‹‹የኢሕአዴግ ፀባይ እኛን መተንበይ የማንችል መሪዎች አድርጎ ነው ያስቀመጠን›› = ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ፣ የመድረክ ፕሬዚዳንት

ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ የተቃውሞ ፖለቲካ ጎራውን በመምራት ላለፉት 25 ዓመታት በአገሪቱ የፖለቲካ መድረክ ከፍተኛ የሆነ ሚና የተጫወቱ ፖለቲከኛ ናቸው፡፡ ከሽግግር መንግሥቱ ምሥረታ ጀምሮ የተለያዩ ኅብረቶችንና የፓርቲዎችን ስብስብ በመምራት የሚታወቁ ፖለቲከኛም ናቸው፡፡ በአሁኑ ወቅትም የአራት ፓርቲዎች ስብስብ የሆነው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) ፕሬዚዳንት ናቸው፡፡ ባለፉት 25 ዓመታት በአገሪቱ የፖለቲካ ውጣ ውረድና በተቃዋሚ ፓርቲዎች ተጠናክሮ አለመውጣት፣ በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ ስለተከሰተው ድርቅና በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ነአምን አሸናፊ (Reporter Amharic )  አነጋግሯቸዋል፡፡

ሪፖርተር፡- በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ከሽግግር መንግሥቱ ጊዜ ጀምሮ ሲሳተፉ ቆይተዋል፡፡ በአጠቃላይ የአገሪቱን የፖለቲካ ምኅዳር ባለፉት 25 ዓመታት ያለፈበትን መንገድ እንዴት ይገልጹታል? ውጤትና ፈተናዎቹስ ምን ይመስሉ ነበር?

ፕሮፌሰር በየነ፡- የተነሳው ጥያቄ ውስብስብ የሆነ መልስ የሚሻ ነው፡፡ አንደኛ እዚህ አገር የሚያስማማ ዓይነት ለውጥ ለማምጣት ከማመን ተነስቶ የፖለቲካ መድረክ ላይ የመጣ መንግሥት ወይም አመራር የያዘ ፓርቲ የለም፡፡ ለውጥ ማምጣት ስንል በዘመናዊ መልኩ በዴሞክራሲያዊ ሥርዓት በሚባለው መተማመን የሚቻልበት የፖለቲካ ምኅዳር ለመፍጠር እምነት ያለው ፓርቲ ሥልጣን አልያዘም፡፡ የችግሮቹ ሁሉ እናት ይህ ነው፡፡ ይህ እምነት እስከሌለ ድረስ ያየናው ያለፉት 25 ዓመታት ሙሉ ቅንነት የላቸውም፡፡ በፖለቲካ ቅንነት ምናምን ማለት የዋህ ያሰኛል፡፡ ፖለቲካ ከሥልጣን ጋር ተቆራኝቶ ስለሚታይ ብዙ ጊዜ ለሥልጣን ሽኩቻ የሚነሳ ጥያቄና አስተያየት ነው ሊባልም ይችላል፡፡ ያም ሆኖ ግን በጣም ጎልቶ የወጣና እኔ በግሌ እርግጠኛ የሆንኩበት ኢሕአዴግ በብልጣብልጥነት፣ በማጭበርበር፣ በማታለልና በማስመሰል ሥልጣን ላይ ቆይቶ በረሃ በነበሩ ጊዜ የታያቸውን አንዳንድ ህልሞችን፣ ከህልምም በላይ አልፎ ቅዥቶችን ተግባራዊ አደርጋለሁ ብሎ ሙሉ ለሙሉ ራሱን ተገዥ የማድረግና የቀረውን ደግሞ ያለማዳመጥ ነገር ጎልቶ የወጣ ነው፡፡ ችግሩ እዚያ ላይ ነው፡፡ አንደኛ ደርግ ዝም ብሎ እንደ እምቧይ ካብ መውደቅ አልነበረበትም፡፡ በድርድር ከሥልጣን መወገድ የነበረበት አካል ነው፡፡ ችግሩ እዚያ ላይ ነው ያለው፡፡ የኃይለ ሥላሴ ሥርዓትም በድርድርና የተሰጠውን አስተያየት ተቀብሎ ቢሆን ኖሮ ደርግን የመሰለ ጭራቅ ባልመጣ ነበር፡፡ ኢሕአዴጎችም ሥልጣን ላይ ሲወጡ ተደራድረውና በኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ ብቃት ያላቸው ፓርቲዎችን፣ ግለሰቦችንና እንቅስቃሴዎችን ዋጋ መስጠት ነበረባቸው፡፡ ስለዚህ በድርድር ያልመጣ ለውጥ በመሆኑ የአሸናፊ ፍትሕ ሆኖ ነው ያየነው፡፡

ለአንድ ችግር መፍትሔ ለማግኘት ሁለት ወገን ያስፈልጋል፡፡ ነገር ግን እነሱ ደርግን አሸንፈናል አሉ፡፡ መደረግ ያለበትን ነገር የራሳቸውን አቋም ለጠፉ፡፡ ብትወዱም ባትወዱም የምትከተሉት ይህንን ነው አሉ፡፡ ይህ ነገር ትክክል አይደለም፡፡ ቻርተሩ ላይ የተስማማነው ይህንን አይደለም ብለን ከኢሕአዴግ ውጪ ያለነው ለመንቀሳቀስ ሞከርን፡፡ ከአቶ መለስ ጋር ለመገናኘት ሞከርን፡፡ ነገር ግን ያኔም የሚከተሉት ሥልት ከእነሱ ውጪ የነበረውን መከፋፈል ላይ ያለመ ነበር፡፡ ሌላው ኢሕአዴግ ያኔም ቢሆን አሁን የወሰደው ግምት የኢትዮጵያ ሕዝብ በሙሉ ደርግን ስላስወገድንለት አመሥጋኝ ነው የሚለው ነው፡፡ በቃ ደርግን የሚያህል አምባገነንና ጨፍጫፊ ነገር አስወገደልን ብሎ ያመሠግናል፣ ስለዚህ በቃ አለቀ ምንም ሊያደርግ ይችላል የሚል አስተሳሰብ ነው፡፡ ነገር ግን ይህ እንዳልሆነና ከዚያም አልፎ የኢትዮጵያ ሕዝብ እኛንም አዳምጡን፣ እሺ ደርግ ተወግዷል ወደፊት ለሚሆነው ነገር መነጋገር ስላለብን እኛንም ስሙን አዳምጡን የሚል መሆኑን ጨርሶ ከግምት ውስጥ አላስገቡም፡፡ ስለዚህ ዝም ብሎ መጋጨት ሆነ፡፡ የመጀመሪያው ስለምርጫ ሕዝብ ይወስን የሚባለው ቅድመ ምርጫ ምርጫ (Snap Election) በሚባለው ነው፡፡ ከ1984 ዓ.ም. ምርጫ በፊት ማን ምርጫውን ያስተዳድር የሚለውን መልስ ለመስጠት የአካባቢ አስተዳዳሪዎች ይሰየሙ? ለሚለው ጥያቄ የየቀበሌው ሕዝብ ይጠራና በእጅ ማንን ትመርጣላችሁ እየተባለ እንዲካሄድ ተወሰነ፡፡ በዚያ ምርጫ አዲስ አበባ ላይ 20 በመቶ ድምፅ ብቻ ነው ያገኙት፡፡ በኦሮሚያ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ነው የተሸነፉት፡፡

አንዱ ሌላው ትልቁ ድክመት ደግሞ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ለዚህ አገር መልካም ያስባል የሚል አመለካከት አለመያዛቸው ነው፡፡ አገራችን በእውነቱ ብትለማ፣ ብትሻሻል የሚጠላ ኢትዮጵያዊ አለ? ሕዝቦች እኩል ቢሆኑ የሚጠላ ነፍስ ያለው ፍጡር አለ? ማንም የሚያነሳው ይህ በአግባቡ ይስተዳደር የሚል ጥያቄ ነው እንጂ፣ ከዚያ አልፎ ለዚህች አገር ዝም ብሎ ክፋት የሚያስብ ወገን በዚያ ረድፍ እነርሱ ደግሞ ለዚህች አገር መልካም የሚያስቡ ወገን አድርገው ራሳቸውን መፈረጃቸው ሌላው ችግር ነው፡፡ ከእነሱ እጅ ውጪ ትንሽ ነገር ቢወጣ ሥልጣናቸው ትንሽ ቢከለስ ይህች አገር አደጋ ላይ ትወድቃለች የሚባለው ከፍርኃት የተነሳ ሐሳብ ነው የችግሮቹ ምንጮች፡፡ ኢሕአዴግ እዚህች አገር ላይ ማኅበራዊ ሙከራ ሲሠራ ነው የነበረው፡፡ ሙከራው ግን የተደረገው የተሻለውን ውጤት አግኝቶ ተግባር ላይ ለማዋል ሳይሆን፣ የዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ አስተሳሰብ ለማምታታት ነው፡፡ ምርጫውን ከፈቱ፣ ምርጫ በየአምስት ዓመቱ ያካሂዳሉ፣ ወዘተ የሚባለው በልማት ስም የሚመጣውን ድጋፍ በዘላቂነት ለማቆየት የሚጠቀሙበት ድራማ እንጂ፣ በእውነቱ መድበለ ፓርቲ ሥርዓት እዚህ አገር ዕውን እንዲሆን ያለመ አይደለም፡፡ ኢትዮጵያውያን ዜጎች ድርጅቶች አቋቁመው መልካም ነገር ለዚህ አገር ያስባሉ የሚለውን ታሳቢ ተቀብሎ የፖለቲካ ምኅዳሩን ለማስተካከል ፈቃደኛ ያልሆነ ቡድን ነው ኢትዮጵያ ውስጥ ሥልጣን የያዘው፡፡ ስለዚህ ይኼ ነው ችግሩ፡፡

ሪፖርተር፡- ባለፉት 25 ዓመታት ገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግ የፖለቲካ ምኅዳሩ እንዲስተካከል አለመፈለጉን በሰፊው አብራርተዋል፡፡ የገዥው ፓርቲ ድርሻና የሚጫወተው ሚና እንደተጠበቀ ሆኖ፣ እርስዎ ደግሞ በአገሪቱ የፖለቲካ ምኅዳር ላይ በተለይ የተቃውሞ ጎራውን በመምራት ከፍተኛ ሚና እንደመጫወትዎ መጠን፣ በተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በኩል ገዢው ፓርቲን ለመፎካከር፣ ሕዝቡን ለማደራጀትና ኅብረት ከመፍጠር አንፃር ያለው ችግርስ ምንድነው?

ፕሮፌሰር በየነ፡- ተቃዋሚ ፓርቲዎች ዘንድ ያለው ችግር አንደኛ እኛ ኢትዮጵያውያን ዝም ብለን የምናልማትን ኢትዮጵያ ሳይሆን ጠለቅ አድርገን ውስጡ ገብተን በምናይበት ጊዜ የጥያቄዎቹ መብዛት፣ እንዲሁም ፓርቲዎቹ በእነዚያ ጥያቄዎች ዙሪያ የተሰባሰቡ መሆናቸው፣ አብዛኛዎቹ ፓርቲዎች ደግሞ ርዕዮተ ዓለማዊ ሳይሆኑ የብሶት ፓርቲዎች ናቸው፡፡ የጊዜው ችግር የፈጠራቸው፡፡ ፓርቲዎቹ በአብዛኛው የድሮዎቹ እንደ ኢሕአፓና መኢሶን የሚባሉት ትንሽ የርዕዮተ ዓለም መስመር ተከተለው ድሮ የተቋቋሙ ናቸው፡፡ እነርሱ ደግሞ በታሪካዊ ሒደት በደርግ ጊዜ የደረሰባቸውና የሆኑት ይታወቃል፡፡ እዚህ አገር መሬት ረግጠው ለመንቀሳቀስ የማይችሉበት ሁኔታን ደርግ ፈጠረ፡፡ ኢሕአዴግ ደግሞ ያንኑ በር ጨርሶ ዘጋው፡፡ በርዕዮተ ዓለማዊ ፖለቲካ ዓላማን ለማራመድ ከሚፈልጉት አንፃር ማለት ነው፡፡ ከዚያ ወዲህ ተቋቋሙ የሚባሉት ፓርቲዎች በአብዛኛው የብሶት ፓርቲዎች ናቸው፡፡ የወሰደውን ያህል ጊዜ ወስደን ታግለን ይህችን አገር በዚህ ዓይነት የእምነት መተክል ላይ እንድትተዳደር እናደርጋለን የሚሉ ዓይነት ብዙ ፓርቲዎች የሉም፡፡ ስለዚህ በብሔር ብሔረሰብ መሠረት ያደረጉ፣ መብታችን በብቃት አልተከበረም፣ በቂ ዕውቅና አላገኘንም የሚል ነው አጀንዳው፡፡ በጣም ርቆ የማይሄድ ማለት ነው፡፡ ሌሎቹም ደግሞ የሚሰባሰቡ አሉ፡፡ የኢትዮጵያዊነት ፓርቲዎች ምናምን የሚሉ፡፡ እነርሱ ደግሞ ኢትዮጵያ ልትበታተን ነው ይላሉ፡፡ ምን ሆና ነው የምትበታተነው? የኢትዮጵያ ሕዝብ እኮ ድሮም የሚኖረው ስለፈለገ ነው፡፡ አልፈልግም ያለውማ ተገንጥሎ ሄደ፡፡ ይኼ አይደለም የኅብረቱ ማዕከል መሆን ያለበት ለመገናኘትም አብሮ ለመሆንም ማዕከል መሆን ያለበት አንድ መርህ ነው፡፡

እኔ በግሌ ከ1985 ዓ.ም. ጀምሮ ከኢሕአዴግ ሌላ አማራጭ አለን የሚሉትን እንቅስቃሴዎች ለማስተባበር ብዙ ጊዜዬንና ጉልበቴን ነው የተጠቀምኩት፡፡ አሁን መለስ ብለን ስናይ መቼም አንዱ ጋ ያደርሳል በሚል ነበር ስንለፋ የነበረው፡፡ አሁን ግን ስናይ እርሱም እየራቀ ነው፡፡ በተለይ ካለፉት አምስት ዓመታት ወዲህ፡፡ የኢትዮጵያ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎችን ለማሰባሰብ አስቸጋሪ ነው፡፡ ከማን ጋር ተገናኝተህ፣  ምን ዓይነት የፖለቲካ መስመር ከያዘው ጋር ነው ቁጭ ብለህ አንድ ኅብረት እንፍጠር ብለህ የምትደራደረው? ይህንን ደጋግሜ አይቼዋለሁ፣ አስቸጋሪ ነው፡፡ ለመደራደርም ለመሰባሰብም አስቸጋሪ ነው፡፡ ኢትዮጵያችን እንዲህ ሆነች በሚል ይህንን የፖለቲካ እንቅስቃሴዎችን ፈጠርን የሚሉት ሁሉ በስሜታዊነት ነው፡፡ እንዲህ ሲሆን ደግሞ ሌላውን ሥጋት ውስጥ ይከተዋል፡፡ እስካሁን ድረስ ከተሰባሰቡት እንቅስቃሴዎች ውስጥ ለእኔ ጥሩ ምሳሌ አማራጭ ኃይሎች ነው፡፡ ስብስቡ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ የሲቪክ ማኅበራት፣ የሃይማኖት ተቋማት፣ የሙያ ማኅበራት የነበሩበት ነው፡፡ ያንን ሁሉ አሰባስበን ወደፊት ለመሄድ ተነሳን፡፡ ዓለም አቀፍ ዕውቅናን አግኝቶ ነበር፡፡ ከኢሕአዴግ ውጪ ያሉት ኃይሎች አሁን ተሰባሰቡ ብሎ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዕውቅና የሰጠው ነበር፡፡

ስለዚህ ችግሩ ምንድነው? እንዳልኩት ተቃዋሚ ፓርቲዎች የተቋቋሙበት መሠረቱ በጣም በርካታ ስለሆነ፣ አሰባስቦ በአንድ ዓይነት አጀንዳ ማምጣት አቅቶን ነው የቆየው፡፡ መጀመሪያ ታክቲካዊ ጥያቄዎችን መመለስ ተገቢ ነው፡፡ ታክቲካዊ ጥያቄዎች ማለት ደግሞ ዴሞክራሲያዊ ጥያቄ፣ የሰብዓዊ መብት ጥያቄ፣ የመልካም አስተዳደር ጥያቄና የሕግ የበላይነት ናቸው፡፡ በአንዲት ኢትዮጵያ ክልል ውስጥ ፈቃደኛ የሆኑት ፓርቲዎች ሁሉ ይህንን እንደ ቅድመ ሁናቴ ይዘው ዝርዝር አጀንዳቸውን ቢተውት ጥሩ ይመስለኛል፡፡ መሬት የግል ይሁን፣ ፌዴራሊዝሙ እንዲህ ይሁን የሚባሉ ዝርዝር ጉዳዮችን ትቶ መጀመሪያ መሠረታዊ የሆነው ነጥብ ላይ ለምንድነው የማንተባበረው ሲባል፣ አይ የእኔ መብት እዚህ ጋ አልተከበረም እየተባለ ወደ ዝርዝሩ ይገባል፡፡ ወደ ዝርዝሩ ይገባና እኛ ሳናውቅ አኩርፎ ትቶ ይወጣል፡፡ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ታክቲካዊና ስትራቴጂካዊ ፖለቲካዊ አጀንዳን ለይቶ ለማስተናገድ፣ ወይም በዚያ አካባቢ ለመደራደር ብቃት ማነስ ይታያል፡፡ የትም አገር እንደሚታየው ዝም ብለህ መጨረሻ ላይ እደርስበታለሁ የምትለውን ግብ ይዘህ ከማንም ጋር መደራደር አትችልም፡፡ በጣም አስቸኳይ የሆኑት ችግሮች ምንድን ናቸው የሚለው ላይ መጀመሪያ መስማማት አለብን፡፡

በዚህ አገር በነፃነት ተደራጅቶ ነፃ ምርጫ ስለሚካሄድበት ሁኔታ መደራደር ነው፡፡ የፈለገውን የፖለቲካ መስመር ሊያቀነቅን ይችላል፡፡ ግን ይህንን ለማምጣት አንድ ላይ ሆነን ባለው ሥርዓት ላይ ጫና እንፍጠር ስንል አንድ ላይ መቆም አልተቻለም፡፡ ምሳሌ ልስጥህ፡፡ ለአንዳንዶች በኢትዮጵያ ፖለቲካ ወርቃማ ጊዜ እየተባለ በሚጠራው የ1997 ዓ.ም. ምርጫ ወቅት ቅንጅት ኅብረትን አቅም ለማሳጣት የተፈጠረ ቡድን ነው፡፡ ከኅብረቱ ውስጥ የወጡ ሁለት ፓርቲዎች ሌሎች ለጊዜው የይድረስ የይድረስ የተዘጋጁ ሁለት ፓርቲዎችን በማካተት አራት ፓርቲዎች ስለሆኑ ቅንጅት ተብለናል በማለት አርቲፊሻል ነገር የተፈጠረበት ሁኔታ አንዱ ምሳሌ ነው፡፡ ይህም ጊዜው ሲደርስ የምንፅፈውና በዝርዝር የምናስቀምጠው ይሆናል፡፡ ለዚህም ኃላፊ የሆኑ ሰዎች አሁንም ከእኔ በላይ ማንም የለም የሚል ነገር ሲናገሩና መጽሐፍ ሲጽፉ አያለሁ፡፡ ይህ ትዝብት ነው፡፡

ሪፖርተር፡- መድረክ ምርጫ 2007 በተቃረበበት ሰሞን ተደጋጋሚ መግለጫዎችን በማውጣትና በተለያዩ መንገዶች ደጋፊዎችንና መራጩን ሕዝብ ለማግኘት የተለያዩ ሥራዎችን እየሠራ ነበር፡፡ የምርጫውን መጠናቀቅ ተከትሎ ግን በመድረክ ብቻ ሳይሆን በአብዛኛዎቸ የፖለቲካ ፓርቲዎች ያን ያህል የጎላ ሥራ ሲሠራ አይስተዋልም፡፡ መድረክ በአሁን ወቅት ምን እየሠራ ነው?

ፕሮፌሰር በየነ፡- መድረክ እንግዲህ ትልቅ ጉዳት ደርሶበት ነው ከምርጫው የወጣው፡፡ ጉዳት ስልህ በቁሳቁስ፣ በሰው ኃይል እንዲሁም ከሁሉም በላይ ሥነ ልቦናዊ ጉዳት በገዢው ፓርቲ ደርሶበታል፡፡ እኛም የመድረክ መሪዎች ከፍተኛ የሆነ ሸክም የተሰማን ጊዜ ነው፡፡ መቼም ይህ አገር እኮ ‹የተናገሩት ከሚጠፉ የወለዱት ይጥፋ› የሚል ሕዝብ ያለበት አገር ነው፡፡ እኛ ሕዝባችንን ማሸነፍ ይቻላል ብለን ነው ስንቀሰቅስ የነበረው፡፡ እናንተ ብቻ ጠንክራችሁ ተደራጁ ተዘጋጁ እንጂ ማሸነፍና በቂ መቀመጫ ማግኘት ይቻላል ብለን ነው የቀሰቀስነው፡፡ እንግዲህ ያንን ከውጤቱ ጋር አገናኘው፡፡ ምን ይዤ ነው ሕዝቡ ጋ የምሄደው? ዋሾው በየነ ብሎ እንዲጠራኝ ነው? አንድ የፖለቲካ መሪ ሊከሰት የሚችለውን ነገር ማንበብ አለበት፡፡ አለዚያ መሪ አይደለም፡፡ ያሉትን ነገሮች መተንበይ አለበት፡፡ ያሉትን ታሳቢዎች በሙሉ ቀምረህ ውጤቱ ይኼ ሊሆን ይችላል ብለህ መተንበይ መቻል አለብህ፡፡ የኢሕአዴግ ፀባይ እኛን መተንበይ የማንችል መሪዎች አድርጎ ነው ያስቀመጠን፡፡ እኔ በዚህ ምርጫ መቸም ሒሴን መዋጥ ይኖርብኛል፡፡ ይህ መቶ በመቶ የማሸነፍ ውጤት ይመጣል የሚል ነገር ኢሕአዴጎች ራሳቸው መቼም ጤነኞች ናቸው ነው የምለው እብዶች አይደሉም፡፡ ያለፈው 99.6 በመቶ ነው ያሉት፡፡ አሁን ደግሞ ከዚያ በላይ አልፈው ይደግሙታል የሚል በፖለቲካ ለመተንበይ የማይቻል ነገር ነው፡፡ ምክንያቱም 99.6 በመቶ አሸነፍን ባሉበት ጊዜ ብዙ ወቀሳና ትችት ከኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ደርሶባቸው ነበር፡፡ እና ይህ ሲሆን መቼም እነዚህ ሰዎች ያለፈው ትንሽ ሳያሳፍራቸው አይቀርም ከሚል ትንሽ ይከፍታሉ የሚል ትንበያ ነው የነበረኝ፡፡ ያን ሁሉ እንደሌለ አደረጉት፡፡ በዚህም ምክንያት መድረክ ክፉኛ ተጎድቶ ነው የወጣው፡፡ ያለችንን ሀብት አሟጠን ተጠቅመናል፡፡ ይህን ሁሉ ስናደርግ ዋናው ግባችን የነበረው ከእኛ ቀረ እንዳንል ነው፡፡

ቢያንስ እኛ በቂ ጥረት ስላላደረግንና ስላልቀሰቀስን ነው እዚህ እዚህ አካባቢ የተፍረከረከው፣ ወይም ሽንፈት ያጋጠመን እንዳንል ጉልበታችንንና ሀብታችንን አሟጠን ነው የተጠቀምነው፡፡ ስለዚህ ያን ሁሉ አድርገን በእኔ እምነት በተወዳደርንበት ቢያንስ ሦስቱ ዋነኛ ክልሎች [ደቡብ፣ ትግራይና ኦሮሚያ] ከእኛ ቀረ የምንለው ነገር አልነበረም፡፡ ቢያንስ በቂ መቀመጫዎች ለማግኘት የሚያስችለን ነበር፡፡ ያን ሁሉ ዜሮ ሲያደርጉ ሕዝባችንን ግዴለም ታሸንፋለህ ብለን የነገርነውን አንዲት መቀመጫ እንኳን ማሳየት ሲያቅተን ለምንድነው የሚያምነኝ? ሕዝቡ የሚጠይቀን እኮ ለምንድነው የምታስቸግሩን? አሁን የምታካሂዱት ምርጫ ካለፈው በምን ይለያል ብላችሁ ነው? የሚሉ ጥያቄዎች ነው፡፡ አሁን ምን እየሠራችሁ ነው ላልከው፣ በመሠረቱ ቀውስን የመቆጣጠር (Crisis Management) ላይ ነው እየሠራን ያለነው፡፡ አገሪቱ ውስጥ የተፈጠሩ አለመረጋጋቶችን የመከታተል ላይ ያተኮረ ነው፡፡ ያ ማለት በየገጠሩ በየአካባቢው ያለንን አደረጃጀታችንን በሙሉ አጥፈን ቤታችሁ ግቡ ያልንበት ጊዜ አይደለም፡፡ ሕዝቡ አሁንም በየቤቱ ባንዲራ ሰቅሎ ይህ ጽሕፈት ቤት ነው እያለ እኮ እየተፋለመ ነው፡፡ አርሶ አደሩ እስካሁን ድረስ ኢሕአዴግ ማሸነፉን አምኖ አልተቀበለም፡፡ ምንድን ነው የሚለን አሁንም አዲስ ነገር የለም እንዴ? እነዚህ ሰዎች እንዲሁ ሊቀጥሉ ነው እንዴ? ማን የሰጠውን ድምፅ ነው አሸንፈናል የሚሉት? የሚል ነው፡፡ ሕዝቡ እስካሁን አያምንም የሚቀየር ነው የሚመስለው፡፡ የእኛ ፓርቲ በስፋት በተወዳደርንባቸው ስፍራዎች አርሶ አደሩ በእርግጠኝነት እንዳልተሸነፈ ነው የሚያውቀው፡፡

ሪፖርተር፡- ከምርጫው በኋላ ባለው ጊዜ አባላት ባለው አሠራር እየሠሩ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ እርሱ እንደተጠበቀ ሆኖ ከደጋፊዎቻችሁ ጋር እንዴት ነው እያተገናኛችሁ ያላችሁት?

ፕሮፌሰር በየነ፡- ሕዝቡን በስፋት ለማግኘትና ስሜቱን ለማዳመጥ የምናደርገውን ጥረት ሙሉ በሙሉ መንግሥት ዘግቶታል፡፡ አሁን እየተነገረን ያለው ነገር ያልሆነ ነገር ነው፡፡ አዲስ አበባ ውስጥ ስብሰባ ስለሚካሄድ፣ በምታልፉበት ቦታ ትምህርት ቤቶች ስላሉ፣ ግንባታ የሚካሄድበት ስለሆነ፣ ከዚያም በላይ ደግሞ በጊዜው ባለው መንፈስ ምክንያት ደግሞ መፍቀድ ወይም ዕውቅና መስጠት አንችልም ይሉሃል፡፡ እኛ ፍቀዱ አላልንም፡፡ በዚህ ቀን ሠልፍ ልንወጣ ነውና ዕወቁት ነው ያልነው፡፡ ልናውቅ አንችልም ይሉሃል፡፡ ድሮውንም ትልቅ ችግር ውስጥ ባለንበት ወቅት እኛ አሳውቀናል ብለን ወጥተን ሌላ ችግር እንዲደርስ አንፈልግም፡፡ ይህ የሕግ የበላይነት የማያውቅ ሥርዓት እንግዲህ ሁላችንንም ሰብስባችሁ እሰሩን ብንል ለአንድ ሰሞን ዜና ሊሆን ይችላል፡፡ ግን እኛ ደግሞ እንዲሁ ተነሳስተን የምናደርገውን ትንሿንም ጥረት እንዲያጠፏት አንፈልግም፡፡ ከዚህ ሁሉ በመነሳት የተቆጠብንባቸው ሁኔታዎች አሉ፡፡ ለመሰብሰብ ጠይቀናል፣ ለመሠለፍ ጠይቀናል፡፡ ለዚህ ሁሉ የሚሰጠው ምላሽ አናውቅም የሚል ነው፣ ዕውቅና አንሰጥም ነው፡፡ እንግዲህ ዕውቅና ያልተሰጠውን ነገር ደግሞ ብናደርግ እንደለመደው ወጥቶ መተኮስ ሊጀመር ነው፡፡

ለዚህ ዓይነቱ ነገር ደጋፊያችንንና ሕዝባችንን ማጋለጡ ተገቢ አሠራር አይሆንም ብለን ነው ቆጠብ ብለን ያለነው፡፡ በኢትዮጵያ ምድር የትም ቦታ እንሰበሰብ፣ እንሠለፍ ብለን ብንጠይቅ ይህ ሥርዓት አይፈቅድም፡፡ ስለዚህ መድረክ ከሕዝቡ ጋር መገናኘት ማለት ትልቅ የሚፈራው ነገር ሆኖበታል፡፡ ይህን እንዴት እናድርግ? ይህ መንግሥት የሚፈልገው ግጭት ነው፡፡ ሕጉ የሚለው አሳውቁ ነውና አሳውቀን እንወጣለን ስንል መጋጨት፣ ስብሰባ ልንቀመጥ ነው ስንል መጋጨት፡፡ ቀደም ብሎ የተፈጠረውን ግጭት መፍትሔ መስጠት ባልተቻለበት ሁኔታ በችግር ላይ ችግር እየጨመሩ መሄድ ለዚህ አገር ጤነኛ የፖለቲካ ድባብ አይሆንም፡፡ ያም ያሳስበናል ማለት ነው፡፡ ሁሉም ነገር ከቁጥጥር ውጪ የወጣበት ሁኔታ ቢፈጠር እዚህች አገር ላይ ምንድነው ሊከሰት የሚችለው የሚለው ደግሞ ያስስበናል፡፡ በዚህም ምክንያት ሰብሰብ የማለት ጉዳይ እንጂ ዕቅዶቹ ጠፍተውን አይደለም፡፡ ምን ማድረግ እንዳለብን እናውቃለን፡፡

ሪፖርተር፡- የሕግ ባለሙያዎችና የፖለቲሳ ሳይንስ ጠበብቶች የሚያስቀምጡት ‹‹ሻዶው መንግሥት›› (Shadow Government) የሚባል ጽንሰ ሐሳብ አለ፡፡ ይህ ምንድነው ተቃዋሚ ፓርቲዎች በመንግሥት መዋቅር ሥር እንዳሉ መሥሪያ ቤቶችና ኃላፊዎች ሁሉ ራሳቸውን በማዘጋጀት፣ አመራሮቻቸውን የማብቃት ሥራ ይሠራሉ፡፡ ከዚህ አንፃር በመድረክ በኩል ነገሮችን በቅርብ እየተከታተለና ስህተቶችን እየነቀሰ የሚያወጣ ሥርዓት ከመዘርጋት አንፃር የሚደረግ ጥረት አለ?

ፕሮፌሰር በየነ፡- ለኢትዮጵያ ፖለቲካ ይህ ሁሉ ቅንጦት ነው፡፡ አሁን አንተ የምትነግረኝ የቅንጦት ፖለቲካ ነው፡፡ እኛ የምንናገረው እኮ ስለመሠረታዊ አሠራሮች ነው፡፡ ልክ ዝንጀሮዋ ‹‹መጀመሪያ የመቀመጫዬን›› እንዳለችው፡፡ ምን ላይ ተቀምጠህ የት ላይ ቆመህ ነው ይህንን የምታስበው? እያንዳንዱ ትንንሽ መሰባሰብ በትልቁ ጥርጣሬ በሚታይበት፣ መንግሥት በምላስ ብቻ የተናገረን ሰው እንኳን የቁም እስረኛ አድርጐ ከዚህ ብትወጣ እንገልሃለን የሚልና ከሕግ በላይ የሆነ ፀባይ በሚያሳይበት አገር፣ እንዲያው ዝም ብለን ሁሉንም ነገር አንሞክርም፡፡ አንድን ሥርዓትንም ሆነ የሰው ልጅን የሚገዛው እኮ ሕግ ነው፡፡ ሕግ አለ ብለን ነው እኮ መጥተን የምንሄደው፡፡ ይህ መንግሥት ግን ይህን እምነት እየጣሰ ነው፡፡ ስለዚህ ይህን ያህል የዋህ ሆነን እንዲያው የመቀመጫችንን እንኳን ሳናረጋግጥ ወደዚህ ዓይነት ነገር ውስጥ ለመግባት ዱለታ ነው የሚሆነው፡፡

ሪፖርተር፡- ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር በሚያግባቧችሁ የጋራ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመሥራት ንግግር እንደጀመራችሁ በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን ሲገለጽ ነበር፡፡ የሁለቱ ፓርቲዎች ውይይት ምን ደረጃ ላይ ይገኛል?

ፕሮፌሰር በየነ፡- አብረን በሚያግባቡን ጉዳዮችና አንዳንድ እንቅስቃሴዎች ላይ አቅማችንን አስተባብረን እንንቀሳቀስ የሚሉ ደብዳቤዎች ተለዋውጠናል፡፡ በተለዋወጥናቸው ደብዳቤዎች መስማማት ነው እንጂ፣ አከራካሪ ወይም ያልተስማማንበት መንፈስ የለም፡፡ ከዚህም በመነሳት በጋራ ከመድረክም ወገን ከሰማያዊም ወገን ሁኔታዎችን የሚከታተሉ ሰዎች መድበን የጋራ ኮሚቴ አቋቁመናል፡፡ ያ ኮሚቴ ለምሳሌ ይህንን ሰላማዊ ሠልፍ አብሮ እንዲያቅድ ነው ተልዕኮ የተሰጠው፡፡ አሁንም ከፊታችን የምናስባቸውን ቀጣይ ዕቅዶችና እንቅስቃሴዎች ይህ መንግሥት ዕድሉን ከሰጠን አብረን ነው የምናቅደው፡፡ እናም ሌሎችንም እነደዚሁ ሕዝባዊ የሆኑ ጉዳዮችን አብሮ ለማስተጋባትና አንዱ አቅም ባነሰው ጊዜ ሌላኛው እየደገፈው የሕዝብን ጥያቄ አጉልቶ ለማውጣት፣ ያለውንም ሥርዓት ወደ ውይይት መድረክ እንዲመጣ ለመጋበዝ የሚያስችሉ እንቅስቃሴዎችን አብረን እናቅዳለን፣ ተግባራዊም እናደርጋለን፡፡ ይኼ ነው መቋጫው ሌላ ብዙ ዝርዝር ነገር የለውም፡፡ በአቋም ጉዳይ በዓላማ ጉዳይ እዚያ ውስጥ አልገባንም፡፡ በተግባራዊ እንቅስቃሴ ላይ አብረን ለመሥራት አዎ ተስማምተናል፡፡

ሪፖርተር፡- በአሁኑ ጊዜ በአገሪቱ አስከፊ የሆነ ድርቅ ተከስቷል፡፡ መድረክ በዚህ ጉዳይ ላይ ምን ሠርቷል? ምን እያደረገ ነው? የፓርቲው አመራር አባላትስ ድርቅ በተከሰተባቸው አካባቢዎች በመገኘት የአቅማችሁን አስተዋጽኦ የማድረግና ከሕዝቡ ጎን መቆማቸውን አሳይተዋል?

ፕሮፌሰር በየነ፡- ጉዳዩን እየተከታተልን ነው፡፡ በጣም ሰፋ ባለ ሁኔታ ሕዝቡ መሀል በመገኘት ይህንን የድርቁን መጠንም ሆነ ሁኔታ ገምግማችኋል ወይ ለምትለው፣ በእርግጠኝነት ለማስቀመጥ አመራሩ ከዚህ ተነስቶ ሄዶ እዚያ ተገኝቶ ነገሮችን የሚገመግምበት አቅም የለንም፡፡ ድርቅ የተከሰተባቸው አካባቢዎች ደግሞ ቆላ ቀመስ የሆኑ ራቅ ራቅ ያሉ አካባቢዎች ናቸው፡፡ ይህ ሲሆን ግን በየአካባቢው አባላት አሉን፡፡ ከእነሱ ዘወትር ሪፖርት እናገኛለን፡፡ መኪና አስነስተን ሄደን ደርሰን የደረስንበትን ሁሉ በመታዘብ ልንሰጥ የሚገባውን የሞራል ድጋፍ አድርገናል አልልም፡፡ ለዚህ አልታደልንም፡፡ ይህም አላስፈላጊ ሆኖ አግኝተነው ሆኖ ሳይሆን ሁኔታዎች የፈጠሩብን ነው፡፡ ነገር ግን ከየአካባቢው ካሉ አባሎቻችን ሁልጊዜ ሪፖርት ይደርሰናል፡፡

 

የህዝባችን እንባ ለማቆም ሁላችንም አምርረን እንታገል !  

def-thumb
ኢትዮጵያ አገራችን ከፍተኛ የሆነ የህልውና ስጋት ተደቅኖባታል። ልጆቿ በያቅጣጫውዋይታቸውን እያሰሙ ነው። የወያኔ የተበላሸ ስርዓት እና የስግብግብነት ተፈጥሮተደማምረው ህዝባችንን በቃላት ሊገለጽ በማይቻል ሰቆቃ ውስጥ ከተውታል። ህሊናይዘው መፈጠራቸው ጥያቄ ውስጥ እስከሚገባ ድረስ፣ ቅልብ የወያኔ ገዳይ ወታደሮችበኦሮሞ እናቶችና ህጻናት ላይ የፈጸሙት ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ በረጅሙ ታሪካችንያላየነውና ያልሰማነው ነው። ባለፉት መንግስታት ለነጻነታቸው የጮሁ ወጣቶችበስርዓቱ የጸጥታ ሃይሎች መገደላቸው ታሪክ የመዘገበው ሃቅ ነው፣ ነገር ግን ህጻናትናታዳጊዎች እጅግ ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ ግንባራቸውንና ደረታቸውን በጥይት እየተመቱ ሲወድቁ ስንመለከትይህ በታሪካችን የመጀመሪያ ነው። አለም በፍጥነት እየተለወጠ ባለበት በዚህ ዘመን እንዲህ አይነት ጭካኔየተሞላበት እርምጃ መወሰዱ ደግሞ የአገዛዙ ቁንጮዎችንና እነሱን ተከትለው ወደ ጥፋት አረንቋ የሚተሙትንሁሉ ከሰው መፈጠራቸውን እንድንጠይቅ የሚያደርግ ነው። የኦሮሞ ህዝብ በአጋዚ ወታደሮችና በፌደራል ፖሊሶችበግፍ ለተነጠቀው ልጆቹ ድምጹን ከፍ አድርጎ አልቅሷል፤ ቁጭቱን በቻለው መንገድ ሁሉ ሊገልጸው ሞክሯል።ነገር ግን እስካሁኗ ሰአት ድረስ መገደሉ፣ መታሰሩ፣ መሰደዱ፣ መዋረዱ አለቆመም። አገዛዙ ለአንድ ቀን በስልጣንላይ ውሎ እስካደረ ድረስ ይኸው ግፍ ይቀጥላል።
የወልቃይት ህዝብ እኛ እንደፈለግን እንጅ አንተ እንደፈለክ አትኖርም ተብሎ ተፈርዶበት ያለፉትን 25 ዓመታትበስቃይ አሳልፏል። አሁንም እንደገና ” እኛ እናውቅልሃለን እየተባለ” መከራውን እየበላ ነው። በአካባቢውያንዣበበው የሞት ደመና እጅግ አደገኛ ነው። እየተረጨ ያለው መርዝ ካልቆመ፣ አካባቢው በአጭር ጊዜ የግጭትአውድማ መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው። ዘራፊው የህወሃት ቡድን ግጭትን ከማባበስ በተረፈ ችግሩን የማስቆምፍላጎት አላሳዬም።
በዚሁ አካባቢ የአንድ አገር ሎጆችን ቅማንትና አማራ እያሉ እርስ በርስ ለመከፋፈልና ለማጋጨት ወያኔ እየዘራውያለው ይጥፋት ዘር እስካሁን ከደረሰው እልቂት በላይ ሌላ እልቂት ይዞ እየመጣ ነው። የአገር ሰላምና ጸጥታእናስከብራለን ብለው መሳሪያ የታጠቁ ሃይሎች በሁለቱም ወገን ግጭት ለመቀስቀስ ሲዶልቱ፣ ሲያቅራሩና ሲሸልሉውለው እያደሩ ነው። ከዚህ ሁሉ የእልቂት ጀርባ ያሉት ዜጎችን ካላጋጩ ውለው ማደር የማይችሉት የወያኔመሪዎችና ግብረአበሮቹ ናቸው።
የደቡብ ህዝብም ልጆቹን በሞት እየተነጠቀ ነው። በሺዎች የሚቆጠሩ ልጆቹም በየእስር ቤቱ ታጉረዋል፡፡ ዛሬ ወደኮንሶ፣ አርባምንጭ፣ ቁጫ፣ ሃመር ወዘተ ብንሄድ የምንሰማው ዋይታና ለቅሶ ነው።
የሶማሌው ወገናችን በልዩ ሃይል አባላት የዘረ ፍጅት እየተፈጸመበት ነው፤ አፋሩ ፣ ጋምቤላውና ቤንሻንጉሉከቀየው እየተፈናቀለ፣ መሬቱን እየተነጠቀ ለሞትና ለዘላለማዊ ድህነት ተዳርጓል።
ይሄ ሁሉ መከራና ግፍ ሳያንስ ከ20 ሚሊዮን በላይ የሚሆነው ህዝባችን በረሃብ እየተጠቃ መሆኑ በሰፊውእየተነገረ ነው። በአብዛኛው የአገሪቱ ክፍል በተፈጥሮ በሚሳበብ የአየር መዛባት ችግር ምክንያት ባለፈው የምርትዘመን የተዘራው ሰብል እንዳለ ወድሞአል:: በዚህም የተነሳ በህዝባችን ላይ ያንዣበበው የረሃብ አደጋ እስከዛሬካየነው ሁሉ የከፋ እንደሚሆን አለማቀፍ ድርጅቶች እያስጠነቀቁ ነው። ላለፉት 10 አመታት በእጥፍ አሃዝየኢኮኖሚ እድገት አስመዝግቤያለሁ እያለ ህዝብ ሲያደነቁርና የለጋሽ አገሮችን ቀልብ ለመሳብ ሲባዝን የኖረውወያኔ ግን በፈጠራ ታሪክ የገነባው ገጽታ እንዳይበላሽበት ረሀቡን ለመደበቅና የጉዳት መጠኑን ለማሳነስ ብዙ ርቀትተጉዟል። ያም ሆኖ የችግሩ ግዝፈት እያየለ ሲመጣና ተጎጂዎች ከቀያቸው ተፈናቅለው ወደየ አጎራባች ከተሞችመሸሽ ሲጀምሩ ሳይወድ በግድ ለማመን ተገዷል። ። በሰሜን ወሎ፣ በትግራይ፣ በአማራ፣ በአፋር፣ በደቡብናበኦሮምያ በድርቁ ምክንያት በምግብ እጥረት እየተሰቃዩ የሚገኙ እናቶችና ህጻናት ቁጥራቸው ከጊዜ ወደ ጊዜእየጨመረ ቢመጣም፣ ወያኔ ግን እንደ ኢኮኖሚው ሁሉ እዚህም ላይ የቁጥር ጨዋታ በመያዙ አሁንም ተገቢውእርዳታ ለህዝባችን በጊዜ እንዳይደርስ እየተከላከለ ለህዝብ መከራ ደንትቢስነቱንና ጨካኝነቱን እያሳየ ይገኛል።
ወያኔ በህዝባችን ላይ የደገሰው የሞት ድግስ በዚህ ብቻ አያበቃም። የኑሮ ውድነቱ ጣሪያ በመንካቱ ህዝቡእያንዳንዷን ቀን የሚያሳልፈው በጣርና በጭንቅ ነው፤ ከጥቂት የወያኔ ባለስልጣናትና ሸሪኮቻቸው ውጭ ያለውኢትዮጵያዊ ኑሮው ሲኦል ሆኖበታል። ችግሩና መከራው እየከፋ ሲሄድ እንጅ እየቀነሰ ሲሄድ አይታይም።በሚብለጨለጩና የህዝቡን መሰረታዊ የፍጆታ ችግር በማይቀርፉ ስራዎች ላይ በማትኮር ህዝብን በልማት ስምለመሸንገል ሙከራ ቢደረግም፣ አልተሳካም። ከኑሮ ውድነት በተጨማሪ ስራ አጥነቱ፣ አፈናው ፣ ስደቱ እስርናእንግልቱ፤ ሙስናው፣ የፍትህ እጦቱ ወዘተ የአገራችን ህዝብ ኑሮውን በጉስቁል እንዲገፋ አድርጎታል።
አርበኞች ግንቦት 7 አገራችንና ህዝባችን ከዚህ ሁሉ መከራና ስቃይ መውጣት የሚችለው አገዛዙ የዘረጋውየተበላሸ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ፖሊሲዎች ሲለወጡና ከህዝብ፡በህዝብ ለህዝብ የሚቆም የመንግሥት ሥርዓትበአገራችን እውን መሆን ሲችል ብቻ ነው ብሎ ያምናል:: የወያኔ የሥልጣን ዕድሜ በተራዘመ ቁጥር በህዝባችንላይ የሚደርሰው በደልና ሰቆቃም እንዲሁ እየተራዘመ ይሄዳል:: ህዝባችን ከሚደርስበት ለቅሶና መከራ እንዲገላገልሁላችንም በያለንበት አምርረን እንታገል::

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ
አርበኞች ግንቦት7

U.N. Secretary General Ban Ki-moon told African leaders on Saturday they should not use legal loopholes or undemocratic constitutional changes to “cling to power”, and that they should respect term limits. Posted on January 30, 2016by syitda

Ban ki-moon

ADDIS ABABA: U.N. Secretary General Ban Ki-moon told African leaders on Saturday they should not use legal loopholes or undemocratic constitutional changes to “cling to power”, and that they should respect term limits.

Ban was addressing a two-day summit the African Union, a group of 54 states where several leaders have been in power for decades, some have changed constitutions so they can stay on and others are accused of seeking to remove limits.

The debate about term limits has gained momentum after triggering unrest in places such as Burundi and Congo Republic.

“Leaders should never use undemocratic constitutional changes and legal loopholes to cling to power. We have all seen the tragic consequences when they do,” Ban told the gathered presidents, including Zimbabwe’s veteran leader Robert Mugabe.

It echoed remarks made by U.S. President Barack Obama in the same AU hall on a trip to Ethiopia in July.

Mugabe, who turns 91 in February and the only leader Zimbabweans have known since 1980, made one of his regular swipes at Western powers who he accuses of still harbouring colonial ambitions and of monopolising power at the United Nations.

“Do we allow that group to continue … to harass us even in our independent countries,” Mugabe asked after Ban had spoken.

One of the top items on this summit’s agenda is the crisis in Burundi, where violence erupted after President Pierre Nkurunziza announced his bid for a third term that opponents said was illegal. He won a disputed election in July.

Supporters cite a court ruling that said he could run.

In neighbouring Rwanda, a constitutional change approved in a referendum means President Paul Kagame, who has been in office since 2000 and effectively in power far longer, can now run again in 2017 and could stay on until 2034 if he wishes.

Western powers criticised Kagame for not stepping aside, saying he should set an example.

Uganda’s Western allies have said President Yoweri Museveni, bidding for another term in a February vote after three decades in office, should consider quitting although the Ugandan constitution does not set any term limits.

“Leaders must protect their people, not themselves,” Ban said. “I commend those leaders who committed to stepping aside and respect constitutional term limits.”

Tanzania’s Jakaya Kikwete left office after a maximum two terms last year. However, the candidate of Kikwete’s CCM party that been in power for more than half a century won the vote.

(Writing by Edmund Blair; Editing by Raissa Kasolowsky)

– Reuters

ከአፍሪካ ህብረት አጀንዳዎች ይልቅ የሙጋቤ መልእክት ትኩረት አግኝቷል

የአፍሪካ ህብረት የሊቀመንበርነት ጊዜያቸውን ያጠናቀቁት የዚምቧቡዌው ፕሬዘዳንት ሮበርት ሙጋቤ በ26ኛው የመሪዎች ስብሰባ ለተተኪያቸው ቦታቸውን ከመልቀቃቸው አስቀድሞ ህብረቱን በመወከል በተባበሩት መንግስታት፣በነጮችና በባራክ ኦባማ ላይ ጠንከር ያለ ወቀሳ ሰንዝረዋል፡፡

ሙጋቤ ንግግር ለማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው ቦታ ሲያመሩ ከአጋሮቻቸው ደመቅ ያለ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፣ ፕሬዘዳንቱ በንግግራቸው ከተለመደው ከፋ ባለ መልኩ ምዕራባዊያንን፣ነጮችንና የአሜሪካውን ፕሬዘዳንት አብጠልጥለዋል፡፡
የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሐፊ ባንኪ ሙን የ91 ዓመቱ ሙጋቤን ንግግር እያደመጡ በተቀመጡበት ወንበር በጭንቀት ተውጠው ተስተውለዋል፣ ‹‹ሞተዋል አልያም በጠና ታመዋል›› የሚሉ ወሬዎች ሲነዙባቸው የሰነበቱት ሙጋቤ አፍሪካ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ቋሚ ውክልና ካላገኘች ድርጅቱን ለቅቃ እንደምትወጣ ዝተዋል፡፡
‹‹የጸጥታው ምክር ቤት እንዲሻሻል ደግመን ደጋግመን ጠይቀናል››ያሉት ተሰናባቹ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ‹‹አፍሪካዊያን ለውጥና ውጤት በሌለው የድርጅቱ ወሬ ተሰላችተዋል››ብለዋል፡፡
አፍሪካዊያን እውነተኛ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አባላት አይደሉም ያሉት ሙጋቤ ‹‹አባላቶቹ ባለነጭ ቆዳዎቹ ብቻ ናቸው፣ አንድ ቀን ግን አፍሪካዊያን ከወሰኑ ከድርጅቱ ጋር ገደል ግቡ ብለው ሊወጡ ይችላሉ››ማለታቸው ተሰምቷል፡፡
‹‹የተባበሩት መንግስታት በህይወት እንዲቆይ ከተፈለገ እኛ አፍሪካዊያን እኩል መብት ያለን አባላቱ መሆን አለብን››በማለት ተናግረዋል፡፡ሙጋቤ ጣታቸውን ወደ ባንኪሙን ቀስረውም ‹‹እርስዎ ጥሩ ሰው ነዎት ነገር ግን እኛ እንዲታገሉልን አናስገድድዎትም፣ ግዳጅዎም ይህ አይደለም ነገር ግን እኛ ስለራሳችን ማንነትና ስብዕና እንደ አፍሪካዊ እንታገላለን››ብለዋል፡፡
ለተባበሩት መንግስታት አድርሱልን በማለትም ሙጋቤ ባንኪ ሙንን ‹‹አፍሪካዊያንም መንፈስ ሳይሆኑ አለም የምትገባቸው ሰዎች መሆናቸውን ንገሩልን››ብለዋቸዋል፡፡
የድርጅቱ ዋና ጽህፈት ቤት በኒውዮርክ መገኘቱን ‹‹ስህተት›› ያሉት ሙጋቤ ዋና ጽህፈት ቤቱ ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር ባላቸው አገሮች ለምሳሌ በቻይና፣በህንድ ወይም በአፍሪካ አህጉር መገኘት ይገባው ነበር ብለዋል፡፡
አፍሪካዊያንና ሌሎች በኒውዮርክ መገኘታቸውን በመጥቀስም ‹‹ነገር ግን በዚያ ነጫጭ ፊቶችና ፒንክ አፍንጫ ያላቸው ከእኛ ቀጠለው ይገኛሉ ፣እነርሱ ከእኛ ጋር በቁጥር ሲነጻጸሩ ምን ያህል ይሆናሉ?›› በማለት ባንኪሙንን ጠይቀዋል፡፡
ሙጋቤ ባንኪሙንን በንግግራቸው መሐልም ማወደሳቸው አልቀረም ‹‹አፍሪካ ኢቦላን እንድትዋጋ፣ሽብርተኝነትን እንድትከላከልና ሌሎች ቀውሶች ባጋጠሟት ወቅትም ከአፍሪካዊያን ጎን መቆምዎን አንዘነጋም›› ብለዋቸዋል፡፡
የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማን ‹‹የነጮች አሻንጉሊት›› በማለት የወረፏቸው ሙጋቤ ‹‹ነጮቹ አፍሪካዊያንን በየውቅያኖሱ ሲወረውሩ እንደነበር የዘነጉ ጥቁሮች በተለይም ኦባማ አሁን ጥቁሮች ነጻ ሰዎች እንደሆኑ ያስባሉ፣ ነገር ግን እርሱ (ኦባማ) ምንድን ነው ? የእነርሱን ቋንቋ ለመናገር ድምጽ የተሰጠው? የእኛን ሳይሆን የእነርሱን እንቅስቃሴ የኮረጀ አይደለምን? እነርሱ (ነጮች)እስካሁን ድረስ የበላይ ናቸው››፡፡
ሙጋቤ ጥቁሮች በአሜሪካ እስካሁን ድረስ የበታቾች መሆናቸውን በመጥቀስ ትምህርትና የጤና መድህን ዝቅተኛ በሆነበት ኒውዩርክ ውስጥ በሚገኘው ሃርለም በብዛት እንደሚኖሩ ጠቅሰዋል፡፡ ‹‹ጥቁሮች በመንገድ ላይ በጥይት ይመታሉ ፣ ማንም ይህንን ለመናገር የሚፈልግ አይመስልም፡፡ ነገር ግን እነርሱ(ነጮቹ) ስለ እኛ መናገር ይፈልጋሉ››ብለዋል፡፡
የቅኝ ግዛት ዘመን ካበቃ በኋላ እንኳን የቀድሞዎቹ ቅኝ ገዢዎች በሁሉም የአፍሪካ ክፍሎች በእርዳታ ድርጅቶች ስም እንደሚገኙ ያወሱት ሙጋቤ ‹‹ሰላዩችና አስመሳዩች ቢሆኑም አንዳንዶች እኛን ለመደገፍ ነው እዚህ የሚገኙት ሲለ ይደመጣሉ፡፡ሌላው ቀርቶ የስርዓት ለውጥ እንዲደረግ ታጣቂ ቡድኖች መካከልም ይገኛሉ››በማለት የነጮችን ጣልቃ ገብነት ተቃውመዋል፡፡
አስር ደቂቃ ለንግግር ተሰጥቷቸው የነበሩት ሙጋቤ ለአንድ ሰዓት ያህል በመድረኩ ላይ ቆይተዋል፡፡በንግግራቸው ማጠቃለያም የሊቀመንበርነት ቦታቸውን ለተረከቡት ለቻዱ ፕሬዘዳንት ኢድሪስ ዴቤይ ‹‹አጠገብዎ የምገኝ በመሆኑ በፈለጉኝ ሰዓት ሊደውሉልኝ ይችላሉ፣ አምላክ ከእኛ በፊት የሄዱትን እንድቀላቀል እስኪጠራኝ ድረስ እዚሁ ነኝ››ብለዋቸዋል፡፡
ሙጋቤ ወደ መቀመጫቸው ከማምራታቸው አስቀድሞም በጥቁሮች የስልጣን ሰላምታ ጉባኤውን ተሰናብተዋል፡፡የደቡብ አፍሪካው ፕሬዘዳንት ጃኮብ ዙማ ሲቀሩ ለሙጋቤ ቀሪዎቹ ፕሬዘዳንቶች ከመቀመጫቸው ብድግ ብለው አክብሮታቸውን አሳይተዋቸዋል፡፡

 posted by Aseged Tamene

Starvation threatens millions in Ethiopia: UN

Starvation in Ethiopia threatens millions

The United Nations (UN) has warned that millions of people in Ethiopia, including children, are in danger of starvation as the African country faces dire food shortages.

The UN Office for the Coordination of Humanitarian Affairs (OCHA) warned Thursday that a break in food deliveries to the country could leave huge numbers without life saving aid.

“We need urgent, rapid action to scale up our support to the Ethiopian government and people,” the OCHA said in a report.

“Without additional resources, the food sector projects a full pipeline break in a couple of months,” read the report. “The country is once again facing devastating climatic conditions: rains have failed; millions of people need food aid; children are suffering from severe malnutrition.”

At least 10.2 million people need food aid in Ethiopia, a figure that the UN said could rise sharply.

The El Nino weather phenomenon sparked a dramatic rise in the number of people going hungry in East Africa. It has caused entire harvests to be lost in some regions in the region.

In another report, the OCHA warned earlier this month that Ethiopia “is once again facing devastating climatic conditions: rains have failed; millions of people need food aid; children are suffering from severe malnutrition.”

Source: Press TV

እራስን ያለመሆን በሽታ! | አገሬ አዲስ

አንድ ሕዝብ ወይም ሰው የሚታወቅበት የራሱ የሆነ የማንነት መግለጫ ባህሪያት፣ታሪክ፣ባህል መልክ፣ቦታና ስም… ወዘተ አለው፡፤እነዚህን የመታወቂያ ገጾች ለሌሎች ሲል አሳልፎ የማይሰጠው ወይም የማይቀይረው እሴቶቹ ናቸው።ሌሎች ማንነቱን አክብረው  እንዲቀበሉት ማድረግ እንጂ ለሌሎች ሲል ማንነቱን ስሙን፣ባሕሉን፣ታሪኩን ለውጦና ቀይሮ መቅረብ በራሱ ላይ ቸንፈትንና ድክመትን አምኖ መቀበል፣በራስ አለመተማመን እንጂ ዘመናዊነትና ብስለት አይደለም።

Tensaye

ይህን አጭር ትችትና አስተያየት ለመሰንዘር የተገደድኩበት ዋናው ምክንያት በአሁኑ ጊዜ በእኛ በኢትዮጵያውያን ጎልተው በመታየት ላይ ያሉ ድክመቶች እንዲታረሙና ወደማንነታችን እንድንመለስ፣በራሳችን እንድንኮራና እንድንተማመን የሚረዳ ሃሳብ ስለመሰለኝ ነው።

ከመግቢያው ላይ ለማሳየት እንደሞከርኩት እኛ ኢትዮጵያውያን በሌላው የዓለም ህብረተሰብ የምንታወቅበት ብዙ የሚያኮራ ታሪክና ባህል ሲኖረን አንዳንድ የምናፍርባቸው ግን ልናርማቸው የምንችላቸው ድክመቶችም አሉን።ከነዚህ ድክመቶቻችን ውስጥ ለውጭ ሃይሎች፣እምነቶች፣ ባህሎች፣ ልማዶች ፣ስያሜዎች መንበርከካችንና ማጎብደዳችመን ነው።

ሌላውን ብዥታ ወደጎን ትተን ትንሹንና አንዱን ፣ በስማችን ዙሪያ ያለውን ያለመሆን ችግር ነጥለን ብናይ ምን ያህል በራሳችን የምናፍርና የማንተማመን መሆናችንን ለመረዳት እንችላለን።

የሌላውን አገር ሕዝብ ከእኛው ሁኔታ ጋር ብናስተያየው ድክመታችንን ለማየት ይረዳናል።

በአሁኑ ጊዜ በእኛ በኢትዮጵያውያን በተለይም በአዲሱ ትውልድ የሚታየው እራስን ያለመሆን በሽታ እየተስፋፋ በመሄድ ላይ ነው።ስምን ለውጦ የባዕድ አገር ስም መተካቱ እንደዘመናዊነት ወይም ስልጣኔ ተቆጥሮ የማንነት ውዥንብር ፈጥሯል።

በቅኝ ገዢዎች ወረራ ዘመን የተወራሪው አገር ዜጋ በተለይም ወጣት ወራሪዎቹ ለመጥራት እንዲመቻቸው በሚያወጡት  ስም እንዲጠራና እንዲቀበል እንደሚያስገድዱት  በሰባዎቹ መጨረሻ ላይ ዘ ሩት (The Root) የሚለው ፊልም ኪንታኩንቴ የሚባለው ወጣት አፍሪካዊ አገልጋይ የነጭ ጌታው ባወጣለት ቶቢ በሚልው ስም ለመጠራት አሻፈረኝ በማለቱ የደረሰበትን ስቃይ እንደምሳሌ መጥቀሱ ይበቃል።አሁንም የዚያ ውጤት በተለያዩ የቅኝ ግዛት በነበሩ አገሮች ዜጎች የስም ስያሜ ላይ ትልቅ ተጽእኖ እንዳሳደሩበት በገሃድ ይታያል።ተወላጁ ብቻ ሳይሆን መሬትና አገሩ ሳይቀር ነጮች በሚመቻቸው ስያሜ ይጠሩ እንደነበረና አሁንም እንደሚጠሩ እናውቃለን።አንዳንዶቹ አገሮችም ተነጥቀው የነበረውን የማንነትና አገር ስያሜ እያስመለሱ፣ከሰፈረባቸው የቅኝ ግዛት ተጽእኖ ለመላቀቅ ሞክረዋል።በመሞከርም ላይ ናቸው።ለምሳሌ ሮዴዚያ፣በዚምባብዌ፣ዳሆሜ በቤኒን…ወዘተ እየተተካ መጥቷል።

ኢትዮጵያውያን ግን የቀድሞ አባቶቻችን  ምስጋና ይድረሳቸውና ለዚህ ግዳጅ የተጋለጡ አልነበሩም፤እኛንም አላጋለጡንም።ለወራሪዎች ባለመንበርከካቸው አገራቸውን አሳልፈው አልሰጡም፤በዚያም ምክንያት ታሪክና ባህላቸውን፣ማንነታቸውን ሳያስደፍሩ ቆይተዋል።

ያ በአባቶቻችን ተከብሮ የቆየ የማንነት ስያሜ አሁን በምን ደረጃ ላይ ይገኛል ብለን ብንጠይቅ መልሱ የሚያሳፍር ሆኖ እናገኘዋለን።

በአገራችን ልማድ አንድ ልጅ ሲወለድ ስም የሚወጣለት፣ደስታን፣ተስፋን፣ምኞትን የሚያንጸባርቅ ወይም የነበሩበትን ሁኔታ የሚያስታውስ ትርጉም ያለው አጠራር ነበር።የአንዳንድ አገር ሕዝብም ለልጁ የሚያወጣው ስም ቋንቋው ቢለይም ከዚህ አይነቱ ስሜት እንደሆነ መገመት ይቻላል።የልጁን ስም ለሌላው ዜጋ ለአጠራር እንዲመችና እንዲቀለው ብሎ በማሰብ ብቻ ወይም የራሱን አሰያየም በመናቅና በመጥላት የሌላውን አገር ዜጋ የስም  አወጣጥ ካልተገደደ በቀር ወዶ የሚቀበል የለም።በእድገት የመጠቁ አገሮች እንደ ጃፓን፣ቻይና፣ሩስያ፣ህንድ…ወዘተ ያሉትን አገሮች የስም አወጣጥ ብናይ አንዱ የማንነታቸው መግለጫ በመሆኑ ከጊዜው ጋር እየቀያየሩ አለመምጣታቸውን እንገነዘባለን።ስማቸው ብቻ ሳይሆን አለባበሳቸው፣አመጋገባቸው፣ አነጋገራቸው ሳይቀር ሲወርድ ሲዋረድ የመጣውን ማንነታቸውን የሚያንጸባርቅ ነው።እዚህ ላይ የሚታረመው አልታረመም ማለት አይደለም፣እንደአስፈላጊነቱ መሰረቱን ሳይለቅ የተሻሻለ አቀራረብ ጨምረውበታል፤ያም ተገቢና አስፈላጊ ነው።

ወደእኛ መለስ ብለን ውስጣችንን ብንመረምር፣ኢትዮጵያውያን ከመሆን እያፈገፈግን የመጣን መሆናችንን እንረዳለን፤በፖለቲካው ዙሪያ ወይም በጎሳው መነጽር ለሚታዩት ድክመቶች መነሻ  በራስ አለመተማመንና እራስን ያለመሆን በሽታ ነው።እራስን መሆን ደግሞ ስም፣ባህልንና እምነትን ጠቅልሎ የያዘ ማንነት ነው።

በአገራችን ከሃምሳ ዓመት ወዲህ ያቆጠቆጠው እራስን ያለመሆንና የመጥላት በሽታ አሁን ከሚታይበት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል።ወላጅ ልጅ ሲወልድ የሚሰጠው ስም እንደቀድሞው ማንነትን ፣ኢትዮጵያዊነትን፣እምነትን፣ተስፋን፣ምኞትን የሚያንጸባርቅ ሳይሆን ከውጭ አገር የስም አሰያየም፣ክርስቲያኑ ከይሁዲ፣እስላሙ ከሙስሊም አገሮችና ሕዝቦች ጋር ያለውን ትስስር የሚያጎላና የሚያጠናክር ሆኖ ይታያል።አብዛኛው ወጣትም እናትና አባቱ፣ያወጡለትን ትርጉመ ሰፊና ብዙ የሆነውን ስሙን  በማይናገረው ቋንቋ፣በውጭ አገር በተለያም በፈረንጆቹ አጠራር  ዩሃንስ በጆኒ፣ሙሉጌታ በሙለር፣ጎሳዬ በጎሲ፣ታደለ በቴዲ፣እመቤት በኤሚ፣ጃክሶ በጃኪ፣እጅግ አየሁ በጂጂ…ወዘተ እየለወጠ ወዶና ፈቅዶ ጥገኛ ለመሆን ሲወስን ይታያል።ለምን ቢባል ኢትዮጵያዊ ያልሆነው ለመጥራት እንዲመቸው ነው ይባላል።ያ ለመጥራት እንዲመቸው የሚታሰብለት የውጭ አገር ዜጋ ግን ኢትዮጵያዊያን ለመጥራት እንዲመቻቸው ብሎ ስሙን አልቀየረላቸውም።

አንድ ገጠመኝን ላካፍላችሁና ልደምድም

የልጅነት አብሮ አደግ ጓደኛዬ ጋር ከተለያየን ብዙ ዘመናት አልፈዋል፤የት ደርሶ ይሆን? እያልኩ ሳስብ ቈይቻለሁ።የዃላ ዃላ ወደውጭ አገር፣ወደ አሜሪካ መውጣቱንና ያለበትን ከተማ ለማወቅ ቻልኩ።በጣም ደስታ ተሰማኝ ፤ለመገናኘት በሚኖርበት አካባቢ የሚኖሩትን የማውቃቸውን ኢትዮጵያውያን  አድራሻውን እንዲሰጡኝ ወይም የእኔን እንዲሰጡት  ጥያቄ አቀረብኩ ግን ያቀረብኩላቸው ጥያቄ  ሳይሳካ ቀረ።ስሙ ብርሃኑ ነበር ፣በብርሃኑ ብዙ ተሞከረ፣ግን አቤት የሚል ብርሃኑ ጠፋ።ከዓመታት ሙከራ በዃላ በሰሜን አሜሪካው የኢትዮጵያውያን የስፖርት በዓል ዝግጅት አጋጣሚ ሆነና ከምፈልገው የልጅነት ጓደኛዬ እኔ በብርሃኑ ደምሴ የማውቀው ቤሪ ዴምስ ተብሎ አገኘሁት።ይህን ተለጣፊ ስሙን ግን እናትና አባቱ በአገር ቤት የሚኖሩት ዘመዶቹ በተለይም ገጠር የሚኖሩት ሳያውቁትና ሳይጠሩበት እስከአሁን እኔ በማውቀው ስሙ በብርሃኑ ደምሴነቱ እየጠሩት ይኖራሉ።ለፈረንጆቹ እንዲቀል ብሎ ያወጣው ስሙ ለቤተሰቡ አልተመቸም።እንደውም እንዴት ያወጣንለትን ስም ይቀይራል፣ምን  ነካው?ታሞ ነው በጤናው በማለት በተለይም ወላጅ አባቱ ምርር ብለው ማዘናቸውን ተረድቻለሁ።

ያገሬ ልጆች ኢትዮጵያውያን ሁሉ፣ለትንሽ ጥቅም፣ብላችሁ እራሳችሁን አትጥሉ፣በማንነታችሁ አትፈሩ፣እራሳችሁን አክብራችሁ አስከብሩ፣ስማችሁን፣ማንነታችሁን ፣ታሪካችሁን ለማስከበር ጠበቃ ሁናችሁ ቁሙ፤በወዶገባ፣ወይም በፈቃዳችሁ ማንነታችሁን አትካዱ።ስማችሁና ኢትዮጵያዊነታችሁ የማንነታችሁ ምልክት ተስፋ፣ምኞት ፍቅር ገላጭ የሆነ ባለብዙ ትርጉም ያለው ነው።እድገትና ስልጣኔ ስም በመለወጥ ሳይሆን እራስን በእውቀት መለወጥ ሲቻል ነው።ጎጅውን ባህል፣የመለያየትንና የጥላቻን መንፈስ፣እራስ ወዳድነትንና ቂም በቀልን ለማሶገድ መጣርና መወዳደር ተገቢ ነው።ከሌላው አገር ዜጋ ጋር መደረግ ያለበት ውድድር በችሎታ ዙሪያ እንጂ የራስን መታወቂያ ቀዶ በመጣልና የተውሶ ማንነትን ወይም እነሱ የሚፈልጉትን በመቀበል አይደለም።ሌላው ዜጋ ስማችሁን ለውጦ ቢጠራችሁ እንኳን አትቀበሉት፣በትክክለኛ ስማችሁ እንዲጠራችሁ አሳስቡት።እናንተ የውጩን ዜጋ በስሙ እንደምትጠሩት ሁሉ፣እናንተም በኢትዮጵያዊው ስማችሁ ለመጥራት ስታስገድዱት አስተካክሎ እንደሚጠራችሁ እመኑ።እራስን መሆንና በራስ መተማመን ከዚህ ይጀመራል።አገራችሁንም በሚያዳክምና በሚነጣጥል መልኩ፣ ማንነታችሁ በክልል አጥር ውስጥ ተወስኖ እንዲቀር ሲደረግ አትቀበሉ።ትልቅነታቸሁን በትንሽነት አትለውጡት።

ኢትዮጵያዊነትና ኢትዮጵያ ለዘላለም ይኑሩ!!

 

 

‹‹ማዕከላዊ ነው እንዴ ያለነው?›› (ክፍል ፪)

በናትናኤል ፈለቀ
(ካለፈው የቀጠለ)
የማታው የመፀዳጃ ሰዓት አብቅቶ እስረኞችን ቆጥረው በሩን የሚቆልፉት ፖሊሶች መጡ፡፡ ሼህ ጀማል ዘወትር እንደሚያደርጉት የመጡት ፖሊሶችን ሰዓት ጠየቋቸው፡፡ አልፎ አልፎ በቁጣ ተሞልተው ከሚመጡት ፖሊሶች በስተቀር ሰዓት ለመናገር አብዛኞቹ ተባባሪዎች ናቸው፡፡ 12 ሰዓት ከ10 ደቂቃ እንደሆነ የተነገራቸው ሼህ ለመግሪብ ጸሎት የቀረው ግማሽ ሰዓት እንደሆነ ክፍሉ ውስጥ ለነበሩ የእስልምና እምነት ተከታዮች አሳወቁ ኡመድ ለፈረሃን ተረጎመለት፡፡
ደቂቃዎች አልፈው የፀሎት ዝግጅት ላይ እያሉ ከሳይቤሪያ ኮሪደር መግቢያ ላይ የሚንቆጫቀጭ የካቴና ድምፅ በከስክስ ኮቴ ታጅቦ ተሰማ፡፡ ድምፁ ምን ማለት እንደሆነ ክፍሉ ውስጥ ያሉት 14ቱም ይገባቸዋል፡፡ በእስር ለቆዩት ሰዎች ግር ያላቸው ነገር ተቆጥረው በር ከተዘጋ በኋላ በዚህ ፍጥነት ለምርመራ የሚጠራ ሰው መኖሩ ነው፡፡ የካቴናው ድምጽ 7 ቁጥር በር ላይ ሲደርስ ቆመና በሩ ተከፈተ፡፡ ‹‹ፈረሃን ኢብራሂም›› ከውጭ የመጣው ጥሪ አስተጋባ፡፡ ለምርመራ ሲጠራ የመጀመሪያው የሆነው ፈረሃን ምን ማድረግ እንዳለበት ግር ብሎት ተደናበረ፡፡ ተነስቶ ቆመ፡፡ ‹‹ፈረሃን ኢብራሂም እዚህ አይደለም?›› ከውጭ የቆመው ፖሊስ ጠየቀ፡፡ ኡመድ ፈርሃን እንዲወጣ በምልክት ወደበሩ ጠቆመው፡፡ ፈረሃን ኮፍያ ያለውን ሹራብ ደረበና ወጣ፡፡
ውስጥ የቀሩት ሰዎች እርስ በርስ ለምን በዚህ ሰዓት ሊጠራ እንደቻለና ምን ሊከሰት እንደሚችል የራሳቸውን መላምት እየሰጡ ክፍሉን በጫጫታ ሞሉት፡፡ በሼህ ጀማል የተመራው ፀሎት ተጠናቆ ብዙም ሳይቆዩ ወደ 7 ቁጥር እየቀረበ የመጣ የእግር ኮቴ ሰምተው ደግሞ ማን ይሆን ባለተራ ብለው በሰቀቀን በር በሩን ያዩ ጀመር፡፡ በሩ ተከፈተና ፈረሃን ገብቶ በሩ ተዘጋ፡፡ ከሄደ ግፋ ቢል ግማሽ ሰዓት ቢሆነው ነው፡፡ በዚህ ፍጥነት የሚጠናቀቅ የመጀመርያ ምርመራ የለም፡፡ ቢያንስ በምርመራ ወቅት እስኪሰለች ድረስ በተደጋጋሚ የሚጠየቀው የሕይወት ታሪክ ከ30 ደቂቃ በላይ መፍጀት አለበት፡፡
ፈረሃን በተፈጠረው ነገር እንደተገረመ ፊቱ ላይ ያስታውቃል፡፡ ኡመድ ምን እንደተከሰተ ሊጠይቀው ሲል ፈረሃን ቀድሞ ጭንቅላቱን እየነቀነቀ ‹‹እነዚህ ሰዎች የሚደንቁ ናቸው!›› አለ፡፡ ‹‹እንዴት?›› የኡመድ ተጠባቂ ጥያቄ ነበር፡፡ ፈረሃን ጭንቅላቱን መወዝወዙን ሳያቋርጥ፡ ‹‹ኮሪደሩን እንደጨረስን የለበስኩትን ሹራብ አስወልቆ ፊቴ ላይ አሰረው፡፡ በጣም አጥብቆ ስላሰረው እንዳመመኝ እና መተንፈስ እንደተቸገርኩ ብነግረውም ምንም ውጤት አልነበረውም፡፡ ከዛ እየመራ የሆነ ክፍል ውስጥ ከተተኝ፡፡ ስሜን፣ ከየትኛው የሱማሌ ጎሳ እንደሆንኩኝና ለምን ወደኢትዮጵያ እንደመጣሁኝ ጠየቁኝና ጨርሰናል ብለው መለሱኝ፡፡›› ብሎ በእጁ አንጠልጥሎት የገባውን ሹራብ መልበስ ጀመረ፡፡ ‹‹ሲያናግሩህም ፊትህን ሸፍነውህ ነበር?›› ኡመድ ተገርሞ ጥያቄውን ቀጠለ፡፡ ‹‹ኮሪደሩን ስንጨርስ እንዳሰረኝ መልሰውኝ እዛው ስደርስ ነው ከፊቴ ላይ የፈቱልኝ፡፡›› ነገርየው ይበልጥ እንቆቅልሽ የሆነበት ኡመድ ሌላ ጥያቄ አስከተለ ‹‹ስንት ሆነው ነው ያናገሩህ?››፡፡ ‹‹ሁለት ድምፆች መስማቴን እርግጠኛ ነኝ›› አለ ፈረሃን፡፡ ፈረሃን በጥያቄዎቹ መሰላቸቱን ኡመድ ቢረዳም ጉጉቱን ግን ማሸነፍ አልቻለም፤ ‹‹ሊያናግሩ የወሰዱህን ክፍል አቅጣጫ ታስታሰዋለህ?›› ሲል ጠየቀ፡፡ ‹‹ደረጃ ይዘውኝ ስለወጡ ፎቅ ላይ መሆኑን ብቻ ነው የማውቀው፡፡›› ፈረሃን መለሰ፡፡ ኡመድ ማዕከላዊ በቆየባቸው አንድ ወር ከግማሽ ጊዜ ውስጥ እንዲህ ያለ ነገር ሲገጥመው የመጀመሪያው ነው፡፡ በርግጥ እራሱም ወደ 11፡30 አካባቢ አንድ ቀን ተጠርቶ ነበር፡፡ የዛኔ ምርመራ ያደረገበት ምንም የማያውቅ ግን ብዙ የሚያውቅ ለማስመሰል የሚጥር ከደኅንነት መሥሪያ ቤት የመጣ ሰውዬ ነበር፡፡ ሰውየውን አይቶታል፡፡ ለምርመራ ሲወስዱትም ዓይኑን አልሸፈኑትም፡፡ ፈረሃን የነገረውን እየተረጎመ ለሌሎቹ ሲነግራቸው ፈረሃን በመኻል አቋረጠውና ‹‹የአንደኛው ሰውዬ ድምፅ ግን ካረፍኩበት ሆቴል ይዘውኝ ሲመጡ ሲቪል ለብሶ የነበረውን ሰውዬ ድምፅ ይመስላል፡›› አለ፡፡ ሁሉም በሰሙት ነገር ተገርመው እያወሩ እንቅልፍ አንድ በአንድ ጣላቸው፤ ሌንጂሳ እስኪጠራ ድረስ፡፡
በማግስቱ ማክሰኞ ፈረሃን በተመሣሣይ ሰዓት ተወስዶ ሩብ ሰዓት እንኳን የሞላ ምርመራ ሳይወስድ ተመለሰ፡፡ በዚህኛው ምርመራ ደግሞ ሲጠየቅ የነበረው ወደኢትዮጵያ አብሮት የመጣ የሚያውቀው ሰው እንዳለ እና ጢያራ ማረፊያ ተገኝቶ የተቀበለው አስጎብኚን ማን እንዳስተዋወቀው ነበር፡፡ ፈረሃን አዲስ አበባ ዓለም አቀፍ ጢያራ ማረፊያ ከመጣበት ጢያራ ሲወርድ ሰላምታ ከተለዋወጠው አንድ ሴንት ፓውል በመልክ ብቻ ከሚያውቀው ተለቅ ያለ ሱማሌ ውጪ ሌላ የሚያውቀው ሰው በመንገዱ ላይ እንዳላጋጠመው እና አስጎብኚ ያሉት ሰው የእናቱ የወንድም ልጅ እንደሆነ ፊቱን ሸፍነው ለሚመረምሩት ሰዎች አስረድቶ ተመለሰ፡፡
***
እጅግ አስቸጋሪ እና በአደጋ የተሞላ ቢሆንም ሳይቤርያ ያሉ እስረኞች መልዕክት የሚለዋወጡበት ዘዴ አበጅተዋል፡፡ የምርመራ ሂደታቸው ምን እንደደረሰ፣ እየተጠየቁ ያሉት ጥያቄዎች ምን ምን እንደሆኑ እና ከማዕከለዊ ውጭ ስላለ ነገር መረጃ ሲደርሳቸው ሌላ ክፍል ውስጥ ያለ ጓደኛቸው ጋር መልዕክት ይለዋወጣሉ፡፡ እንደዚህ በሚስጥር ካልሆነ በቀር ሁለት የተለያዩ የሳይቤሪያ ክፍሎች ውስጥ ያሉ ታሳሪዎች በፍፁም አይገናኙም፡፡ ይህንን የታዘበው ፈረሃን ኡመድን ውለታ ጠየቀው፡፡ አብረውት ፍርድ ቤት የቀረቡት ሱማሌዎች ያሉበትን ክፍል እና የምርመራቸው ሂደት እንዴት እንደሆነ እንዲያጣራለት ነበር የፈለገው፡፡
ኡመድ ሳይቤሪያ ሌላ ክፍሎች ውስጥ ባሉ አብረውት በታሰሩ ጓደኞቹ በኩል ባደረገው ማጣራት መውሊድ የሚባለው ከፈረሃን ጋር ፍርድ ቤት አብሮ የቀረበው ሱማሌ 3 ቁጥር ውስጥ እንደሚገኝ እና ኢብራሂም የሚባለው ደግሞ 4 ቁጥር ውስጥ እደሚገኝ አወቀ፡፡ ፈረሃን ለሁለቱም በያሉበት የድብቅ መልዕክት ልኮ ያሉበትን አጠቃላይ ሁኔታ እንዲያስረዱት ቢጠይቃቸውም መልስ ግን አልመጣም፡፡ ሁለት ቁጥር ውስጥ ታስሮ የነበረው አብሯቸው ፍርድ ቤት የሄደው ሽማግሌ ግን ‹‹እስካሁን ለምርመራ ወስደውኝ አልወሰዱኝም›› የሚል መልዕክት መለሰ፡፡ ፈረሃን ለሽማግሌው በላከው የመልስ መልስ ሽማግሌው ለምርመራ ከተወሰደና ‹‹ፈርሃንን ታውቀዋለህ ወይ?›› የሚል ጥያቄ ከተነሳበት ‹‹ፈረሃንን አውቀዋለሁ፤ በጣም ጥሩ ባሕሪ ያለው ልጅ ነው፡፡›› እንዲልለት ለመነው፡፡
***
ፋይሰል 8 ቁጥር ካሉት ክፍሎች ውስጥ በስተግራ በኩል ወዳለው የመጀመርያ ክፍል ነበር የተዘዋወረው፡፡ በመጀመርያ የገባ ቀን ጋህነም ውስጥ የከተቱት ነበር የመሰለው፡፡ የክፍሉ አየር መታፈን ሳያንስ የሚተኛበት ፍራሽ ደግሞ የሆነ የሚረብሽ ጠረን ነበረው፡፡ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ መርማሪዎቹ ደግሞ በተከታታይ እየጠሩ ታውቃለህ የሚሉትን እንዲያምንላቸው ልብሱን አስወልቀው ይደበድቡታል፤ የውስጥ እግሩን በኤልክትሪክ ሽቦ ይገርፉታል፡፡ ከዚህ ሻል ያለ ቅጣት በሚቀጣ ቀን እጁን ወደላይ ሰቅሎ ቁጭ ብድግ እንዲሰራ ይገደዳል፡፡
ለብቻው የታሰረበት ክፍል ውስጥ ስለታሰረበት ጉዳይ እንኳን ባይሆን ስለሌላ ተራ ጉዳይ የሚያወያየው ሰው ማጣቱ ጭንቅ ውስጥ ከቶታል፡፡ ሰው ማጣት እንደዚህ ያሰቃየኛል ብሎ አስቦ አያውቅም፡፡ ሌላ ግዜ በራሱ ፍላጎት ብቻውን ሲሆን እንኳን እንደሚያደርገው ቁርዓን እንዳይቀራ፣ ቁርዓን የለውም፡፡ ቢኖረውም ኖሮ በየትኛው ብርሃን ሊያነብ፡፡ የተወለደበትን ቀን አምርሮ ረገመ፡፡
ክፍሉ ውስጥ የሚተኛበት ፍራሽ፣ ለኡዱ ማድረጊያ በላስቲክ ቀድቶ የሚያስቀምጠው ውኃ እና ለመጸዳጃ የሚሆነው ባሊ አለ፡፡ የሚተኛበት ፍራሽ ቁመት ከክፍሉ ርዝመት ስለሚበልጥ በአግድሞሽ ካልሆነ እግሩን ዘርግቶ መተኛት አይችልም፡፡ ፋይሰል የሚያስበውም፣ የሚበላውም፣ የሚጸዳዳውም፣ የሚተኛውም እዚችው ክፍል ውስጥ ነው፡፡
8 ቁጥር አጠገቡ ካሉት ሦስት ክፍሎች ውስጥ አብረውት ፍርድ ቤት ከቀረቡት አምስት ሱማሌዎች መካከል አንዳቸውም እንደሌሉ አረጋግጧል፡፡ ለምን እሱ ላይ እንዲህ ያለ ሰቆቃ እየተፈፀመበት እንደሆነ ለመረዳት ተቸገረ፡፡ የአጎቱ ልጅ በፍርሐት ያልሆነ ነገር ተናግሮ እንደሆን ጠረጠረ፡፡ አብረውት ፍርድ ቤት ከቀረቡት መካከል ብቸኛው የውጭ ሀገር ፓስፖርት ባለቤት አለመሆኑ ለዚህ እንደዳረገው እንዴት ሊጠረጥር ይችላል?
***
በሳምንት አንድ ቀን ተራ ወጥቶላቸው ሳይቤርያ ያሉ ማረፊያ ቤቶች ለግማሽ ቀን ያክል ክፍሉ ውስጥ ባሉ ታሳሪዎች ይጸዳሉ፡፡ ሁሉም እስረኞች ገላቸውን መታጠብ የሚፈቀድላቸውም ክፍላቸውን በሚያጸዱበት ቀን ብቻ ነው፡፡ ረቡዕ ከሰዓት ፋይሰል ያለበትን ክፍል እንዲያጸዳ እና ገላውን እና ልብሶቹን እንዲያጥብ ታዘዘ፡፡ የተባለውን ለመፈፀም የሚተኛበትን ፍራሽ ወደኮሪደሩ ይዞት ሲወጣ ፍራሹ ላይ ያየው ነገር ሆዱን እረበሸው፡፡ ወዲያው ከፍራሹ ይወጣ የነበረው መጥፎ ጠረን ምን እንደሆነ ገባው፡፡ ከሱ በፊት እዛ ክፍል ውስጥ ታስሮ የነበረው ሰው ደም የፍራሹን ራስጌ ቀይ ቀለም አልብሶታል፡፡ እስከዛ ቀን ድረስ ደም ላይ ተኝቶ እንደነበር ሲያስብ የበላው ምሣ እንዳለ ወጣ፡፡
***
2 ቁጥር ውስጥ ያለው ሽማግሌ ለፈረሃን መልዕክቶች መልስ መመለስ አቁሟል፡፡ ፈረሃን በሁኔታው ግራ ተጋብቷል፡፡ በመጀመሪያ ቀን መውሊድ እና ኢብራሂም እንኳን መልዕክት መላክ ባልቻሉበት ግዜ ፈጥኖ መልስ የላከው እሱ ነበር፡፡ ከዛን ግዜ ወዲህ ግን በተገላቢጦሽ ከነመውሊድ ጋር በተደጋጋሚ መልዕክት ሲለዋወጥ ለሽማግሌው የሚልከው መልዕክት ግን የውኃ ሽታ ሆኖ ነው የሚቀረው፡፡ መውሊድ እና ኢብራሂም ከፈረሃን የተለየ ምርመራ አልተደረገላቸውም፡፡ የተለየ ነገር የነበረው መውሊድ ከፈረሃን ጋር የት እንደሚተዋወቅ መጠየቁ ነው፡፡ ሽማግሌው ሰውዬ ግን ለምርመራ ይወሰድ አይወሰድ፣ ስለፈረሃን ጠይቀውት ጭራሽ አላውቀውም ይበል ወይንም ልመናውን ተቀብሎ ስለ‹ጥሩ› ባሕሪው ምስክር ሆኖለት ይሆን ማወቅ አልቻለም፡፡
ሴቷ ወጣት ሱማሌ ደግሞ ሳይቤሪያ ባሉ ማረፊያ ቤቶች ውስጥ ያሉ ታሳሪዎች በቀን ለ10 ደቂቃ የሚፈቀድላቸው የፀሐይ ብርሃን ከሚያገኙበት ቦታ ፊት ለፊት በተለምዶ ጣውላ ቤት በመባል የሚጠራው የሴት እስረኞች እና ጓደኞቻቸው ላይ ምስክር ለመሆን የተስማሙ ወንድ እስረኞች የሚቆዩበት ሕንፃ ላይ ያለ ክፍል ውስጥ ስለሆነ ያለችው ፈረሃን ከሷ ጋር መልዕክት መለዋወጥ አልቻለም፡፡
***
ፍርድ ቤት የቀረቡ ዕለት በሽማግሌው እና በወጣቷ ሴት መካከል ያስተዋለው መቀራረብ የቆየ ትውውቅ እንዳላቸው እንዲጠረጥር አድርጎት ነበር፡፡ ፋይሰል ጥርጣሬው ልክ እንደነበር የገባው ምርመራው ቀሎለት ከብቸኛ ክፍሉ ከ8 ቁጥር ወደ 10 ቁጥር ከተዘዋወረ በኋላ ከሽማግሌው ጋር ባደረገው የመልዕክት ልውውጥ ነበር፡፡ ሽማግሌው የዴንማርክ ነዋሪ ሲሆን ወደኢትዮጵያ የመጣው ሚስት ለማግባት ነበር፡፡ ዕቅዱ ተሳክቶለት ኢትዮጵያ በስደት ላይ የነበረችውን ለግላጋ ወጣት በእጁ አስገብቶ ወደ ዴንማርክ ለመመለስ አዲስ አበባ ሲመጣ ነው ከነሚስቱ ጫጉላቸውን ማዕከላዊ እንዲያሳልፉ የተገደዱት፡፡
ፈረሃን ስለሽማግሌው እዲያጣራለት ባዘዘው መሠረት አንዱ ቀን አመሻሽ ላይ ፋይሰል ለአጎቱ ልጅ መልዕክት ላከ፡፡ መልዕክቱ የሽማግሌውን እና ሴቷን ግንኙነት ካስረዳ በኋላ ሽማግሌው ለምን የፈረሃንን መልዕክት መመለስ እንዳቆመም ያትት ነበር፡፡ ሽማግሌው ከፈረሃን ጋር ግንኙነት ያቋረጠው የመጀመርያ ቀን መልዕክት ሲለዋወጡ ስለባሕሪው እንዲመሰክርለት የጠየቀው ፈረሃን የሆነ ጥፋት አጥፍቶ ለመሸፈን እየሞከረ እንደሆነ ስለተሰማው ነበር፡፡
***
ፈረሃን የሽማግሌውን ታሪክ ለኡመድ አጫውቶት ነበር፡፡ አንድ ቀን ከሰዓት ፀሐይ እየሞቁ ከፊት ለፊታቸው ካለው ጣውላ ቤት አንዱ ክፍል በር ላይ ፔርሙዝ እያጠበች የነበረችውን ሱማሌ እንዲያይ ፈረሃን ለኡመድ ጠቆመው፡፡ ኡመድ ልጅቷን ካያት በኋላ ፈረሃን ምን ሊነግረው እንደፈለገ ጠየቀ፡፡ ፈረሃን ወጣቷ ሱማሌ 2 ቁጥር ያለው ሽማግሌ ሚስት እንደሆነች ነገረው፡፡ 2 ቁጥር ውስጥ የነበረውን ሽማግሌ በደንብ የሚያውቀው ኡመድ በባልና ሚስቱ መኻከል ያለው የዕድሜ ልዩነት ደንቆት ጭንቅላቱን ወዘወዘ፡፡ ኡመድ መገረም የገባው ፈረሃን በእስር ቆይታው አሳክቶ የተናገራት የመጀመርያም የመጨረሻም ዓረፍተ ነገር ወረወረ፡ ‹‹ገንዘብ ካለህ በሰማይ መንገድ አለ፡፡›› ፈረሃን አማርኛ አሳክቶ መናገሩ ለኡመድ ሌላ ግርምት ሆነበት፡፡ በመጀመርያ ስለምን እንዳወሩ እንኳን የማያውቁት የ7 ቁጥር እስረኞች ፈረሃን በሰማይ መንገድ መኖሩን ለመጠቆም የተጠቀመበት የእጅ እንቅስቃሴ እና በአማርኛ በቅጡ ለመግባባት ሳይችል ይህችን ተረት መተረቱ ደንቋቸው እየተሳሳቁ 10 ደቂቃዋ አልቃ ወደክፍላቸው ተመለሱ፡፡
***
በእስር ቆይታው መጀመርያ ላይ ለሁለት ቀናት በድምር አንድ ሰዓት ለማይሞላ ምርመራ ከመወሰዱ ውጭ ሌሎች ክፍሉ ውስጥ ያሉ እስረኞች እየተመላለሱ ሲመረመሩና ሲደበደቡ እሱ ሌላ ምርመራ አልተደረገበትም፡፡ ከሁለት ሳምንት በኋላ በጥዋት ሥሙ ተጠራ፡፡ አብረውት ፍርድ ቤት ከሄዱት ሱማሌዎች ውስጥ ከውጭ ሀገር የመጡት ሦስቱ በተለምዶ ሸራተን ወደሚባለው ምርመራ የጨረሰ ሰው ወደሚቆይበት ማረፊያ ቦታ ተዘዋውረዋል፡፡ ሳይቤሪያ የቀሩት እሱና የአጎቱ ልጅ ፋይሰል ብቻ ነበሩ፡፡ የነመውሊድ ዝውውር በተደረገ ማግስት በጥዋት ሲጠራ እሱም ወደሸራተን ሊሄድ እንደሆነ ገምቶ ነበር ነገር ግን ጥሪው እቃውን እንዲይዝ ትዕዛዝ ባለመጨመሩ ግምቱ የተሳሳተ እንደሆነ ተረዳ፡፡
የጠራው ፖሊስ ሁል ግዜ ምርመራ የሚሄድ ሰው እንደሚደረገው ፈረሀን እጅ ላይ ካቴና አጠለቀለት፡፡ ምርመራ በተደረገለት ሁለት ቀናት ሹራቡን አስወልቆ ፊቱን ያሰረበትን ቦታ ዝም ብሎ ሲያልፈው ‹ዛሬ መርማሪዎቼን ላያቸው ነው፡፡› ሲል አሰበ፡፡ ከ7 ቁጥር ጠርቶ ይዞት የመጣው መለዮ የለበሰ ፖሊስ ለሌላ ሲቪል ለለበሰ ፖሊስ አስረከበው እና ከአዲሱ ሰውዬ ጋር ሆኖ አሮጌ ጣውላ ደረጃዎችን አልፎ አንድ ቢሮ በር ላይ እንዲቆም ታዘዘ፡፡ በሩ ላይ ሲቪል የለበሰው ፖሊስ ፈረሃን እጅ ላይ የነበረውን ካቴና ፈትቶ ወደክፍሉ እንዲገባ በሩን ከፈተለት፡፡ ፈረሃን ክፍሉ ውስጥ ሲገባ የእናቱ ወንድም (የፋይሰል አባት) ከተቀመጡበት ተነስተው ተጠመጠሙበት፡፡ ሁለት ሳምንት የገቡበት ጠፍቷቸው ሲያፈላልጉ ቆይተው ከጎዴ መጥተው ነበር ያገኙት፡፡
ወደማረፊያ ቤት ሲመለስ ዓይኖቹ ቀልተው ፊቱ ፍም መስሎ ነበር፡፡ አጎቱን በማግኘቱ የደስታ እምባ ያነባውን ያክል ያለምክንያት እስር ቤት መወርወሩ ያጠራቀመበት እልህ ላይ የልጆቹ እና ሚስቱ ናፍቆት ተጨምሮበት በአንሶላ ተጠቅልሎ እዬዬውን አቀለጠው፡፡ ክፍሉ ውስጥ የነበሩት እስረኞች ‹‹ምን አግኝተውበት ደበደቡት?›› ሲሉ አንሾካሾኩ፡፡
ምሣ ሰዓት ከመድረሱ በፊት ከቤተሰብ የተቀበሉትን ስንቅ ለእስረኞች የሚያድሉት ፖሊሶች መጥተው የፈረሃን ሥም ተጠራ፡፡ ክፍሉ ውስጥ የነበሩት ሁሉ ጠዋት የተጠራው ቤተሰብ ለማግኘት እንደሆነ ገባቸው፡፡ ኡመድ ፈረሃንን ቀስቅሶ የመጣለትን ምግብ እንዲቀበል አደረገ፡፡ የፈረሃን አጎት ያመጡትን የሱማሌ እንጀራ ከሞፎ እና በሪስ ጋር በሉ፡፡ የሱማሌ እንጀራው ለኡመድ በጣም ስለተመቸው ሁልግዜ አጎቱ ሲመጡ ይዘው እንዲመጡ እንዲጠይቃቸው ፈረሃንን ተለማመጠው፡፡
***
አብረውት 7 ቁጥር ውስጥ የነበሩ እስረኞች ሁሉ በምርመራ ወቅት ተደብድበዋል መባሉን አምኗል፤ ከዝምተኛው መላጣ ሽማግሌ በቀር፡፡ ሰውየው ከአክሱም አካባቢ እንደመጡ ከተነገረው ጀምሮ እንደውም በጥርጣሬ ነው የሚያያቸው፡፡
አንድ ቀን እኝሁ ሽማግሌ ተጠርተው ወጡ፡፡ ግማሽ ቀን ሙሉ ቆይተው ሲመለሱ የሸሚዛቸው ቁልፎች ግማሾቻቸው ተበጥሰው ቀሪዎቹ ደግሞ ተዛንፈው ተቆልፈው ነበር፡፡ እንደተመለሱ ማንንም ሳያናግሩ ወደፍራሻቸው አምርተው ተኙ፡፡ ተደብድበው እንደሆነ ከፈረሃን በስተቀር ሁሉም አምነዋል፡፡ ቆይተው ሲነሱ ኡመድ አግባብቶ ምግብ እንዲበሉ ካደረገ በኋላ ምን እንደተፈጠረ ጠየቃቸው፡፡ የተፈጠረውን ለኡመድ ሲያስረዱት ዓይኖቻቸው እምባ አቅርረው፣ ድምፃቸውን ሲቃ እየተናነቀው እና የሰውነታቸው የደምስሮች ሁሉ ተገታትረው ነበር፡፡ ፈረሃን ሽማግሌው ለኡመድ የነገሩትን እንዲተረጉምለት ወተወተው፡፡ በሐዘን ድባብ ውስጥ ሆኖ ኡመድ ለፈረሃን የሆነውን ነገረው፡፡ እንዲህ ነበር የሆነው፤ አቶ ጎበዛይ ገ/ስላሴ ጭቅጭቅ እና እንግልቱ ሲሰለቻቸው ግዜ የማያውቁትን ‹አውቃለሁ›፣ ያልሰሩትን ‹ሰርቻለሁ› ብለው አምነው ለፖሊስ የተከሳሽነት ቃላቸውን ይሰጣሉ፡፡ ይህ አልበቃ ያለው ፖሊስ ይህንኑ ቃል ፍርድ ቤት ቀርበው ዳኛ ፊት ቃላቸውን እንዲሰጡ ፍርድ ቤት ይወስዷቸዋል፡፡ ፍርድ ቤት ዳኛ ፊት ሲቆሙ ፈፅመኻል ስለተባሉት ወንጀል ምንም የሚያውቁት ነገር እንደሌለና እንደውም ፖሊስ አስገድዶ የተከሳሽነት ቃል እንደተቀበላቸው በመግለጽ ‹‹በሕግ አምላክ ፍረዱኝ›› ብለው ይጮኻሉ፡፡ በነገሩ እጅግ የበገኑት መርማሪዎቹ ከፍርድ ቤት ሲመለሱ በቀጥታ ወደምርመራ ክፍል ወስደው ልብሳቸውን አስወልቀው መሬት ላይ ጥለው እየረጋገጡ ደበደቧቸው፡፡
ፈረሃን በሰማው ነገር ግራ በመጋባት ‹‹ይህማ ሊሆን አይችልም!›› ሲል ድምፁን ከፍ አድርጎ ተናገረ፡፡ በዕድሜ የገፋ ሽማግሌ፤ ለዛውም እንኳን እንዲህ ሊንገላቱ ቀርቶ ጭራሽ ይታሰራሉ ብሎ ከማያስባቸው የትግራይ ተወላጅ ላይ ተፈፀመ የተባለውን ማመን አልቻለም፡፡ ኡመድ ‹‹አንድ ስለአቶ ጎበዛይ የማታቀው ነገር ልጨምርልህ፤ ሕወሓት ከደርግ ጋር ባደረገችው ትግል ውስጥ ለ11 ዓመታት አብረው የታገሉ ሰው ናቸው፡፡ እዚህ አብረውን የነበሩት ቄስ ጎይቶም ወደ 8 ቁጥር ከመቀየራቸው በፊት የውስጥ እግራቸውን ተገርፈዋል፡፡ እዚህ የምታያቸው ሼህ ጀማል የአስም ሕመማቸው እንዲያሰቃያቸው ነው ሽንት ቤት አጠገብ ያለ ክፍል ውስጥ የታሰሩት፡፡ ሌላ ብዙ ልልህ እችላለሁ፤ የማዕከላዊ ግፍ እና ማዋረድ በዕድሜ፣ በፆታ፣ በዘውግ ወይንም በሃይማኖት አባትነት የሚለይ አይደለም›› አለ ንዴቱ እንዳይታወቅበት እየጣረ፡፡
ፈረሃን ኢትዮጵያን እየገዛ ስላለው ስርዓት ያስብ የነበረው እና እራሱ እየመሰከረ ያለው ክፉኛ ተጋጭተው እስካሁን እውነቱን ለመፈለግ ያደረገው ሙከራ ትንሽነት አሳፈረው፡፡
***
ቀኑ መሽቶ እየነጋ 28 ቀን አለፈና የቀጠሮው ቀን ደረሰ፡፡ ብዙዎቹ አብረውት 28 ቀን ያሳለለፉት የ7 ቁጥር እስረኞች የሚለቀቅበት ቀን እንደሆነ ገምተዋል፡፡ ፖሊስ ከዚህ በላይ ፈረሃንን ማቆየት የሚፈልግበት ምክንያት አልታያቸውም፡፡ በ28 ቀን ውስጥ ሁለት ቀን ለዚያውም ተደምሮ አንድ ሰዓት እንኳን የማይሞላ ምርመራ የተደረገበት ሰው ለምን ለተጨማሪ ግዜ ይፈለጋል?
ጠዋት ሲጠበቅ የነበረው የፈረሃን ፍርድ ቤት ጥሪ ሳይመጣ ቀረ፡፡ ምሣ ሰዓት በመድረሱ የሁሉም ተስፋ አደገ፡፡ በቀጠሮው ቀን ፍርድ ቤት ካልተወሰደ፣ ፖሊስ ብቻውን ቀርቦ ምርመራዬን ስለጨረስኩ የግዜ ቀጠሮ መዝገቡ ይዘጋልኝ ብሏል ማለት ነው፡፡ ይህ ከተከሰተ ደግሞ ከሁለት ነገሮች አንዱ ይከተላል ማለት ነው፡፡ የመጀመርያው ከእስር መፈታት ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ የክስ ምስረታ ነው፡፡ በአንድ ሰዓት ምርመራ ደግሞ ክስ ሊመሰረት እንደማይችል እና እነዚህን መሳሰሉ ትንተናዎች እየተጨዋወቱ ምሣ ከበሉ በኋላ በድንገት በሩ ተከፈተና ፈረሃን ተጠራ፡፡ ክፍሉ ውስጥ የነበሩት ሰዎች ሁሉ ሲጠበቁት የነበረው የፍቺ ጥሪ ግን አልነበረም፡፡
ፈረሃን ከሄደበት ተመልሶ ሲመጣ እጅግ ተስፋ መቁረጥ ይስተዋልበት ነበር፡፡ ተጨማሪ 28 ቀናት እንደተቀጠረበት ለኡመድ ሲያስረዳው ሁሉም ተደናገጡ፡፡ እየሆነ ያለውን በፍፁም ሊረዱት አልቻሉም፡፡ ‹‹ምን ዓይነት ዳኛ ናት? 28 ቀን ምን ሠራችሁ ብላ ሳትጠይቅ ሌላ 28 ቀን የምትሰጣቸው?›› ሲል ኡመድ አማረረ፡፡
***
ቅዳሜ ግንቦት 30ቀን 2006 ዓ.ም ከሰዓት ፈረሃን ካረፈበት ሆቴል ትንሽ የእግር ጉዞ ለማድረግ ፈልጎ እየወጣ እንዳለ የሆቴሉ የእግዳ መቀበያው ላይ አንድ የሚያውቀው ፊት ያየ መሰለው፡፡ ተጠግቶ ሲያረጋግጥ የሚኖርበት ሴንት ፖውል ሚያውቀው ሱማሌ ወጣት ነበር፡፡ ያረፈበት ሆቴል አዲስ አበባ ውስጥ ሱማሌዎች የሚበዙበት አካባቢ እንደሚገኝ እና ሆቴሉ ውስጥም በብዛት የሚያርፉት የሱማሌ ዲያስፖራዎች እንደሆኑ ፋይሰል ነግሮት ስለነበር በሺዎች ማይል ርቀት የሚያውቀው መውሊድን እዚህ ማግኘቱ ብዙም አልገረመውም፡፡ መውሊድ ፈረሃን ያቀረበለትን ግብዣ ተቀብሎ የአዲስ አበባ ከሰዓት አየር እቀዘፉ የቦሌን አካባቢ ቃኙት፡፡ ከመስቀል አደባባይ እስከ ቦሌ ዓለም አቀፍ ጢያራ ማረፊ ድረስ የተዘረጋው አፍሪቃ ጎዳና የተሠራበት ደረጃና ከጎዳናው ግራና ቀኝ የተሰለፉት ሕንፃዎችን አይተው ግርምታቸውን ተለዋወጡ፡፡ ፈረሃን አብሮት ላለው የሴንት ፖውል ወዳጁ ሌላ የተደመመበት ጉዳይንም አጫውቶት ነበር፡፡ አባቱን ለማስታመም የሚሄድበት ጎዴን ከጅግጅጋ የሚያገናኝ አዲስ የአስፋልት መንገድ በቅርቡ መዘርጋቱን እና ቀድሞ መንገዱ ከሚወስደው ግዜ አሁን በግማሽ እንደቀነሰ በአድናቆት አጫወተው፡፡
በአንፀባራቂ ሕንፃዎቹ መስታወት ውስጥ የድኃ ኢትዮጵያውያን ችጋር አልታያቸውም ነበር፡፡ አዲስ እና አሮጌ መኪኖች እንደፈለጉ የሚፈሱበት ጎዳና ኢትጵያውያን ላይ የተጫነው ጭቆና ማራዘሚያ እንደሆነ አልተገነዘቡም፡፡ ፈረሃን እና መውሊድ እነዚህን ጉዳች ለመረዳት በከባዱ መንገድ መማር ነበረባቸው፡፡ ከዛች አስደሳች ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ በድጋሚ የተገናኙት ሰኞ ዕለት ፍርድ ቤት ቀርበው ፖሊስ በሽብርተኝነት እንደሚጠረጥራቸው የሰሙ ግዜ ነበር፡፡
ሦስተኛ ተጠርጣሪ ሆኖ ችሎት ከጎናቸው የቆመው ኢብራሂም በትውልድ ኬንያዊ ሱማሌ ሲሆን ከሚኖርበት አሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ የመጣው የኢትዮጵያ ሱማሌ ክልል ፕሬዝዳንት በአሜሪካን ሚኒሶታ ግዛት ተገኝተው ኢትዮጵያ እና ክልላቸው ለኢንቨስትመት ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠራቸውን እና ማንም ሰው ኢንቨስት ለማድረግ ቢመጣ በደስታ እንደሚያስተናግዱት የገቡትን ቃል አምኖ እና አንዳንድ መገናኛ ብዙኃን በየግዜው ስለኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብት መመንደግ ሚያወጡት ዘገባ አጓጉቶት ከእናት ሀገሩ ኬንያ ይልቅ በኢትዮጵያ መዕዋለ ነዋዩን ቢያፈስ የተሻለ የትርፍ ሕዳግ እንደሚያገኝ ተማምኖ ነበር፡፡
***
ለሁለተኛ ግዜ ፍርድ ቤት በቀረበ ማግስት መጀመርያ ተጠሪ ፈረሃን ነበር፡፡ ማንም ባልጠበቀው ሁኔታ የማክሰኞ ሐምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም ጠዋት የመጣው ጥሪ ፈረሃንን ጓዙን ጠቅልሎ እንዲወጣ የሚያዝ ነበር፡፡ ፖሊስ ተጨማሪ 28 ቀን ፈረሃን እና ጓደኞቹ ላይ የጠየቀው ፍርድ ቤቱን ታዛዥነት ለማረጋገጥ ነው እንጂ ሌላ ምክንያት አልነበረውም፡፡ ፍርድ ቤቱም ታዛዥነቱን በሚገባ አረጋግጧል፡፡
በሕመም አልጋ ላይ የወደቁት አባቱን እንዲጎበኝ እንኳን ዕድል ሳይሰጠው ፈረሃን ወደመጣበት ሀገር እራሱ በቆረጠው ትኬት እንዲመለስ ቀጭን ትዕዛዝ ተሰጠው፡፡ የታዘዘውን ከማድረግ ውጪ አማራጭ አልታየውም፡፡ ምንያቱም ይህች በአዲስ ዓይኑ ማየት የጀመራት ኢትዮጵያ ናት፡፡ ፖሊሶች እየጎተቱ ከ7 ቁጥር ሲያስወጡት እምባው ጉንጩ ላይ እየወረደ እንዲህ አለ፤ ‹‹ኡመድ፤ የተበደላችሁትን አልረሳም፡፡ ሁሉንም እንደምናፍቃቸው ንገርልኝ፡፡››
ይህ ታሪክ ለአንባቢ ምቾት ሲባል ከተደረገለት ዘይቤያዊ ማስተካከያ በስተቀር እውነተኛ ታሪክ ነው፡፡
ተፈፀመ

IN ETHIOPIA, A MIX OF REGULATIONS AND REPRESSION SILENCE INDEPENDENT VOICES

by Simegnish “Lily” Mengesha. 

After a tense year marked by widely-criticized elections in which Ethiopia’s ruling party won 100 percent of parliamentary seats, 2015 concluded with yet more repression in the East African nation. During the last weeks of December, the Committee to Protect Journalists reported the arrests of two journalists, while five Zone 9 bloggers who had been acquitted of terrorism charges in October were summoned back to court as state prosecutors appealed their earlier acquittal.

Lili

These detentions occurred amid widespread protests in Oromia state, Ethiopia’s largest region. Human Rights Watch reported that since the protests began in mid-November 2015, police and security forces had killed 140 protesters and wounded many others, while hundreds of demonstrators and activists have been jailed; Ethiopian government officials have only publicly acknowledged five deaths.

The trigger for this recent crisis was the Integrated Regional Development Plan for Addis Ababa. Commonly known as “The Addis Ababa Master Plan,” its implementation would have expanded the capital city into parts of the neighboring Oromia region, potentially displacing a large number of local farmers, threatening their constitutionally-protected right to livelihood, and eroding local authority. One Ethiopia analyst, Tsegaye R. Ararssa, noted that the Master Plan violated Articles 39 and 105(2) of Ethiopia’s Constitution, which authorize alterations to state boundaries only by a referendum of self-determination or a constitutional amendment. Although the government recently decided to scrap the Master Plan, the decision was made primarily to silence the protests and falls short of addressing the protestors’ underlying concerns about the lack of good governance, access to information, and freedom of expression in Ethiopia.

The Ethiopian government prides itself on having one of the world’s fastest growing economies (the International Monetary Fund ranks the country among the top five globally). But the authorities often promote growth at the expense of citizens’ basic human rights, and many citizens feel that they have not benefitted from the country’s economic growth. The United Nations Development Program’s Human Development Index ranks Ethiopia 174 out of 187 countries, and despite the government’s growth plans, 29 percent of Ethiopia’s population lives below its national poverty line.

The recent Oromia protests are a clear indication of what happens when the population feels that development is being imposed. If the government genuinely believes in inclusive economic growth, its plans would benefit from better communication with the people. Instead, the authorities have closed most venues for two-way communication and use state media to control media narratives and disseminate propaganda about their development plans.

In my January 2016 Journal of Democracy article, I describe how Ethiopia’s authorities have used legal and economic methods to suppress civil society and independent media. Ethiopia’s criminal code and press law, which have long been highly restrictive, have tightened significantly in the years since Ethiopia’s 2005 general elections, when mass protests erupted over vote-rigging allegations. Media repression became even more organized and systematic in 2009 after Ethiopia adopted the Anti-Terrorism Proclamation (ATP). Ostensibly intended to counter security threats, since its adoption the ATP has only ever been used to bring charges against political activists and members of independent media.

The Civil Society Proclamation (CSP), adopted in 2009 around the same time as the ATP, has also curtailed the efforts of most human rights organizations. Restrictions on foreign funding and regulations which limit how much a civil society organization (CSO) can dedicate toward its administrative and operations costs make it extremely difficult for CSOs to survive. According to one study, the number of federally-registered local and international CSOs in Ethiopia dropped by 45 percent (from 3,800 to 2,059) between 2009 and 2011. Ethiopia’s Charities and Societies Agency (CSA) claimed in 2014 that 3,174 CSOs were registered in Ethiopia, but a 2014 study by the joint European Union’s Civil Society Fund (EU-CSF II) found that of the total number of CSOs registered by Ethiopia’s Civil Society Agency, only 870 were actually operational. USAID’s 2014 CSO Sustainability Index for Sub-Saharan Africa noted that the impact of CSOs in Ethiopia is limited by national policies, funding restrictions, and a lack of government interest.

As a result of policies like these, platforms which normally serve to facilitate communication and feedback between government and citizens, such as media and civil society organizations, have been silenced by heavy government censorship and the criminalization of dissent. The lack of accountable communication channels makes the population feel alienated from the government, and the only remaining avenue for the public to express its concerns—peaceful demonstration—typically results in a harsh crackdown, as the last few months have shown.  In December, Ethiopia’s Prime Minister Hailemariam Dessalegn appeared on state television to defend the government’s use of physical repression against Oromia protestors, saying the government will take “merciless legitimate action against any force bent on destabilizing the area.”

These remarks betray the authorities’ insecurity. The increased intensity of repression against independent media, associations, and civil society organizations reflect a government that feels threatened by independent voices. Like most authoritarian regimes, Ethiopia’s government worries that the more informed and connected the people are, the more empowered they will be to hold the government to account. In other words, Ethiopia’s attempt to gag the media and choke civil society is not a sign of the government’s strength, but rather of its weakness.

Simegnish “Lily” Mengesha is a visiting fellow and former Reagan-Fascell Democracy Fellow at the National Endowment for Democracy’s International Forum for Democratic Studies. A seasoned journalist, media consultant, and translator, she previously served as director of the Ethiopian Environment Journalists Association.

The views expressed in this post represent the opinions and analysis of the author and do not necessarily reflect those of the National Endowment for Democracy or its staff.

Source: http://www.resurgentdictatorship.org/in-ethiopia-a-mix-of-regulations-and-repression-silence-independent-voices/#sthash.zuYb5eSh.2pI6oDZ6.dpuf

ኢትዮጵያ “ነፃነት የሌለባት”፤ ኤርትራ “ከክፉዎች የከፋች” ተባሉ

HRW - satenaw 2በዓለም ዙሪያ የሚሰማው የምጣኔ ኃብት ድቀት እና የማኅበራዊ ነውጥ ፍራቻ አምባገነን መንግሥታት በአውሮፓ አቆጣጠር ባለፈው 2015 ዓ.ም ይበልጥ አፋኝና ጨቋኝ እንዲሆኑ ሰበብ ሳይሰጣቸው እንዳልቀረ ዛሬ የወጣ የዓለም የነፃነት ሁኔታ ሪፖርት አስታውቋል፡፡

በዓለም ዙሪያ የሚሰማው የምጣኔ ኃብት ድቀት እና የማኅበራዊ ነውጥ ፍራቻ አምባገነን መንግሥታት በአውሮፓ አቆጣጠር ባለፈው 2015 ዓ.ም ይበልጥ አፋኝና ጨቋኝ እንዲሆኑ ሰበብ ሳይሰጣቸው እንዳልቀረ ዛሬ የወጣ የዓለም የነፃነት ሁኔታ ሪፖርት አስታውቋል፡፡

ፍሪደም ሃውስ የሚባለው ነፃ ቡድን በዚህ ሪፖርቱ የሃገሮችን የዴሞክራሲያዊ የነፃነት ይዞታዎች ገምግሞ በደረጃ አስቀምጧቸዋል፡፡ አምባገነን አገዛዞች ባለፈው የአውሮፓ ዓመት በ2015 ዓ.ም ይበልጥ የከፉ መሆናቸውን ይህ ዛሬ የወጣ የዓለም የነፃነት ይዞታ ሪፖርት ይናገራል፡፡

መንግሥታቱ የሚጠቀሙባቸው እጅግ የከፉ የአፈና ዘዴዎች፣ የሽብር ፈጠራ ጥቃቶች መብዛት እና የምጣኔ ኃብት መላሸቅ፣ ነፃነት በዓለም ዙሪያ እየተጉላላች፣ ይዞታዋ ወደ አስፈሪ ሁኔታ እያዘገመ መምጣቱ እያሰጋ መሆኑን ሪፖርቱ ይጠቁማል፡፡

ተቀማጭነቱ ዋሺንግተን ዲሲ ዩናይትድ ስቴትስ የሆነው ፍሪደም ሃውስ የሚባለው የሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ ተሟጋች ቡድን ባለፈው የአውሮፓ 2015 ዓ.ም የዓለም የነፃነት ይዞታ ለአሥረኛ ተከታታይ ዓመት እያሽቆለቆለ የመጣበት ዓመት እንደነበረ አስታውቋል፡፡

የፍሪደም ሃውስን ሪፖርት ለማግኘት ይኽንን ይጫኑና ይከተሉ፤ የሂዩማን ራይትስ ዋችን ሪፖርት ለማግኘት ይኽንን ይጫኑና ይከተሉ፤ ለተጨማሪ ዘገባ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

የአባይ ፀሃዬ የለውበትም የት ያደርስ ይሆን? – ግርማ ሰይፉ

 

የአባይ ፀሃዬ የለውበትም የት ያደርስ ይሆን?

 

Abay Tsehaye - satenawወዳጆች መቼም የዚህ ሀገር ነገር ግራና ቀኙ ጠፍቶዋል እንበል እንዴ? የፌዴራል ሹሞች የበታች ሹሞችን በፖለቲካ ውሳኔ በሚመጡ ጉዳዮ ጭምር እጃቸውን ወደታች መቀስር ጀምረዋል፡፡ ይህ ጉዳይ አዲስ አይደለም፡፡ ከዚህ በፊትም አማርኛ ተናጋሪዎች ተለይተው ከመኖሪያቻው ሲፈናቀሉ፣ ተጠያቂ የተደረጉት “ጥቂት ኪራይ ስብሳቢ” የተባሉ የበታች ሹሞች ናቸው፡፡

አሁን ደግሞ የአዲስ አበባና በዙሪያ ያሉ ከተሞች የተቀኛጀ ማስተር ልማት ይዞት የመጣው ጦስ በቀላሉ የሚገላገሉት አይመስልም፡፡ ጎምቱ የሚባሉት ባለስልጣናትም ቢሆን ስህትት ከመስራት የሚያግዳቸው ኃይል ሊገኝ አልቻለም፡፡ የዛሬ ፅሁፌ መነሻ የሆነው ደግሞ አቶ አባይ ፀሃዬ በሚዲያ የሰጡት የመከላከያ መልስ እጅግ ስለአስገረመኝ ነው፡፡

ባጠቃላይ መንግሰት የሚባለው አካል እንደ አካል ይህ ጦሰኛ የተቀናጀ ማስተር ፕላን ግራ አጋብቶታል፡፡ ግራ ተጋብቶ ግራ እያጋባን ይገኛል:: የአዲስ አበባ መሰተዳደር በግሉ ማስተር ፕላኑን ተግባራዊ ያደርጋል የሚል ዜና የሰማነው የኦሮሚያ/የኦህዴድ ሰራ አስፈፃሚ የተቀናጀ ማስተር ፕላኑን ተግባራዊ እንዳይሆን ውድቅ ባደረገ ማግስት ነው፡፡ አዲስ አበባ በተናጥል ማስተር ፕላኑን ተግባራዊ ሲያደርግ በዙሪያ ያሉት ከተሞች ላይ የሚያሰከትለው በጎም ሆነ አሉታዊ ተፅህኖ እንዴት እንደሚታይ የነገረን የለም፡፡ ለማነኛውም ይህን እናቆይ እና ለፅሁፌ መነሻ ወደ ሆነው ጉዳይ ልግባ፡፡

በእኔ እምነት በኦሮሚያ አካባቢ ለተነሳው ንቅናቄ ዋነኛው ነገር ቆስቋሽና አቀጣጣይ የነበሩት አቶ አባይ ፀሃዬ ናቸው ብዬ አምናለሁ፡፡ አሁን ደግሞ ኦቶ አባይ ፀሃዬ እጅ እና እግር የለሌለው ክስ በየደረጃው ወደሚገኙት የኦሮሞ ካድሬዎች ላይ አቅርበዋል፡፡ ወደዚህ ጉዳይ በዝርዝር ከመግባቴ በፊት ግን በዚህ ጦሰኛ ማስተር ፕላን ነገር ቆስቋሽና አቀጣጣይ ያልኩበትን ምክንያት ማስረዳት ይኖርብኛል፡፡

አቶ አባይ ፀኃዬ በአሁኑ ሰዓት ያላቸው ስልጣን ጠቅላይ ሚኒስትሩን በፖሊሲና ጥናት ጉዳዮች ማማክር እንደሆነ ይታወቃል፡፡ እንደሚታወቀው ይህ ስልጣና በቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር የስልጣን ዘመን የነበረ አይደለም፡፡ ኦቶ አባይ ይህንንም ስልጣናቸውን የገለፁበት መንገድ ጠብ የሚፈልግ ካለ ወይም ከተገኘ ለጠብ የሚመች ነው፡፡ “ጠቅላይ ሚኒስትር የእለት ተእለት ስራ ስለሚበዛባቸው በዋና ዋና ጉዳዮች ላይ እንደንስራ ተመደብን” ሲሉ በመጀመሪያ ያድረኩት የህገ መንግሰቱን አንቀፅ 79 መመልከት ነበር፡፡ ይህ ህገ መንግስት ካልተቀየረ በሰተቀር የፖሊሲ ጉዳዮችን ሸክም የሚወስድላቸው ሌላ ሰው መድበው እርሳቸው በሌላ የእለት ተዕለት ስራ መጠመድ አይገባቸውም ነበር፡፡ አቶ አባይ ፀሃዬ በዚሁ ስልጣናቸው መነሻ ባለፈው ሁለት ዓመት ግድም በኦሮሚያ በተለይ አምቦ አካባቢ በተነሳው ግርግር ማግስት ቆም ብሎ የነበረውን የተቀናጀ ማስተር ፕላን ጉዳይ ከምርጫው በኋላ በአሸናፊነት መንፈስ ከኦህዴድ ካድሬዎች ጋር ባደረጉት ውይይት “ይህንን ፕላን በግዳቹ ትተግባራለችሁ ብለዋል የሚለው ነው”፤ ይህን አይሉም ሊባል የማይችለው የኦህዴድ ባለስልጣናትም እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የነበራቸው አቋም ተግባራዊ ለማድረግ ምን እናድርግ? የሚለው እንጂ ተግባራዊ አናደርግም የሚል ሰለ አልነበረ ነው፡፡

ይህች በግድ የምትል ቃል እልህ አስገብታ ይህን ሁሉ እሳት የጫረች እንደሆነች መገንዘብ አያሰቸግርም፡፡ ከአቶ መለስ ዜናዊ እልፈት በፊት ኦሮሚያ በእጅ አዙር ይቆጣጠሩት እንደነበር፤ ለዚህም እንደ አለማየሁ አቶምሳ እና ሙክታር የመሰሉ የመለስ ቀኝ እጆች እንደነበሩ ይታወሳል፡፡ ሉሎችም አሉ፡፡ ከመለስ ዜናዊ ሞት በኋላ የኦሮሚያ ባለስልጣናት ከህውሃት ሰዎች ጋር ትከሻ መለካከት እንደጀመሩ ብዙ ማሳየዎች አሉ፡፡ አቶ አባይ ፀሃዬ ከመለስ ሞት ማግስት ጀምሮ ከአንገታቸው ቀና ካሉት ሰዎች አንዱ ቢሆኑም በኦሮሚያ ሰፈር የተፈጠረውን ትከሻ መለካካት ያጤኑት አይመስለኝም፡፡ይህን ትከሻ መለካካጽ ልብ ብለውት ቢሆን ኖሮ “በግዳችሁ ትተገብራላችሁ” የምትለው ጦሰኛ ቃል አትውጣም ነበር፡፡ በግድ ማርም ቢሆን አይጥምም!!!

በእኔ እምነት አሁን በኦሮሚያ አካባቢ የተነሳው በዋነኝነት “እምቢ ማስተር ፕላን” ተቃውሞ በኦሮሚያ በሚገኙ ኦህዴድ ካድሬዎች ቀጥተኛ ድጋፍ እንዳለው ምንም ጥርጥር የለኝም፡፡ ድጋፋቸውን የሚሰጡበት መንገድ የተለያየ ቢሆንም፡፡ ኦህዴድ ዛሬ እንደ ከዚህ ቀደሙ በኢህአዴግ በሚቀመጥለት አቅጣጫ የኦህዴድ ካደሬዎችን አፍሶ እስር ቤት ማሰገባት የሚችል አይመሰለኝም፡፡ ዶክተረ ነጋሶ በአንድ ወቅት እንደነገሩን በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ካድሬዎችን አባረው እና እስር ቤት አስገብተዋል፡፡ የዚያን ጊዜው ኦህዴድ አሁን ያለ አይመስለኝም፡፡ የአሁኑ ኦህዴድ ያለው እድል ካድሬዎቹን ተለማምጦ በስልጣን መቆየት ነው የሚኖርበት፡፡ ሰለዚህ አቶ አባይ እንዳሉት በግድ መተግበር ሳይሆን ማስተረ ፕላኑን መሰረዝ ነው፡፡

አቶ አባይ ፀሃዬ እራሳቸውን ሲቀጥልም እናት ፓርቲያቸውን ሕውሃትን ለመከላከል ብለው የሰጡት ምለሽ በእርግጥ ሌላ ዙር ቀውስ የሚጠራ ነው፡፡ ይህ የአባይ ፀሃዬ የለውበትም መልስ የት እንደሚያደርስ ግን አላውቅም፡፡ መልሳቸው ባጠቃላይ አሁን በኦሮሚያ አካባቢ የተነሳው ንቅናቄ መንስዔ “በኦሮሚያ የተለያየ እርከን የሚገኙ የኦህዴድ ሹሞች ሌቦች በመሆናቸው፣ ህዝቡ የሚጠይቀውን የመልካም አስተዳድር ምላሽ መሰጠት ባለመቻላቸው፣ ወዘተ” የሚል ነው፡፡ በዚህ የመከላከያ መልሳቸው በቀጥታ ላለመንካት የፈለጉት የኦህዴድ ከፍተኛ ሹሞችን ብቻ ነው፡፡ በእኔ እምነት ከወረዳ እሰከ ዞን ብሎም ክልል ድረስ ያሉት ሹሞች ሃላፊነት የተሰጣቸው በኦህዴድ ከፍተኛ ሹሞች ነው፡፡ በክስ ውስጥ ሊዘሏቸው ቢፈልጉም የበታቾቻቸውን መከላከል ወይም አብረው መከሰሳቸው መረዳት ግድ ነው የሚሆነው፡፡ የኦህዴድ ባለስልጣናት አቶ አባይ ፀሓዬን የሚጠይቁት ጥያቄ ያለ ይመስለኛል፡፡ ለማነኛውም አቶ አባይ ፀሓዬ ከግላቸው አልፈው ህውሃትም ሆነ ፌዴራል መንግሰት አሁን በተፈጠረው ጉዳይ አያገባውም ጉዳዩ የኦህዴድ እና የኦህዴድ ሾሞች ብቻ ነው ብለው እጃቸውን ለመታጠብ ሞክረዋል፡፡ ይህ በፍፁም የሚሳካ አይመስለኝም፡፡

በእኛ አረዳዳ ኦህዴድ የሚባል ፍጡር በኢህአዴግ በሚመራው ስርዓት ውስጥ የተለይ ነው ብለን አናምንም፡፡ ኦህዴድ የወሰዳቸው የግል ውሳኔዎች አሉ ብለን አናምንም ስለዚህ ሁሉም የኢህአዴግ አመራር አባሎች እና የፌዴራል መንግሰቱ ባለስልጣናት በዚህ ውሳኔ ውስጥ እንዳሉበት እናምናለን፡፡ ሰለዚህም አሁን አቶ አባይ ፀሃዬ ያቀረቡት መከላከያ ተቀባይነት የለውም፡፡ እርሳቸው እንደሚሉት አንዳንዶቻችንም እንደምንስማማው የተቀናጀ ማስተር ፕላን በድፍኑ ክፋት የለውም፤ ክፋቱ የመጣው “በግድ ትተገብራላችሁ” የሚለው ማስፈራሪያ እና ጥቅም ካለው ማስገደድ እና ማስፈራራት ምን አመጣው? የሚለው እንደምታ ነው፡፡ ሰለዚህ ማርም ቢሆን በግድ ይመራል የምንለው!!!

በነገራችን ላይ ተጠያቂነት የሚባለው ነገር አቶ አባይ ፀኃዬ ከሃያ አራት ዓመት የስልጣን ዘመን በኋላም እንዴት ሊረዱት ተሳናቸው? ለምን ይህን የሚያክል ሀገራዊ ውሳኔ ወደ ወረዳና ዞን ሹሞች ሊወረውሩት ፈለጉ? ሌላው ደግሞ በኦሮሚያ አለ የሚሉት “መሬት መሸጥ፣ የመልካም አስተዳድር እጦት፣ ሙስና፣ ወዘተ እኛን አይመለከትም፡፡ ሕዝቡ የጠየቀው ትክክለኛ ጥያቄ ነው መልስ መስጠት ሲያቅታቸው አባይ፣ ሕውኃት፣ ፌዴራል” ይላሉ ብሎ ከሃላፊነት መሽሽ ይቻላል ወይ?ብለን መጠየቅ አለብን፡፡ በእኔ እምነት አሁንም ቢሆንም ማስተር ፕላኑ ተተግብሮ ውጤት ቢገኝ ጭብጨባውን ለመውሰድ ወደኋላ እንደማትሉት ሁሉ በዚህ መነሻ ለተነሱት መሰረታዊ የመልካም አስተዳድርና የነጻነት ጥያቄ መልስ መስጠት ካቃታችሁም ተጠያቂነቱንም አብራችሁ መሆን ይኖርበታል፡፡ በመጨረሻ አቶ አባይ ፀሃዬ የኦህዴድ የበታችና የመካከለኛ አመራር ላይ ክስ አቅርበዋል፡፡ እነዚህ የኦህዴድ አመራሮች በድርጅት መስመር ሄደው ይህ ክስ በይፋ ይነሳልን፣ ስናስፈፅም የነበረው ከፍተኛ አመራሩ የሰጠን መመሪያ ነው ማለት አለባቸው፡፡ ካለበለዚያ ደግሞ በጋራ ጥያቄያቸውን በኢህአዴግ ፎረም ላይ አቅርበው ሊገማገሙበት ይገባል፤ የአቶ አባይ የግል ከሆነም ግለ ሂስ እንዲያወርዱ ማድረግ አለባቸው፡፡ መቼም ኢህአዴግም ሆነ ኦህዴድ ስልጣን መልቀቅ ስለማይወዱ ብዬ ነው ከስልጣን ይውረዱ ያላልኩት፡፡ ስልጣኑን በግድ እስኪለቁ ግለ ሂስ ያውርዱ ለማለት ነው፡፡

ቸር ይገጠመን!!!