነግና ግብረ አበሮቹ አሁን እየሰሩት ያለው የቆሸሸና ታሪክ ይቅር የማይለው ጥፋት ይህንኑ ነው፡፡ ከመላው ኢትዮጵያውያን ጋር በመተባበር የሁሉም ጠላት በሆነው በወያኔ ላይ ክንዳቸውን ማንሳት ሲገባቸው እንገነጠላልን፤ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊነት እንዲሁም  በባንዲራዋ ላይ መደራደር ይገባናል ይሉናል፡፡ ሀገረ ውስጥ ያለው የህወሓት ቡችላ  ኦህዴድም በአዲስ አበባ ላይ እየሰራ የሚገኘው ሴራ ከኦነግ  ጋር በመተባበር ነው፡፡ ለመሆኑ ግን ከሃዲውና ዘራፊው ወያኔ ያለማንም ተከላካይ የሚተላልፈው የክህደት ውሳኔ ተቀብሎ የሚኖር ህዝብ ሊኖረ እንደማይችል እንዴት ኦህዴዶች/ኦነጎች መረዳት ተሳናቸው? ኦህዴዶች እና ኦነጎች የሸዋ  ኦሮሞ ጀግኖችን እያዋረዱ ለምን በአዲስ አበባ ላይ መስገብገብ አበዙ? የሸዋ ጀግኖችን  ከጠሉ ጀግኖቹ ከሌላው ወገናቸው ጋር ተባብረው የመሠረቷትን ከተማ ለምን ይፈልጓታል?  ግለሰቡን ከጠሉ ንብረቱን መመኝት አያስኬድም፡፡ የኦህዴዶችና ኦነጎች ዘዴ ግልጽ ነው፡፡ የገቢያ ግርግር ለሌባ ይመቻል እንደሚባለው የወቅቱን የፖለቲካ  ቀውስና የአማራን አለመጠናከር ተጠቅመው አዲስ አበባን  በግርግር ለመንጠቅ  ነው፡፡ የወያኔ ስልትም እንዲሁ  ግልጽ ነው፡፡ የአማራን የትግል አቅጣጫ ማስቀየርና ጠላቱንም ማብዛት ነው፡፡

 

ወደ ማጠቃለያ መልክቴ ስመለስ በአማራ ስም ተደራጅታችሁ አማራን  ከጨርሶ መጥፋት ለመከላከል   እየተንቀሳቀሳችሁ የምትገኙ ቡድኖች ሁሉ መረዳት የሚገባችሁ አብይ ጉዳይ  አማራ  ከፍተኛ  ፈተና ውስጥ የገባ መሆኑን ተርድታችሁ ይህን ከፍተኛ ፈተና በአሸናፊነት ለማለፍ በአንድነትና በጽናት በመቆም  ቆራጥ እና  ሀገር ወዳድ ወገናችሁን ማደራጀትና ወደ ትግል መምራት ይኖርባችኋል፡፡ እያንዳንዱ አማራም በሀወሓት ትግሬና በግበረ አበሮቹ  የተገፈፈውን ነፃነቱን ለማስመለስ የትኛውንም አይነት መሰዋትነት ለመክፈል ዝግጁ  መሆን ይኖርበታል፡፡ ልጆቻችን  በኢትዮጵያ እንደዜጋ  ተከብረውና መብታቸው ተጠብቆ እንዲኖሩ ከፈለግን እኛ  መሰዋት ልንከፍል የግድ ነው፡፡  ማለፋችን ላይቀር ስደትንና ውርደትን ልጆቻችን አውርሰን ማለፍ የለብንም፡፡

 

ድል  ለኢትዮጵያ!

የማለዳ ወግ… ይድረስ ለሚመለከታችሁ ባለስልጣናት (ነቢዩ ሲራክ)

ነቢዩ ሲራክ

* ለአንባሳደር አሚንና ለአንባሳደር ውብሸት ባላችሁበት
* ቅጅ /ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶር ወርቅነህ ገበየሁ

መረጃን ማቀበሌ ወንጀል ሆኖ “የነቢዩ ሲራክ ልጆች ከሚማሩበት የጅዳ ኮሚኒቲ ትምህርት ቤት እንዲታገዱ” የሚለው የካድሬዎች ሀሳብ ያን ሰሞን ቀርቦ እንደነበርEthiopian immigrants in Saudi Arabia በድጋሜ በማረጋገጤ አዝኘ ነበር ያደርኩት ። … ስለ እውነት ለመናገር ፣ ስለ እውነት እየተገፉ መኖር ግድ ይላል ብዬ የሚሰራው ባይደንቀኝም በዘመነ ኦሪት እንኳ ባልታዬ ህግ ልጆች በአባታቸው ” ወንጀል ” ስማቸው ሲጠራ መስማት ልቤን በሀዘን ሰብሮት አድሯል 😦 እናም ሁሉንም ለመርሳት ልጆቸን እረፍት ወደ ማይሰማ ወደ ማይናገረው ቀይ ባህር ይዣቸው ዘና ልበል ብዬ ማልጀ ስነሳ ሌላ አሳዛኝ መረጃ ደረሰኝ ። መረጃው እንዲደርሰኝ ያደረገው ደግሞ አንድ አደር ባይ ወዳጄ ነበር ፣ ወዳጄን እኔን ያመመኝ አሞት ስለማያውቅ የዜጎች ጉዳይ አግብቶኝ የተገፊውን ድምጽ ሳሰማ ” ሥራ ፈት ነህ !” እያለ ያላግጥብኝ ነበር። ዛሬ ግን የራሱ የሆነች እህት በሪያድ አየር መንገድ ለቀናት በደረሰባት እንግልት ተደናግጦ” አገር ይያዝ” ጩኸት አሰማኝ ። ቀጠለና ዜጎች እየተሰቃዩ ነው የታላችሁ በማለት ከጅዳ ቆንስል እስከ ሪያድ ኢንባሲ ሹም ወዳጆቹን ጨምሮ መረጃውን እኔው ጋር አድርሶታልና አዘንኩ … ደጋግሞ ሲደውልልኝና መረጃ ሲሰጠኝ ዝም ብየ ሰማሁትና ለመሆኑ እኔ ስናገር ሥራ ፈት እያልክ አልነበር? ዛሬ ችግሩ በዘመድህ መጥቶ መናገር መናደድ ጀመርክ? እስከ አሁንስ የት ነበርክ ? ማለቴ አልቀርም ። እሱ ግን አፈረ ፣ እኔም ያፈረውን አድርባይ ወዳጄን መጎሻሸሙን አልወደድኩትም …በወዳጄ ዛሬ መቆርቆር አላዘንኩም የሰጠኝን መረጃ ተከትዬ ያሰባሰብኩት እውነት ግን በእርግጥም ያስከፋል ። ይህን መልዕክት እንድጽፍ ላችሁ ያነሳሳኝ ጉዳይም ይኸው የደረሰኝ መረጃ ነው ።

ላለፉት ሶስት ወራት ሌት ተቀን ግሩም በሆነ ዝግጅት የከረመው የኢንባሲና የቆንስል መረጃ ቅበላ በመቋረጡ የተከተለውን ውዥንብር እንደ ዜጋ ታዝቤያለሁ ። የኢንባሲና የቆንስል መረጃ ቅበላ በማቆሙም ቦታውን ባልተካም በመረጃ እጦት ስደተኛው እንዳይንገላታ ባሳለፍናቸው ሁለት ሳምንታት የምችለው ለማድረግ ሞክሬያለሁ ። አሁንም የምቀጥለው በዚሁ መንፈስ ነው … የኢንባሲና የቆንስል ለመረጃ የተዘጋው በር ከተከፈተ እኔ ብዙም ላይክና ሸር ፈላጌ ዝር ላልል ቃል ልግባላችሁ ! ብቻ ለዜጋው መረጃ ያስፈልገዋልና የተዘጋውን በር ክፈቱለት ለማለት ለመማጸንና ለመምከርም ጭምር ነው ።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ችግር በጅዳና በሪያድ አየር መንገዶች እየተንገላታ ያለው ሰው ለቅሶ ዛሬም ደርሶኛል። በምህረት አዋጁ መራዘም ዙሪያ በሚናፈሰው መረጃ ለሚዋልለው ዜጋ እያደረጋችሁ ያለውን ጥረትና እውነቱን አስረዱት። “የምህረቱ ጊዜ አብቅቷል!” ተብሎ በሳውዲ ፖስፖርት ፖሊሶች እንዳይሳፈሩ መመለስ ስለመጀመሩ ጉዳይ ግልጽ መረጃ ከእናንተ ይጠበቃል። ከቀናት በፊት በጀዛን ትናንት ደግሞ በጅዳ አንዳንድ ተመላሾች ” የምህረቱ ጊዜ አብቅቷል !” ተብለው በፖስፖርት ፖሊሶች እንዳይሳፈሩ ተከልክለው እንደነበር ከጅዳ ቆንስል ኃላፊዎች በግል መረጃውን አረጋግጫለሁ። በዚህና በዚያ በተለያዬ አቅጣጫ የሚሰማው መረጃ ብዙዎችን ግራ እያጋባ ይገኛል ።

በሚሰራጩት መረጃዎች ፣ እየተደረገ ስላለው ጥረትና ተዛማጅ የተመላሽ ዜጎች ጉዳይ በሳውዲ የኢትዮጵያ መንግስት ተወካዮች በምህረት አዋጁ ወቅት ያደርጉት እንደነበረው ሳያቋርጡ መረጃን ሊሰጡ ይገባል የሚለው የብዙ ወዳጅ ተከታዮቸ መልዕክት ነው ። በእርግጥም ወቅታዊ መረጃን ሲሰጡ ከርሞ አሁን በወሳኙ ጊዜ ማቋረጥ በመቶ ሽዎች የሚቆጠር ዜጋ ብቻ ሳይሆን በመላ አለም ያለው ሚሊዮን ሀገር ወዳድ እንዳይረጋጋ ያደርጋል ። በውል የተጠና የመረጃ ቅበላው ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል። በሪያድ የኢትዮጵያ ኢንባሲ እና የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት በወሳኙ ጊዜ ያቋረጣችሁትን የመረጃ ቅበላ ትቀጥሉ ዘንድ እመክራለሁ ! በየአየር ማረፊያዎች ቀንና ማታ ቀርቶ ለሰአታት መቋቋም በሚከብደው ደረቅ ሀሩር ጸሃይ ሙቀት እየተለበለበ ያለው ወገን ያለበትን ሁኔታ መከታተልና መደገፍ ፣ መረጃ ፣ ማብራሪያ በሉት ምክር ካስፈለገ በቦታው እየተገኙ መስጠት ተገቢ ነው እላለሁ !

ይህን ምክር እንድጽፍ ያነሳሳኝ መታበይ እንዳይመስላችሁ ። በቂ ምክንያት አለኝ ” ላለፉት ሶስት ቀናትበሪያድ አየር መንገድ አውላላ ሜዳ ላይ ተሰቃየን ” በሚል የሚደርሱኝ መረጃዎች እጅግ ውስጥን ይረብሻሉ 😦 እናንተም በዚህ ዙሪያ ምንም አይነት ወቅታዊ መረጃ ስለማታቀርቡ በእንግልት ላይ ያሉ ዜጎች የመረጃ እጦት ሌላ ፈተና እንደሆነባቸው መረዳት ችያለሁ ! እባካችሁ ዜጎች መረጃን ከእናንተ ከህዝብና መንግስት አገልጋዮች የማግኘት መብታቸውን አለንና እሱኑ መብት አክብሩልን !

የግርጌ ማስታወሻ

ለወዳጆቸና ለተካታታዮቸ ፣ ይህ መልዕክት ለኃላፊዎች እንዲደርስ  Share እና Like ማደረጋችሁን አትዘንጉ ፣ ሁላችንም ስለተገፉት ዜጎች ድምጽ መሰማትና መፍትሔ ማግኘት መትጋት ግድ ይለናል !

ከአክብሮት ሰላምታ ጋር

ነቢዩ ሲራክ
ሰኔ 21 ቀን 2009 ዓም

የሀይል አሰላለፉ ጎራው ሲፈተሽ [ቬሮኒካ መላኩ] – “የኦሮሞ ብሔረተኝነት ፖለቲካ ከሌለ የትግራይ ህዝብ አደጋ ላይ ይወድቃል” ገብሩ አስራት 

[ቬሮኒካ መላኩ]

“የኦሮሞ ብሔረተኝነት ፖለቲካ ከሌለ የትግራይ ህዝብ አደጋ ላይ ይወድቃል”
ገብሩ አስራት 

ይሄን ከዚህ በላይ የተፃፈውን የተናገረው የቀድሞው ታጋይ እና የህውሃት ማእከላዊ ኮሚቴ አባል የነበረው ገብሩ አስራት ነው ።
በሌላ በኩል የቀድሞው የኦነግ ሊቀመንበር አቶ ሌንጮ ለታ ከሁለት ወር በፊት ከOMN ጋር ባደረገው ቃለምልልስ ላይ የ OMN ጋዜጠኛ :
<< ኦነግና አንተም በግልህ ረጅም አመታት ታግላችሁ ለኦሮሞ ህዝብ ያመጣችሁት ለውጥ አለ ብላችሁ ታስባላችሁ ወይ? >> በማለት ሲጠየቀው አቶ ሌንጮ ቃል በቃል እንደዚህ በማለት መልሶ ነበር
<< ሀሌ ሉያ! የኦሮሞ ህዝብ እኛ ካሰብነው ከገመትነው በላይ ግዛት ያለው ክልል አግኝተናል ። ይሄ ትልቅ ስኬት ነው ።>> በማለት መልሷል ።

ዛሬ ይችን እጅግ አጨር ማስታወሻ ለመፃፍ የፈለኩት በተለይ ለአማራ ብሄርተኞች አሁን ያለውን የፖለቲካ ቡድኖች ያለውን የሀይል አሰላለፍ በመገንዘብ ትግላችንን መረር አድርገን እንድንየዘው ለማስታወስ ነው።

ወያኔ የአናሳ ( Minority) ቡድን ነው ።ማንኛውም አናሳ ቡድን ስልጣን ላይ ለመቆየት ዜዴ ያስፈልገዋል። አንዱ ዜዴ ጠመንጃ ነው ጠመንጃው አልሆን ሲል ከብዙሃን ጋር በመጣበቅ ነው ።
ህውሃትና የኦሮሞ ብሄርተኞች በፖለቲካ የሀይል አሰላለፍ ብዙ ጊዜ ተመጋጋቢ ናቸው። ህውሃት የኦሮሞ ብሄርተኞችን እንደ ስትራቴጅካል አጋር ሲወስደው በአንፃሩ የኦሮሞ ብሄርተኞች በህውሃት እየተገደሉም ወደ እስር ቤት እየታጎሩም ቢሆን ከህውሃት በሚወረወርላቸው የፖለቲካ ቅንጥብጣቢ በመርካት ህውሃትን እንደ ስልታዊ አጋር ይመለከቱታል ።

በዚህ የሃይል አሰላለፍ ውስጥ ሁለቱን ቡድኖች በዚህ ያልተቀሰ ጋብቻ ያቆራኛቸው እንደ አደጋ የሚቆጥሩት የአማራ ህዝብ ነው ። እነዚህ ቡድኖች በአይነ ቁራኛ እና በጠላትነት የሚመለከቱት የአማራን የፖለቲካ ሀይል ነው ። በህውሃት በኩል የኦሮሞ ብሄርተኞችን የሚጠቀምባቸው እንደ ስልጣን እድሜ ማራዘሚያ የፖለቲካ ኪኒን ሲሆን በኦሮሞ በኩል ከህውሃት የሚወረወረው ቅንጥብጣቢ እስካልቆመ ድረስ ህዝባቸውን የሚመጥን የአገርን መሪነት ቦታ የሚፈልጉ አይመስልም ። የኦሮሞ ብሄርተኞች በኢትዮጵያ ለሚደረግ ስር ነቀል ለውጥ አጋር ሊሆኑ አይችሉም ። የእነሱ ፍላጎት ስርአቱን በጥገናዊ ለውጥ እንድያደርግ በመርዳት በሂደቱ የፖለቲካ ትርፍራፊ መለቃቀም ነው።

በፖለቲካ አለም አንድ የተለመደ አባባል አለ “በፖለቲካ ውስጥ ዘላቂ ጥቅም እንጅ ዘላቂ ወዳጅም ሆነ ዘላቂ ጠላት የለም ።” ይባላል ። ይሄ አጠቃላይ የሆነ መርህ (General Principle) አሁን ባለው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ለአማራ ህዝብ የሚሰራ አይመስለኝም። ወያኔ ለአማራ ህዝብ ዘላቂ ጠላት እንጅ ጊዚያዊ ወዳጅ መቼም ሊሆን አይችልም ።

በዚህ የሃይል አሰላለፍ ለጊዜው አማራው ብቻውን ነው።

አማራው ምን ማድረግ አለበት? 
አማራ አሁን ካለው የፖለቲካ ንቃት በተጨማሪ እንደ እሳት የሚንቀለቀልና አስፈላጊ ሲሆን እንደ ቮልካኖ የሚፈነዳ ብሄርተኝነት ማዳበር አለበት።

ጀርመናዊው የማህበረሰብ ፈላስፋ Max Weber << The future will be an Iron Cage> > እንዳለው ወደ ፊት ከጠላቶቹ ጋር በዚህ ተመሳሳይ የጉስቁልና እና የጨቋኝ ተጨቋኝ ድራማ የሚያበቃበትና ለውጥ አስፈላጊ መሆኑን በመረዳት፤ ከለውጡ ቅኝት ጋር ተስማሚ የሚሆን አቋም በመያዝ፤ ለለውጥ ፈላጊው የአማራ ህብረተሰብ ጥያቄ ምላሽ በሚሰጥ አኳኋን ራሳችንን አስተካክለን በመሄድ፤ በፖለቲካዊ ግጭት ምክንያት ሊፈጠር የሚችልን አደጋ በመቀነስ ብሎም በአሸናፊነት ለመወጣት ዝግጁ ሆኖ መጠበቅ ነው።

የመቶ አለቃ ጌታቸው መኮንን “ነፃ” ነት

ከማህሌት ፋንታሁን*
መቶ አለቃ ጌታቸው መኮንን በአማራ ክልል፤ ምዕራብ ጎጃም ዞን የመኢአድ ፓርቲ ዋና ጸሀፊ ነበር። ከዚህ በፊት በ1989ዓ.ም‹‹የመአድ አባል በመሆን መንግስት ለመገልበጥ ሞክረሃል››በሚል ከነፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ጋር ተከሶ 20 ዓመት ተፈርዶበት፤በአመክሮ 14 ዓመት ከ6 ወር ታስሮ በ2003 ዓ.ም ነበር የተፈታው፡፡ በእስር ሳለም ‹‹ከእስር ቤት ልታመልጥ ሞክረሃል›› ተብሎ በጥይት እግሩን ተመቶ ለረጅም ጊዜ ይሰቃይ ነበር። ከተፈታ ከአራት ዓመታት በኋላ፤ በ2007ዓ.ም በጥቅምት ወር መጨረሻ ላይ ከታሰሩት በአማራ ክልል የሚገኙ 16 የመኢአድ፣ የአንድነት እና የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች አንዱ ነው። በአሁኑ ሰአት እድሜው 48 የደረሰው መቶ አለቃ ጌታቸው፤በእስር ላይ እያለ የልጅ አባት ሆኗል:: መቶ አለቃ ጌታቸው ከታሰረ ከአንድ አመት ከስምንት ወራት እስር በኋላ ጉዳዩን የሚከታተለው የከፍተኛው ፍርድ ቤት 4ኛ ወንጀል ችሎት ሰኔ 9/2009ዓ.ም ቀን በሰጠው ብይን”ነፃ” ተብሎ ዳግም ከ”እስር” ተፈቷል።

የክሱሒደት
በመዝገቡ 1ኛ ተከሳሽ የሆነው መቶ አለቃ ጌታቸው መኮንን ከሌሎቹ 15 የተቃዋሚ አመራሮች ጋር ‹‹የአርበኞች ግንቦት 7 አባላት ናችሁ›› ተብለው የፀረ ሽብርተኝት አዋጁን አንቀፅ 7(1)ን በመተላለፍ በሚል ክስ ተመስርቶበታል። ከአራት ወር በላይየማዕከላዊ የስቃይ ቆይታ በኋላ ግንቦት 18/2007 ፍርድ ቤት ቀርቦ የተነበበለት ክስ የአርበኞች ግንቦት 7 አባል በመሆን የፀረ ሽብር ህጉን አንቀፅ 7(1)ን በመተላለፍ፡
"ከጥቅምት ወር 2004 ዓ.ም ጀምሮ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ(አዴኃን) አባል በመሆን 
እንዲሁም ጥር ወር 2006 ላይ በሑመራ በኩል  ኤርትራ እንዲገባ እና ከሽብር ድርጅቱ ጋር እንዲቀላቀል
 የቀረበለት ጥያቄ በመቀበል በየካቲት ወር 2006 የሽብር ድርጅቱን በአባልነት በመቀላቀል፤ ከባህር ዳር
 ከተማ በመነሳት ወደ ኤርትራ በመሄድ ከሽብር ድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች 
ጋር በመገናኘት የሽብር ድርጅቱ አባል በመሆን፤ ከዛም ወደ 
ኢትዮጵያ በመመለስ አባላትን መልምሏል።"

የሚል ነው። አቃቤ ህግ ክሱን ያስረዳልኛል ብሎ ያቀረበው ማስረጃ በማዕከላዊ የሰጠውን 10 ገፅ የእምነት 
ቃል እና ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት ቢሮ የቀረበ የስልክ ልውውጥ ብቻ ነበር።"
መቶ አለቃ ጌታቸው ማዕከላዊ ከመምጣቱ በፊት የነበረበት ደህንነት ቢሮም ሆነ ማዕከላዊ ከባድ ድብደባ ተፈፅሞበታል፡፡ ማዕከላዊ እያለ ብልቱ ላይ ሁለት ሊትር ‹የሃይላንድ ውሃ› አስረውበት መርማሪዎች አድርገሃል ያሉትን እንዲያምን ያሰቃዩት እንደነበረ፤ በዚህም ብልቱ እንደቆሰለ እና ሕክምና እንዳያገኝ ተከልክሎ እንደቆየ ግንቦት 18/2007 ቀን ክሱ በችሎት የተነበበ ቀን ለዳኞች አስረድቷል። በድብደባ የደረሰበትን አደጋ ለማሳየት ዳኞችን ሲጠይቅ በመከልከሉ ሱሪውን አውልቆ ብልቱ ላይ ያለውን ቁስለት ለዳኞችና ችሎቱን ለታደሙ ማሳየቱና ዘሩን መተካት እንዳይችል መደረጉን መናገሩ የሚታወስ ነው። ከማዕከላዊ ወጥቶ ቂሊንጦ ከተዛወረ በኋላ ለመንቀሳቀስ እጅግ ይቸገር እንደነበር ይናገራል፡፡
ፍርድ ቤቱ ሰኔ 21 ቀን 2008 ዓ.ም ቀን በዋለው ችሎት የቀረበበትን ክስ እንዲከላከል በተበየነው መሰረት አራት የሰው ምስክሮችን አስደምጧል። ምስክሮቹ መቶ አለቃ ጌታቸው መኮንን ማዕከላዊ እያለ ለፓሊስ የሰጠው ቃል በግዳጅ መሆኑን ለፍርድ ቤቱ ያስረዱ ናቸው።
ጉዳዩን የሚከታተለው የከፍተኛው ፍርድ ቤት 4ኛ ችሎት ዳኞች የጥፋተኝነት ፍርድ ሰኔ 9/2009 ቀን ባሰሙ ወቅት መቶ አለቃ ጌታቸውን በተመለከተ ያነበቡት ብይን በአጭሩ እንዲህ የሚል ነው
"ተከሳሹ በማዕከላዊ እያሉ አካላቸው [ብልታቸው ለማለት ነው። ዳኞች የአካሉን ስም እንደማይጠቅሱ ተናግረዋል።]
 በድብደባ የተጎዳ መሆኑ እና በዛ አካላታቸውም መገልገል እንደማይችሉ ፍርድ ቤቱ እየከለከላቸውም ቢሆን በችሎት 
ያሳዩት ጉዳይ በመሆኑ፤ ከፊሎቹ መከላከያ ምስክሮችም አብረዋቸው በማዕከላዊ ‹ሳይቤሪያ› የሚባለው ጨለማ ክፍል 
የነበሩ ሲሆን ብልታቸው ላይየደረሰውን መቁሰልያዩ እናበድብደባ ሳቢያ ‘ከምትሞት የሚሉህን ፈርም‘ ብለው የቀረበበትን
 ክስ አምኖ ቃል እንዲሰጥ መምከራቸውን የመሰከሩ በመሆኑ እንዲሁም የተቀሩት ምስክሮች በማዕከላዊ ለመከሰስ
 የሚዘጋጁ እስረኞች በሚቀመጡበት ‹ሼራተን› ክፍል ተከሳሹን ያገኙት መሆኑን ገልፀው ‘ከምሞት ብዬ ያሉኝን 
ፈረምኩ‘ ብሎ እንደነገራቸው በመመስከራቸው"
በማዕከላዊ የሰጠው ቃል በግዳጅ እንደሆነ የሚያሳይ ነው በማለት አቃቤ ህግ ያያዘውን የመቶ አለቃ ጌታቸው ቃል ውድቅ እንዳደረጉት ገልፀዋል። ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት ቢሮ የቀረበው ማስረጃን በተመለከተ ፍርድ ቤቱ፡”ከኤጀንሲው የቀረበው ማስረጃ ላይ የስልክ ልውውጡ የተደረገበት ስልክ ባልተጠቀሰበት ሁኔታ” የስልክ ልውውጡ መቶ አለቃ ጌታቸው ያደረገው ነው ለማለት እንደሚያስቸግር በመግለፅ፤ አቃቤ ህግ ያቀረበበትን ማስረጃ በበቂ ሁኔታ በመከላከሉ በነፃ እንዲሰናበት ውሳኔ ተሰጥቷል፡፡
አስገድዶ የእምነት ቃል መቀበል
መቶ አለቃ ጌታቸው ብቻ አይደለም “መርማሪ” ባደረሰበት ድብደባ አካሉ የጎደለ፡፡ በተመሳሳይ መዝገብ 4ኛ ተከሳሽ የሆነው አወቀ ሞኝሆዴም በ “ምርመራ” ወቅት ተመሳሳይ ጥቃት ደርሶበት በተመሳሳይ “ነፃ” ተብሎ ከእስር ወጥቷል፡፡ መቶ አለቃ ጌታቸው እና አወቀ ሞኝሆዴም ብቻ አይደሉም፤ በ “መርማሪዎች” ድብደባ ህይወታቸውን ያጡ፣ አካላቸው የጎደለ፣ የእድሜልክ በሽታ የሸመቱ፣ አካላቸው እንዲጎድል የሆነ፤የስነ ልቦና ችግር ተጠቂ የሆኑ በርካቶች ናቸው፡፡ የወንድ ብልት ላይ ውሃ ማንጠልጠል፣ የውስጥ እግር መግረፍ፣ ሃይለኛ ጥፊ ፣ ከባድ ድብደባ፣ የሴት ጡት መግረፍ፣ ማህፀን ውስጥ ባእድ ነገር ማስገባት፣ መድፈር፣ እርቃን ማስቆም፣ ስፖርት ማሰራት፣ ጥፍር መንቀል፣ ማዋረድ፣ መስደብ፣ ማስፈራራት፣ መዛት፣ ቤተሰብ እና ጠበቃ አለማገናኘት፣እና ስነ ልቦናዊ ጫናዎች የሚያደርሱ ሌሎች መሰል ኢ-ሰብአዊ እንዲሁም ኢ- ሕገመንግስታዊ ድርጊቶች በ ”ምርመራ” ወቅት “መርማሪዎች” ጠርጥረናችኋል የሚሏቸው ግለሰቦች ላይ የሚፈለገውን ‹ወንጀል ሰርተናል› ብለው እንዲያምኑ እና ቃል እንዲሰጡ የሚፈፅሟቸው ወንጀሎች ናቸው፡፡ ይህ አይነት ወንጀል በአብዛኛው በሽብርተኝነት ወንጀል የተጠረጠሩ ወይም የተከሰሱ ግለሰቦች ላይ የሚፈፀም ቢሆንም በሌላ ወንጀሎች የተጠረጠሩ ወይም የተከሰሱ ግለሰቦች ላይም ወንጀሎቹ የሚፈፀሙባቸው አጋጣሚዎች ጥቂት አይደሉም፡፡
ሕጉ ምን ይላል?
የኢትዮጵያ ሕገ መንግስተ አንቀፅ 19(5) ላይ፡ “የተያዙ ሰዎች በራሳቸው ላይ በማስረጃነት ሊቀርብ የሚችል የእምነት ቃል እንዲሰጡ ወይም ማናቸውንም ማስረጃ እንዲያምኑ አይገደዱም፡፡ በማስገደድ የተገኘ ማስረጃ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡” ይላል፡፡የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ስርዓት ሕጉም በተመሳሳይ አንቀፅ 27(1) ላይአንድ ግለሰብ ለቀረበበት ክስ ወይም የክስ አቤቱታ ቃሉን ለመስጠት እንደሚጠየቅ ይገልፃል፤ አንቀፅ 27(2) ደግሞ፡ “ሰውየው ምላሽ እንዲሰጥ ለማስገደድ አይቻልም፡፡ ነገር ግን ምላሽ ለመስጠት ነጻ እንደ ሆነና ፈቅዶ የሚሰጠው ማናቸውም ቃል በማስረጃነት የሚቀርብ መሆኑ ጠያቂው ፓሊስ ለተጠያቂው መንገር ይገባዋል፡፡” በማለት ይገልፃል፡፡ በቅርቡም ከሰበር ሰሚ ችሎት በተሰጠ ብይን (ያልታተመ)፤ ተጠርጣሪዎች ለፖሊስ ቃላቸውን የሰጡት በማስረጃነት የሚቀርብ መሆኑ ሳይነገራቸው ከሆነ ማስረጃው (ቃሉ) ተቀባይነት እንደማይኖረው የሕግ ትርጓሜ ተሰጥቶበታል፡፡ በተጨማሪም የኢትዮጵያ የወንጀል ሕግ በምርመራ ወቅት በሕግ የተከለከሉ ተግባራትን የሚፈፅሙ ፖሊሶች በወንጀል እንደሚጠየቁ ይደነግጋል፡፡
ይሁን እንጂ በሕጎቹ ላይ የተደነገጉት የተከሰሰ ወይም የተጠረጠረ ሰው መብቶች ከወረቀት ባለፈ ሲተገበሩ ማየት የማይታሰብ ነው፡፡
የፀረ ሽብርተኝነት አዋጁ
በሕገ መንግስቱ እና በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ስርዓት ሕጎ ላይ ላይ ከተደነገገው በተፃራሪ የማስረዳት ሸክምን በሚያቀል መልኩ፤ በ2001 ዓ.ም የወጣው የፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ አንቀፅ 23 ላይ ተቀባይነት የሚኖራቸው ማስረጃዎችን ይዘረዝራል፡፡ በአዋጁ አንቀፅ 23(5) ላይ “በሽብርተኝነት ድርጊት ከሚጠረጠር ሰው በፅሁፍ፣ በድምፅ መቅረጫ፣ በቪዲዮ ካሴት፣ ወይም በማናቸውም ሌላ ሜካኒካል ወይም ኤሌክትሮኒክ መሳሪያ የተቀረፀ የእምነት ቃል፡፡” ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተቀባይነት ያለው ማስረጃ መሆኑን ያትታል፡፡በዚህም ምክንያት አቃቤ ህግ በሽብርተኝነት የሚከሱትን ግለሰብ በግዳጅ የተቀበሉትን የ ”እምነት” ቃል ብቻ [ሌላ ምንም ማስረጃ ሳይኖረው] በማያያዝ ክስ ለመመስረት ያስችለዋል፡፡ በተግባርም እየሆነ ያለው ይሄው ነው፡፡
የፍርድ ቤት ውሳኔ
አንድ ግለሰብ የፀረ ሽብርተኝት አዋጁን በመተላለፍ የተከሰሰ እንደሆነለ “መርማሪ” ፖሊስ ወንጀል እንደሰራ አምኖ በግዳጅ የሰጠው ቃል ማስረጃ ሆኖ ይቀርብበታል፤ ክሱንም እንዲከላከል ለማስፈረድ የሚያስችል ማስረጃ ነው፡፡ ተከሳሹ በሚከላከልበት ወቅት በማስረጃነት የቀረበበት ቃል በግዳጅ ወይም በኃይል የተሰጠ መሆኑን የማስረዳት ግዴታ አለበት፡፡ አለበለዚያ ተከሳሹ ለ “መርማሪ” ፖሊስ ወንጀል እንደሰራ አምኖ በግዳጅ በሰጠው ቃል ብቻ ጥፋተኛ ተብሎ የእስር ቅጣት ይበየንበታል፡፡
በሽብርተኝነት ወንጀል ተከሰው እንደ መቶ አለቃ ጌታቸው መኮንን ቃላቸውን መከላከል ችለው ከክሳቸው “ነፃ” ሲባሉ ያየኋቸው ጥቂት ግለሰቦች ናቸው፡፡ተከሳሹ በማስረጃነት የቀረበበት ቃል በግዳጅ የሰጠው ስለመሆኑ “መርማሪ” ፖሊስ አስገድዶ ቃሉን ሲቀበል በአይን ያዩምስክሮችን ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ ከተከሳሹ ጋር አንድ ክፍል የነበሩ ምስክሮች፤ ለምርመራ ሲጠራ ጤነኛ እንደነበረ ሲመለስ ግን እመን እየተባለ በደረሰበት ድብደባ አካላቱ ቆስሎ/ጎድሎ እና መራመድ እያቃተው መመለሱን ማየታቸውን እንዲሁም እርዳታ ያደርጉለት እንደነበረ ሲመሰክሩ“መርማሪው ሲደበድበው አይተኻል ወይ?”፣ “የእምነት ቃል እንዲሰጥ መገደዱን እንዴት አወቅክ?” እና “አደጋው የደረሰበት ወደ መርመራ ማዕከሉ [ማዕከላዊ] ከመምጣቱ በፊት የተከሰተ ነገር አለመሆኑን በምን እርግጠኛ ሆንክ?”የሚሉ መስቀለኛ ጥያቄዎች ከአቃቤ ህግ እንዲሁም ተመሳሳይ ማጣሪያ ጥያቄዎች ከዳኞች በተለያዩ መዝገቦች ላይ ሲሰነዘሩ እንደ መስማት የሚያሳምም ነገር ምን አለ? እንዴት አንድ የፍትህ ስርዓትአካል የሆነ [ዳኞች እና አቃቢያን ህግ] ይህን መሰል ታሪክ ለብዙ ዓመታት እየሰማ እንዳልሰማ በዝምታ ማለፍ ይቻለዋል?!
ጥቂቶቹ፤ የደረሰባቸውን ቋሚ ጉዳት በችሎትለማሳየት የደፈሩ፣ በአይን የሚታይ ጉዳት የደረሰባቸው፣ ወንጀሉ በተፈፀመባቸው ወቅት እድለኛ ሆነው የህክምና ማስረጃ ማግኘት የቻሉ እና“መርማሪ” ፖሊስ በግዳጅ ቃላቸውን ሲቀበላቸው በአይን ያየ/ዩ ምስክር/ሮች የሚያገኙ ተከሳሾች በማስረጃነት የተያያዘባቸውን ቃል ዳኞች ውድቅ የሚያደርጉባቸው አጋጣሚዎች ውስን ቢሆንም አልፎ አልፎ ይከሰታል፡፡ ልክ እንደ መቶ አለቃ ጌታቸው መኮንን፡፡ ዳኞች በመቶ አለቃ ጌታቸው መኮንን ጉዳይ የቀረበላቸውን ማስረጃ መዝነው፤ በግዳጅ በተለይም ደግሞ አካሉን አጥቶ (ሰብዓዊ መብቱ ተጥሶ)፤የሰጠው የእምነት ቃል መሆኑንን አረጋግጠውማስረጃውን (በግዳጅ የተሰጠውን ቃል) ውድቅ አድርገው ከክሱ “ነፃ” ነህ ብለው ውሳኔ ሰጥተዋል፡፡ ነገር ግን ዳኞቹ ማስረጃውን ውድቅ ከማድረግ ባሻገር መስጠት የሚገባቸው ተጨማሪ ውሳኔ ወይም ትእዛዝ መኖር አልነበረበትም ወይ? መቶ አለቃ ጌታቸው አንድ አመት ከስምንትወራት አላግባብ መታሰሩእንዲሁምበ “ምርመራ” ወቅት የደረሰበት የአካል ጉዳት በምንድነው የሚካሰው?ወንጀሉን የፈፀመው አካል ዝም መባል አለበት ወይ? ከክሱ ነፃ መባሉ ብቻ ፍትህ አግኝቷል ያስብላል ወይ?
“መርማሪዎች” ተከሳሾች እና ተጠርጣሪዎች ላይ በሚፈፅሙት ወንጀል መጠየቅ ያለባቸው ፍ/ቤት ድርጊቱን ባረጋገጠበት ጊዜ ብቻ አይደለም፡፡ነገር ግን ቢያንስ ፍርድ ቤት ድርጊቱን ባመነበት አምኖም ተከሳሹን ከክሱ ነፃ ባወጣበት አጋጣሚ ግን ተከሳሹ የሚካስበትን እና ወንጀሉን ያደረሰው አካል/ግለሰብ ደግሞ በሕግ የሚጠየቅበትን አግባብ ፍርድ ቤቱ ራሱ ሐላፊነቱን ወስዶ ተበዳይ ወገን ፍትህ እንዲያገኝ ማድረግ አለበት ብዬ አምናለሁ፡:
*የዞን 9 ጦማሪዋ ማህሌት ፋንታሁን ይህን ጽሁፍ ያስቀመጠችው በፌስቡክ ገጿ ነበር:: ለዘ-ሐበሻ አንባቢዎች ይመጥናል ብለን ስላሰብን በድረገጻችን ላይ አትመነዋል::